#ኢራን
የኢራን ፕሬዚዳንት ኢብራሂም ራይሲ ተሳፍረውባት በነበረው ሄሊኮፕተር በደረሰው አደጋ ህይወታቸው አልፏል።
ይህንንም የሀገሪቱ የመንግሥት አረጋግጧል።
ከሳቸው በተጨማሪ በሂሊኮፕተር ውስጥ አብረው የነበሩት የአገሪቱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆሴይን አሚር አብዶላሂያን እና ሌሎች በርካታ ሰዎች ሞተዋል።
ሮይተርስ በአደጋው ፕሬዚዳንቱ ሲጓዙባት የነበረችው ሄሊኮፕተር #ሙሉ_በሙሉ መቃጠሏን " አንድ የኢራን ባለስልጣንን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል።
" የፕሬዜዳንት ኢብራሂም ራይሲ ሄሊኮፕተር በአደጋው ሙሉ በሙሉ ተቃጥላለች። በሚያሳዝን ሁኔታ ሁሉም ተሳፋሪዎች ሳይሞቱ አልቀሩም " ብለዋል ስማቸው ያልተጠቀሰው ባለስልጣን።
#ሮይተርስ
@tikvahethiopia
ሕብር የሴቶች የቁጠባ ሒሳብ - ለአንቺ የሚገባሽ!
ሕብር የሴቶች የቁጠባ ሒሳብ ከመደበኛው የቁጠባ ሒሳብ ላቅ ያለ ወለድ የምታገኚበት!
ሕብረት ባንክ
በሕብረት እንደግ!
ለበለጠ መረጃ ወደ 995 ነፃ የጥሪ ማዕከል ይደውሉ፡፡ አዳዲስ መረጃ እንዲርሶ የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎች ይጫኑ፡፡
ቴሌግራም- /channel/HibretBanket
ሊንክዲን- https://www.linkedin.com/company/hibretbank/
ዌብሳይት- https://www.hibretbank.com.et/
#Hibretbank
#ስፖርት
ማንችስተር ሲቲ የእንግሊዝ ፕሪሜየር ሊግ 2023/2024 ሻምፒዩን ሆነ።
ቡድኑ በተከታታይ ለ4 ዓመታት የፕሪሚየር ሊጉን ዋንጫ በማንሳት አዲስ ታሪክ ጽፏል።
ዘንድሮ እስከ ዛሬው የመጨረሻ መርሀግብር ከ #አርሴናል ጋር አንገት ለአንገት የተናነቀው ሲቲ 91 ነጥብ በመሰብሰብ ነው ዋንጫውን ያሸነፈው።
እጅግ ብርቱ እና ጠንካራ አመትን ያሳለፈው አርሴናል 89 ነጥብ በመያዝ በሁለተኛነት ማጠናቀቅ ችሏል።
አርሴናል ባለፈው አመትም ለዋንጫ ተቃርቦ ዋንጫውን ማግኘት ሳይችል መቅረቱ አይዘነጋም።
ዘንድሮም በ2 ነጥብ ተበልጦ ዋንጫውን ሳያገኝ ቀርቷል።
ሊቨርፑል አመቱን በ3ኛነት ሲያጠናቅቅ አስቶን ቪላ 4 ፣ ቶተንሃም 5 እንዲሁም ቼልሲ 6 ሆነው ጨርሰዋል።
ባለ ብዙ ታሪኩ ማንቸስተር ዩናይትድ እጅግ በጣም ደካማ የተባለ አመትን በማሳለፍ በታሪኩ ዝቅተኛ የተባለው 8ኛ ደረጃ ይዞ ጨርሷል።
የእንግሊዝ ፕሪሜየር ሊግ በመላው ዓለም በብዙ ሚሊዮን ተመልካችን ማግኘት የቻለ ጠንካራ የእግር ኳስ ፍልሚያ ሲሆን በሀገራችን #በኢትዮጵያም ሚሊዮኖች በተለይ ወጣቶች ውድድሩን ይከታተሉታል።
ቲክቫህ ስፖርት /channel/+VvwzStMNcNHmhK0x
@tikvahethiopia
የታገተችው ታዳጊ ጉዳይ ከምን ደረሰ ?
ታግታ ከተወሰደች በኃላ ለማስለቀቂያ 3 ሚሊዮን ብር የተጠየቀባት የታዳጊዋ ተማሪ ማህሌት ተኽላይ ጉዳይ እስከአሁን እንቆቅልሽ ሆኖ ቀጥሏል።
መጋቢት 10 ቀን 2016 ዓ.ም በዓድዋ ከተማ ልዩ ቦታው " ዓዲ ማሕለኻ " ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች ታግታ የተሰወረችው ታዳጊ ተማሪ ማህሌት ተኽላይ ከታገተች ዛሬ ግንቦት 10/2016 ዓ.ም 60 ቀናት አስቆጥራለች።
ታጋች ታዳጊዋ እስከ አሁንዋ ደቂቃ ሰአትና ቀን አልመገኘትዋን ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ አባል እገታ ወደ ተካሄደበት ከተማ ድረስ በመሄድ አረጋግጧል።
የመቐለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ አባል ፥ ዓድዋ ድረስ በመጓዝ ወላጅ አባትዋን እና ቤተ ዘመድ ጠይቆ ባገኘው መረጃ የታዳጊዋ የእገታ ጉዳይ ከትግራይ የፀጥታ አካላት አልፎ የፌደራል የፀጥታ አካላትም እንዲያውቁት ተደርጓል።
የዓድዋ ከተማ ፓሊስ ከሳምንታት በፊት ታጋችዋን ታዳጊ ለማስለቀቅ ከከተማ እስከ ክልል የተቀናጀ የክትትልና ምርመራ ስራ እየሰራን መሆኑና በቁጥጥር ስር የዋሉ ተጠርጣሪዎች እንዳሉ ገልጾ ነበር።
የታዳጊዋን መታገት በማስመልከት ቤተሰቦችዋ መጋቢት 10 ቀን 2016 ዓ.ም ሪፓርት ካደረጉበት ቀንና ሰዓት ጀምሮ ፓሊስ ጉዳዩን ለደቂቃ ያህል ችላ እንዳላለው ገልጾ የነበረ ቢሆንም አሁንም ድረስ ጉዳዩ መቋጫ ሳያገኝ ይሄው 60 (ሁለት ወር) ተቆጥረዋል ሲሉ የማህሌት ወላጅ አባት ተኽላይ ግርማይ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
" የህግ አካላት የክትትል እና ምርመራ መላላት የልጃችን አጋቾች በህግ ቁጥጥር ስር እንዳይውሉ ምክንያት ሆኗል " ያሉት ወላጅ አባት አቶ ተኽላይ " በአንዲት ትንሽ ከተማ የተፈፀመ የእገታ ወንጀል በምንም መመዘኛ ከክልሉና የፌደራል የፀጥታ አካላት አቅም በላይ ሊሆን አይችልም " ሲሉ አክለዋል።
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle
@tikvahethiopia
አምባሳደር ማይክ ሐመር ከነማን ጋር ተገናኙ ?
በአፍሪካ ቀንድ #የአሜሪካ_ልዩ_መልዕክተኛ የሆኑት ማይክ ሐመር ከሰመኑን በኢትዮጵያ ቆይታ አድርገዋል።
ኢትዮጵያ የመጡት ፦
° የፕሪቶሪያን ስምምነት አፈጻጸም ለመገምገም፤
° በአማራ እና ኦሮሚያ ክልሎች ያሉ ግጭቶች በድርድር እልባት እንዲያገኙ ለማድረግ፤
° የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች መመርመር አስፈላጊነት ላይ ለመወያየት ነው።
በዚህም ወቅት ፦
- ከፌዴራይል ባለስልጣናት ጋር መክረዋል።
- ከአሜሪካው አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ ጋር ወደ #መቐለ አምርተው ከትግራይ ክልል አመራሮች ጋር መክረዋል።
- ከአፍሪካ ህብረት ተወካዮች ጋር ተወያይተዋል።
- ከኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ ጋር መክረዋል።
- ከኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ሊቀመንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ እና ከኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) ሊቀመንበር ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና ጋር ተወያይተዋል።
አምባሳደር ማይክ ሐመር የፕሪቶሪያው ግጭትን በዘላቂነት የማስቆም ስምምነት እንዲፈረም ከፍተኛ ሚና ተጫውተዋል የሚባልላቸው የአሜሪካ ባለስልጣን ናቸው።
@tikvahethiopia
#Tecno #Camon30Pro5G
በካሜራ ጥራቱ እና በስልኩ ዲዛይን የተመሰከረለት አዲሱ Tecno camon 30 pro 5G ምርጫዎ ያድረጉ!
#Camon30Et #Camon30pro5GEt #Camon30 #Camon30Pro5G #TecnoEt
🇪🇹 የፖለቲካ ፓርቲዎች ምን ይላሉ ? 🇪🇹
" ግጭቶች ከትንሽ ነገር እየተነሱ እያደጉ ነው አሁን ያሉበት ደረጃ የደረሱት። ይሄ ደግሞ በመንግስት ቸልተኝነት ፣ ትዕግስት ማጣት የሚመጣ ነው " - ኢዜማ
በኢትዮጵያ ለሚስተዋሉ ዘርፈ ብዙ ችግሮች ያለውን ግምገማ በተመለከተ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ (ኢዜማ) የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ የሆኑት አቶ ዋሲሁን ተስፋዬ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጋር ቆይታ አድርገዋል።
Q. በተለያየ ጊዜ ዜጎች በሰላም ወጥተው መግባት እንደማይችሉ ይገለጸል። ከሰው ሕይወት የሚበልጥ ነገር ደግሞ የለም። እንደ ፓርቲ ለመፍትሄ ምን እየሰራችሁ ነው ?
አቶ ዋሲሁን ተስፋዬ ፦
" ችግሮችን በየትኛውም ወገን በኃይል ለማስፈጸም ከመሞከር በፊት በውይይት እንዲፈቱ በተደጋጋሚ ጠይቀናል።
ነገር ግን በየትኛውን አካል ተሰሚነት አላገኙም። ላለማግኘታቸው ማስረጃዎቹ አሁን ያሉት ግጭቶች ናቸው።
ግጭቶች ከትንሽ ነገር እየተነሱ እያደጉ ሂደው አሁን ያሉበት ደረጃ ላይ የደረሱት። ይሄ ደግሞ በመንግስት ቸልተኝነት፣ ትዕግስት ማጣትም ጭምር የሚመጣ ነው። የግጭቶቹን መንስኤ በማየት እንዲፈቱ ማሳሰቢያዎችን እየሰጠን ነው። "
Q. አንዳንዶች " መንግስት በኢትዮጵያ የሚስተዋለውን ግጭት ስለሚፈልገው እንጂ ማስቆም አቅቶት አይደለም " የሚሉ ትችቶች ሲያቀርቡ ይስተዋላል። በዚህ ጉዳይ ፓርቲዎ ምን ይላል ?
አቶ ዋሲሁን ተስፋዬ ፦
" አንድ መንግስት የተረጋጋ ሰላም ሲኖር ነው ሊጠቀም የሚችለው ብለን እናምናለን።
ችግሮች ባሉበት መንግስት ዘላቂ የስልጣን ማራዘም፣ የልማት ውጤት ማምጣት አይችልም። ስለዚህ ግጭቶቹ እንዲባባሱ ፍላጎት አለው ብለን አናምንም።
ግን ለ5 ዓመታት መንግስት ለምን ችግሮቹን ማስቆም አልቻለም ? ብለን ካየን አንደኛ የግጭቶቹን ባሕሪ መውሰድ ያስፈልጋል።
ቀውሶቹ ውጫዊና ውስጣዊ ብለን ብንከፍል እንኳ ግጭቶች እየተነሱ ያሉት ብልጽግና ውስጥ ባሉ ኃይሎች ነው።
የክልል ልዩ ኃይልን ትጥቅ ከማስፈታት፣ ተፈናቃዮችን ከማስመለስ ጋር ተያይዞ መንግስት ይወስዳቸው የነበሩ እርምጃዎች ፓለቲካዊ ጉዳዮች ፓለቲካዊ የሆነ መፍትሄ ማግኘት ሲገባቸው ያንን ላለማድረግ እየተፈጠረ ያለ ግጭት ነው። "
Q. ፓርቲያችሁ ኢዜማ “ የመንግስት ተለጣፊ ” የሚል ስያሜ / አስተያዬት ሲሰጠው ይስተዋላል። ምላሽዎ ምንድን ነው ?
አቶ ዋሲሁን ተስፋዬ ፦
" መንግስት እየሰራቸው ያሉ ግድፈቶችን እያስቀመጥን ነው። እንደዛ የሚባለው በምን መስፈርት እንደሆነ አይገባኝም። እኛ በአግባቡ ስራችንን እየሰራን ነው።
ለሚነሱ አሉቧልታዎች ምላሽ መስጠት አንችልም ፤ ጊዜ የለንም ፤ እኛ ሥራ ላይ ነን።
እንደዚህ የሚሉት መስራት የማይችሉ ሰነፎች ናቸው። "
Q. በኢትዮጵያ ስላለው የጸጥታ እና የደኀንነት ሁኔታ የፓርቲዎን ግምገማ ቢያጋሩ ?
አቶ ዋሲሁን ተስፋዬ ፦
" የጸጥታና ደህንነት ጉዳይ በተለይ ባለፉት 3 ዓመታት እየተባባሰና መልኩን እየቀየረ ያለበት ሁኔታ ነው ያለው።
መጠኑ በተለያየ ደረጃ ይሁን እንጂ በተለያዩ ክልሎችና ወረዳዎች ላይ ያሉ ግጭቶች የጸጥታ ሁኔታውን እያወኩት ይገኛሉ።
የሚታዩት የጸጥታና ደህንነት ችግሮች ዜጎች በነፃነት ተንቀሳቅሰው ጉዳያቸውን እንዳይፈጽሙ ፤ የፓለቲካ ፓርቲዎችም #በነፃነት_ተንቀሳቅሰን የምንፈልገውን የፓለቲካ ሥራ እንዳንሰራ እንቅፋት እየፈጠረ ነው። "
Q. የኑሮ ወድነቱ ሕዝቡን በእጅጉ ፈትኖታል። ለዚህም “ መንግስት ትኩረት አልሰጠም ” የሚሉ ቅሬታዎች ሲሰነዘሩ ይስተዋላል። መንግስት ኃላፊነቱን እየተወጣ ነው ?
አቶ ዋሲሁን ተስፋዬ ፦
" ኑሮ ውድነቱ በተለይም #መካከለኛ_ገቢ የሚኖረው ህብረተሰብ ተመግቦ ማደር የማይችልበት፣ ልጆቹን የማያስተምርበት ደረጃ ላይ ደርሷል።
የኑሮ ውድነቱ በየቀኑ ከቁጥጥር ውጪ እየወጣ ነው ያለው።
በዚህ ሁኔታ እንኳ ሠራተኞች የወራት ደመወዝ ሳይከፈላቸው እየሰሩ ነው።
በተቃራኒው ደግሞ መንግስት ለቅንጡ ፕሮጀክቶች የሚያወጣቸው በጀቶች አሉ። መንግስት እየሄደበት ያለው መንገድ ኑሮ ውድነቱን የዘነጋ ነው። "
Q. እንደ ፓርቲ የሚደርስባችሁ ጫና ምንድን ነው ? ለቀጣዩ ምርጫስ ዝግጅት እያደረጋችሁ ነው ?
አቶ ዋሲሁን ተስፋዬ ፦
" የጸጥታው ችግር የፓለቲካ ፓርቲዎች በሚፈለገው ደረጃ ተንቃሳቅሰው አባሎቻቸውን እንዳይቀሰቅሱ፣ ደጋፊዎቻቸውን እንዳያገኙ አድርጓል። እኛም ያንን እያደረግን አይደለም።
ተፎካካሪ ፓርቲዎች የመንግስት ሚዲያዎችን እንኳ መጠቀም አይችሉም።
የመንግስት ሚዲያዎች የብልጽግና ልሳን ሆነዋል። የብልጽግና እንጂ የመንግስት ሚዲያ ሊባሉ አይችሉም።
ስለዚህ የፓለቲካ ምህዳሩ ከቀን ቀን እየጠበበ ነው። ይሄ ደግሞ መድብለ ፓርቲ በታወጀበት አገር ላይ አይጠቅምም።
የመድብለ ፓርቲ ስርዓትን እያራመድን ነው እንላለን፤ መሬት ላይ ያለው ሀቅ ግን አንድ አውራ ፓርቲ ብቻ ኖሮ (ብልጽግና) እሱን ብቻ እያሞገስን እንድንኖር ነው።
ብልጽግና በቀጥታ እየሄደ ያለው ራሱን ወደ አውራ ፓርቲ ለመቀየር እንቅስቃሴ እያደረገ ነው።
‘ 13 ሚሊዮን ፣ 14 ሚሊዮን #አባላትን_አፍርቻለሁ ’ ይላል፤ ከመራጩ ሕዝብ ግማሹን አባል አድርጌአለሁ የሚል ከሆነ ምርጫ ቢመጣም ትርጉም የለውም። ለይስሙላ የሚደረግ ምርጫ ነው። "
#TikvahEthiopiaFamilyAA
#EZEMA #የፖለቲካፓርቲዎችምንይላሉ?
@tikvahethiopia
#SirajChiffon
የተለያዩ ምርጥ ሽፎኖች በተመጣጣኝ ዋጋ !
አድራሻ ፦ መርካቶ አዲሱ ሚሊተሪ ተራ / የሱቅ ቁጥር: F1-133C
ያናግሩን ፦ @bilalsiraje
ስልክ ፦ +251929091179 or +251931223346
የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
/channel/siraj1945
#Update
የ2016 ትምህርት ዘመን የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ (12ኛ ክፍል) የበይነ መረብ (Online) ተፈታኞች መፈተኛ ይፋ ሆነ፡፡
የ2016 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና በወረቀትና በበይነ መረብ ይሰጣል።
በዚሁ መሠረት በበይነ መረብ ፈተናውን የሚወስዱ ተፈታኞች ከላይ በተገለጸው አድረሻ ብቻ የሚፈተኑ ይሆናል፡፡
ፈተናውን ከመውሰዳቸው በፊት ሁሉም ተፈታኞች በቂ ልምምድ ማድረጋቸው አስፈላጊ በመሆኑ ከዛሬ ቅዳሜ ግንቦት 10 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ በአድራሻው ተፈታኞች በሚገኙበት ክልል የተደለደሉ ስለሆነ ልምምድ ማድረግ ይችላሉ ተብሏል።
ተፈታኞች ልምምድ ለማድረግ ከዚህ በፊት ለክልል / ከተማ አስተዳደር ቀድሞ የተላከውን የይለፍ ቃልና ስም (User Name and Password) ከየትምህርት ቤቶቻቸው ማግኘት እንደሚችሉ ተገልጿል።
መጀመሪያ ወደ መፈተኛ ሲሰተሙ እንደገቡ የማይረሱትን የግላቸውን የይለፍ ቃል የሚቀይሩ ይሆናል፡፡
ተፈታኞች #ከተደለደሉበት_ክለስተር_ዉጪ ሲሰትሙን መጠቀም #የማይችሉ መሆኑን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል።
@tikvahethiopia
#ቢሾፍቱ
ቢሾፍቱ ከተማ የሚገኘው የመከላከያ ሪፈራል ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ዛሬ ተመርቆ ወደ ስራ ገብቷል።
ሆስፒታሉ የኢፌዴሪ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ እና የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በተገኙበት ነው የተመረቀው።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሆስፒታሉ ፦
- እጅግ ዘመናዊ የሆነ የሞሎኪዩላር ላብራቶሪ፣
- የአጥንት ምርመራ ማዕከል፣
- ባዮሜዲካል ኢንጂነሪንግ ክፍል
- እንደ የኩላሊት እጥበት፣ የነርቭ፣ የሳምባ እና መተንፈሻ አካላት የህክምና አገልግሎቶችን የሚሰጥ እንደሆነ ገልጸዋል።
" በሀገራችን ውስጥ ካሉ ግምባር ቀደም ዘመናዊ ሆስፒታሎች አንዱ ነው " ብለውታል።
ፊ/ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በበኩላቸው " ሆስፒታሉ ለሰራዊቱ ብቻ ሳይሆን ለህዝባችንም ትልቅ ጠቀሜታ ይዞ መጥቷል " ብለዋል።
" ታካሚዎችን ውጭ አገር ሲላኩበት የነበረውን የአሰራር ሂደት ይቀይራል ፤ በሀገር ወስጥ ከፍተኛ ሕከምና መሰጠት ስለሚያስችል የውጭ ምንዛሬ ወጪን ያስቀራል " ብለዋል።
ሆስፒታሉ 425 የህሙማን ተኝቶ መታከሚያ አልጋ አለው ተብሏል።
@tikvahethiopia
BK C O M P U T E R S
ማንኛውንም አይነት አዳዲስ ላፕቶፖች ዱባይ ዩዝድ ላፕቶፖች ዴስክ ቶፖችን ጨምሮ ከብዛትና ቅናሽ ጋር ያዘንላቹ መተናል።
ለቢሮዎች ፣ ለተማሪዎች፣ለግሪፊክስ ዲዛይን ባለሙያዎች ፣ ለጌመሮች እንዲሁም ለጨረታ የሚሆኑ በጥራት እና በ ብዛት ከ1 አመት ዋስትና ጋር እኛ ያገኛሉ።
የላፕቶፕ አማራጮችን ለማየት የቴሌግራም ፔጃችንን Join ያድርጉ /channel/BKComputers
Inbox @bkcomputer27
አድራሻ አዲስ አበባ መገናኛ ሲቲ ሞል ከ መሰረት ደፋር ህንፃ አጠገብ 1 ፎቅ ላይ እንገኛለን ፤ 0911448148. 0955413433
we make IT easy!
10 ዓመት ?
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በአሶሳ ዞን ባምበሲ ወረዳ መንደር 44 ቀበሌ በሁለት #የ8_አመት_ህፃናት ላይ የግብረ-ስጋ ድፍረት (አስገድዶ የመድፈር) ወንጀልን የፈፀመ የ41 አመት ጎልማሳ በ10 አመት ፅኑ እስራት መቀጣቱ ተሰምቷል።
ተከሳሽ አብዱ ወዚር የሚባል ሲሆን ነዋሪነቱ አሶሳ ዞን ባምበሲ ወረዳ መንደር 44 ቀበሌ ነው።
በጥር 3 ቀን 2016 ዓ/ም ከቀኑ 9 ሰዓት በአካባቢው የማሽላ ሰብል ማሳ ውስጥ በመደበቅና ህፃናቱን " ጥንቅሽ ልስጣችሁ ኑ ብሉ " ብሎ በመጥራት ወደ ውስጥ ካስገባቸው በኋላ ሁለቱንም በሀይል አስሮ የግብረ ስጋ-ድፈረት (አስገድዶ መድፈር) መፈፀሙ ተገልጿል።
በተጨማሪም በህፃናቱ ላይ ያደረሰባቸውን ሁለንተናዊ ጉዳትም ለማንም ትንፍሽ እንዳይሉ አስፈራርቶ እና በገንዘብ አታሎ ከቦታው ይሰወራል።
ፓሊስም ግለሰቡ በቁጥጥር ስር አውሎ ፍርድ ቤት ያቀርበዋል።
የባምበሲ ወረዳ ፍርድ ቤትም ግለሰቡ በ10 አመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኗል።
ግለሰቡ ግን " በፍርድ ውሳኔው ላይ ቅር ተሰኝቻለሁ " በማለት ይግባኝ ብሎ ጉዳዩ በአሶሳ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በኩል እንዲታይ ይጠይቃል።
የአሶሳ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤትም " የ10 አመት " ፅኑ እስራት ውሳኔው አስተማሪ ነው በማለት አጽድቆ መዝገቡን ዘግቷል"
Via @TikvahethMagazine
#BiluChiffon
የተለያዩ ምርጥ ሽፎኖች በተመጣጣኝ ዋጋ !
አድራሻ ፦ መርካቶ አዲሱ ሚሊተሪ ተራ / የሱቅ ቁጥር: F1-133C
ያናግሩን ፦ @bilalsiraje
ስልክ ፦ 0929091179 or 0931223346
#SouthEthiopiaRegion
➡️ " ... በረሀብ ከምንሞት መብታችን እየጠየቅን አደባባይ ላይ መሞት መርጠን ነው ወደ ርእሰ መስተዳድሩ ቢሮ የሄድነው " - የሶዶ ዙሪያ የመንግስት ሰራተኞች
➡️" ማንም መብቱን በነጻነት የመጠየቅ መብት አለው " - የደቡብ ክልል ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ሃፊዉ አቶ ወገኔ ብዙነህ
የ2 ወራት ደሞዛችን ይከፈለን ያሉ የወላይታ ዞን የመንግስት ሰራተኞች አደባባይ መውጣታቸዉን ተከትሎ በርካታ ያልጠበቋቸዉ ጉዳዮች እንደገጠሟቸዉ ገልጸዋል።
ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቃላቸውን የሰጡ ሰራተኞች ፥ " ጥያቄያችን ለመጠየቅ የተገደድነዉ ረሀቡ ስለጠናብን ነው " በማለት ላለፉት ወራት ከፍተኛ ችግር ውስጥ መቆየታቸውን ተናግረዋል።
አሁን ላይ ደሞዝ ከወሰድን 2 ወራችን ነዉ የሚሉት ሰራተኞቹ ከዚያ በፊትም በፐርሰንት እየተቆራረጠ ይሰጥ የነበረው ደሞዝ የማንወጣው እዳ ውስጥ አስገብቶን ነበር ብለዋል።
" በፐርሰንት ሲከፈለን በነበረበት ወቅት ችግሩን ለመቋቋም አበዳሪ ተቋማት ጋር ሂደን የምንበደረው ገንዘብ ወለዱ አሰቸጋሪ መሆኑ ሳያንስ ደሞዝ ሲቀርብን ደግሞ ሌላ ጣጣ ውስጥ ገባን " በማለት የችግራቸዉን ውስብስብነት አስረድተዋል።
" በዚህ ምክንያት በረሀብ ከምንሞት መብታችን እየጠየቅን አደባባይ ላይ መሞት መርጠን ነው ወደ ርእሰ መስተዳድሩ ቢሮ የሄድነዉ " በማለት ተናግረዋል።
ሰራተኞቹ " እስካሁን በየደረጃዉ የነበሩ የመንግስት አካላትን ስንጠይቅ ውክቢያና ማስፈራራት ነበር የሚገጥመን በተለይም መጀመሪያ ወደ ዞን አስተዳዳሪ ስናመራ ፖሊስ በትኖን መልሰን መሰባሰብ ሁሉ ከብዶን ነበር " ብለዋል።
" በመጨረሻ ወደ ርእሰ መስተዳድሩ ቢሮ ስንሄድ ሌላዉ ቢቀር ሀሳባችን ሰምተዉ አካሄዱን በማስረዳት ሀሳባችን በደብዳቤ እንድንገልጽ ፈቅደዉልናል " ብለዋል።
" ይሁንና አሁንም ጥያቄያችን ምላሽ አላገኘም " የሚሉት ሰራተኞቹ ተመልሰን ጥያቄያችን የት ደረሰ እንዳንልም ስላልተደራጀን በየጊዜዉ መሰባሰቡ ከበደን ብለዋል።
በመጀመሪያዉ ቀን የሰላማዊ ሰልፍ ሙከራ " ፖሊስ ሰራተኛዉን በትኗል " መባሉን በተመለከተ ጥያቄ ያቀረብንላቸዉ የክልሉ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ሀላፊዉ አቶ ወገኔ ብዙነህ በጉዳዩ ሰራተኛዉ ጥያቄ መጠየቁን እንጅ ከፖሊስ ጋር ግጭት እንደገባ መረጃ እንደሌላቸዉ ገልጸዋል።
ያም ሆኖ " ማንም መብቱን በነጻነት የመጠየቅ መብት አለው " ሲሉ ገልጸው " ችግሮች ተከስተዉ ከሆነ ወደፊት መረጃ እንሰጣችኋለን " ሲሉ ቃል ገብተዋል።
#TikvahEthiopiaFamilyHawassa
@tikvahethiopia
ኢትዮጵያ ለሚገኙ ወጣት ሴቶች ለ2ተኛ ዙር የቀረበ ጥሪ!
ስቴም ፖወር (STEMpower) ከፊንላንድ ኤምባሲ (Embassy of Finland Ethiopia) እና ከአይቢኤም (IBM) ጋር በመተባበር በኢትዮጵያ ከ1,000 በላይ ሥራ አጥ ወጣት ሴቶችን ተግባራዊ የሥራ ክህሎት ለመስጠት ያለመ "ትጋት" የተሰኘ ፕሮግራም አስተዋውቀዋል።
በመጀመያ ዙር 700 በላይ ለሚሆኑ ሴቶች በ Project Management, Web Development , Cyber Security, Digital Marketing , Data Analytics , Information Technology , Job Readiness , Work Readiness ስልጠና የሰጠ ከመሆኑ በተጨማሪ የስራ እድል በመፈጠር ተጠቃሚ እንዲሆኑ እድል አመቻችቷል፡፡
#ነጻ በሚሰጠውና ዓለም አቀፍ እውቅና ያለው ሰርተፊኬት በሚያስገኘው በዚህ ስልጠና እነዚህን ኮርሶች ለመውሰድ ፍላጎት ያላችሁ ሴቶች ምዝገባ የጀመርን መሆኑን እያሳወቅን ምዝገባው የሚቆየው ከ ግንቦት 7 - 20, 2016 ዓ/ም ሲሆን ቀድማችሁ በመመዝገብ የእድሉ ተጠቃሚ እንድትሆኑ እንጋብዛለን፡፡
እነዚህን ኮርሶች ለመውሰድ ፍላጎት ያላችሁ
👉 https://forms.office.com/r/i0fNZG4021
#Tecno #Camon30Pro5G
ቪድዮዎች እና ምስሎችን በከፍተኛ ጥራት ማንሳት እንዲያስችል Sony Imx890 የካሜራ ሴንሰርን የተገጠመለት አዲሱ Tecno Camon Pro 5G ምርጫዎ ያድርጉ
#Camon30Et #Camon30pro5GEt #Camon30 #Camon30Pro5G #TecnoEt
#IRAN🇮🇷
የኢራኑ ፕሬዝዳንት እና አብረዋቸው የነበሩ ከፍተኛ ባለስልጣናት (የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩን ጨምሮ) እየተፈለጉ ነው።
ህዝቡ መሪዎቹ ምንም ሳይሆኑ በህይወት ተርፈው ይመለሱ ዘንድ ፈጣሪውን እየለመነ ይገኛል።
ፕ/ት ኢብራሂም ራኢሲ እና ሌሎች ባለስልጣናት ኢራን ከአዘርባጀን ጋር በምትዋሰንበት አካባቢ ላይ የተገነቡ 2 ግድቦችን መርቀው ከከፈቱ በኋላ በሂሊኮፕተር ወደ ታብሪዝ ከተማ ሲያመሩ ነው ደብዛቸው የጠፋው።
ሄሊኮፕተሯ በአስቸጋሪ የአየር ሁኔታ ሳቢያ ከተራራ ጋር እንደተጋጨች ተነግሯል።
ሂሊኮፕተሯ ተጋጭታለች የተባለበት #ትክክለኛው ቦታ እስካሁን ድረስ ባይለይም ተጋጭታለች ተብሎ በታሰበበት እያንዳንዱ ቦታ ላይ ግን የነፍስ አድን ርብርብ እየተደረገ ይገኛል።
የአየር ሁኔታው ግን እጅግ በጣም ከባድ እንደሆነ ተሰምቷል።
ቪድዮ፦ ቀን እና ማታ ላይ የነበረውን የህዝቡን ሁኔታ የያሳያል።
@tikvahethiopia
#ኢራን
የኢራን ፕሬዝዳንት የሆኑት ኢብራሂም ራኢሲ ሲጓዙበት የነበረ ሄሊኮፕተር " #በአደገኛ_ሁኔታ " መሬት ላይ ማራፉን የኢራን መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።
የሀገሪቱ ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር ሂሊኮፕተሩ በአደገኛ ሁኔታ አርፎበታል ወደተባለበት ስፍራ ላይ አስቸጋሪ የአየር ሁኔታ እንዳለ ገልጿል።
የነፍስ አድን ሠራተኞች ወደ ቦታው ለመድረስ ጥረት እያደረጉ ይገኛሉ ሲል አሳውቋል።
ፕሬዝዳንቱ ሀገራቸው ከአዘርባጀን ጋር በምትዋሰንበት አካባቢ የተገነቡ ሁለት ግድቦችን መርቀው ከከፈቱ በኋላ ወደ ሰሜን ምዕራቧ የአገሪቱ ከተማ ታብሪዝ እያመሩ ነበር።
ሄሊኮፕተሩ አርፎበታል በተባለው ስፍራ ላይ ባለው ከባድ ጭጋግ ምክንያት የነፍስ ማዳን ፍለጋ ሥራው አስቸጋሪ እንደሆነ ተነግሯል።
Credit - FARS
@tikvahethiopia
#AddisAbaba
ገንዘብ ለማግኘት ሲሉ ብቻ ምንም ሳይታመሙ " ታመናል " ወይም ልጃቸው / ቤተሰባቸው ሳይታመም እንደታመመ አስመስለው እርዳታ የሚጠይቁ ሰዎች በትክክል ሊረዱ የሚገባቸው ሰዎችን እንዳይረዱ ያደርጋሉ።
ከዚህ ቀደም በውሸት ገንዘብ በእርዳታ መልክ ሲሰበስቡ ስለተያዙ ሰዎች መረጃ መለዋወጣችን አይዘነጋም።
ትላንት ደግሞ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጤናማ ልጁን " የካንሰር ህመምተኛ ነው " በማለት ሲለምንበት የተገኘ ወላጅን እና ግብረ-አበሩን ይዞ ምርመራ እያጣራ መሆኑን አሳውቋል።
በወንጀሉ የተጠረጠረው አባት (ጃዋር አብዱላሂ) ልጁን የካንስር ህመምተኛ በመሆኑ ለማሳከም ከአዋሽ 7 ወደ አዲስ አበባ መምጣቱንና ልጁን ለማሳከም እና ለምግብ እንዲሁም ለማደሪያ መቸገሩን በመግለፅ ከግብረ-አበሩ (አህመድ ከሊፈ) ጋር በመሆን በአ/አ በተለያዩ ቦታዎች ሲለምን ቆይቷል።
ትላንት ግን አንድ የፖሊስ አባል ነገሩን ተጠራጥሮ የህክምና ማስረጃ ሲጠይቃቸው ማሳየት አልቻሉም።
ፖሊስም ይዞ ፖሊስ ጣቢያ አስገብቷቸዋል።
የህፃኑ አባት እና ግብረ አበሩ ልጁ ታማሚ እንዲመስል አንገቱ ላይ ፕላስተር ለጥፈውበት የነበረ ሲሆን ፕላስተሩ ሲነሳ አንገቱ ላይ ምንም ቁስል የለም።
ህፃኑ በፖሊስ ጣቢያ ሲጠየቅ ጤነኛ መሆኑን ገልጿል።
#ኢትዮጵያዊ የተቸገረን ሰው መርዳት የቆየ ባህሉ ነው፤ ካለው ሰው ሲለምነው ጥሎ መሄድን አያውቅም ፤ ነገር ግን በውሸት / በማጭበርበር የሚካሄድ ተግባር እውነተኛ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ሰዎች እንዳይረዱ ያደርጋል።
እርዳታ ሲሰጥ የህክምና ማስረጃዎች መጠየቅ ይገባል።
@tikvahethiopia
#DStvEthiopia
🔥 የዘንድሮውን የፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮን በኤቨርተን እና ዌስትሃም ዛሬ ምሽት ይወስናሉ
⚽️ Manchester City vs Westham በ SS Premier League
⚽️ Arsenal vs Everton በ SS Liyu
🤔ዋንጫው የማን ነው? የእርሶን አስተያየት ያጋሩን
👉 ጨዋታዎችን ከትንታኔ ፣ ከተጫዋች ብቃት እስከ ቡድን ወኔ በሱፐርስፖርት ለመከታተል ዛሬውኑ ደንበኝነትዎን ያራዝሙ!
የዲኤስቲቪ አገልግሎቶችን ለማግኘት ከታች ያለውን የMyDStv Telegram bot ሊንክ ይጫኑ!
👇
https://mydstv.onelink.me/vGln/eth2
#PremierLeagueOnDStv #ሁሉምያለውእኛጋርነው #DStvEthiopia #DStvSelfServiceET
" ጥቃት አድራሾቹ #ባልና #ወንድም በቁጥጥር ስር ውለዋል " - የሀላባ ዞን ሰላምና ጸጥታ መምሪያ
ትላንት በባለቤቷ እንዲሁም በባለቤቷ እህት እና ወንድም ከፍተኛ ድብደባ እንደተፈጸመባት ገልጻ የህግ ድጋፍ ስለጠየቀችው ወይዘሮ አበባ ቦረና መረጃ ማጋራታችን ይታወሳል።
ጥቃት የደረሰባት ግለሰብ በሀላባ ከተማ ነዋሪ ስትሆን ጥቃት ካደረሰባት ባለቤቷ ጋር 4 ልጆች አፍርታለች።
ወ/ሮ አበባ " ተሰብስበዉ ሲደበድቡኝ ለመገላገል የገባዉን የመጀመሪያ ልጃችንም የጥቃቱ ሰለባ ሆኗል " ማለቷ አይዘነጋም።
በጉዳዩ ላይ ቃላቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የሰጡት የሀላባ ዞን ጸጥታ መምሪያ ሀላፊ አቶ ሙደሲር ጉታጎ ፥ " የሴት ልጅን ጥቃት አንታገስም " በማለት ከሀላባ ከተማ ፖሊስ ጋር በመተባበር ሁኔታውን መመልከት እንደጀመሩ ገልጸው ነበር ።
ዛሬ አቶ ሙደሲር ባደረሱን መረጃ ጉዳቱን ካደረሱ በኋላ ተደብቀዉ የነበሩት ወንድማማች ጥቃት አድራሾች ፖሊስ ባደረገዉ ጥረት ተገኝተው በቁጥጥር ስር ውለዋል።
አቶ ሙደሲር የግል ተበዳዩዋን በስልክ ደውለዉ ማነጋገራቸውን ገልጸውልናል።
" አሁን ላይ ሰዎቹ በህግ ቁጥጥር ስር ውለዋል " ያሉት ኃላፊው " ህጋዊ ምርመራ እንዲካሄድ ተበዳይ ሰኞ በአካል ቀርባ ክስ መመስረት ትችላለች " ብለዋል።
#TikvahEthiopiaFamilyHawassa
@tikvahethiopia
#OnlineNationalExam
የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዘንድሮ በኦንላይን ለሚሰጠው የሀገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና ተማሪዎች እንዴት የኦንላይን ፈተናውን መውሰድ እንደሚችሉ የሚያሳይ አንድ በአንድ የተዘረዘረ መመሪያ ይፋ አድርጓል።
ቪድዮ ፦ https://youtu.be/PdAu-FI-Q5M?si=PhIga8FlMtVsDUS2
#EAES
@tikvahethiopia
#Yonatan_BT_Furniture
ዮናታን ቢቲ ፈርኒቸር
የዘመናዊነት ተምሳሌት!
አድራሻችን፦
1. ዊንጌት አደባባዩን ተሻግሮ: +251 995 27 2727
2. ፒያሳ እሪ በከንቱ : +251 957 86 8686
3. ሲ ኤም ሲ አደባባዩን አለፍ ብሎ: +251 993 82 8282
👉 Telegram: /channel/yonatanbt_furniture
👉 Facebook: https://www.facebook.com/profile.php?id=100087238034736
👉 TikTok: yonatanbtfurniture" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@yonatanbtfurniture
👉 Instagram: https://www.instagram.com/yonatanbtfurniture/
#ሀላባ
- " ባለቤቴ ከወንድሙና እህቱ ጋር በመሆን ፊቴ እስኪበላሽ ደበደቡኝ " - ተበዳይ
- " እንዲህ አይነቱን የሴት ልጅ ጉዳት አንታገስም " - የሀላባ ዞን ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ሀላፊዉ አቶ ሙደሲር ጉታጎ
በሀላባ ከተማ " ባለቤቴ ከእህትና ወንድሙ ጋር በመሆን አደጋ አድርሶብኛል " ያለች ተበዳይ የህግ ድጋፍ ስጡኝ ስትል በማህበራዊ ሚዲያ ጥያቄ አቅርባለች።
ጉዳዩን የተመለከተው የሀዋሳ የቲኪቫህ ቤተሰብ አባል ባደረገዉ ማጣራት ፥ ተጎጅዋ ፊቷ ላይ ጉዳት መደረሱን በተጨማሪ የሷና የመጀመሪያ ልጇ ሰዉነት ትክሻቸዉ አካባቢ ' ጥርስ ንክሻ ' እንደደረሰባቸዉ ለማወቅ ችሏል።
የግል ተበዳዩዋ እናት ለቲክቫ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል ፤ ልጃቸዉና የልጅ ልጃቸዉ በደም ተዘፍቀዉ በምሽት ወደቤት እንደመጡና በወቅቱ ከፍተኛ ድንጋጤ ውስጥ ገንተው እንደነበር ገልጸዋል።
የግል ተበዳዩዋ ወ/ሮ አበባ ቦረና ፤ " ምንም እንኳን የጋራ አራት ልጆች ቢኖሩንም ካሁን በፊት በመካከላችን በነበረ ግጭት ምክኒያት በፍርድ ቤት ለመለያየት ጫፍ ከደርሰን በኋላ በሽማግሌ ተመልሰን አንድ ላይ መኖር ከጀመርን 3 ወር አልሆነም " ብላለች።
" ምንም እንኳን ቀን ላይ ቀላል ጭቅጭቅ ውስጥ ብንገባም ከቤተሰቡ ጋር ሆኖ እንዲህ ያደርጋል ብዬ ፍጹም አልጠበኩም " ስትል ተናግራለች።
" በተለይ ተሰብስበዉ ሲደበድቡኝ ለመገላገል የገባዉን የመጀመሪያ ልጃችን ላይ ላይ በዚህ ልክ ይጨክናል ብዬ አላሰብኩም ነበር " ብላለች።
ጉዳዩን በተመለከተ የጸጥታ አካላት ምን እየሰሩ ነዉ ? በማለት የጠየቅናቸው የሀላባ ዞን ሰላምና ጸጥታ ሀላፊ አቶ ሙደሲር ጉታጎ ፤ " እንዲህ አይነቱን የሴት ልጅ ጉዳት አንታገስም " ብለዋል።
ጉዳዩን በሰሙ ቅጽበት የከተማው ፖሊስ በፍጥነት ችግር ፈጣሪዎችን ይዞ እንዲያጣራ ማዘዛቸዉንም ነግረዉናል።
አቶ ሙደሲር ጉዳዩ ተጣርቶ የሚደረስበትን ውጤት እንደሚያጋሩን ቃል ገብተዋል።
#TikvahEthiopiaFamilyHawassa
@tikvahethiopia
ኢሕአፓ ምን አለ ?
የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ / #ኢሕአፓ / ፥ " ኢትዮጵያ እንደ አገር እንድትቀጥል በአገራችን የሕግ የበላይነት ሊኖር ይገባል " አለ።
ፓርቲው በላከው መግለጫ ላይ ፥ " የአገር ሕገ -መንግሥት ዜጎች ብቻ ሳይሆኑ መንግሥትም የሚገዛበት የአገሪቷ ሉዓላዊ ሕግ መሆኑ መታወቅ ይኖርበታል " ብሏል።
" የመንግሥት ፈርጣማ ጉልበት በሕገ መንግሥት የሚገታ ካልሆነ አንድ መንግሥት ሕዝብን ብቻ እንዳፈተተኝ አስተዳድርበታለሁ ካለ ሕገ መንግሥቱ ቅቡልነት አይኖረውም " ሲል ገልጿል።
ፓርቲው " የመንግሥት አካላት ዜጎችን እንደፈለጉ ፦
- ማሰር፣
- መግደል፣
- ማፈናቀል፣
- መደብደብ፣
- ማፈን፣
- ማንገላታት፣
- ማሳደድ፣
- ቤት ንብረታቸውን መቀማት ከጀመሩ መንግሥትንና ሕዝቡን የሚያስተሳስረው ሕግዊ ሥርዓት ትርጉም-አልባ ሆኗል ማለት ነው " ብሏል።
" መንግሥት በቅድሚያ ሕግ አክባሪ ሲሆን ነው ሕግን ማስከበር የሚችለው " ሲልም አክሏል።
" በኢትዮጵያ ውስጥ እስከዛሬ ድረስ የፈሰሰው የደም ጎርፍ ሊበቃ ይገባል " ያለው ኢሕአፓ " የብልጽግና መንግሥት በአገራችን ሠላምን ለማስፈን ተቀዳሚ እርምጃ ፦
° በሕዝብ ላይ ጦር መስበቁን፣
° ሠራዊት ማዝመቱን፣
° በድሮን
° በአየር ኃይል ሠላማዊ ሕዝብን መፍጀቱን በአስቸኳይ ማቆም ይኖርበታል፡፡ ሕዝብን ከዕልቂት ሀገርንም ከውድመት ማዳኛው ብቸኛው መንገድ ዛሬም ሠላማዊ የትግል መንገድ ነውና " ብሏል።
ፓርቲው በመግለጫው ሊቀመንበሩ፣ ረ/ፕሮፌሰር ዝናቡ አበራን ጨምሮ የታረሱ አባላቱ እንዲፈቱ ጠይቋል።
አባላቱና ሌሎች የእስረኞች አያያዙ እና ቆይታው ሰቅጣጭ በሆነበት " አዋሽ አርባ " እንደታሰሩ ነው ያመለከተው።
" እስር እና ማሰቃየት የስልጣን መንበርን ለአጭር ጊዜ ሊያጸና ይችል ይሆናል እንጂ ዘለቄታ የለውም " ያለው ፓርቲው " ገዢው ፓርቲ አገራችን እንደ አገር እንድትቀጠል እንዲሁም የወገኖቻችን ደህንነት እንዲጠበቅ ፣ ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን እስራቱ ፣ አፈናው ፣ ግድያው ፣ ወከባው ፣ ማስፈራራቱ ፣ ሕግን መጣሱ ማብቃት አለበት " ብሏል።
" የተለየ ሃሳብ ያላቸውን ሁሉ ማፈን አምባገነናዊ የሆነ ሥርዓትን ማንበርና በፍርሃት እየተናጡ ሌሎችንም እፎይታ ነስቶ መቆየትን እንጂ ለአገር ሠላም እና መረጋጋትን አያመጣም፣ ወደ ማኅበራዊና ኤኮኖሚያዊ እድገትም በፍጹም አይወስድም " ሲል አሳውቋል።
(ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል)
@tikvahethiopia
#Axum
" የሃውልቱ ዲዛይንና መሬት ላይ የተገነባው ለየቅል ነው ፤ አይገናኝም ! "
ዛሬ በአክሱም ከተማ የማህሌታይ ቅዱስ ያሬድ ሃውልት ተመርቋል።
ነገር ግን ከሃውልቱ ግንባታ ጋር በተያያዘ በርካቶች " አይመጥንም " በሚል ተቃውመዋል።
በአክሱም በይፋ የተመረቀው የማህሌታይ ቅዱስ ያሬድ ሃወልት ለግንባታው አራት (4) አመት መፍጀቱን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለመስማት ችሏል።
በምረቃ ስነ-ሰርዓቱ የተገኘው የመቐለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል በሃውልቱ ግንባታ ዙሪያ የተነሳው ተቃውሞ ተከታትሏል።
በምረቃ ስነ-ስርዓት ላይ የተገኙ ምእመናን እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች የኢትዮጵያና የዓለም የዜማ አባት የሆነው ማህሌታይ ቅዱስ ያሬድ የሚያስታውስ ሃወልት መቆሙ ቢያስደስታቸውም " ሃውልቱ የዜማ አባቱን ክብርና ዝና የሚመጥን አይደለም " ሲሉ ቅሬታቸውን ገልጸዋል።
በስነ-ሰርዓቱ ላይ የተገኙት የአክሱም ገዳማት ወ አድባራት አስተዳዳሪ ንቡረ እድ ጎደፋ መርሃ ምእመናኑና እና ታዳምያን " ሃወልቱ አይመጥንም " ሲሉ ያነሱትን ቅሬታ ተጋርተውታል።
የምረቃ ስነ-ሰርዓቱ በሚድያ ለህዝብ ይፋ ከሆነ በኃላ ' ሃወልቱ ቅዱስ ያሬድን አይወክልም ፤ አይመጥም ' የሚል በሀገር ውስጥ እና በውጭ ያለው ወገን ተቃውሞውን በማህበራዊ ሚድያ ትስስር ገጾች ላይ በስፋት እያጋራ ነው።
ከዚህ አለፍ ሲል ፈርሶ ድጋሜ እንዲገነባና ሃወልቱ ማህሌታይ ያሬድን በሚመጥን መልኩ በሀገር ያሉና በውጭ ያሉ ባለሞያዎችን አሳትፎ እንዲገነባ " ገንዘብ እናዋጣለን " እንዲሁም እውቀታችንን እናካፍላለን ያሉ አሉ።
" የሃውልቱ ዲዛይን እና መሬት ላይ የተገነባው ለየቅል ነው አይገናኝም " ያሉ አንዳንድ አስተያየት ሰጪዎች ደግሞ የትግራይ የባህልና ቱሪዝም ባለመከታተሉ ወቅሰዋል።
ሃወልቱ #በመቐለ_ዩኒቨርስቲ እና በአክሱም ገዳማት ወ አድባራት አስተዳደር ትብብር የተገነባ ሲሆን ለግንባታው ከ1 ነጥብ 6 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ ተደርጎበታል ተብሏል።
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle
@tikvahethiopia
" እኛም በተፈጠረው በጣም አዝናል ፤ ነገር ግን ተደጋጋሚ የሚባለው ፍፁም ትክክል አይደለም " - ሀዋሳ የሚገኘው የንብ ባንክ ህንጻ
ረቡዕ በሀዋሳ ከተማ በነበረው ንፋስ የቀላቀለ ከባድ ዝናብ ወቅት ፒያሳ ከሚገኘው የንብ ባንክ ህንጻ ላይ ወደታች የወደቀ መስታወት የአንድ ወጣት የካፌ አስተናጋጅን ህይወት ቀጥፏል።
ጉዳዩን በተመለከተ ጥቆማ እየሰጡ አንድ የሀዋሳ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ፤ ችግሩ ተደጋጋሞ ይከሰታል የሚል ቃላቸውን ሰጥተው ነበር።
የሀዋሳ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጠው ቃል ፥ እሮብ ከህንጻው በወደቀ መስታወት አንድ ወጣት የካፌ አስተናጋጅ ተጎድቶ ሆስፒታል ቢወሰድም ህይወቱ ሊተርፍ እንዳልቻለ አረጋግጦ ነበር።
ነገር ግን " ተደጋጋሚ ችግር አለ " ለሚባለው ቅሬታ " ምንም አይነት የደረሰ አደጋን የሚመለከት ሪፖርት ከዚህ ቀደም እንዳልመጣለት አሳውቋል።
ዛሬ ህንጻው አስተዳደር ክፍል ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ምላሽ ሰጥቷል።
አንድ ቃላቸውን የሰጡ አካል ፤ እሮብ የተፈጠረው ትክክል ስለመሆኑ ማረጋገጫ ሰጥተው በተፈጠረው ነገር ሁሉም እጅግ ማዘኑን ገልጸዋል።
ነገር ግን " ከዚህ ቀደም ተደጋጋሚ ችግር ተስተውሏል " የሚለው ፍጹም ትክክል እንዳልሆነ እና ህንጻው ጉድለት እንደሌለበት አስገንዝበዋል።
" ተደጋጋሚ ችግር " ተብሎ የተሰጠው ጥቆማ ምናልባትም ከወር በፊት ከጎን ካለ #የአዋሽ_ባንክ ህንጻ በንፋስ ምክንያት ወደ ታች የወደቀ ቁስ በንብ ህንጻ ስር ባለ ካፌ የመኪና ማቆሚያ ላይ ያደረሰውን ጉዳት ዋቢ ተደርጎ ሊሆን ይችላል እንጂ ህንጻው ከዚህ ቀደም ምንም ችግር ገጥሞት አያውቅም ብለዋል።
የሀዋሳ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ የሰጠው መረጃም ትክክለኛ ነው ሲሉ ተናግረዋል።
#TikvahEthiopiaFamilyHawassa
@tikvahethiopia
#Tecno #Camon30Pro5G
የሞባይል ቴክኖሎጂን ጨምሮ የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ ብራንድ አምራች የሆነው እና ከ70 በላይ ሀገራት
ምርቶቹን በስፋት የሚያቀርበው ቴክኖ አዲስ የሞባይል ቴክኖሎጂ ውጤት የሆነውን ካሞን 30 ፕሮ 5G ሞዴል በአዲስ አበባ ሸራተን አዲስ ሆቴል የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች፣ ከፍተኛ ባለስልጣናት፣ እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት አስተዋወቀ።
አዲሱ ካሞን 30 ፕሮ 5G የሶኒ(SONY) የካሜራ ሴንሰር ቴክኖሎጂን ጨምሮ የተለያዩ የቴክኖ ምርምር ውጤት የሆኑ የቴክኖሎጂ ግብዓቶችን አካቶ የተመረተ ሞዴል ነው።
የኢትዮ ቴሌኮም ቺፍ ማርኬቲንግ ኦፊሰር የሆኑት አቶ ሰኢድ አራጋው በዝግጅቱ ላይ እንደተናገሩት ‘’ ኢትዮ ቴሌኮም እና ቴክኖ ሞባይል በጋራ በመሆን ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ ይሰራሉ’’ ብለዋል።
#Camon30Et #Camon30pro5GEt #Camon30 #Camon30Pro5G #TecnoEt
#Hawassa
➡️ " ንፋስ በመጣ ቁጥር ጉዳት እየደረሰ ነው። እሮብ የአንድ ሰው ህይወት አልፏል " - የሀዋሳ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል
➡️ " ጉዳት የደረሰበት የካፌ አስተናጋጅ ነው። በወቅቱ ወደህክምና ተወስዶ የህክምና እርዳታ ቢደረግለትም ህይወቱ ግን ሊተርፍ አልቻልም " - የሀዋሳ ከተማ ሰላምና ጸጥታ
በሀዋሳ ከተማ ፤ ፒያሳ በሚገኘው ንብ ባንክ ህንጻ ላይ የወደቀ መስታወት የአንድ ወጣት ህይወት ቀጥፏል።
ህንጻው በዝናብና ንፋስ ወቅት እቃ ሲወድቅበት የመጀመሪያው እንዳልሆነ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከሀዋሳ የቤተሰብ አባላቱ ጥቆማ ደርሶታል።
በቅርቡ የተመረቀዉ የንብ ህንጻ ከዘጠነኛ ፎቅ ላይ የወደቀ መስታወት የህንጻው ወለል ላይ ስራ ላይ የነበረ ሰራተኛ ላይ ማረፉን ተከትሎ ሰራተኛው ህይወቱ አልፏል።
በሀዋሳ እሮብ ከ9 ሰአት በኋላ የነበረው ከባድ ዝናብና ውሽንፍር ባስከተለዉ ነፋስ ከህንጻዉ ላይ የወደቀ መስታወት የሰዉ ህይወት ማጥፋቱን ለማረጋገጥ ችለናል።
አንድ የሀዋሳ የቤተሰባች አባል ፤ " ንፋስ በመጣ ቁጥር ከህንጻው ላይ በሚወድቅ ቁስ ተደጋጋሚ ጉዳት በግለሰቦች ላይ ሰራተኞች ላይ እየደረሰ ነው። እሮብ አንድ ሰራተኛ መስታወት ወድቆበት እጁ የመቆረጥ ፣ አናቱ ላይ የመጎዳት በኃላም ህይወቱ አልፏል። ህንጸው ግልጽ የሆነ የግንባታ ጉድለት ይታይበታል " ሲል ቃሉን ሰጥቷል።
በዚህ ጉዳይ ላይ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ማብራሪያ የሰጡት የሀዋሳ ከተማ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ሀላፊ አቶ ወንድማገኝ ቶርባ ፤ ጉዳት የደረሰበት ወጣት የካፌ አስተናጋጅ መሆኑንና በወቅቱ ወደህክምና ተወስዶ የህክምና እርዳታ ቢደረግለትም ህይወቱ ግን ሊተርፍ እንዳልቻለ ገልጸዋል።
ይሁንና " ህንጻው ላይ ተደጋጋሚ ችግር ተስተውሏል " ለሚባለዉ ቅሬታ ካሁን በፊት የደረሰ አደጋን የተመለከተ ሪፖርት የለም ሲሉ ገልጸዋል።
በወቅቱ በዚህ ህንጻ ውስጥ ከደረሰዉ አደጋ ውጭ በከተማዉ የተከሰተዉ ነፋስ በርካታ የንብረት ጉዳት ማስከተሉንም አስታውሰዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ የህንጻዉን አስተዳዳሪዎች በጉዳዩ ዙሪያ ለማነጋገር ያደረገዉ ሙከራ አልተሳካም። ምላሽ አለም ካሉ መስተናገድ ይችላሉ።
#TikvahEthiopiaFamilyHawassa
@tikvahethiopia
በተማሪ ደራርቱ ለሜሳ ግድያ ዙሪያ የአሶሳ ፖሊስ ምን አለ ?
የአሶሳ ዩኒቨርስቲ ተማሪ በነበረችው ደራርቱ ለሜሳ ግድያ ወንጀል የተጠረጠረ ግለሰብ በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያጣራ እንደሚገኝ የአሶሳ ከተማ ፖሊስ አስታውቋል።
ፖሊስ የወንጀል ድርጊቱ የተፈጸው በአሶሳ ከተማ አስተዳደር ወረዳ አንድ ልዩ ቦታው " ሰላም ሰፈር " ተብሎ በሚጠራው አከባቢ ረቡዕ ከጧቱ በግምት 2:45 ላይ እንደሆነ አመልክቷል።
" በሟች እና በተጠርጣሪው መካከል በተፈጠረ በሀሳብ ያለመግባባት ምክንያት ተጠርጣሪው በአሰቃቂ ሁኔታ ጀርባዋ ላይ #በጩቤ_በመውጋት የተማሪዋ ህይወት እንዲያልፍ አድርጓል " ሲል ፖሊስ ገልጿል።
ተጠርጣሪውን ግለሰብ በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያጣራ እንደሚገኝም አሳውቋል።
የከተማው ፖሊስ የወንጀል ድርጊቱ የተፈጸመው ከዩኒቨርስቲው ግቢ ውጭ እንደሆነ አመልክቷል።
ተጠርጣሪው የግቢ ተማሪ ያልሆነና ከአዲስ አበባ ዱከም ከተማ አቋርጦ ወደ አሶሳ ከተማ ለስራ ጉዳይ በመምጣት የወንጀል ድርጊቱን እንደፈጸመ ገልጿል።
በአንዳንድ ማህበራዊ ሚድያዎች " ድርጊቱ የተፈጸመው በግቢ ውስጥ ነው " በሚል የሚሰራጨው እና የብሔር ግጭት አስመስለው የሚወራው ፍጹም ከእውነት የራቀ እና ሁለቱም የአንድ ብሔር ተወላጅ እንዲሁም በጓደኝነት አብረው የነበሩ መሆኑን የአሶሳ ከተማ ፖሊስ አሳውቋል።
#AssosaPolice
@tikvahethiopia