theideaofs | Unsorted

Telegram-канал theideaofs - የዘር ሐሳቦች/ Yezer Hasaboch

1126

እያንዳንዱ ሐሳብ ዘር ነው

Subscribe to a channel

የዘር ሐሳቦች/ Yezer Hasaboch

#የሰዎችን_ውድቀት_ናፋቂ_ሰዎች!!

የክቡር ከበደ ሚካኤል አንድ የታወቀ ግጥም አለ፦

"ጽድቅና ኩናኔ ቢኖርም ባይኖርም
ከክፋት ደግነት ሳይሻል አይቀርም።"

የሰዎችን ውድቀት የመፈለግ አባዜ በብዙ መልኩ ሊገለጥ ይችላል፦

፨ በቀጥታ ሰውየውን በመቃወም ላይ ሊመሰረት ይችላል

፨ በተዘዋዋሪ ከጀርባ በማጥቃት ላይ ሊመሰረት ይችላል ( ወሬ፣ጥላቻና፣ ሐሜትን፣ ሰውየውን ማጣጣል) ወይም በሰውየው ፊት ወዳጅ ከጀርባው ደበኛ በመሆን

፨ ሰውየውን ከሚጠሉ ሰዎች ጋር ግንኙነት በመፍጠር ሐይልን አደራጅቶ መውጋት ሊሆን ይችላል (ሌሎችን በማታለቅ ሰውየውን በመተቸት ላይ የተመሰረተ ሊሆን ይችላል)

ክፉ ልብ የሰይጣን በር ነው። ክፉ ሐሳብና ድርጊት መገለጫዎቹ ናቸው። የሰዎች ውድቀት ላይ ተግቶ የሚሰራ፣ በራሱ ነገር ላይ የሚያተኩር ሰዎች ላይ እንዳደረገ በእርሱ ላይ መደረጉ አይቀርም። ሰው የሚቀበለው የሚሰጠውን ነው። ነግ በኔ ነው።

ጭካኔ የበዛበት ጊዜ ይህ ጊዜ ይመስለኛል። ሰዎች በየቦታው በሚዲያቸው ቁጭ ብለው የሚያወሩት፣ የሚመኙት እና የሚፈልጉት የሌሎችን ሰዎች ውድቀትን ሆኖ ሲታይ እጅግ አሳዛኝ ጊዜ ላይ እንዳለን አመላካች ነው። የሰዎች ውድቀት እኮ እኛን የአንድ ነጥብ ያህል ከፍታን አይጨምርልንም።

"ሁልጊዜም ሳስበው ምስጢር የሚሆንብኝ አንድ ጥያቄ አለ። እርሱም ' ሌላውን የሰው ልጅ በውርደት በማሳቀቅ አንድ ሰው እንዴት ክብር ይሰማዋል? የሚል ነበር።"

ማሃትማ ጋንዲ

የሚሻለው ለሰዎች መልካም ማሰብ ከቻልን መልካም ማድረግ፣ ካልቻልን መልካም መመኘት ብቻ ነው። መልካምነት ዘር ነው። የሰዎችን ከፍታና ስኬት መመኘት፣ ለዚያም መስራት ለእኛን ከፍታና ድምቀት ይጨምረዋል። መደብዘዝ ያለው ለሰዎች ክፋትን በማሰብና በማድረግ ውስጥ ነው።

ለሰዎች ያለን ማንኛውም አመለካከት (መልካም ሆነ ክፉ) በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የእኛን ህይወት ይነካዋል። የሰዎችን ውድቀት የሚናፍቁ ሰዎች አስቀድመው እነርሱ ወድቀዋል።

ዘሪሁን ግርማ

/channel/theideaofs

Читать полностью…

የዘር ሐሳቦች/ Yezer Hasaboch

ከቅኖች ጀርባ እግዚአብሔር ይቆማል።

Читать полностью…

የዘር ሐሳቦች/ Yezer Hasaboch

የጎብኚዎች ስብስብ በሀይቁ መኃል በተንሳፋፊ ነገር የአዞ እርባታ ይጎበኛሉ። የእርባታው ጌታ "ሐይቁን ዋኝቶ ለወጣ የ10 ሚሊዮን ዶላር ሽልማት እሰጣለሁ" ብሎ አምባረቀ። ፀጥታው ሰፈነ።

ድንገት ግን አንድ ሰው ወደ ሀይቁ ዘለለ፣ አዞዎችም አሳደዱት፣ ነገር ግን እንደ ዕድል ሳይጎዳ ተረፈ። ባለቤቱ "አሸናፊ ሰው አግኝተናል" ሲል አወጀ።

ሽልማታቸውን ከወሰዱ በኋላ እሱና ሚስትዬው ወደ ክፍላቸው ተመለሱ። ሰውዬው "ከኋላ ተገፍቼ እንጂ በራሴ አልዘለልኩም" ብሎ ለሚስቱ ነገራት።

ሚስትም ፈገግ፣ ቀዝቀዝ ብላ "እኔ ነበርኩኝኮ" አለችው።

Moral of the story - "ከያንዳንዱ ስኬታማ ወንድ ጀርባ፣ ዘወትር በትንሹ ገፋ የምታደርገው ሴት አለች" 😁😃🙄
__ 🏃🏿

ለፈገግታ 😀😀😁

ከፌስ ቡክ የተገኘ

Читать полностью…

የዘር ሐሳቦች/ Yezer Hasaboch

"በቦታህ መምህር፤ ያለቦታህ ደግሞ ተማሪ ሁን"

፨ምክርን ብትሰማ በነጻ ትማራለህ። ምክርን አልሰማ ብትል ግን በዋጋ እንደምትማር እወቀው። በዋጋ መማር ግን አድካሚ ደግሞ የሚያስመርር ነው። ብልህ ከሆንህ በሰው ከደረሰው ትማራለህ፤ ሞኝ ከሆንህ ግን በራስህ ሲደርስ ትማራለህ።

፨ የታየህን አሳይ፣ ያልታየህን አጥራው። በደንብ ያልተረዳኸውን አታስተምረው። ያልቀመስከውን ለሰው አትጋብዝ። የሰማኸውን ሁሉ አትመን። ያየኸውን ሁሉ ስጡኝ አትበል፣ የተናገርከውን ሁሉ ፈጽሙ አትበል። የሰጠኸውን እርሳ እንጂ አታውራ። ፍጻሜውን ሳታይ ምስጋና አታብዛ። ቀኑ ሳይመሽ ቀኑ ጥሩ ነው አትበል።

/channel/theideaofs

Читать полностью…

የዘር ሐሳቦች/ Yezer Hasaboch

"መለወጥ የማትችላቸው ነገሮች ላይ ዋጋ አትክፈል፣ በምትለውጠውና ፍሬያማ የሚያደርጉህ ነገሮች ላይ አተኩር።"

/channel/theideaofs

Читать полностью…

የዘር ሐሳቦች/ Yezer Hasaboch

#አገልግሎት_መፎካከሪያ_አይደለም!

አገልግሎትና አገልጋይነት ከሌላው የተሻልን እንደሆንን የምናሳይበት የፉክክርና ራሳችንን የምናሳይበት ሜዳ አይደለም። የተሰጠንን አደራ ልንፈጽም የተጠራንበት ጥሪ ነው። አገልግሎት ወድድር፣ ማሸነፍና፤ መሸናነፍ መብለጥና፣ መበላለጥ፣መቅደምና፣ኃላ መቅረት የለውም። አገልግሎት በግል የተሰጠን የምንሮጠው ሩጫ ነው። ለአንድ መንግስት እየሰሩ መበላለጥና ከወንድም በልጦ ለመታየት ማሰብ መፅሐፍ ቅዱሳዊ አይደለም። በእግዚአብሔር መንግስት መበላለጥና መፎካከር መቀዳደም የሚባል ነገር የለም። ሁሉም የሚቀበለው በሰራው ስራና እንደ ተሰጠው ጥሪና መክሊት ነው።

ሁሉም የሚሮጠው የተሰጠውን ነው። ማንም የሚጠየቀው በተሰጠው ልክ ነው። አንድን ነገር አንዱ ወንድማችን ስላደረገው እኛ ያንኑ ከዚያ በተሻለ ለማሰየት መታገል የለብንም። እኛ ራሳችን የተሰጠን የስራ ድርሻ አለን። እርሱን እንሩጠው። ሩጫችን ከተሰጠን ጥሪ እንጂ አጠገባችን ካለው ወንድማችን እንደምንበልጥ ማሳያ አይደለም።

እግዚአብሔር ዋጋን ሲከፍለን ከእንትና የበለጠ አገልግለሃልና አንደኛ ነህ አይልም ዋጋህ የሚተመነው ለአንተ በተሰጠህ መክሊትና ባፈራህው መጠን ነው። የምንሰራው ለመንግስቱ አላማ እስከሆነ ራስን ለማሳውቅና ለመግነን በልጦ ለመታየት መሯሯጥ የእግዚአብሔር ፈቃዱና መንገዱ አይደለም።

የእኛ ቤተክርስቲያን የእኛ አገልግሎት እኛ መጋቢችን ላይ ያለው ቅባት የትም የለም፤ የሚል እሳቤና ትምህክት የክርስቶስን መንገድ ካለማወቅ የመነጨነ፣ ካልተለወጠ የግል ባህሪና ፍለጎት የመነጨ ነው። ወንድምን ለመጣል የሚደረግና ሩጫና በልጦ ለመታየት የሚደረግ ሩጫ ዋጋና ፍሬ የሌለው ነው። ሁሉም በተሰጠው ነገር ላይ ይስራ!!

የለበስነው ማሊያ አንድ ነው። ቁጥሩ ይለያይ ይሆናል እንጂ፣ አጥቂው ጎል ቢያገባ ብቻውን ለመክበር ሳይሆን ክለቡን እንዲያሸንፍ ለማድረግ ነው። እርስ በእርስ አንሸናነፍም። ግን ልንወርሰው የተገባን ትልቅ እርሻ አለን። በተለያዩ ቦቻዎች የሚያገለግሉ አገልጋዮች ማሰብ ያለባቸው ሁሉም አገልጋይ ለመንግስቱ ስራ የተጠራና ለግል ሳይሆን ለእግዚአብሔር መንግስት አላማ የምንሰራ መንፈሴዊ ቤተሰቦች መሆናችንን ማወቅ ማመንና መቀባበል አለብን። አገልግሎት ውድድር የለውም። የምንጠየቀው በተሰጠን መጠን ነው። ሁላችንም የተሰጠን አንድ አይነት አገልግሎት አይ ደለም የተለያየ ነው። በዚያው ልክ ልናፈራና እግዚአብሔርን ልናከብር ተጠረተናል።

ዘሪሁን ግርማ

/channel/theideaofs

Читать полностью…

የዘር ሐሳቦች/ Yezer Hasaboch

#በትናንት_ማንነትህ_ማንም_እንዲያሸማቅቅህ_አትፍቀድ!

አብርሃም ሊንከን ወደ አሜሪካን ፕሬዝዳንትነት በመጣበት ጊዜ አባቱ ጫማ ሠሪ ነበር። በፅንፈኞች ዘንድም "የጫማ ሠሪ ልጅ" ወደ ፕሬዝዳንትነት መምጣቱ ያልታሰበና ብዙዎቹንም ያስከፋ ነበር። በበአለ ሲመቱ ቀንም አብርሃም ሊንከን የመጀመሪያ ንግግሩን ሊያደርግ በምክር ቤት ተገኘ። ድንገትም ከመሐል አንድ ባላባት ተነሣና፦ "አብርሃም ሊንከን ሆይ፥ አባትህ ለቤተሰቤ ጫማ እንደሚሠራ ልትዘነጋ አይገባም" ሲል ምክር ቤቱ በአንድ አፍ ሳቀ፤ ባላባቱ አብርሃም ሊንከን ላይ አላገጠበት ብለው አስበዋልና።

አንዳንድ ሰዎች ግን ሲፈጥራቸውም ልዩ አርበኛነትን ተላብሰዋልና ሊንከን ያላገጠበትን ሰውዬን ዐይን ዐይኑን እያየ እንዲህ አለ፦ "ጌታዬ ሆይ፥ አባቴ ለቤተሰብዎ ጫማ እንደሚሠራ አውቃለሁ፤ በዚህ ምክር ቤት ውስጥ ለሚገኙ ለበርካቶችም ጭምር፤ ምክንያቱም እሱ ጫማ እንደሚሠራው ማንም ሰው አይሠራምና። እሱ ፈጣሪ ነው። የርሱ ጫማዎች ጫማዎች ብቻ አይደሉም፤ ነፍሱን በመላ ያፈሰሰባቸው የተሰጥኦ ውጤት እንጂ። እስቲ ልጠይቆት፣ አባቴ በሚሠራቸው ጫማዎች ቅሬታ አለዎት? - ምክንያቱም እኔ የጫማ ሙያን ጠንቅቄ ስለማውቅ ምንም አይነት ቅሬታ ቢኖርዎት ሌላ ጫማ ልሠራልዎት እችላለሁ። ይሁንና እኔ እስከማውቀው ድረስ ማንም ሰው በአባቴ ጫማዎች ላይ ፈፅሞ ቅሬታ አቅርቦ አያውቅም። እጅግ ብልህና ታላቅ ሥራ ፈጣሪ ስለሆነ እኔም በአባቴ እኮራለሁ"። ምክር ቤቱ ረጭ አለ፤ ሁሉም ሰው አንገቱን አቀረቀረ።

ልብ በል፤

• ምንጊዜም ቢሆን፤ የገጠመን ነገር ሳይሆን ለገጠመን ነገር (ጉዳይ) የሰጠነው ምላሽ አይነት ነው እኛን የሚጎዳን ወይም የሚያጸናን።

• መርከቦች ዙሪያቸውን በከበባቸው ውሃ አይሰጥሙም፣ ወደ ውስጣቸው በሚያስገቡት ውሃ እንጂ፤ ልክ እንዲሁ በዙሪያህ እየሆነ ያለውን ነገር ወደ ውስጥህ እንዲገባና ተጭኖም እንዲጥልህ አታድርግ።

ማንም ሰው ይሁን ምንም ነገር አንተን ሊጎዳ የሚችለው ፍቃድህን ከሰጠኸው ብቻና ብቻ ነው!!

በድጋሚ የተለጠፈ

/channel/theideaofs

Читать полностью…

የዘር ሐሳቦች/ Yezer Hasaboch

#በሰዎች_ስኬት_የሚቀኑ_ሰዎች!!

ስኬትን የሚሰጥ እግዚአብሔር ነው። በስራህ በትዳርህ፣ በአገልግሎትህና በሞገስ የሚባርክ እግዚአብሔር ብቻ ነው፤ የእውነተኛ ስኬት ምንጭ እግዚአብሔር ነው። ስኬታማ መሆን ስትጀምር ግን የስኬትህን ጠላቶች ማየት ትጀምራለህ።

ስኬትህን መቀበል የማይፈልጉ ሰዎች ሁልጊዜ ይኖራሉ። በሚያሳዝ መልኩ እንደነዚህ አይነት ሰዎች የሚያጋጥሙት የቅርቤ ከምንላቸው አካባቢ ጭምር እናያለን። ስኬትህ የሚያስደስታቸው በእርግጥ ውድቀትህ ያሳዝናቸዋል፣ ስኬትህ የሚያናዳድዳቸው ውድቀትህ ያስደስታቸዋል። ይጠብቁታልም።

እነዚህ አይነት ሰዎች የሰራህንውን የማጣጣል፣ በሰዎች በፊት ውጤትህን በማዋረድ አንተን ዝቅ የሚያደርጉ ይመስላቸዋል። እነዚህ አይነት ሰዎች ይፈሩሃል፣ ሐሳባቸው አንተ ብቻ ነህ። እነርሱ እንዴት ስኬታማ መሆን እንዳለባቸው ከማሰብ ይልቅ የአንተ ስኬት ያ.ን.ገ.በ.ግ.ባ.ቸ.ዋ.ል።

የለፋህውን ትልቅ ልፋት ሳይሆን የተሳሳትከውን ጥቂት ስህተት ይቆጥራሉ። የመጣህበትን መንገድ ርዝመትና የብቸኝነት ትግል ላለመቀበል፣ ለስኬትህ እነ እንትና ረድተውት እኮ ነው ይላሉ። እንደዚህ አይነት ሰዎች 'አውቀዋለሁ' እርሱ እንዲህ እኮ ነው ማለትን ያወዳሉ። ቢሆንላቸው አንተ ያለህበት ስኬት ጋር መምጣት ምኞታቸው ነው፣ ስላላገኙት ብቻ ያገኙትን ሰዎች ለማሸማቀቅ ይሰራሉ። ስኬት የስራ ውጤት እንጂ የትችት ውጤት አይደለም።

ስኬትህን ላለመቀበል ጥረህን ላለማድነቅ የስራህን ምስጋና ለሌላ ሰው ይሰጣሉ። ማጣጣል እና ማናናቅ መጠቀሚያ ቀስታቸው ነው። ቢሆንላቸው ጓደኛቸው እንድትሆን ይፈልጋሉ ካልሆነላቸው ይቃወሙሃል፣ በፊት እንደፈለጉ ያደርጉህ የነበሩ ስኬትን ማግኘት ስትጀምር ጦራቸው ይነሳል፣ ምክንያቱም አንተን እንደፈለጉ የማድረግ ሐይላቸው ስለሚያጡት።

የሰዎች ደስታ ደስታችን፣ ስኬታቸው ደስታችን ነው። ጥረታቸውን እናደንቃለን ስኬታቸውን እናከብራለን። ቅናትና ምቀኝነት፣ እበለጣለሁ ብሎ ማሰብና የልብ ክፋት ሰዎች ሲያድጉ ደስ እንዳይለን የሚያደርጉ ነገሮች ናቸው። የሰው ስኬት የአንተን ስኬት በፍጹም አይነካም። ውድቀት ያለው ሰዎችን ከስኬታቸው ለመጣል በምታደርገው ጉዞ ውስጥ ነው።

ትንሽ ለውጥና ትንሽ ስኬት ስትጀምሩ ከስር ብቅ ብቅ ብለው የሚርመሰመሱ የቅርብ-ጠላቶችን ማስተዋል ትጀምራላችሁ። ያን ጊዜ የስኬት ጉዞን እንጀመራችሁ አስተውላችሁ ጉዞአችሁን ቀጥሉ። የእውነት በሆነ የስኬት ጎዳና ስትሆን ደግሞ እግዚአብሔር የስኬትህ ጠባቂና ባራኪህ ይሆናል።

ዘሪሁን ግርማ


/channel/theideaofs

Читать полностью…

የዘር ሐሳቦች/ Yezer Hasaboch

#ብዙ_ጉራ - #ጥቂት_እውቀት!

ማሃትማ ጋንዲ "The Story Of My Experiments with Truth" በተሰኘው የህይወት ታሪ መጽሐፋቸው (ማሃትማ-ጋንዲ ተብሎ በአማርኛ ተተርጉሟል) በገጽ 81 ላይ እርሳቸው በነበሩበት ዘመን አንዱ አስቸጋሪው ነገር 'ብዙ ጉራ ጥቂት እውቀት' እንደነበር ይናገራሉ።

ይህም ዘመን ልክ እንደዚያኛው ዘመን በሁሉም የህይወት ዘርፎች ላይ ብዙ ጉራና ጥቂት እውቀት የበዛበት ጊዜ ይመስለኛል። ሰው ሁሉ ራሱን እንደ አዋቂ የሚቆጥርበት ነገር ግን እውቀት ጠል የሆነበት ዘመን ነው! በብዛት። ህይወትም ብዙ ጉራ በተሞሉ ቀረብ ስትላቸው ምንም እውቀት የሌላቸው ሰዎች መገኛ እየሆነች ነው።

እውቀት ባለበት ጉራ አይኖርም። ብዙ መመካትና ብዙ ጉራ ባለበት ደግሞ እውቀት ተግባራዊ አይሆንም። በፖለቲካው፣ በመንፈሳዊ ቤቶች፣ በሰዎች ትዳር፣ በማህበረሰብ ውስጥ ብዙ እውቀት ያላቸው ሰዎች ሳይሆን ያሉን ብዙ ጉራ ያላቸው ሰዎች ናቸው ብል ትክክል ነው።

ጉረኛ ከማንም ለመማር የተዘጋጀ አይደለም፣ ይልቅ ሁሉም እንደሚያውቅ ያስባል። በዚህ ዘመን ውስጥ ብዙ ጉራና ጥቂት እውቀት ያላቸው ሰዎች በሁሉም መንገድ ያጋጥሙናል። ይህ ዘመን ከእውቀት ይልቅ ጉራ ከፍ ያለበት ጊዜ ነው ብል ማጋነን አይመስለኝም።

ብዙ እውቀት ያላቸው ሰዎች ጉራን ስለሚጠሉ እውቀታቸው ታላቅ ስብዕናን ስለሚሰጣቸው ጉረኛና ትምህክተኛ አይሆኑም። ትክክለኛ እውቀት የሚሰጠንን ትህትናን ነውና። እኛ ከእነዚህ አይነት ሰነፎች (ጉረኞች) መሐል እንዳንሆን ራሳችን ላይ መስራት አለብን። ብዙ እውቀትን= የበዛ ትህትናን ማዳበር ይኖርብናል።

ዘሪሁን ግርማ

/channel/theideaofs

Читать полностью…

የዘር ሐሳቦች/ Yezer Hasaboch

#የእኛ_የሆነ_ዕድሜ_የለንም_የተሰጠን_እንጂ!

ትናንት አንዲት ጓደኛዬ ስለነበረችበት ለቅሶ ቤት ስትነግረኝ የሞተው ልጅ ገና ወጣትና 20 አመት የሆነው ወጣት ልጅ እንደሆነ አዝና አጫወተችን። የሞተው የ70 ወይም የ80 አመት ሰው ቢሆን ሐዘኑ ይቀንሳል መኖር ያለባቸውን ዕድሜ ኖረዋልና። ላወራ የፈለኩት የዕድሜ ቅነሳ ጉዳይን ነው ብዙዎች ሰዎች ዕድሜን ቀንሶ የመናገር ችግር አለብን (አብሶ ሴቶች) ይህን ስል ወንዶችም የሉም ለማለት አይደለም። ምክንያቱ ብዙ ቢሆንም፣ እንዱ እርጅናን መፍራት ብለን መውሰድ እንችላለን፣ ሌላኛው አለማግባት አላሳካናቸውም የምንላቸው ነገሮች ሲኖሩ ዕድሜያችንን መናገር እንፈራለን ወይም ቀንሰን እንናገራለን። እርጅና ክብር ሲሆን በተሰጠን ዕድሜ ትክክለኛ ነገር ሰርቶ ማለፍ ደግሞ ጥበብ ነው።

ብዙዎቻችን ያለ ዕድሜያቸው የሞቱ ወጣቶችን በተመለከተ እናዝናለን፣ ደግሞ የኖርንባቸውን ቀኖች ቀንሰን እንናገራለን። የዕድሜን የመኖርን ትርጉም የሚገባን ያለ ዕድሜ መቀጨት የሚባል ነገርን ስላልተረዳን ይሆን? ስለዚህም ስለሰጠን ዕድሜ ልናመሰግን ይገባል።

የእኛ የሆነ ዕድሜ የለንም የተሰጠን እንጂ። ስለ ኖርባቸው ቀኖች እግዚአብሔር ይመስገን ስለ ምንኖርባቸው ቀኖችም እግዚአብሔር ይመስገን። የኖርንባቸው ሆነ የምንኖርባቸው ቀኖች ከእግዚአብሔር የተሰጡን ናቸው።

የማንወዳቸው ወይም ጥሩ ያልሆኑ ጊዜያትን ያላሳለፍንባቸው ወቅቶች ቢኖሩንም እንኳ፣ ዋናው ነገር ዛሬ በህይወት አለን። የተሻለ ህይወት የመኖር ዕድሉ አለን ቀኖች በአጋጣሚ አይሰጡንም። ትናንት እንዲሆኑ ፈልገን ያልሆኑልን ነገሮች ዛሬ ዕድሜያችን የተቀጠለባቸው ምክንያት ሊሆኑም ይችላሉ ማን ያውቃል? ነገሮች ትናንት ያልሆኑትን ለዛሬ ሊጠብቀን ሊሆን ይችላል። እግዚአብሔር ለእኛ ያሰበው በረከት እኛ በህይወት እስካለን ድረስ አለ። ማወቅ ያለብን ቀኖች አጥረውባቸው ብዙ ነገር ለመፈጸም እያሰቡ ያለፉ ብዙዎች አሉ ዛሬ አንተ እነርሱ ያጡትን ትንፋሽ እየተነፈስክ አለህ። በምንም ነገር ውስጥ እያለፋችሁ ይሆናል ህይወታችሁ እናንተ በፈለጋችሁት መንገድ እየሄደ ላይሆን ይችላል፣ ተስፋ የሌለው የሞተ ብቻ ነው። በህይወት እስካላችሁ ድረስ ሁሉንም ነገር የመቀየር ዕድሉ አላችሁ።

በተጨመረልህ ቀን ዕድሜን መቀነስ እግዚአብሔር እንድንኖር አስረዝሞ የሰጠንን ዕድሜ እንደማሳጠር ነው። እኛ ያልፈጠርነውን ተፈጥሮ የተሰጠንን ዕድሜ መቀነስ የእግዚአብሔርን ቸርነት እንደ አለመቀበል ነው። ማወቅ ያለብን የተሰጠን ዕድሜ ከኃላችን ጋር እያየን እንድናዝን ሳይሆን ወደ ፊት እየሄድን በደስታ እንድንኖርበት ነው። በየቀኑ ማለዳ ስንነሳ ይህን መዝሙር መዘመር አለብን

የዕድሜን ቀናት የጨመርክልኝ
ደጉ ጌታዬ ተመስገንልኝ
......

ነጋልኝ ደግሞ ላመስግነው
............

ዘሪሁን ግርማ

/channel/theideaofs

Читать полностью…

የዘር ሐሳቦች/ Yezer Hasaboch

#መርዛማ_ንግግሮች (የእፉኝት መንደፊያ)

በማህበራዊ ሚዲያዎች፣ በሰዎች የዕለት ተዕለት ህይወት ውስጥ፣ እንዲሁም ባለን በማንኛውም ግንኙነት ውስጥ ቀስ ብሎ የሚገል መርዝ የሆነ ነገር መርዛማ ንግግሮች ናቸው። ብዙ አገልጋዮችን ሽባ አድርገዋል ብዙ ሰዎችን ፈሪ አድርገዋል። የሚነገሩ ንግግሮች በሰዎች ትልቅ ተጽዕኖ ስላላቸው ነው።

“ማንም ሰው የሚናገር ቢሆን፥ እንደ እግዚአብሔር ቃል ይናገር.."
— 1ኛ ጴጥሮስ 4፥11

በፌስ ቡክ በዩቲዩብና በቲክቶች የሚደረጉ ንግግሮችና ከሰዎች አንደበት የሚወጡ ጥላቻ የተሞሉ እና የተንኮልን ዘር ያነገቡ፣ ጠላት ሰዎችን በሰዎች አንደበት አልፎ ለመግደል ወጥሮ ያዘጋጃቸው ቀስቶች ናቸው። አንዳንዶቹ ከመንፈሳዊ 'ነኝ' ከሚል ሰው ቀርቶ ከማንኛውም ሰው የማይወጡ ናቸው። ቃል አዋቂዎች እና ነገር ሰንጣቂዎች ስለሆኑ የገዛ ወንድማቸው ላይ ጠንካራና ነፍስ የሚሰብር ንግግር ሲናገሩ ርኅራኄ አይሰማቸው።

በሰዎች ላይ የምንረጫቸው መርዛማ ቃሎች የሰዎችን አገልግሎት ብቻ ሳይሆን፣ የትዳር አጋራቸውና የልጆቻቸውን ስነልቦና ላይ ጭምር መርዝ እንደ መጨመር ነው። እንደዚህ አይነቶች በመንፈሳዊ ቋንቋ የዳበረ የክፋት ቃል አላቸው። የሚያቀርባቸው ንግግሮች ለጌታ ያሰቡና ለቤቱ የቀኑ በሚመስል መንፈሳዊ ንግግሮች ተሸፍነዋል። ነገር ግን መጽሐፍ ቅዱሳዊ የሆነው ንግግራችን "በጨው እንደ ተቀመመ ይሁን" ሳይሆን 'በመርዝ እንደተለበጠ' ዳቦ ነው። መምከር፣ መገሰጽ፣ ማረምና፣ ማቅናት በራሱ ጸጋን ይጸልጋልና።

“ለእያንዳንዱ እንዴት እንድትመልሱ እንደሚገባችሁ ታውቁ ዘንድ ንግግራችሁ ሁልጊዜ፥ በጨው እንደ ተቀመመ፥ በጸጋ ይሁን።”
— ቆላስይስ 4፥6

ጨዋዊ፣ ክርስቲያናዊ፣ መጽሐፍ ቅዱሳዊ የእርምት መንገዶች አሉ እኮ፣ ፍቅርንና እውነትን የተከተሉ የሆኑ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሰረቶች አሉ እኮ። አጠፋ የምንለውን ሰው የምንናገረው ለማዳን ከሆነ አላማችን የሚገሉ ቃሎችን ለምን እንጠቀማለን? አጠፋ ብለን ለምንጠራው ሰው 'የሞትነውና የተሰቀልነው' እኛ አይደለንም የማረ፣ የታገሰ፣ የወደደ፣ ይቅር ያለ አምላክ አለ። ልክ እኛን ይቅር እንዳለን።

ሰዎች በሰዎች ቀንተው እንዲሁም ካላቸው ጥላቻ መርዛማ ንግግሮችን ሲናገሩ መስማት የተለመደ ነው። የአብዛኞቹ ምንጭ ይህው ቅናትና ጥላቻ ነው። ሌላው ሰዎች ደከመው ሲገኙ ሰዎች ነገ ከጥፋቸው ተነስተነው ወደ አገልግሎት የሚመልስ 'መጽሐፍ ቅዱሳዊ' መሰረትን የተከተለ አነጋገርና ማስተማርና እያለ የሰዎችን ህይወት የሚሰብር፣ የትዳር አጋራቸውን እና ቤተሰቦቻቸውን የሚያሸማቅቁ ቃሎች እና አነጋገሮች ሰዎችን ለመስበር ሰይጣን በሰዎች ውስጥ የወጣራቸው መርዛማ ቀስቶች ናቸው። ሁላችንም ስለ ምናገራቸው ንግግሮቻችን መልስ እንሰጥበታለን።

“አንደበትም እሳት ነው። አንደበት በብልቶቻችን መካከል ዓመፀኛ ዓለም ሆኖአል፤ ሥጋን ሁሉ ያሳድፋልና፥ የፍጥረትንም ሩጫ ያቃጥላል፥ በገሃነምም ይቃጠላል።”
— ያዕቆብ 3፥6

ዘሪሁን ግርማ

/channel/theideaofs

Читать полностью…

የዘር ሐሳቦች/ Yezer Hasaboch

ለዘር ሐሳቦች ገጽ ቤተሰቦችን እንኳን ለትንሳኤው መታሰቢያ ቀን አደረሳችሁ።

Читать полностью…

የዘር ሐሳቦች/ Yezer Hasaboch

#የአፍ_ወለምታ_በቅቤ_አይታሽም!!

ሳትናገረው ነበር እንጂ ከተናገርከውማ በኃላ አንዴ ካ'ፍህ ወቷል ምን ታደርጋለህ? ሰው በልቡ እንዳሰበ እንደዚያው ነው። ስለዚህ ሰው በልቡ ያስብ የነበረውን ነገር ባልታሰበ ሰአት ሊናገረው ይችላል ወይም ደግሞ ያልተጠበቀ ንግግር በድንገት አምልጦት ሊናገር ይችላል። እንደዚህ አይነት ቃላት አብሶ ከወዳጅ ከጓደኛ፤ ከቤተሰብ፤ ወይም ከቅርብ ሰው ሲወጣ ጉዳቱ ቀላል አይሆንም።

ያልተጠበቀ ነገር መናገር፤ ውሸትን መናገር፤ የሌለ ነገር ፈጥሮ ማውራት የሚጎዳ ነገርን መናገር የብዙ ሰዎችን ህይወት ሊያዳክም፤ ሊጎዳቸው ይችላል። አንዳንድ ሰዎች ንግግራቸው ብቻ ሳይሆን የሚጎዳው ወዳጅነታቸው እና ያልተጠበቀ ቃል ሊሆን ይችላል። የአፍ ወለምታ በቅቤ አይታሽም ንግግርን መቆጣጠር መልመድ ብስለት ነው።

ንግግርህን መቆጣጠር ልክ ከተማን እንደ መቆጣጠር ነው። የመጣልህን ከመናገር፤ ውሸትን ከመናገር፤ ሐሜትን ከማውራት መቆጠብ ብስለት ነው። እንደዚህ አይነት ነገር ለብዙ ዘመን የገነባህውን ወዳጅነት ሊያሻክር፥ አስፈላጊ ሰዎችን ሊያሳጣን ይችላል። ከመናገር በፊት ማሰብ እንጂ ከተናገርን በኃላ ማሰብ ጥበብ አይደለም። አንዴ ካመለጠን በኃላ ያንን ነገር ለማደስ መፍትሄው ይቅርታ ብቻ ነው። ምክንያቱም ከአፍህ አንዴ ካመለጠ በምንም አታስተካክለውም!! ለንግግርህ እና ለአነጋገርህ ትክክለኛ መስመር ካበጀህ አንተ በስለሃል ማለት ነው።

ንግግርህን ብቻ ሳይሆን አነጋገርህን ጭምር መቀየር ማስተካከልና እንደ መጽሐፍ ቅዱስ ማድረግ ያስፈልጋል። ንግግር ከአፍ አንዴ ከወጣ አይታረምም። አብረውን ስላሉ ሰዎች ለምናወራቸው ማንኛውም አይነት በፊታቸው ሆነ ከጀርባቸው ስለ ምንናገራቸው ነገሮች ጠንቃቃ መሆን ወዳጆችን ከማጣት ይረዳናል። ለዚህ ነው መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ የሚለን፦

ያዕቆብ 3
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁵ እንዲሁም አንደበት ደግሞ ትንሽ ብልት ሆኖ በታላላቅ ነገር ይመካል። እነሆ፥ ትንሽ እሳት እንዴት ያለ ትልቅ ጫካ ያቃጥላል።
⁶ አንደበትም እሳት ነው። አንደበት በብልቶቻችን መካከል ዓመፀኛ ዓለም ሆኖአል፤ ሥጋን ሁሉ ያሳድፋልና፥ የፍጥረትንም ሩጫ ያቃጥላል፥ በገሃነምም ይቃጠላል።

ዘሪሁን ግርማ

/channel/theideaofs

Читать полностью…

የዘር ሐሳቦች/ Yezer Hasaboch

"ፈቃድህ በሰማይ እንደሆነ እንዲሁም በምድር ትሁን።"

** በፈቃድህ ፣ ለፈቃድህ ብቻ ልኑር !

* የማልደርስበትን ጉዞ አታስጀምረኝ

* የማላሸንፈውን ጦርነት አታዋጋኝ

* የማይመለስ ጥያቄ አታስጠይቀኝ

* የማላገኘውን ነገር አታስፈልገኝ

* የማይጸድቅ ችግኝ አታስተክለኝ

* የማይፈታ ሕልም አታሳልመኝ

** በቃ ! በፈቃድህ ፣ ለፈቃድህ ብቻ ልኑር !

/channel/theideaofs

Читать полностью…

የዘር ሐሳቦች/ Yezer Hasaboch

#እየሄድክ...#እየሄድሽ!!

ህይወት ወደ ነገ እንጂ ወደ ትናንት አታድግም። ከትናንት ከተማርንበት ዛሬ ብርታት ለነገ ደግሞ አቅም ይሆናል። ማንኛውም ሰው ትናንት ነበረው ዛሬ አለው እግዚአብሔር ከፈቀደለት ነገ አለው። ሰው በሶስቱ የተገመደ ሲሆን ፍጻሜው ግን ነገ ነው። ወደ ትናንት የሚጎትት ነገር ብዙ ሲሆን ዛሬ ላይ እንድትቀር የሚታገልም ብዙ ነው። ውጤቱ ግን ያለው ነገ ላይ ነውና እየሄድክ..እየሄድሽ።

ወደ ፊት እየሔድክ ካልሆነ በትናንት ታስረሃል ወይም ዛሬ ላይ አንቀላፍተሃል። መርሳት የሌለብህ ነገር በትናንትና ላይ ከቆየህ ሰው አይቃወምህ ዛሬም እንደ ተራ ካለህ ማንም አይቃወምህም ነገ ላይ ለመቆም ስትራመድ ግን ከትናንትህ ድካም፥ ከዛሬው ያልተሳኩ ነገሮች ትግል ይገጥምሃል። ቢሆንም ግን እየሄድክ...እየሄድሽ።

ጉዞአችን በእርሱ በወደደን እና በተሸከመን ነውና ህይወታችን እርሱ ነውና፥ አምላካችን ተደግፈን በእርሱ እየተመራን፥ በመንገዳችን እንሄዳለን።

“ኃይልን በሚሰጠኝ በክርስቶስ ሁሉን እችላለሁ።”
— ፊልጵስዩስ 4፥13

“ኃይልን የሚያስታጥቀኝ፥ መንገዴንም የሚያቃና፥”
— 2ኛ ሳሙኤል 22፥33

"እግዚአብሔር ከሚራመድ ጋር ይረመዳል፥ ከሚሮጥ ጋር ይሮጣል፥ ከሚበር ጋር ይበራል፥ ከሚሰራ ጋር ይሰራል፥ ከሚቀመጥ ጋር ግን አይቀመጥም"
ወንጌላዊ ሪንሃርድ ቦንኬ

ስለዚህ እየሄድክ..እየሄድሽ..እየሄድን..እንጂ ተቀምጠን አንገኝ።

©ዘሪሁን ግርማ

/channel/theideaofs

Читать полностью…

የዘር ሐሳቦች/ Yezer Hasaboch

#ስኬት የሚመዘነው በሚታየው ነገር ላይ ሳይሆን ስር በሰደድክበትና በተመሰረትክበት ትክክለኛ መሰረት አንጻር ነው። ስር ያልሰደደና በትክክለኛ መሰረት ላይ ያልተመሰረተ ስኬት ለጊዜው የብዙዎችን ልብ ቢማርክም፣ የሚጸናና የሚወርስ ግን አይሆንም። እንዲታይልህ ከምትፈልገው ስኬት ይልቅ መሰረትህ ላይ ስራ ያኔ ዘላቂ ስኬት ይኖርሃል።

Читать полностью…

የዘር ሐሳቦች/ Yezer Hasaboch

#ለምጣዱ_ሲባል_አይጧ_ትለፍ!!

ይህ አባባል የቆየ የአገራችን አባባል ነው። ይህን አባባል አሁን በግል ህይወታችን ሆነ እንደ አገር ለምናልፍበት ሁኔታ ልንመነዝረው እንችላለን። አንዳንድ ሁኔታዎችን የመታገሱ ምክንያት ሆነ ወይም አልፎ የመሔዳችን ምክንያት የአይጧ ትልቅነት ወይም የህይወታችን ወሳኝ ነገር ሆና ሳትሆን ያረፈችበት ምጣድ ለእኛ ብዙ ነገራችን ስለሆነ ነው።

በተለያዩ መንገድ እንደ አይጧ ያሉ ሆኔታዎች ያጋጥሙናል። በግል ህይወት፣ በቤተሰብ፣ በስራ፣ በአገልግሎታችን ባለን ማንኛውም ነገር የምንታገሳቸው። ያለ ትዕግሥትና ጥበብ አይጧን ለመግደል ስንነሳ ያረፈችበት ምጣድ ለህይወታችን አስፈላጊ ነገር ነው። ስለዚህም እንታገሳለን።

እንደ አይጧ ያሉ ሁኔታዎች እስኪያልፉ ስንታገሳቸው የታገስናቸው እነሱን ሳይሆን ሞጣዱን ስለምንፈልግ መሆኑን አይረዱም። ለታላቁ ነገር ስንል ትንንሽ ነገሮችን ማለፍ ታላቁን ነገር ያተርፈዋል። ከታናናሽ ነገሮች ጋር መፋለም አሰልቺ ቢሆንም፣ ታላላቅ ነገሮችን የምንጠብቀው አንዳንዴ እንደ አይጧ ያሉ ነገሮች እስኪያልፉ በመታገስ ጭምር ነው።

ትላልቅ ነገሮችን ለማዳን ትናንሽ ነገሮች እስኪያልፉ መታገስ ያስፈልጋል።

ዘሪሁን ግርማ

/channel/theideaofs

Читать полностью…

የዘር ሐሳቦች/ Yezer Hasaboch

#ግብዝነት_ከሞላበት_ህብረት_ራስን_መጠበቅ

ፍቅር ከሌለበት መተቃቀፍ፥ ከልብ ካልሆነ ፈገግታ በማስመሰል ከሆነ ህብረት፥ ሌሎችን በመኮነን ውስጥ ካለ ራስን ማጽደቅ፥ ግለኝነትና ለቤተክርስቲያን ተቆርቋሪ መስሎ ለመታየት ከሚደረግ ጎራ ራስን መጠበቅ እጅግ ያስፈልገናል። ቤተክርስቲያን የክርስቶስ ናት እርሱ ደግሞ ለዳኑት ሁሉ አባት ነው። የምናደርገውን ሁሉ በፍቅር ማድረግ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ነው ከዚያ ውጪ ከሆነ ግን ማስመሰል አይጠበቅብንም። ግብዝነት ሐጢያት ነው። ሰዎችን ለማረም ስንነሳ ወይም ህብረት ስናደርግ ከፍቅር ማድረግ ያስፈልገናል። የምናደርገው ሁሉ ከፍቅር ከጎደለ ምንስ ጥቅም አለን?

ዘሪሁን ግርማ

/channel/theideaofs

Читать полностью…

የዘር ሐሳቦች/ Yezer Hasaboch

#ለመወደድ_ራስህን_ባሪያ_አታድርግ!!
ዘሪሁን ግርማ

"ለስኬት የሚዳርጉ መንገዶችን ሁሉ ባላውቅም ለውድቀት የሚዳርግ ትልቁ ነገር ሰዎችን ለማስደስት ( በሰዎች ለመወደድ) መስራት ነው።"
ሪክ ዋረን

መውደድና መወደድ ከህጻንነት ዘመናችን ጀምሮ በውስጣችን ያለ ጤናማ ተፈጥሮ ነው። ሰው ያለ ፍቅር መኖር አይችልም። የህይወት ትልቁ ገመድ የታሰረው እዚህ ፍቅር ጋር ነው። የእናትና የአባት ፍቅር፤ የእህት ወንድም ፍቅር፤ የጓደኛ ፍቅር፤ የተቃራኒ ጾታ ፍቅር፤ የሚስትና የልጆች ፍቅር ፤ የአገር ፍቅር ወዘተ እያልን መቀጠል እንችላለን።

ሰዎች ስለሆንን የማፍቀር ስሜት ብቻ ሳይሆን ያለን የመፈቀርና የመወደድ እንዲሁም የመፈለግ ስሜታችን ከፍ ያለ ነው። እንደዛ ቢሆንም ትልቁ ችግር የሚጀምረው ሰዎች እንዲወዱንና እንዲቀበሉን 'ብቻ' ስንሰራ ነው። የእኛ ስራ ሰዎችን መውደድና ትክክለኛ ስራ መስራት ብቻ ነው እንጂ እንዲቀበሉን ማስገደድ ወይም ማሳመን አይደለም። ሰዎችን እንዲወዱን ማስገደድ አንችልም።

ማንነታችንን በሰዎች ላይ ከገነባን የሰዎች ስሜት በተለዋወጠ ቁጥር ህይወታችን ይመሰቃቀላል ጭንቀትና ፍርሃት ይይዘናል። ሁላችንም ውስጥ ያለመፈለግና ያለመወደድ ፍርሃት አለብንና። ሰዎች ባይወዱኝስ የሚል ፍርሃት ትልቁ የህይወት ፈርሃት ነው። ከዚህ የተነሳ የሰዎችን ፍቅር ለማግኘትና ለመወደድ ስንል ያልተገባ መሰጠትና ሰዎችን የማስደሰት ባርነት ውስጥ ልንገኝ እንችላለን።

ሰዎችን መወደድ ስትችል ሰዎች ይወዱሃል። ባይወዱህ እንኳ የአንተ ሐላፊነት ሰዎችን መውደድና ማንነትህን አክብረህ መሔድ ብቻ ነው። ለመወደድ ብለህ አትስራ ትክክለኛን ነገር ስራ። ስራህ ትክክል ከሆነ ሰዎቹ ባያስተውሉት እንኳ ስራህ መልሶ ያከብርሃል። ሰዎችን ለማስደሰት መስራት የሰዎቹ ባሪያ ያደርግሃል። በኑሮም እንደዛው ነው። አንተ መሆን የምትችለው መሆን ያለብህን ነው። ፍቅርና ጎሽታን ለማግኘት ብለህ ባሪያ አትሁን።

፨ሰዎቹ ፈገግ ባሉልህ ጊዜ ደስ የሚልህ ሲሶሳተሩ የምትደነግጥ አሻንጉሊት አትሁን። የራስህ አቋምና ማንነት ይኑርህ።

፨ የተገባህን ነገር አድርግ፤ እንዲወዱህ ብለህ በምንም መልኩ የሰዎች ባሪያቸው አትሁን።

.......
Zerihun G Girma
ቴሌግራም ቻናሌን ይቀላቀሉ!!
/channel/theideaofs

Читать полностью…

የዘር ሐሳቦች/ Yezer Hasaboch

#በመልቀቅ_መዳን!!

የምንታገልባቸው ብዙዎቹን ነገሮች ስንመለከት የእኛ አይደሉም ወይም፣ ያለ ቦታቸው ቦታ ሰተናቸዋል፣ ወይም ያለ አግባብ የያዝናቸው ናቸው። በዚያም ምክንያት ያለ አግባብ ዋጋ እንከፍላለን። ግንኙነቶች፣ ጓደኝነት የተቃራኒ ጾታ ጓደኝነት ( Relationship) ወይም ከሰዎች ጋር ያለን ማንኛውም አይነት እንደማይቀጥሉ እየገባን ግን በትግል ለማስኬድ የምንታገልባቸው ግንኙነቶች ጉዳታቸው ከፍተኛ ነው። ባለ መልቀቅ ውስጥ የሚደረግ ዋጋ መክፈል ይባላል።

በግድ፣ በትግል፣ ከአንድ ሰው ብቻ በሚደረግ ጥረት የተገነባ ግንኙነት አስፈላጊ አይደለም ። በዚህ አይነት ግንኙነት ውስጥ ከሆንክ ለቀቅ አድርገው ለጊዜው የተጎዳህ ቢመስልም ነገ ግን ህይወትህን ዕድሜህንና ሐይልህን ትታደግበታለህ። የአንተ ያልሆነውን በግድ የአንተ ለማድረግ መታገል ከንቱ ዋጋ መክፈል ነው።

በዚህ አይነት ግንኘቱነት ውስጥ ከሆንክ ልቀቅ (ቂ) የአንቺ ካልሆነው ስትታገይ የአንቺ የሆነው ያመልጥሻል (ሃል) ልቀቅ (ቂ)። የአንቺ ህይወት የማይቀጥለው ያለ አንቺ ብቻ ነው። ከሚያደክም ከማያፈራና፣ ፍጻሜ ከሌለው ግንኙነቶች ተላለቀቁ።

ዘሪሁን ግርማ

/channel/theideaofs

Читать полностью…

የዘር ሐሳቦች/ Yezer Hasaboch

#ባለራዕይ_እና_አገልጋይ_መሪነት

መሪነት ትልቅ ስራ የምንሰራበት እና ትልቅ ውጤት የምናመጣበት እንዲሁም በትክክል ካልሰራንበት ትልቅ ጥፋት የምናደርስበት ስፍራ ነው። ከሁሉ በላይ ግን መሪነት በራሱ በመጀመሪያ ረድፍ ያለ ከባድ ስራ ነው። ከዚህ መሐል በመሪነት አቅጣጫ ሁለት አይነት አመራርን ስትከተል ደግሞ መንገዱ እጅግ ያታግላል። እጅግ በጣም በጥቂቱ ስለ ሁለቱ አንነት መሪነቶች አንይ። ባለራዕይ አገልጋይ መሪ።

ባለራዕይ መሪ

ከምንም በላይ መሪ ባለራዕይ መሆን ይኖርበታል። የሚመራውን ህዝብ፣ ተቋም ወዴት እንደሚያደርስ ማወቅ ይኖርበታል። መሪነት ሁሉም ጣቱን አንተ ላይ ለመቀሰር ምቹ ነው ያለኸው ከፊት ነህና፣ የምታመጣቸው ሐሳቦች ሁልጊዜ ሶስት አይነት ጠማማ ልብ ባላቸው ሰዎች ተቃውሞ ይደርስበታል

፨ እነርሱ አይሰሩም ያንተን መስራት ግን በማይፈልጉ ሰዎች፣ እንከን ለቃሚዎች ሁልጊዜ ስራህን የማይታዘዙ ሰዎች

፨ የሐሳብ ልዕልና ስለሌላቸው ሐሳብህን መከተል ወይም በተሻለ ሐሳብ አንተን መምራት ስለማይችሉ ሁልጊዜ የምታደርገውን ነገር ሁሉ ይቃወማሉ

፨ ክፉ ልብና የማይታዘዝ አኪያሄድ አላቸው፦ ልክ እንደ ብዙዎች መሪዎች ላይ የመሰናክል ድንጋይ ያስቀምጣሉ እንጂ መመራት አይችሉም። ብዙዎች ሐሳብ የላቸውም ሐሳብን ግን ይቃወማሉ

ባለማወቅ የሚያጠፉም አሉ፤ እነዚህን አስተምሮ ወደ ማወቅ ማምጣት የመሪ ሐላፊነት ነው። ባለራዕይ መሪ ስትሆን ከላይ ያነሳቸው ነገሮች እጅግ ያጋጥሙሃል። እነዚህን አይነት መሰናክሎች ማለፍ ካልቻልክ ራዕይህን መፈጸም አትችልም።

ሁሉም ሰው በሚባል ደረጃ ራዕይ ይዘህ ስትመራ ይቃወምሃል ወይም ከአንተ ጋር ባለመተባበር ሐይሉን ይከለክልሃል፣ ውጤት ስታመጣ ግን ይከተልሃል፣ ያጨበጭብልሃል። ብቸኝነትን ከፈራህ ውጤታማ ባለራዕይ መሪ መሆን አትችልም። እየታገልክ ያለኸው በገሃድ የሌለን ነገር ለማምጣት ነው። ባለራዕይ መሪ ሁልጊዜም ተቃውሞ አያጣውም፣ በኃላ ላይ ግን ታሪክ ሰሪው እርሱ ነው።

አገልጋይ መሪነት

መሪ አገልጋይነት እጅጉን በጣም ሰፊ ልብና በእኔነት የጸዳ መሆን ይኖርበታል። ብዙ አይነት መሪነቶች አሉ። ከሁሉም ከፍ ያለው አገልጋይ መሪነት ነው። የኢየሱስ አይነት አመራር ይህ ነው። ብዙዎች አገልጋይ መሪነትን አይመርጡም ምክንያቱም ዋጋ የሚያስከፈል ስለሆነ፣ እንደ ብዙዎቹ እንዳየነው ብዙዎቹ የሚፈሩት፣ የሚያከብሩትና ጸጥ ብለው የሚመሩለት ሃይለኛ፣ ጨቋኝ እና ተጭኖ የሚመራን መሪ ነው።

አገልጋይ መሪነት ለመሪው እጅግ ከባድ ነው፣ መሪነቱ የሚመራውን ማህበረሰብ እና ተቋም ለማገልገል ስለሆነ ራሱን እንደ ጨካኝ አለቃ ሳይሆን እንደ አገልጋይ ነው የሚያየው። በሰዎች አዕምሮ ውስጥ የተለመደው መሪ ሆኖ አለቃ እንጂ መሪ ሆኖ አገልጋይ ስላልሆነ ብዙዎች አይከተሉትም። አገር ሆነ ቤተክርስቲያን የምታርፈው መሪዎች የአገልጋይነት መንፈስ ሲኖራቸው ነው።

የመሪ አገልጋይ ደካማ ጎን ተብሎ የሚቀመጠው ብዙውን ጊዜ ውሳኔ መስጠት አይችልም ይላሉ። ብዙውን ጊዜ ሰዎችን በማገልገል መንፈስ ውስጥ ያለ መሪ የሚቸገርበት አንዱ ምክንያት ሊሆን ይችላል። ነገር ግን በአስፈላጊው ጊዜ አስፈላጊውን ውሳኔ መወሰን አለበት። በመሪነት ውስጥ መወሰን የተገባን ውሳኔ አለመወሰን፣ መወሰን የሌለበትን ውሳኔ መወሰን ሁለቱም ዋጋ ያስከፍላሉ።

መሪ ራሱን ወደ ባለራዕይ እና አገልጋይ መሪነት ማሳደግ አለበት።

ዘሪሁን ግርማ


/channel/theideaofs

Читать полностью…

የዘር ሐሳቦች/ Yezer Hasaboch

#የጎለበትና_የበሰለ_ሂስ_የእድገት_በር_ነው!

የሚያንጽ፣ የሚያቀና፣ የሚያርም፣ የሚያስተምር፣ የሚያርም ሂስ (Construction Criticism) ሁልጊዜም አስፈላጊ እና ጠቃሚ ነው። ይህን ለማድረግ የሚያስችል ስነ-ልቦና እና ብቃት ያላቸው (በእውቀት፣ በማንነት፣ በፍቅር፣ በትህትና) የሚያርሙ እና ሂስ የሚሰጡ ሰዎች የሚባሉት እንኳን ደህና መጣችሁ ነው።

ሂስ በራሱ ደስ አያሰኝም ነገር ግን ለማደግና የተሻለ ስብዕናን ለመገንባት ጠቃሚው ነገር ነው። ሂስ የማይሰጥበት መንግሰት፣ ቤተ ክርስቲያን፣ አገልጋይ፣ ዘማሪ፣ ጸሐፊ በምንም ስም የሚጠራ ተቋምና ግለሰብ የበሰለና የበለጸገ ስብዕናን መገንባት አይችልም።

ሰዎች ሙሉ ያልሆንባቸውና ያልበቃንባቸው ነገሮች አሉን። ስለዚህም በምንሰራቸው ስራዎች መሐል ስህተት አያጣንም። ስለዚህ ሂስ ሊሰጥብን ይችላል። በሚያም ነገር ውስጥ ለተሻለ ስብዕና የምንሰራበት መንገድ ገንቢ-ሂስ ይባላል።

የአንዳንድ ሰዎች ሂስ ጥላቻን የተሸከመ፣ ቅናትን ያነገበ፣ ከእውቀትና ከፍቅር የጎደለ አፍራሽ-ሂስ ነው። ስለዚህም የእነዚህ አይነት ሂስ መነሻ ነጥባቸው እውነትን ያዘለ ቢመስልም፣ ከጀርባው ያለው ሐሳብ መጣልና ማሳጣት ነው።

የጎለበተና የበሰለ (Constructive) ሂስ ልክ በህመም ውስጥ የሚመር መድሃኒት እንደ መውሰድ ነው። ይመራል ግን ያድናል፣ ይመራል ግን ያስሽለናል። እውነት ነው ማንም ሰቅ የሚመር ነገር መውሰድ ይከብደዋል፣ ቢሆንም የበሰለና የጎለበተ ሂስ ቢከብድም የመለወጥ አቅሙ ከፍተኛ ነው። የሂስን ጥቅም የተረዱ ሰዎች ሁልጊዜም Construction Criticism Always Welcome የሚሉ ናቸው። ሂስ ጠል ሰዎች መለወጥ አይችሉም።

ዘሪሁን ግርማ

/channel/theideaofs

Читать полностью…

የዘር ሐሳቦች/ Yezer Hasaboch

#ምክር_ቢጤ_ወንዶችን_በተመለከተ_ለሴቶች

ሴት እህቶች፣ ጓደኛዎች፣ ፍቅረዎች ብዙ ጊዜ ከወንዶች ጋር በሚያደርጓቸው ግንኙነት (Relation) መሐል ወንዶች እንደማይገባቸው የማይረዱት ነገር አንዱ ወንዶች ቀጥተኛ ግንኙነትን እንደሚከተሉ ነው። ሴቶችን በተመለከተ የወንዶች ሐላፊነት እንዳለ ሆኖ ከወንዶች መጠበቅ የሌለባችሁን ነገሮች መረዳትም እጅግ ይጠቅማችኃል። 'እኔ' እንዳስተዋልኩት፣ ሴቶች ወንዶችን በተመለከተ ከሚሳሳቱባቸው ነገሮች መሐል፦

፨ ምን እንደሚፈልጉ ሳይናገሩ ወይም ሳያመለክቱ ከወንዶች የሆነ ነገር የመጠበቅ ችግር ነው። ወንድ ልጅ በራሱ አስቦ የሚያደርገው ነገር ቢኖርም ነገር ግን በዕለት ተዕለት ግንኙነት መሐል ቀጥተኛ 'አድርግልኝ' መባልን ወይም ምን እንደምትፈልጉ 'አመላካች' እንድትሆኑ ይፈልጋል። ያንን ሳታደርጉ የሆነ ነገርን መጠበቅ ከዚያም አልፎ መበሳጨት ራስን ግንኙነታችሁን ከመጉዳት ያለፈ ምንም ፈይዳ የለውም።

፨ ከወንዶች ለሁሉም የሴቶችን ስሜት በተመለከተ ለሁሉም ነገር ምላሽ እንዲሰጥ የመጠበቅ ችግር ነው። ሴቶች በሚሰሟቸው ስሜቶች እና በሚያጋጥሟቸው ነገሮች ወንዶች ለሁሉም ነገር ምላሽ መስጠት እንዳለባቸው ያስባሉ። ለተገቢና ለአስፈላጊ ነገሮች ተገቢውን ምላሽ መስጠት ወንዶች ቢኖርባቸውም ሴቶች ለሚሰሟቸው የተለያዩ ስሜቶች የተለየ ነገር እንዲያሳዩን መጠበቅ አግባብ አይደለም። ወንዶች የማይችሏቸው ነገሮች እንዳሉም መረዳት አግባብ ነው። ወንዶች የሚችሏቸውና የማይችሏቸው ነገሮች አሏቸው።

፨ ከወንዶቹ ውጪ በሆኑ ጉዳይ በሚያጋጥሙአችሁ ነገሮች 'ሁሉ' ወንዶቹን በማይመለከቱ ነገሮች ጭምር ከወንዶች የተለየ ምላሽ መጠበቅ- ለምሳሌ ከሴት ጓደኞቻችሁ
ጋር በሚያጋጥማችሁ ግጭት ወንድ ልጆችን በወሬ የምታጉላሉ😁 የግጭታችሁን አጀማመር፣ ታሪካዊ አመጣጥና ታሪካዊ ዳራ የተጣላችሁበትን እያዳንዱን ምክንያት ሁሉ እንዲሰማችሁ የምትፈልጉ እህቶች፣ በሌላ መልኩ ደግሞ ከሴት ጓደኞቻችሁ ጋር ያረጋችሁትን እያንዳንዱን የገባችሁበትን ካፌ ያወራችሁትን ወሬ ሁሉ ወንዶች እንዲሰሟችሁ የምትፈልጉ እንዲህ የማድረግ ተፈጥሮ አብዛኛውን ወንድ የለውም። እህቴ እንዲህ ስታደርጊ ወንድ ልጅ ዝም ብሎ ከሰማሽ አንቺን ስለሚያስደስት ወይም ስለሚወድሽ እንጂ ወንድ ልጅ እንዲህ አይነት ነገር በእርግጠኝነት አይመቸውም። ይህን ለማወቅ ወንዶቹን በሌላ ቀን ያወራችኃቸውን ነገሮች ጠይቋቸው አብዛኛውን ጊዜ ይረሱታል፣ ድሮም ፈልገውት አይደለምና።

ወንድ ልጅን በማያስፈልጉና እሱን በቀጥታ ሆነ በማይመለከቱ ነገሮች ከማድከም ይልቅ እርሱ ማድረግ በሚገባው ነገሮች ላይ እንዲያተኩር መርዳት ለተሻለ ግንኙነት ይረዳል ብዬ አስባለሁ።

ዘሪሁን ግርማ


/channel/theideaofs

Читать полностью…

የዘር ሐሳቦች/ Yezer Hasaboch

ስለመፅሐፍ የተነገሩ አባባሎች!


ወዳጆች ዛሬ የንባብ ባህላችን እንዲዳብር ሊያነሳሱን የሚችሉ ስለመፃሕፍት የተነገሩ የተለያዩ ሠዎችን አባባል ዛሬ ልንዘክር ብዕራችንን ከወረቀቱ አገናኝተናል፡፡
መፅሐፍ የሚሠጡት ጥቅም የታወቀ ቢሆንም በማንበብ ብቻ ግን አዋቂ መሆን አይቻልም ባይ ነኝ፡፡ ምክንያቱም መፃሕፍትን ከማንበብ ባሻገር በንባብ ያገኘናቸውን ሃሳቦች ከሃሳባችን ጋር በማስተያየትና በማሻሻል፣ በማሠላሠልና በማስተዋል አዲስ ሃሳብ ካልፈጠርንበት መፅሐፍ ማንበብ ሳይሆን መፅሐፍ መቁጠር ነው የሚሆነው፡፡ ባነበብነው ሃሳብ ተገዝተንና አዲስ የባህሪ ለውጥ ወይም አዲስ ነገር ካልፈጠርንበት ማንበባችን ዕውቀት አይሆንም፡፡ ምክንያቱም ዕውቀት ስንል በተጨባጭ በተግባር የሚገለፅ ነውና፡፡
ለማንኛውም አባባሎቹን እነሆ እላለሁ..! ሃሳብና አስተያየታችሁ የተጠበቀ ነው፡፡ መልካም ንባብ!

‹‹መፅሐፍ አንድ ቁምነገር አለው፡፡ ይሄም እግርህን ከቤትህ ሳታነሳ ዓለምን እንድትዞር ያደርግሃል›› (ጁምባ ራሂሪ)

‹‹አንባቢ ከመሞቱ በፊት አንድ ሺ ኑሮ ይኖራል፡፡›› (ጆርጅ ማርቲን)

‹‹መፅሐፍት ተንቀሳቃሽ አስማቶች ናቸው›› (ስቴፈን ኪንግ)

‹‹እንደመፅሐፍ ያለ ታማኝ ጓደኛ የለም፡፡›› (ኸርነስት ኸርሚንግወይ)

‹‹ አንድ ነገር አንርሳ! አንድ መፅሐፍ፣ አንድ እስኪብርቶ፣ አንድ ሕፃን፣ አንድ መምህር ዓለምን መለወጥ ይችላሉ፡፡›› (ማላላ ዮሶፍዜ)

‹‹ዓለም መፅሐፍ ናት፡፡ ዓለምን ተጉዘው ያላዩ መፅሐፍ ይግለጡ፡፡›› (ቅዱስ አውግስጦስ)

‹‹መፅሐፍ በየዕለቱ የሚያጋጥመንን የህይወት ጉድፍ የሚያስወግድልን የነፍሳችን ማጠቢያ ነው፡፡›› (ያልታወቀ ሠው)

‹‹ማንበብ ለአዕምሮ ሲሆን አዕምሮም አካላችን ምን ማድረግ እንዳለበት ያቀናጃል›› (ያልታወቀ ሠው)

‹‹መፅሐፍ ከባድ መሆን አለበት፡፡ ምክንያቱም ዓለሙ ሁሉ በእርሱ ታጭቋልና፡፡›› (ኮሜሊያ ፈንክ)

‹‹ዛሬ አንባቢ የሆነ ነገ መሪ ይሆናል፡፡›› (ማርጋሬት ፉለር)

‹‹ዛሬ ልታነበው የምትችለውን መፅሐፍ ለነገ አታቆየው፡፡›› (ያልታወቀ ሠው)

‹‹ካነበብኩ መላው ዓለም ለእኔ ክፍት ነው፡፡›› (ሜሪ ማክሎድ ቤቱን)

‹‹አንዳንድ መፅሐፍት ነፃ ይተዉናል፡፡ አንዳንዶቹ ደግሞ ነፃ አድርገው ይሠሩናል፡፡›› (ራልፍ ዋልዶ ኤመርሠን)

‹‹መፅሐፍ ወደፊት ልንሆን የምንፈልገውን የያዘ ህልማችን ነው፡፡›› (ኔል ጌማን)

‹‹ቤተ-መፃሕፍቶች ልክ እንደጥሩ ትዝታ መዓዛቸው ያውደኛል፡፡›› (ጃኩሊን ውድሰን)

‹‹መፅሀፍ አስተሳሰባችንን የሚያቀጣጥል መሣሪያ ነው፡፡›› (አላን ቤኔት)

‹‹እኔ በቀላሉ የመፅሐፍ ጠጪ ነኝ›› (ኤል ኤም ሞንቶጎሞሪ)

‹‹ሌላ ሠው ያነበበውን ብቻ እያነበብክ ከሆነ ሌላ ሠው የሚያስበውን ብቻ ነው እያሠብክ ያለኸው፡፡›› (ሐሩኪ ሙራካሚ)

‹‹ቤት ያለመፅሐፍት ማለት አካል ያለነፍስ ማለት ነው፡፡›› (ሲስሮ)

‹‹ተራ ሠዎች ትላልቅ ቲቪ አላቸው፡፡ ብልህ ሠዎች ግን ቤተመፃሕፍት ናቸው፡፡›› (ያልታወቀ ሠው)

(ከልዕቀት የንባብ ማዕከል የቴሌግራም ቻናል የተወሰደ)

/channel/theideaofs

Читать полностью…

የዘር ሐሳቦች/ Yezer Hasaboch

#ወደፊት_ተመለከት_ወደፊት_ተጓዝ
       

" እልፍ ሲሉ እልፍ ይገኛል" ይላሉ አበው። ወደፊት መመልከትና ወደፊት እልፍ ብሎ መጓዝን የመሰለ ታላቅ ነገር የለም። በህይወታችን የሚገጥሙንን ማንኛውም መሰናክሎች፤ ችግሮች፤ ተግዳሮቶች የዘገዩ ነገሮች፤ ያልተሳኩ ነገሮችን እያሰብን ባለንበት አንቁም ወይም ወደ ኃላ አንመለስ? ወይስ ወደፊት እንሂድ? በትዕግሥት ወደፊት ተራመድ። ከዛሬ ጨለማ ቀኖች የተሻለ የብርሃን ዕለቶች  አሉና።

     በአገልግሎትህ ትግልና ችግር አጋጠመህ? በገንዘብ ችግር ላይ ነህ? ወይስ ሰዎች አልተረዱህም? ወይስ የጠበከው ነገር ካሰብከው ውጪ ሆነ? መልሱ ወደ ፊት ተመለከት ወደፊት ተጓዝ። በየዕለቱና በየጊዜያቱ የሚከቡንንነገሮች ላይ ካተኮረን መዘግየታችን ወይም ወደ ኃላ መቅረታችን ነው። ሰዎች ስለ እኛ የሚያስቡት ነገር ወይም የሚያወሩት ነገርም ላይ አናተኩር። ወደ ፊት እንመልከት ወደፊት መራመዳችንን አናቁም። ማቆም ወይም መቆም መሸነፍ ነው።

   ዕለት ዕለት የሚከበንን ሸክም ወይም ሐጢያት ወይም ድካም ወይም መሰናክል እያለፍን፣ ኢየሱስን እየተመለከትን ሩጫችንን በትዕግሥት እንሩጥ። (ዕብ 12:1-4)  ብዙ አድካሚ ነገሮች በምድር ኑሮአችን ያጋጥማሉ። እኛ ግን ኢየሱስን ተመለክተን ወደፊት እንመልከት ወደፊት እንጓዝ።

    /channel/theideaofs

Читать полностью…

የዘር ሐሳቦች/ Yezer Hasaboch

ፈር-ቀዳጆች= #የትውልድ_መንገድ_ጠራጊዎች

ታዋቂው የቴሌቪዥን ፕሮግረም አዘጋጅና (Host) ኮሜድያን እንዲሁም የፈልም አክተር፣ ሬድዮ አዘጋጅ፣ የመፅሐፍት ፀሐፊ ስቲቭ ሐርቪ (Setve Harve) የተለያዩ ሾዎችን በማዘጋጀት ይታወቃል። ካሉት ፕሮግራሞች መሐል Ask Steve Harve, little big shots (ታለንት ላላቸው ህፃናት)፣ Forever Young (ከ60 አመት በላይ ለሆኑ) ፕሮግራም አለው።

በዚህ አዲስ በጀመረው Forever Young በሚለው ፕሮግራሙ S1 E1 ላይ አንድ #አርተን_ዲንከን የተባለ የ80 አመት ሰው ይጋብዛለ። ይህ ሰው የዛሬ 60 አመት አካባቢ ለጥቁር አፍሪካ-አሜሪካውያን የቴሌቪዥን ፕሮግራም በማይሰጥበት ዘመን፣ እንደውም ብዙዎቹ ጥቁሮች ቴሌቪዥን በሌላቸው ዘመን ማለት ይቻላል፤ ቤዲ ዋይት የምትባል የተባለች ታዋቂ የቴሌቪዥን አዘጋጂ በዚያ ዘመን ለዚህ አርተን ዲንከን ለተባለ ሰው ፕሮግራሙን በእርሷ ሾው ላይ እንዲያዘጋጅ እድል ትሰጠዋለች፤ ሰውየው ዳንሰኛ ነበር። ጥቁሮች በማይታሰቡበት ዘመን ይህ ሰው የዳንስ ሾው በናሽናል ቲቪ ላይ ነበረው።

ስቲቭ ሐርቪ የተናገረውን ነው ዛሬ ላነሳው የፈለኩት "በዚያ ዘመን ለጥቁር አፍሪካ-አሜሪካውያን ቴሌቭዥን ፕሮግራም አይሰጥም ነበር። እሱ በዚያ ቴሌቭዥን ላይ ሾው ባያደርግ ኖሮ እኔ ዛሬ እዚህ ይህን ሾው አላደርግም ነበር" አለ። ፈር ቀዳጆች ከኃላ ለሚመጣው ትውልድ መንገድ ጠራጊዎች ናቸው። በእነርሱ ዘመን የማይቻለውን ለኃለኛው ትውልድ ወደ መቻል ያመጡታል። በአሁን ሰአት BET የተባለ ቀጥቁሮችና ለጥቁሮች ብቻ የሚዘጋጅ ትልቅ የአዋርድ ዝግጅት ጥቁሮቹ አላቸው።

ፈር ቀዳጆች ብዙ ዋጋ ቢከፍሉም፣ ሌላው ትውልድ በቀላሉ እንዲሄድበት ያደርጉታል። በአሁን ሰአት አፍሪካ-አሜሪካውያን በሁሉም መስክ ታላላቅ ሰዎች ያላቸው ታወቂ ሚሊየኖሮችና ቢሊየነሮች ያሏቸው፤ በፈለጉት ቦታ መግባት የሚችሉ ናቸው። የአሜሪካ ፕሬዚደንት ጥቁር አፍሪካ-አሜሪካዊ ባራክ ኦባማ እስከመሆን ደርሷል። ለዚያ መንገድ ግን እንደነ ማልኮም ኤክስ (Malcom X)፣ ማርቱን ሉተር ኪንግ (Martin Luter King) ደም እስከ ማፍሰስ ተጋድተዋል፣ በወጣትነታቸው ተገለዋል።

በቤተክርሰቲያንም በሐገርም ደረጃ እንደነዚህ አይነት ሰዎች አሉ፣ ለትውልድ መንገድን የጠረጉ (Legend's) አሁን ያለው ትውልድ ቤቱን የገነባባቸው፣ ብዙ ታላላቅ ሰዎች አሉ። ለእነርሱ እውቅና መስጠት የአዋቂ ባህሪ ነው። ጥቁሮቹ የአንድ ቢሮ ሰራተኛ በማይችሉበትና፣ ከነጭ እኩል መማር በማይችሉበት ዘመን ከላይ እንደጠቀስኳቸው ያሉ ፈር ቀዳጆች እነርሱ ተገፍተውና ተጠልተው ለቀጣዩ ትውልድ ድልድይን ሰርተዋል። በልቶ ከማደር ባለፈ ለትውልድ መኖር የሚችሉ ያስፈልጋሉ።

ባራክ ኦባማን ፕሬዝዳንት ያደረገው፣ የእሱ አዋቂ መሆን ብቻ ሳይሆን ከእርሱ በፊት ምንም ነገር በማይታይበት "ራዕይ አለኝ"
(I have a dream) ያሉ መንገድ ጠራጊዎች ውጤት ነው። በትናንት ላይ ያልሰራ ዛሬን የተሻለ ማድረግ አይችልም። ራዕይ የሚያዩ (ትውልድን የሚቀይር ሐሳብ) ከሌሉ ራዕዩን አስፈፃሚዎች አይመጡም።ትናንት በማይቻሉ ሁኔታዎችን አልፈው ለእኛ ዛሬን የሰጡንን እናመሰግናለን። እኛ ደግሞ በቤተክርስቲያንም ፣ በሃገርም ለነገ ትውልድ መንገዶች መስራት አለብን፣ ብዙ ትውልድ እንዲመላለስበት ማለት ነው። ሁሉም ሰው በመፈጠር አንድ ቢሆንም በማንነት ግን ይለያያል። ታላላቆችን (Legendary) እናከብራለን፣ ታላላቅ ትውልድ እንገነባለን ታላላቅ ፈር ቀዳጆች ከሌሉ ታላላቅ ከፍታዎችን መፍጠር አንችልም።

©ዘሪሁን ግርማ

/channel/theideaofs

Читать полностью…

የዘር ሐሳቦች/ Yezer Hasaboch

#የዛሬ_ሳር_የነገ_ችንካር!!

አንድ አባት ወንድ ልጁ ጎጂ ሱስ ውስጥ እየገባ እንደሆነ ስላመነ አንድ ምሁር አዛውንት ጋር ወስዶ ልጁን ከመጥፎ ልምዶቹ እንዲያስወጡት ለመናቸው፡፡ ምሁሩም ወጣቱን በአትክልት ስፍራ ውስጥ አብሮአቸው እንዲንሸራሸር ይዘውት ወጡ። በመሃል ቆም ብለው ልጁን በአትክልቱ ስፍራ ካሉ ጥቃቅን ተክሎችን ውስጥ አንዱን እንዲነቅል ጠየቁት።

ወጣቱ ተክሉን በቀላሉ በአውራ ጣቱ እና በሌባ ጣቱ መካከል በመያዝ ነቀለው። ከዚያ ሽማግሌው ትንሽ ተለቅ ያለ ተክል እንዲነቅል ጠየቁት፡፡ ወጣቱም ጠንከር ባለ ኃይል ጎተተ እና ነቀለው ሥሮቹ ሰፊ ነበርና ከነአፈሩ ተነሳ፡፡ “አሁን ደግሞ ያንን ” አሉ ምሁሩ ወደ አንድ ቁጥቋጦ እያመለከቱ፡፡ ልጁም ቁጥቋጦውን ለመንቀል ያለ የሌለ ሃይሉን እና ጥንካሬውን መጠቀም ነበረበትና ከብዙ ትግልና ሙከራ በኋላ ተሳክቶለት ነቀለው፡፡

“አሁን ደግሞ ይህንን ንቀልና አምጣ” አሉ ሙህሩ ወደ መሃከለኛ ዛፍ እያመለከቱ ፡፡ ወጣቱ ግንዱን በመያዝ ለመንቀል ሞከረ ። ግን አልተሳካም፡፡ ልጁም “የማይቻል ነው” አለ በረጅሙ በመተንፈስ

ጠቢቡም “እስካሁን ስትነቅላቸው የነበሩ ተክሎች የመጥፎ ሱስ ምሳሌዎች ናቸው፡፡ ገና በለጋነታቸው ትንሽ ሆነው ሳላ ለመንቀል እንደቀለለህ ሁሉ መጥፎ አመልም በእንጭጭነቱ ልታሰወግድው ቀላል ነው። ስራቸውን እየሰደዱና ውስጥክ እያደጉ ሲመጡ ለመንቀል ትቸገራለህ፡፡ መጥፎ አመልህን አሁኑኑ ነቅለህ ካልጣልከው ነገ ከነገወዲያ ዛፍ ሆኖ ሕይወትክን ይፈትናዋል፡፡” ብለው አስረዱት ፡፡ ይህን ምሳሌ ከዚህ ቀደምም ሰምታችሁ ይሆናል ምሳሌው ግን ወሳኝ መልዕክት ይዟል። የዕብራውያን መጽሐፍ ጸሐፊ እንዲህ ይለናል።

“የእግዚአብሔር ጸጋ ለማንም እንዳይጎድለው፥ ብዙዎቹም የሚረክሱበት አንድ መራራ ሥር ወደ ላይ በቅሎ እንዳያስጨንቅ፥ ሴሰኛም የሚሆን እንዳይገኝ፥”
— ዕብራውያን 12፥15

ሁልጊዜ በጊዜ ያልነቀልነው እና ያልሳስተካከልነው ነገር የነገ መጨነቂያችን ይሆናል። መስራት የሚገባንን አለመስራት፣ መጣል የሚገባንን አለመጣል ነገ ዋጋ ያስከፍለናል። የአሁኗ ቤተ ክርስቲያን ዛሬ ለጋ እያለ መንቀል ያለባት ካደገ ነገ ጭንቅ የሚሆንባት ምን ይሆን? በስልጣም ምክንያት መገፋፋት፤ በፍቅር ስም መሸነጋገል፣ በወንጌል ስም ንግድ፤ በነጻነት ስም ልቅነት ስንፍና፣ ጥላቻ የያዘን ምን ይሆን ዛሬ ከቤተክርስቲያን መነቀል ያለበት? በግል ህይወታችንስ ምን ይሆን ነገ ጠንክሮ እንዳያስቸግረን ዛሬ መንቀል ያለብን ነገር? ሰውን ማየት ሳይሆን ራስን ማየት ያስመልጣል።

©ዘሪሁን ግርማ

የቴሌግራም ቻናሌን ይቀላቀሉ
/channel/theideaofs

Читать полностью…

የዘር ሐሳቦች/ Yezer Hasaboch

#የሙዚቃው_ዕንቁ- #ዕንቁ_ግርማ

እትናስ ይሳል ጥበብ ቤቷን ሰርታበታለች፣ እንትናስ ይጻፍ በመጻፍ ተክኗል፣ እትናስ ይስበክ ስብከት ስጦታው ነው ይባላል። ሙዚቃን ዕንቁ ይጫወት ሙዚቃን መጫወት ያወቅበታል ብቻ ሳይሆን፣ ሙዚቃ ራሷ ዕንቁ ይጫወተኝ የምትል ይመስለኛል። በሙዚቃ አቅጣጫ የተገለጠ እጅግ አስደናቂ ስራን ከሰሩ እና በቤተክርስቲያን የዝማሬና የሙዚቃ አገልግሎት የራሳቸውን አሻራ ካሳረፉ ሙዚቀኞች አንደኛው ዕንቁ ግርማ ነው። እጅግ በጣም የምንወዳቸው በርካታ አልበሞችና ዝማሬዎች አሻራውን አሳርፏል። ዕንቁ የሰራቸውን ስራዎች በሙሉ ለመዘርዘር ብዙ ነገር ማገለበጥና እርሱን አግኝቶ መጠየቅ ያስፈልናል። በሙሉ አልበም ደረጃ የተለያዩ ዝማሬዎች ላይ በማቀናበርና እንዲሁም በሚክሲንግ ተሳትፏል። ከሰራቸው ስራዎች በጥቂቱ ለአብነት ያህል እንመልከት።

በሙሉ አልበም ደረጃ
የዘማሪት ምህረት ኢተፋ ቁ 1 አልበም
የሐረር አማኑኤል ከ ቁ 1-3 ሶስት አልበሞች
የናዝሬት አማኑኤል አልበም
የዘማሪት ሶፊያ ሽባባው ቁ 2 አልበም ተጠቃሽ ናቸው።

ዝማሬን ካቀናበረላቸው ዘማሪያን በጥቂቱ የዘማሪ ሳሚ ተስፋ ሚካኤል፤ የዘማሪ ተከስተ ጌትነት፣ የዘማሪ አውታሩ ከበደ፣ የዘማሪ ዮሴፍ አያሌው፣ ዘማሪት ምህረት ኢተፋ ቁ 3 ና 4 አልበሞች ላይ የተለያዩ ኮሌክሽኖች ላይ እጅግ የተወደዱ ስራዎችን ሰርቷል። ሙዚቃን ማቀናበር ብቻ ሳይሆን እጅግ በርካታን ዝማሬዎችን እና አልበሞችን Mix አድርጓል።

በእርሱ በኃላ በመጡት ብዙ ሙዚቀኞች ላይ የራሱን መልካም ተጽዕኖ አሳርፏል። በብዙ ሙዚቀኞች ዘንድ ጭምር ስራዎቹ እጅግ ተወዳጅ ናቸው። ዕንቁ በሙዚቃ አቅጣጫ ለክርስቶስ አካል ቤተ ክርስቲያን ስላበረከትከው መልካም አስተዋጽኦ እግዚአብሔር ይባርክህ። ስላገለገልከን እናመሰግናለን። ገና ብዙ ስራዎችን ከአንተ እንጠብቃለን።

©ዘሪሁን ግርማ

Читать полностью…

የዘር ሐሳቦች/ Yezer Hasaboch

#ለወንድም_ይጸለያል_እንጂ_አይጸለይበትም!!

እኛ ልጆች ሆነን ከነበርንበት ቤተክርስቲያን ትንሽ ራቅ ብሎ አንድ ከእኛ ቤተክርስቲያን ሞቅ ያለ በዝማሬና ወጣቶችን የሰበሰበሰ አዲስ የተተከለ ቤተክርስቲያን ነበር። የእኛው ቤተክርስቲያን አንዳንድ አገልጋዮች አዲስ በተጀመረው ቤተክርስቲያን ላይ የተለያየ ወሬዎችንና ተቃውሞችን ማሰማት ጀመሩ። ከዚያም በዚያ ቤተክርስቲያኑ ላይ እና ሲጸለይ እንደነበር አስታውሳለሁ ከዚያም አልፎ እነ አትንትና ስተዋል ተብሎ ስማቸው እየተጠራ ሲጸለይባቸውም አስታውሳለሁ። ይህ አሳዛኝ እውነታ ነው። ይህን አይነት ተሞክሮዎች በሌላው ላይ መጸለይ፤ በጸሎት ቅዱሳንን መቃወም አድጎ "ከረገምኩህ" " ከአፌ ቃል ከወጣብህ" አትበረክትም የሚል አይነት በትዕቢት የተነፉ ከመጽሐፍ ቅዱስ ያፈነገጡ በዚህ ጊዜም አሉ። እኔ "ቃል አወጣብሃለሁ እረግምሃለሁ" ያለኝ አገልጋይም አውቃለው።

፨ የተባረኩትን መርገን ሐጢያት ነው! ዳግም የተወለደ እና በመንፈስ ቅዱስ የተሞላ የእግዚአብሔር ልጅ የሆነ ወንድምህ ላይ ቢደክም እንኳ ይጸለይለታል እንጂ አይጸለይበትም። አብሶ አንዳንድ አገልጋዮች በሆነ ነገር አትመቻቸው ብቻ የፈጠሩህ እና የሰሩህ እነርሱ ይመስል እንደ ሚነቅሉህ በትዕቢት ይናገራሉ።

አንዳንድ ክርስቲያኖችም ያስቸገራቸውን ሰው በጸሎት "ለማስነቀል" አገልጋዮች ጋር የሚያጸልዩ የሚያስቸግሯቸው ሰው በጸሎት ሽባ ለማድረግ የሚጸልዩም ብዙዎች አሉ። ሰው እንዴት በጌታ ወንድሙ የሆነ ሰው ላይ ለእርግማን ይጸልያል? እንዴት ሰው በጸሎት ሰውን ለመጉዳት ይጸልያል? ይህ ከሟርተኝነት እና ከጥንቆላ አሰራር በምንም አይለይም።

፨አንዳንድ ቤተክርስቲያን ውስጥ የሚያገለግሉ ቅዱሳኖች ካሉበት ቤተክርስቲያን የማይወጡበት (ትክክል ያልሆነ ነገር እያዩ) የአገልጋያቸው ከዚህ ከወጣችሁ እንዲህ እና እንዲህ ትሆናላችሁ በሚል በፍርሃት ተይዘው ነው።

፨ ለደከመው መጸለይ፤ ለወደቀው መጸለይ የሳተው እንዲመለስ የማቅናት ስራ መስራት መጽሐፍ ቅዱሳዊ መርህ ነው። ከዚያ ውጪ ለእኛ ያልተመቸን ሰው በሙሉ ላይ የእርግማን ቃሎች ማዥጎድጎ እርግማንን ወደ ቤታችን መጥራት ነው። እንደ እግዚአብሔር ስርአት የማይሄዱትን ለመገሰጽና ለማረም የሚያስችል መጽሐፍ ቅዱሳዊ መርሆች አሉን።

፨ ክርስቲያን የተጠራው ለበረከት (ለመባረክ ነው) ነው እንጂ ለእርግማን አይደለም። የምንቃወመው የጨለማውን ስራ፣ የዲያቢሎስን መንግስት ነው።
በወንድምህ ላይ መጸለይ ሐጢያት ነው። የተባረከን መርገን ለእርግማን መሆን ነው። ለወንድም ይጸለያል እንጂ አይጸለይበትም።

ዘሪሁን ግርማ

የቴሌግራም ቻናሌን ይቀላቀላሉ
/channel/theideaofs

Читать полностью…

የዘር ሐሳቦች/ Yezer Hasaboch

#እኔ_አውቅልሃለሁ!!

አንዳንድ ሰዎች ሰዎችን ከሚያጠምዱበት መንገድ አንዱ "እኔ ነኝ የማውቅልህ" የሚሉ አመለካከትና ድርጊታቸው ነው። አንተ ስለ ራሰህ አታውቅም እኔ ግን ስለ አንተ አውቃለሁ ይሉሃል። እኔ አውቅሀልሃለሁ ማለት አንተ ስለ ራስህ ምንም አታውቅም ማለት ነው። የእነዚህ አይነት ሰዎች ምልክቶች

፨ አንተ እንዲህ ነህ ይሉሃል፦ እኔ እንዲህ ነኝ ከምትለው ይልቅ እነርሱ እንዲህ ነህ በሚሉት ነገር ደምድመው ጨርሰው ስለ አንተ ለአንተ የሚያስረዱ ናቸው። ለአንተ አንተን ይተርኩልሃል። የእነዚህ አይነት ሰዎች አደጋው አንተን ሳትሆን እነርሱን የፈጠሩትን አንተን ይነግሩሃል። ደምድመው በዚያ ልክ ይሰፉልሃል።

፨ ይቃወሙሃል፦ እነርሱ ነህ ከሚሉህ ውጪ ስትሆንና ራስህን መቀበል ስትጀምር ደግሞ ይቃወሙሃል ከዚያም ያጣጥላሉ። ሰዎች ሁልጊዜ እነርሱ ነህ በሚሉህ ስትመላለስ ደስተኞች ናቸው አይደለሁም ብለህ የራስህን ማንነት ተቀብለህ ስትሄድ ይቃወሙሃል ያኮርፉሃል ያገሉሃል።

፨ ስኬትህን አይቀበሉም፦ እነዚህ አይነት ሰዎች እነርሱ ከሚሉህ ውጪ ስትሆንና ከሰፉልህ ልክ ስትወጣና በራስህ መንገድ ስኬታማ ስትሆን ያንን ስኬት መቀበል አይፈልጉም። የአንተ እውነተኛ ማንነት መቀበል ስለማይፈልጉ ስኬታማነትህን ይገፋሉ። የምትናገረውን መቀበል አይፈልጉም በእነርሱ ሐሳብ ቁጥጥር ውስጥ እንድትሆኑ ብቻ የእናንተን ማንኛውም ነገር በማጣጣል ይሄዳሉ።

ስለ ሰዎች በተወሰነ መልኩ ልናውቅ እንችላለን ሰዎችን ግን አውቀን ልንጨርስ አንችልም። አውቅልሃለሁ የሚሉህ ሰዎች እነርሱ በቀደዱልህ ቦይ ብቻ እንድትፈስ ይፈልጋሉ ከዚያ ወጥተህ ራስህን በቀደድከው መንገድ ስትሄድ ደግሞ በፍጹም አይቀበሉህም። ሁልጊዜም ከሰዎች የምንማረው ነገር ቢኖርም ሰዎች በፈጠሩልን መንገድ ግን እንድሄድ አልተፈጠርንም። የበላይ የመሆን፣ ሰዎችን በቁጥጥር ስር የማድረግ ፍላጎት ያላቸው ሰዎች የሚንጸባርቁት አንደኛው ነገር አውቅልሃለሁ ማለትን ነው።

ዘሪሁን ግርማ

/channel/theideaofs

Читать полностью…
Subscribe to a channel