#Update
የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) የከፍተኛ አመራሩን ጃል በቴ ኡርጌሳን ግድያ በማውገዝ አፋጣኝ ነጻ፣ ገለልተኛ እና አድሏዊ ያልሆነ ምርመራ እንዲደረግ ጠየቀ።
ፓርቲው በግድያው ዙሪያ መግለጫ አውጥቷል።
በመግለጫው ፤ የፓርቲው አባል እና የፖለቲካ ኦፊሰር ጃል በቴ ኡርጌሳ ዘግናኝ እና አሰቃቂ በሆነ ሁኔታ መገደላቸውን አመልክቶ የተሰማውን ሀዘን ገልጿል።
" በነቁ የኦሮሞ ፖለቲከኞች እና በታዋቂ ሰዎች ላይ የሚደረገው ግድያ ቀጥሏል " ያለው ኦነግ የታወቂውና ተወዳጁ አርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ሳይረሳ እና ቤተሰቦቹ እስካሁን ፍትህ ሳያገኙ የበቴን ኡርጌሳን ግድያ መስማት እጅግ አሳዛኝ ነው ብሏል።
ጃል በቴ በተወለዱበት መቂ ከተማ #በጥይት ተደብድበው መገደላቸውን በመግለጫው ላይ አመልክቷል።
" ምንም እንኳን ሁኔታው ለሁላችን እጅግ በጣም ከባድ ቢሆንም በግድያው ላይ ተጨማሪ ምርመራ እያደረግን ነው " ሲል ገልጿል።
" ሁሉም የሰብአዊ መብቶች ድርጅቶች እና ሰላም ወዳድ ህዝቦች አፋጣኝ ነጻ፣ ገለልተኛ እና አድሏዊ ያልሆነ ምርመራ እንዲያደርጉ " ጥሪ አቅርቧል።
@tikvahethiopia
" በተለያዩ አጋጣሚዎች ለእስር እና ለእንግልት ቢዳረግም የበቀል ሰው አልነበረም " - አቶ ጃዋር መሀመድ
የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) ከፍተኛ አመራር አቶ ጃዋር መሀመድ በአቶ በቴ ኡርጌሳ ግድያ ዙሪያ ምን አሉ ?
" የትኛው እጅ ነው ጨክኖ በቴ ኡርጌሳን በለሊት ከእንቅልፋቸው አስነስቶ የሚረሽነው ? እንዴትስ በቴን የሚያውቅ ሆዱ አስችሎት አይኑ እያያ ሊገድለው ቻለ ? ወገኖች ይህ ምን ይባላል አሁን ?
በቴን ቢያንስ አውቀዋለሁ ጠንካራ የሆነ የፖለቲካ አቋም ቢኖረውም ለማንም ሆነ ለየትኛውም ቡድን ክፉ የሚያስብ ሰው አልነበረም።
እ.ኤ.አ ነሀሴ 2016 በተካሄደው ሰላማዊ ሰልፍ ተይዞ ከፍተኛ ድብደባ ተፈፅሞበት ሞተ ተብሎ ለረጅም ጊዜ በሆስፒታል ውስጥ ቆይቷል።
ከዚያ ጊዜ ጀምሮ በተለያዩ አጋጣሚዎች ለእስርና ለእንግልት ቢዳረግም የበቀል ሰው አልነበረም። ይህ ለበቴ አይገባም ነበር። " ሲሉ የአቶ በቴን ግድያ አውግዘዋል።
የኦነግ ከፍተኛ አመራር የሆኑት አቶ በቴ ኡርጌሳ ትላንት ለሊት በትውልድ ከተማቸው መቂ ካረፉትበት ሆቴል ተውስደው ተገድለው መንገድ ላይ ተጥለው ተገኝተዋል።
ወደ መቂ ያቀኑት የእርሻ ስራቸውን ለመመልከት እንደነበር ቢቢሲ አፋን ኦሮሞ የቅርብ ጓደኛቸውን ዋቢ አድርጎ አስነብቧል።
እስካሁን ድረስ ፓርቲያቸው ኦነግ በይፋ መግለጫ አልሰጠም። በመንግስት በኩልም የተባለ ነገር የለም።
@tikvahethiopia
አቶ በቴ ኡርጌሳ ተገደሉ።
የተቃዋሚው የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ፓርቲ (ኦነግ) ከፍተኛ አመራር / የፖለቲካ ኦፊሰር የሆኑት አቶ በቴ ኡርጌሳ ትላንትና ለሊት በመቂ ከተማ መገደላቸው ከቅርብ ወዳጆቻቸው ተሰምቷል።
" ካረፉበት ሆቴል ውስጥ ትላንት ለሊት ተወስደው ተገድለው ነው አስክሬናቸው መንገድ ላይ የተገኘው " ተብሏል።
አቶ በቴ ኡርጌሳ በተደጋጋሚ ጊዜ ለእስር ሲዳረጉ የቆዩ ሲሆን በቅርቡም " ሁከት እና ብጥብጥ በማስነሳት " ወንጀል ተጠርጥረዋል በሚል ታስረው በ100 ሺህ ብር ዋስ ከእስር ተለቀው ነበር።
ትላንትና በመቂ ከተማ ተገድለው አስክሬናቸው መንገድ ላይ ተገኝቷል።
ፓርቲያቸው እስካሁን ስለግድያው በይፋ የሰጠው መግለጫ የለም።
@tikvahethiopia
ዘማሪ ሙሉቀን መለሰ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ።
ዘማሪው ወደ መንፈሳዊው ህይወት ሳይገባ በፊት ለረጅም ዓመታት ዘፋኝ የነበረ ሲሆን በሙዚቃ አድማጮች ዘንድ እጅግ ተወዳጅ የሆኑ ስራዎች ነበሩት።
ሙሉቀን መለሰ የዘፈንን ህይወት እርግፍ አድርጎ ከተወ እና ዘማሪ ከሆነ በኃላ የተለያዩ የመዝሙር ስራዎችን ለወንጌል አማኞች አቅርቧል።
ዘማሪው ከሀገር ወጥቶ አሜሪካ መኖር ከጀመረ ረጅም ዓመታት ያለፈው ሲሆን በዛው ባለበት ሀገር አሜሪካ ነው ከዚህ ዓለም በሞት የተለየው።
ከዘማሪ ሙሉቀን መለሰ ስራዎች አንዱ ፦
ኢትዮጵያ !
" ኢትዮጵያ #ኢትዮጵያ ፈጥነሽ እጆችሽን ወደ እግዚአብሔር ዘርጊ፤
በመከራሽ ዘመን የሚረዳሽ አምላክሽ ነውና ወደእርሱ ተጠጊ።
አድገዋል አውቀዋል ያልሻቸው #ልጆችሽ፤
ሁሉም እሾህ ሆነው እየወጉ #አደሙሽ፤
የአንድነት ማሰሪያው መቀነት ይኑርሽ ይኑርሽ፤
እግዚአብሔር ነይ ይላል ወደእሱ ተመለሽ።
#ጦርነት #ረሃብ #ስደት ደርሶብሻል፤
ችግር በየፈርጁ ተፈራርቆብሻል፤
በመከራሽ ብዛት የአፍረት ማቅ ለብሰሻል፤
የሚታደግ አዳኝ ኃያል ብሩት አጥተሻል።
ኢትዮጵያ ፈጥነሽ እጆችሽን ወደ እግዚአብሔር ዘርጊ፤
በመከራሽ ዘመን የሚረዳሽ አምላክሽ ነውና ወደእርሱ ተጠጊ። "
#TikvahEthiopia
@tikvahethiopia
#መንገድ
“ መንገዱ ከፈረሰበት እስካሁን ጊዜ ድረስ እዛ የጠፋው የአገር ንብረት 4 ጊዜ ያንን አስፓልት ያሰራል ” - የከባድ መኪና አሽከርካሪዎች ማኀበር
ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብና መሰል ሜጋ ፕሮጀክቶች የግንባታ ግብዓቶች ፣ ማዳበሪያ፣ ነዳጅ፣ ዘይት እና ሌሎች ኢትዮጵያ ገቢ እና ወጪ ግብዓቶችን የምታከናውንበት የጂቡቲ መንገድ ጥገና ካሻው ከ10 ዓመታት በላይ ቢያስቆጥርም ባለመጠገኑ በተሽከርካሪዎች ንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያስከተለ መሆኑን የከባድ መኪና አሽከርካሪዎች ማኀበር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።
ማህበሩ ምን አለ ?
- “ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ ትራንስፖርት ሚኒስቴር ውስጥ እያለች ጂቡቲ ድረስ መጥታ መንገዱን አይታ የተፈራረመችው ሰነድ ነበር ከ4 ዓመታት በፊት። ምን ላይ እንደደረሰ አላውቅም። ከውሃ ልማት ዲኬል እስከሚባል ቦታ ድረስ ያለው መንገድ እጅግ ፈታኝና አስቸጋሪ፣ የአገሪቱ ንብረት የሚወድምበት ነው። ”
- “ በእርግጠኝነት መናገር እችላለሁ መንገዱ ከፈረሰበት እስካሁን ጊዜ ድረስ እዛ የጠፋው የአገር ንብረት አራት ጊዜ ያንን አስፓልት ይሰራል። መንገሥት ያን መንገድ እንዲጠገን ማድረግ አለበት። ”
- “ ስምምነቱ ያለው በኢትዮጵያም ሆነ በጂቡቲ መንግሥት በኩል መንገዱ መጠገን እንዳለበት ነው፣ የተሰራው 20 ኪ.ሜ ብቻ ነው። በቀሪው 80 ኪ.ሜ ብዙ ኤክስፖርት የያዙ ተሽከርካሪዎች ይወድቃሉ። ለኢትዮጵያ ሜጋ ፕሮጀክት ማሽን የጫኑ ተሽከርካሪዎች አስቸጋሪ ሆኖባቸው አንዳንዴ ማሽኑ የሚወድቅበት ሂደት አለ። ”
- “ የመንገዱን መፈራረስ ተከትሎ በከፍተኛ Currency የሚገቡ Spare parts በቶሎ ይበላሻሉ ይህም የአገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ ከፍተኛ ኪሳራ አለው። የዚህ ችግር ዋነኛ ምክያት ደግሞ የመንገዱ አለመጠገን ነው። ”
- “ የ80 ኪ/ሜ መንገድ #ከ10_ሰዓታት_በላይ ጉዞ ይወስዳል። ከዓመት ወደ ዓመት ችግሩ እየተባባሰ ነው የመጣው። መንገዱ የተቆፋፈረ፣ አቧራማ፣ አካባቢው ሞቃታማ በመሆኑ ከተጠቀሱት ችግሮች በተጨማሪ ለጤናም ጠንቅ ነው። ”
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለቅሬታው ምላሽ እንዲሰጡ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አማካሪ የሆኑትን ዶክተር ቶሎሳን አነጋግሯል። እሳቸውም ምላሽ ሰጥተዋል።
ምን አሉ ?
ዶ/ር ቶሎሳ ፦
° “ ግንባታው የዘገየገው ከዚህ በፊት በጂቡቲ በኩል በነበረ አለመግባባት ነበር፡ በኋላ ላይ ግን መግባባት ላይ ተደርሶ ጥገናው ተጀምሯል። ”
° “ የጩኸቱ መንስኤ ስላላቀ ነው እንጂ አሁን መግባባት ላይ ተደርሶ መንገዱ እየተሰራ ነው ለ2 ኮንትራክተሮች ተሰጥቶ (በእኛ እስከተወሰነ ድረስ በእነርሱ እስከተወሰነ ድረስ ያለው) ። ”
Q. ቲክቫህ ኢትዮጵያ እውነትም አሁን በመሰራት ላይ ያለ አለ ? ብሎ ጠይቋል።
° “ Exactly አሁን በመሰራት ላይ ነው ያለው። ከጋላፊ እስከ ዲኬሌ ድረስ (ወደ ጂቡቲ ማለት ነው) ለቻይና ኮንትራክተር ተሰጥቶ እርሱ ጥሩ ሁኔታ ላይ ነው ያለው። በሳዑዲ መንግሥት ነው የፋይናንስ ድጋፍ የተደረገው። ከዲኬሌ እስከ ጂቡቲ ድረስ ደግሞ በእኛ (በኢትዮጵያ) በኩል አንድ የእኛ አገር ኮንትራክተር ይዟል። ”
° “ ትንሽ ችግሩ ያለበት እርሱ ላይ ነው። ለችግሩ መንስኤው የፋይናንስ አጥረት ነው። በአጠቃላይ የግንባታውን ሂደት በተመለከተ መረጃዎችን እየተከታተልን የምናቀርብ ይሆናል። ”
#TikvahEthiopia
@tikvahethiopia
#Vote 🗳
"ጥበብ እንደ የፈውስ መንገድ" (Art As path to Healing) በሚል ርዕስ በሪድም ዘ ጀነሬሽን አዘጋጅነት በትግራይ ክልል በተዘጋጀውና 59 ታዳጊዎችና ወጣት ሰአልያን በ10 ቡድኖች ያሳተፈው የሥዕል ውድድር ተመልካቾች ድምጽ እንዲሰጡበት ቀርቧል።
እስከ ሐሙስ ሚያዝያ 3 ድረስ ክፍት በሚሆነው የድምጽ አሰጣጥ ወጣቶቹ እና ታዳጊዎቹ የሰሯቸውን ሥዕሎች በሚከተለው ሊንክ በመግባት ሥራቸውን በማየት መምረጥ ትችላላችሁ።
ለመምረጥ https://redeem.tikvahethiopia.net/ ይጠቀሙ።
@TikvahethMagazine
#IOM
በጅቡቲ የባህር ዳርቻ የ38 ሰዎች አስክሬን ተገኘ።
በጀልባ መስጠም አደጋ የህፃናትን ጨምሮ አጠቃላይ 38 ሰዎች ሞተው አስክሬናቸው መገኘቱን የዓለም አቀፉ የስድተኞች ድርጅት አሳውቋል።
6 ሰዎች የገቡበት ያልታወቀ ሲሆን ሳይሞቱ እንዳልቀረ ተነግሯል።
ከሞት የተረፉ 22 ሰዎች በጅቡቲ እርዳታ እየተደረገለቸው ይገኛል።
@tikvahethiopia
#እንድታውቁት #አዲስአበባ
ከለሊቱ 10:00 ሰዓት ጀምሮ መንገዶች ይዘጋሉ።
ከ1445ኛው የኢድ አልፈጥር በዓል ጋር ተያይዞ የበዓሉ የኢድ ሶላት ተጀምሮ እሰከሚጠናቀቅ በአዲስ አበባ ከተማ ለተሽከርካሪ ዝግ የሚሆኑ መንገዶችን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል።
በዚህም መሰረት ፦
- ከፒያሳ በቸርችል ጎዳና ወደ ለገሃር የሚወስደው መንገድ ቴዎድሮስ አደባባይ ላይ
- ከጎተራ ማሳለጫ ወደ ስታዲዮም የሚወስደው አጎና ሲኒማ ላይ
- ከሜክሲኮ ወደ ለገሃር የሚወስደው መንገድ ሜክሲኮ አደባባይ ላይ
- ከብሔራዊ ቤ/መንግስት ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ፓርላማ መብራት ላይ
- ከኦሎሚፒያ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ኦሎምፒያ አደባባይ ላይና ታች እንዲሁም ግራና ቀኝ
- ከመገናኛ ወደ ኡራኤል ቤተ ክርስቲያን የሚወስደው መንገድ 22 መስቀለኛ መንገዱ አካባቢ
- ከጥቁር አንበሳ ሼል ወደ ለገሀር የሚወስደው መንገድ ጥቁር አንበሳ ሼል አጠገብ
- ከሲግናል እና ከአቧሬ ወደ ካዛንቺስ የሚመጣው መንገድ አቧሬ ሴቶች አደባባይ ላይ
- ከመስቀል ፍላወር ወደ መስቀል አደባባይ የሚመጣው መንገድ ጋዜቦ አደባባይ ላይ
- ከቄራ በአዲሱ መንገድ ወደ ቂርቆስ ቤ/ክርስቲያን የሚወስደው መንገድ ቂርቆስ ቤ/ክርስቲያን መገንጠያ ላይ
- ከጌጃ ሰፈር በሰንጋተራ ወደ ለገሐር ለሚመጡ አሽከርካሪዎች ሰንጋ ተራ 40/60 የጋራ መኖሪያ ቤት አካባቢ
- ከአብነት በጌጃ ሰፈር ወደ ብሔራዊ ቴአትር የሚወስደው መንገድ ጎባ ቁጠባ አጠገብ
- ከተክለ ሐይማኖት አካባቢ በሜትሮሎጂ ወደ ብሔራዊ ቴአትር ሜትሮሎጂ መ/ቤት ላይ
- ከተክለ ሐይማኖት አካባቢ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የኋላ በር ወደ ብሔራዊ ቴአትር ለሚሄዱ ጥቁር አንበሳ ሼል ድሬንስ አካባቢ
- ከተክለ ሐይማኖት አካባቢ በጎላ ሚካኤል ውስጥ ለውስጥ ወደ ለገሐር ለሚሄዱ አሽከርካሪዎች ጎላ ሚካኤል መስቀለኛው ላይ
... ይለፍ ለሌላቸው ተሽከርካሪዎች ከለሊቱ 10 ሰዓት ጀምሮ ዝግጅቱ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ዝግ ይሆናሉ።
መላው ህብረተሰቡ / አሽከርካሪዎች አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ ፖሊስ ጥሪ አቅርቧል።
@tikvahethiopia
#4WCOMPUTERS
አዲስና በብዙ አማራጭ የአሜሪካ የአውሮፓ የዱባይ ላፕቶፖችን በተመጣጣኝ እና ከገበያዉ በተሻለ ዋጋ ከመልካም መስተንግዶ ከተሟሉ ሶፍትዌሮች ጋር ይዘን እንጠብቆታለን። በተጨማሪ የ1 ዓመት ዋስትና እንዲዉም የ30 ቀን የመሞከሪያ ግዜ እንሰጣለን። የተለያዩ ዓይነት ላፕቶፓች ለማየት ና ለመምረጥ ሊንኩን ይጠቀሙ 👉 t.me/computers4w
ስልክ፦ 0911867992
አድራሻ - መገናኛ ማራቶን ህንፃ 1ኛ ፎቅ -ፎርደብሊ ኮምፒውተር
#Update
የአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ምን አለ ?
የአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ዛሬ ማምሻውን ይፋዊ መግለጫ ሰጠ።
በዚህም መግለጫው ባለፉት #8_ወራት በአማራ ክልል በመንግስትና በታጣቂ ቡድኖች መካከል የተፈጠረዉ ግጭት ህዝቡን እጅግ የከፋ ዋጋ እያስከፈለዉ መሆኑን ገልጿል።
" በዋናነት በሙስሊሞች ላይ እየደረሰ ያለዉ ግፍ፣ መፈናቀል፣ ዘረፋ፣ መታገትና መገደል ከጊዜ ጊዜ #እየተባባሰ በመሄድ ላይ ነው " ብሏል።
" ሌላ ትርጉም እንዳይሰጠዉ ብለን በሆደ ሰፊነት ብንታገስም ጉዳዩ ከቀን ወደ ቀን ንጹሀን ዜጎችን በማገትና በመሰወር እንዲሁም በመግደል የክልሉን ህዝብ በተለይ ሙስሊሙን ማህበረሰብ መከራ ዉስጥ ጨምሮታል " ሲል ምክር ቤቱ አስረድቷል።
እንደማሳያም ፦
➡️ በቀን በ29/7/16 በባህር ዳር ከተማ ቀበሌ 14 የመቅሪብ ሶላት ሰግደዉ ወደ ቤታቸዉ በሚሄዱ አማኞች ላይ ማንነታቸዉ ያልታወቁ የታጠቁ ኃይሎች 4 የአንድ ቤተሰብ አባላትን እና 1 ጎረቤታቸዉን በመግደል ተሰዉረዋል፡፡
➡️ በ28/07/16 በጎንደር ከተማ ማክሰኝት አካባቢ 4 ሙስሊሞች ተገድለዋል፡፡
➡️ 29/07/16 በሞጣ ከተማ አንድን ወጣት ካገቱ በኋላ ቤተሰቦቹን በማስፈራራት 300 ሺህ ንር ተቀብለዉ ታጋቹን በአሰቃቂ ሁኔታ #ገድለዉ ጥለዉታል፡፡
➡️ በቢቸና ከተማ በቀን 26/07/16 ንጹሀን ባልና ሚስት " ለምን ለመንግስት ግብር ከፈላችሁ " ተብለዉ በግፍ ተገድለዋል፡፡
ምክር ቤቱ በአጠቃላይ በክልሉ በተለያዩ ቦታዎች ባለፉት 8 ወራት ፦
- ከ80 በላይ ሙስሊሞች መገደላቸውን
- በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ ሙስሊሞች መፈናቀላቸውን
- አርባ ሰባት (47) ሰዎች መታገታቸውን
- ከ260 በላይ ዘረፋዎች መፈፀማቸውን አሳውቋል።
" ይህን ዘረፋ፣ ብዙ ስቃይ እና እንግልት፤ መገደልና መፈናቀል በጽኑ እናወግዛለን " ብሏል።
" ይህንን እኩይ ተግባር ለማስቆም መንግስት ፣ ሰላማዊዉ የክልሉ ህዝብ፣ የሌላ እምነት ተከታይ ወገኖች ፣ የኃይማኖት አባቶች እንዲሁም ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት በሙሉ የበኩላቸውን እንዲወጡ " ሲል ም/ቤቱ ባወጣው መግለጫ ጥሪ አቅርቧል።
@tikvahethiopia
#BREAKING
ዛሬ በሳዑዲ አረቢያ አካባቢ ጨረቃ ባለመታየቷ የዒድ አልፈጥር በዓል ረቡዕ ዕለት እንደሚውል ተገልጿል።
Via Haramain
@tikvahethiopia
የትምህርት ቤት መፀዳጃ ቤት #ተደርምሶ የ3 ታዳጊ ተማሪዎች ህይወት ተቀጠፈ።
ዛሬ በትግራይ ምስራቃዊ ዞን የጉሎመኻዳ ወረዳ በሚገኘው " መረታ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት " መፀዳጃ ቤት ተደርምሶ 3 ተማሪዎች ወዲያው ህይወታቸው አልፏል።
የመደርመስ አደጋው በእረፍት ጊዜ ከረፋዱ በ4:00 ሰአት የደረሰ ሲሆን የሴቶች የጋራ መፃዳጃ ቤት ሲጠቀሙ ከነበሩ 6 እንስት ተማሪዎች 3ቱ ወድያውኑ ሲሞቱ 3ቱ ቆስለው ህክምና እየተደረገላቸው ይገኛል።
ትምህርት ቤቱ ፤ ለመፀዳጃ ቤቱ መደርመስ መንስኤው በአከባቢው የዘነበ ከባድ ዝናብ እና መፀዳጃ ቤቱ ለረጅም ጊዜ ማገልገሉ እንደሆነ ገልጿል።
አደጋው በት/ቤቱ ተማሪዎች ፣ መምህራን እና ወላጆች ላይ ከፍተኛ ድንጋጤና ሃዘን መፍጠሩን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከድምፂ ወያነ ቴሌቪዥን ያገኘው መረጃ ያሳያል።
@tikvahethiopia
' ስታርት አፕ '
በኢትዮጵያ ለ ‘ስታርት አፕ’ ዘርፍ ዕድገት መሠረት የሚጥሉ የተለያዩ የሕግና የፋይናንስ አሠራር ማሻሻያዎች መደረጋቸውን የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር አሳውቀዋል።
ምንድነው የተደረጉት ማሻሻያዎች / የተዘረጉት አዳዲስ አሰራሮችስ ምንድናቸው ?
- የፈጠራ ሃሳብ ያላቸው ወጣቶች ሃሳባቸውን ወደ ተግባር ለማዋል በሚፈልጉበት ወቅት ያለምንም የንግድ ቤት ኪራይ ውል ሥራ መጀመር ይችላሉ።
- ማንኛውም የውጭ ሀገር ፈንድ ያገኘ ስታርት አፕ ሙሉ በሙሉ የውጭ ምንዛሪውን ለሚፈልገው ሥራ ማዋል ይችላል።
- አዲስ ፈጠራ ያላቸውና ሥራቸው ወደ ገቢ መቀየር የሚችሉ ወጣቶች በውጭ ሀገራት ለተለያዩ አገልግሎቶች ክፍያ በሚጠየቁበት ወቅት በባንኮች በኩል መንግሥት በሚያመቻቸው አሠራር ክፍያ መፈጸም የሚችሉበት አማራጭ ይመቻቻል።
- በፈጠራ ላይ ለተመረኮዙ ቴክኖሎጂ መር ሥራ ፈጣሪዎች በጉምሩክ አሠራር ሂደት የሚያጋጥሙ ክፍያዎችን የሚቀንስና የጉምሩክ ድጋፍ የሚያገኙበት ማዕከል ይቋቋማል።
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል ፥ " ወጣቶች እንደሀገር የተመቻቸላቸውን ዕድል በመጠቀም ሃሳባቸውን አውጥተው ሥራ ላይ ማዋልና የተሻለ ገቢ ማግኘት አለባቸው " ብለዋል። #ኢፕድ
@tikvahethiopia
#ባህርዳር
በአማራ ክልል መዲና በባህር ዳር ከተማ ቀበሌ 14 ትላንት መጋቢት 29 የመግሪብ ሰላት ሰግደው ሲመለሱ የነበሩ አባት ከ3 ልጆቹ እንዲሁም አንድ ጎረቤታቸውን ጨምሮ አጠቃላይ 5 ሰዎች በተከፈተባቸው የጥይት እሩምታ መገደላቸው ተነግሯል።
ትላንትና ምሽት በግፍ የተገደሉት ፥ አቶ ሙሄ ፣ ልጃቸው አበባዉ ሙሄ ፣ ሽኩር ሙሄ ፣ ሙላት ሙሄ እና ጎረቤታቸው አቶ እንድሪስ የተባሉ ሲሆኑ ስርዓት ቀብራቸው በዛሬው ዕለት ተፈፅሟል።
እስካሁን ገዳዮች ስለመያዛቸው የተባለ ነገር የለም።
በከተማዋ ከተገደሉት ሰዎች ባሻገር ባህርዳር ከተማ አባይ ማዶ የሚገኘው መስጂድ ከፍተኛ የመሳሪያ ድብደባ እንደተፈፀመበት ተገልጿል።
ከዚሁ ጋር በተያያዘ ዛሬ የባህር ዳር ሙስሊሞች በክልሉ በሙስሊሞች ላይ አነጣጥረዋል ያሉትን ግድያ እና እገታ በመቃወም ሰልፍ ማድረጋቸውን " ሀሩን ሚዲያ " ዘግቧል።
እስካሁን በአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤትም ሆነ በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የተሰጠ አስተያየት የለም።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ በክልሉ ተፈፅመዋል ስለተባሉ ግድያዎች ፣ ጥቃቶች ፣ ዘረፋና እገታዎች የአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት እና የሚመለከታቸው አካላትን ለማነጋገር ጥረት እያደረገ ይገኛል፤ ምላሽ እንዳገኘ ተጨማሪ መረጃዎችን ያቀርባል።
@tikvahethiopia
#Update
ኦክሎክ ሞተርስ ኃ/የተ/የግ/ማሕበር “ ገንዘብ ተጨምሮብናል ” በማለት እያለቀሱ ቅሬታ ላቀረቡ የታክሲ ቆጣቢዎች ምን ምላሽ ሰጠ ?
የመኪና ቆጣቢዎች በ " ኦኮሎክ ሞተርስ " ላይ ያላቸውን ቅሬታ በገለጹበት ወቅት እያለቀሱ መንግሥት መፍትሄ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል።
አንዲት እናት፣ “ እኔ 1.5 ሚሊዮን ብር ነው #የተጨመረብኝ። እውነት ድርጅቱ ጨምሮበት ነው ወይስ የድሃ እንባ ፈልጎ ነው? ” ሲሉ እያለቀሱ መናገራቸው መረጃ አድረሰናችሁ ነበር።
ሌሎች እናቶች፣ አባቶች እያለቀሱ ያላቸውን ቅሬታ አሰምተዋል።
ቆጣቢዎች ፦
➡️ " ኦክሎክ ጀነራል ትሬዲንግ ኃላ/የተ/የግ/ማኀበር (ኦክሎክ ሞተርስ) መኪናውን በወቅቱ አላስረከበንም "
➡️ " የገንዘብ ጭማሪ አደረገብን " ላሉት ቅሬታ ምላሻችሁ ምንድነው ሲል ቲክቫህ ኢትዮጵያ የኦክሎክ ሞተርስ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ታመነ ካሳሁንን ጠይቋል።
የኦክሎክ ሞተርስ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ታመነ ካሳሁን ፦
“ እኔ እዚህ ላይ ትኩረት አድርጌ መልስ መስጠት እፈልጋለሁ፣ ምክንያቱም ' በእናንተ ድርጅት እዳለቀሱ ነው ' የሚለው የተሳሳተ ግንዛቤ ነው የሚል ሙሉ አቋም አለን።
በውላችን መሠረት 35 ፐርሰንት ለእኛ ይከፍላሉ ውሉን ሲዋዋሉ። ከዚያ መኪናው ከመምጣቱ ከአንድ ወር በፊት 65 ፐርሰንት ከፍሎ 100 ፐርሰንት ሲሞላ መኪናውን ይወስዳል።
ስለዚህ አልቅሰዋል የተባሉት እናትም ይሁኑ አባት 35 ፐርሰንት ለድርጅታችን ከፍለው፣ 65 ፐርሰንትም ወይ ከአበዳሪ ድርጅት ወይ ከራሳቸው ካሽ ከፍለው መኪና ሳንሰጥ ቀርተን ነው ወይ ያለቀሱት ? ወይስ 35 ፐርሰንት ወይም 20 ፐርሰንት ከፍያቸሁና ስጡኝ ነው ጥያቄው ? ”
ይሄ ነው ትክክለኛ ያልሆነው። ያለቀሰ ሰው ሁሉ ትክክለኛ ነው ማለት አይደለም። ያላለቀሰ ሰው አይ ተስማምቷል ማለት እንዳልሆነው ሁሉ” ብለዋል።
1.5 ሚሊዮን ተጨሞሮብኛል ያሉትን ቅሬታ አቅራቢ ቆጣቢ እናትን በተመለከተም ፦ “ እኝህ እናት 1.5 ሚሊዮን ብር ተጨመረብኝ ካሉ እንግዲህ እኔ ደጋግሜ ነው የምናገረው ወይ መኪና ቀይረዋል ” ሲሉ መልሰዋል።
ያሉት 1,500 ተመዝጋቢዎች እንደሆኑ ፣ ከዚህ ውስጥ 400 የሚሆኑት 35 ፐርሰንት እንደከፈሉ፣ አሁንም 200 መኪናዎች እንዳሉት ማኀበራቱ ቀሪውን ከፍለው መውሰድ እንደሚችሉ ኦክሎክ ሞተርስ አስታውቋል።
#TikvahaFamilyAddisAbaba
@tikvahethiopia
#Update
በአቶ በቴ ኡርጌሳ ግድያ ላይ አፋጣኝ፣ ገለልተኛና ሙሉ ምርመራ እንዲደረግ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ጥሪ አቀረበ።
የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ ፥ " ኮሚሽኑ ከተቃዋሚው የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ፓርቲ አባል በቴ ኡርጌሳ ግድያ ጋር ተያይዞ ወንጀለኞቹ በህግ እንዲጠየቁ በሁለቱም በኦሮሚያ ክልል እና በኢትዮጵያ ፌዴራል ባለስልጣናት #አፋጣኝ፣ #ገለልተኛ እና #ሙሉ_ምርመራ እንዲደረግ ይጠይቃል " ብለዋል።
አቶ በቴ ኡርጌሳ ትላንት ማክሰኞ ለሊት በትውልድ ከተማቸው መቂ ካረፉበት ሆቴል እንዲወጡ ተደርገው ተገድለው አስክሬናቸው መንገድ ላይ ተገኝቷል።
@tikvahethiopia
#ዒድ_አልፈጥር
1445ኛው የዒድ አል ፈጥር በዓል እየተከበረ ይገኛል።
በዓሉ በተለያዩ ሃይማኖታዊ ስርዓቶች እየተከበረ ሲሆን ጥዋት ላይ የዒድ ሶላት ስነስርዓት ተከናውኗል።
በየከተሞቹ ባሉ የዒድ ሶላት መስገጃ ስፍራዎች ህዝበ ሙስሊሙ በጋራ በመሰባሰብ የዒድ ሶላት ስነስርዓት አከናውኗል።
ከዒድ ሶላት በኃላ ምዕመኑን በየቤቱ ፣ ከዘመድ አዝማዱ፣ ከወዳጆቹ ጋር በመሆን የ1445ኛውን ዒድ አልፈጥር በዓል እያከበረ ነው።
በየከተሞቹ የነበረውን የዒድ ሶላት ስነስርዓት በፎቶ ይመልከቱ @tikvahethmagazine
በድጋሜ መልካም በዓል !
ፎቶ፦ ፎቶግራፈር አቤል ጋሻው (አዲስ አበባ)
@tikvahethiopia
#ዒድ_አልፈጥር
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ1445ኛው የዒድ አልፈጥር በዓል አደረሳችሁ። ዒድ ሙባረክ !
በዓሉ #የሰላም፣ #የአንድነት፣ #የፍቅርና #የመተሳሰብ ይሆን ዘንድ እንመኛለን።
መልካም በዓል !
#TikvahFamily❤️
@tikvahethiopia
#እንዳትደናገጡ
ነገ የሚከበረውን የኢድ አል ፈጥር በዓል ምክንያት በማድረግ ከንጋቱ 12:00 ሰዓት ላይ 9 ጊዜ መድፍ እንደሚተኮስ የሀገር መከላከያ ሚኒስቴር ማስታወቁን የአዲስ አበባ ፖሊስ ገልጿል።
@tikvahethiopia
ለዒድ እጥፍ ድርብ ስጦታ!
ለመጪው ዒድ አል-ፈጥር በዓል ባህርማዶ ከሚኖሩ ወዳጅ ዘመዶችዎ ከ 99 ብር ጀምሮ የሞባይል አየር ሰዓት ወይም ጥቅል በአጋሮቻችን በኩል ሲላክልዎ ለ15 ቀናት የሚያገለግል የ200% ስጦታ ይበረከትልዎታል!
ዒድ ሙባረክ!
ደንብና ሁኔታዎች ተፈጻሚ ይሆናሉ
https://bit.ly/487Y93d
#Ethiotelecom #telebirr #DigitalAfrica #DigitalEthiopia #RealizingDigitalEthiopia
" 38 #ኢትዮጵያውያን ፍልሰተኞች ህይወታቸው አልፏል " - በጅቡቲ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ
በጅቡቲ የባህር ዳርቻ ፍልሰተኞችን አሳፍራ ወደ #የመን በመጓዝ ላይ በነበረች ጀልባ ላይ በደረሰ የመስጠም አደጋ 38 ኢትዮጵያውያን ፍልሰተኞች ህይወታቸውን እንዳጡ በጅቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አሳውቋል።
ትላንትና ሰኞ በጅቡቲ ሰሜን ምስራቅ " #ጎዶሪያ " በሚባል የባህር ዳርቻ አቅራቢያ ስልሳ (60) ኢትዮጵያውያን ፍልሰተኞችን አሳፍራ ወደ #የመን ትጓዝ የነበረች ጀልባ ላይ በደረሰው የመገልበጥ አደጋ የ38 ፍልሰተኞች ሕይወታቸውን አጥተዋል።
በጅቡቲ የኢፌዴሪ ሚሲዮንም አደጋው ከደረሰ በኋላ ወደ ስፍራው በመጓዝ የአደጋውን መንስኤ በማጣራት ላይ እንደሚገኝ ተገልጿል።
ኤምባሲው ፥ በየዓመቱ ከ200 ሺህ የሚበልጡ ፍልሰተኞች ከጅቡቲ ባህር ዳርቻ የኤደን ባህረ ሰላጤ በመነሳት መካከለኛው ምስራቅ አገራት ለመድረስ በየብስና በባህር አደገኛ ጉዞ ያደርጋሉ ብሏል።
ባለፉት አምስት ዓመታት #በጀልባ_መስመጥ አደጋ ብቻ የ189 ዜጎቻችን ሕይወት እንዳለፈ ጠቁሟል።
በየጊዜው የሚደርሰው አደጋ እንዳለ ቢሆንም የፍልሰተኞቹ ቁጥር ግን አሁንም #እየጨመረ እንደሆነ ገልጿል።
ዜጎች በህገ ወጥ #ደላሎች የሀሰት ስብከት በመታለል ውድ ሕይወታቸውን አደጋ ላይ ጥለው በዚህ አደገኛ የጉዞ መስመር ከመንቀሳቀስ እንዲቆጠቡ አስጠንቅቋል።
የፍትህ አካላት ሕገ ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎችን #ከገጠራማ የአገራችን አካባቢዎች ዜጎችን በመመልመል ለስደት በሚዳርጓቸው ግለሰቦች ላይ ተገቢውን እርምጃ እንዲወስዱ በጅቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አሳስቧል።
@tikvahethiopia
#መግለጫ
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በአማራ ክልል ውስጥ እየተፈፀሙ ይገኛሉ ያላቸውን #ሙስሊሞችን ዒላማ ያደረጉ ጥቃቶች በማስመልከት ዛሬ ሚያዚያ 1 /2016 መግለጫ አውጥቷል።
የመግለጫው ዝርዝር ከላይ ተያይዟል።
@tikvahethiopia
#ሴጅ_ማሰልጠኛ
የፊታችን ቅዳሜ ሚያዚያ 05/2016 ዓ.ም 19ኛ ዙር የግራፊክስ ዲዛይን፣ ቪዲዮ ኤዲቲንግ፣ ሞሽን ግራፊክስ እና ዲጂታል ማርኬቲንግ ስልጠና ይጀምራል። ቀድመው ይመዝገቡ!
👉 100% በተግባር የተደገፈ ስልጠና
👉 Advanced Graphics + Video Editing + Motion Graphics + Digital Marketing በአንድ ላይ
👉 ከ15 በላይ ፕሮጀክቶች ያሉት
👉 የሥራ ላይ ስልጠና (Internship) የተመቻቸለት
ስልክ ፦ 0906777799 / 0906777755
አድራሻ፦ ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ
Telegram: /channel/sagetraininginstitute
Facebook: https://www.facebook.com/sagetraininginstitute
Instagram: https://www.instagram.com/sage_training_institute/
#የፀሀይ_ግርዶሽ
ዛሬ ሰኞ በተለያዩ ሀገራት ሙሉ የፀሀይ ግርዶሽ እየታየ ይገኛል።
በተለይ በሜክሲኮ እና አሜሪካ የተለያዩ ግዛቶች ሙሉ የፀሐይ ግርዶሽ እየታየ ነው።
የተለያዩ ቦታዎች በፀሀይ ግርዶሹ ምክንያት ከ3 ደቂቃ ለበለጠ ጊዜ በሙሉ #ጨለማ_ተውጠው ታይተዋል።
ክስተቱንም በብዙ ሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች እየተመለከቱት ነው።
የፀሀይ ግርዶሽ #ጨረቃ በምድር እና በፀሀይ መካከል ስታልፍ የፀሀይን እይታ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል በምትጋርድበት ጊዜ የሚከሰት ነው።
@tikvahethiopia
የዒድ አልፈጥር በዓል ረቡዕ ነው።
ዛሬ የሸዋል ወር ጨረቃ አልታየችም ፤ በመሆኑም የዒድ አልፈጥር በዓል ረቡዕ ይከበራል።
ነገ ማክሰኞ የረመዷን #የመጨረሻው ሰላሳኛ ቀን ይሆናል።
@tikvahethiopia
#Update የሸዋል ጨረቃ ፍለጋ ከደቂቃዎች በኃላ ይጀምራል።
ጨረቃ ዛሬ ከታየች የዒድ አልፈጥር በዓል ነገ ይውላል። ጨረቃ ዛሬ ካልታየች በዓሉ ረቡዕ ይውላል።
#Haramain #Tumair #SaudiArabia
@tikvahethiopia
#ዒድአልፈጥር
የዒድ አልፈጥር በዓል #ጨረቃ ዛሬ ከታየች ነገ #ማክሰኞ ካልታየች ደግሞ #ረቡዕ ይከበራል።
በሳዑዲ አረቢያ የሸዋል ጨረቃ ለማየት በቱማይር እና ሱዳይር የመመልከቻ ቦታ አስፈላጊ ዝግጅት መደረጉ ተነግሯል።
@tikvahethiopia
#4WCOMPUTERS
አዲስና በብዙ አማራጭ የአሜሪካ የአውሮፓ የዱባይ ላፕቶፖችን በተመጣጣኝ እና ከገበያዉ በተሻለ ዋጋ ከመልካም መስተንግዶ ከተሟሉ ሶፍትዌሮች ጋር ይዘን እንጠብቆታለን። በተጨማሪ የ1 ዓመት ዋስትና እንዲዉም የ30 ቀን የመሞከሪያ ግዜ እንሰጣለን። የተለያዩ ዓይነት ላፕቶፓች ለማየት ና ለመምረጥ ሊንኩን ይጠቀሙ 👉 t.me/computers4w
ስልክ፦ 0911867992
አድራሻ - መገናኛ ማራቶን ህንፃ 1ኛ ፎቅ -ፎርደብሊ ኮምፒውተር
#Update
ታግታ ከተወሰደች በኃላ ለማስለቀቂያ 3 ሚሊዮን ብር የተጠየቀባት ታጋዲዋ ተማሪ ማህሌት ተኽላይ ታግታ ከተወሰደች 20 ቀናት ሆኗታል።
ቤተሰቦቿ " ልጃችንን አፋልጉን " ሲሉ በፈጣሪ ስም ተማጽነዋል። መላው ኢትዮጵያ ህዝብ እና የፀጥታ ኃይል ልጃቸውን እንዲፈልግላቸው ጥሪ አቅርበዋል።
የታዳጊ ተማሪ ማህሌት ቤተሰቦች ከትግራይ ዓድዋ ከተማ ያስተላለፉት የአፋልጉን የተማፅኖ ጥሪ ምን ይላል ?
የማህሌት ተኽላይ ቤተሰቦች ፦
" ታዳጊ ልጃችን ተማሪ ማህሌት ተኽላይ መጋቢት 10/2016 ዓ.ም ከ 11:00 ሰዓት በኃላ ወደ ቋንቋ ትምህርት ቤት በመሄድ ሳለች በትግራይ ዓድዋ ከተማ ዓዲ ማሕለኻ ተብሎ ከሚጠራ ልዩ ቦታ ለጊዜው ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች ታፍና ተወስዳለች።
አጋቾቹ በወሰዱዋት ቀን በራስዋ ሞባይል ስልክ ወደኛ በመወደወል ለማስለቀቅያ 3 ሚሊዮን ብር እንድንከፍላቸው ጠይቀውናል። ከዛ በኃላ ግን በደውሉበት የልጃችን የሞባይል ቁጥር ብንደውልም አናገኛቸውም፤ በሌላ የሞባይል ቁጥር ደውለውም ያሉን ነገር የለም።
ስለሆነም እኛ የታዳጊ ተማሪ ማህሌት ተኽላይ ወላጆች በከፍተኛ ጭንቅና ሃዘን ውስጥ እንገኛለን። ስለዚህ ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብና የፀጥታ አካላት የአፋልጉን የተማፅኖ ጥሪ እናቀርባለን። "
ማህሌት ተኽላይ የሚመለከት ማንኛውም አይነት መረጃ ለመስጠት ፦
+251938819844 ሙሴ ተኽላይ
+251992733943 ደጀን ተኽላይ
+251935036100/
+251962529287 ሚልዮን ተኽላይ
በሚሉ የሞባይል ቁጥሮች እንድትጠቀሙ በትህትና እንጠይቃለን። "
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ሁኔታውን እንዲያብራሩ የታዳጊ ተማሪ ማህሌት ተኽላይ ቤተሰቦችን ጠይቆ ፥ " የዓድዋ ፓሊስ እኛን መልሶ ምን አዲስ ነገር አለ ብሎ ይጠይቀናል ? " ሲሉ መልሰዋል።
የመቐለው የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ስለ ጉዳዩ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ወደ #ዓድዋ እና #አክሱም ያደረገው ጉዞ በፓሊስ አመራሮች ስብሰባ ምክንያት አልተሳካም።
#TikvahFamilyMekelle
@tikvahethiopia
#SamiTech
አዳዲስ ላፕቶፕች ከአንድ ዓመት ዋስትና ጋር!!
@samcomptech
በአገልግሎት አሰጣጣችን ላይ እና በዕቃዎቻችን ጥራት ላይ ደንበኞቻችን ምስክሮቻችን ናቸው። ዛሬም ብዛትንም ጥራትንም ሳንቀንስ እያስተናገድን እንገኛለን።
ለቢሮዎች፣ ለተማሪዎች ፣ ለዲዛይን ባለሙያዎች ፣ ለጌመሮች ወ.ዘ.ተ
አቅምን ካገናዘቡ እስከ ቅንጡ ላፕቶፖች ይህ ቀረ ሳይሉ የሚያገኙበትን ሱቃችንን ይጎብኙ። የቴሌግራም ቻናሉን ይቀላቀሉ ባሉበት ሆነው ይዘዙን እናደርሳለን።
የዕቃዎች ዋጋ፣ ዓይነት እና አድራሻ ለማግኘት ይሄን 👉 @samcomptech ተጭነው በቴሌግራምው ማየት ይችላሉ።
@sww2844 0928442662 / 0940141114
https://maps.app.goo.gl/H3PM1NrTcQ4SWkK17