#የማያድግ_ልጅ_አባቶቹን (#ታላላቆቹን) #ይሳደባል!!
በቀደሙት ዘመናት በአገራችን እናትና አባትን እንዲሁም ትልልቆችን ማክበር ባህልና እሴታችን ነበር። አሁን ጨርሶ ጠፍቷል ባልልም፣ እየጠፋ እንዳለ እሙን ነው። አንደኛው ምክንያቱ ምሳሌ የሚሆኑ አባትና እናት መብዛት እንዳለባቸው ያመላክታል። ግብረ ገብ ተብሎ በፊት በትምህርት የሚሰጠው ትምህርት ብዙዎቹን በስነ ምግባር የታነጹ እንዲያድጉ እንዳደረገ የታወቀ ነው። ሰው እግዚአብሔርን ካላስቀደመና ታላላቆቹን ካላከበረ ተማረም አልተማረም የህይወቱ ፍጻሜ አያምርም።
አሁን አሁን አዲሱ ትውልድ ደግሞ እናትና አባትን አለማክበር ብቻ ሳይሆን በዕድሜ ትላልቅ እንዲሁም በስራቸው ታላላቅ የሆኑትን ማክበርን እየረሳ እየመጣ ነው። ይህን በስርአቱ በማስተማር ረገድ ቤተሰቦች፣ መምህራን፣ ለአገር ታላላቅ ነገር ያበረከቱ ታላላቅ ሰዎችን፣ የቤተክርስቲያን አባቶችን እንዲያከብሩ ማስተማር ማህበረሰቡ ሐላፊነት የነበረበት ቢሆንም፣ አሁንም ይህ ትውልድ ነቅቶ ራሱን ማረም አለበት። መጽሐፍ ቅዱስ “አባትህንና እናትህን አክብር፤ እግዚአብሔር አምላክህ በሚሰጥህ ምድር ዕድሜህ እንዲረዝም።” ይለናል።
የምናፍራቸው አባቶች፣ ታላላቅ ሰዎች ያስፈልጉናል። ይህን ነገሬን ቢሰሙ ምን ይሉ ይሆን? ብለን የምናፍራቸው፣ የምንሰማቸው፣ የሚመክሩን ሰዎች ያስፈልጉናል። የምንገሰጽላቸው ታላላቅች ያስፈልጉናል፣ የምንሰማቸው ታላላቆች ያስፈልጉናል።
በሩቅ ምስራቅ "ሽማግሌ በእግዚአብሔር ይመሰላል" ይላሉ። ታላላቆች ህይወትን በብዙ መንገዴ አልፈው በትናንት ዛሬን ወልደው ትልውዱን እዚህ አድርሰዋል። በህንድ አገር ያለ ታላቅ ስርአት አለ። ይህውም እናትና አባታቸውን ታላላቅ ሰዎችን ዝቅ ብሎ እግር የመንካት ልምድ ነው። ይህ በእነርሱ ቋንቋ "አሺርቫት" ወይም "ምርቃት መቀበል" ይሉታል። ታላላቆች ላይ አፍን መክፈት ይቅርና አለማክበር በራሱ ክፍያ አለው። ሽማግሌዎች (አባቶች) አያጠፉም የሚል አመለካከት ባይኖረኝም፣ አይናቁም ወይም እነርሱን ከማክበር መጉደል የለብንም።
አባቶችም፣ መከበር በሚገባቸው መስመር መኖር እንዳለባቸው አምናለሁ። በአኪያሄዳቸው የማንከተላቸው አባቶች ቢኖሩ እንኳ፣ በአባትነታቸው (በሽምግልናቸው) መከበር አለባቸው።
አንዳንዴ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ቁጭ ብለው በዕድሜ የሸመገሉትን የሚዘረጥጡ፣ ብዙ አመት ያገለገሉት ላይ አፍ የሚያላቅቁን ሳይ ስለ ነገአቸው እፈራለሁ። አባትና እናትን ያለማክበር አደጋዎች ብዙ ናቸው። ከእነዚህ መሐል ሁለቱን ላንሳ፦ ያለ ማክበር አደጋዎችን ሳነሳ በማክበር ውስጥ ያለን በረከትና ተስፋ በተቃራኒው እንረዳለን።
፨ አጭር ዕድሜ (ያለ ጊዜ መሞት)
መጽሐፍ ቅዱስ በብሉይ ኪዳንም በአዲስ ኪዳንን መጻሕፍት ውስጥ ካስቀመጣቸው መሰረታዊ ህግጋት መሐል አባትና እናትን (በስጋም የወለዱንን እንዲሁም መንፈሳዊ አባቶችን) በማክበር ያሉትን መርህ ይናገራል።
እግዚአብሔር አስርቱን ትዕዛዛት ለሙ ሲጀምር የጀመረው በዚህ ወርቃማ መርህ ነው።
“አባትህንና እናትህን አክብር፤ እግዚአብሔር አምላክህ በሚሰጥህ ምድር ዕድሜህ እንዲረዝም።”
ዘጸአት 20፥12
“መልካም እንዲሆንልህ ዕድሜህም በምድር ላይ እንዲረዝም አባትህንና እናትህን አክብር፤ እርስዋም የተስፋ ቃል ያላት ፊተኛይቱ ትእዛዝ ናት።”
ኤፌሶን 6፥2-3
ከላይ ያየናቸው መጽሐፍ ቅዱሳዊ እውነት ይሰራል። ወጣቱ ትውልድ አባትና እናቱን ባለ መክበር የሚርስበት ነገር አንደኛው Premature Death ወይም "ያለ ጊዜው መሞት ነው። አባትና እናቱን የማከብር ልጅ እያድግም፣ አያፈራም። በምድር ላይ ላይ የምንኖረው ዕድሜ ፍሬያማና፣ ረጅም እንዲሆን አባትና እናትህን ማክበር መለኮታዊ ትዕዛዝ ነው።
፨በረከታቸው ያስፈልገናል!!
አባትና እናት ላይ እግዚአብሔር ስልጣን አስቀምጧል። አንደኛው ስልጣን የመባረክ ስልጣን ነው። ያዕቆብ "በዘመናችሁ የሚያገኛችሁን እነግራችሁ ዘንድ ተሰብሰቡ" አላቸው። ዘፍ 49:1 ተሰበሰቡም። ያዕቆብም በሁሉም ላይ የሚሆነውን ነገራቸው። እግዚአብሔር ነገአቸውን በያዕቆብ አፍ ሆኖ ለሁሉም ነገራቸው። ሁሉም ያዕቆብ ከነገራቸው ነገር ውጪ የተለየ የኖረ የለም።
በተጨማሪነት የያዕቆብንና የኤሳውንም የመባረክ ሒደት ስንመለከት ያዕቆብ በይስሐቅ በረከት እንዲባረክ ርብቃ ያደረገችበት መንገድ ከዚያም ኤሳው ሊባረክ ሲመጣ በረከቱ ወንድሙ መውሰዱን ስናይ በአባት ያለ በረከት የህይወታችን ፍጻሜ እንደሚወስነውና እንረዳለን። በአባቱ እና በእናቱ የተባረከ ትውልድ ብሩክ ነው። መንፈሳዊ አባትና እናት እግዚአብሔር ከሰጠን፣ እነርሱንም ማክበር እንዲያው ለበረከት ይዳርገናል። ሽበታሙንም ማክበር እንዲያው ከእግዚአብሔር ዘንድ ሞገስ ያሰጠናል።
.....
ዘሪሁን ግርማ
/channel/theideaofs
#ወይ_ምላስ!
ምላስ የስንቱን መንገድ አስቀየረ! የስንቱን ህይወት አጠፋ! ስንቱን በፍርሃት ወጥመድ ውስጥ ጣለ! የስንቱን መልካም ስም አጠለሸ! የስንቱን አገልግሎት አበላሸ! ምላስ። ስንቶች የሰዎችን ምላስ ፍራቻ የማይፈልጉትን፣ የማያምኑበትን ህይወት ሲኖሩ፣ የሚያምኑበትን ሲደብቁ አየን። ወይ ምላስ።
መጽሐፉ እንደሚል “አንደበትም እሳት ነው። አንደበት በብልቶቻችን መካከል ዓመፀኛ ዓለም ሆኖአል፤ ሥጋን ሁሉ ያሳድፋልና፥ የፍጥረትንም ሩጫ ያቃጥላል፥ በገሃነምም ይቃጠላል።”
ያዕቆብ 3፥6
አንደበት እሳት ነው ማለቱ የምናነገረው ነገር የሰዎችን ነገር ይበላል ማለቱ ነው። በሰዎች የምላስ አንደበት መገረፍ የህይወት ዘመን ፈሪ ያደርጋል። መጽሐፉ አንደበቱን የገዛ ሁለንተናውን የገዛ የበሰለ ሰው ያለው ያለ ምክንያት አይደለም። ስንታይ ጨዋና ትሁት የምንመስል ስንነካ፣ ከአንደበታችን ሰዶምና ገሞራን እናዘንባለን። አንደበቱን የገታ በሳል ሰው ነው።
ምላስ እኛም፣ ሰይጣንም፣ እግዚአብሔርም ይጠቀሙበታል።
በሌላ መልኩ ደግሞ ምላስ የብዙዎችን መንገድና ህይወት ያቀናል። መልካም ምክሮች፣ ጥበቦች፣ እውቀቶች፣ ፍቅር በረከትም በምላስ ላይ ናቸው። በምላስ ላይ በረከትም እርግማን፣ ፍቅርም ጥላቻም፣ ጥበብም ውድቀትም፣ ስንፍናም ትጋትም፣ ቅንነትም ጥመትም፣ መደገፍም መጣልም አሉ። ህይወታችንን የተከራየው የትኛው ይሆን? የሚያንጸው ወይስ የሚያፈርሰው?
ጌታ እግዚአብሔር ይርዳን፤ በጸጋው ይደግፈን።
ምንጭስ ከአንድ አፍ የሚጣፍጥንና የሚመርን ውኃ ያመነጫልን?
ያዕቆብ 3:11
..
ዘሪሁን ግርማ
/channel/theideaofs
What attracts God is not your speaking ability and activity, but the soundness of your heart (Motive).
Читать полностью…#የመሪ_ስነ_ምግባር
እግዚአብሔር ሁልጊዜ ለአገር ለቤተክርስቲያን ለቤተሰብ መሪን ይሰጣል። እግዚአብሔር መሪዎችን በመስጠት በረከትን ይሰጣል። እግዚአብሔር መሪዎችን በመስጠት የሚታወቅ አምላክ ነው። እግዚአብሔር ሲባርክህ ትክክለኛ መሪን ይሰጠናል። እግዚአብሔር የሚመራን በሚሰጠን መሪዎች ጭምር ነው። ጤናማ መሪ ያላት ቤተክርስቲያን እና ሃገር የተባረከች ናት።
መሪ የራሱ ስነ ምግባር አለው። መሪ ከእግዚአብሔር የተገኘ ምንም ቢሆን እንኳ መሪዎች ስነ ምግባር ሊኖረው ይገባል። መሪ የስነ ምግባር መርሆችን ካልተከተለ የሚመራው ተቋም ላይ መከፋፈልና፣ አለማደግን ይመጣል።
የመሪ ስነ ምግባር ከሌለ ውጤት የለም። በጸጋ ብቻ የሚመጡ ውጤቶች ዘላቂ አይሆኑም ጸጋውን ይዘን የምንቀጥልበት የበሰለ መሪነት ያስፈልገናል፣ ስነ ምግባር ከሌለ እውነተኛ ለውጥ የለም። መሪነት ከእግዚአብሔር የሚሰጥ ጸጋ ሲሆን፣ ራሳችን ላይ በመስራት የምናሳድገው ጭምር ነው። የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን አንደኛው ተግዳሮች በስነ ምግባር የታነጹ መሪዎች ጉድለት ነው። ስነ ምግባር ማለት እግዚአብሔር ለሰጠን የመሪነት አደራ ራሳችንን በእግዚአብሔር ቃልና በበሰለ አመራር የምናበቃት መንገድ ማለት ነው።
እንከን አልባ መሪ የለም። አይኖርምም። አንድ እንከን አልባ መሪ ኢየሱስ ብቻ ነው። ነገር ግን ዕለት ዕለት ራሳችን ላይ በመስራት በተሰጠንን አደራ ራሳችንን በማብቃት ከሰራን፤ ጥሪው ካለንና ጥሪያችንን ካሳደግን ውጤታማ መሪ እንሆናለን።
መሪ ስነ ምግባር አለው ስንል ከመሪ የሚጠበቁ መሰረታዊ ነገሮች አሉ ማለታችን ነው። መሪ ቀዳሚ እንደመሆኑ ምሳሌ መሆንና ለሚመራቸው ትክክለኛ መሪ መሆን አለበት። እስቲ በጥቂቱ የመሪ ስነ ምግባር የሆኑትን እንመልከት።
የመሪ ስነ ምግግባር
1፣ መሪ ይቅርታ አይራጊ ነው። መሪ ምሬትና ጥላቻ የተሞላ መሆን የለበትም። መሪ በተለያዩ ሰዎች ከቅርብም ከሩቅም፣ በውሸት፣ በመከዳት ጥለውት በሚሄዱ ሰዎች፣ በተለያዩ መንገድ ውስጥ ሊያልፍ ይችላል። መሪ በይቅርታ ለመመላለስ ራሱን ማዘጋጀት አለበት። መሪነት ሰዎች ብዙ በደል በመሪው ላይ የሚፈጽሙበት ስፍራ ነው፣ ይቅርታ ለማድረግ ካልፈቀደ መሪነቱን ቢለቅ ይሻለዋል። ስለዚህ ከመሪ መለየት የሌለበት ይቅርታ ማድረግ ነው።
2፣ አመስጋኞች መሆን አለብት። መሪ እግዚአብሔር ስለ ሰጠው ሰዎች፣ ስለ ተሰራው ስራ፣ በአገልግሎቱ ወይም በሚያስፈልገው ነገር አብረውት ስለቆሙ ሰዎች ተገቢ ምስጋና መስጠት አለበት፣ ከምንም በላይ አምላኩን አመስጋኝ መሆን አለብት። ማጉረምረምና መሳበብ መሞላትም የለበትም። ሰዎች ስላደሰጉለት ጥቂት ነገር አመስጋኝ የሆነ መሪ ውጤታማ መሪ ነው።
3፣ ትሁት መሆን አለበት። ከመሪ ህይወት የሚጠቀቀው ሌላኛው ነገር ትህትና ነው። ሁለቱ መሪዎች ማለትም ኢየሱስ እና ሙሴ ትሁቶች ነበሩ። ትህትና ለመሪነትን ሞገስ የሚጨምር በንግግር እና በስብከት ብቻ የማይገለጥ ነገር ግን በመኖር የሚታይ ህይወት ነው ትህትና። እግዚአብሔር ትሁት መሪዎችን ይስጠን።
4፣ አማኝ መሆን መቻል አለበት። መሪ በምንም መንገድ ውስጥ ቢያልፍ በእግዚአብሔር ማመን እና ለሚመራቸው እምነቱን ማጋራት አለበት። መሪው ያላመነውን ነገር ሌላው እንዲያምነው አይጠበቅም። ማለትም መሪው ያልኖረውን ህይወት ሌሎች እንዲኖሩት ግድ አይባልም።
5፣ የጸሎት ሰው መሆን አለበት። መንፈሳዊ መሪ የጸሎት ሰው፣ የራሱም ለሚመራት ቤተ ክርስቲያን እና ለምዕመናን፣ ለአገልግሎቱ ጭምር የሚጸልይ መሆን አለበት። መሪ የምዕመኖቹን መንፈሳዊ ህይወት በጸሎት ወደ እግዚአብሔር የሚያቀርብ፣ በድምጽ ምዕመናኑን የሚመራ ነው። የማይጸልይ መሪ አገልግሎቱን በትግልና በሰው ምድራዊ ጥበብ ይመራል።
6፣ መሪ ሰጪ ነው። የመጽሐፍ ቅዱሱ መሪ የምናውቀው ሰጪ ነው። ንፉግነት የመሪ መገለጫ አይደለም። መሪ ገንዘቡን፣ ጊዜውን ያለውን ነገር ሁሉ የሚሰጥ ነው። መቀበል ላይ የተመሰረተ አስተምህሮ መጽሐፍ ቅዱሳዊ አይደለም፣ በመስጠት ውስጥ ያለ መቀበል እንጂ። መሪ ሰጪ ሲሆን እግዚአብሔር በሚሰጡት ሰዎች ይባርከዋል።
7፣ መሪ ትጉህ ነው!! መሪ ብሎ ሰነፍ ከሆነ አረም የሞላበት ተክል የሚጠብቅን ጠባቂ ይመስላል። መሪ ትጉህ ካልሆነ በመንጋው መካከል፣ አረም፣ ያልተገባ ነገር ይኖራል። ስንፍና ምንባቸው ይሆናል። ምክንያት እየፈጠረ ከሐላፊነት የሚሸሽ መሪ አይደለም። መሪ ትጉህ ነው፣ በተሰጠው ነገር በመትጋፍ ፍሬያማ ነው። የመሪ ሐብቱ ያቀደውን ነገር ለማስፈጸም መትጋቱ ነው። ምክንያት ደርዳሪነትና ስንፍና የመሪ መገለጫዎች አይደሉም።
8፣ መሪ የፍቅር ሰው ነው። መሪ የፍቅር ሰው መሆን ይጠበቅበታል። መንፈሳዊ መሪ ሲሆን ደግሞ ዋናው መሪ ኢየሱስ የፍቅር ሰው እንደ መሆኑ የእርሱ ፈለግ የተከተለ መሪ መሆን አለበት። መሪ ሁሉም ሰው ሊወደው አይችልም፣
ነገር ግን ሁሉን የመውደድ ግዴታ ግን አለብን። መሪ ከፍቅር ከጎደለ አመራሩ ሁሉ የወደቀ ይሆናል። የመሪነት ዋነኛው ቁልፉ ፍቅር ነው።
9. ሌሎችን የሚያነሳሳ ነው። መሪ የሚመራቸውን አካላት ለተሻለ ስራና አገልግሎት የሚያነሳሳ መሆን አለበት። ሌሎች መሪዎች ወደ መሪነት እንዲመጡ የሚያነሳሳ፣ ምዕመናኑን ለተለያዩ መንፈሳዊ ሐላፊነቶች እንዲበቁ የሚያነሳሳ መሆን አለበት። ትክክለኛ መሪ ሌሎች ለስራ ሲነሳሱ ደስተኛ ነው።
10፣ መሪ ሌሎችን አክባሪ ነው!! የማያከብር ሰው አይከብርም፣ ሌሎችን የሚያጣጥልና የሚያናንቅ መሪ ነገ በተከታዮቹ ያ ዕጣ ይደርሰዋል። መሪ የሚቀበለው ሁሌም የሰጠውን ነውና። ሰዎችን ባወቅን ቁጥር ማክበር ይበልጣል። ማክበር የመሪ ባህሪ ነው። የሚያከብር መሪ የሚከባበሩና፣ የሚያከብሩት ምዕመናንን ያበዛል። አገልጋዮችን ላይ የሚቀልዱ፣ በመንፈሳዊ ነገር የሚሳለቁ መሪዎች ልቅ ትውልድ ያፈራሉ። መሪ አክባሪ ነው።
11፣ መሪ መልካም ምክር ሰጪም ተቀባይም ነው። መሪ ለሚመራቸው መልካም ምክርን ይሰጣል። ምክርን በተገቢው ቦታ ለተገቢው ሰው ይሰጣል። ከሌሎች ምክርን ይቀበላል። ምክርን ላለመቀበል ግትር አይደለም። ጠቃሚ ምክሮችን ለመቀበል ትሁት ነው።
12 መሪ ገበና ሸፋኝ ነው!! መሪ በሚመራቸው ምዕመናን ህይወት የሰማውን ነገር ለስብከት ማጣፈጫ አያደርግም፣ ለሌሎች ለማይመለከታቸው የሰዎችን ማንኛውን ገመና አደባባይ አያሰጣል። መሪ ገመና ሸፋኝ ነው።
13, መሪ አንባቢ ነው፣ መሪ ራሱን ላይ በንባብ እና በትምህርት የሚሰራ ነው። ትናንት የተረዳውን ሰምቶ የመጣን ትውልድ የትናንቱን ስብከት በመደጋገም አያጸናውም። ከዚያ ይልቅ ቃሉን ያነባል ይቆፍራል። ያስተምራል፣ ይመራል።
/channel/theideaofs
ቀኖችን ፈጥሮ የሰጠን፣ ዘመናትን ያቀዳጀው እርሱ እግዚአብሔር ነው። በቀኖቹ ስንሰራባቸው እንለወጥባቸዋለን፣ ቀኖቹ ላይ ካልሰራንባቸው ቀኖቹ በላያችን ላይ ይለዋወጣሉ። በ 2017 ምን ብንጨምር ወይም ብንተው የምንላቸው ነገሮችን ምን ይሆኑ ብዬ ከራሴ ያወራሁትን ላጋራችሁ፤ እግዚአብሔር ዘመንና ጊዜን ከሰጠን አይቀር፣ መጨመር ያለብን፦
፨ እግዚአብሔር በሰጠን ዕድል ሁሉ አመስጋኝ መሆንን፣
፨ ባለራዕይነትንና ትጋትን፣ ራስ ላይ መስራት
፨ ፍቅርንና አብሮሰራተኝነትን
፨ መልካምነትንና ካለን ማካፈልን
፨ የሰዎችን ዋጋ መረዳትንና ማክበርን
፨ ቅንነትንና እውነተኛነትን
፨ አገልጋይነትና ጽናትን
፨ ሰላም ወዳድነት በሰላም መኖርን
መተው ያለብን
፨ አስመሳይነትና ሽንገላን
፨ ስንፍንና ማመካኘትን
፨ ጥላቻና ግለኝነትን
፨ ከልክ ያለፈ ራስ ወዳድነት
፨ ጥቅመኝነትና ብልጣብልጥነት
፨ ሁከትንና ሰላም ጠልነትን
፨ እኔነትና (Ego) ስሜታዊነትን
ቀኖች ልክ እንደ ደም ጠብታ ናቸው፣ ጊዜያቶች ሁልጊዜም ውድ ስጦታዎች ናቸው። ራሳችን ላይ ስንሰራባቸው ቀኖችና አመታት የእኛ ሜዳ ይሆናል። እናንተም ብንጨምር ወይም ብንተዋቸው የምትሉትን ሐሳብ አካፍሉን። ለሁላችሁም መልካምና የበረከት አመት ይሁንላችሁ። ብሩክ 2017።
ዘሪሁን ግርማ
/channel/theideaofs
#አውቆ_የተኛን.........
አንድ ልጅ ሞቻለሁ ብሎ ያምን ነበር። ብዙ ሰዎችን "በህይወት አለህ አልሞትክም እኮ" ይሉታል። እሱ ግን "በህይወት የለውም ሞቻለሁ" ይላል። ከዚያው እንዲታይ ወደ ዶክተር ጋር ወሰዱት ዶክተሩም በምን ሊያስረዳው እያሰበ ቆየና "አንተ አልሞትክም በህይወት አለህ" አለው ወጣቱ ልጅም "የለም ሞቻለሁ"። ይላል ከዚያም ዶክተሩ "እንዳልሞትክ ላሳይህ የሞተ ሰው ደም የለውም አንተ ግን በህይወት ስላለህ ደም አለህ" ብሎ በመርፌ ወግቶ ደሙን ሲያሳየው ልጁም "ለካ የሞተ ሰው ደም አለው" ብሎት እርፍ።
(ታሪኩን ያጫወተኝ አንድ ወዳጄ ነው😀)
አንዳንድ ሰው አንተ የምትለው ይገባዋል ግን እሱ የሚለውን አይለቅም ከዚያም አልፎ ያንን ሐሳብ ያሰበበት ጉዳይ እስኪፈጸም ድረስ ምንም ብታስረዳውና የምታስረዳው ምንም እውነት ቢሆን እንኳ ሊቀበልህ አይፈልግ። ይህን አይነቱን ሰው አባቶቻችን "አውቆ የተኛን ቢቀሰቅሱት አይነሳም" ይላሉ ውሃ ካልደፉበት በቀር😀
እየገባን እንዲገባን የማፈልግ ከሆነ እና የሚነገረንን እውነት እኛ አስቀድመን በያዝነው ውሸት ምክንያት የምንገፋ ከሆነ እና 'በህይወት አለህ ስንባል' 'የለሁም' ለማለት "የሞተ ሰው ደም አለው" የሚል ትምህርት የምንፈጥር ከሆነ በምንም የማንማር፣ የማንለወጥ ከሰማነው እውነት ይልቅ የተሸከምነው ወሸት ይግደለን ብለን የወሰንን ነን።
©ዘሪሁን ግርማ
/channel/theideaofs
ሁሉም ሰው እንዲቀበልህ ማድረግ አትችልም፣ ሁሉም ሰው እንዲወድህ ማድረግ አትችልም፣ ትክክለኛውን ነገር እያደረክ እንኳ። ሐይልህን ሰዎች እንዲቀበሉህ በመታገል አትጨርስ!! ይህ የህይወት አድካሚው መንገድ ነው። ይልቅ ከራስህ ጋር ተስማማ፣ የመረጠህ አብሮ ይጓዛል፣ የማልፈልግ ይለይሃል። እነዚህ ሁለት የህይወት መንገዶች ናቸው። አንተ ብቻ ከራስህ ጋር ተስማማ።
/channel/theideaofs
ቀናችሁን አታስወስዱ
ሁልጊዜ ብዙዎቻችን ቀኖቻችንን ወይ በትናንት ተጽእኖ፣ ወይ ደግሞ በነገ ፍርሃት እንነጠቃለን። የትናንት ተጽዕኖና ነገን አስመልክቶ ባለ ፍርሃት ውስጥ ስንኖር ዛሬን እንነጠቃለን። ያለን ዛሬ ብቻ ነው፣ የምናውቀውም አሁን ምን ማድረግ እንዳለብን ብቻ ነው ስለ ቀናችን ሁሉ እንኳን ብዙ ላናውቅ እንችላለን፣ በእጃችን ያለው አሁን ነው ማለት አሁን ላይ አትኩሮት አድርገን አንስራ። በእግዚአብሔር እና በሰጠን ቀን ደስተኛ እንሁን።
ስለ ትናንት አትዘን ምንም ይሁን ምን እግዚአብሔር አሳልፎህ እዚህ ደርሰሃልና፣ ስለ ነገም አትጨነቅ ነገን የሚያውቅ እግዚአብሔር ብቻ ነውና፣ ስለ ዛሬህ አመስግን።
ብሩክ ቀን ይሁንላችሁ!!
ዘሪሁን ግርማ
/channel/theideaofs
#የበላን_ያላበላነው_ነው!!
"የበላን ያላበላነው ነው።"
ገጣሚ ታገል ሰይፉ
ትውልድ ይሄዳል ትውልድ ይተካል። ቀዳሚው ትውልድ በቀጣዩ ትውልድ የራሱ የሆነ አሉታዊና አዎንታዊ ተጽዕኖ አለው። የቀደመው ትውልድ ያልሰራበት የመጣው ትውልድ የራሱን መንገድ ለመፍጠር ይገደዳል። የተሰጠው ከሌለ ወይ የራሱን በመሰለው ይገነባል፣ ወይም ደግሞ በተሳሳተ መንገድ ነገሮችን ይገነባል።
ቀድመው ተገቢውን ምግብ ያልሰጠነው ልጅ አድጎ ሲመጣ የሚመግበን በመንገድ ላይ የተመገበውን ምግብ ነው። ለዚህ ነው ቀድመን ትውልድ ላይ መስራት የሚገባን፣ በቤተ ክርስቲያንም፣ በአገርም አሁን ያለው መልክ የመጣው ቀድመን ማብላት ያለብንን ነገር ያላበላነው ነው።
አሁንም ትውልዳችንን ምን መመገብ እንዳለብን ወይም ምን እየመገነው እንዳለ ማወቅና መረዳት ያስፈልጋል። እኛ ያላበላነው፣ ያልሰራንበት፣ ያላበላነው ምንንና ማንን እንደሚበላ ማወቅ አለብን። እንደ አገርም እንደ ቤተ ክርስቲያንም ይህ ችግር ችግራችም አይመስላችሁንም? ትውልድን ምን መመገብ እንዳለብን እስካልተረዳን ያልመገብነው ትውልድ ቦታውን ሲይዝ እኛኑ የሚያጠፋ እንዳይሆን እርግጠኞች አይደለንም።
ትውልድን እንመግብ!!
ዘሪሁን ግርማ
ጥሪ የሌለው እርሱ በፍፁም አይረዳውም🙏 🤍
በ ቭላድሚር ሳይመን
ትርጉም:- ኢያሱ ሲሳይ
ቢሾፕ ቲዲ ጄክስ ለመንፈሳዊ ልጁ ስቴቨን ፈርቲክ ስለ አገልግሎት ትግል የመከረው ምክር ።
መምራት ከባድ ነው
1 -ከቤተሰቦችህ መተዳደሪያ ገንዘብ ወስደህ ወደ ቤተክርስቲያን ስራ እንድታውል ትገደዳለህ።
2- የምትከፍለው ገንዘቡ ከየት እንደሚመጣ ሳታውቅ መከፈል ያለባቸውን ነገሮች (ዕዳዎች) እንዲከፈሉ ሀላፊነቱን ትወስዳለህ
3- ከቤተሰቦችህ ጋር ማሳለፍ የሚገባህን ጊዜ ቸርች ውስጥ በማሳለፍ ዋጋ ትከፍላለህ።
4- የንተ ነገር ግን ደህና ሳይሆን የሌሎች ሰዎች ነገር ደህና እንዲሆን ለመስበክ ጠንካራ መሆን አለብህ።
5-ያንተን ችግር እግዚአብሔር ገና ሳይፈታው እግዚአብሔር ችግሮቻችሁን ይፈታል ብለህ ለመስበክ ጠንካራ መሆን አለበህ።
6-የረዳሀቸው ሰዎች ይክዱሀል።
7-መቼም ካንተ እንደማይለዩ የማሉልህ ሰዎች ትተውህ ይሄዳሉ።
8-በሌሎች ሰዎች ተመርዘው ሰዎች ላንተ ያላቸውን አክብሮት ሲያቆሙ ታያለህ
9-ከፊትህ አባቴ እያሉ ነገር ግን ከጀርባህ ግን ላንተ አክብሮት የሌላቸውን አስመሳይ ሰዎች ትመከታለህ።
10-አንዳንድ ሰዎች ስብከትህን በተሳሳተ መንገድ ቀጥተኛ እንዳለሆነ ይተረጉሙታል።
11-ሚስትህን እና ቤተሰብህን የማያከብሩ ሰዎችን ታያለህ።
12-ያለህ ንብረት ወይም ንግድ ምንጩ ከቸርች የወሰድከው እንደሆነ አስመስለው ጥያቄ እንዲነሳ የሚያደርጉ ሰዎችን ታያለህ።
13-አንዳንድ ሰዎች ከቸርች ሲለቁ ስላንተ ታሪክ ይፈጥራሉ።
14- አንዳንድ ዕድል የሰጣሀቸው ሰወች ራዕይህን ያጣጥላሉ።
15- አንተ ያሰለጠንካቸው ሰዎች በውይይቶች ላይ ትክክል እንዳልሆንክ እኑሱን እንድትሰማቸው ሊያሳምኑህ ይሞክራሉ።
16-አንዳንዶች እንዲሰብኩ አበረታትሀቸው ነገር ግን በሗላ ላይ የነሱን ስብከት ካንተ ጋር ያወዳድራሉ።
17- አንዳንድ ሰዎች ጭንቀት ውስጥ እንደሆንክ እና ትኩረት ማድረግ እንዳቃተህ ያስባሉ።
18- አንዳንድ ሰዎች ካንተ የተሻሉ መንፈሳዊ እንደሆነ እና የተሻለ ዕውቀት እንዳላቸው ያስባሉ።
19-አንዳንድ ሰዎች ሌሎች ላንተ ያላቸውን አክብሮት እንዲቀይሩ መጥፎ ሰው ነው እንዲሉ ተፅዕኖ ያደርጉባቸዋል።
20-ሌሎች ምስጋናቢስ ይሆናሉ ለሰጠሀቸው ዕድሎች ምንም ዕውቅና አይሰጡም ።
21-አንዳንዶች ቸርችን መከፋፈል ይፈልጋሉ።
22-አንዳንዶች ላንተ ምንም አክብሮት የላቸውም ግራ መጋባትን እየፈጠሩ ችግሮችን እየፈጠሩ አንተን እየወነጀሉ እነሱ ተጠቂ እንደሆኑ ያስባሉ ።
በአገልግሎት ውስጥ ያላችሁ ይህንን መረዳት ይገባችኋል ..
#አሳራፊ_ያድርጋችሁ፣ #የሚያሳርፏችሁን_ይስጣችሁ!!
እግዚአብሔር እነዚህን ሁለት በረክቶች በህይወታችን ያብዛልን። አንደኛው በረከት የብዙዎችን ልብ የሚያሳርፍ ሰው እንዲደርገን ሲሆን፣ ሁለተኛው ደግሞ የሚሳርፉንን ሰዎች እንዲያበዛልን ነው። ሰው በእነዚህ ሁለት በረከትቶች እግዚአብሔር ከባረከው በእርግጥም የተባረከ ነው። ማረፍ ማለትም ከመልዕክቴ አንጻር ቅዱሳን በህይወቱ የሚያምኑበት፣ የሚደሰቱበትና፣ ተስፋ የሚጥሉበት፣ የእግዚአብሔር ሐሳብና ቅዱሳንን ለማገልገል ራሱን ያዘጋጀ ብለን ልንተረጉመው እንችላለን።
ለሰዎች እረፍት መሆን በእግዚአብሔር የመባረክ ውጤት ነው። የሰዎች ልብ በእኛ ካረፈና ከተባረከ ለእኛም እግዚአብሔር የሚያሳርፉንን ሰዎች ይስጠን። ማሳረፍ ማለት ለሰዎች በተገቢው ጊዜ ተገኝቶ ከእግዚአብሔር ለጠየቁት ጥያቄ መልስ በእናንተ በኩል ሲሰጥ ማለት ነው። ሐዋሪያው ጳውሎስ በፊሊሞና መልዕክት ውስጥ ለፊሊሞና ይህን መልዕክት ጽፎለት ነበር።
“የቅዱሳን ልብ በአንተ ስራ ስለ ዐረፈ፥ ወንድሜ ሆይ፥ በፍቅርህ ብዙ ደስታንና መጽናናትን አግኝቼአለሁና።”
ፊልሞና 1፥7
በፊሊሞና አገልግሎት ብዙ ቅዱሳኖች አርፈው ነበር።
ሐዋሪያው ጳውሎስ ስለ ሄኔሲሮሩ ቤተ ሰዎች እንዲህ የሚል መልዕክት ጽፏል። የጳውሎስን ሐሳብ በሁለት መንገድ ልንመለከተው እንችላለን። የመጀመሪያው ብዙ ጊዜ እነርሱ ቤት አርፏል፣ ሁለተኛው ደግሞ በአገልግሎቱ ብዙ በተለያዩ መንገዶች ለሐዋርያው ጳውሎስ ዕረፍት ሆነውለናታል ማለት ነው።
“ጌታ ለሄኔሲፎሩ ቤተ ሰዎች ምሕረትን ይስጥ፥ ብዙ ጊዜ አሳርፎኛልና፤”
2ኛ ጢሞቴዎስ 1፥16
እግዚአብሔር በተለያዩ ነገሮቻችሁ ልባችሁ የሚያርበትን ሰዎች ይስጣችሁ፣ እናንተንም ለብዙዎች እረፍት ምክንያት ያድርጋችሁ።
ዘሪሁን ግርማ
/channel/theideaofs
#ባጣሁት_ሳይሆን_ፈልጌ_በጣልኩት_ነገር_አታስቀኑኝም!
ድሮ ድሮ የሚባሉ እንዳንድ አባባሎች ነበሩ የመጀመሪያው "ቆራጴ" ነው ይባላል ቆራጥ ጴንጤ ነው ማለት ነው። ሁለተኛው "አራጴ" አራዳ ጴንጤ ማለት ነው። ሶስተኛው "ግራጴ" ግራ የተጋባ ጴንጤ ማለት ነው።
የቤተክርስቲያን መልክ እያደበሱ ካሉ ነገሮች መሐል ክርስትናን እና አለማዊነትን ለማጋባት የሚደረገው የቅልቅል መንገድ ይመስለኛል። ቤተ ክርስቲያን ከክርስቶስ ኢየሱስ የተቀበለቸውን ንጹህ መንገድ ይዛ የተሰጣትን የወንጌል አደራ በምድር እንድትፈጽም ተጠርታለች። አሁን አሁን አንዳንድ አገልጋዮች በአለም ተትቶ የተመጣውን ኮተት ወደ ቤተክርስቲያን በማስገባት የ "አራጴ" አራዳ ጴንጤ ተግባር ሲያራምዱ ይገርመኛል።
ፈልገን አተነው ሳይሆን እኛ አንፈልገውም ብለን ንቀን የጣልነውን ነገር አንስቶ ማንም አያስቀናንም። ለክርስቶስ ወንጌል በአለም ያለን አለማዊነትን እንደ ጉድፍ ንቀን መተን ያንን ተሸክመው በሚመላለሱ ሰዎች እንዴት እንቀናለን? ያሳዝኑናል እንጂ እናፍራለን እንጂ። በዚህ ዘመን አለማዊነትንና-ክርስትናን የምንለይበት ቀዩ መስመር እየጠፋ እንደሆነ ይታያል። መጽሐፍ ቅዱሳዊ መመሪያዎችን፣ የክርስትና ውበቶቻችንን፤ የአስተሳሰብ ንጽህናችን፣ መንፈሳዊነታችን አጥብቀን መጠበቅ ያለብን ጊዜ ይህ ነው። ውጪ የጣልነውን አለማዊነት ይዘው ከክርስትና ጋር አጋብተው የሚሄዱን ልናስተምር፣ ልናርምና ልንገስጽ ይገባል። አለም ላይ ያለን አራዳ አራዳ ጨዋታ በጌታ መንግስት መጫወት የመንግስቱ ስርአት አይፈቅድም።
የወንጌልን እና የጽድቅን መንገድ የጣለ አለማዊነት፤ መንፈሳዊነትን ያላማከለ ዘመናዊነት፤ ክርስትናን ከአለም ጋር ለማጋባት የሚደረግ ጥረት በሙሉ በዚህ ጊዜ ያለችው ቤተክርስቲያን ተግዳሮት ነው። ጥለነው በመጣነው ነገር አንቀናም፤ ከዚያ ይልቅ በዚህ አለም ሰዎች "ፋራ" ተብለው ወንጌልን በያዙ፤ የእግዚአብሔር መንግሥት ለማስፋት በሚተጉ፤ ጽድቅንና ቅድስናን የዳኑበት ኑሮ መሆኑን የተረዱ፤ በሰው አለም "የዘገዩ" "ያልነቁ" "ሞኝ" የተባሉ፤ በሰማዩ ርስት የሚመዘገብ ስራ ባላቸው ጀግና የክርስቶስ ደቀ መዝሙሮች እና አገልጋዮች እንማረካለን፤ ደስ ይለናል፤ እንባረካለን። አራጴዎች ሆይ እባካችሁ ቆራጴ እንሁን!!
....
የቴሌግራም ቻናሌን ይቀላቀሉ
ዘሪሁን ግርማ
/channel/theideaofs
#የመሻሸቂያ "ወንጌል" የለም!!
መድረኮቻችን ወንጌል ተኮር ከመሆን ይልቅ ለተለያዩ ሰዎች የመልስ ምት ማስተላለፊያ እየሆኑ ከመጡ እየሰነበቱ ነው። ምስባኩ የወንጌል፣ አላማውም ቅዱሳንን ለማነጽ መሆን ተገብቶት ሳለ፣ አንደኛው ለአንደኛው አገልጋይ፣ አንደኛው አገልጋይ የሌላኛውን ስም ማጠልሻ መንገድ እየሆኑ ነው። ስጋ ስጋ የሚሸቱ ትምህርቶችና እንቅስቃሴዎች በግልጽ በየ ምስባኩ ይገለጣሉ።
በተለያየ የህይወት ምዕራፍ እያለፈ ያለው ምዕመን እግዚአብሔር በቃሉ ቢናገረኝ፤ ከዚህ ህይወቴ የምሻገርበት የእግዚአብሔርን ጸጋ እካፈላለሁ ብሎ ወደ ጉባኤ ሲገባ፣ እርሱ በማያውቀው ጦርነት መድረኩ ተሞልቶ ይጠብቀዋል። የመበሻሸቂያ ስብከት ብቻ ሳይሆን የማብሸቂያ መዝሙሮች፣ ጸሎቶችና አዋጆች ጭምር መድረኮች ማየት ጀምረናል።
ምስባኩ የእግዚአብሔር ነው፣ እጅግም የከበረ ስፍራ ነው። ብዙ ጊዜ የእግዚአብሔር ቃል እጥረት (ድርቀት) ሲኖረን፣ ወይም ከሌሎች ጋር ፉክክር እና መገፋፋት ሲኖር የውድድር "ስብከት" በተለያዩ መንገዶች ይተላለፋል። ወደ መድረክ ለመስበክ ከመውጣታችን በፊት የዝግጅትና የጸሎት ጊዜ፤ የእግዚአብሔርን መንፈስ ምሪት የማዳመጥ ጊዜ፣ ለጉባኤው ለመጣው ህዝብ የእረፍትና የመመለስ መልዕክቶች ለማስተላለፍ በተቻለው መጠን ራስን ማዘጋጀት ያስፈልጋል።
የምንመራው ህዝብ ለእኛ የግል ጦርነት መሳሪያ ማድረግ እጅግ ታሪካዊ ክስተት ነው። አንዱ በመድረክ ቆሞ የሚናገረው ነገር ለማን እንደሆነ ግልጽ በሆነ መልኩ ሲተላለፍ ይታያል። ምዕመኑም በግልጽ እስኪያውቅ ድረስ። ያ ጉዳይ ለምዕመናኑ ምንም ፋይዳ የለውም።
እውነት ለመነጋገር የተለየ ጥቅም ከሌለ በቀር አንዳንዶች ለምን እንደሚገፋፉ መረዳቱ ራሱ ይገመርኛል። ሁሉም በተሰጠው ስፍራ የተሰጠውን የእግዚአብሔር አደራ መልዕክት ማስተላለፍ ሲገባ ምስባኩን ሰው ሰው የሚሸት መንፈስ ቅዱስ የሌለበት ከማድረግ ልንቆጠብ ንስሐ ልንገባም ጭምር ያስፈልገናል። መልዕክት ከሌለን የግድ መጨነቅ እኮ የለብንም መድረኩን በትክክል ለሚያገለግሉ ማስተላለፍ ይቻላል።
ይህ አይነቱ ችግር እያደገና እየሰፋ አንዱ ከአንዱ በሚኖረው የግል ጦርነት ውስጥ ሌሎች የሚመስሉትን አገልጋዮች በመፈለግ የራሱን ጎራ ለማደራጀት ይጠቀማል። ጎራና ግለኝነት እነዚህ ሁለቱ የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ችግሮች እየሆኑ ነው።
በቅንነት ለመናገር ያህል እነዚህ ነጥቦችን ብናስተውላቸው መልካም ነው
፨ መድረኩ የእግዚአብሔር ከሆነ ህዝቡም የእግዚአብሔር ነው!!
፨ የተሰጠን ህዝብ የእግዚአብሔር አደራ ነው!
፨ የተሰጠን መድረክ የእግዚአብሔር ወንጌል ለመስበክ ታላቅ እድል ነው!
፨ ብዙ ምዕመን በብዙ ችግር ውስጥ እያለፈ ወደ ቤተክርስቲያን ሲመጣ ካለበት ነገር የሚያወጣው መልዕክት ይፈልጋል (ያስፈልገዋልም)
፨ በየ መድረኮቻችን የምንናገረው ነገሮች በእግዚአብሔር ፊት የሚያስጠይቁን ናቸው
፨ አለማዊነትና ስጋዊነት በውጪ ሞልቶ ሳለ ህዝቡ የእግዚአብሔር የሆነን ነገር ከቤቱ ለማግኘት ፈልጎ ይመጣል።
ስለዚህ በየ ምስባኮቻችን ላይ ቃሉን እንስበክ እናስተምር፣ መበሻሸቂያና ሌሎች አገልጋዮችን መቃወሚያ ጥቅስ አይጠቀም። በሾርኔም በእግዚአብሔር መድረክ ሰዎችን አንማ።
.....
ዘሪሁን ግርማ
/channel/theideaofs
Surround yourself with people whose eyes light up When see you coming
አንተን ሲያዩ ደስ በሚላቸው ሰዎች ራስህን ክበብ!!
በሰዎች መከናወን ስትቀናና ስትናደድ በረከትህ ይያዛል፣ በሰዎች መከናወን ደስ ሲልህ እግዚአብሔር ይባርክሃል። የሰዎች ክንውን የአንተን መንገድ በምንም መልኩ ሊዘጋው አይችልም። በሰዎች ደስታ ውስጥ የአንተን ደስታ ተመልከት፤ በአንተ ደስታ ውስጥ እግዚአብሔር እንዲከብር። ይህን የህይወት ዘመንህ መርህ ስታደርገው በሁሉም ነገሮችህ ሞገስ ይሆንልሃል።
/channel/theideaofs
#ዋጋችን_በተገኘንበት_ቦታ_ይወሰናል!!
አባት ለሴት ልጁ እንዲህ አላት "በክብር ከዩንቨርስቲ ከተመረቅሽ ለብዙ አመታት ያስቀመጥኳት መኪና አለችን የብዙ አመታት ዕድሜ ያላት ለአንቺ እሰጥሻለሁ። ለአንቺ ከመስጠቴ በፊቴ ወደ ዳውንታውን ውሰጅና ስንት እንደምታወጣ ጠይቂያቸው" አላት።
ልጅቷ የአባቷን ቃል ሰምታ ወደ አንድ መኪና መሸጫ ወሰደችው ተመልሳም ለአባቷ "$1000 ብር ገመቱልኝ አለችው።" አባትየውም ወደ ሌላ የመኪና መሸጫ ውሰጂው አላት። ልጅቷም አባትየው "መኪናዋ አሮጌና ያረጀች ስለሆነች $100 አሉኝ" አለችው።
በመጨረሻም አባትየው "ወደ ቆዩት መኪና ማሳያ (Car Club) ውሰጂው" አላት። ወሰደችው ሰዎቹም "$100.000 ገመቱልኝ ይህች Nissan Skyline R34, መኪና ታሪካዊ መኪና ናት ብለው።" አለችው። አባትየውም ልጁ እንዲህ አለት "ትክክለኛ ቦታሽ ትክክለኛ ዋጋሽን ያሰጥሻል። ሰዎች ትክክለኛ ዋጋ ካልሰጡሽ አትናደጁ በትክክለኛው ቦታ አይደለሽም ማለት ነው። ዋጋሽን የሚያውቁ ያከብሩሻል። መርሳት የሌለብሽ ሁሌም ለአንቺ ዋጋ (value) ከማይሰጡ ሰዎች ጋር መቼም እንዳሆኚ።" አላት። ዋጋችን ባለን ነገር ብቻ ሳይሆን ባለንበትም ቦታ ጭምር ይወሰናል። ምን ይዘን የት ነን?
የምትሰጣቸውን ፍቅር ከሚያጣጥሉ፤ ቅን ስትሆን እንደ ሞኝ ከሚቆጥሩህ፤ በውስጥህ ያለውን ህልም ከሚያጣጥሉ ትልቅ ነገር በውስጥህ እያለ እንደ ምንም በሚቆጥሩህ ሰዎች ዘንድ አትገኝ። አንተ የሆንከውን እንጂ ያልሆንከውን እንድትሆንና ያለቦታህ ከሚመድቡህ ሰዎች ዘንድ አትገኝ። ቦታህ የት ነው በቦታህ ሁን። ዛሬ ምንም የሌለው ቢመስልህ እንኳ ማፍራቱ አይቀርም። ምን ይዘን የት ነን?
/channel/theideaofs
#አዲስ_አመትና_የእቅዶቻችን_ነገር......
"ከዚህ በፊት ያልነበረህን ነገር ለማግኘት ከዚህ በፊት አድርገህ የማታውቀውን ነገር ማድረግ አለብህ።"
ዴንዚል ዋሽንግተን
አዲስ አመት ሲመጣ ብዙ ሰው ያቅዳል "በዚህ አመት እንዲህ አደርጋለሁ" "እማራለሁ" "ስራ ቀይራለሁ" "አገልግሎቴን አሰፋለሁ" "አገባለሁ" "ይህን እተዋለሁ" "ይህን ጨምራለሁ" እያልን አዲስ አመት በመጣ ቁጥር ብዙ እናስባለን እናቅዳለንም። ማቀድ ጥሩ ነው። ዘመናችን በሁለት ነገሮች እጅ ናቸው የመጀመሪያው በእግዚአብሔር እጅ ሲሆን ሁለተኛው በእኛ እጅ ነው። በእቅዶቻችንን የእግዚአብሔር እጅ እና ጣልቃ ገብነት፤ ምሪትና እርዳታው ያስፈልገናል። እግዚአብሔር አንዳንዴ ባላቀድነው በረከት ሊባርከን እንደሚችል ባምንም ህይወታችን ግን በራዕይ በእቅድ እንዲሆን ይፈልጋል።
እቅድን በተመለከተ በየአመቱ አቅደን ከነበረና በህይወታችን ምንም ለውጥ ካላየን ባቀድነው እቅድ መጠን አልሰራንም ማለት ነው። አሁን ባለንበት የህይወት እንቅስቃሴ ውስጥ ምንም የተለየ እንቅሰቃሴ ሳናደርግ ምንም የተለየ ውጤት አናገኝም። እቅድ ካወጣህ ከዚህ በፊት በነበረህ አረዳመድህ አሁን ካለህበት የተሻለ ህይወት ሊኖርህ አይችልም። ከቀድሞ የተለየ አኪያሄድ ካልተራመድክ አሁን ካለህ የተሻለ ውጤት አይኖርም። እቅድ ካወጣህ እቅድህ የሚፈልገው አይነት እንቅስቃሴ ማድረግ ይጠበቅብሃል።
የማትተገብረው እቅድ ስላቀድከው ብቻ ምንም ለውጥ አያመጣም። እቅድ የራሱ እንቅስቃሴ ድርጊት (Action) ይፈልጋል። አሁን ከምትሰራው በላይ በትጋት ካልሰራህ ከቀደመው የተለየ ውጤት በህይወትህ አይመጣም። መንፈሳዊ ሆነ ምድራዊ ስራዎች ትጋት ይፈልጋሉ ውጤቶቻቸውም እንደ ትጋታቸው ነው። ህይወት በእድል አይመራም።
በሌላ እሳቤ የተለየ ውጤት ለማግኘት የተለየ እርምጃ ያስፈልጋል። በ2014 ምን አቅደናል? እንደ ቤተክርስቲያን፤ በግል ህይወት፤ በቤተሰብ ምን እንዲሆንልን እንፈልጋለን? ያቀድናቸው ነገሮች በእግዚአብሔር እርዳታና በእኛ ትጋት ውጤትን ይሰጣሉ። እንደ መንፈሳዊ ሰው እንጸልይ የእግዚአብሔርን ፈቃድ እንጠይቅ ከዚያም ባቀድናቸው ነገሮች ተግተው እንሰራ። አንድ ነገር በህይወታችን ለመጨመር አኪያሄዳችንን እውቀታችንን አዋዋልና መጨመር እና እቅዳችንን የሚመጥን ማድረግ አለብን። አዲስ ውጤት ለማግኘት አዲስ አረማመድ እና አኪያሄድ ይኑረን። በእቅድ ውስጥ ለሚሰራ ቀኖች ሁሉ የውጤት ድልድዮች ናቸው።
ዘሪሁን ግርማ
/channel/theideaofs
እንደ ሰውኛ አቆጣጠር 2016 አመት እያለቀ ወደ 2017 ልንገባ በደጅ ነን። ይህን አመት ወደ ኃላ ስንመለከት እግዚአብሔር የምናመሰግንበት ምክንያት ብዙ ነው። በየቀኑ ምህረቱን አግንኖልናል። በህይወት እንድንኖር ጠብቆናል፣ የሚያስፈልጉንን ነገሮች ሰቶናል፣ ችግሮች ቢበዙብን እንኳ ያንን የምናልፍበት ጸጋን አብዝቶልናል። እረ ስንቱ።
በራሳችን ሐይል እየኖርን ይመስለናል አብሶ ሁሉም ነገር በተሳካልን ጊዜ፣ ነገር ግን ብዙ ስኬት ያገኙ ሰዎች ያለ እርሱ ምህረት እና እገዛ አንድም ቀን በህይወታቸው ያለ እርሱ መጨመር አይችሉም።
በህይወታችን ጥቂት ያልተመለሱ ጥያቄዎች ቢኖርንም እንኳ፣ የምናመሰግንበት ግን እለፍ ምክንያቶች አሉ። አየር እስካላጠረን የአየር ጥቅም አይገባንም፣ ስለ ምንተነፍሰው አየር ጨምሮ ይህን ጽሑፍ ካነበብክ አሁን በህይወት አለህ ማለት ነው። ስለዚህ አመስግን።
ያለ እግዚአብሔር መሆን የማንችለው ብዙ ነው፣ በራሳችን የምንችለው ጥቂት ነው እርሱም ከእርሱ የተገኘ ነው። ስለ ተሰጡን ሰዎች እናመስግን፣ ሰዎች ከእኛ ሲለዩ ዋጋቸው አይግባን አሁን አብረውን ሳለ እናመስግን። ስላለን ነገር እናመስግን፣ የሌለንን እያሰብን እናማርር።
ያለ እግዚአብሔር የሆነው (የሆነልን) አንድም ነገር የለም። ስለ ሁሉም ነገር እግዚአብሔር ይመስገን። ስለ አገራችን፣ ስለ ቤተሰባችን፣ ስለ ስራችን፣ ትዳራችን፣ ጤንነታችን፣ ስለ አገልግሎታችን ስለ ጓደኞቻችን ስለ ሁሉም ነገር እግዚአብሔር ይመስገን።
"ስለ ሁሉ አመስግኑ" 1 ኛ ተሰ 5:22
/channel/theideaofs
#ሁለንተናዊ_የዕድገት_በሮች!!
ሁላችንም በሚባል ደረጃ ዕድገቶቻችን የተወሰኑ ወይም በአንድ አቅጣጫ ብቻ ናቸው። ሁለንተናዊ ዕድገት ስንል ደግሞ በሰዎች እይታ ልክ የተለያዩ ቢሆኑም፣ እኔ ሁለንተናዊ ዕድገት ላይ ሰው የሚቃለው ምን ምን ሲኖረው ነው ብዬ አስቤ አራት ነጥቦችን ማንሳት ወደድኩ።
፨ መንፈሳዊነት
፨ ራዕይ ወይም ስራ
፨ ከሰዎች ጋር ያለን ግንኙነት
፨ ለሁለንተናዊ ዕድገት የሚጠቅሙ መርሆችን መረዳት ናቸው።
ዕድገት በአንድ አቅጣጫ ብቻ ከሆነ ምሉዕ በሆነ ህይወት አናድግም። አንዳንድ ሰው ብዙ ሊያስተምር፣ ሊጸልይና ሊዘምር ይችላል ከሰዎች ጋር ተግባብቶ የመኖር ክህሎት የለውም። ወይም ጥሩ ስራ ወይም ብዙ ገንዘብ ሊኖረው ይችላል ነገር ግን መንፈሳዊ የህይወት መርሆች ከሌሉት ገንዘቡ ብቻ ዕድገቱን ሙሉ አያደርገውም። እስቲ እነዚህ አራት ነገሮችን በጥቂቱ እንመልከት።
#መንፈሳዊነት በዚህ ውስጥ በእግዚአብሔር ማመን፣ ዳግም ውልደት፣ በቃሉ ማደግ፣ መጸለይ፣ አምልኮ፣ ከቅዱሳን ጋር ህብረትን ማድረግ፣ ማካፈል፣ ስለ መንፈሳዊና ምድራዊ አኗኗር ጭምር መጽሐፍ ቅዱሳዊ መረዳትን መያዝ፣ በፍቅር መመላለስ፣ በምስጋና መቆም፤ ስለ እግዚአብሔርና ስለ ሰዎች ትክክለኛውን መረዳት መያዝ እያልን ልንዘረዝራቸው እንችላለን። አንድ ሰው ይህ አይነት ነገሮችና ተጨማሪ ቃሉአዊ ነገሮችን ሲይዝ መንፈሳዊ ይባላል። መንፈሳዊነት ከታች ለምናነሳቸው ነጥቦች መሰረት ናቸው።
#ራዕይ_ወይም_ስራ መጽሐፍ ቅዱስ ከሚቃወማቸው ነገሮች አንዱ ስንፍናን ነው። ሰው በውስጡ ባለው ራዕይ ወይም በሚሰራው ስራ ላይ ትጉ መሆን አለበት። ታላልቅ ሰዎችን መቀየር የሚችሉ ሐሳቦችን ተግባራዊ በማድረግ ውጤታማ መሆን መቻል አለብን ወይም በስራችን ውጤታማ መሆን አለብን። የማይሰሩ፣ ታካችና ሰነፍ ሰዎችን እግዚአብሔር ይቃወማል። እግዚአብሔር ራሱ ያረፈው በሰባተኛው ቀን ስድስት ቀን ሰርቶ፣ እግዚአብሔር ሰራተኛ ነበር፣ ኢየሱስም ሰራተኛ ነበር። በዕረፍት መኖር ማለት ያለ ስራ መኖር ማለት ሳይሆን፣ በክርስቶስ ባለው የዕረፍት መንፈስ መመላለስ ማለት ነው። አገልጋይ ከሆንክ ፍሬያማና ትጉ አገልጋይ ሆን። ሰራተኛ ከሆንክ በስራው ውጤታማ የሆነ ሰራተኛ ሁን።
#ከሰዎች_ጋር_ያለን_ግንኙነቶች ሰዎች በመሆናችን ከሰዎች ጋር ጤናማ ግንኙነት እንዲኖረን ነው ያስፈልጋል። በትዳር፣ በስራ፣ በጓደኝነት፣ በአገልግሎት፣ በጉርብትና ወዘተ ከሰዎች ጋር ጥሩ ግንኙነት ማዳበር አለብን። ከላይ እንዳልኩት በገንዘብ ወይም በተለያዩ ስኬት ላይ የደረሱ ከሰዎች ጋር በመልካም መርሆች የመኖር ብስለት የሌላቸው ሰዎች ብዙ አሉ። ሁለንተናዊ እድገት አንደኛው መለኪያው ከሰዎች ጋር የሚኖረን መልካም ግንኙነት ነው። ሁለንተናዊ እድገት ሰዎችን እንዴትና በምን መልኩ መያዝ እንዳለብን ስንማር የሚመጣ ነውና ራሳችንን በዚህ ብቁ ለማድረግ መስራት አለብን።
#ለሁለንተናዊ_ዕድገት_የሚጠቅሙ_መርሆች
እነዚህ መርሆች እንደ ሰዎቹ ማንነትና የህይወት ምልከታ የተለያየ ቢሆንም ከዚህ በታች የማነሳቸው ነጥቦች እጅግ አስፈላጊ ናቸው።
ጥቃቅን የሚመስሉ ነገር ግን ለሁለንናዊ ዕድገት መሰረት የሆኑ ነገሮች፦
፨ አትኩሮት (Focus) (የምትሰራቸውን ነገሮች ላይ ትኩረት ማድረግ)
፨ ጊዜን መጠቀም (ሰአት ማክበር)
፨ ማንበብ (ራስ ላይ መስራት)
፨ አገልጋይነት (ማህበረሰብን መጥቀም)
፨ ካለን ማካፈል (ማካፈል የዕድገት አንዱ አካል ነው። ሰው ሲያድግ ለሌሎች ይተርፋል)
ዘሪሁን ግርማ
/channel/theideaofs
Good Morning my fellow Ethiopians!
ሰላም የሞላበት ቀን እንዲሆንላችሁ!
ዛሬና መጪው ሳምንት የሰላም ውሎ እንዲሆንላችሁ ከፈለጋችሁ እነዚህን ሃሳቦች ላቀብላችሁ . . .
1. ምንም ብታደርጉም ፈጽሞ ለውጥ የማታመጡትን ነገር ስታሰላስሉ አትዋሉ፡፡
መለወጥና ማስተካከል በማንችለው ነገር ላይ ጊዜያችንንና ስሜታችንን ካባከንን ሰላማችን ይናጋል፡፡
2. እጃችሁ ከገባ በኋላ የት እንደምትወስዱትና ምን ነገር ላይ እንደምታውሉት የማታውቁትን መረጃ ለመስማት ከመሞከር ተቆጠቡ፡፡
ከቀንደኛው የሰላም ጸሮች መካከል አንዱ፣ እኛ ጋር ከደረሰ በኋላ ለምንም ነገር የማይጠቅም መረጃን የመሰብብ ልማድ ነው፡፡ ስራ ላይ የማናውለው መረጃ ውስጣችንን ታምቆ ሰላም ይነሳል፡፡
3. ማስታወስ በሚገባችሁና በማይገባችሁ ያለፉ ልምምዶች መካከል ለመለየት ሞክሩ፡፡
ጤና-ቢስ ልምምዶቻችሁን አንድ ጊዜ ትምህርታችሁን ካገኛችሁባቸውና ወደፊት ከተራመዳችሁ በኋላ እንደገና ላለማስታወስ ሞክሩ፡፡ ያለፉትን ጤና-ቢስ ልምምዶች ማሰላሰል ልምምዱን እንደገና እንደመኖር ያህል ነው፤ ውስጥም ያደክማል፤ ሰላም ይነሳል፡፡
4. ምንም ያህል ከእነሱ ጋር የመሆን ፍላጎት ቢኖራችሁም እንኳን፣ ከእናንተ ውጪ መሆንና መኖር የተመቻቸውን ሰዎች መልቀቅን ተማሩ፡፡
ከእናንተ ውጪ መሆን ስለተመቻቸው ያንን የመረጡ ሰዎች ከእናንተ ጋር ቢሆኑ ስለማትመቿቸው ሰላማችሁን ሊነሷችሁ ይችላሉ፡፡
የሰላም ቀን ይሁንላችሁ፡፡
/channel/Dreyob
https://m.youtube.com/user/naeleyob623
https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
#መርዛማ_ንግግሮች (የእፉኝት መንደፊያ)
በማህበራዊ ሚዲያዎች፣ በሰዎች የዕለት ተዕለት ህይወት ውስጥ፣ እንዲሁም ባለን በማንኛውም ግንኙነት ውስጥ ቀስ ብሎ የሚገል መርዝ የሆነ ነገር መርዛማ ንግግሮች
ናቸው። ብዙ አገልጋዮችን ሽባ አድርገዋል ብዙ ሰዎችን ፈሪ አድርገዋል። የሚነገሩ ንግግሮች በሰዎች ትልቅ ተጽዕኖ ስላላቸው ነው።
“ማንም ሰው የሚናገር ቢሆን፥ እንደ እግዚአብሔር ቃል ይናገር.."
— 1ኛ ጴጥሮስ 4፥11
በፌስ ቡክ በዩቲዩብና በቲክቶች የሚደረጉ ንግግሮችና ከሰዎች አንደበት የሚወጡ ጥላቻ የተሞሉ እና የተንኮልን ዘር ያነገቡ፣ ጠላት ሰዎችን በሰዎች አንደበት አልፎ ለመግደል ወጥሮ ያዘጋጃቸው ቀስቶች ናቸው። አንዳንዶቹ ከመንፈሳዊ 'ነኝ' ከሚል ሰው ቀርቶ ከማንኛውም ሰው የማይወጡ ናቸው። ቃል አዋቂዎች እና ነገር ሰንጣቂዎች ስለሆኑ የገዛ ወንድማቸው ላይ ጠንካራና ነፍስ የሚሰብር ንግግር ሲናገሩ ርኅራኄ አይሰማቸው።
በሰዎች ላይ የምንረጫቸው መርዛማ ቃሎች የሰዎችን አገልግሎት ብቻ ሳይሆን፣ የትዳር አጋራቸውና የልጆቻቸውን ስነልቦና ላይ ጭምር መርዝ እንደ መጨመር ነው። እንደዚህ አይነቶች በመንፈሳዊ ቋንቋ የዳበረ የክፋት ቃል አላቸው። የሚያቀርባቸው ንግግሮች ለጌታ ያሰቡና ለቤቱ የቀኑ በሚመስል መንፈሳዊ ንግግሮች ተሸፍነዋል። ነገር ግን መጽሐፍ ቅዱሳዊ የሆነው ንግግራችን "በጨው እንደ ተቀመመ ይሁን" ሳይሆን 'በመርዝ እንደተለበጠ' ዳቦ ነው። መምከር፣ መገሰጽ፣ ማረምና፣ ማቅናት በራሱ ጸጋን ይጸልጋልና።
“ለእያንዳንዱ እንዴት እንድትመልሱ እንደሚገባችሁ ታውቁ ዘንድ ንግግራችሁ ሁልጊዜ፥ በጨው እንደ ተቀመመ፥ በጸጋ ይሁን።”
— ቆላስይስ 4፥6
ጨዋዊ፣ ክርስቲያናዊ፣ መጽሐፍ ቅዱሳዊ የእርምት መንገዶች አሉ እኮ፣ ፍቅርንና እውነትን የተከተሉ የሆኑ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሰረቶች አሉ እኮ። አጠፋ የምንለውን ሰው የምንናገረው ለማዳን ከሆነ አላማችን የሚገሉ ቃሎችን ለምን እንጠቀማለን? አጠፋ ብለን ለምንጠራው ሰው 'የሞትነውና የተሰቀልነው' እኛ አይደለንም እኮ የማረ፣ የታገሰ፣ የወደደ፣ ይቅር ያለ አለ። ልክ እኛን ይቅር እንዳለን።
ሰዎች ነገ ከጥፋቸው ተነስተነው ወደ አገልግሎት የሚመልስ 'መጽሐፍ ቅዱሳዊ' መሰረትን የተከተለ አነጋገርና ማስተማርና እያለ የሰዎችን ህይወት የሚሰብር፣ የትዳር አጋራቸውን እና ቤተሰቦቻቸውን የሚያሸማቅቁ ቃሎች እና አነጋገሮች ሰዎችን ለመስበር ሰይጣን በሰዎች ውስጥ የወጣራቸው መርዛማ ቀስቶች ናቸው። ሁላችንም ስለ ምናገራቸው ንግግሮቻችን መልስ እንሰጥበታለን።
“አንደበትም እሳት ነው። አንደበት በብልቶቻችን መካከል ዓመፀኛ ዓለም ሆኖአል፤ ሥጋን ሁሉ ያሳድፋልና፥ የፍጥረትንም ሩጫ ያቃጥላል፥ በገሃነምም ይቃጠላል።”
— ያዕቆብ 3፥6
ዘሪሁን ግርማ
/channel/theideaofs
ከሶስት አይነት ሰዎች ተጠበቅ
፨ እንደ እነርሱ ካላሰብክ ትክክል ነህ ብለው የማያምኑ፣ ትክክለኛነትን ከእነርሱ ጋር በሚኖርህ ግንኙነት ብቻ የሚመዝኑ፣
፨ የሚወዱትን እንድትወድ፣ የሚጠሉትን እንድትጠላ፣ የሚፈልጉትን ያንን ካላደረግ ተቀጽላ ስም የሚሰጡ፣
፨ እኔ አውቅልሃለሁ፣ አንተ ስለ ራስህ አታውቅም የሚሉ፣ አንተ በራስህ ፈትነህ ነገሮችን አይተህ እንዳትሄድ የማይፈልጉ "አዋቂዎችህ" ነን ባዮች እነዚህም የህይወትህ ዋነኛ ችግሮች ናቸው።
ሰው የተፈጠረው ከእግዚአብሔርና ከሰዎች የሚማር ትሁት ልብ እንዲኖረው፣ ሰዎችን እየወደደና ለገባው እውነት እየቆመ፣ በገባው ልክ እንዲኖር እንጂ ሰዎች በሰሩለት ልክ እንዲኖር አይደለም።
መልካም ቀን ይሁንላችሁ።
/channel/theideaofs
#የከፍታ_መንገድ_የሚገኘው_በዝቅታ_ውስጥ_ነው!!
እግዚአብሔራዊ ከፍታ የሚገኘው በዝቅታ ውስጥ ነው። ለከፍታ የሆነ ዝቅታ ያስፈልጋል። አንዳንድ ሰው የታወቀ አስተማሪ መሆንን ይሻል፣ ነገር ግን ዝቅ ብሎ መማርን አይሻም። አንዳንድ ሰው ብዙ ህዝብ መምራት ይፈልጋል፣ ነገር እግዚአብሔር የሰጠውን ጥቂት ህዝብ አክብሮ አያገለግልም። አንዳንድ ሰው ብዙዎች እንዲታዘዙት ይሻል፣ እርሱ ግን ሊታዘዛቸው የሚገባቸውን ሰዎች አይታዘዝም። አንዳንድ ሰው መባረክን ይሻል፣ ግን ለእግዚአብሔር ታማኝ አይደለም።
እግዚአብሔር እንድናፍበት የፈለገው ዝቅታ ካለ ወደ ከፍታ መውጫ ድልድይ ነው። በዝቅታ የተገኘ ከፍታ ከፍታው ለእግዚአብሔር በረከት ይሆናል። እግዚአብሔር የሚሰጠን ከፍታውም፣ የተከፈተ በርም ቢሰጠን፣ ለእግዚአብሔር ክብር፣ ለሰዎች ጥቅም ለእኛ በረከት፣ የሰይጣንን መንግስት እንድናፈርስ ነው። ከፍታው ለእርሱ ክብር ብቻ ነው።
“ተቀምጦም አሥራ ሁለቱን ጠርቶ፦ ሰው ፊተኛ ሊሆን ቢወድ ከሁሉ በኋላ የሁሉም አገልጋይ ይሁን አላቸው።”
ማርቆስ 9፥35
“በእናንተስ እንዲህ አይደለም፤ ነገር ግን ማንም ከእናንተ ታላቅ ሊሆን የሚወድ የእናንተ አገልጋይ ይሁን፥”
ማርቆስ 10፥43
ወደፊት የሚያመጣህ አገልጋይነት ነው የምታገለግለው ደግሞ ፊተኛ ለመሆን አይደለም ስታገለግሉ ግን ፊተኛ ትሆናላችሁ። ከፍታ በእወጃ ብቻ አይመጣም፣ እወጃም የሚጸናው በእግዚአብሔር ቃል መሰረት ነው። የታላቅነት መርሁ ዝቅ ብሎ በማገልገል ነው፣ በምታገለግሉት አገልግሎት በታማኝነተ ስታገለግሉ፣ ታማኝ ፍሬዎችን ይሰጣችኋል።
ዘሪሁን ግርማ
/channel/theideaofs