tikvahethiopia | Unsorted

Telegram-канал tikvahethiopia - TIKVAH-ETHIOPIA

1519094

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው። @tikvahuniversity @tikvahethAfaanOromoo @tikvahethmagazine @tikvahethsport @tikvahethiopiatigrigna #ኢትዮጵያ

Subscribe to a channel

TIKVAH-ETHIOPIA

አዳዲስ ላፕቶፕች ከአንድ ዓመት ዋስትና ጋር!!
@samcomptech

በአገልግሎት አሰጣጣችን ላይ እና  በዕቃዎቻችን ጥራት ላይ  ደንበኞቻችን ምስክሮቻችን ናቸው። ዛሬም ብዛትንም ጥራትንም ሳንቀንስ እያስተናገድን እንገኛለን።

👉ለቢሮዎች፣ ለተማሪዎች፣ ለዲዛይን ባለሙያዎች ፣ ለጌመሮች ወ.ዘ.ተ

አቅምን ካገናዘቡ እስከ ቅንጡ ላፕቶፖች ይህ ቀረ ሳይሉ የሚያገኙበትን ሱቃችንን ይጎብኙ። የቴሌግራም ቻናሉን ይቀላቀሉ ባሉበት ሆነው ይዘዙን እናደርሳለን።

የዕቃዎች ዋጋ  ፣ዓይነት እና አድራሻ ለማግኘት ይሄን 👉 @samcomptech
ተጭነው በቴሌግራምው ማየት ይችላሉ።
@sww2844 0928442662 / 0940141114

https://maps.app.goo.gl/H3PM1NrTcQ4SWkK17

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#ቲክቶክ

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በዓለም ላይ ትልቅ ተፅእኖ የፈጠረው በቻይናው ባይትዳንስ ኩባንያ የሚተዳደረው " ቲክቶክ " የተሰኘው መተግበሪያ በአሉታዊም ይሁን አውንታዊ መንገድ ስሙ ይነሳል።

በቻይና ያለው የቲክቶክ ይዘት እና በተቀረው ዓለም ያለው ልዩነት አለው የሚሉም ብዙ ናቸው።

አንዳንድ ሀገራት ልጆች እና ወጣቶችን ከአጉል ባህል ለመጠበቅ በሚል በሙሉ ሲያግዱት ፣ አንዳንዶች ደግሞ ከደህንነት ጋር በተያያዘ ከመንግሥት ቁሳቁሶች ፣ ከመ/ቤቶች አግደዋል።

ለመሆኑ ቲክቶክ በቻይና እና በተቀረው ዓለም ይለያያል ?

ትሪስታን ሃሪስ ፤ የቀድሞው የጉግል ሰራተኛ እና ለማህበራዊ ሚዲያ ስነምግባር ተሟጋች ሲሆኑ ፤ በቻይና ያለው የቲክቶክ ይዘት እና በተቀረው ዓለም ያለው ይዘት ልዩነት አለው ባይ ናቸው።

ዶዪን የቻይናው ቲክቶክ ልጆችን / ትውልድ ታሳቢ ያደረገ ነው ብለዋል።

" የመተግበሪያው ባለቤቶች ቴክኖሎጅ በልጆች እድገት ላይ ያለው ተጽዕኖ በደንብ አድርገው የተገነዘቡ ናቸው " የሚሉት እኚሁ የማህበራዊ ሚዲያ ስነምግባር ተሟጋች ፤ " በቲክቶክ የሀገር ውስጥ (ቻይና) ስሪታቸው ከ14 ዓመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች ፦
* በቤት ውስጥ ሊያደርጓቸው የሚችሏቸው የሳይንስ ሙከራዎችን፣
* የሳይንስ እና ሌሉች ሙዚየም ኤግዚቢቶችን
* የሀገር ፍቅር ቪዲዮዎችን፣
* ትምህርታዊ የሆኑ ቪዲዮዎችን ያሳያሉ " ብለዋል።

እንዲህም ሆኖ እራሱ በሀገሪቱ ያሉት ታዳጊዎች / ልጆች በቀን ውስጥ በቲክቶክ ላይ የሚያጠፉት ሰዓታቸው የተገደበ መሆኑንም አንስተዋል።

በዩኤስ እና ቻይና በታዳጊዎች ላይ አንድ የተደረገ ጥናት እንደነበር የሚያነሱት ተሟጋቹ ይኸውም " ወደፊት የምትፈልጉት የምኞት ስራ ምንድን ነው ? " የሚል እንደሆነ በዚህም ውጤቱ ፦
- በዩኤስ ውስጥ ቁጥር 1 የማህበራዊ ሚዲያ ተፅእኖ ፈጣሪ፤
- በቻይና ደግሞ ቁጥር 1 #የጠፈር_ተመራማሪ የሚል እንደነበር ገልጸዋል።

ከዚህ ወራት በፊት የቲክቶክ ዋናው ስራ አፈፃሚ በአሜሪካ ኮንግረስ ቀርበ ጠንካራ ጥያቄ በቀረበባቸው ወቅት አንዱ የተነሳው ፤ በቻይና ያለው ቲክቶክ ለልጆች የሚያስተዋውቀው ፦
° ሳይንስ
° የሒሳብ / ሌሎች የትምህርት ቪድዮዎችን ነው ፤ የሚያዩበት / የሚቆዩበት ሰዓትም ገደብ አለው ዩኤስ ውስጥ ግን የሚገፉት ቪድዮዎች ልጆች ራሳቸውን እንዲጎዱ የሚያደርግ ነው ይህ ለምን ? የሚል ነበር።

ቲክቶክ ሱስ የማስያዝ አሰራር እንዳለው የሚያነሱ ሌሎች ባለሞያዎች የሰዎችን ስሜት በማንበበ ረጅም ጊዜ እዛ ላይ እንዲያሳልፉ ያደርጋል ባይ ናቸው።

ለታዳጊዎ/ልጆች ተብሎ የተለየ ስሪት ስለሌለው ይተቹታል።

በቲክቶክ ላይ የመቆያ ጊዜ እንደ #ፍላጎት እና ያልተገደበ መሆኑም በተለይ ለወላጆች ፈተና እንደሆነ ያነሳሉ።

ምንም እንኳን በተለይ #አሜሪካውያኑ እያደረሰ ነው የሚሉት የማህበራዊ ተፅዕኖው እንዳለ ሆኖ ከደህንነትና ከቻይና ጋር ባላቸው ሁኔታ እንዲታገድ ወይም ድርሻ #እንዲሸጥላቸው በይበልጥ ቢፈልጉም በርካቶች በትውልድ ላይ ቀውስ እየፈጠረ ነው ፣ ቁጥጥርም የለው በሚል እንዲታገድ / የይዘት ቁጥጥር እንዲደረግበት ይፈልጋሉ።

ከዚህ በተቃራኒው ቲክቶክ በዩኤስ ሆነ በሌላው ዓለም የበርካታ ወጣቶችን ህይወት በገንዘብ ቀይሯል።

በርካቶችን ለብዙሃን አስተዋውቋል። ብዙ ገንዘብ እንዲሰሩም አድርጓል። አልጎሪዝሙ በትንሽ ድካምና ስራ ሚሊዮኖች ጋር ማድረስ መቻሉ ሰዎች በአንድ ሌሊት ብቻ የዝና ማማ ላይ ቁጭ እንዲሉ አድርጓል።

ከደህንነት ጋር በተያያዘ ለሚነሱ ሰፊ ጉዳዮች አስተዳዳሪዎቹ የተጠቃሚዎችን ምንም መረጃ ለቻይና መንግሥት አሳልፈው እንደማይሰጡ ደጋግመው ተናግረዋል። ሌሎች ወቀሳዎችንም አጥብቀው ይሞግታሉ።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#Update

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፤ የዲጂታል ባንክ አግልግሎት ሙሉ በሙሉ መጀመሩን ገለጸ።

ባንኩ ፤ በሲስተም ችግር ምክንያት ፦
- በቅርንጫፎች፥
- በኢንተርኔት ባንኪንግ፥
- በሞባይል ባንኪንግ፥ እንዲሁም በሲቢኢ ብር የአገልግሎት መቋረጥ አጋጥሞ እንደነበር አስውሷል።

በቅርንጫፍ እና በኤቲኤም የሚሰጡ አገልግሎቶች ቀደም ብለው መጀመራቸውን ገልጾ አሁን ደግሞ በዲጂታል የሚሰጡ የባንክ አገልግሎቶች ሙሉ በሙሉ መጀመራቸውን አሳውቋል።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

“ ከአምስት ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ የአዕምሮ እድገት ውስንነት ያለባቸው ዜጎች ኢትዮጵያ ውስጥ ይኖራሉ ” - ፍቅር ኢትዮጵያ የአዕምሮ እድገት ውስንነት ብሔራዊ ማኀበር

ኦቲዝምና ዳውንሲንድረም ያለባቸው ልጆች የትምህርት እና ሌሎች መሰል አገልግሎቶችን የሚሰጡ 5 ማኀበራት ፣ ማህበረሰቡ እንዲህ አይነት የአዕምሮ እድገት ውስንነት ላለባቸው ልጆች ያለው አመለካከት በፍረጃ የተሸበበ መሆኑን ፣ መንግሥትም ለዘርፉ የሚገባውን ትኩረት እንዳልሰጠ ገልጸዋል።

ያንብቡ ፡ https://telegra.ph/Tikvah-Ethiopia-03-16

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#Update

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎቻቸው እና ሌሎችም የተቋሙ አካላት በካሽ የወሰዱትን እና ለሌላ ሶስተኛ ወገን ያስተላለፉትን ገንዘብ እንዲመልሱ አስጠነቀቁ።

በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሲስተም ላይ ካጋጠመው ችግር ጋር በተያያዘ በርካቶች ገንዘብ ያለገደብ ሲያወጡና ሲያስተላልፉ ነበር።

በተለይም የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች እና የዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ አካላት ትላንት ካጋጠመው ችግር ጋር በተያያዘ ገንዘብ ወጭ ሲያደርጉና ወደ ሌላም ሲያስተላልፉ እንደነበር ተነግሯል።

ይህንን ተከትሎ የራሳቸው ያልሆነን ገንዘብ ያወጡና ያስተላለፉ እንዲመልሱ ተቋሞቻቸው እያሳሰቡ ይገኛሉ።

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱ ባንኩ የተፈጠረዉን ችግር በተመለከተ ፦
* ከኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ፤
* የመረጃ እና ደህንነት እንዲሁም ከሌሎች ከሚመለከታቸዉ ተቋማት ጋር በመሆን እየሰራ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።

በባንኩ የተፈጠረዉን የሲስተም መቋረጥ ምክንያት እንደ አጋጣሚ በመጠቀም ፦
➡️ የራሳቸው ያልሆነን ገንዘብ #በካሽ ወጭ ያደረጉና በማንኛዉም የባንኩ የድጅታል አማራጮች የተቀበሉ
➡️ ወደ 3ኛ ወገን ያስተላለፉ ተማሪዎች እና የዩንቨርሲቲ ማህበረሰብ አባላት የወሰዱትን እና የተላለፈላቸውም አካላት ገንዘቡን ተመላሽ እንዲያደርጉ አስጠንቅቀዋል።

ገንዘቡ ተመላሽ የሚደረገው በአቅራቢያ ባለ የባንኩ ቅርንጫፍ መሆኑን አሳውቀዋል።

ለመመለስ ፈቃደኛ ካልሆኑ ጉዳዩ የሕግ ተጠያቂነትን የሚያስከትል መሆኑንም እየገለጹ ናቸው። ገንዘብ ያወጡ ተማሪዎች እና የዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ አባላት ስም ዝርዝር እንዳላቸውም ጠቁመዋል።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#ግሎባል_ባንክ
መልዕክቱን ያጋሩ፣ ከ1ሺህ ብር ጀምሮ ተሸላሚ ይሁኑ! የግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ይፋዊ የቴሌግራም ቻናል፦
1. በመጀመሪያ ቀጣዩን የቦት ሊንክ ይጫኑ፡- /channel/global_bank_referral_bot?start=476862805
2. START የሚለውን ይጫኑ፣
3. JOIN CHANNEL የሚለውን ይጫኑ፣
4. ወደ መጀመሪያው ቦት ይመለሱ፣
5. CONTINUE የሚለውን ሲጫኑ የመጋበዣ ሊንክዎን ያገኛሉ፣
6. መልዕክቱን ቢያንስ ለ50 እና ከዚያ በላይ ወዳጅ ዘመድዎ ሼር ሲያደርጉ ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ በየሳምንቱ ከአንድ ሺ ብር ጀምሮ ልዩ ልዩ ሽልማቶችን ያበረክታል፡፡

ሽልማቱ በየሳምንቱ ለተሸላሚዎች ይደርሳል፡፡

ደንብና ሁኔታዎች ተፈፃሚ ናቸው፡፡
ለተጨማሪ ጥያቄዎች በነፃ የጥሪ ማዕከል ቁጥር 8118 ይጠቀሙ!
ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ
ለጋራ ስኬታችን

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

ንግድ ባንክ አገልግሎት መቋረጡን ገለጸ።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሲስተም ችግር ምክንያት በባንኩ አገልግሎቶች ላይ ማለትም ፦
- በቅርንጫፎች፥
- በኢንተርኔት ባንኪንግ፥
- በሞባይል ባንኪንግ፥ እንዲሁም በሲቢኢ ብር የአገልግሎት መቋረጥ እንዳጋጠመው አሳውቋል።

አገልግሎቱን መልሶ ለማስጀመር በርብርብ እየተሰራ ነው ያለው ባንኩ ደንበኞቹ በትዕግስት እንዲጠብቁ ጠይቋል።

ለተፈጠረው መጉላላትም #ይቅርታ ጠይቋል።

ከአንድ ወር ገደማ በፊት በፋይበር ኦፕቲክስ ገመድ ላይ በደረሰ ጉዳት ሁሉም አገልግሎቶች ተቋርጠው እንደነበር እና በሰዓታት ውስጥ ችግሩ መፈታቱ አይዘነጋም።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

*SafaricomEthiopia

የመጨረሻው ዙር ተረክ አድራጊዎች ታውቀዋል! እንኳን ደስ ያላችሁ !
ደንበኛ ከአርሲ ፤ ነጋዴ ከጅግጅጋ መኪናዋን ተረክ አድርገዋታል!
ከዲላ ፣ከሐረር አራተኛ ፣እንዲሁም ከእንጅባራ ባጃጇን ተረክ አድርገዋታል!

M-PESA ላይ እንመዝገብ ፣ በM-PESA እንገበያይ፣ እንሸለም!

🔗 የM-PESA ሳፋሪኮምን መተግበሪያ በዚህ ሊንክ እናውርድ፡ https://bit.ly/M-PESA_SafaricomEthiopia

ስለ አገልግሎታችን ማንኛውንም ጥያቄ ወይም መረጃ  በቴሌግራም   ቻናላችን /channel/Safaricom_Ethiopia_PLC 24/7 ማግኘት ይቻላል!

#MPESASafaricom #TerekBeMPESA
#FurtherAheadTogether

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#ወንጂ🕯

ለስራ በወጡበት #በታጣቂዎች ታግተው ከቆዩ በኃላ ተገድለው ከተገኙት ዜጎች መካከል አንዱ አቶ ግርማ በላቸው እንደሚባሉና የኢትዮ ስኳር ፋብሪካ ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ አ/ማ የስራ ባልደረባ እንደነበሩ ተነግሯል።

ከሌሎች ባልደረቦቻቸው ጋር ሆነው በታጣቂዎች ታግተው ፤ በግፍ ተገድለው የተገኙት ለወንጂ ስኳር ፋብሪካ ድጋፍ ለመስጠት በወጡበት ነው።

በኦሮሚያ ክልል ፤ በቅርቡ የጥታዊው የዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም 4 አባቶች ታግተው በግፍ መገደላቸው የሚዘነጋ አይደለም።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

ሜጀር ጄነራል ክንፈ ዳኘው ከእስር ተለቀቁ።

የቀድሞው የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) ዋና ዳይሬክተር ሜጀር ጄነራል ክንፈ ዳኘው፤ ከ5 ዓመት ከ4 ወራት እስር በኋላ ዛሬ ከሰዓት ከእስር መፈታታቸውን ጠበቃቸው ለ" ኢትዮጵያ ኢንሳይደር " ድረገፅ በሰጡት ቃል ተናግረዋል።

ጠበቃቸው አቶ ሓፍቶም ከሰተ የቀድሞው የሜቴክ ዋና ዳይሬክተር ዛሬ ከቀኑ 10 ሰዓት ገደማ የተለቀቁት ፤ አብዛኛውን የእስር ጊዜያቸውን ካሳለፉበት ከቃሊቲ ማረሚያ ቤት መሆኑን አስረድተዋል።

ከእስር ሲለቀቁ በቤተሰቦቻቸው አቀባበል እንደተደረገላቸው ጠበቃቸው ተናግረዋል።

ሜጀር ጄነራል ክንፈ በከባድ የሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በፌደራል ፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋሉት ህዳር 3/2011 ዓ.ም. ነበር።

ከእስር የተፈቱት በእርሳቸው ላይ ቀርበው የነበሩ ተደራራቢ ክሶች በፍትህ ሚኒስቴር መቋረጣቸውን ተከትሎ ነው።

የፍትህ ሚኒስቴር ክስ የተቋረጠው " ለዘላቂ የህዝብ ጥቅም " ሲባል ነው ማለቱ ይታወሳል።

በትላንትናው ዕለት የቀድሞ የሶማሌ ክልል ፕሬዜዳንት አብዲ ኢሌ ከእስር መፈታታቸው ይታወሳል።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#AddisAbaba

ፒያሳ የሚገኘው የዓድዋ ድል መታሰቢያ ከነገ ጀምሮ ለጎብኚዎች ክፍት እንደሚሆን ተነግሯል።

የድል መታሰቢያው የሚጎበኝበት ዋጋ ዝርዝርም ይፋ ሆኗል።

የጀግኖች ምስለ ቅርፅና ድሉን የሚያወሱ ቁሳቁሶች በመታሰቢያው ለጎብኚዎች ክፍት የሚሆኑ ሲሆን ክፍያው በቴሌ ብር፣ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መፈፀም ይችላል ተብሏል።

በዚህም መሰረት ፦

➡ ለመደበኛ 150፣
➡ ለተማሪዎች 75
➡ ለልዩ ልዩ 550 ብር እንደሆነ ተገልጿል።

መታሰቢያው ከ2:30 እስከ 11:30 ሰዓት ተኩል ለጎብኚዎች ክፍት ይሆናል። #ኤፍቢሲ

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

አዲሱን የ5G ኔትወርክ የሚያስጠቅሙ የ ZTE ስልኮችን ከአጓጊ የጥቅል ስጦታ ጋር!

የ ZTE ብሌድ ኤ73 5ጂ ስልኮችን በመግዛት ፈጣኑን የአምስተኛውን ትውልድ ፍጥነት ያጣጥሙ ።

ስማርት ስልኮቹን በተመጣጣኝ ዋጋ ሲገዙ የአንድ ዓመት 2 ጊ.ባ ወርሃዊ የዩትዩብ ጥቅልን ጨምሮ፣ ለተከታታይ ሶስት ወራት 20 ጊ.ባ ወርሃዊ ዳታ ከ 500 ደቂቃ የድምጽ ጥቅል ስጦታ ጋር አቅርበናል፡፡

በአቅራቢያዎ በሚገኙ የአገልግሎት መስጫ ማዕከሎቻችን ወይም በቴሌገበያ ድረ ገጽ https://telegebeya.ethiotelecom.et/ ይገኛሉ!

#BeyondConnectivity
#Ethiotelecom #telebirr #RealizingDigitalEthiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

" ከቀን ወደ ቀን እየተበባሰ የመጣው የኑሮ ውድነት ለጤና ባለሙያዎች ትልቅ ፈተና ሆኖባቸዋል " - የኢትዮጵያ ጤና ባለሙያዎች ማኀበር

የኢትዮጵያ ጤና ባለሙያዎች ማኀበር ፕሬዚዳንት አቶ ዮናታን ዳኛው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል፣ " መንግሥት ለዘርፉ በሰጠው ያነሰ ትኩረት ምክንያት ብዙዎች የሚወዱትን የሙያ ዘርፍ በመልቀቅ፣ በመቀየር እንዲሁም አገር ጥለው በመውጣት ላይ ይገኛሉ " ብለዋል።

እንዲህ የሆኑት ምን ያህል የጤና ባለሙያዎች ናቸው ? ተብሎ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ የቀረበላቸው አቶ ዮናታን፣ " በቁጥር ይህ ነው ብዬ ባልገልጽም በonline apply እያደረጉ ብዙ ጤና ባለሙያዎች፦
- ነርሶች፣
- ሀኪሞች፣
- ሚድዋይፎች፣
- ጤና መኮነኖች በተለያዩ መንገዶች አገር ጥለው እየወጡ ነው " የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

" ወደ ፊላንድ፣ ጀርመን፣ ፈረንሳይ፣ ካናዳ በህጋዊም በህገ ወጥም መንገድ ብዙ ጤና ባለሙያዎች ከአገር እየለቀቁ ነው። ብዙ የጤና ባለሙያዎች የህክምና ሙያቸውን ጥለው ወደ ንግድ እንዲሁም ወደ ተለያዩ ዘርፎች እየቀየሩ እንደሆነ ብዙ ተጨባጭ መረጃዎች አሉን። በየቀኑ ከተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች ቅሬታዎችን የምንቀበልበት አካሄድ አለን " ሲሉ አክለዋል።

“ ጤና ባለሙያዎች ከፍተኛ ውጤት አምጥተው ወደ ዩንቨርስቲ የሚቀላቀሉ ቢሆኑም በተቃራኒው ግን በኢትዮጵያ ዝቅተኛ ደመወዝ ተከፋዮች ሆነው ይገኛሉ " ነው ያሉት አቶ ዮናታን።
 
በሥራ ላይ ያሉትም፣ " ከ2011 ዓ/ም ጀምሮ በሰላማዊ መንገድ የመብት ጥያቄዎችን ለመንግሥት ቢያቀርቡም እስካሁን ምንም አይነት ምላሽ አለመሰጠቱ በባለሙያዎች ላይ ከፍተኛ ቅሬታን ፈጥሯል " ያሉት የማኀበሩ ፕሬዚዳንት፣ ቅሬታዎቹን እንዲጠቅሱ ሲጠየቁም፣ ከ2011 ዓ/ም ጀምሮ የጤና ባለሙያዎች ለመንግሥት ያቀረቧቸው ዋና ዋና ጥያቄዎች፦
* የደሞዝ ማሸሻያ፣ 
* የነፃ ህክምና፣
* የHouse allowance፣
* የRisk /ተጋለሠጭነት /
* የቤት፣
* የትርፍ ስሃት ክፍያ ጥያቄዎች መሆናቸውን ጠቅሰው፣ " በሰላማዊ እና በሰለጠነ መንገድ የመብት ጥያቄዎችን ማቅረብ እንደ ነውር ሊታይ አይገባም። የሰላማዊ ድምፆች ሊደመጡ ይገባል " ብለዋል።

" ከቀን ወደ ቀን እየተበባሰ የሚገኘዉ የኑሮ ውድነት  ለጤና ባለሙያዎች ትልቅ ፈተና ሆኖባቸዋል" ብለው፣" መንግሥት በጤና ስርዓቱ ላይ የሚከተለውን ፓሊስ ቆም ብሎ ሊመረምረው ይገባል። የቱንም ያክል የዘመነ እና የረቀቀ የጤና ፓሊሲ ቢኖር ጤና ባለሙያዎችን መሠረት ያላደረገ ፓሊሲ ምንም ያክል እርቀት አይሄድም፣ የታቀደውንም ውጤት አያመጣም " ሲሉ አስገንዝበዋል።

“ መሠረታዊ ፍላጎቱን ማሟላት የማይችል ጤና ባለሙያ ለታካሚዎች ተገቢዉን ህክምና ይሰጣል ብሎ ማሰብ በፍፁም አይቻልም። መንግስት በጤና ባለሙያዎች ላይ እየደረሱ ያሉትን ዘርፈ ብዙ ችግሮች እና የሚነሱ የመብት ጥያቄዎችን ችላ ከማለት ወጥቶ በአገር ላይ የከፋ ችግር ከማስከተላቸው በፊት መፍትሄ ይሰጣቸው ዘንድ ጥሪን አቀርባለሁ ” በማለት አሳስበዋል።

በሌላ በኩል ፤ " የጸጥታ ችግር ባለባቸው አካባቢዎች ከፍተኛ የሆነ ችግሮች አሉ። የእኛም ማኀበር ይህን በተመለከተ በመግለጫ ሁኔታዎች እንዲስተካከሉ ጠይቋል። ችግሩ ግን መፍትሄ አላገኘም አሁንም ብዙ ቅሬታዎች አሉ " ብለዋል።

መረጃውን ተዘጋጅቶ የተላከው የአ/አ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#ICS #Ethiopia

" በአሁን ሰዓት የተጠራቀመ ፍላጎት ሙሉ በሙሉ አጠናቀናል " - ICS

የኢሚግሬሽን እና ዜግነት ጉዳዮች አገልግሎት በትግራይ ተቋርጦ የሚገኘውን የኢሚግሬሽን አገልግሎት ለማስጀምር እየሰራ መሆኑን አስታውቋል።

አገልግሎቱ ትላንት በሰጠው መግለጫ ነው ይህን ያለው።

በሌላ በኩል ፤ ባለፉት 6 ወራት ከ1.1 ሚሊዮን በላይ የፓስፖርት ቡክሌቶችን ከውጭ ሀገር በማስገባት 640 ሺህ ፓስፓርት ፐርሰናላይዜሽን ህትመት በመስራት ለተጠቃሚዎች ማድረሱን አሳውቋል።

• ለአዲስ አበባ 260,371፣
• በየአካባቢው ላሉ ቅ/ጽ/ቤቶች 269,358፣
• በአስቸኳይ 35,394 እና በውጭ ለሚኖሩ ኢትዬጵያዊያን 81,416 እንደሆነ አመላክቷል።

የውስጥ ህትመት አቅምን በተመለከተ ከዚህ ቀደም በቀን 2 ሺህ ይታተም የነበረው አሁን ወደ 10 ሺህ በላይ ወደማተም ደረጃ መደረሱን ገልጿል።

መ/ቤቱ በአሁን ሰዓት የተጠራቀመ ፍላጎት ሙሉ በሙሉ እንዳጠናቀቀ በይፋ አሳውቋል።

ከዚህ ባለፈ በእጁ ላይ 80 ሺህ ፓስፖርት ስላለ ያመለከቱና ተራው የደረሳቸው በስልክ በሚደርሳቸው መልዕክት መሰረት እንዲወስዱ ጥሪ ቀርቧል።

ፓስፖርት ለማውጣት ከዚህ ቀደም ይወስድ የነበረው የአንድ አመት ጊዜ ከመጋቢት 16 /2016 በኃላ እንደሚቀረፍ የኢሚግሬሽን እና ዜግነት ጉዳዮች አገልግሎት ገልጿል።

ከዚህ በባለፈ ፤ ባለፉት 6 ወራት ውስጥ ፦
➡️ከዋና ቢሮ፣
➡️ ከቅርንጫፍ ጽ/ቤት፣
➡️ ከቦሌ፣
➡️ከኬላዎች በድምሩ 205 የሚሆኑ ሠራተኞች ውጭ ካሉ #ደላሎች ጋር በመተባበርና የአሰራር ክፍተትን በመጠቀም ከህብረተሰቡ ያልተገባ ጥቅም ለማግኘት ሲሰሩ መረጃ ተገኝቶባቸው ለህግ አካላት እንዲቀርቡ እንደየጥፋታቸውም ከስራ እንዲታገዱና የህግ ውሳኔ እንዲሰጣቸው መደረጉን አስረድቷል።

ህብረተሰቡ ፦

* ተመሳስለው ከተሰሩ ዌብሳይቶች ራሱን እንዲጠብቅ
* በግለሰብ አካውንት ምንም አይነት ገንዘብ ገቢ እንዳያደርግ፣
* ዜግነት ማጣራት ጋር በተያያዘ ሂደት ያለው ስለሆነ የሚጠየቁ ሰነዶችን በትዕግስት እንዲያቀርብና እንዲተባበር፣
* ፖስፖርት ውሰዱ ተብለው የጽሁፍ መልዕክት ሲደርሳቸው በተባለው ቀን እና ሰዓት እንዲወስዱ፣
* አስቸኳይ ፓስፖርት በኦንላይን የማይሰጥ ስለሆነ አስቸኳይ የሚያሰጥ ሰነድ ያላቸው ተገልጋዬች በዋናው ቢሮ ብቻ በአካል በመገኘት  መስተናገድ እንዳለባቸው አሳስቧል።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

አዳዲስ ላፕቶፕች ከአንድ ዓመት ዋስትና ጋር!!
@samcomptech

በአገልግሎት አሰጣጣችን ላይ እና  በዕቃዎቻችን ጥራት ላይ  ደንበኞቻችን ምስክሮቻችን ናቸው። ዛሬም ብዛትንም ጥራትንም ሳንቀንስ እያስተናገድን እንገኛለን።

👉ለቢሮዎች፣ ለተማሪዎች፣ ለዲዛይን ባለሙያዎች ፣ ለጌመሮች ወ.ዘ.ተ

አቅምን ካገናዘቡ እስከ ቅንጡ ላፕቶፖች ይህ ቀረ ሳይሉ የሚያገኙበትን ሱቃችንን ይጎብኙ። የቴሌግራም ቻናሉን ይቀላቀሉ ባሉበት ሆነው ይዘዙን እናደርሳለን።

የዕቃዎች ዋጋ  ፣ዓይነት እና አድራሻ ለማግኘት ይሄን 👉 @samcomptech
ተጭነው በቴሌግራምው ማየት ይችላሉ።
@sww2844 0928442662 / 0940141114

https://maps.app.goo.gl/H3PM1NrTcQ4SWkK17

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#DStvEthiopia

ደማቁ የኤፍ ኤ ካፕ ጨዋታዎች ቀጥለዋል💥

🔥 ወደ ግማሽ ፍፃሜ ሚደርሱትን ቡድኖች ይገምቱ!

🔥 የኤፍ ኤ ካፕ ጨዋታዎችን በቀጥታ በዲኤስቲቪ ሱፐርስፖርት ቻናሎች ይከታተሉ!

👉ከጥር 6 እስከ መጋቢት 22 ደንበኝነትዎን ሲያሳድጉ... እኛም ቀጣዩን ለአንድ ወር እንጋብዝዎታለን!

ለሚሰጡን አስተያየት በቅድሚያ እያመሰገንን፣ ስለ አገልግሎታችን ጥራት የሚደርስዎትን የፅሁፍ መልዕክት ሊንኩን በመጫን መጠይቁን እንዲሞሉ በትህትና እንጠይቃለን።

የዲኤስቲቪ አገልግሎቶችን ለማግኘት ከታች ያለውን የMyDStv Telegram bot ሊንክ ይጫኑ!
👇
https://mydstv.onelink.me/vGln/eth2

#FACupAllOnDStv #ሁሉምያለውእኛጋርነው #DStvEthiopia #DStvSelfServiceET

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#AmharaRegion #Gojjam

ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጋርዱላና ኧሌ ዞኖች ተነስተው ለደን ምንጣሮ ስራ ወደ ታላቁ የሕዳሴ ግድብ እያመሩ በአማራ ክልል ምስራቅ ጎጃም ጎዛምን አካባቢ በ " ፋኖ ታጣቂዎች " የተያዙ የቀን ሰራተኞችን ለማስለቀቅ ጥረት እያደረገ መሆኑን የምልመላና የቅጥር ሂደቱን የፈፀመው " ኒኮቲካ ኮንስትራክሽንና ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግል ማህበር አሳውቋል።

የታገቱት ሰራተኞች ብዛታ 272 እንደሆነ ተነግሯል።

የድርጅቱ የፕሮጀክት ስራ አስኪያጅ አቶ ሙልጌታ አለነ ምን አሉ ?

➡ " በአጠቃላይ 4 ሺህ ሰራተኛ ነው ያስፈቀድነው። 272 ሰራተኛ ከጋርዱላና አሌ ዞን ወስደን መንገድ ላይ ችግር ገጥሞናል። ችግሩን በአካል እኔው እራሴ ሄጄ በሽማግሌም፣ በምንም እንዲፈታ እየሞከርን ነው " ብለዋል።

➡ ቁጥርን በተመለከተ ፤ " ከጋርዱላ 246 እና ከአሌ 38 በድምሩ 282 ሰራተኞች ነው የሄዱት " የሚባለው እጅግ በጣም ስህተት ነው ብለዋል። " ዶክመንት አለን እያንዳንዱ ዶክመንት ስላለን በዛ ነው የምናወራው ፤ የሰው ልጅ ነው የወስድነው ማንም እየተነሳ ይሄ ነው ማለት አይችልም። ስንወስዳቸውም በህጋዊ መንገድ ተፈራርመን ነው። ቁጥራቸው 272 ነው " ብለዋል።

➡ ይሄን ያህል ብዙ ኪ/ሜ ርቀት ሄዶ ለህዳሴ ግድብ ሰራተኛ መመልመሉን ምን አመጣው ? ለሚለው ጥያቄ ፤ " ጠንካራ ሰራተኞች ስለሆኑን ነው " ሲሉ መልሰዋል። ባለፈው ዓመት ድርጅቱ በተመሳሳይ ከየክልሉ ከአማራ፣ ከቤኒሻንጉል፣ ከደቡብ፣ ከሁሉም ሰራተኛ ወስዶ እንደነበር አስታውሰው በተደረገው ግምገማ በስራቸው ውጤታማ ስለሆኑ ነው ደብዳቤ ተፅፎ ሰራተኞቹ የተወሰዱት የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

➡ በአማራ ክልል ውስጥ ጦርነት እንዳለና መረጋጋት እንደሌለ እየታወቀ ለምን በዚህ መንገድ እንዲሄዱ ተደረገ ? በሚል ለቀረበው ጥያቄ ፤ " እኛ የያዝነው የሀገር ፕሮጀክት ነው። ውል ገብተናል በውሉ መሰረት መስራት አለብን። መንገዱም ሌላ መንገድ የለውም አምናም (በ2015 ዓ/ም) ከ2 ሺህ በላይ ሰራተኞችን ከኮንሶ ስንወስድ በዚሁ በራሱ መንገድ ነው። አሁንም ህዳር ላይ ነበር የምንገባው ባለው ሁኔታ ሳንገባ ቀረን ሲረጋጋ ተረጋግቷል ግቡ ተባልን ገባን " ሲሉ መልሰዋል።

➡ ' ከፋኖ ታጣቂዎች ለታጋቾች #ገንዘብ ተጠይቋል ፣ ድርጅቱ ገንዘብም ሰጥቷል '' እየተባለ ስለሚነገረው ጉዳይ በተመለከተ ፤ " እኛ ሙሉ መረጃ በሁለት ቀን እንሰጣለን ከዚህ በላይ ማለት ያለብኝ የለም " ብለዋል።

➡ የሰራተኞቹ ደህንነትን በተመለከተ " ደህንነታቸው በጣም ሰላም ነው " ብለዋል። ይህን ያረጋገጡት እዛው ቅርብ ስለሆነ መሆኑን ገልጸዋል። አሁን በአካል እዛው አካባቢ በቅርብ ሆነው እየተከታተሉ እና #በሽምግልና ልጆችን ከእገታ ለማስወጣት ጥረት እያደረጉ እንደሆነ አስረድተዋል።

ድርጅቱ በኢትዮጵያ የንግድ ህግ የተመዘገበ ከመላው ሀገሪቱ ሰራተኞችን ለስራ እየመለመለ የሚቀጥር እንደሆነ አሳውቀዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በ 'ፋኖ ታጣቂ ኃይሎች' የተያዙ ሰራተኞች ቤተሰቦች ሰራተኞቹ ፦
* አስቸጋሪ ሁኔታ ላይ እንዳሉ፣
* ጫካ ውስጥ ታስረው እንደሚገኙ፣
* ምግብም እያገኙ እንዳለሆነ፣
* ወታደራዊ ስልጠና እንዲወስዱና ወደ ውጊያ ውስጥ እንዲገቡ የማስገደድ ሁኔታ እንዳለ፣
* የግድያ / ርሸና ዛቻም እንደሚደርስባቸው ተናግረዋል።

ወጣቶቹ ታግተው ከተወሰዱ 4ኛው ሳምንት እየጀመረ ቢሆንም እስካሁን ድረስ ይህ ነው የሚባል መፍትሄ የሰጣቸው አካል እንደሌለ ቤተሰቦች ገልጸዋል። የፌዴራልም የክልል መንግሥትም ዝም ማለታቸው እንዳሳዘናቸው ተናግረዋል።

ቃላቸውን ለቪኦኤ ሬድዮ ጣቢያ የሰጡት ' የአማራ ፋኖ የጎጃም ቃል አቀባይ ነኝ ' ያሉት ፋኖ ማርሸት ፀሀዩ ፤ " ... ከተቻለ በ72 ሰዓታት ውስጥ ወጣቶቹን ለቀይ መስቀል እናስረክባቸዋልን " ብለዋል።

ስለ ጉዳዩ በዝርዝር ምን አሉ ?

➢ " እኛ ያረጋገጥነው እነዚህ ልጆች አውቀውም ይሁን ተጭበርብረው ጎጃም ውስጥ ወደሚገኘው የብርሸለቆ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ሲወሰዱ ነው ያገኘናቸው " ብለዋል።

➢ የታገቱ ወጣቶች ብርሸለቆ ወታደራዊ ማሰልጠኛ እየተወሰዱ ስለመሆኑን ምን ማስረጃ አላችሁ ? ለሚለው ጥያቄ ፤ " ተጨባጭ የሆነ ማስረጃ አለን። በወታደራዊ ቋንቋ ጠርናፊ የሚባል ቃል አለ ይህ ማለት አንድን የሚንቀሳቀስ ወታደራዊ ኃይል፣ ምልምል / የታጠቀ ኃይል የሚመራ ማለት ነው። የነዚያ ተጓዦች ተርናፊዎች የአስር አለቃ ማዕረግ ሳይቀርብያላቸው አክቲቭ ወታደሮች መሆናቸውን ከራሰቸው መታወቂያ ዕዛቸውን፣ ኮራቸው፣ ክ/ጦራቸውም ፣ ሻለቃቸውን የሚጠቅስ መታወቂያ ይዘዋል። የመከላከያ አርማ ያለው መታወቂያና አክቲቭ መሆናቸውን አረጋግጠናል " ብለዋል።

➢ "ከያዝናቸው ውስጥ ያነጋገርናቸው ወደ መሰረታዊ ውትድርና እንደሚገቡ እንደሚያውቁ ፣ በዛ ያሉት ግን ግንዛቤው እንደሌላቸው ግን ከፍተኛ ገንዘብ እንደሚከፈላቸው ነው ያረጋገጥነው" ሲሉ አክለዋል።

➢ ሌላው ከተለያየ ኢትዮጵያ ክፍል ወደህዳሴ ግድብ የሚሄዱ ሰራተኞችም ሆነ ጎብኝዎች አዲስ አበባን ረግጠው ፣ በአምቦ አድርገው በነቀምት ፣ አሶሳ ነው ወደ ጉባ የሚገቡት በአማራ ክልል አቋርጠው የሚሄዱበት ታሪክ አልነበረም ሲሉ ተደምጠዋል። " አሁን ላይ በአማራ ክልል ውጊያ እንዳለ እየታወቀ በአ/አ አማራ ክልል አድርገው ወደ ጉባ የሚሄዱበት ምክንያት የለም " ሲሉ አክለዋል።

➢ የወጣቶቹን ቀጣይ ዕጣ ፋንታ በተመለከተ እኚሁ ቃል አቀባይ ፤ " ስለ ፋኖ ዓላማ ፣ ስለ አማራ ትግል አስፈላጊውን ትምህርት ሰጥተናቸው ለቀይ መስቀል ልናስረክባቸው በዝግጅት ላይ ነን " ብለዋል። " ቀይ መስቀል ወደኛ እየመጣ ስለሆነ ከተቻለ በ72 ሰዓት ካልሆነም በ100 ሰዓት ውስጥ ለማስረከብ ዝግጁ ነን። ሁኔታውን አጥንተው ስለሚገቡ በደረሱበት ሰዓት እናስረክባለን። " ብለዋል።

➢ በታጋቾች ላይ እየተፈፀመነው ስለሚባለው የግድያ ዛቻ፣ በግዳጅ ወደ ውጊያ እንዲገቡ የማድረግ ጉዳይ ተጠይቀው ፤ " ከያዝናቸው 240 ሰዎች ፦
• አንድም ሰው የአካል ድብደባ ደርሶበት ከሆነ፣
• በግድ ፋኖ እንዲሆን ጠብመንጃ እንዲሸከም ተገዶ ከሆነ ፣
• አንድም ሰው ያለ ፍላጎቱ እኛ የፈለግነውን ፕሮፖጋንዳ እንዲናገር ተገዶ ከሆነ የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ፣ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ፣ ሂውማን ራይትስዎች አስፈላጊው አጣሪ ኮሚቴ ልከው ማጣራት ይችላሉ " ብለዋል።

የጋርዱላ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ብርሃኑ ኩናሎ ምን አሉ ?

° የፌዴራል መንግሥት ፤ የአማራ ክልልም መንግሥት ከዞኑ ጋር በቅንጅት እየሰሩ መሆኑን ነገር ግን እስካሁን ውጤት እንዳልመጣ ተናግረዋል።

° ታጋቾች #በነፍስ_ወከፍ_300_ሺ_ብር እንዲከፍሉ መጠየቁን ነገር ግን ለማስቀለቅ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ይህንን መረጃ ያገኘው ከቪኦኤ ሬድዮ መሆኑን ያሳውቃል።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

በትላንትና ዕለት የወጣው የመምህራን የጋራ መኖሪያ ቤት ዕጣ የዕድለኞች #ስም_ዝርዝር ይፋ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ አሳውቋል።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#እንድታውቁት

ነገ በአዲስ አበባ ፤ መስቀል አደባባይ ከሰዓት በሗላ ከቀኑ 7፡30 እስከ 12፡00 ሰዓት ድረስ የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል የፀሎት መርሐ-ግብር እንደሚያከናወን ተገልጿል፡፡

ይህን መርሐ-ግብር ተከትሎ ለተሽከርካሪ ዝግ የሚደረጉ መንገዶችን የአዲስ አበባ ፖሊስ አሳውቋል።

በዚህም ፡-

➡ ከቅዱስ ኡራኤል አደባባይ ወደ መስቀል አደባባይ ለሚጓዙ ተሽከርካሪዎች ኡራኤል አደባባይ ላይ

➡ ከቦሌ ጌቱ ኮሜርሻል አቅጣጫ ወደ መስቀል አደባባይ ኦሎምፒያ አደባባይ በታች እና በላይ እንዲሁም ግራና ቀኝ

➡ የቀድሞው አራተኛ ክፍለጦር (ጥላሁን አደባባይ ላይ )

➡ ከለገሀር መብራት ወደ መስቀል አደባባይ ለሚጓዙ ለገሀር መብራት ላይ

➡ ከሀራምቤ መብራት ወደ መስቀል አደባባይ ሃራምቤ መብራት ላይ

➡ ከብሔራዊ ቤተ መንግስት ወደ መስቀል አደባባይ ብሔራዊ ቤተ መንግስት አጠገብ እሑድ መጋቢት 8 ቀን 2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡ 00 ጀምሮ ፕሮግራሙ እስከሚጠናቀቅ ድረስ መንገዶቹ ለተሽከርካሪ ዝግ ይሆናሉ ተብሏል፡፡

ፕሮግራሙ በሚከበርበት ዙሪያ እና በአካባቢው በግራና በቀኝ ለረጅምም ሆነ ለአጭር ጊዜ ተሽከርካሪ አቁሞ መሄድ ፍፁም የተከለከለ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ አሳስቧል፡፡

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#Update

" የሳይበር ወይም ሌላ ተመሳሳይ ጥቃት አልደረሰብኝም " - የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

የኤቲኤም (ATM) አገልግሎት መጀመሩን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አስታወቀ።

ባንኩ ፤ ተቋርጦ የነበረው የኤቲኤም(ATM) አገልግሎት ሙሉ በሙሉ ስራ የጀመረ መሆኑን  ገልጾ በቀጣም ሁሉንም ዲጂታል የባንክ አገልግሎቶች ሥራ እናስጀምራለን ብሏል።

በሌላ በኩል ባንኩ ፤ በሲስተም ችግር ምክንያት በጊዜያዊነት የተከሰተውን የአገልግሎት መስተጓጎልን ምክንያት በማድረግ ሀሰተኛ መረጃዎች በማህበራዊ ትስሥር ገፆች በመዘዋወር ላይ ይገኛሉ ብሏል።

" የተከሰተው የአገልግሎት መቋረጥ በባንኩ የውስጥ የሲስተም ችግር ነው " ያለው ባንኩ   ፤ ከባንኩ ውጭ በደረሰ የሳይበር ወይም ሌላ ተመሳሳይ ጥቃት የለም የሚሰራጨው መረጃም ሀሰት ነው ብሏል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፤ አስተማማኝ የሳይበር ደህንነት ጥበቃ እንዳለው ገልጾ ከዚህ ጋር በተያያዘ ደንበኞቹ ምንም አይነት ስጋት እንዳይገባቸው አሳስቧል።

ሌሎች ያልተጀመሩ አገልግሎቶች በሰዓታት ልዩነት ሙሉ በሙሉ በማስተካከል እንዲጀምሩ እየተሰራ መሆን አሳውቋል።

በሌላ በኩል ፤ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከባንኩ ደንበኞች ባገኘው መረጃ ከባንኩ አገልግሎት መስተጓጎል ጋር በተያያዘ የኤቲኤም ማሽን የታዘዘውን ገንዘብ ሲሰጥ እንደነበር (በአካውንታቸው ገንዘብ ለሌላቸው) ፣ በሞባይል ባንኪግም ገንዘብ በአካውንታቸው የሌላቸው ሰዎችም ሲያስተላልፉ እንደነበር ተረድቷል።

በተለይ አንዳንድ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ገንዘብ ሲያወጡ ነው።

ይህ ተከትሎ ተቋማት በትላንትናው ዕለት መጋቢት 6 2016 ዓ.ም ከኢትዮጰያ ንግድ ባንክ ኤቲ ኤም ላይ በትርፍ የሌላቸውን ገንዘብ በማወቅም ባለማወቅም ያወጡ በፍጥነት እንዲመልሱ እያሳሳቡ ይገኛሉ።

ተማሪዎቹ ያወጡትን ገንዘብ ቅርንጫፍ ቀርበው እንዲመልሱ ነው ማሳሰቢያ የተሰጣቸው።

የማይመልስ ተማሪ ላይ አስተዳደራዊ እርምጃ እንደሚወሰድበትና በህግ እንደሚጠየቅ ገልጸዋል። የሌላቸውን ገንዝብ ያወጡ ተማሪዎች ስም ዝርዝርም እንደተላከላቸው አመላክተዋል።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#Update

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሲስተም ምክንያት ተቋርጦ የነበረው #የቅርንጫፎች_አገልግሎት መጀመሩን አሳውቋል።

የባንኩ ቅርንጫፎች ዛሬ እስከ ምሽቱ 2፡00 ሰዓት አገልግሎት እንደሚሰጡም አሳውቋል።

በተመሳሳይ ዲጂታል የባንክ አገልግሎቶች ፦
- ኢንተርኔት ባንኪንግ፥
- ሞባይል ባንኪንግ፥
- ሲቢኢ ብር ለማስጀመር እየሠራ መሆኑን ገልጾ ለተፈጠረው የአገልግሎት መስተጓጎል በድጋሚ ይቅርታ ጠይቋል።

ባንኩ በምን ምክንያት የሲስተም ችግር እንደተፈጠረ የሰጠው ማብራሪያ የለም።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

አዳዲስ ላፕቶፕች ከአንድ ዓመት ዋስትና ጋር!!
@samcomptech

በአገልግሎት አሰጣጣችን ላይ እና  በዕቃዎቻችን ጥራት ላይ  ደንበኞቻችን ምስክሮቻችን ናቸው። ዛሬም ብዛትንም ጥራትንም ሳንቀንስ እያስተናገድን እንገኛለን።

👉ለቢሮዎች፣ ለተማሪዎች፣ ለዲዛይን ባለሙያዎች ፣ ለጌመሮች ወ.ዘ.ተ

አቅምን ካገናዘቡ እስከ ቅንጡ ላፕቶፖች ይህ ቀረ ሳይሉ የሚያገኙበትን ሱቃችንን ይጎብኙ። የቴሌግራም ቻናሉን ይቀላቀሉ ባሉበት ሆነው ይዘዙን እናደርሳለን።

የዕቃዎች ዋጋ  ፣ዓይነት እና አድራሻ ለማግኘት ይሄን 👉 @samcomptech
ተጭነው በቴሌግራምው ማየት ይችላሉ።
@sww2844 0928442662 / 0940141114

https://maps.app.goo.gl/H3PM1NrTcQ4SWkK17

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#Tigray

የትግራይ ክልል የማህበረሰብ ተወካዮች ጥያቄ እና የጠቅላይ ሚኒስትሩ ምላሽ ምን ነበር ?

ከትግራይ ወደ አ/አ የመጡ የማህበረሰቡ ተወካዮችና እዚህም ያሉ ተወላጆች ከጠ/ሚር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ጋር በነበራቸው ቆይታ ፤ የትግራይ ህዝብ ከማንም ህዝብ ጋር  መጋጨት እንደማይፈልግ ገልጸው ፓለቲከኞችም ልጓም ማበጀት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።

በአፅንኦት በጦርነቱ ከቄያቸው የተፈናቀሉ ወደ ቦታቸው እንዲመለሱና የክልሉ አስተዳደራዊ ወሰን እንዲከበር ጠይቀዋል።

በጥቅሉ ያነሷቸው ጥያቄዎች  ምንድናቸው ?

- የመከላከያ አባላት የነበሩት ጨምሮ ሌሎች የፓለቲካ እስረኞች ይፈቱ፤
- የትግራይ ነጋዴዎች ከጦርነቱ በፊት የወሰዱት የብድር ወለድና ቅጣት ይነሳ፤
- የመንግስት ሰራተኞችና የጡረተኞች ውዙፍ ደመወዝና አበል ይከፈል፤
- ከትግራይ ሰራዊት (TDF) ለተሰናበቱ ታጣቃዊች ማቋቋምያ ይከፈል፤
- ተፈናቃዮች ወደ ቄያቸው ይመለሱ የትግራይ ሉአላዊ ግዛት ይከበር፤
- ከረሃብ ጋር በተያያዘ እርዳታ ይደረግ ፤
- የህወሓት የህጋዊነት ጥያቄ ለምን ዘገየ ?
የሚሉና ሌሎች ይገኙባቸዋል።

ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ምን መለሱ ?

➡ ከፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት በኃላ ብዙ ስኬቶች እንዳሉ አሁንም ግን የሚቀር ብዙ እንዳለ ገልጸዋል። ከሰላም ስምምነቱ በኃላ በጥይት ሰው እንዳልሞተ ተናግረዋል። በትግራይ መረጋጋት ፤ መንግሥት መመስረት ፣ ህወሓት (TPLF) ከሽብርተኝነት መፋቅ የስምምነቱ ውጤት ነው ብለዋል።

➡ ከስምምነቱ በኃላ በርካታ ቢሊዮን ብሮች በካሽም በቁሳቁስም ወደ ትግራይ ክልል መላኩን ገልጸዋል።

➡ እስረኞችን መፍታት በተመለከተ ፦

" ስብሃትን ፈትቼው የለም እንዴ ? ፣ አልፈልግም እንዲታሰሩ።

የመከላከያን በተመለከተ እራሱ ይነግራችኋል (ዶ/ር አብርሃምን ማለታቸው ነው) አላውቅም በእኔ እውቀት #አንድም_የታሰረ_ሰው_የለም።  ከስራ ያቆምናቸው ታጋዮች ነበሩ እርቁ ሲፈፀም መፍታት እኮ አይደለም ወደቦታቸው ነው የመለስናቸው። አሃዱ አለቃ ናቸው ሁሉም በየቦታው በየደረጃው ኃላፊዎች ናቸው መከላከያ ውስጥ ...

እስረኛ በሌብነት ምክንያት ካለ አላውቅም ፤ እስረኛ ሰው ገድሎ የታሰረ ወንጀለኛ ካለ አላውቅም። ከግጭቱ ጋር የሚያያዝ ግን በመከላከያ ወጥተው የነበሩት ተመልሰው መከላከያ ውስጥ ገብተዋል።

እኛ እንደዚህ አይነት ፍላጎት የለንም። የምናውቀውም የለም። እኛ እስረኛ ፈተን ስራ አስፈፃሚ ፈተን ጌታቸው ጋር የቀሩ እስረኞች ነበሩ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ያልፈታቸው ። "

➡ ትግራዋይ ተፈናቃዮችን በሚመለከት ፤ ተፈናቃዮች በስምምነቱ መሰረት ቤታቸው መመለስ አለባቸው ብለዋል።

አቶ ጌታቸው ረዳ ፣ የአማራ ክልሉ አቶ አረጋ ፣ ዶ/ር አብርሃም ያሉበት ኮሚቴ ተቋቁሞ ሰሞኑን ንግግር ይደረጋል ሲሉ ገልጸዋል።

የፌዴራል መንግሥት ፍላጎት መጀመሪያ የተፈናቀሉ ሰዎች በሙሉ ቤታቸው እንዲመለሱ ነው ያሉ ሲሆን " በማንኛውም ሰዓት ነገ ሁመራ ያለው ቤቴ መመለስ እፈልጋለሁ የሚል ካለ እኛ ለመመለስ ዝግጁ ነን " ብለዋል።

#መከላከያ በአካባቢው የትግራይም ይሁን የአማራ ፀጥታ ኃይል እንዳይኖር ኃላፊነት እንደተሰጠው ገልጸዋል።

ሁሉም ሰዎች ወደ ቤታቸው #ከተመለሱ_በኃላ እራሱ ህዝቡ አስተዳዳሪውን እንዲመርጥ እንደሚደረግና ከተረጋጋ በኃላ ህዝቡ ሪፈረንደም በማድረግ " እኔ አማራ ነኝ ፤ እኔ ትግራይ ነኝ " የሚለውን እንደሚወስን ተናግረዋል።

➡ ጠ/ሚኒስትሩ ተፈናቃዮች መቐለ ፣ ሽረ መቀመጥ እንደማያስፈልጋቸውና ወደ ቦታቸው እንዲመለሱ ጥሪ አቅርበዋል። በዚህ ረገድ ፌዴራል መንግሥት የሚጠበቅበትን እንደሚያደርግ ተናግረዋል።

➡ በነበረው ሁኔታ ውጭ ሀገር የሄደ ባለሃብት ካለ መመለስ ይችላል ፣ ከባላሃብቶች ጋር በተያያዘ ችግር ካለም ይፈታል ብለዋል።

➡ #ረሃብን በተመለከተ ጉዳዩን ፖለቲካዊ ማድረግ እንደማይገባና ትግራይ ተርባ ሌላው የኢትዮጵያ ክፍል በልቶ ጠግቦ እንደማያድርግ ገልጸዋል። " ጌታቸውንም ወቅሼዋለሁ ረሃብ ካለ መደወል ነው እኔ ጋር ያለ አምጡ አግዙ ማለት ነው ቀላል ነው በትዊተር ከሆነ ግን እኛ በትዊተር አንነጋገርም ብሄዋለሁ ለሌሎች ነው የነገርከው እንጂ እኔ አልሰማሁም " ሲሉ ገልጸዋል። " ረሃብ ረሃብ ችግር ችግር አለ የሚል ፖለቲካ " ማድረግ ተገቢ አይደለም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኮሚቴ ተቋቁሟል ሄዶ ጥናት አድርጎ መደረግ ያለበት ይደረጋል ሲሉ ገልጸዋል።

➡ የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ/TPLF እውቅናን በተመለከተ ጉዳዩ የምርጫ ቦርድ ቢሆንም " በእኛ በኩል መሰጠት አለበት ብለን እናምናል ፤ በቅርብም #አነጋግረናቸዋል የሚፈታ ይመስለኛል ፤ ብዙም ከባድ አይደለም " የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

➡ #ከባንክ ጋር በተያየዝ ጉዳዩ ውስብስብ መሆኑን በማስረዳት መናገር ያልፈለጉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የቢሯቸው አማካሪዎች እና ጉዳዩን በቀጥታ የሚያዩ የሚመለከታቸው አካላት ተነጋገረው የሚቻል ነገር ካመጡ ለማገዝ ፍላጎት እንዳላቸው ጠቁመዋል።

➡ ከባንክ ብድር ጋር በተያያዘ " ብድር ተከለከልን " የሚሉ ባላሃብቶች ካሉ ከዶ/ር አብርሃም እና ከሌሎች የሚመደቡ ሰዎች ጋር እንዲነጋገሩ አቅጣጫ ሰጥተው አልፈዋል። በመንግሥት ፖሊሲ ሊፈታ የሚችል ካለ ግን እንደሚታይ ገልጸዋል።

➡ በኤርታራ መንግሥት (በሻዕብያ ኃይል) ስለተያዙ መሬቶች በተመለከተ ፤  የፌዴራል እና ከትግራይ የጋራ ኮሚቴ መቋቋሙን በዚህም የሀገር መከላከያ ከትግራይ ጓዶች ጋር በመሆን ቦታዎችን እንዲያዩ እንደሚደረግ ገልጸዋል። " #ከአልጀርስ_ስምምነት ውጭ የሆነ ካለ ሪፖርቱ ሲመጣ እናያለን ፤ ማንም የማንንም ቦታ በኃይል ይዞ ለዘላለም መኖር አይችልም እንዳንዋጋ፣ ዳግም ግጭት እንዳይፈጠር ትርፍ ነገር የተካሄደ ካለ አይተን ቦታውን ለይተን ኦፊሻሊ እነዚህ ነገሮች ይስተካከሉ ብለን በንግግር መልክ ልናበጅ እንችላለልን " ብለዋል። ውጤቱ ታይቶ ለህዝብ ይፋ ይደረጋል ሲሉ ተግረዋል።

➡️ የጡረተኞችን ውዝፍ ክፍያን በተመለከተ ምንም ሳይሉ አልፈው በአቶ ጌታቸው በኩል ያለውን ነገር እንደሚያሳውቁ ገልጸዋል።

ሌሎችም አንዳንድ በተነሱ ጥያቄዎች ላይ በቀጥታ አስተያየት ባይሰጡም በጥቅሉ በክልሉ ካሉ ጉዳዮች ጋር በተያያዘ በውይይት በምክክር እንደሚፈቱ ቃል ገብተዋል።

#TikvahFamilyMekelle
#TikvahFamilyAddisAbaba

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#ወንጂ🕯

ለ2 ሳምንት ያህል ታግተው የነበሩ 5 የወንጂ ስኳር ፋብሪካ ሠራተኞች ተገድለው መገኘታቸውን ስሜ አይጠቀስ ያሉ አንድ የፋብሪካው ኃላፊ ተናገሩ።

እኚሁ ኃላፊ ለቢቢሲ አማርኛው ክፍል በሰጡት ቃል ፤ የአምስቱ ሠራተኞች አስከሬን ዛሬ ጠዋት መጋቢት 6/2016 ዓ.ም. መገኘቱን ገልጸዋል።

" አስከሬናቸው ከፋብሪካው ማሳ ወጣ ብሎ ጨካ በሚባል የገጠር አካባቢ ነው የተገኘው " ብለዋል።

ከተገደሉት መካከል 3ቱ ሠራተኞች ከወንጂ አካባቢ ሲሆኑ፣ የቀብር ሥነ ሥርዓታቸው ዛሬ ተፈፅሟል።

ሁለቱ ሠራተኞች አንደኛው ከአዳማ የመጣው ቀብሩ ዛሬ የተፈፀመ ሲሆን ሌላኛው ከደሴ የመጣው ግለሰብ አስከሬን ወደ ስፍራው ተልኳል ተብሏል።

4ቱ ሠራተኞች በፋብሪካው ውስጥ በትራክተር ኦፕሬተርነት ለረጅም ጊዜ ያገለገሉ እና ዕድሜያቸው ከፍ ያለ እንደሆኑም ተገልጿል።

ሌላኛው የኤሌክትሪክ ሠራተኛ (ፎርማን) ወጣት ሲሆን በቅርብ የተቀጠረ እና ለአንድ ዓመት ያህል በፋብሪካው አገልግሏል።

አንደ ኃላፊው ገለጻ ከሆነ ግለሰቦቹ ከሁለት ሳምንታት በፊት የአዳር ስር ላይ ምሽቱን አሳልፈው ጥዋት ላይ በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ አርሲ ዞን " ዶዶታ " ከሚባለው ፋብሪካው ከሚገኝበት ስፍራ በታጣቂዎች ታግተው ተወስደዋል።

ሠራተኞቹን ያገቷቸው ሰዎች ገንዘብ ጠይቀው እንደነበር ? ወይም የጠየቋቸው ጉዳዮች እንዳሉ ዝርዝሩን እንደማያውቁ አስረድተዋል።

ነገር ግን ፋብሪካው ከአጋቾቹ በኩል ምንም ነገር እንዳልተጠየቀ ገልጸው፣ ወዲያውኑ ለመንግሥት አካል ማሳወቃቸውን ተናግረዋል።

ፓሊስም ሠራተኞቹን ለማስለቀቅ እየተከታታለ እንደነበር የገለጹት ኃላፊው ነገር ግን አስከሬናቸው ዛሬ ጥዋት 2 ሰዓት አካባቢ ተገኝቷል ብለዋል።

ስለ ግድያው እንዴት ? እና ስንት ሰዓት ? ተፈጸመ የሚለውን ባያውቁም ምናልባትም ትናንት ምሽት ተገድለዋል ብለው እንደሚጠረጥሩ የተናገሩት ኃላፊው ሰራተኞቹ መገደላቸውን ሰምተው ወደ አካበቢው ሲሄዱ አስከሬናቸውን አግኝተናል ብለዋል።

በፋብሪካው እንዲህ እገታ ሲያጋጥም የመጀመሪያ መሆኑን እና እስካሁን ባለው ሁኔታ ሰላማዊ እንደነበርም አስረድተዋል።

ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የቢቢሲ አማርኛው አገልግሎት ነው።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#Amhara

በአማራ ክልል ከመንግሥት የፀጥታ ኃይል ጋር የትጥቅ ትግል እያደረጉ የሚገኙት እና ታጥቀው የሚንቀሳቀሱት እነ ምሬ ወዳጆን ጨምሮ 27 ተከሳሾች #የጋዜጣ_ጥሪ እንዲደረግላቸው እና እንዲቀርቡ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ መስጠቱ ተሰማ።

የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 2ኛ የህገ መንግስትና በህገ መንግስት ስርዓት ላይ የሚፈጸሙ የወንጀል ጉዳዮችን የሚመለከተው ችሎት ፤ በሽብር ወንጀል በተከሰሱት እነ ዶክትር ወንደሰን አሰፋ መዝገብ ተካተው ያልቀረቡ ተከሳሾች የጋዜጣ ጥሪ እንዲደረግላቸውና ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ ማዘኑን ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል።

የጋዜጣ ጥሪ ይደረግላቸውና ይምጡ የተባሉት በአሁን ሰዓት ነፍጥ አንግበው በአማራ ክልል እየተንቀሳቀሱ የሚገኙት ምሬ ወዳጆን ጨምሮ 27 ተከሳሾች ናቸው።

እነ ዶክተር ወንደሰን አሰፋ እና መስከረም አበራን ጨምሮ 23 ተከሳሾች በአማራ ክልል ካለው ሁኔታ ጋር በተያያዘ ታስረውና " በሽብር ወንጀል " ተከሰው የፍርድ ሂደታቸው እየታየ እንደሆነ ይወቃል።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎች ወደ ሜዳ ተመልሰዋል 💥

👉የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎችን በሱፐርስፖርት ልዩ ቻናል 240 እንዲሁም በሱፐርስፖርት ልዩ2 ቻናል 239 በ አማርኛ ኮሜንትሪ ከጎጆ ፓኬጅ ጀምሮ በቀጥታ ይመልከቱ!

📣 አዲስ ነገር ይዘን መጥተናል!

👉ከጥር 6 እስከ መጋቢት 22 ለቻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታዎች ደንበኝነትዎን ወደ ሜዳ ፕላስ ፓኬጅ ሲያሳድጉ...
እኛም ቀጣዩን የፕሪሚየም ፓኬጅ ለአንድ ወር እንጋብዝዎታለን!

የዲኤስቲቪ አገልግሎቶችን ለማግኘት ከታች ያለውን የMyDStv Telegram bot ሊንክ ይጫኑ!
👇
https://bit.ly/2WDuBLk

#EthiopianPremierLeague #ሁሉምያለውእኛጋርነው #DStvSelfService #DStvEthiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ 430 የጋራ መኖሪያ ቤቶች #ለመምህራን በዕጣ መተላለፋቸውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ አሳውቀዋል።

ዛሬ የተላለፉት ቤቶች ከዚህ በፊት ለመምህራን ተላልፈው ከነበሩ 5,000 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ውስጥ ውል ሳይፈጸምባቸው የቆዩ 435 ቤቶች ከተለዩ በኃላ መሆኑን ገልጸዋል።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

 #Update

" ለፍትሃዊ ጥያቄ ፍትሃዊ ምላሽ መሰጠት አለበት ፤ መንግስት የገባው ቃል ካልተገበረ ማህበሩ መብቱን ለማስከበር ይንቀሳቀሳል " - የትግራይ መምህራን ማህበር

የትግራይ መምህራን ማህበር የተገባለት ቃል እንዲተገበር ጠየቀ።

ማህበሩ ባወጣው መግለጫ፤ መምህሩ የተማሪው የትምህርት ጥማት ለማርካት እየሰራ ቢገኝም ላቀረበው ጥያቄ ተገቢ ምላሽ ባለማግኘቱ በኑሮ ውድነት ከፉኛ እየተጎዳ ይገኛል ብሏል።

ባለፈው ጥር 2016 ከጊዚያዊ አስተዳደሩና የትምህርት ቢሮ ጋር ባደረገው ወይይት የ2015 ዓ.ም የ5 ወራት ዉዝፍ ደመወዝ በአጭር ጊዜ እንደሚከፈል መግባባት ላይ ተደርሶ እንደነበር ይታወሳል።

በውይይቱ ላቀረባቸው ጥያቄዎች የሚጨበጥና ተስፋ ሰጪ መልስ ማግኘቱን በይፋ ለመምህራን አሳውቆም ነበር።

በወቅቱ በነበረው ውይይት የተነሱት ነጥቦች ፦
✔ የ2015 ዓ.ም የ5 ወራት ዉዝፍ ደመወዝ፣
✔ የ2014 ዓ.ም የ 12 ወራት ዉዝፍ ደመወዝ፣
✔ ከደደቢት ማይክሮፋይናስ ስለተወሰደ የብድር ወለድ ስለሚነሳበት ሁኔታ፣ 
✔ የመምህራን የትራንስፖርት አገልግሎት ሰርቪስ ስለማግኘት፣ የሚሉ እንደነበሩ ይታወሳል።

በውይይቱ ፦
* በተለይ ዉዝፍ ደመወዝ የሚመለከት የ2015 ዓ.ም የ5 ወራት በአጭር ጊዜ እንደሚከፈል የ2014 ዓ.ም የ12 ወራት ዉዝፍ ደመወዝ መከፈል የሚመለከት ጥያቄ ወደ ፌደራል መንግስት መቅረቡ ፣

* ከደደቢት ማይክሮፋይናንሰ የተወሰደ የብድር ወለድ ስለሚነሳበት ሁኔታ ቀጣይ ውይይት እንደሚካሄድ ፣

* የከተማ የመምህራን ሰርቪስ የሚመለከት ጥያቄ በአጭር ጊዜ እንደሚመለስ መግባባት ላይ ተደርሶ እንደነበር ማህበሩ ይፋ አድርጎ ነበር።

ነገር ግን እስከአሁን የተመለሰ ጥያቄ የለም ብሏል።
            
ከማህበሩ ጥያቄ አንድም ባለመመለሱ መምህራን በአኗኗራቸውን በሙያቸው አሉታዊ ጫና እንደፈጠረባቸው  የገለፀው ማህበሩ ፤ ጊዚያዊ አስተዳደሩ የገባው ቃል የማይፈፅም ከሆነ ምክር ቤት በመጥራት ችግሩ ላይ ተወያይቶ አቋም በመያዝ ተግባራዊ ለማድረግ እንደሚገደድ አስጠንቅቋል።

ማህበሩ በቀጣይ እወሰድዋለሁ ስላለው እርምጃ የሰጠው ፍንጭ የለም።

መረጃውን አዘጋጅቶ የላከው የመቐለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው።
                            
@tikvahethiopia            

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

ፎቶ ፦ ከትግራይ ተጉዘው አዲስ አበባ የተገኙ ከትግራይ ክልል ከተለያየ የህብረተሰቡ ክፍል የተውጣጡ ተወካዮች ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር መከሩ።

በዛሬው ዕለት ጠ/ሚ ዶክተር ዐቢይ አህመድ ከትግራይ ክልል ተጉዘው ከመጡ የኅብረተሰብ ተወካዮች ጋር በተለያዩ ጠቃሚ ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን አሳውቀዋል።

" በትግራይ ክልል ሰላም እና ልማትን ለማስገኘት ያለን ቁርጠኝነት ሁልጊዜም ፅኑ ነው " ያሉት ጠ/ሚስትሩ " የዛሬው ውይይታችንም ይህንኑ የጋራ አላማ ለማሳካት ተጨማሪ አቅም የሚሰጥ ነው “ ብለዋል።

ዛሬ በተካሄደው የውይይት መድረክ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደርፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ እና የመከላከያው ሚኒስትር ዶ/ር አብርሃም በላይ ተገኝተው ነበር።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከሰሞኑን ከሁሉም ክልል ተወካዮች ጋር እንዲሁም ከሃይማኖት አባቶች ጋር ምክክር ሲያደርጉ ሰንብተዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ባገኘው መረጃ የትግራይ ተወካዮቹ ከሁሉም የትግራይ ዞኖች የተውጣጡ ሲሆኑ ብዛታቸው 200 ይጠጋል።

በቻርተር  አውሮፕላን እንዲጓዙ ተደርጎ ነው አዲስ አበባ የመጡት። አዲስ አበባ ከመጡ በኃላ ትላንት የዓድዋ መታሰቢያንን ጨምሮ ሌሎች ቦታዎችን እንዲጎበኙ ተደርጓል። ዛሬ ደግሞ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ተገናኝተው መክረዋል።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#አቢሲንያ_ባንክ

ወርሃዊ ክፍያዎችን በፍጥነት ባሉበት ሆነው ለመፈጸም የአቢሲንያ የሞባይል ባንኪንግ መተግበርያን ይገልገሉ። 

ሊንኩን በመጠቀም መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ!

ለአንድሮይድ ስልኮች https://

play.google.com/store/apps/details?id=com.boa.boaMobileBanking&hl=en&gl=US

ለአፕል ስልኮች  https://apps.apple.com/us/app/boamobile/id6463218765

ለሁዋዌ ስልኮች https://appgallery.huawei.com/app/C110106115

Читать полностью…
Subscribe to a channel