tibyaan54 | Unsorted

Telegram-канал tibyaan54 - 💎ቲብያን 💎 የተለያዩ ዳዕዋዎች የሚተላለፉበት ቻናል!

2303

🍂የቲብያን ቻናል ዋና አላማው አላህ ኢኽላሱን ይስጠንና በተቻለን አቅም ጠቃሚ ናቸው የምንላቸው ወቅታዊ ሙሃደራዎችን እንዲሁም ጠቃሚ ማስታወሻዎች አጫጭር ፁሁፎችና ፎቶዎችንምን ! ላልደረሳቸው ማድረስ ነው። «السلفية منهجي» https://t.me/joinchat/AAAAAEPOgchGXF37Mja27A

Subscribe to a channel

💎ቲብያን 💎 የተለያዩ ዳዕዋዎች የሚተላለፉበት ቻናል!

ኳስ የዘመናችን ጣዖት
~
ዛሬ ላይ ኳስ ከተራ መዝናኛነት አልፏል።
* በአላህ መንገድ ላይ የማይወጣው በቢሊዮን ዶላር የሚቆጠር ወጭ ይወጣበታል። ሚሊዮኖች እየተራቡ፣ በክህ -ደት ሰባኪዎች እየተጠለፉ ከግለሰቦች እስከ መንግስታት ለዚህ ቆሻሻ ነገር ግን የማይገመት ወጭ ያወጣሉ።
* ዘረኝነት ይንፀባረቅበታል።
* በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ አስካሪ መጠጥ ይተዋወቅበታል።
* የጭፈራና የዘፈን ድግስ ይቀርብበታል።
* እጅግ በርካቶች ለሱ ሲሉ ግዴታ የሆነባቸውን ሶላት ያሳልፋሉ።
* እጅግ በርካቶች ለሱ ሲሉ ጎረቤት ይበጠብጣሉ፣ የወላጅ ሐቅ ይጥሳሉ፣ እርስ በርስ ይጋጫሉ፣ ለሱ ሲሉ ይወዳሉ፣ ይጠላሉ።
* የመገናኛ አውታሮች፣ ማህበራዊ ሚዲያዎች፣ ጋዜጦችና መፅሔቶች፣ ግለሰቦች፣ በቤትም በውጭም፣ በየጎዳናው፣ በየ ካፌው፣ ቆመው ተቀምጠው፣ ... ለዲንም ይሁን ለዱንያ በሚጠቅም ጉዳይ ላይ ከሚጮሁት እጅግ በላቀ ስለዚህ ርካሽ ነገር ሆኗል ውትወታቸው። እንዲያውም ቀላል የማይባሉ ጥራዝ ነጠቆች ስለ ኳስ መተንተንን የንቃት ማሳያ አድርገውታል። ስለ ኳስ አለማወቅን ፋራነት አድርገውታል። ከዚህ በላይ ምን ዝቅጠት አለ?!
* በዚህ ቆሻሻ ነገር የተነሳ እጅግ በርካታ ወጣቶቻችን ከሃዲዎችን፣ የሉጥ ህዝቦችን ተግባር የሚፈፅሙ፣ ለሱ ጥብቅና የሚቆሙ ርካሽ ፍጡሮችን እንዲያደንቁ ሆነዋል። ደካማ ሰበብ እየደረደሩ ራሳቸውን አደንዝዘዋል።
* ከዚህ ሁሉ በኋላ አንዳንዶች ጂሃድ ሊያስመስሉት ሲዳዳቸው ይታያሉ። ኳስ በዚህ በመከራ በተከበበ ህዝብ ላይ የተከፈተ ወደን የተቀበልነው ጦርነት ነው።
ይሄ ሁሉ እውነታ በገሃድ ፈጦ የሚታይ ከመሆኑ ጋር ቢያንስ ሸሩን በመቀነስ ላይ እንኳ ዱዓቶች እየሰሩ አይደለም። የዱዓት ትልቁ በሽታ ሰፊው ህዝብ የወደቀባቸውን ጉዳዮች ለመጋፈጥ ወኔ ማጣት ነው። መሬት ላይ ባለው ተጨባጭ (ዋቒዕ) መሸነፍ። አትጠራጠር ወንድሜ! ኳስ ከዘመናችን ብዙ ዓይነት ጣዖቶች ውስጥ አንዱ ጣዖት ሆኗል። አደራ! ሌላው ቢቀር ቢያንስ ለዚህ የቦዘኔዎች ስራ ብለን ሶላት ከወቅቱ የምናሳልፍ እንዳንሆን እንጠንቀቅ። ለዚህ የጂላጂሎች ስራ ብሎ መስጂዶቻችንን ማራቆት የሚያሳፍር ጉዳይ ነው። ስለዚህ ነፍሲያችንን እንርገጥ። ተቅዋን እናስቀድም።

ማሳሰቢያ፦
- ያወራሁት ስለ ኳስ እንጂ ስለ ቀጠር አይደለም።
=
የቴሌግራም ቻናል፦
/channel/IbnuMunewor

Читать полностью…

💎ቲብያን 💎 የተለያዩ ዳዕዋዎች የሚተላለፉበት ቻናል!

«ከንግግር አንድንም አይናገርም
አጠገቡ ተጠባባቂና ዝግጁ(የተጣዱ)
መላይኮች ያሉበት ቢሆን እንጂ።»


[ሱረቱ‘ቃፍ]

/channel/ibrahim_furii

Читать полностью…

💎ቲብያን 💎 የተለያዩ ዳዕዋዎች የሚተላለፉበት ቻናል!

#አስቸኳይ_ነው‼️
#እያለቀሱ_ነው

አንድ ልበደግ ወንድማችን ስልክ ደወለልን!!"አንዲት እናት እያለቀሱ ቀራንዮ መንገድ ላይ አገኘኋቸው!ምን ላድርግ?"ብሎ ጠየቀን!!

እማማን የሚታይ ፎቶ አንሳቸውና ላክልን አፋልጉኙን በቶሎ እንለጥፋለን እስከዛ ፖሊስ ጣቢያ ውሰዳቸው" አልነው!!
እንደነገርኩት ፎቶ አንስቶ የሚሄድበትን ጉዳይ ትቶ ጦርሀይሎች ፖሊስ ጣቢያ ይዟቸው ሄደና "እማማ ጠፍተው ነው ቤተሰብ እስኪገኝ እዚህ ይሁኑ?" ብሎ በትህትና ጠየቃቸው!ፖሊሶቹ እንደተለመደው "አንቀበልም እኛን አይመለከተንም" ብለው መለሱት!!

ወንድማችን ተሜ መልሶ ወደኛ ደውሎ "ምን ላድርግ እምቢ አሉኝ እኮ ካልሆነ ቤት ልውሰዳቸው እንዴ?" አለን!!በደስታ አዎ አሁን ልጆቻቸው መገኘታቸው አይቀርም አልነው! #እናንተን_ተማምነን!
ስሜ #ዘህርያ_ሁሴን የልጆቼ ስም መኑር ሁሴን፣ሀሰን ሁሴን እና ፈድሉ ሁሴን፣ይባላል ብለውናል!! #ሼር አድርገን እናገናኛቸው🙏
"ለመልካም ስራ ረፍዶ አያውቅም"
#ባይሽ_ኮልፌ_በጎ_አድራጎት
0939684393-ተመስገን
0913559189-ሄኖክ
0912121942-ውብሸት
0921058424-ኤደን

Читать полностью…

💎ቲብያን 💎 የተለያዩ ዳዕዋዎች የሚተላለፉበት ቻናል!

🌿 የኡስታዝ አብዱሰላም ዚያራ
-------------------------

ከፎቅ ላይ ወድቆ የተጎዳው ወንድማችን ኡስታዝ አብሱሰላም አህመድ ዛሬ ዚያራ ተደርጎለታል።

በዚያራው ላይ በርካታ ወንድሞችና ኡስታዞች በመገኘት አበሽረውታል።

ኡስታዝ አብዱሰላምም የተሰማውን ደስታ ገልጿል።


https://youtu.be/cpF8u_TRM9U
https://youtu.be/cpF8u_TRM9U
https://youtu.be/cpF8u_TRM9U

Читать полностью…

💎ቲብያን 💎 የተለያዩ ዳዕዋዎች የሚተላለፉበት ቻናል!

አማትን "እናቴ" "አባቴ" ... እያሉ መጥራት
~
* መነሻ የሆነኝ የሚከለክል ፈትዋ ሲሰራጭ ማየቴ ነው።

አንድ ሰው የሚስቱን ወላጆች (እማ፣ አባ) እያለ ቢጠራ፣ ወይም አንዲት ሴት የባሏን ወላጆች በዚህ መልኩ ብትጠራ ምንም የሚከለክል ማስረጃ የለም። ሐራም ማለት አላህ ሐራም ያደረገው ነው። ክልክልነታቸውን የሚጠቁም ሸሪዐዊ መረጃ እስካልቀረበ ድረስ የተለያዩ ይዘቶች ካሏቸው የመሻይኽ ፈትዋዎች ውስጥ ከልካዩን ብቻ መዝዘን መሰል ልማዶችን ሐራም ማድረግ አያስኬድም። መሰል ልማዶች መሰረታቸው ፍቁድነት ነው። ከዚህ መሰረት አውጥቶ ሐራም ለማለት ተጨባጭ መረጃ ያስፈልጋል። ልብ በሉ! በእንዲህ ዓይነት ጉዳይ ላይ መረጃ የሚጠየቀው ፈቃጅ ሳይሆን ከልካይ ነው።
ደግሞም አማቷን "እማዬ" ስትል "እናትሽ ቢሆኑማ ባልሽ ወንድምሽ ይሆን ነበር" ማለት ልክ አይደለም። የሚፈለገው አክብሮት እንጂ በትክክል ወላጅ እናቴ ናቸው ለማለት እንዳልሆነ ግልፅ ነውና። አማትን በዚህ መልኩ መጥራት በብዙ ባህሎች የተለመደ ነው። ስለዚህ ይሄ ባህል በተለመደበት ሃገር ላይ በተሳሳተ መልኩ ሰዎች እንዳይረዱ የሚለው ሰበብ ውሃ የሚያነሳ አይሆንም።
አዛውንቶችን፣ ዑለማዎችን "አባታችን" እያሉ በአክብሮት መጥራት በሰፊው አለ። ለምሳሌ ያህል ታላላቅ ዐሊሞችን "ሰማሐቱል ዋሊድ" ሲሉ ማየት የተለመደ ነው። መቼስ ይህንን ለሚል ሁሉ ያ ሸይኽ በትክክል ወላጅ ስለሆኑት አይደለም እንዲህ የሚባለው።

ማሳሰቢያ:-

1- አንድ ሰው አባቱ ባልሆነ ስም መጠራት አይፈቀድም። ማለትም የሌላን ሰው ስም በአባት ስም ቦታ ተክቶ ለመጠሪያነት መጠቀም አይቻልም። ይሄ ግልፅ ማስረጃ የመጣበት ጉዳይ ነው። ነገር ግን ይሄኛው ነጥብ ከያዝነው ጉዳይ ጋር የሚገናኝ አይደለም። በመጠሪያ ስምነት ስለ መጠቀም አይደለም እያወራን ያለነው።
2- "ሸይኽ እከሌ ግን አይፈቀድም ብለዋል" የሚል እንደሚኖር እጠብቃለሁ። እኔም እሱን አይቼ ነው ይህንን የፃፍኩት። ከተጨባጭ መረጃ ጋር ያልተቆራኘ ፈትዋ ማስፈራሪያ ሆኖ መቅረብ የለበትም። በዚያ ላይ ችግር እንደሌለበት የጠቆመ ዓሊምም መጥቀስ ይቻላል። ለምሳሌ ኢብኑ ዑሠይሚን ረሒመሁላህ።

ሰዎች ከልካዩን ፈትዋ ይዘው ከልማድ ባፈነገጠ መልኩ ቢጓዙ በንቀትና አለማክበር ተተርጉሞ መቀያየም ሊያስከትል ይችላል። ውጤቱን ፈርተው ቢቀጥሉ እንኳ የጥፋተኝነት ስሜት እየተሰማቸው ሊኖሩ ይችላሉ። ወይም "አሁንስ አበዛችሁት!" ዓይነት የመሰላቸት ስሜት ሊያድር ይችላል። ስለዚህ መሰል ጉዳዮችን ከማሰራጨታችን በፊት "ሌሎችስ ምን ይላሉ?" የሚል ትንሽ ፍተሻ ብናደርግ መልካም ነው። ወላሁ አዕለም።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
/channel/IbnuMunewor

Читать полностью…

💎ቲብያን 💎 የተለያዩ ዳዕዋዎች የሚተላለፉበት ቻናል!

#ቀልብ ቂመኛ፣ ምቀኛ፣ በራሱ የሚደነቅና የሚኮራ ከሆነ ንፁሕ ልብ አይሆንም።
《ኢብኑል ዐረቢ አልማሊኪ》
【አሕካሙል ቁርኣን:(3/459)】

Читать полностью…

💎ቲብያን 💎 የተለያዩ ዳዕዋዎች የሚተላለፉበት ቻናል!

كتاب قواعد الإملاء وعلامات الترقيم
كتبه : الأستاذ عبدالسلام بن محمد بن هارون -رحمه الله تعالى-
የኪታቡ አዘጋጅ፦ አል-ኡስታዝ አብዱሰላም ሙሐመድ ሓሩን
✍Abu Uwais Nafyad Kasim
ትምህርቱን በቴሌግራም ለመከታተል 👇👇
/channel/AbuUweis

Читать полностью…

💎ቲብያን 💎 የተለያዩ ዳዕዋዎች የሚተላለፉበት ቻናል!

ገና ሰው ከፈጅር ሶላት እየተመለሰ 3 ትንንሽ ልጆቹን ከፊት ይዞ፣ ቦርሳዎቻቸውን ተሸክሞ እየተዋከበ ሲሄድ አየሁት። ባቅራቢያ የመንግስት ትምህርት ቤት ስለሌለ ራቅ ወዳለ ሰፈር መሄድ አለባቸው። ለዚያ ነው በማለዳ መውጣቱ። የትራንስፖርት መክፈል ስለማይችል ነው በሌሊት የሚያዋክባቸው። እያሰብኩት ቤቴ ገባሁ። ብዙ ነገር መጣብኝ። ለማስተማር ያለውን ቁርጠኝነት አሰብኩ። በዚህ ዘመን አለመማር እድሜ ልክ የሚዘልቅ ትልቅ ጠንቅ ነው። በዚህ በኩል ራሱን እያንገላታ፣ አካሉ አልቆ ለልጆቹ ትልቅ ውለታ እየዋለ ነው። ልጆች ይህንን ውለታ ይረዱ ይሆን? ለዲናቸውስ ይሄን ያህል ቦታ ይሰጥ ይሆን? አላህ ያግዘው። ለታክሲ የተቸገረው ሰው ቤት ውስጥ ኑሮው እንዴት ይሆን? ሳስበው ጨነቀኝ። ከሱም የባሰ ብዙ አለ። ግን በያካባቢያችን መቸገሩን የማይናገር ችግር ክፉኛ የሚያንገላታው ስንት ሰው አለ?! የጎረቤት ሐቅ እንዳያስጠይቀን እናስብ ይሆን? ለማንኛውም ነብዩ ﷺ እንዲህ ይላሉ፦
ليس المؤمنُ الذي يشبعُ وجارُه جائِعٌ إلى جنبهِ
"ጎረቤቱ ከጎኑ እየተራበ የሚጠግብ ሰው አማኝ አይደለም።" [ሶሒሑል ጃሚዕ፡ 5382]

ሸይኹል አልባኒይ ረሒመሁላህ በዚህ ሐዲሥ ስር እንዲህ ይላሉ፦
"ሃብታም ጎረቤት ጎረቤቶቹን እየተራቡ መተው ሐራም እንደሆነ በሐዲሡ ውስጥ ግልፅ መረጃ አለ። እናም ረሃብን የሚያስወግዱበት ያህል ሊሰጣቸው ግዴታ አለበት። ታርዘው ከሆነም እንዲሁ ሊያለብሳቸው ይገባል። ሌሎችም እነዚህን የመሳሰሉ መሰረታዊ ጉዳዮች ላይ እንዲሁ።" [አሶሒሐ፡ 1/230]
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
/channel/IbnuMunewor

Читать полностью…

💎ቲብያን 💎 የተለያዩ ዳዕዋዎች የሚተላለፉበት ቻናል!

《 #እኛና_የዱኒያ_ህይዎት》

#በክራይ ቤት እየኖርን ባለቤቱ መጥቶ
-ቀደሞ ካሳወቀን በሗላ- ቤቴን ለቀህ ውጣ ጊዜህን ጨርሰሃል ቢለን አልወጣም እንደማንለው ሁሉ
ሀያሉ ጌታችን አሏህ
(كُلُّ نَفْسٍ ذَائِقَةُ الْمَوْتِ ۗ وَإِنَّمَا تُوَفَّوْنَ أُجُورَكُمْ يَوْمَ الْقِيَامَةِ ۖ ِ)
[ ነፍስ የተባለች በሙሉ ሞትን ትቀምሳለች ዋጋቹን የምታገኙት የቂያማ ቀን ነው ] ብሎ ከነገረን በሗላ
አጀላችን ሲደርስ መለከል መውት መጥቶ ነፍሲያችንን ከሰውነታችን መዞ ስያወጣት አልወጣም ማለት አትችልም!
ይህን ሁሌም እናስታውስ ልብ እንበል ሞት ለማንም እንደማይቀር ሁላችንም እናውቃለን ነገር ግን በድንገት ሊመጣ እንደሚችል አብዛኞቻችን እንዘነጋለን በዚህም ምክንያት ከጌታችን ጋር ያለን ግንኙነት የተበላሸ ይሆናል

#ኡስታዝ_አሕመድ_ሸይኽ_ኣደም (ሓፊዘሁሏህ)

/channel/ahmedadem

Читать полностью…

💎ቲብያን 💎 የተለያዩ ዳዕዋዎች የሚተላለፉበት ቻናል!

ነብዩ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ለይለተል ኢስራ ወል ሚእራጅ ሰባት ሰማያትን አቋርጠው ሲሄዱ በያንዳንዱ ሰማይ ያገኟቸው ነብዮች የሚከተሉት ናቸው

1ኛው ሰማይ ላይ ነብየላህ አደም፣

2ኛው ሰማይ ላይ ነብየላህ ዒሳን እና የህያ፣

3ኛው ሰማይ ላይ ነብየላህ ዩሱፍ፣

4ኛው ሰማይ ላይ ነብየላህ ኢድሪስ፣

5ኛው ሰማይ ላይ ነብየላህ ሀሩን፣

6ኛው ሰማይ ላይ ነብየላህ ሙሳ፣

7ኛው ሰማይ ላይ ነብየላህ ኢብራሂም ናቸው።

/channel/SadatKemalAbuMeryem

Читать полностью…

💎ቲብያን 💎 የተለያዩ ዳዕዋዎች የሚተላለፉበት ቻናል!

ብንንጫጫስ ምን እናመጣለን?!

  አላህ ባሮቹን በተለያየ ነገር ሊፈትን ይችላልⵑ
▪️የትክክለኛ አማኝ መለያና ግዴታ በፈተና ጊዜ መታገስና መቻል ነው።
ከዚህም አልፎ ሁሉም ለበጎ ነው ብሎ በማመን እራስን ማጽናናትና ከችግር በኋላ ድሎና ደስታ እንደሚመጣ እርግጠኛ መሆን ነው የሚገባው።
▪️ የአላህን ውሳኔ መቃወምና ለምን እንዲህ አይነት ችግር ደረሰብኝ ብሎ መቆጣት፣ መናደድ የተከለከለና ከባድ ወንጀል ነው። ከዚህም አልፎ እስከ ኩፍር (ክህደት) ሁሉ ሊያደርስ ይችላል!  
▪️ መበሳጨትና ከዚህስ ሞት ይሻላል ወዘተ እያሉ ማማረር፣ ልብስን መቅደድና አካላትን መደብደብ ክልክልና በአደጋና ችግር ጊዜ ግዴታ የሆነውን ትዕግስት የሚጻረር ተግባር ነው። 
▪️የሰው ልጆች ላይ የሚደርሱ ፈተናና ችግሮች በሙሉ ብዙና የላቁ ጠቀሜታዎች ስላሏቸው ጥሩ ጎናቸውን በማየት መረጋጋትና አላህን ማመስገን ይጠበቅብናል።
▪️ ከአላህ እዝነትና ችሮታ ተስፋ መቁረጥም የከሳሪ ሰው ተግባር ስለሆነ ነገ ከዛሬ ይሻላል እያሉ በተስፋ መኖር ብልህነት ነው።

   ብንንጫጫስ ምን እናመጣለን?!
አላህ የሻውን ሰሪ ነውና ⵑ


▪️ይልቅ በውሳኔው ተደስቶ እሱን በማስደሰት ውዴታና ምህረቱን ማግኘቱ ነው የሚሻለው።ሰዎች ላይ የሚደርሱ ችግሮች መነሻ አብዛኛውን ጊዜ የራሳቸው ወንጀልና ጥፋት በመሆኑም ጥፋትን አምኖ፣ እራስን ወቅሶ፣ ተጸጽቶ ወደ አላህ መመለስም ተገቢ ነው።
  አላህ በችግር ጊዜ ከሚታገሱ፣ በድሎት ጊዜ ከሚያመሰግኑ፣ ሲያጠፉ ተጸጽተው ከሚመለሱና በልብ ዓይኖቻቸው የነገራቶችን ጥበብና ከጀርባቸው የሚኖሩ መልካም ነገሮችን አሻግረው ከሚያዩ ባሮቹ ያድርገን "ኣሚን"
✍ኡስታዝ አሕመድ ሸይኽ ኣደም
8/ 4/1444ዓ.ሂ
@ዛዱል መዓድ
~~~~
💥 በተጨማሪም የተለያዩ ትምህርቶችን ለማግኜት ከታች ያሉትን ሊንኮች ይጠቀሙ
🔸🔹🔸🔹🔸🔹
🌐/channel/ahmedadem
~
🌐/channel/zad_qirat
~~~~
🔗https://www.facebook.com/yenegew/
~~~~
📶  http://www.youtube.com/c/ZadulMaad
አላህ በተከበረው ቃሉ እንዲህ ይላል:-
🔅وَتَزَوَّدُوا فَإِنَّ خَيْرَ الزَّادِ التَّقْوَىٰ ۚ وَاتَّقُونِ يَا أُولِي الْأَلْبَابِ 
"ስንቅ ያዙ፤ ከስንቆች ሁሉ በላጩ አላህን መፍራት ነው፤ የአእምሮ/ የልብ ባለቤቶች ሆይ ፍሩኝ" ሱረቱል በቀራ /197.

Читать полностью…

💎ቲብያን 💎 የተለያዩ ዳዕዋዎች የሚተላለፉበት ቻናል!

አጅነብይ ለሆነ ወንድ/ሴት ለአላህ ብዬ እወድሀለሁ/ እወድሻለሁ ማለት⁉️

🎙ኢብኑ ኸይሩ


t.me/Sadik_Ibnu_Heyru

Читать полностью…

💎ቲብያን 💎 የተለያዩ ዳዕዋዎች የሚተላለፉበት ቻናል!

#ከአቡ ሁረይራ (ረዲየላሁ ዐንሁ )ተይዞ የአላህ መልእክተኛ{ ﷺ }እንዲህ ብለዋል፡-
«من حسن إسلام المرء تركه ما لا يعنيه».
“ከአንድ ሰው የኢስላም ውበት የሆነው የማያገባውን መተው ነው።” [ቲርሚዚና ሌሎችም ዘግበውታል።]

Читать полностью…

💎ቲብያን 💎 የተለያዩ ዳዕዋዎች የሚተላለፉበት ቻናል!

➫ስልጤ ዞን ምዕራብ አዘርነት በርበሬ ወረዳ ቢላሎ ቀበሌ ውስጥ አንድ አባት ሁለት የ20 አመት እና የ25 አመት ወንድ ልጆቻቸው የአዕምሮ ታማሚ ሆነውባቸው እጅግ አሳዛኝ ሁኔታ ውስጥ ነው ያሉት።አባት ያላቸውን ነገር እነዚህ ልጆቻቸውን ለማሳከም ጨርሰዋል።አንዲት የታማሚዎች እህት ሰው ቤት ተቀጥራ እየሰራች ልብስም እያጠበች አባቷን እያገዘች የነበረ ቢሆንም አሁን ላይ ነገሩ ከአቅማቸው በላይ ሆኖባቸዋል።

➫ስርዝር ሁኔታውን በአላህ ፍቃድ በቪዲዮ ስልጤ ዞን የምትገኙ ኸይረኞች ቀርፃችሁ ወደ ሚዲያ ብታመጡት የእኚህን አባት እና የቤተሰቡን ጭንቀት በተወሰነ መልኩ ማቃለል ቢቻል ኢንሻ አላህ የረበናን ውዴታ እናገኝ ይሆናል።

➫ አሁንላይ አንዱ ልጃቸውን ይዘው ወራቤ ሀኪም ቤት ይገኛሉ አንደኛው ልጃቸው እዛው ገጠር መድሀኒት የወሰደ ነው።
እኛም ስደት ላይ ያለን እህቶች የአቅማችንን ልከናል ግን ለጊዜው ነው እነዝህ ልጆች ምናልባት ጥሩ ህክምና ቢያገኙ በአላህፍቃድ ይዱኑ ይሆናል ።ሰበብ እንሁንላቸው።

➫የአባት ስልክ ቁጥር እና አካውንት ቁጥር ኢሜጁ ላይ ያገኙታል
👆👆👆👆

Читать полностью…

💎ቲብያን 💎 የተለያዩ ዳዕዋዎች የሚተላለፉበት ቻናል!

#ጫማ ስትለብሱ ከቀኝ እግራችሁ ጀምሩ፣ ስታወልቁ ደግሞ ከግራ እግራችሁ ጀምሩ።

ነብዩ ሶለላሁ ዓለይሂ ወሰለም

ምንጭ፦ ቡኻሪ (5855) ሙስሊም (2097)

Читать полностью…

💎ቲብያን 💎 የተለያዩ ዳዕዋዎች የሚተላለፉበት ቻናል!

🍃💌🍃

በየቀኑ ከቁርአን ልንቀራው ያሰብነውን ቂርአት ፕሮግራማችን በፍፁም አይሳካም በእነዚህ 5 ነገሮች እንጂ :
1⃣የአላህ ተውፊቅ(ማግራት)
2⃣አላህ እንዲያግዘን ሁሌ መለመን
በዱዐ መታገዝ .
3⃣ከስንት ሰአት እስከ ስንት ሰአት
በየትኛው ሰአት ምን ያህል መቅራት
አለብኝ የሚል ፕሮግራም ማስቀመጥ.
4⃣ከወንጀሎች በቻልነው መራቅ .
5⃣ምላስን ከሀሜት ከቅጥፈት በሰዎች
ክብር ላይ ከመልቀቅ መጠንቀቅ.

አላህ ይወፍቀን እስቲ ሁላችንም እንሞክረው
🌿🌿📩🌿🌿


@bin_Husseynfurii

Читать полностью…

💎ቲብያን 💎 የተለያዩ ዳዕዋዎች የሚተላለፉበት ቻናል!

ኢብኑ ተይሚያ ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፦
"ጥሩ ነፍሶች ይቅር በማለትና መልካም በመዋል ይረካሉ።
መጥፎ ነፍሶች በክፋትና ወሰን በመተላለፍ ይረካሉ።"
[ነቅዱ ተእሲሲል ጀህሚያ፡ 1/529]
=
የቴሌግራም ቻናል፦
/channel/IbnuMunewor

Читать полностью…

💎ቲብያን 💎 የተለያዩ ዳዕዋዎች የሚተላለፉበት ቻናል!

ማህበራዊ ሚዲያን ለዲንም ለዱንያም መጠቀም
~
ማህበራዊ ሚዲያን ሃይማኖታችንን ለመማማር መጠቀም ትልቅ ስኬት ነው። ነገር ግን እዚህ ላይ መቆም አይገባም። ሁሉም እንደተገራለትና እንደ ተሰጥኦው ወገኑን በመርዳት ላይ ቢተጋ መልካም ነው። የህክምና ግንዛቤ ያለው ጠቃሚ ትምህርቶችን ያሰራጭ። የስራ ፈጠራና ጠቃሚ የቢዝነስ ሃሳቦች ያሏችሁ ችላ ሳትሉ የምክር አገልግሎት በመስጠት ወገናችሁን እርዱበት። ኤሌክትሮኒክስ ወይም ሌላ ቴክኖሎጂ ተኮር እውቀቱ ያላችሁ መረጃ በመስጠት ማገዝ ትችላላችሁ። በተናጠል የሚከብድ ከሆነ ተመሳሳይ ሙያ ያላቸው ተቀናጅተው ቢሰሩት ብዙ ህዝብ መጥቀም፣ ብዙ አጅር ማፈስ ይቻላል።
ከዚህም አልፎ ማህበራዊ ሚዲያን ለነፃ ግልጋሎት ብቻ ሳይሆን ቢዝነስን ለማቀላጠፍ መጠቀምም ይገባል። የራስንም ይሁን የሌሎች ወንድም እህቶችን ምርትና ሌሎች አቅርቦቶችን፣ ሙያና አገልግሎቶችን ማስተዋወቅ፣ ግብይት ማከናወን፣ ዛሬ እየታየ እንዳለው ድለላ መስራት፣ ተቋማትንና የሚሰጡትን አገልግሎት ማስተዋወቅ፣ ... አስፈላጊ እንቅስቃሴ ነው። ስለዚህ የገባችሁበትም፣ ዝንባሌው ኖሯችሁ እያሰባችሁ ያላችሁም በታማኝነትና በሃላፊነት ለመጥቀምም ለመጠቀምም ነይታችሁ ስሩ።
ባይሆን አላህን ፍሩ! ውሸትን ተጠንቀቁ። የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
” يا مَعشرَ التُّجّارِ ! إياكُم والكذبَ “
እናንተ ነጋዴዎች ሆይ! ውሸትን ተጠንቀቁ!" [ሶሒሑ ተርጊብ: 1793]

ብዙ ነጋዴዎች በተለይ በዚህ ዘመን አመፅ የነገሰባቸው፣ ዱንያ አላህን ከመፍራት የጋረዳቸው ሆነዋል። ወደ ዲን የቀረቡ የሚባሉት እንኳ ከሌሎች የተሻሉ መሆን እያቃታቸው ነው። ያስተውሉ! ነብዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፡-
إن التجار يبعثون يوم القيامة فجارا، إلا من اتقى الله وبر وصدق
“ነጋዴዎች በትንሳኤ ቀን አመፀኞች ሆነው ነው የሚቀሰቀሱት። አላህን የፈራ፣ መልካምን የሰራ እና እውነትን ያወራ ሲቀር።" [አሶሒሓህ፡ 994]
=
የቴሌግራም ቻናል፦
/channel/IbnuMunewor

Читать полностью…

💎ቲብያን 💎 የተለያዩ ዳዕዋዎች የሚተላለፉበት ቻናል!

ሞራላቸው ለተሰበረ አካላት ጠጋኝ ሁን!
የሌሎችን ስብራት ሚጠግን የእርሱ ስብራት እንደሚጠገንለትና ለሌሎች የሚያዝን ለእርሱ እንደሚታዘንለት እወቅ! የሌሎችን ስሜት በመጠበቅ ላይ ዲናችን እጅግ አነሳስቷል።
✍Abu Uwais (Naaf)
/channel/AbuUweis

Читать полностью…

💎ቲብያን 💎 የተለያዩ ዳዕዋዎች የሚተላለፉበት ቻናል!

🔻ጥቂት ምክሮች
ለሙስሊም እህቶች

🔊በኡስታዝ አሕመድ ሼይኽ ኣደም (ሓፊዘሁሏህ)

/channel/Tibyaan54

Читать полностью…

💎ቲብያን 💎 የተለያዩ ዳዕዋዎች የሚተላለፉበት ቻናል!

ነቢያት በጌታቸው ያላቸው መተማመን
~
1⃣- ኑሕ ﷺ :-
{إِنَّ رَبِّی لَغَفُورࣱ رَّحِیمࣱ}
{ጌታዬ በእርግጥ መሓሪ አዛኝ ነው።} [ሁድ፡ 41]

2⃣- ሁድ ﷺ :-

{إِنَّ رَبِّی عَلَىٰ كُلِّ شَیۡءٍ حَفِیظࣱ}
{ጌታዬ በነገሩ ሁሉ ላይ ጠባቂ ነው።} [ሁድ፡ 57]

3⃣- ሷሊሕ ﷺ :-

{إِنَّ رَبِّی قَرِیبࣱ مُّجِیبࣱ}
{ጌታዬ ቅርብ (ልመናን) ተቀባይ ነው።} [ሁድ፡ 61]

4⃣- ኢብራሂም ﷺ :-

{إِنَّ رَبِّی لَسَمِیعُ ٱلدُّعَاۤءِ}
{ጌታዬ በእርግጥ ልመናን ሰሚ ነው።} [ኢብራሂም፡ 39]

5⃣- ሹዐይብ ﷺ :-
{إِنَّ رَبِّی رَحِیمࣱ وَدُودࣱ}
{ጌታዬ አዛኝ ወዳድ ነው።} [ሁድ፡ 90]

6⃣- ዩሱፍ ﷺ :-
{إِنَّ رَبِّی لَطِیفࣱ لِّمَا یَشَاۤءُۚ}
{ጌታዬ ለሚሻው ነገር እዝነቱ ረቂቅ ነው።} [ዩሱፍ፡ 100]

7⃣- ሙሳ ﷺ :-
{إِنَّ مَعِیَ رَبِّی سَیَهۡدِینِ}
{ጌታዬ ከእኔ ጋር ነው። በእርግጥ ይመራኛል።} [ሹዐራእ፡ 62]

8⃣- ሱለይማን ﷺ :-

{فَإِنَّ رَبِّی غَنِیࣱّ كَرِیمࣱ}
{ጌታዬ ተብቃቂ ቸር ነው።} [ነምል፡ 40]

📚 ምንጭ፦ [ፈራኢድ ወፈዋኢድ ሚነል ቁርኣኒል ከሪም]
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
/channel/IbnuMunewor

Читать полностью…

💎ቲብያን 💎 የተለያዩ ዳዕዋዎች የሚተላለፉበት ቻናል!

ባለቤት ከወሰነው በላይ ጨምሮ መሸጥ ይቻላል?
~
ጥያቄ፦
ሱቅ ውስጥ የሚሰራ አንድ ሰው አለ። እቃው ለምሳሌ አንድ ሺ ብር ዋጋ ወጥቶለታል። እሱ ግን 2 ሺ ይሸጠዋል። ከዚያም ጭማሪውን ይወስዳል። ይሄ ነገር ይፈቀዳል?

መልስ፦

ይሄ ተግባር አይፈቀድም። እቃው አንድ ሺ ብር ዋጋ ወጥቶለታል። እሱ 2 ሺ ይሸጠዋል። ከዚያ ጭማሪውን ይወስዳል። ይሄ የማይፈቀድ ተግባር ነው።
አንደኛ፦ ሰዎችን መጉዳት አለበት። በግብይቱ ለሰዎች በመልካም እንዲያስተናግድ ታዞ ሳለ እሱ እየጨመረ ነው።
ሁለተኛ፦ ለባለ ሱቁ ክህደት መፈፀም ነው። ዋጋውን ከፍ ሲያደርግ ሌላ ዘንድ በቅናሽ ስለሚያገኙት ወደዚህ እንዳይመለሱ ያደርጋቸዋል። ይሄ አንድ ነጥብ ነው። በሌላ በኩል የሽያጩ ባለቤት ባለ ሱቁ ነው። ስለሆነም ያገኘው ጭማሪም የባለሱቁ ሐቅ ነው። እንጂ የተቀጣሪው አይደለም።
وفقنا الله وإياكم.
ፈትዋውን የሰጠው ሸይኽ ሙሐመድ ብኑ ሒዛም
ምንጭ፦ /channel/ibnhezam/12749
=

የቴሌግራም ቻናል፡-
/channel/IbnuMunewor

Читать полностью…

💎ቲብያን 💎 የተለያዩ ዳዕዋዎች የሚተላለፉበት ቻናል!

•┈•❀•┈•
وَتَوَكَّلْ عَلَى اللَّهِ ۚ وَكَفَىٰ بِاللَّهِ وَكِيلًا
በአላህም ላይ ተመካ፡፡ መመኪያም በአላህ በቃ፡፡ ሱረቱ አል አሕዛብ (3)
•┈•❀•┈•✍

Читать полностью…

💎ቲብያን 💎 የተለያዩ ዳዕዋዎች የሚተላለፉበት ቻናል!

የአላህን መስጊዶች የሚሠራው በአላህ እና በመጨረሻው ቀን ያመነ፣ ሶላትንም በደንቡ የሰገደ፣ ግዴታ ምጽዋትንም የሰጠ ከአላህም ሌላ ማንንም ያልፈራ ሰው ብቻ ነው፦
9፥18 የአላህን መስጊዶች የሚሠራው በአላህና በመጨረሻው ቀን ያመነ፣ ሶላትንም በደንቡ የሰገደ፣ ግዴታ ምጽዋትንም የሰጠ ከአላህም ሌላ ማንንም ያልፈራ ሰው ብቻ ነው፡፡ እነዚያም ከተመሩት ጭምር መኾናቸው ተረጋገጠ፡፡ إِنَّمَا يَعْمُرُ مَسَاجِدَ اللَّهِ مَنْ آمَنَ بِاللَّهِ وَالْيَوْمِ الْآخِرِ وَأَقَامَ الصَّلَاةَ وَآتَى الزَّكَاةَ وَلَمْ يَخْشَ إِلَّا اللَّهَ ۖ فَعَسَىٰ أُولَـٰئِكَ أَن يَكُونُوا مِنَ الْمُهْتَدِينَ

✍ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
/channel/Wahidcom

Читать полностью…

💎ቲብያን 💎 የተለያዩ ዳዕዋዎች የሚተላለፉበት ቻናል!

🏷️የዛዱል መዓድ ፈታዋ 🌾
فتاوى زاد المعاد
          ቁ/195

ማክሰኞ 7/4/1444 ዓ.ሂ

🔊በኡስታዝ አሕመድ ሸይኽ ኣደም

የዳውንሎድ ሊንኩን ይጫኑ
⏬  ⏬   ⏬   ⏬   ⏬  ⏬

🔎https://bit.ly/3gUDERD
   🔹 🔸 🔹 🔸 🔹 🔸

~~~~
▪️1/ስለ ዛር በሽታ ጥቂት ያብራሩልን ማለትም ዛር አለብን ብለዉ የሚያጎሩና የሚያርዱ ጨሌና መሠል ተግባር ሲያደርጉ የሽርክ ተግባር ነዉ ስንላቸዉ ዛራችን እኮ ነዉ ይላሉ ከአላህ ዉጪ ለምንም ይሁን ለምን ማረድ ማሻረክ እንደሆነ አዉቃለሁ እነሡን ግን  ስለ ዛር እንዴት እናስረዳቸዉ ምንም ቢያደርጉ ከበሽታዉ መፈወስ ይችላሉ

▪️2/ጆሮየን  አመልያ  አድርጌ ነበር  በሠላም  ከወጣሁ  አንድ በግ  አርጀ  ለቤተሠቡ  ሁሉ  አዳርሣለሁ  ወይም  ቤትጠርቸ  አበላለሁ  ብየ ነበር  አልሀምዱሊላህ  በሠላም  ወጣሁ  ባለቤቴን  አርደህ  አከፋፍልልኝ  ወይ ጥራቸው  ሥለው   እንደወጣሽ  አርጃለሁ   አለኝ    ይሄ  ይበቃል እንዴ?  የሡን  ቤተሠቦች ነው ያበላው።

▪️3/ ዝምድና ያላቸው ሰወች ሰውን በመድሀኒት የመግደል ሙከራ ያደርጋሉ
ያ ሰው የሚደረግበት ግን አያቅም ወዳጅ ዘመድ  መሰለው ነው ይህንን አፀያፊ ስራ የሚሰሩት በመሀላቸው ምንም የሚያንገናኝ ነገር የለም ከቅናትና ከምቀኝነት ዉጭ እና ይህንን አፀያፊ ስራቸውን የሚያስተው ምክር ቢለግሱልኝ  እኔም ይህንን ምክር ብልክላቸው ሰምተው ከእዚህ አፀያፊ ስራቸው አላህን ፈርተው  ቢወገዱ ካልተው እነዚህን ሰወች መራቁ እንዴት ይታያል?

▪️4/ባሏ የሞተባት ሴት 4 ወር ከ10 ቀን ከሃጃ በስተቀር ከቤት ማትወጣበት ሃጃው እስከምን ድረስ ነው ሚፈቀደው? ያብራሩልን

▪️5/ሀይድ ላይ ሆኜ እኔ ብዙ ጊዜ ቁርአንን ላለማቋረጥ ብዬ በስልኬ እቀራለሁ ነገር ግን የሀፈዘችና የማይጠፋባት  ከሆነ መቅራት የለባትም ሲሉ   ሰማኋቸው  እኔ ግን አይጠፋኝም  ግን ቶሎ ደጋግሜ ለማክተም በሚል አቋርጨ አላውቅም በዚህ ስራዬ ተጠያቂ እሆናለሁ ወይ? ለምሳሌ በጁማአ ቀን ሱረቱል ከህፍን መቅራት አለ በረመዷንም እነደዚሁ ታዲያ አይጠፋኝም ወይም አውቃለሁ ብዬ 7 ቀን ሙሉ ማቋረጥ አለብኝ እንዴ አብራሩልኝ ስህተት ላይ እሆናለሁ ብዬ ስለምጠራጠር ነው

▪️6/ኢትዮጵያ  ቦታ ገዝቸ አምስት አመት ሊሆነዉ ነዉ አንዴም ዘካ ወቶለት አያዉቅም ይሸጥ ብል ብሩን ያጠፉብኛል ተሽጦ ዘካ አዉጡልኝኳ ብል ልክ እንደ ሠደቃ ትንሽ ብር ብቻ ነዉ አዉጥተን ሠጠንልሽ የሚሉኝ ለማን እንደሚሠጡትም ብዙ አያዉቁም እዛዉ በዛዉ ይጠቃቀሙበታል እና እኔ ሀገር ስገባ ቦታዉን ሸጨ የአምስት አመት በአንዴ ባወጣ እንዴት ይታያል?

▪️7/እህቶቼና አክስቶቼ ከእናቴ ጋር ተጣልተው እያንገራገሩም ታረቁ ብላቸው እምቢ አሉ እኔ እውጭ ነኝ እባካችሁ ምክር ስጡልኝ ስለ ሲለተረሂም በእህቴ ባል በኩልም ችግር አለ ምከሩልኝ

▪️8/እኔ አረብ ሀገር ነዉ ያለሁት ባሌ ኢትዮጵያ  ነዉ እናም አልፎ አልፎ ጫት ይቅማል ተዉ ይህንን ጫት ስለዉ ለዱዓ ሳይሆን የምጠቀመዉ አንዳንዴ ከድብርቴ ለመላቀቅ ነዉ እናም አንቺ ስትመጪ እተወዋለሁ ይለኛል እናም ከሔድኩ በኃላ ቀስ በቀስ የማይተዉ ከሆነ እሡን መጣለት እችላሉሁ?ይሠግዳል ይቀራል ይፆማል የቢዲዓ ተግባር ችግሮችም የሉበትም

▪️9/እኔ ላገባ ነበር የልጅቷ የእናቷ ወንድም ሳውዲ አረቢያ ነው ያለው ውክልና ከአባቷ ከኢትዮጵያ ተቀብሎ መዳር ይችላል?

▪️10/ በገጠር አካባቢ ነው ተወልጄ ያደኩትና በማህበረሰቡ ዉስጥ ተደባዳቢ ሰው እንደ ጀግና ይቆጠር ነበርና ብዙ ሰዎችን ደብድብያለሁ፤ ደም አፍስሻለሁ አሁን ላይ ብዙ የዲን እውቀቶችን እያገኘሁ፤ ወደ ሰላት ወደኢባዳ ስመለስ ያ የሰራሁት ነገር እንቅልፍ ነሳኝ ከፋራውን ቢነግሩኝ።

▪️11/ ስለሙቶ መቀስቀስ ሳናምን እየወላወልን የስም ሙስሊም ሆነን ኖረናል ተውበት አድርገን የአላህን ውዴታ የምናገኝበትን መንገድ ቢያመላክቱን?

▪️12/ዱአ ሲደረግ አላህን በመልካምና ባማሩ ሥሞችህ፣ባህርያቶችህ፣ በፈጠርካቸው ተአምራቶችህ ይሁንብህ ብሎ መለመን ይቻላል?

▪️13/ 'አልሐምዱ' ብሎ ሥም መሠየም አይቻልም የሚሉ ሠዎች አሉ በሸሪዓ እንዴት ይታያል?

~~~~
💥 በተጨማሪም የተለያዩ ትምህርቶችን ለማግኜት ከታች ያሉትን ሊንኮች ይጠቀሙ
🔸🔹🔸🔹🔸🔹
🌐/channel/ahmedadem
~
🌐/channel/zad_qirat
~~~~
🔗https://www.facebook.com/yenegew/
~~~~
📶  http://www.youtube.com/c/ZadulMaad

አላህ በተከበረው ቃሉ እንዲህ ይላል:-
🔅وَتَزَوَّدُوا فَإِنَّ خَيْرَ الزَّادِ التَّقْوَىٰ ۚ وَاتَّقُونِ يَا أُولِي الْأَلْبَابِ
"ስንቅ ያዙ፤ ከስንቆች ሁሉ በላጩ አላህን መፍራት ነው፤ የአእምሮ/ የልብ ባለቤቶች ሆይ ፍሩኝ" ሱረቱል በቀራ /197

Читать полностью…

💎ቲብያን 💎 የተለያዩ ዳዕዋዎች የሚተላለፉበት ቻናል!

ሳዑዲና ሃሎዊን
~
ሰሞኑን በሳዑዲ ሪያድ ውስጥ ሃሎዊን የሚያከብሩ ሰዎች መታየታቸውን ተከትሎ ጫጫታ እያየን ነው። የሳዑዲ መንግስት ላይ፣ ከዚያም በሱ በኩል አቆራርጦ ዑለማዎቹ ላይ፣ አሁን ካሉትም አልፎ ሸይኽ ሙሐመድ ብኑ ዐብዲል ወሃብ ላይ የሚዘምቱ ሰዎችን በተደጋጋሚ አይቻለሁ። የሆነ ነገር በለጠፍኩ ቁጥር ደጋግመው እየመጡ 'ኮሜንት' ላይ ብዙ ነገር የሚለቀልቁም ገጥመውኛል። "ስለዚህ ግን ትንፍሽ አትሉም" ይላሉ። ብዙዎቹ ከሁኔታቸው መውሊድን በማውገዛችን ቂም ያረገዙ እንደሆኑ ያስታውቃሉ።

ሃሎዊን ምንድነው?
-
የእንግሊዝኛ መዝገበ ቃላት ስመለከት ያገኘሁት እንዲህ የሚል ነው፦
Halloween "የሁሉም ቅዱሳን ቀን" ማለት ሲሆን በአብዛኛው እንግሊዝኛ ተናጋሪ በሆኑ ሃገራት የሚከበር በዓል ነው፡፡ የሚከበረውም በፈረንጆች October 31 ነው። ህፃናት የተለዩ አስፈሪ ልብሶችን በመልበስ በየቤቱ እየዞሩ ከረሜላና መሰል ነገሮችን ይጠይቃሉ።
ምንጭ፦ http://en.wiktionary.org/wiki/Halloween

መነሻው ኬልቲክ አካባቢ ቢሆንም አሜሪካ ከገባ በኋላ ወደሌሎች ሃገራት ተሰራጭቷል። ከህፃናት አልሮ በ"አዋቂዎችም" ይከበራል። የሰይጣን አምልኮ ነው እያሉ የፃፉ አይቻለሁ። ሊሆን ይችላል። እኔ ግን ማረጋገጥ አልቻልኩም። በዓሉ መነሻው የጣዖታውያን ልማድ እንደሆነ፣ ከዚያም ከፊል ክርስቲያኖችና የሁዶች እንደሚያከብሩት፣ ከክርስቲያኖችና የሁዶች ውስጥ እራሱ አጥብቀው የሚያወግዙት እንዳሉ አንብቤያለሁ።

ሃሎዊን በኢስላም
~
በኢስላም የትኛውንም የጃሂሊያ (ኢስላማዊ ያልሆነ) ስርአት በዓል ማክበር አይፈቀድም። ነብያችን ﷺ የመዲና ሰዎች ሲያከብሯቸው የነበሩ የፋርስ ዞራስቲያኒዝም ሃይማኖት በዓላትን መከልከላቸው የሚታወቅ ነው። በተጨማሪም "በሰዎች የተመሳሰለ ከነሱው ነው" ብለዋል። [አቡ ዳውድ፡ 4031] ይሄ እጅግ አስፈሪ ማስጠንቀቂያ ነው።

ሃሎዊን በሳዑዲ
~
ሳዑዲ ውስጥ እስከ ቅርብ አመታት ድረስ የሃሎዊን በዓል አልነበረም። የሚፈልግ ስለሌለ ሳይሆን በመንግስት ስለተከለከለ ነበር። የክልከላውን መላላት ወይም መነሳትን ተከትሎ ግን - በአንድ ዌብሳይት ላይ እንዳየሁት - ከባለፈው ዓመት ጀምሮ እየተከበረ ነው። ይሄ በጣም ዘግናኝ ጥፋት ነው። ጥፋቱ በሳዑዲ ስለተፈፀመ የሚቀየር ብይን የለም። ማንም ለዚህ ወግኖ የሚከራከርም የለም። ከኖረም ባይፈፅመው እንኳ የጥፋቱ አካል ነው።

ለኢኽዋኖ - አሕባሽ መን-ጋዎች!
~
ለብዙኛ ጊዜ ደጋግሜ የምናገረው ነገር ቢኖር ሳዑዲ ውስጥ ከዚህም ውጭ ብዙ ጥፋቶች እንዳሉ እናውቃለን። አንዳንድ .. ሎች እንደሚያስቡት ሳዑዲን ፍፁም አድርገን የምንስል አይደለንም።
ግን እናንተ የመጮሁንም የማስጨሁንም ሞራል ከየት አገኛችሁት? ምዬ እናገራለሁ ከአብዛኛቻችሁ ጩኸት ጀርባ ያለው ለኢስላም መቆርቆር አይደለም። የጩኸታችሁ ቀዳሚ መንስኤ ቡድናዊ ልዩነት ነው። ይሄ በዓል'ኮ ዘንድሮ ብቻ ሳይሆን ቀደም ብሎ ጀምሮ ቱርክ ውስጥ ይከበራል? በዚህ መልኩ አስጩሃችሁት ታውቃላችሁ? ለምን? አንዱ ሳዑዲን በዚህ ሰበብ እያብጠለጠለ በለቀለቀበት ረዥም ፅሑፍ ውስጥ ኳታርን ሲያወድስ አይቻለሁ። እስኪ Halloween in Qatar ብለህ ጉግል ላይ ፈልግ። የእውነት ለዲን መቆርቆር ከሆነ ምክንያታችሁ ምነው ስለ ኳታር እስከዛሬ አልጮሃችሁም?! እነዚህ አካላት በተመሳሳይ ጊዜ ብዙ ፊት የሚያሳዩ፣ በተመሳሳይ ጉዳይ የተለያየ ስፍር የሚሰፍሩ፣ ሃይማኖትን ለፖለቲካዊ ንግድ የሚጠቀሙ ቆሻ - ሻ ፍጥረቶች ናቸው።
ሲጀመር የኢኽዋን አንጃ በምን መለኪያ ነው ከሳዑዲ መንግስት የሚሻለው? የቡድኑ መሪ ዑመር ቲልሚሳኒይ ገንዘብ እየከፈልኩ የፈረንጅ ዳንስ ተምሬያለሁ፣ ሲኒማ ለማየት ብዬ ሁለት ሶላቶችን በአንድ ላይ ጀምዕ እያደረግኩ እሰግድ ነበር አላለም? ቀርዷዊ ነፃነትን መተግበር ከሸሪዐ ይቀድማል አላለም? የቡድኑ መስራች ሐሰነል በናና ዩሱፍ አልቀረዳዊ በተጨባጭ ሐዲሥ የተረጋገጠውን የመህዲን መምጣት አላስተባበሉም? መውዱዲ የደጃልን መምጣት አላስተባበለም? ቱራቢ በርካታ መረጃዎችን ረግጦ የቀብር ቅጣት የሚባል የለም፣ ነኪርና ሙንከር የሚባል የለም አላለም? ነብያት መዕሱም አይደሉም አላለም? የዒሳን ዳግም መምጣት አላስተባበለም? ቀረዳዊና ሙርሲ የክህደት ቁንጮ ለሆኑ ጳጳሶች አላህ እንዲምራቸው ዱዓ አላደረጉም? ሰይድ ቁጥብ ከሶሐቦች አልፎ ነቢያትን አልጎነተለም? ሙስሊሙን ኡማ በጅምላ ከኢስላም እያስወጣ አልፃፈም? ሰዕድ አልከታቲኒ በግብፅ ምርጫ ብናሸንፍ አስካሪ መጠጥ አንከለክልም፣ የብልግና ድረ ገፆችን አንዘጋም አላለም? እስኪ ምናችሁ ተሽሎ ነው ምላሳችሁን የምታሾሉት?
የእውነት ለኢስላምና ለሙስሊሞች ተቆርቁራችሁ ከሆነ ይሄንን እያንሸዋረረ የሚያሳያችሁን ቡድናዊ መነፅር አሸቀንጥራችሁ ጣሉና በስርአት አስተምሩ። ኢስላም በሚያስተምረው መልኩ ከሃሎዊንም፣ ከቫሌንታይኑም፣ ከሳዑዲ ብቻ ሳይሆን ከሌሎች ሃገራት ብሄራዊ በአላትም፣ ከኢሬቻም፣ ከገናም፣ ከመስቀልም ፣ ከመውሊድም፣ ወዘተ አስጠንቅቁ። ከፊሎቻችሁ'ኮ ለመስቀል ስታፀዱ እናውቃችኋለን! ከፊሎቻችሁኮ ኢሬቻን ለማውገዝ የምትሽኮረመሙ ናችሁ። ከሌሎቻችሁ'ኮ ሉሲን ተከትላችሁ ከሃገር ሃገር ስትዞሩ ነበር። የምን ማስመሰል ነው? እምቢ ብላችሁ ስለ ሳዑዲ ብቻ ከሆነ ማውራት የምትፈልጉት ቢያንስ በሌላ ሃገር የሌለ ጥፋት እየጠበቃችሁ ብትጮሁ ይሻላችኋል! ያለበለዚያ ግን ጧት ማታ ሙገሳ በምትሰፈሩላቸው ሃገራት ውስጥ ያለው ሲወጣ አስመሳይነታችሁ ይጋለጣል።

በርግጥ ለኛም ቢሆን የሳዑዲ ጥፋት ይለያል! ምክንያታችን ግን እንደናንተ የገነፈለ ጥላቻ አይደለም። አዎ ከሌሎቹ በበለጠ ሳዑዲ ላይ ይሄ መሆኑ ያመናል። ተሽለው መገኘት እንዳለባቸው ስለምናምን። ለሃገሪቱ ካለን መቆርቆር። የኢስላምና የሙስሊሞች ምልክት (symbol) በመሆኗ።
የአሕባሸና የኢኽዋን ጩኸት ግን "ከፍየሏ በላይ ነው።" የተጠራቀመ ቂም ስላላቸው አጋጣሚ እየጠበቁ ከሳዑዲ መንግስት አልፈው ዑለማዎች ላይ ዘመቻ ለመክፈት ነው አድብተው የሚጠብቁት። የሙዚቃ ኮንሰርት ሲካሄድ ልክ ዑለማዎቹ የፈቀዱ ይመስል እነሱም ላይ ጭምር ይዘምታሉ። ልክ በግልፅ ሙዚቃ የሚፈቅደውን ቀረዷዊን ሲያንቆለጳጵሱ እንደማናውቃቸው። ልክ ቱርክና ኳታር የሙዚቃ ድግስ፣ ከዚህም አልፎ ብዙ ነገር እንደሌለ። ይሄው በቅርቡ ለሚካሄደው የዓለም ዋንጫ ኳታር ውስጥ የሙዚቃ ድግስ እየተዘጋጀ እንደሆነ አልጀዚራ እየዘገበ ነው። ሪያድ ሲሆን እንደምታወግዙት ደውሐ ሲሆን ታወግዙታላችሁ? አታደርጉትም። ምክንያቱም መስፈሪያችሁ የሚታወቅ ነው። حصانة إخوانية
.
ሁኔታችሁን እያየሁ ልመለስ እችላለሁ፣ ኢን ሻአ'ላህ።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
/channel/IbnuMunewor

Читать полностью…

💎ቲብያን 💎 የተለያዩ ዳዕዋዎች የሚተላለፉበት ቻናል!

አሰላሙዓለይኩም ወራህመቱሏህ ወበረካቱህ

ማንን ጓደኛ አድርገን እንደምን ትዝ እንመልከት

ረሱል ﷺ እንዲህ አሉ፦

"ሰዉ በጓደኛዉ ዲን (ሃይማኖት) ላይ ነዉ። አንዳቹህ ማንን ጓደኛ አድርጎ እንደሚይዝ ይመልከት"

📚 [مسند أحمد 8417

Читать полностью…

💎ቲብያን 💎 የተለያዩ ዳዕዋዎች የሚተላለፉበት ቻናል!

አደራ! ቁርኣን እንቅራ
~
በርግጠኝነት እዚህ ሶሻል ሚዲያ ላይ ከሚርመሰመሱ ወገኖቻችን ውስጥ ቁርኣን ያልቀሩ ብዙ ወገኖች ይኖራሉ። ወላሂ ሊቆጨን ይገባል። በዚህ አማራጮች በበዙበት ዘመን እንዴት ድንቁርናን አሚን ብለን ተቀብለን በጨለማ ውስጥ እንኖራለን? የትም ብንሆን ካለንበት ቦታ ሆነን መማር እንደሚቻል የሚታወቅ ነው። አላህ ባገራልን መንገድ እንማር። ነብያችን ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም "ከናንተ በላጫችሁ ቁርኣንን የተማረና ያስተማረው ነው" ብለዋል። [ቡኻሪ፡ 5027]
ስለዚህ ያልተማርን ጊዜ ሰጥተን እንማር። የተማርን መልክቱን እንማር፣ ባወቅነው እንስራ። በየቀኑ ከጊዜያችን ውስጥ ለቁርኣን ድርሻ ይኑረን። በምንችላት መጠን ለመሐፈዝ እንሞክር። የእድሜ መግፋት ቁርኣን ከመማር አያግድም። በርካታ ሶሐቦች በጎልማሳነት ዘመናቸው ነው ቁርኣን የቀሩት። ሸይኽ ዐብዱል ሙሕሲን አል0ባድ "አንድ ሰው ከሃምሳ አመቱ በኋላ ቁርኣን ሊሐፍዝ ይችላል ወይ?" ተብለው ተጠይቀው ነበር። ምላሻቸው እንዲህ የሚል ነበር፦
"አዎ! እኔ ራሱ ከሃምሳ በኋላ ቁርኣን ከሐፈዙት ውስጥ ነኝ። ሶሐቦች - ረዲየላሁ ዐንሁ - ትልልቅ ሰዎች ሆነው ነው ኢስላም ያገኛቸው። ከመሆኑም ጋር ቁርኣንን ሐፍዘዋል።"
ስለዚህ በየትኛውም ምክንያት በልጅነቱ ቁርኣን ያልቀራ ሁሉ እራሱን አያዳክም። "በአላህ ፈቃድ እችላለሁ" ብሎ ይነሳ። ኢንሻአላህ ይችላል። አለማወቅን ታቅፈን ፈፅሞ ምቾት ሊሰማን አይገባም። ሰው እንዴት ቁርኣን ሳይቀራ እድሜውን ይፈጃል?!
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
/channel/IbnuMunewor

Читать полностью…

💎ቲብያን 💎 የተለያዩ ዳዕዋዎች የሚተላለፉበት ቻናል!

🕰 ጊዜን በአግባቡ ስለመጠቀም… አጭር ማስታወሻ

🔖 በኦዲዮ (MP3)

🎙በሸይኽ ኢልያስ አሕመድ
/channel/ustazilyas/839
____
🏳️ የኡስታዝ ኢልያስ አህመድ የትምህርት መድረክ
https://www.facebook.com/ustathilyas

Читать полностью…

💎ቲብያን 💎 የተለያዩ ዳዕዋዎች የሚተላለፉበት ቻናል!

ሪሳለቱ-ል-ሒጃብ ከክፍል ①–⑨
በኡስታዝ አሕመድ ሸይኽ ኣደም

Читать полностью…
Subscribe to a channel