#እንድታውቁት🚨
2 የወተት ምርቶች የደህንነትና የጥራት መስፈቶች አሟልተው ባለመገኘታቸው ምክንያት ህብረተሰቡ እንዳይጠቀማቸው ማሳሰቢያ ተላለፈ።
1ኛ. #Sultan Instant Full Cream Milk Powder (400g) , (PD 19/02/2024, & Exp 18/02/2026 B.NO.56
2ኛ. #Nura Super Instant Full Cream Milk Powder (400g) PD 01/11/2023 እና Exp 31/10/2025 BT 23246006 LOT No. 230915 291123003127
የወተት ምርቶች የደህንነትና የጥራት መስፈርቶች ያላሟሉ በመሆኑ ህብረተሰቡ እንዳይጠቀማቸው የንግድና ቀጠናዊ ትስስስር ሚኒስቴር አሳስቧል።
@tikvahethiopia
#Update
የአሜሪካ ፕረዚደንት ጆ ባይደን በሜክሲኮ በኩል ወደ አገሪቱ የሚገቡ ስደተኞችን ለመቆጣጠር ሲባል የሀገሪቱን ፍልሰተኞች ሕግ አጥብቀዋል።
ይህ የጆ ባይደን ውሳኔ ባለሥልጣናት በሜክሲኮ በኩል ድንበር አቋርጠው የገቡ ስደተኞችን / ጥገኝነት ጠያቂዎችን በቀጥታ በኃይል ወይም በግዳጅ እንዲመልሷቸው ሥልጣን የሚሰጥ ነው።
ጉዳያቸው የሚመዘገቡ ሰዎች ዕለታዊ ኮታ ከተሟላ የተቀሩት ከአሜሪካ በኃይል እንዲወጡ ይደረጋሉ።
ከዚህ ባለፈ ለአሜሪካ ብሔራዊ ጥቅም አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ የውጪ ዜጋ ወደ አገር እንዳይገባ " #እንዲታገድ " የሚል ትዕዛዝ ፕሬዜዳንቱ አስተላልፈዋል።
#ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ በርካታ አፍሪቃውያን በሜክሲኮ በኩል ወደ አሜሪካ እንደሚሻገሩ ይታወቃል።
አሜሪካ የፍልሰተኞችን ፍሰት ለመግታት በሚል ከሜክሲኮ የሚያዋስናትን ድንበር ከማጠር ጀምሮ በርካታ እርምጃዎችን ስትወስድ ቆይታለች።
ይህ የአሁኑ የፕሬዜዳንት ባይደን ውሳኔ ስደተኞች የጥገኝነት ጥያቄያቸው ለሚመለከተው የስደተኞች ጉዳይ መስሪያ ቤት ቀርቦ ሳይታይ #በቀጥታ እንዲባረሩ የሚያደርግ ነው ተብሏል።
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ፤ የስደተኞች ጉዳይ ኮሚሽን ግን ሕጉ የስደተኞችን መሰረታዊ መብት ይጥሳል ሲል ተቃውሟል።
መረጃው የጀርመን ዜና አገልግሎት፣ የዶቼ ቨለ እና ቢቢሲ ነው።
@tikvahethiopia
#Update
“ 12 ሰዎች እስር ላይ ናቸው። 15 ቀናት አለፋቸው ፤ ምግብ አይገባላቸም ” - የታሳሪ ቤተሰቦች
ከወለጋ ተፈናቅለው በአማራ ክልል ፤ ቡሬ እና ሌሎች አካባቢዎች የነበሩ ተፈናቃዮች ወደ ወለጋ እየተመለሱ በነበረበት ወቅት “ ሰንቶም ” የሚባል ቦታ ሲደርሱ በሚሊሻ የተያዙ እንደነበሩ ከዚህ ቀደም ተዘግቦ ነበር።
አሁንስ የተያዙት ተፈናቃዮቹ ከምን ደረሱ ?
ቤተሰቦቻቸው ለቲክቫህ በሰጡት ቃል፣ “ ያኔ ከመኪና አስወርደው ‘ቁጫ’ የሚባል ቦታ ላይ ለአንድ ሳምንት አሰሯቸው። በኋላም ከ‘ቁጫ’ ወደ ቡሬ አመጧቸው” ብለዋል።
የቡሬ አካላትን ሲጠይቁም ፥ “ ወደ አገራቸው ይሄዳሉ ብለን ላክናቸው መንገድ ላይ አስቀሯቸው። አሁን እዚህ አምጥተው አሰሯቸው። መከላከየ ነበር የያቸው ” እንዳሏቸው አስረድተዋል።
“ 12 ሰዎች በእስር ላይ ናቸው። 15 ቀናት አለፋቸው ፤ ምግብ አይገባላቸም። ገብቶ መጠየቅም አይቻልም ” ብለው፣ የሚመለከታቸው አካላት መፍትሄ እንዲያሰጧቸው ጠይቀዋል።
ተፈናቃዮቹ ለምን እንደታሰሩ እንዲሁም እንዲለቀቁስ ምን እየተሰራ እንደሆነ የጠየቅናቸው “ ተፈናቃዮቹን ፈርመው የላኩ ” የቡሬ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ሃይማኖት ሥራ ላይ እንደሆኑ ገልጸው ስልክ ዘግተዋል።
ቆይት ብለው በላኩት የፅሑፍ መልዕክትም ፣ “ በጣም ይቅርታ የፀጥታ ስራ በመስራት ላይ ሆኘ ነው ” ያሉ ሲሆን፣ የማይመቼዎ ከሆነ ለቀረበው ጥያቄ የፅሑፍ ምላሽ ይስጡ ቢባሉም የሰጡት ቃል የለም።
ወደ ወረዳው የብልጽግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት እንዲሁም የኦሮሚያና አማራ ክልሎች ኮሚዩኒኬሽን ቢሮዎች ተጨማሪ ሙከራ ቢደረግም ስልክ ለማንሳት ፈቃደኛ አልሆኑም።
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
#ማስታወሻ
" የመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥር እና አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1320/2016 " ምን ይዟል ?
➡ የመኖሪያ ቤት አከራዮች #በዘፈቀድ የኪራይ ዋጋ መጨመር #አይችሉም።
➡ አከራይ የኪራይ ዋጋ ጭማሪ ማድረግ የሚችለው ተቆጣጣሪ አካል #በዓመት_አንድ_ጊዜ ነባራዊ የኢኮኖሚውን ሁኔታ እና ሌሎች አግባብነት ያላቸውን ጉዳዮች ከግምት በማስገባት ሊወስን የሚችለውን የመኖሪያ ቤት ኪራይ ጭማሪ መሠረት በማድረግ ነው።
➡ ማንኛውም የቤት ኪራይ ጭማሪ በተቆጣጣሪው አካል በሰኔ 1 ለሕዝብ ይፋ ተደርጎ ከሰኔ 30 ጀምሮ ለአንድ አመት የፀና ይሆናል።
➡ የቤት ኪራይ ውል ዘመን #ሳይጠናቀቅ ተከራይን ከቤት ማስወጣት ወይም በዚህ አዋጅ ከተፈቀደው ሁኔታ ውጪ የዋጋ ጭማሪ ማድረግ አይቻልም። ይህም አስገዳጅ ድንጋጌ ነው።
➡ አከራዮች #ከ2_ወር_የቤቱ_ኪራይ_በላይ ቅድመ ክፍያ መጠየቅ #አይችሉም።
➡ የቤት ኪራይ ክፍያዎች በባንክ ወይም በሌላ ሕጋዊ የኤሌክትሮኒክ ዘዴ መፈፀም አለባቸው። አከራይ እና ተከራይ የቤት ኪራይ ክፍያ ሰነዶችን አደራጅተው #የመያዝ_ግዴታ አለባቸው።
➡ ማንኛውም የቤት ኪራይ ውል በጽሁፍ የሚደረግ ሆኖ በተቆጣጣሪው አካል መረጋገጥ እና መመዝገብ አለበት።
➡️ መኖሪያ ቤት ኪራይ ውል #ከሁለት_ዓመት ሊያንስ አይችልም።
NB. በአዋጁ መሠረት " ተቆጣጣሪው አካል ፣ ማለት የመኖሪያ ቤት ኪራይ ውልን እና ዋጋን እንዲቆጣጠር በክልሎች ወይም በአዲስ አበባ እና ድሬዳዋ ከተማ አስተዳደሮች የሚሰየም አካል ነው፡፡
More : /channel/tikvahethiopia/86580?single
#Ethiopia
#የመኖሪያ_ቤት_ኪራይ_ቁጥጥርና_አስተዳደር_አዋጅ
@tikvahethiopia
#እንድታውቁት
ከነገ ግንቦት 28 /2016 ዓ/ም ጀምሮ የሁሉም የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በስራ ላይ በነበረበት ዋጋ እንዲቀጥል የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር አሳውቋል።
ስራ ላይ ያለው የነዳጅ ምርቶች ዋጋ ስንት ነው ?
- ቤንዚን ➡️ ብር 78.67 በሊትር
- ነጭ ናፍጣ ➡ ብር 79.75 በሊትር
- ኬሮሲን ➡ ብር 79.75 በሊትር
- የአውሮፕላን ነዳጅ ➡ ብር 70.83 በሊትር
- ቀላል ጥቁር ናፍጣ ➡ ብር 62.36 በሊትር
- ከባድ ጥቁር ናፍጣ ➡ ብር 61.16 በሊትር ነው።
@tikvahethiopia
#Update
የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በአዲስ አበባ ከተማ ደረጃ ለ7 ቀናት ሲያደርገው የነበረውን የአጀንዳ ማሰባሰብ መርሐ ግብር ዛሬ አጠናቋል።
በማጠቃለያው መርሐ ግብር ላይ የተገኘው ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለኮሚሽኑ ኮሚሽነር ዶ/ር ዮናስ አዳዬ የተለያዩ ጥያቄዎችን አቅርቧል።
Q. የ7ቱ ቀናት በአ/አ ደረጃ አጀንዳ የማሰባሰብ ሂደትና ውጤቱ ምን ይመስላል ?
ዶ/ር ዮናስ አዳዬ ፦
“ ትኩረቱ የነበረው 3 ነጥቦች ላይ ነው።
የመጀመሪያው ትኩረት በቅንነት ፣ ያለአንዳች መከልከል ፣ ያለመሸማቀቅ ሕዝባችን እንዲወያይ ነበር።
ሁለተኛው ደግሞ የአካባቢን ሁኔታ መሠረት ያደረገ ከጀንዳ ማቅረብ ነበር።
ሦስተኛው ተወካይ መምረጥ ነበር። በአጠቃላይ ሁሉም የተሳካ ነበር። ”
Q. በአ/አ ደረጃ የተሰበሰቡ አጀንዳዎች ምንድን ናቸው ?
ዶክተር ዮናስ አዳዬ ፦
“ አጀንዳዎቹን በሙሉ ሰብስበን፣ ኮሚሽኑ ካጠናቀረ በኋላ እነዚህ የአዲስ አበባ እነዚህ የእነዛ ብሎ መናገር ይሻላል።
አሁን ባለበት ሁኔታ ግን መናገሩ አስፈላጊ አይደለም። ምክንያቱም ሌሎች የሚያስቡትን ማበላሸት ስለሚሆን። ”
Q. በአዲስ አበባ የተደረገው የተወካዮች መረጣ ከኃይማኖትና ፆታ ስብጥር አንፃር ምን ይመስላል ?
ዶክተር ዮናስ አዳዬ ፦
“ እኛ እስከገባን፣ እስካደረግነው ሥራችን ድረስ ፦
° ፆታን፣
° አካል ጉዳተኝነትን፣
° ሃይማኖትን
° የማህበረሰብ ክፍሎችንም፣ ሌላው ቀርቶ የብሔር ስብጥርን የወከለ ይመስላል።
ሴቶችን ለማካተት ተብሎ የታቀደው 30 በመቶ ነው።
በአገራችን የሴቶቻችን ብቃት ምን ያህል ነው? ምን ያህሉ ተማሩ ? በተለያዩ ዘርፎች ሴቶቻችን ብዙ አልተማሩም። ስለዚህ 50 በመቶ ብንል እንዋሻለን። ”
Q. ኢሕአፓ ከምክክሩ እንዳገለለ፣ ኦፌኮና ኦነግ በምክክሩ ዙሪያ ቅሬታ አላቸው። ከጅምሩ የሚስተዋሉ እንዲህ አይነት ተቃርኖዎች ምክክሩን አያደናቅፉትም ? ኮሚሽኑ ችግሩን ለመቅረፍ ምን እየሰራ ነው ?
ዶክተር ዮናስ አዳዬ ፦
“ ስንጀምር ከ60 ፓርቲዎች አብረውን ለመስራት የተስማሙት 2 ወይም 3 ፓርቲዎች ነበሩ። አሁን ደግሞ የቀሩት 3 ወይም 4 ናቸው። 50 ፓርቲዎች ከእኛ ጋር እየሰሩ ነው።
ለምን ? ከተባለ አካሄዳችንን አይተዋል። አካታች፣ ለማንም ያልወገንን ግን ለኢትዮጵያ የወገን፣ ለእውነት የቆምን መሆናችንን ተገንዝበው መጥተዋል።
አሁንም #ለኦፌኮም #ለኦነግም ደብዳቤ ጽፈን ሰጥተናል እንዲመጡ። እና እነርሱ ባይመጡም ሌሎቹ አብረዋቸው የነበሩ እየመጡ እንዳሉ ማዬት ይቻላል።
እንደዚህ አይነት አለመግባባቶች ካሉ፣ ቢኖሩም ብዙም አይገርመንም። ምክክሩም ያስፈለገው እንዲህ አይነት መከፋፈል ስለነበረ ነው። ”
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
ፎቶ፦ የነቀምቴ ኤርፖርት በቅርቡ ስራ ለመጀመር ዝግጁ መሆኑ ተነግሯል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከሰኔ 10/2016 ዓ/ም ጀምሮ በረራ እንደሚጀመር መገለጹ ይታወሳል።
ወደ ነቀምቴ የሚደረገው በረራ በሳምንት 4 ጊዜ ነው።
#Ethiopia #Oromia #Wollega #Nekemte
Photo Credit - #ENA
@tikvahethiopia
#USA
የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በሜክሲኮ በኩል ወደ አሜሪካ የሚገቡ ስደተኞችን ለመቆጣጠር ያለመ አዲስ እና መጠነ ሰፊ ፕሬዝዳንታዊ ትዕዛዝ ዛሬ ይፋ እንደሚያደርጉ ተነግሯል።
ውሳኔው የአሜሪካ ኢሚግሬሽን ባለሥልጣናት በየዕለቱ ከሚመለከቱት በሕገ ወጥ መንገድ የገቡ ተጥገኝነት ጠያቂዎች ቁጥር በላይ አመልካቾች የሚቀርቡ ከሆነ ጥያቄያቸውን ሳይመለከቱ በቀጥታ ከአገር እንዲባረሩ ማድረግ የሚያስችል ሥልጣን ይሰጣል።
ይህም ድንበር ላይ ያሉ ባለሥልጣናት አሜሪካ የሚገቡ #ስደተኞች ቁጥርን እንዲገድቡ እንደሚያስችላቸው ተነግሯል።
ፕሬዝዳንት ባይደን ሥልጣን ላይ በቆዩባቸው ባለፉት 4 ዓመታት ውስጥ ከ6.4 ሚሊዮን በላይ ስደተኞች በሕገ ወጥ መንገድ ወደ አሜሪካ ለመግባት እንደሞከሩ ተነግሯል።
ይህም እስካሁን ከታየው ከፍተኛው ነው።
የአሜሪካ መገናኛ ብዙኃን ፤ ባይደን አሁን ላይ በ1952 የወጣውን በአሜሪካ ጥገኝነት የማግኘት ሥርዓትን ለመገደብ የሚያስችለውን ሕግ ለመጠቀም እያሰቡ እንደሆነ ዘግበዋል።
212 (ኤፍ) በመባል የሚታወቀው ሕግ ወደ አሜሪካ የሚገቡ የውጭ ዜጎች " ለአገሪቱ ብሔራዊ ጥቅም አስጊ የሚሆኑ ከሆነ " ፕሬዝዳንቱ " እንዳይገቡ ማገድ " የሚያስችለው ነው።
#BBC
#USA #Immigration
@tikvahethiopia
#AmazonFashion
አማዞን ፋሽን ለተማሪዎች እንኳን ለመመረቂያ ቀናቹ አደረሳቹ እያለ በዚህ አመትም ለተመራቂ ተማሪዎች ልዩ ቅናሽ አድርገናል።
ኮት ብቻ 3 ሺ ብር ሙሉ ልብስ በ5 ሺ ና በ8 ሺህ፣ ሸሚዝ በ1200 ፣ ጫማ በ2200 ብር ብቻ ።
አድራሻ ፦ ፒያሳ የገበያ ኣዳራሽ ወይም ፒያሳ የድሮው ዳውንታውን ህንፃ ምድር ላይ።
ስልክ ፦ 0920880443/ 0919339250
Telegram👉https://t.me/joinchat/AAAAAEc8iQJX1Zjgepjq1w
ኦነግ እና ኦፌኮ በውይይቱ ተገኝተው ነበር ?
#አልተገኙም
" ውይይት መደረጉን የሰማነው እራሱ በሚዲያ ነው " - ኦፌኮ
በኦሮሚያ ክልል ይንቀሳቀሳሉ ከተባሉ ፓርቲዎች ጋር የክልሉ መንግሥት አድርጎታል በተባለው ውይይት ላይ የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) እና የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) #አልተሳተፉም።
የኦፌኮ ዋና ፀሀፊ አቶ ጥሩነህ ገምታ ለቪኦኤ ሬድዮ ፥ " ውይይቱ መደረጉን የሰማነው ከብዙሃን መገናኛ ነው። እንደ ግለሰብ ይሁን እንደ ተቋም የደረሰን ጥሪ የለም የኮሚኒኬሽን ክፍተቱ ከማን በኩል እንደሆነ አላውቅም " ብለዋል።
ኦፌኮ የክልሉ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አባል ቢሆንም ባለው ቅሬታ ሙሉ ተሳትፎ እያደረገ እንዳልሆነ ገልጸዋል።
አቶ ጥሩነህ ፤ ለውይይት በም/ቤት ይሁን በመንግስት ጥሪ አልደረሰንም ብለዋል።
የኦነግ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ለሚ ገመቹ በበኩላቸው ፤ ፓርቲያቸው በውይይቱ #እንዳልተሳተፈ ገልጸዋል።
" ለውይይቱ ጥሪ ሊደረግ ይችላል እኛ ግን የምንፈልገው በአንድ አካል አቅራቢነት የሚደረገውን ውይይት ሳይሆን ሁሉም በእኩልነት የሚሳተፍበትን ውይይት ነው። " ብለዋል።
" የምንፈልገው አንድ ሀገርን የሚያስተዳደር መንግሥት በሚሰጥህ ቦታ ተወስኖ መወያየት ሳይሆን እራሳችንን የመፍትሄ አካል ነን ብለን የምናይ አካላት በአንድ ላይ ሆነን በተመሳሳይ ድምጽ ተወያይተን ዘላቂ መፍትሄ የምናስቀምጥበት ካልሆነ ኦነግ በአንድ አካል ጥሪ የሚሳተፍበት መድረክ አይኖርም " ሲሉ ተናግረዋል።
የኦሮሞን ችግር የሚፈተው በእውነታ ላይ የተሰመሰረተ አካታች ውይይት እንደሆነ የገለጹት አቶ ለሚ ፤ ውይይት ሂደቱን ጠብቆ አካታች በሆነ መልኩ መከናወን አለበት አሁን ያለው አካሄድ ሂደቱን ያልጠበቀ ቅንነት የሌለው በአንድ አካል ብቻ ተጎትቶ እየሄደ ያለ ነው ሲሉ ቅሬታቸውን ገልጸዋል።
የክልሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች ም/ቤት ሰብሳቢ እና የአዲስ ትውልድ ፓርቲ ፕሬዜዳንት አቶ ሰለሞን ታፈሰ ኦነግ እና ኦፌኮ ከውይይት መቅረታቸውን አረጋግጠዋል።
" በድረገጻችን ላይ ለቀናል፣ በዋትስአፕ ላይ ተለቋል። እንደምንሄድ ኮሚቴው ሲወስን ተለቋል። በአካል አነጋሬያለሁ የሚመለከታቸውን ኦሮሚያ የኢትዮጵያ እምብርት ናት እናተ ስለሚመለከታችሁ ለምን አብረን አንሄድም? ብዬ ነግሬያቸዋለሁ። ተጋብዘዋልም " ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል።
#Ethiopia
#Oromia #VOA
#OFC #OLF
@tikvahethiopia
#EthiopianAirlines
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለበረራ ኤርፖርት የሚመጡ ሁሉ የመንገድ መዘጋቱን ታሳቢ እንዲያደርጉ አሳሰበ።
የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ በመንገድ ኮሪደር ልማትና የአስፓልት ንጣፍ ስራ ምክንያት ወደ ቦሌ ዓለም-አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የሚወስዱ አንዳንድ መንገዶች በከፊል ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚሆኑ አስታውቋል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድም መንገደኞች ለበረራ ወደ ኤርፖርት በሚሄዱበት ወቅት ይህን ታሳቢ በማድረግ ሊከሰት ከሚችል መዘግየት ራሳቸው እንዲጠብቁ አሳስቧል።
የሚዘጉት መንገዶች #የትኞቹ_ናቸው ? በዚህ ሊንክ ይመልከቱ ፦ /channel/tikvahethiopia/88048
#EthiopianAirlines
@tikvahethiopia
ፎቶ ፦ በሚያዝያ ወር መጀመሪያ አዲስ አበባ ቦሌ ሚሊኒየም አዳራሽ አካባቢ ከፖሊስ ጋር በተደረገ የተኩስ ልውውጥ የተገደሉት ሁለት የፋኖ አባላት ቤተሰቦች አስከሬናቸውን ሳያገኙ ፍትሃትና ባህላዊ የሽኝት ሥነ ሥርዓት ጎንደር ውስጥ ፈጽመዋል።
ሁለቱ ወጣቶች ማለትም ፦
- ናሁሰናይ አንዳርጌ
- አቤኔዘር ጋሻው በተኩስ ልውውጥ ከተገደሉ በኃላ ወላጆቻቸው ወደ አዲስ አበባ በመምጣት አስከሬናቸውን አግኝተው ቀብር ለመፈጸም ፌደራል ፖሊስ ፣ አዲስ አበባ ፖሊስ ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት ድረስ ጥያቄ ቢያቀርቡም ምላሽ ሳያገኙ 2 ወር ለሚጠጋ ጊዜ መጠበቃቸውን እና በመጨረሻም ተስፋ መቁረጣቸውን ተናግረዋል።
ዛሬ ግንቦት 26 ቀን 2016 ዓ.ም. ጎንደር ውስጥ የናሁሰናይ አንዳርጌ አስከሬኑ በሌለበት በባህላዊ መንገድ በቤተሰብና በወዳጆች ፍትሃቱና የሽኝት ሥነ ሥርዓቱ በአባ ጃሌ ተክለሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ተፈጽሟል።
አንድ የቤተሰብ አባል ፤ ለቀስተኛው ካለ አስከሬን በተካሄደው የስንብት ሥነ ሥርዓት ላይ ለመታደም ወደ ቤተ-ክርስቲያን እያመራ ሳለ የመንግሥት ፀጥታ ኃይሎች የናሁሰናይ ፎቶ እና ስም ያለበትን 2 ባነር በኃይል ተቀብለዋል። ከዚህ ውጭ ምንም የተፈጠረ ነገር የለም " ብለዋል።
የአቤኔዘር ጋሻው የሽኝት በተመሳሳይ ቤተሰቡ አስከሬኑ ባላገኘበት ሁኔታ ቀደም ብሎ መከናወኑን የቤተሰቡ አባላት ገልጸዋል።
#Credit - BBC AMHARIC
@tikvahethiopia
በየትኛውም ስፍራ፣ በማንኛውም ሰዓት!
ሕብር ሞባይል ባንኪንግን በማውረድ ሂሳብዎን በቅርበት እና በቀላሉ ይከታተሉ፡፡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ!
https://www.hibretbank.com.et/hibir-mobile-landing-page/
ሕብረት ባንክ
በሕብረት እንደግ!
ለበለጠ መረጃ ወደ 995 ነፃ የጥሪ ማዕከል ይደውሉ፡፡ አዳዲስ መረጃ እንዲርሶ የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎች ይጫኑ፡፡
ቴሌግራም- /channel/HibretBanket
ሊንክዲን- https://www.linkedin.com/company/hibretbank/
ዌብሳይት- https://www.hibretbank.com.et/
#Hibretbank
#እንድታውቁት #AddisAbaba
በመንገድ ኮሪደር ልማትና በአስፓልት የማንጠፍ ስራ ምክንያት ከመስቀል አደባባይ ወደ ቦሌ አየር መንገድ የሚወስደው ዋናው መንገድ በከፊል ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚሆን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡
መዚህ መሰረት ፡-
- ከለገሐር በመስቀል አደባባይ ወደ ቦሌ አየር መንገድ
- ከእስጢፋኖስ በቀጥታ ወደ ቦሌ አየር መንገድ
- ከኡራኤል በመስቀል አደባባይ ወደ ቦሌ አየር መንገድ
እንዲሁም #በውስጥ_ለውስጥ ወደ ዋናው ቦሌ አየር መንገድ የሚወስዱ መንገዶች ከዛሬ ግንቦት 26 ቀን 2016 ዓ/ም ጀምሮ #በየዕለቱ ስራው እስኪጠናቀቅ ድረስ ከቀኑ 8:00 ሰዓት እስከ ንጋቱ 12:30 ሰዓት ለተሽከርካሪ በከፊል ዝግ ይሆናሉ።
አሽከርካሪዎች የትራፊክ መጨናነቅ እንዳያጋጥማቸው ሌሎች አማራጭ መንገዶችን መጠቀም እንዳለባቸው አዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡
#AddisAbabaPolice
@tikvahethiopia
#ሴጅ_ማሰልጠኛ
21ኛ ዙር የግራፊክስ ዲዛይን፣ ቪዲዮ ኢዲቲንግ፣ ሞሽን ግራፊክስ እና ዲጂታል ማርኬቲንግ ስልጠና ምዝገባ ላይ ነን። ቀድመው ይመዝገቡ!
👉 100% በተግባር የተደገፈ ስልጠና
👉 Advanced Graphics + Video Editing + Motion Graphics + Digital Marketing በአንድ ላይ
👉 ከ50 በላይ ፕሮጀክቶች ያሉት
👉 የሥራ ላይ ስልጠና (Internship) የተመቻቸለት
ስልክ፦ 0906777799 / 0906777755
አድራሻ፦ ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ
Telegram: /channel/sagetraininginstitute
Linkedin: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute
#StateofEmergency #EHRC
" በእስር የቆዩ ሰዎች ሊለቀቁ ይገባል " - ኢሰመኮ
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (#ኢሰመኮ) ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አተገባበር ጋር በተያያዘ በእስር የቆዩ ሰዎች እንዲለቀቁ ጠየቀ።
በአማራ ክልል በመንግሥት እና በታጣቂ ኃይሎች (በተለምዶ “#ፋኖ”) መካከል ከሚካሄደው የትጥቅ ግጭት ጋር ተያይዞ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ከሐምሌ 28 ቀን 2015 ዓ/ም ጀምሮ ተግባራዊ የነበረው እና ጥር 24 ቀን 2016 ዓ/ም ለተጨማሪ 4 ወራት የተራዘመው የአስቸኳይ ጊዜ ሁኔታ አዋጅ ተፈጻሚነት አብቅቷል።
ይህንን ተከትሎ በእስር የቆዩ ሰዎችን የመልቀቅ ሂደት እንዲቀጥል ኢሰመኮ አሳስቧል።
ኮሚሽኑ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ አፈጻጸም በሰብአዊ መብቶች አያያዝ ላይ ያለውን ተጽዕኖ በተመለከተ ክትትልና ምርመራ ሲያደርግ መቆየቱን ገልጿል።
ከአዋጁ ትግበራ ጋር የተስተዋሉ ክፍተቶችንና የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶችን የሚያመላክቱ፣ እንዲሁም ምክረ ሐሳቦችን ያካተቱ ግንቦት 20 ቀን 2016 ዓ.ም. ይፋ ያደረገውን ጋዜጣዊ መግለጫ ጨምሮ በተለያዩ ጊዜያት በርካታ የክትትልና የምርመራ ሪፖርቶች ይፋ ሲያደርግ የቆየ መሆኑ አስታውሷል።
በዚሁ አዋጅ አተገባበር ዐውድ ውቅጥ #በእስር የቆዩ ሰዎች እንዲለቀቁ ማድረግን ጨምሮ ወደ መደበኛው የሕግ አተገባበር ሂደት መመለስ፣ እንዲሁም በተለያዩ የክልል አካባቢዎች የተጣሉ የእንቅስቃሴ ገደቦች እንዲነሱ እና ሌሎችም ማኅበረሰባዊ #አገልግሎቶች እንዲመለሱ ኢሰመኮ ጥሪ አቅርቧል።
#EHRC #Ethiopia #StateofEmergency
@tikvahethiopia
#Update #Axum
የአክሱም ኤርፓርት ሰኔ 2/2016 ዓ/ም ዳግም የበረራ አገልግሎት መስጠት ይጀምራል።
በትግራይ ጦርነት ከፍተኛ የሆነ ጉዳት የደረሰበት የአክሱም አፄ ዮውሀንስ አራተኛ ኤርፖርት ሰኔ 2 የመጀመሪያ ዳግም በረራውን ያደርጋል።
እሁድ ሰኔ 2 በኤርፓርቱ ዳግም መደበኛ የበረራ አገልግሎት ስነ-ሰርዓት ማስጀመሪያ ጥሪ የተደረገላቸው የክልልና የፌደራል ባለስልጣናት እንደሚገኙ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከአክሱም ከተማ ኮሙኒኬሽንና ህዝብ ግንኙነት ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle
@tikvahethiopia
#ሴጅ_ማሰልጠኛ
5ኛ ዙር ADVANCED STANDARDS AND PRACTICES OF ACCOUNTING ስልጠና ምዝገባ ላይ ነን። አሁኑኑ ይመዝገቡ!
👉 IFRS + Peachtree + Asset Valuation + IFRS Conversion + IPSAS + Quick Book በአንድ ላይ
👉 ስልጠናው ለ5ወር የሚቆይ ነው።
👉 ስልጠናው ሙሉ በሙሉ በተግባር የተደገፈና ፒስትሪ (Peachtree Software) ላይ የሚሰጥ ነው።
ስልክ፦ 0906777799 / 0906777755
አድራሻ፦ ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ
Telegram: /channel/sagetraininginstitute
Tiktok: sage_training_institute" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@sage_training_institute
Linkedin: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute
#AddisAbaba
በአዲስ አበባ ከተማ የአከራይ እና ተከራይ ህጋዊ ውል ምዝገባ ሰኔ 1 ቀን 2016 ዓ.ም እንደሚጀመር የቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ አስታውቋል።
የመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥር እና አስተዳደር አዋጅ መጽደቁ ይታወቃል፡፡
በዚህም አስተዳደሩ አዋጁን በመመሪያ በማስደገፍ ወደ ስራ ለማስገባት ዝግጅቶቹን ማጠናቀቁ ተገልጿል።
ከሰኔ 1 እስከ 30 ቀን 2016 ዓ.ም በከተማዋ ውስጥ የሚገኙ የግል ቤት አከራዮች ከተከራዮቻቸው ጋር ህጋዊ ሰነዶቻቸውን ይዘው በመቅረብ ምዝገባ ማድረግ ይችላሉ ተብሏል።
ቤት አከራዮች ፦
➡️ ህጋዊ የምዝገባ ውል ለመፈጸም ወደ ወረዳ ጽ/ቤቶች በሚሄዱበት ወቅት ቤቱ የራሳቸው ስለመሆኑ ወይንም ህጋዊ ተወካይ መሆናቸውን የሚገልጽ ሰነድ ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል።
ተከራዮች ፦
➡️ ማንነታቸውን የሚገልጽ #መታወቂያ ወይም ሌላ ህጋዊ ማንነታቸውን የሚያረጋግጥ ሰነድ ይዘው መቅረብ አለባቸው።
በስራ ሰዓት መመዘግብ የማይችሉ አከራይና ተከራዮች ቅዳሜና እሁድ እንዲሁም በስራ ቀን ማታ ከ12 ሰዓት በኋላ ህጋዊ የውል ምዝገባውን መፈጸም ይችላሉ።
#ENA
#Ethiopia
#AddisAbaba
@tikvahethiopia
🇪🇹 #NationalDialogue 🇪🇹
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለአገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር ፕ/ር መስፍን ዓርዓያ ፦
° እናት ፓርቲ ፣
° ኢሕአፓ ፣
° የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) እና የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ፓርቲዎች በምክክሩ ዙሪያ ቅሬታ አላቸው።
አንዳንዶቹ እኛ እየሰማን ያለነው በመገናኛ ብዙሃን ነው የሚሉ አሉ። በዚህ ጉዳይ ላይ እርሶ ምን ይላሉ ? ሲል ጠይቋል።
ፕ/ር መስፍን አርአያ ፦
“ በጣም የሚያደክሙ ጥሪዎች አድርገናል። በደብዳቤ ሳይቀር፣ ለኦነግ፣ ለኦፌኮ ለሁሉም ፓርቲዎች ጽፈናል።
የፓለቲካ ፓርቲዎች ከእኛ ጋር እንዳውም ውስጣችን ገብተው እየሰሩ ነው።
በእርግጥ በአሁኑ ሰዓት በአንዳንዶቹ የደረሱ ክስተቶች አሉ። እነዚህን ክስተቶች በጽሞና እያየናቸው ነው በአቅማችን።
እናት ፓርቲም መግለጫ አውጥተዋል ፤ አጀንዳዎቻቸውን ቀደም ብለው ሰጥተውናል።
እናም ያ ሀገራዊ ምክክሩ እስኪደርስ ድረስ መቼም ጥቂት ወራት መፍጀቱ አይቀርም። እነዛ ሁሉም ነገሮች በአምላክ ፈቃድ ይስተካከሉ ይሆናል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ።
ወደ 50 የሚሆኑ ፓርቲዎች አብረውን እየሰሩ ነው። ሁሉንም እናካትታለን፤ ዝም ያሉትንም #ዱር ያሉትንም። ”
#NationalDialogue
#Ethiopia
#TikvahEthiopia
@tikvahethiopia
20 % ተጨማሪ የገንዘብ ስጦታ + የዕድል ጨዋታ!
በአጋሮቻችን በኩል ባሕር ማዶ ከሚኖሩ ወዳጅ ዘመዶችዎ የተላከልዎትን ገንዘብ በቀጥታ በቴሌብር ዓለም አቀፍ ሃዋላ ሲቀበሉ 20% ተጨማሪ የገንዘብ ስጦታ እና የአየር ሰዓት የሚያሸልም የዕድል ጨዋታ ውስጥ ይካተታሉ፡፡
እስከ ሰኔ 23 ቀን 2016 ዓ.ም የሚቆይ!
ለበለጠ መረጃ ማስፈንጠሪያውን bit.ly/3ArwoEO ይጠቀሙ፡፡
#Ethiotelecom #telebirr #DigitalAfrica #DigitalEthiopia #RealizingDigitalEthiopia
ፎቶ ፦ የአክሱም አፄ ዮውሀንስ አራተኛ ኤርፖርት #በተያዘለት_የጊዜ_ሰሌዳ አገልግሎት መስጠት እንዲጀመር የሚያስችሉት የጥገና ስራዎች አሁን ላይ ወደመጠናቀቁ መሆናቸው ተነግሯል።
በትግራይ ጦርነት ከፍተኛ የሆነ ጉዳት የደረሰበት ኤርፖርቱ የጥገና ስራው ቀን እና ሌሊት እየተሰራ ነበር።
የጥገና ተቆጣጣሪ አካል የአውሮፕላን ማረፍያው የሚገባውን ጥራት በያዘ ደረጃ ስራው እየተሰራ መሆኑን ጠቁሟል።
በረራው እንዲጀመር በተቀመጠለት የጊዜ ሰሌዳ በረራው እንዲጀመር የማጠናቀቅ ስራ እየተሰራ እንደሆነ ገልጿል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከሰኔ 1 ቀን 2016 ዓ/ም ጀምሮ ወደ አክሱም መደበኛ በረራ እንደሚጀመር ማሳወቁ ይታወሳል።
#Ethiopia #Tigray #Axum
Photo Credit - Tigray TV
@tikvahethiopia
#Update
ፓርላማው ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ ( #ህወሓት ) ዳግም ህጋዊ እውቅና ሊያገኝ የሚችልበትን / በድጋሚ እንዲመዘገብ የሚፈቅድለትን የአዋጅ ማሻሻያ አጽድቋል።
" የኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ እና የምርጫ ስነምግባር አዋጅን " የሚያሻሽለው የህግ ረቂቅ የጸደቀው በ2 የፓርላማ አባላት ተቃውሞ፣ በአንድ ድምጸ ተዐቅቦ፣ በአብላጫ ድምጽ ነው።
" በአመጽ እና በህገ-ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀስ የነበሩ " የፖለቲካ ፓርቲዎችን " በልዩ ሁኔታ " እንዲመዘገቡ የሚያስችለው የህግ ማሻሻያ፤ የፖለቲካ ቡድኖቹ ሊያሟሉ የሚገባቸው መስፈርቶችን እና የምርጫ ቦርድን ኃላፊነት የዘርዘረ ነው።
የጸደቀው የአዋጅ ማሻሻያ ፥ " ኃይልን መሰረት ያደረገ የአመጻ ተግባር ላይ ተሰማርቷል " በሚል " ህጋዊ ሰውነቱ እንዲሰረዝ " የተደረገው ህወሓት #በድጋሚ እንዲመዘገብ የሚያስችሉ አንቀጾችን በውስጡ ይዟል።
" አንድ የፖለቲካ ቡድን ኃይልን መሰረት ያደረገ የአመጽ ተግባር ውስጥ የተሳተፈ እንደሆነ እና ይህንን ተግባር ማቆሙን እና ሕገ መንግስታዊ ዲሞክራሲያዊ ስርዓትን አክብሮ ለመንቀሳቀስ መስማማቱ በሚመለከተው የመንግስት አካል ከተረጋገጠ፣ የፖለቲካ ቡድኑ በልዩ ሁኔታ እንደ ፖለቲካ ፓርቲ ሊመዘገብ ይችላል " ሲል አዋጁ ደንግጓል።
#EthiopiaInsider
#TPLF
@tikvahethiopia
ወጣትነት በዘህራህ ልዩ ከወለድ ነጻ የሴቶች ቁጠባ ሒሳብ ሲታገዝ፣ የስኬት ጉዞ ከመቼውም ይልቅ ይፋጠናል!
አቢሲንያ አሚን ዕሴትዎን ያከበረ!
የተለያዪ ጠቃሚ ምክሮችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ ።
/channel/BoAEth
#AbyssiniaAmeen #IFB #bankofabyssinia #አቢሲኒያአሚን
#ዘህራ #የሴቶችቁጠባ #የሁሉም_ምርጫ
#OROMIA #PEACE
" የመንግሥት ወታደሮች ፣ ሌላም ፣ ንጹሃንም ዋጋ መክፈል የለባቸውም፤ ... ለሰላም ክፍት ነን ድርድሮችም እንዲቀጥሉ እንፈልጋለን " - የኦሮሚያ ክልል መንግሥት
የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት አሁንም ቢሆን ያሉ ችግሮች #በሰላም እንዲፈቱ መንግሥት #ለድርድር ዝግጁ መሆኑን አሳውቋል።
የክልሉ መንግሥት አመራሮች ከኦሮሚያ ክልል የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ጋር በአዲስ አበባ እንደመከሩ ተነግሯል።
በምክክሩ ላይ የተገኙት የአዲስ ትውልድ ፓርቲ ፕሬዜዳንት እና የኦሮሚያ ክልል የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ም/ቤት ሰብሳቢ አቶ ሰለሞን ታፈሰ ውይይቱ ልማትና ጸጥታ ላይ ትኩረት ያደረገ ነው ሲሉ ለቪኦኤ ተናግረዋል።
በውይይቱ ፦
- የልማት ስራ ያለ ሰላም ውጤት አልባ እንደሆነ / ሰላም ለሁሉም ነገር መሰረት እንደሆነ ፤
- ሰው ሰርቶ የሚበላው ፣ ወልዶ የሚስመው ሰላም ሲኖር እንደሆነ አጽንኦተ ተሰጥቶበታል ብለዋል።
" ሰላም ለመንግሥት ብቻ የተተወ ስላልሆነ እንዴት ነው አብሮ መስራት የሚቻለው ? " የሚለውም መነሳቱን አስረድተዋል።
" መንግሥት እና ሸኔ የጀመሩት ድርድር ፤ በተለያየ ምክንያት አኩርፈው ጫካ የገቡ ነፍጥ ያነገቡ ጓዶች አሉ ፤ መንግሥት በሆደ ሰፊነት ዛሬ ነገ ሳይል እነዚህን አካላት ጠርቶ በጠረጴዛ ዙሪያ መነጋገር አለበት ይህ ሲደረግ ደግሞ ለሰዎቹ እውቅና ተሰጥቶ የህግ ከለላ ተሰጥቶ ነው ውይይት መደረግ ያለበት " የሚለውም መነሳቱን ገልጸዋል።
" በመንግሥት በኩል ' ዛሬም ቢሆን ክፍት ነው እንነጋገራለን ፣ ችግሮችን በጋራ ተነጋግረን እንፈታለን ' የሚል ምላሽ ነው የተሰጠን " ሲሉ ተናግረዋል።
የኦሮሚያ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍቃዱ ተሰማ አሁንም ቢሆን የክልሉ መንግሥት በውይይት ያምናል ብለዋል።
" የመንግሥት ወታደሮች ፣ ሌላም ፣ ንጹሃንም ዋጋ መክፈል የለባቸውም፤ ሙሉ ትኩረታችን ወደ ሰላም ማምጣት ነው ያለብን። የፈለግነውን ነገር በአዳራሽ መወያይት ይቻላል። ጥረቶች ብዙ ነው ያደረግነው አሁንም ለሰላም ክፍት ነን እኛ 3ኛ ዙር ይሁን፣ 5ኛ ዙር ይሁን ፣ 10ኛ ዙር ድርድሮች እንዲቀጥሉ እንፈልጋለን " ብለዋል።
#Ethiopia
#Oromia #VOA
@tikvahethiopia
🇪🇹 #NationalDialogue 🇪🇹
➡️ " በሃገራዊ ምክክሩ #ሁሉም አካላት ካልተሳተፉ ምክክሩ ውጤት ላያመጣ ይችላል " - የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት
➡️ " ያኮረፉ እና ጫካ የገቡ #ታጣቂዎች በምክከሩ እንዲሳተፉ ከሲቪል ማህበረስብ እና ከተለያዩ ሀገራት #ኤምባሲዎች ጋር እየሰራን ነው " - ኮሚሽኑ
የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ም/ቤት እየተደረጉ ያሉ ግጭቶች ቆመው ሁሉም አካላት ወደ ንግግር አንዲመጡ ጠይቋል
የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ጫካ የሚገኙት ታጠቂዎች በምክክሩ ላይ እንዲሳተፉ ከለላ እንዲደረግላቸው መንግስትን የመጠየቅ ፍላጎት እንዳለው ገልጿል።
የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ም/ቤት ሰብሳቢ ደስታ ዲንቃ " በሃገራዊ ምክክሩ ሁሉም አካላት ካልተሳተፉ ምክክሩ ውጤት ላያመጣ ይችላል " ብለዋል፡፡
በጫካ ያሉ ታጣቂዎች በምክክሩ አንዲሳተፉ ለዚህ ሁኔታዎች እንዲመቻቹ ምክር ቤቱ የጠየቀ ሲሆን ፥ " ይህ ካልሆነ ግን የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ስራ ውጤት ላያመጣ ይችላል " ሲል የጋራ ም/ቤቱ ስጋቱን ተናግሯል።
#ሌላው_ስጋት ብሎ ያነሳው ደግሞ የምክክር ኮሚሽኑ የተቋቋመበት አዋጅ ግጭቶችን የማስቆም ሃላፊነት አልተሰጠውም ግጭት ሳይቆም በግጭት ውስጥ የሚደረግ ምክክር ደግሞ ውጤት ላያመጣ ይችላል ብሏል፡፡
የጋራ ም/ቤቱ ከጅምሩ ጀምሮ " በምክክሩ አንሳተፍም " ያሉ ፓርቲዎችን፣ በተለያየ ክልሎች ያሉ ታጣቂዎች በምክክሩ እንዲሳተፉ እንዲደርግ ኮሚሽኑን ጠይቋል፡፡
የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር የሆኑት ዶክተር ዮናስ አዳዬ ምክክሩ አሳታፊ እንዲሆን፣ ያኮረፉ እና ጫካ የገቡ ታጣቂዎች በምክከሩ እንዲሳተፉ ከሲቪል ማህበረስብ እና ከተለያዩ አለም ሀገራት ኤምባሲዎች ጋር እየሰራን ነው ሲሉ ተናግረዋል።
" ጫካ የገቡ አካላት በምክክሩ እንዲሳተፉ በመገናኛ ብዙሃን ተደጋጋሚ ጥሪዎችን እያደረግን ነው " ያሉት ዶ/ር ዮናስ " ሕጋዊ የሆነ መስሪያ ቤት ስለሌላቸው ጥሪ ለማድረግ ተቸግረናል፣ እዚህ ነን አለን የሚሉ ከሆነ የተመካከሩ ጥሪ ወረቀት ይዘን ለመሄድ ዝግጁ ነን " ብለዋል፡፡
Credit - Sheger FM 102.1
@tikvahethiopia
#WKU
" አሳይመንቱን ቤት ድረስ አምጥተሽ ስጪን " በማለት ተማሪውን ደፍሯል የተባለው የዩኒቨርሲቲ መምህር ጉዳዩ በፍርድ ቤት እየታየ ይገኛል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ሰሞኑን ከወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ #ሴት ተማሪዎች መልዕክቶችን ተቀብሏል።
ይህም " የሴቶች ጥቃት አሳስቦናል " የሚል ነው።
ተማሪዎቹ የመደፈር እና የጥቃት ወንጀል በመምህር ሳይቀር መፈጸሙን በመግለጽ ስጋታቸውን ገልጻዋል።
በየጊዜው እንዲህ ያለ ነገርም እንሰማለን ነው ያሉት።
ከጠቆሙት አንዱ ጉዳይ በመምህሯ የተደፈረችን ተማሪ የሚመለከት ነው።
በተማሪዎች ስለሚነሳው ጉዳይ ተቋሙ ምን ይላል ? በማለት ጥያቄ አቅርበናል።
ስማቸው እንዲገለጽ ያልፈለጉ የዩኒቨርሲቲው አመራር የመምህሩ ጉዳይ #ከ2_ወራት_በፊት መከሰቱን እና ከአስገድዶ መድፈር ጋር በተያያዘ በቅርብ የተፈጸመ ጥቃት አለመኖሩን ገልጸዋል።
" ወንጀሉን ከ2 ወራት በፊት እንደፈጸሙ የተጠረጠሩት መምህር በህግ ቁጥጥር ስር ውለው ፍርዳቸውን እየተጠባበቁ ነው " ብለዋል።
ድርጊቱ እንዴት ተፈጸመ ?
በወቅቱ አንድ የሂሳብ መምህር በክፍል ውስጥ ሆነው ከተማሪዎቻቸው አሳይንመንት በመቀበል ላይ ነበሩ። የአንደኛዋን ተማሪያቸውን ወረቀት ግን ሳይቀበሉ ነበር የወጡት።
ይሁንና " #አልቀበልሽም " የተባለችው ተማሪም ምን አድርጌ / ምንስ አጥፍቼ ነው ? ብላ በምትጨነቅበት ሰአት ከክፍሉ ተጠሪ ያገኙትን ስልክ ተጠቅመው የደወሉላት መምህር " አሳይመንትሽን ቤቴ መጥተሽ ማስረከብ ትችያለሽ " ይሏታል።
ተማሪዋም በተሰጣት አድራሻ ተመርታ ወደተባለችው ቦታ ትሄዳለች። የጠበቃት ግን አሳይመንቱን መቀበል ሳይሆን ሌላ ነበር።
ተማሪዋ እያነባች ጓደኛዋን ይዛ ወደሆስፒታል ካመራች በኃላ በሆስፒታል ህክምና አግኝታለች።
የሆስፒታል ማስረጃዋን ይዛም ወደ ዩኒቨርሲቲዉ ሂዳ አመልክታቸለች።
በወቅቱ ዩኒቨርሲቲው በተማሪዋ አቤቱታና በቀረበዉ የህክምና ማስረጃ መሰረት ጉዳዩን ወደ #ዲስፕሊን በመዉሰድ በፍጥነት መምህሩን ከስራ ሊያግድ ችሏል።
መምህሩ ድርጊቱን ከፈጸመ በኋላ #ራሱን_ደብቆ እና ስልኩን አጥፍቶ ቆይቷል ተብሏል።
የዩኒቨርስቲው አስተዳደር #የስራ_እግድ ማሳለፉንም ተከትሎ ከተደበቀበት በመዉጣት ሲመለስ ጉዳዩን ከዩኒቨርስቲው በመረከብ ይዞ መምህሩን ሲያፈላልግ የነበረው ፖሊስ #በቁጥጥር_ስር ሊያውለው ችሏል።
አሁን ላይ የምርመራ ሂደቱ አልቆ ፍርዱን እየተጠባበቀ ሲሆን ወደፊት የፍርድ ሂደቱ የሚገለጽ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል።
ከሰሞኑ በዚሁ በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ አንድ ሽጉጥ የታጠቀ ወጣት በዩኒቨርሲቲው ውስጥ ተኩስ በመክፈቱ አንዲት ተመራቂ ወጣት ተማሪና አንድ መምህር መጉዳቱን መረጃ መለዋወጣችን ይታወሳል👉 /channel/tikvahethiopia/88025
@tikvahethiopia
#SouthAfrica
ከሰሞኑን በደቡብ አፍሪቃ " የ2024 ምርጫ " ተደርጎ ነበር።
በምርጫው ማንም አሸናፊ አልሆነም።
የዘንድሮ ምርጫ ገዢው ፓርቲ የአፍሪቃ ብሔራዊ ምክር ቤት / ANC / 40.18 በመቶ ድምጽ በማግኘት ቀዳሚ ቢሆንም መንግሥት መመስረት የሚያስችለውን ድምጽ ግን አላገኘም።
ፓርቲው በ30 ዓመታት የመሪነት ታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ አብዛኛውን የምክር ቤት መቀመጫ ተነጥቋል።
በዚህም መንግሥት ለመመስረት ከተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች መጣመር ግድ ይለዋል።
ፓርቲው ምክር ቤቱ ካለው 400 መቀመጫዎች 159 ብቻ ነው ያሸነፈው።
የወቅቱ የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎዛ መንግሥት ለመመስረት #ከተቃዋሚዎች ጋር እንደሚነጋገሩ አመልክተዋል።
በምርጫው 87 መቀመጫዎችን ያሸነፈው የመሃል ቀኝ ዘመሙ ዴሞክራሲያዊ ጥምረት (DA) ነው።
ከገዢው ፓርቲ ጋር ጥምር መንግሥት ለመመስረት የሚያስችል ንግግር ለማድረግ መዘጋጀቱን አስታውቋል።
ሶስተኛ ሆኖ ያጠናቀቀው የቀድሞ ፕ/ት ጃኮብ ዙማ ፓርቲ MK ሲሆን ከገዢው ፓርቲ ጋር የመነጋገር ፍላጎት ቢኖረውም " ራማፎዛ ሥልጣን ላይ እያሉ ንግግር አላደርግም " ማለቱን ዶቼ ቨለ ዘግቧል።
በዘንድሮ ሀገር አቀፍ ምርጫ እጅግ በርካታ #ወጣቶች ድምፅ መስጠታቸው የተሰማ ሲሆን ገዢውን ፓርቲ የአፍሪቃ ብሔራዊ ምክር ቤት /ANC/ በድምጻቸው #ቀጥተውታል።
ለዚህ ደግሞ ፦
- የከፋ ሙስና
- የመልካም አስተዳደር ችግር
- ስራ አጥነት መፋፋት
- የወንጀል መባባስ ... ዋነኞቹ ምክንያቶች እንደሆኑ ተነግሯል።
@tikvahethiopia
#Axum #Tigray
" በጦርነቱ ጊዜ እኮ #መከራው ከባድ ነበር !! "
ወ/ሮ በላይነሽ መኣሾ (የአክሱም ነዋሪ ለድምጺ ወያነ) ፦
" ሰላም በመሆኑ ጥሩ ነው ያለው። ብርሃን አየን።
በሰላም እየተንቀሳቀስን ነው። #ሕጻናት እየተጫወቱ ነው።
ብዙ ለውጥ ነው ያለው።
በጦርነቱ ጊዜ እኮ #መከራው እጅግ ከባድ ነበር። አሁን በጣም በጣም ይሻላል ፤ ቢያንስ #እፎይ ብለን መተኛት እንችላለን።
ቢሆንም ግን #የከፋው_ሰው_አለ ፤ ሰው የሚበላው የሚጠጣውን አጥቶ በጣም ከፍቶታል ፣ የመንግስት ሰራተኛውም ያለፉት ዓመታት ደመወዝ ባለመከፈሉ ለተለያዩ ችግሮች ተጋልጦ ነው ያለው ፣ የተፈናቃዮች ነገርማ #አይወራም ፣ ሕጻናት ልጆች የሚበሉትን አጥተው በየከተማው #በልመና ነው ተሰማርተው ያሉት። "
#Ethiopia #TigrayRegion #Peace
@tikvahethiopia
#AmazonFashion
አማዞን ፋሽን ለተማሪዎች እንኳን ለመመረቂያ ቀናቹ አደረሳቹ እያለ በዚህ አመትም ለተመራቂ ተማሪዎች ልዩ ቅናሽ አድርገናል።
ኮት ብቻ 3 ሺ ብር ሙሉ ልብስ በ5 ሺ ና በ8 ሺህ፣ ሸሚዝ በ1200 ፣ ጫማ በ2200 ብር ብቻ ።
አድራሻ ፦ ፒያሳ የገበያ ኣዳራሽ ወይም ፒያሳ የድሮው ዳውንታውን ህንፃ ምድር ላይ።
ስልክ ፦ 0920880443/ 0919339250
Telegram👉https://t.me/joinchat/AAAAAEc8iQJX1Zjgepjq1w