tibyaan54 | Unsorted

Telegram-канал tibyaan54 - 💎ቲብያን 💎 የተለያዩ ዳዕዋዎች የሚተላለፉበት ቻናል!

2303

🍂የቲብያን ቻናል ዋና አላማው አላህ ኢኽላሱን ይስጠንና በተቻለን አቅም ጠቃሚ ናቸው የምንላቸው ወቅታዊ ሙሃደራዎችን እንዲሁም ጠቃሚ ማስታወሻዎች አጫጭር ፁሁፎችና ፎቶዎችንምን ! ላልደረሳቸው ማድረስ ነው። «السلفية منهجي» https://t.me/joinchat/AAAAAEPOgchGXF37Mja27A

Subscribe to a channel

💎ቲብያን 💎 የተለያዩ ዳዕዋዎች የሚተላለፉበት ቻናል!

የአሚን ሆስፒታል ባለቤት ዶ/ር ሙሐመድ ሽኩር ይህንን የ10 ሚሊዮን ብር ሽልማት ካገኘሁ አንድም ሳልቀንስ ሙሉ ሽልማቱን መታከሚያ ላጡ ወላድ እናቶችና ጨቅላ ህፃናት የሕክምና አገልግሎት እለግሰዋለሁ ስላለ፤ በገንዘብ እጦት ለሚሰቃዩ እናቶችና ህፃናት ስንል ዶ/ር ሙሐመድን (Mosmige) ወደ 9355 አጭር የጽሑፍ መልዕክት BIW03 በመላክ እንምረጠው።

BIW03 ብለን ስንልክ በBIW እና 03 መካከል ክፍት ቦታ መኖር የለበትም፣ BIW የሚለው በsmall letter biw ሳይሆን BIW ነው። በትክክል መምረጣችሁን ለማወቅ፤ ከላካችሁ በኋላ ወዳውኑ«You have voted for ( Dr Mohamed shikur ). Thank you for your participation. Abbay TV 'Ethiopia's Best'» የሚል መልዕክት ከመጣላችሁ በትክክል መርጣችኋል። በርቱ! በተለያዩ ገፆች መልዕክቱን አሰራጩት።

Читать полностью…

💎ቲብያን 💎 የተለያዩ ዳዕዋዎች የሚተላለፉበት ቻናል!

🍃 "እውነተኛ ደስታና ሰላም ሊገኝ የሚችለው ለዚህች አለም ፈጣሪ እና ጠባቂ ለሆነው ጌታችን አላህ ትዕዛዝ ተገዢ በመሆን ብቻ ነው"።

#ላቅ ያለው አላህ በተከበረው ቃሉ እንዲህ ይላል

🔹الَّذِينَ آمَنُوا وَتَطْمَئِنُّ قُلُوبُهُم بِذِكْرِ اللَّهِ ۗ أَلَا بِذِكْرِ اللَّهِ تَطْمَئِنُّ الْقُلُوبُ

[ ሱረቱ አል- ረዕድ፥ - 28 ]

(እነሱም) እነዚያ ያመኑ ልቦቻቸውም አላህን በማውሳት የሚረኩ ናቸው፡፡ ንቁ! አላህን በማውሳት ልቦች ይረካሉ፡፡

Читать полностью…

💎ቲብያን 💎 የተለያዩ ዳዕዋዎች የሚተላለፉበት ቻናል!

ከፊል ወንዶች  በጣም  ይገርማሉ መኪናቸውን  አቧራ፣ ፀሀይ እዳያገኝባቸው  ይሸፍናሉ።
ሚስታቸውን እና ልጃቸውን ግንአይሸፍኑም!?

ለሚያስተነትን ሰው እሚገርም ንግግር!!


➛ግርድፍ ትርጉም

Читать полностью…

💎ቲብያን 💎 የተለያዩ ዳዕዋዎች የሚተላለፉበት ቻናል!

⇒አንድ ሰው ለዐብደሏህ ኢብኑ ዲናር ምከረኝ አለው ፡ ዐብደሏህም እንዲህ አለው ፦ |"ለብቻህ በምትሆንባቸው ጊዜያቶች ላይ አላህን ፍራ "|

(ሒልየቱል አውሊያእ ፥ 10/359)

Читать полностью…

💎ቲብያን 💎 የተለያዩ ዳዕዋዎች የሚተላለፉበት ቻናል!

ለነገ ስንቅ ያዙ!
•>ከስንቆች ሁሉ የተሻለው /በላጩ/ አላህን መፍራት {ያዘዘውን መስራትና የከለከለውን መከልከል}  ነው።
ዛዱል መዓድ

Читать полностью…

💎ቲብያን 💎 የተለያዩ ዳዕዋዎች የሚተላለፉበት ቻናል!

ሞት!

አጭር ግጥም
اللهم إنا نسألك حسن الخاتمة ونعوذ بك من سوء الخاتمة.
اللهم ارزقني قبل الموت توبة وعند الموت شهادة وبعد الموت جنة  
اللهم ارزقني حسن الخاتمة

Читать полностью…

💎ቲብያን 💎 የተለያዩ ዳዕዋዎች የሚተላለፉበት ቻናል!

☞በማለዳው ወዴት ነው የምትሄደው?
☞ወደ ስራ!
☞ፈጅር ሰግደሃል?
☞አይ! ሶላት አልሰግድም። ሂዳያ እንዲሰጠኝ ዱዓ አድርግልኝ።
☞አደርጋለሁ።ግን ወደ ስራ አትሂድ! !
☞ለምን?
☞ሪዝቅ እንዲሰጥህ ዱዓ አደርግልሀለሁ!!
منقول

Читать полностью…

💎ቲብያን 💎 የተለያዩ ዳዕዋዎች የሚተላለፉበት ቻናል!

ያ........ኔ………

በኹሹዕ ስትሰግድ ፣ ቁርዓን በተደቡር ስትቀራ ፣ ከጌታህ ጋር የነበረህ ሁኔታ እጅግ ያማረ በነበረ ጊዜ ፣ ልብህ በኢማን ተሞልታ ፍንድቅ ስትል በሚታወቅህ ወቅት ፣ ፊትህ ኑር በተላበሰች እና ከጌታህ ጋር በየትኛውም ወቅት ለመገናኘት ዝግጁ የሆንክበትን ጊዜያቶችን………
አስታወስክ !?
ታድያ አሁን የት አለህ!?
ምን ሆንክ !?
ወደነዚያ ጣፋጭና ውብ ጊዜያት መመለስን አላሰብክምን!?

💫/channel/mengdengaw

Читать полностью…

💎ቲብያን 💎 የተለያዩ ዳዕዋዎች የሚተላለፉበት ቻናል!

ጌታውንም «እኔ የተሸነፍኩ ነኝና እርዳኝ» ሲል ጠራ፡፡

Читать полностью…

💎ቲብያን 💎 የተለያዩ ዳዕዋዎች የሚተላለፉበት ቻናል!

መውሊድ ወደ አላህ የሚያቃርብ ድርጊት ቢሆን ኖሮ ነቢዩ ﷺ ይጠቁሙን ነበር።
«ከኔ በፊት አንድም ነቢይ አልነበረም፣ ለህዝቡ የሚያውቀውን  መልካም ነገር በሙሉ መጠቆም እና  ለነሱ መጥፎ እንደሆነ የሚያውቀውን ነገር ማስጠንቀቅ ግዴታ ቢሆንበት እንጂ።»
የአላህ መልክተኛ ﷺ
(ሙስሊም ዘግበውታል።)

Читать полностью…

💎ቲብያን 💎 የተለያዩ ዳዕዋዎች የሚተላለፉበት ቻናል!

➻ይህች ናት ሙስሊሟ እህታችን!

🎙
በኡስታዝ አሕመድ አደም {ሐፊዘሁላህ}

አጭር መልዕክት 5:47 ደቂቃ

መጠን፦ 2.8 MB
Mp3

https://t.me/joinchat/AAAAAEPOgchGXF37Mja27A

Читать полностью…

💎ቲብያን 💎 የተለያዩ ዳዕዋዎች የሚተላለፉበት ቻናል!

ነቢዩ ﷺ ላይ የመዋሸት መዘዝ

🔅ነቢዩ ﷺ ላይ መዋሸት ማለት እሳቸው ያላሉትን ብለዋል ወይም ያላደረጉትን አድርገዋል ማለት ሲሆን ይህ ከከባባድ ወንጀሎች መካከል አንዱ ነው።
ከመሆኑም ጋር በዚህ የሶሸል ሚዲያ ማዕበል በፈነዳበትና ንግዱም በተጧጧፈበት ዘመን ይህን ከባድ ወንጀል ብዙ ሰዎች አውቀውም ይሁን ሳያውቁ ሲዳፈሩትና ነቢዩ ﷺ ያላሉትን ብለዋል፤ ያላደረጉትንም አድርገዋል ሲሉ እንሰማለን።
እነሆ ይህ ድርጊት ወደ ጀሀነም የሚውሰድ መንገድ በመሆኑ የኣኺራህ ጉዳይ የሚያሳስበው በሙሉ ከዚህ እኩይ ተግባር ሊቆጠብና ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል ወይም አድርገዋል ከማለቱ በፊት ቆም ብሎ ሊያስብና ከርሳቸው ጋር አያይዞ ሊናገረው ያሰበው ነገር እውነትና ትክክል መሆኑን ቀድሞ ሊያረጋግጥ እርግጠኛ ካልሆነ ዝምም ሊል ይገባል።
ይህ ካልሆነ ግን እርግጠኛ ያልሆነበትን ነገር ነቢዩ ﷺ ላይ እየቀጠፈና እየለጠፈ የሚናገር ሰው ነገ ጀሀነም ይገባል!

🔅ሩኅሩህና መካሪ ነቢያችን ﷺ በዚህ ዙሪያ ሲናገሩና ሲያስጠነቅቁ የሚከተለውን ብለዋል፥
"የቅጥፈት ሁሉ ቅጥፈት እኔ ያላልኩትን ብሏል ብሎ መናገር፤ በህልም ያላዩትን አይቻለሁ ማለትና ወላጁ ያልሆነን ሰው ወላጄ ነው ብሎ መናገር ነው " ብለዋል።
አል-ቡኻሪ ሐ/3509፣ ሙስነድ አሽሻፊዒ ሐ/1213 ላይ ዘግበውታል።

"እኔ ላይ አትዋሹ! እኔ ላይ የሚዋሽ እሳት ይገባል! " ሙስሊም ሙቀዲመህ ላይ ዘግበውታል።

"እኔ ላይ የሚዋሽ ሰው ጀሀነም ውስጥ ቤት ይሰራለታል" ሙስነድ አሕመድ ሐ/4742፣ ሙስነድ አሽሻፊዒ ሐ/1215 ላይ ዘግበውታል።

💥 በእውቀት ማነስ ወይም ሆነ ብሎ ለርካሽ አላማ፤ እንዲሁም በድፍረትና በግዴለሽነት አላህና መልዕክተኛው ላይ ከመዋሸትና ከሚያስከትለውም መዘዝ አላህ ራሱ ይጠብቀን!

✍ ኡስታዝ አሕመድ ሸይኽ ኣደም

ዛዱል-መዓድ
/channel/ahmedadem

Читать полностью…

💎ቲብያን 💎 የተለያዩ ዳዕዋዎች የሚተላለፉበት ቻናል!

በሃገረ ሳዑዲ ዐረቢያ የወርሃ ዙል-ሒጃህ ጨረቃ ዛሬ ሐሙስ ስለታየች ነገ ጁሙዓህ ግንቦት 30, 2016 E.C. የዙል-ሒጃህ ወር የመጀመሪያው ቀን ይሆንና ወርቃማዎቹ የዙል-ሒጃህ 10 ቀናት ከነገ ይጀምራሉ። ስለሆነም ቅዳሜ ጁን 15, 2024 (ሰኔ 08, 2016 E.C.) የዕለተ ዐረፋህ ቀን ሲሆን እሁድ ጁን 16 (ሰኔ 09) ዒደ-ል-አዽሓህ ይሆናል። አላህ በሰላም ያድርሰን‼

እነዚህን ወርቃማ ቀናቶች በዒባዳህ ለማሳለፍ ከወዲሁ ዝግጅት አድርጉ። ቀናቶቹን ከምታሳልፉባቸው ዒባዳዎች መካከል፤ ጾም፣ ዚክር፣ ቁርኣን መቅራት፣ ሶደቃ፣ ለቻለ ሰው ሐጅና መሰል በጎ ተግባራትን ማከናወን ይገኙበታል። አላህ ያበርታን።

ሌሎችንም አስታውሱ!

✍ሙራድ ታደሰ

Читать полностью…

💎ቲብያን 💎 የተለያዩ ዳዕዋዎች የሚተላለፉበት ቻናል!

ያንተ ሪዝቅ ምናልባት ከምንም አይነት በሽታ ነፃ ሁነህ ጤነኛ መሆንህ ሊሆን ይችላል…

ወይም ለምትሰራቸው ጥፋቶችና ወንጀሎች የአላህ ሲትር ሊሆን ይችላል…

ወይም ባሮቹ ዘንድ ተቀባይነት እንዲኖርህ ሊያደርግ ይችላል…

ወይም በፍቅር የተሞላ ቤተሰብ የሰጠህ ሊሆን ይችላል…

ወይም ጠቃሚ የሆነ እውቀትን ሰጥቶህ ሊሆን  ይችላል…

የአላህ ሲሳዮች ብዙ ናቸው … በገንዘብና በቁሳዊ ነገሮች ብቻ የሚገደቡ አይደሉም ።
አላህ በውሳኔዎቹ ላይ መደሰትን ከለገሰህ  …ሁሉም ነገር ጥሩ ሪዝቅ ሁኖ ይታይሀል ።

በአላህ ውሳኔ መደሰትን ያጣህ እንደሆነ… ዱንያን በአጠቃላይ ብትይዝ እንኳ አትደሰትም።

ለአንተ የተወሰነ ነገር ከሆነ በሁለት ተራሮች መካከልም ቢሆንም ይመጣልሀል…

ለአንተ ያልተወሰነ ነገር ከሆነ ደግሞ በእጆችህ መካከል ቢሆንም እንኳ አይሆንህም …

ለአንተ የተፃፈ ነገር ከሆነ በእርግጥም ደካማ ብትሆንም እንኳ ታገኘዋለህ …

ሲጀመርም ለአንተ ያልሆነ ነገር ደግሞ ጠንካራ ብትሆንም እንኳ አታገኘውም…  

አላህ ለአንተ የከፈተውን በር የሰው ልጆችም አጋንንትም ቢተባበሩ አንኳ ሊዘጉብህ እንደማይችሉ አውቀህ ህይወትህን ተረጋግተህና በአላህ ተማምነህ ኑር !!!

/channel/mengdengaw

Читать полностью…

💎ቲብያን 💎 የተለያዩ ዳዕዋዎች የሚተላለፉበት ቻናል!

وعليكم السلام ورحمة الله وبركاته
🌹تقبل الله منا ومنكم صالح الأعمال 🌹

Читать полностью…

💎ቲብያን 💎 የተለያዩ ዳዕዋዎች የሚተላለፉበት ቻናል!

የዑመቶቼ እድሜ ከስልሳ እስከ ሰባ ድረስ ባለው መካከል ነው፡ ከዚህ የሚያልፉት ጥቂቶች ናቸው።

#ነብዩ ሙሀመድ( ሶለላሁ ዓለይሂ ወሰለም)

📗ምንጭ፦ ሶሒሁ ቲርሚዚ (3550)

Читать полностью…

💎ቲብያን 💎 የተለያዩ ዳዕዋዎች የሚተላለፉበት ቻናል!

ሶላት ሪዝቅን ታመጣለች፣ ጤናን ትጠብቃለች፣ ልብን ታጠነክራለች፣ ፊትን ታበራለች፣ ነፍስን ታስደስታለች፣ ስልቹነትን ታስወግዳለች።
ኢብኑል ቀይም

📝ምንጭ፦ ዛዱል መዓድ (4/304)

Читать полностью…

💎ቲብያን 💎 የተለያዩ ዳዕዋዎች የሚተላለፉበት ቻናል!

«ሰዎች በግልፅ ከሚያንፀባርቁት እምነትና አላማ ውጭ ከነርሱ ራሳቸው በቀር አላህ እንጂ ማንም ሊያውቀው ስለማይችለው የሆዳቸው ሚስጥር መላ መምታት ጥፋት እንጂ ብልሃት አይደለም።»

ሸይኽ ኢልያስ አሕመድ(ሓፊዘሁሏህ)

Читать полностью…

💎ቲብያን 💎 የተለያዩ ዳዕዋዎች የሚተላለፉበት ቻናል!

ጦለበተል ዒልም የሆናችሁ እነዚህ የድምፅ ቅጂዎች ብታዳምጧቸው ትጠቀማላችሁ ኢንሻአላህ።

Читать полностью…

💎ቲብያን 💎 የተለያዩ ዳዕዋዎች የሚተላለፉበት ቻናል!

"በጨለማ ወደ መስጂድ የሚጓዙትን በቂያማ ቀን ሙሉ በሆነ ብርሀን አበስራቸው።"
ረሱል(ﷺ)
(ሰሂህ አቡ ዳውድ:561)

Читать полностью…

💎ቲብያን 💎 የተለያዩ ዳዕዋዎች የሚተላለፉበት ቻናል!

"ዱንያንም አኼራንም የፈለገ እውቀትን ይማር።"
¶ ሱፍያኑ ሰውሪ
ምንጭ፦ ሚፍታህ ዳሩ ሰዓዳህ (1-257)

Читать полностью…

💎ቲብያን 💎 የተለያዩ ዳዕዋዎች የሚተላለፉበት ቻናል!

ሰራተኛን በየትኛውም መልኩ አትበድሉ። በምግብ አትቅጡ። አትምቱ። ልጆቻችሁ ሰራተኛ ላይ አይቅበጡ። በነሱ ላይ ከአላህ ጋር የሚያጣላችሁን ክፉ ቃል አትናገሩ። ራሳችሁ ላይ ቢሆን በማትፈልጉት መልኩ እንቅልፍና ረፍት አትንሱ። ከአቅም በላይ የሆነ ስራ አትስጡ። ሐቃቸውን ሳትሸራርፉ ስጡ። ሶላት እንዲሰግዱ እዘዙ። የነሱ ሐቅ በናንተ ላይ ከሚኖር፣ የናንተ ሐቅ ቢቀር ይሻላል። ደካማ ላይ ጉልበተኛ አትሁኑ። ከውጭም ይሁን ከውስጥ ልክስክስ ወንዶች ወይም ጎረምሳ ልጆች ከነሱ ጋር እንዳይባልጉ ጥንቃቄ አድርጉ። ሰበብ አድርሱ። በባህሪም ይሁን ሃላፊነትን በመወጣት በኩል ሁኔታቸው የማይጥም ከሆነ በነሱ ሰበብ ወንጀል ላይ ከመውደቅ በሰላም መሸኘት ይሻላል።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
/channel/IbnuMunewor

Читать полностью…

💎ቲብያን 💎 የተለያዩ ዳዕዋዎች የሚተላለፉበት ቻናል!

📌"አንተ ከየትኞቹ ጋር ነህ"⁉

🔸የዱናያ ሰዎች ዱኒያን ይኻድሟታል
☞የአኼራ ሰዎች ግን ዱኒያ እነሱን ትኻድማቸዋለች

🔹የዱኒያ ሰዎች ዘንድ ዱኒያ ያለችው ልባቸው ውስጥ ነው ያለው፣
☞የአኼራ ሰዎች ግን ዱኒያ ያለችው እጃቸው ወይም ኪሳቸው ላይ ነው

🔸የዱኒያ ሰዎች ሲያገኟት ደስ ይላቸዋል ስያጧት ደግሞ ይከፋቸዋል፣
☞የአኼራ ሰዎች ደግሞ እሷን ከማጣታቸው ይልቅ ማግኘታቸው ያሳስባቸዋል

🔹የዱኒያ ሰዎች ነገ ሲለዯት በጣም ያዝናሉ፣
☞የአኼራ ሰዎች ግን እሷን የተሰናበቱ እለት ደስታቸው ልዩ ነው!

🔸ዐሊይ ኢብኑ አቢጣሊብ رضي الله عنه  እንዲህ ይላሉ፥ ( ዱኒያም ልጆች አሏት አኼራም ልጆች አሏት ከአኼራ ልጆች ሁኑ ከዱኒያ ልጆች አትሁኑ!)
🔹🔑አላህም በቁርኣኑ እንዲህ ይለናል:–

🔹 يَا قَوْمِ إِنَّمَا هَٰذِهِ الْحَيَاةُ الدُّنْيَا  مَتَاعٌ وَإِنَّ الْآخِرَةَ هِيَ دَارُ الْقَرَارِ
مَنْ عَمِلَ سَيِّئَةً فَلَا يُجْزَىٰ إِلَّا مِثْلَهَا وَمَنْ عَمِلَ صَالِحًا مِّن ذَكَرٍ أَوْ أُنثَىٰ وَهُوَ مُؤْمِنٌ فَأُولَٰئِكَ يَدْخُلُونَ الْجَنَّةَ يُرْزَقُونَ فِيهَا بِغَيْرِ حِسَابٍ
🔹{ወገኖቼ ሆይ፥ ይህች የአዱኒያ ህይወት እኮ ጊዜያዊ መጠቃቀሚያ ናት መርጊያና ማረፊያ ማለት አኼራ ናት
መጥፎን ስራ የሰራ ሰው የስራውን ስራ ዋጋ እንጂ አያገኝም በጌታው ከማመንጋር መልካምን ስራ የሰራ ሰው ወንድም ይሁን ሴት ጀነት ይገባል
ያለቁጥር ስፍርም ሲሳይን ይሰጣል ይመነዳል}

         📜(ሱረቱ አል ጛፊር 39–40)

💎 አላህ ሆይ፥ ዱኒያን ትልቁ ጭንቀታችንና የእውቀታችን መጨረሻ አታድርጋት❗

✍ ኡስታዝ አሕመድ  ሼይኽ ኣደም (ሀፊዘሁላህ)

🌐🔗/channel/ahmedadem

🌐🔗/channel/ahmedadem

Читать полностью…

💎ቲብያን 💎 የተለያዩ ዳዕዋዎች የሚተላለፉበት ቻናል!

➪የአላህ መልክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
◾️"የጁምዓ ለሊት እና ቀኑ ላይ በኔ ላይ ሰለዋት ማውረድን አብዙ፣በኔ ላይ አንድ ሰላት ያወረደ በርሱ ላይ አስር ሰላትን ያወርድለታል።"

[ሲልሲለቱ አሰሒሃ ሊል አልባኒይ ሐዲስ ቁጥር 1407]

💎/channel/Tibyaan54

Читать полностью…

💎ቲብያን 💎 የተለያዩ ዳዕዋዎች የሚተላለፉበት ቻናል!

شرح أصول الإيمان

📚የኡሱል አል-ኢማን
(የእምነት መሰረቶች) ማብራሪያ


⏳ዝግጅት- ሸይኹል-ኢስላም
ሙሐመድ ኢብኑ ዐብዲል ወሃብ

🔊 ማብራሪያ:-በኡስታዝ አሕመድ
     ሸይኽ ኣደም

  📚  የኪታቡን ፒ.ዲ.ኤፍ ለማግኜት
           ⬇  ⬇  ⬇  ⬇

🔎 https://is.gd/mDP2w4
🔹🔸🔹🔸🔹🔸

▪️ሙሉውን ትምህርት ከታች ባለው
ሊንክ የኦዲዮ ፋይል ያገኙታል
       የዳውንሎድ ሊንኩን  ይጫኑ
🔽 🔽 🔽 🔽 🔽 🔽

🔎  https://urlz.fr/rAot
       🔸🔹🔸🔹🔸🔹

ክ/1
🔅የሸይኹ አጭር የሕይወት ታሪክና
        የ2 ሐዲሶች ማብራሪያ

      
/channel/zad_qirat/1567

ክ/2
🔅የአላህ ሁሉን አዋቂነት
/channel/zad_qirat/1569


ክ/3
🔅የአላህ አዛኝነት፣ በባሮቹ ተውበት
     መደሰትና ከዐርሹ በላይ መሆን


/channel/zad_qirat/1571

ክ/4
🔅የመተዛዘን አስፈላጊነት፣
የአላህ እዝነት ዓይነቶችና
መመስገንን ስለ መውደዱ


/channel/zad_qirat/1573

ክ/5
🔅የአላህ ቅጣት ብርቱነትና የምህረቱ ሰፊነት፤ ሙስሊምን "አላህ አይምረውም!" እንደማይባል፣የጀነትና የጀሀነም ቅርብነት

/channel/zad_qirat/1575

ክ/6
🔅 ተውሒድና ኣኺራን የመውደድ ምስጢር

/channel/zad_qirat/1577

ክ/7
🔅አላህ በየሌሊቱ ወደ ቅርቧ ሰማይ አንደሚወርድና ኣኺራህ ላይም
    እንደሚታይ ማመን


/channel/zad_qirat/1579

ክ/8
🔅በመላዕክት (መላኢካህ) ማመን

/channel/zad_qirat/1583

ክ/9
🔅የአላህ ልቅና እና ኃያልነት

/channel/zad_qirat/1585

ክ/10
🔅የአላህ ልቅና እና ኃያልነት  ቁ/ 2

-አላህ አርሽን ከመፍጠሩ በፊት የት ነበረ?
-የሰው ልጅ አላህን ሰደበ፣ አስቸገረ፣ አስዋሸ የሚባለው ምን ሲልና ሲያደርግ ነው?

/channel/zad_qirat/1587

ክ/11
🔅በቀደር ማመንን የሚመለከቱ
          ወሳኝ ነጥቦች

/channel/zad_qirat/1589

ክ/12

🔅በቀደር ማመንን የሚመለከቱ
      ወሳኝ ነጥቦች
     ቁ/2
-የጀነትና የጀሀነሙ ቀድሞ ከተለየ፣ ሁሉ ነገር አላህ ዘንድ ቀድሞ ከተወሰነ ስራ መስራት ለምን አስፈለገ?

/channel/zad_qirat/1591

ክ/13

🔅በቀደር ማመንን የሚመለከቱ
          ወሳኝ ነጥቦች
ቁ/3

/channel/zad_qirat/1593

ክ/14
🔅በቀደር ማመንን የሚመለከቱ
          ወሳኝ ነጥቦች ቁ/4

/channel/zad_qirat/1595

ክ/15
🔅በቀደር ማመንን የሚመለከቱ
          ወሳኝ ነጥቦች ቁ/5


-ሰሓቢዩ ጣዕረ-ሞት ላይ ሆነው ለልጃቸው በቀደር ዙሪያ የሰጡት ምክር፣
-ሩቃ/ህክምና እና ቀደር፣
-አላህ ዘንድ ተወዳጁ ጥንካሬ የቱ ነው?


/channel/zad_qirat/1597

ክ/16
🔅በመላእክት ማመንን
       የሚመለከቱ ወሳኝ ነጥቦች


/channel/zad_qirat/1599

ክ/17

🔅በመላእክት ማመንን
     የሚመለከቱ ወሳኝ ነጥቦች ቁ/2


/channel/zad_qirat/1601

ክ/18
🔅በመላእክት ማመንን
      የሚመለከቱ ወሳኝ ነጥቦች ቁ/3


/channel/zad_qirat/1605

ክ/19
🔅በቁርእንና በሌሎችም መጽሐፍት ማመንን የሚመለከቱ ወሳኝ ነጥቦች

/channel/zad_qirat/1607

ክ/20
🔅በቁርኣን ማመንና እርሱንም
    መከተል ማለት ምን ማለት ነው?


/channel/zad_qirat/1609

ክ/21

🔅በቁርኣን ማመንና እርሱንም መከተል ማለት ምን ማለት ነው?  ቁ/2

-ቁርኣን ውስጥ አሻሚ አንቀጾች አሉን?
-የሌላ እምነት ተከታዮችን ሐይማኖታዊ
  መጽሐፍት ማንበብ...
-ቁርኣን የአላህ መንገድና የጽናት ምንጭ


/channel/zad_qirat/1611

ክ/22
🔅በነቢዩ ﷺ ማመንን፣ እሳቸውን  መታዘዝንና መውደድን የሚመለከቱ
      ወሳኝ ነጥቦች

/channel/zad_qirat/1613

ክ/23
🔅በነቢዩ ﷺ ማመንን፣ እሳቸውን  
   መታዘዝንና መውደድን የሚመለከቱ
      ወሳኝ ነጥቦች ቁ/2

/channel/zad_qirat/1613

ክ/24

🔅በነቢዩ ﷺ ማመንን፣ እሳቸውን መታዘዝንና መውደድን የሚመለከቱ
     ወሳኝ ነጥቦች  ቁ/3


- ነቢዩን ﷺየሚከተል ሰው ባይታወርነት፣
- ሰዎችን ወደመልካም ነገር የመጣራት ትሩፋት፣
- ወደመጥፎ ነገር የመጣራት መዘዝ፣
- የአስተማሪ ኀላፊነትና ያለ ዕውቀት ማስተማር ጉዳቶች

/channel/zad_qirat/1615

ክ/25

🔅 እምነትን ዕውቀት ላይ የተመሰረተ
         የማድረግ አንገብጋቢነት

  - ትክክለኛው የዕውቀት
       መፈለጊያ መንገድ

/channel/zad_qirat/1617

ክ/26

🔅 እምነትን ዕውቀት ላይ የተመሰረተ
   የማድረግ አንገብጋቢነት ቁ/2

  - ትክክለኛው የመማርና
   የማስተማር መንገድ
-የዕውቀት ማነስና ያለብቃት
   ማስተማር መዘዞች

-የሌላ ሐይማኖት መጽሐፍትን ማንበብ

/channel/zad_qirat/1619

ክ/27
🔅 እምነትን ዕውቀት ላይ የተመሰረተ
      የማድረግ አንገብጋቢነት
ቁ/3

- የዒልምና ዑለማዎች ደረጃ
- ያለበቂ ዕውቀት ቁርኣን የመተርጎምና
  ፈትዋ የመስጠት ክልክልነትና ጉዳት
- ዓሊም ማነው? ዓሊምነቱንስ ማነው የሚመሰክረው?
- ዕውቀትን እንዴትና ከማን እንማር?


/channel/zad_qirat/1621

ክ/28
🔅 እምነትን ዕውቀት ላይ የተመሰረተ
     የማድረግ አንገብጋቢነት ቁ
/4
-ዒልም የሚጠፋው መቼና እንዴት ነው?
-ጠቃሚ ዕውቀት ማለት ምን ማለት ነው?
-ያለ ዕውቀት መምራትና መናገር ማለት
      ምን ማለት ነው?


/channel/zad_qirat/1623

ክ/29

🔅 እምነትን ዕውቀት ላይ የተመሰረተ
     የማድረግ አንገብጋቢነት ቁ/5

-ዒልም ስንማር ለማንና ለምን ብለን
      ነው መማር ያለብን?

-ዒልምን ለማግኘት ከክርክርና ተከራካሪዎች መራቅ ይገባል።
-አራቱ ለጀሀነም እሳት የሚዳርጉ ብልሹ
     ዕውቀት መፈለጊያ ዓላማዎች!
-ለመታወቅና ለመወደድ ብለህ አትማር


/channel/zad_qirat/1625

ክ/30(የመጨረሻው ክፍል)

🔅ስርዓተ- ንግግር
- የነቢዩ ﷺ  ንግግርና አነጋገር
           ምን ይመስል ነበር?
- ንግግር ላይ አብዝቶ መራቀቅና ጉዳቱ
-  ዳዒና አስተማሪዎች ምን ዓይነት ቃላት/ቋንቋ መጠቀም ይገባቸዋል?


/channel/zad_qirat/1627

🌐/channel/ahmedadem

📚"ዒልም ማለት አላህን መፍራት ነው!"
አል-ኢማሙ ማሊክ

Читать полностью…

💎ቲብያን 💎 የተለያዩ ዳዕዋዎች የሚተላለፉበት ቻናል!

📢 ማስታወቂያ

💥ዛዱል-መዓድ የቁርኣን ሒፍዝና የተርቢያ ማዕከል ለመጪው ዓመት (1446 ዓ.ሂ/2017 ዓ.ል) የቀን ሙሉ ተመላላሽ የቁርኣን ሒፍዝና ተያያዥ ትምህርቶች የሚሰጥበት ፕሮግራም እንዲሁም የጠዋት (ግማሽ ቀን) የእናቶችንና የከሰዓት (ከትምህርት መልስ) ተማሪዎችን ቂርዓት ፕሮግራም ምዝገባና ተያያዥ መረጃዎችን እነሆ ይላል።

☄ የቀን ሙሉ ተመላላሽ የቁርኣን ሒፍዝና ተያያዥ ትምህርቶች ፕሮግራም

✨መስፈርቶች✨

🔅ለሴቶች፥

1⃣ ተመዝጋቢዎች እድሜያቸው ከ13 በላይ እና ከ21 በታች መሆን፤
2⃣ ቁርኣን በማየት (በነዞር) በተጅዊድ ያኸተመች መሆን፤
3⃣ በሁለት ዓመት ውስጥ ቁርኣንን ሐፍዛ ለመጨረስና ተያያዥ ትምህርቶችን በስርዓቱ ለመከታተል ዝግጁና ብቁ መሆን፤
4⃣ የመግቢያ ፈተና (ቃለ መጠየቅ)ን በስኬት ማለፍ፤
5⃣ የመርከዙን ጠቅላላ ህገ-ደንብ ሙሉ በሙሉ ለመቀበልና ለማክበር፣ ህገ ደንቡንም የሚተላለፉ ላይ በየደረጃው የሚወሰደውን የቅጣት እርምጃ ያለመከራከርና ያለማንገራገር
ለመቀበል ዝግጁ የሆኑ ወላጆችና ተማሪዎች መሆን አለባቸው።

🔅ለወንዶች፥

1⃣ ተመዝጋቢዎች እድሜያቸው ከ13 በላይና ከ23 በታች መሆን አለበት፤
2⃣ ቁርኣን በማየት (በነዞር) በተጅዊድ ያኸተመ መሆን፤
3⃣ በሁለት ዓመት ውስጥ ቁርኣንን ሐፍዞ ለመጨረስና ተያያዥ ትምህርቶችን በስርዓቱ ለመከታተል ዝግጁና ብቁ መሆን፤
4⃣ የመግቢያ ፈተና (ቃለ መጠየቅ)ን በስኬት ማለፍ፤

5⃣ የመርከዙን ጠቅላላ ህገ-ደንብ ሙሉ በሙሉ ለመቀበልና ለማክበር፣ ህገ ደንቡንም የሚተላለፉ ላይ በየደረጃው የሚወሰደውን የቅጣት እርምጃ ያለመከራከርና ያለማንገራገር ለመቀበል ዝግጁ የሆኑ ወላጆችና ተማሪዎች መሆን አለባቸው።

🗓 የምዝገባ ቀንና ሰዓት:- እሁድ ሙሐረም 22 ወይም ሐምሌ 21 ጠዋት ከ4:30 እስከ 11:30 ድረስ ብቻ።

📌የምዝገባ አድራሻ ፉሪ በድር መስጂድ አካባቢ ዛዱል-መዓድ የሴቶች መርከዝ ቅጥር ግቢ ውስጥ።

⚡️ለምዝገባ ሲመጡ ተመዝጋቢ ተማሪዎች ከሁለቱም ወላጆች/አሳዳጊዎች ጋር መገኘት አለባቸው።

☄ የጠዋት (ግማሽ ቀን) የእናቶች ቂርዓትና የከሰዓት (ከትምህርት መልስ) ተማሪዎች ፕሮግራም

✨መስፈርቶች✨

✅ ፕሮግራሙ ላይ በቋሚነት ለመሳተፍ ዝግጁ መሆን

✅ ኢስላማዊ የሆነን አለባበስ መጠበቅ

✅ በመርከዙ የሚወጡ ህገ-ደንቦችን ለመቀበል ዝግጁ መሆን
 
⚡️የከሰዓቱ (ከትምህርት መልስ) ያለው ፕሮግራም ለሴቶችም ለወንዶችም የተዘጋጀ ነው።

🗓 የምዝገባ ቀንና ሰዓት:- እሁድ ሙሐረም 29 ወይም ሐምሌ 28 ጠዋት ከ3:30 እስከ 6:30 ፤ ከሰዓት ከ8:00 እስከ 11:00 ።

📌የምዝገባ አድራሻ ፉሪ በድር መስጂድ አካባቢ ዛዱል-መዓድ የሴቶች መርከዝ ቅጥር ግቢ ውስጥ።

⚠️ማሳሰብያ⚠️

📛 ለየት ያለና ተመክሮ የማይታረም ሌሎችን ሊበክል የሚችል መጥፎ ፀባይ፣ ቋሚ ህመምና ከሩቃ ጋር ተያያዥ ችግር  ያለበትን ተማሪ እንደማንቀበል ከይቅርታ ጋር ከወዲሁ እናሳውቃለን፤ ከተመዘገበ በኋላም ችግሩ ያለበት ተማሪ ይመለሳል። ስለዚህም ወላጆች ሲያስመዘግቡ ሐቁን መናገር ይገባቸዋል!።

⛔️ ሁሉም ፕሮግራሞች ላይ ያለን ቦታ ውስን ከመሆኑ አንፃር ቅድሚያ የሚሰጠው ቀድሞ ለመጣ ነው።

⛔️ ከላይ ከተገለጹ የምዝገባ ቀናትና ሰዓታት በኋላም ይሁን በፊት ምዝገባ የማይኖር መሆኑን ከወዲሁ በጥብቅ እናሳስባለን።

#ትምህርት የሚጀመርበትን ቀን ከምዝገባ መጠናቀቅ በኋላ ወደፊት ለወላጅ እናሳውቃለን።

☎️ለበለጠ መረጃ

ለሴቶች፡
+251973574851
ወይም
+251947346787

ለወንዶች፡ ‎
0911414886
ወይም
‎0972344383
ወይም
0947483030

Читать полностью…

💎ቲብያን 💎 የተለያዩ ዳዕዋዎች የሚተላለፉበት ቻናል!

اللَّهُ أكبَرُ
اللَّهُ أكبَرُ
لَا إِلَهَ إِلَّا اللَّهُ

اللَّهُ أَكْبَرُ
اللَّهُ أكبَرُ
وَلِلَّهِ الحَمد

اللَّهُ أكبَرُ كَبيرًا
وَالْحَمْدُ لِلَّهِ كَثِيرًا
وسُبحَانَ اللَّهِ بُكرَةً وأَصيلًا ..

Читать полностью…

💎ቲብያን 💎 የተለያዩ ዳዕዋዎች የሚተላለፉበት ቻናል!

🤲 ኢላሂ !
በውዴታቸው ቅን  የሆኑ የዲን ወንድሞችን ለግሰን!

ዑመር ኢብኑል ኸጣብ - አላህ ይዘንላቸውና - እንዲህ ብለዋል፡-

"ከእስልምና ቀጥሎ ከጥሩ ወንድም በላይ ምንም አይነት በላጭ ነገር አንድ ሰው አልተሰጠም።"

ቁወቱ አል–ቁሉብ - (178/2)

ኢማም አሽ– ሻፊኢይ - አላህ ይዘንላቸውና፡-

“የዲን ወንድሞች ጋር መጓዳኘት የሚያክል ደስታ የለም፣ ወንድሞቻችን መለያየት የሚያክል ሐዘን የለም።

ሹዐቡል ኢማን - (504/6))

Читать полностью…

💎ቲብያን 💎 የተለያዩ ዳዕዋዎች የሚተላለፉበት ቻናል!





الله أكبر
الله أكبر
الله أكبر
لا إله إلا الله

والله أكبر
الله أكبر 
ولله الحمد

⠀⠀

Читать полностью…

💎ቲብያን 💎 የተለያዩ ዳዕዋዎች የሚተላለፉበት ቻናል!

السلام عليكم ورحمة الله وبركاته
عيدكم مبارك
تقبلﷲ منا ومنكم صالح الأعمال
አሏህ መልካም ስራዎቻችንን ይቀበለን ‼

Читать полностью…
Subscribe to a channel