የተወደዳቹ በመንፈሳዊ ህይወታቹ ወይ ደግሞ በሌላ ጉዳይ ላይ ህይወታቹ ውስጥ ጥያቄ የሆነባቹ ነገር ካለ ንገሩኝና በዛ ጉዳይ ላይ የማውቀውን ላካፍላቿ...ጥያቄዎቻቹን 👉
@messengerofchristt ፃፉልኝ
ዛሬ አንድ ነገር ገባኝ....
ትዝ ይላቿል ከዛሬ 5 አመት በፊት COVID-19 በሽታ ሲመጣ እነ BBC እና CNN Break News ብለው በሽታውን ለአለም አብስረው ነበር የእኛም ሚዲያዎች በየ ጊዜው በጦርነትና በተለያዩ ምክንያቶች ሰበር ዜና ብለው ልብ አንጠልጣይ ዜናዎችን አፈራርቀው ዘግበው ነበር ነገር ግን እነዛ በሰዓቱ ልባችንን ላይ ትኩስ የነበሩት ሰበር ዜናዎች ሁሉ ዛሬ ላይ ትዝታ ሆነው እንደ አዲስ የሚሰማቸው ሰው ጠፍቷል ነገር ግን ሰማይ ከዛሬ 2000 አመታት በፊት ሰበር ዜና ብሎ ያበሰረውን ድል ዛሬም ስንሰማው እንደ አዲስ ዜና ልባችን ይደነግጥለታህ... የአለም ሰበር ዜናዎች ሁሉ በጊዜ ሂደት ደብዝዘዋል የትንሳኤው ዜና ግን ዛሬም ሰበር ነው ኢየሱስ ተነስቷል።
@thedayofpentecost
@thedayofpentecost
ወጣት አገልጋዮች እናንተ ነገ ላይ
አስር ሺ ብር
የምታገኙ ከሆነ ሰይጣን ዛሬ ላይ በኃጢአት አጅቦ አንድ ሺ ብር በነፃ ቢሰጣቹ በፍፁም አይከስርም...
ትዝ ካላቹ ሰይጣን ሳምሶን ላይ ያለውን ክብር ለማሶሰድ ደሊላን ማምጣት እንዲሁም የዮሴፍን ንግስና ለማስቀረት ዝሙት የሚደርግበት እድል ማመቻቸት አልከበደውም ፤ እናንተ ብቻ የያዛቹትን ጣሉለት እንጂ አሁንም ሰይጣን አማላይ ሴትና ወንድ ልጆችን ወደናንተ ህይወት ማምጣት ፣ እናንተን ታዋቂ ማድርግ ፣ለእናንተ ብዙ ሚሊዮን ብሮችን መስጠት አይከብደውም፤ እናንተ የያዛቹትን አንዷን ዘር ነው የምታዩት እርሱ ግን የያዛቹት ዘር መልካም መሬት ላይ ቢወድቅ ስንት ሆኖ እንደሚያፈራ ነው የሚያየው ስለዚህ የተወደዳቹ የአባቴ ልጆች ጌታ የሰጣቹን ክብር ሰይጣን ዛሬ ላይ ትልቅ በሚመስል እና በሚያጓጓ የአለም ነገር አታሎ እንዳይወስድባቹ ተጠንቀቁ።
@thedayofPentecost
@thedayofPentecost
ለራሳቹ ጊዜ ስጡ
ጠዋት TikTok video ትንሽ ቆይታቹ ደግሞ YouTube ከዛ Facebook እያላቹ ቀኑ ሳታውቁት ያልቅባቿል ማታ ለመፀለይ ታስቡና ቀን የዋላቹበት ጉዳይ እያባበለ ስቦ ወደ ስልካቹ ይዉስዳቿል ከዛም ፀሎቱና ቃሉን ለነገ ብላቹ ቀጠሮ ትይዡለታላቹ ነገም ያላቹት ቀን ሲመጣ ከትናትናው ጋር አንድ አይነት ይሆንባቿል ከዛም እንዲ እንዲያ እያላቹ የጌታን ፍቅር ሳቀምሱት ዘመናቹ ውጪ ውጪውን እንዳየ ያልቃል ማለት ነው ☹️ የተወደዳቹ እንዲህ የምናገራቹ እንድትነቁ እና ለራሳቹ ጊዜ እንድትሰጡት ስለምፈልግ ነው ቢያንስ በየቀኑ ውስጣቹን የምትሰሙበት ፣ቃሉን የምታጠኑበት፣ የምትፀልዩበት 1 ሰዓት ለራሳቹ ይኑራቹ በያዛቹት የጥምና ጊዜ ላይ ዳግም ማንም እንዳይረብሻቹ ስልካቹን ዝጉት ከዛም ቀስ በቀስ ህይወታቹ ላይ ትልቅ ለውጥ ማየት ትጀምራላቹ።
@thedayofPentecost
@thedayofPentecost
ፎቷቹ ራሱ ይናገራል ☺️
እስቲ ከዛሬ 10 ዓመት በፊት የተነሳቹትን ፎቶ ተመልከቱት፤ እርግጠኛ ነኝ የሁላቹም ፎቶ ፈገግ ያስብላል☺️ " ወይኔ ይሄ ሰው እኔ ነበርኩ " ትሉም ይሆናል ምክንያቱም ከትናንትናቹ አንፃር ሲታይ የዛሬው ማንነታቹ የተሻለ ስለሆነ፤ ልክ እንደዚሁ ደግሞ ከዛሬ 10 ዓመት በኃላ ምን እንደምቶኑ እግዚአብሔር አይኖቻቹን ገልጦ ቢያሳያቹ የዛሬው ፎቷቹ ሊያስቃቹ ይችላል ምክንያቱም ከጌታ ጋር የሰነባበተ ሰው የዛሬ ህይወቱ ትናንት ላይ እንደነበረው ስለማይሆን፤ ከአንድ ባለሀብት ጋር ራሱ ጥቂት ቀን ስትቆዩ ሳትፈልጉት ኑሯቹ ይቀየራል ከጌታ ጋር ሲሆን ደግሞ የነገው ህይወታቹ ምን እንደሚሆን ለእናንተ አልነግራቹም☺️
@thedayofPentecost
@thedayofPentecost
አንድ ነገር ልበላቹ
.
..
ሃያላን ሃያላን እረ አቤት በሉኝ ሃያላን እሺ ሃያል🧒 ሃያል ነሽ👩🦰 አቤት ኤርሚ የሚለኝ ሰዉ ይጥፋ... ወይ የዘንድሮ ልጆች😀🥰 እሺ ወደ ቁም ነገሩ ልግባ🏃ቁም ነገሩ ቆይ ቁም ነገሩ ምን ነበር አያቹ የናንተ ነገር አስጠፋቹኝ ቲሽ 🙆...
ምን ነበር 🤔 ቆይ ምንነበር ልላቹ ያሰብኩት 🤔 አዎ አስታወስኩት ስለ ወጣቱ ዮሴፍ ላወራቹ ነበር ትዝ ይላቿል ዮሴፍ በጴጢፋራ ሚስት የተፈተነውን ፈተና ? የጴጢፋራ ሚስት ዮሴፍን " ና አብረን እንተኛ " ስትለው እርሱ ግን እግዚአብሔርን ፈርቶ እንቢ ስላላት ብቻ በሀሰት ከሳው እስር ቤት አስገባችው፤ ቆይ ግን ነገሩን እሺ ብሎ ቢያደርገው ኖሮ ምን ይፈጠር ነበር ? ቢያደርገውማ ኖሮ በተቃራኒው ጥሩ የሚባል ህይወት እንዲኖር ታደርገዋለች ነገር ግን ይሄ ለዮሴፍ ምን ያደርግለታል እግዚአብሔር ካዘጋጀለት ንግስና የሚያስቀረው ከሆነ፤ ወዳጆቼ ሰይጣን በኃጢአት የሚፈትናቹ የታየላቹን ክብር ሊያስጥላቹ አስቦ እንደሆነ አትርሱ ፣ ሰይጣን እግዚአብሔር ለእኛ የያዘውን መልካሙን ሀሳብ ሊያስቀይር አይችልም ነገር ግን እኛን በኃጢአት ይዞ ያንን ሀሳብ እንዳንፈፅም ማድረግ ይችላል ፤ ለዚህም ነው እግዚአብሔር ከሀሳቡ እንዳንጠፋበትና ያየልንን ክብር እንድናየው ስለሚፈልግ አስር ጊዜ ተቀደሱ የሚለን።
ውዶቼ እናንተ ብቻ እንደ ዮሴፍ ኃጢአትን እንቢ በሉለት እንጂ እግዚአብሔር እናንተ ከእስር ቤት አውቶ ንጉስ ማድረግ አይከብደውም።
@thedayofPentecost
@thedayofPentecost
አጉል ስሜታዊነት ☛ በ R/Ship ህይወት ውስጥ
ሁሉም ሰው ማለት በሚቻል መልኩ R/Ship ለመጀመር እንደ ትልቅ መስፈር የሚወስደው በአይን የሚታየውን ነገር ነው አብዛኛውን ጊዜ የሰውነት መልክ ፣ የሀብት ደረጃ እና አለባበስን ሰዎች እንደ መስፈርት ያዮቸዋል አነኚን ነገሮች አይተው የፍቅር ግንኙነታቸውን የሚጀምሩ ሰዎች ደግሞ ለስሜታዊነት ቅርብ ይሆናሉ በዚህም ምክንያት የ R/Ship ህይወታቸው ከሁለት እና ከሶስት ወር በላይ የመዝለቅ አቅም አይኖረውም ምክንያቱም ቀድሞም ቢሆን ግንኙነቱ ከእውነተኛ ፍቅር ይልቅ ለስሜታዊነት ቅርብ ስለነበር፤ የተወደዳቹ የአባቴ ልጆች የፍቅር ግንኙነት ከስሜትና ከጊዜያዊ ፍላጎት ያለፈ ትርጉም እንዳለው ልነገራቹ ፈልጋለው ከምንም በላይ ደግሞ ትዳር ወደሚባለው ወደ እግዚአብሔር ሃሳብ የሚወስደን መንገድም ጭምር ነው፤ ስለዚህ ነገ ላይ " ምነው እንዲ ባላረኩ " የምትሉበትን ውሳኔ እንድቶስኑ ከሚያደርጋቹ በጊዜው ከሚመጣ አጉል ስሜታዊነት ይልቅ የእግዚአብሔር ሃሳብ ያለበትን ትክክለኛ የሆነውን ህይወት እንድትመርጡ መክራቿለው።
@thedayofPentecost
@thedayofPentecost
ይሄን puzzle Game ተጫውታቹ ታውቃላቹ ?ዛሬ አንድ ህይወቴ ላይ ትልቅ ለውጥ ያመጣውን የመንፈን ቅዱስን ትምህርት ላካፍላቹ..
ይሄ ከላይ የምትመለከቱት የምስል ጨዋታ Puzzle Game ይባላል ጫወታውን ከመጀመራቹ በፊት ፐዝሎቹን ገጣጥማቹ ምን አይነት ምስል ማምጣት እንዳለባቹ ታያላቹ ከዛም እንደምታዩት ብዙ puzzle ይሰጣቹና የአንድ ሰው ምስል ስሩ ትባላላቹ እናንተም አንድ በአንድ የሰውነቱን ክፍል እየፈለጋቹ አይኑን በአይን በቦታው ላይ አፍንጫውንም በአፍንጫው ቦታ ላይ እያረጋቹ ትክክለኛውን ምስል ለማምጣት ትሞክራላቹ አንዳንዴ ግን ተሳስታቹ ቅንድቦቹን በጺም ቦታ ላይ ልታደርጓቸው ትችላላቹ እንዲህ ከሆነባቹ ደግሞ ትክክለኛው ምስል ስለማይመጣላቹ የግድ አፍርሳቹ ማስተካከል ይኖርባቿል አሁን ነገርዬውን ወደኛው ህይወት ላምጣው የተወደዳቹ ልክ እንደ ምስሉ እኛም ብዙ የህይወት ፐዝሎች አሉን ነገር ግን የእኛን የህይወት ፐዝሎቹ እየገጣጠመ ትክክለኛውን የእኛነታችንን ምስል የሚያመጣው አላማችንን የሚያውቀው እግዚአብሔር ነው፤ ትምህርት ፣ ስራ ፣ ትዳር ፣ ልጅ ፣ አገልግሎት ፣ ጥቂቶቹ የህይወት ፐዝሎቻችን መካከል ናቸው፤ እነዚን ፐዝሎች እግዚአብሔር ለእኛ ቢሰጠን ኖሮ ደስ ባለንና እንደሚመቸኝ አድርገን በገጣጠምነው ነበር ለምሳሌ ትዳሩን ከስራ በፊት እናደርግና አንዱን ጥለን ደስ ያለንን እንጨምር ነበር ነገር ግን እግዚአብሔር ትክክለኛ ማንነታችንን እኛ እንድንሰራው አሳልፎ አልሰጠንም፤ ስለዚህ የተወደዳቹ ትክክለኛው ምስላቹ በእግዚአብሔር ተሰርቶ እስኪያልቅ ድረስ " ለምን እንዲ አልሆነ፣ ለምን ህይወቴ እንዲ ሆነ "አትበሉ ይልቁኑስ ሳትፈጠሩ በፊት የሚያውቃቹ እግዚአብሔር እናንተ መሆን ያለባቹን ያንን ሰው እንድትሆኑ እየሰራቹ እንደሆነ አስቡ።
@thedayofPentecost
@thedayofPentecost
🎙️ ውዴ 😭
አውቃለው ደጅ እንዳስጠናሁህ😢
በውድቅቱ ለሊት እንዳስቆምኩ😔
ይገባኛል ብዙ እንደታገስከኝ😭
ጠልን ብርድን ችለህ እንደጠበከኝ😢እባክህን አትሂድ ጠብቀኝ...🙏🙏
የመዝሙሩን ግጥሞች አስተውላቹ ስሙ
@thedayofpentecost
@thedayofpentecost
ታውቃላቹ አይደል ከኢየሱስ ሌላ የሚራራልን ፣ እንደ አባት የሚሰማን
ወዳጅ ፈልገን እንደማናገኝ... ባይገርማቹ ሰው ድካማቹን አይቶ ፊቱን ያጠቁርባቿል ሰው አለባበሳቹን ፣ የኑሯቹን ደረጃ አይቶ ይንቃቿል ኢየሱስ ግን..ኢየሱስ ግን😭 ብቻ እንዲህ ነው አልላቹም ታውቁታላቹ
፤ ዘማሪዋም ይሄ እውነት ገብቷት ይመስለኛል " ማንም የለኝ ከኢየሱስ በላይ ስመላለስ በዚች ምድር ላይ ነፍሱን ለኔ ቤዛ ያረገው እውነተኛ ወዳጄ እርሱ ነው " ብላ የዘመረችው፤ አዎ ልክ ብላለች ማንም የለም እንደ ኢየሱስ ፣ ህመማችን የሚገባው 😭😭ማንም የለም እንደ ኢየሱስ ሸክማችንን የሚሸከምልን 😭😭 " ኢየሱስ" ከማንም በላይ የቅርባችን ነው
@thedayofpentecost
@thedayofpentecost
እንደ ወንድም አንድ ነገር ልበላቹ ያው ብዙዎቻቹ ወጣቶች ናቹ ወጣት ደግሞ በየቀኑ ፈተና ውስጥ ነው በተለይ ደግሞ በዚህ ጊዜ .... ለምን ከጌታ ቤት Back አታደርግም፣ ለምን Porn አታይም ፣ ለምን ከአለም ጋር አትመሳሰልም፣ የሚሉ ድምጾች በየቀኑ የያዛቹትን ታላቅ እውነት ከእጃቹ ላይ ነጥቀው ተራ ሰው ሊያደርጓቹ
ይታገላሉ ... አዎ ልክ ነው በዚህ ዘመን ሁሉም መጥፊያው መረብ ውስጥ ሊያስገባቹ ይሞክራል ነገር ግን የተወደዳቹ ምን ያህል ጥላት ሊያጠፋቹ ቢሞክርም እናንተን የያዛቹ ጌታ ግን ፈፅሞ እንደማይጥላቹ እወቁ ብዙ ልብ ሰራቂዎች
፥ ብዙ በኃጢአት እንድትወድቁ የሚፈልጉ ሀሳቦች ቢኖሩም ከሁሉም በላይ ግን ፀንታቹ እንድትቆሙ የሚያደርጋቹ የምህረት እጅ እንዳለ አትርሱ ፤ በዚህ ሰዓት ደክማቹ፣ አቅም አታቹ ይሄን መልዕክቴኝ የምታነቡ የአባቴ ልጆች ካላቹ
እግዚአብሔር የደከሙበትን ልጆቹን ወደ እርሱ የሚጠራበት ምህረት የሚባል የፍቅር ቋንቋ እንዳለው ልነገራቹ ፈልጋለው።
@thedayofPentecost
@thedayofPentecost
የበሰበሰ ሬሳ 🔥🔥እንዴት ?
እግዚአብሔር በእኔ ተጠቅሞ የበሰበሰ ሬሳ ራሱ አስነስቷል 😱ሐዋሪያው ንጉሴ ሮባ.... ከላይ ሙሉ ምስክርነቱን ስሙት ርሀቡ ካላቹ ደግሞ የዚህን ትልቅ የእግዚአብሔርን ሰው የህይወት ታሪክ YouTube ላይ ፈልጋቹ ብታዩት ይጠቅማቿል.... እግዚአብሔር ዛሬም ይሰራል🔥
@thedayofpentecost
@thedayofpentecost
እንደ ልማድ ሳይሆን ከልባቹ ይሄን ቃል እንድትሉት ፈልጋለው
ትናንትናቹን አስቡና እግዚአብሔር ታማኝ ነው በሉ! የነገራቹን እያሰባቹ እግዚአብሔር ታማኝ ነው በሉ... በሉ እያላቹ አይደለም ድምፆቹን ከፋ አድርጋቹ እግዚአብሔር ሆይ አንተ እኮ ታማኝ ነክ በሉት... እግዚአብሔር አልዋሸንም ለዚህ ነው ታማኝ ነክ የምንለው በቃ ዝም ብላቹ አንተ ለኔ ታማኝ አባት ነህ በሉት፤ እግዚአብሔር ታማኝ ነው
@thedayofPentecost
@thedayofPentecost
🎙️እንዳትተወኝ 🙏
ሁላቹም በዚህ መዝሙር ራሳቹን እዩ... የምትችሉ ከሆነ ደግሞ ብቻቹን ስቶኑ ስሙት
@thedayofPentecost
@thedayofPentecost
ደስታቹን ፈትሹት ያው እንደምታውቁት ሁላችንም ምቾቶቻችን ባሉበት ስፍራ ላይ ነው መቆየት የምንፈልገው....
ደስ የሚለን ኳስ ከሆነ ኳስ እያየን ስለ ኳስ ቀኑን ሙሉ ብናወራ አንሰለችም፣ ደስታችን ፊልምም ከሆነ ደግሞ የስልካችን ባትሪ እስከፈቀደ ድረስ ተከታታይ ፊልም እያየን ብንውል ምንም አይመስለንም፤ ችግሩ ግን እነኚ የደስታ ምንጮቻችን ከጥቅማቸው ይልቅ ጉዳታቸው ይበልጣል እንደውም አንዳንዴ እነሱን ፍለጋ ስንሮጥ ብዙ ለህይወታችን የሚጠቅሙንን ነገሮች ልናጣ እንችላለን ለዚህም ነው ደስታቹን ፈትሹት የምላቹ ....አሁን ላይ አስተዋይ ከሆናቹ ትርፍ ከሌለው ጊዜያው ደስታ ራሳቹን አድናቹ አይኖቻቹን የነገው ስኬታቹ ላይ ታደርጋላቹ ካላስተዋላቹ ደግሞ ኳስ፣ ፊልም ፣ ጓደኛ በሚመሳሰሉት ምቾቶቻቹ ተከባቹ ምኑንም ሳትይዙት ወጣትነታቹ በከንቱ ይባክንባቿል ፤ ምርጫው የእናንተ ነው የሚጠቅማቹን ምረጡ።
@thedayofpentecost
@thedayofpentecost
ይድኔ ይሄን መዝሙር ሲፅፍ የኢየሱስን ስቃይ መስቀል ላይ እያየ የፃፈው ነው የሚመስለኝ🥰 እኔ መዝሙሩን በሰማሁት ቁጥር
እገረማለው..
.
የኢየሱስን የመስቀል ፍቅር እያሰባቹ ስሙት።
@thedayofpentecost
@thedayofpentecost
ውዴ ምን አጠፋ 😭
ትናንት በየመንገዱ ስንቱን እንዳልማረ አሁን ውዴ ላይ ምን እግኝተውበት ነው እንዲ ያለምህረት የሚያሰቃዩት ? ትናንት ብዙዎችን ከእስር እንዳልፈታ አሁን ምን ታይቷቸው ነው ውዴን በገመድ ያሰሩት ስበብስ እየፈለጉ በጥፊ የሚመቱት፣ የሚተፉበት ፣ የሚያሾፉበት የእውነት ምን ቢያደርጋቸው ነው እንዲህ የጨከኑበት፤ ውዴን አለውል የሚለው ወዳጁ እስኪክደው ድረስ 😭 እየተቀያየሩ ገረፉት በዚሁ ቢተውት ጥሩ ነበር ነገር ግን ያ ሽቶ ያፈሰስኩበትን የጌታዬን ስጋ በጅራፋቸው ተለተሉት ይሄ አልበቃ ብሏቸው በዛ ሰው ሊያየው በማይደፍረው ስጋ ላይ መስቀል አሸክመው እንደ በግ ይነዱት ጀመር... ውዴን ተጫወቱበት እንደዛ ቁጭ ብዬ የማያቸው እግሮቹ በደም ርሰው ቆሳስለው አየዋቸው ውዴ ያ ሽቶ የቀባሁት አልመስል አለኝ ፤ ሽቶዬን የሰበርኩለትን ጌታዬን እስኪበቃቸው ድረስ አሰቃዩት ከዛም እየገፈታተሩ መስቀል አሸክመው ሰው ሁሉ እያየው እንዲሳለቅበት ከፍ ባለ ተራራ ላይ እርቃኑን ሰቀሉት 😭😭 ያ እኔን በፍቅር ያቀፈበት እጆቹ በችንካር ተመቱ እኔ ያስጠጉኝ ጉኖቹ ውስጥ ጦር ገባባቸው😭😭 በዚህ ሰዓት የውዴ የተተለተለው ስጋውና የፈሰሰው ደሙ ከእንግዲህ ጭለማ " በቃ " ሞት " በቃ "ባርነት " በቃ " ሲሉኝ ሰማኃቸው፤ ውዴም በታላቅ ድምፅ ተፈፀመ ብሎ ጮኽ።
@thedayofPentecost
@thedayofPentecost
🎙️ሀብተ _ሰማይ ይሄን መዝሙር ስሰማ የሰማዩ ቤቴ ናፈቀኝ😭 ...
በጌታ መዝሙሩ ልባቹ ላይ እስኪቀር ድረስ ደጋግማቹ ስሙት🔥
@thedayofPentecost
@thedayofPentecost
ይሄን መዝሙር እስከዛሬ እንዳልሰማ ሰው ሆናቹ ስሙት
በእጆችህ አጥብቀህ እኔን ይዘህኛል፣
ይሄንንም እውነት ቃልህ ይናገራል
ነገሩ ከገባኝ እንቁ መሆንህ 💯
ለምን አንተ ብቻ እኔም ልያዝክ 🙏
@thedayofPentecost
@thedayofPentecost
እግዚአብሔር ዝም ሲል 😢
አስተውላቹ ከሆነ እግዚአብሔር ዝም ሲል ተናጋሪ ይበዛል ኢዮብ ትዝ ይላቿል ምንም በማያውቀው ጉዳይ ምክንያት ያለው ንብረት ሁሉ አንድ በአንድ ሲጠፋበት፣ የገዛ ሚስቱ እንኳን ስትክደው ፣ ሰውነቱም በገል ብረት ሲቆሳስል እግዚአብሔር ግን በዚህ ሁሉ ፈተና ውስጥ ዝም ሲለው ነበር ፤ ነገር ግን ኃላ ላይ እግዚአብሔር በኢዮብ ላይ የነበረውን ሀሳብ ሲጨርስ በታላቅ ክብርና በብዙ ደስታ እንደ ገና እንዳሰበው መጽሐፍ ይነግረናል። የተወደዳቹ የአባቴ ልጆች የእግዚአብሔር ድምጽ በጣም አስፈልጓቹ ድምጹን ግን ሳትሰሙት ስትቀሩ እግዚአብሔር በህይወታቹ ላይ እናንተ ሳታውቁ የሆነ ትልቅ ስራ እየሰራ እንደሆነ አስቡ፤ አንዳንዴ ደግሞ በእግዚአብሔር ዝም ውስጥ እናንተ በብዙ ፈተናዎች ውስጥ ልታልፉ ትችላላቹ ነገር ግን ከብዙ ዝምታዎች በኋላ የሚመጣውን የእግዚአብሔርን ድምፅ ስትሰሙ የቀድሞ ዝምታው ለምን እንደነበር ይገባቿል።
ዝምታው ውስጥ ክብር አለ 🔥
@thedayofPentecost
@thedayofPentecost
አባት ሆይ እስከ ዛሬ የጠየቋቸውን ጥያቄዎቼን ሁሉ ተዋቸውና ይሄን ጥያቄዬን ብቻ መልስልኝ..
“እባክህ፤ ክብርህን አሳየኝ”😭😭 ክብርህን ብቻ😭😭
— ዘጸአት 33፥18
ምን አይነት ፍቅር ነው 🙆
መግደላዊት ማርያም ትባላለች ኢየሱስን በጣም ከመውደዷ የተነሳ " በቃ ጌታሽ እኮ ሞቷል " ተብላ እንኳን ሽቶ ልቀባው ነው በሚል ሰበብ የሞተ ስጋውን ለማየት ለሊቱ እስኪነጋላት አጠብቅም ፤ ባይገርማቹ ሌሎቹ ደቀ መዛሙርቶች ኢየሱስ በህይወት እያለ " አንተ ጌታችን ነህ " ብለውት ነበር ነገር ግን ኃላ ላይ እንደ ሰው ሲሞት ሀሳብ ቀይረው ሁሉም ወደ ኋላ ተመለሱ ይቺ ድንቅ ሴት ግን በህይወት እያለ በራሷ ላይ
ብቸኛ ጌታ ያረገችውን
ኢየሱስን ሞቶም እንኳን ልትቀይረው አልፈለገችም፤ ምን አይነት ፍቅር ነው 😭
ምን አይነት መረዳት ቢኖራት ነው ኢየሱስ ሞቶም እንኳን ለእርሱ ያላት ፍቅር አልቀዘቅዝ ያለው እናንተዬ ለካስ ኢየሱስ እንዲም ይወደዳል....ትዝ ካላቹ ኢየሱስ ከሞት ከተነሳ በኋላም ለመጀመሪያ ጊዜ ራሱን የገለጠው ለዚች ድንቅ ሴት ነበር 🔥የተወደዳቹ ትናንት ላይ ይቺን ሴት የነካት ይሄ ታላቅ ፍቅር ዛሬ ላይ ሁላችንንም እንዲነካን ፀሎቴ ነው 🔥🔥
@thedayofpentecost
@thedayofpentecost
Almost ከግማሽ በላይ ልጆች ለመንፈሳዊ ህይወታቹ መድከም ምክንያት ነው ያላቹት የገዛ ስልካቹን ነው... ታዲያ ለምንድነው የመድከማቹን ምክንያት እያወቃቹ ዝም የምትሉት ? ? እናንተ መፀለይ ፈልጋቹ ስልካቹ ግን እንድትፀልዩ ካላደረጋቹ፣ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ህብረት ከከለከላቹ ፣ ውዱን ለእርሱ ትርፍራፊውን ደግሞ ለጌታ እንድትሰጡ ካደረጋቹ በእርግጠኝነት እኮ ይሄ ነገር እየገደላቹ ነው
ለዚያውም
ሳይታወቃቹ
...
Social media ይጠቅማቿል እርሱ ምንም ጥያቄ የለውም ነገር ግን መንፈሳዊ ህይወታቹን የሚጎዳባቹ ከሆነ ቢቀርባቹ ትጠቀሙ ይሆናል እንጂ በፍፁም አትጎዱም....
@thedayofpentecost
@thedayofpentecost
ውሀው ባህሪውን ቀየረ.
..
አንድ ጊዜ ጴጥሮስ ኢየሱስ በውሀ ላይ ሲራመድ ያይና " ጌታ ሆይ እኔም በውሀ ላይ እንድሄድ ጥራኝ " ይለዋል ኢየሱስም "ና "ብሎ በአንዲት ቃል በውሀ ላይ እንዲሄድ ፍቃድ ይሰጠዋል፣ ጴጥሮስም ውሀ ያሰጥማል የሚለውን እውቀት ወደ ጎን ትቶ ያሰምጥ በነበረው ውሀ ላይ እየተራመደ ወደ ኢየሱስ ይሄዳል ነገር ግን መሀል ላይ ሲደርስ አይኖቹን "ና "ብሎ ከጠራው ከጌታ ላይ አንስቶ በመአበሉ ላይ ማድርግ ሲጀምር ያ የቆመበት ውሃ ከድቶት መስመጥ ጀመረ፤ እናንተዬ🥰 ለካስ መጀመሪያም ውሀው ባህሪውን የቀየረው ጴጥሮስ ኢየሱስን ማየት ስለጀመረ ነው እንጂ ውሀው ከቀድሞ የተለየ ሆኖ አይደለም...
እስቲ ይሄን ነገር ወደ እናንተው ህይወት አምጡትና እስከ ዛሬ ስንት በህይወታቹ ላይ መሆን የሚችሉ ነገር ግን እናንተ ኢየሱስን ማየት ባለመቻላቹ ብቻ ሳይሆኑ የቀሩትን ነገሮቻቹን አስቡ...
የተወደዳቹ እኛ እስከ ዛሬ ጌታን ባለማየታችን ምክንያት ብዙ ነገሮች አቅም አግኝተው አሸንፈውን ይሆናል ነገር ግን አይናችንን ከሚታየው መአበል ይልቅ ኢየሱስ ላይ ማድረግ ከቻልን የሚያሰምጠው ውሀ ራሱ ባህሪውን ቀይሮ መንገድ ይሆነናል።
@thedayofPentecost
@thedayofPentecost
ከልባቹ ደጋግማቹ ስሙት
ፊትህን ማየት ባይኖር 😭🥺
ፀሎት ባይሆን መደበቂያ🥺🥺
ፀጋህ ባይደግፈኝ😭😭
ምን ቃል ያፅናናኝ ነበረ?🤷♀🤷♀
አላገናኘውም ጥያቄና ፊትህን🥺
አኩርፌ ልርቀህ ስፍራዬን ልለቅ🥺
በእንባ ነገሬ ላንተ ስሞታ😭
አልፈን የለ ወይ አባጣና ጎርባጣ🥺
@thedayofPentecost
@thedayofPentecost
እረ ተዉዉዉ 🗣️
በየቀኑ በየ Social media ው ምንም ቁም ነገር ለሌው ነገር Like እና Comment 💌እየሰጣቹ " እረ የዚህ ልጅ ቀልዶች አይጠገቡም .... ዛሬ ደግሞ እንትና ምን ሆና ነው እንዲህ የለበሰችው... አየክ YouTube ላይ የተለቀቀውን የእከሌን ጉድ ... Instagram ላይ የዛችን ልጅ አለባበስ እየሽው አይደል እንዴት አባቱ እንደሚያምር 💃.... እያላቹ ከቆያቹ በኋላ ራሳቹ መስሚያ ጥቂት ጊዜ ስታገኙ ደግሞ ኤርሚ ባይገርምህ መንፈሳዊ ህይወቴ እኮ ደከመብኝ ፣ እንደ ዱሮም መፀልይ አቁሚያለው ስትሉኛላቹ ☺️ የተወደዳቹ እናንተ በየ እለቱ እንደ ቀላል እያያቿቸው የምታደርጓቸው ነገሮች የእናንተ መንፈሳዊ ህይወት የማድከምም የማጠንከርም አቅም እንዳላቸው ማወቅ አለባቹ... ቁኑን ሙሉ በመንፈስ እንዳትሆኑ በሚያደርጓቹ ሁኔታዎች ተከባቹ ቆይ እንዴት ነው ከጌታ ጋር ጊዜ ማሳለፍ የምትችሉት ?
በፍፁም አትችሉም ! ሲጀመር ቀልድ ቀልድን እንጂ ፀሎትን የመሳብ አቅም የለውም ለዚህ ነው ውሏቹን ቃሉን እንድታጠኑና እንድትፀልዩ በሚያደርጓቹ ነገሮች መካከል ማድረግ ያለባቹ።
@thedayofpentecost
@thedayofpentecost
የዚህን ሰው የፀሎት ህይወት ያነበበ ሰው Normal መሆን አይችልም🔥
APOSTLE JOSEPH AYO BABALOLA ይባላል🔥🔥
APOSTLE BABALOLA በናይጄሪያ አገር የተነሳ የመጀመሪያው ሐዋርያ ነበር፤ ከላይ የምታዩት የጉልበት አሻራ የዚህ ድንቅ የእግዚአብሔር ሰው የጉልበት አሻሮች ናቸው፤ እግዚአብሔር ለዚህ ሀያል ሰው በፀሎት ስፍራው የጉልበቶቹ አሻራዎች በአለት ላይ ለታሪክ አስቀምጦለታል፤ እንዴት አንድ ሰው ለ 7 ቀናት ሳይነሳ ያለማቋረጥ መፀለይ ይቻላል? ለሐዋርያው አዮ ባባሎላ ግን የተለመደ ነው
፤ ይህ ብቻ አይደለም እጅግ ብዙ ተራሮችን እየመነጠረ የፀሎት ስፍራ እንዲሆኑ ያደረገ ሰው ነበር፤ በዚህ ሀያል ሰው እጅ በአንድ ሳምንት ብቻ 100 ለምፃሞች ተፈውሰዋል፣ ከ50 በላይ አንካሶች ዘለዋል፣ 30 የሚያክሉ አይነስውራን አይኖቻቸው አይተዋል፤
አሁን ላይ የዚህ ሰው የፀሎት ስፍራ በመንግስት ጥበቃ እየተደረገለት ብዙ ቱሪስቶች ይጓበኙታል።
ፀልዩ የሚፀልይ ሰው ክብር ያያል🔥
@thedayofpentecost
@thedayofpentecost
እረኛዬዬዬ
🐑 ቆይ እረኛዬዬ እኔን ምን ያህል ቢወደኝ ነው እስካሁን ሳይሰለቸኝ በእቅፉ ሊይዘኝ የቻለው ? ጥሩ ፀባይ ኖሮኝ ነው ወይስ ከቤቱ የሚያባርረኝ ከባድ በደል ሳይገኝብኝ ቀርቶ ? እኔንጃ ብቻ አንድ ነገር አውቃለው እረኛዬ ለእኔ ምህረቱን አብዝቷልኛል 😭 ብዙ ጊዜ የአለም ነገር አማሎኝ እረኛዬ ካሰማራኝ ስፍራ ጠፍቼ ሩቅ መንገድ ሄዴ አውቃለው እና በዚህ ጊዜ ያ የሚፈልገኝ ተኩላ 🐺 ከመንጋው ተለይቼ ብቻዬኝ አቅም እንደማይኖረኝ አውቆ ሊበላኝ ይመጣ ነበር ነገር ግን ይሄ ይወደኛል ያልኳቹ እረኛዬ ድንገት መጥቶ ከበላተኛው እጅ ነጥሎ ይወስደኛል😭 እረኛዬዬዬ... እረኛዬ ካሰማራው መንጋ መካከል ለአንድ አፍታም ቢሆን ርቄ እንድሄድበት አይፈልግም ፤ አንዳንዴ እንደውም ከመንጋው መካከል የእኔ ልቤ በአለም ነገር መሰረቁን ሲረዳ ቀረብ ብሎ ስሬ ይቀመጥና በዛ ውብ እጆቹ ያሻሻኛል ወደ እቅፉም አስጠግቶ አይን አይኔን እያየ " ለአንቺ መልካም እረኛ እኔ ነኝ ለዘላለም እጠብቅሻለው ከእጄ ማንም አይወስድሽም ብሎ ይነግረኛል 😭
ኢየሱስ
የእኔ እረኛ 💯
@thedayofPentecost
@thedayofPentecost