ገንዘባችንን ከየትኛውም ባንክ ወደ M-PESA ፤ ከM-PESA ወደ የትኛውም ባንክ በመላክ ቀላል እና የተቀላጠፈ ክፍያ እንፈጽም!
M-PESA ላይ እንመዝገብ፣ በM-PESA እንገበያይ!
🔗 የM-PESA ሳፋሪኮምን መተግበሪያ በዚህ ሊንክ እናውርድ፡ https://bit.ly/M-PESA_SafaricomEthiopia
ስለ አገልግሎታችን ማንኛውንም ጥያቄ ወይም መረጃ በቴሌግራም ቻናላችን /channel/Safaricom_Ethiopia_PLC 24/7 ማግኘት ይቻላል!
#MPESASafaricom #TerekBeMPESA #FurtherAheadTogether
በሩዋንዳው #ጄኖሳይድ ወቅት የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ምን አደረገ ?
ከ800 ሺህ እስከ 1 ሚሊዮን የሚደርሱ ሰዎች ባለቁበት የሩዋንዳ የዘር ጭፍጨፋ ወቅት የዓለም መሪዎች ምንም እንኳን ስለ ዘር ጭፍጨፋው (ጄኖሳይድ) ቢያውቁም ጣልቃ አልገቡም ነበር።
ለረጅም ጊዜ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ' ጄኖሳይድ ' የሚለውን ቃል ከመጠቀም ተቆጥቦ ነበር ፤ ይህም #በአሜሪካ ጫና እንደሆነ ይነገራል።
አሜሪካም ወታደሮቿን ወደ ሩዋንዳ ለመላክ ያልፈለገች ሀገር ናት።
የቀድሞ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ሃላፊ ባን ኪሙን በ20ኛው ዓመት የዘር ጭፍጨፋው መታሰቢያ ወቅት " ድርጅቱ የዘር ማጥፋት ወንጀሉ መከላከል ባለመቻሉ አሁንም ድረስ ያፍራል " ሲሉ ተናግረው ነበር።
ጭፍጨፋው ከመጀመሩ በፊት (እኤአ በ1994 መጀመሪያ ላይ) ተመድ ወደ ሩዋንዳ የላከው ኃይል UNAMIR አዛዥ ጄኔራል ሮሜዮ ዳላይር ስለ ግድያው / ጭፍጨፋው በቂ የደህንነት መረጃ ደርሶት ነበር። በሁቱዎቹ የተከማቸ ሚስጥራዊ የጦር መሳሪያ (እንደ ገጀራዎች) እንዳለ አውቆ ነበር።
ከጥር እስከ መጋቢት ወር ድረስ 5 መልዕክቶችን ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት ልከዋል።
በዚህም በሩዋንዳ ያላቸው ተልእኳቸው እንዲሰፋ ሁቱዎች ያከማቿቸው መሳሪያዎች በቁጥጥር ስር እንዲውሉ እና የተመድ የሰራዊት ቁጥር እንዲጨምር ቢጠይቁም እዛ ያሉት ሰዎች ግን ማስጠንቀቂያዎቹን ችለ ብለው ትተዋቸዋል።
ግድያው ሲጀመር ተመድ እና የቤልጂየም መንግሥት የUNAMIR ሰላም አስከባሪዎችን አስወጡ።
የፈረንሳይ እና የቤልጂየም ሰላም አስከባሪዎች ቱትሲዎችን ለመርዳት ፍቃደኛ ሳይሆኑ በመቅረት በተሽከርካሪ የነበሩ የሌላ ሀገር ዜጎችን አስወጥተዋል።
ሳይወጡ የቀሩና ትንሽ የተረፉ የተመድ ኃይሎች በኪጋሊ ውስጥ እንደ " ሆቴል ዴ ሚሌ ኮሊንስ " እና " አማሆሮ ስታዲየም " ባሉ ቦታዎች የተሸሸጉ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ጥበቃ አድርገዋል።
በአንድ አጋጣሚ ግን በኪጋሊ ኢኮሌ ቴክኒክ ኦፊሴሌ (የቴክኒክ ት/ቤት) የተጠለሉ 2,000 ሰዎችን የሚጠብቁ ወታደሮች ቦታቸውን የውጭ ዜጎችን ለማስወጣት ሲሉ ቦታቸውን ለወቀው ሲወጡ በትምህርት ቤቱ እልቂት / ጭፍጨፋ ተፈፅሟል።
ቱትሲዎችን ለማጥፋት እቅድ እንዳለው እያወቀች የፕሬዝዳንት ሃብያሪማናን መንግሥት ስታስታጥቅ የከረመችው ፈረንሳይ በግድያዎቹ የመጀመሪያ ቀናት ጭምር ከሁቱ መንግስት ጋር መተባበሯን ቀጥላ ነበር። RPFንም ለፍራንስ አፍሪካ ግንኙነት ጠንቅ ነው ብላ ታስብ ነበር።
በመጨረሻ ተመድ ግንቦት 17/1994 በሩዋንዳ ላይ የጦር መሳሪያ እገዳ ጣለ፣ UNAMIRን ለማጠናከር ውሳኔ አሳለፈ። እስከ ሰኔ ድረስ ግን አዲስ ወታደሮች ሩዋንዳ መግባት አልጀመሩም ነበር።
ይህ ሁሉ እስኪሆን አብዛኛው ግድያ ተፈጽሞ ነበር።
የምዕራቡ ዓለም የሚዲያዎችም ጭፍጨፋውን “ የእርስ በርስ ” ወይም “ የጎሳ ” ጦርነት በማለት ነው ሲገልጹ የቆዩት።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
Rwandan genocide
Apr 7, 1994 – Jul 15, 1994
Al Jazeera
@tikvahethiopia
#DStv
🔥ከባድ ትንቅንቅ የማያጣው ማንቸስተር ዩናይትድ ከ ሊቨርፑል ዜሬ ከሰዓት 11፡30 በ ኦልድትራፎርድ ይገናኛሉ🔥
🤔ዩናይትድ ወደ አሸናፊነት መንገድ ይመለሳል?
እንዳያመልጥዎ…
👉 ይህንን ድንቅ ፍልሚያ ጨምሮ ሌሎች የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎችን በቀጥታ በዲኤስቲቪ ሱፐርስፖርት ይመልከቱ።
👉 ዛሬውኑ ፓኬጅዎን ያሳድጉ። ጨዋታዎችን ከትንታኔ ፣ ከተጫዋች ብቃት እስከ ቡድን ወኔ በሱፐርስፖርት ልዩ በቀጥታ ይከታተሉ!
የዲኤስቲቪ አገልግሎቶችን ለማግኘት ከታች ያለውን ሊንክ ይጫኑ!
👇
https://mydstv.onelink.me/vGln/eth2
#PremierLeagueOnDStv #ሁሉምያለውእኛጋርነው #DStvEthiopia #DStvSelfServiceET
#Update
ኦክሎክ ሞተርስ “ስሜን አጥፍቷል” ላለው ቱሪስት ታክሲ ማኀበራት ምን ምላሽ ሰጠ ?
ኦክሎክ ጀነራል ትሬዲንግ ኃላ/የተ/የግ/ማኀበር ፤ በቱሪስት ታክሲ ማኀበራት " የስም ማጥፋት ዘመቻ ተፈጽሞብኛል " በማለት ኮንኗል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ፤ የኦክሎክ ጀነራል ትሬዲንግ ኃላ/የተ/የግ/ማኀበር ሥራ አስኪያጅ አቶ ታመነ ካሳሁንን የድርጅቱ ስም ጠፋ ያሉበትን ምክንያት ጠይቋል።
አቶ ታመነ ካሳሁን ፦
“ ‘ሕዝቡ ከ1.2 ሚሊዮን በላይ ድሃዎችን እያስለቀሰ ነው። 1.2 ቢሊዮን ብር ወስዶ እየሰራበት ነው’ የሚለው በሕዝብም በመንግሥትም ዘንድ ተቀባይነት እንድናጣ ለማድረግ የተደረገ ሩጫ ነው። ” ብለዋል።
በተጨማሪ ፦
“ ... እነዚህ ሰዎች (1.2 ቢሊዮን ብር ከፈሉ የተባሉት) የከፈሉት 110 ሚሊዮን ብር ነው። ያመጣነው መኪና ግቢ ውስጥ እንኳ የቆመው ብቻ 200 መኪና ነው። 200 መኪና በትንሹ እንኳ በ1 ሚሊዮን 950 ሺሕ ብር ስናባዛው ከ400 ሚሊዮን በላይ ነው። ስለዚህ የዛን ያህል ዋጋ ከፍለን ስናመጣ እኛ ከእነርሱ (ከማኀበራቱ) የተቀበልነው ገንዘብ ግን ያን ያህል (110 ሚሊዮን ብር) ነው ” ሲሉ ገልጸዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ፦
- ኦክሎክ #ከሄሎ_ታክሲ ጋር የነበረው ውል ምንድን ነው ? ለምን ተቋረጠ ?
- የቱሪስት ታክሲ ማኀበራት አባላት ፥ “ ኦክሎክ በስማችን የመጣውን መኪና #እየሸጠ_ነው ” ስለሚለው ምን ምላሽ አላችሁ ? የሚሉና ሌሎችም ጥያቄዎች አቅርቧል። የኦክሎክ ሥራ አስኪያጅ በዚህ ላይ ምላሽ ሰጥተዋል።
በዝርዝር ያንብቡ👇
https://telegra.ph/Tikvah-Ethiopia-04-07-2
@tikvahethiopia
#SamiTech
አዳዲስ ላፕቶፕች ከአንድ ዓመት ዋስትና ጋር!!
@samcomptech
በአገልግሎት አሰጣጣችን ላይ እና በዕቃዎቻችን ጥራት ላይ ደንበኞቻችን ምስክሮቻችን ናቸው። ዛሬም ብዛትንም ጥራትንም ሳንቀንስ እያስተናገድን እንገኛለን።
ለቢሮዎች፣ ለተማሪዎች ፣ ለዲዛይን ባለሙያዎች ፣ ለጌመሮች ወ.ዘ.ተ
አቅምን ካገናዘቡ እስከ ቅንጡ ላፕቶፖች ይህ ቀረ ሳይሉ የሚያገኙበትን ሱቃችንን ይጎብኙ። የቴሌግራም ቻናሉን ይቀላቀሉ ባሉበት ሆነው ይዘዙን እናደርሳለን።
የዕቃዎች ዋጋ፣ ዓይነት እና አድራሻ ለማግኘት ይሄን 👉 @samcomptech ተጭነው በቴሌግራምው ማየት ይችላሉ።
@sww2844 0928442662 / 0940141114
https://maps.app.goo.gl/H3PM1NrTcQ4SWkK17
ፎቶ ፦ ላለፉት ዓመታት በእስር ላይ የነበሩት እና በቅርቡ ከእስር የተፈቱት የቀድሞው የ #ሜቴክ ዋና ዳይሬክተር ሜጀር ጄነራል ክንፈ ዳኘው ዛሬ መቐለ ገብተዋል።
መቐለ ሲደርሱ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
የፍትህ ሚኒስቴር የሜጄር ጄነራል ክንፈ ዳኘውና የቀድሞ የሶማሌ ክልል ፕሬዜዳንት አብዲ ኢሌ ክስ ተቋርጦ ከእስር የተፈቱት " ለዘላቂ የህዝብ ጥቅም ሲባል ነው " ማለቱ ይታወሳል።
Photo Credit - Demtsi Woyane
@tikvahethiopia
#ኢትዮጵያ
በነዳጅ የሚሠሩ እንዲሁም ሙሉ በሙሉ ውጪ ተገጣጥመው ወደ ሃገር ውስጥ በሚገቡ አውቶሞቢሎች ላይ የውጪ ምንዛሬ እቀባ ተደረገ።
የጉምሩክ ኮሚሽን በነዳጅ ከሚሠሩ እና ሙሉ በሙሉ ውጭ ተገጣጥመው ወደ ሃገር የሚገቡ አውቶሞቢሎች ላይ የውጪ ምንዛሬ እቀባ መጣሉን አሳውቋል።
ዕቀባው ያስፈላገበት ዋና ምክንያት ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሪክ እና በሃይብሪድ /በኤሌክትሪክ እና በነዳጅ/ የሚሠሩ ተሽከርካሪዎች ወደ ሃገር ውስጥ እንዲገቡ ለማበረታት ነው ተብሏል።
አሰራሩ ፥ የአረንጓዴ ልማትን ተግባራዊ ለማድረግ እና ለነዳጅ እና በነዳጅ ለሚሰሩ አውቶሞቢሎች ግዢ ይወጣ የነበረውን የውጪ ምንዛሬ ለመቀነስ ይረዳል ሲል ኮሚሽኑ አመልክቷል።
ይህ እቀባ #ቀጣይነት ሊኖረው እንደሚችል ተገልጿል።
በነዳጅ የሚሠሩ አውቶሞቢል ተሽከርካሪዎችን ወደ ሃገር ውስጥ የሚያስገቡ አስመጪዎችም ጥንቃቄ እንዲያደርጉ #ማሳሰቢያ ተላልፏል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃው ከገቢዎች ሚኒስቴር ነው ያገኘው።
@tikvahethiopia
#እንድታውቁት
በአዲስ አበባ ፤ ' መስቀል አደባባይ ' ከሚደረግ የመንግስት የድጋፍ ሰልፍ ጋር በተያያዘ ተዘግተው የነበሩ መገዶች ተከፍተዋል።
ሰልፉ #መጠናቀቁን ተከትሎ ተዘግተው የነበሩት መንገዶች ለተሽከርካሪ ክፍት ሆነዋል።
@tikvahethiopia
#ፊቼጨምባላላ
የፊቼ ጨምበላላ በዓል እየተከበረ ይገኛል።
የበዓሉ ዋነኛ መለያው ሰላም ፤ አንድነትና ፍቅር ሲሆን በዚህ በዓል ተጣሉ ሰዎች ይታረቃሉ ፤ ሃዘን ላይ የነበሩ ሰዎችም የሃዘን ልብሳቸውን ይቀይራሉ።
ከቀዬው ርቆ የነበረ ሰው ለፊቼ ጨምበላላ ወደቀዬው ይመለሳል። ለዚህ በዓል ተብሎ እርድ አይፈጸምም ፤ ስጋም አይበላም። ክብቶችን መምታትም ክልክል ነው። ላሞች ሳር የበዛበት መስክ ላይም እንዲሰማሩ ይደረጋል።
በሲዳማ ሕዝብ ዘንድ በፊቼ ጨምበላላ በዓል ወቅት ማረስ ነውር ሲሆን ለዚህም ምክንያቱ ደግሞ የፊቼ ጨምበላላ በዓል የሲዳማ ሕዝብ ብቻ ሳይሆን የተፈጥሮም ነው ተብሎ ስለሚታመን ነው።
በዓሉ የሲዳማ ሕዝብ ማንነቱን ከተረዳበት ጊዜ አንስቶ ሲከበር ቆይቷል። እንደ ሲዳማ የአገር ሽማግሌዎች " ፊቼ ጫምባላላ " መከበር ከጀመረ ከ1800 ዓመታት በላይ አስቆጥሯል።
መልካም በዓል !
@tikvahethiopia
ከተጠቀሱት የባንክ አማራጮች ወደ M-PESA ገንዘብ በመላክ እስከ 50 ብር ስጦታ እናግኝ!
M-PESA ላይ እንመዝገብ፣ በM-PESA እንገበያይ!
🔗የM-PESAን ሳፋሪኮም መተግበሪያ በዚህ ሊንክ እናውርድ ፡ https://play.google.com/store/apps/details?id=et.safaricom.mpesa.lifestyle
የቴሌግራም ቻናላችንን እዚህ እንቀላቀል 👉/channel/Safaricom_Ethiopia_PLC
ስለ አገልግሎታችን ማንኛውንም ጥያቄ ወይም መረጃ በቴሌግራም ቻናላችን /channel/Safaricom_Ethiopia_PLC 24/7 ማግኘት ይቻላል!
#MPESASafaricom #FurtherAheadTogether
#መቐለ
ዛሬ በመቐለ #ሰላማዊ_ሰልፍ የወጡ የመቐለ ዩኒቨርሰቲ ተማሪዎች በፖሊስ ድብደባና እስራት እንደተፈፀመባቸው ዶቼ ቨለ ሬድዮ ተማሪዎቹን ዋቢ በማድረግ ዘግቧል።
ተማሪዎቹ ተራዝሟል ያሉትን የመመረቂያ ግዜን በመቃወም ሰልፍ የወጡ ሲሆን የትግራይ ክልል የፀጥታ ኃይሎች ከፍተኛ ድብደባ እና እንግልት እንደፈፀሙባቸው ተናግረዋል።
10 ተማሪዎች መታሰራቸውም ተገልጿል።
ተማሪዎቹ ዛሬ ረፋድ 4 ሰዓት ከመቐለ ዩኒቨርሲቲ አሪድ ግቢ ተነስተው ያሏቸውን ቅሬታዎች ለማሰማት ወደ መቐለ ከተማ ጎዳናዎች ሰላማዊ ሰልፍ ባደረጉበት ወቅት ነው ድብደባና እስቱ የገጠማቸው።
ተማሪዎቹ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ ለምን #ተገደዱ ?
በተለያዩ ችግሮች #ለዓመታት ትምህርታቸው ሲስተጓገል ቆይቶ ዘንድሮ 2016 ለመመረቅ እየተጠባበቁ የነበረ ቢሆንም ፤ ዩኒቨርሲቲው ሌላ ተጨማሪ ዓመት መማር እንደሚጠበቅባቸው ከገለፀላቸው በኃላ ነው ሰልፍ የወጡት።
ከሰላማዊ ሰልፉ በፊት ግን ለዩኒቨርሲቲው በተደጋጋሚ ቅሬታቸውን ማቅረባቸውን እና ከዩኒቨርሲቲው ምላሽ አለማግኘታቸውን ለሬድዮ ጣቢያው ገልጸዋል።
@tikvahethiopua
#እንድታውቁት
ነገ በአዲስ አበባ መንገዶች ይዘጋሉ።
በአዲስ አበባ ' መስቀል አደባባይ ' ነገ #ቅዳሜ ከሚደረግ የድጋፍ ሰልፍ ጋር በተያያዘ መንገዶች እንደሚዘጉ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።
ከንጋቱ 11፡00 ሰአት ጀምሮ ሰልፉ እስኪጠናቀቅ ድረስ ፦
- ከቴዎድሮስ አደባባይ በብሄራዊ ቴአትር ወደ ወደ መስቀል አደባባይ ሚወስደው መንገድ ቴዎድሮስ አደባባይ
- ከኡራኤል አደባባይ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ኡራኤል አደባባይ ላይ
- ከቦሌ አቅጣጫ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው ኦሎምፒያ አደባባይ ላይ እና ታች እንዲሁም ግራና ቀኝ
- ከመስቀል ፍላወር ወደ ኦሎምፒያ የሚወስደው መንገድ ጋዜቦ አደባባይ ላይ
- ከጎተራ ማሳለጫ ወደ መስቀል አደባባይ አጎና ሲኒማ
- ከቅ/ቂርቆስ ቤ/ክርስቲያን በአዲሱ መንገድ ወደ መስቀል አደባባይ ለሚሄዱ ለገሀር መብራት
- ከሜክሲኮ ወደ መስቀል አደባባይ ቴሌ ለሚጓዙ ለገሀር መብራት
- ከጌጃ ሰፈር አቅጣጫ ወደ መስቀል አደባባይ ለሚመጡ ተሽከርካሪዎች ሰንጋተራ ትራፊክ መብራት ላይ
- ከሃራምቤ መብራት ወይም ከአምባሳደር ሲኒማ ወደ መስቀል አደባባይ ሃራምቤ መብራት ላይ
- ከብሔራዊ ቤተ መንግስት ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ብሔራዊ ቤተ መንግስት አጠገብ
- ከካዛንቺስ ሼል ወደ ባምቢስ የሚወስደው መንገድ ከዛንቺስ ሼል አጠገብ
- ከጁፒተር ሆቴል ወደ ECA ሚወሰደው መንገድ ባምቢስ ሳልኮት ህንፃ አጠገብ ለተሽከርካሪ #ዝግ ይሆናሉ ተብሏል።
አሽከርካሪዎች መንገዶቹ እንደሚዘጉ አውቀው አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ ፖሊስ ጥሪ አቅርቧል።
ከዚህ ባለፈ በተጠቀሱት መንገዶች ከዋዜማው ምሽት 12:00 ሰዓት ጀምሮ እስከ ሰልፉ ፍፃሜ ድረስ ተሽከርካሪ አቁሞ መሄድ ወይም ማሳደር ተከልክሏል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ የነገው የመስቀል አደባባይ ሰልፍ #መንግሥትን የሚደግፍ ሰልፍ መሆኑን ለማወቅ ችሏል።
@tikvahethiopia
የጥሪ ማሳመሪያ አገልግሎት በተጨማሪ የምዝገባ አማራጮች (Micro Packages) ቀረቡ!
ከ2ብር ጀምሮ የሳምታዊ ፣ የአስራ አምስት ቀናት እና ወርሃዊ የጥሪ ማሳመሪያ ጥቅል ለመመዝገብ ወደ 822 ወይም *822# በመደወል አልያም በ www.crbt.et ለአገልግሎቱ ተመዝግበው ሙዚቃዎችን ወይም መንፈሳዊ ዜማዎች ይግዙ!
#CRBT #Ethiotelecom #telebirr #RealizingDigitalEthiopia
#AddisAbaba
“ በለበሰው ሹራብ የኮፍያ ገመድ አንቀው ነው የገደሉት። ተሽከርካሪውን ይዘው ተሰውረዋል ” - የሟች ቤተሰብ
“ ተጠርጣሪዎቹን በቁጥጥር ሥር ለማዋል የተለያዩ ሥራዎች እየተሰሩ ነው ” - የአዲስ አበባ ፓሊስ
ወጣት ሶፎኒያስ አስራት የሚባል ሹሬር ማክሰኞ መጋቢት 24 ቀን 2016 ዓ/ም ከሌሊቱ 8 ሰዓት ገደማ ሰዎችን አሳፍሮ እንደወጣ አለሙለሱን፣ በመጨረሻም ሹፌሩን ገድለው ፣ ተሽከርካሪውን ይዘው እንደተሰወሩ፣ ገዳዮቹ አስካሁን #እንዳልተያዙ፣ በዚህም መሉ ቤተሰቡ መራራ ሀዘን ውስጥ መሆናቸውን የሟች ቤተሰብ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።
የሟች ቤተሰብ በሰጡት ቃል፣ “ ከላፍቶ ነበር መነሻውን ያደረገው (ልዩ ስሙ መስቀልኛ የሚባለው አካባቢ ናሆም ሆቴል የሚባል አለ)። ከዚያ ነበር ሦስቱንም ተሳፋሪዎች ማክሰኞ ከሌሊቱ 8 ሰዓት አካባቢ ያሳፈራቸው። መዳረሻቸውን ‘ቦሌ ሚካኤል’ ብለው ነበር መሳፈር የፈለጉት ” ብለዋል።
“ ትንሽ ወረድ እንዳለ/እንደተጓዘ ከእኔ ጋር ተገናኝተናል። አብረን የምንሰራበት ቦታ ነው። ሦስት ሰዎች እንዳሳፈረ አይቻለሁ” ያሉት የሟች ቤተሰብና የዓይን እማኝ፣ “ሶፊ ወዴት ነህ ስለው ‘መጣሁ። ቦሌ ሚካኤል አድሻቸው ልምጣ’ አለኝ። በቃ ደርሰህ ና ስራ የለም እንገናኛለን ተባባልን። በዛው እንደወጣ አልተመለሰም ” ሲሉ ሁነቱን አስረድተዋል።
አክለውም፣ ጠዋት ላይ ላፍቶ ፓሊስ ጣቢያ ሲያመለክቱ የቃሊቲ ፓሊስ ጣቢያ እንዲጠይቁ እንደነገሯቸው፣ ቃሊቲ ፓሊስ ጣቢያ ሲጠይቁ ፓሊስ ስለተፈላጊው ሰው ሙሉ መለያ መረጃ ከጠየቃቸው በኋላ “ እንግዲህ ጠንከር በሉ። ኤቲኤሙን አግኝተናል። አሁን ያለው ጳውሎስ ሆስፒታል ነው። አዲስ አበባ ፓሊስ ሂዳችሁ ቃል ሰጥታችሁ ትወስዳላችሁ ” ብለው #መገደሉን እንዳረዷቸውም ተናግረዋል።
“ ማሰልጠኛ ተሻግሮ ወደ አቦ ቤተክርስቲያን በሚወስደው መንገድ ዳር ላይ ነው ሞቶ የተገኘው። ፓሊሶች አስከሬኑን ያነሱት ጠዋት 12 ሰዓት ላይ ነው። ከጥበቃ ሥራ የሚመለሱ አንድ አባት ናቸው በወደቀበት አግኝተውት ጥቆማ አድርገው ፓሊስ የሄደው ” ነው ያሉት።
“ በለበሰው ሹራብ የኮፍያ ገመድ አንቀው ነው የገደሉት። ተሽከርካሪውን ይዘው ተሰውረዋል ” ያሉት የሟች ቤተሰብ፣ ማንም ጋ ፀብ እንዳልነበር ገልጸው፣ ሙሉ ቤተሰቡ ሀዘን ላይ እንደሆነ፣ ቢያንስ ገዳዮቹ እንዲያዙ ፓሊስ ርብርብ እንዲያደርግ ጠይቀዋል።
ስለጉዳዩ ምላሽ እንዲሰጡ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ ያቀረበላቸው የአዲስ አበባ ፓሊስ ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ምክትል ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ፣ ስለሟች ሁኔታ ጠይቀው ጉዳዩን እንዲያጣሩ ፋታ እንዲሰጣቸው ከጠየቁ በኋላ በሰጡት ቃል ፣ “ አረጋግጫለሁ። ፓሊስ ሥራ ላይ ነው ያለው። የተለያዩ ዝርዝር መረጃዎችን ለመግለጽ የሚያስፈልግ የተለያዩ ሥራዎች እየተሰሩ ነው ተጠርጣሪዎቹን ለመያዝ ” ብለዋል።
“ መረጃ እየተሰበሰበ ነው ያለው ” ያሉት ኮማንደር ማርቆስ፣ “ አንተ ማክሰኞ ሌሊት 8 ሰዓት አልከኝ እንጂ፣ ስጠይቅ ረቡዕ ለሐሙስ አጥቢያ 8 ሰዓት ላይ ነው ወንጀሉ የተፈጸመው የሚል መረጃ ነው ያለው። ተጠርጣሪዎቹን በቁጥጥር ሥር ለማዋል የተለያዩ ሥራዎች እየተሰሩ ነው ያሉት ” የሚል ማብራሪያ ሰጥተዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ በበኩሉ ወንጀሉ የተፈጸመው ማክሰኞ ሌሊት 8 ነው ያሉት የሟች ቤተሰብ በስህተት እንዳይሆን በሚል በድጋሚ የጠየቀ ሲሆን፣ ማክሰኞ ለረቡዕ ሌሊት 8 ሰዓት እንደሆነ፣ ረቡዕ ማታ ጣቢያ አስክሬን እንዳገኙ አስረድተዋል።
መረጃው በአ/አ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ኢዮብ ትኩዬ የተዘጋጀ ነው።
@tikvahethiopia
#forfreemarket
እነዚህን👆የቤት ዕቃዎች በሱቃችን በቅናሽ ዋጋ እየተሸጡ ነው። የነዚህንና ሌሎች በርካታ ዕቃዎቻችንን ዋጋ ይሄንን ተጭነው ማየት ይችላሉ። 👉 /channel/forfreemarket
አድራሻ፦ ፒያሳ ጣይቱ ሆቴል ጊቢ ውስጥ ቢሮ ቁ04 ፣ መገናኛ መተባበር ሕንፃ 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁ316 ፣ ሳር ቤት ካናዳ ኤምባሲ ፊትለፊት ሸዋ ሱፐርማርኬት ያለበት ህንፃ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁ11
ለማዘዝ እነዚን ቁጥሮች ይጠቀሙ ፦ 0911100302 / 0911887579
በቴሌግራም ለማዘዝ ➡️ @Akdat
ሚዲያ የሩዋንዳውን የዘር ጭፍጨፋ (ጄኖሳይድ) እንዴት አቀጣጠለ ?
በ100 ቀናት ከ800,000 እስከ 1,000,000 ቱትሲዎችና ለዘብተኛ የሚባሉ ሁቱዎች ባለቁበት የሩዋንዳው የዘር ጭፍጨፋ/ጄኖሳይድ ሚዲያዎች ከፍተኛ ድርሻ ነበራቸው።
እንዴት ?
- ራዲዮ-ቴሌቭዥን ሊብሬስ ዴስ ሚልስ ኮሊንስ (RTML) እንዲሁም መንግታዊው ' ሬድዮ ሩዋንዳ ' በቱትሲዎች ላይ በመላ ሀገሪቱ ጥላቻ እንዲፈጠርና የሩዋንዳ ጄኖሳይድ እንዲፈፀም ዋና አቀጣጣይ ነበሩ።
- RTML ሚዲያ በወቅቱ በብዙ ወጣቶች ዘንድ ተደማጭነት የነበረው ነው። ጣቢያው በወጣቶች ዘንድ እጅግ የሚወደዱ ሙዚቃዎችን እያስተላለፈ #በመሃል ያቋርጠውና ቱትሲዎችን በመጥቀስ " እነዚያ ሰዎች እጅግ ቆሻሻ ቡድን ናቸው " የሚሉ አዋራጅና ቀስቃሽ መልዕክቶችን ያስተላልፋል። በስርጭቶቹ ውስጥ "#በረሮዎች" እና "#እባቦች" የሚሉ ቃላት በተደጋጋሚ ጥቅም ላይ ያውላል።
- RTML ሚያዚያ 6 /1994 ፕሬዜዳንት ጁቬናል ሃብያሪማና የነበሩበት አውሮፕላን ተመቶ ሲወድቅ በቅድሚያ ድርጊቱን የፈፀመው RPF ነው ብሎ የፈረጀ እና ንፁሃንን ለጭፍጨፋ ያመቻቸ ሚዲያ ነው።
- በጭፍጨፋው ወቅት ጨፍጫፊዎቹ በአንድ እጃቸው ሬድዮ በአንድ እጃቸው ደግሞ #ቆንጨራ ይዘው ነበር ሲንቀሳቀሱ የነበሩት። በዚህም ወቅት RTML እና ሬድዮ ሩዋንዳ ቱትሲዎች እና እነሱን የሚሸሽጉ ሁቱዎች እንዲገደሉ ያሉበትን አድራሻ ጭምር ሲገልጹ ነበር።
- ሚዲያዎቹ ጎረቤት በጎረቤቱ ላይ እንዲነሳ እና ቱትሲ የሚባሉትን በጠቅላላ እንዲያጠፏቸው ሲሰብኩ ነበር። በዚህም ብዙዎቹ ሁቱዎች የገዛ ጎረቤታቸውን አንዳንዶቹ ከቱትሲ ጋር የተዛመዱ #ዘመዶቻቸውን ጭምር ጨፍጭፈዋል።
- ሚዲያዎቹ የተለያዩ አነሳሽ ቃላቶች በመጠቀም ቱትሲዎች #እንዲጠሉ ፣ #እንዲገደሉ ሰዎችን ሲያበረታቱ ነበር። ትንንሽ ልጆች ፣ ታዳጊዎች ሳይቀሩ በራሳቸው ወገን #ጥላቻ እንዲሞሉ አድርገዋል።
- የሁቱ ሚዲያዎች በቀደመው ጊዜ #ቱትሲዎች ሀገሪቱ ውስጥ ትልቅ ስፍራ ይዘው በነበረበት ወቅት " በደል ፈፅመዋል " በማለትና " የሀገሪቱ ችግሮች እነሱናቸው እስከመጨረሻ ካልጠፉ በቀር ምንም መፍትሄ የለም " በማለት ሁቱዎችን ይቀሰቅሱ ነበር።
በነገራችን ላይ ከጭፍጨፋው ጅማሮ #በፊትም የሀገሪቱ መንግሥት ሚዲያዎችን በመጠቀም ሰፊ የሆነ የጥላቻ ፕሮፖጋዳንዳ ሲሰራ ቆይቷል።
በተለይ ቱትሲዎችን ከRPF ኃይል ጋር በማገናኘት ሁቱዎች ውስጣቸው በከፍተኛ ጥላቻ ታውሮ የገዛ ወገናቸውን እንዲጨፈጭፉ ሰርቷል።
አጠቃላይ በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ የታየ እጅግ አስከፊው የዘር ጭፍጨፋ የአንድ ሌሊት ውጤት አልነበረም፤ በሂደት የመጣ እንጂ።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
Rwandan genocide
Apr 7, 1994 – Jul 15, 1994
@tikvahethiopia
#ሩዋንዳ
ዛሬ የሩዋንዳ የዘር ጭፍጨፋ (ጄኖሳይድ) 30ኛ ዓመት መታሰቢያ ነው።
በ1994 እ.አ.አ ሩዋንዳ ውስጥ በቱትሲ ጎሣ ላይ የደረሰው የዘር ማጥፋት ዘመቻ በሰው ልጆች ዘመናዊ ታሪክ ውስጥ ከደረሱት አሰቃቂ የዘር ጭፍጨፋዎች አንዱ ነው።
በ100 ቀናት ገደማ ውስጥ ብቻ ከ800,000 እስከ 1,000,000 የሚሆኑ ሰዎች እንዳለቁ ይገመታል።
ከተገደሉት ሰዎች መካከል አብዛኞቹ ቱትሲዎች ናቸው፤ ሆኖም በጭፍጨፋው ለመካፈል ፈቃደኛ ያልሆኑ የሁቱ ጎሣ አባላትም የግድያው ሰለባ ሆነዋል።
በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ ሴቶች ተደፍረዋል።
የሩዋንዳ ጄኖሳይድ እንዴት ተፈፀመ ?
- በ10 ሚሊዮን የሚቆጠሩ የሩዋንዳ ዜጎች ለዘመናት እራሳቸውን እንደ #አንድ ነው ሲያዩ የኖሩት።
- በ1916 (እ.አ.አ) ቤንጂየም ሩዋንዳን በቅኝ ግዛት ትይዛታለች። በኃላም በቁጥር የሚበዙትን ሁቱዎች በቁጥር ከሚያንሱት ቱትሲዎች የሚለዩበትን አዲስ ሲስተም የመታወቂያ ወረቀት በመስጠት ዘረጋች። (የብሄር መታወቂያ አከፋፈለች)
- ቱትሲዎቹ በቤልጂየምዎቹ ፦
° በትምህርት ፣
° በስራ፣
° በስልጣን ከፍ ያለ ቦታ እንዲሰጣቸው ተደረገ። ሁቱዎቹ ግን ብዙ ቁጥር ኖሯቸው የትምህርት ፣ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ተነፈጋቸው።
- ቤንጂየሞቹ ቱትሲዎቹ ከብዙሃኑ ሁቱዎቹ የተሻሉ አድርገው እንዲሳሉ አደረጉ።
- በ1959 ሩዋንዳ ነጻነቷን ስታገኝ ሁቱዎች በማመፅ እና የመንግሥትን ስልጣን በመያዝ #ቱትሲዎችን ገደሉ ፣ ከሀገር እንዲሰደዱ አደረጉ። በዚህ ወቅት በመቶ ሺዎች ወደ ጎረቤት ሀገር ተሰደዋል።
- በ1990 በቱትሲ የሚመራው የRwanda Patriotic Front (RPF) ከኡጋንዳ በመሆን በሁቱ በሚመራው መንግሥት ላይ ጥቃት ከፈተ። ይህም የእርስ በእርስ ጦርነት መጀመሪያ ሆነ። በዚህ ወቅት ፈረንሳይ የሩዋንዳን መንግሥት ታስታጥቅ፣ ታሰለጥን ፣ ትደግፍ ነበር። ሩዋንዳም በፕሬዜዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ አማካኝነት በፖል ካጋሚ የሚመራውን ኃይል ትደግፍ ነበር።
- በሩዋንዳ መንግሥትና በRPF ኃይል መካከል የነበረው ጦርነት በ1993 የሰላም ስምምነት እንዲቆም ተደረገ። የUN ኃይልም ስምምነቱ እንዲከበር ለማመቻቸት ዘንድ ወታደራዊ ኃይሉን ላከ።
- በዚህ ሁሉ ጊዜ ውስጥ በሁቱ እና በቱስቲዎች መካከል ያለው ውጥረት እጅግ በጣም እየከፋ ነበር የሄደው። የጥላቻ ፕሮፖጋንዳውን ከፍ ብሎ ነበር። በእርስ በእርስ ጦርነቱ ወቅት የሩዋንዳ መንግሥት RPFን እንደ ጠላት፣ እንደ ሀገር ካጅ፣ ባንዳ፣ እያደረገ ፕሮፖጋንዳ ሲሰራ ነበር።
- ሚያዚያ 6 ቀን 1994 የሁቱ ጎሳው ፕሬዜዳንት ጁቬናል ሃብያሪማና ተሳፍረውበት የነበረው አውሮፕላን ኪጋሊ በሚገኝ ኤፖርት አካባቢ ተመትቶ ወደቀ። ፕሬዜዳንቱም ህይወታቸው አለፈ። በወቅቱ የቡሩንዲው ፕሬዝዳንት ሳይፕሪን ንታያሚራ አብረዋቸው ነበሩ እሳቸውም ሞቱ።
- ፕሬዚዳንቱን የገደላቸው ማን እንደሆነ በግልጽ ባይታወቅም ሁቱዎቹ የቱትሲ አማፂ ቡድን ነው የፈፀመው ብለው በሚዲያ አስወሩ። ሁቱዎች እየወጡ ቱትሲዎችን እንዲገድሉ በሚዲያ ጥሪ አቀረቡ።
... በቃ #ግድያው ተጀመረ። ከ800 ሺህ እስከ 1,000,000 ቱትሲዎች እና ለዘብተኛ ሁቱዎች አለቁ። ከ100 ቀን በኃላ የRPF ኃይል ወደ ኪጋሊ ሲቃረብ ግድያው አቆመ ሁቱዎቹም መሸሽ ጀመሩ፣ በተለይ ሲገድሉ ሲያስተባብሩ የነበሩት ሀገር ጥለው ወጡ።
ሚዲያዎች ? የውጭ ሀገር ኃይሎች ? ተመድ በዚህ ውስጥ ምን ሚና ነበራቸው ? በቀጣይ ፅሁፍ እንዳስሳለን።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
Rwandan genocide
Apr 7, 1994 – Jul 15, 1994
@tikvahethiopia
#ትግራይ #መምህራን
" ጥያቄያችን ፍትሃዊ ምላሽ ካላገኘ ወደ ቀጣይ እርምጃ እንገባለን " - የትግራይ መምህራን ማህበር
የትግራይ መምህራን ማህበር ፤ ጥያቄያችን ፍትሃዊ መልስ ካላገኘ በምክር ቤት አስወስነን ለቀጣይ ትግል እንዘጋጃለን " አለ።
የትግራይ መምህራን ማህበር ፤ ጊዚያዊ አስተዳደሩ የ5 ወራት ውዙፍ ደመወዝ ለመክፈል የገባው ቃል እስከ አሁን አልተገበረም ብለዋል።
መምህራን ውዙፍ ደመወዝ ባለመከፈላቸው ምክንያት ለከባድ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ተጋልጠዋል ሲል አሳውቋል።
ማህበሩ ፤ ጊዚያዊ አስተዳደሩ የትግራይ መምህራን ካለቸው ያልተከፈለ የ17 ወራት ውዙፍ ደመወዝ መካከል የ5 ወራት እንደሚከፈል በወርሃ ጥር መግባባት ተደርሶ እንደነበር አስታውሷል።
ነገር ግን እስከ አሁን አለመተግበሩ እንዳሳዘነው ገልጿል።
መምህራኑ ያላቸው 17 ወራት ውዝፍ ደመወዝ አለመከፈላቸው እየታወቀ ፣ ከጦርነቱ በፊት ከደደቢት ማይክሮ ፋይናንስ የወሰዱት ብድር ወለድ የወለድ ወለድና ቅጣት እንዲከፍሉ እየተገደዱ መሆኑን የገለጸው ማህበሩ " ጉዳዩ መንግስታዊ መፍትሄ ያሻዋል " ብሏል።
" ፍትሃዊው ጥያቄያችን ፍትሃዊ የሆነ መላሽ እንዲያገኝ ተደጋጋሚ መግለጫ አውጥተናል ፤ ከሚመለከተው አካል ጋር ተወያይተናል ነገር ግን ምልስ የማያገኝ ከሆነ በማህበሩ ምክር ቤት በማስወሰን ለቀጣይ እርምጃ እንዘጋጃለን " ሲል ማህበሩ አስጠንቅቋል።
' ቀጣይ እርምጃው ምን እንደሆነ ' ግን በግልፅ አላብራራም።
መረጃው በመቐለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ተዘጋጅቶ የተላከ ነው።
@tikvahethiopia
#ቅሬታ
“ እኔ 1.5 ሚሊዮን ብር ነው #የተጨመረብኝ። እውነት ድርጅቱ ጨምሮበት ነው ወይስ የድሃ እንባ ፈልጎ ነው ? ”- እያለቀሱ ቅሬታ ያቀረቡ ቆጣቢ እናት
2012 ዓ.ም መጨረሻ አካባቢ በኦክሎክ ጀነራል ትሬዲንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኀበር አማካኝነት መኪና ለማስመጣት ገንዘብ ሲቆጥቡ የነበሩ ከ40 በላይ በሆኑ ማኀበራት ሥር የሚገኙ ከ2 ሺህ 800 በላይ ቆጣቢዎች፣ ውል የገባላቸውን መኪና አስመጪ ማኀበሩ በውሉ መሠረት መኪናውን እንዳላቀረበላቸው ገልጸዋል።
ከቅሬታ አቅራቢዎቹ መካከል አንዱ ቆጣቢ፣ “ እኔ በሥነ ስርዓት መረጃ አለኝ። በእኛ ስም እየመጣ እየተሸጠ ነው። ለዚህ እኔ ምስክር ነኝ ” ሲሉ ኦክሎክ ጀነራል ቲሬዲንግን ኮንነዋል።
ሌሎች ቅሬታ አቅራቢዎች በሰጡት ቃል ምን አሉ ?
➡️ አንድ ቅሬታ አቅራቢ፣ “ ገንዘባችንን ሰጥተን ለማኝ እየሆንን ነው። ገንዘባቸውን ከፍለው እንደገና የጥበቃ ሰራተኛ ሆነው ተጠግተው መኪና ያገኙ ራሱ አሉ ” ብለዋል።
➡️ ሌላኛው አባት በበኩላቸው፣ “ መኪናውን የሚጠብቁ ሁለት ልጆች አሉኝ። ገናኮ ለየትኛው እንደምሰጥ እያሰብኩ ነው ያለሁት” ሲሉ የነበራቸውን ተስፋ አስረድተው፣ “ ጎዳና ላይ ከምታድር ድሃ መቀነቷን ፈትቶ እንደመውሰድ ነው። ችግር ካለ ስብስቦ ሊጠይቀን ይችል ነበር። ግን በስማችን መነገድ ነው የፈለገው ” ብለዋል።
➡️ ሌላኛዋ ቆጣቢ በበኩላቸው ፦
“ ውላችን ከ3 እስከ 6 ወራት፣ ካልሆነ ደግሞ እስከ 1 ዓመት ነበር፣ 60 ሺሕ ከፍለን የሚለው። 25 በመቶ መኪናው አገር ውስጥ ከገባ በኋላ ገንዘብ እንከፍላለን የሚል ነው ውላችን ላይ የነበረው። 60 ሺሕ ከፍለን እያለ 2013 ዓ/ም ላይ 25 ፐርሰንት ክፈሉ ተብሎ የመኪናውን ዋጋ 25 በመቶ ስንከፍል፣ እኔ ተመዝግቤ የነበረው መኪና 520 ሞዴል ነበር። የመኪናው ዋጋ 520 ሺሕ ብር ነበር።
በመካከል 25 በመቶ ክፈሉ ‘የቻንሲና የሞተር ቁጥር መጥቷል’ ተብሎ ተከፈለ። ነገር ግን ‘ይህን መኪና ፋብሪካው ማምረት ስላቆመ 690 ሺሕ የሚመረተውን መኪና ቀይሪ’ ተብዬ 690 ሺሕ ብር የመኪናውን 25 ፐርሰንት 2013 ዓ/ም ኀዳር ወር ከፍዬ እየጠበኩ ሁለት ዓመታት ተቆጠሩ።
በ2014 ዓ.ም ከ2,800 በላይ አባላት በተገኙበት ኦሮሚያ የባህል አዳራሽ ተሰብስቦ ‘ከጠቅላይ ሚኒስቴር ቢሮ የመጣሁ ነኝ መኪናችሁን 1 ሳምንት ባልሞላው ጊዜ ውስጥ ተውስዳላችሁ። እንባችሁ ታብሷል ” ያላቸው አካል እንደነበር ገልጸው፣ ምንም መፍትሄ ስላልተገኘ፣ መንግሥት ይዳኘን " ሲሉ ጠይቀዋል።
➡️ አንዲት እያለቀሱ ቅሬታቸውን ያቀረቡ እናት በመጀመሪያ የነበረውን ውል መሠረት በማድረግ ተስማምተው እንደገቡ ገልጸው፦ “ ሁለት ወራት ጠበቁና 35፣ ‘45 ፐርሰንት ጨምሩ’ አሉን። ያን አድርገን ሳንጨርስ (ተበድረን ያስገባነውን ጉድ) መልሰው ሦስት ወራት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ‘400 ሺሕ ብር ጨምሩ፣ አበዳሪ ተገኝቷል በሁለት ወራት ውስጥ ገጣጥመን እናስገባለን’ አሉ። እኔ 1.5 ሚሊዮን ብር ነው የተጨመረብኝ። እውነት ድርጅቱ ጨምሮበት ነው ወይስ የድሃ እንባፈልጎ ነው?። አልገባኝም። #መንግሥት_ይዬን ። ” ሲሉ እያለቀሱ ቅሬታ አቅርበዋል።
➡️ ሌላኛው ቆጣቢ በበኩላቸው፣ “ ትዳራችንን ልናፈርስ ጫፍ ላይ ደርሰናል። አብዛኞቻችን ደግሞ የተሸወድነው የመንግሥት ባለስልጣንና ባንክ ቁጭ አድርጎ ቃል ሲገባልን ነው ” ነው ያሉት።
#TikvahaFamilyAddisAbaba
@tikvahethiopia
#ኩሽ #ሴራሊዮን
የሴራሊዮን መንግሥት በአገሪቷ በተንሰራፋው ‘ #ኩሽ / Kush ’ እየተባለ በሚጠራው የአደንዛዥ እፅ ምክንያት ብሔራዊ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አወጀ።
' ኩሽ ' የተለያዩ ሱስ የሚያስይዙ ግብዓቶችን በመደባለቅ የሚሰራ አደገኛ እፅ ሲሆን ለዓመታት በአገሪቷ ተንሰራፍቶ ይገኛል።
በአደንዛዥ እጹ ውስጥ ከሚጨመሩ ግብዓቶች መካከል አንዱ የተፈጨ #የሰው_አጥንት ነው።
በዚህም ምክንያት #ከመቃብር ውስጥ አፅም ለማውጣት የሚቆፍሩ #ሱሰኞችን ለማስቆም የጸጥታ አካላት በመካነ መቃብር ሥፍራዎች የሚያደርጉትን ጥበቃዎች አጠክረው ቆይተዋል።
የሴራሊዮን ፕሬዚደንት የሆኑት ጁሊየን ማዳ ባዮ አስተዳደራቸው አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲያውጅ ያስገደደውን ይህንን እፅ / ኩሽ “ የሞት ወጥመድ ” ሲሉ የገለጹት ሲሆን በአገሪቷ ላይም የህልውና ቀውስና ስጋት ፈጥሯል ብለዋል።
ፕሬዚደንት ባዮ ፤ በእፁ ምክንያት የሚሞቱ ሰዎች ቁጥርም እንዳሻቀበ ተናግረዋል።
በመሆኑም በ ' ኩሽ ' እፅ ምክንያት የሚደርሰውን ቀውስ ለመከላከል በሀገሪቱ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ታውጇል ፤ ብሔራዊ ግብረ ኃይል እንዲቋቋምም መደረጉን ቢቢሲ አስነብቧል።
ፎቶ/ቪድዮ ፦ ቻናል 4 እና አፍሪካ ኒውስ (ፋይል)
@tikvahethiopia
#Update
ወጣት ሶፎኒያስ አስራትን ገድለው ተሽከርካሪውን ዘርፈው የተሰወሩ ማንነታቸው ያልታወቁ ወንጀል ፈፃሚዎችን በ48 ሰዓት ውስጥ ከዘረፉት ተሽከርካሪ ጋር በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያጣራ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል።
ሟች ወጣት ሶፎኒያስ መጋቢት 24/2016 ዓ/ም ከንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 ናሆም ሆቴል አካባቢ ከሌሊቱ 8፡00 ሰዓት ላይ ማንነታቸው የማይታወቁ ሦስት ግለሰቦችን አሳፍሮ ወደ ቦሌ ሚካኤል ለማድርስ መሄዱን ጉዳዩን ለመከታተል የተቋቋመው የፖሊስ የምርመራና የክትትል ቡድን አባላት ባደረጉት ክትትል አረጋግጠዋል።
ወንጀል ፈፃሚዎቹ ወንጀል ለመፈፀም አቅደው እና ተደራጅተው የትራንስፖርት አገልግሎት ፈላጊ መስለው ሹፌሩን በመቅረብ ከተሳፈሩ በኋላ አንገቱን በገመድ አንቀው በመግደል አስክሬኑን በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 አሽከርካሪዎች ማሰልጠኛ አካባቢ ወደ አቦ ቤተክርስቲያን በሚወስደው መንገድ ላይ በመጣል አይነቷ ቪትዝ የሴሌዳ ቁጥር ኮድ 2A 93488 ተሽከርካሪ ጨምሮ 2 ሞባይል ስልኮችን ዘርፈው ይሰወራሉ፡፡
ፖሊስ ሌት ተቀን ባደረገው ብርቱ ክትትል ወንጀል ፈፃሚዎቹ የሰረቁትን ተሽከርካሪ ለመሸጥ እየተስማሙ መሆኑን በበቂ ማስረጃ ካረጋገጠ በሗላ ክትትሉን በመቀጠል ሦስቱን ዋና ወንጀል ፈፃሚዎች የሰረቁትን መኪና በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 ልዩ ቦታው ቦሌ ቡልቡላ አካባቢ ለመሸጥ እየተደራደሩ እንዳለ በቁጥጥር ስር በማዋል የተሰረቀችውን መኪና ፣ 2 ሞባይል ስልኮችን ልዩ ልዩ ኤግዚቢቶችን ይዞ ምርመራውን መቀጠሉን ገልጿል።
ፖሊስ ባደረገው ክትትልና ምርመራ ማንነታቸው የማይታወቁ ወንጀል ፈፃሚዎችን በ48 ሰዓት ጊዜ ውስጥ በመለየት 3 ዋና ወንጀል ፈፃሚዎችንና 3 ግብራበሮቻቸውን በቁጥጥር ስር ማዋሉ ታውቋል፡፡
የምርመራ ሥራው እንዳበቃ የፍርድ ሂደት ውጤቱን በቀጣይ ለህዝብ እንደሚገለፅ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል።
@tikvahethiopia
የኢድ አልፈጥር በዓል መቼ ነው ?
የ #ኢድ_አልፈጥር በዓል ጨረቃ በመጪው ሰኞ ማታ ከታየች #ማክሰኞ ካልታየች ደግሞ #ረቡዕ አንደሚከበር የፌዴራል ጠቅላይ ሸሪዓ ፍርድ ቤት ዛሬ ባወጣው መግለጫ አሳውቋል።
@tikvahethiopia
#እንድታውቁት
የደብር ብርሃን - ደሴ ዋና የፌዴራል መንገድ ከዛሬ መጋቢት 28/2016 ዓ.ም. ጀምሮ ለመንገደኞች ክፍት እንደሚሆን የማዕከላዊ ሸዋ ኮማንድ ፖስት ገልጿል።
ከፀጥታ ጋር በተያያዘ ከየካቲት 16 /2016 ዓ.ም አንስቶ ተቋርጦ የቆየው ይኸው መንገድ ከዛሬ አንስቶ ለህዝብ ትራንስፖርት ክፍት ይደረጋል ተብሏል።
@tikvahethiopia
#BK_COMPUTERS
ማንኛውንም አይነት አዳዲስ ላፕቶፖች ዱባይ ዩዝድ ላፕቶፖች ዴስክ ቶፖችን ጨምሮ ከብዛት እና ከታላቅ ቅናሽ ጋር ያዘንላቹ መተናል። ቢሮዎች፣ ለተማሪዎች፣ ለግሪፊክስ ዲዛይን ባለሙያዎች፣ ለጌመሮች እንዲሁም ለጨረታ የሚሆኑ በጥራት እና በ ብዛት ከ1 አመት ዋስትና ጋር እኛ ያገኛሉ
ለተጨማሪ መረጃ እና የላፕቶፕ አማራጮችን ለማየት የቴሌግራም ፔጃችንን Join ያድርጉ።
👉 /channel/BKComputers
Inbox @bkcomputer27
አድራሻ ፦ አዲስ አበባ መገናኛ ሲቲ ሞል ከመሰረት ደፋር ህንፃ አጠገብ 1 ፎቅ ላይ እንገኛለን። 0911448148/ 0955413433 we make IT easy!
#መቐለ
" ዲግሪ ለመያዝ 8 ዓመታትን መማር #ፍትሃዊ አይደለም " - ተማሪዎች
ዛሬ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ አደባባይ የወጡ የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በፖሊስ በኃይል እንዲበተኑ ተደርገዋል።
ተማሪዎቹ ምንድነው ጥያቄያቸው ?
" አንድ ዲግሪ ለመያዝ 8 (#ስምንት) ዓመታትን መማር #ፍትሃዊ አይደለም " ያሉት ተማሪዎቹ " ከሌሎች ዩኒቨርስቲዎች የምንለይበት ምክንያት የለም ፤ የመውጫ ፈተና መፈተን አለብን " ብለዋል።
" ተመርቀን ወጥተን ስራ መስራት ፤ ህይወትን ማሸነፍ ባለብን በዚህ እድሜያችን የመጀመሪያ ዲግሪ ለማግኘት 8 ዓመታት መጠበቅ የለብንም ፣ የወጣትነት እድሜያችን ያሳስበናል ፤ ብንጮህ ብንጮህ ሰሚ አላገኘንም " ሲሉ ገልጸዋል።
" በዚህ ዓመት መመረቅ ሲገባን ሌላ ተጨማሪ ጊዜ ትማራላችሁ እያሉን ነው ይሄ በፍፁም የማንቀበለው ነው " ብለዋል።
ዛሬ ተማሪዎቹ ከመቐለ ዩኒቨርስቲ ዋናው ግቢ በመነሳት የተለያዩ መፈክሮች በመያዝ ወደ ከተማ ለማምራት ሲሞክሩ በፓሊስ እንግልትና ድብደባ ተፈፅሞባቸዋል።
የትራፊክ ፖሊስ አባላት ሰልፉን ለማደናቀፍ መንገድ ሲዘጉ ፤ ታጣቂዎች ሰልፈኛ ተማሪዎች ሲደበድቡ ታይተዋል።
ጥያቄ ካነሱ ሰላማዊ ሰልፈኞች መካከል ሶስት ሴት ተማሪዎች በፓሊስ #ሲደበደቡ መመልከቱን ህሉፍ በርሀ የተባለ የአይን እማኝ ገልጿል።
ከዛሬው ሰልፍ ጋር በተያያዘም አንድ የፖሊስ አባል አንዲት #ሴትን እያንገላታ #ገፍትሮ መሬት ላይ ሲጥላት የሚያሳይ ቪድዮ ብዙዎችን አስቆጥቷል።
የመቐለ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ሰላማዊ ስልፍ በማስመልከት የዩቨርስቲው አስተዳደር እና የትምህርት ሚንስቴር እንዲሁም የከተማው ፖሊስ እስከ አሁን ያሉት ነገር የለም።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ተቋማቱ የሚሉት ካለ ተከታትሎ ያቀርባል።
መረጃው በመቐለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል የተዘጋጀ ነው።
@tikvahethiopia
#Update
" የወሰዱትን ገንዘብ እስካሁን ድረስ አልመለሱም " ልያላቸው ግለሰቦችን #ፎቶግራፍ በተለያዩ ሚዲያዎች ማውጣት የቀጠለው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዛሬ ደግሞ ከ64 ሺህ እስከ 71 ሺህ ብር " ያለአግባብ የወሰዱትን ገንዘብ አልመለሱም " ያላቸውን ገለሰቦች ፎቶግራፍ አሰራጭቷል።
@tikvahethiopia
#እንድታውቁት
የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በነበረበት ይቀጥላል።
የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ መጋቢት ወር ሲሸጥ በነበረበት ዋጋ የሚቀጥል መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታውቋል።
የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ስንት ነው ?
- ቤንዚን በሊትር 77 ብር ከ65 ሳንቲም
- ነጭ ናፍጣ በሊትር 79 ብር ከ75 ሳንቲም
- ኬሮሲን በሊትር 79 ብር ከ75 ሳንቲም
- ቀላል ጥቁር ናፍጣ በሊትር 62 ብር ከ36 ሳንቲም
- ከባድ ጥቁር ናፍጣ በሊትር 61 ብር ከ16 ሳንቲም ነው።
@tikvahethiopia
#አቢሲንያ_ባንክ
ወደ አፖሎ አካውንት አንድ ሰው ባስመዘገቡ ቁጥር የ50 ብር ጉርሻ!
ባንካችን አቢሲንያ በተለያዩ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚገኙ ተማሪዎችን የአፖሎ የተማሪ አምባሳደር በማድረግ፣ አፖሎን ለደንበኞች በማስተዋወቅ እና በምዝገባ ባሳኩት መጠን የኮሚሽን ክፍያ መክፈል ጀምሯል፡፡ ስለሆነም የአፖሎ አምባሳደር ለመሆን ፍላጎት ያላቸውን የከፍተኛ ትምህርት ተቌማት ተማሪዎች አወዳድሮ እየወሰደ ነው፡፡
የከፍተኛ ትምህርት ተቌማት ማለትም
1. ዩኒቨርሲቲ
2. ኮሌጅ
3. ቴክኒክ እና ሙያ ማሰልጠኛ ተቋማት ናቸው
የዚህ እድል ተሳታፊ ለመሆን በቀላሉ ከታች ያለውን መስፈንጠሪያ በመጠቀም ይመዝግቡ፡፡
https://apolsup.bankofabyssinia.com/studentAgent
የ50 ብር ኮሚሽን አግኙ!
ከአፖሎ ጋር ተፍ ተፍ በሉ፡፡
ከስራ በፊት ስራ ጀምሩ፡፡
#ትግራይ
የኤርትራ ሰራዊት ከሶስት የኢትዮጵያ የትግራይ ምስራቃዊ ዞን ወረዳዎች ' 93 ወጣቶች ' አግቶ መሰወሩን የአካባቢው አስተዳዳሪዎች ገልጹ።
እገታው የተፈፀመው ኢትዮጵያ በትግራይ በኩል ከኤርትራ ከምትዋሰንባቸው የዛላንበሳ ከተማ የጉሎመኻዳ እና የኢሮብ ወረዳዎች ላይ ነው ተብሏል።
ይህን የተገለፀው የከተማ እና የወረዳዎቹ አስተዳዳሪዎች ከኤርትራ ድንበር በ35 ኪሎ ሜትር ርቀት በምትገኘው የዓዲግራት ከተማ መጋቢት 25 ቀን 2016 ዓ.ም ከአፍሪካ ህብረት ወታደራዊ ታዛቢዎች (AU military attaches) ባካሄዱት ውይይት ነው።
የዛላአንበሳ ከንቲባ መምህር ብርሀነ በርሀና ፣ የጉሎመኻዳ ዋና አስተዳዳሪ ሃፍቶም ባራኺ በጋራ ከአፍሪካ ህብረት ወታደራዊ ታዛቢዎች በነበራቸው ቆይታ እንደገለፁት ከፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት በኃላ :-
➡ በአከባቢያቸው የተለወጠ የፀጥታ ሁኔታ አለመኖሩ ፤
➡ ጦርነቱ ተከትሎ የተፈጠረው ችግር እንዳልተፈታ፤
➡ የኤርትራ ሰራዊት የዛላአንበሳ ከተማ ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥሮ እንደሚገኝ፤
➡ ከዛላኣንበሳ ከተማ መግብያ በቅርብ ርቀት ዝባን ሑፃ ተብሎ በሚጠራ አከባቢ ኬላ አቋቁሞ ፍተሻ እንደሚያካሂድ ፤
➡ የኤርትራ ሰራዊት ከዛላኣንበሳ ከተማ 15 ፣ በቁጥጥሩ ስር ከሚገኙ የጉሎመኻዳና የኢሮብ ወረዳዎች የተለያዩ ቀበሌዎች 78 ባጠቃላይ 93 ወጣቶች አግቶ የወሰዳቸው ወጣቶች ያሉበት ሁኔታ እንደማይታወቅ አብራርተዋል።
ከዚህ በተጨማሪ በኤርትራ ሰራዊት ቁጥጥር ስር በሚገኙ የጉሎመኻዳ እና የኢሮብ ወረዳዎች 10 ቀበሌዎች የሚኖር ህዝብ እርዳታ ጨምሮ የጤና የትምህርት እንዲሁም ሌሎች የመንግስት አገልግሎቶች እንደማያገኝ አስተዳዳሪዎቹ ለአፍሪካ ህብረት ወታደራዊ ታዛቢዎች በዝርዝር አስረድተዋል።
በስብሰባው ወቅት የኢትዮጵያ የሀገር መከላከያ ሰራዊት እና የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ተወካዮች መሳተፋቸውን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከትግራይ ምስራቃዊ ዞን ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ያገኘው መረጃ ያሳያል።
የሀገር መከላከያ ሚንስትሩ ዶክተር አብራሃም በላይ በየካቲት 2016 ዓ.ም የመጨረሻው ሳምንት ላይ በትግርኛ ቋንቋ ለኢትዮጵያ ቴሌቪዥን በሰጡት ቃለመጠይቅ ፥ " የሻብዕያ ሰራዊት " ብለው የገለፁት የኤርትራ ጦር ከኢትዮጵያ መሬት ስለመውጣት ጉዳይ ፤
" ከፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት በፊት በበርካታ የትግራይ አከባቢዎች የሻዕብያ ሃይል ገብቶ ነበር ፣ ከስምምነቱ በኋላ እንዲወጣ ተደርጓል ፣ አሁንም የተቀሩ ቦታዎች ካሉ ቦታዎቹ እና ቀበሌዎች ከፌደራልና ከትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር የተውጣጣ ቡድን በዝርዝር አጥንቶ እንዲያቀርብና መፍትሄ እንዲሰጠው እየሰራን ነው ሁሉም ልክና መስመር ይይዛል " ማለታቸውን መዘገባችን ይታወሳል።
መረጃው በመቐለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው የተዘጋጀው።
@tikvahethiopia
#BK_COMPUTERS
ማንኛውንም አይነት አዳዲስ ላፕቶፖች ዱባይ ዩዝድ ላፕቶፖች ዴስክ ቶፖችን ጨምሮ ከብዛት እና ከታላቅ ቅናሽ ጋር ያዘንላቹ መተናል። ቢሮዎች፣ ለተማሪዎች፣ ለግሪፊክስ ዲዛይን ባለሙያዎች፣ ለጌመሮች እንዲሁም ለጨረታ የሚሆኑ በጥራት እና በ ብዛት ከ1 አመት ዋስትና ጋር እኛ ያገኛሉ
ለተጨማሪ መረጃ እና የላፕቶፕ አማራጮችን ለማየት የቴሌግራም ፔጃችንን Join ያድርጉ።
👉 /channel/BKComputers
Inbox @bkcomputer27
አድራሻ ፦ አዲስ አበባ መገናኛ ሲቲ ሞል ከመሰረት ደፋር ህንፃ አጠገብ 1 ፎቅ ላይ እንገኛለን። 0911448148/ 0955413433 we make IT easy!