ገደብ ወይም ድንበር M-PESA ጋር አይሰራም! ከኬንያ ገንዘባችንን በ M-PESA ተቀብለን ተጨማሪ የ1ጊ.ባ. ነጻ የኢንተርኔት ስጦታችንን አሁኑኑ እንቀበል!
የ M-PESA ሳፋሪኮም መተግበሪያን በዚህ ሊንክ እናውርድ፦ https://play.google.com/store/apps/details?id=et.safaricom.mpesa.lifestyle
የቴሌግራም ቻናላችንን እዚህ እንቀላቀል 👉 /channel/Safaricom_Ethiopia_PLC
ስለ አገልግሎታችን ማንኛውንም ጥያቄ ወይም መረጃ በቴሌግራም ቻናላችን /channel/Safaricom_Ethiopia_PLC 24/7 ማግኘት ይቻላል!
#MPESASafaricom #FurtherAheadTogether
#የሥራ_ቅጥር_ዕድል_ጥቆማ
#WerabeUniversity
ወራቤ ዩኒቨርሲቲ በሶሲዮሎጂ እና በጂኦግራፊ የትምህርት ክፍሎች መምህራንና ቴክኒካል ረዳቶችን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል፡፡
➤ የሥራ መደብ፦ በሁለት የትምህርት ክፍሎች
➤ ተፈላጊ ባለሙያዎች ብዛት፦ 6
➤ ተፈላጊ የትምህርት ደረጃ፦ 2ኛ ዲግሪ
➤ የሥራ ቦታ፦ ወራቤ ዩኒቨርሲቲ
መስፈርቱን የምታሟሉ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ከታህሳስ 1/2017 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት ተከታታይ አስር የሥራ ቀናት ማመልከት ትችላላችሁ ተብሏል፡፡ አመልካቾች ሙሉ የህይወት ታሪካቸውን (CV) እና ሙሉ የትምህርት ማስረጃችሁን ዋናውና የማይመለስ ኮፒ በመያዝ በዩኒቨርሲቲው የብቃትና ሰው ሃብት አስተዳደር ሥራ አስፈጻሚ ቢሮ ቁ. 3 መመዝገብ ትችላላችሁ፡፡
@tikvahuniversity
ደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ተመድቦለታል።
ታደሰ ረጋሳ (ዶ/ር) ከታህሳስ 1 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ የደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ሆነው መመደባቸውን በትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) በቀን ህዳር 30/2017 ዓ.ም ተፈርሞ የወጣ የምደባ ደብዳቤ ያሳያል።
ለታ ተስፋዬ (ዶ/ር) የደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ ሆነው ሲያገለግሉ መቆየታቸው ይታወቃል።
@tikvahuniversity
ራያ ዩኒቨርሲቲ በቀጣይ ወር የሚሰጠውን ሀገር አቀፍ የመውጫ ፈተና ለሚወስዱ መደበኛ እና ኢ-መደበኛ ተማሪዎች ሞዴል የመውጫ ፈተና ሰጠ።
ሞዴል ፈተናው ተፈታኞችን በጥር ወር 2017 ዓ.ም ለሚሰጠው ሀገር አቀፍ የመውጫ ፈተና (Exit Exam) ለማዘጋጀት ግብ ያደረገ መሆኑ ተገልጿል፡፡
ነሐሴ 2014 ዓ.ም በፀደቀው የመውጫ ፈተና ማስፈጸሚያ መመሪያ መሰረት፣ በከፍተኛ ትምህርት ቆይታቸው ሁሉንም ኮርሶች ወስደው ያጠናቀቁ ወይም የመጨረሻ ዓመት የሁለተኛ ሴሚስተር ተማሪዎች ሊሆኑ ይገባል፡፡
@tikvahuniversity
#ጥቆማ
እንግሊዝኛ ቋንቋን ያለምንም ክፍያ በማንኛውም ጊዜ እና በየትኛውም ቦታ ሆነው ይማሩ!
ትምህርት ሚኒስቴር ያዘጋጀውን የመምህራን እና የተማሪዎችን እንግሊዘኛ ቋንቋን ለማሻሻል የሚያግዝ ፖርታል ይጠቀሙ፡፡
ፖርታሉ ከቅድመ አንደኛ ደረጃ ጀምሮ ለሁሉም የክፍል ደረጃዎች የተዘጋጀ ሲሆን፤ በቀላሉ ለመረዳት በሚቻሉ በድምፅ፣ በፅሁፍ እና በምስል በተቀናበሩ ማስተማሪያዎች የእንግሊዝኛ ቋንቋን ለማሻሻል የሚያስችል ትምህርት ያገኛሉ።
ፖርታሉን ለመጠቀም ኢንተርኔት የሚያስፈልግ ቢሆንም ገንዘብ የማይቆርጥ ሲሆን፤ በስማርት ስልክ፣ ስማርት ቴሌቪዥን፣ በታብሌት እና በኮምፒውተር በማንኛውም የዌብ መፈለጊያ (browser) መጠቀም ይቻላል፡፡
ፖርታሉን ለማግኘት 👇
http://learn-english.moe.gov.et
@tikvahuniversity
20ኛ ዙር ሙሉ የሒሳብ መዝገብ አያያዝ (Principle and Practice of Accounting) የስድስት ወር የቅዳሜ እና እሑድ ስልጠና በፒያሣ እና በመገናኛ ካምፓስ ምዝገባ ላይ ነን!
👉 100% በተግባር የተደገፈ ስልጠና
👉 መሠረታዊ የአካውንቲንግ እና ኦዲት አሰራር፣ ሙሉ የአካውንቲንግ ሒሳብ አሰራር በፒስቺሪ ተደግፎ እና የግብር አያያዝ ትምህርቶችን አካቶ የሚሰጥ
👉 የሥራ ላይ ስልጠና (Internship) የተመቻቸለት
☎️ 0906777799 / 0906777755
አድራሻ፦ ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ እና ቁ.2 መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ
Telegram: /channel/sagetraininginstitute
TikTok: sage_training_institute" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@sage_training_institute
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute
📽 😍 የምርጥ አስሩን ቆይታ እንከታተል!
የሳፋሪኮም #1Wedefit ዲጂታል የሙዚቃ ውድድር ኮከቦቻችን ያደረጉትን አስደሳች ቆይታ የመጀመሪያ ክፍል ቅዳሜ ምሽት 3:00 ሰዓት በአርትስ ቲቪ እንዲሁም እሁድ ከሰዓት 9፡00 በአባይ ቲቪ እንድትከታተሉ እንጋብዛችኋለን!
#SafaricomEthiopia
#1Wedefit
#FurtherAheadTogether
#DigitalMusicChallenge
360 ሺህ ወጣቶች "የአምስት ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ኮደርስ" የስልጠና መርሐግብርን እየተከታተሉ ነው፡፡
መርሐግብሩ እስካሁን 360 ሺህ ሰልጣኞች መመዝገባቸውንና ከ78 ሺህ በላይ ሰልጣኞች የምስክር ወረቀት ማግኘታቸውን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ይሽሩን አለማየሁ (ዶ/ር) ለኢዜአ ተናግረዋል።
ፕሮጀክቱ በቀጣዮቹ ሦስት ዓመታት አምስት ሚሊዮን ኢትዮጵያውያንን በዌብ ፕሮግራሚንግ፣ በአንድሮይድ ማበልፀግ እና በዳታ ሳይንስ መሠረታዊ የዲጂታል ክህሎት እንዲጨብጡ የሚያስችል ነው።
ለመመዝገብ 👇
https://www.ethiocoders.et/
@tikvahuniversity
የግራፊክ ዲዛይን፣ ቪዲዮ ኢዲቲንግ፣ ሞሽን ግራፊክ እና ዲጂታል ማርኬቲንግ ስልጠና በፒያሣ እና መገናኛ ካምፓስ ምዝገባ ላይ ነን!
👉 100% በተግባር የተደገፈ ስልጠና
👉 Advanced Graphics + Video Editing + Motion Graphics + Digital Marketing በአንድ ላይ
👉 ከ50 በላይ ፕሮጀክቶች ያሉት
👉 የሥራ ላይ ስልጠና (Internship) የተመቻቸለት
☎️ 0906777799 / 0906777755
አድራሻ፦ ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ እና ቁ.2 መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ
Telegram: /channel/sagetraininginstitute
TikTok: sage_training_institute" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@sage_training_institute
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute
ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ ሆነው ተመድበዋል፡፡
የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትሯ ከህዳር 18/2017 ዓ.ም ጀምሮ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ ሆነው በትምህርት ሚኒስቴር መመደባቸው ታውቋል፡፡
የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ኃላፊ እና የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር አለምፀሐይ ጳውሎስ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ የቦርድ ሰብሳቢ በመሆን ሲያገለግሉ ቆይተዋል፡፡
@tikvahuniversity
የደቡብ አፍሪካው ዩኒቨርሲቲ UNISA 62 የድኅረ-ምረቃ ፕሮግራም ተማሪዎችን በአዲስ አበባ ስካይላይት ሆቴል አስመርቋል።
ተመራቂዎቹ 59 በፒ.ኤች.ዲ. እና ሦስት በማስተርስ ፕሮግራም ስልጠናቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ መሆናቸው ተገልጿል።
የ UNISA የኢትዮጵያ ትምህርት ማዕከል በደቡብ አፍሪካ እና በኢትዮጵያ መንግሥታት ስምምነት የተመሰረተ ሲሆን፤ ማዕከሉ እስካሁን 1,099 በድኅረ-ምረቃ ፕሮግራም የሰለጠኑ ምሩቃንን አፍርቷል።
በኢትዮጵያ የUNISA ምሩቃን በመንግሥት ተቋማት፣ በዩኒቨርሲቲዎች፣ መንግሥታዊ ባልሆኑ አካባቢያዊ ተቋማት እና ሌሎች መሰል ድርጅቶች በከፍተኛ ኃላፊነቶች ላይ የሚገኙ መሆናቸውን ዩኒቨርሲቲው ለቲክቫህ የላከው መግለጫ ያሳያል።
ከተቋቋመ 150 ዓመት የሆነው UNISA፥ በርቀት ትምህርት እና ኢ-ለርኒንግ በአፍሪካ ግዙፍ ተቋም ሲሆን፤ ለሰልጣኞቹ ዓለም አቀፍ ዕውቅና ያለው ዲግሪ ይሰጣል።
@tikvahuniversity
Top Training Institute ከአሁን ቀደም ከሚሰጣቸው የኮምፒውተር እና የቋንቋ ስልጠናዎች በተጨማሪ በ Photography, Videography & Cinematography ስልጠናዎችን ዘመናዊ ካሜራዎችን በማሟላት በሙያው የረጅም ጊዜ ልምድ ባላቸው አሰልጣኞች መስጠት የጀመረ መሆኑን በአክብሮት ይገልጻል።
አድራሻ፦
● መገናኛ መተባበር ህንፃ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁ. 419 (ሊፍት ይጠቀሙ) ☎️ 0991929303
● ሜክሲኮ ኬኬር ህንፃ 6ኛ ፎቅ ቢሮ ቁ. 639 (2ኛውን ሊፍት ይጠቀሙ) ☎️ 0991929304
● ጀሞ 1 አንደኛ በር ካኩ ቢዝነስ ሴንተር 3ኛ ፎቅ ☎️ 0991926707
@Top_trainings
Join our Telegram Channel:
/channel/topinstitutes
#OdaBultumUniversity
በ2017 ዓ.ም ለሪሚዲያል ፕሮግራም በኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ታህሳስ 7 እና 8/2017 ዓ.ም ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።
ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦
- የ8ኛ ክፍል ስርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
- የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ዋናውና ኮፒው፣
- ከ9ኛ-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
- አራት ፓስፖርት መጠን ፎቶግራፍ፣
- አንሶላ፣ ትራስ ጨርቅ፣ ብርድ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ።
የምዝገባ ቦታ፦
ጭሮ ከተማ በሚገኘው የዩኒቨርሲቲው አዲሱ ካምፓስ
@tikvahuniversity
#BuleHoraUniversity
በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ ሀገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ በ2017 ዓ.ም ለሪሚዲያል ፕሮግራም ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ ገቢ ተማሪዎች ሪፖርት ማድረጊያ ቀናት ታህሳስ 7 እና 8/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።
ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦
- ከ8ኛ-12ኛ ክፍል የትምህርት ማስረጃዎች ዋናውና ኮፒው፣
- ስምንት 3X4 ጉርድ ፎቶግራፍ፣
- ትራስ ጨርቅ፣ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ፡፡
@tikvahuniversity
#DillaUniversity
በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ ሀገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ ለሪሚዲያል ፕሮግራም ውጤት አምጥታችሁ ዲላ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ ገቢ ተማሪዎች ሪፖርት ማድረጊያ ቀናት ታህሳስ 14 እና 15/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።
የምዝገባ ቦታ፦
ኦዳያኣ ግቢ ሬጂስትራር ጽ/ቤት
ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦
- ከ9ኛ-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
- የ8ኛ ክፍል ካርድ ዋናውና ኮፒው፣
- አራት 3X4 ጉርድ ፎቶግራፍ፣
- ትራስ ጨርቅ፣ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ፡፡
@tikvahuniversity
#ጥቆማ
በ2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በቀን መርሐግብር በሁለተኛ እና በሦስተኛ ዲግሪ እንዲሁም በማታ መርሐግብር በሁለተኛ ዲግሪ መማር የምትፈልጉ ተቋሙ ያስቀመጣቸውን መስፈርቶች በማሟላት እስከ ታህሳስ 11/ 2017 ዓ.ም ድረስ ማመልከት ትችላላችሁ፡፡
ታህሳስ 17 እና 18/2017 ዓ.ም የመግቢያ ፈተና እንደሚሰጥ ተገልጿል።
ከታህሳስ 23/2017 ዓ.ም እስከ ጥር 2/2017 ዓ.ም የመመዝገቢያ ጊዜ ነው የተባለ ሲሆን፤ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሬጅስትራር ቢሮ ቁ. 203 በአካል በመገኘት የትምህርት ማስረጃ ማስገባት ይጠበቅባችኋል ተብሏል፡፡
@tikvahuniversity
የኢንቴሪየር ዲዛይን (Interior Design) ስልጠና ምዝገባ ላይ ነን!
👉 Sketch-Up, Revit, Rhino, 3D Max እና Lumion ሶፍትዌሮችን በአንድ ላይ
👉 ከንድፈ ሀሳብ እና ሶፍትዌር ስልጠና በተጨማሪ በተግባር በወርክሾፕም የሚሰጥ
☎️ 0906777799 / 0906777755
አድራሻ፦ ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ እና ቁ.2 መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ
Telegram: /channel/sagetraininginstitute
TikTok: sage_training_institute" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@sage_training_institute
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute
የመጀመሪያው ብሔራዊ የተማሪዎች የሽልማትና ዕውቅና መርሐግብር በዚህ ወር መጨረሻ ይካሔዳል፡፡
መርሐግብሩ ታህሳስ 26 ቀን 2017 ዓ.ም በአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም ለማካሄድ ቅድመ ዝግጅት ማጠናቀቁን የሽልማት ድርጅቱ መስራችና ሥራ አስኪያጅ አቶ ቢንያም ጫኔ ለቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ተናግረዋል፡፡
በ2016 ዓ.ም ሀገር አቀፍ ፈተና ወስደው ከፍተኛ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች፣ ሴቶችና አካል ጉዳተኞች፣ ባለተሰጥኦ ተማሪዎች፣ በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና አስፈትነው ሙሉ በሙሉ ተማሪዎቻቸውን ያሳለፉ ትምህርት ቤቶች እንዲሁም ምስጉን መምህራን ዕውቅና ይሰጣቸዋል ብለዋል፡፡
በመርሐግብሩ ውጤታማ ተማሪዎች እንዲሁም ለትምህርት እድገት ጉልህ ሚና የተጫወቱ ግለሰቦች፣ ተቋማትና ድርጅቶችን ጨምሮ 50 ለሚሆኑ አካላት ዕውቅና ይሰጣል ተብሏል፡፡
የሽልማት ፕሮግራሙ ከሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር የሚዘጋጅ መሆኑን ሰመተናል።
የሽልማት ዘርፎች
- ለዩኒቨርስቲ መግቢያ ውጤት በሀገር አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ነጥብ ያመጡ ተማሪዎች
- ለዩኒቨርሲቲ መግቢያ ከፍተኛ ነጥብ ያመጣች ሴት ተማሪ እና አካል ጉዳተኛ ተማሪ
- 100% ወደ ዩኒቨርሲቲ ያሳለፉ ትምህርት ቤቶች
- በኮሚቴው መለኪያ ያለፉ በጀነሬሽን ሦስት ዩኒቨርሲቲዎች
- ምርጥ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት (ሦስት)
- ምስጉን መምህራን (ሦስት)
- ባለተሰጦኦ ተማሪዎች
- የፈጠራ ባለቤቶች (ሦስት)
- በትምህርት ልማት የተሳተፉ አምስት ባለሃብቶች
- ለትምህርት ዕድገት የላቀ ሚና ለተወጡ ዓለም አቀፍ ተቋማት (ሦስት)
- የህይወት ዘመን ተሸላሚ በተለያዩ ዘርፎች
- ልዩ ተሸላሚ
@tikvahuniversity
Top Training Institute ከአሁን ቀደም ከሚሰጣቸው የኮምፒውተር እና የቋንቋ ስልጠናዎች በተጨማሪ በ Photography, Videography & Cinematography ስልጠናዎችን ዘመናዊ ካሜራዎችን በማሟላት በሙያው የረጅም ጊዜ ልምድ ባላቸው አሰልጣኞች መስጠት የጀመረ መሆኑን በአክብሮት ይገልጻል።
አድራሻ፦
● መገናኛ መተባበር ህንፃ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁ. 419 (ሊፍት ይጠቀሙ) ☎️ 0991929303
● ሜክሲኮ ኬኬር ህንፃ 6ኛ ፎቅ ቢሮ ቁ. 639 (2ኛውን ሊፍት ይጠቀሙ) ☎️ 0991929304
● ጀሞ 1 አንደኛ በር ካኩ ቢዝነስ ሴንተር 3ኛ ፎቅ ☎️ 0991926707
@Top_trainings
Join our Telegram Channel:
/channel/topinstitutes
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ 319 የተቋሙን የቅድመ-ምረቃ እና የድህረ-ምረቃ ተማሪዎች በቻይና ኢትዮጵያ ወዳጅነት ስኮላርሺፕ ተጠቃሚ አደረገ።
በቻይና ኢትዮጵያ ወዳጅነት ስኮላርሺፕ ሽልማት መርሐግብር ላይ የተገኙት አዲሱ በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ቹን ሀይ 2100 መጻሕፍት እና 30 ታብሌት ኮምፒዩተሮችን ለዩኒቨርሲቲው አበርክተዋል፡፡ #AAU
@tikvahuniversity
የመጀመሪያው ብሔራዊ የተማሪዎች ሽልማት መርሐግብር ሊካሔድ ነው!!!
የኢትዮጵያ ብሔራዊ የተማሪዎች ሽልማት (Ethiopian National Students' Award) የተባለ በትምህርት ላይ ለመስራት የተቋቋመ መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት፣ በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነውን ብሔራዊ የተማሪዎች ሽልማት በታህሳስ 2017 ዓ.ም ያካሒዳል፡፡
ፕሮግራሙ ውጤታማ ተማሪዎችን፣ ምስጉን መምህራንን እንዲሁም በመማር ማስተማር ምሳሌ የሆኑ የመንግሥት እና የግል የትምህርት ተቋማትን እንደሚሸልምና ዕውቅና እንደሚሰጥ ድርጅቱ ለቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ገልጿል፡፡
ድርጅቱ በተያዘው ወር የሚያካሒደውን የሽልማት ስነ-ስርዓት አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ ነገ ረቡዕ ታህሳስ 2/2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ገነተ ልዑል አዳራሽ ጠዋት 3፡30 ይሰጣል፡፡
@tikvahuniversity
የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ በ2018 ዓ.ም ወደ ከፊል ራስ-ገዝ ዩኒቨርሲቲ ለመሸጋገር የተለያዩ ሥራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝ ገለፀ፡፡
ተቋሙ ራስ-ገዝ ለመሆን የሚያደርገዉ ጉዞ ሁለተኛ ምዕራፍ ሂደት ላይ የደረሰ ሲሆን፤ የተለያዩ ሕጎች፣ መመሪያዎች እና ፖሊሲዎች ማዘጋጀቱ ተገልጿል፡፡
ዩኒቨርሲቲው ባዘጋጀው "የተማሪዎች ምልመላ፣ መረጣና ቅበላ ረቂቅ ፖሊሲ” ላይ ግምገማዊ ወርክሾፕ አካሒዷል፡፡
ረቂቅ ፖሊሲው ለመጀመሪያ ዲግሪ፣ ለሁለተኛ ዲግሪ እና ለሦስተኛ ዲግሪ ተማሪዎች (የውጪ ሀገር አመልካቾችን ጨምሮ) ከምዝገባ ጀምሮ እስከ ተማሪዎችን ተቀብሎ ማስተማር ድረስ ያለው ሒደት እና መስፈርት በዝርዝር ተካቷል፡፡
@tikvahuniversity
ቦንጋ የትምህርት ኮሌጅ የአዲስ ገቢ አንደኛ ዓመት ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ታህሳስ 3 እና 4/2017 ዓ.ም እንዲሁም በቅጣት ታህሳስ 7/2017 ዓ.ም መሆኑን አሳውቋል፡፡
ትምህርት ታህሳስ 7/2017 ዓ.ም ይጀምራል ተብሏል፡፡
@tikvahuniversity
ነጻ የትምህርት ዕድል
ባህርዳር ዩኒቨርሲቲ በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ የማጠቃለያ ፈተና ወስደው ከፍተኛ ውጤት (500 እና ከዛ በላይ ከ600) ያስመዘገቡ ተማሪዎችን ሙሉ ነጻ የትምህርት ዕድል በመስጠት በ2017 ዓ.ም በመደበኛ መርሐግብር ማስተማር ይፈልጋል፡፡
የማመልከቻ ጊዜ የሚያበቃው፡-
ታህሳስ 3/2017 ዓ.ም
ለማመልከት የሚያስፈልጉ፦
➭ የ12ኛ ክፍል ካርድ ውጤት ዋናውና ኮፒ፣
➭ የማመልከቻ ክፍያ 300.00 (ሦስት መቶ) ብር
የማመልከቻ ቦታ፦
በየአካዳሚክ ክፍል ባሉ ሬጅስትራር ጽ/ቤቶች
የትምህርት ፕሮግራም ምደባ ከሌሎች የመደበኛ ተማሪዎች ጋር በውድድር እንደሚመደቡ ዩኒቨርሲቲው ገልጿል፡፡
@tikvahuniversity
በቅዳሜ ጠዋት የልጆች የኮምፒውተር ኮዲንግ እና ግራፊክ ዲዛይን ስልጠና ምዝገባ ላይ ነን!
👉 ዕድሜያቸው ከ 8-18 ዓመት ለሆኑ ልጆች የሚሰጥ ስልጠና
👉 ልጆች ፕሮጀክቶች እየሠሩ የሚሰለጥኑበት
👉 ተግባርን ከንድፈ ሀሳብ ያስተሳሰረ ስልጠና
☎️ 0906777799 / 0906777755
አድራሻ፦ ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ እና ቁ.2 መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ
Telegram: /channel/sagetraininginstitute
TikTok: sage_training_institute" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@sage_training_institute
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute
ተስፋዬ ለማ (ዶ/ር) የወለጋ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ሆነው ተመድበዋል።
በትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) በቀን ህዳር 26/2017 ዓ.ም ተፈርሞ የወጣ ደብዳቤ፥ ተስፋዬ ለማ (ዶ/ር) ከህዳር 27/2017 ዓ.ም ጀምሮ የወለጋ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ሆነው መመደባቸውን ያሳያል።
ተስፋዬ ለማ (ዶ/ር) በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ መምህር እንዲሁም ከዚህ ቀደም የምርምር ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንት በመሆን አገልግለዋል።
ሃሰን ዩሱፍ (ዶ/ር) ላለፉት ዓመታት የወለጋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት እንደነበሩ አይዘነጋም።
@tikvahuniversity
በሁሉም የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የተማሪዎች የምግብ በጀት ተመን ላይ ማሻሻያ ተደረገ።
በዚህም "የተማሪዎች የምግብ በጀት ተመን በቀን በአንድ ተማሪ የነፍስ ወከፍ ወጪ ብር 100.00 (አንድ መቶ) ሆኖ ከታህሳስ 1 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ሥራ ላይ እንዲውል" መንግሥት ወስኗል።
ማሻሻያው በትምህርት ሚኒስቴር የቀረበን የምግብ በጀት ተመን ማሻሻያ ጥናት ከወቅቱ የገበያ ዋጋና ከመንግሥት የመክፈል አቅም አኳያ በማየት የተወሰነ መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ለትምህርት ሚኒስቴር በላከው ደብዳቤ ተገልጿል።
በሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች የተማሪዎች የምግብ አቅርቦት በወጥነት እንዲከናወንና ከምግብ በጀት ተመን ማሻሻያው ጋር የተጣጣመ ስታንዳርድ የምግብ ሜኑ በማዘጋጀት እንዲጠቀሙበትና በአግባቡ ስራ ላይ መዋሉን ትምህርት ሚኒስቴር ክትትል እንዲያደርግ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ኃላፊ ክና የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር አለምፀሐይ ጳውሎስ በቀን ህዳር 25/2017 ዓ.ም የተፈረመ ደብዳቤ ያሳያል።
ዩኒቨርሲቲዎች ከዚህ ቀደም በቀን አንድ ተማሪ ቁርስ፣ ምሳ እና እራት ለመመገብ በመንግሥት የሚመድብላቸው 22 ብር በጀት ብቻ እንደነበር ይታወሳል።
(የማሻሻያ ውሳኔው ለሁሉም የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች መነገሩን ቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ አረጋግጧል።)
@tikvahuniversity
#EthiopianAviationUniversity
የኢትዮጵያ አቪዬሽን ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የሙያ መስኮች ያሰለጠናቸውን 450 የአቪዬሽን ባለሙያዎች አስመረቀ፡፡
ዩኒቨርሲቲው ያሰለጠናቸውን 115 የአውሮፕላን አብራሪዎች፣ 84 የአውሮፕላን ቴክኒሺያኖች፣ 123 የበረራ መስተንግዶ ባለሙያዎች እና 128 የማርኬቲንግ ባለሙያዎች በዛሬው ዕለት አስመርቋል፡፡
ሰልጣኞቹ ከኢትዮጵያ እንዲሁም ከተለያዩ የአፍሪካ እና የኤሲያ ሀገራት የተውጣጡ መሆናቸው ተገልጿል።
@tikvahuniversity
የዓለም አቀፍ ግብይት (Import and Export Business) ስልጠና ፈላጊዎች ምዝገባ ላይ ነን።
🔔 ፈጥነው ይመዝገቡ!
👉 ተግባርን ከንድፈ ሀሳብ ያስተሳሰረ ስልጠና
👉 ሀገራዊ እና ዓለም አቀፋዊ አሰራሮች የሚተነተኑበት
👉 በዘርፉ ልምድ ባላቸው አሰልጣኞች የሚሰጥ
☎️ 0906777799 / 0906777755
አድራሻ፦ ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ እና ቁ.2 መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ
Telegram: /channel/sagetraininginstitute
TikTok: sage_training_institute" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@sage_training_institute
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ አዲስ ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ተመደበለት።
ትምህርት ሚኒስቴር እና የዩኒቨርሲቲው አስተዳደር ቦርድ በጻፉት ደብዳቤ፤ የዩኒቨርሲቲውን ፕሬዝዳንት ዳምጠው ዳርዛ (ዶ/ር) እና ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች ከኃላፊነት አንስተዋል።
በዚህም የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዳምጠው ዳርዛ (ዶ/ር)፣ የአካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዝዳንት ዓለማየሁ ጩፋሞ (ዶ/ር)፣ የምርምርና ትብብር ም/ፕሬዝዳንት በኃይሉ መርደኪዮስ እንዲሁም የአስተዳደርና ልማት ም/ፕሬዝዳንት ታሪኳ ወ/መድኅን ከአመራርነት መነሳታቸው ታውቋል።
በምትካቸውም አብደላ ከማል (ዶ/ር) ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት፣ ቦጋለ ገ/ማርያም (ዶ/ር) የአካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዝዳንት፣ ተክሉ ወጋየሁ (ዶ/ር) የምርምርና ትብብር ም/ፕሬዝዳንት እንዲሁም ፕ/ር ጳውሎስ ታደሰ የአስተዳደርና ልማት ም/ፕሬዝዳንት ሆነው ከታኅሣሥ 01/2017 ጀምሮ በውክልና እንዲሠሩ መመደባቸው ተገልጿል፡፡
የዩኒቨርሲቲው ነባር አመራሮች አዲስ ከተመደቡ አመራሮች ጋር በዛሬው ዕለት ውይይት አካሒደዋል፡፡
@tikvahuniversity