tibyaan54 | Unsorted

Telegram-канал tibyaan54 - 💎ቲብያን 💎 የተለያዩ ዳዕዋዎች የሚተላለፉበት ቻናል!

2303

🍂የቲብያን ቻናል ዋና አላማው አላህ ኢኽላሱን ይስጠንና በተቻለን አቅም ጠቃሚ ናቸው የምንላቸው ወቅታዊ ሙሃደራዎችን እንዲሁም ጠቃሚ ማስታወሻዎች አጫጭር ፁሁፎችና ፎቶዎችንምን ! ላልደረሳቸው ማድረስ ነው። «السلفية منهجي» https://t.me/joinchat/AAAAAEPOgchGXF37Mja27A

Subscribe to a channel

💎ቲብያን 💎 የተለያዩ ዳዕዋዎች የሚተላለፉበት ቻናል!

🌴 በልጅ አስተዳደግ ዙሪያ
ለወላጆች የተሰጠ ምክር 🌴



የዕለት እሁድ 2/3/1445ዓ.ሂ

ሙሓደራ

🔊በኡስታዝ አሕመድ ሸይኽ ኣደም

የዳውንሎድ ሊንኩን ይጫኑ
⬇ ⬇ ⬇ ⬇

🔎 https://urlz.fr/nD5R
🔸 🔹 🔸 🔹 🔸
🌐/channel/ahmedadem
~~~~
https://www.facebook.com/yenegew/
~~~~
📶http://www.youtube.com/c/ZadulMaad

📚"ዒልም ማለት አላህን መፍራት ነው!"
አል-ኢማሙ ማሊክ

Читать полностью…

💎ቲብያን 💎 የተለያዩ ዳዕዋዎች የሚተላለፉበት ቻናል!

ቢያውቁ ኖሮ...

🔅ይህች የዱኒያ ህይወት በውስጧ ከያዘቻቸው ሃብትና አጓጊ ጌጣ-ጌጦች ጋር በሙሉ መታለያና ከጊዜ በኋላ የሚያበቃ ጨዋታ ብቻ እንጂ ሌላ ምንም አይደለችም።

🔅እውነተኛ እና የዘላለም ህይወት ማለት የኣኺራህ ሃገር ህይወት ነው። ሰዎች ይህን ቢያውቁ ኖሮ የዚችህን ጠፊና አላቂ ዓለም ህይወት ከኣኺራህ ባላስበለጡ፤ በርሷም ተታለው ኣኺራቸውን የሚያበላሽ ስራ ባልሰሩ ነበር።

✍ኡስታዝ አሕመድ ሸይኽ ኣደም
30/12/1444 ዓ.ሂ
@ዛዱል መዓድ
🔹🔸🔹🔸🔹🔸🔹
🌐/channel/ahmedadem
አላህ በተከበረው ቃሉ እንዲህ ይላል:-
🔅وَتَزَوَّدُوا فَإِنَّ خَيْرَ الزَّادِ التَّقْوَىٰ ۚ وَاتَّقُونِ يَا أُولِي الْأَلْبَابِ
"ስንቅ ያዙ፤ ከስንቆች ሁሉ በላጩ አላህን መፍራት ነው፤ የአእምሮ/ የልብ ባለቤቶች ሆይ ፍሩኝ" ሱረቱል በቀራ /197

Читать полностью…

💎ቲብያን 💎 የተለያዩ ዳዕዋዎች የሚተላለፉበት ቻናል!

🍃ዘምዘም ውኃ የመጠጣት
አደብና ዱዓእ

▪️የዘምዘም ውኃ የተባረከ፣ ምድር ላይ ካሉ ውኃዎች ሁሉ የላቀና በላጩ፤ ለተራበ ሰው ምግብና ለታማሚ ፈውስ እንደሆነ ነቢዩ ﷺተናግረዋል።
አላህ ዘምዘምን ከቦታዎች ሁሉ መርጦ ከተከበረው ቤቱ (ከዕባህ) ዘንድ ማድረጉም የዘምዘምን ክብር ከሚያሳዩ ነገሮች መካከል አንዱ ነው።

▪️ዘምዘምን በጥሩ ኒያህ (መልካምን ነገር አቅዶ) መጠጣት ተወዳጅ ተግባር ነው።ለምሳሌ ኢማንና የዲን ዕውቀትን፣ ጥሩና ደጋግ ልጆችን፣ ጤንነትን፣ ሰፊና ንጹሕ ሲሳይን ወዘተ ማግኘትን አቅዶና ነይቶ፣ እንዲሁም ዱዓእ አድርጎ መጠጣት ይገባል።
ታላቁ ሰሓቢይ ዐብዱሏህ ኢብኑ ዐባስ ዘምዘም ሲጠጡ የሚከተለውን ዱዓእ ያደርጉ እንደነበረ ዳረቁጥኒይና ሌሎችም ዘግበዋል፥
"اللهم إني أسألك عِلما نافعا ورزقا طيبا وشِفاءً مِن كلِ داء"
አላህ ሆይ ጠቃሚ ዕውቀትን፣ ሰፊ/መልካም ሲሳይን፣ ከበሽታዎች በሙሉ ፈውስን እጠይቅሃለሁ"::

ዘምዘም ሲጠጣ:-
▪️1/ቀድሞ ቢስሚላህ ማለት፣
▪️2/ቀድመው ሁለት ጊዜ ትንንሽ ፉት እያሉ በመቅመስ ሶስተኛው ላይ በደምብ ግጥም አድርጎ መጠጣት፣
▪️3/ ሲጠጡ በዛ አድርጎ (ጠግቦና ሆድን ሞልቶ) መጠጣት፣
▪️4/ጠጥተው እንደጨረሱ ከላይ የተገለጸውን ወይም ተመሳሳይና የግል ጉዳይን የሚገልጽ ዱዓእ ማድረግ ይመረጣል።
በርካታህ ሊቃውንት ሰሒሕ/ትክክለኛ ባሉት ሐዲሥ እንደተነገረው "ዘምዘም ውኃ ለተጠጣለት ዓላማ ይሆናል"። መካህ ሐረም ከሚገኘው ዘምዘም ውጪ ዓለም ላይ የትም ተመሳሳይ ትሩፋትና ጥቅም ያለው የተባረከ ውኃ የለም። ሊኖርም አይችልም።

✍️ኡስታዝ አሕመድ ሸይኽ ኣደም
@ ዛዱል-መዓድ

🔎 /channel/ahmedadem

Читать полностью…

💎ቲብያን 💎 የተለያዩ ዳዕዋዎች የሚተላለፉበት ቻናል!

📢 ማስታወቂያ

🕋ልዩ የሐጅና ዑምራ አፈጻጸም ስልጠና ኮርስ
በኡስታዝ አሕመድ ሸይኽ ኣደም


☄ቦታ፥ ፉሪ በድር መስጂድ
ቀን የፊታችን እሁድ ዙል-ቀዕዳህ 8/1444 ዓ.ሂ
#(ግንቦት 20/2015)

🕰ሰዓት፥ ከጠዋቱ 3:00- 6:00

☄ስልጠናው ለወንዶችም ለሴቶችም ሲሆን ትምህርቱ በምስል የተደገፈ ይሆናል።
#ታዳሚዎች ስለሐጅና ዑምራ ለሚኖራቸው ጥያቄም መልስና ማብራሪያ ይሰጣል
      🔸🔹🔸🔹🔸🔹
🌐/channel/ahmedadem
~~~~
🔗https://www.facebook.com/yenegew/
~~~~
📶  http://www.youtube.com/c/ZadulMaad

📚"ዒልም ማለት አላህን መፍራት ነው!"
አል-ኢማሙ ማሊክ

Читать полностью…

💎ቲብያን 💎 የተለያዩ ዳዕዋዎች የሚተላለፉበት ቻናል!

ሰበር!
የረመዷን ጨረቃ በዛሬው እለት ማየት አልተቻለም። ስለዚህ ነገ ሻዕባን 30 ሆኖ ይውላል።

Читать полностью…

💎ቲብያን 💎 የተለያዩ ዳዕዋዎች የሚተላለፉበት ቻናል!

"#ሁሉም ጸሐፊ ያልፋል፤ነገር ግን የፃፈው በሙሉ ይቀራል፤አላህ በሰጠህ እጆችህ የቂያማህ ቀን ስታየው የሚያስደስትህንና የሚያኮራህን ነገር እንጂ አትፃፍ!"
✍ኡስታዝ አሕመድ ሼይኽ አደም (ሓፊዘሁሏህ)

/channel/ahmedadem

Читать полностью…

💎ቲብያን 💎 የተለያዩ ዳዕዋዎች የሚተላለፉበት ቻናል!

መሬት መንቀጥቀጥ መንስዔው ምንድነው?

ኢብኑ ባዝ ረሂመሁላህ እንዲህ ይላሉ፦
“በነዚህ ቀናት በተለያዩ አቅጣጫዎች የተከሰቱት የመሬት መንቀጥቀጦች፤ አላህ ጥራት ይገባውና ባሮቹን ለማስፈራራት እና ለማስጠንቀቅ ከሚያሳያቸው ምልክቶች አንዱ ለመሆኑ ምንም ጥርጥር የለውም። ከመሬት መንቀጥቀጥ እና ሌሎችም ሰዎች የሚጎዱ እና የተለያዩ ጉዳቶችን የሚያስከትሉ እና ሰዎችን የሚያስከፉ ክስተቶች ሁሉ ከሺርክ እና ከአመፅ መንስኤዎች የተፈጠሩ ናቸው።”
📚መጅሙዕ ፈታዋ ወመቃላት (9/149)


/channel/sultan_54

Читать полностью…

💎ቲብያን 💎 የተለያዩ ዳዕዋዎች የሚተላለፉበት ቻናል!

አሳምረህ ለምን
----------------------

ኡስታዝ ሻሚል ሙዘሚል

𒊹︎︎︎አጫጭርና ጠቃሚ መልዕክቶች ለማግኘት ይቀላቀሉን☟︎︎︎ ☟︎︎︎
𑁍𑁍𑁍𑁍𑁍𑁍𑁍𑁍𑁍𑁍𑁍𑁍
❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀
☀️ሁዳ መልቲሚዲያ/Huda Multimedia

ቴሌግራም 👇
t.me/huda4eth

ፌስቡክ👇
fb.com/huda4eth

ዩትዩብ👇
http://www.youtube.com/c/HudaMultimedia

Читать полностью…

💎ቲብያን 💎 የተለያዩ ዳዕዋዎች የሚተላለፉበት ቻናል!

በቤተ ክርስቲያናቸው ውስጥ የተፈጠረውን ልዩነት የሚይዙበት መንገድ የሚገርም ነው። "አዛን ለምን በኦሮምኛ አይደረግም?" አይነት ሙግት በዘመቻ መልክ ይዘዋል። ሁሌ መርሃቸው ምቀኝነት ነው። በትምህርት ተቋማት ሙስሊሞች መብታቸውን ሲጠይቁ የምቀኝነት ጥያቄ ያነሳሉ። "ለኛም የፀሎት ቦታ ይሰጠን" "ለኛም ነጠላ ይፈቀድልን" ይላሉ። ሰው እንዴት ምቀኝነትን ቀኖና አድርጎ ይይዛል?
በመጅሊሱ ገብቶ ማቡካት! በቤተ ክህነቱ ችግር ዙሪያም ወደ ኢስላምና ሙስሊሞች ጣትን መቀሰር! የሚገርሙ ናቸው። በተረፈ ቤ/ክ ለምን የመብት ጥያቄ እንደሚነሳባት ራሳችሁን ጠይቁ። የኢትዮጵያን ታሪክ በስሱ የሚያውቅ ሁሉ የሚደርስበት ነው። ዛሬም ታቦት ወረደ፣ ፀበል ፈለቀ እየተባለ የሚፈፀመው የመሬት ወረራ ያስመረራቸው ብዙ አካላት አሉ። እንዲህ አይነቱን ነውር "አዛን በኦሮምኛ ለምን አይደረግም" እያሉ ማስቀየስ አይቻልም። አዛን በአማርኛም አይደረግም። አዛንና ሶላት ቁርኣን በወረደበት ነብያችን ﷺ ባስተማሩበት ቋንቋ በዐረብኛ ነው የሚፈጸሙት። ግእዝን ከዚህ ጋር ማነፃፀር የማይመስል ነገር ነው። መፅሀፍ ቅዱስ በግእዝ አልወረደም። እየሱስም ﷺ በግእዝ አላስተማረም። እንዴት ነው ታዲያ ዐረብኛ ከግእዝ ጋር የሚነፃፀረው? በዚያ ላይ ግእዝ ተናጋሪ ህዝብ የሌለው ጣረሞት ላይ ያለ ቋንቋ ነው።
የሆነ ሆኖ ችግራችሁን በራሳችሁ መንገድ ለመፍታት እንደ መሞከር አጉል ብልጠት መጠቀማችሁ አያዋጣችሁም።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
/channel/IbnuMunewor

Читать полностью…

💎ቲብያን 💎 የተለያዩ ዳዕዋዎች የሚተላለፉበት ቻናል!

💰"ሰደቃ እና በአላህ መንገድ ላይ መታገል (ጂሃድ) ይመሳሰላሉ። ፈሪ የሆነ ሲርበተበት ጀግናው ደግሞ በፅናት መለገሱን ይቀጥላል።"
📖ኢብኑ ተይሚያ (አልፈታዋ: 14/95)

Читать полностью…

💎ቲብያን 💎 የተለያዩ ዳዕዋዎች የሚተላለፉበት ቻናል!

የረጀብ ወር ለየት ያለ ዒባዳ አለውን?

🔸ብዙ ሰዎች በርካታ ግዴታነታቸው ወይም ሱናነታቸው የተረጋገጡ ነገሮችን እየተዉ በዲኑ መሰረት የሌላቸው ቢድዓ የሚባሉ ነገሮች ላይ ሲሸቀዳደሙ ይታያል! ይህ ከሸይጣን ዘዴዎች መካከል አንዱ መሆኑን በማወቅ ልንጠነቀቅውና የተፈቀደልንን ብቻ በመስራት ወደ ጌታችን ልንቃረብ ይገባናል::

በካላንደር መሰረት ከነገ ወዲያ ጁምሙዓ አንድ(1) ብሎ የሚጀምረውን የረጀብን ወር በተመለከተ በሰሒሕ ሐዲሥ የተነገረለት ተጨማሪ/ለየት ያለ ሰላትም ይሁን ጾም አልተደነገገምና ከቢድዓ እንጠንቀቅ በሱናው እንብቃቃ!

ኢስራእና ሚዕራጅም ቢሆን በረጀብ ወር እንደነበረ በትክክለኛ ዘገባ አልተነገረም:: ቢነገርና መች እንደነበረ ቢታወቅ እንኳ ኢስራእና ሚዕራጅ ተብሎ የሚከበር በዓል የለም ነቢዩም صلى الله عليه وسلم ይሁን ሰሓቦች رضي الله عنهم አላደረጉትም

ረጅብ ወር ላይ የአብሬት መውሊድ እያሉ መጓዝና ማክበርም የነቢዩን
صلى الله عليه وسلم
ዲን ከተረዳና ሱናቸውን ከሚከተል ሰው የሚጠበቅ ተግባር አይደልም!

✍ ኡስታዝ አሕመድ ሸይኽ ኣደም
ረቡዕ 29/6/1440 ዓ.ሂ
@ዛዱል መዓድ

🔹🔸🔹🔸🔹🔸🔹
🌐/channel/ahmedadem

Читать полностью…

💎ቲብያን 💎 የተለያዩ ዳዕዋዎች የሚተላለፉበት ቻናል!

🏷️የዛዱል መዓድ ፈታዋ 🌾
فتاوى زاد المعاد
          ቁ/206

ረቡዕ 25/6/1444 ዓ.ሂ

🔊በኡስታዝ አሕመድ ሸይኽ ኣደም

የዳውንሎድ ሊንኩን ይጫኑ
⏬  ⏬   ⏬   ⏬   ⏬  ⏬

🔎https://bit.ly/3GHxQUU
   🔹 🔸 🔹 🔸 🔹 🔸
~~~~
▪️1/ካልሲ አድርገን መፀዳጃ ቤት ብንጠቀም እና ካልሲያችን ላይ ሽንት ተረጭቶብናል ብለን ከሰጋን ወይም በትክክል ተረጭቶብን ከሆነ ውሀ በመርጨት ብቻ ማፅዳት እንችላለን ?

▪️2/ከመጝሪብ በኋላ እቃ መከደን እንዳለበት አውቃለሁ ግን ውኃ በአካባቢያችን የሚመጣው በሳምንት አንድ ቀን ነው እና ባለው እቃ ሁሉ እንሞላለን በዚህም ለሁሉም እቃ ክዳን ስለማናገኝ በተገኘው ማንኪያ ወይም እንጨት ነገር ጣል እናደርግበታለን ይህ ነገር እንዴት ይታያል ?

▪️3/ኸምር የሚዞርባቸው ሆቴል ውስጥ ከኸምር ጋ ሳይነካኩ ሌላ አዳራሽ ወይም ክፍል ውስጥ ሰርግ ለመደገስ፣ለምሳ ግብዣ፣ለስራ ጉዳይ ስብሰባ እና ለዲን መሹራዎች መጠቀም በሸሪአ እንዴት ይታያል?

▪️4/አንዲት ሴት ያለባልዋ ፈቃድ የወሊድ መከላከያ መያዝ ትችላለች

▪️5/ለሴት ልጅ ሂል(ሶሉ ድፍን ሆኖ ከፍ ያለ) ጫማ ማድረግ ይቻልላታል ወይ?

▪️6/የባለቤቴ ወንድም ትዳር መያዝ ይፈልጋል ግን በቂ የሆነ ብር የለውም ባለቤቴ ዛካ የሚያወጣው ብር ለሱ መስጠት ይችላል ወይ?ከተቻለስ በተሰጠው ብር ትዳር ቢይዝበትስ? አብሮን ነው የሚኖረው እሱም በአቅሙ ዘካ ያወጣል

▪️7/ባሌ  በአንድ ከፈታኝ ብርኃላ ወደ ቤተሰቦቼ አልሄድኩም ልጆች ስላሉን እዛው ቤት ውስጥ ነው ያለሁት ባሌም  አለ እሱ ሲኖር እንደአጅ ነቢይ  እጠነቀቃለው ከተፋታን አመታት ተቆጥረዋል አንድ ቤት መኖር እዴት ይታያል ጀዛኩሙላህ ኸይር

▪️8/እኔ በሰው ሀገር ልጅ ወልጄ ነበር ሰዎች በተደጋጋሚ ልጀን በተደጋጋሚ ከሰው ጋር እንደማልከው ምየ ነበር ነገር ግን እዚህ ስለተቸገርኩ ከሰው ጋር ላኩት መሃላየ ከፋራ አለው?ምን ያህል ጊዜ እንደማልኩ አላውቅም ያብራሩልኝ

▪️9/እናትና አባቴ አይስማሙም ከ10አመት ወዲህ አባቴ በጣም ያስቸግራታል እሷ ገጠር አሱ አዲስ አባ ነው  ሉለሰራችውን አይበላም ምግብ ሲሰጠው ተቀብሎ ይደፋዋል ወይ ም ለድመት ይሰጣል ቅመቅመሞችን ይደብቃል ረመዷንን ራሱ በስርኣት መፆም አልቻለችም ሩቃ ስናስደርገንለት መድሃኒቱን ይደፋዋል ፣እናቴ አዲስ አባ በቤት ተከራይታችሁ ውሰዱኝ አለችኝ እኛንም ለእናታችን የሆነ ነገር ስናደርግ ይረግመናል እሷ ፍች ብትጠይቅ ሀራም ይሆናል?እኛስ ለሷ ለብቻዋ ብንከራይላት እሱ እሺ ስለማይል እርግማን ይደርስብናል?ያብራሩልን

▪️10/እህቴ ስታገባ በሰው ሀገር ነበር እኔም እናቴን በተደጋጋሚ አጎቴን እንዲያሳስር አድርጊ ብያት እሺ ብላኝ እህቴ አገባች አሁን 3ልጅ ወልዳለች አሁን ላይ እናቴ አጎቴ እንዳላሳሰራትና የአካባቢ ሰዎች ቃልቻ ጠርተው እንዳሳሰሯት ነገረችን ኒካው ልክ ነው ወይስ ምን ማድረግ ይሻላል?ያብራሩልን

▪️11/አንድ ሰው እህቴን ለጋብቻ ጠይቆ ነበር ነገር ግን ምንም ዲንም ሆነ የዲን አሰር አይታይበትም ሆኖም መቀየር እንደሚፈልግ ነግሮናል እሷ ግን ማሻአላህ በዲኗ ጎበዝ የምትባል አይነት ናት ስለዚህ ምን ማድረግ አለብን? የመቀየር ፍላጎት እንዳለው በምን ማወቅ እንችላለን

▪️12/የፈጅር ሶላት እንቅልፍ እያሞኘኝ  12ሰኣት ነው የምነሳው አንዳንዴ 11ተኩል ነው የምነሳው ፀሃይ ከወጣች በኃላ የተጠላ ነው ሲባል ሰምቼ  ስላጠራጠርኝ ሱናውን አልሰግድም ምን ያህል ሰኣት ድረስ እንደሚቻል ያብራሩልኝ

▪️13/ሴት ተማሪዎች ትምህርት ቤት ውስጥ የኡዱእ ማድረጊያው ከወንዶች ጋር  አንድ ቦታ ላይ ነው ፊታችንን ስንታጠብ እጃችንንም እስከርናችን ስናጥብ ወንዶች ያዩናል እንደዞሁም ራሳችንን ለማበስ ሻርፕ ስናወልቅም ያዩናል
በዚህ ሁኔታ ሻርፑን ሳናወልቅ ማበስ እንችላለን?አስተባበሱስ ከጆሮም ጭምር ነው?ቢያብራሩልኝ።

▪️14/ከፈርድ ውጪ በቀን 12 ረካኣ የሱና ሶላቶችን የሰግደ  አላህ በጀነት ቤት ይገነባለታል የሚለው ሀዲስ ሁሉንም የሱና ሶላቶችን ያካትታል ?ወይስ የተነገሩ አሉ?

▪️15/የተገነጣጠሉ ወይም የተቀዳዱ ቁርኣኖችን እንዴት እንያዝ?ማቃጠሉስ እንዴት ይታያል?

▪️16/አንድ ቀን እየተፆመ አንድ ቀን እየታለፈ የሚፆም ሱና ፆምን ስንፆም  ሰኞና ሀሙስ ከሁለት አንዱ የሚታለፍበት ቀን ሲሆን ከምናጣው ብለን ችግር አለው?

~~~~
💥 በተጨማሪም የተለያዩ ትምህርቶችን ለማግኜት ከታች ያሉትን ሊንኮች ይጠቀሙ
🔸🔹🔸🔹🔸🔹
🌐/channel/ahmedadem
~
🌐/channel/zad_qirat
~~~~
🔗https://www.facebook.com/yenegew/
~~~~
📶  http://www.youtube.com/c/ZadulMaad

አላህ በተከበረው ቃሉ እንዲህ ይላል:-
🔅وَتَزَوَّدُوا فَإِنَّ خَيْرَ الزَّادِ التَّقْوَىٰ ۚ وَاتَّقُونِ يَا أُولِي الْأَلْبَابِ
"ስንቅ ያዙ፤ ከስንቆች ሁሉ በላጩ አላህን መፍራት ነው፤ የአእምሮ/ የልብ ባለቤቶች ሆይ ፍሩኝ" ሱረቱል በቀራ /197

Читать полностью…

💎ቲብያን 💎 የተለያዩ ዳዕዋዎች የሚተላለፉበት ቻናል!

አዳማ/Adama#
🦯በጥምቀቱ ዋዜማ አሁን 11 ቀበሌ አቡበክር መስጂድ ከጁሙዓህ ኹጥባህ በፊት ሁለት ወጣት ክርስቲያኖች እስልምናን ተቀብለዋል፤ ስማቸውንም በራሳቸው ምርጫ አንዱ ሁሰይን ብሎ እራሱን ሲሰይም ሌላኛው ደግሞ ሀሰን ብሎ እራሱን ሰይሟል። አሏሁ አክበር!!
የኹጥባውም ርዕስ "ወጣቶች ማንን ነው አርዓያ ማድረግ ያለባቸው?" የሚል ነው።
✍Abu Uwais Nafyad
/channel/AbuUweis

Читать полностью…

💎ቲብያን 💎 የተለያዩ ዳዕዋዎች የሚተላለፉበት ቻናል!

🌸"ጌታችን ሆይ ምላሳችንን አስረህ የሰውነታችን ክፍሎች በሚመሰክሩበት ቀን በራህመትክ ሰትረን"!🤲

Читать полностью…

💎ቲብያን 💎 የተለያዩ ዳዕዋዎች የሚተላለፉበት ቻናል!

በሰው ስራ ትልቅ ሰው አይኮንም

▪️ከእገሌ ጋ ፎቶ ተነሳሁ፣እገሌ ፈረመልኝ፣ እገሌን ትመስላለህ ተባልኩ!
እሱ እኮ ዘመዴ ነው፣ የእገሌ አድናቂ ነኝ!
▪️በዚህ አንተ ምን ትጠቀማለህ?!
ጊዜህን በሚጠቅም ነገር ማሳለፍ ትትህ በነዚህና መስል ነገሮች ራስህን አታታልል።
የምታደንቀው ሰው ጥሩ ስራ ሰርቶ ከሆነ ትልቅ የሆነው አንተም ሰርትህ ትልቅ ሰው ለመሆን ጣር።
لا تقل أصلي وفصلي أبدا-
إنما أصل الفتى ما قد حصل.
▪️እኔ የእገሌ ልጅ ነኝ፣ የእገሌ ወላጅ ነኝ፣ አባቴ፣ ወንድሜ፣ እንዲህ ነበር፣ እንዲህ ነገር አላቸው ወዘተ... አትበል።
ሰው በሰራው መልካም ስራ፣ ባለው ሙያና ችሎታው ነው የሚከበረውና ክብርን የሚያተርፈው።
▪️ሰውን ዱኒያም ይሁን ኣኺራህ ላይ የሚጠቅመውና እውነተኛ ክብርን የሚያከብረው ራሱ ደክሞ የሰራው ስራ ብቻ ነው።
▪️ዱኒያ ላይ ለፍተው የከበሩ ሰዎች አድናቂና ለስኬታቸው (አጨብጫቢ) ብቻ መሆን ዳገትን ወጥቶ ከፍታ ላይ መኖርን በመፍራት ሁሌም ገደልና ጉድጓድ ውስጥ መኖርን መምረጥ ነው።
▪️ኣኺራም ላይ ቢሆን "ከአላህ የሚያርቅ ትልቅነትና የትልቅ ሰው ቤተሰብ አባል መሆን አይጠቅምም" ነው የተባለው።

🔅በዘመናችን ሰርቶ መክበር ያቃታቸው፣ ስንፍና የተቆጣጠራቸው፣ አካላቸው ትልቅ አዕምሯቸው ትንሽ የሆነ፣ ከመተኛትና ከመብላት ውጪ ምንም ሳይሰሩ ኸይርም ይሁን ሸር ሰርተው ዕውቅና ካተረፉ ሰዎች ጎን በመቆም ታዋቂነትና ትልቅነት ለማግኘት የሚጥሩ ሰዎች በዝተዋል።
ትልቅ ከሚሏቸው ሰዎች ጋ አብሮ ለመታየትና ፎቶ ለመነሳት ራሳቸውን ስተው ይሮጣሉ (ይቀብጣሉ)።

▪️ወንድሜ እውነተኛ ትልቅነት የሚገኘው በስራ ነው።
ዋናው ነገር  የአኺራህ ትልቅነት ነው።
▪️ይህ ደግሞ አላህን በመፍራት፣ በመልካም ስነምግባርና በበጎ ስራ ነው የሚገኘው!!

🔅ጊዜን በማይጠቅም ነገር ማጥፋትና እንደ ሕጻን እቃቃ መጫወቱን ትተን ፡ ያዘዘንን በመታዘዝ፣ የከለከለንን በመከልከል፣ የነገረንን አምኖ በመቀበል፣ በውሳኔው በመደሰት ከአላህ ጋር ያለንን ግንኙነት እናሳምር።

▪️ለማይቀረው ጉዞም ስንቅ እናዘጋጅ።

▪️የተፈጠርነው ለጫወታና ለመዝናናት እንዳልሆነም አውቀን ለሞት እንዘጋጅ።

▪️በሁለቱም ዓለም ትልቅነት፣ ደስታና ስኬት የሚገኘውም በዚህ ነው።

✍️ኡስታዝ አሕመድ ሸይኽ ኣደም
3/6/1444ዓ.ሂ
@ዛዱል መዓድ

🔸🔹🔸🔹🔸🔹
🌐/channel/ahmedadem
~
የኪታብ ደርሶችን ብቻ ለማግኘት
🌐/channel/zad_qirat
~~~~
🔗https://www.facebook.com/yenegew/
~~~~
📶  http://www.youtube.com/c/ZadulMaad

📚"ዒልም ማለት አላህን መፍራት ነው!"
አል-ኢማሙ ማሊክ

Читать полностью…

💎ቲብያን 💎 የተለያዩ ዳዕዋዎች የሚተላለፉበት ቻናል!

ዓሹራን የመጾም ትሩፋት

🔅ቡኻሪይ እንደዘገቡት ዐብዱሏህ ኢብን ዐባስ ረዲየሏሁ ዐንሁ የዓሹራን ጾም አስመልክተው ሲናገሩ የሚከተለውን ብለዋል (ነቢዩም ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለ እንደ ዓሹራ ቀንና እንደ ረመዷን ወር ሆን ብለው <በጉጉት ጠብቀው> ሲጾሙ አይቻቸው አላውቅም! )
ብለዋል ነቢዩም፥
( የዓሹራ ቀን ጾም ያለፈውን ዓመት ወንጀል ያስምራል(ያስሰርዛል) ብዬ አሏህ ላይ ተስፋ አደርጋለሁ ) ብለዋል።

🔅አንድን ቀን በመጾም የዓመት ወንጀል መማር ለሙእሚኖች ታላቅ የአሏህ ሱብሓነሁ ወተዓላ ስጦታ ነው እድሉም ለሁሉም ክፍት ነው መሽቀዳደም እና መወዳደር ያማረው ሰው በሙሉ እንዲህ አይነቱ የኸይር ስራ ሜዳ ላይ ይሽቀዳደም!
🔅የዓሹራ ቀን ጾም ያለፈውን ዓመት ወንጀል ያስምራል ያሰርዛል በቀላል ስራ ይህን የሚያህል ምንዳ የሚገኝ ሆኖ ሳለ ብዙ ለአኼራቸው ግድ የለሽ የሆኑ ሰዎች እድሉን ችላ ሲሉ እንመለከታለን፤አዱኒያዊ ጥቅም ቢሆን ግን አይዘናጉም ነበር፤ አልፎም እድሉ ላይ በመሻማት ይፋጁ ነበር ግን {አብዛኞች የሰው ልጆች አያውቁም} አርሩም 6

☄የዓሹራእ ጾም ሙሐረም ስንተኛው ቀን ላይ ነው?...
የዓሹራእ ጾም ማለት የሙሐረም ወር 10ኛው ቀን ላይ ሲሆን ከፊቱ ወይም ከኋላው አንድ ቀን (9ኛውን ወይም 11ኛውን) ቀን ጨምሮ መጾም ይመረጣል ምክንያቱም ነቢዩ ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም ዓሹራን ሲጾሙና ሷሓባዎችም እንዲጾሙት በመከሯቸው ጊዜ አይሁዶች የሚያከብሩት ቀን እንደሆነ ለነቢዩ ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም ሲነግራቸው የሚከተለውን ብለዋል፤ ( አሏህ ካለ የሚመጣው ዓመት ላይ 9ኛውንም ቀን እንጾማለን ) ብለዋል ከዚህም በመነሳት ዑለማዎች ዘጠነኛውንም ቀን መጾም ሱና ነው ብለዋል።

🔅ከዓሹራ ጋር 9ኛውን ቀን መጾም ምክንያቶች አሉት ከነዚህም መሀል አንዱ 10ኛውን ቀን ብቻ መጾም ከአይሁዶች ጋር መመሳሰልን ስለሚያመጣ አንድ ቀን ጨምሮ መጾሙ ከነሱ ጋር መለያየትን ያስገኛል፤ ከጠመሙ ህዝቦች ጋር መመሳሰል በዲናችን ክልክል ከመሆኑ አንጻር እነሱን ለመቃረን ተብሎ ሸሪዓችን አንድን ነገር ማድረግ ሲከለክል ወይም ደግሞ ሲያዝ ሁሉ እናያለን ይህም ሆኖ ሳለ ግን ብዙ ሙስሊሞች አይሁድና ነሳራ ያደረጉትን ለማድረግ ሲሽቀዳደሙ እንመለከታለንል!

🔅ይህ በእንዲህ እንዳለ ምናልባት የቀን አቆጣጠር ላይ ስህተት ቢፈጠር እና የወሩ መግቢያ አሻሚ ቢሆን ሁለቱን ቀናት መጾም የዓሹራን ቀን ማግኘት ላይ እርግጠኛ ያደርጋል፤በላጩ 9 እና 10ኛውን ቀን መጾሙ ሲሆን ያልተመቸው ሰው 10 እና 11ኛውን ቀን መጾም ይችላል።እንዲሁ ዋናውን የዓሹራን ቀን ብቻ እንጂ ሌላ ተጨማሪ ቀን መጾም ያልቻለ ሰው ብቻውን መጾም እንደማይከለከል ዑለማዎች ገልጸዋል።

🔅ጁሙዓ ወይም ቅዳሜ ቀንን ለብቻው (ከፊት ወይም ከኋላ አንድ ቀን ሳይጾሙ) ነጥሎ መጾም እንደማይቻል በሐዲሶች የተገለጸ ሲሆን አጋጣሚ ዓሹራ ጾም በጁሙዓ ወይም ቅዳሜ ዕለት ቢሆን መጾም አይከለከልም።
🔅ዓሹራ ጾም ብቻ ሳይሆን ሌሎችም እንደ ቀዷ ወይም የነዝር (ስለት) እና መሰል ምክንያት ያላቸው ጾሞችንም መጾም አይከለከልም።

☄ዓሹራን መጾም የቱን ወንጀል ነው የሚያስምረው?
ዓሹራን መጾም ያለፈውን ዓመት ወንጀል እንደሚያሠርዝ ጠቅሰናል ይህ ምህረት ጥቃቅን ወንጀሎችን ነው የሚመለከተው ወይስ ከባባዶችንም ጭምር?
ይህን አስመልክተው ኢማም አንነወዊይ የሚከተለውን ብለዋል፤
" የዓረፋ ጾምም ይሁን የዓሹራ ሌሎችም ወንጀልን ያስምራሉ የተባሉ ኢባዳዎች ጥቃቅን የሚባሉ ወንጀሎችን በሙሉ ያሰርዛሉ ጥቃቅን ወንጀሎች የሌሉበት እንደሆነ በምትኩ መልካም ስራዎች ይመዘገቡለታል አላህ ዘንድም ያለው ደረጃ ይጨምራል ጥቃቅን ወንጀሎች የሌሉበት ሆኖ አንድ ወይም ከዛ በላይ ከባድ ወንጀል ያለበት እንደሆነ ወንጀሉን ያቀለዋል ብለን አሏህ ላይ ተስፋ እናደርጋለን"

☄ቀዷ ያለበት ሰው ዓሹራ መጾም ይችላልን?
እንደ ዓሹራ ያሉ ሱና ጾሞችን ያለምንም ጥርጣሬ ለመጾም ያለብንን ቀዷ ፈጠን ብለን ማውጣቱ ይመረጣል።ቀዳውን ሳይጾም ወቅቱ የሚያልፍ የሱና ጾም የደረሰበት ሰው በቀጣይ ለቀዳ ሰፊ ጊዜ እስካለው ድረስ ፈርዱን ቀዳ ሳያወጣ ሱና ቢጾም ችግር አይኖረውም።
🔅ከዓሹራ ጋር በተያያዘ የሚፈጠሩ ቢድዓዎች  ታላቁ የዲን መሪ ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያ ይህን በተመለከተ የሚከተለውን ጥያቄ ተጠየቁ
"በዓሹራ ቀን ሰዎች ገላቸውን ሲታጠቡ፤ ሲኳኳሉ፤ሂና ሲቀቡ፤ልዩ ሰላምታ ሲለዋወጡና ሲጨባበጡ፤ልዩ ምግብም ሲሰሩ እና ልዩ ደስታ ሲደሰቱ ይታያል ይህ ነገር በሸሪዓችን መሰረት አለውን?" እሳቸውም ሲመልሱ {{ ይህን አስመልክቶ ከነቢዩ ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም የተገኘ አንድም ሷሒሕ ሐዲስ የለም ሷሓቦቻቸውም ይህን አስመልክተው ያሉት ነገር የለም ቀደምት የዲን መሪዎችም አራቱም መሪዎች (ኢማም፥አቡ ሐኒፋ፣ማሊክ፣ሻፊዒ እና አሕመድ) ይሁን ሌሎችም ከነሱም ውጪ ያሉት ታዋቂ የሸሪዓ እውቀት ምንጭ የሚባሉ መጻህፍት ባለቤቶችም በዚህ ጉዳይ ከነቢዩም ይሁን ከሷሓቦች ወይም ከተከታዮቻቸው ምንም የዘገቡት ነገር የለም) ብለው መልሰዋል።
💥ከቢድዓ በመጠንቀቅ በዲኑ የተፈቀዱ ነገሮችን ብቻ በመስራት ወደ አላህ እንቃረብ!

💥የዘንድሮ (የ1445ዓ.ሂ) ዓሹራ የሚሆነው የፊታችን ጁሙዓህ (ከነገ ወዲያ) ሙሐረም 10 (እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር ሐምሌ 21 /2015) ሲሆን ከፊቱ ሐሙስን ወይም ከኋላው ቅዳሜን መጾም ተገቢ ነው። ከ11ኛው ቀን ይልቅ ከፊት ያለውን 9ኛውን ቀን መጾሙ ተመራጭ ነው። በተለይ ዘንድሮ 9ኛው ቀን ዕለቱም ሐሙስ ስለሆነ ሐሙስ ቀን የመጾምን ትሩፋትም ያስገኛል።
ሁለት ቀን መጾም የሚከብደው ሰው 10ኛውን ቀን ብቻ መጾምም ይችላል።
አላህ ይወፍቀን!

✍ ኡስታዝ አሕመድ ሸይኽ ኣደም
@ዛዱል መዓድ
🔸 🔹 🔸🔹 🔸🔹🔸
🌐/channel/ahmedadem

Читать полностью…

💎ቲብያን 💎 የተለያዩ ዳዕዋዎች የሚተላለፉበት ቻናል!

📢ማሳሰቢያ

💥ፉሪ በድር መስጂድ ውስጥ በኡስታዝ አሕመድ ሸይኽ ኣደም የሚሰጡ በዓረፋ በዓል ምክንያት ቆመው የነበሩ ትምህርቶች በሙሉ በአላህ ፈቃድ ከዛሬ ጁሙዓህ ዙል-ሒጃ 19/1444 ዓ.ሂ (ሰኔ 30/2015) ጀምሮ ይቀጥላሉ።

🔅ጁሙዓህ ከመግሪብ እስከ ዒሻእ

مختصر سيرة الرسول.
ሙኽተሰሩ ሲረት አር-ረሱል (ሊሙሐመድ ኢብን ዐብዲል ወሃብ)

🔅ቅዳሜና እሁድ ከመግሪብ እስከ ዒሻእ

تفسير القرآن الكريم.
የቁርኣን ተፍሲር

🔅እሁድ ከዝሁር ቡሃላ

رياض الصالحين.
ሪያዱስ'ሳሊሒን(ሊኢማም አንነወዊይ)

🔅ሰኞና ማክሰኞ ረፋድ 4:00 ጀምሮ (የሴቶች ደርስ)

الوجيز من عقيدة السلف الصالح.
አል-ወጂዝ ሚን ዐቂደቲስ'ሰለፍ አስ'ሷሊህ

🔅ዕሮብና ሐሙስ ከመግሪብ እስከ ዒሻእ

بلوغ المرام.
ቡሉጉል-መራም(ሊኢብኑ ሐጀር አል ዐስቀላኒ)


@ዛዱል መዓድ

/channel/ahmedadem

Читать полностью…

💎ቲብያን 💎 የተለያዩ ዳዕዋዎች የሚተላለፉበት ቻናል!

📖ከሱረቱ አን‘ናስ–ሱረቱል ፊል

ከሀለቃ ቂራዓት የተወሰደ


🎙ኢብራሒም ኸይረዲን

📱/channel/ibrahim_furii

Читать полностью…

💎ቲብያን 💎 የተለያዩ ዳዕዋዎች የሚተላለፉበት ቻናል!

📮ተራዊሕ በመስገድ ከሚገኙ  ጥቅሞች...

🔹ተራዊሕ የረመዷን ወር ምሽቶች ላይ በጋራም ይሁን በተናጠል የሚሰገድ ነቢዩ صلى الله عليه وسلم እና ሰሓቦቻቸው  የተገበሩት ተወዳጅና ሱናህ ዒባዳህ ነው።

የተራዊሕ ሰላት በርካታ ጠቀሜታዎችና ምንዳዎችም አሉት፤
ከነዚህም በጥቂቱ:-

① ቀኑን በጾም፣ ሌሊቱን በሰላት በማሳለፋችን ከደጋግ የአላህ ባሪያዎች መሆን ያስችላል።

② ቁርኣን በብዛት በማድመጣችን የአላህን እዝነት እናገኝበታለን።

③ ተራዊሕ በዛ ያለ ሩኩዕና ሱጁድ ስላለበት ሰፊ የዱዓና የዚክር እድል እናገኛለን።

④ ከወንጀልና ከማይጠቅሙ ነገሮች ርቀን ጊዜያችንን በመልካም ስራ እናሳልፋለን።

⑤ ዒባዳህ ላይ መታገስን እንማርበታለን።

⑥ አመቱን ሙሉ ሰላተል-ለይል ለመስገድ ልምምድ እናደርግበታለን።

⑦ በተደጋጋሚ ከኢማምና ከማእሙሞች ጋር "ኣሚን" በማለታችን ወንጀላችን ይማራል።

⑧ መስጂድ ስንሄድና ስንመለስ በእርምጃችን ልክ ወንጀሎች ተራግፈው መልካም ስራዎች ይጻፉልናል።

⑨ ሰላት እየጠበቀን በምናሳልፋቸው ጊዜያቶች መላኢካዎች ምህረት ይጠይቁልናል።

①∅ የሙስሊሞችን ጀማዓ በማብዛት ሸይጣንና አጋዦችን እናስቆጫለን።

①① ከመልካም ሰዎች ጋር በመቀላቀላችን መልካም ስራዎቻችን ወደ ሰማይ እንዲወጡና ተቀባይነት እንዲያገኙ እድል ይፈጥራል።

①② ከአልባሌ ነገሮች ለመራቅና ዲን ላይ ቀጥ ማለት ለሚፈልገው ወጣት መልካም አርዓያና ማበረታቻ እንሆናለን።

①③ ካመኑበትና ጥቅሙን ካወቁት ሁሉም ነገር ቀላልና የሚቻል መሆኑን በተጨባጭ እንረዳበታለን።

①④ ቁርኣንን በብዛት በመስማታችን እንገሰጻለን፤ እንዲሁም የተለያዩ አንቀጾችን በተደጋጋሚ በመስማታችን ትክክለኛውን የቁርኣን አቀራር ለማወቅም ይረዳናል።

①⑤  በቁኑት ዱዓ ወቅት ብዙ እኛ ያላሰብናቸውና መግለጽ የማንችላቸው ነገሮች ዱዓ ተደርጎ "ኣሚን" በማለታችን ትርፋማ እንሆናለን።

①⑥ ከኢማሙ ጋር እስከሰላቱ ፍጻሜ ድረስ አብረን እየሰገድን ከቆየን ሌሊቱን በሙሉ ሲሰግድ ያደረን ሰው እጅር /ምንዳ እናገኛለን።

①⑦ ለሰላት ረጅም ጊዜ መቆማችን የቂያማ ቀን መቆምን ያቀልልናል፤ ዱኒያ ላይ ለጌታው ብሎ ረጅም ሰዓት የቆመ የቂያማ ቀን መቆም አይከብደውምና።

①⑧ ሰግደን ስንመለስ አላህ የሚወደውን ስራ በመስራት የሚገኘውን የውስጥ ደስታና እፎይታ እናገኛለን።

💠ሌሎችንም የዱኒያም የኣኺራህ በርካታ ጥቅሞችን እናገኛልንና ተራዊሕን መቼም አንተው! አላህ ያግራልን።

اللهم أعز الإسلام والمسلمين وأذل الشرك والمشركين ووحد صفوفنا وقنا شرور أنفسا يارب العالمين
✍ኡስታዝ አሕመድ ሼኽ ኣደም
@ዛዱል መዓድ ረመዷን 1444 ዓ.ሂ
🔸   🔹  🔸  🔹  🔸  🔹

🌐/channel/ahmedadem

Читать полностью…

💎ቲብያን 💎 የተለያዩ ዳዕዋዎች የሚተላለፉበት ቻናል!

🌾የጁሙዓ ኹጥባ በአማርኛ  🌾

             ቁ/201


ነቢዩ ﷺ ሸዕባን ላይ ጾም ያበዙ
የነበረው ለምንድነው?


     እሁድ  28/7/1444 ዓ.ሂ

🔊በኡስታዝ አሕመድ ሸይኽ ኣደም

    የዳውንሎድ ሊንኩን ይጫኑ
      ⬇ ⬇ ⬇ ⬇

🔎 https://bit.ly/3IeoNLM
🔹 🔸 🔹 🔸 🔹 🔸

🌐/channel/ahmedadem

📚"ዒልም ማለት አላህን መፍራት ነው!"
አል-ኢማሙ ማሊክ

Читать полностью…

💎ቲብያን 💎 የተለያዩ ዳዕዋዎች የሚተላለፉበት ቻናል!

ነፍሲያችን እንድትስተካከል...

ዘውትር ለመተኛት አልጋ/ፍራሽ ላይ ሲወጡ ከተኛሁበት ላልነሳና በዛው ወደ ኣኺራህ ልሄድ (ከአልጋ ወደ ቃሬዛ፣ ከብርድ ልብስ ወደ ከፈን፣ ከቤት ወደ መቃብር ልሸጋገር ) እችላለሁ እያሉ ማሰብ፤ ለመተኛት መብራት ሲያጠፉም የቀብርን ጨለማ ማስታወስና በሰላም ተኝተው ከተነሱም ከእንቅልፍ ሲነቃ የሚባለውን ዚክር ትርጉሙን እያስተዋሉ ማለት
ነፍስያችን አደብ እንድትገዛ፣ የጌታዋንና የሰው ልጆችንም ሐቅ እንድትጠብቅ፣ እንዲሁም ከወንጀል እንድትርቅ ከሚያደርጉ ነገሮች መካከል ጥቂቶች ናቸው።
ዛዱል-መዓድ
/channel/ahmedadem

Читать полностью…

💎ቲብያን 💎 የተለያዩ ዳዕዋዎች የሚተላለፉበት ቻናል!

በአላህ ስም እጅግ በጣም አዛኝ፤ እጅግ በጣም ሩህሩህ በሆነው
አሰላሙ ዓለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱሁ

የኢርሻድ ቁርአን ሂፍዝ ማዕከል ምርቃት

ለ ……………………………………………………………

በገደባኖ
ጉታዘር ወለኔ ወረዳ በኢንጌ ከተማ የኢርሻድ ቁርአን ሂፍዝና ኢስላማዊ ትምህርት ማዕከል ግንባታ መጠናቀቁን ተከትሎ የካቲት 19/2015 ዓ.ል ከጠዋቱ 3፡00 ጀምሮ በማዕከሉ ቅጥር ግቢ ውስጥ ታላላቅ እንግዶች፣ ዑለማዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ታላላቅ ዳዒዎችና ሌሎችም በተገኙበት በተለያዩ አስተማሪ በሆኑ ፕሮግራሞች በድምቀት ስለሚመረቅ  እርስዎም የዚህ ታላቅ ኘሮግራም ተሳታፊ እንዲሆኑ በአክብሮት ጠርተንዋታል ::

ከሰላምታ ጋር
የኢርሻድ መርከዝ ኮሚቴ
ከኢብኑ መስዑድ ኢስላሚክ ሴንተር ጋር በመተባበር


t.me/yenebizene

Читать полностью…

💎ቲብያን 💎 የተለያዩ ዳዕዋዎች የሚተላለፉበት ቻናል!

🌸 #በጁምዓ ቀን እና በጁምዓ ሌሊት እኔ ላይ አብዝታችሁ ሶለዋት አውርዱ: እኔ ላይ አንድ ሶለዋት ላወረደ ሰው አላህ በርሱ ላይ 10 ሶለዋት ያወርድለታል ።

᯾ ☆ረሱል ሶለላሁ ዓለይሂ ወሰለም☆᯾
📚ሶሒሁል ጃሚዕ (1209)

༄💎/channel/Tibyaan54

Читать полностью…

💎ቲብያን 💎 የተለያዩ ዳዕዋዎች የሚተላለፉበት ቻናል!

🏷️የዛዱል መዓድ ፈታዋ 🌾
فتاوى زاد المعاد
          ቁ/207

ረቡዕ  3/7/1444 ዓ.ሂ

🔊በኡስታዝ አሕመድ ሸይኽ ኣደም

የዳውንሎድ ሊንኩን ይጫኑ
⏬  ⏬   ⏬   ⏬   ⏬  ⏬

🔎https://bit.ly/3WGBOmy
   🔹 🔸 🔹 🔸 🔹 🔸
~~~~
▪️1/ አንዳንድ ሰዎች እንቅፋት ሲመታቸው ወይም ሲያማቸው እኔን ካልተባሉ ደስ አይላቸውም እኔን ማለት ይቻላል?

▪️2/ እኔ በጣም ያመኛል ሲህር አለብኝ እና መንጃ ፍቃድ አውጥቼ ነበርና የኮምፒተር ፈተናውን በጉቦ ነው ሰጥቼ ያለፍኩት ምክንያቱም ሳጠና በጣም ያመኛል፣እንዴት ትላላችሁ?

▪️3/ አንድ ሰው ቁርአን ሀፍዞ ከጨረሰ በኋላ ማሰገድን የግድ የሚያደርጉ አሉ መፍትሄውን ቢነግሩንና የኢማምነትን መስፈርት ቢያብራሩልን።

▪️4/ አንዲት ሴት ስታገባ ባሏ ምን ትፈልጊያለሽ ሲላት ኒካህ በእጄ እንዲሆን አለችው እሱም እሺ ሰጥቸሻለሁ አላት። ሲጣሉም ፈታሁህ አለችው። ይህ እንዴት ይታያል?

▪️5/ ቤትን ከወለድ ነፃ ላልሆነ ባንክ ማከራየት ይቻላል?ስራስ ባንክ ቤት ተቀጥሮ መስራት?

▪️6/ ወንድሜ መርካቶ ውስጥ እቁብ ሰብሳቢ ነው በየቀኑ ከፍተኛ ብር ነው ሚሰበስበው ሁሉም የእቁቡ አባላቶች እጣ ከደረሳቸው በኋላ የመጨረሻው አንዱ እጣ ለሰበሰበበት ተብሎ ለሰብሳቢው (ለወንድሜ) ይሰጠዋል ለሰበሰበበት ተብሎ የሚሰጠው የአንዱ እጣ ገንዘብ እጅግ በጣም ብዙ ነው ሀራም ይሆንበታል ወይ? እቁብ መሰብሰብም ይሁን መጣል ሀራም ሚሆንበተ ሁኔታ ካለ ቢብራሩልኝ።

▪️7/ ኢስላም ባርያነትን ለማጥፋት ብዙ ህጎችን ደንግጓል እየተባለ በሌላ መልኩ ደግሞ ረሱል ﷺ እንደሚስትነት የያዟቸው ሁለት ባርያዎች ነበሯቸው ሲባል ሁለቱ ነገሮች አይጋጩምን ?

▪️8/ እኔ ትናንሽ ልጆችን መድረሳ ስር ቃኢዳ እንዲሁም በተጅዊድ ቁርዓን አስቀራቸዋለው ልጆቹም ወላጆቻቸውም ኡስታዝ እያሉ ሲጠሩኝ ደስ አይለኝም እኔ በዲን እውቀት ጠልቄ ያልገባሁ ስለሆነ በስሜ እንዲጠሩኝ ነው ምፈልገው ኡስታዝ የሚለውን ስም ያዋረድኩት ይመስለኛል አንድ ሰው ኡስታዝ ለመባል ምን ማሟላት አለበት?እኔ ለኡስታዝነት ሳልበቃ ኡስታዝ ብለው ቢጠሩኝ እነሱም እኔም ወንጀለኛ እንሆናለን ወይ?በአሁን ሰአት የወጣውን የወረደውን ሁሉ ሸይኽ ኡስታዝ ሚሉ ሰዎች በዝተዋል ምን ይመክሩናል።

▪️9/ የማስቀራበት መድረሳ ስር አንዳንድ ወላጆችና ልጆች ለቁርዓንና ለዲን ትምህርት ብዙም ቦታ አይሰጡም ትምህርት ሲዘጋ ክረምት ላይ ዚያራ ብለው ወላጆች ልጆቻቸውን ወደ ተለያየ ቦታ ይወስዱና ለቀናት አንዳንዴም ለወራት መድረሳ አይመጡም በቀሩበት ብዙ ደርስ ያመልጣቸዋል ትምህርት ሲከፈት መልሰው ወደ መድረሳው ያመጧቸዋል በዚህም ወላጆች እንዲሁም ልጆቹ ለዲን ትምህርት ያላቸውን የዘቀጠ አስተሳሰብ ሳይ ልጆቹን ከመድረሳ አባርራቸዋለው ይሄን በማድረጌ አላህ ፊት ያስጠይቀኛል ወይ?ለዚህ ችግር ጥሩ መፍትሄ አለ ምትሉትን ጠቁሙኝ

~~~~
💥 ተጨማሪም የተለያዩ ትምህርቶችን ለማግኜት ከታች ያሉትን ሊንኮች ይጠቀሙ
🔸🔹🔸🔹🔸🔹
🌐/channel/ahmedadem
~
🌐/channel/zad_qirat
~~~~
🔗https://www.facebook.com/yenegew/
~~~~
📶  http://www.youtube.com/c/ZadulMaad

አላህ በተከበረው ቃሉ እንዲህ ይላል:-
🔅وَتَزَوَّدُوا فَإِنَّ خَيْرَ الزَّادِ التَّقْوَىٰ ۚ وَاتَّقُونِ يَا أُولِي الْأَلْبَابِ
"ስንቅ ያዙ፤ ከስንቆች ሁሉ በላጩ አላህን መፍራት ነው፤ የአእምሮ/ የልብ ባለቤቶች ሆይ ፍሩኝ" ሱረቱል በቀራ /197

Читать полностью…

💎ቲብያን 💎 የተለያዩ ዳዕዋዎች የሚተላለፉበት ቻናል!

ብዙ ታመው የሚሰቃዩ አይቻለው በህይወቴ ግን እንደዝች እህት አይነት አላየሁም ካለንን ከምንጎርሳት አካፍለን እንርዳት ። ቪድዮን ሼር ማድረግም ማየትም አልቻልኩም
ኢናሊላሂ ወኢና ኢለይሂ እራጂዑን

ባንክ አካውንት 1000471815543

ስልክ ቁጥር +251965084646

ዋትሳፕ ጉሩፕ 👇👇👇

https://chat.whatsapp.com/FsMm820B9xZGFzzNKhTYm4

https://fb.watch/idZzFJKZGK/?mibextid=win574

Читать полностью…

💎ቲብያን 💎 የተለያዩ ዳዕዋዎች የሚተላለፉበት ቻናል!

#የሸሪዓ ትምህርት እድል ለህፃን መስዑድ

ወድ እና የተከበራቹህ ሙስሊም ወንድሞች እና እህቶች መስዑድ የተባለን ታዳጊ ህፃን መርከዝ አቡ ሙሳ የቁርአን ሂፍዝ የሸሪዓ እውቀቶች ማእከል ሙሉ ወጪውን ሸፍኖ ቁርአን ለማስሀፈዝ እና መሰረታዊ የሸረዓ እውቀቶችን ለማስተማር ስለሚፈልግ የልጁን ቤተሰቦች በማናገርም ሆነ ከኛ ጋር በማገናኘት የበኩላችሁን አስተዋፆ እንድታበረከት በአላህ ስም እንጠይቃለን ።

የተቋሙ አድራሻ
0913939993 or 0930547776

የማእከሉ የቴሌግራም አድራሻ
/channel/Kurantejwid

Читать полностью…

💎ቲብያን 💎 የተለያዩ ዳዕዋዎች የሚተላለፉበት ቻናል!


هَلۡ أَتَىٰكَ حَدِيثُ ٱلۡغَٰشِيَةِ (1) وُجُوهٞ يَوۡمَئِذٍ خَٰشِعَةٌ (2) عَامِلَةٞ نَّاصِبَةٞ (3) تَصۡلَىٰ نَارًا حَامِيَةٗ (4) تُسۡقَىٰ مِنۡ عَيۡنٍ ءَانِيَةٖ (5) لَّيۡسَ لَهُمۡ طَعَامٌ إِلَّا مِن ضَرِيعٖ (6) لَّا يُسۡمِنُ وَلَا يُغۡنِي مِن جُوعٖ (7) وُجُوهٞ يَوۡمَئِذٖ نَّاعِمَةٞ (8) لِّسَعۡيِهَا رَاضِيَةٞ (9) فِي جَنَّةٍ عَالِيَةٖ (10) لَّا تَسۡمَعُ فِيهَا لَٰغِيَةٗ (11) فِيهَا عَيۡنٞ جَارِيَةٞ (12) فِيهَا سُرُرٞ مَّرۡفُوعَةٞ (13) وَأَكۡوَابٞ مَّوۡضُوعَةٞ (14) وَنَمَارِقُ مَصۡفُوفَةٞ (15) وَزَرَابِيُّ مَبۡثُوثَةٌ (16) أَفَلَا يَنظُرُونَ إِلَى ٱلۡإِبِلِ كَيۡفَ خُلِقَتۡ (17) وَإِلَى ٱلسَّمَآءِ كَيۡفَ رُفِعَتۡ (18) وَإِلَى ٱلۡجِبَالِ كَيۡفَ نُصِبَتۡ (19) وَإِلَى ٱلۡأَرۡضِ كَيۡفَ سُطِحَتۡ (20) فَذَكِّرۡ إِنَّمَآ أَنتَ مُذَكِّرٞ (21) لَّسۡتَ عَلَيۡهِم بِمُصَيۡطِرٍ (22) إِلَّا مَن تَوَلَّىٰ وَكَفَرَ (23) فَيُعَذِّبُهُ ٱللَّهُ ٱلۡعَذَابَ ٱلۡأَكۡبَرَ (24) إِنَّ إِلَيۡنَآ إِيَابَهُمۡ (25) ثُمَّ إِنَّ عَلَيۡنَا حِسَابَهُم (26)

🌐/channel/ibrahim_furii

Читать полностью…

💎ቲብያን 💎 የተለያዩ ዳዕዋዎች የሚተላለፉበት ቻናል!

🌴አጫጭር መልዕክቶች 🌴

🏷️ ለጌታህ ፍርድ ታገስ
            

     ሀሙስ 19/6/1444 ዓ.ሂ


🔊በኡስታዝ አሕመድ ሸይኽ ኣደም


       የዳውንሎድ ሊንኩን  ይጫኑ
           ⬇ ⬇ ⬇ ⬇

🔎 https://bit.ly/3GBTc5T
🔸🔹🔸🔹🔸🔹

🌐/channel/ahmedadem

📚"ዒልም ማለት አላህን መፍራት ነው!"
አል-ኢማሙ ማሊክ

Читать полностью…

💎ቲብያን 💎 የተለያዩ ዳዕዋዎች የሚተላለፉበት ቻናል!

አንርሳቸው በ... እናስታውሳቸው!

▪️ወዳጅ ወይም ዘመድ ሲሞት ለቀናት ወይም ለሳምንታት፣ ጥቂቶቻችንም ለወራት፣ በጣም ጥቂቶችም እንደራሳቸው የዲን ጥንካሬና እንዳጡት ሰው ቅርበትና ደረጃ ለውስን አመታት ዱዓና ኢስቲግፋር እናደርጋለን።ከዛ በኋላ ግን በንግግር መሃል የሟች ስም ሲነሳ እንኳ በስርዓቱ "አላህ ይዘንለት/ላት" ማለቱን እንረሳለን!

🔸እውነተኛ ወዳጅ መቼም ቢሆን ወዳጁን አይረሳም።በተለይ ወልደው ብዙ ዋጋ ከፍለው ያሳደጉን ወላጆቻችንን፣
ጌታችንና ዲናችንን እንድናውቅ ያደረጉን አስተማሪዎቻችንን፣በችግር ጊዜ ከጎናችን የቆሙ ባለውለታዎቻችንን፣ምንም ባያደርጉልን በዲን ገመድ የተሳሰርናቸው ሙስሊም ሙታንን፣በተለይ በተለይ ደግሞ ዱኒያ ላይ ዘርና ዘመድ ኖሮ ዱዓና ኢስቲጝፋር የሚያደርግላቸው፣ ሰደቃ የሚሰጥላቸው ወገን የሌላቸው (ሰለምቴ፣ በላጤነት የሞቱና መሰል ብቸኛዎችን) አስታውሰን ለሁሉም ዱዓእ፣ ኢስቲጝፋርና እንደ አቅማችን ሰደቃ ልናደርግ ይገባል።

▪️ዛሬ ቀድመውት ወደ ኣኺራህ ለሄዱ ወገኖቹ ኣኺራህ ላይ የሚጠቅማቸውን ነገር የሚያደርግ ሰው ነገ እሱም ተራው ደርሶ ወደ ማይቀረው ኣኺራህ ሲሄድ በህይወት ካሉ ሰዎች ውስጥ አስታውሶት እዛ የሚጠቅመውን ነገር የሚያደርግለትን ሰው አላህ ያቆምለታል።

🔅ከቀደምት መልካም አርዓያዎቻችን ውስጥ ሐጅ ሳያደርጉ ለሞቱ ሐጅ የሚያደርጉ፣ ዘር ለሌላቸው ሙታንም ነይተው ሰደቃ የሚያደርጉላቸው ነበሩ።

አሁን ባለንበት ዘመንም ሐጅ ሳያደርጉ ለሞቱ የዲን ሊቃውንት በየተራ ሐጅ የሚያደርጉ ደጋግ የአላህ ባሪያዎች አሉ!

▪️እኛ ግን ብዙዎቻችን አይደለም ለሌሎች ኣኺራህ አስበንና ተጨንቀን የሚጠቅማቸውን  ነገር ማድረግ ይቅርና የራሳችንን ኣኺራም ዘንግተናል!

🔸በህይወት እያለን ስንት ነገር የምናደርግላቸውና የማይሆነውን ሁሉ የምንሆንላቸው ሰዎች ስንሞት በምን ዓይነት ፍጥነት እንደሚረሱን ብናውቅ ኖሮ ለሰዎች አንድም ደቂቃ አልሰጥም ባልን ነበር!ስለዚህ የሰዎችን ዱኒያ እያሳመርን የራሳችንን ኣኺራህ አናበላሽ!ለሌሎች ብቻ እየተሯሯጥን እራሳችንን አንጣል።በህይወት እስካለን ድረስ ለነፍሳችንም ለሌሎችም የሚጠቅም ነገር እንስራ።

አላህ አርቆ የሚያስብ ልብ ይስጠን ዱኒያና ኣኺራችንም ያሳምርልን!
ለመላው ሙስሊም ሙታን ምህረትና እዝነቱን ይለግስልን ፣በተለይም ባስታወስናቸው ቁጥር ልባችን ለሚደነግጥና ዓይናቸው ለሚናፍቀን ወላጅ፣ ዘመድና ወዳጆቻችን በሙሉ!

✍️ ኡስታዝ አሕመድ ሸይኽ ኣደም
  10/6/1444ዓ.ሂ
@ዛዱል መዓድ

ኣሚን- ኣሚን

🔹 🔸 🔹 🔸 🔹 🔸

🌐/channel/ahmedadem

📚"ዒልም ማለት አላህን መፍራት ነው!"
አል-ኢማሙ ማሊክ

Читать полностью…

💎ቲብያን 💎 የተለያዩ ዳዕዋዎች የሚተላለፉበት ቻናል!

ነሲሓ ቲቪ የሳተላይት ስርጭቱ መቋረጡ ታውቋል
ድጋፍ ለማድረግ ለምትፈልጉ ወንድም እና እህቶች በተከታዩ የባንክ አካውንት ድጋፍ በማድረግ ለነሲሓ ቲቪ ቀጣይነት አስተዋፅኦ ያበርክቱ
***
ኢብኑ መስዑድ ኢስላሚክ ሴንተር

-ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 444
ወይም 1000145615929

– ኦሮሚያ ኢንተርናሽናል 1445091300001

– አቢሲኒያ ባንክ 73169062

– ንብ ኢንተርናሽናል 7000025634638

– ዘምዘም ባንክ 7122

– አዋሽ ባንክ 01410844116300

ነሲሓ ቲቪ... ኢስላማዊ ዕውቀት ለሁሉም!

Читать полностью…
Subscribe to a channel