#Update
" የቀን ህልም ነው ... ምንም የማይረባ ፤ እኛን አያሳስበንም " - ሶማሌላንድ
" የሶማሊያ መንግሥት አንዳች ስልጣን የለውም " - ፑንትላንድ
#ፑንትላንድ እና #ሶማሌላንድ የሶማሊያ ፌዴራል መንግሥትን ማስጠንቀቂያ ውድቅ አደረጉ።
የሶማሊያ መንግሥት ፤ #ኢትዮጵያ ከሶማሌላድ ጋር ያደረገችውን የመግባቢያ ስምምነት ምክንያት በማድረግ ሞቃዲሹ ያሉት የኢትዮጵያ አምባሳደር በ72 ሰዓት ከሀገሪቱ ለቀው እንዲወጡ አዟል።
ከዚህ ባለፈ ግን በሶማሌላድ ፣ #ሀርጌሳ እና በፑንትላንድ፣ #ጋሮዌ የሚገኙት የኢትዮጵያ ቆንስላ ፅ/ቤቶች በ7 ቀን እንዲዘጉ አስጠንቅቋል። ካልሆነ ወደሌላ እርምጃ ገባለሁ ብሏል።
ለዚህ ማስጠንቀቂያ ፑንትላንድ እና ሶማሌላንድ ምላሽ ሰጥተዋል። የሶማሊያ ፌዴራል መንግስትን ማስጠንቀቂያም ውድቅ አድርገዋል።
ዛሬ ምሽት ለቪኦኤ ሬድዮ ጣቢያ ሶማሊኛ ክፍል አጭር ቃላቸውን የሰጡት የሶማሌላንድ የውጭ ጉዳይ ምክትል ሚንስትር አምባሳደር ሮዳ ኤሊ ፥ " የቀን ህልም ነው፤ ...ምንም የማይረባ ፤ እኛን አያሳስበንም " ሲሉ ማስጠንቀቂያውን አጣጥለዋል።
የሶማሊያ መንግሥት ስልጣኑ በቪላ ሱማሊያ እና በሙቃዲሾ ዘሌን ቤዝ የተወሰነ መሆኑን በመግለጽ " በውስጥ ጉዳዩ ላይ ቢያተኩር ነው የሚሻለው ... ከአቅሙ በላይ በሆነ ጉዳይ ጊዜ ማባከኑን ማቆም አለበት " ብለዋል።
የፑንትላንድ የማስታወቂያ ሚኒስትር ማህሙድ አይዲድ ድሪር በበኩላቸው " የሶማሊያ ፌደራል መንግስት በጋሮዌ የሚገኘውን የኢትዮጵያ ቆንስላ ጽህፈት ቤት የመዝጋት አንዳችም ስልጣን የለውም " ብለዋል።
@tikvahethiopia
" በቦምብ ጥቃቱ 31 ተማሪዎች ተጎድተዋል " - ፖሊስ
ዛሬ በፍኖተ ሰላም ከተማ አስተዳደር ዳሞት መሰናዶ ቁጥር 1 ት/ቤት ላይ በተፈፀመ የቦምብ ጥቃት በ31 ተማሪዎች ላይ ጉዳት መድረሱን የፍኖተ ሰላም ከተማ ፖሊስ ጽ/ቤት ገለጸ።
በት/ቤቱ በተፈፀመው የቦምብ ጥቃት 6 ተማሪዎች ላይ ከባድ ጉዳት ደርሷል ብሏል።
የቦምብ ጥቃቱ (ቦምቡ የተጣለው) ጥዋት 2፡30 ሰዓት ተማሪዎች በፈተና ላይ እንዳሉ መፈፀሙን የገለጸው ፖሊስ ፤ ከባድ ጉዳት የደረሰባቸው 6ቱ ተማሪዎች ለከፍተኛ ህክምና ሪፈር ተፅፎላቸዋል ህክምና ላይ ናቸው ብሏል።
15 ተማሪዎች ደግሞ በፍኖተ ሰላም ጠቅላላ ሆስፒታል ህክምና እያገኙ ሲሆን 10 ተማሪዎች ላይ ቀላል ጉዳት እንደደረሰባቸው አመልክቷል።
አደጋውን ተከትሎ አንድ ተጠርጣሪ #ተማሪ መያዙን ፤ እጁና እግሩ ላይም መቁሰሉን ያሳወቀው ፖሊስ ሌሎች በድርጊቱ የተሳተፉ አካላትን በቁጥጥር ስር ለማዋል እየሰራ እንደሆነ ገልጿል።
@tikvahethiopia
#ኢትዮጵያ
መንግስት ጀማሪ ስራ ፈጣሪዎች/startups እንዲያብቡ በርካታ የፖሊሲ ለውጦችን ለማድረግ መወሰኑ ተሰማ።
ከነዚህም መካከል ፦
- ከስራ ፈቃድ፣
- ከግብር፣
- ከቢሮ ኪራይ፣
- ከፋይናንስ አቅርቦት፣
- ከጉምሩክ አሰራር ጋር በተያያዘ ወሳኝ ለውጥ የሚደረግባቸው ይሆናሉ ተብሏል።
ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ በተገኙበት ዛሬ ይፋ የተደረጉ ለውጦች በተለይ ስራ ፈጣሪዎች ከውጭ ለሚኖራቸው ግዥ የቀጥታ ክፍያ መፈፀም እንዲችሉ እንዲሁም ያገኙትን የውጭ ምንዛሪ ሙሉ ለሙሉ መጠቀም እንዲችሉ የሚፈቅድ መሆኑን " ካፒታል ጋዜጣ " አስነብቧል።
@tikvahethiopia
MAMA'S kids ማማስ ኪድስ
▶️ ኦርጅናል እና ጥራታቸውን የጠበቁ የልጆች እቃዎች ለማግኘት ቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ 👉/channel/mamaskids
አድራሻችን ፦ መገናኛ ዘፍመሽ ግራንድ ሞል 2 ተኛ ፎቅ የሱቅ ቁጥር 225
👉 ውድ ደምበኞቻችን ሱቃችን 225 ቁጥር መሆኑን እና የራሳችን ሎጎ መኖሩን ያረጋግጡ እናመሰግናለን።
ለበለጠ መረጃ ፦ በ0965809005 / በ0938309171 ይደውሉልን።
#Somalia
° " ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ተደርጓል " - የሶማሊያ ባለልስጣናት
° " ስለዚህ ጉዳይ መረጃው የለኝም " - አቶ ነብዩ ተድላ
ሶማሊያ ፥ በሶማሊያ #የኢትዮጵያን_አምባሳደር የሆኑትን ሙክታር ሞሃመድ ዋሬን ወደ ሀገራቸው #እንዲመለሱ ማድረጓን ሁለት ከፍተኛ የሶማሊያ ባለስልጣናትን ዋቢ በማድረግ ሮይተርስ ዘግቧል።
ሶማሊያ የኢትዮጵያን አምባሳደር ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ያደረገችበት ምክንያት ከሶማሊላንድ ጋር የገባቸው የወደብ መግባቢያ ስምምነት እንደሆነ ተነግሯል።
ከዚህ ባለፈ ሶማሊያ በፑንትላንድ እና ሶማሊላንድ ያሉ የኢትዮጵያን ቆንስላ ጽህፈት ቤቶችን ዘግቻለሁ ብላለች።
የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ቃል አቀባይ አምባሳደር ነብዩ ተድላ በጉዳዩ ዙሪያ ምንም አይነት መረጃ እንደሌላቸው እንደነገሩት ሮይተርስ አስነብቧል።
የፑንትላንድ እና ሶማሊላንድ ነገር ?
ፑንትላንድ ከሕገ-መንግስት ማሻሻያ ጋር በተያያዘ ለሶማሊያ ፌደራል መንግሥት ዕውቅና መስጠት ማቆሟን ከቀናት በፊት ይፋ ማድረጓ ይታወሳል።
ከአሁን በኃላም ማንኛውም ፍላጎቷን ለማስጠበቅ ከማዕከላዊ የሶማሊያ መንግሥት እውቅና ውጪ በራሷ የውጭ ግንኙነትም እንደምታደርግ ገልጻለች።
ሶማሌላንድም ምንም እንኳን እስካሁን ሶማሊያ ' የራሴ ግዛት ነሽ ' ብትላትም ራሷን እንደ ነጻ ሀገር መቁጠር ከጀመረች አመታት አልፈዋል። የውጭ ግኝኑነቶችንም ታደርጋለች።
የሰሞኑን የፑንትላንድ ነገር ለሶማሊያ ፌዴራል መንግሥት " በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ " ሆኖበታል።
ከፊል ራስ ገዟ ፑንትላንድ ሰሞኑን ፥ " ከሶማሊያ ፌዴራል መንግሥት ጋር ተቆራጠናል ፤ እውቅናም አልሰጥም " ካለች በኃላ ከፍተኛ ባለስልጣናቷ ኢትዮጵያ / አዲስ አበባ ለውይይት መግባታቸው መነጋገሪያ ሆኗል።
እዚህ አዲስ አበባ የመጣው በገንዘብ ሚኒስትሯ ሞሃመድ ፋራህ ሞሀመድ የተመራ ልዑክ ነው።
ልዑኩ ከኢፌዴሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አረጋ ጋር መክሯል።
በዚህም ኢትዮጵያ ከፑንትላንድ ጋር ያላትን ዘርፍ ብዙ ትብብሮች ለማጠናከር ቁርጠኛ መሆኗ ተገልጿል።
የፑንትላንድ ልዑክም ፥ ኢትዮጵያ በፑንትላንድ በጸጥታና በትምህርት ዘርፍ ድጋፍ እያደረገች መሆኑን ገልጾ የፑንትላንድ መንግሥት ከኢትዮጵያ ጋር ያለውን ግንኙነት የማሳደግ ፍላጎት እንዳለው አረጋግጧል።
በዚህ ወቅት የፑንትላንድ ባለስልጣናት ኢትዮጵያ መምጣታቸው ግጥምጥሞች ወይስ ከወቅታዊ ሁኔታው ጋር የተያያዘ ነው ?
" ጉብኝቱ የቆየ ቀጠሮ ነው " - አቶ ነብዩ ተድላ
ዛሬ በወቅታዊ የዲፕሎማሲ ጉዳዮች ላይ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ አቶ ነብዩ ተድላ መግለጫ ሰጥተው ነበር።
በዚህም ወቅት ፑንትላንድ በገንዘብ ሚንስትሯ መሀመድ ፋራህ የተመራ ልዑክ በኢትዮጵያ አ/አ ጉብኝት ማድረጉን ገልጸዋል።
ይህ ጉብኝት ከሰሞነኛው የፑንትላንድ ወቅታዊ ጉዳይ ጋር #የማይገናኝ እንደሆነ እና የጉብኝት ፕሮግራሙም የቆየ ቀጠሮ መሆኑን አስረድተዋል።
@tikvahethiopia
#ኢንተርን
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ኢንተር ሀኪሞች ከስራ ሰዓትና ክፍያ ጋር በተያያዘ ቅሬታ እንዳላቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።
ኢንተርን ሀኪሞቹ ምን አሉ ?
“ ከጥቂት ዓመታት በፊት የሆስፒታሉ የኢንተርን ሀኪሞች የሥራ ሰዓት ወደ 24 ሰዓታት ዝቅ እንዲል ተደርጎ ነበር።
ነገር ግን የኮሌጁ ግለሰብ / #ዳይሬክተር ሲቀየር በራሱ ውሳኔ የራሱን መላምት በመፍጠር መልሶ ወደ 36 ሰዓታት ከፍ አድርጎታል።
ይህን ውሳኔ ተከትሎ የሥራ ሰዓት ከዚህ በፊት ሴኔቱ በወሰነው መሠረት ይሁንልን ብለን ጠየቅን። ይህንንም በመጠየቃችን የተበሳጨው የዲፓርትመንት አስተባባሪ ፦
• ከቀዶ ጥገና፣
• ከህፃናት፣
• ከማህፀንና የፅንስ ዲፓርትመንት ጋር መከረ። እነዚህ ዲፓርትመንቶች አስገድደውን ሥራ ጀመርን።
የሥራ ሰዓታችን እንዲስተካከል በተደጋጋሚ ጠየቅን።
በዲፓርትመንት ደረጃ እየተሰበሰቡ ' ከዚህ በኋላ ይህን ጥያቄ የሚያየሳ ሀኪም እስከ ዲሲሚሳል ድረስ እንቀጣቸዋለን ' አሉ። ከዚህ በተጨማሪ የቀን ሥራ ሰዓታትን በአንድ ሰዓት ከፍ እንዲል ከነበረው ሕግ ውጪ ሆነብን።
ያንን ሁሉ ችለን ደመወዝ ይከፈለናል ብለን ብንጠብቅም ሳይከፈለን መጋቢት 14/2016 ዓ/ም 10ኛ ሳምንታት ጨርሰናል። ” የሚል ቅሬታ አቅርበዋል።
ለተነሳው ቅሬታ ምላሽ እንዲሰጡን በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የህክምና ሳይንስ ኮሌጅና አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ቺፍ ኤክሴኩይቲቭ ዳይሬክተር ዶ/ር አይንሸት አዳነን ጠይቀናል።
ምን አሉ ?
ዶ/ር አይንሸት ፥ “ የሰዓት ጭማሪ ለሚለው እኔ ባለኝ መረጃ መሠረት የተጨመረ ነገር የለም። ከድሮው የተቀየረ አሰራር የለም። እኔ ባለኝ መረጃ መሠረት እነርሱን #ያስፈራራቸው_ሰው_የለም ” ብለዋል።
Q. ቲክቫህ ኢትዮጵያ የኢንተርን ሀኪሞች የሥራ ሰዓት ስንት ተብሎ ነው የተወሰነው ? ሲል ጥያቄ አቅርቧል።
ዶ/ር አይንሸት አዳነ ፦
“ በክሬዲት ደረጃ ይህን ያህል የትርፍ ፤ ይህን ያህል የመደበኛ ተብሎ የተቀመጠ ነገር የለም።
ለበርካታ አመታት ሲሰራበት ከነበረው መንገድ የተለየ እነርሱ ጋ የተጨመረ ነገር የለም። ”
Q. ዩኒቨርሲቲው 36 ሰዓታት የነበረውን የሥራ ሰዓት ወደ 24 ሰዓታት ዝቅ እንዳደረገ መረጃዎች ያሳያሉ ፣ ሀኪሞቹም ወደ 24 ሰዓት ዝቅ ተደርጎ የነበረ ወደ 36 ሰዓት ከፍ እንዳለባቸው ገልጸዋል ፣ እርስዎ ደግሞ የተወሰነ ሰዓት እንደሌለ እየገለጹ ነው ለዚህስ ያለዎት ማብራሪያ ምንድን ነው ? ስንል ጠይቀናል።
ዶ/ር አይንሸት አዳነ ፦
“ የሆነ ጊዜ ጫናው ስለበዛ በኢንተርን ሀኪሞች ጥያቄ ተነሳና ዲፓርትመንቶች ራሳቸው ከኢንተርን ሀኪሞች ጋር ውይይት አድርገው (የተወሰኑ ዲፓርትመንቶች እንዲያውም ሙሉ አይደለም) አምነውበት ወደ ተግባር ተገባ። አሳማኝ ስለሆነ የሥራ ጫናው።
ይሁን እንጂ ለተወሰነ ወራት ተግባራዊ ከተደረገ በኋላ አድረው በሚወጡትና ተተኪ ሆነው በሚገቡት ኢንተርን ሀኪሞች መካከል የርክክብ ክፍተት መፈጠሩ የጤና አገልግሎት ላይ ተፅዕኖ ስላመጣ፣ የኢንተርን ሀኪሞች ተመርቀው ሲወጡ የተሟላ እውቀት እንዳይቀስሙ ያደርጋል በሚል ወደ ነበረበት ይመለስ ተብሎ ተመልሷል። ”
Q. ‘ደመወዝ አልተከፈለንም’ ሚለው የሀኪሞቹን ቅሬታስ?
ዶ/ር አይንሸት አዳነ ፦
“ ሀኪሞቹ አጠያየቃቸው ልክ አልነበረም።
ኦረንቴሽን እንዲሰጣቸው በደብዳቤ ጭምር ቢጠሩም መገኘት አልቻሉ።
‘ይህ ካልተደረገልን (ቅሬታው ምላሽ ካላገኘ) ሥራ አንገባም’ በማለታቸውና ሳምንቱን ሙሉ ከሥራና ት/ት ገበታ ባለመገኘታቸው የሕክምና ትምህርት ቤቱ ባሳለፈው ውሳኔ፣ የ3 ወራት ደመወዝ ነው የተቀጡት። ያለ ደመወዝ እንዲሰሩ ነው የህክምና ት/ቤቱ የወሰነው። ”
#ቲክቫህኢትዮጵያ
@tikvahethiopia
#forfreemarket
እነዚህን👆የቤት ዕቃዎች በሱቃችን በቅናሽ ዋጋ እየተሸጡ ነው። የነዚህንና ሌሎች በርካታ ዕቃዎቻችንን ዋጋ ይሄንን ተጭነው ማየት ይችላሉ። 👉 /channel/forfreemarket
አድራሻ፦ ፒያሳ ጣይቱ ሆቴል ጊቢ ውስጥ ቢሮ ቁ04 ፣ መገናኛ መተባበር ሕንፃ 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁ316 ፣ ሳር ቤት ካናዳ ኤምባሲ ፊትለፊት ሸዋ ሱፐርማርኬት ያለበት ህንፃ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁ11
ለማዘዝ እነዚን ቁጥሮች ይጠቀሙ ፦ 0911100302 / 0911887579
በቴሌግራም ለማዘዝ ➡️ @Akdat
#ጥቆማ
" የ2024 ESP ማመልከቻ ማስገባት ይቻላል " - የአሜሪካ ኤምባሲ በኢትዮጵያ
በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ የEducation USA Scholars Program (#ESP) 2024 ማመልከቻ ክፍት መሆኑን አሳውቋል።
ESP በአካዳሚክ ጠንካራ የሆኑ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ወደ አሜሪካ ኮሌጆች እና ዩኒቨርሲቲዎች #እንዲያመለክቱ የሚረዳ የአራት ሳምንታት የሥልጠና መርሃ ግብር ነው።
ዓላማውም ደግሞ የነገዋን ኢትዮጵያ ለመገንባት የሰለጠኑ እና ከፍተኛ የትምህርት ዝግጅት ያላቸውን መሪዎችን ማፍራት እንደሆነ ኤምባሲው አመልክቷል።
ከአመልካቾች 20 ከፍተኛ የአካዳሚክ ብቃት ያላቸውን ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች በኤምባሲው ይለያሉ። ተማሪዎቹ በአካዳሚክ ሪከርዳቸው፣ እንዲሁም በኢንተርቪው እንዲለዩ ይደረጋል።
ከጠቅላላው 20 የመጨረሻ እጩዎች መካከል፣ 15 ከፍተኛ ብቃት ያላቸው፣ በኢኮኖሚ የተቸገሩ ተማሪዎች ከመደበኛ ፈተናዎች፣ ከአሜሪካ ቪዛ ክፍያ ጋር የተያያዙ ወጪዎችን በሚሸፍነው የOpportunity Program Fund (#OPF) ፕሮግራም ተጠቃሚ እንዲሆኑ ይመረጣሉ።
የመጀመሪያዎቹ ጥቂት ስኬታማ ዕጩዎች ወደ አሜሪካ የራውንድ ትሪፕ ትኬት ያገኛሉ።
ቀሪዎቹ 5 ተማሪዎች በስልጠና ፕሮግራሙ ላይ #በነጻ ይሳተፋሉ ነገር ግን የዝግጅት ወጪን ከራሳቸው ምንጭ ይሸፍናሉ። የሞባይል ዳታ ወጪዎች ለሁለቱም የፕሮግራም ተሳታፊዎች በኤምባሲው ይሸፈናሉ።
ማመልከቻ እስከ ሚያዚያ 10/2024 (5:00 pm EAT) ማስገባት ይችላል ተብሏል።
ለማመልከት አስፈላጊ መስፈርቶች ምንድናቸው ?
➡ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖሩና ትምህርታቸውንም እዚሁ ኢትዮጵያ እየተከታተሉ ያሉ።
➡ ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገበ/ች #ኢትዮጵያዊ ተማሪ፣
➡ በዚህ የትምህርት አመት መጨረሻ 11ኛ ክፍልን ያጠናቅቁ እና ከመስከረም 2024 ጀምሮ 12ኛ ክፍል የሚማሩ፣
➡ በጠቅላላ 4 ሳምንታት የESP መርሃግብር ለመሳተፍ ቃል መግባት የሚችሉ መሆን አለባቸው።
ስታመለክቱ የሚያስፈልጉ ፦
1ኛ. የሁለተኛ ደረጃ ትራንስክሪፕት (9፣ 10፣ 11)
2ኛ. ከትምህርት ቤት የድጋፍ ደብዳቤ
3ኛ. የኢኮኖሚ ችግር ያለባቸውና ለOpportunity Fund Program (OFP) የሚያመለክቱ ከትምህርት ቤት ወይም ከቀበሌ የቤተሰብን #ዝቅተኛ የኢኮኖሚያ ሁኔታ የሚያረጋግጥ ደብዳቤ ማቅረብ ያስፈልጋል።
የማመልከቻ ሊንክ እና ተጨማሪ ዝርዝር መረጃ በዚህ ይመልከቱ ፦ https://sites.google.com/amspaceseth.net/educationusa-esp2024
@tikvahethiopia
ፎቶ ፦ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከ95 ሺህ እስከ 80 ሺህ ያለአግባብ የወሰዱትን ገንዘብ ያልመለሱ ግለሰቦችን ፎቶግራፍ አሰራጨ።
ባንኩ አለግባብ የወሰዱትን ገንዘብ የማይመልሱ ግለሰቦችን ምስል ከተጨማሪ መረጃዎች ጋር ለህዝብ ይፋ እንደሚያደርግ በተደጋጋሚ ማስጠንቀቁን አስታውሷል።
በዚህም ለ2 ዙር የወሰዱትን ገንዘብ ያልመለሱ ገለሰቦችን ፎቶ ማሰራጨቱን አመልክቶ አሁን ደግሞ በ3ኛ ዙር ያልመለሱት የገንዘብ መጠን ከ95 ሺህ እስከ 80 ሺህ ብር ድረስ የሆነ ግለሰቦችን መረጃ ለማውጣት መገደዱን ገልጿል።
@tikvahethiopia
#Update : የመኖሪያና ንግድ ቤቶች ጨረታ የአሸናፊዎች ስም ዝርዝር ይፋ ተደረገ።
የአዲስ አበባ ከተማ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽንና የአዲስ አበባ ከተማ ዲዛይን እና ግንባታ ስራዎች ቢሮ አስገንብተው ለጨረታ ያቀረቧቸው የመኖሪያ እና የንግድ ቤቶች ጨረታ አሸናፊዎች ዝርዝር ከላይ ተያይዟል።
በከተማው በመንግስት በተመደበ ካፒታል በጀት በተለያዩ ክፍለ ከተሞች የተሰሩ የመኖሪያ እና የንግድ ቤቶች ለጨረታ መቅረባቸው ይታወሳል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ የአሸናፊዎች ስም ዝርዝሩን የያዘው ፋይል ምንጭ የአ/አ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ መሆኑን ይገልጻል።
@tikvahethiopia
#AddisAbaba
በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ የሞተር ሳይክል እና የኤሌክትሪክ ሞተር ሳይክል የትራንስፖርት አገልግሎት አሰጣጥን የሚወስን አዲስ መመሪያ መዘጋጀቱን የትራንስፖርት ቢሮ አሳውቋል።
አዲሱ መመሪያ ቁጥር 155/2016 የሚባል ሲሆን ተግባራዊም አድርጓል፡፡
በመመሪያው ፦
➡ ከአሽከርካሪው ውጪ ሌላ ሰው መጫን እንደማይቻልና ለእቃ ማመላለሻ ብቻ አገልግሎት መስጠት እንደሚገባ፣
➡ ከኤሌክትሪክ ሞተር ሳይክል ውጪ አዲስ የአገልግሎት ፍቃድ እንደማይሰጥ፣
➡ ከ250 አባላት ጀምሮ በማህበር በመደራጀት ፍቃድ እንደሚሰጥና አሁን በስራ ላይ የሚገኙ የሞተር ሳይክሎች በቀጣይ ቢሮው በሚያስቀምጠው የጊዜ ገደብ መነሻነት ወደ ኤሌክትሪክ የሞተር ሳይክል መለወጥ እንደሚገባ ተገልጿል።
ቢሮው ባወጣው መመሪያ መሰረት አገልግሎቱን የማይሰጡ ባለንብረቶች እና አሽከርካሪዎች በመመሪያ ቁጥር " 155/2016 " መሰረት እንደ ጥፋቱ እርከን ቅጣት እንደሚጣልባቸው ማሳሰቢያ ተላልፏል።
Via /channel/thiqahEth
@tikvahethiopia
MAMA'S kids ማማስ ኪድስ
▶️ ኦርጅናል እና ጥራታቸውን የጠበቁ የልጆች እቃዎች ለማግኘት ቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ 👉/channel/mamaskids
አድራሻችን ፦ መገናኛ ዘፍመሽ ግራንድ ሞል 2 ተኛ ፎቅ የሱቅ ቁጥር 225
👉 ውድ ደምበኞቻችን ሱቃችን 225 ቁጥር መሆኑን እና የራሳችን ሎጎ መኖሩን ያረጋግጡ እናመሰግናለን።
ለበለጠ መረጃ ፦ በ0965809005 / በ0938309171 ይደውሉልን።
#AddisAbaba
በአዲስ አበባ ከተማ #ለአፓርትመንት_ቤቶች እና #ለጋራ_መኖሪያ_ቤቶች ወይም ኮንዶሚኒየም ቤቶች አማካኝ የሽያጭ ዋጋ ተመን በ34 በመቶ እንዲቀንስ ተደርጓል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ይህን ጉዳይ በተመለከተ ለሁሉም ክ/ከተሞች የአፈፃፀም መመሪያ መጻፉን ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ ዘግቧል።
በከተማዋ የቤት ሽያጭ ዋጋ ተብሎ በገዥ እና ሻጭ መካከል የሚደረግ ውል ላይ የሚቀርበው ዋጋ እጅግ በተጋነነ መልኩ ዝቅተኛ በመሆኑ እና በባለሙያ የሚወሰድ የቤት ግምት ዋጋ ወቅታዊ ባመሆኑ መንግስት ከቤት ሽያጭ ተገቢውን ገቢ እየሰበሰበ እንዳልነበረ ቢሮው ገልጿል።
ይህንን ችግር ለመፍታት እንዲቻል ካለፈው ዓመት ሰኔ 8 ቀን 2015 ዓ/ም ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረግ ወቅታዊ የቤት ሽያጭ ዋጋ ተግባራዊ መሆኑን ጠቅሷል፡፡
ይሁን እንጂ በከተማ ደረጃ ተጠንቶ ተግባራዊ የተደረገ የቤት ሽያጭ ዋጋ እና አሰራሩ ላይ ከህብረተሰቡ በርካታ ቅሬታዎች እየቀረቡ በመሆኑ በመሬት ልማትና አስተዳደተር ቢሮ እና የመሬት ይዞታ ምዝገበና መረጃ አጄንሲ በጋራ ጥናት በማድረግ የተለዩ ክፍተቶችና እና የቤት ሽያጭ ግምት ላይ ማሻሻያ ተደርጓል ብሏል።
በተደረገው ማሻሻያ ለአፓርትመንት ቤቶች እና ኮንዶሚኒየም ቤቶች የሽያጭ ዋጋ ተመን አምና በሰኔ ወር ከነበረው 34 በመቶ እንዲቀንስ ተደርጓል።
በተሻሻለው የቤት ሽያጭ ዋጋ ተመን መሰረት ከኮንደሚንየም እና አፓርትመንት ውጪ ለሆኑ ግንባታዎች፦
➡️ የግንባታ ነጠላ ዋጋ በጭቃ የተሰራ ቪላ ቤት (G+0) ነጠላ ዋጋ በካሬ 15,000 ብር፣
➡️ በብሎኬት የተሰራ የቪላ ቤት (G+0) ነጠላ ዋጋ በካሬ 20,000 ብር፣
➡️ የህንጻ ወለላቸው ከG+1 እስከ G+5 25,000 ብር እና፣
➡️ G+6 እና በላይ የሆኑ ቤት ወይም ህንጻ ነጠላ ዋጋ በካሬ 30,000 ተደርጓል፡፡
የቦታው መገኛ ዋጋ ('location value') ለከተማው የቦታ ደረጃ የጸደቀው ወቅታዊ አማካይ የሊዝ ጨረታ ዋጋ እንዲሆን መደረጉም ተገልጿል።
የቤት ስም ንብረት ዝውውር ክፍያ ማለትም አሹራ 4 በመቶ እና የቴምብር ቀረጥ 2 በመቶ ከጠቅላላ የቤቱ ሽያጭ ዋጋ ተሰልቶ ከ ከመጋቢት17 ቀን 2016 ዓ/ም ጀምሮ እንዲከፈልም ቢሮ አዟል።
ባለፈው ዓመት ሰኔ ወር ጀምሮ ተግባራዊ የተደረገው የቤት ሽያጭ ዋጋ ተመን #መሻሩንም ቢሮ ጠቅሷል።
በፍርድ ቤት እና በባንክ ሃራጅ ሽያጭ የስም ንብረት ዝውውር የሚጠየቅባቸው ይዞታዎችን በተመለከተ ይዞታ አገልግሎትና መብት ፈጠራ ደንብ ላይ በተቀመጠው አግባብ ተፈጻሚ ይሆናል ተብሏል።
ይህ ማሻሻያ መምሪያ ከመውጣቱ በፊት የስም ንብረት ዝውውር አገልግሎት ጠይቀው በሂደት ላይ ሆኖ ክፍያ የፈጸሙ ተጋልጋዮች በቀድሞ አሰራር በከፈሉት ክፍያ መሰረት ይስተናገዳሉ ተብሏል።
ግንባታቸው ያልተጠናቀቁ ህንፃዎች የትመና ስራ የሚሰራላቸው ግንባታው በደረሰበት ወይም አሁን ላይ ባለበት ግንባታ ደረጃ እንደሚሆን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ለሁሉም ክ/ከተሞች የፃፈውን የአፈፃፀም መመሪያ ዋቢ በማድረግ ሬድዮ ጣቢያው ዘግቧል።
Info - ShegerFm
Pic Credit - WZNews
@tikvahethiopia
ወ/ሮ አያንቱ ሙስጠፋ ላይ የተፈፀመው ምንድነው ?
➡ ወ/ሮ አያንቱ ሙስጠፋ ነዋሪነቷ በምስራቅ ሀረጌ ዞን ኮምቦልቻ ወረዳ ቀበሌ 02 ነው።
➡ በ2008 ዓ/ም ነው ከባለቤቷ አቶ አሪፍ አልዬ ጋር በጋብቻ የተሳሰረችው።
➡ ላለፉት 8 ዓመታት በትዳር ስትቆይ 2 ወንድ ልጆችን አፍርተዋል።
ጥር 15 ቀን 2016 ዓ/ም ፍፁም ባልጠበቀችው ሁኔታ በገዛ ባለቤቷ እና የልጆቿ አባት ዘግናኝ በሆነ መንገድ በአሲድ ተቃጥላለች። አንድ አይኗንም አጥታለች።
ከባለቤቷ ጋር በተደጋጋሚ አለመግባባቶች ቢፈጠሩም ይህን ያደርግብኛል ብላ በፍፁም አልጠበቀችም።
ወ/ሮ አያንቱ ሙስጠፋ ፦
" በዕለቱ (ጥር 15 ቀን 2016) ቀን ስራ ውዬ ልጆቼን ከቤተሰቦቼ ጋር ይዤ ወደ ቤት ገባሁ።
ማታ ተሰብስበን እራታችንን በላን እጅግ ደክሞኝ ስለነበር ልጆቼን በግራ እና በቀኝ አስተኝቼ እኔም ተኛው።
በዛ ቀን ምን ክፉ ደግ አልተነገርንም። ከለሊቱ 9 ሰዓት ተኩል አካባቢ #አሲድ በማስታጠቢያ አድርጎ በተኛሁበት በጭንቅላቴ አፈሰሰብኝ።
ወይኔ ጭንቅላቴን ተቃጠልኩ ! ብዬ ከተኛሁበት ተነስቼ እጁን ልይዘው ስሞክር ' ገና መቼ ተቃጠልሽ ' ብሎ አሲዱን አይኔ ውስጥ ጨመረው።
ያኔ አንዱ አይኔን ለማትረፍ በእጄ ሸፍኜ በሩን ለመክፈት ስሞክር የተረፈውን አሲድ ጀርባዬ ላይ ረጨብኝ።
ለረጅም ጊዜ #በቅናት ምክንያት ያስቸግረኝ ነበር። ከዛሬ ነገ ይሻለዋል እያልኩኝ አብሬው ቆየሁ። በዚህ ውስጥ ነው 2 ልጆች የወለድነው።
በተደጋጋሚ ይዝትብኝ የነበረ ቢሆንም እንዲህ ይጨክናል ብዬ አላሰብኩም። "
እንደ ሀረማያ የሕይወት ፋና ሆስፒታል መረጃ ከሆነ በወ/ሮ አያንቱ ላይ የደረሰው ቃጠሎ 3ኛ ደረጃ የሚባለው ነው። የአሲድ ጥቃቱ በአይኗ፣ በጭንቅላቷ፣ ፊቷ ላይ ፣ ደረቷ ፊት ፣ እጇ ላይ ጉዳት ደርሷል።
የቀኝ አይኗ ላይ በአሲድ ቃጠሎው ምክንያት የብሌን ጉዳት ስላጋጠመ ማየት አትችልም። የግራውን ግን በህክምና ማትረፍ ተችሏል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለመረጃው ባለቤት የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ (ጋዜጠኛ ቴዎድሮስ ታደሰ) እውቅና ይሰጣል።
@tikvahethiopia
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መጋቢት 6 / 2016 ዓ/ም ለሊት ችግር በገጠመው ጊዜ " የህዝብን ገንዘብ ያለአግባብ ወስደው እስካሁን #አልመለሱልኝም " ያላቸው ግለሰቦች በተለያዩ ሚዲያዎች ፎቷቸውን እያሰራጨ ይገኛል።
ከሚዲያዎች በተጨማሪ በየባንኩ ቅርንጫፎች እንዲሁም በከፍተኛ ትምህርት ተቋም በር ላይ ለህዝብ በሚታይ መልኩ " ገንዘቡን አልመለሱም " ያላቸውን ግለሰቦች ፎቶግራፍ በትልልቅ ባነር በማሰራት ለጥፏል።
ከዚሁ ጉዳይ ጋር በተያያዘ " ብር ተመላሽ አድርገን እስካሁን ፎቷችን በሚዲያዎች እንዲሰራጭ እየሆነ ነው " ያሉ ቅሬታ አቅራቢዎች ባንኩ ገንዘብ የመለሱትንም በፎቶግራፍ ማውጣት እንዳለበት ገልጸዋል።
" የወሰድነውን ብር ተመላሽ አድርገን ሳለ ባንኩ ብር ካልመለሱት ጋር አደባልቆ ፎቶፍራፋችንን ማሰራጨቱ ተገቢ አይደለም በመሆኑንም ህዝብ በሚያውቀው መንገድ መመለሳችንን ሊያሳውቅ ይገባል " ብለዋል።
@tikvahethiopia
#ፎቶ
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መጋቢት 6 ከባንኩ ገንዘብ " ያለአግባብ ወስደው አልመለሱልኝም " ያላቸውን ግለሰቦች ፎቶ ማሰራጨት ቀጥሏል።
ዛሬ ከ80 ሺ እስከ 70 ሺ ብር ወስደው ያልመለሱ ግለሰቦችን ፎቶግራፍ አሰራጭቷል።
ባንኩ ባለፉት ቀናት ለ3 ዙር ያህል ፎቶግራፍ ማሰራጨቱ ይታወሳል።
@tikvahethiopia
#Update
የሶማሊያ መንግሥት ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት #ለማቋረጥ በመወሰን በአገሪቱ የሚገኙ የኢትዮጵያ አምባሳደር እና ዲፕሎማቶች ለቀው እንዲወጡ ማዘዟ ተሰምቷል።
አዲስ አበባ ያሉትን አምባሳደሯንም ጠርታለች።
የሶማሊያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ያሳለፈውን ውሳኔ ተከትሎ የአገሪቱ የውጭ ጉዳይ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሚኒስቴር ይፋ እዳደረገው በሶማሊያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሙክታር ሞሐመድ ዋሬ በ72 ሰዓታት ውስጥ ሞቃዲሾን ለቀው እንዲወጡ አዛለች።
በተጨማሪም ከሶማሊያ ነጻ አገርነቷን ባወጀችው ሶማሊላንድ እና በከፊል ራስ ገዟ ፑንትላንድ ውስጥ የሚገኙት ቆንስላ ጽህፈት ቤቶች በ7 ቀናት ውስጥ እንዲዘጉ መወሰኑን ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ባወጣው መግለጫ አመልክቷል።
በተመሳሳይም ሶማሊያ በአዲስ አበባ የሚገኙትን አምባሳደሯን “ ለአጠቃላይ ምክክር ” ከኢትዮጵያ ለቀው እንዲወጡ መታዘዛቸው ተገልጿል።
የሶማሊያ እርምጃ ኢትዮጵያ #ሶማሌለንድ ጋር የመግባቢያ ስምምነት ማድረጓን ተከትሎ " በውስጥ ጉዳዬ ጣልቃ ገብታለች " በሚል ምክንያት ነው።
ሮይተርስ ከሰዓት በፊት የሶማሊያ ባለሥልጣናትን ዋቢ በማድረግ ባሰራጨው መረጃ የኢትዮጵያ አምባሳደር ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ተደርገዋል ብሎ የነበረ ሲሆን አሁን የሶማሊያ መንግሥት በይፋ አምባሳደሩ በ72 ሰዓታት ለቀው እንዲወጡ ማዘዙን አሳውቋል።
የሶማሊያን መንግሥትን ውሳኔን በተመለከተ የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ ነብዩ ተድላ በዚህ ጉዳይ መረጃ እንደሌላቸው ገልጸው ነበር።
መረጃው የቢቢሲ እና ሮይተርስ ነው።
@tikvahethiopia
#AddisAbaba
ምንም አይነት የጤና ችግር የሌለበት ጓደኛቸውን ሁለቱም ኩላሊቶቹ ከጥቅም ውጪ የሆኑ በማስመሰል በህክምና ሰበብ ገንዘብ ሲያሰባስቡ የነበሩ 10 ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ገለጸ።
ግለሰቦቹ በቁጥጥር ስር የዋሉት በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 14 ልዩ ቦታው " አዲስ ሰፈር " አካባቢ መሆኑን አሳውቋል።
ግለሰቦቹ የሰሌዳ ቁጥር " ኮድ 3- B21705 አ.አ " የሆነ ሚኒባስ ተሽከርካሪን በመጠቀም ገንዘቡን ሲሰበስቡ የቆዩት " የኩላሊት ታማሚ ነው " ያሉትን ጓደኛቸውን መኪና ውስጥ በማስተኛት ነው።
በተያዙበት ወቅት ከ5 ሺህ ብር በላይ ገንዘብ እጃቸው ላይ መገኘቱን ፖሊስ ገልጿል።
የአዲስ አበባ ፖሊስ ፤ በከተማው በተለያዩ አካባቢዎች ተመሳሳይ የድጋፍ ጥያቄዎች ሲቀርቡ የሚስተዋል መሆኑን ገልጾ ነገር ግን ህብረተሰቡ እንዲህ አይነት #የማታለል ተግባርም የሚፈፅሙ ሰዎች መኖራቸውን ተገንዝቦ ድጋፍ ሲያደርግ ከህክምናው ጋር የተያያዙ አግባብነት ያላቸውን #ሰነዶች በማየትና ትክክለኛነቱን በማረጋገጥ ሊሆን ይገባል ሲል አሳስቧል።
@tikvahethiopia
" 480 ስደተኞች #በሊቢያ የባህር ጠረፍ ላይ ተይዘዋል " - IOM
ባሳለፍነው ሳምንት ብቻ 480 ስደተኞች በሊቢያ የባህር ጠረፍ ላይ መያዛቸው ተነግሯል።
የዓለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት/IOM ሰኞ'ለት ባወጣው መግለጫ 480 ስደተኞች በባህር ላይ ጠባቂዎች መያዛቸውን አስታውቋል።
ድርጅቱ "ከመጋቢት 24 እስከ 30,2024 ውስጥ 480 ስደተኞች ተይዘው ወደ ሊቢያ ተመልሰዋል " ነው ያለው።
ከተያዙት ስደተኞች ውስጥ 26 ሴቶች እንዲሁም 5 ህፃናት እንደሚገኙበትም ተነግሯል።
የስደተኞች 2 #አስክሬንም ተገኝቷል።
በዚህ ዓመት በጠቅላላ 3,791 ስደተኞች የተያዙ ሲሆን፣ ከእነዚህም ውስጥ 120ዎቹ #ሲሞቱ ፣ ሌሎች 250 የሚሆኑት #ጠፍተዋል መባሉን MDN ዘግቧል።
ፎቶ ፦ ፋይል
Via t.me/+LM-bJ8NzZMcxMjA8
@tikvahethiopia
#ደመወዝ #የትርፍሰዓትክፍያ
➡ “ ከ9 ወር በላይ ለሚሆን ጊዜ የትርፍ ሰዓት ክፍያ አልተከፈለንም ”- ከ200 በላይ የጤና ባለሙያዎች
➡ “ የትርፍ ሰዓት በየወሩ እየተከፈለ አይደለም እሱ ትክክል ነው። የከተማ አስተዳደሩ ለመክፈል ቃል ገብቷል ” - የጋሞ ዞን ጤና መምሪያ
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፤ ጋሞ ዞን ፤ በሰላምበር ከተማ አስተዳደር የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የሚያገለግሉ የጤና ባለሙያዎች ከ9 ወራት በላይ ለሚሆን ጊዜ የትርፍ ጊዜ ሰዓት ክፍያ እንዳልተከፈላቸው ፣ ደመወዝም የሚገባላቸው እየተቆራረጠ መሆኑን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።
የጤና ባለሙያዎችን ወክለው ቃላቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የሰጡ አንድ የጤና ባለሙያ ተከታዩን ብለዋል።
- “ ከ9 ወራት በላይ ለሚሆን ጊዜ የትርፍ ሰዓት ክፍያ አልተከፈለንም። ሳይከፈለን 10ኛ ወር እየሰራን ነው ያለነው። ”
- “ በሌላ በኩል ደግሞ ዋና ደመወዝ ሁሌም እየተቆራረጠ ነው የሚገባው። ግማሹ ብቻ ያስገቡና ግማሹ ደግሞ ሳይገባ ወሩ ያልቃል። ”
- “ የደመወዝ ሆነ የትርፍ ሰዓት ክፍያ በተመለከተ ቅሬታ ያለን 113 ጤና ባለሙያዎች (የትርፍ ሰዓት ያልተከፈላቸው) ፣ 103 ድጋፍ ሰጭ ባለሙያዎች (የትርፍ ሰዓት ክፍያ የማይመለከታቸው) ናቸው። ”
- “ ያልተከፈለው የክፍያ መጠን እንደ ጤና ባለሙያው ፤ አሁን ለምሳሌ የእኔ 5,000 ነው በወር የሚሆነው። 15 ሺሕ የሚከፈለው አለ። 30 ሺሕ የሚከፈለው አለ እንደ ስፔሻሊቲ ከሆነ። ”
በጉዳዩ ላይ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ፦
* የሰላምበር የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የCOA ተወካይ አቶ ደካሶ ዲቻ፣
* የሰላምበር ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ዘነበ ወንተ
* የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ እንደሻው ሽብሩን አግኝቶ ምላሽ እንዲሰጡ ቢሞክርም ፈቃደኛ አልሆኑም።
የጋሞ ዞን ጤና መምሪያ ግን ለተነሳው ቅሬታ ምላሽ ሰጥቷል። የዞኑ ጤና መምሪያ ቢሮ አቶ ሰይፉ ዋናካ ቃላቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ሠጥተዋል።
አቶ ሰይፉ ዋናካ ምን አሉ ?
° “ ቅሬታ ሲቀርብ ወርደን እናወያያለን። ከሁለት ወራት በፊት ወርደን አወያይተን፣ አግባብተን የትርፍ ሰዓት በየወሩ እየተከፈለ አይደለም እሱ ትክክል ነው። ግን ያው የተወዘፈም እየተከፈለ ነው ያለው። ”
° “ ችግሩ ካለ ወርደን እናስከፍላለን። የደመወዝ፣ የትርፍ ሰዓት ጉዳይ ከእኛ አቅም በላይ አይደለም። ”
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ጉዳዩ ካቅማችሁ በላይ ካልሆነ ከ9 ወራት በላይ ለምን ዘገዬ ? ሲል ጠይቋል።
ምላሽ ፦
° “ የከተማ አስተዳደሩ ችግርም ፣ አገራዊ ችግሮችም አለ። ሁሉ ወጥ አይሆንም። የከተማ አስተዳደሩ ለመክፈል ቃል ገብቷል። ስለዚህ የ10 ወራቱም ቢሆን ይከፈላል። ”
ጤና ባለሙያዎቹ በበኩላቸው፣ ከወራት በፊት ፒቲሽን ሰብስበው የትርፍ ሰዓት ሥራ እንደማይሰሩ አቋማቸውን ሲገልጹ ኃላፊዎች ቢያወያዩአቸውም ክፍያው እንዳልተሰጣቸው አስረድተዋል።
መረጃው በአ/አ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል የተዘጋጀ ነው።
@tikvahethiopia
#DStv: ቀላል እና ፈጣን መላ ለዲኤስቲቪ ደንበኞች በሙሉ!
ወደ ዲኤስቲቪ የጥሪ ማዕከል ሳይደውሉ በማንኛውም ሰዓት በሞባይልዎ *9299# በመደወል እና My DStv App ስምዎንና የስማርት ካርድ ቁጥርዎን አስገብተው የዲኤስቲቪ ክፍያ መጠንዎንና ቀኑን በቀላሉ ለማወቅ ፓኬጅ ለመቀየር ብሎም በቴሌብር ፣ በሲቢኢ ብር እና በአዋሽ ብር መክፈል ይችላሉ።
የMyDStv
- የቴሌግራም
- የፕሌይ ስቶር
- የአፕ ስቶር ሊንክ ይጫኑ!
በተጨማሪም ስለ አገልግሎታችን ጥራት በሚደርስዎት የፅሁፍ መልዕክት ላይ ሊንኩን በመጫን መጠይቁን እንዲሞሉ በትህትና እንጠይቃለን።
ይሞክሩትና የማይጠገብ የመዝናኛ አማራጭ ያለማቋረጥ ያጣጥሙ ፤ የእርስዎንም አስተያየት ያጋሩ!
#ሁሉምያለውእኛጋርነው #DStvEthiopia #DStvSelfServiceET'
" አደጋዉ እጅግ አሰቃቂ ነበር " - ኢኒስፔክተር ተስፋዬ ደምሴ
በቅርቡ በመኪና አደጋ በርካታ ልጆቿን አጥታ ገና ሀዘኗ ያልወጣላት ሀዋሳ ዛሬም ሌላ ሀዘን አስተናግዳለች።
በዛሬዉ እለት ከሰዓት መነሻዉን ከሀዋሳ ያደረገ " ዶልፊን " የሚሰኘው ተሽከርካሪ ከቅጥቅጥ አዉቶብስ ጋር " ሀዊላ ወረዳ ቱላ አዋሳኝ " ሲደርስ በመጋጨቱ በህይወት እና በንብረት ላይ አደጋ ደርሷል።
የበርካታ ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በርካቶችም ቀላልና ከባድ አደጋ አስተናግደዋል።
አሁን ላይ ተጎጅዎች በሀዋሳ ከተማ ውስጥ በሚገኘዉ ሪፈራል ሆስፒታል እርዳታ እያገኙ ይገኛሉ።
የሟች ቁጥርን በተመለከተ ለጊዜው የተረጋገጠ መረጃ ማግኘት አልተቻለንም።
የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ኮሚኒኬሽን አደጋው በተመለከተ ባወጣው መረጃ መጀመሪያ 15 ሰዎች ህይወታቸው እንዳለፈ ቢገልጽም በኃላ ላይ ቁጥሩ 4 ብሎ ቀይሮታል (እስካሁን ያለውን)።
በአደጋው ዙሪያ ያነጋገርናቸው የሀዋሳ ከተማ ትራፊክ ፖሊስ አስተባባሪ ኢንስፔክተር ተስፋዬ ደምሴ " አደጋዉ እጅግ አሰቃቂ ነበር " ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።
ለጊዜው የሟቾችን ትክክለኛ ቁጥር በተመለከተ መረጃ ለመስጠት አልወደዱም።
አደጋዉ ሀዋሳ አዋሳኝ በመሆኑ ዝርዝር መረጃ ከመስጠት የተቆጠቡት ኢንስፔክተር ተሰፋዬ ፤ አሁን ላይ በሚታወቀው በርካታ ተሳፋሪዎች ለህልፈት መዳረጋቸውን ገልጸዋል።
ዝርዝር ማብራሪያዉን የሚመለከታቸዉ አካላት ለማህበረሰቡ እንደሚያደርሱ ተናግረዋል።
መረጃው ተዘጋጅቶ የተላከው በሀዋሳው የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው።
@tikvahethiopia
#NewsAlert
በአዲስ አበባ ከአሁን በኋላ የሚገነቡ ማንኛውም ግንባታዎች ከዋና ከመንገድ በ10 ሜትር ርቀት መሆን እንደሚገባቸው ውሳኔ ተላለፈ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ 3ኛ ዓመት 11ኛ መደበኛ ስብሰባ በ3 ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል።
ከውሳኔዎቹ አንዱ ግንባታዎችን የሚመለከት ነው።
በዚህም የከተማዋን ስታንዳርድ እና መዋቅራዊ ፕላን ለማስጠበቅ እንዲሁም መልሶ ማፍረስ እንዳይገጥም ፤ ግንባታዎች ከመንገድ ያላቸው ርቀት ከዚህ በኋላ ወጥነት ያለው የከተማ አሰራር አንዲኖር በማሰብ ከመንገድ መራቅ ያለባቸውን 3 ደረጃዎች ወጥተዋል።
ከአሁን በኋላ የሚገነቡ ማንኛውም ግንባታዎች ፦
➡ ከዋና ከመንገድ በ10 ሜትር ርቀት መሆን እንደሚገባው ፤
➡ ከንዑስ ዋና መንገድ 5 ሜትር ርቀት፤
➡ ሰብሳቢ መንገድ ደግሞ 3 ሜትር ርቀት
➡ በተጨማሪ የውስጥ ለውስጥ መንገድ 2 ሜትር ርቀት መጠበቅ እንዳለባቸው ካቢኔው ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል።
ሌለው ውሳኔ የተላለፈበት ጉዳይ የከተማዋን የተሽከርካሪ አስተዳደር ህግ እና ሥርዓት ለማስከበር የከተማ አስተዳደሩ ባወጣው የተሽከርካሪ ማቆሚያ አገልግሎት አሰጣጥ ረቂቅ ደንብን ላይ ሲሆን ለአሰራር በሚያመች መልኩ ሀሳብ ተሰጥቶበት ደንቡ ፀድቋል።
ከዚህ በተጨማሪ " የነገዋ የሴቶች ተሀድሶ እና ክህሎት ማበልፀጊያ ማዕከል " ማቋቋሚያ ደንብ ማዕከሉን በተለይም ፦
- ለጎዳና ህይወት ፤
- ለፆታዊ ጥቃት ሰለባ እና ለወሲብ ንግድ ተጋላጭ ለሆኑ ሴቶች ፣ መጠለያ፣ ማገገሚያ እና የተመሰቃቀለ ህይወታቸውን እንደገና ለማደስ የሚያስችል የሙያ እና ክህሎት ሥልጠናዎች የሚያገኙበትን እና በዘላቂነት እንዲቋቋሙ የሚያግዝ አቅም ያለዉ ማዕከል እንዲሆን ለማስቻል በሚያግዘው ማቋቋሚያ ደንብ ላይ ካቢኔው ተወያይቶ አጽድቋል።
@tikvahethiopia
#AddisAbaba
በአዲስ አበባ ከተማ በመሬት አገልግሎት ላይ ተጥሎ የነበረው እግድ መነሳቱ ተነግሯል።
ላለፉት 3 ወራት እግድ ተጥሎበት የነበረው የመሬት አገልግሎት ካለፈው ሰኞ መጋቢት 23 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ መነሳቱን ሪፖርተር ጋዜጣ ዘግቧል።
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በተጠናው የመዋቅር ጥናት መሠረት የሰራተኞች ድልድል ተካሂዶ ምደባ እስከሚካሄድ ድረስ በሚል ነበር ከጥር 21 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ላለፉት 3 ወራት የመሬት አገልግሎት ታግዶ የቆየው።
የከተማ አስተዳደሩ አጠቃላይ የሰራተኛ ድልድሉ በመጠናቀቁ ከመጋቢት 23 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ የመሬት አገልግሎት የተጀመረ መሆኑን እንዳስታወቀ ጋዜጣው አስነብቧል።
@tikvahethiopia
#ትግራይ
የኤርትራ ሰራዊት በተቆጣጠራቸው የኢሮብ የኢትዮጵያ የትግራይ አከባቢዎች ለሚገኙ ነዋሪዎች ማስጠንቀቅያ ሲሰጥ የሚያሳይ የቪድዮ መረጃ የኢሮብ ብሄረሰብ ተወላጆችን አሰቆጥቷል።
የኤርትራ ሰራዊት ተወካይ የኢሮብ ተወላጆች ስብስቦ ማስጠንቀቅያ ሲሰጥ የሚያሳየው የቪድዮ መረጃ በማህበራዊ የትስስር ገፆች በመሰራጨት ላይ ሲሆን በክልሉ ሚድያዎችም ሽፋን ሰጥተውታል።
የቪድዮው የድምፂ ቅጂ ምን ይላል ?
"... እናንተ ህዝብ ናችሁ። የምትኖሩበት መሬት ደግሞ የኤርትራ ነው። ኤርትራውያን ከሆናችሁ ለዚሁ አከባቢና መሬት ተገዢ እንዲሁም እዚህ ላለው ሰራዊት የማገዝ ግዴታ አለባችሁ።
አገራዊ አገልግሎት የመስጠት ግዴታም አለባችሁ። በትወልዱም በትጠሉም አንድ የኤርትራ ዜጋ የሚያሳልፈውን ህይወት ልታልፉ ግድ ይላል።
አንድ ሰው ከዚህ አከባቢ ወደ አገራዊ አገልግሎት ከሄደ ለኤርትራ አገሩ ብሎ ነው የሚሄደው። ስለዚህ እያንዳንዳችሁ አገራዊ አገልግሎት እንደሚመለከታችሁ ማወቅ አለባችሁ። አባቶች የሃይማኖት መሪዎች ስሙ ከመካከላችሁ ኢትዮጵያዊ ነኝ የሚል ካለ የኤርትራ መንግስት እዚህ አስገድዶ አያኖረውም። ወደ ኢትዮጵያ የመሄድ መብት አለው። የኤርትራ መሬት ደግሞ ኤርትራውያን ይኖሩበታል።
ወደ አገራዊ አገልግሎት መሄድ ካለብህ ትሄዳለህ፤ ረሃብ ካለ እንደ ሌላው ኤርትራዊ ትራባለህ። በቃ ተካፍለህ ትኖራለህ። ላንተ ተብሎ የሚደረግ የተለየ ነገር የለም። ልቅ የሆነ አካሄድ ነው የቆየው ይህ ከአሁን በኃላ አይቀጥልም። " ሲል ያስጠንቅቃል የኤርትራ ሰራዊት ተወካዩ።
ቪድዮውን የተመለከቱ የኢሮብ ብሄረሰብ ተወላጆች የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደርና የፌደራል መንግስት በፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት መሰረት ከጥፋት እንዲታደግዋቸው ተማፅነዋል።
ብርሃን ወዲ ኢሮብ የተባለው የብሄረሰቡ ተወላጅ በሰጠው አስተያየት " ... አራት ዓመት ሙሉ በሁለት ተከፍለን ኮምፓስዋ እንደጠፋት መርከብ ሆነን ተሰፋችን ጨልሞብናል። ብሄረሰባችን እየጠፋ አረ የሰሚ ያለህ.." ሲል ምሬቱን ገልጿል።
የኤርትራ ሰራዊት በትግራይ ምስራቃዊ ዞን ፦
- የዛላኣንበሳ ከተማ
- በጉሎመኸዳ ወረዳ ማርታ ፣ አዲስ ተስፋ ፣ አዲስ ዓለም ፣ ሸዊት ለምለምና ሰበያ
- በኢሮብ ወረዳ እንዳልጌዳ ፣ ወርዓትለ ዓገረ ሎኽማና ዓሊቴና የተባሉ የኢትዮጵያ አከባቢዎች ተቆጣጥሮ ይገኛል።
በትግራይ ሰሜናዊ ምዕራብ ዞን በታሕታይ ኣድያቦ የኩናማ ማህበረሰብና ሌሎች የሚኖሩባቸው ገማህሎ ፣ አደመይቲ ፣ የባድመ ከተማና አከባቢው ፣ ዓዲ ፀፀር ፣ ለምለም ሸዊት ፣ ሸምበሊና ፣ መንጠብጠብ ፣ ዓዲ ኣሰር ፣ ሰየምቲ አድያቦ እንደሁ ተቆጣጥሮ እንደሚገኝ በተደጋጋሚ መዘገባችን ይታወሳል።
መረጃው በመቐለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል የተዘጋጀ ነው።
@tikvahethiopia
በርከትከት ያለ ኢንተርኔት ከሳፋሪኮም !
የሳፋሪኮም የቀን፣ የሳምንት እና የወር እንደልብ ጥቅሎችን እየገዛን በፈጣኑ የሳፋሪኮም 4G ኢንተርኔት እንንበሽበሽ!።
በM-PESA APP ተጠቅመው የእንደልብ ጥቅሎችን በመግዛት ጊዜያችንን ያለሃሳብ ዘና ፈታ እያልን እናሳልፍ!
ያልተገደበ ወርሃዊ በ999ብር ብቻ
ያልተገደበ ሳምንታዊ በ350 ብር ብቻ
ያልተገደበ ዕለታዊ በ60ብር ብቻ
የሳፋሪኮም ኢትዮጵያን ትክክለኛ መረጃዎችን በቀላሉ ለማግኘት ቀጥሎ በሚገኙት ይፋዊ የማህበራዊ ሚዲያዎች እንዲከታተሉ እንጋብዛለን።
👉Facebook: https://www.facebook.com/SafaricomET
👉Telegram: /channel/Safaricom_Ethiopia_PLC
👉Twitter:
https://x.com/SafaricomET?t=y2XAHAhPNvFeZqXa2YE6aQ&s=08
👉Instagram: https://www.instagram.com/safaricomet?igsh=MWJtcjJrMzNhMzVsNg==
👉 YouTube: safaricomethiopia2751?si=w2o8uz61oHeZM9gm" rel="nofollow">https://youtube.com/@safaricomethiopia2751?si=w2o8uz61oHeZM9gm
#ኢትዮጵያ
የኢዴፌሪ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመኖሪያ ቤት ኪራይ ጭማሪ የመንግሥት ተቆጣጣሪ አካል በሚወስነው መሠረት በዓመት አንድ ጊዜ ብቻ እንዲተገበር የሚያደርግ አዋጅ አፅድቋል።
አዋጁ የቤት አከራይ ከ2 ወር የቤቱ ኪራይ በላይ ቅድመ ክፍያ መጠየቅ እንደማይችልም ያስገድዳል።
አዋጁ ምን ይላል ?
➡ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ዋጋን የተመለከተው የአዋጁ አንቀጽ የመኖሪያ ቤት አከራዮች በዘፈቀድ የኪራይ ዋጋ እንዳይጨምሩ ይከለክላል።
➡ አከራይ የኪራይ ዋጋ ጭማሪ ማድረግ የሚችለው ተቆጣጣሪው አካል በዓመት አንድ ጊዜ ነባራዊ የኢኮኖሚውን ሁኔታ እና ሌሎች አግባብነት ያላቸውን ጉዳዮች ከግምት በማስገባት ሊወስን የሚችለውን የመኖሪያ ቤት ኪራይ ጭማሪ መሠረት በማድረግ ነው።
➡ በአዋጁ መሠረት የሚደረገው የመኖሪያ ቤት ኪራይ ጭማሪ፤ በተቆጣጣሪው አካል በሰኔ አንድ ለሕዝብ ይፋ ተደርጎ ከሰኔ 30 ጀምሮ ለአንድ አመት የፀና ይሆናል።
➡ የቤት ኪራይ ውል ዘመን ሳይጠናቀቅ ተከራይን ከቤት ማስወጣት ወይም በዚህ አዋጅ ከተፈቀደው ሁኔታ ውጪ የዋጋ ጭማሪ ማድረግ አይቻልም። ይህም አስገዳጅ ድንጋጌ ነው።
➡ አከራዮች ከሁለት ወር የቤቱ ኪራይ በላይ ቅድመ ክፍያ መጠየቅ #አይችሉም።
➡ የቤት ኪራይ ክፍያዎች በባንክ ወይም በሌላ ሕጋዊ የኤሌክትሮኒክ ዘዴ መፈፀም አለባቸው። አከራይ እና ተከራይ የቤት ኪራይ ክፍያ ሰነዶችን አደራጅተው የመያዝ ግዴታ አለባቸው።
➡ ማንኛውም የቤት ኪራይ ውል በጽሁፍ የሚደረግ ሆኖ በተቆጣጣሪው አካል መረጋገጥ እና መመዝገብ አለበት። ሁለቱም ወገኖች የቤት ኪራይ ውሉ በተፈረመ ሰላሳ ቀናት ውስጥ ውሉን አቅርበው እንዲረጋገጥ እና እንዲመዘገብ የማድረግ ግዴታ አለባቸው። ያልተረጋገጠ እና ያልተመዘገበ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ውል እንዳልተደረገ ይቆጠራል። አዋጁን ተከትሎ የሚደረግ መኖሪያ ቤት ኪራይ ውል ከሁለት ዓመት ሊያንስ አይችልም።
NB. በአዋጁ መሠረት ተቆጣጣሪ አካል ማለት የመኖሪያ ቤት ኪራይ ውልን እና ዋጋን እንዲቆጣጠር በክልሎች ወይም በአዲስ አበባ እና ድሬዳዋ ከተማ አስተዳደሮች የሚሰየም አካል ነው፡፡ #HoPR #ቢቢሲ
@tikvahethiopia
#ፎቶ
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከ121 ሺህ እስከ 95 ሺህ ገንዘብ ያለአግባብ የወሰዱና እስካሁን ያልመለሱ ግለሰቦችን ፎቶግራፍ አሰራጨ።
በትላንትናው ዕለት 108 ሺህ እስከ 305 ሺህ ገንዘብ ወስደው ያልመለሱ ግለሰቦችን ፎቶግራፍ ማሰራጨቱ ይታወሳል።
@tikvahethiopia
በቢዝነስ ኤክሴል ንግድዎን ያዘምኑ!
ሥራዎን የሚያቀሉ ቴምፕሌቶች እና ስለንግዱ ዓለም ወሳኝ መረጃዎችን ያገኛሉ።
በተጨማሪ ይህን መድረክ በመጠቀም በሳምንታዊ ጥያቄና መልስ ውድድር በመሳተፍ በየሳምንቱ 50,000 ብር ተሸላሚ መሆን ይችላሉ።
ለመመዝገብ ok ብለው ወደ 6424 ይላኩ
በቀን 2ብር ብቻ፤ ለ3 ቀናት በነፃ
ለተጨማሪ https://www.businessexcel.et ይጎብኙ
#Ethiotelecom #telebirr #RealizingDigitalEthiopia