tikvahuniversity | Unsorted

Telegram-канал tikvahuniversity - Tikvah-University

308824

Subscribe to a channel

Tikvah-University

የፊታችን ቅዳሜ ታህሳስ 12/2017 ዓ.ም የኢንቴሪየር ዲዛይን (Interior Design) ስልጠና በመገናኛ ካምፓስ ይጀምራል። 

👉 Sketch-Up, Revit, Rhino, 3D Max እና Lumion ሶፍትዌሮችን በአንድ ላይ
👉 ከንድፈ ሀሳብ እና ሶፍትዌር ስልጠና በተጨማሪ በተግባር በወርክሾፕም  የሚሰጥ።

☎️   0906777799 / 0906777755

አድራሻ፦
ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ እና ቁ.2 መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ

Telegram: /channel/sagetraininginstitute
TikTok: sage_training_institute" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@sage_training_institute
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute

Читать полностью…

Tikvah-University

#ጥቆማ

በ2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በቀን መርሐግብር በሁለተኛ እና በሦስተኛ ዲግሪ እንዲሁም በማታ መርሐግብር በሁለተኛ ዲግሪ መማር የምትፈልጉ ተቋሙ ያስቀመጣቸውን መስፈርቶች በማሟላት እስከ ታህሳስ 11/ 2017 ዓ.ም ድረስ ማመልከት ትችላላችሁ፡፡ 

ታህሳስ 17 እና 18/2017 ዓ.ም የመግቢያ ፈተና እንደሚሰጥ ተገልጿል።

ከታህሳስ 23/2017 ዓ.ም እስከ ጥር 2/2017 ዓ.ም የመመዝገቢያ ጊዜ ነው የተባለ ሲሆን፤ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሬጅስትራር ቢሮ ቁ. 203 በአካል በመገኘት የትምህርት ማስረጃ ማስገባት ይጠበቅባችኋል ተብሏል፡፡

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

#ጥቆማ

የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ ሶሳይቲ ባዘጋጀው የ2025 #ነጻ የኢንተርንሺፕ ፕሮግራም ለመሳተፍ ይመዝገቡ!

የዩኒቨርሲቲ ተማሪ ወይም በቅርቡ የተመረቁና ለስፔስ ሳይንስ ልዩ ፍላጎት ካለዎት፥ የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ ሶሳይቲ ባዘጋጀው የሦስት ወራት #ነጻ የ Space Internship Program እንዲሳተፉ ተጋብዘዋል፡፡

የማመልከቻ ጊዜ የሚያበቃው 👇
እሑድ ታህሳስ 13/2017 ዓ.ም ለሊት 6፡00

ምላሽ ኢሜይል ታህሳስ 14/2017 ዓ.ም የሚላክ ሲሆን፤ ቃለ-መጠይቅ ከታህሳስ 16-18/2017 ዓ.ም ይደረጋል፡፡

ለማመልከት 👇
https://telegra.ph/Space-Internship-Programme-2025-12-16

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ በ2017 ዓ.ም ለሪሚዲያል ትምህርት የተመደቡ ተማሪዎችን በመቀበል ላይ ይገኛሉ፡፡

ዩኒቨርሲቲው በ2017 ዓ.ም 2,200 የሚጠጉ የሪሚዲያል ተማሪዎች የተመደቡለት ሲሆን፤ ታህሳስ 7 እና 8/2017 ዓ.ም የተማሪዎች ምዝገባ ለማከናወን ጥሪ ማስተላለፉ ይታወሳል፡፡

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

#ጥቆማ

አክሱም ዩኒቨርሲቲ የፈረንሳይኛ ቋንቋ ትምህርት ለመስጠት ምዝገባ ጀምሯል፡፡

ለበለጠ መረጃና ለመመዝገብ 👇
0929264591

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

የራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎች የምግብ ወጪ መጋራት በሦስት ዓይነት አሠራሮች እንደሚተገበር ተገለፀ፡፡

በመንግሥት ምደባ በራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲዎች የሚማሩ ተማሪዎች ዕለታዊ የምግብ አገልግሎት ተጠቃሚ ከሆኑ የወጪ መጋራት ግዴታ እንደሚመለከታቸው በትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ የአስተዳደር ጉዳዮች ኃላፊ አብዱ ናስር ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡

በራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲዎች ሦስት ዓይነት ተማሪዎች እንደሚገኙ የገለፁት ኃላፊው፤ ሙሉ ለሙሉ ክፍያቸውን የሚችሉ፣ ዩኒቨርሲቲው ወጪያቸውን የሚሸፍንላቸው እና የወጪ መጋራት የሚመለከታቸው መሆናቸውን ጠቁመዋል፡፡

የተማሪዎች ዝቅተኛው የትምህርት ቆይታ ጊዜ አራት ዓመት ሲሆን፣ በዚህ ጊዜ ውስጥ የአንድ ተማሪ የምግብ ወጪ መጋራት ሲሰላ 120,000 ብር እንደሚሆንና የሰባት ዓመት ቆይታ ያለው የሕክምና ትምህርት ደግሞ 210,000 ብር እንደሆነ ገልፀዋል፡፡

የተማሪዎች የምግብ ወጪ መጋራት ተመን በየትምህርት ዘርፍ የዋጋ ልዩነት ያለው ሲሆን፤ ይህም በተማሪዎች የትምህርት ፕሮግራም ቆይታ ስሌት መሠረት እንደሚሆን ኃላፊው አስረድተዋል፡፡

ራስ ገዙ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ዘንድሮ 5,000 ተማሪዎች የተቀበለ ሲሆን፤ 2,500 በራሳቸው ከፍለው የሚማሩና ወጪ መጋራቱ የማይመለከታቸው ናቸው፡፡ የተቀሩት 2,500 ተማሪዎች ደግሞ መደበኛው የመንግሥት ወጪ መጋራት የማይከመለታቸው ሲሆኑ፤ ከእነዚህ ውስጥ ዩኒቨርሲቲው ወጪያቸውን የሚሸፍንላቸው እንዳሉ አስረድተዋል፡፡

የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ዕለታዊ የምግብ ወጪ ተመን ከታህሳስ 1/2017 ዓ.ም ጀምሮ 100 ብር እንዲሆን ተወስኗል። ትምህርት ሚኒስቴር ወጥ የሆነ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የምግብ ሜኑ በማዘጋጀት ለሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች መላኩም ይታወቃል፡፡ #ሪፖርተር

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

#AAU

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በቀን እና ማታ መርሐግብር የመልሶ ቅበላ (Re-admission) አመልካቾች ለ2017 ሁለተኛ ሴሚስተር የመልሶ ቅበላ መጠየቂያ ጊዜ የመጀመሪያ ዙር ከታህሳስ 7-11 2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

የሁለተኛው ዙር የመልሶ ቅበላ መጠየቂያ ጊዜ ከታህሳስ 14-18/2017 ዓ.ም መሆኑ ተመላክቷል።

የመልሶ ቅበላ መጠየቂያ ቅፅ ለመሙላት፦

➫ portalaau.edu.et ላይ መለያ ቁጥር (User name) እና ሚስጢር ቁጥር (Password) በመጠቀም Withdrawal ለመሙላት Registration > Withdrawal Request ይሙሉ።

➫ መለያ ቁጥር እና ሚስጢር ቁጥር በመጠቀም Readmission ለመሙላት Registration > Re-admission Request ይሙሉ።

የመልሶ ቅበላ ቅፅ መሙላት የሚቻለው ከላይ የተጠቀሱትን የኦንላይን ፎርም ሲሞሉ ብቻ ሲሆን፤ ለሁለተኛ እና ለሦስተኛ ዲግሪ የመልሶ ቅበላ ቅፅ ለመሙላት ሲሔዱ ስፖንሰር ከሚያደርግዎት ተቋም በቅርብ የተፃፈ የድጋፍ ደብዳቤ ማያያዝ ያስፈልጋል፡፡

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ በ2017 ዓ.ም ወደተቋሙ ለተመደቡ የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች ጥሪ አላደረገም።

በተለያዩ የማኅበራዊ ሚዲያ ገጾች እየተዘዋወረ የሚገኘው ዩኒቨርሲቲው ጥሪ እንዳደረገ የሚገልፅ የጥሪ መልዕክት ስህተት መሆኑን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

የ2017 ዓ.ም የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ወደፊት ይገለፃል ተብሏል፡፡

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

በሦስቱም ቅርንጫፎቻችን ( መገናኛ፣ ሜክሲኮ እና ጀሞ) እና በኦንላይን በምንሰጣቸው ስልጠናዎች በ Advanced Level እና 90% Practical በሆነ ካሪኩለምና ዘመኑ ያፈራቸውን የስቱዲዮ እቃዎች በማሟላት ከሁሉም ስልጠናዎቻችን ላይ ታላቅ የዋጋ ቅናሽ አድርገናል! አሁኑኑ ይመዝገቡና ትልቅ ለውጥ ወደሚያመጡበት ተቋም ይቀላቀሉ!

ከትምህርትና ስልጠና ጥራትና ቁጥጥር ባለስልጣን ሙሉ ዕውቅና ካለው ሰርተፊኬት ጋር! የብዙ ዓመት ልምድ እና ብቃት ባላቸው አሰልጣኞች!

🎯 Graphics Design
🎯 Video Editing
🎯 Digital Marketing
🎯 Photography
🎯 Videography
🎯 Cinematography
🎯 Adobe Photoshop
🎯 Full-stack Web App Development
🎯 Programming Language
🎯 Interior Design
🎯 English Language
🎯 Database
🎯 Basic Computer
🎯 Accounting Softwares
🎯 Engineering Softwares
🎯 SPSS & STATA
🎯 MS-Project
🎯  Foreign & Local Languages

አድራሻ፦
1. መገናኛ መተባበር ህንፃ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁ. 419 (ሊፍት ይጠቀሙ)  ☎️ 0991929303
2. ሜክሲኮ ኬኬር ህንፃ 6ኛ ፎቅ ቢሮ ቁ. 639 (ሊፍት ይጠቀሙ ሁለተኛውን ሊፍት) ☎️ 0991929304
3. ጀሞ 1 አንደኛ በር ካኩ ቢዝነስ ሴንተር 3ኛ ፎቅ ☎️ 0991926707

Telegram: /channel/topinstitutes

Читать полностью…

Tikvah-University

የድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በ2017 ዓ.ም የሚሰጠውን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ መልቀቂያ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎች ምዝገባ በኦንላይን እንደሚከናወን ገለፀ፡፡

ዘንድሮ የ12ኛ ክፍል ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎች የኦንላይን ምዝገባ በአስተዳደሩ ስር በሚገኙ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ተግባራዊ እንደሚደረግ በቢሮው የትምህርት ምዘናና ፈተና ማስተባበሪያ ገልጿል።

የተፈታኝ ተማሪዎች ምዝገባ ከታህሳስ 7-30/2017 ዓ.ም ይከናወናል ተብሏል፡፡

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

#BahirDarUniversity

የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በ Health Genomics የማስተርስ ፕሮግራም አስጀመረ፡፡

በ Health Genomics የማኅበረሰብ ጤና ማስተርስ ፕሮግራም በኢትዮጵያ ሲከፈት ለመጀመሪያ ጊዜ መሆኑ ተገልጿል፡፡

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

#WachemoUniversity

በ2017 ዓ.ም ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ መደበኛ የሪሚዲያል ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ታህሳስ 21 እና 22/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

በቅጣት ምዝገባ ታህሳስ 23/2017 ዓ.ም የሚከናወን ሲሆን፤ ትምህርት ታህሳስ 23/2017 ዓ.ም ይጀምራል ተብሏል።

በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ በግል የሪሚዲያል ትምህርት ለመማር የተመዘገባችሁ ተማሪዎች ትምህርት ታህሳስ 25/2017 ዓ.ም እንደሚጀምር ተገልጿል።

ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

➫ የ8ኛ ክፍል ካርድ ዋናውና አንድ ኮፒ፣
➫ ከ9ኛ-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት፣
➫ ስምንት 3×4 ጉርድ ፎቶግራፍ፣
➫ ትራስ ጨርቅ፣ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ።

የካምፓስ ምደባ፦

► የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ስማችሁ ከ A-G የሚጀምር በዱራሜ ካምፓስ፥ ዱራሜ
► የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ስማችሁ ከ H-Z የሚጀምር በዋናው ግቢ፥ ሆሳዕና
► የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ስማችሁ ከ A-J የሚጀምር በዱራሜ ካምፓስ፥ ዱራሜ
► የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ስማችሁ ከ K-Z የሚጀምር በዋናው ግቢ፥ ሆሳዕና

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

#JinkaUniversity

ጂንካ ዩኒቨርሲቲ ለ2017 ዓ.ም ሪሚዲያል ተማሪዎች ጥሪ አላደረገም።

"ዩኒቨርሲቲው ለ2017 ዓ.ም ሪሚዲያል ተማሪዎች ለታህሳስ 11 እና 12/2017 ዓ.ም እንደጠራ" ተደርጎ በማኅበራዊ ሚዲያ የተሰራጨው መረጃ ሐሰት መሆኑን ተቋሙ ገልጿል።

ለጊዜው ምንም አይነት ጥሪ አለመተተላለፉን አውቃችሁ፣ በይፋ ጥሪ እስከሚደረግ ድረስ ተማሪዎች በትዕግስት እንዲጠብቁ ዩኒቨርሲቲው ጠይቋል።

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

#MoE

ትምህርት ሚኒስቴር ከተሻሻለው የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ዕለታዊ የምግብ ተመን ጋር የተጣጣመ ስታንዳርድ የምግብ ሜኑ አዘጋጀ፡፡

የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ዕለታዊ የምግብ ወጪ ከታህሳስ 1/2017 ዓ.ም ጀምሮ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) እንዲሆን መወሰኑ ይታወቃል። በዚህም የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የምግብ ሜኑ በሁሉም ተቋማት ወጥነት እንዲኖረው እየተሠራ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር መግለጹ አይዘነጋም።

ሚኒስቴሩ ከተሻሻለው የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ዕለታዊ የምግብ ተመን ጋር የተጣጣመ ስታንዳርድ የምግብ ሜኑ በማዘጋጀት ለሁሉም የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ልኳል።

የምግብ ሜኑው ዝቅተኛውን መስፈርት መሠረት በማድረግ የተዘጋጀ ሲሆን፤ ተቋማት ከባቢያዊ ነባራዊ ሁኔታን ከግምት ውስጥ በማስገባት በአንድ ተማሪ ሳምንታዊ ወጪ ከብር 700.00 (ሰባት መቶ ብር) ባልበለጠ መልኩ ሥራ ላይ መዋል ያለበት መሆኑን ሚኒስቴሩ ገልጿል፡፡

ዕለታዊ ወጪው ብር 100.00 (አንድ መቶ) ሆኖ፣ የሁሉም ተቋማት የቁርስ፣ የምሳ እና የእራት የምግብ ሜኑ በዝርዝር ተቀምጧል፡፡ (ሙሉ የሜኑው ዝርዝር ከላይ ተያይዟል፡፡)

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

#አቢሲንያ_ባንክ

ይሸለሙ!
ቀጣይ ዙር የጥያቄ እና መልስ ውድድር ቅዳሜ ታህሳስ 5 ከረፋዱ 4:30 በፌስቡክ ፔጃችን ላይ ይደረጋል። በየሳምንቱ አስር አሸናፊዎች ይሸለማሉ! ዛሬውኑ የፌስቡክ ፔጃችን በመቀላቀልና ቀላል ጥያቄዎችን በመመለስ ይሸለሙ!

የፌስቡክ ሊንክ 👇
https://www.facebook.com/BoAeth

አቢሲንያ የሁሉም ምርጫ!
#Facebook #giveaway #contest #Boa #bankinginethiopia #banksinethiopia #bankofabyssinia #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ

Читать полностью…

Tikvah-University

#UniversityOfGondar

በ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ የማጠቃለያ ፈተና ወስዳችሁ ለሪሚዲያል ፕሮግራም ጎንደር ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች ሪፖርት ማድረጊያ ቀናት ጥር 1 እና 2/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

የምዝገበ ቦታ፡-
- የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ማራኪ ግቢ፣
- የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች አጼ ፋሲል ግቢ።

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

የምስራች! 🥳

💫 አስተማማኙን 4G ኔትወርካችንን ወደ ጎዴ ይዘን ገብተናል!

ጥንታዊ የንግድ ማዕከል የነበረችውና የኡጋስ ሚራድ አየር ማረፊያ ባለቤት የሆነችውን ጎዴ እናንተስ በምን ታስታውሷታላችሁ?

አሁንም ፈጣኑን ኔትወርክ ማዳረሳችንን እንቀጥላለን! 🙌🏼 አስተማማኙን ኔትወርክ ዛሬውኑ እንቀላቀል!

የቴሌግራም ቦታችንን /channel/official_safaricomet_bot በመጠቀም የአየር ሰዓት ወይም ልዩ ልዩ ጥቅሎችን እንግዛ!

#MPESASafaricom #SafaricomEthiopia #1Wedefit
#Furtheraheadtogether

Читать полностью…

Tikvah-University

የፊታችን ቅዳሜ ታህሳስ 12/2017 ዓ.ም 4ኛ እና 5ኛ ዙር የጋዜጠኝነት ስልጠና በፒያሣ እና በመገናኛ ካምፓስ ይጀምራል።

👉 መሠረታዊ የጋዜጠኝነት መርሆች
👉 የመዝናኛ ፕሮግራም ጋዜጠኝነት፣ የፕሮግራም ዝግጅት እና የዶክመንተሪ ዝግጅት
👉 የሞባይል ጋዜጠኝነት እና YouTube Journalism አካቷል
👉 የሥራ ላይ ስልጠና (Internship) አካቷል፡፡

ስልጠናው ለስድስት ወር የሚቆይ ሲሆን፤ በቅዳሜና እሑድ መርሐግብር ይሰጣል።

☎️ 0906777799 / 0906777755
አድራሻ፦
ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ እና ቁ.2 መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ

Telegram: /channel/sagetraininginstitute
TikTok: sage_training_institute" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@sage_training_institute
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute

Читать полностью…

Tikvah-University

በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ ሀገር አቀፍ ፈተና ወስደው የሪሚዲያል ትምህርት ለመከታተል ኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ የተመደቡ ተማሪዎች ወደ ተቋሙ መግባት ጀምረዋል፡፡

ተማሪዎቹ እስከ ነገ ታህሳስ 8/2017 ዓ.ም ወደ ዩኒቨርሲቲው መግባት እንደሚቀጥሉ ተገልጿል፡፡

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

በሦስቱም ቅርንጫፎቻችን ( መገናኛ፣ ሜክሲኮ እና ጀሞ) እና በኦንላይን በምንሰጣቸው ስልጠናዎች በ Advanced Level እና 90% Practical በሆነ ካሪኩለምና ዘመኑ ያፈራቸውን የስቱዲዮ እቃዎች በማሟላት ከሁሉም ስልጠናዎቻችን ላይ ታላቅ የዋጋ ቅናሽ አድርገናል! አሁኑኑ ይመዝገቡና ትልቅ ለውጥ ወደሚያመጡበት ተቋም ይቀላቀሉ!

ከትምህርትና ስልጠና ጥራትና ቁጥጥር ባለስልጣን ሙሉ ዕውቅና ካለው ሰርተፊኬት ጋር! የብዙ ዓመት ልምድ እና ብቃት ባላቸው አሰልጣኞች!

🎯 Graphics Design
🎯 Video Editing
🎯 Digital Marketing
🎯 Photography
🎯 Videography
🎯 Cinematography
🎯 Adobe Photoshop
🎯 Full-stack Web App Development
🎯 Programming Language
🎯 Interior Design
🎯 English Language
🎯 Database
🎯 Basic Computer
🎯 Accounting Softwares
🎯 Engineering Softwares
🎯 SPSS & STATA
🎯 MS-Project
🎯  Foreign & Local Languages

አድራሻ፦
1. መገናኛ መተባበር ህንፃ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁ. 419 (ሊፍት ይጠቀሙ)  ☎️ 0991929303
2. ሜክሲኮ ኬኬር ህንፃ 6ኛ ፎቅ ቢሮ ቁ. 639 (ሊፍት ይጠቀሙ ሁለተኛውን ሊፍት) ☎️ 0991929304
3. ጀሞ 1 አንደኛ በር ካኩ ቢዝነስ ሴንተር 3ኛ ፎቅ ☎️ 0991926707

Telegram: /channel/topinstitutes

Читать полностью…

Tikvah-University

የፊታችን ቅዳሜ ታህሳስ 12/2017 ዓ.ም 6ኛ ዙር Advanced Standards and Practices of Accounting ስልጠና በመገናኛ ካምፓስ ይጀምራል።

👉 IFRS + Peachtree + Asset Valuation + IFRS Conversion + IPSAS + Quick Book በአንድ ላይ
👉 ስልጠናው ሙሉ በሙሉ በተግባር የተደገፈና ፒስትሪ (Peachtree Software) ላይ የሚሰጥ ነው።

☎️ 0906777799 / 0906777755
አድራሻ፦
ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ እና ቁ.2 መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ

Telegram: /channel/sagetraininginstitute
TikTok: sage_training_institute" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@sage_training_institute
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute

Читать полностью…

Tikvah-University

#BahirDarUniversity

በ2017 ዓ.ም ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ የአቅም ማሻሻያ (Remedial Program) ተማሪዎች ምዝገባ ከጥር 5-7/2017 ዓ.ም በዩኒቨርሲቲው ግሽ አባይ ግቢ እንደሚከናወን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

➫ የ8ኛ እና 12ኛ ክፍል ካርድ ዋናውና ኮፒው፣
➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
➫ አራት 3x4 ጉርድ ፎቶግራፍ፣
➫ ብርድ ልብስ፣ አንሶላ፣ ትራስ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ።

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

#HaramayaUniversity

በ2017 ዓ.ም በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርታችሁን እንድትከታተሉ የተመደባችሁ ተማሪዎች ሪፖርት ማድረጊያ ቀናት ከጥር 2-4/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

የምዝገባ ቦታ፦
የኅብረተሰብ ሳይንስ ተማሪዎች በቬተርነሪ ካምፓስ፤ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች በቴክኖሎጂ ካምፓስ።

ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

➫ የ8ኛ ክፍል ካርድ፣
➫ ከ9ኛ-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት፣
➫ የ12ኛ ክፍል ሰርተፍኬት ዋናውና ኮፒው፣
➫ አራት ፓስፖርት መጠን ፎቶግራፍ፣
➫ ብርድ ልብስ፣ እንሶላ እና ትራስ ልብስ

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2017 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ መልቀቂያ ፈተና የተፈታኞች የኦንላይን ምዝገባ የፊታችን ሰኞ ይጀምራል፡፡

በከተማ አስተዳደሩ የ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች የኦንላይን ምዝገባ ከታህሳስ 7 እስከ ጥር 6/2017 ዓ.ም እንደሚካሔድ የአስተዳደሩ ትምህርት ቢሮ ገልጿል፡፡

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

በአማራ ክልል የ2017 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የተፈታኞች ምዝገባ የፊታችን ሰኞ ይጀምራል፡፡

በክልሉ የ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች ምዝገባ ከታህሳስ 7/2017 ዓ.ም ጀምሮ እንደሚካሔድ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ገልጿል፡፡

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

የጋዜጠኝነት ስልጠና ቅዳሜ ታህሳስ 12/2017 ዓ.ም ይጀምራል!

👉 መሠረታዊ የጋዜጠኝነት መርሖች
👉 የመዝናኛ ፕሮግራም ጋዜጠኝነት፣ የፕሮግራም ዝግጅት እና የዶክመንተሪ ዝግጅት
👉 የሞባይል ጋዜጠኝነት እና YouTube Journalism አካቷል
👉 የሥራ ላይ ስልጠና (Internship) አካቷል፡፡

ስልጠናው ለስድስት ወር የሚቆይ ሲሆን፤ በቅዳሜና እሑድ መርሐግብር ይሰጣል።

☎️ 0906777799 / 0906777755
አድራሻ፦
ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ እና ቁ.2 መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ

Telegram: /channel/sagetraininginstitute
TikTok: sage_training_institute" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@sage_training_institute
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute

Читать полностью…

Tikvah-University

በ M-PESA በነፃ ገንዘባችንን እንላክ!

ለወዳጅ ስጦታ ለመላክ ወይም ለገንዘብ ልውውጥ ወደ የትኛውም የሳፋሪኮም ቁጥር በነፃ ብር እንላክ! ያለተጨማሪ ወጪ በነፃው አገልግሎት ዘና እንበል !

የ M-PESA ሳፋሪኮም መተግበሪያን በዚህ ሊንክ እናውርድ፦ https://play.google.com/store/apps/details?id=et.safaricom.mpesa.lifestyle

የቴሌግራም ቻናላችንን እዚህ እንቀላቀል 👉 /channel/Safaricom_Ethiopia_PLC

ስለ አገልግሎታችን ማንኛውንም ጥያቄ ወይም መረጃ በቴሌግራም ቻናላችን /channel/Safaricom_Ethiopia_PLC 24/7 ማግኘት ይቻላል!

#MPESASafaricom #FurtherAheadTogether

Читать полностью…

Tikvah-University

የመቱ ዩኒቨርሲቲ የቀድሞው ፕሬዝዳንት ሚኒስትር ዴኤታ ሆነው ተሹመዋል፡፡

መቱ ዩኒቨርሲቲን ለአምስት ዓመታት በፕሬዝዳንትነት ሲያገለግሉ የቆዩት እንደገና አበበ (ዶ/ር) የፌደራል ሹመት ተሰጥቷቸዋል፡፡

እስከ ጥር 2016 ዓ.ም ድረስ የመቱ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት የነበሩት እንደገና አበበ (ዶ/ር) በቱሪዝም ሚኒስቴር የፕሮሞሽን እና ግብይት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ሆነው መሾማቸው ተሰምቷል፡፡

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

በቅዳሜ ጠዋት የልጆች የኮምፒውተር ኮዲንግ እና ፕሮግራሚንግ ስልጠና ነገ ቅዳሜ ታህሳስ 5/2017 ዓ.ም ይጀምራል!

👉 ስልጠናው ዕድሜያቸው ከ 8-18 ዓመት ለሆኑ ልጆች የሚሰጥ
👉 ልጆች ፕሮጀክቶች እየሰሩ የሚሰለጥኑበት
👉 ተግባርን ከንድፈ ሀሳብ ያስተሳሰረ ስልጠና

☎️ 0906777799 / 0906777755
አድራሻ፦
ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ እና ቁ.2 መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ

Telegram: /channel/sagetraininginstitute
TikTok: sage_training_institute" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@sage_training_institute
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute

Читать полностью…

Tikvah-University

#MoE

ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ዕድገት እንዳይሰጡ በድጋሜ እገዳ ተጣለባቸው፡፡

ከታህሳስ 1 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ በየትኛውም የከፍተኛ ትምህርት ተቋም የተሰጠ እና የሚሰጥ የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ዕድገት ተቀባይነት እንደማይኖረው ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል፡፡

ከጥቅምት 4/2013 ዓ.ም ጀምሮ በሥራ ላይ የነበረውንና በትግበራ ወቅት ክፍተት የታየበት "የአካዳሚክ ሠራተኞች የደረጃ ዕድገት መመሪያ" በመሻሻል ላይ እንደሚገኝ ሚኒስቴሩ አስታውሷል፡፡

በዚህም ማሻሻያው ተጠናቆ ለሁሉም ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እስከሚላክ ድረስ በሁሉም ተቋማት የፕሮፌሰርነት ዕድገት አሰጣጥ ለጊዜው መታገዱን ሚኒስቴሩ ሐምሌ 24 ቀን 2016 ዓ.ም ለተቋማቱ በጻፈው ደብዳቤ ገልጾ ነበር፡፡

ይሁን እንጂ "አንዳንድ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ክልከላውን በመጣስ፣ መመሪያውን ባልተከተለ፣ ግልጽነት በጎደለው፣ ወጥነት በሌለው እና ከትምህርት ጥራት ማስጠበቂያ ሪፎርሞች ጋር በሚጣረስ መልኩ የፕሮፌሰርነት ዕድገት መስጠት መቀጠላቸውን ለመረዳት ችለናል" ብሏል በትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) በቀን ታህሳስ 1/2017 ዓ.ም ተፈርሞ ለተቋማቱ የተላከ ደብዳቤ።

ከታህሳስ 1 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ በየትኛውም የከፍተኛ ትምህርት ተቋም የተሰጠ እና የሚሰጥ የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ዕድገት ተቀባይነት እንደማይኖረው የገለፀው ትምህርት ሚኒስቴር፤ የተቋማቱ ከፍተኛ አመራር አካላት እና የሥራ አመራር ቦርድ የተሻሻለው መመሪያ ተጠናቅቆ እስኪደርሳችሁ ድረስ በትዕግስት እንዲጠብቁ ጠይቋል፡፡

@tikvahuniversity

Читать полностью…
Subscribe to a channel