thedayofpentecost | Unsorted

Telegram-канал thedayofpentecost - አዶናይ

3069

ኢየሱስ ዛሬም በፍፁም ፍቅሩ ይወዳቿል

Subscribe to a channel

አዶናይ

ዳዴ ላይ አትቆዩም

ለሚያስተውል ሰው የህፃናት እድገት በህይወታችን ውስጥ ለሚያልፉት ሁኔታዎች ሁሉ ጥሩ አስተማሪዎች ናቸው፤ የህፃናት ህይወት ሁልጊዜ በለውጥ ውስጥ ነው፤ ከእናታቸው ጀርባ ከወረዱ በኋላ ጉልበታቸውን ለማጠንከር ማንም ሳያስተምራቸው በጉልበቶቻቸው መንፏቀቅ ይጀምራሉ፤ በጣም የሚገርመው ነገር እድገታቸው ዳዴ ላይ አለመቆሙ ነው፤ ቀስ በቀስም ጉልበቶቻቸውን በደንብ ካጠነከሩ በኋላ በእግሮቻቸው ይቆማሉ፤

ወላጆቻቸውም ልጄ ዳዴ ላይ እድገቱ ይቋረጣል ብለው ሰግተው አያቁም ምክንያቱም ገና ያልተራመደበት እግር እንዳለው ስለሚያውቁ፤ ልክ እንደ ህጻናት እናንተም በህይወታቹ ላይ ያላወቃቹት እግዚአብሔር ግን ቀድሞ ያዘጋጀው እንቁ ማንነት በውስጣቹ አለ፤ ከእናንተ ሚጠበቀው አሁን ያላቹበት ሁኔታ የህይወታቹ መጨረሻ እንዳልሆነ ማወቅ ነው።

@thedayofpentecost
@thedayofpentecost

Читать полностью…

አዶናይ

🦋 ውድ የአባቴ ልጆች እንኳን ለጌታችን ለመዳኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የትንሳኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ ይህ ቀን የመስቀሉ ፍቅር ለገባን ለኛ ከሞታን ሰፈር ወደ ህያዋን፣ ከድቅድቅ ጭለማ ወደሚደነቅ ብርሃን የተሻገርንበት እንጂ እንደ ብዙዎች የመብልና የመጠጥ ብቻ ቀን አይደለም፤ የክርስቶስ የመስቀሉ ፍቅር ዛሬም ህያው ነው፤ የምኖደው ጌታ ሞትን ድል ነስቷል።

🚨 መልካም ቀን መልካም በአል እንኳን አደረሳቹ🥰


@thedayofpentecost
@thedayofpentecost

Читать полностью…

አዶናይ

🚨 የዘውትር ፀሎቴ ነው.... አባ ያለ ብዙ ነገር መኖር እችል ይሆናል ያለ ህልውናህ ግን መኖር ይከብደኛል እባክህ አባት ሆይ ለአንድም ሰከንድ ያህል እንኳን ያለ ህልውናህ አትተወኝ😭😭😭🔥🔥🔥

🦋 ዘወትር ፊቱን እንድትፈልጉ የሚያደርጋቹ የእግዚአብሔር ህልውና ከናንተ አይወሰድ

Читать полностью…

አዶናይ

🦋 ሁልጊዜ መሽቶ ሲነጋ እጅግ በጣም ውድ የሆነ ስጦታ ይደርሰኛል፤ እርሱም የእግዚአብሔር ምህረት ነው።

መሽቶ የሚነጋው ልማድ ስለሆነ ሳይሆን ምህረቱ ስለበዛልን ነው።

@thedayofpentecost
@thedayofpentecost

Читать полностью…

አዶናይ

🚨 መፀለይ አለባቹ

🦋 ፀሎት ጀምራቹ ለምታቋርጡ ሰዎች እጅግ በጣም ጠቃሚ ትምህርት

🦋 ከዚህ ትምህርት ብኃላ በርግጠኝነት የብዙዎች የፀሎት ህይወት ይታደሳል።

ሼር ይደርግ😍

💯SHARE 💯SHARE 💯
@thedayofpentecost
@thedayofpentecost

Читать полностью…

አዶናይ

መግደል ስለማይችሉ አልነበረም

ዳንኤል የተባለ ፃድቅ የእግዚአብሔር ሰው ለምን ትፀልያለይ በሚል ሰበብ ምረት በማያቁት በአንበሶች ጉድጓድ ውስጥ ለአንበሶች ጨክነው ይሰጡታል፤እነኚ አንበሶች ግን ይህንን ፃድቅ ሰው መብላት አቃታቸው፤ይህ ሰው በአንበሶች ያልተበላው አንበሶቹ መብላት ስለማይችሉ አልነበረም ነገር ግን ዳንኤል የታመነው አምላኩ መልአኩን ልኮ የበላተኛውን አፍ ስለ ዘጋለት እንጂ፤ እንዲሞት ታስቦ በአንበሶች ጉድጓድ ውስጥ የተጣለው ዳኒኤል ምንም ሳይሆን ማንም ገብቶበት ከማይተርፍበት ጉድጓድ ውስጥ በሰላም ወጣእንደ ጥላቶቻችን ሀሳብ ቢሆንማ ኖሮ ከጥርሳቸው ንክሻ ባልተረፍን ነበር ነገር ግን እንደ እግዚአብሔር ፍቃድ ገዳዮች የተባሉት ሳይገሉን፤ ልክ እንደ ዳንኤል ብዙ ጊዜ ከገዳዮቻችን ውጥመድ በብዙ ሰላም ወጥተናል።

@thedayofpentecost
@thedayofpentecost

Читать полностью…

አዶናይ

በርባኑ እኔ ነኝ

አመፃን በፍቅር፣ በደሌን በይቅርታ፣ ሞቴን በህይወት ቀይሮልኝ ያ ሁሉ ኃጢአቴን በፍቅሩ ሽሮልኝ፤ ሞቴን ስጠባበቅ ነፃ ነህ ተብዬ በምህረት የተፈታሁ የዘመኑ በርባን እኔ ነኝ፤ ቅጣቴ የሞት ፍርድ ለዛውም የዘላለም ሞት፤ ይሄ ሁሉ በደሌ ተትቶልኝ በነፃ የተለቀኩት የቅጣቴ ጊዜ ማለቅ ስለማይችል ምንም ኃጢአት የማያቀው ክርስቶስ ኢየሱስ በኔ ቦታ ስለሆነልኝ ነው፤እርሱም የኔን ስቃይና መከራ ለራሱ ወስዶ የሱን ፅድቅና ህይወት ለኔ ሰጠኝ፤
እኔ ላይ የበረቱብኝ ሞትና ኃጢአት በጌታዬ ፊት አቅም አጡ፤
ከዛም ከኔ ኃጢአት የእርሱ ፍቅር በለጠና በምህረቱ ቀና ብዬ ቆምኩኝ።

ጌታ ሆይ ስለማይመረመረው ታላቁ ፍቅርህ አመሰግናለሁ🙏🙏🙏

@thedayofpentecost
@thedayofpentecost

Читать полностью…

አዶናይ

ፀልዩ

በዚች ምድር ላይ ስትኖሩ በየእለቱ አንድ ነገር ማድረግ ይኖርባቿል እርሱም መፀለይ ነው፤ ኢየሱስ ቀኑን ሙሉ ካገለገለ በኋላ ደከመኝ ሳይል ለሊቱን ደግሞ ብቻውን ወደ ተራራ ወጥቶ አብዝቶ ይፀልይ እንደነበር መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል፤ አብዝቶ መፀለይን ያስተማረን ኢየሱስ ነው፤ የተወደዳቹ የአባቴ ልጆች ሴጣን የተሳካለት እናንተን ፀሎት ያስቆማቹ እለት ነው፣ ስለዚህ በምንም ሁኔታ ውስጥ ብትሆኑ መፀለይን የሚያክል ትልቁን ሀብታቹን በፍፁም በጥላት እንዳታሰርቁት ፤ ብቻ ዝም ብላቹ በብርቱ ፀልዩ ድንገት ሳታውቁት የአምላካቹ የእግዚአብሔር ፊት በእናንተ ላይ ማብራት ይጀምራል።

ጌታ ዘመናቹን ይባርክ

@thedayofpentecost
@thedayofpentecost

Читать полностью…

አዶናይ

እምቢ የአለምን ጥሪ፣
እምቢ የአለምን ግብዣ፣
ከቶ አንገናኝም እስከ መጨረሻ👋
እግዚአብሔርን መፍራት ያዋጣኛልና፣
እጅ አልሰጥም ላለም ሞት አለበትና።


እምብየሁ እምቢ😣

@thedayofpentecost
@thedayofpentecost

Читать полностью…

አዶናይ

እግዚአብሔርን የሚፈልግ ልብ ምንም ነገር ብትሰጡት አይረካም፤ ራሱ እግዚአብሔር እስካላገኘ ድረስ፤ እግዚአብሔርን የሚፈልግ ልብ እንዴት የታደለ ነው🥰

የኢየሱስን መቃብር ለማየት ሶስት ሰዎች ሆነው ወደ መቃብር ስፍራው ሄዱ፤ ሁለቱ ደቀ-መዝሙሮች የማርያምን ያህል ኢየሱስን የመፈለግ ልብ ስለሌላቸው መቃብሩ ባዶ እንደሆነ ብቻ አይተው ተመለሱ መግደላዊት ማርያም ግን............

የዮሐንስ ወንጌል 20፥1 ጀምሮ ያለውን ቃል አንብቡት እግዚአብሔርን መፈለግ ከመግደላዊት ማሪያም ትማራላቹ።

@thedayofpentecost
@thedayofpentecost

Читать полностью…

አዶናይ

🚨 ክብርህ ራበኝ 😭

በዚህ መዝሙር የመንፈሱ ርሀብ ያግኛቹ

ክብርህ ራበኝ ክብርህ ራበኝ ፊትህን ማየት አማረኝ🔥⛈️🔥⛈️

@thedayofpentecost
@thedayofpentecost

Читать полностью…

አዶናይ

ይልን እንቀበላለን

ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ በእናንተ ላይ በወረደ ጊዜ ኃይልን ትቀበላላችሁ፥ በኢየሩሳሌምም በይሁዳም ሁሉ በሰማርያም እስከ ምድር ዳርም ድረስ ምስክሮቼ ትሆናላችሁ አለ።”
— ሐዋርያት 1፥8

@thedayofpentecost
@thedayofpentecost

Читать полностью…

አዶናይ

አንድ መተማመኛ አለን!

አምላክ ባይረዳን ፅናትና ትዕግስቱን ባይሰጠን የማናልፋቸው ጊዜያት ነበሩ፤ አያቹ ከዚህ በኋላ ለሚገጥሟቹ ከባድ ፈተናዎች ሁሉ የሚያበረታ እግዚአብሔር የሚባል አንድ መተማመኛ አላቹ!

ወዳጄ ዝቅ ያልክ ሲመስልህ ከፍ የሚያደርግህ፤ ብታጎነብስም ቀና አርጎ በናቁህ ፊት በክብር የሚያቆምህ አንድ ብርቱ መተማመኛ አለክ፤ ስለዚህ የሚጠብቅህና የሚደግፍህ አምላክህ መቼም አይተውህምና ተመስገን በለው!

@thedayofPentecost
@thedayofPentecost

Читать полностью…

አዶናይ

የምንጠብቀው ክብር እኛን እየጠበቀ ነው ⛈️🔥⛈️🔥⛈️🔥⛈️🔥⛈️🔥⛈️🔥

@thedayofpentecost
@thedayofpentecost

Читать полностью…

አዶናይ

የቤተሰብ ፀሎት

በብዙ ክርስቲያን ቤቶች ውስጥ የቤተሰብ ፀሎት የተለመደ ነበር፤ አሁን ላይ ግን ይህ የፀሎት ህይወት በሚጠፋውና ምንም በማይጠቅመን ከንቱ ነገሮች ተተክቷል፤ ቲዢ፣ ዜና፣ ፊልም፣ ቴሌግራም፣ ይህንን ውድ ሀብት ያሳጡን ይመስለኛል።

ዱሮ ዱሮ church ለመሄድ እሁድ ሲረዝምብን፤ ትንሿ ቤተ-ክርስቲያናችን የቤተሰብ ፀሎት ህብረታችን ነበር፤ በቤተሰብ ፀሎት እኔ በበኩሌ በብዙ ተጠቅሚያለሁ፤ የቀድሞ ትጋታቹን ያልተዋቹ በቤተሰብ ፀሎት የምታምኑ አሁንም እየፀለያቹ ያላቹ ያባቴ ልጆች በእጅጉ ተባረኩልኝ፤ ደግሞም ሳትሰለቹ ቀጥሉበት፤ የቤተሰብ ፀሎት የተዋቹ ካላቹ ደግሞ ዛሬ ይህንን መልዕክት ካነበባቹ በኋላ ያንን ውድ የፀሎት ህብረታቹን ዳግም አስጀምሩት።


👇👇👇👇👇👇👇👇
@thedayofpentecost
@thedayofpentecost

Читать полностью…

አዶናይ

🎙️ኢየሱሴን የነካው ሰው 🔥

ይህንን መዝሙር ደጋግማቹ ስሙት

🚨 ኢየሱሴ ፊትህን ማየት ናፈቀኝ

@thedayofpentecost
@thedayofpentecost

Читать полностью…

አዶናይ

. | #በእጆቹ_ቀዳዳ|

ዘማሪ እዮብ አሊ

@thedayofpentecost
@thedayofpentecost

Читать полностью…

አዶናይ

ሴጣን አደገኛ ቁማርተኛ ነው

የተወደዳቹ የአባቴ ልጆች ሰው ሆናቹ በምድር ላይ እስከኖራቹ ድረስ የምታደርጉትን ነገር ሁሉ በማስተዋልና በጥበብ መንፈስ ማድረግ ልመዱ፣ ለሰው ልጆች ሁሉ የተተነበየ አንድ ግዴታ መሆን ያለበት ትንቢት አለ እርሱም ሞት ነው፤ ሞት ለጥቂቶች የሹመት ለብዙዎች ደግሞ የስቃይ ማምጫ መንገድ ነው፤ ሴጣን ይሄንን እውነት ጠንቅቆ ስለሚያውቅ በጊዜያዊው የእድሜ ቆይታችን ጊዜያዊ እና ጠፊ የሆነው ሀብት፣ ደስታ፣ ስሜት፣ ክብር፣ አስይዞን የነገውን የዘላለም ሕይወታችንን ሊነጥቀን ዘውትር ይተጋል፤ ብዙዎቹንም 80 በማትሞላዋ የእድሜ ቆይታቸው የምድርን ሀብትና ደስታ ሰጥቶ ፍፃሜ የሌለውን የዘላለም ሕይወት ነጥቋቸዋል፤

መቼም ቢሆን የዘላለም ሕይወት ከዚች ከንቱ አለም ጋር ማነፃፀል አንችልም፤ እናንተ ግን የሰነፍን ሞት እንዳትሞቱ ሴጣን የሚያቀርብላቹን ጊዜያዊ ደስታን ወደ ጎን ትታቹ ፤ የምቶዱት ጌታ እስኪመጣ ወይም እናንተ ወደ እርሱ እስክቴዱ ድርስ በበጉ ሠርግ ላይ በክብር ለመቅረብ ዘወትር በፀሎት ትጉ።


እወዳቿለሁ😍

@thedayofpentecost
@thedayofpentecost

Читать полностью…

አዶናይ

በመጨረሻዋ ቀን

ብዙ የእግዚአብሔር ሰዎች ይቺን ቀን በኔ ዘመን አድርጋት ብለው ፀልየዋል፤ በዚች ቀን ፍጥረት በናፍቆት የሚጠብቋቸው የእግዚአብሔር ልጆች በሀይል በምድሪቷ ሁሉ ላይ ይገለጣሉ፤ ይህ ደግሞ ሊሆን በብዙ ወጣቶች፣እናቶች፣አባቶች፣ታዳጊዎች ላይ የመንፈስ ቅዱስ ርሀብ ከመቼውም ጊዜ በላይ መጥቷል።

የሚፀልይና መንፈሱን የሚራብ በዚች ቀን ከሚገለጠው ሀይልና ክብር ተካፋይ ይሆናል፤ በርቱና ፀልዩ ልክ እንደ ባለ ሃምሳው ቀን ሰዎችን ግራ የሚያጋባ የመንፈስ ቅዱስ ጉብኝት ሊሆን ነው።

@thedayofpentecost
@thedayofpentecost

Читать полностью…

አዶናይ

የመዝሙር ግብዣዬ😍

🚨መንፈስ ቅዱስ

🦋 ብቻዬን አይደለሁም አለኝ የሚያፅናናኝ

🦋 ብቻዬን አይደለሁም አለኝ መንፈስ ቅዱስ


👇👇👇👇👇👇👇👇
@thedayofpentecost
@thedayofpentecost

Читать полностью…

አዶናይ

በነፃነት መኖር!

በህይወት ስንኖር አንድ ልብስ ብቻ መልበስ ቢኖርብን የምናደርገውን ጥንቃቄ አስቡት እስኪ?
ያ ልብስ እንዳይቆሽሽ ስንጠነቀቅ፣ ከቆሸሸብን ደግሞ ስናጥበው እንዳይሳሳ ስንጠነቀቅ፣ እንዳይቀደድ ስንሳቀቅ ብቻ በተቻለን አቅም እኛ ሳናልቅ እሱ ቀድሞ እንዳያልቅ ዋጋ እንከፍላለን።

የተሰጠን ህይወት እንደዚህ ልብስ ነው፤ ሌላ ተቀያሪ የለንም። ታዲያ ለምንድነው ግድየለሽ የምንሆነው? ሰዎች ምን ይሉኛል ብለን የማንፈልገውን የምናደርገው? አንድ አይን ያለው ሰውኮ በአይን አይቀልድም! ወዳጄ የተሰጠህን የመኖር ዕድል በነፃነት የፈለከውን ሆነህ የፈለከውን አሳክተህ መኖር አለብህ!

#Inspire_Ethiopia

@thedayofpentecost
@thedayofpentecost

Читать полностью…

አዶናይ

መንፈስ ቅዱስ ያስፈልገናል

አንዲት ትንሽ ክብሪት እሳት ለመሆን የክርቢቱ ቀፎ መጫሪያን ብቻ ነው ምትፈልገው፤ ይቺ ክርቢት እሳት ሆና ብዙዎችን ለማቀጣጠል ከመጫሪያው ጋር መገናኘት ይጠበቅባታል፤ ልክ እንደዚሁ እኛም በነገር ሁሉ ለመስፋትና ለማደግ ከፈለግን አፅናኝ ሆኖ ከተሰጠን ከመንፈስ ቅዱስ ጋር መስማማትና ህብረት ማድረግ ይኖርብናል።

ማንም ሊያበርደውና ሊያጠፋው በማይችለው በመንፈስ ቅዱስ ህብረት ውስጥ መኖር ይሁንልን🔥🔥🔥🔥


@thedayofpentecost
@thedayofpentecost

Читать полностью…

አዶናይ

በህልውናው ውስጥ መዘፈቅ ይሁንልን ⛈️🔥⛈️🔥⛈️🔥

@thedayofpentecost
@thedayofpentecost

Читать полностью…

አዶናይ

ጥያቄ + እምነት = መልስ

ከክርስቲያኖች እጅግ በጣም ብዙ ጥያቄዎች ወደ እግዚአብሔር በየቀኑ ይጎርፋሉ፤ ጥቂት ጥያቄዎች ግን መልስን ይዘው ይመለሳሉ፤
ለምን እግዚአብሔር ለሁሉም ጥያቄዎች መልስን አልሰጠም??

እግዚአብሔር አምላክ ለጥያቄያችን ብቻ መልስ የሚሰጥ ቢሆን ኖሮ በዚች ምድር ላይ ምንም ጥያቄ ባልነበረ ነበር፤ ምክንያቱም እግዚአብሔር መመለስ የማይችለው ጥያቄ ስለሌለ፤ ፀሎታቸውን በእምነት በአምላካቸው ፊት የሚያቀርቡ አማኞች ሁል ጊዜ መልስ ይኖራቸዋል፤ ስለዚህ በእግዚአብሔር ፊት የምታቀርቧቸውን ጥያቄዎች በእምነት መጠቅለያ ጠቅሏቸው ከዛም እምነታቹ ራሱ መልሳቹን ሲወልድላቹ ታያላቹ።

@thedayofpentecost
@thedayofpentecost

Читать полностью…

አዶናይ

በእውነተኛ ፍቅር ፅኑ

ዱሮ ዱሮ ወንድምና እህቶቻችን የፍቅር ጓደኝነት ጥያቄ ሲቀርብላቸው " እስቲ ልፀልይበት የእግዚአብሔር ፍቃድ ላይሆን ይችላል" ነበር የሚሉት፤ አሁን አሁን ግን ለፍቅር ጓደኝነት በእግዚአብሔር ፊት መቅረብም ሆነ መፀለይ እየቀረ ነው ምክንያቱም ከእግዚአብሔር ፍቃድ ይልቅ የእኛ ስሜትና ፍቃድ ስለቀደመ፤ አንዳንድ ልጆች የፍቅር ጓደኛ መምረጥ የኔ ስራ ነው ይላሉ፤ ከዛም ጓደኛ የመቀያየር ሱስ ይይዛቸውና ወዳልተፈለገ መጥፎ ልምምድ ውስጥ ይገባሉወዳጆቼ እግዚአብሔር ብቻ ነው የሚሆነንን የሚያውቀው ስለዚህ የፍቅር ጓደኛ ከመያዛቹ በፊት የእግዚአብሔርን ፍቃድ ጠይቁ፤ ፍቅር ጊዜያዊ ስሜት ሳይሆን በበጎነት የምንኖርበት ቋሚ ቃልኪዳን ነው።

👇👇👇👇👇👇👇👇
@thedayofpentecost
@thedayofpentecost

Читать полностью…

አዶናይ

ለካ አልሰማ ብሏቸው ነው

በመጽሐፍ ቅዱሳችን ላይ ብዙ መልዕክቶችን የፃፈው ሐዋሪያው ጳውሎስ ሐዋሪያ ሆኖ ከመጠራቱ በፊት አማኞችን አሳዳጅ ሰው እንደነበር መጽሐፍ ይናገራል፤ አንድ ጊዜ ሳውል( የቀድሞ ስሙ) በዚያን ጊዜ የነበረውን የመንፈስ ቅዱስ እንቅስቃሴን ባለማወቅ ይቃወም ስለነበር ክርስቲያኖችን ለማጥፋት በደማስቆ መንገድ ላይ እየሄደ ሳለ ድንገት ኢየሱስ በብርሀን ተገልጦለት የቀድሞ ማንነቱን እንደቀየረው እንመለከታለን፤ በመጥፎ ስራው የሚታወቀውን ሳውል( ጳውሎስ) ጌታ ለመልካሙ ስራዬ መርጬዋለሁ፤ በእርሱ ስሜን አከብረዋለሁ ብሎ ደቀ-መዝሙር ለነበርው ለሐናንያ በራዕይ ተገልጦ ሲነግረው፤ ሐናንያ እንዲ ነበር ያለው:-

ሐዋርያት 9
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹³ ሐናንያም መልሶ እንዲህ አለው፤ “ጌታ ሆይ፤ ይህ ሰው እኮ በኢየሩሳሌም ባሉ ቅዱሳንህ ላይ ምን ያህል ጒዳት እንዳደረሰ ከብዙ ሰው ሰምቻለሁ፤
¹⁴ ወደዚህም የመጣው ስምህን የሚጠሩትን ሁሉ ለማሰር ከካህናት አለቆች ሥልጣን ተቀብሎ ነው።”
¹⁵ ጌታም እንዲህ አለው፤ “ሂድ፤ ይህ ሰው በአሕዛብና በነገሥታት ፊት እንዲሁም በእስራኤል ሕዝብ ፊት ስሜን እንዲሸከም የተመረጠ ዕቃዬ ነው፤
¹⁶ እኔም ስለ ስሜ ምን ያህል መከራ መቀበል እንዳለበት አሳየዋለሁ።”

ሰዎች ልብን የማየት ጥበብ አልተሰጣቸውም ስለዚህ የውጪውን መልካቹንና የትናንትናውን መጥፎ ስራቹን አይተው፤ ኩላሊትንና ልብም በሚመረምርው አምላክ ፊት ይከሷቿል፤ ሐናንያ የጳውሎስን የትናንት ህይወት አይቶ በእግዚአብሔር ፊት ለአገልጋይነት እንዳይመረጥ ብዙ ምክንያቶችን አቅርቦ ነበር ነገር ግን እግዚአብሔር የነገውን ጳውሎስ አይቶ ስለነበር የሐናንያን ክስ አልተቀበለም።

የትናንት መጥፎ ስራቹ አይተው የሚከሷቹ ሰዎች የነገውን መልካሙን ስራቹን ማየት ስለማይችሉ ነው፤ እግዚአብሔር ግን ነጋቹን አይቶ ስለሚመርጣቹ በትናንትናው መጥፎ ስራቹ ለሚከሷቹ ሰዎች መልስ አይሰጥም።



👇👇👇👇👇👇👇👇
@thedayofpentecost
@thedayofpentecost
@thedayofpentecost

Читать полностью…

አዶናይ

ኢየሱስ እጅግ በቅርብ ቀን ይመጣል

2 ሰዓት አካባቢ ላይ ከወንድሜ ጋር በጣም በሚገርም ፀሎት ከቆየን በኋላ በመንፈስ ቅዱስ እሳት እየተቀጣጠልንና በልሳን እየተናገርን ፀሎታችንን በምስጋና ጨረስን፤ ከዛም ሁለታችንም ከተንበረከክንበት ተነስተን ተቀመጥን፤ የሁለታችን ፊት በእንባ ርሷል፤መንፈስ ቅዱስ በሀይል በላያች ላይ ነበር፤ ወንድሜም ድንገት ሳላስበው ኤርሚ ኢየሱስ እኮ በቅርብ ቀን ይመጣል አለኝ፤ እኔም አዎ በቅርብ ይመጣል ብዬ መለስኩለት፤ ወንድሜ ግን ስለየሱስ መምጣት የመጽሐፍ ቅዱስን ቃል እያጣቀሰ ከወትሮ በተለየ ሁኔታ ማውራቱን ቀጠለ፤ አዎ፣ ልክ ነህ እያልኩት ድንገት አይኔን ከመጨፈኔ ከተቀመጥኩበት ደንግጬ ተነሳውወንድሜም ምነው ምን ሆነሀል ሲለኝ ያየሁትን መናገር አቅቶኝ በልሳን መናገር ጀመርኩ፣ ኢየሱስን አየሁት😭😭 ኢየሱስን በዙፋኑ ላይ ሆኖ አየሁት😭፣ በቢጫ እንቁ የተሞላ ዙፋን ላይ በክብር እያበራ አየሁት እያልኩ ማልቀስ ጀመርኩ፤ ምንም ሳናስበው ለደቂቃዎች ሁለታችንም በልሳን እየተናገርን መፀለይ ቀጠልን፤ ወይኔ ኢየሱስን አየሁት 😭😭 ቤትኛው ቅድስናዬ እንዴ ሊሆን ቻለ፣ አባ አይኖቼ አንተ አዩ እያልኩ ማልቀሴን ቀጠልኩ፤ ያየሁትን ማመን አልፈለኩም ነገር ግን አሁንም ማልቀሴን አላቆምኩም፤ አባ አይኖቼ አንተን አዩ! ይቅር በለኝ ብዬ ተንበርክኬ በግንባሬ ተደፋው፤ አሁንም ኢየሱስን በድጋሚ አየሁት😭😭 ያየሁትን ማመን አቃተኝ ወይኔ ቢኒ አሁንም አየሁት እኮ ብዬው በእግሮቼ ቆምኩ፤ ወንድሜም ምን ምን ምን አየህ እያለ ይጠይቀኝ ጀመር፤ እኔም አሁንም ደግሞ ልክ እንደ ቅድሙ ከዛ ዙፋን በታች እጅግ በጣም ብዙ ወርቃማ የሚያበሩ ሰዎችን አየሁ ብዬ ነገርኩት፤

ከዛም ያየሁት ራዕይ ስለ ክርስቶስ ዳግም ምጽአት የሚናገር እንደሆነ መንፈስ ቅዱስ አስረዳኝ፤


የምኖደው ጌታ ድንገት ይመጣል፤ወዳጆቼ ብዙ ጊዜ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ መምጣት አንብባቹም፤ሰምታቹም ታውቃላቹ፤ አሁንም እኔ ደግሜ ላሳስባቹ እወዳለሁ፤ እናንተ በዚች ምድር ላይ እንግዶች ናቹ፤ ስለዚህ እንደ እንግድነታቹ ተመላለሱ፤ ኢየሱስ እጅግ በጣም በቅርብ ቀን ይመጣል።

👇👇👇👇👇👇👇👇
@thedayofpentecost
@thedayofpentecost

Читать полностью…

አዶናይ

ይህ ወር የተወሰደባቹ ምርኮ በጌታ በኢየሱስም ይመለስ ደስተኛ የሚያደርግ የሚያስገርም እጅን በአፍ የሚያስጭን እና

☞የፀሎት ምርኮ
☞የእምነት ምርኮ
☞የሰላም ምርኮ
☞የጤንነት ምርኮ
☞የትዳር ምርኮ
☞የስራ ምርኮ
☞የአገልግሎት ምርኮ
☞የስኬት ምርኮ

ከቀድሞ በሰባት እጥፍ ይመለሳል
ይሆንልኛል አምናለሁ ያለ ብቻ አሜን ይበል

@thedayofpentecost
@thedayofpentecost

Читать полностью…

አዶናይ

ወንጌልን ስሰብኩ እንዲ አጋጥሟቹ አያቅም😂😍

እንዲህም አለ ለፈገግታ ያህል😍

@thedayofpentecost
@thedayofpentecost

Читать полностью…

አዶናይ

ማን ያምናል

ሳኦል የተባለ የእስራኤል ንጉሥ እንዴት ንጉስ ሆንክ ቢሉት መልስ የለውም፤ ምክንያቱም አህያ ጠፍቶበት ሊፈልግ በወጣበት ድንገት ንጉሥ ስለሆነ፤ የሳኦል ቤተሰቦችና ጓደኞች የሚያውቁት ሳኦል አህያ ሊፈልግ እንደውጣ ብቻ ነው ታዲያ አሁን ማን ያምናል ሳኦል ንጉስ ሆኗል ብለው ቢነግሯቸው፤ እርግጠኛ ነኝ ማንም አያምንም

ልክ እንደ ሳኦል የእናንተም ታሪክ እንዲ ነው ሚሆነው፤ በእናንተ አዕምሮ ያልታሰበ ነገር ግን በእግዚአብሔር አላማ ውስጥ በእናንተ ህይወት ላይ ሊሆን የሚገባው፤ ቤተሰቦቻቹን፣ ጓደኞቻቹን እንዲ ሆንኩ እኮ ብላቹ ስትነግሯቸው ሊያምኑት የማይችሉት ፤ አንተ አጠቅምም ፤ አንቺማ ምንም ዋጋ የለሽም ብለው ያሏቹን ሰዎች አፍ የምታሲዙበት እጅግ ድንቅ ነገር እግዚአብሔርን በእናንተ ህይወት ማድረግ ይጀምራል።

@thedayofpentecost
@thedayofpentecost
@thedayofpentecost

Читать полностью…
Subscribe to a channel