ስበብ አታብዙ😠
አይ ቆይ አሁን ደክሞኛል ሌላ ጊዜ ልፀልይ ሌላ ጊዜ ቃል ላንብብ ሌላ ጊዜ ልፁም እያላቹ ለመንፈሳዊ ህይወታቹ ቀጠሮ አትስጡ፤ ውሀ ጠምቷቹ አይ ቆይ ነገ ጠጣለው ትላላቹ ? በእርግጠኝነት አትሉም
ተነስታቹ
ውሀቹን ትጠጣላቹ
እንጂ፤
ልክ እንዲሁ ለመንፈሳዊ ህይወታቹም ቆራጥ ሁኑ ለስጋቹ የምትሰጡትን ትኩረት ለነፍሳቹም ስጧት ስጋ ሁሉ ጊዜ ደካማ ነው መንፈስ ግን ንቁ ነው፤ ስጋን የሚሰማ ስበብ ያበዛል፤ የምትሰሙትን ምረጡ።
@thedayofpentecost
@thedayofpentecost
መንፈስ ቅዱስ እንደገና ሰርቶኛል መንፈስ ቅዱስ ታሪኬን ቀይሮታል መንፈስ ቅዱስ የኢየሱስ አድርጎኛል መንፈስ ቅዱስ ባለ ራዕይ አድልጎኛል በቃ መንፈስ ቅዱስ አሸንፎኛል፤ መንፈስ ቅዱስ ሆይ ምንም አማራጭ እንደሌለው ሰው እንፈልግሀለን፤ ና እንደገና ለየን ና እንደገና ስራን ልባችን ሁሌም ላንተ ክፍት ነው 😭
መንፈስ ቅዱስ ርሀባችን ነህ🔥🔥
@thedayofpentecost
@thedayofpentecost
ይህንን መዝሙር እየሰማቹ በመንፈስ ቅዱስ ተሞሉ🔥🔥
🎙️ ና... ና የአባቴ መንፈስ ና ና
@thedayofpentecost
@thedayofpentecost
ይህን ቃል በህይወታቹ ላይ ደጋግማቹ አውጁ፤ የምታምኑ ከሆነ ይህ ቀን በድጋሚ የናንተ ይሆናል🔥🔥🔥
@thedayofpentecost
@thedayofpentecost
ራሳቹን ተለዩ
☞ ለእግዚአብሔር ፍቃድ ራሳቹን ለዩ
☞ ለእግዚአብሔር ስራ ራሳቹን ለዩ
☞ ከአለምና ከስራዋ ራሳቹን ለዩ
☞ ነጋቹን ከማይሰሩላቹ ነገሮች ራሳቹን ለዩ
☞ ከማይፀልይና ፌዘኛ ከሆነ ጓደኛ ራሳቹን ለዩ
☞ ኢየሱስን ከማታዩበት ከየትኛውም ቦታ ራሳቹን ለዩ
☞ መንፈሳዊ ህይወት ከቀለለባቸው አገልጋይ ነን ባዮች ራሳቹን ለዩ
☞ የጌታ መገኘት ከሌለበት ስፍራ ራሳቹን ለዩ
☞ ውስጣቹ ያለውን አቅም ከሚገሉ ሰዎች ራሳቹን ለዩ
☞ ለእግዚአብሔር ሀሳብና ፍቃድ ስትሉ ከምቾታቹ ራሳቹን ለዩ
በነገር ሁሉ በተሰጣቹ ውድ ህይወት ዙሪያ ጥበበኛ መሆን ይኖርባቿል፤ ማንም እንደፈለገ የሚያዘውና የሚመራው ህይወት ሊኖራቹ አይገባም፤
መለየት ካለባቹ አሁኑኑ ጊዜ ሳትፈጁ ነጋቹን ከማይሰሩላቹ ነገሮች ራሳቹን ለዩ።
@thedayofpentecost
@thedayofpentecost
እንደ ኢየሱስ የሚወደን እኮ የለም
ሰው ሁሉ ንፁ ሆኖ እኔ ግን ብቆሽሽ
በምድር ላይ እኔ ብቻ በኃጢአት ብበላሽ
መሞት የሚገባኝ እኔ ብቻ ብሆን
የሱስ ለብቻዬ ይመጣልኝ ነበር
እንደ ኢየሱስ በምድር ላይ ፈልጌ አጣሁ እሱን መሳይ ስለዚህ እኔ አመልካለሁ ቀሪ ዘመኔ የኢየሱስ ነው😭😭😭
ጴጥሮስ ግን .....😂😍
ጴጥሮስ ጥድፍ ጥድፍ እያለ ብዙ ጥያቄዎችን ኢየሱስን ባይጠይቀው ኖሮ አሁን ላይ አንዳንድ አስፈላጊ መልሶችን ልናጣ እንችል ነበር ብዬ አስባለሁ፤
ለምሳሌ ውሀ ላይ ለመራመድ እምነት ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ ትንሽም ቢሆን ሰጥሞ አሳይቶናል፤ በራሱም የመውደድ አቅም "እኔ መቼም ቢሆን አልክድህንም "ብሎት ዶሮ ከመጩሁ በፊት ሶስቴ በገረድ ፊት ክዶት፤ ከላይ ካልተሰጠ በቀር በራስ አቅም ኢየሱስን መውድድ እንደማይቻል አስተምሮናል፤ በጥቂት ሰዎች ፊትም በድፍረት ቆሞ ስለ ኢየሱስ መመስከር ከብዶት ከመንፈስ ቅዱስ ሙላት በኃላ ግን በብዙ ሺዎች ሰዎች ፊት ቆሞ በድፍረት
ስለ ኢየሱስ ሲናገር ካለ መንፈስ ቅዱስ እገዛ ኢየሱስን መስበክ እንደማይቻል በግልፅ ነግሮናል።
ጴጥሮስ ባለውለታችን ነው 😍
@thedayofpentecost
@thedayofpentecost
ልባቹ ስንት ክፍል ቤት ነው😊?
በልባችን ውስጥ የፍቅር ክፍል፣ የደስታ ክፍል፣ የሀዘን ክፍል፣ የንዴት ክፍል፣ የድፍረት ክፍል
ብቻ እንደ ሰውዬው ማንነት ልብ ብዙ ክፍሎች ይኖሯታል "አንተ ምን አስበህ ነው የገዛ ልባችንን የከፋፈልከው!" የሚለኝ አንባቢ ካለ ይህንን ሁሉ ክፍል መከራየት የሚፈልግ አካል እንዳለ ልነግረው እፈልጋለሁ እንደውም የሚሸጥ ሰው ካለ ይህ ያልኳቹ ሰው ለመግዛትም ዝግጁ ነው። ተከራዩ ኢየሱስ ይባላል፤ የእውነት ቤታቹን ለዚህ ተከራይ አከራዩት፤ ይሄው እኔ ከጥቂት አመታት በፊት ሙሉውን ክፍል እንዲኖርበት ሰጥቼው ቤቴን እንዴት አሳምሮልኛል መሰላቹ፤ ዱሮ ላይ ንዴት የሚባል እቃ ነበረኝ አሁን ላይ ግን ይህ ተከራይ ንዴት፣ ኃጢአት፣ ራስን አለመግዛት የመሳሰሉትን የራሴን እቃዎች ከቤቴ ቀስ በቀስ እያስወጣ አሁን ላይ ቤቱን በሚገርም ሁኔታ አድሶት የራሱ የሆኑትን፤ ፍቅር፣ ደስታ፣ይቅርታ፣ ራስን መግዛት፣ ፀሎትና
እጅግ በጣም በርካታ ደስ የሚሉ የራሱን እቃዎች ከቶበታል፤ እንደ ወንድም የእውነት ቤታቹን ካከራያቹ ላይቀር ለዚህ እያኖረ ለሚያኖረው ኢየሱስ ለተባለው ተከራይ አከራዩት።
@thedayofpentecost
@thedayofpentecost
እመኑ ይህ ይሆናል ! አሁን ላይ የትውልዱ አይን ኢየሱስን እንዳያይ የጋረዱ የሀይማኖት ስርዓቶች ሁሉ አስታዋሽ እስኪናጡ ድርስ ይረሳሉ፤ ይጠፋሉ፤ የትውልዱ ልብ ኢየሱስን እንዳያስተውል በትምህርቶቻቸው ብዛት ቆልፈው የያዙ የሀይማኖት ሰባኪዎችን በእግዚአብሔር ይቀጣሉ።
ኢየሱስ ግን
በትውልዱ አይምሮ ውስጥ ብቻውን ንጉስና ገዚ ይሆናል እመኑ በመጨረሻው ሰዓት የእግዚአብሔር ጣት ይህንን ያደርጋል።
@thedayofpentecost
@thedayofpentecost
በቃል ፍቅራቹን ለመግለፅ ሞክሩ
ላንድ ለምቶዱት ሰው ፍቅራቹን ትገልፁለት የለ፤ ልክ እንዲሁ ትንሽ ከበድ ቢልም እስቲ ለኢየሱስ ያላቹን ፍቅር ለመግለፅ ሞክሩ......
ስለ ኢየሱስ በጥቂቱ......
ውሽማዎች አይኑሯቹ😄
በድብቅ የዋናውን ቦታ ለመያዝ የሚፈልግ ካለ ቦታው የመጣ ደባል ነገር ሁሉ ውሽማ ይባላል፤ ከኢየሱስ ውጪ ልባቹን ሊይዙ የሚፈልጉ ብዙ ነገሮች አሉ፤ እነኚ ነገሮች ከናንተ ፍቃድ ካገኙ ከልባቹ ንጉስ ጋር እንደ ደባል ሆነው መኖር ይፈልጋሉ፤ ስንቶቻቹ በልባቹ ውስጥ እንደ ውሽማ Act የሚያደርጉ ነገሮችን እንደሰራቹ አላቅም ነገር ግን ከኢየሱስ ውጪ በልባቹ ውስጥ ቦታ ለመያዝ የሚሽቀዳደሙ ነገሮችን ሁሉ
ከደባልነት አልፈው ባለቤት መሆናቸው ስለማይቀር ፈጥናቹ አሁኑኑ ከህይወታቹ አስወግዷቸው።
@thedayofpentecost
@thedayofpentecost
ድንግል አምላኳን ወለደች
እረ ኡኡሁሁሁሁ ምን አይነት ፍቅር ነው፤ ምን አይነት ምህረት ራሱ በሰራው ማህፀን ውስጥ ለማደር መወሰን መፈለግ፤ በየትኛውም ሂሳብ ይሄን ሊያደርግ የሚችል አፍቃሪ የለም የእኛ ኢየሱስ ግን ከዛሬ 2000 አመታት በፊት በድንግሊቷ ሴት ማህፀን ውስጥ አድሮ
ዳግም ሊወልደን ተወልዷል፤ በዚህ በአል ከምግብና ከመጠጥ አልፈልን በሰማያዊ አምልኮ ከሰማይ መልአክቶች ጋር በምስጋና ቅኔ የኢየሱስን ልደት እናከብራለን፤ የገና ቀን ማለዳውን ኢየሱስ እውድሀለሁ ብላቹ ጀምሩ፤ ስትበሉ ኢየሱስ፤ even እንጀራውን ስትቆርሱ ራሱ በኢየሱስ መወለድ ያገኛቹትን በረከት እያሰባቹ ቁረሱ፤ በቃ ኢየሱስ ኢየሱስ ኢየሱስ ኢየሱስ ኢየሱስ
ከሺ አመታት በፊት ሊወልደን ተወልዷል፤ ዛሬ ደግሞ በአዲስ ማንነት በአዲስ ህይወት በመንፈሳዊ ቅኔና ዝማሬ ለውዳችንን እንዘምርለታለን።
መልካም ገና እወዳቿለሁ😍
@thedayofpentecost
@thedayofpentecost
መንፈስ ቅዱስ ሆይ እንደገና በሌላ ሙላት በአዲስ መገለጥ በጥልቅ ርሀብ በሚደንቅ ሰላም በሚገርመው መገኘትህ በብዙ ክብርህ ወደኛ ናናና....🔥 🔥
Читать полностью…እርጉዝ ሴት🤰
እርጉዝ ሴት🤰 በማህፀኗ ልጅ ከያዘች በኃላ ብዙ ለውጦችን ማሳየት ትጀምራለች፤ ከእርግዝናው በፊት የፈለገችውን ልብስ የምትለብስ ከሆነ በርግዝና ሰዓት ግን ለፅንሱ የሚመቸውን አይነት ልብስ መልበስ ትጀምራለች፤
ነፍሰጡር ሴት አረማመዷ እንኳን ያስታውቃል፤ ፅንስ በሆዷ ከመያዟ በፊት የምትቻኮል ከሆነ በእርግዝናዋ ጊዜ ግን የቀድሞዋ አረማመድ ፅንሱን እንዳይጎዳው አረማመዷን እንኳን ትቀይራለች፤ የራሷን ፍቃድና ደስታ ትታ ለሚመጣው አዲስ ህፃን ልጅ ምቾት ስትል መኖር ትጀምራለች፤
የተወደዳቹ የእውነት ጌታ በማንኛችንም ውስጥ አንድ እንድንኖርለት ያስቀመጠው ፅንስ እንዳለ አምናለሁ፤ ብዙዎቻችን ግን ለዚህ ፅንስ ደስታ ከመጨነቅ ይልቅ ለራሳቹ ደስታ ነው የምንጨነቀው፤ እግዚአብሔር ውስጣቹ ያስቀመጥኩት ነገር አለ ካላቹ ለምን ለዛ ነገር መኖር አትጀምሩም ትናንት ምንም ሳይታወቃቹ በፊት እንደ ልባቹ የምቶኑ ከሆነ አሁን ግን ለያዛቹት ፅንስ መኖር ጀምሩ፤ ለጥቂት ጊዜ ሁሉ ነገራቹን ሰጥታቹ ያሳደጋቹት ነገር ነገ ላይ ተወልዶ ለብዙዎች መዳን ምክንያት ይሆናል።
@thedayofpentecost
@thedayofpentecost
ያቺ የበለስ ዛፍ ግን ልክ አልሰራችም😔
[ ማቴዎስ 21፥18 ] ኢየሱስ እርቦት አንዲት በለስ አይቶ ቀረብ ብሎ ፍሬ እንድትሰጠው ጠየቃት እሷ ግን የለኝም አለቺው፤ ይቺ የበለስ ዛፍ የጠየቃት ማን እንደሆነ ብታውቀው ኖሮ ካለ ጊዜዋም ቢሆን ታፈራ ነበር ብዬ አስባለሁ፤ እሷ ግን ያለችበትን ወቅት አሳባ ፍሬዋን ከለከለቺው፤
ኢየሱስ የበለሷ ዛፍ ፍሬ በምታፈራበት ወቅት ለምን አልመጣም? ነገሩን ወደኛው ላምጣው... ጌታ የሚጠይቀን ከሙሉነታችን ሳይሆን ከጎዶላችን እንደሆነ ማወቅ አለብን፤ ከጎዶላችን የምንሰጠው ስጦታ ዘመናችንን በሙሉነት እንድንኖር ይደርገናል፤ መጽሐፍ ሲናገር በለሲቷን ከእንግዲ በኃላ ፍሬ አይኑርብሽ ብሎ ረገማት ይለናል፤ ነገር ግን በዛ ሰዓት ፍሬ ኖሯት መስጠት ብትችል ኖር ከእንግዲ በኃላ ፍሬ አይታጣብሽ ብሎ ሊባርካት ይችል ነበር፤
የተወደዳቹ ጌታ ሊባርካቹ ሲፈልግ ምንም ውሀ በሌለበት እልም ባለ በርሀ ላይ ለአንድ ቀንም እንኳን ህይወቴን ያቆይልኛል ብላቹ የያዛቹትን ውሀ ሊጠይቃቹ ይችላል በዚህ ጊዜ የናንተ ምላሽ የነጋቹ ህይወት የመስራት አቅም አለው፤ ሁሉም ነገር የራሱ የሆነለት ጌታ ከናንተ ህይወት የሚፈልገው ነገር ካገኘና ከጠየቃቹ ቸግሮት ሳይሆን ሊባርካቹ እንደፈለገ እወቁ።
@thedayofpentecost
@thedayofpentecost
ልታስቡበት ይገባል.....
እንፀልይ ከሚላቹ ይልቅ እንጫወት እንቀልድ፣ እንዙር የሚላቹ ጓደኛ ካላቹ
ጓደኝነታቹን
ብታስቡበት ይሻላል
የያዛቹት ስልክ ከኢየሱስ ላይ ትኩረታቹን የሚያነሳ ከሆነ ስልካቹንም አስቡበት
የፍቅር ጓደኛሽ ልቡ ውስጥ ከፍቅር ይልቅ ስሜት ከነገሰ፤ ከመንፈሳዊ ነገርም ይልቅ የአለምን ውበት ደጋግሞ የሚያወራሽ ከሆነ
ፍቅረኛ ተብዬውንም አስቢበት
ብቻ አስቡበት እስካሁን አርቃቹ ባለማሰባቹ የተነሳ ብዙ ነገሮችን አጥታቹ ይሆናል አሁን ላይ ግን ቆም ብላቹ ማሰብ ጀምሩ፤ መወሰን ያለባቹ ነገሮች ላይ አሁኑኑ ወስኑ።
@thedayofpentecost
@thedayofpentecost
መንፈስ ቅዱስ ተስፍችን ነህ እንፈልግሀለን😭 ና ሙላን ና እንደገና አግኘን አንተ ስትኖር ነው ህይወታችን ጣዕም የሚኖረው😭😭😭 መንፈስ ቅዱስ ታስፈልገናለህ
Читать полностью…መንፈስ ቅዱስ ኢትዮጵያን ክደን
በየቤቱ ግባ ህፃናቶችን ንካ ወጣቶችን ንካ 🔥🔥🔥🔥🔥🔥
መንፈስ ቅዱስ እኛ ካንተ ውጪ ማሰብ አቅቶናል ና እንደገና ና በሌላ ክብር ናናና..... መንፈስ ቅዱስ🔥
@thedayofpentecost
@thedayofpentecost
ለምንድነው ብርት ጥፍት የምትሉት😔
መዝሙር ስትሰሙ፣ መልዕክት ሲመጣላቹ እንዲሁም የሚያንፁ ትምህርቶችን ስትሰሙ ውስጣቹ ያለው የፀሎት ሀይል ይነቃቃል፤
ከትናንት በተሻለ ከጌታ ጋር ጊዜ ለማሳለፍ ትሞክራላቹ ይሄ ትጋታቹ ግን ከ አንድ ወር በላይ አይዘልቅም ድጋሚ ወደቀድሞ ቦታችሁ ትመለሳላቹ፤ አንድ ጊዜ ንግግራቹ ሁሉ ኢየሱስ ኢየሱስ፣ መንፈስ ቅዱስ ክብር ይሆንና ሌላ ጊዜ ደግሞ በፀሎት ሰዓታቹ ጊዜ ስትፈለጉ አትገኙም መጽሐፍ ቅዱሳቹንም አርቃቹ ታስቀምጡታላቹ፤ አላቅም ብቻ አንድ ሰው የምለው ነገር ይገባዋል። እንደዚህ አይነት ህይወት የምትኖሩ ልጆች እኔ አንድ ምክር ልከራቹ... ከምንም በላይ ከምትሰሙትና በምታዩት ነገር ተቆጠቡ፤ ቀልዶች፣ ፊልሞች ፣ ማህበራዊ ሚዲያ ብቻ ጌታን ከማያስደስቱ ስፍራዎች ራሳቹን አግልሉ ይህን ስታደርጉ ትንሽ ሊከብዳቹ ይችላል ነገር ግን ቀስ በቀስ ከጌታ ጋር ያላቹ ህብረት እጅግ በጣም የጠበቀ እንዲሆን ታደርጉታላቹ።
@thedayofpentecost
@thedayofpentecost
🎙️ዘመቻ ውጡ
እኔ እንደዚህ አይነት መዝሙር ሰምቼ አላውቅም፤ ራሴን መቆጣጠር እንኪያቅተኝ ድርስ ነው በዚህ መዝሙር የተነካሁት።
ለኢየሱስ ዘመቻ ውጡ......
@thedayofpentecost
@thedayofpentecost
ፀጉራቹን አታስቆርጡ😳
የብዙ ወጣቶች ችግር ውስጣቸው የተቀመጠውን አቅም ለጥቂት ጊዜ ትኩረት በሚሰጡት ጉዳይ እንደሚነጠቁ አለማወቃቸው ነው፤
ለምሳሌ ያህል ጊዜዊ ስሜት የብዙ ባለራዕዮችን አቅም ባጭሩ ከሚያስቀሩ ነገሮች ውስጥ አንዱ ነው ፤ "በቃ እግዚአብሔር ቀብቷቸዋል ብዙ ትውልዶችን ይታደጋሉ" ብለን ተስፍ ስናደርግ እነርሱ ግን ለ 1 ሁለት አመት
በጥሩ ሁኔታ ይቆዩና ኃላ ላይ ግን ሰይጣን በሚያሳያቸው ማባበያ እንደ ሳምሶን ሀገርን የሚጠቅም ቅባት ያረፈበትን ፀጉር ያስቆርጣሉ፤ አገልጋዮች አስተዋይ ሁኑ አለምን የሚጠቅም ቅባት ይዛቹ ጊዜውን ጠብቆ በሚመጣ ሰይጣን የልብ ማባበያ እንዳትታለሉ።
ከሳምሶን ተማሩ😍
@thedayofpentecost
@thedayofpentecost
እስቲ ይህን መዝሙር ልጋብዛቹ😍
🎙️የልብ ምቴ
እኔ እንዳንተ ጨርቄን የጣልኩለት የለም ....
እኔ እንዳንተ አቅም ያጣሁለት የለም....
እኔ እንዳንተ የተሸነፍኩለት የለም 😭
የጌታን ፍቅር እያሰባቹ ስሙት
@thedayofpentecost
@thedayofpentecost
ለምን ግን😔
ሰው በዚህ ጊዜ ከጌታ ጋር ህብረት ካላደረገ እንዴት ሊዘልቅ ይችላል ??ውስጣቹ እየደረቀ እየመጣ እያወቃቹ ለምንድነው ዝም የምትሉት?
ህይወታቹ መበላሸት የሚጀምረው መፀለይ ማቆም የጀመራቹ ለት ነው።
ፀልዩ ፀልዩ በህይወታቹ አትቀልዱ!
@thedayofpentecost
@thedayofpentecost
ኢየሱሴን መራቤን መቼም አላቆምም! ትኩረቴን ከኢየሱስ ላይ እንዳነሳ የሚፈልግ ሰይጣን ይስማ እኔ በፍፁም ኢየሱሴን መፈለጌን መራቤን መጠማቴን አላቆምም።
ርሀባቹን አታቋርጡ
@thedayofpentecost
@thedayofpentecost
የመዝሙር ግብዣዬ😍
🎙️ ባለ እዳ ነኝ
ይህን መዝሙር ግን አስተውላቹ ሰምታቹት ታውቃላቹ.......
@thedayofpentecost
@thedayofpentecost
ኢየሱስን በጉባኤው ውስጥ አየቺው😭😭
ኢየሱሴ ያውና አይታያቹም......😭😭😭
የመጨረሻ ክፍል ነው አውርዱና ስሙት፤ እናንተም ማየት ይሆንላቿል🔥🔥
@thedayofpentecost
@thedayofpentecost
ለመንፈስ አለም Online ስትሆኑ
ለምሳሌ በአዶናይ ቻናል ላይ የምልክላቹን መልዕክቶች እኔ በለቀኩበት ሰዓት online ከሆናቹ መልዕክቱን ከ 2 ሰዓት በኋላ ቴሌግራም ከሚገባው ሰው ይልቅ ቀድማቹ ታዩታላቹ፤ በወር በሁለት ወር የሚገባ ሰው ደግሞ የላኩትን መልዕክት የሚያየው እኔ መልዕክቱን ከለቀኩ ከወር በኃላ ነው ማለት ነው ፤ ልክ እንዲሁ በመንፈስ አለምም በየቀኑ ከእግዚአብሔር ወደኛ የሚላኩልን መልዕክቶች አሉ ብዬ አምናለሁ፤
ነገር ግን ሁል ጊዜ በመንፈስ ስለማንሆን የሚላኩልንን ህልሞች፣ ራዕዮች ብቻ ብዙ ለሕይወታችን የሚያስፈልጉን መልዕክቶች ያመልጡናል፤ አንዳንዴ ዘውትር በመንፈስ በምትሆኑበት ጊዜ ከእግዚአብሔር እንደሆኑ የሚያስታውቁ ድምፃችንና ህልሞችን በተደጋጋሚ ስታዩ ታስተውላላቹ፤ ይህ የሆነው ዱሮም ድምፅ ሳይመጣ ቀርቶ ሳይሆን በዛ ሰዓት መንፈሳቹ ከመንፈሳዊ አለም ለሚመጡ ልምምዶች ክፍት ስለሆነ ነው፤ ስለዚህ ዘውትር በመንፈስ እየተቃጠላቹ ለመንፈስ አለም ውስጣቹን ክፍት አድርጉት ያኔ የእውነት ከጌታ ጋር ያላቹ ህብረት የአባትና የልጅ ህብረት እንደሆነ ትረዳላቹ።
@thedayofpentecost
@thedayofpentecost
ወንጌላችን ገደብ አያቅም
የእሳት አደጋ ሰራተኛ እየተቃጠለ ያለ ቤትን በር አንኳክቶ አይገባም፤ የቤቱ በር ለሱ ምኑም አይደለም የእርሱ አላማ በቤቱ ውስጥ ያሉትን ሰዎች በህይወት ማውጣት ነው፤
አሁን በምድራችን ላይም እየሆነ ያለው የወንጌል እንቅስቃሴም ትላልቅ የተባሉትን የሀይማኖት ተቋማትን ክብር መጠበቅ ሳይሆን በውስጣቸው ያሉትን ያልዳኑ ሰዎችን ከጭለማ ወደሚደነቅ ብርሃን ማምጣት ነው፤ "ወንጌል
እስከዚህ ድረስ ነው ድንበርህ! አይባልም የሰው ልጆች ሁሉ ሊቀበሉት የሚገባ የዘላለም ሕይወት ስለሆነ አይነኬ የተባሉትን ሰዎች ሳይቀር አንበርክኮ እየማረከ ይቀጥላል፤
በየዘመኑ ለወንጌል እንቅስቃሴ ገደብ ሊያበጁለት የጣሩ ሰዎች ሁሉ ደቀዋል፤ እግዚአብሔር ለሰው ልጆች ሁሉ መዳን ምክንያት ያደረገውን ወንጌልን ከማቆም የምድርን ስርዓት ማቆም ይቀላል።
@thedayofpentecost
@thedayofpentecost