theideaofs | Unsorted

Telegram-канал theideaofs - የዘር ሐሳቦች/ Yezer Hasaboch

1133

እያንዳንዱ ሐሳብ ዘር ነው

Subscribe to a channel

የዘር ሐሳቦች/ Yezer Hasaboch

ከሁለቱ አይነት "ጓደኞች" እግዚአብሔር ይጠብቃችሁ!!

ሁልጊዜም ሁለት አይነት ጓደኞች በእርኝጠኝነት አጋጥመውናል፣ ወይንም አብረውን አሉ፣ ወይም እነዚያ ጓደኞች እኛው ራሳችን ልንሆን ይችላሉ። ጓደኛ ማለት ጓ-ደኛ ማለት ነው። የቤት ውስጥ አዋቂ የቅርብ ሰው ማለት ነው። ስለዚህ በዚህ ስያሜ ተቀምጠው ያሉትን ይመለከታል። ይህ ጽሑፍ በአጋጣሚ ወይም ባለመቻል እንደዚህ አይነት ነገር ላይ የማይገኙትን ሳይሆን፣ እንደዚህ አይነት ሐሳብና አኪያሄድ ያላቸውን ብቻ ይመለከታል።

፨ በደስታችን የሚኖሩ በሐዘናችን ጊዜ የሌሉ፦ እነዚህ አይነት ጓደኞች ነገሮቻችን የቀኑ በሚመስል ጊዜ ሁሉ አብረውን ናቸው። በደስታ ጊዜ፣ ባለን ጊዜ፣ በተሳካልን ጊዜ ሁሉ ከዙሪያችን የማይጠፉ የደስታ ጊዜ ብቻ ጓደኞች ናቸው። እነዚህ ነገሮቻችን ሲለወጡ ከአጠገባችን የሚጠፉ ናቸው።

፨ በሐዘናችን የሚገኙ በደስታችን ጊዜ የሌሉ፦ እነዚህኞቹ ደግሞ የተለያዩ ችግሮች ሲኖሩ አብረውን ናቸው። በተቸገርን ጊዜ አሉ ነገር ግን ሲሳካልን ነገሮች ሲቀኑልን አብረውን ደስታችንን የማይካፈሉ፣ ተቸግረን ሲያዩን አለሁ አለሁ የሚሉን ከደስታችን አብሮ ደስ የማይላቸው አይነት ጓደኞች ናቸው። ይህም ከባድ ችግር ነው።

እውነተኛ ጓደኛ ከላይ ያልኳቸውን ሁለት ነገሮች ያለፈ ነው። ጓደኛ ጓ-ደኛ፣ ቤተኛ፣ የቅርብ ሰው ማለት ነውና። እኛም እንዲህ አይነት ከሆንን ራሳችንን እንድናይ ተጻፈ።

ዘሪሁን ግርማ

/channel/theideaofs

Читать полностью…

የዘር ሐሳቦች/ Yezer Hasaboch

#የሰይጣንን_ውሸት_አትመኑ!

የእግዚአብሔርን እውነት እንዳናምን ሁልጊዜም በሰይጣን የተደራጀና የተዘጋጀ ውሽት አለ። እግዚአብሔር በቃሉ ውስጥ ከገለጠው እውነት በላይ እውነት የለም፣ ከክርስቶስ በላይም እውነት የለም። ሰይጣን ሁልጊዜም በእግዚአብሔር እውነት ላይ ይዋሻል ማለትም እግዚአብሔር በተናገረው ተቃራኒ ሌላ ውሸት ያደራጃል።

በህይወታችን ውስጥ እግዚአብሔር በቃሉና በመንፈሱ ከተናገረን በላይ እውነት የለም። እግዚአብሔር ብሎ ውሸት የለም፣ ሰይጣን ብሎ እውነት የለም። ሐዋሪያው ጳውሎስ፦

“ነገር ግን እባብ ሔዋንን በተንኰል እንዳሳታት ምናልባት የእናንተም ልቡና ተበላሽቶ ለክርስቶስ ካላችሁ ቅንነትና ንጽሕና እንዳትወሰዱ እሠጋለሁ።”
— 2ኛ ቆሮንቶስ 11፥3 (አዲሱ መ.ት)

ይለናል። ሔዋን የሆነችው እግዚአብሔር በነገራት እውነት ተቃራኒ በሰይጣይ የተዘጋጀ የውሽት ወጥመድ ውስጥ ገባች። ሪክ ጆይነር የተባለ ጸሐፊ "እውነተኛ ሶስት ብር ከሌለ፣ የሐሰት ሶስት ብርም አይኖርም።" ይላል።

ሰይጣን በእግዚአብሔር እውነት ምትክ ነው ውሸትን የሚተካው (replace)። ለዚህ ነው ብዙ ክርስቲያኖች በሰይጣን እግዚአብሔርን የመጠራጠር ወጥመድ ውስጥ የሚገቡት። የእግዚአብሔር እውነት ባለበት ቦታ ሁሉ ላይ የሰይጣን የውሸት እንቅስቃሴዎች አሉ። በዚህ ዘመን ደግሞ ብዙ ክርስቲያኖች እግዚአብሔር በቃሉ ከተናገራቸው እውነት ይልቅ፣ የሰይጣን ውሸት ጥቃት ውስጥ ይገባሉ።

ማንኛውም ሰው ከእግዚአብሔር ቃል ሲፋታ፣ ከሌላ ነገር ይጋባል። ከእግዚአብሔር እውነት በራቅን ቁጥር ለሰይጣን ውሸት ተጋላጮች እንሆናለን። እግዚአብሔር ሲናገረን እርሱ በራሱ ጊዜ ስለሚሰራ፣ ሰይጣን እግዚአብሔር በተናገረን ቃል ላይ ስለሚዘራቸው የአይፈጸምም የውሽት ዘሮች እንዳንጋለጥ መጠንቀቅና መንቃት አለብን።

ነገሮቻችን የዘገዩ ሲመስለን፣ እግዚአብሔር የተናገረን ቃልን እንድንጠራጠር ካደረገን በቀጣዩ ለሰይጣን ውሸት እንጋጣለን። የሰይጣን ውሸትን ስናምን፣ የእግዚአብሔር እውነት ይሸፈንብናል፣ ለሰይጣን ጥቃት ተጋላጮች እንሆናለን። ሰይጣን የውሸት አባት ስለሆነ ምንም መልካም በመሰሉ ቢቀርበን ውሸቱን ነው።

ይህን ጽሑፍ እንድጽፍ (Inspire ) ያነሳሳኝ በዋረን ዌርዝቢ ተጽፎ በጳውሎስ ፈቃዱ የተተረጎመው "ሰይጣናዊ ስልቶች" የተሰኘው መጽሐፍ ነው። ይህን መጽሐፍ ብታነቡ በእርግጥ ትጠቀማላችሁ። ከዚህ መጽሐፍ አንድ ሐሳብ ልውሰድ፦

"ሰይጣን ውሸትን እንድታምኑ ካደረጋችሁ በህይወትታችሁ መሥራት ይጀምርና ወደ ኅጢአት ይመራችኋል።" ገጽ 9

ሰይጣን አንድ ነገር እንድናምን ከታገለን መንገዱ ምንም ይሁን ምን መጨረሻው ጥፋት ነው። የእግዚአብሔር እውነት ወደ ህይወታችን ሲመጣ የሰይጣን ውሸት አብሮ ይንቀሳቀሳል።
እግዚአብሔር ወደ አዳም መጥቶ ትዕዛዝ ከመስጠቱ በፊትም ሰይጣን ነበር ወደ ህይወታቸው ግን የመጣው እግዚአብሔር ትዕዛዝን ከሰጠ በኃላ ነው።

የእግዚአብሔር እውነት ላይ ሰይጣን ሁልጊዜ ይዋሻል። ጸንታችሁ ስትቆሙ ብቻ ተሸንፎ ይሄዳል። የሰይጣን ድምጽ ሁልጊዜም መልካም፣ ከእግዚአብሔር ሐሳብ ይልቅ የተሻለና ዐሳቢ መስሎ ወደ ህይወታችን ይመጣል። እግዚአብሔር ወደ ህይወታችን እንዳይመጡ ያስቀራቸውን ነገሮች እግዚአብሔር እኛን ለመበደል አድርጎ እንዳዘገየ ሊያሳምነን ይመጣል። በኢየሱስም ላይ ይህን ሙከራ ሞክሯል። (ማቴዎስ 4:1-11)

በህይወታችሁ ከእግዚአብሔር በተማራችሁት እውነት ቁሙ፣ መንፈስ ቅዱስ በነገራችሁ ድምጽ ላይ ቁሙ፣ እግዚአብሔር የተናገረው ይፈጸማል። በእግዚአብሔር በሆነው የቃሉ እውነት ላይ ማደግ፣ ከሰይጣን የተገለጠም፣ የተሰወረም ውሸት፣ ሽንገላና ማታለል መሻገሪያ መንገድ ነው።

ሰይጣን በምክሩ እውነተኛ ሆኖ አያውቅም።
.....
ዘሪሁን ግርማ

/channel/theideaofs

Читать полностью…

የዘር ሐሳቦች/ Yezer Hasaboch

#የተበላሸ_ባህሪህ_ማንነትህን_ያሳጣሃል!!

"ገንዘብህን ካጣህ ምንም አላጣህም (ገንዘብ መልሶ የሚገኝ ነገር ነውና) ጤናህን ካጣህ የሆነ ነገር ታጣለህ፥ ባህሪህ ከተበላሸ ሁለንተናህን ታጣለህ።"

" If you lose your money you lose noting , If you lose your health you lose something, but you lose your Character you lose everything."

ይህን አባባል በቲክ ቶክ ያየሁት አንድ ቪዲዮ ላይ አንድ በዕድሜ ተለቅ ያለ ሰው ለአንድ ወጣት ሲመክረው የተናገረው ነው። በዚህ ሐሳብ እስማማለሁ ባህሪህ ከተበላሸ ሁሉ ነገርህን ታጣለህ።

ይህ የእኛ ዘመን ትውልድ በዚህን ጊዜ (ሁሉም ባይሆንም አብዛኛውን) ለባህሪ፥ ለስነ ምግባር፥ ሌሎችን ለማክበር፥ ለሚናገረው ነገር መጠንቀቅ፥ ድርጊትን መርጦ ትክክለኛውን ለማድረግ በጣም እየተቸገረ እንዳለ የምናየው ነው። ይህን ለማየት በየ ቲክቶኩ፥ በዩቱዩብና በፌስ ቡክ ላይ የምናየው ነገር በቂ ነው።

ባህሪን (Character) በጣም አስፈላጊ የሆነ ነገር ነው። የሰዎች ባህሪ ከተበላሸ ሁለንተናቸው የተበላሸ ነው። ለዚህ ነው በህይወታችን ራሳችን ላይ ባህሪያችን ላይ መስራት አለብን። ውሸት የቀለለበት፥ እውነት የረከሰበት፥ ስድብ ስጦታው የሆነ፥ ጋብቻና መልካም ጓደኝነት ስፍራ ያጣበት፥ በዘመናዊነት እሳቤ ሰውነት የረከሰበት፥ ቤተሰብን ማክበር ታላላቅችን ማክበር የቀለለበት፥ ቅንነት እንደ ሞኝነት የሚታይበት፥ ከሰውየው በላይ ከሰው ጥቅም ብቻ የሚፈለግበት፥ ሰው ሁሉ እንደ መሰለው እንደ ፈለገው የሚናገርበት፥ የሰውን ነገር መዝረፍ ህጋዊ የሆነበት (በመንፈሳዊ ስም ሆነ በምንም መንገድ)፣ የሌላቸውን እንዳላቸው አድርገው የሚዋሹ ሰዎች መብዛታቸው፥ ሌሎችንም እዚህ ጋር ብንጨምራቸው ብዙዎቹ የባህሪህ-ብልሹነት የወለዳቸው ናቸው።

የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን አሁን አየተናጠች ያለችው ህይወታቸው እንደ እግዚአብሔር ቃል ባልተሰራ እና ባህሪያቸው በክርስቶስ ባህሪይ ባልተገራ በአንዳንድ አገልጋዮችና መሪዎች ምክንያት ነው። ሰው ባህሪው የተበላሸ ከሆነ በአካሉ ውስጥ የሚያደርጋቸው ነገሮች በሙሉ ለአካሉ ብልሽትን ይፈጥራሉ። የተስተካከለ ባህሪይ እንዲኖረን መጽሐፍ ቅዱስ በቂ መመሪያ ነው። ጥሩ የማገልገል ስጦታ ቢኖረን፥ ሰዎችን የሚያስደንቅ ጸጋ ቢኖርህ፥ ምንም አይነት ተጽዕኖ ቢኖርህ ባህሪይ ብልሹ ከሆነና ራስህን ለመለወጥ ካልተዘጋጀህ እመነህ ዛሬ ባይሆን ወይ ነገ ወይም የሆነ ዘመን ላይ የሚያደናቅፍህን መሰናልክል እያስቀመጥክ ነው።

እንደ አገርና እንደ ቤተክርስቲያን የባህሪ ብልሹ ታማሚነት ያላቸውን ሰዎች እያደንን እንዲታከሙ ካላደረግን ኃላ ላይ ለብዙዎች መታመም እና የባህሪ መበላሸት ምክንያት መሆናቸው አይቀሬ ይሆናል። እንዳንረሳ ባህሪያቸው የተበላሸ ሰዎች ሁሉንተናቸው ያጡ እና የብዙዎችን ጤንነት የሚያሳጡ ይሆናሉ። ሚዲያህን እንዴት እና በምን መንገድ መጠቀም እንዳለብህ ካልተረዳህ እና በአልባሌ እና በማይጠቅም ነገር ከሞላህው ያለህን ሐላፊነት ያለ አግባቡ ከተጠቀምከው ያው በአንድም በሌላ ምክንያት ባህሪይ ተበላሽቷል። ያ ደግሞ ማንነትህን ያሳጣሃል። ብዙ ወጣቶች፣ አገልጋዮችና፣ መሪዎች እንደ እግዚአብሔር ቃል የተለወጠ፣ በክርስቶስ የተሰጠን እውነተኛ ማንነት ላይ እንዲኖረንና እንዲኖራቸው መስራት ያስፈልጋል። አንዳንድ መሪዎች ቁጣ፣ ንዴት፣ ትዕቢትና- እኔነት ሲታይባቸው፣ አንዳንዶቹ ደግሞ በተለየ መልኩ የተለያዩ ባህሪያት ይንጸባረቅባቸዋል። ራስ ላይ መስራት ባህሪን ለመቀየር ወሳኙ መንገድ ነው።

የመልካም ባህሪያት መገለጫዎች ብዙ ቢሆኑም
እነዚህ ግን ዋነኞቹ ይመስሉኛል ሌሎቹን እናንተ ጨምሩባቸው። እውነተኛነት፥ ታማኝነት፥ ሰዎችን አክባሪነት፤ በምናገረው አስዋይነት (በማንኛም መንገድ)፥ የሰዎችን ነገር አለመፈለግ፥ አገልጋይነት፥ ታላላቆችንና ቤሰቦችን የገባውን ክብር መስጠት፥ ሰላማዊነት ወ.ዘ.ተ ናቸው። ያልተገባ ባህሪን ለመለወጥና፣ የተገባውን ባህሪይ ለማሳደግ ራሳችን ላይ መስራት አለብን።

ዘሪሁን ግርማ

ቴሌግራም ቻናሌን ይቀላቀላሉ
/channel/theideaofs

Читать полностью…

የዘር ሐሳቦች/ Yezer Hasaboch

#የበታችነት_መንፈስ- #አደገኛው_በሽታ!!

ከጥቂት አመት ወዲህ እየገባኝ ከመጡ ነገሮች መሐል የበታችነት ስሜት ያለባቸው ሰዎች ያሏቸውን አደገኛ ባህሪያት አስተውያለሁ። ሁላችንም በተለያየ ምክንያት የዚህ ስሜት ተጠቂ ሆነን ልናድግ እንችላለን። በቤተሰብ መሐል ባለ አስተዳደግ፣ በሰዎች በደረሰብን ጫና፣ በመናፍስት ጥቃት እና በተለያዩ ምክንያቶች የዚህ መንፈስ ተጠቂ ልንሆን እንችላለን።

ማንኛውም ሰው፤ እንዲሁም የቤተክርስቲያን መሪ ሆነው ወይም አገልጋይ ሆነው በዚህ መንፈስ ከተያዙ ደግሞ ወዲያው ነቅተው ይህን ችግር ካልቆረጡት ለብዙ ችግር ይዳርጋቸዋል። በእኔ ምልከታ በበታችነት ስሜት የተያዙ ሰዎች በእኔ'ነት (ስለራሳችው የተጋነነ አመለካከት) ካላቸው ወይም በትዕቢት ከተያዙ ሰዎች ይለያሉ። እኔ'ነት ወይም ትዕቢት ለውድቀት የሚዳርግ ትልቅ ችግር ሲሆን የበታችነት መንፈስ መጠቃትም ሌላው ችግር ነው። የበታችነት መንፈስ ያለበት ሰው ያሉበትን አስቸጋሪ ባህሪያት በሙሉ ባላውቅም እኔ የገቡኝን በጥቂቱ ላስቀምጥ።

፨አጉል ድፍረት፦ የበታችነት መንፈስ ከባድ ችግር በውስጣችን በሚፈጠር ያለመፈለግ፤ እናቃለሁ ብሎ የመፍራት፤ እበለጣለሁ ብሎ፣ አይወዱኝም ብሎ በማሰብና በሌሎች ምክንያት ውስጥ ከሆንን ያንን በውስጣችን ያለውን ትግል ለማሸነፍ አጉል ደፋር መስሎ ለመታየት የተለያዩ እንቅስቃሴዎች ማሳየት እና ማድረግ ያጠቃልላል። ጤናማ ድፍረት ችግር ባይኖረውም በውስጣችን ያለውን የበታችነት ስሜት ለመሸፈን የምናንጸባርቀው አጉል ድፍረት ብዙ ነገራችን ይባስ ያበላሻል።

፨ አግላይ መሆን፦ ብዙ የበታችነት ስሜት የሚመጣው ከኃላ ካለፍንባቸው መንገዶቻችን ተሞክሮ ስለሆነ የበታችኝነት ስሜት ሰዎችን የማግለል ችግርን ይዞ ሊመጣ ይችላል። አብሶ በቤተክርስቲያን ስራ ውስጥ እግዚአብሔር አብረውን እንዲሰሩ በተለያዩ ምክንያት የሚሰጠንን ሰዎች በእበለጣለሁ ወይም እቀማለሁ በሚል እሳቤ ሰዎቹን የመግፋት እና የማግለል አኪያሄድ ሊኖረን ይችላል። አቅራቢና አቃፊ መሆን ትልቅ ነው። ብዙዎች በዚህ ምክንያት እግዚአብሔር የሰጠንን ሰዎች ልናጣ እንችላለን።

፨ አልችልም ማለት፨ በዚህ ስሜት የሚጠቁ ሰዎች ሌሎችን ትልቅ ራሳቸውን ትንሽ፣ ሌሎች የሚችሉ እነርሱ የማይችሉ እንደሆኑ ያስባሉ። በሁሉም ነገር በሰዎች ላይ ተንጥልጥለው መራመድ እንጂ ራስን በራስ ለማቆም እችላለሁ ብለው አያምኑም። አልችልም ብሎ ማሰብ አደጋ ነው። በእርግጥ የማንችላቸው ነገሮች የሉም ለማለት ሳይሆን አልችልም በሚል መንፈስ መያዝ ግን አንደኛው የበታቸኝነት ስሜት መገለጫ ሊሆን ይችላል።

፨አዋቂ መምሰል፨ አለማወቅ ችግር አይደለም ለማወቅ አለመፈለግ ነው ችግር። ሁልጊዜም ሰዎች የማናውቃቸው ነገሮች ይኖሩናል። በዚህ መንፈስ የተጠቁ ሰዎች ሳያውቁ እንደሚያውቁ እና ማንም ሳዬጠይቃቸው አዋቂ እንደሆኑ ሊያንጸባርቁ ይችላሉ።

፨ ያልተገቡ ድርጊቶች (Over Acting)፨ ብዙ በጉራ እና በውጫዊ ነገር ብቺ ራስን ለማሳየት የሚደረግ ድርጊት፣ ቀደም ቀደም ማለት፣ ባልተገባ ቦታ እንደሚችሉ ለማሳየት መሮጥ፤ በሆነ ነገር ይበልጠናል ብለን በምናስባቸው ሰዎች ፊት "እርሱ እንዲህ ነው" እንዲሉን የምናሳየው ያልተገባ ድርጊት እንደኛው ምክንያት የበታችነት ስሜት ነው።

ሰው ከዚህ መንፈስ በእግዚአብሔር ቃል በመንፈስ ቅዱስ እገዛ ሊፈወስ እንደሚችል አምናለሁ። በአጭሩ የበታችነት መንፈስ " ራስን በትክክለኛ መንገድ እና እውቀት አለመቀበል ነው" ለዚህ ደግሞ የእግዚአብሔር ቃል እና መጸለይ ፍቱን መድሃኒት ናቸው። ስለ ራስ ያልተጋነነ ግን ትክክለኛ አመለካካከትን እንደ እግዚአብሔር ቃል ራሳችንን ላይ እንገንባ።

“ሸለቆው ሁሉ ከፍ ይላል፥ ተራራውና ኮረብታውም ሁሉ ዝቅ ይላል፤ ጠማማውም ይቃናል፥ ስርጓጕጡም ሜዳ ይሆናል፤”
— ኢሳይያስ 40፥4

ዘሪሁን ግርማ

በድጋሚ የተለጠፈ

/channel/theideaofs

Читать полностью…

የዘር ሐሳቦች/ Yezer Hasaboch

ቀን 1 #እማማ_ባሎቴ

#ጌታ_ባሌን_ለአገልግሎት_ሲጠራው_እኔንም
#ጠርቶኛል- #ባሎቴ

ባሎቴ እግዚአብሔር ወንጌልን ከወላይታ ወደ ጎፋ አቅጣጫ እንድታደርስ እግዚአብሔር የተጠቀመባት ሴት ናት። ሚሽነሪዎች ወደ ወላይታ ከገቡ በኃላ ከአባባ ዋንዳሮ ቀጥሎ ፊደል የቆጠረች የእግዚአብሔር ሴት ናት። ባል ካገባች በኃላ ቧላ ለወንጌል ስራ ወደ ጎፋ ሲሄድ በሽፍቶች ተገደለ። አንድ ልጅ ወልደው ነበር። በዚያ ወቅት ሚሽነሪዎቹ 'አንቺ እዚህ ተቀመጪ" አሏት። እርሷም "እግዚአብሔር ባሌን ሲጠራው እኔንም ጠርቶኛል" በማለት የወንጌልን ስራ ለመስራት ተነሳች።

ባሎቴ ታላቅ የወንጌል ሴት ብቻ ሳትሆን የብዙዎች እናት ናት። በ1940 ዎቹ ወንጌልን ምንም በማታውቀው ሐገር ለብቻዋ ለማስተማር የቆረጠች ታላቅ ሴት ናት። ባሎቲ በጎፋ አካባቢ ወንጌልን ለማስፋፋት የተጠቀመችባቸው መንገዶች አንዱ እናቶችንና ህፃናትን መፅሐፍ ቅዱስ በማስተማር ብዙ ጊዜዋን ታሳልፍ ነበር። እናቶች ስራ እንዲሰሩ ልጆቹን ቅድሚያ ካስተማረች በኃላ በከሰአቱ ደግሞ እናቶቹን ወንጌልን፣ መፃፍና ማንበብን ታስጠናቸው ነበር። ይህ አኪያሄድ ለብዙዎቹ በወንጌል መወረስ ምክንያት ሆነ ጌታም ብዙ መወደድና ብዙ ነፍሳትን ሰጣት።

ባሎቴ ሌሎች ወንጌላውያን ሲተኳት በጎፋ አካባቢ እየዞረች እናቶችን ልጃገረዶችን በማስተማር ስራ ተያዘች። በዚያን ጊዜ ልጅዋ ደሲታን የአካባቢው እናቶች ይንከባከቡላት ነበር። ከዚያም አልፎ ብዙዎቹን ወንጌላውያንን ትረዳ ነበር። የጠረጋ መፅሐፍ ፀሐፊ ሬይሞንድ ዴቪስ "ሰዎች ወንጌል ሰምተው ጌታን በተቀበሉበት አካባቢ የሚሰሩ ወንጌላውያንና ሚስቶቻቸው ባሎቴን ሁልጊዜ ወደ እነርሱ ይጠሩአት ነበር" ይለናል። (ገፅ 146) ባሎቴ ወንጌል በሰበከችበት በጎፋ ብቻ በአሁን ሰአት (ጠይቄ እንዳገኘሁት መረጃ) 16 ቤተክርስቲያናትና በ32 ቀበሌዎች 158 አጥቢዎች አሉ። የህዝቡ ብዛት መረጃ ማግኘት ባልችልም በብዙ መቶ ሺዎች እንደሚሆን እገምታለሁ። ይህ ማለት ከጎፋ ክልል ውጪ ወንጌል ይዘው ወደ ሌላ ክፍለ ሐገራት ወንጌል ይዘው የሄዱትን ሳይጨምር ነው። ያ በራሱ ብዙ ጥናት ይፈልጋል።

"ባሎቴ በፀሎት ታማኝ እንደ ነበረች ሁሉ በገንዘብም ታማኝ ነበረች። ከምታገኘው ብር ሁሉ አስራት ታወጣለች፣ እንዲሁም ሴቾች ይሆን እንዲያደርጉ ታስምራለች" ብሏል። (የኢትዮጵያ የወንጌልን መልእክተኞች በዲክ ማክሌላን ገፅ 50 )። ባሎቲ የትውልድ እናት ናት። ብዙዎች በእርሷ አገልግሎት ወደ ጌታ መተዋል ብዙ ቤተክርስቲያናት ተተክለዋል። ለጎፋ አካባቢ የመጀመሪያ ወንጌላዊ እንደመሆኗ አሁን እዛ ያሉት ቤተክርስቲያን ቅዱሳን የእሷ ፍሬዎች ናቸው። ለወንጌል በሄደችበት ባሏን ብትነጠቅም እግዚአብሔር ግን በብዙ ትውልድ ባርኳታል።

ባሎቴ ከብዙ ስራ በኃላና በጎፋ አካባቢ ያለው ስራ ሲደላደል ወደ ሶዶ እንድመለስና ወንጌልን እንድታስምር ተደረገች። ሶዶ ቪዳን በወንጌል ስራን ታግዛት ነበር። ባሎቲ ኢትዮጵያዊ የወንጌል ጀግና ነች። በጣም ብዙ ፍሬን በመከራ ውስጥ ያፈራች የወንጌል ጀግና እናት ናት።
......
ዘሪሁን ግርማ

....
እማማ ባሎቴ በወላይታ ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን ቀደምት ከሆኑት የወንጌል መልዕክተኞች አንዷ ናቸው። ዘመናቸውን ሁሉ ለወንጌል ምሥክርነት የሰጡ ብርቱ እናት። መጽሐፍ ቅዱሳቸውን ባረጀች ኮሮጆ ውስጥ አንጠልጥለው ከብብታቸው ሥር አውርደው አያውቁም ነበር። ሳይደናቀፉ በተቀላጠፈ አማርኛ ማንበባቸውንም ተመልክቻለሁ። ዕድሜያቸው ከመቶ አልፎአል ሲያነቡ መነጽር አለመጠቀማቸውን እንደ ልዩ ጸጋ እናይ ነበር። ታላቅ የጸሎት ሴት።

ታላቅ የወንጌል አርበኛ። በአንድ ወቅት ያቀረቡትን የወላይትኛ ዝማሬ አቅርቤላችኋለሁ። ትርጉሙ “እግዚአብሔር አይተወንም አይረሳንም።” ይላል።

ቪዲዮው ከ Worknhe D. Koyra ገጽ የተገኘ

ስላገለገሉን እናመሰግናለን።

Читать полностью…

የዘር ሐሳቦች/ Yezer Hasaboch

በአንድ ወቅት ከመጋቢ (ጋሽ) በቀለ ወልደኪዳን ጋር አስፈላጊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ላወራው ተቀጣጠርን አስቀድሜም ቃለ መጠይቅ ላደርገው እንደፈለኩት ስነግረው "በደስታ" ብሎኝ በቀጠሮው ሰአት መጣ፡፡ ሁሌም ጋሽ በቄ አረማመዱ የወጣት ከመሆኑም በላይ አስተሳሰቡም ሁሌም አዲስ ነገር የሚያመነጭ ነውና ሁሌም እገረማለሁ፡፡ ከእርሱ ጋር ያደረኩትን ቆይታ አብረው ይከከታተሉ፡፡
#ዘሪሁን_ግርማ

እኔ ፦ ፓስተር በቀለ ማነው? በአጭር ራስህን ግለጽ ብትባል እንዴት ትገልጠዋለህ?

ፓስተር በቀለ ፦ አሁን በደረስኩበት ሁኔታ በነገር ሁሉ ኢየሱስን ሞዴሉ (ምሳሌው) ለማድረግ ሁልጊዜ የሚታገል ሰው አድርጌ አየዋለው፡፡

እኔ ፦ጣልቃ እየገባ' በሚለው የህይወት ታሪክ መጽሐፍህ ላይ በ75 አመቴ ላይ ወደ ጌታ እሄዳለው ብለሃል አሁን ደግሞ 74 አመት ከአንድ ወር ነው፡፡ ስለዚህ ጉዳይ ጌታ ተናግሮህ ነው? ወይስ?

ፓስተር በቀለ፦ እዛ መጽሐፌ ላይ እንደገለጽኩት ስለዚህ ጉዳይ እኔ ከራሴ አንዳንድ ጉዳይ ተነስቼ ብዙ ጊዜ ፀልያለው፡ እንደዚያ እንዲሆነልኝ፡፡ በኃላ ላይ ደግሞ ጁላይ 4 ,2010 አመተ ምህረት እ/ ር ልመናዬን የተቀበለው እንዲመስልኝ ያደረገ መልዕክት ከእ/ር ሰማሁ፡፡ ይህንን ጻፍኩ፡፡ ለዚህ የተለያዩ ምላሾች ነው ከአንባቢዎቼ ያገኘሁት፡፡ኑርልን አትሙትብን ያሉኝ አሉ፥ እንደዛ እንዳይሆን እኛም እንጸልያለን ያሉም አሉ፤ እንደዚህ ተብሎ አይፀለይም እግዚአብሔር ያደረገውን መቀበል ነው እንጂ ወስኖ መፀለይ ትክክል አይደለም ያሉም አሉ ፤ የስህተት አስተማሪ ነህ ያሉም አሉ፡፡ ለመንኩ እግዚአብሔር ያፀናልኝ ይመስለኛል እሱን ሲደርስ የምናየው ነው ፡፡

እኔ ፦ጋሽ በቄ ይህ ማለት እኮ 11ወር ነው የቀረኝ እያልክ እኮ ነው፡፡

ፓስተር በቀለ፦ እስከ ማርች ከታሰበ እንዳልከው 11 ወር ነው የሚቀረው እስከ ጁላይ የታሰበ ከሆነ ወደ 14 ወር ሊሄድ ይችላል፡፡

እኔ ፦በዕንፀት የባለፈው ወር እትም ላይ ስለ እ/ርሰው ታምራት ታረቀኝና ስለ ሌሎች ጉዳዮችም በሰፊው አውርተሃል፡፡ ከዚያ በሻገር ደግሞ ቤቴል መጽሔት አንተ ላይ ልላ ጽሑፍ አውጥቷል፡፡ስለዚህ ጉዳይ ምን ትላለህ?

ፓስተር በቀለ፦ ነቢይ ታምራትን ሆነ ሌሎቹን ጉዳዮች በሚመለከት ዕንፀት መጽሔት ላቀረበችልኝ ቃለ መጠይቅ የማምንበትን መልስ ሰጥቻለው፡፡ የዕንጸትን አንባቢዎች በሙሉ ያጠግባቸዋል ያረካቸዋል የሚል ግምት ከመጀመሪያው የለኝም፡፡ ስለዚህ ቤቴል መጽሔትም ሆነች ሌሎች ሰዎች ሆኑ እኔ ባልኩት ካልተስማሙ እኔ ምንም ችግር የለብኝም፡፡(ያንን ስላላደረጉ) ምንም ቅያሜም የለኝም፡፡

እኔ ፦ጋሽ በቄ ከቅርብ ጊዜ ወደዚህ ከወጣት አገልጋዮች ጋር ተባባሪ ሆኗል፤ እንትና እዚህ ተነሳ ሲባል እዚያ ተነሳ ሲባል ዝም ብሎ ይደግፋል፡፡ አጥርቶ አያያቸውም፤ አያበጥርም ይሉሃል ለዚህ ምላሽህ ምንድነው፡፡

ፓስተር በቀለ ፦እኔ ቢሆንልኝ አቅሜ አይፈቅድም እንጂ አቅሙ የሚፈቅድለት ሰው ብሆን፡ ከዚህም በላይ ወጣቶችን ብደግፍ ደስ ይለኛል፡፡ መጨረሻ ባወጣሁት መጽሐፌ (ሪቫይቫል ኢትዮጵያ ና የመለከት በአል) ላይ እ/ር ራሱ የወጣቶች ደጋፊ መሆኑን አስቀምጫለው፡፡ ሰይጣን ደግሞ የሰው ልጆች ጠላት በተለይም ወጣቶችን ለማጥፋት የሚያነጣጥርባቸው እንደሆነ አውቃለው ምክንያቱም ለእኔ ግለፅ ነው፡፡ በኢትዮጵያ ዕድሜያቸው ከ30 አመት በታች የሆኑ 70% በላይ ናቸው፡፡ እንደ እኔ ከ60 ዎቹ በላይ የሆኑ 5% በታች ናቸው፡፡ ስለዚህ ብዙ መበረታታት ፤ መደገፍ ፣ ብዙ አይዞአችሁ መባል ያለባቸው ወጣቶች ናቸው፡፡ለዚህ ነው፡፡

እኔ ፦ሪቫይቫል በሚለው መፅሐፍህን በአዲስ ምክ ድጋሚ በቅርቡ ታተሞአል፡፡ እኔ በግሌ በጣም የምወደው መጽሐፍ ነው፡፡ ብዙ ሰዎች ግን ጋሽ በቄ በዚህ መፅሐፍ ላይ ሪቫይቫልን ከሙሉ ወንጌል ንቅናቄ ጋር አያይዞታል ፤ ሌሎቹ ንቅናቄዎች ምንድናቸው ትላለህ?

ፓስተር በቀለ ፦ ቃሉን ለመተርጎም ሞክሬአለው ፡፡ ሪቫይቫል ማለት ቀድሞ ህይወት ለነበረው ፤ ግን ለሞተ ፥ ህይወቱ ለደከመ ፥ ለከሰመ እንደገና ነፍስ መዝራት ነው፡፡ ስለዚህ ሪቫይቫል በትርጉሙ አማኞች ለሆኑ ግን ህይወታቸው ለደከመባቸው ሰዎች እንደገና ህይወት የሚሰጥ ነው፡፡ ጌታን ለማያውቁ መቶ ሺህና በሚሊዮኖች ወደ ጌታ የሚመልስ አገልግሎት ከሆነ እሱ እዚህ ትርጉም ውስጥ አይገባም፡፡ አዲስ ገና ህይወት ያገኙ ስለሆኑ፡፡ ጠንካራ የወንጌል ስርጭት ወይም እ/ር የባረከው የሚሲዮን አገልግሎትን አከብራለው፡፡ ትርጉሙን ነው እንጂ እግዚአብሔር የሰራውን ስራ ለማናናቅ አይደለም፡፡ ለምሳሌ ፥ በ20 ዎቹ መጀመሪያ በደቡብ ኢትዮጵያ የተደረጉትን ትልቅ ስራዎች ይህ ትርጉም (ሪቫይቫል) አያቅፋቸውም፡፡ ግን ትልቅ ስራዎች ናቸው፡፡ ትርጉሙ ነው ያከራከረን እንጂ ስራውን አቃልዬ አይደለም፡፡

እኔ ፦በሚቀጥሉት አመታት የኢትዮጵያ መንፈሳዊ እንቅስቃሴ ደረጀ እንዴት እየሆነ ይሄዳል ብለህ ታስባለህ ?

ፓስተር በቀለ ፦ ኢትየጵያ ራሷ ሐገሯ፤ ቤተከርስቲያን ሁሉንም የሚያካትት ማለትም ካቶሊክ ፤ ኦርቶዶክስ ፤ ፕሮቴስታንቱን የወጣቶች ሐገር ናት ፡፡
ይህንን ትውልድ በእግዚአብሔር ቃል፥ በመንፈስ ቅዱስ ፤ ከያዝነው ካሳደግነው፤ ከኮተኮትነው ፥ አፍሪካን ፤ መካከለኛ ምስራቅን፤ አለምን በሙሉ ትደረሳለች ብዬ ነው የማምነው፡፡

እኔ ፦በኢትዮጵያ ቤ/ን ውስጥ ያሉ አባቶች ወጣቱን እንዴት ይረዱት ብለህ ትመክራለህ? ምንም አይነት የቃል መገለጥ ያምጣ፤ ምንም ያህል የጸጋ እንቅስቃሴ ይኑረው፥ ምንም አይነት አገለግሎት በላዩ ይገለጥ፦ የሐሰት አስተማሪ ነው፥ አናውቀውም እንደዚህና እንደዚያ እየተባለ ብዙ ሰልፍ ይሆናል፡፡ አባቶቻችን፥ እንደ አንተ ያሉ ቤተክርስቲያንን ለብዙ አመት የመሩ ሰዎች ወጣቱን እንዴት እንዲረዱት ትመክራለህ?

ፓስተር በቀለ፦ እኔ በወጣትነቴ ነው ወደ ጌታ የመጣሁት፡ ጌታን ሳገኝ 32 አመቴ ነበረ፡፡ ወዲያው ነው በስብከት ማገልገል የጀመርኩት፤ ብዙ ስህተት ተሳስቻለው፤ ዛሬም ከስህተት የጸዳሁ አይደለሁም፡፡ በዙሪያዬ ያሉ የቀደሙ ወንድሞና እህቶች ፥ እየመከሩኝ ፤ ስህተቴን እያሳዩኝ፤ ትክክለኛውን ነገር ራሳቸው እየሰሩ እያሳዩኝ ፥ ከእነርሱ እየተማርኩ ፥ ስህተቴን እያረምኩ ነው እዚህ የደረስኩት፡፡ ይህም ሁሉ ሆኖ ዛሬም እሳሳታለው፡፡ ስለዚህ እኔ የምለው፡ በእኔ አይነት ዕድሜ ያሉ ሰዎች ልጆቻቸውን በቤት እንዴት ነው የሚሳድጉት ? ልጆቻቸው ሳያጠፉ ቀጥታ ጎልማሳ ሆነውላቸው ያውቃሉ ? ልጆች ያጠፋሉ ፡ ሳንቲም ይሰርቃሉ ውጪ ወተው ፓስቲ ፤ ከረሜላ ይበላሉ፡ ብዙ ስህተት ይሰራሉ፡ ያኔ ወላጅ ምንድን ነው የሚያደርገው?
ከቤት አስወጥቶ ያባረዋል? ይፈነክተዋል ? ተቀጥቶ መክሮ ነው የሚያሳድገው፡፡ ቤ/ን ውስጥ እንደዚህ ነው መደረግ ያለበት፡፡ ቤተክርስቲያን ውስጥ ያሉ ልጆች ልክ አንደ ስጋ ልጆች ያጠፋሉ
ልጆቼ ናቸው የሚል ልክ ስጋ ልጆቹ እየታገሰ ፤ እደወደደ፥ እየቆጣቸው፥ ራሳቸውን እስኪያውቁ ፥ በሁለት እግራቸው እስኪቆሙ ድረስ መረዳት አለበት፡፡ እኔ እንደዚህ ነው ፤የማምነው ቢሆንልኝ እንደዚህ ያለ አባት ለመሆን ነው የምመኘው፡ ሆኛለው አልልም ፡ ግን እግዚአብሔር እንደዚህ ያለ አባቶች ነው የሚፈልገው፡፡

እኔ፦ ጋሽ በቄ ስለሰጠኽኝ ቃለ ምልልስ አመሰግናለሁ

ፌብራሪ 6 2017 የተደረገ ቃለ መጠይቅ

/channel/theideaofs

Читать полностью…

የዘር ሐሳቦች/ Yezer Hasaboch

#ህልም_ይኑርህ #ህልምህንም_እውን_አድርገው
©ዘሪሁን ግርማ

በ1957 ካሊፎርኒያ ውስጥ የሚኖር የአስር አመት ልጅ አንድ ግብ አስቀመጠ። ጂም ብራውን በአሜሪካን ፉት ቦል ጨዋታ ፈጣን በነበረበት በዚያን ጊዜ ይህ ረጅም ቀጫጫ ልጅ የእርሱን ፊርማ ማግኘት ፈለገ። ይህ ወጣት ግቡን ለማሳካት አንዳንድ እንቅፋቶችን ማሸነፍ ነበረበት።

ያደገው ጥቁሮች ብቻ በሚኖሩበት የተጨናነቀና ለኑሮ የማይመች ቦታ ነበር። በበቂ ሁኔታ ምግብ ስለማይገኝ፣ የምግብ እጠረት ጎድቶት ነበረ። እና ሪኬትስ በሚባል በሽታ ወረሃ የሆኑ ቀጫጭን እግሮቹ በብረት ተደግፈው ታስረዋል። ጨዋታውን ለማየት ቲኬት መግዣ ገንዘብ ስላልነበረው ጨዋታው አልቆ ጂም ብራውን ወደ መልበሻ ክፍል እስኪመለስ ድረስ በትዕግስት እየተጠባበቀ ነበር።

ብራውንን በጨዋነት እንዲፈርምለት ጠየቀው። ብራውን እየፈረመለት ልጁ "ሚስተር ብራውን ቤቴ ግድግዳ ላይ ፎቶህን ለጥፌዋለሁ። ሪኮርዶቹን ሁሉ የያዝከው አንተ እንደሆንክ አውቃለሁ። አንተ የእኔ አርአያ ነህ" አለው።
ብራውን ፈገግ ብሎ ሊወጣ ሲል ልጁ የሚናገረውን ገና አልጨረሰም ነበርና " ሚስተር ብራውን አንድ ቀኝ የያዝካቸውን ሪኮርዶች ሁሉ እሰብራቸዋለሁ" አለው
ብራውን በመገረም " ስምህ ማነው?" አለው።
ልጁ መለሰለት "ኦሪየንታል ጀምስ። ጓደኞቼ ኦጄ ብለው ነው የሚጠሩኝ" አለው።
(ከዚያ በኃላ ያ ትንሽ ልጅ አድጎ በአሜሪካ አልፎም በአለም አቀፍ ደረጃ የታወቀ የፉት ቦል ተጫዋት ሆነ።)

ኦጄ ሲምሰን (ትንሽ ልጅ የነበረው) በጉዳት ምክንያት የአሜሪካ ፉት ቦል የመጫወት ፍላጎቱ በአጭር ሳይቀጭ በፊት በጂም ብራውን (ልጅ ሳለ ባስፈረመው) ተይዘው ከነበሩት ሪኮርዶች ከሶስቱ በስተቀር ሁሉንም መስበር ችሎ ነበር። ህልም ማለትና ግብ ማስቀመጥ ለሰው ልጆች መነሳት ጠንካራው ሃይል ነው። ህልምን አልም! እውን እንዲህንም አድርገው።

የምኖርበት አለም ብዙ ከፍታና ዝቅታ ብዙ መቻልና አለመቻል ብዙ እውነትና ውሸት ብዙ መታመንና ክህደት ብዙ መሳካትና ውድቀት አለባት። በማንኛውም መንገድ ውስጥ ብናልፍ ራሳችንን ለተስፋ መቁረጥ ሳይሆን ለማሸነፍ ማነሳሳት አለብን። የተስፋዎች ሁሉ ምንጭ እግዚአብሔር ነውና ከእግዚአብሔር እንዲሁም ከቃሉ መማርና በጸሎትም ከመንፈስ ቅዱስ በሆነ ድምጽ መጽናትና መራመድ የሁልጊዜ ልምዳችን መሆን አለበት።
ከዛም በተጨማሪ በብዙ የማይቻሉ (Impossible) ከማይታሰቡ የህይወት ትግል ውስጥ የወጡና ያሸነፉ ሰዎችን ተሞክሮ (Examples) በመከተል ራሳችንን ለተሻለ ስራና ህይወት ማነቃቃት (Inspired) አስፈላጊ ነው። ብዙ መንገድ ላይ የቀሩና የተሸነፉ ሰዎችን ታሪክ አትከተል። ይልቅ ከማይቻል ህይወት ወተን እንደ ከዋክብት በየመንገዳቸው ያበሩ ሰዎችን ተሞክሮ (ምሳሌነት) ተከትለህ ወደ አንተ እንደ ኮከብ ወደ መሆን ና እንጂ ከአባትህ ድህነትን ተቀብለህ ድሃ ሆነህ አትሙት።

አሸናፊነትን ማመን ስነ ልቦናዊ እድገት ነው። ሰዎች ባሸነፉበት የህይወት መንገዳቸው ንጉስ ናቸው። ወድቀህ ወይም ተሳስተህ ወይም ተቀባይነት አተህ ከሆነ ተነስተህ አኪያሄድህን ቀይር እንጂ ግብህን አትቀይር። መቼም። እንዳትረሳ ከቤተሰብ ገንዘብ ሐብታም ሆነው ከተወለዱ ይልቅ በማንነታቸው (በአስተሳሰባቸው) ሐብታም የሆኑ ይበልጣሉ። ኦጄ ሲምሰን በዘመኑም እስከ አሁንም ድረስ በጣም የተከበረከ ታላቅ ተጫዋች ነው። ከድሃ ቤተስብ መወለድ አፍሪካ አሜሪዊ (ጥቁር) መሆን አላገደውም።

በኦጄ ህይወት ውስጥ የምንመለከተው ታላቅ ጥበብ ለአንድ አላማ መነቃቃቱ (Inspired) መሆኑ ያንን ህልሙን ተከትሎ እውን ማድረጉ ነው። የመጨረሻው ደግሞ ከእርሱ በፊት ታላቅ ስኬት ላይ የደረሰን ሰው ምሳሌ አድርጎ መከተሉም ነው።

/channel/theideaofs

Читать полностью…

የዘር ሐሳቦች/ Yezer Hasaboch

#የተበላሸ_ባህሪህ_ማንነትህን_ያሳጣሃል!!

"ገንዘብህን ካጣህ ምንም አላጣህም (ገንዘብ መልሶ የሚገኝ ነገር ነውና) ጤናህን ካጣህ የሆነ ነገር ታጣለህ፥ ባህሪህ ከተበላሸ ሁለንተናህን ታጣለህ።"

" If you lose your money you lose noting , If you lose your health you lose something, but you lose your Character you lose everything."

ይህን አባባል በቲክ ቶክ ያየሁት አንድ ቪዲዮ ላይ አንድ በዕድሜ ተለቅ ያለ ሰው ለአንድ ወጣት ሲመክረው ያለው አባባል ነው። በዚህ ሐሳብ እስማማለሁ ባህሪህ ከተበላሸ ሁሉ ነገርህን ታጣለህ።

ይህ የእኛ ዘመን ትውልድ በዚህን ጊዜ (ሁሉም ባይሆንም አብዛኛውን) ለባህሪ፥ ለስነ ምግባር፥ ሌሎችን ለማክበር፥ ለሚናገረው ነገር መጠንቀቅ፥ ድርጊትን መርጦ ትክክለኛውን ለማድረግ በጣም እየተቸገረ እንዳለ የምናየው ነው። ይህን ለማየት በየ ቲክቶኩ፥ በዩቱዩብና በፌስ ቡክ ላይ የምናየው ነገር በቂ ነው።

ባህሪን (Character) በጣም አስፈላጊ የሆነ ነገር ነው። የሰዎች ባህሪ ከተበላሸ ሁለንተናቸው የተበላሸ ነው። ለዚህ ነው በህይወታችን ራሳችን ላይ ባህሪያችን ላይ መስራት አለብን። ውሸት የቀለለበት፥ እውነት የረከሰበት፥ ስድብ ስጦታው የሆነ፥ ጋብቻና መልካም ጓደኝነት ስፍራ ያጣበት፥ በዘመናዊነት እሳቤ ሰውነት የረከሰበት፥ ቤተሰብን ማክበር ታላላቅችን ማክበር የቀለለበት፥ ቅንነት እንደ ሞኝነት የሚታይበት፥ ከሰውየው በላይ ከሰው ጥቅም ብቻ የሚፈለግበት፥ ሰው ሁሉ እንደ መሰለው እንደ ፈለገው የሚናገርበት፥ የሰውን ነገር መዝረፍ ህጋዊ የሆነበት (በመንፈሳዊ ስም ሆነ በምንም መንገድ)፣ የሌላቸውን እንዳላቸው አድርገው የሚዋሹ ሰዎች መብዛታቸው፥ ሌሎችንም እዚህ ጋር ብንጨምራቸው ብዙዎቹ የባህሪህ-ብልሹነት የወለዳቸው ናቸው።

የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን አሁን አየተናጠች ያለችው ህይወታቸው እንደ እግዚአብሔር ቃል ባልተሰራ እና ባህሪያቸው በክርስቶስ ባህሪይ ባልተገራ አገልጋዮች ምክንያት ነው። ሰው ባህሪው የተበላሸ ከሆነ በአካሉ ውስጥ የሚያደርጋቸው ነገሮች በሙሉ ለአካሉ ብልሽትን ይፈጥራሉ። የተስተካከለ ባህሪይ እንዲኖረን መጽሐፍ ቅዱስ በቂ መመሪያ ነው። ጥሩ የማገልገል ስጦታ ቢኖረን፥ ሰዎችን የሚያስደንቅ ጸጋ ቢኖርህ፥ ምንም አይነት ተጽዕኖ ቢኖርህ ባህሪይ ብልሹ ከሆነና ራስህን ለመለወጥ ካልተዘጋጀህ እመነህ ዛሬ ባይሆን ወይ ነገ ወይም የሆነ ዘመን ላይ የሚያደናቅፍህን መሰናልክል እያስቀመጥክ ነው።

እንደ አገርና እንደ ቤተክርስቲያን የባህሪ ብልሹ ታማሚነት ያላቸውን ሰዎች እያደንን እንዲታከሙ ካላደረግን ኃላ ላይ ለብዙዎች መታመም እና የባህሪ መበላሸት ምክንያት መሆናቸው አይቀሬ ይሆናል። እንዳንረሳ ባህሪያቸው የተበላሸ ሰዎች ሁሉንተናቸው ያጡ እና የብዙዎችን ጤንነት የሚያሳጡ ይሆናሉ። ሚዲያህን እንዴት እና በምን መንገድ መጠቀም እንዳለብህ ካልተረዳህ እና በአልባሌ እና በማይጠቅም ነገር ከሞላህው ያለህን ሐላፊነት ያለ አግባቡ ከተጠቀምከው ያው በአንድም በሌላ ምክንያት ባህሪይ ተበላሽቷል። ያ ደግሞ ማንነትህን ያሳጣሃል።

የመልካም ባህሪያት መገለጫዎች ብዙ ቢሆኑም
እነዚህ ግን ዋነኞቹ ይመስሉኛል ሌሎቹን እናንተ ጨምሩባቸው። እውነተኛነት፥ ታማኝነት፥ ሰዎችን አክባሪነት፤ በምናገረው አስዋይነት (በማንኛም መንገድ)፥ የሰዎችን ነገር አለመፈለግ፥ አገልጋይነት፥ ታላላቆችንና ቤሰቦችን የገባውን ክብር መስጠት፥ ሰላማዊነት ወ.ዘ.ተ ናቸው።

ዘሪሁን ግርማ

ቴሌግራም ቻናሌን ይቀላቀላሉ
/channel/theideaofs

Читать полностью…

የዘር ሐሳቦች/ Yezer Hasaboch

#በመዘግየት_የሚመጣ_በረከት!!

በህይወታችን አንዳንድ ነገሮች በምናውቀውም በማናውቀውም ሁኔታ ይዘገያሉ። እኛ 'ይህ ጊዜው ነው ይህ ነገር መሆን ያለበት አሁን ነው' ብለን የምንላቸው ከእኛ አለመብቃት ወይም ስንፍና ውጪ በሆነ ምክንያት ሊዘገዩ ይቻላሉ።

በተቃራኒው ጊዜን ባለመዋጀት በራሳችን ምክንያት ከተለያዩ ነገሮች መዘግየት ም አለ። የዛሬው ሐሳቤ የሚያጠነጥነው በእኛ ትጋት ማነስ ወይም ስንፍና ወይም እግዚአብሔር በሰጠን ጊዜ ባለመጠቀማችን ስለሚያጋጥመን መዘግየት አይደለም። በእርሱ በእግዚአብሔር ፈቃድ ስለሚዘገዩ ነገሮች ናቸው። በማይገባን መልኩ ወይም እግዚአብሔር ለእኛ ካሰበው ከተሻለ ነገር የተነሳ ወይም በሰአቱ ያንን ነገር ብናገኘው መሸከም ሳንችል ቀርተን እንዳጠፋን ወይም በእግዚአብሔር በራሱ ምክንያት የሚዘገዩ ነገሮች ፍጻሜያቸው መልካም ነው።

የእግዚአብሔር በረከት የሚሰራው በመፍጠን ውስጥ ብቻ ሳይሆን በመዘግየት ውስጥ ነው። ማንም የጠየቀው ነገር ወይም የሚፈልገው ነገር ሲዘገይበት ደስ የሚለው የለም። በእግዚአብሔር ፈቃድ ውስጥ የሚዘገይ ነገር ያለ እግዚአብሔር ፈቃድ ፈጥኖ ከምናገኘው 'በረከት' በብዙ የተሻለ ነው።

መዘግየት ማለት አለማግኘት ማለት ሳይሆን ነገሩን በእግዚአብሔር ጊዜ እንጂ በእኛ ጊዜ አለማግኘት ማለት ነው። በእግዚአብሔር ሐሳብና ፈቃድ ውስጥ ዘግይቶ የምንቀበለው ትክክለኛ በረከት ሁልጊዜ በተፈተነ ማንነት ላይ እንደሚቀመጥ አደራ ነው። መጽሐጽ ቅዱስ፦

“በለሱን የጠበቀ ፍሬዋን ይበላል፥ ጌታውንም የሚጠብቅ ይከብራል።”
— ምሳሌ 27፥18

የምንጠብቀው የዘገየ ነገራችን በእግዚአብሔር የላቀ ምክንያት ከሆነ የተሻለ ፍሬ አለው። ያ ማለት የሚመጣው ነገር የተትረፈረፈ ነው ማለት ብቻ ሳይሆን በመዘግየት ውስጥ ባለ ጥበቃ በተሰራ ማንነት ላይ የሚመጣው ማለት ነው። እያንዳንዱ መጠበቅ እኛም የሚሰራው ነገር አለው። ማንኛውም በረከት በረከት የሚባለው በትክክለኛ ማንነት፥ ጊዜ እና ቦታ የምንባረከው በረከት ሲሆን ነው።

ዘሪሁን ግርማ

Repost

የቴሌግራም ቻናሌን ይቀላቀሉ

/channel/theideaofs

Читать полностью…

የዘር ሐሳቦች/ Yezer Hasaboch

"#ሳያድጉ_ማደግ_ያዳግማል!
®ዘሪሁን ግርማ

እድገት የሂደት ውጤት ነው። ሳያድጉ አድጌያለሁ ማለት እድገትን አይሰጥም። በስጋ አካላዊ እድገትና በመንፈሳዊ እድገት መሐል ልዩነት አለ። ማለትም በስጋ ያለን እድገት ስለሚታይና እድሜ ስለሚቆጠር ስጋዊ እድገትን በአካላዊ አይን እናየዋለን። መንፈሳዊ እድገት ግን ከዚህ የተለየ ነው። ሰው በመንፈሳዊ ህይወቱ ለማደግ የማደግ ደረጃዎች አሉት። ፀጋን መሞላትና በተለያየ አገልግሎት ውስጥ መገኘት ማደግን አይመለክትም። የማደግ ህይወት የዕለት ዕለት ህይወት ነው። የማያቋርጥም ነው።

ሳያድግ አድጌያለሁ ብሎ የሚያስብና ለማደግ ራሱን የማያዘጋጅ ሰው፤ በህይወቱ በማደግ ብቻ የሚታለፉ ደረጃዎች ላይ ሲደርስ ተፈትኖ ይወድቃል። ህይወትን ይደግማታል። ልክ እንደ ት/ት ቤት ማለት ነው። በእውቀት ባላደክ ማጠን ክፍልን ትደግማለህ።

ህይወትን በልሳንና በመዝሙር አናሳድገውም። በቃሉ እውነት ውስጥ በመኖር እንጂ። ሌሎቹ ፀጋዎች ፍሬን የሚሰጡን በእውነተኛው የማደግ መርህ ውስጥ ስንሆን ነው። ሐዋሪያው ጳውሎስ ለጢሞቴዎስ የሰጠው ምክር እንዲህ ነው።

" ይህን እዘዝና አስተምር። በቃልና በኑሮ በፍቅርም በእምነትም በንጽሕናም ለሚያምኑቱ ምሳሌ ሁን እንጂ፥ ማንም ታናሽነትህን አይናቀው።
እስክመጣ ድረስ ለማንበብና ለመምከር ለማስተማርም ተጠንቀቅ። በትንቢት ከሽማግሌዎች እጅ መጫን ጋር የተሰጠህን፥ በአንተ ያለውን የጸጋ ስጦታ ቸል አትበል።ማደግህ በነገር ሁሉ እንዲገለጥ ይህን አስብ፥ ይህንም አዘውትር። ለራስህና ለትምህርትህ ተጠንቀቅ፥ በእነዚህም ጽና፤ ይህን ብታደርግ፥ ራስህንም የሚሰሙህንም ታድናለህና።"
1ኛ ጢሞቴዎስ 4:11-16

ማንበብ አብሶ መፅሐፍ ቅዱስን ማንበብ ለክርስቲያን ሁሉ የክርስትና እድገታችን መጀመሪያ አይመስለንም። ብዙ አገልጋዮች በስም ብቻ አገልጋይ የሚኮን ስለሚመስላቸው ነው 'መሰለኝ' ከቃሉ ጋር ብዙ ህብረት የላቸውም። ታዲያ ከቅዱሳኑ ምን እንጠብቃለን? ፀሐፊ ጳውሎስ ፈቃዱ "የብርሃን አንጓዎች መፅሐፉ ላይ ""የተገኘውን" እንሰብካለን" በሚለው ክፍል ላይ ወሳኝ ጥያቄ ይጠይቀናል። "የምናመልከው የመፅሐፍ ቅዱሱን እግዚአብሔር ነው። እግዚአብሔርን ያወቅነውና የተከተልነው መፅሐፍ ቅዱስ ነግሮን ነው። ታዲያ መፅሐፍ ቅዱሳችንን ከተውነው የትኛውን እግዚአብሔር እንከተላለን? መፅሐፍ ቅዱሳችንን ፊት ከነሳነው ( ከተውነው) ህይወታችን ወዴት ያመራል?" ገፅ 166

እድገታች ከቃሉ ጋር ካለን ህብረት ይጀምራል። ቃሉ ነው ምን ማድረግ እንዳለብን የሚነግረን! ማንና ምን እንደሆንን የሚያሳየን! የትና ወዴት መጓዝ እንዳለብን የሚያስተምረን! ማደግ የምንናገረው ሳይሆን የሚታይና ፍሬ ያለው ነው። መፅሐፍ ቅዱስን ካልተማርን የማደግ ህይወት ውስጥ አንገባም። በአካሉ መሐል የፀጋ ስጦታዎች በጣም ወሳኝ ቢሆኑም እነርሱ በራሳቸው እድገት ሳይሆኑ፤ በእውነተኛው መርህ በቃሉ ውስጥ በማደግ ፍሬን የሚሰጡ በረከቶቻችን ናቸው። ለአካሉ እድገት አስፈላጊ ቢሆኑም፣ እነርሱ ስላሉን ብቻ ግን አድገናል ማለት አይደለም። ቃሉን በማንበብ በመጀመር የእድገትን መንገድን እንጀምር።

ሆድን በጎመን ቢሸውዱት ጉልበት የሚፈተነው በተራራ ላይ ነውና። የእድታችን መንገድ የህይወታችንን ጎዳናና ፍፃሜ ይወስነዋል። ህይወታችንን በቃሉ አጥንት እንገንባው፤ ጉልበታችን ያን ጊዜ በተራራዎች ላይ አሸናፊ ይሆናል። እድገት ደግሞ በአንድ ቀን የሚገለጥ ሳይሆን በሂደት የምንሆነው ነው።

በእግዚአብሔር መንግስት ውስጥ ሳያድጉ ማደግ ያዳግማልና፤ በቃሉና በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት በማደግ ወደ ሙላት እንጂ፤ ከድግግሽ እንወጣ። በክርስትና እድገት ውስጥ በአቋራጭ ማደግ ወይም ደብል መምታት የለም። #ሳያድጉ_ማደግ #ያዳግማል።

የቴሌግራም ቻናሌን ይቀላቀላሉ

/channel/theideaofs

Читать полностью…

የዘር ሐሳቦች/ Yezer Hasaboch

#ፍርሃት_የተሸነፈ_ተዋጊ

ፍርሃት ያልተዋጋው ማን አለ? ወይስ የማይታገለው ማን አለ? ኢየሱስን ታግሏል፥ ጳውሎስን ታግላል ፤ መጥምቁ ዮሐንስን አሸንፏል።

የተለያዩ አይነት ፍርሃቶች ወደ ህይወታችን ሁሌም ይመጣሉ። የማጣት ፍርሃት ፣ የመታመም ፍርሃት፣ በአገልግሎት አካባቢ ያለ ፍርሃት፣ የእወድቃለው ፍርሃት እረ ስንቱን መጥራት ይቻላል። አብሶ እኛ ባለንበት በዚህ ዘመን የፍርሃት ምንጮች ብዙ ናቸው። በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ " አትፍራ" የሚል ቃል ከ360 ጊዜ በላይ እንደተጻፈ ይነገራል። ፍርሃት በራሱ ማነው?

ፍርሃት የአጋንንት በር ነው

ሁልጊዜም የምንፈራባቸው ነገሮች በሐሳባችን አማካኝነት ሁለንተናችንን ይቆጣጠራሉ። በመጀመሪያ ደረጃ የመፍራትና የአለመፍራት ጦርነት ሐሳባችን ላይ ውጊያ ካደረገ በኃላ ነው ሐሳባችንን ካሸነፈ ሁለንተናችንን የሚቆጣጠረው። ፍርሃት በገሃድ አለም የተገለጠ አካል ሳይሆን በበአህምሮአችን ውስጥ ተጸንሶ የሚወለድ የእኛ እይታ ውጤት ነው። ሰው አህምሮው በፍርሃት ሐሳብ ካልተሸነፈ ሁለንተናውን የፍርሃት መንፈስ አይዘውም። ብዙ አይነት የፍርሃት መንፈስ አሉ ፤ ለምሳሌ፦ ያለማግባት ፍርሃት፣ የአይሳካልኝም ፍርሃት! የሁሉ ፍርሃት ምንጭ አመለካከታችን ሲሆን የአመለካታችን ምንጭ ደግሞ የፍርሃት መንፈስ ነው። በፍርሃት መንፈስ አስተሳሰባቸው የተጠቃ ሰዎች ጋር አምስት ደቂቃ ስትቀመጥ ፍርሃት ምን ያህል ፍርሃት አስተሳሰባቸውን እንደተቆጣጠረ ማየት ትችላለህ።

ያልተሸነፈ ፍርሃት የለም

እኔም እፈራለው፤ ፈርቼም አውቃለው መንፈስ ቅዱስ ይህን ነገር ካስረደኝ በኃላ ግን ህይወቴን ተለውጧል። እምነት ፍርሃትን የምናስወግድበት ትልቁ መንገድ ሲሆን፤ እምነት በራሱ የሚያድግ ነገር ነው። ባዶ አህምሮ ፍርሃት ካገኘ ሁልጊዜም መቆጣጠሩ አይቀርም። ባዶ አህምሮ ውስጥ ደግሞ እምነት የለም። በሮሜ 10:17 ላይ" እምነት ከመስማት ነው መስማትም በእግዚአብሔር ቃል ነው" ይለናል።

የእግዚአብሔር ቃል ህይወት በሙላት ከሌለን እምነት ውስጣችን አይገነባሞ እምነት ካልተገነባ ደግሞ ፍርሃትን ማሸነፍ አንችልም። እምነት ማለት እኮ የተለያዩ ነገሮች በውስጣችን ለሚፈጥሩት ድምጾች እንደ እግዚአብሔር ቃል ምላሽ መስጠት ማለት ነው።

በእምነት ስትመላለስ ሰይጣን በአንተ ህይወት ላይ ርስት የለውም። በእግዚአብሔር ቃል አስተሳሰብ ውስጥ ስትኖር በኢየሱስ ያልተሸነፈ ነገር እንደሌለ ትረዳለህ። በቃሉ አስተሳሰብ ራስህን ስትገነባ የአሸናፊነት ህይወት ውስጥ ትገባለህ።

" የማይጸልዩ ክርስቲያኖች"

የፍርሃት መንፈስ ከሚዋጋቸው ሰዎች የማይጸልዩ ክርስቲያኖችን ነው። ፍርሃት ሐሳብ ሆኖ ወደ ህይወታቸው ሲመጣ እንዲ ተብሎ ተፅፏል በማለት ገስጸው የማያበሩ ክርስቲያኖች ሁሌ ይዋጋል። ብዙ ክርስቲያኖች ፍርሃትን ከመቃወምና ረግጦ ከመኖር ይልቅ እየፈሩ የማይፈሩ መስለው ይኖራሉ። ስንፀልይ እግዚአብሔር ከእኛ በላቀ የሆኑ ነገሮችን ይቆጣ ራል። በሁሉ ነገር በራሳችን ስለማንበረታ ስንፀልይ ጸጋ ይበዛልናል፣ ስንፀልይ እግዚአብሔር ከእኛ በላይ ለሆኑ ጉዳዮች ሐላፊነት ይወስዳል። ስንፀልይ ከትግል ህይወት እንወጣለን። ፍርሃት ፍርሃት የሚሆነው ስንፈራው ብቻ ነው ስንረግጠው ግን ከጉንዳን ያነሰ ነው ፤ ፍርሃት ከወረሰን ደግሞ አየሩ ሳር ቅጠሉ ሰውነታችን ሁሉ የፍርሃት ድምጾች ይመስሉናል። በእግዚአብሔር ቃል (በእምነት) በጸሎት በእግዚአብሔር በመደገፍ ፍርሃትን ማሸነፍ እንችላለን።

ዘሪሁን ግርማ

/channel/theideaofs

Читать полностью…

የዘር ሐሳቦች/ Yezer Hasaboch

ካመለጡህ ሶስት ነገሮች መመለስ የማትችላቸው ነገሮች፦

ጊዜ (Time)
ንግግሮችን (Words)
ዕድል ወይም አጋጣሚዎች (Opportunity)

፨ጊዜህን በአግባብ ተጠቀምበት (ጊዜ ተመልሶ የማይገኝ ዕንቁ ነው)
፨ ንግግርህን አስበህ ተናገር (የአፍ ወለሞታ በቅቤ አይታሽምና)
፨ የተሰጡህን አጋጣሚዎች በአግባቡ ተጠቀምባቸው

(የጠቢባን ምክር)

/channel/theideaofs

Читать полностью…

የዘር ሐሳቦች/ Yezer Hasaboch

#የፌሚኒዝም_መርዞች!!

"ሴት በማንነቷና በቦታዋ ውብ ናት።"

ሴቶችን በተጋነኑና፣ ያልሆኑትን በመንገር የሚገነባ እውነት የለም። ይህ ዘመን እጅግ በጣም ወጣትና ታዳጊ የሆኑ ሴቶች ላይ ክፉ ዘርን እየዘራ ያለውን የፌሚኒዝም ክፉ ዘር መንቀልና በምትኩ ትክክለኛን ዘር መዝራት አለብን።

ሴት ልጆችን እንደ ሳሎን ዕቃ ብቻ የሚያስቡ ወንዶች እንዳሉ ሁሉ፣ ሴቶችን ከሁሉም በላይ እንደሆነች የሚያስቡ ሴቶችም ቀላል አይደሉም። ሴቶች በተፈጥሮአቸው የሚሞሉትን ክፍተት አለ የተፈጠሩበት አላማም አለ። ክፍተት የሚሞሉትን ክፍተት አለ ማለት በእነርሱ ህይወት ደግሞ በወንድ የሚሞላ ሌላ ክፍተት አላቸው።

ሴቶችን ከማንነታቸው በላይ እንደሆኑ ማሰብና ያለቦታቸው በማስቀመጥ የሚፈጠር ከበሬታ እና መውደድ የለም። ወደ ልቅነት የሚያመራ ህይወት እንጂ። የሴት የበላይነት የሚባል ነገር የለም የሴት የበታችነት የሚባል ነገር የለም።

የግንኙነታቸው መሰረት ገንዘብ 'ብቻ' ያደረጉ ሴቶች ራሳቸውን ለሽያጭ እንደቀረቡ ዕቃዎች አድርገው ማየት አለባቸው። ሴት ልጅ በወንድ ህይወት ውስጥ እንደ "ንግስት" የምትሆነው ወንዱ "ንጉስ" ከሆነ ብቻ ነው።

ፌሚኒስት ሴቶች፦

፨ ያለ ወንድ (ባል) መኖር እንደሚችሉ ያስባሉ
፨ ያለ አባት ልጅ ማሳደግ እንደሚችሉ ያስባሉ
፨ ገንዘብ ካላቸው ነጻና የበላይ እንደሆኑ ያስባሉ ( እያንዳንዱ ነጻነት ራሱን የቻለ ሐላፊነት አለው)
፨ በገንዘባቸው ሁሉን ማድረግ እንደሚችሉ ያስባሉ
፨ ለትዳር ዋጋ መክፈል አይፈልጉም
፨ ወንድን ይንቃሉ፣ ባሎቻቸውን ማክበር ያቆማሉ፣
፨ ከሁሉም ነገር በላይ ተፈጥሮንና የመጽሐፍ ቅዱስ መመሪያዎችን ይጥሳሉ።

ሴቶች ላይ የሚደርስን ማንኛውም ጥቃቶችን መቃወም የሴቶች ብቻ ሳይሆን የወንዶች ሐላፊነት ጭምር ነው። ያ ማለት ትክክል ያልሆኑ ነገሮችን ለመቃወም የባሰ ትክክል ያልሆነ ነገር መፍጠር ማለት ደግሞ የስህተት በር መክፈት ነው። ፌሚኒዝም በትውልዳችን መሐል እየተረጨ ያለ መርዝ ነው። ትዳር ጠል የሆነ ትውልድ እየፈጠርን፣ ተፈጥሮን የሚቃወም ስርአት እየገነባን እንድንሄድ የሚያደርግ የክፋት በር ነው። ልንቃወመው የሚገባ አመጻ ነው።

ይቀጥላል..

ዘሪሁን ግርማ

/channel/theideaofs

Читать полностью…

የዘር ሐሳቦች/ Yezer Hasaboch

#በራስ_ነገር_ላይ_ማተኮር!!

ህይወታችን የእኛ ብቻና ስለ እኛ ብቻ ባትሆንም፣ ህይወታችንን የመምራት የመጀመሪያው ሐላፊነት ግን የእኛ ነው። በራስ ላይ ለማተኮር የራስን ነገር አስቀድሞ ማወቅ አስፈላጊና ዋና ነገር ሲሆን፣ ያንን ስናውቅ በራሳችን ነገሮች ላይ ማተኮር እንጀምራለን። ህይወታችንን ውጤታማ ለማድረግ ደግሞ የምናተኩርበት የእኛ የሆነ የአትኩሮት አቅጣጫ ሊኖረን ይገባል። የምናተኩርበት የራሳችን ነገር ከሌለን በሌላ ጉዳይና በማይመለከተን ላይ እያተኮርን ነው ማለት ነው።

እንደምታውቁት አዲስ አመት ሲመጣ በጣም ብዙ ሰው ብዙ እቅድ ያወጣል፣ ያወጣውን ዕቅድ እዳንኖር ከሚያደርገን ነገር አንዱ በራስ ጉዳይ አለማተኮር ነው። የራስ ባልሆነ ነገር ላይ ማተኮር፣ የራስህን እንዳትሰራ ያደርግሃል።

በማያገባው የሚገባና በማያድግበት ወይም በማያፈራበት መንገድ የሚጓዙ፣ በሰዎች ጉዳይ ገብቶ የሚፈተፍትና ስለ ሰዎች ብቻ እያወራ የሚኖር ሰው የራሱ የሚያተኩርበት ነገር የለውም። ስለዚህም በራሳችን ነገር ላይ እናተኮር። ይህ አመት በራሳችን ነገር ላይ እያተኮርን፣ ለሌሎችም የምንተርፍበት አመት ይሁንልን።

ዘሪሁን ግርማ

/channel/theideaofs

Читать полностью…

የዘር ሐሳቦች/ Yezer Hasaboch

#ከምርጫዬ_በላይ_መረጠልኝ

የማውቅ መስሎኝ ስለራሴ
  መንገዴን ቀይሼ ፈልጌ ጨርሼ
በፍቅር ተይዛ ተጠላልፋ ነፍሴ
መረጥኩትና ጉዞ ጀመርኩ
ሮጥኩ ታገልኩ የራሴ አደረኩ
   ምርጫዬ ትክክል እንዳልነበር አይቶ
ነገ እንደሚውጠኝ አስተውሎ
"ወዳጄ" ከእኔ ላይ ምርጫዬን አስጣለኝ
በጊዜው ቢከፋኝ ቢያመኝ
  ቆይቼ ያረገልኝን አስተዋልኩኝ
የእኔ ምርጫ መጥፊያዬ
የእርሱ ምርጫ መዳኛዬ ሆነልኝ
ከምርጫዬ በላይ እርሱ መረጠልኝ
ምርጫዬን አስጥሎ በምርጫው አዳነኝ!!
ተጠነቀቀልኝ!

     (ተጻፈ በዘሪሁን ግርማ)

/channel/theideaofs

Читать полностью…

የዘር ሐሳቦች/ Yezer Hasaboch

#ጥሪ_አንዱ_ከአንዱ_አይበላለጥም!!

ባልተሰጠው ነገር የሚለፋ፣ በማያፈራበት መንገድ የሚታገል እርሱ ባልጠራበት ቦታ ሐይሉን የሚጨርስ ነው። ማወቅ ያለብን እግዚአብሔር ከጠራን በዚያው በጠራን ጥሪና ስፍራ ጥሪውን የምናስፈጽምበትን ጸጋ፣ ቅባትና መረዳት እንዲሁም የተከፈተ በርን ይሰጠናል። ያልተሰጠንን ለመሆን መፈለግ ደግሞ ያለ ጸጋው እና ያለ እግዚአብሔር አብሮነት መታገል ነው። ሰዎች በተሰጣቸውና በተጠሩበት የጥሪ ስፍራ በታማኝነት ማገልገል አለባቸው።

በአንዳንድ አገልጋዮች ዘንድ አገልግሎትን የበላይ ነው ብለን በሚያስቧቸው የአገልግሎት ቢሮዎች የመጠራት ግብ ግብ እናያለን። ይህም ደግሞ ጥሪውን ያልተከተለ ሹመት፣ ጥሪን ያላማከለ አገልግሎት ለመብዛቱ ምክንያት ነው። የተጠራንበት ጥሪ ምንም አይነት ይሁን ምን አክሊላችን ያለው እዚያ ጋር ነው። ሰው ከተጠራበትና ከተሾመበት የአገልግሎት ውጪ ምንም ፍሬ አይኖረውም።

ወንጌላዊነትን በመተው መጋቢ መባል፣ መጋቢነትን በመተው ነብይ መባል ከዚያም ሐዋሪያ ለመባል ወይም ባልተሰጠን የአገልግሎት ቢሮ ለመሾም የሚደረግ ሩጫ ውጤት አልባ ነው። ይህ አይነት ሰው ባልተቀጠረበት መስሪያ ቤት ደመወዝ የሚጠብቅ አይነት ሰው ነው። በሰማይ ዋጋህ የሚመዘገበው በምድርም የምታፈራው የተሰጠህን ቦታ ላይ ስትሰራ ብቻ ነው። ያልሆኑት በመባልና በማለት ራሳቸውን የሚጠሩና ነን የሚሉ ብዙ አይቆዩም አገልግሎታቸውም አይፀናም።

ለቤተ ክርስቲያን ሁሉም ቢሮዎች እኩል አስፈላጊ ናቸው። ሁሉም ቢሮዎች በአንዱ ቢሮ ቢጠቀለሉ ኖሮ አምስቱን ቢሮዎች መጽሐፍ ቅዱስ አይጠቅስልንም ነበር። ማንም ወንጌላዊ ሆኖ የተጠራ ወንጌላዊ የሚመዘነው በሰራው ስራና ባፈራው ፍሬ እንጂ ከሐዋርያው ጋር ተወዳድሮ ወይም በዚያ ተመዝኖ አይደለም።

አምስቱ ቢሮዎች ሐዋሪያ፤ ነቢይ፣ ወንጌላዊ መጋቢና አስተማሪ ለመንግስቱ ስራ በቅዱሳን መካከል የክርስቶስን መልክ ለመግለፅና የቤተክርስቲያንን ሙላት ለማምጣት የተሰጡ እንጂ አንዱ ከአንዱ የሚበላለጡ ወይም የምንሞካሽባቸው አይደሉም። በአህምሮአችን ሐዋሪያ መሆን ወንጌላዊ ወይም መጋቢ ከመሆን ይበልጣል ብለን የምናስብ ከሆነ ሐሳባችን የሳተ ነው። አገልጋይ ስንሆን መጋቢ ተባልክ ሐዋሪያ ዋናው መባልህ ሳይሆን በተጠራህበት ጥሪ አንፃር ሐላፊነት አለብህ ማለት ነው። እግዚአብሔር በእነዚህ ቢሮዎች ከሆንክም የሆንከው ለስራ ነው።

"እርሱም አንዳንዶቹ ሐዋርያት፥ ሌሎቹም ነቢያት፥ ሌሎቹም ወንጌልን ሰባኪዎች፥ ሌሎቹም እረኞችና አስተማሪዎች እንዲሆኑ ሰጠ፤ ሁላችን የእግዚአብሔርን ልጅ በማመንና በማወቅ ወደሚገኝ አንድነት፥ ሙሉ ሰውም ወደ መሆን፥ የክርስቶስም ሙላቱ ወደሚሆን ወደ ሙላቱ ልክ እስክንደርስ ድረስ፥ ቅዱሳን አገልግሎትን ለመሥራትና ለክርስቶስ አካል ሕንጻ ፍጹማን ይሆኑ ዘንድ።"
ኤፌሶን 4፡11-13


#ሹመት_ጥሪ_እንጂ_ፍላጎት_አይደለም

የሚሰጠን አገልግሎት እግዚአብሔር ፈልጎን መርጦ የሚሰጠን እንጂ እኛ ይህን የአገልግሎት ሹመት እፈልጋለሁ ይህን አልፈልግም ብለን የምለጥፈው ማዕረግ አይደለም። ሐዋሪያ ወይም ነቢይ ተብለን የማናፈራ ከሆነና ለመንግስቱ የማንሰራ ከሆነ ቦታችንን ፈልገን ማግኘት አለብን። በሁሉም የአገልግሎት ቦታ ያለ ጥሪያችን ካለን ስፍራችንን መፈለግ አለብን። በተጠራንበት ከሆንን ማፍራታችን አይቀርም። ቤተ ክርስቲያን በድቁና አገልግል በማስተማር፣ በማጽዳት አገልግል ወይም በመዘመር ያ ስፍራህ ከሆነ ታፈራለህ፤ እግዚአብሔርም አብሮህ ይሰራል።
የአገልግሎት አብሮ ሰራተኛው እግዚአብሔር ነው በጠራህ ቦታ ስትሆን እርሱ አብሮ ይሰራል። ባላስቀመጠህ ስፍራ ስትሆን ለብቻህ ትሰራለህ።

ሁሉም አገልግሎት የሚመዘነው በፍሬው ነውና። ትክክለኛው ነገር መንፈስ ቅዱስ እኛን ለስራው የሚመርጠን እንጂ እኛ ለማርኬት ብለን ያልሆነውን ለመሆን የምፈበርከው አይደለም።

ብንጠራም ለስራ ነው። የተለየ አላማ የለውም። እርሱን ለማገልገል መጠራት በራሱ ዕድል ነው፣ በረከት ነው። የአገልግሎት ጥሪው ምንም ይሁን ምን።

አገልግሎት ለመበላለጥ አይደለም። እንደ ቃሉ ከተመላለስን በእግዚአብሔር መንግስት ስራ ውስጥ መበላለጥ የሚባል ነገር የለም ሁሉም የሚጠየቀው በተሰጠው መጠን ነው። እግዚአብሔር የሚመዝነን እንድንሰራ በሰጠን መጠን ነው። የተሰጠን ጥሪው ምንም ይሁን ምን መጥራቱን የሚያደርገው መንፈስ ቅዱስ ነው እንጂ፣ ጥሪያችንን ይህን ነው የምፈልገው ብለን ከሱቅ መርጠን የምንገዛው አይነት ዕቃ በእኛ ምርጫ አይደለም።

“ይህን ሁሉ ግን ያ አንዱ መንፈስ እንደሚፈቅድ ለእያንዳንዱ ለብቻው እያካፈለ ያደርጋል።”
1ኛ ቆሮንቶስ 12፥11

ጸጋና ትህትና ይብዛልን!!
.......

ዘሪሁን ግርማ

/channel/theideaofs

Читать полностью…

የዘር ሐሳቦች/ Yezer Hasaboch

#ይራራልናል_ያስብልናል!!
(ለሚያስፈልገው አንድ ሰው የተጻፈ መልዕክት)

እግዚአብሔር የመጽናናት አምላክ ነው፣ ያጽናናል። እግዚአብሔር ለህዝቡ ይራራል፣ የሰዎችን ህመም ይረዳል፣ ሰዎችን በድካማቸው ያግዛል፣ የወደቁትን ያነሳል፣ ተስፋ የቆረጡትን ተስፋ ያድሳል። እርሱ በእውነት ይራራል። ሁላችን የእርሱ ቸርነትና ምህረት ጥገኞች ነን፣ የእርሱ ርህራሄ ውጤቶች ነው። ቁስላችን ያመዋል፣ ህመማችን ይገባዋል። መጽሐፍ ቅዱሳችን፦

“እርሱ ራሱ ተፈትኖ መከራን ስለ ተቀበለ የሚፈተኑትን ሊረዳቸው ይችላልና።”
— ዕብራውያን 2፥18

በመከራ ውስጥ እየተፈተኑ ላሉት ይራራል፣ በድካም ላሉት ይራራል፣ በሐዘን ላሉት ይራራል፣ ተስፋ ላጡ ይራራል፣ በውድቀት ላሉት ይራራል። ዛሬ በምን ህይወት ውስጥ ነው ያላችሁት፣ ምንስ አስጨንቋችኃል? በምን ጥያቄ ተይዛችሁ፣ ምንስ አስፈርቷችኃል? ምን አጥታችሁ በምን ተቸግራችኃል? በምን መንገድ ሄዳችሁ ምን አልተሳካላችሁም? በምን ህመም ውስጥ ሆናችሁ በምን ፈውስ አስፈልጓችኃል? ምን አስባችሁ ምን ጨንግፎባችኃል? በማን ተከድታችሁ ተጎድታችኃል? ማንን አጥታችሁ በምን ሐዘን ውስጥ ገብታችኋል? በምን ውስጥ ነህ? በምን ውስጥ ነሽ፣ በምን ውስጥ ናችሁ?
እርሱ በእርግጥ ያስብልናል፣ ይራራልናል።

ዘማሪት ምህረት ኢተፋ በመዝሙርዋ

ተጽናኑ ዛሬ ይሄ እንደዚህ ያልፋል
ነገ ደግሞ መልካም ይሆናል /2× ስትለን

ዘማሪት ሐና ተክሌ ደግሞ

ያየናል የማያይ ሲመስል
ይሰማናል በብርቱ ዝም ሲል
አለ የሚረዳን በዙፋኑ
ሚደርስልን በማዳኑ
.
.
ይራራልናል ያስብልናል
በጊዜው ሰርቶ ደግም ያስቀናል
ይመጣል ነገ ዛሬ ያልቅና
ደግሞ እንስቃለን ቆመን በትናንትና

እውነት ነው፦ እንደ ሃገር፣ እንደ ቤተክርስቲያን ፣ እንደ ቤተሰብ፣ እንደ ግል ህይወት ላሉብን ጥያቄዎች፣ ላልተጽናንባቸው ነገሮቻችን እርሱ ከላይ ያየናል፣ ይራራልናል፣ ያስብልናል ደግሞ ይመጣልናል።

“አጽናኑ፥ ሕዝቤን አጽናኑ ይላል አምላካችሁ።”
— ኢሳይያስ 40፥1

ዘሪሁን ግርማ

/channel/theideaofs

Читать полностью…

የዘር ሐሳቦች/ Yezer Hasaboch

#የደስታችሁ_ምንጭ_ምንድነው?

ደስታ ልባችንን ባስቀመጥንበት ነገር ይወሰናል። ልባችንን ያስቀመጥንበት ነገር ለደስታችን ሆነ ለሐዘናችን ምክንያት የሚሆነው። ለዚህም ነው መጽሐፍ ቅዱሳችን፦

"ሁልጊዜ በጌታ ደስ ይበላችሁ፤ ደግሜ እላለሁ፥ ደስ ይበላችሁ።”
— ፊልጵስዩስ 4፥4

የደስታችሁ ምንጭ ምንድነው ነው ? ወይም ማነው? ይህን ያለወቀ ደስተኛ ሊሆን አይችልም፡፡ ደስታን ያለ ትክክለኛ ምንጩ ማግኘት አንችልም፡፡ እንደ ሰዉኛ ደስ ልንሰኝ እንሰኝባቸዋለን ብለን የምንናስባቸው ብዙ ነገሮች ይኖሩናል። "ይህ ቢሳካ ደስተኛ እሆናለሁ!" "ይህ ቢኖረኝ ደስተኛ እሆናለሁ።" ልንል እንችላለን። እኛ የምንፈልጋቸው ነገሮች ያላቸው ደስተኛ ሳይሆኑ ሊያጋጥሙን ይችላሉ። ደስታ ከትክክለኛው ምንጭ ሲጀምር ዘላቂ ደስታን እናገኝበታለን።

"በጌታ ደስ ይበላችሁ።"

ለደስታችን ምንጭ አድርገን የያዝናቸው ነገሮች እነማን ናቸው? ቤተሰባች ነውን? ወይስ ስራችሁ? እጮኛችሁ ነውን ወይስ ትዳራችሁ? የተማራችሁት ትምህርት ወይስ ያላችሁ ገንዘብ? እነዚህ ነገሮች በራሳቸው የሚሰጡን ደስታ ይኖራቸዋል። ከእግዚአብሔር ጋር ባለን ህብረት የሚያህል ደስታ ግን የለም።

War Room የሚል አንድ ፊልም የሆነ ጊዜ ላይ አይቻለሁ። ፊልሙ የሚያወራው ስለ ፀሎት ነው፡፡ ፊልሙ የአንዲት ባለትዳር ትዳር እንዴት በፀሎት እንደዳነ ይተርካል፡፡ እዚያ ፊልም ላይ ሴትዮዋ በፀሎቷ መሀል ስትፀልይ "ሰይጣን ከእንግዲህ ትዳሬን አያሳየህ ደስታዬን አትሰርቅም የደስታዬ ምንጭ ኢየሱስ ነው ትዳሬ አየደለም።" ትላለች።

ዓይናችንን የምንጥልባቸው ነገሮች የደስታ ምንጭ መሆን አይችሉም። ከጌታ ውጪ። እውነቱን እንነጋገር ብዙ ክርስቲያን በሐዘን የሚዋጠው ደስታውን ከተሳሳተ ነገር ስለሚጀምር ነው። እንደ ክርስቲያን በረከትን ሁሉ የምንቀበለው ከእግዚአብሔር
ነው፡፡ ከእግዚአብሔር ውጭ የሆነ በረከት ልናገኝ ብንችልም ጊዜያዊ ደስታ፣ ብዙ ሀዘን እንከናነባለን፡፡
ከመንፈስ ቅዱስ የተቀበልነው ደስታ፣ እግዚአብሔር ለእኛ የሰጠው በረከት ነው።

ደስተኛ ስንሆን አመስጋኝ፣ ደስተኛ ስንሆን ባለን የምንረካ እንሆናለን። ደስታን ከተሳሳተ ምንጭ መጀመር ለበረከት አይዳርግም። ሐዋሪያው ጳውሎስ የፊሉጵስዩስ መልዕክትን ሲጽፍ በእስር ቤት ነበር። ሰው በእስር ቤት ሆኖ እንዴት ስለ ደስታ ይጽፋል? ሲባል ደስታ ሐይል ነው። በእግዚአብሔር መደሰት። በእግዚአብሔር ደስታ ውስጥ የምትሆነው ነገሮች ስለተሳኩ ወይም ስላልተሳኩ አይደለም። ደስታ የመንፈስ ቅዱስ ስጦታ ነው። ደስታ ከምንመካበት ነገርይመነጫል፣ በእግዚአብሔር ከተመካን ደስታችን ፍጹም ይሆናል።

የማይሰረቅ የደስታ ምንጭ ኢየሱስ ነው።

ሌሎቹ ደስታዎች ጊዜያዊ፣ እግዚአብሔርም
የማይከብርባቸው፣ የአለም ደስታዎች ናቸው፣ አድካሚ መንገዶችም ናቸው፡፡

'ሁልጊዜ በጌታ ደስ ይበላችሁ ደግሜ እላለው 'ደስ' ይበላችሁ።" ፊሊ 4:4

በጌታ ለመደሰት ሚሊየንስ ምክንያት አለን
በራሳችን ለመደሰት ያለ እርሱ አንድም ምክንያት የለንም፡፡ ደስታ ከምንጩ ይጀምራል ምንጩ እግዚአብሔር ነው።

ዘሪሁን ግርማ

/channel/theideaofs

Читать полностью…

የዘር ሐሳቦች/ Yezer Hasaboch

#በመልቀቅ_መዳን!!

የምንታገልባቸው ብዙዎቹን ነገሮች ስንመለከት የእኛ አይደሉም ወይም፣ ያለ ቦታቸው ቦታ ሰተናቸዋል፣ ወይም ያለ አግባብ የያዝናቸው ናቸው። በዚያም ምክንያት ያለ አግባብ ዋጋ እንከፍላለን። ግንኙነቶች፣ ጓደኝነት የተቃራኒ ጾታ ጓደኝነት ( Relationship) ወይም ከሰዎች ጋር ያለን ማንኛውም አይነት ጉዳዮች እንደማይቀጥሉ እየገባን ግን በትግል ለማስኬድ የምንታገልባቸው ግንኙነቶች ጉዳታቸው ከፍተኛ ነው። ባለ መልቀቅ ውስጥ የሚደረግ ዋጋ መክፈል ይባላል።

በግድ፣ በትግል፣ ከአንድ ሰው ብቻ በሚደረግ ጥረት የተገነባ ግንኙነት አስፈላጊ አይደለም ። በዚህ አይነት ግንኙነት ውስጥ ከሆንክ ለቀቅ አድርገው ለጊዜው የተጎዳህ ቢመስልም ነገ ግን ህይወትህን ዕድሜህንና ሐይልህን ትታደግበታለህ። የአንተ ያልሆነውን በግድ የአንተ ለማድረግ መታገል ከንቱ ዋጋ መክፈል ነው።

በዚህ አይነት ግንኘቱነት ውስጥ ከሆንክ ልቀቅ (ቂ) የአንቺ ካልሆነው ስትታገይ የአንቺ የሆነው ያመልጥሻል (ሃል) ልቀቅ (ቂ)። የአንቺ ህይወት የማይቀጥለው ያለ አንቺ ብቻ ነው። ከሚያደክም ከማያፈራና፣ ፍጻሜ ከሌለው ግንኙነቶች ተላለቀቁ።

በሰዎች ተበድለን ይቅርታ ባለማድረግ ውስጥ ካለን፣ ሰዎችንና በደላቸውን ባለመልቀቅ ራሳችንን ለበለጠ ጉዳት እናጋልጣለን። በሰዎች ከተበድልነው በላይ፣ ሰዎችን ባለመልቀቅ (ይቅር ባለማለት) በባሰ መጎዳት ውስጥ እናልፋለን። ይቅርታ ማድረግ የበደሉንን ሰዎች መፍታት ብቻ ሳይሆን ራሳችንን ነጻ ያወጣናል። ነክሰን የምንዛቸው ነገሮች መልሰው ጉዳታቸው ለእኛው ነው። ስለዚህ ለቀቅ።

ባለመልቀቅ የምንጎዳባቸው ነገሮችን በመልቀቅ ልንድንባቸው እንችላለን። የእኛ ያልሆኑ ነገሮች የእኛ አይደሉም። ይህ ነገር በተለያዩ ጉዳዮቻችን ያግጥመናል። የእኛ የሆነና ትክክለኛ ነገር ዋጋ አያስከፍለንም፣ መልቀቅ እያለብን የታቀፍነው ነገርም አደጋው ከፍተኛ ነው። በመልቀቅ እንዳን።

ዘሪሁን ግርማ

/channel/theideaofs

Читать полностью…

የዘር ሐሳቦች/ Yezer Hasaboch

#አጥቢያ_ቤተክርስቲያን_የሌላቸው_'ታዋቂ'#አገልጋዮች

በተለያዩ አብያተክርስቲያናት የአገልግሎት በር ተከፍቶላቸው የሚያገለግሉ አገልጋዮች ግን ደግሞ አጥቢያ ቤተክርስቲያን የሌላቸውን አገልጋዮች ይመለከታል የዛሬው ጽሑፍ። ጉዳዩ ዘርፈ ብዙና ብዙ ልንሰራበት የሚገባን ጉዳይ ነው። የአገልግሎትን ንጽህና የምንጥቀው አንደኛው አገልጋዮች በአንድ አጥቢያ ቤተክርስቲያን መሆን ሲችሉ ነው። አጥቢያ ቤተክርስቲያን የሌላቸው አገልጋዮች ለተለያዩ ችግሮች ተጋላጭ መሆናቸውን ለመናገር እወዳለሁ።

እያንዳንዱ አገልጋይና ምዕመን ስለ እርሱ የምትመሰክርለትና ህይወቱን የምታውቀው ቤተክርስቲያን ታስፈልገዋለች። ቤተክርስቲያን በክርስቶስ የተመሰረተች ስለሆነች፣ ብዙ ህዝብ ይኑራት አይኑራት ታዋቂ ናት አይደለችም አይባልም። ቤተክርስቲያን ስልጣኗ ክርስቶስ በሰጣት ስልጣን ልክ ነው። የክርስቶስ መልዕክትና የያዘችና ጤነኛ ትሁን እንጂ።

ብዙ የምናውቃቸው አገልጋዮች ጭምር የት ቤተክርስቲያን እንደሆኑ የማይታወቁ (ወይም ቤተክርስቲያን የሌላቸው) አንዳንዶቹ ደግሞ ቀድሞ በነበሩበት ስም (ለስም ብቻ) የሚጠሩ ግን ቤተ ክርስቲያናቸው ከሄዱ አመታት ያለፋቸው ብዙዎች ናቸው። በአገልግሎት ብቻ የምናውቃቸው ናቸው። ድሮ ድሮ ለአገልግሎት ስትጋበዝ ቤተክርስቲያንህና ምስክርነትህ ይጠየቅ ነበር፣ አሁን አሁን ደግሞ ሰዉ ያውቀዋል ወይ እንጂ የት ቤተክርስቲያን ነው አይባልም።

ከቤተክርስቲያን በላይ የሆነ አገልጋይ የለም። ቤተክርስቲያን የእግዚአብሔር መንግስት ወኪል ናት፣ አገልጋዮቹ ደግሞ የመንግስቱ ሰራተኞች ናቸው። ስለዚህ እያንዳንዱ አገልጋይ አካል የሚሆንባት ቤተክርስቲያን ያስፈልገዋል ብቻም ሳይሆን ህይወቱንና አገልግሎቱን የምታይና የምታውቅ ያስፈልገዋል። ብዙ ሰው ሊያውቅህ ይችላል!! ቤተክርስቲያን ግን ያስፈግሃል።

እዚህ ጋር ችግሮቹ ያለው አገልጋዮቹ ብቻ ጋር ሳይሆን ቤተክርስቲያን መሪዎቹም እንደነዚህ አይነት አገልጋዮችን የሚይዙበት ጸጋና መሪነት ብዙም አይታይባቸው። አንዳንድ ቤተክርስቲያናት ሰውየውን ለህይወቱ ሳይሆን ለአገልግሎቱ ስም ስላለው ብቻ ሲፈልጉት፣ አንዳንድ ቤተ ክርስቲያናት ደግሞ በሰውየው ላይ ያለውን ጸጋ አክብረው ከመጠቀም ይልቅ አብሯቸው ስላለ ብቻ ቦታም አይሰጡትም። በሌላ ስፍራ አገልግሎት ተፈላጊ ስለሆነ ያ ሰው ደግሞ በዚያ ስፍራ ላይጸና ይችላል።

በአብያተክርስቲያናት የአገልግሎት በር ያለው አገልጋይ አጥቢያ ቤተክርስቲያን ያስፈልገዋል ማለት ቤተክርስቲያን ያንን ሰው በላዩ ላይ እንዳለው ጸጋና ለአካሉ በይበልጥ እንዲጠቅም አድርገው ላቅ ባለ መሪነት መያዝ አለባቸው ማለት ነው። አንዳንድ አገልጋዮች ደግሞ በር ስለተከፈተላቸውና ሰው ስላወቃቸው፣ በራሳቸው የቆሙና በቤተክርስቲያን ውስጥ መሆን እንዳለባቸው አያምኑም፣ ብልት ምንም አይነት ብልት ይሁን መኖር ያለበት በአካሉ ውስጥ ነው። አይን ወይም አፍንጫ ለብቻው አይቆምምና።
መንፈስ ቅዱስ ለተለየ የአገልግሎት አላማና ምሪት ካልሰጣቸው በቀር ሁሉም አገልጋዮች በአጥቢያ ቤተክርስቲያን ውስጥ መሆን አለባቸው። ይህም ደግሞ ለተለየ ተልዕኮ ጥሪ ላላቸው ብቻ ነው።

ሌላው ችግር ያልሰራህበት አገልጋይ በቤተ ክርስቲያን እያለ ጸጋውን ያልተጠቀምክበት ወይም ዕድል ያልሰጠው አገልጋይ፣ እግዚአብሔር በድንገት በር ከፍቶለት በሌላ ስፍራ ጸጋው ሲወጣና ብዙዎች ሲጠቀሙበት መልሰህ በቤተክርስቲያን ተቀምጥ ማለትም አይቻልም። ሰውየው ትሁት ካልሆነ በቀር። የብዙ አገልጋዮች ከቤተክርስቲያን የወጡበት መንገድ ይህ ነው። ቤተክርስቲያን በውስጥዋ ጸጋ ያላቸውን አገልጋዮች ለይታ፣ አሳድጋ የአገልግሎት ዕድል መስጠት መልመድ አለባት። ይህ ነው የመሪነት አንደኛው አቅም።

አንድ ታዋቂ ወጣት ዘማሪ "የት ቤተክርስቲያን እንድያዝ ትመክረኛለህ?" ሲለኝ ያልኩት "ጸልየህ እግዚአብሔር በመራህ ስፍራ ሁን።" አልኩት። አሁንም ሁሉም አገልጋይ መሆን በተገባው ስፍራ እግዚአብሔር በመራው መንገድ አጥቢያ ቤተክርስቲያን ውስጥ መሆን አለበት። አገልጋዩ ጸጋ ስላለው ብቻ ጸጋውን ተጠቅመው ግን ደግሞ አገልጋዩን የማይደግፉና የማይፈልጉ፣ ስለ አገልጋዩ ህይወት ግድ የማይላቸው፣ የቤተክርስቲያን አመራሮች እጅግ ሊታረሙ ይገባል። ይህ አይነቱ ችግር በቆዩትም ቤተክርስቲያናት፣ በአንድ አመራር (One Man Leadership) ስር ባሉ ቤተክርስቲያን ውስጥ አለ።

ይህ ሐላፊነት አስቀድሞ ለቤተክርስቲያን መሪዎች ሲሆን፣ ሌላው የአገልግሎት በር ኖሯቸው አጥቢያ ቤተክርስቲያን ለሌላቸው አገልጋዮች ነው። የቤተ ክርስቲያን መሪዎች በመጽሐፍ ቅዱስ እውነታ መከተላቸው፣ የህይወት ንጽህናቸው፣ ምሳሌ መሆን የሚችል አመላለሳቸው፣ የአመራር ብቃታቸው፣ በአገልጋዮች ላይ ያለውን ጸጋ የመቀበል ልባቸው፣ መጋቢያዊ ክትትላቸው እጅግ ወሳኝ ነው።

በመጨረሻም፦ ቤተክርስቲያን የአገልግሎት ብቻ ሳትሆን የህብረት ቦታ ናት። እርስ በእርስ የምንተያይበት የምንተናነጽበት የምንደጋገፍበት ስፍራ ናት። እያንዳንዱ አገልጋይ ሆነ ምዕመን የተፈጠረው በቤተሰብ መሐል እንዲመላለስ ነው። በክርስቶስ ባለች በየትኛዋም ቤተክርስቲያን ውስጥ ሁን፣ አጥቢያ ቤተክርስቲያን ግን ይኑርህ።
አንድ ሰው አጥቢያ ቤተክርስቲያን ከሌለው ለክፉ ጥቃት የመጋለጥ አደጋ ላይ ነው። ቤተክርስቲያን የህብረት ስፍራ ናት፣ ህብረት ባለበት ጥበቃ ጭምር አለ።

ሐሳቡ ከዚህ በላይ መስፋት የሚችል፣ ችግሩም ሰፊና ብዙ ስራ የሚፈልግ ነው። ለማሰላሰል ይበቃ ዘንድ ይህን ካልኩ እዚህ ጋር ላብቃ።
.....
ዘሪሁን ግርማ

/channel/theideaofs

Читать полностью…

የዘር ሐሳቦች/ Yezer Hasaboch

#ከቅኖች_ጀርባ_እግዚአብሔር_ቆሟል!!

“በቅኖች በረከት ከተማ ከፍ ከፍ ትላለች፤ በኀጥኣን አፍ ግን ትገለበጣለች።”
— ምሳሌ 11፥11

ቅንነት በእግዚአብሔር ፊት ታላቅ ዋጋ አለው።
በዚህ ዘመንና አሁን ባለው በአብዛኛው ትውልድ ዘንድ ዋጋ የሌለውና፣ ያለፈበት የሚመስለው፤ ጊዜው የብልጣብልጦችና የአስመሳዮች እንደሆነ በሚነገርበት፣ ቅኖች አላዋቂዎች እና ኃላ ቀሮች ተደርገው በሚታሰቡበት በዚህ ዘመን፣ እግዚአብሔር ግን የሚቆመው ከቅኖች ጋር ብቻ ነው።

ቅንነትን በሚያስጥል ትግል ውስጥ ያላችሁ ቅን- ወገኞቼ ይህቺ አጭር ጽሑፍ ለእናንተ ናት። ቅንነታችሁን ጠብቁ፣ የእግዚአብሔር አብሮነት ያለው ከልበ ቅኖች ጋር ነው። ቅንነት ሞኝነት አይደለም ነገር ግን በህይወታችን ከእግዚአብሔር ዘንድ ዋጋ ያለው ውድ ስጦታ ነው።

ቅን-መንገድን መከተልና ልበ ቅኖች እንድንሆን እግዚአብሔር በሁሉ ያግዘን። ዘመኑ ምንም ያህል ቢከፋ፣ ሰዎች በክፉ ልብና፣ ጥመት በተሞላ መንገድ ቢጓዙ፣ የእግዚአብሔር ቃል ግን አይሻርም።

“ቅኖች ቅንነታቸው ትመራቸዋለች፤”
— ምሳሌ 11፥3

ቅንነት ከልብ ጋር የተያያዘ ነው፣ ጤናማ የልብ አቀማመጥ ነው። ቅኖችን እግዚአብሔር ይወዳል። ቅን ሰው ለጋስ ነው፣ ቸር ነው፣ አመስጋኝ ነው።

“በቅኖች መካከል ግን ቸርነት አለች።”
— ምሳሌ 14፥9

እግዚአብሔር በቅኖች ማደሪያ ይገኛል። በሌሎች ስኬት የሚደሰቱ፣ በሌሎች ውድቀት የሚያዝኑ፣ እነርሱ ልባቸው የተባረከ ቅን ሰዎች ናቸው።

“የኀጥኣን ቤት ይፈርሳል፤ የቅኖች ማደሪያ ግን ያብባል።”
— ምሳሌ 14፥11

ቅንነት በእግዚአብሔር ዘንድ ደመወዝ አለው።
ቅኖች የእግዚአብሔር ፊት ያዩታል። ቅኖች እንድንሆን እግዚአብሔር ይርዳን!! ቅንነታችንን እንድንጠብቅ እግዚአብሔር ይርዳን።

ዘሪሁን ግርማ

/channel/theideaofs

Читать полностью…

የዘር ሐሳቦች/ Yezer Hasaboch

#መዝሙር_91_አልበም ዳኒ (ዳዊት) ወልዴ!!

አፌን ሞላው በሳቅ ዝማሬ
ተረጋጋ ዙሪያ ሰፈሬ
ስለ ስሙ ያደረገው
ምስጋናው እጅግ ብዙ ነው

ይህ አልበም ከወጣ ከወጣ ባልሳሳት ከ15 አመታት በላይ ይሆነዋል። እኔ ከስልኬ እንዲጠፉ ከማልፈልጋቸውና፤ እስከዛሬም ድረስ በስልኬ ከጠበኳቸው ጥቂት 'ወርቃማ' አልበሞች አንዱ ይህ "መዝሙር 91" የዳኒ (ዳዊት) ወልዴ አንዱ ነው። ዝማሬዎቹን የሰማ በሙሉ ከዚህ በታች የማነሳቸውን ሐሳቦች ይጋራኛል ብዬ አስቤያለሁ። ስለ አልበሙ ከማውራቴ በፊት እነዚህን እውነታዎች ላንሳ፦

፨ ይህ አልበም በወጣበት ጊዜ እጅግ ብዙ ተቃውሞ የደረሰበት አልበም ነው። እኔ በዚያ ልክ ተቃውሞ የገጠመው አልበም አላውቅም። ለምሳሌ አንዳንድ ቤተክርስቲያን ውስጥ እንደ ዘፈን ተቆጥሮ ነው መሰል ካሴቶቹ ተሰብስበው እንደተቃጠሉ ሰምቻለሁ። በዚያን ወቅት ብዙ ወገራ አልፎበታል ሙዚቃው ዘንፈን ይመስላል፣ የዘማሪው ጸጉር (ጎፈሬው) የአለማውያን ነው። አልበሙ እንደዚህና እንደዚያ የሚሉ የተቃውሞ ውግረቶችን አስተናግዷል። አልበሙን ደጋግሜ እንደመስማቴና ወደፊትም ለመስማት ራሱን እንዳዘጋጀ የአልበሙ ወዳጅ ይህን ያህል ተቃውሞ በዳኒ ላይ የደረሰበት ምክንያት እስከአሁን አልገባኝም።

፨ ሌላው ዳኒ ይህን አልበም ካወጣና ብዙ ታቃውሞ ካለፈበትና ወደ አሜሪካ ከሄደ በኃላ በዝማሬ ምን እየሰራና አግልግሎቱን በተመለከተ ምንም መረጃ የለም። የሚያውቅ ሰው ካለ ቢያጋራኝ ደስ ይለኛል። ዳኒ ተጨማሪ ዝማሬዎቹን ቢሰራ ብለው ከሚፈልጉ መሐል ነኝ። ወደ ኢትዮጵያ መቶ ቢያገለግል፤ ይህ ትውልድ ዝማሬዎቹን እንደሚወድና እንደሚባረክበት ቢያውቅ ደስ ይለኛል።

እኔ ማመልከው ጌታዬ
አባት ወንድም ጓደኛዬ
የጸና ጽኑ መሸሸጊያዬ
በፍቅር ተማርኬያለሁ
ፈቅጄ አመልከዋለሁ
ለዘላለም ለእርሱ እገዛለሁ

ዝማሬዎቹን በተመለከተ በቀጣይ ጽሑፎቼ እመጣለሁ። በእኔ ምልከታ አልበሙ ባለፉት ሃያ አመታት ወዲህ ከወጣ ድንቅ አልበሞች አንዱ ነው። ዳኒ ይህን አልበም ስላበረከትክልን እናመሰግናለን።

ክብር ለእግዚአብሔር
ክብር ለኢየሱስ
ክብር ለመንፈስ ቅዱስ
ስሙ በአለም ይንገስ
....
ዘሪሁን ግርማ


/channel/theideaofs

Читать полностью…

የዘር ሐሳቦች/ Yezer Hasaboch

#አላበቃም_አልዘገየምም!!

አንዳንዴ ይህች አለም እንደገና እድል የማትሰጥ ሆና እናያታለን። በዙሪያችን ያሉ አንዳንድ ሰዎችም ነገሮቻችን የእንደገና ዕድል እንዳለው አይነግሩም። ነገር ግን ያበቃ ያከተመና ያለቀ በሚመስሉ ነገሮች ላይ ተስፋ እንዳለን የማመን ተስፋ ሊኖረን ይገባናል። እግዚአብሔር።

እግዚአብሔር ለእኛ ያለቀ፣ ያበቃና ያከተመ የተባለውን ነገራችንን ቀጥሎልን አለን። ሁሌም በሰዎች አለም አልፎም በእኛ እሳቤ ነገሮቻችን ያለቀ፣ የዘገየን፣ የተቀደምን ብለን በዘጋናቸው ነገሮቻችን ላይ እግዚአብሔር ሁሌም እንደገና አለው።

የተቋረጡ ነገሮች ሊቀጠሉ፣ የሞቱ ነገሮች ህያው ሊሆኑ፣ የተበላሹ ነገሮች ሊስተካከሉ፣ የጠወለጉ ነገሮች ሊለመልሙ፣ ተስፋ በማጣት ጨለማ ውስጥ ያሉ ነገሮች በተስፋ ብርሃን ሊሞሉ፣ ያረጁ ነገሮቻችን ሊታደሱ ዛሬም ይችላሉ። በእግዚአብሔር ነገሮቻችን ሊቀየሩ ይችላሉ። እኛ የእግዚአብሔር የመቻል አቅም ውጤቶች ነን። ዛሬም በሆነ የ" አልችልም አቅቶኛል" በሚል የህይወት መንገድ ላይ አንድ ሰው፣ ነገሩ የተቃናለት፣ ቃናው የጣፈጠለት፣ መአዛው የተቀየረለት፣ ነገሩ የተቀጠለለት ሰው (የእኔ) መልዕክት ይህ ነው። እግዚአብሔር ይችላል፣ በእግዚአብሔር ሁሉም ይቻላል። ዛሬም ተስፋ አለን፣ ነገራችን አላበቃም አልዘገየምም።

/channel/theideaofs

Читать полностью…

የዘር ሐሳቦች/ Yezer Hasaboch

#ሁለንተናዊ_የዕድገት_በሮች!!

ሁላችንም በሚባል ደረጃ ዕድገቶቻችን የተወሰኑ ወይም በአንድ አቅጣጫ ብቻ ናቸው። ሁለንተናዊ ዕድገት ስንል ደግሞ በሰዎች እይታ ልክ የተለያዩ ቢሆኑም፣ እኔ ሁለንተናዊ ዕድገት ላይ ሰው የሚቃለው ምን ምን ሲኖረው ነው ብዬ አስቤ አራት ነጥቦችን ማንሳት ወደድኩ።

፨ መንፈሳዊነት
፨ ራዕይ ወይም ስራ
፨ ከሰዎች ጋር ያለን ግንኙነት
፨ ለሁለንተናዊ ዕድገት የሚጠቅሙ መርሆችን መረዳት ናቸው።

ዕድገት በአንድ አቅጣጫ ብቻ ከሆነ ምሉዕ በሆነ ህይወት አናድግም። አንዳንድ ሰው ብዙ ሊያስተምር፣ ሊጸልይና ሊዘምር ይችላል ከሰዎች ጋር ተግባብቶ የመኖር ክህሎት የለውም። ወይም ጥሩ ስራ ወይም ብዙ ገንዘብ ሊኖረው ይችላል ነገር ግን መንፈሳዊ የህይወት መርሆች ከሌሉት ገንዘቡ ብቻ ዕድገቱን ሙሉ አያደርገውም። እስቲ እነዚህ አራት ነገሮችን በጥቂቱ እንመልከት።

#መንፈሳዊነት በዚህ ውስጥ በእግዚአብሔር ማመን፣ ዳግም ውልደት፣ በቃሉ ማደግ፣ መጸለይ፣ አምልኮ፣ ከቅዱሳን ጋር ህብረትን ማድረግ፣ ማካፈል፣ ስለ መንፈሳዊና ምድራዊ አኗኗር ጭምር መጽሐፍ ቅዱሳዊ መረዳትን መያዝ፣ በፍቅር መመላለስ፣ በምስጋና መቆም፤ ስለ እግዚአብሔርና ስለ ሰዎች ትክክለኛውን መረዳት መያዝ እያልን ልንዘረዝራቸው እንችላለን። አንድ ሰው ይህ አይነት ነገሮችና ተጨማሪ ቃሉአዊ ነገሮችን ሲይዝ መንፈሳዊ ይባላል። መንፈሳዊነት ከታች ለምናነሳቸው ነጥቦች መሰረት ናቸው።

#ራዕይ_ወይም_ስራ መጽሐፍ ቅዱስ ከሚቃወማቸው ነገሮች አንዱ ስንፍናን ነው። ሰው በውስጡ ባለው ራዕይ ወይም በሚሰራው ስራ ላይ ትጉ መሆን አለበት። ታላልቅ ሰዎችን መቀየር የሚችሉ ሐሳቦችን ተግባራዊ በማድረግ ውጤታማ መሆን መቻል አለብን ወይም በስራችን ውጤታማ መሆን አለብን። የማይሰሩ፣ ታካችና ሰነፍ ሰዎችን እግዚአብሔር ይቃወማል። እግዚአብሔር ራሱ ያረፈው በሰባተኛው ቀን ስድስት ቀን ሰርቶ፣ እግዚአብሔር ሰራተኛ ነበር፣ ኢየሱስም ሰራተኛ ነበር። በዕረፍት መኖር ማለት ያለ ስራ መኖር ማለት ሳይሆን፣ በክርስቶስ ባለው የዕረፍት መንፈስ መመላለስ ማለት ነው። አገልጋይ ከሆንክ ፍሬያማና ትጉ አገልጋይ ሆን። ሰራተኛ ከሆንክ በስራው ውጤታማ የሆነ ሰራተኛ ሁን።

#ከሰዎች_ጋር_ያለን_ግንኙነቶች ሰዎች በመሆናችን ከሰዎች ጋር ጤናማ ግንኙነት እንዲኖረን ነው ያስፈልጋል። በትዳር፣ በስራ፣ በጓደኝነት፣ በአገልግሎት፣ በጉርብትና ወዘተ ከሰዎች ጋር ጥሩ ግንኙነት ማዳበር አለብን። ከላይ እንዳልኩት በገንዘብ ወይም በተለያዩ ስኬት ላይ የደረሱ ከሰዎች ጋር በመልካም መርሆች የመኖር ብስለት የሌላቸው ሰዎች ብዙ አሉ። ሁለንተናዊ እድገት አንደኛው መለኪያው ከሰዎች ጋር የሚኖረን መልካም ግንኙነት ነው። ሁለንተናዊ እድገት ሰዎችን እንዴትና በምን መልኩ መያዝ እንዳለብን ስንማር የሚመጣ ነውና ራሳችንን በዚህ ብቁ ለማድረግ መስራት አለብን።

#ለሁለንተናዊ_ዕድገት_የሚጠቅሙ_መርሆች
እነዚህ መርሆች እንደ ሰዎቹ ማንነትና የህይወት ምልከታ የተለያየ ቢሆንም ከዚህ በታች የማነሳቸው ነጥቦች እጅግ አስፈላጊ ናቸው።
ጥቃቅን የሚመስሉ ነገር ግን ለሁለንናዊ ዕድገት መሰረት የሆኑ ነገሮች፦

፨ አትኩሮት (Focus) (የምትሰራቸውን ነገሮች ላይ ትኩረት ማድረግ)
፨ ጊዜን መጠቀም (ሰአት ማክበር)
፨ ማንበብ (ራስ ላይ መስራት)
፨ አገልጋይነት (ማህበረሰብን መጥቀም)
፨ ካለን ማካፈል (ማካፈል የዕድገት አንዱ አካል ነው። ሰው ሲያድግ ለሌሎች ይተርፋል)


/channel/theideaofs

Читать полностью…

የዘር ሐሳቦች/ Yezer Hasaboch

#ጊዜ_ጀግናው

" እኔም ተመለስሁ፥ ከፀሐይ በታችም ሩጫ ለፈጣኖች፥ ሰልፍም ለኃያላን፥ እንጀራም ለጠቢባን፥ ባለጠግነትም ለአስተዋዮች፥ ሞገስም ለአዋቂዎች እንዳልሆነ አየሁ፤ ጊዜና እድል ግን ሁሉን ይገናኛቸዋል። "
(መጽሐፈ መክብብ 9:11)

አንዳንድ ጊዜ ሰዎች ያልሰሩበትን ሞገስ ሲያገኙ፣ በዚያ ጉዳይ የሰሩ ደግሞ ትዝም ሳይባሉ ሲቀር፣ የተጋ ሳይሆን ያልተጋ ዋጋ ሲወስድ ስንመለከት ስናይ ሰዎቹ ሳይሆኑ ጀግናው ጊዜ ነው። ጊዜ ሁሉ ነገር ነው። ጊዜ ዳኛ ነው። ጊዜ ከፍታና ዝቅታ ነው። ጊዜ የምንኖርበት ተስፋም ነው። ትናንት አንድ ነገር እንዲሆን የተጉና ዋጋ የከፈሉ ሰዎች ያ ነገር ሲሆን የሚከብሩት ሌሎች ሲሆኑ አንዳንዶቻችን የምንተጋው ለነገ ጊዜው ላይ ለሚገዙ ሰዎች ሊሆን ይችላል። አንዳንዴ ይሆን ነገር ይከሰታል። ጊዜ እግዚአብሔር ሰዎችን የሚክስበት መንገድም ነው። በሌሎች መዋረድ የከበሩ ሰዎች የከበሩት ተገብቶአቸው ሳይሆን፤ ጊዜ ጀግናው እድል ሰቷቸው ነው።

ዘሪሁን ግርማ


/channel/theideaofs

Читать полностью…

የዘር ሐሳቦች/ Yezer Hasaboch

ሶስት መጠንቀቅ ያለብን የሰዎች አመካከቶች

፨ እንደ እነርሱ ካላሰብክ ትክክል ነህ ብለው የማያምኑ፣ ትክክለኛነትን ከእነርሱ ጋር በሚኖርህ ግንኙነት ብቻ የሚለኩ፣

፨ የሚወዱትን እንድትወድ፣ የሚጠሉትን እንድትጠላ፣ የሚፈልጉትን ያንን ካላደረግ ተቀጽላ ስም የሚሰጡ እነዚህም የህይወት ችግሮች ናቸው።

፨ እኔ አውቅልሃለሁ፣ አንተ ስለ ራስህ አታውቅም የሚሉ፣ አንተ በራስህ ፈትነህ ነገሮችን አይተህ እንዳትሄድ የማይፈልጉ "አዋቂዎችህ" ነን ባዮች እነዚህም የህይወትህ ዋነኛ ችግሮች ናቸው።

ሰው የተፈጠረው ከእግዚአብሔርና ከሰዎች የሚማር ትሁት ልብ እንዲኖረው፣ ሰዎችን እየወደደና ለገባው እውነት እየቆመ፣ በገባው ልክ እንዲኖር እንጂ ሰዎች በሰሩለት ልክ እንዲኖር አይደለም።

/channel/theideaofs

Читать полностью…

የዘር ሐሳቦች/ Yezer Hasaboch

" ያየሃቸው ህልሞችህን የሰው ውሳኔ አይሽራቸውም።"

Читать полностью…

የዘር ሐሳቦች/ Yezer Hasaboch

#አባቶች_አገልጋዮች እና #ወጣት_አገልጋዮች!

በአንድ ወቅት አባባ ሻኛ በተገኙበት አንድ ጉባኤ አንድ የተጋበዘ አገልጋይ "እኛ ይህን ያህል ዘመን አገልግለን እያለ.." ይናገራል። ሰባኪው በድጋሚ "በአገልግሎት ያየነው" እያለ ስለ ከፈለው መከራ ደጋግሞ መስበኩን ቀጠለ። በዚህ መሐል አባባ ሻኛ ወደ አንድ አጠገባቸው ወዳለ አገልጋይ ዞር ብለው "ምን ያህል አመት አገልግሎ ነው?" ብለው ጠየቁ አጠገባቸው ያለው ሰውም " አስር አመት ቢሆነው ነው።" ብሎ መለሰላቸው። እርሳቸውም "ገና ምኑ ተይዞ ጉዞው!" አሉ ይባላል።

በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ ረጅም ዘመን ያለገለገሉ አገልጋዮች የጽናት፣ ተፈትኖ የማለፍ፣ የብዙ ልምድ፣ የብዙ ፍሬና የብዙ ተሞክሮ ባለቤት ያደርጋል። ረጅም ዘመን ያለገለገሉ አገልጋዮች የታመኑ አገልጋዮች በመካከላችን ካሉ ሚዛናዊነት ይኖረናል። ያንን ስንል ሰው ረጅም አመት ስላገለገለ ብቻ የትክክለኛነት መገለጫ ነው ማለት ባንችልም፣ ነገር ግን በብዙ መንገድ አልፈው በመካከላችን ያሉ ቀደምት አገልጋዮች ብዙ ነገር የምንማርባቸው ህያው መጻሕፍት ናቸው።

ብዙ ያለገለገልን ሲመስለንና ስንደክም ከእኛ ቀድመው ብዙ አመታት ያገለገሉ አገልጋዮች ለእኛ ምሳሌና ተነሳሽነት ይሆኑናል።

ከዚያ ተያይዞ ደግሞ ቤተክርስቲያን ወጣት አገልጋዮች ያስፈልጓታል። የአባቾችን አደራ ማስቀጠል የሚችሉ፣ ከአባቶች የተማሩ ከመጽሐፍ ቅዱስ አባቶች የተማሩ፣ ቀደምት ካለገለገሉ አባቶች የተማሩ ወጣቶች ያስፈልጋሉ። ወጣቶች ስራ፣ ትጋትና አቅም ሲሆኑ፣ አባቶች ምክር፣ ትምህርት እና ተግሳጽ ይሆናሉ። ወጣቶች አገልጋዮች ቶሎ ሲረኩና ሲደክሙ፣ የረጅም ዘመን አገልግሎት በጽናት ያለፉ አባቶች ተስፋና አቅምን ይሰጣሉ።

ይህን ስል ሁሉም አባቶች ወጣቶችን ይመክራሉ ይታገሳሉ ማለት ባይሆንም፣ አባቶችን የማይሰሙና የማይከተሉ ወጣቶችም አሉ።
ማወቅ ያለብን ሁለቱ አካላት መያያዝ ያለባቸው ነገሮች ናቸው። ብዙ ወጣት አገልጋዮችን የቤተ ክርስቲያን በረከት አድርጎ ሰቶናል። ነገር ግን አባቶች ጋር ያለ ትምህርት፣ ምክርና ተግሳጽ ከሌለ የወጣቶቹ አገልግሎት በብዙ ድካምና ብርታት፣ በብዙ መውደቅና መነሳት ትግል ውስጥ ያልፋሉ።

የነገዋ ቤተክርስቲያን ያለ ወጣት አገልጋዮች አትቀጥልም፣ የወጣቶች አገልግሎት ደግሞ ያለ ትክክለኛ (ለወጣት አገልጋዮች ፍቅርና ሸክም ያላቸው) መካሪ አባቶች፣ ምክር፣ ትምህርት፣ እና ተግሳጽ አይቀጥልም።

ዘሪሁን ግርማ

/channel/theideaofs

Читать полностью…

የዘር ሐሳቦች/ Yezer Hasaboch

#ከሰዎች_ሁሉ_ጋር_በሰላም_ኑሩ!!

ሰው ያለ "ሰላም" አብሮ አይኖርም። ሰላም እርስ በእርስ ላለን ቀጣይ መንገድ መሰረት ነው። ከሰዎች ጋር ባለን ማንኛውም ጉዞ 'በእኛ በኩል' ሰላም መሆን አለብን፣ ነገር በእነርሱ በኩል ሰላም ካልሆኑስ? ሰዎች በራሳቸው አህምሮ በፈጠሩት ነገር ከእናንተ ጋር ጠበኛ ሊሆኑ ይችላሉ፣ በቅናትና በፉክክር መንፈስ ጠበኛ ሊሆኑ ይችላሉ፣ ስለ እኔ እንዲህ ነው የሚያስበው ብለው ጠበኛ ሊሆኑ ይችላሉ፣ ወይም የሆነ ምክንያት ኗሯቸው ወይም ፈጥረው ጠበኛ ሊሆኑ ይችላሉ። ታዲያ ምን ልናደርግ እንችላለን? መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይለናል።

“ቢቻላችሁስ በእናንተ በኩል ከሰው ሁሉ ጋር በሰላም ኑሩ።”
— ሮሜ 12፥18

መጽሐፍ ቅዱስ በጣም አስደናቂ መጽሐፍ ነው።
"ቢቻላችሁ" "በእናንተ በኩል" "ከሰዎች ሁሉ ጋር" "በሰላም ኑሩ" ይለናል። የመጀመሪያው ቢቻላችሁ ሲል ከሰዎች ጋር በሰላም መኖር መፈለግ ዝም ብሎ የሚመጣ ሳይሆን ከተሰራ የህይወት መልካም ማንነት የሚመጣ ነው።

ከሰዎች ጋር እርስ በእርስ በሰላም መኖር የጋራ ጉዞ ነው። አንዳንድ ሰው በእርሱ ጋር በሰላም ለመጓዝ የምታደርጉትን ቅንነትና ትህትና በትዕቢት እያጣጣለ ሲቀጥል "ቢቻላችሁ በእናንተ በኩል" የሚለው ቃል ተግባራዊ ለማድረግ በእናንተ በኩል ሰላማችሁን ጠብቃችሁ መጓዝ ግድ ይሆናል። ያንን ስታደርጉ እንደ ሞኝና ፈሪ ልትቆጠሩ ትችላላችሁ አስታውሱ በዚህ አለም ላይ ሰላምን መጠበቅ እንጂ ጸብን መጫር ከባድ ሆኖ አያውቅም። ለዚህም ነው መጽሐፍ "ቢቻላችሁ" የሚለው።
በጸብ የሚያተርፈው ዲያቢሎስ ሲሆን ተጎጂዎች እኛው ነን።

"ከሰዎች ሁሉ ጋር" በሰላም መኖር ሐላፊነት የሚሰማውና የበሰለ ሰው ባህሪ ነው። ከሰዎች ሁሉ በሚያምኑም ከማያምኑም፣ ከሚቀርቡንም ከማይቀርቡንም ሰዎች ጋር በሰላም መኖር ግዴታ ነው። ሰዎች ቢጠሉህስ? ቢያሳድዱህስ? መጽሐፍ ቅዱስ መልሰህ አሳድ፤ ወይም ጥላቸው የሚለው ትምህርት የለውም።

አዎ አንዳንድ ሰው የሆነ ነገር ስለ አንተ ክፉ አውርቶ አንተ መልሰህ ያንን እንድታደርግ ሊያነሳሳህ ይችላል፤ ያንን ስትመልስ በክፋት ተሸንፈሃል ማለት ነው። ከላይ ባነሳነው ክፍል በቁጥር 17 ላይ እንዲህ ይለናል፦

“ለማንም ስለ ክፉ ፈንታ ክፉን አትመልሱ፤ በሰው ሁሉ ፊት መልካም የሆነውን አስቡ።”
— ሮሜ 12፥17

በሰላም የምንኖረው ለክፋት ክፋትን እየመለስን ክፋትን እያደረግን አይደለም። በሰላም ከሰዎች ጋር የሚኖሩ ሰዎች የበሰሉና ራሳቸውን የሚገዙ ሰዎች ናቸው። በሰላም ውስጥ መክሰር የለም ትርፍ እንጂ፣ በጠብ ውስጥ ትርፍ የለም ኪሳራ እንጂ። ሰላምን እንከተል። ከሰዎች ሁሉ ጋር በሰላም እንኑር። ሰላምን ከሚያደፈርሱ ነገሮች ራሳችንና መንገዳችንን እንጠብቅ።

ዘሪሁን ግርማ

/channel/theideaofs

Читать полностью…

የዘር ሐሳቦች/ Yezer Hasaboch

#የሰንበት_ትምህርት_ቤት /#የልጆች #አገልግሎት/ (Sunday School)

#ልጆችን_ለእግዚአብሔር_አላማ_ማዘጋጀት

እግዚአብሔር ልጆችን ለቤተክርስቲያን ሲሰጥ አባል ለማብዛት ሳይሆን የእርሱን መልክ የሚገልጡ ትውልዶች በቤተክስቲያን በኩል ተሰርተው እንዲወጡለት ነው። ልጆች አደራ የተሰጡን የእግዚአብሔር ርስቶች ናቸው።

ታላቁ የወንጌል አገልጋይ ዲ ኤል ሙዲ "አንድ ህፃን ልጅ ጌታን ሲያገኝ ሙሉ ሰው ዳነ" ይል እንደነበር "ልጆችን ወደ እውነት መምራት" ከሚለው የአለማየሁ ማሞ መፅሐፍ ላይ አንብቤያለሁ። ቤተክርስቲያን ልጆችን የማስተማር፣የመምራት፣ አልፎም የልጆቹ ቤተሰቦች ላይ መስራት ይጠበቅባታል። ምክንያትም ወደ ቤተክርስቲያን ሲመጡ ሙሉ ነገራቸውን ይዘው ነው የሚመጡት የምንስል ባቸው ስዕል ነው የሚታይባቸው ስለዚህ ምን እንደምንስልባቸው እንጠንቀቅ።

ቤተክርስቲያን በልጆች አገልግሎት ዙሪያ የቅርብና የሩቅ እቅዶችን ዘርግታ በልጆች አገልግሎት ላይ መስራት አለባት። ብቃትና ሸክም ያላቸውን አስተማሪዎችን መመደብና ለአስተማሪዎቹ በየጊዜው ስልጠናን ማዘጋጀት አለባት። የልጆች አስተማሪ መሆን የሚገባቸው የተማሩና ከልጆች ጋር መግባባት የሚችሉበት አቅም ያላቸው አስተማሪዎች እንጂ፣ ስራ የሌላቸውን ሰዎች ዝም ብለን ልጆች ላይ መመደብ የለብንም።

የህፃናትንና የታዳጊ ወጣቶችን አገልግሎት በተደራጀ መልኩ መስራት አለብን። ዛሬ የማንሰራበት ልጅ ነገ ቤተ ክርስቲያንን በምን መልኩ ነው የነገ ተረካቢ ማድረጌ የምንችለው? በምንስ መልኩ ነው ለቤተ ክርስቲያን፣ የሐገርና፣ ለቤተሰቡ አልፎም ለማህበረሰቡ መጥቀም የሚችለው?

#ክፍተታችንን_እንወቅ!!

ቤተክርስቲያን በህፃናትና በታዳጊ ወጣቶች ዙሪያ ላለው ችግር ሐላፊነትን መውሰድ አለባት። ይህ ጉዳይ ችግር መስሎ ካልታያት በዚህ ጉዳይ ለመስራት አትዘጋጅም። በትውልድ ላይ ካልሰራን የሚያስፈራው ነገር ቤተ ክርስቲያን ልትቋቋመው የማትችለው የትውልድ ክስረት እንደሚጠብቃት አንጠራጠርም። የጌታን ቃል ከአለም ለይቶ የማያውቅ ጠዋት ቤተክስቲያን ማታ ናይት ክለብ የሚዞር ትውልድና ማህበረሰብ የሚመነጨው ከልጅነታቸው ጀምሮ የተደራጀ በቃሉ ላይ የቆመ አሰራር የለንም።

በልጆች ህይወት ላይ ቤተክርስቲያን የመንፈሳዊ ነገር ላይ ብቻ ሳይሆን በምድራዊ ነገራቸውም ላይ መስራት መጀመር አለባቸው። እንደ እኔ እምነት ከወንጌል ስራ በመቀጠል ቤተክስቲያን ገንዘቧንና ሐይሏን በሙሉ መጠቀም ያለባት በዚህ አገልግሎት ላይ መሆን አለባት።

#ምሳሌ_መሆን_የሚችል_ቤተሰብ

"ያልተንኳኲ በሮች" መፅሐፍ ላይ ፀሐፊ ጳውሎስ ፈቃዱ "እነርሱ ቤተክርስቲያን ከመሄድ ይልቅ ከአልጋቸው ሳይወርዱ፣ ወይም ቴሌቪዥን ሲመለከቱ ለመዋል መርጠው ፣ ልጆቻቸውን ወደ ቤተ ክርስቲያን የሚሸኙ ወላጆች ምን ይባላሉ? ልጆቻቸውን "ፀልዩ" እያሉ እነርሱ የማይፀልዩ እነርሱ እየዋሹ ልጆቻቸውን እንዳይዋሹ የሚመክሩትስ እንዴት ነው?" (ገፅ 84) ይለናል።

በሰአት ስንመለከተው አንድ ልጅ ከቤተክርስቲያን ውጪና በትምህርት ቤት ውጪ ብዙዉን ጊዜ የሚያሳልፈው በቤቱ ነው። ቤተሰብ ልጅን በመቅረፅ ደረጃ ትልቁን ድርሻ ይይዛል። ልጅን ከመንፈሳዊ ነገር የሚያራርቁ ቤተሰቦችና በህይታቸው ምሳሌ የማይሆኑ ቤተሰቦች ልጅን ወለዱ እንጂ በትክክለኛ ህይወት አሳደጉ አይባልም። አንድን ልጅ አይተህ ቤተሰቦቹ ምን አይነት እንደሆኑ ማወቅ ትችላለህ።

ልጅን በህይወትህ ካልመራህውን በንግግር አትመራውም። ጠያቂ ትውልድ ጋር ነው እየደርስን ነው። ልክ እንደ ቤተክርስቲያን ሁሉ ቤተሰቦችንም ልጆቻቸው እነርሱ የፈጠሯቸው ሳይሆኑ ከእግዚአብሔር የተሰጣቸው፣ አደራዎች ናቸው። ምሳሌ በመሆን ልጆችን መምራት አስፈላጊ ነው። በልጆች ላይ እየሰሩ ያሉ ቤተክርስቲያናት እጅግ ሊመሰገኑ ይገባል።

ዘሪሁን ግርማ

/channel/theideaofs

Читать полностью…
Subscribe to a channel