thedayofpentecost | Unsorted

Telegram-канал thedayofpentecost - አዶናይ

3069

ኢየሱስ ዛሬም በፍፁም ፍቅሩ ይወዳቿል

Subscribe to a channel

አዶናይ

R/Ship ከመጀመራቹ በፊት.... part 1

ብዙዎቻቹ ስለዚህ ጉዳይ እንዳማክራቹ ስትጠይቁኝ ነበር ስለዚህም R/ship ለጀመራቹ እንዲሁም ገና ላልጀመራቹ ሰዎች ይጠቅማል ብዬ የማስበውን ሀሳብ በክፍል ከፋፍዬ እናንተ ወጣቶች በምትረዱትና ደስ በሚላቹ መልኩ ለማስተማር አስቤለሁ፤ ትምህርቶቹም ከመንፈሳዊ ህይወትና ከእግዚአብሔር ቃል አንፃር እንደሆኑ እንድታውቁልኝ እፈልጋለሁ፤ ለዛሬ ክፍል አንድን.....

R/ship ከመጀመራቹ በፊት Part 1

የብዙ ወጣት ልጆች ችግር የፍቅር ጓደኛ ለመያዝ መቸኮላቸው ነው፤ አንዳንዱ ገና ለገና ጓደኛዬ R/ Ship ጀምሯል እኔስ ለምን ይቀርብኛል ብሎ ጓደኛ ይይዛል ሌላው ደግሞ ለጊዜው የተፈጠረበት ስሜት ፍቅር ይመስለውና R/Ship ለመጀመር ያስባል፤ ጉዳቱ ግን የእንደነዚህ አይነት የፍቅር ህይወት አጀማመሮች ብዙም ዘላቂ አይደሉም በስሜት ስለተጀመሩ በስሜት ይፈርሳሉ፤ ስለዚህ R/Ship ከመጀመራቹ በፊት መጀመሪያ ለዚያ ሰው የእውነት ፍቅር ነው ወይስ ጊዜዊ ስሜት የሚለውን ጥያቄ መመልስ ይኖርባቿል፤ ብዙዎቻቹ የያዛቹ ፍቅር ሊመስላቹ ይችላል ነገር ግን የኃላ ኃላ ስሜት እንደነበር ትረዳላቹ በተለይ ወንዶች በእንደዚህ አይነት ነገር እንታማለን😊 ስለዚህ ከአንድ ሰው ጋር R/Ship ከመጀመራቹ በፊት መጀመሪያ ያንን ሰው የወደዳቹበት መውደድ ምን አይነት እንደሆነ ቆም ብላቹ አስቡ።

@thedayofpentecost
@thedayofpentecost

Читать полностью…

አዶናይ

🎙️ ለክብርህ የሚሆን እቃ😭

ይሄ መዝሙር በጣም ደጋግሜ ከምሰማቸው መዝሙሮች ውስጥ አንዱ ነው፤ በራሴ ብርታት ጌታን በቅድስና ማገልገል እንደማልችል ስለማውቅ እንዲ ብዬ ዘምራለሁ፤ ለክብርህ የሚሆን እቃ አርገኝ ጌታ😭

@thedayofpentecost
@thedayofpentecost

Читать полностью…

አዶናይ

መሀሉ አይነገርም😊

እግዚአብሔር እስራኤላውያንን ከግብፅ ሳያወጣ በፊት ማርና ወተት ወደምታፈሰው ከነዓን ወደምትባል ምድር አስገባቿለሁ ብሏቸው ነበር፤ ነገር ግን ከከነዓን በፊት ያለውን ግዡፉ የኤርትራ ባህር፣ እንዳለ አልነገራቸውም፤ እስራኤላውያንም በጉዟቸው መሀል ያጋጠማቸውን ፈተና አይተው ከግብፅ ምድር ሳይወጡ በፊት ከነዓን አስገባቿለሁ ያላቸውን አምላካቸውን ባለማመናቸው ጠረጠሩት፤ ወዳጆቼ እግዚአብሔር ወደናንተ መቶ የሚያወራቹ የገው ህይወታቹን ስኬት እንጂ ከስኬታቹ በፊት ያለውን የመከውን ትልቅነት አይደለም ይህን የሚያደርገው ደግሞ እርሱ ያላቹ ቦታ ላይ እስክትደርሱ ድርስ ማህል ላይ የሚያጋጥማቹን መአበል በሀይሉ ብርታት ፀጥ እንደሚያደርገው ስለሚያውቅ ነው፤ ስለዚህ ጌታ ትደርሳላቹ ያላቹ ስፍራ ምንም ያህል መንገዱ ፈተና ቢበዛበትም የተናገራቹ እግዚአብሔር እስከሆነ ድረስ እርሱ ያየላቹ ስፍራ መድረሳቹ አይቀርም።

@thedayofpentecost
@thedayofpentecost

Читать полностью…

አዶናይ

ሰዎች በእግዚአብሔር ክብር ተነክተው በመልአክቶች ዜማ ሲዘምሩ.....

እንደዚህ አይነት Encounter ይብዛልን🔥

@thedayofpentecost
@thedayofpentecost

Читать полностью…

አዶናይ

ምንድነው ይዛቹ ይመጣቹት?

ይሄንን ጥያቄ ሁላቹም ራሳቹን እንድትጠይቁ ፈልጋለው፤ ተወለዱ....በሉ ጠጡ... አደጉ... ተማሩ.... ሰሩ... አገቡ.... ወለዱ....ሸመገሉ እድሜ ጠግበው ሞቱ በቃ! የብዙዎች የህይወት መስመር እንዲ ናት፤ እናንተ ግን ይህንን ለማድርግ ብቻ አልተፈጠራቹም ወደዚች ምድር ስትመጡ አንድ ይዛቹት የመጣቹት ሀብት አለ፤ ይህንን ውድ ሀብት ደግሞ ሳታሳዩን መሞት የለባቹም፤ ራሳቹን ጠይቁ ምንድነው ይዛቹት ይመጣቹት? ጌታ ምን እንድታደርጉለት ነው ወደዚች ምድር የላካቹ?

እግዚአብሔር በውስጣቹ ያስቀመጠውን ውድ ሀብት ያላወቃቹ ልጆች በርግጥ አንድ ትልቅ ነገር እንደደበቃቹን እወቁ፤ እስቲ ይህንን አቅም ከውስጣቹ አውጡትና ህዝብ ይባረክበት ትውልድም ይዳንበት ከዛም ለምን ፈጠርከኝ ለሚለው ጥያቄ በቂ መልስ ይኖራቿል።

@thedayofpentecost
@thedayofpentecost

Читать полностью…

አዶናይ

ከናንተ ብዙ ተምሪያለሁ❤️❤️😍😍

Читать полностью…

አዶናይ

ግን አልተለወጠም ምህረቱ 😭

በነኚ አጭር የመዝሙር ስንኞች ጌታ እስከ ዛሬ ያረገላቹን ምህረት እያሰባቹ ጌታን አመስግኑ።

@thedayofpentecost
@thedayofpentecost

Читать полностью…

አዶናይ

ለየን መንፈስ ቅዱስ 😭

@thedayofpentecost
@thedayofpentecost

Читать полностью…

አዶናይ

🎙️ላይህ ናፍቃለሁ😭

መቼ ትሆን ያቺ ቀን ......

ኢየሱስን የበለጠ እንድናፍቀው ያረገኝ መዝሙር....

@thedayofpentecost
@thedayofpentecost

Читать полностью…

አዶናይ

ብቻ ጌታ ይናገራቹ.....

እኔ በጣም ከምደነቅባቸው ነገሮች ውስጥ አንዱ የእግዚአብሔር ድምፅ ነው፤ አንዳንዴ ኢየሱስ ይወዳቿል ተብለን እንሰበካለን እኛም ያው እንደ ልማድ ይሆንብንና አሜን ብለን እናልፈዋለን፤ ነገር ግን እየፀለያቹ ወይ ደግሞ መጽሐፍ ቅዱሳቹን እያጠናቹ ይሄው ቃል ድንገት ወደናንተ ይመጣና ፊታቹን እንባ በንባ ያረጋቿል፤ እንዲ የምንሆንበት ምክንያቱ አንድ ነው እርሱ የሰማነው ድምፅ የሰው የልብ ሀሳብ ያልተቀየጠበት ንፁህ ጌታ ድምፅ ስለሆነ ነው፤ የተወደዳቹ በህይወት ዘመናቹ አንዴ ብቻ የጌታን ድምፅ በትክክል ብትሰሙ በርግጠኝነት እድሜያቹን ሙሉ አንዴ በሰማቿት በዛች ድምፅ መኖር ትችላላቹ

እግዚአብሔር ድምፁን ያሰማቹ🔥

@thedayofpentecost
@thedayofpentecost

Читать полностью…

አዶናይ

🎙️አምላክ እንደ ሰው

ይህን ድንቅ ዝማሬ ተጋበዙልኝ😍

@thedayofpentecost
@thedayofpentecost

Читать полностью…

አዶናይ

ትላንትናቹ ይጠቅማቿል

ብዙ ሰዎች ትላንትናቸው ለዛሬው ህይወታቸው እንደሚያስፈልጋቸው አያውቁም፤ ዳዊት ገና በልጅነቱ ጎሊያድን ብቻውን ካለምንም መሳሪያ በወንጭፍ ብቻ እንደሚገጥመው ሲናገር የእስራኤል ንጉሥ ዳዊትን አምኖት ወደ ጦር ሜዳ የላከው አቅም ስላለው ሳይሆን ትናንት በእረኝነቱ ጊዜ ከአንበሳና ድብ ጋር ታግሎ እንደሚያሸንፍ ስለነገረው ነበር፤ እግዚአብሔር ዳዊትን በጎሊያድ ፊት ሊያቆመው ስለፈለገ ትናንት በእረኝነቱ ዘመን ከአንበሶች ጋር ድልን ያለማምደው እንደነበር መጽሐፍ ይናገራል፤

የተወደዳቹ የአባቴ ልጆች እግዚአብሔር ዛሬ በህይወታቹ ላይ በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ እንድታልፉ የሚያደርጋቹ ነገ ለምደርሱበት ህይወት ማሳያና ትምህርት እንዲሆኗቹ ስለፈለገ ነው፤

@thedayofpentecost
@thedayofpentecost

Читать полностью…

አዶናይ

🦋 ለመነሳት ወስን ወስኚ

ይህንን ምክር ስሙት👂

በአገልጋይ ዮናታን አክሊሉ


👇👇👇👇👇👇👇👇
@thedayofpentecost
@thedayofpentecost

Читать полностью…

አዶናይ

መንፈሳዊ ህይወታቹ እንዲጠነክር ይህንን አድርጉ.....

ራሳቹን ማሸነፍ ልመዱ

ውስጥህ ዛሬ መሽቷል ደግሞም ደክሞሀል ሳትፀልይ ተኛ ባይሆን ነገ ጠዋት ትፀልያለህ ሲልህ፤ አይ መፀለይ አለብኝ ብለህ ከሴጣንና ከስጋህ የሚወረወርብህን ሀሳብ ወደ ጎን ትተህ መፀለይ ከጀመርክና በሂደትም ይህንን ባህሪ እየተለማመድከው ከመጣህ በየትኛውም ሁኔታ ውስጥ ብትሆን የነገሮች አለመመቻቸት እንዳትፀልይና የእግዚአብሔርን ቃል እንዳታነብ አያደርጉህም፤ ስለዚህ ዘወትር ራስህን ማሸነፍ ልማድህ ማድረግ ጀምር፤ ይህንን ማድረግ ስጀምር ሳታውቀው በህይወት ላይ አስገራሚ ለውጦችን ማየት ትጀምራለህ።

እህቶች ይህ ምክር ለናንተም ነው 😍

@thedayofpentecost
@thedayofpentecost

Читать полностью…

አዶናይ

ይህንን ጌታ ዘወትር እንዲ እያሉ ማምለክ ነው የናፈቀኝ😭

ሀያ አራቱ ሽማግሌዎች በዙፋን ላይ በተቀመጠው ፊት ወድቀው፥ ከዘላለም እስከ ዘላለም በሕይወት ለሚኖረው እየሰገዱ፦ ጌታችንና አምላካችን ሆይ፥ አንተ ሁሉን ፈጥረሃልና ስለ ፈቃድህም ሆነዋልና ተፈጥረውማልና ክብር ውዳሴ ኃይልም ልትቀበል ይገባሃል እያሉ በዙፋኑ ፊት አክሊላቸውን ያኖራሉ።”
— ራእይ 4፥10-11

@thedayofpentecost
@thedayofpentecost

Читать полностью…

አዶናይ

እግዚአብሔር በቅርቡ አንድ ያልተለመደን ነገር ሊያደርግ እንደሆነ ይሰማኛል🔥

የእግዚአብሔር ልጆች በሀይልና በስልጣን ለትውልዱ የሚገለጡበት ጊዜው ደርሷል ትጉና ጸልዩ አንድ እንግዳ ነገር እየመጣ ነው🔥

@thedayofpentecost
@thedayofpentecost

Читать полностью…

አዶናይ

ተዉ ግን😠

በራሳቹ ፍቃድ R/Ship ትጀምራላቹ አልሆን ሲላቹ ደግሞ በስሜታቹ ተገፍታቹ ሌላ ሰው ጋር ትሄዳላቹ፤ ቀኑን ሙሉ ከአንዱ Social media ወዳንዱ Social media እየዞራቹ አምላክ የሰጣቹን ውድ ጊዜ በከንቱ ታባክናላቹ፤ የራሳቹን ነፍስ በራሳቹ ፍቃድ ብዛት ከመጥፎ ነገሮች ጋሱስ ታሲዟታላቹጌታ እድል ሲሰጣቹ ደግሞ "እባክህ ጌታ ሆይ የራስህ አድርገኝ ብላቹ በእንባ ትፀልያላቹ" ከዛም በንጋታው የማታውን ፀሎት ከሚቃረኑ ነገሮች ጋር ሄዳቹ ትውላላቹ፤ እንደዚህ የምታደርጉ ልጆች😠 ግን ተው እናንተ የእውነት ታዛዝኑኛላቹ ከኔ በላይ ደግሞ ጌታ ይታዘባቿል።

ከአለም ጋር በፍቅር ተጣብቃቹ ለጌታ መሆን እፈልጋለሁ ማለት ዘበት ነው ።

@thedayofpentecost
@thedayofpentecost

Читать полностью…

አዶናይ

በዚው ዘመን በዚው ትውልድ በቅርብ ጊዚያቶች ውስጥ አንድ የሚሆን ነገር አለ የተወደዳቹ ትጉና ፀልዩ ...ፀልዩ ...ፀልዩ .....ፀልዩ...

በእኛ ትውልድ ዘመን ሰው ሁሉ ኢየሱስን ማወቅ አለበት!

@thedayofpentecost
@thedayofpentecost

Читать полностью…

አዶናይ

አሳዛኝ ዜና😭😭

ታላቁ የወንጌል አረበኛ ቄስ በሊና ሳርካ ዘመናቸውን ሰጥተው ወዳገለገሉት ጌታ ሄደዋል😭😭😭

እነኚ የእግዚአብሔር ሰው በ63 አመታት የወንጌል ጉዞ 56 ቤተ ክርስቲያናትን ተክለው በመጨረሻው የምድር ተልዕኳቸውን በክብር ጨርሰው ወዳገለገሉት ጌታ ሄደዋል 😭😭

የሚጠብቃቸው የክብር አክሊል አለ

@thedayofpentecost
@thedayofpentecost

Читать полностью…

አዶናይ

🎙️ይሁን ፍቃድህ

ምን አይነት መዝሙር ነው በጌታ እስቲ ጊዜ ሰጥታቹ ስሙት

@thedayofpentecost
@thedayofpentecost

Читать полностью…

አዶናይ

መንፈሳዊ ስካር

መንፈሳዊ ስካር እንዲሁ በቀላሉ የምንገባበት አለም አይደለም መንፈሳዊ ስካር ጥልቅ በሆነ ርሀብና መሰጠት ውስጥ ስትሆኑ የምትገቡበት የርሀብተኞች አለም ነው፤

መንፈሳዊ ስካር የራሳቹን ስሜት፣ ፍቃድና ሀሳብ ረስታቹ የምትኖሩበትና የእግዚአብሔር መገኘት በሙላት የሚመላለስበት የክብር ክልል ነው

መንፈሳዊ ስካር ለምንም ነገር እንዳትሆኑ አድርጎ ለኢየሱስ የከበር እቃ የሚያዘጋጃቹ ጥልቅ የሆነ የመንፈስ ቅዱስ መነካት ነው።

በኢየሱስም ዛሬ ፀልይላቿለሁ ጥልቅ በሆነ መፈሳዊ ስካር ውስጥ መግባት ይሁንላቹ
✋✋🔥🔥🔥🔥🔥

@thedayofpentecost
@thedayofpentecost

Читать полностью…

አዶናይ

በትዕግስት ጠብቁት

ሁላችንም ነገ የሚባለውን ቀን እንደ ትናንትናችን ጠንቅቀን ማወቅ ብንችል ኖሮ አንዳንድ ጉዳዮቻችንን ጌታንም ሳናስቸግረው ለራሳችን መወሰን እንችል ነበር፤ እውነታው ግን የሰው ልጅ ነገ የሚባለውን ቀን ማወቅ አለመቻሉ ነው ለዚህም ነውሁላችንም ነገ ቀድሞ ያየውን ጌታን መጠበቅ የሚያስፈልገን፤ አሁን ላይ ካለጌታ ፍቃድ በስሜት የምትወስኗቸው ውሳኔዎች ቀን ጠብቀው መልሰው የሚጎዷቹ እናንተኑ ነው፤ ስለዚህ ምንም ስህተት የሌለበት የእግዚአብሔር ፍቃድ በህይወታቹ እስኪፈፀም ድረስ በትዕግስት ጌታን ጠብቁት።

@thedayofpentecost
@thedayofpentecost

Читать полностью…

አዶናይ

ጌታ 2 + 2 = 7 ነው ቢላቹም እንኳን ማመን ነው ያለባቹ

ሒሳብ አስተማሪ 2+2 ስንት ነው ቢላቹ 4 ነው ትሉታላቹ እግዚአብሔር ሲጠይቃቹ ግን አንተ ታውቃለህ ነው ማለት ያለባቹ፤ አንዳንዴ ከመንፈስ አለም ጋር የማንግባባው ለዚህም ይመስለኛል፤በእኛ አለም ልክ ነው የምንለው ነገር በእግዚአብሔር አለም ሲታይ ስህተት ሆኖ ሊገኝ ይችላል፤ ነገር ግን ምንም ይሁን ምን በመንፈስ አለም እግዚአብሔር ልክ ነው ያለው ነገር ምንም እንኳን ለኛ ልክ ባይመስለንም የእርሱ እውነት ግን 100 በ100 ካለምንም ደጋፊ ትክክል ነው፤ እናንተ በልባቹ ሊሆን አይችልም ያላቹትን ነገር ጌታ ግን አደርገዋለሁ ካላቹ ካለምንም ቅድመ ሁኔታ ጌታ የተናገራቹን ቃል ማመን ነው ያለባቹ።

@thedayofpentecost
@thedayofpentecost

Читать полностью…

አዶናይ

የዚህን ሰው የፀሎት ህይወት ያነበበ ሰው Normal መሆን አይችልም🔥

APOSTLE JOSEPH AYO BABALOLA ይባላል🔥
🔥

APOSTLE BABALOLA በናይጄሪያ አገር የተነሳ የመጀመሪያው ሐዋርያ ነበር፤ ከላይ የምታዩት የጉልበት አሻራ የዚህ ድንቅ የእግዚአብሔር ሰው የጉልበት አሻሮች ናቸው፤ እግዚአብሔር ለዚህ ሀያል ሰው በፀሎት ስፍራው የጉልበቶቹ አሻራዎች በአለት ላይ ለታሪክ አስቀምጦለታል፤ እንዴት አንድ ሰው ለ 7 ቀናት ሳይነሳ ያለማቋረጥ መፀለይ ይቻላል? ለሐዋርያው አዮ ባባሎላ ግን የተለመደ ነውይህ ብቻ አይደለም እጅግ ብዙ ተራሮችን እየመነጠረ የፀሎት ስፍራ እንዲሆኑ ያደረገ ሰው ነበር፤ በዚህ ሀያል ሰው እጅ በአንድ ሳምንት ብቻ 100 ለምፃሞች ተፈውሰዋል፣ ከ50 በላይ አንካሶች ዘለዋል፣ 30 የሚያክሉ አይነስውራን አይኖቻቸው አይተዋል፤ አሁን ላይ የዚህ ሰው የፀሎት ስፍራ በመንግስት ጥበቃ እየተደረገለት ብዙ ቱሪስቶች ይጓበኙታል።

የሚፀልይ ሰው ክብር ያያል🔥

@thedayofpentecost
@thedayofpentecost

Читать полностью…

አዶናይ

ታጅባቹ የምታዩት ክብር አይኖርም!

ዘፍጥረት 32፥24 ላይ አንድ በጣም የምወደው ቃል አለ ይህም ቃልያዕቆብ ግን ለብቻው ቀረ፤ አንድ ሰውም እስከ ንጋት ድረስ ይታገለው ነበር።” የሚል ነው።

ያዕቆብ በዚህ ስፍራ የሚወዳትን ሚስቱን እንኳን ከርሱ ጋር እንድቶን አልፈለገምምክንያቱ ደግሞ በዛች ለሊት መታገል የፈለገው አካል ስለነበር ነው፤ የተወደዳቹ እግዚአብሔርን ከናንተ በሚያርቁ ሰዎች ተከባቹ ምንም የሚታያቹ ክብር አይኖርም ይልቁንስ ክብሩን ለማየት እርሱን ከናንተ የሚያርቁትን ሰዎችን አርቃቹ ከስራቹ ሸኟቸው ከዛም ለሊቱን እግዚአብሔር ርሀባቹን ሊያጠግብ ወደናንተ ይመጣል።

@thedayofpentecost
@thedayofpentecost

Читать полностью…

አዶናይ

እኔ አንድ መስፈርት አለኝ

በህይወት ዘመኔ በየጊዜው ብዙ ነገሮች ተራቸውን ጠብቀው ወደ ህይወቴ ይመጣሉ እነኚ ነገሮች ግን እኔ ጋር መጥተው ለመኖር አንድ መስፈርት ማሟላት ይኖርባቸዋል፤ መስፈርቱም የመጡት ነገሮች እኔ ጋር ለመቆየት በእኔና በጌታ መካከል ያለውን ህብረት የማይረብሹና የማያቀዘቅዙ መሆን አለባቸው፤ ካለዚያ ግን ወደ ህይወቴ የመጡት ነገሮች ምንም ያህል መልካም ቢሆኑም ከእኔ ጋር ግን እንዲቆዩ አልፈቅድላቸውም።

ወዳጆቼ በየጊዜው ወደናንተ የሚመጡ ብዙ ነገሮች ይኖራሉ፤ ለምሳሌ ጓደኛ፣ ገንዘብ፣ ዝና ፣ክብር፣ ሀብት ብቻ ብዙ ነገሮች ጊዜያቸውን ጠብቀው ይመጣሉየሚመጡት ነገሮች ግን በእናንተና በጌታ መካከል ያለውን ህብረት የሚረብሹ ከሆኑ ፈጥናቹ ከህይወታቹ አርቋቸው፤ ካልሆነ ግን በጊዜ ብዛት የምቶዱትን ጌታ ከልባቹ ውስጥ የማውጣት አቅም ያገኛሉ።

@thedayofpentecost
@thedayofpentecost

Читать полностью…

አዶናይ

የመዝሙር ግብዣዬ😍 ..…

🎙️እንደ ባለ_ሃምሳ ቀን 🔥😭

🦋 መንፈስ ቅዱስ ካንተ ውጪ የምናስቀድመው አንድም ነገር አይኖረንም፤ሊኖረንም አይችልም
⛈️🔥⛈️🔥⛈️🔥⛈️🔥⛈️🔥⛈️

@thedayofpentecost
@thedayofpentecost

Читать полностью…

አዶናይ

ሀይልን ስንቀበል🔥

🦋 ኢየሱስ ያድናል?
የሁላቹም መልስ አዎ ያድናል ነው፤
ነገር ግን እስቲ እንደሚያድን በተግባር አሳዩኝ ብሏቹ ማንም ደፍሮ ማዳኑን በተግባር አያሳያቸውም፤

🦋 ሁላችንንም ኢየሱስ የሞተን ያስነሳል ብለው ቢጠይቁን? አዎ ያስነሳል የሁላችን መልስ ነው፤ ይሁን እንጂ እስቲ የሞተን ማስነሳቱን የሞተ ሰው አምጥተው በስሙ ጉልበት አስነሱት ቢሉን እንኳን ለማስነሳት ሬሳውንም የማየት ድፍረት አይኖረንም።


ኢየሱስ ያድናል የሚለው ሰው ብዙ ነው፤ ኢየሱስ እንደሚያድን በተግባር የሚያሳየን ሰው ግን ጥቂት ሰው ነው፤ እግዚአብሔር እኛን የጠራን የልጁን ማዳን እንድናወራለት ብቻ ሳይሆን የልጁን መልክ በውስጣችን ስሎ የእርሱን ማዳን በፍጥረት መካከል እንድንገልጥለትም ጭምር ነው።

በዘመን መጨርሻ ማለትም በዚህ በኛ ዘመን ኢየሱስ እንደሚያድን በአፍ ብቻ ሳይሆን በተግባር የሚያሳዩ፤ ሀይልን ተቀብለው በአደባባዮች ላይ ልዩነትን የሚፈጥሩ አምላኬ ይሄ ነው ብለው በድፍረት የሚናገሩ ትውልዶች ይነሳሉ🔥🔥🔥🔥⛈️⛈️⛈️⛈️

“እኛም ሁላችን በመጋረጃ በማይከደን ፊት የጌታን ክብር እንደ መስተዋት እያብለጨለጭን መንፈስ ከሚሆን ጌታ እንደሚደረግ ያን መልክ እንመስል ዘንድ ከክብር ወደ ክብር እንለወጣለን።”
— 2ኛ ቆሮ 3፥18

@thedayofpentecost
@thedayofpentecost

Читать полностью…

አዶናይ

🎙️ በአዝመራ ጊዜ መኝታ

🦋 ይህንን መዝሙር ሁላቹም መስማት አለባቹ

ነፍሴ ወዳምላኳ ስጋም ወዳፈሩ ሳይመለስ ሌተቀን ልትጋና ሩጫዬን ልጨርስ።

@thedayofpentecost
@thedayofpentecost

Читать полностью…

አዶናይ

ኢየሱስ ብለህ የሚጣላህ ካለ ይጣላህ

Prophet Eyu Chufa

@thedayofpentecost
@thedayofpentecost

Читать полностью…
Subscribe to a channel