#በራስ_ነገር_ላይ_ማተኮር!!
ህይወታችን የእኛ ብቻና ስለ እኛ ብቻ ባትሆንም፣ ህይወታችንን የመምራት የመጀመሪያው ሐላፊነት ግን የእኛ ነው። በራስ ላይ ለማተኮር የራስን ነገር አስቀድሞ ማወቅ አስፈላጊና ዋና ነገር ሲሆን፣ ያንን ስናውቅ በራሳችን ነገሮች ላይ ማተኮር እንጀምራለን። ህይወታችንን ውጤታማ ለማድረግ ደግሞ የምናተኩርበት የእኛ የሆነ የአትኩሮት አቅጣጫ ሊኖረን ይገባል። የምናተኩርበት የራሳችን ነገር ከሌለን በሌላ ጉዳይና በማይመለከተን ላይ እያተኮርን ነው ማለት ነው።
እንደምታውቁት አዲስ አመት ሲመጣ በጣም ብዙ ሰው ብዙ እቅድ ያወጣል፣ ያወጣውን ዕቅድ እዳንኖር ከሚያደርገን ነገር አንዱ በራስ ጉዳይ አለማተኮር ነው። የራስ ባልሆነ ነገር ላይ ማተኮር፣ የራስህን እንዳትሰራ ያደርግሃል።
በማያገባው የሚገባና በማያድግበት ወይም በማያፈራበት መንገድ የሚጓዙ፣ በሰዎች ጉዳይ ገብቶ የሚፈተፍትና ስለ ሰዎች ብቻ እያወራ የሚኖር ሰው የራሱ የሚያተኩርበት ነገር የለውም። ስለዚህም በራሳችን ነገር ላይ እናተኮር። ይህ አመት በራሳችን ነገር ላይ እያተኮርን፣ ለሌሎችም የምንተርፍበት አመት ይሁንልን።
ዘሪሁን ግርማ
/channel/theideaofs
#ከምርጫዬ_በላይ_መረጠልኝ
የማውቅ መስሎኝ ስለራሴ
መንገዴን ቀይሼ ፈልጌ ጨርሼ
በፍቅር ተይዛ ተጠላልፋ ነፍሴ
መረጥኩትና ጉዞ ጀመርኩ
ሮጥኩ ታገልኩ የራሴ አደረኩ
ምርጫዬ ትክክል እንዳልነበር አይቶ
ነገ እንደሚውጠኝ አስተውሎ
"ወዳጄ" ከእኔ ላይ ምርጫዬን አስጣለኝ
በጊዜው ቢከፋኝ ቢያመኝ
ቆይቼ ያረገልኝን አስተዋልኩኝ
የእኔ ምርጫ መጥፊያዬ
የእርሱ ምርጫ መዳኛዬ ሆነልኝ
ከምርጫዬ በላይ እርሱ መረጠልኝ
ምርጫዬን አስጥሎ በምርጫው አዳነኝ!!
ተጠነቀቀልኝ!
(ተጻፈ በዘሪሁን ግርማ)
/channel/theideaofs
#ስሜትና- #ሚዛናዊነት (ምክንያታዊነት)
ስሜትና- ሚዛናዊነት በሰው ልጆች ማንነት ውስጥ ትልቅ ሚና ያላቸው ነገሮች ናቸው። ስሜትም በቦታው- ሚዛናዊነትም በቦታው እጅግ አስፈላጊ ነው። በስሜት መመራት ቀላሉና ነገር ሲሆን፣ ሚዛናዊነት ደግሞ በመብሰል ውስጥ ያለ ሂደት ነው። በትዳር፣ በስራ ግኖኙነት፣ በአመራር መሐል ትልቁ አስፈላጊ ነገር ሚዛናዊነት ወይም ምክንያታዊነት ነው። ሰው በተፈጥሮ ስሜት ስላለው ስሜቱ ላይ የመስራት የስሜት ብስለት (ልዕቀት) ያስፈልገዋል ማለት ነው።
በዶክተር መክብብ ጣሰው የተጻፈው 'የስሜት ልህቀት' መጽሐፍ በገጽ 35 ላይ በዚህ ጉዳይ ላይ፦
".... ምክንያታዊ የሆነው የአህምሮአችን ክፍል ጥቂት ጊዜን ይወስዳል። ስሜታችን ከምክንያታዊ የአእምሯችን ክፍል ከ 80-100 እጥፍ በላይ ይፈጥናል። የሚሰማን ከማሰባችን በፊት ማለትም ወደ ተግባር የምንለውጠው ከማሰባችን በፊት ነው። ምስጢሩ እዚህ ጋራ ነው። ስሜታችን እጅግ ፈጣን ነው። ምክንያታዊ የሆነው የአእምሮአችን ክፍል ጊዜን ይፈልጋል። ጊዜን ካልሰጠነው እንዲያስብ ካልረዳነው በስሜታችን ብቻ የመነዳተ ዕድላችን ከፍተኛ ነው ለዚህም አደጋ ይጋረጥብናል።" ይላል።
ምክንያታዊነት በስሜት በሚመሩ ሰዎች መሐል ከባድ ልዩነትና አለመግባባት ይፈጠራል። ነገር ግን ሁልጊዜም አሸናፊ የሚሆነው ሚዛናዊ የሆነው ግለሰብ ነው። ምክንያቱ ደግሞ ስሜት በራሱ እጅግ አስፈላጊ ነገር ቢሆንም፣ ሚዛናዊነት ግን ዘላቂ የሆነን መንገድ ያበጃል።
በአመራር፣ በትዳር፣ በስራ ግንኙነት በወዳጅነት መሐል ሚዛናዊነትን ማዳበር ነገራችን ዘላቂ እንዲሆን ያደርጋል። ስሜት በቦታው የራሱ ጥቅም ቢኖረውም፣ በውሳኔ አቅጣጫ ግን ሚዛናዊ መሆንን የሚያክል አይደለም። ሚዛናዊ ስትሆን ፈጥነህ ስለማትወስን ስህተትን ትቀንሳለህ። ስለዚህን ስሜትን በቦታው፣ ህይወትን በሚዛናዊነት መምራት ብስለት ነው።
ዘሪሁን ግርማ
/channel/theideaofs
#ከመላመድ_መናናቅ_መጠበቅ!!
ከሰው ጋር መቀራረብ አብሶ መስራት እና ይበልጥ መተዋወቅ እጅግ ጠቃሚ ነው። ለሰው አስፈላጊ ከሆኑ ነገሮች መሐል ሰውን ማወቅ፥ አብሮ መስራት ህብረት ማድረግ ነው። ከሰው ጋር መስራት ደግሞ መላመድ የሚባልን ነገር ያመጣል። መላመድ በራሱ ችግር ባይኖረውም በመላመድ ውስጥ በጣም መቀራረብ አለና ያኔ ሰውየውን መሰልቸትና መናናቅ እንዳይመጣ መጠንቀቅ ያስፈልጋል።
'ሰዎች በጣም ስትቀርባቸው የሚንቁህ በጣም ስትርቅ የሚያከብሩህ' ምክንያቱ ሰትቀርባቸው አንተንና የአንተን ነገር ስለሚላመዱ እና መላመድ ደግሞ ሚዛናዊ ሰው ካልሆነ መናናቅና መሰላቸትን ስለሚያመጣ ነው። ይህን ለማወቅ ሰዎች በሩቅ ሲያውቁህ ስላንተ ያላቸው ግምት ከፍ ብሎ የነበረ ከነበረና እያገኙህ ሲመጡ ግን ከቀለልክባቸው እነዚህ አይነት ሰዎች የመላመድ በሽታ ውስጥ ናቸው።
መላመድ እጅግ ጥሩ ነው። እንደ በሰለ ሰው ከተጠቀምንበት ሰዎችን ለማወቅና ለመረዳት እና ለመርዳት ይጠቅማል። ማወቅ ያለንብን ቀረብ ብለን ስናየው ማንኛውም ሰው የራሱ የሆነ ክፍተት አለው። ወደ ማንኛውም ሰው ከመቅረባችን በፊት ስለ ሰዎች ያለንን 'የተጋነነ' አመለካከት ማስተካከል ከቀረብነው በኃላ በሚዛናዊነት መሔድ ያስፈልጋል። የመላመድ ሌላው ችግር በሰዎች ውስጥ ያለውን እቅም እንዳይቀበል ማድረጉ ነው።
ሌሎች ሰዎች እንዲቀርቧቸው የማይፈልጉ ብዙ ሰዎች አሉ። ምክንያቱ ደግሞ የመላመድ በሽታ የሚያመጣውን ችግር ስለማይፈልጉ ነው። ለበሰለ ሰው መላመድ የመፋቀር በር ነው። ሰውን በጣም ባወቅነው ቁጥር ልንወድው እንጂ እንድንንቀው አይገባም። ከሰዎች ጋር ያለ ልክ ተቀራርበህ እና ተላምደህ ከሚያሳዩህ ነገር የተነሳ ከመጣላት ተራርቆ ተዋዶ መኖር ሌላኛው አማራጭ ነው።
ዘሪሁን ግርማ
የቴሌግራም ቻናሌን ተቀላቀሉ
/channel/theideaofs
#አትገኝ!!
ትንንሽ አህምሮ ያላቸው ሰዎች ሐሜትና ክርክር ላይ ያተኩራሉ፣ ጠንካራ አህምሮ ያላቸው ሰዎች ሐሳብ ላይ ያተኩራሉ። ትንንሽ አህምሮ ያላቸው ሰዎች ሐሳብ የማውራት አቅም ስለሌላቸው በማይረባ ክርክር ላይ ያተኩራሉ። እንደነዚህ አይነት ሰዎች እነርሱ በፈጠሩት አለም ላይ ሊያስገቡህ ሲፈልጉ፣ አትገኝ። ሐሳብ ያለው ሰው ከወሬ ተራ ራሱን አይከትም።
/channel/theideaofs
#ንግግር_የማስረዘም_ችግር!!
©ዘሪሁን ግርማ
ታገል ሰልፉ "ብስጦሽ ቁዋጭ ቁዋጣሽ ቆር" በተሰኘው በአዲሱ ልብ ወለድ መጽሐፉ ላይ ስለ ንግግር የሚያስረዝሙ ሰዎች ሲናገር " አራት ሰአት ሙሉ ከተናገሩ በኃላ "ብዙ በማውራት ወርቃማ ጊዜያችሁን ማባከን ስለማልፈልግ ንግግሬን በዚሁ አበቃለሁ" ስለሚሉ ትሁት መሳይ መሪ ይናገራል።" (ብስጦሽ ቁዋጭ ቁዋጣሽ ቆር ፦ በታገል ሰይፉ ገጽ 11)
ንግግር ለመግባባት ነው። በቤተክርስቲያን ሆነ በአካል፣ በስልክ ሆነ በጽሑፍ ንግግር ሲረዝም ያሰለቻል። ይሰለቻልም። አንዳንድ ሰዎች ከተናገሩት ረጅም ንግግር መሐል ፍሬ ሐሳቡን ለመለየት ብዙ ጊዜ እንቸገራለን። ፍሬ ሐሳቡን ጨምቆ ነጥቡን መናገር ፍሬያማ ያደርጋል ወይም የንግግራችንን ፍሬ ሐሳብ በጥቂት ቃላት መግለጽ በቂ ነው።
ንግግር ካላስረዘሙ የተሰሙ የማይመስላቸው ወይም የማይረኩ ሰዎች በብዛት አሉ። አብሶ በስልክ ሲሆን ደግሞ አቤት ሲያሰለች!💀💀። ሰዎቹ ትልቅ ሰው ሆነው የንግግራቸው ርዝማኔ ሲያስቸግርህ ውይ መከራህ አቁሙ አትላቸው ነገር! የሚናገሩትን ካልሰማህ የሚያኮርፉም አሉ። እንደ ደበረህ በፊትህ እያሳየሃቸው እንኳ የማያቆሙም አሉ።
ንግግር ለመግባቢያ ከሆነ ጉዳዩ ከማስረዘሙ ጋር አይደለም ሐሳብን ከመግለጽ አንጻር ነው። እኔ በግሌ ንግግር ሲበዛ ከሚሰለቹ መሐል ነኝ። በቸርች ውስጥ ሐሳብ ዝም ብለው የሚያስረዝሙ ሊያስተላልፉት የሚፈልጉትን መልዕክት በውል የማያውቁ ሰባኪያን በጣም ያሰለቸኛል። ልንለምደው የሚገባ ነገር ልንናገርበት የምንፈልገውን ሐሳብ ማወቅ፤ ያንን ሐሳብ በትክክኛ መንገድና አገላለጽ መናገር ነው። ከዛ ሲያልፍ ጥቅም የለውም።
የሰው አህምሮ ለመስማት የሚችልበት ደረጃ አለው ከዚያ ካለፈ ሰውየው እየሰማህ አይደለም። ቢሰማህም አያስተውልም። ይህችን ካልኩ በቂ ነው እኔም ንግግሬን እንዳልስረዝም በዚሁ እንሰነባበት።
.....
Repost
የቴሌግራም ቻናሌን ይቀላቀሉ
/channel/theideaofs
#በራስህ_አስብ!!
ብዙዎች እነርሱ እንደሚያስቡት ስታስብ ትክክለኛ እንደ ራስህ ስታስብ፣ የተለየ ነገር ስለ አንተ ማውራት ይጀምራሉ። እንደራስህ አስብ። በመንጋ ማሰብ ቀላል ሲሆን በራስህ ማሰብ ግን የብልሆች ነው። አህምሮ የተሰጠህ እንደ ራስህ እንድታስብ ነው። ብቻህን ሆነህ ትክክል ልትሆን ትችላለህ። የተፈጠርነው በጋራ አንድ አይነት ሐሳብ እንዲኖረን አይደለም። ስለዚህ እኔ እንደ አንተ ማሰብ አይጠበቅብኝም፣ ወይም አንተ እንደ እንትና ማሰብ አይጠበቅብህም።
በራሳቸው አህምሮ የመመራት አቅም ጋር ያልደረሱ ሰዎች፣ ሁልጊዜ በዙሪያቸው ባሉ ሰዎች ሐሳብ ይመራሉ። ከሰዎች የምንማረው ነገር ብዙ ቢኖርም ማሰብ ግን ያለብን እንደ ራሳችን ነው። ከሰዎች ተማር፣ እንደ ራስህ አስብ። በራስህ ማሰብ ስትጀምር በራስህ መቆም ትጀምራለህ። ማስብ ያቆሙ ሰዎች የሌሎች ሐሳቦች ይመሯቸዋል።
የሐሳብ ትክክለኛነት የሚመዘነው በተቀበለው ሰው ብዛት ብቻ ሳይሆን፣ በእውነተኛነቱና በፍሬው ነው። በመንጋ የሚያስቡ ሰዎች ምንም ለውጥ የማያመጡ ሰዎች ናቸው። ስትፈጠር የተፈጠርከው በራስህ እንድትታስብ ነው።
ማሰብ መቻል ከመንገድ ዳር የሚገኝ አይደለም። በማንበብና ራስ ላይ በመስራት የሚመጣ ነው። ሰው በተፈጥሮ እኩል ነው ማንነቱ ግን የሚለካው ህይወቱን በሚመራበት የአስተሳሰብ ልክ ነው። በግልህ አስብ፣ በራስህ ኑር።
ዘሪሁን ግርማ
/channel/theideaofs
#ዘርህን_ዝራው!!
" እያንዳንዱ ዘር ውስጡ ደን አለው"
ዶ/ር ማይልስ ሙንሮ
" ፍላጎትህ ማሟላት ካቃተህ ወደ ዘር ቀይረው" ኦራል ሮበርትስ
ሁሉ ነገር የዘር ውጤት ነው፡፡ እግዚአብሔር ደግሞ በሰው ሁሉ ውስጥ ዘር አስቀምጧል፡፡ ሐሳብን አስቀምጧል፡፡
ሁሉ ነገር የሚጀምረው ከዘር ነው፡፡ ኢየሱስ ፦ " የስንዴ ቅንጣት መሬት ላይ ወድቃ ካልበሰበሰች ፍሬን አታፈራም" ያለን ስለ ራሱ ህይወት እየነገረን ቢሆንም እኛ ከዚህ ሐሳብ የምንማረው ተዘርተን እንደምናፈራ ነው፡፡
እንድንዘራው የተሰጠንን ዘር ካልዘራነው ፍሬን አንሰበስብም፡፡ ብዙ ክርስቲያኖች ገንዘብን ሊፈጥር የሚል ዘር (ሐሳብ) ይዘው ሳይዘሩት ገንዘብን በምኞት ብቻ ሊሰበስቡ ሲያስቡ ይገርመኛል፡፡
የማይክሮ ሶፍት ካንፓኒ ባለቤት ቢልጌል በአሁን ሰአት ቢሊየነር ነው፡፡ እንደዚህ የሆነው በውስጡ የነበረውን ዘር (ሐሳብ) ዘርቶት ፍሬ ስለሰጠው ነው፡፡ ገንዘብ ሆነለት ቅድሚያ ግን የነበረው (ሐሳብ) ዘር ነው፡፡ የፌስ ቡክ መስራች ማርክ ዙከንበርግ አንድ ተራ የሐርቫርድ ተማሪና ምንም የሌለው ተራ ሰው ነበር፡፡ በውስጡ ግን የአለምን ታሪክ የሚቀይር ዘር ነበረው፡፡ ዘራው ብዙዎችን የሚሸከም ዛፍ ሆነ፡፡
ታውቃለህ አንተ ውስጥ ያለው ዘር ብዙ ትውልድ መቀየር እንደሚችል? ዛሬ ምንም ላይኖርህ ይችላል፥ ወይም እግዚአብሔር ለአገልግሎት ጠርቶህ የራዕይ ዘር ውስጥህ ኖሮ እንዴት መግለጥ እንዳለብህ ግራ ተጋብተህ ይሆናል፥ ወይም አንድ ንግድ ለመጀመር አስበህ (ዘር ተሸክመህ) ግን ምን ማድረግ እንዳለብህ ላታውቅ ትችላለህ፥ ወይም ራዕይ ይዘህ፣ ዘር ይዘህ ግን እንዴት መሆን አንዳለብህ ላታውቅ ትችላለህ ወዘተ፤ ምስጢሩን ልንገርህ በመሬትህ ላይ ዝራው ይበቅላል፡፡ ብዙ ሰዎች ብዙ ዘር አላቸው ስለማይዘሩት ፍሬን አይሰጥም፡፡
እግዚአብሔር የማትዘራውን ዘር አይሰጥህም፡፡ አንተም ያልዘራህውን አታጭድም፡፡
ኦራል ሮበርትስ ያሉትን ሐሳብ ላስፋው፦
አንድን ነገር ሞክረህ ካልተሳካልህ ወይም ካልሆነልህ እንደ ገና ወደ ዘርነት (ወደ ፀንሰ ሐሳብ) ቀይረው እንደገና ዝራው፡፡ ታውቃለህ አንዴ ዘርተህ ካልሆነልህ አትተወው መልሰህ ዝራ ፡፡ እግዚአብሔር እንድትዘራው የሰጠህን ዘር ዝራ ፡፡ ተዘርቶ ማይበቅል ነገር የለም ፡፡
ብዙ ጊዜ ለምንድነው ሰው በአባቱ የሚጠራው በእናቱ ለምን አልሆነም ፥ ብዙ የምትለፋው እናት ናት የሚል ጥያቄ አልፎ አልፎ አስብ ነበረ ኃላ ላይ ሲገባኝ መልሱም አገኘሁት ዘር ያለው ለካ አባት ውስጥ ነው!! ትውልድ የሚያስቀጥል ዘር፡፡ ውስጥህ ትውልድን የሚፈጥር ዘር አለህ።
ትውልድን የሚገልጥ ለአንተ ብቻ የተሰጠህ የራዕይ ዘር ወይም የራዕይ ሐሳብ አለ ዝራው፡፡ በአለም ላይ የተሳካላቸው አገልጋዮች ሆኑ ስኬታማ ግለሰቦች ያላቸውን ዘር ወጤቱ አሁን ያሉበትን ፈጠረ፡፡ እስካዛሬ ዘር ተሸክመህ ካልዘራኽው ዛሬ ርስትህ ላይ መዝራት ጀምር ፡፡ ዘርህን አሳድግ፥ አብዛ፡፡ ዛሬ ጀምር፡፡ የጀመርክ ደግሞ ፍሬ እስኪሰጥ ጠብቅ፡፡ አፍሩ፡፡
ዘሪሁን ግርማ
/channel/theideaofs
#ቻርልስ_ፊኒ_ታላቅ_የወንጌል_አርበኛ!!
በወንጌል አገልግሎት ዙሪያ ብዙ ፍሬን ካፈሩ የወንጌል አገልጋዮች አንደኛው ቻርልስ ፊኒ ነው። ቻርልስ ከወንጌል አማኝ ቤተሰብ ቢወለድም ጌታን ለመቀበል እስኪገባው ድረስ ጌታን አልተቀበለም። በቤተ ክርስቲያን ያሉ አገልጋዮች ንስሃ እንዲገባ ሊጸልዩለት ሲነግሩት "ሐጢያተኛ መሆኔ ሲገባኝ ትጸልዩልኛላችሁ" ይላቸው ነበር። ቻርልስ ፊኒ የዕብራይስጥ፤ የላቲን፤ የግሪክ ቋንቋዎችን ያጠና ሲሆን በተጨማሪም በህግ ተመርቋል። ቻርልስ ምንም እንኳ አገልጋዮች ንስሃ ግባ ሲሉት እንቢ ይል የነበረ ቢሆንም ግን ደግሞ ጌታም ከተቀበለ በኃላ እጅግ በጣም ተጸጽቷል።
ቻርልስ በወንጌል ከተለወጠ በኃላ በየመንደሩ ስለ ኢየሱስ ይመሰክር ነበር። መንፈስ ቅዱስ ህይወቱን ስለቀየረው ወንጌል መመስከር ስራው አደረገው። የሚያውቃቸው ሰዎች ሲያገኝ በየጎዳናው ለሚያገኛቸው ሰዎች ሁሉ ከሐይማኖት መልክ ሳለው ከስም ክርስትና እንዲላቀቁ ይናገር ነበር። ቻርልስ በ1824 በፕሪስፒቴሪያን ኮሌጅ ከተማረ በኃላ በዛችው ቤተክርስቲያን ተሹሞ ማገልገል ጀመረ።
ፊኒ የ18ኛው ክፍለ ዘመን በአሜሪካ ታላቁ ወንጌላዊ ይባል ነበር። የተለያዩ መጽሐፍትን የጻፈ ሲሆን "ነፍሳትም ለክርስቶስ መማረክ" የተሰኘው መጽሐፉ ብዙዎችን በወንጌል ስለመድረስ ይናገራል። የፊኒ አገልግሎት ንግግሩ ቀላልና በመንፈስ ቅዱስ የተሞላ ስለነበር ብዙ ሰዎች በቀላሉ ራሳቸውን ለጌታ ይሰጡ ነበር። እንደዛ ቢሆንም እርሱ በሚያገለግበት ዘመን የቤተክርስቲያን መልክ እጅግ አስከፊ ሁኔታ ላይ ደርሶ ነበር። በእርሱ ዘመን የነበረው ሁኔታ አሁን የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ያለችበት ሁኔታ ይመስል ነበር። ኢዮብ ገብረእግዚአብሔር "ብርቅዬዎች የወንጌል አገልጋዮች" በሚለው መጽሐፉ በገጽ 105 ላይ በዛ ዘመን ያለውን ሁኔታ እንዲህ ይገልጸዋል
"ቻርልስ ፊኒ ጌታ ለአገልግሎት በጠራው ጊዜ በአሜሪካ ቤተክርስቲያን (አብያተክርስቲናት) ክፍፍል የነበረ ሲሆን የክፍፍሉ ምክንያት አንደኛው ወገን " ከህግ እስራት ተላቀሃልና እንፈለክ መኖር ትችላለህ" የሚል ሲሆን ሌላኛው ወገን ደግሞ "እግዚአብሔር ሁልጊዜ የሚቆጣና መአተኛ አምላክ እንደሆነ ያስተምሩ ነበር።" ይላል።
ፊኒ ይህን ተግዳሮት አልፎ የጸጋ ወንጌል እንዳነው ሚዛናዊ በሆነ መንገድ ማስተማር ነበረበት። ይህንንም በተመለከተ በክርስቶስ ኢየሱስ የሚገኝ መዳን ሰዎች ጋር ሁሉ ይደርስ ዘንድ በዘመኑ ከነበረው የቤተክርቲያን ተግዳሮት በላይ በጸጋና በእውቀት ብዙ ሰዎችን በወንጌል ይደርስ ነበር። በፊኒ አገልግሎት ትልቅ ቦታ የነበረው የጸሎት ህይወቱ ነበር። ሁልጊዜ ለወንጌል አገልግሎት ከመውጣቱ በፊት እጅን ሰፊ ሰአት ይጸልይ ነበር። በጸሎት ያምን ስለነበር ስለ አንዲት ባሏ ወደ ቤተ ክርስቲያን እንዳትሄድ ስለከለከላት ሴት በጸሎት ስለተፈጠረው ነገር እንዲህ ብሏል።
"ባሏ ወደ ፕሮግራማችን እንዳትመጣ የከለከላት ሴት ነበረች፤ ፕሮግራሙ ሊጀመር ግማሽ ሰዓት ሲቀረው ጀምሮ በፀሎት በጌታ ፊት ቆየች። የሚያስጀምረው ደወል ሲሰማ ወደ ሳሎን በመሄድ ባሏን አገኘችው። እሱም ያላት እንደምን ዋልሽ? ሳይሆን ወደ ፕሮግራም ሂጂ ነው። . . . ሰውየው ለሚስቱ የፈቀደው በመወቀሱ ብቻ ሳይሆን ከሷ ጋር ወደ ስብሰባው ሄዶ ወሬ ለመልቀምና ለማላገጥ ነበር። በስብከቴ መሀል በሀይል የሚጮህ ድምፅ ሰማሁ፤ በጉባኤው መሀል አቋርጬም ወደ ስፍራው አመራሁ፤ ያ ሰው ነበር። እንደ ህፃን ልጅ ያለቅሳል። ንስሐ ገብቶ ወደ ቤቱ ሲሄድ ለመንቀሳቀስ አቅም አልነበረውም። ጓደኞቹን አንድ ባንድ መሰከረላቸው። በሙሉ ጊዜ ለማገልገል ሲወስን ወር እንኳ አልፈጀበትም። ብዙም ሳይቆይ የቤተክርስቲያን ሽማግሌ ሆኖ ማገልገል ጀመረ።"
(እነማን ነበሩ፣ በዓለማየሁ ማሞ)
በዘመኑ ብዙዎችን በግልም በጉባኤ ስብከትም ይደረስ ነበር። ከቻርልስ ፊኒ ህይወት የምንማረው ትልቁ ነገር ወንጌልን ስራ ማድረግና አጥብቆ መጸለይን ነው። ትንሽ ስለ እርሱ ታውቁ ዘንድ በጥቂቱ አልኩ። ስለ እርሱ የተጻፉ መጽሐፍት ብዙ አሉና አንብቡአቸው። ፊኒ በዮሐንስ 3:16 ስብከቱ 2250 ሰዎች ሲድኑ በእግሊዝ ርዕሰ ከተማ ለንደን ደግሞ በአንድ ቀን ከ1500-2000 የሚደርሱ ግለሰቦች ጌታን ተቀብለዋል፡፡ ፊኒ በተሳተፈበት የ1858-59 (እ ኤ አ ) ታላቁ የመንፈስ ቅዱስ እንቅስቃሴ አገልግሎት በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ 600,000 የሚደርሱ ሰዎች ድነዋል፡፡ ክብር ለኢየሱስ ይሁን።
©ዘሪሁን ግርማ
(የቴግራም ቻናሌን ይቀላቀሉ)
/channel/theideaofs
#ወዳጆችና-#አለማማጆች
(ዘሪሁን ግርማ)
እግዚአብሔር ያለ አስቸጋሪ ሰዎች አንተን አይሰራህም። በህይወትህ ፣ በአገልግሎትሀ፣ በማናቸውም ማህበራዊና በየቀን እንቅስቃሴያችን ወስጥ መለማመጃዎችና ወዳጆች ያጋጥሙሃል።
ሳትበደል ይቅርታ ማድረግን አትማርም ይቅርታ ማድረግን ካልተማርክ የክርስቶስን ባህሪ አናዳብርም። ስለዚህ እግዚአብሔር ይቅርታ ማድረግን ትማር ዘንድ የሚበድሉህን ሰዎች ወደ ህይወትህ ያመጣል ወይም ይመጣሉ። የሚያሳዝነው ግን ብዙ ሰዎች ጥላቻና ምሬት ይታይባቸዋል እንጂ ይቅር በማለት ወደ ማፍቀር አይመጡም። ልምምድ ከሌለ ፍጹም የሚባለው ማንነት አይኖርህም።
ሰዎች ሁልጊዜ አለማማጅ ሰዎች ይሰጣቸዋል። ስታምናቸው የሚከዱ ፣ ስትቅርባቸው የሚሸሹ ፣ ስትደገፋቸው የሚጥሉህ ፣ ስትወዳቸው የሚጠሉ ፣ ስምህን በከንቱ የሚያጠፋ ፣ አንተን ሳይሆን ከአንተ ጥቅም ብቻ የሚፈልጉ፣ የሚዋሹህ ፣ ክፉ ዘርን የሚዘሩ ሁሉ በህይወትህ ወደ ታላቅነት የሚያሻግሩ አለማማጆች ናቸው።
ለዚህ ነው አየሱስ በአንድ ስፍራ ላይ " የሚወዱአችሁን ብትወዱ ምን ዋጋ አላችሁ ያንን አህዛብ እንኳ ያደርጉታል" ያለው። ሰው እስኪነካ ማንነቱ መልአክ ነው ሲነካ ግን አውሬው የሚገለጥበት፣ ስለዚህ እግዚአብሔር አለማማጅ ሰዎችን ወደ ህይወትህ ይልካል። መከራ የሚያበላህ አለቃህ ትዕግስትን ካስተማረህ ወደ ተሻለ ማንነት እያሳደገህ ነው።
ህይወት ስላወክ ብቻ ሳይሆን የምትሰራው በትክክለኛ መፈተን ውስጥ ስታልፍ ነው። እግዚአብሔር የአንዳንዶቹን ድካም በእውቀት ሲቀይር የአንዳንዶቹን ማንነት በፈተና መቀየሩ ይገርማል። ወደ ህይወትህ የሚመጡት ሁሉ ወዳጆች መሆን አይችሉም። ብዙ ሰዎች ባለፈው ከጎዱዋቸው ሰዎች ተምረው ወደ ተሻለ ህይወት ከመግባት ይልቅ እንዲህ ተደርጌ በሚል ስሜት ውስጥ ይመላለሳሉ።
በዚህ ዘመን ብዙ ወጣቶች አሉ ትላልቅ ራዕይና አላማ ያላቸው እውቀትና ብቃት ያላቸው ናቸው የሚጎላቸው ግን ያንን ለማስፈጸም ሊከፈል የሚገባው ነገር ጋር ሲደርሱና ብዙ አለማማጅ ሰዎች ሲያጋጥሙአቸው ምን በወጣኝ ይላሉ። ወዳጅ የሆነ ሰው አቅም እንደሚሆንህ ሁሉ አለማማጅ የሆነ ሰው ደግሞ ጥንካሬንና ጥበብን ይሰጥሃል ። ሁሉ ሰው እንዲወድህ አትጠብቅ እሱ ሞኝነት ነው።
"የሚወዱህ ሰዎች ከሚሰሩህ በላይ የሚጠሉህ ሰዎች ይሰሩሃል"።
ብዙ ታላላቅ መሪዎች በቤተክርስቲያንም ያሉ በአለም ያሉ ትላልቅ የመጠላትና የትግል ደረጃዎች አልፈው ነው ብዙ ታላላቅ ስራ የሚሰሩት ። እድሜ ለአለማማጅ እየታገለ ጠንካራ አድርጓቸዋል።
" ፍቅርን መስጠት የምትማረው በማይመቹ ሰዎች ሰዎቸ መሐል ነው።"
ለሚወዱህ ብቻ ፍቅርን መስጠት ራስወዳድ ሲያደርግህ፣ የሚጠሉህን መውዱድህ ግን አፍቃሪ ያደርግሃል። ኢየሱስ ያንን ነው ያደረገው። ወዳጅነት ከመሬት አይገኝም ። እግዚአብሔር በየዘመናቱ ሁሉ ወዳጆች ይሰጠናል። እኔ ስለ ተሰጡኝ ትላልቅና ትናንሽ ወዳጆቼ ጌታን አመግናለው። የወዳጅ ሚና ትልቅ ነው። ከአለማማጅ በተቃራኒ ዎጋ ሳትከፈል የምትሰራውም በወዳጅ ምክር፣ ተግሳፅና ፣ ፍቅር ነው። ወዳጆችህን አትግፋ ብዙ ነገርህን ታጣለህና።
በህይወታችሁ አለማማጅም ወዳጅም አያሳጣችሁ። ሰው ዝም ብሎ ትዕግስትን አይማርም በነገሮች ካልተፈተነ በቀር። ብዙ ክርስቲያኖች የክርስቶስን ፍቅር ተካፍለናል ይላሉ እውነትም ነው። ግን የክርስቶስ ፍቅር የሚፈተነው ለሚጠሉን ሰዎች በምንሰጠው ምላሽ ነው። ፍቅር ድርጊትም ነው ሐሳብ ብቻ አይደለም። ስለ ፍቅር የሰበኩ ሰዎች እውቀቱን በማንበብም በመስማትም ያመጡታል። ፍቅር ግን ስጡ ብትላቸው ከየት ይመጣል ? ፍቅር የመሰራት ውጤት ነውና።
እንግዲህ መሰሪያ የሆኑ ሰዎች ወደ ህይወታችን ሲመጡ ከፍ ልንልና የተሻለ ነገር ወስጥ ልንገባ ነው ማለት ነው። አለማማጅ ሰዎችንና የሚመክሩን ወዳጆች አያሳጣን እላለሁ።
#repost
/channel/theideaofs
#በመልቀቅ_መዳን!!
የምንታገልባቸው ብዙዎቹን ነገሮች ስንመለከት የእኛ አይደሉም ወይም፣ ያለ ቦታቸው ቦታ ሰተናቸዋል፣ ወይም ያለ አግባብ የያዝናቸው ናቸው። በዚያም ምክንያት ያለ አግባብ ዋጋ እንከፍላለን። ግንኙነቶች፣ ጓደኝነት የተቃራኒ ጾታ ጓደኝነት ( Relationship) ወይም ከሰዎች ጋር ያለን ማንኛውም አይነት እንደማይቀጥሉ እየገባን ግን በትግል ለማስኬድ የምንታገልባቸው ግንኙነቶች ጉዳታቸው ከፍተኛ ነው። ባለ መልቀቅ ውስጥ የሚደረግ ዋጋ መክፈል ይባላል።
በግድ፣ በትግል፣ ከአንድ ሰው ብቻ በሚደረግ ጥረት የተገነባ ግንኙነት አስፈላጊ አይደለም ። በዚህ አይነት ግንኙነት ውስጥ ከሆንክ ለቀቅ አድርገው ለጊዜው የተጎዳህ ቢመስልም ነገ ግን ህይወትህን ዕድሜህንና ሐይልህን ትታደግበታለህ። የአንተ ያልሆነውን በግድ የአንተ ለማድረግ መታገል ከንቱ ዋጋ መክፈል ነው።
በዚህ አይነት ግንኘቱነት ውስጥ ከሆንክ ልቀቅ (ቂ) የአንቺ ካልሆነው ስትታገይ የአንቺ የሆነው ያመልጥሻል (ሃል) ልቀቅ (ቂ)። የአንቺ ህይወት የማይቀጥለው ያለ አንቺ ብቻ ነው። ከሚያደክም ከማያፈራና፣ ፍጻሜ ከሌለው ግንኙነቶች ተላለቀቁ።
በሰዎች ተበድለን ይቅርታ ባለማድረግ ውስጥ ካለን፣ ሰዎችንና በደላቸውን ባለመልቀቅ ራሳችንን ለበለጠ ጉዳት እናጋልጣለን። በሰዎች ከተበድልነው በላይ፣ ሰዎችን ባለመልቀቅ (ይቅር ባለማለት) በባሰ መጎዳት ውስጥ እናልፋለን። ይቅርታ ማድረግ የበደሉንን ሰዎች መፍታት ብቻ ሳይሆን ራሳችንን ነጻ ያወጣናል። ነክሰን የምንዛቸው ነገሮች መልሰው ጉዳታቸው ለእኛው ነው። ስለዚህ ለቀቅ።
ባለመልቀቅ የምንጎዳባቸው ነገሮችን በመልቀቅ ልንድንባቸው እንችላለን። የእኛ ያልሆኑ ነገሮች የእኛ አይደሉም። ይህ ነገር በተለያዩ ጉዳዮቻችን ያግጥመናል። የእኛ የሆነና ትክክለኛ ነገር ዋጋ አያስከፍለንም፣ መልቀቅ እያለብን የታቀፍነው ነገርም አደጋው ከፍተኛ ነው። በመልቀቅ እንዳን።
ዘሪሁን ግርማ
/channel/theideaofs
ሰዎች አልፈህ ለሰዎች ከራስ ወዳድነት በነጻ መልኩ ቅንና ለጋስ ስትሆን "ምን ፈልጎ ነው?" "የሆነ ነገር አስቦ ነው እንጂ ያለምክንያት እንዲህ አያደርግም" እንዲህ እንዲያ በሚል ሐሳብ ተይዘው የምታደርጋቸውን መልካም ነገር በፍርሃት ሊያዩ ይችላሉ። ምክንያቱ ደግሞ ሁለት ነው የመጀመሪያው፦ ሰዎች ስንባል እኛ አልፈን የማድረጉ ልምድ ከሌለን አልፈው የሚያደርጉትን በሙሉ 'የሆነ ነገር ፈልጎ ነው' ወደሚል እሳቤ ውስጥ ልንከታቸው እንችላለን። ሁለተኛው ደግሞ፦ እኛ ምንም ሳናደርግለት እርሱ ሲያደርግልን፣ መልካምነቱን በተለየ ፍርሃት ልናየውም እንችላለን። ምክንያቱም ያለንበት አለም የጥቀመኝ ልጥቀምህ አለም ነውና። እርስ በእርስ መጠቃቀም በራሱ ችግር ባይኖረውም ሰዎች ባይጠቅሙንም ልንጠቅማቸው አይገባም ማለት ግን ራስ ወዳድነት ይመስለኛል። አንዳንድ ብልጣብልጥ መልካም ሚመስሉት ከሰዎች የፈለጉትን እስኪያገኙ ሊሆን ይችላል፣ መልካምነት ግን መሆን ነው መልካም መሆን።
የዚህ አለም መልክ ቀማኛና ስግብግብ፣ ራስ ወዳድነት ስለሚበዛበት በዚህ አለም ውዱ ነገር መልካምነት ነው። መልካም ለማድረግ መተዋወቅ እና የሆነ ተጠቃቃሚነት መኖር አለበት የሚል መርህ በዚህ አለም ስርአቱ ውስጥ ገኗል።
እኛ የመጽሐፍ ቅዱሱ ሰዎች በጌታ ያመንን የዳነው 'እንዲሁ በነጻ' ዮሐንስ 3:16 በሆነ አዳዳን ነው በጸጋው በሆነ ህይወት ውስጥ ነው የገባነው ኤፌ 2:8 እኛ ባልከፈልንበት እርሱ ግን በከፈለበት ህይወት ነው። ለእኛ መልካም ለመሆን ምንም ምክንያት አያስፈልገንም። እኛ ያለነው በእርሱ መልካምነት ብቻ ነው። ከተሰጠን ማካፈል፣ ለሰዎች ሁሉ መቆረስ እኛ የመጣንበት ከክርስቶስ የተካፈልነው የህይወት ስርአት ነው። ከሰዎች ምንም ምላሽ ሳንጠብቅ መልካምን ማድረግ የበሰለ ሰው ህይወት አኗኗር ነው።
ዘሪሁን ግርማ
/channel/theideaofs
#ለምጣዱ_ሲባል_አይጧ_ትለፍ!!
ይህ አባባል የቆየ የአገራችን አባባል ነው። ይህን አባባል አሁን በግል ህይወታችን ሆነ እንደ አገር ለምናልፍበት ሁኔታ ልንመነዝረው እንችላለን። አንዳንድ ሁኔታዎችን የመታገሱ ምክንያት ሆነ ወይም አልፎ የመሔዳችን ምክንያት የአይጧ ትልቅነት ወይም የህይወታችን ወሳኝ ነገር ሆና ሳትሆን ያረፈችበት ምጣድ ለእኛ ብዙ ነገራችን ስለሆነ ነው።
በተለያዩ መንገድ እንደ አይጧ ያሉ ሆኔታዎች ያጋጥሙናል። በግል ህይወት፣ በቤተሰብ፣ በስራ፣ በአገልግሎታችን ባለን ማንኛውም ነገር የምንታገሳቸው። ያለ ትዕግሥትና ጥበብ አይጧን ለመግደል ስንነሳ ያረፈችበት ምጣድ ለህይወታችን አስፈላጊ ነገር ነው። ስለዚህም እንታገሳለን። እንደ አይጧ ያሉ ሁኔታዎች እስኪያልፉ ስንታገሳቸው የታገስናቸው እነሱን ፈልገን ሳይሆን ሞጣዱን ስለምንፈልግ መሆኑን አይረዱም። ለታላቁ ነገር ስንል ትንንሽ ነገሮችን ማለፍ ታላቁን ነገር ያተርፈዋል። ከታናናሽ ነገሮች ጋር መፋለም አሰልቺ ቢሆንም፣ ታላላቅ ነገሮችን የምንጠብቀው አንዳንዴ እንደ አይጧ ያሉ ነገሮች እስኪያልፉ በመታገስ ጭምር ነው።
ትላልቅ ነገሮችን ለማዳን ትናንሽ ነገሮች እስኪያልፉ መታገስ ያስፈልጋል።
ዘሪሁን ግርማ
/channel/theideaofs
#ከሰዎች_ሁሉ_ጋር_በሰላም_ኑሩ!!
ሰው ያለ "ሰላም" አብሮ አይኖርም። ሰላም እርስ በእርስ ላለን ቀጣይ መንገድ መሰረት ነው። ከሰዎች ጋር ባለን ማንኛውም ጉዞ 'በእኛ በኩል' ሰላም መሆን አለብን፣ ነገር በእነርሱ በኩል ሰላም ካልሆኑስ? ሰዎች በራሳቸው አህምሮ በፈጠሩት ነገር ከእናንተ ጋር ጠበኛ ሊሆኑ ይችላሉ፣ በቅናትና በፉክክር መንፈስ ጠበኛ ሊሆኑ ይችላሉ፣ ስለ እኔ እንዲህ ነው የሚያስበው ብለው ጠበኛ ሊሆኑ ይችላሉ፣ ወይም የሆነ ምክንያት ኗሯቸው ወይም ፈጥረው ጠበኛ ሊሆኑ ይችላሉ። ታዲያ ምን ልናደርግ እንችላለን? መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይለናል።
“ቢቻላችሁስ በእናንተ በኩል ከሰው ሁሉ ጋር በሰላም ኑሩ።”
— ሮሜ 12፥18
መጽሐፍ ቅዱስ በጣም አስደናቂ መጽሐፍ ነው።
"ቢቻላችሁ" "በእናንተ በኩል" "ከሰዎች ሁሉ ጋር" "በሰላም ኑሩ" ይለናል። የመጀመሪያው ቢቻላችሁ ሲል ከሰዎች ጋር በሰላም መኖር መፈለግ ዝም ብሎ የሚመጣ ሳይሆን ከተሰራ የህይወት መልካም ማንነት የሚመጣ ነው።
ከሰዎች ጋር እርስ በእርስ በሰላም መኖር የጋራ ጉዞ ነው። አንዳንድ ሰው በእርሱ ጋር በሰላም ለመጓዝ የምታደርጉትን ቅንነትና ትህትና በትዕቢት እያጣጣለ ሲቀጥል "ቢቻላችሁ በእናንተ በኩል" የሚለው ቃል ተግባራዊ ለማድረግ በእናንተ በኩል ሰላማችሁን ጠብቃችሁ መጓዝ ግድ ይሆናል። ያንን ስታደርጉ እንደ ሞኝና ፈሪ ልትቆጠሩ ትችላላችሁ አስታውሱ በዚህ አለም ላይ ሰላምን መጠበቅ እንጂ ጸብን መጫር ከባድ ሆኖ አያውቅም። ለዚህም ነው መጽሐፍ "ቢቻላችሁ" የሚለው።
በጸብ የሚያተርፈው ዲያቢሎስ ሲሆን ተጎጂዎች እኛው ነን።
"ከሰዎች ሁሉ ጋር" በሰላም መኖር ሐላፊነት የሚሰማውና የበሰለ ሰው ባህሪ ነው። ከሰዎች ሁሉ በሚያምኑም ከማያምኑም፣ ከሚቀርቡንም ከማይቀርቡንም ሰዎች ጋር በሰላም መኖር ግዴታ ነው። ሰዎች ቢጠሉህስ? ቢያሳድዱህስ? መጽሐፍ ቅዱስ መልሰህ አሳድ፤ ወይም ጥላቸው የሚለው ትምህርት የለውም።
አዎ አንዳንድ ሰው የሆነ ነገር ስለ አንተ ክፉ አውርቶ አንተ መልሰህ ያንን እንድታደርግ ሊያነሳሳህ ይችላል፤ ያንን ስትመልስ በክፋት ተሸንፈሃል ማለት ነው። ከላይ ባነሳነው ክፍል በቁጥር 17 ላይ እንዲህ ይለናል፦
“ለማንም ስለ ክፉ ፈንታ ክፉን አትመልሱ፤ በሰው ሁሉ ፊት መልካም የሆነውን አስቡ።”
— ሮሜ 12፥17
በሰላም የምንኖረው ለክፋት ክፋትን እየመለስን ክፋትን እያደረግን አይደለም። በሰላም ከሰዎች ጋር የሚኖሩ ሰዎች የበሰሉና ራሳቸውን የሚገዙ ሰዎች ናቸው። በሰላም ውስጥ መክሰር የለም ትርፍ እንጂ፣ በጠብ ውስጥ ትርፍ የለም ኪሳራ እንጂ። ሰላምን እንከተል። ከሰዎች ሁሉ ጋር በሰላም እንኑር። ሰላምን ከሚያደፈርሱ ነገሮች ራሳችንና መንገዳችንን እንጠብቅ።
ዘሪሁን ግርማ
/channel/theideaofs
#የሰንበት_ትምህርት_ቤት /#የልጆች #አገልግሎት/ (Sunday School)
#ልጆችን_ለእግዚአብሔር_አላማ_ማዘጋጀት
እግዚአብሔር ልጆችን ለቤተክርስቲያን ሲሰጥ አባል ለማብዛት ሳይሆን የእርሱን መልክ የሚገልጡ ትውልዶች በቤተክስቲያን በኩል ተሰርተው እንዲወጡለት ነው። ልጆች አደራ የተሰጡን የእግዚአብሔር ርስቶች ናቸው።
ታላቁ የወንጌል አገልጋይ ዲ ኤል ሙዲ "አንድ ህፃን ልጅ ጌታን ሲያገኝ ሙሉ ሰው ዳነ" ይል እንደነበር "ልጆችን ወደ እውነት መምራት" ከሚለው የአለማየሁ ማሞ መፅሐፍ ላይ አንብቤያለሁ። ቤተክርስቲያን ልጆችን የማስተማር፣የመምራት፣ አልፎም የልጆቹ ቤተሰቦች ላይ መስራት ይጠበቅባታል። ምክንያትም ወደ ቤተክርስቲያን ሲመጡ ሙሉ ነገራቸውን ይዘው ነው የሚመጡት የምንስል ባቸው ስዕል ነው የሚታይባቸው ስለዚህ ምን እንደምንስልባቸው እንጠንቀቅ።
ቤተክርስቲያን በልጆች አገልግሎት ዙሪያ የቅርብና የሩቅ እቅዶችን ዘርግታ በልጆች አገልግሎት ላይ መስራት አለባት። ብቃትና ሸክም ያላቸውን አስተማሪዎችን መመደብና ለአስተማሪዎቹ በየጊዜው ስልጠናን ማዘጋጀት አለባት። የልጆች አስተማሪ መሆን የሚገባቸው የተማሩና ከልጆች ጋር መግባባት የሚችሉበት አቅም ያላቸው አስተማሪዎች እንጂ፣ ስራ የሌላቸውን ሰዎች ዝም ብለን ልጆች ላይ መመደብ የለብንም።
የህፃናትንና የታዳጊ ወጣቶችን አገልግሎት በተደራጀ መልኩ መስራት አለብን። ዛሬ የማንሰራበት ልጅ ነገ ቤተ ክርስቲያንን በምን መልኩ ነው የነገ ተረካቢ ማድረጌ የምንችለው? በምንስ መልኩ ነው ለቤተ ክርስቲያን፣ የሐገርና፣ ለቤተሰቡ አልፎም ለማህበረሰቡ መጥቀም የሚችለው?
#ክፍተታችንን_እንወቅ!!
ቤተክርስቲያን በህፃናትና በታዳጊ ወጣቶች ዙሪያ ላለው ችግር ሐላፊነትን መውሰድ አለባት። ይህ ጉዳይ ችግር መስሎ ካልታያት በዚህ ጉዳይ ለመስራት አትዘጋጅም። በትውልድ ላይ ካልሰራን የሚያስፈራው ነገር ቤተ ክርስቲያን ልትቋቋመው የማትችለው የትውልድ ክስረት እንደሚጠብቃት አንጠራጠርም። የጌታን ቃል ከአለም ለይቶ የማያውቅ ጠዋት ቤተክስቲያን ማታ ናይት ክለብ የሚዞር ትውልድና ማህበረሰብ የሚመነጨው ከልጅነታቸው ጀምሮ የተደራጀ በቃሉ ላይ የቆመ አሰራር የለንም።
በልጆች ህይወት ላይ ቤተክርስቲያን የመንፈሳዊ ነገር ላይ ብቻ ሳይሆን በምድራዊ ነገራቸውም ላይ መስራት መጀመር አለባቸው። እንደ እኔ እምነት ከወንጌል ስራ በመቀጠል ቤተክስቲያን ገንዘቧንና ሐይሏን በሙሉ መጠቀም ያለባት በዚህ አገልግሎት ላይ መሆን አለባት።
#ምሳሌ_መሆን_የሚችል_ቤተሰብ
"ያልተንኳኲ በሮች" መፅሐፍ ላይ ፀሐፊ ጳውሎስ ፈቃዱ "እነርሱ ቤተክርስቲያን ከመሄድ ይልቅ ከአልጋቸው ሳይወርዱ፣ ወይም ቴሌቪዥን ሲመለከቱ ለመዋል መርጠው ፣ ልጆቻቸውን ወደ ቤተ ክርስቲያን የሚሸኙ ወላጆች ምን ይባላሉ? ልጆቻቸውን "ፀልዩ" እያሉ እነርሱ የማይፀልዩ እነርሱ እየዋሹ ልጆቻቸውን እንዳይዋሹ የሚመክሩትስ እንዴት ነው?" (ገፅ 84) ይለናል።
በሰአት ስንመለከተው አንድ ልጅ ከቤተክርስቲያን ውጪና በትምህርት ቤት ውጪ ብዙዉን ጊዜ የሚያሳልፈው በቤቱ ነው። ቤተሰብ ልጅን በመቅረፅ ደረጃ ትልቁን ድርሻ ይይዛል። ልጅን ከመንፈሳዊ ነገር የሚያራርቁ ቤተሰቦችና በህይታቸው ምሳሌ የማይሆኑ ቤተሰቦች ልጅን ወለዱ እንጂ በትክክለኛ ህይወት አሳደጉ አይባልም። አንድን ልጅ አይተህ ቤተሰቦቹ ምን አይነት እንደሆኑ ማወቅ ትችላለህ።
ልጅን በህይወትህ ካልመራህውን በንግግር አትመራውም። ጠያቂ ትውልድ ጋር ነው እየደርስን ነው። ልክ እንደ ቤተክርስቲያን ሁሉ ቤተሰቦችንም ልጆቻቸው እነርሱ የፈጠሯቸው ሳይሆኑ ከእግዚአብሔር የተሰጣቸው፣ አደራዎች ናቸው። ምሳሌ በመሆን ልጆችን መምራት አስፈላጊ ነው። በልጆች ላይ እየሰሩ ያሉ ቤተክርስቲያናት እጅግ ሊመሰገኑ ይገባል።
ዘሪሁን ግርማ
/channel/theideaofs
#Misunderstood_የመደረግ_ፈተናዎች!!
ሰዎች የምታደርጉትን መልካም ነገሮች ሳይረዱ ሲቀሩ ወይም በተሳሳተ መንገድ ሲረዱ ጉዳቱ ቀላል አይሆንም። የምትለፉበትን ነገር የማይገባቸው፣ ማንኛውም የምታደርጉአቸውን ጥረቶች የማይረዱ ሰዎች አብሶ የቅርብ ሰዎች ሲሆኑ ከባድ ፈተና።
ሁላችንም በአንድም በሌላም መንገድ እንደዚህ አይነት የሰዎች ምላሽ ሊያጋጥመን ይችላል። በመልካም አስባችሁ ያደረጋችሁት በክፉ ሲተረጎም፣ ለምታደርጓቸው ነገሮችን በተሳሳተ መንገድ የሚረዱ ሰዎች ሲያጋጥሙ እነዚህን ነገሮችን የምናልፍበት ጥበብ ሊበዛልን ይገባል።
ሁሉም ሰው እኩል አይረዳም፣ አንዳንዱ ወዲያው አይረዳም (ይህ አይነቱ በቆይታ የሚረዳ ነው) አንዳንዱ በልቡ ካለው ክፋት አንጻር ደግሞ አውቆ መረዳት ላይፈልግ ይችላል። ሰዎች በተሳሳተ መንገድ ሲረዱህ የምትወስደው ውሳኔ ወሳኝ ነው።
እንደነዚህ አይነት ሰዎች ሲገጥሙን በትዕግስት ማለፍ እንደሁኔታው አስፈላጊውን መንገድ መከተል ሊጠይቅ ይችላል። እነዚህን አይነት ፈተናዎች የምናልፍበትን ጥበብና እውቀት እንዲሁም ትዕግስት ልናዳብር ይገባል። እነዚህ አይነት ፈተናዎች የመገለልና፣ ያለመፈለግ እንዲሁም ስም የማጥፋት ነገሮች ሊኖሩት ይችላል።
Misunderstood ከመደረግ ነጻ አንሆንም፣ ይህን ለማወቅ እኛም ለመልካም አስበው እኛ በክፉ የተረዳናቸው ሰዎች እንዳሉት ሁሉ ማለት ነው። በእውነት ቆሞ በተሳሳተ መንገድ የታማና የተጠላ፣ ያደረገው ነገር ሁሉ በክፋት የታየበት ሁሉ የኃላ ኃላ አሸናፊ መሆኑ አይቀርም።
ዘሪሁን ግርማ
/channel/theideaofs
#ስህተትህን_ለለውጥ_ተጠቀምበት!
በቅርቡ ከተወሰኑ ወዳጆቼ ጋር በአንዳንድ ጉዳይ እያወራን በመሐል በቦታው መነገር የሌለበትን ነገር በድንገት ተናግሬ የውይይታችንን አቅጣጫ ወደ ሌላ ነገር ቀየርኩት። ነገርየው ውስጤ ይብሰለሰል ስለነበር አወጣሁት። የተናገርኩት ነገር ምንም ትክክልና እውነተኛ ቢሆንም፣ በጊዜው ያ ቦታ ቦታው አልነበረም። ከሶስት ቀናት በኃላ ያደረኩት ትክክል እንዳልነበር ስለ ገባኝ፣ አንደኛው ጋር ደውዬ ይህን ነገር በዚህ ቦታ ማንሳቴ ትክክል አልነበረም። ይቅርታ አልኩት። ከዚህ ከራሴ ስህተት የተማርኩት ነገር የምንናገረው ነገር እውነተኛ መሆኑንና አለመሆኑን ብቻ ሳይሆን የምናገርበት ቦታና የምንነግራቸው ሰዎች ጉዳዩ ይመለከታቸዋልን? ብዬ መጠየቅ እንዳለብኝ ነው።
ልክ እንደ እኔ ሁላችንም በተለያየ ምክንያቶች እንሳሳታለን፣ ወይም ልንሳሳት እንችላለን። ነገር ግን የተሳሳትነው ጉዳይ ላይ ደግመን ላለ መሳሳት ትምህርትን መውሰድና በዚያ አቅጣጫ ራሳችን ላይ መስራት ይኖርብናል። ስህተትና ድካም የሰው ልጆች በህይወት ሳሉ የሚያጋጥማቸው ነገር ሲሆን ከስህተት-መማር እና ከድካም- መበርታት የሚባሉ ነገሮች አብረው አሏቸው። እያንዳንዱ የተሳሳተ ሰው ከስህተቱ የመማር ዕድል ይኖረዋል! እያንዳንዱ የደከመ የመበርታት ዕድል አለው።
ስህተቶቻችንን ራሳችንን ለማረም ልንጠቀምበት ሁሌም እንችላለን። የመለወጥና ከስህተቱ የመታረም ዕድል የሌለው ሞተ ሰው ነው።
ዘሪሁን ግርማ
/channel/theideaofs
#በንጹህ_ሞቲቭ_በሚያገለግሉ_እረኞች_ስር_የወደቁ #መንጋዎች!!
"ንጽህና" ስንል የህይወት ንጽህና፣ የትምህርት ንጽህና፣ የኑሮ ንጽህና፣ የተቃራኒ ጾታ ንጽህና፣ የአገልግሎት ንጽህና፣ የህብረት ንጽህና፣ የፍቅር ንጽህና፣ የልምምድ ንጽህና፣ የአስተሳሰብ ንጽህና እነዚህና የመሳሰሉትን ያካትታል። ንጹህ ያልሆነ ማለት ከእነዚህ በተቃራኒው ማለት እንደሆነ ግልጽ ነው።
Motive የሚለው ቃል " የምናገለግልበት ከጀርባ ያለ ምክንያት" የሚለውን ሐሳብ ለመግለጽ የምጠቀመው ሲሆን የቃሉ ቀጥተኛ ፍቺ "ምክንያት" ማለት ነው። ሁልጊዜም አንድን ነገር የምናደርግበት ከኃላ ያለው ምክንያት እጅግ ወሳኝ ነው። የምናገለግልበት ምክንያት ከተሳሳተ አገልግሎታችን በራሱ የሳተ ነው።
አገልጋይ እውነተኛ አገልጋይ ከሆነ ለተጠሪው በሆነ አላማ እግዚአብሔርን የሚያገለግል ሲሆን የተስተካከለ ሞቲቭ ያለው አገልጋይ የሚኖረውና የሚያለግለው፦
፨ ለእግዚአብሔር ክብር
፨ ለመንጋው ጥቅም
፨ ለራሱ በረከት
፨ የዲያቢሎስን መንግስት ለማፍረስ ነው!!
መጋቢ ጻድቁ አብዶ በአንድ ንግግራቸው ፦ በንጹህ ሞቲቭ በማያገለግሉ እረኞች ስር ያሉ
መንጋዎች "በእረኞችም ይበላሉ፣ በአራዊትም ይበላሉ።" ብለዋል።
"ንጹህ ያልሆነ ሞቲቭ" ይዘው የሚያገለግሉ አገልጋዮች መንጋውን ለእግዚአብሔር አላማ ከማብቃት ይልቅ ለራሳቸው ጥቅም ብቻ መንጋው ላይ ይበዘብዛሉ። መበዝበዝ ገንዘብ ብቻ ሳይሆን፣ ጊዜ፣ አቅምንና ህይወትን ይጨምራል። መንጋውን በቀጥታ ሆነ በተዋዋሪ ለግል ጥቅማቸው ያዘጋጁታል፣ ይሰሩታል፣ ይጠቀሙበታል። ከእረኛው ተርፎ የሚወጣው ደግሞ በውጪ ባለው አሰፍስፎ ላለው ሌላ አውሬ ተጋላጭ ይሆናል።
ንጹህ ባልሆነ ሞቲቭ የሚያገለግሉ አገልጋይ ባህሪያትን በጥቂቱ እንመልከት፦
፨ ገንዘብ ይወዳሉ፦ ገንዘብ ለእግዚአብሔር መንግስት ስራ አስፈላጊ ቢሆንም፣ ነገር ግን እነዚህኞቹ እረኞች ገንዘብን ለራሳቸው ጥቅም ተመኝተው ባልተቀደሰ መንገድ መንጋውን የሚመዘብሩ ናቸው።
፨ የታዋቂነት ጣኦት አለባቸው፦ በአገልግሎት አቅጣጫና ለአገልግሎት አላማ ሞገስንና መሰማትን የሚሰጥ እግዚአብሔር ነው። እነዚህ አይነት እረኞች የሚያሳስባቸው ስለሚያገኙት አንቱታና ከበሬታ እንጂ አትኩሮታቸው መንጋው ላይ በመስራት ፍሬያማ ማድረግ ላይ አይደለም። እነዚህ አይነት እረኞች የተሻለ ብለው የሚያስቡአቸውን ሰዎች ካገኙ ቀድሞ አብረው የቆዩትን ለመተው ግድ የማይሰጣቸው ናቸው።
፨ ቸልተኛ እረኛ ናቸው፦ መንጋው ስለሚማረው ትምህርት፣ ስለ መንጋው ህይወት መጠበቅና ማደግ፣ ስለ መንጋው ፍሬያማነት ግድ የላቸውም አዳራሹን ከሞላና ገንዘብ እስከ ሰጠ ድረስ ምንም ችግር የለባቸውም። ሞያተኛ ናቸው።
፨ በመንጋው ላይ ይሰለጥናሉ፦ እነዚህ አይነት እረኞች ፈቃዳቸውን በሙሉ በመንጋው ላይ የመጫን አሰራርን ይከተላሉ። መንጋውን ለክርስቶስ ለሚሆን ህይወት ለማብቃትና በትክክለኛው መስክ ከማሰማራት ይልቅ በእነርሱ በሚመች መልኩ ይገነባሉ።
መንጋውም የእረኛውን ህይወትና አኪያሄዱ እንደ እግዚአብሔር ቃል መሆኑንና አለመሆኑን ማየት አለባቸው።
©ዘሪሁን ግርማ
/channel/theideaofs
#የትኩረት_ናፋቂነት_ሱስ (በሽታ)
The great Comeback የተባለለት በዚህም ሳምንት የተለቀቀው የ Chris Rock "Selective Outrage" በተሰኘው ስታንድአፕ ኮመዲ ካነሳቸው ከብዙ ሐሳቦች አንጻር በስፋት መነጋገሪያ ሆኗል። በኮሚዲ ስራው መሐል " በአሜሪካ ትልቁ ሱስ ትኩረት የመፈለግ ሱስ (the addiction of attention) ነው" ይለናል። ይህ መልዕክት አሁን ያለውን ትውልድ ቅልብጭ አድርጎ ያሳያል።
ሰዎች በአካል እንወድሃለን ከሚሉን ይልቅ በየፌስ ቡክና ማህበራዊ ሚዲያዎች ፎቶአችን ላይ በሚያደርጉት react ላይክና ኮሜንት ሱስ ውስጥ ገብተናል። የሰዎችን ትኩረት የመፈለግ ከልክ ያለፈ ፍላጎት (ሱስ) ውስጥ ተጠምዷል። አንድ ፎቶ በፌስ ቡክ ወይም በኢንስታግራም ላይ ለጥፈን አስሬ እየገባን ላይክ የምንቆጥርና🤔🙄😀😂 በብዛት ላይክ ካልተደረገ ልባችን የሚወርድ ስንቶቻችን እንደሆንን ራሳችንን እናውቃለን።
ማህበራዊ ሚዲያዎች ከመጡ በኃላ ሰዎች ከሰዎች ላይክና ኮሜንት ሆኗል ያንን ክሪስ ሮክ ትኩረት የመፈለግ ሱስ ይለዋል። ስነ ልቦናችን ሰዎች በብዛት ላይክ ካደረጉት እንደተወደድን የምናስብ ካልተደረገ ደግሞ ራሳችንን የምናጣጥል ማንነታችንን በሰዎች ላይክና ኮሜንት የምንመዝን ትውልድ የበዛበት የትኩረት ናፋቂነት በሽታ የተስፋፋበት ዘመን ላይ ነን። ከልክ ያለፈ ትኩረት ናፋቂነት ሱስ ብቻ ሳይሆን በሽታም ነው።
በዚህ ዘመን ብዙ ወጣቶች በዚህ በሽታ ተጠቂ ናቸው። ራሳቸውን የሚቀበሉት ሰዎች በሚሰጧቸው ኮሜንት ላይ፣ ማንነታቸውን የገነቡት በሰዎች ላይክ ብዛት ላይ ነው። ከዚህ ሱስ ለመውጣት ራሳችንን ወደ ራሳችን ማየትና ራስን መቀበል ላይ መሆን አለበት። ከልክ ያለፈ ትኩረት ናፋቂነት በብዙ መንገድ ሊገለጽ ይችላል ምንጩ ግን ራስን በልክ አለመቀበልና፣ ደስታንና በራስ መተማመንን ሰዎች በሚሰጡን አስተያየት ላይ የመመስረት አባዜ ነው። ህይወት ከሰዎች አስተያየት፣ ማንነት ከሰዎች አድናቆት በላይ ነው።
ዘሪሁን ግርማ
/channel/theideaofs
ያለ እነርሱ የምንቀጥል ለማይመስላቸው!!
የመጣንበትን መንገድ የማያውቁ፣ የታገለንን ያሸነፈልንን እና እግዚአብሔር እኛን የመራበትን የህይወት መንገዶች ያልተረዱ አንዳንዶች ዛሬም ያለ እነርሱ ህይወታችን የማይቀጥል የሚመስላቸው፣ ከእኛ ጀርባ ትናንትን ያሻገረን እግዚአብሔር እንደቆመ ያላዩ ናቸው። ያለ እናንተ ነበርን ያለ እናንተም እንኖራለን። የሆነውን ሁሉ የሆነው በእግዚአብሔር ብቻ ነው ነገም የምንቀጥለው በእርሱ ነው።
/channel/theideaofs
#የመጽሐፍ_ቅዱስ_ስልጣን!!
"መጽሐፍቶችን አንብብ፣ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ኑር።" ቻርልስ ስፐርጀን
በአለም ታላላቅ መጽሐፍት የሚባሉ ብዙ መጽሐፎች አሉ። ብዙዎቹ የሰው አህምሮና ልብ ውጤቶች ሲሆኑ፣ ጥቂቶች በሐይማኖት ሰዎች የተጻፉ ናቸው። ነገር ግን የመጽሐፍ ቅዱስን ያህል ለዋጭ፥ አስተማሪና፣ የሚያርም፣ የሚተክል፣ የሚመክር የዘላለም ህይወት እውቀት የሚገኝበት ብቸኛ መጽሐፍ የለም። የእግዚአብሔር ቃል ስልጣን ማመን ማለት፣ የእግዚአብሔር ስልጣን መረዳት ማለት ሲሆን፣ በቃሉ ማመን ደግሞ በቃሉ ውስጥ የተጻፈው ሁሉን መቀበል ነው። ማንም ከዚህ ቃል በታች እንጂ በላይ መሆን አይችልም።
የተጻፈው በእግዚአብሔር መንፈስ መሪነት፤ አስጻፊነት፤ ተቆጣጣሪነት ነው። በእግዚአብሔር መንፈስ መሪነት ስለተጻፈ የእግዚአብሔር ቃል ነው። በሰው ልጆች ሁሉ ላይ ስልጣን ያለው መጽሐፍ ነው፣ ላመኑት የዘላለም ምንጭ የሆነ መጽሐፍ ሲሆን ላላመኑት ፍርድም ያለበት መጽሐፍ ነው። የተጻፈልን ግን ለህይወትና ለትምህርታችን ነው። የመጽሐፍ ቅዱስ ስልጣን ለመረዳት የደራሲውን ስልጣን ማወቅ አስፈላጊ ነው።
የመፅሐፍ ቅዱስ ስልጣን፦
* ከወጎችና ከስርአት በላይ ነው
* ከምክንያታዊነት (Logic) በላይ ነው ።
* ከስልጣናትና ከሃይሎች በላይ ነው
* በምድር ላይ ካሉ መፅሐፍት ሁሉ በላይ ነው
* የሰው ማንነት ልብና አህምሮ ማፍለቅ ከሚችለው በላይ ነው።
* ከሰው አገዛዝና አስተዳደር በላይ ነው
* ከቤተክርስቲያንና በውስጥዋ ካሉ አገልጋዮች ስልጣን በላይ ነው
* ከስጋዊ ልምምዶች ከማንኛውም እውቀቶች በላይ ነው
* ከነገስታትና ከገዢዎች ስልጣን በላይ ነው
* ለማስተማር ፣ ለመለወጥ፣ ለመገሰጽ የሚችል ብቸኛ መጽሐፍ ነው
*ነፍስን ጅማትን መንፈስንና ልብን መመርመር የሚችል ብቸኛ መፅሐፍ ነው።
* ከጸጋ ስጦታዎችና በቤተክርስቲያን ውስጥ ካሉ ማናቸውም ልምምዶች በላይ ነው።
የቤተክርስቲያንና የአገልጋዮች ውድቀት የሚጀምረው ከእግዚአብሔር ቃል ስልጣን ስንወጣና መንፈሱ ከሚናገረው ሐሳብ ስትወጣ ነው። ቤተክርስቲያናት አገልጋዮች ምንም ስኬት ላይ ይኑሩ ቃሉ ሁሌም ህያው መካሪያቸውና መሪያቸው ነው የአንዲት ቤተክርስቲያን ክብርና ስኬት በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ባላት አቋም የተመሰረተ ነው። ቤተክርስቲያን ወደ ቃሉ ህይወት መመለስ አለባት። ብዙ አገልጋዮችም የእግዚአብሔር ቃል እንሰብካለን እያሉ ቃሉን አለማንበባቸውንና አለማክበራቸውን ስናይ ማንንና ምን አይነት ቃል ነው የሚሰብኩት ታዲያ ያስብላል?
የላቭ ኦፍ ኦሲስ ቤተክርስቲያን ዋና መጋቢ የነበረው ጆን ኦስቲን " ይህ መጽሐፍ ቅዱስ የእኔ ነው ነህ ያለኝን ነኝ" ይል ነበር። እዚያ ቤተክርስቲያን መጽሐፍ ቅዱስ ይዞ የማይመጣ የእሱ አባልን ይገስጽ ነገር። ሪቫይቫል ሊመጣ ይችላል የምትጠብው ግን በቃሉ ህይወት ላይ ስትጸና ነው። ራሳቸውን ለቃሉ ስልጣን የሚያስገዙ አስተማሪዎችና መሪዎች ያስፈልጉናል። የቃሉ ስልጣን ከምንም ነገርና በሁሉም ላይ ባለስልጣን ነው። ቃሉን እናንብብ፣ እናጥና፤ ያን ጊዜ የእግዚአብሔር ጥበብና እውቀት ህይወታችንን ይለውጣል።
ዘሪሁን ግርማ
(በድጋሚ የተለጠፈ)
/channel/theideaofs
#ከሰዎች_ጋር_አትታገሉ!!
ሰዎች ስለ ራሳቸው ያውቃሉ፣ ስህተት እያደረጉ እንኳን ለመመለስ በምትሄደው ርቀት ውስጥ ወይም ለመደገፍ በምትሄደው ጉዞ የሰዎች መልስ 'አለመፈለግ' ከሆነ ተዋቸው። ከሰዎች ጋር ለሰዎቹ ጉዳይ አትታገል። አባቶቻችን 'ከባለቤቱ በላይ ያወቀ ቡዳ ነው' ይላሉ።
ለሰዎች ተብሎ የሚከፈል ማንኛውም ዋጋ በሰዎቹ ምላሽ ላይ የተመሰረተ መሆን ይኖርበታል። የአንተ ዋጋ መክፈልህ ለእነርሱ ለመደገፍ መስሎ ካልታያቸው ብዙም አትታገል። ተዋቸው። ዋጋ የምትከፍልበትን ቦታ ምረጥ፣ የምታፈራበትና ሰዎችን የምትጠቅምበት ከሆነ መልካም ማድረግ መልካም ነው አድርገው። ከዚያ ውጪ በህይወታቸው መኖርህ ዋጋ ከሌለው ሰዎች ጋር ብዙ አትድከም። እመነኝ ይህን ካልተረዳህ በህይወትህ ከፍለህ ከምትማራቸው ነገሮች አንዱ ይህ ይሆናል።
በአጭሩ የእናንተን አስፈላጊነት ከማይታያቸው፣ ለእነርሱ የምትከፍሉት ዋጋ ከማይገባቸው ሰዎች ጋር አትታገሉ። ሰዎቹ ስለ ራሳቸው ያውቃሉና ስለ ራሳችሁ እወቁ። ይህ ጽሑፍ ለቅኖችና መልካም ልብ ላላቸው ነው።
/channel/theideaofs
#ሁለት_የሳቱ_ሐሳቦችና_አደራረጎች!!
በቤተክርስቲያን እና በአገልግሎት ህይወቴ ሁለት አይነት ሰዎች ይገርሙኛል። የመጀመሪያው- አገልጋይ የሆነ ሰው በአንዳች ነገር ሲስት፣ የሳተውን አገልጋይ ሆነ ግለሰብ "ትክክል አልሰራህም" ብለው እንደ እግዚአብሔር ቃል የሚናገርሙና ለማረም የሚሰሩ ሰዎችን "ቢወድቅ ለጌታው ነው" ነው "እናንተ ምን አገባችሁ?" አይነት ነገርን የሚናገሩ ደጋፊ አራጋቢ ሰዎች ስህተቱን (ስህተት ስንል የትምህርት፣ የልምምድ፣ የሞራል ወዘተ ሊሆን ይችላል) በጭፍን የሚደግፉ ሰዎች ድርጊቱን በቀጥታ ባይተባበሩትም በተዘዋዋሪ ደጋፊ ናቸው። እነዚህ አይነት ሰዎች አገልጋዮቹ እንዳይታረሙ የሚሟገቱ ናቸው እንጂ አገልጋዮቹን የሚጠቅሙ አይደሉም።
እንኳን አገልጋዮች ቤተክርስቲያን ራሱ ከእግዚአብሔር ቃል ስልጣን በታች ናት። ቃሉ የማይገራትና የማያርማት የማይመራት ቤተክርስቲያን የክርስቶስ እንዳልሆነች ሁሉ እንደ እግዚአብሔር ቃል ባልሆነ የህይወት አኪያሄድ የማይሄድ አገልጋይ በሙሉ ራሱን ማረም፤ በሰዎችም ቢሆን መታረም አለበት።
የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ አይልም፣ ብለው ሌሎችን ለማቅናት የሚያርሙ ሰዎችን እንደ "ፈራጅና ኮናኝ" የሚቆጥሩ ጭፍን ምዕመናን በምን መልኩ ክርስቲያናዊ ህይወታቸው ሊሆን ይችላል። አጉል ደጋፊዎች ለእግዚአብሔር ሳይሆን ለግለሰብ የምትሟገቱ ክርስቲያኖች ራሳችሁን አርሙ። የተሳሳቱ ሰዎች ወድቀው እንዲቀሩ ሳይሆን፣ ታርመው እንዲቀጥሉ ማረም እጅግ የሚገባ ነገር ነው።
ሁለተኛዎቹ ደግሞ፥ እያገለገሉ ባልተገባ መንገድ እየሄዱ ራሳቸውን እያወቁ፣ ሰዎችም እያወቁባቸው ምንም ሳይመስላቸው ስህተታቸውን አጠንክረው የሚሄዱ 'አገልጋዮች' በምን መልኩ የክርስቶስ እና የክርስቶስ አካል አገልጋዮች ሊሆኑ ይችላሉ? ሰው በድካም ሊገኝ ይችላል፣ ለድካሙ ትምህርት ሰርቶ፣ በገንዘብ ተደራጅቶ፣ እግዚአብሔር የሰጠውን አደራ እና መንጋ ላይ እየቀለደ እንዴት የእግዚአብሔር አገልጋይ ሊሆን ይችላል? እግዚአብሔር ከታገሰ እንድንታረም እንጂ በዚያው ልምድ እንድንበረታታ አይደለም።
የወደቀ ይነሳል አዎ ይነሳል የሳተ ይመለሳል አዎ ይመለሳል! ነገር እግዚአብሔር የሚያነሳው አጥፍቶ ለመነሳት ራሱን ያዘጋጀውን ሰው ሲሆን የሳተም የሚመለሰው ራሱን ለመመለስ ሲያዘጋጅ ነው። አንድ አገልጋይ በድካም ቢገኝ ራሱን በጌታ ፊት ማድረግና ራሱን ለመለወጥ ጌታ እንዲረዳው የተዘጋጀ መሆን አለበት።
ድካምና ልምድ (Habit) እጅግ ይለያያሉ። ጌታ ከድካማችን ሊያወጣን ዝግጁ ነው ድካም ወደ ልምምድ (Habit) ካደገ ግን መጨረሻው ጥፋት ነው። ዛሬን ሰዎችን ሸውደን ልናልፍ እንችል ይሆናል የማናልፈው ጌታ ግን አለ። ራስን ማንጻት እጅግ ያስፈልጋል። አገልጋይ ማለት ጌታ በእጁ አደራ የሰጠው ሰዎችን በእጁ ያየዘና አደራ ያለበት ሰው ነው። እነዚያን መንጋዎች የሚያሰናክል የህይወት ችግር ካለበት ራሱን በጌታ ፊት ማቅረብ አለበት እንጂ፣ ለጥፋቱ ክልልን የሚያደራጅ መሆን የለበትም።
ዘሪሁን ግርማ
/channel/theideaofs
#ተገኘልህ_ማለት_ርካሽ_ነው_ማለት_አይደለም!!
ትገኛለህ ማለት ርካሽ ነህ ማለት ሳይሆን የተሻልክ ነህ ማለት ነው። ለሰዎች ለመገኘት ቅንነት፤ ራስ ወዳድ አለመሆን እና መልካምነት ነውና። ሰዎች በቀላሉ ካገኘነው ነገር ይልቅ ዋጋ የሚያስከፍለንን ነገር ስንወድ እንገኛለን። እንዲሁ ለሚገኙልን ነገሮች ቦታ አንሰጥም። ማወቅ ያለብን በህይወታችን የተገኙልን ሰዎች ርካሽ ስለሆኑ ሳይሆን መልካም ስለሆኑ ነው። በምንፈልገው ጊዜ ከሚገልኝልን ወዳጅ ይልቅ አዲስ ላወቅነው ሰው ትልቅ ግምት ስንሰጥ እንገኛለን።
እግዚአብሔር የሚባርክህ በሰዎች ጭምር ነው። ሰዎች ተሰተውሃል ማለት እግዚአብሔር ጎብኝቶሃል ማለት ነው። ስለዚህ ወደ ህይወታችን የሚመጡትን ሰዎች በእግዚአብሔር አንጻር መረዳት ብልህነት ነው። ሰዎች ሲርቁን ወይም በስጋ ሲያልፉ ማድነቅ እንወዳለን አጠገችን ሳሉ በህይወታችን ያላቸውን ቦታ መንገር አንወድም።
አጠገባችን ያሉትን ሰዎች ከእኛ ጋር ስለተገኙ ብቻ መሔጃ የሌላቸው፥ ምንም ማድረግ የማይችሉ አድርገን መመልከት ጤናማነት አይደለም። ሰዎች ሲወዱን ሌላ ምርጫ እንደሌላቸው ማሰብ፤ ፍቅር ሲሰጡን እንደ ሞኝ ማሰብ፤ ዋጋ ሲከፍሉልን ቦታ አለመስጠት እጅግ የሚያሳዝን ሞኝነት ነው። ሰው ለእኛ ከሆነ እንዴት ነው ለራሱ መሆን የማይችለው? ምን አልባት የሚጠበቅበት ፊቱን ዞር ማድረግ ብቻ ሊሆን ይችላል።
፨ ሰዎች ሲገኙልህን አመስግናቸው ዋጋቸውን ልንነግራቸውና የተጠቀማችሁን ጥቅም ንገሩአቸው
፨ ሰዎች ሲገኙላችሁ አመስግኗቸው ለመልካምነታቸው እውቅናን ስጡ
፨የወደዱን ሰዎች የሰጡንን ፍቅር ከማቃለል እንቆጠብ፤ ፍቅራቸውን እንደ ሞኝነት አንመልከት
፨በምድር ላይ ከሰዎች በላይ በረከት በህብረት በላይ ከፍታ የለም። በህይወታችን ላሉ ሰዎች እውቅና እንስጥ!!
©ዘሪሁን ግርማ
/channel/theideaofs
#እየሄድክ...#እየሄድሽ!!
ህይወት ወደ ነገ እንጂ ወደ ትናንት አታድግም። ከትናንት ከተማርንበት ለዛሬ ብርታት ለነገ ደግሞ አቅም ይሆናል። ማንኛውም ሰው ትናንት ነበረው፣ ዛሬ አለው እግዚአብሔር ከፈቀደለት ነገ አለው። ሰው በሶስቱ የተገመደ ሲሆን ፍጻሜው ግን ነገ ነው። ወደ ትናንት የሚጎትት ነገር ብዙ ሲሆን፣ ዛሬ ላይ እንድትቀር የሚታገልም ብዙ ነው። ውጤቱ ግን ያለው ነገ ላይ ነውና እየሄድክ..እየሄድሽ።
ወደ ፊት እየሔድክ ካልሆነ በትናንት ታስረሃል ወይም ዛሬ ላይ አንቀላፍተሃል። መርሳት የሌለብህ ነገር በትናንትና ላይ ከቆየህ ሰው አይቃወምህ ዛሬም እንደ ተራ ካለህ ማንም አይቃወምህም ነገ ላይ ለመቆም ስትራመድ ግን ከትናንትህ ድካም፥ ከዛሬው ያልተሳኩ ነገሮች ትግል ይገጥምሃል። ቢሆንም ግን እየሄድክ...እየሄድሽ። ተስፋ አትቁረጥ፣ ብዙ ያታገለን ነገር ማለፉ አይቀርም። እልፍ እንበል አበው እንደሚሉት 'እልፍ ይገኛልናል።'
ጉዞአችን በእርሱ በወደደን እና በተሸከመን ነውና ህይወታችን እርሱ ነውና፥ አምላካችን ተደግፈን በእርሱ እየተመራን፥ በመንገዳችን እንሄዳለን።
“ኃይልን በሚሰጠኝ በክርስቶስ ሁሉን እችላለሁ።”
— ፊልጵስዩስ 4፥13
"እግዚአብሔር ከሚራመድ ጋር ይረመዳል፥ ከሚሮጥ ጋር ይሮጣል፥ ከሚበር ጋር ይበራል፥ ከሚሰራ ጋር ይሰራል፥ ከሚቀመጥ ጋር ግን አይቀመጥም"
ወንጌላዊ ሪንሃርድ ቦንኬ
ስለዚህ እየሄድክ..እየሄድሽ..እየሄድን..እንጂ ተቀምጠን አንገኝ።
©ዘሪሁን ግርማ
/channel/theideaofs
#ማንንም_አትግፋ_ነገን_የሚያውቅ_እግዚአብሔር_ብቻ #ነውና
በእንግሊዝ የነገስታት ታሪክ ከንግስት ኤልዛቤት በመቀጠል ስሟ ገኖ በሚታወቀው ልዕልት ዲያና ናት። ዲያና የእንግሊዝኛ ህዝብ ብቻ ሳይሆን በአለም ላይ በጣም ብዙ ተወዳጅነት ያላት ንግስት ናት። ሁለት ልጆች የወለደች ሲሆን ሁለተኛው ልጇ ሄሪ (Harry) ይባላል።
በአሜሪካ ምድር ደግሞ አንዲት ሜጋን (Meghan) የተባለች ታዋቂ የፊልም አክተር አለች። ሜጋን በእናቷ ጥቁር አሜሪካዊ ስትሆን አባቷ ነጭ ነው። ማለትም ግማሽ አፍሪካ አሜሪካዊ ናት። ሜጋን አግብታ የፈታች ስትሆን የቀድሞ ባሏ (X-Husband) "አልፈልግሽም" ብሎ ያባረራት ናት። ሜጋን በፊልም ስራ እያለች በአጋጣሚ ከንግስት ዲያና ልጅ ከፕሪንስ ሄሪ ጋር ተገናኘች። ሄሪ ወደዳት፣ አፈቀራት በእንግሊዝ የነገስታት ታሪክ ያልታየ ለዛውም ጥቁር አሜሪካዊ የሆነች፣ አግብታ የፈታች ሴት በእንግሊዝ የነገስታት ሰርግ አግብታ ቤተመንግስታቸው ገባች። ባሏ የገፋት ሴት ቤተመንግስት ገባች። ሰውን አትግፋው፣ ሰውየው መልሶ ባይገፋህም እንኳ ትክክለኛ ሰው በመግፋት ዋጋ ልትከፍል ትችላለህ።
ማንንም አንናቅ ዛሬ እኛ የተመካንበት ነገር ነገ አብሮን እንደሚቀጥል እርግጠኛ አይደለንምና፤ ማንንም አትግፋ ነገ ዛሬ የገፋነውን ሰው እግዚአብሔር ምን እንደሚያደርገው አናውቅምና። ከዚህ ሁሉ ግን ማንንም አንግፋ። ማንንም አንናቅ። ነገ የምናፍርበትን ነገር ዛሬ ማንም ላይ አናድርግ።
#ነገ_ያለው_በእግዚአብሔር_እጅ_ነውና!!
መጋቢ ዘማሪ ታምራት ሐይሌ "እግዚአብሔር አዋቂ ነው" የሚል መዝሙር አለው። እንዲህም የሚል ድንቅ መልዕክትም አለው።
እግዚአብሔር አዋቂ ነው አዋቂ ነው (፪x)
ስራችንን ይመዝናል ዋጋችንን ይተምናል
ከፋኝ ብለን አናጉረምርም ስለሁሉ እናመስግነው
ደላኝ ብለን አንታበይ እግዚአብሔር አዋቂ ነው
ቃልን ለመናገር አንደበት ቸኩሎ
ሲያነሳ ሲጥል ባልዋሉበት ውሎ
ለምን እናፍራለን በተናገርንበት
እልፍ ያደላድላል ሁሉንም ትውልድ
ሃሰት ሲሆን እውነት ያልነው
ጸድቆ ሲገኝ የኮንነው
አንተ ያልነው ሲሆን አንቱ
ለእኛ ሚቀረን ትዝብቱ
(ለትምህርታችን ተጻፈ)
/channel/theideaofs
"አቅማችሁን ለሚያሳድጋችሁ ነገር ተጠቀሙበት" በሌላ ቋንቋ "Invest your energy in something that's going to contribute to your growth"
'energy' ስል ያለን ክህሎት፣ እውቀት፣ ጊዜ፣ ገንዘብ፣ ያለንን ግንኙነቶች በአጠቃላይ በእጃችን ያለንን ሐይል እኛን ሊያሳድግ በሚችል መልኩ መጠቀም ራሱ ጥበብ ነው። ብዙ ወጣት ያሉትን አጋጣሚዎች ራሱን ለመገንባት አይጠቀምበትም ወይም ያንን ማድረግ እንዳለበት ላያስተውል ይችላል። እነዚህ ነገሮች ደግሞ ሁሌም ከእኛ የማይኖሩበት አጋጣሚዎች ከመምጣታቸው በፊት ያለንን አቅም ለዕድገታችን እንጠቀም።
የበሰሉና ከእኛ የተሻሉ ሰዎችን ስናገኝ ልናድግ የምንችልበትን እውቀት ከእነርሱ እንቅሰም። በዙሪያችን አቅም መሆን የሚችሉ ነገሮችን ለእኛ ለእድገት እንጠቀም። ጊዜያችንን ለዕድገታችን እንጠቀምበት። አቅም መሆን የሚችሉ ነገሮችን በሙሉ ለዕድገት እንጠቀምባቸው። ከሰዎች መማር የምንችልባቸው፣ ስለ ስራ አመለካከታችንን ሊለውጡ የሚችሉ ሐሳቦች ላይ ሐይላችን እናውል።
ሐይላችንን ባልተገቡና ውጤት በማያመጡ ነገሮች ላይ አናባክን። ብዙ ሐይል በእጃችን አሉ፣ ስራችን ትምህርታችን፣ ግንኙነቶቻችን፣ ጊዜያችን፣ ያለንን ገንዘብ እኛን ማሳደግ በሚችል መንገድ እንጠቀምባቸው። ሐይል አናባክን።
ዘሪሁን ግርማ
/channel/theideaofs