🍂የቲብያን ቻናል ዋና አላማው አላህ ኢኽላሱን ይስጠንና በተቻለን አቅም ጠቃሚ ናቸው የምንላቸው ወቅታዊ ሙሃደራዎችን እንዲሁም ጠቃሚ ማስታወሻዎች አጫጭር ፁሁፎችና ፎቶዎችንምን ! ላልደረሳቸው ማድረስ ነው። «السلفية منهجي» https://t.me/joinchat/AAAAAEPOgchGXF37Mja27A
#ከአንድ_በላይ_ማግባት_ለምን_አስፈለ ⁉
ከክፍል 1―5
🔊በኡስታዝ አሕመድ ሼኽ ኣደም
1//channel/ahmedadem/1273
2//channel/ahmedadem/1289
3//channel/ahmedadem/1308
4//channel/ahmedadem/1351
5//channel/ahmedadem/1373
እኔ በጣም ግርም የሚለኝ ነሲሓን የመሰለ ትልቅ ተቋም በገንዘብ ምክንያት ሲቋረጥ ነው። ሀብታሙን ነጋዴ አቀናጅቶ ለሳተላይትና መሰል ክፍያዎች ብር ማግኘት እንደዚ ከባድ ሆነ ማለት ነው?? ወላሂ በጣም ያሳዝናል!!
@ibnyahya777
🌸#ዲን_ላይ_መጽናትና_አጋዥ_ነገሮች
ክ/4(የመጨረሻው ክፍል)
የዕለተ ረቡዕ 8/6/1440 ዓ.ሂ
ቡታጅራ ከተማ ላይ ከተደረገው
ሙሓደራ የተወሰደ
🔊በኡስታዝ አሕመድ ሼኽ ኣደም
የዳውንሎድ ሊንኩን ይጫኑ
🔸mp3
⬇ ⬇ ⬇ ⬇
🔎 http://bit.ly/2E7kLVL
🔹🔸🔹🔸🔹🔸🔹
🌐/channel/ahmedadem/3035
«ምኞትህን ሁሉ ሱጁድ ላይ አስቀምጠው ፣ጌታህ ዝቅ ብሎ የለመነውን ባሪያውን ፈፅሞ በባዶ አይመልስም»‼️
#صلاة_الفجر
🔊《የትዕግስት አስፈላጊነት》🔊
🔶 #የኢብኑል ቀይም ጫማ ወደ መስጂድ በገቡበት መዘረፍ…………
🎙በኡስታዝ ሲራጅ ንጋቱ
/channel/merkaz_ibnuAbas
🏷️የዛዱል መዓድ ፈታዋ 🌾
فتاوى زاد المعاد
ቁ/200
ረቡዕ 13/5/1444ዓ.ሂ
🔊በኡስታዝ አሕመድ ሸይኽ ኣደም
የዳውንሎድ ሊንኩን ይጫኑ
⏬ ⏬ ⏬ ⏬ ⏬ ⏬
🔎 *https://tinyurl.com/2n23w433*
🔹 🔸 🔹 🔸 🔹 🔸~~~~
▪️1/ሴቶች በጀመዓ ሆነው ዱዓ ብለው ኣሚን የሚሉት እንዴት ይታያል?
▪️2/አንድ ኒቃብ የምትለብስ ሴት ወሊይ ሳይኖራት ቀርቶ ቃዲ ጋር ኒካህ ብታስር ቃዲው እሷን ማየት አለበት ወይ?
▪️3/ውዱእ በምናደርግበት ጊዜ በአንድ አንድ መብቃቃት ፈልገን ግን መጀመሪ ሎሽን ተቀብተን ነበረ ፣መጀመሪያ እሱን ማስለቀቅ አለብን ወይስ በዛው በአንድ አንድ ብቻ ይብቃቃልናል?
▪️4/በትዳር ውስጥ ሆኜ ደስታ የለኝም በተለያየ ግዜ ኢስቲኻራ ስግጄ ኸይሩን ምረጥልኝ ማለት ከሆነም አኑረኝ ካልሆነም ለየኝ ማለት አይቻልም ወይ?
▪️5/ደረቅ የተነጀሰን ምንጣፍ በእርጥብ እግር ረግጦ አልፎ ንፁህ ብቻ ላይ መስገድ ይቻላል?
▪️6/ስለ አቂቃ ሳያውቅ አቂቃ ያላወጣ ወላጅ ህፃን ልጁ ቢሞት ሸፈዓ ይሆናል ወይ?
▪️7/ስለባለቤቴ መጀመሪያ ሲነገረኝ እንደቀራ ነበረ ነገር ግን መኖር ስንጀምር በሱና ላይ ጠንካራ ይሁን እንጂ እንዳልቀራ አረጋገጥኩ ይህ በልጆች ተርቢያ ላይ ትልቅ ችግር ሆኖብኛል ምን ይመክሩኛል?
▪️8/የባለቤቴ ቤተሰቦች አይወዱኝም፣ አይፈልጉኝም ስለዚህ ቤታቸው አልሄድም ባለቤቴና ልጆቼ ይሄዳሉ ይህን
በማድረጌ ዝምድና መቁረጥ ውስጥ እገባለሁ?በመሄዴ ከጥቅሙ ጉዳቱ እያመዘነ ስለሆነ ነው
▪️9/ረዥም የሆነ ስስ ካልሲ ላይ አጭር ቁርጭምጭሚትን የማይሸፍን አጭር ካልሲ ደርበን ልብስን በሱ ላይ ማበስ እንችላለን እንዴ?
▪️10/በጅልባብ ስር ሰፊ የሆነ ሱሪ መልበስ እንችላለን?
▪️11/ሽንት ቤት ውስጥ ተቀምጠን ምራቅ መትፋት አይችልም ይባላል ይህ እንዴት ይታያል?
▪️12/ሴቶች የሰርግ ቀን በራሳቸው ግጥም እያወጡ ሲጨፍሩ ወንዶች ድምፃቸውን ቢሰሙት ወንጀለኛ ይሆናሉ?
በአንድ ላይ ስለሚሉት የማን ድምፅ እንደሆነ ስለማይለይ ጀዛኩሙሏህ ኸይር
▪️13/ባለቤቴ ራሴን እንድጠብቅ በጣም ይፈልጋል እና እሱ ሳያውቅ ከሱ ገንዘብ ወስጄ የሚያስፈልገኝን ነገር መግዛት እችላለሁ ወይ?
▪️14/አንድ ወንድሜ ኒካህ አስሮ ነበረ እና ኒካሁን ሲያስር ለሚስትየው ወልይ ሆኖ የቀረበረው ታናሽ ወንድሟ ነበረ ግን ታናሽ ይሁን እንጂ 15አመት አልፎታል ታላቅ ወንድም እያላት በታናሽ መታሰሩ እንዴት ይታያል?እና ይህ የተደረገው ልጅቷ አባቷም ሆነ አጎት ስለሌላት ነው
▪️15/የጋብቻ ቀለበት ፈርጥ ያለው እንዴት ይታያል? አይቻልም ሲባል ሰምቼ ነው እኛ የምንጠቀው ይህን ነው ምን ይመክሩናል?ጀዛኩሙሏህ ኸይር
▪️16/ባለፈው መፃፍ ሲናበዛ ማስታወሻ እንዴት መያዝ እነግራችኋለሁ ብለው ነበረ ቢነግሩን
▪️17/እህቴ የካንሰር ታማሚ ናትና ኬሞ ስትወስድ ማስታገሻ የሚሰጣት መድኃኒት እንቅልፍ የሚለቅባት ነው እና መጝሪብን ሰግዳ እስከ ዒሻ መቆየት አትችልም ሰአቱ በጣም ያቆያል የምትኖረው አሜሪካ ነው ምን ታድርግ?
▪️18/ሳላውቅ ድመት መትቼ ገደልኩ እርጉዝም ናት ጨነቀኝ ምን ላድርግ?ጀዛኩሙሏህ ኸይረን
▪️19/ህፃን ልጁ ልጅ አፍ ያልፈታ አዝካር ብንልለት ተቀባይነት አለው ወይ?ያብራሩልኝ
▪️20/ኒካህ ሰኞ ወይም ሀሙስ ማድረግ ሱና ነው ሲባል ሰምቼ ለማወቅና ሱና ከሆነ በተባለው ቀን ኒካህ ለማድረግ አስቤ ነው ያብራሩልኝ
▪️21/አንድ ሰው ከሞተ በኋላ ምግብ መስራት ወይም ሰደቃ መስራት ሙሾ እንደ
ማውረድ ይቆጠራል የሚባለው እውነት ነው ወይ?በለቅሶ ጊዜ?~~~~
💥 በተጨማሪም የተለያዩ ትምህርቶችን ለማግኜት ከታች ያሉትን ሊንኮች ይጠቀሙ
🔸🔹🔸🔹🔸🔹
🌐/channel/ahmedadem
~
🌐/channel/zad_qirat
~~~~
🔗https://www.facebook.com/yenegew/
~~~~
📶 http://www.youtube.com/c/ZadulMaad
አላህ በተከበረው ቃሉ እንዲህ ይላል:-
🔅وَتَزَوَّدُوا فَإِنَّ خَيْرَ الزَّادِ التَّقْوَىٰ ۚ وَاتَّقُونِ يَا أُولِي الْأَلْبَابِ
"ስንቅ ያዙ፤ ከስንቆች ሁሉ በላጩ አላህን መፍራት ነው፤ የአእምሮ/ የልብ ባለቤቶች ሆይ ፍሩኝ" ሱረቱል በቀራ /197
ተክቢረቱል-ኢሕራም የጓደኛ መመዘኛ
የታላቁ ሰሓቢይ ኢብኑ መስዑድ رضي الله عنه ልዩ ደረሳና ቅርብ ሰው የሆኑት ታላቅ ታቢዒይ ኢብራሂም አን'ነኸዒይ እንዲህ ይላሉ፥ "አንድን ግለሰብ ተክቢረተል- ኢሕራም (የሰላት መክፈቻ የመጀመሪያው ተክቢረህ) ላይ የሚዘናጋ -ቀድሞ ሶፍ ላይ ተዘጋጅቶ ቆሞ አሰጋጅ አላሁ አክበር እንዳለ ወዲያ ተከትሎ ተክቢር የማያደርግ- ሆኖ ካገኘኸው (ጭቃና መስለ ቆሻሻ እጁን የነካው ሰው እጁን ታጥቦ ከጭቃው እንደሚርቀው) ከዚህ ግለሰብ ራቅ!"
📚አል-ሙኽታር ሚን መናቂቢል አኽያር 1/281።
🔅በዚህም መሰረት ሁሌ ኢቃም ሲሰሙ እንጂ ከቤትና ከሱቅ መቀመጫዎቻቸው የማይነሱ ኋላ ቀሮችን በሙሉ እጅህን ታጥበህ ዳግም ላትነካቸውና ላትቀርባቸው ራቃቸው፤ ተስፋ እስካልቆረጥክ ድረስ ለመምከር ካልሆነ በስተቀር መቼም ተመልሰህ አታግኛቸው።
🔅ኢቃም ተብሎ እየተሰገደ ከመስጂድ ዙሪያ ቆመው ስልክና ሰው የሚያወሩትንም እዚሁ ውስጥ አካታቸው።
🔅 መስጂድ በረንዳ ውስጥ፣ ከዛም አልፎ ወደ ውስጥ ገባ ብለው ከኢማምና መእሙሞች ጀርባ ላይ ቆመው ሰጋጆችን እየረበሹ ውጪ የጀመሩትን የእርሰበርስ ወሬ ወይም ስልክ ከተክቢረተል ኢሕራምና ከሰላት የሚያስበልጡትንም መክረህ አስጠንቅቀህ ካልተመለሱ አብዝተህ ራቃቸው።
🔅ዲኑን በሚገባ የማያከብርና ለሰላት ቦታ የሌለው ላንተ ምንም አይጠቅምህምና!
✍️ኡስታዝ አሕመድ ሸይኽ ኣደም
7/5/1444 ዓሂ
@ዛዱል መዓድ
🔹🔸🔹🔸🔹
💥 በተጨማሪም የተለያዩ ትምህርቶችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ሊንኮች ይጠቀሙ
🔸🔹🔸🔹🔸🔹
🌐/channel/ahmedadem
~
የኪታብ ደርሶችን ብቻ ለማግኘት
🌐/channel/zad_qirat
~~~~
🔗https://www.facebook.com/yenegew/
~~~~
📶 http://www.youtube.com/c/ZadulMaad
📚"ዒልም ማለት አላህን መፍራት ነው!" አል-ኢማሙ ማሊክ
🔅የዐቂደቱል ዋሲጢያህ ኪታብ ማብራሪያ ከመጀመሪያው እስከመጨረሻው በኡስታዝ አሕመድ ሸይኽ ኣደም
ሙሉውን ደርስ በድምጽ ለማግኜት ከታች ያለውን ሊንክ ዳውንሎድ በማድረግ ይጠቀሙ
🔎https://tinyurl.com/2qvkzv8x
@ዛዱል መዓድ
🔸🔹🔸🔹🔸🔹
🌐/channel/ahmedadem
~~~~
🔗https://www.facebook.com/yenegew/
~~~~
📶 http://www.youtube.com/c/ZadulMaad
📚"ዒልም ማለት አላህን መፍራት ነው!"
አል-ኢማሙ ማሊክ
#አላህን የሚፈራ ሰው
♦️ለሱ ከችግሩ መውጫ ቀዳዳን ያደርግለታል።
♦️ከማያስበው በኩል ሲሳይን ይሰጠዋል።
♦️ከሱ ወንጀሉን ይሰርዝለታል።
♦️የመልካም ስራው ምንዳ ያበዛለታል።
📱/channel/ibrahim_furii
🔻#ጥሩና ዲኑ ላይ ቀጥ ያለ ጓደኛው ያለው ሰው እሱም ቀጥ ይላል።
🔻 #ጓደኛው ለዲኑ ግዴለሽ ከሆነ እሱም ግዴለሽ ይሆናል ።
🔻#ጓደኛ ይጎትታል የመስጂድ ሰው ከሆ ጓደኛህ ወደመስጂድ ይጎትትኃል የሜዳና የኸምር፣የሺሻ ቤት ከሆነ ጓደኛህ ወደዛ ይጎትትኃል ።
🔻#ስለ አንድ ሰው ምንነት ማወቅ ከፈለክ እሱ ምንድ ነው አትበል ጓደኛው ማነው? በል ምክኒያቱም ሰው የሚመስለው ጓደኛው ነው ጓደኛው ጥሩ ከሆነ እሱም ጥሩ ይሆናል ።
🔻#የጥሩ ጓደኛ ትልቁ ጠቀሜታ ጀነት ላይ ማእረግህ ከፍ እንዲል የተወሰነ ቅጣት ኖሮብህ እሳት ውስጥ ገብተህ እንደሆነ ከእሳት ያወጣሃል ።
🔻#የጥሩ ጓደኛ ዝቅተኛ ጥቅሙ ከሱ ጋር ስትሆን ወንጀል አሰራም ።
🔹#ከኡስታዝ አሕመድ ሽይኽ ኣደም (ሐፊዘሁሏህ)
☞#ዲን ላይ መፅናት ከሚለው ሙሃደራ የመጨረሻው ክፍል ላይ የተወሰደ
🔻#ጓደኛ ማንን እንደምናደርግ እንመልከት!✍አላህ ለሁላችንም መልካም ጓደኛ ይወፈቀን እኛም ለጓደኞቻችን ጥሩ ጓደኛ ያድርገን!!! አኗኗራችን ከጥሩ ሰዎች ያድርግልን ።!!!
🍃💌🍃
በየቀኑ ከቁርአን ልንቀራው ያሰብነውን ቂርአት ፕሮግራማችን በፍፁም አይሳካም በእነዚህ 5 ነገሮች እንጂ :
1⃣የአላህ ተውፊቅ(ማግራት)
2⃣አላህ እንዲያግዘን ሁሌ መለመን
በዱዐ መታገዝ .
3⃣ከስንት ሰአት እስከ ስንት ሰአት
በየትኛው ሰአት ምን ያህል መቅራት
አለብኝ የሚል ፕሮግራም ማስቀመጥ.
4⃣ከወንጀሎች በቻልነው መራቅ .
5⃣ምላስን ከሀሜት ከቅጥፈት በሰዎች
ክብር ላይ ከመልቀቅ መጠንቀቅ.
አላህ ይወፍቀን እስቲ ሁላችንም እንሞክረው
🌿🌿📩🌿🌿
@bin_Husseynfurii
ኢብኑ ተይሚያ ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፦
"ጥሩ ነፍሶች ይቅር በማለትና መልካም በመዋል ይረካሉ።
መጥፎ ነፍሶች በክፋትና ወሰን በመተላለፍ ይረካሉ።"
[ነቅዱ ተእሲሲል ጀህሚያ፡ 1/529]
=
የቴሌግራም ቻናል፦
/channel/IbnuMunewor
ማህበራዊ ሚዲያን ለዲንም ለዱንያም መጠቀም
~
ማህበራዊ ሚዲያን ሃይማኖታችንን ለመማማር መጠቀም ትልቅ ስኬት ነው። ነገር ግን እዚህ ላይ መቆም አይገባም። ሁሉም እንደተገራለትና እንደ ተሰጥኦው ወገኑን በመርዳት ላይ ቢተጋ መልካም ነው። የህክምና ግንዛቤ ያለው ጠቃሚ ትምህርቶችን ያሰራጭ። የስራ ፈጠራና ጠቃሚ የቢዝነስ ሃሳቦች ያሏችሁ ችላ ሳትሉ የምክር አገልግሎት በመስጠት ወገናችሁን እርዱበት። ኤሌክትሮኒክስ ወይም ሌላ ቴክኖሎጂ ተኮር እውቀቱ ያላችሁ መረጃ በመስጠት ማገዝ ትችላላችሁ። በተናጠል የሚከብድ ከሆነ ተመሳሳይ ሙያ ያላቸው ተቀናጅተው ቢሰሩት ብዙ ህዝብ መጥቀም፣ ብዙ አጅር ማፈስ ይቻላል።
ከዚህም አልፎ ማህበራዊ ሚዲያን ለነፃ ግልጋሎት ብቻ ሳይሆን ቢዝነስን ለማቀላጠፍ መጠቀምም ይገባል። የራስንም ይሁን የሌሎች ወንድም እህቶችን ምርትና ሌሎች አቅርቦቶችን፣ ሙያና አገልግሎቶችን ማስተዋወቅ፣ ግብይት ማከናወን፣ ዛሬ እየታየ እንዳለው ድለላ መስራት፣ ተቋማትንና የሚሰጡትን አገልግሎት ማስተዋወቅ፣ ... አስፈላጊ እንቅስቃሴ ነው። ስለዚህ የገባችሁበትም፣ ዝንባሌው ኖሯችሁ እያሰባችሁ ያላችሁም በታማኝነትና በሃላፊነት ለመጥቀምም ለመጠቀምም ነይታችሁ ስሩ።
ባይሆን አላህን ፍሩ! ውሸትን ተጠንቀቁ። የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
” يا مَعشرَ التُّجّارِ ! إياكُم والكذبَ “
እናንተ ነጋዴዎች ሆይ! ውሸትን ተጠንቀቁ!" [ሶሒሑ ተርጊብ: 1793]
ብዙ ነጋዴዎች በተለይ በዚህ ዘመን አመፅ የነገሰባቸው፣ ዱንያ አላህን ከመፍራት የጋረዳቸው ሆነዋል። ወደ ዲን የቀረቡ የሚባሉት እንኳ ከሌሎች የተሻሉ መሆን እያቃታቸው ነው። ያስተውሉ! ነብዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፡-
إن التجار يبعثون يوم القيامة فجارا، إلا من اتقى الله وبر وصدق
“ነጋዴዎች በትንሳኤ ቀን አመፀኞች ሆነው ነው የሚቀሰቀሱት። አላህን የፈራ፣ መልካምን የሰራ እና እውነትን ያወራ ሲቀር።" [አሶሒሓህ፡ 994]
=
የቴሌግራም ቻናል፦
/channel/IbnuMunewor
ሞራላቸው ለተሰበረ አካላት ጠጋኝ ሁን!
የሌሎችን ስብራት ሚጠግን የእርሱ ስብራት እንደሚጠገንለትና ለሌሎች የሚያዝን ለእርሱ እንደሚታዘንለት እወቅ! የሌሎችን ስሜት በመጠበቅ ላይ ዲናችን እጅግ አነሳስቷል።
✍Abu Uwais (Naaf)
/channel/AbuUweis
🔻ጥቂት ምክሮች
ለሙስሊም እህቶች
🔊በኡስታዝ አሕመድ ሼይኽ ኣደም (ሓፊዘሁሏህ)
/channel/Tibyaan54
🏷️የዛዱል መዓድ ፈታዋ 🌾
فتاوى زاد المعاد
ቁ/202
ረቡዕ 27/5/1444 ዓ.ሂ
🔊በኡስታዝ አሕመድ ሸይኽ ኣደም
የዳውንሎድ ሊንኩን ይጫኑ
⏬ ⏬ ⏬ ⏬ ⏬ ⏬
🔎https://bit.ly/3BRlZBY
🔹 🔸 🔹 🔸 🔹 🔸~~~~
▪️1/መርዝ ጠጥቶ ወይም ታንቆ እራሱን ያጠፋ ሰዉ አላህ ይማረዉ ይባላል ሶላተል ጀናዛስ ይሰገድበታል?
▪️2/ቤተሰቦቼ የዲን እውቀት የላቸውም እናቴ ሪባ ትጠቀማለች ቢድዓውም ሽርኩም ቦታ ትግኛለች ሀራም ነው ብላት አልሰማ አለችኝ አያገባሽም ብላ ትቆጣኛለች በኔ መቃብር አትገቢም የሁል ጊዜ አባባሏ ነው ወንድሞቸም የወንጀል ቦታ አትቅረቡ ብዙ ጊዜ መክሬያቸው የዲን እውቀት ባላቸው ስዎችም አስምከሬያኳቸው ጭራሽ እየባሰባቸው ሄደ እኔም ትቼ ወደ አረብ ሀገር አመራሁ ወደነሱ መመለስ አልፍልግም እነሱ ካሉበት ራቅ ባለ ከተማ ከነሱ ርቆ መኖር እያስብኩ ነው ሀራም ይሆንብኛል? በወላጅ ሀቅ እጠየቃለሁ ብትረግመኝስ ይይዘኛል? ግራ ገብቶኛል ምን እንዳደርግ ይመክሩኛል? ዱአም አድርጉልኝ
▪️3/ማልቀስ ውዱእ ያበላሻል ሲሉ ሰምቻለው ማለት ለቅሶው አላህን ፈርቶ የተለቀሰ ሳይሆን ቤተሰብ የሞተ ዘመድ እንዲሁም ሽንኩርት ስንከትፍ ከአይናችን የሚወጡ እንባዎች እንዲሁም ሰውን ማማት ውዱእ ያበላሻል?
▪️4/ የዊትር ሰላት ሁሌም የምንሰግድ ሰዎች አንዴ እንቅልፍ ወይም በመርሳት ፈጅር ቢያዝን ቀዷ ማውጣት ያለብን አንድ ረካኣ ነው ወይስ ከዛ በላይ?
▪️5/እኔ ወንጀል ወስጥ ወድቄ ነበር ለመተዉ ከራሴ ጋር በጣም እታገል ነበር አንድ ቀን ለመተዉ ስላልቻልኩኝ ለራሴ ቁራአን ይዤ ማልኩኝ ከወንጀል ለመውጣት በጣም እየታገልኩ ነበር ግን ትንሽ ቆይቼ አሁን ስራሁት ይሄ ከሆነ ቆይቷል አሁን አልሃምዱሊላህ ትቻለሁ ተዉበት አደርጌአለሁ አላህ ተዉበቴ እንዲቀበለኝ ዱዓ አደርጉልኝ እና ከፋራ አለብኝ ከፋራዉስ ምንድነዉ ?
▪️6/ስለዘካ ነበር ይህም እህል ምን ያህል ስሆን ነው ዘካ ምወጅብበት? ለምሳሌ አስር ኩንታል ተቀምጦ የከረመ እህል ምን ያህል ዘካ ይወጣበታል?
▪️7/አክስቴ አሏህ ይራህማት ውድ አኺራ በሂደችበት ጌዜ ክርስቲያን ዘመዶች ለማስተዛዘን ገንዝብ ሰጡኝ ያን ገንዘብ ምን ማድረገ አለበኝ!ለምስኪን ልስጠው ብሩን እንዲሁም ወርቅ ነበራት እና ሸጠን ስድቃ ማውጣት ይችላል ! ወይስ ማስቀመጥ?
▪️8/ሙስሊም እህቶቻችን ተምረው ስራ ሲቀጠሩ ኒቃባችሁን አዉልቁ እየተባሉ ከስራ ይባረራሉ በሌላ መንገድ ገቢ ከሌላቸዉ የሰው እጅ ከማየት ብለው ፊታቸውን ተገልጠው ቢሰሩ ሀራም ይሆንባቸዋል ወይ ?
▪️9/አባቴ ከተወለድን እስካሁን የት አለቹ ብሎ ጠይቆን አያውቅም እኔ 23 አመቴ ሲሆን ወንድሜ 20 አመቱ ነው ከእናቴ ጋር ተፋተዋል ግን እኔ ዝምድና የአባት ሀቅ አለብን እያልኩ አንዳንዴ ከወንድሜ ጋር እንጠይቀዋለን ግን እሱ ለጥቅም የምንጠጋዉ ይመስለዋል አንዳንዴ ደሞ ስንሄድ ሰላቱን በወቅቱ አይሰግድም ተነስ ስገድ ስንለው ከኛ ጋር ጥል ይፈጥራል በዛ ምክንያት ካያነው አሁን 1አመት ሞልቶናል እስካሁን ስላላያነው የሱ ሀቅ አለብን እንዴት ይታያል ?
▪️10/ሴት ልጅ በግሩፕ ዱዓ ማድረግ ትችላለች?የነፍስ አድን ግሩፕ ብለው ከፍተው ሴቶች እየገቡም ያወራሉ ዱዓም ያደርጋሉ ይህ እንዴት ይታያል?
▪️11/ትራቪል ኤጀንሲ (የጉዞ ወኪል) ውስጥ ተቀጥሮ መስራት በዲኑ እንዴት ይታያል ስራው ለሰዎች ሆቴል መያዝ የአይሮፕላን ትኬት መቁረጥ መኪና መከራየትን የመሳሰሉ ይገኙበታል ጀዛኩሙላህ ኸይር
▪️12/አንዲት እህት ቤት ከማግባቷ በፊት ለብቻዋ ቤት ሰርታ ነበር ነገር ግን ካገባች በኋላ ሀገር ሄዳ ታማ ሞተች ካሁኑ ባለቤቷ አንድ ልጅ አላት ከበፊት ባሏም እንዲሁ ፣ባለቤቷ መውረስ ይችላል?በርግጥ ባለቤቷ ቤቱ ላይ የእኔ ንብረት አይደለም ብሏል ሽማግሌዎች ግን መውረስ አለበት እያሉ ነው ይህ እንዴት ይታያል? ያብራሩልኝ
~~~~
💥 በተጨማሪም የተለያዩ ትምህርቶችን ለማግኜት ከታች ያሉትን ሊንኮች ይጠቀሙ
🔸🔹🔸🔹🔸🔹
🌐/channel/ahmedadem
~
🌐/channel/zad_qirat
~~~~
🔗https://www.facebook.com/yenegew/
~~~~
📶 http://www.youtube.com/c/ZadulMaad
አላህ በተከበረው ቃሉ እንዲህ ይላል:-
🔅وَتَزَوَّدُوا فَإِنَّ خَيْرَ الزَّادِ التَّقْوَىٰ ۚ وَاتَّقُونِ يَا أُولِي الْأَلْبَابِ
"ስንቅ ያዙ፤ ከስንቆች ሁሉ በላጩ አላህን መፍራት ነው፤ የአእምሮ/ የልብ ባለቤቶች ሆይ ፍሩኝ" ሱረቱል በቀራ /197
ልብ በል !
ብርቱ ሰው ማለት ስሜትና ጎጂ ፍላጎቱን የሚያሸንፍ ሰው ነው።
"መጥፎ ስሜትና ጎጂ ፍላጎንት መቃረን የሰው ልጅ ልቡ፣ አካሉና ምላሱ ብርቱ እንዲሆን ያደርጋል።
አንዳንድ ቀደምቶች (ስሜቱን ማሸነፍ የሚችል ሰው ለብቻው አንድ ከተማ ድል አድርጎ ከሚቆጣጠር ሰው ይበልጥ ጠንካራ ነው) ይሉ ነበር" አል-ኢማም ኢብኑል ቀዩም 📖 ረውደቱል-ሙሒቢን
#ዲንና አኽላቅን በሚጎዳ ነገር ጊዜ ማሳለፍና መዝናናት ጎጂ ፍላጎትን መከተል ነው።
ዛዱል-መዓድ
/channel/ahmedadem
(🌾የጁሙዓ ኹጥባ በአማርኛ 🌾
ቁ/192
🔹" የኳስ ጥቅምና ጉዳት"
ቅዳሜ 23/5/1444 ዓ.ሂ
🔊በኡስታዝ አሕመድ ሸይኽ ኣደም
የዳውንሎድ ሊንኩን ይጫኑ
⬇ ⬇ ⬇ ⬇
🔎 https://bit.ly/3V3UxHZ
🔹 🔸 🔹 🔸 🔹 🔸
🌐/channel/ahmedadem
📚"ዒልም ማለት አላህን መፍራት ነው!"
አል-ኢማሙ ማሊክ
🌸«በአላህ ይሁንብኝ! የምንዋሽ አልነበርንም። ውሸት ምን እንደሆነ ራሱ አናውቅም ነበር።»
🌸አነስ ኢብኑ ማሊክ
አይ መታደል!
አላሆይ ከውሸትና ከውሸታሞች ጠብቀን‼
🌸ለነፍሴ እረፍትን ሰላምን ፈለኩላት
☞ የማይመለከተኝን ነገር እደመተው የተሻለ ነገር አላገኘሁም ፣
📝ዓሊይ (ረዳየሏሁ አንሁ)
قال الشيخ بن_عثيمين - رحمه الله - :
لو كان البشر مخلوقين للدُّنيا لكان أولاهم بالبقاء الأنبياء والرسل ..
فإذا كنا لم نخلق للدنيا فلماذا نُزاحم أهلها عليها
ولماذا ننسى الآخرة، لماذا لا يذكر الإنسان وهو يلبس الثوب الجديد أنه ربما يلبس الكفن في آخر النهار وإن كان في الليل ربما يلبسه قبل الصباح
لكن القلوب في غفلة نسأل الله أن يحيي قلوبنا بالعلم والإيمان .
📚 [ ﺷﺮﺡ ﺍلنونية (٤٧٤/٤) ]
🏷️የዛዱል መዓድ ፈታዋ 🌾
فتاوى زاد المعاد
ቁ/199
ማክሰኞ 5/5/1444 ዓ.ሂ
🔊በኡስታዝ አሕመድ ሸይኽ ኣደም
የዳውንሎድ ሊንኩን ይጫኑ
⏬ ⏬ ⏬ ⏬ ⏬ ⏬
🔎https://tinyurl.com/2jfq7s9u
🔹 🔸 🔹 🔸 🔹 🔸~~~~
▪️1/በቁረአን አምኖ በሀዲስ የማያምን ሰው ይከፍራል ወይ ? በሀዲስ የማያምነው ሀድሱን የጣፈው ሰው ሊሳሳት ይችላል በማለት ነው
▪️2/አንድ ሰው እየሰገደ ከቂያም ወደ ሱጁድ ሲወርድ ቀድሞ መሬት የሚነካው እጅ ወይንስ ጉልበት ያብራሩልኝ ጀዛከላህ ኸይረን
▪️3/ወንድ ዶክተር ነኝ በህክምና ምክንያት የሴት ብልት ምርመራ ካደረግኩ ውዱዬ እንደጠፋ ማወቅ እፈልጋለሁ
▪️4/እኛ በምንሠራበት ሱቅ አንዳንዴ ሌቦች ይገጥሙናል እና ሰርቀው ሲወጡ ከያዝናቸው የሠረቁትን እጥፍ እናሥከፍላቸዋለን አቃውም እንሠጣቸዋለን ግን ጭማሪው ብር ለሙሳፊር እንሠጠዋለን ጭማሪ ማስከፈላችን ሀራም ይሆንብናል ?ቢያብራሩልን
▪️5/በአሁኑ ጊዜ የሙስሊም ስጋ ቤቶች አሉ የእርድን መስፈርት ጠብቀው ይረዱ አይረዱ ምናቀው ነገር የለም። ኢዶች ወይም በአላቶች በመጡ ቁጥር በሬ ወይም በግ ገዝቶ የማረዱ አቅም ከሌለን ስጋ ከሙስሊም ስጋ ቤቶች ገዝተን ነው ምንጠቀመው ይሄ እንዴት ይታያል?
የሙስሊም ስጋ ቤት ከመሆኑ በተጨማሪ ሌሎች መስፈርቶች መመልከት ይኖርብናልን?
▪️6/በአሁኑ ጊዜ ኤልፎራ የሚባል የዶሮ ስጋ አለ ይህንን መብላት በሸሪዐችን እንዴት ይታያል?
▪️7/ከክርስትና ወደ እስልምና የመጣች ሰለምቴ ጋር ለመጋባት አስበን ነበር እና በመስለሟ ምክንያት ቤተሰቦቿ ጋር ጥሩ ግንኙነት የላትም እና ለሷ ወልይ ሁኖ የሚድራት ማን ነው ሌላው እኔ እና እሷ በቪዲዮ ነው የተያየነው ሳንገናኝ ኒካህ ማሰሩስ እንዴት ይታያል እንዴትስ መታሰር አለበት ማለቴ አሁን መገናኘት አንችልም የተዎሰነ እንቆያለን እስከዛ ደግሞ ሀራም ላይ እንዳንወድቅ ፈርተን ነው
▪️8/በእድሜ ለገፉ አባቶች ፊት መገለጥ ይበቃል ወይ እንዲሁም በእድሜ ለገፉ ወንድ አሰሪወቻችንስ ?
▪️9/የጓደኛየ አጎት እሰዉ ጋር ተጣልቶ ነበር እናም ሰዉ በእጁ አጥፍቷል አሁን እሚኖረዉ እጓደኛየ አባት ቤት ነዉ ማለትም እወንድሙ ቤት የጓደኛየ አባትም ቤቱን ልቀቅ ሲባል እምቢ አለ እናም እራሴን የምጠብቅበት መሳሪያ ግዥልኝ አላት መግዛት ትችላለች ወይ?ለጊዜዉ እጆዋ ላይ ብር ስለሌላት አበድሪኝ አለችኝ ባበድራት የወንጀል ተባባሪ ነኝ?አባቷ ክርስቲያን ነዉ ልጅቷ ሙስሊም ነች ያብራሩልኝ
▪️10/አክስቴ ባሏ ካፊር ነው መጀመሪያ ስታገባው እሰለማለው ብሎ ነው ያገባት ስሙንም ቀይሮ ነበር ሙስሊም ሆኛለሁ ብሎ አሁን ግን በግልጽ ካፊር እንደሆነ ታውቃለች ግን አሁንም አንድ ላይ ነው ያሉት።ያኔ ኒካህ ተብሎ የታሰረውም አልወረደም እሄስ እንዴት ይታያል ኒከሃ እነለዋለን? እሷ ትጾማለች ትሰግዳለች ሙስሊሞች ሚያደርጉትን ነገራቶች ታደርጋለች እነደዛውም ደግሞ የካፊሮችንም በአላት በሙሉ ለሱ ተብሎ ቤት ውስጥ በሃይለኛው ይከበራል ከተጋቡ ቢያንስ 35-40 አመት ይሆናል እኛ ደግሞ ስንናገራት ትርቀናለች አንዳንድ ቤተሰቦቻችን ደግሞ ዝምድና መቁረጥ ነው ይሉናል ከሷ ጋር ያለንን ግንኙነት ምን ማድረግ አለብን?
▪️11/ በመሰረቱ ለሴቶች ጁምዓ ሱና ነው አይደል? መስጂድ ሄደው ተከታይ ሆነው ሲሰግዱ ሱና ነው ወይስ ፈርድ ብለው ነው ሚነይቱት? ጀምዓ ነው ወይስ ጁምዓ ነውስ የሚባለው?
▪️12/ ልብስ እና ዕቃ በሚታጠብበት ጊዜ የሚረጨው አረፋ ቢነካን ይነጅሰናል? ማለት አረፋው(ሳሙናው) ነጃሳ ይሆናል?
▪️13/ ከሰላት ቡሀላ ሱና ሰላቶችን(ባዕዲያዎችን) ስንሰግድ በቋሚነት ፈርድ ሰላት ላይ ያጓደልኩትን ነገር ማሟያ ይሆነኛል ብሎ አብሮ ነይቶ መስገድ ችግር አለው? ይከለከላል?
▪️14/ቁርዓን በመሀፈዝ በዱንያም በአኼራም ሚገኘው ትሩፋት ምንድነው?
▪️15/ ሴት ልጅ ፊትዋን መሸፈን ግዴታ ነው?ቢያብራሩልኝ።
▪️16/ እኔ በጣም በጣም ሳቅ አበዛለው አንዳንዴ መሳቅ የሚያሳፍርበት ቦታ ሁሉ ሳቄን መቆጣጠር ያቅተኛ ለመቀነስ ብሞክርም አልቻልኩም በዚህ ፀባዬ ብዙ ጊዜ ተሸማቅቄያለው አፍሬያለውም ከዚህ ችግር የምወጣበትን ነገር አመላክቱኝ። ዱአም አድርጉልኝ።
~~~~
💥 በተጨማሪም የተለያዩ ትምህርቶችን ለማግኜት ከታች ያሉትን ሊንኮች ይጠቀሙ
🔸🔹🔸🔹🔸🔹
🌐/channel/ahmedadem
~
🌐/channel/zad_qirat
~~~~
🔗https://www.facebook.com/yenegew/
~~~~
📶 http://www.youtube.com/c/ZadulMaad
አላህ በተከበረው ቃሉ እንዲህ ይላል:-
🔅وَتَزَوَّدُوا فَإِنَّ خَيْرَ الزَّادِ التَّقْوَىٰ ۚ وَاتَّقُونِ يَا أُولِي الْأَلْبَابِ
"ስንቅ ያዙ፤ ከስንቆች ሁሉ በላጩ አላህን መፍራት ነው፤ የአእምሮ/ የልብ ባለቤቶች ሆይ ፍሩኝ" ሱረቱል በቀራ /197
«(ሚስቶቻችሁን) በመልካም ተኗኗራቸው
ብትጠሉዋቸውም (ታገሱ)አንዳችን ነገር ብትጠሉ
አላህም በእርሱ ብዙ መልካም ነገርን ሊያደርግ
ይችላልና።»
♻️{ሱረቱ አን‘ኒሳዕ}
📱/channel/ibrahim_furii
ኳስ የዘመናችን ጣዖት
~
ዛሬ ላይ ኳስ ከተራ መዝናኛነት አልፏል።
* በአላህ መንገድ ላይ የማይወጣው በቢሊዮን ዶላር የሚቆጠር ወጭ ይወጣበታል። ሚሊዮኖች እየተራቡ፣ በክህ -ደት ሰባኪዎች እየተጠለፉ ከግለሰቦች እስከ መንግስታት ለዚህ ቆሻሻ ነገር ግን የማይገመት ወጭ ያወጣሉ።
* ዘረኝነት ይንፀባረቅበታል።
* በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ አስካሪ መጠጥ ይተዋወቅበታል።
* የጭፈራና የዘፈን ድግስ ይቀርብበታል።
* እጅግ በርካቶች ለሱ ሲሉ ግዴታ የሆነባቸውን ሶላት ያሳልፋሉ።
* እጅግ በርካቶች ለሱ ሲሉ ጎረቤት ይበጠብጣሉ፣ የወላጅ ሐቅ ይጥሳሉ፣ እርስ በርስ ይጋጫሉ፣ ለሱ ሲሉ ይወዳሉ፣ ይጠላሉ።
* የመገናኛ አውታሮች፣ ማህበራዊ ሚዲያዎች፣ ጋዜጦችና መፅሔቶች፣ ግለሰቦች፣ በቤትም በውጭም፣ በየጎዳናው፣ በየ ካፌው፣ ቆመው ተቀምጠው፣ ... ለዲንም ይሁን ለዱንያ በሚጠቅም ጉዳይ ላይ ከሚጮሁት እጅግ በላቀ ስለዚህ ርካሽ ነገር ሆኗል ውትወታቸው። እንዲያውም ቀላል የማይባሉ ጥራዝ ነጠቆች ስለ ኳስ መተንተንን የንቃት ማሳያ አድርገውታል። ስለ ኳስ አለማወቅን ፋራነት አድርገውታል። ከዚህ በላይ ምን ዝቅጠት አለ?!
* በዚህ ቆሻሻ ነገር የተነሳ እጅግ በርካታ ወጣቶቻችን ከሃዲዎችን፣ የሉጥ ህዝቦችን ተግባር የሚፈፅሙ፣ ለሱ ጥብቅና የሚቆሙ ርካሽ ፍጡሮችን እንዲያደንቁ ሆነዋል። ደካማ ሰበብ እየደረደሩ ራሳቸውን አደንዝዘዋል።
* ከዚህ ሁሉ በኋላ አንዳንዶች ጂሃድ ሊያስመስሉት ሲዳዳቸው ይታያሉ። ኳስ በዚህ በመከራ በተከበበ ህዝብ ላይ የተከፈተ ወደን የተቀበልነው ጦርነት ነው።
ይሄ ሁሉ እውነታ በገሃድ ፈጦ የሚታይ ከመሆኑ ጋር ቢያንስ ሸሩን በመቀነስ ላይ እንኳ ዱዓቶች እየሰሩ አይደለም። የዱዓት ትልቁ በሽታ ሰፊው ህዝብ የወደቀባቸውን ጉዳዮች ለመጋፈጥ ወኔ ማጣት ነው። መሬት ላይ ባለው ተጨባጭ (ዋቒዕ) መሸነፍ። አትጠራጠር ወንድሜ! ኳስ ከዘመናችን ብዙ ዓይነት ጣዖቶች ውስጥ አንዱ ጣዖት ሆኗል። አደራ! ሌላው ቢቀር ቢያንስ ለዚህ የቦዘኔዎች ስራ ብለን ሶላት ከወቅቱ የምናሳልፍ እንዳንሆን እንጠንቀቅ። ለዚህ የጂላጂሎች ስራ ብሎ መስጂዶቻችንን ማራቆት የሚያሳፍር ጉዳይ ነው። ስለዚህ ነፍሲያችንን እንርገጥ። ተቅዋን እናስቀድም።
ማሳሰቢያ፦
- ያወራሁት ስለ ኳስ እንጂ ስለ ቀጠር አይደለም።
=
የቴሌግራም ቻናል፦
/channel/IbnuMunewor
«ከንግግር አንድንም አይናገርም
አጠገቡ ተጠባባቂና ዝግጁ(የተጣዱ)
መላይኮች ያሉበት ቢሆን እንጂ።»
[ሱረቱ‘ቃፍ]
/channel/ibrahim_furii
#አስቸኳይ_ነው‼️
#እያለቀሱ_ነው
አንድ ልበደግ ወንድማችን ስልክ ደወለልን!!"አንዲት እናት እያለቀሱ ቀራንዮ መንገድ ላይ አገኘኋቸው!ምን ላድርግ?"ብሎ ጠየቀን!!
እማማን የሚታይ ፎቶ አንሳቸውና ላክልን አፋልጉኙን በቶሎ እንለጥፋለን እስከዛ ፖሊስ ጣቢያ ውሰዳቸው" አልነው!!
እንደነገርኩት ፎቶ አንስቶ የሚሄድበትን ጉዳይ ትቶ ጦርሀይሎች ፖሊስ ጣቢያ ይዟቸው ሄደና "እማማ ጠፍተው ነው ቤተሰብ እስኪገኝ እዚህ ይሁኑ?" ብሎ በትህትና ጠየቃቸው!ፖሊሶቹ እንደተለመደው "አንቀበልም እኛን አይመለከተንም" ብለው መለሱት!!
ወንድማችን ተሜ መልሶ ወደኛ ደውሎ "ምን ላድርግ እምቢ አሉኝ እኮ ካልሆነ ቤት ልውሰዳቸው እንዴ?" አለን!!በደስታ አዎ አሁን ልጆቻቸው መገኘታቸው አይቀርም አልነው! #እናንተን_ተማምነን!
ስሜ #ዘህርያ_ሁሴን የልጆቼ ስም መኑር ሁሴን፣ሀሰን ሁሴን እና ፈድሉ ሁሴን፣ይባላል ብለውናል!! #ሼር አድርገን እናገናኛቸው🙏
"ለመልካም ስራ ረፍዶ አያውቅም"
#ባይሽ_ኮልፌ_በጎ_አድራጎት
0939684393-ተመስገን
0913559189-ሄኖክ
0912121942-ውብሸት
0921058424-ኤደን
🌿 የኡስታዝ አብዱሰላም ዚያራ
-------------------------
ከፎቅ ላይ ወድቆ የተጎዳው ወንድማችን ኡስታዝ አብሱሰላም አህመድ ዛሬ ዚያራ ተደርጎለታል።በዚያራው ላይ በርካታ ወንድሞችና ኡስታዞች በመገኘት አበሽረውታል።
ኡስታዝ አብዱሰላምም የተሰማውን ደስታ ገልጿል።
https://youtu.be/cpF8u_TRM9U
https://youtu.be/cpF8u_TRM9U
https://youtu.be/cpF8u_TRM9U
አማትን "እናቴ" "አባቴ" ... እያሉ መጥራት
~
* መነሻ የሆነኝ የሚከለክል ፈትዋ ሲሰራጭ ማየቴ ነው።
አንድ ሰው የሚስቱን ወላጆች (እማ፣ አባ) እያለ ቢጠራ፣ ወይም አንዲት ሴት የባሏን ወላጆች በዚህ መልኩ ብትጠራ ምንም የሚከለክል ማስረጃ የለም። ሐራም ማለት አላህ ሐራም ያደረገው ነው። ክልክልነታቸውን የሚጠቁም ሸሪዐዊ መረጃ እስካልቀረበ ድረስ የተለያዩ ይዘቶች ካሏቸው የመሻይኽ ፈትዋዎች ውስጥ ከልካዩን ብቻ መዝዘን መሰል ልማዶችን ሐራም ማድረግ አያስኬድም። መሰል ልማዶች መሰረታቸው ፍቁድነት ነው። ከዚህ መሰረት አውጥቶ ሐራም ለማለት ተጨባጭ መረጃ ያስፈልጋል። ልብ በሉ! በእንዲህ ዓይነት ጉዳይ ላይ መረጃ የሚጠየቀው ፈቃጅ ሳይሆን ከልካይ ነው።
ደግሞም አማቷን "እማዬ" ስትል "እናትሽ ቢሆኑማ ባልሽ ወንድምሽ ይሆን ነበር" ማለት ልክ አይደለም። የሚፈለገው አክብሮት እንጂ በትክክል ወላጅ እናቴ ናቸው ለማለት እንዳልሆነ ግልፅ ነውና። አማትን በዚህ መልኩ መጥራት በብዙ ባህሎች የተለመደ ነው። ስለዚህ ይሄ ባህል በተለመደበት ሃገር ላይ በተሳሳተ መልኩ ሰዎች እንዳይረዱ የሚለው ሰበብ ውሃ የሚያነሳ አይሆንም።
አዛውንቶችን፣ ዑለማዎችን "አባታችን" እያሉ በአክብሮት መጥራት በሰፊው አለ። ለምሳሌ ያህል ታላላቅ ዐሊሞችን "ሰማሐቱል ዋሊድ" ሲሉ ማየት የተለመደ ነው። መቼስ ይህንን ለሚል ሁሉ ያ ሸይኽ በትክክል ወላጅ ስለሆኑት አይደለም እንዲህ የሚባለው።
ማሳሰቢያ:-
1- አንድ ሰው አባቱ ባልሆነ ስም መጠራት አይፈቀድም። ማለትም የሌላን ሰው ስም በአባት ስም ቦታ ተክቶ ለመጠሪያነት መጠቀም አይቻልም። ይሄ ግልፅ ማስረጃ የመጣበት ጉዳይ ነው። ነገር ግን ይሄኛው ነጥብ ከያዝነው ጉዳይ ጋር የሚገናኝ አይደለም። በመጠሪያ ስምነት ስለ መጠቀም አይደለም እያወራን ያለነው።
2- "ሸይኽ እከሌ ግን አይፈቀድም ብለዋል" የሚል እንደሚኖር እጠብቃለሁ። እኔም እሱን አይቼ ነው ይህንን የፃፍኩት። ከተጨባጭ መረጃ ጋር ያልተቆራኘ ፈትዋ ማስፈራሪያ ሆኖ መቅረብ የለበትም። በዚያ ላይ ችግር እንደሌለበት የጠቆመ ዓሊምም መጥቀስ ይቻላል። ለምሳሌ ኢብኑ ዑሠይሚን ረሒመሁላህ።
ሰዎች ከልካዩን ፈትዋ ይዘው ከልማድ ባፈነገጠ መልኩ ቢጓዙ በንቀትና አለማክበር ተተርጉሞ መቀያየም ሊያስከትል ይችላል። ውጤቱን ፈርተው ቢቀጥሉ እንኳ የጥፋተኝነት ስሜት እየተሰማቸው ሊኖሩ ይችላሉ። ወይም "አሁንስ አበዛችሁት!" ዓይነት የመሰላቸት ስሜት ሊያድር ይችላል። ስለዚህ መሰል ጉዳዮችን ከማሰራጨታችን በፊት "ሌሎችስ ምን ይላሉ?" የሚል ትንሽ ፍተሻ ብናደርግ መልካም ነው። ወላሁ አዕለም።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
/channel/IbnuMunewor
#ቀልብ ቂመኛ፣ ምቀኛ፣ በራሱ የሚደነቅና የሚኮራ ከሆነ ንፁሕ ልብ አይሆንም።
《ኢብኑል ዐረቢ አልማሊኪ》
【አሕካሙል ቁርኣን:(3/459)】