tikvahuniversity | Unsorted

Telegram-канал tikvahuniversity - Tikvah-University

308824

Subscribe to a channel

Tikvah-University

#ራስ_ገዝ_ዩኒቨርሲቲ

የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ራስ ገዝ አስተዳደር ስትራቴጂክ ዕቅድ እና የሴኔት ሕግ ለማዳበር የተዘጋጀ አውደ ጥናት በአዲስ አበባ በመካሄድ ላይ ነው።

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያው ራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲ መሆኑ ይታወቃል።

በቀጣይ ራስ ገዝ ለመሆን ዝግጅት እያደደረጉ ያሉ ዘጠኝ ዩኒቨርሲቲዎች፦

➫ መቐለ ዩኒቨርሲቲ፣
➫ ጎንደር ዩኒቨርሲቲ፣
➫ ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ፣
➫ አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ፣
➫ አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ፣
➫ ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ፣
➫ ጅማ ዩኒቨርሲቲ፣
➫ ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ እና
➫ አርባ ምንጭ ዩኒቨርስቲ።

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

2ኛ ዙር የኮምፒውተር ጥገና እና ኔትዎርኪንግ (Computer Maintenance and Networking) ስልጠና በፒያሣ እና በመገናኛ ካምፓስ ምዝገባ ላይ ነን።

👉 ንድፈ ሀሳብን ከተግባር ጋር በማዛመድ የሚሰጥ ስልጠና
👉 የሥራ ላይ ስልጠና (Internship) የተመቻቸለት

☎️    0906777799 / 0906777755
አድራሻ

ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ
ቁ.2: መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ

Telegram: /channel/sagetraininginstitute
TikTok: sage_training_institute" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@sage_training_institute
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute

Читать полностью…

Tikvah-University

2ኛ ዙር መሰረታዊ የኮምፒውተር (Basic Computer) ስልጠና በፒያሣ እና በመገናኛ ካምፓስ ምዝገባ ላይ ነን!

👉 Microsoft Word, Excel, Access, PowerPoint, Publisher እና ሌሎች የኮምፒውተር አጠቃቀሞችን አካቶ የሚሰጥ ስልጠና
👉 ለሁለት ወር የሚቆይ ስልጠና

☎️ 0906777799 / 0906777755

አድራሻ

ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ
ቁ.2: መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ

Telegram: /channel/sagetraininginstitute
TikTok: sage_training_institute" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@sage_training_institute
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute

Читать полностью…

Tikvah-University

በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የዳውሮ ታርጫ ካምፓስ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 242 ተማሪዎች አስመርቋል።

በ2007 ዓ.ም የተቋቋመው ካምፓሱ፤ 10ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን በዛሬው ዕለት አክብሯል።

ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ከ2,500 በላይ ተማሪዎችን ትናንት ማስመረቁ ይታወቃል።

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ 74 የህክምና ዶክተሮች እና 129 የቅድመ-ምረቃ የጤና ሳይንስ ተማሪዎችን ዛሬ አስመርቋል፡፡

ዩኒቨርሲቲው 11 የሦስተኛ ዲግሪ እና 252 የማስተርስ ዲግሪ ተመራቂዎችን ጨምሮ በተለያዩ የቅድመ-ምረቃ ፕሮግራሞች በድምሩ 1,028 ተማሪዎችን በዛሬው ዕለት አስመርቋል፡፡

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

አምቦ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያስተማራቸውን 807 ተማሪዎች አስመርቋል።

ከተመራቂዎቹ 2 በሦስተኛ ዲግሪ፣ 192 በሁለተኛ ዲግሪ፣ ሰባት በህክምና ዶክትሬት እንዲሁም 606 በመጀመሪያ ዲግሪ ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ ናቸው።

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ 214 የህክምና ተማሪዎችን አስመርቋል።

ተመራቂዎቹ በሰባት የጤና መስኮች በመጀመሪያ ዲግሪ ፕሮግራም ስልጠናቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ ባለሙያዎች ናቸው።

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 1,240 ተማሪዎችን አስመርቋል።

ተመራቂዎቹ በመደበኛ እና በተከታታይ የትምህርት መርሐግብር ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ ናቸው።

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

We are back for the 3rd year of EdTech Mondays Ethiopia!
Join us on Monday, 24th February 2025, at 8:10 PM EAT on Fana FM 98.1 as we explore “The Role of AI in Upskilling Teachers and Enhancing EdTech Adoption.”

Featuring panelists Tewelde Zemichael (EdTech and Fintech Researcher, CEO and Founder of Geez Education and Training PLC), Milkias Tesfaye (EdTech Program Lead at Edify Ethiopia), and Elias Gudeta (ICT Specialist and Assistance Manager at Destiny), moderated by Rediet Meshesha (Host of Cybergna), this edition.

Don’t miss this critical conversation on advancing education in Ethiopia!

Читать полностью…

Tikvah-University

#MoH
#ERMP_2024_Matching

የ2024 የብሔራዊ የህክምና ስፔሻሊቲ ስልጠና (ERMP) አመልካቾች ምደባ (Matching) ተለቋል።

የማቺንግ ውጤቱ በጤና ሚኒስቴር የቴሌግራም ገፅ /channel/M0H_EThiopia ላይ ይፋ ተደርጓል።

በምደባው ላይ ቅሬታ ያላችሁ ተፈታኞች በሚኒስቴሩ ነጻ የስልክ መስመር 952 በሥራ ሰዓት ብቻ እስከ የካቲት 21/2017 ዓ.ም ማቅረብ ይቻላል።

የተቋም/የፕሮግራም/የስፖንሰር ለውጥ አድርጉልኝ ጥያቄ እንደ ቅሬታዎች የማይወሰዱ በመሆናቸው ተቀባይነት የላቸውም ተብሏል።

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

ዲላ ዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን በመደበኛ፣ በቅዳሜና እሑድ እንዲሁም በክረምት መርሐግብር ሲከታተሉ የቆዩና ለመመረቅ የሚያስፈልጉ ቅድመ ሁኔታዎችን ያሟሉ 518 ተማሪዎች የምረቃ ስነ-ስርዓት ነገ የካቲት 15/2017 ዓ.ም ያከናውናል፡፡

በተመሳሳይ የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ 19ኛ ዙር የተማሪዎች የምረቃ ስነ-ስርዓት በነገው ዕለት ያካሒዳል፡፡

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

"የ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ሁሉም ተማሪዎች በተማሩበት ስርዓተ ትምህርት ይዘት ይዘጋጃል፡፡" - የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት

የ2017 ዓ.ም ተፈታኝ ተማሪዎች ከ9ኛ-10ኛ በነባሩ ስርዓተ ትምህርት፣ ከ11ኛ-12ኛ በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት እንዲሁም ለስርዓተ ትምህርት የሙከራ ትግበራ በናሙናነት ተመርጠው የተሳተፉ ትምህርት ቤቶች ላይ የነበሩ ተማሪዎች 10ኛ ከፍልን በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት የተማሩ መሆናቸውን አገልግሎቱ ገልጿል፡፡

በአማራ ክልል በፀጥታ ችግር ምክንያት በ2016 ዓ.ም ሳይፈተኑ የቀሩና የ11ኛ ክፍልን በነባሩ ስርዓተ ትምህርት የተማሩ ትምህርት ቤቶች ላይ የነበሩ ተማሪዎች በ2017 ዓ.ም የሚፈተኑም አሉ፡፡

በመሆኑም የ2017 ዓ.ም የሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና "ከላይ የተገለፁትን ነባራዊ ሁኔታዎች ከግምት ውስጥ ባስገባና ሁሉንም ተፈታኝ ተማሪዎች በማከለ መንገድ ስታንዳርዱን፣ ደህንነቱንና ሚስጢራዊነቱን ጠብቆ በመዘጋጀት ላይ ይገኛል" ብሏል አገልግሎቱ።

የፈተና ዝግጅቱ ምን ያካትታል?

➫ ከ9ኛ ከፍል ሙሉ በሙሉ ከነባሩ ስርዓተ ትምህርት፣
➫ ከ10ኛ ክፍል በነባሩ እና በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት ተመሳሳይ ይዘቶች፣
➫ ከ11ኛ ከፍል በነባሩ እና በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት ተመሳሳይ ይዘቶች፣
➫ ከ12ኛ ከፍል ሙሉ በሙሉ በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት መሰረት የሚዘጋጅ ይሆናል።

የኢኮኖሚክስ የትምህርት ዓይነት በስርዓተ ትምህርቱ አዲስ የተጀመረ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በ12ኛ ክፍል ይዘት ላይ ብቻ ተመስርቶ ይዘጋጃል ተብሏል።

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

"በ2017 ዓ.ም 150 ሺህ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎችን በበይነ መረብ ለመፈተን ዝግጅት እየተደረገ ነው።" - ትምህርት ሚኒስቴር

ትምህርት ሚኒስቴር የአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ የምክክር መድረክ በማካሔድ ላይ ይገኛል።

በመድረኩ ላይ ንግግር ያደረጉት የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) "በዚህ ዓመት 150 ሺህ የሚደርሱ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ፈተናቸውን በበይነ መረብ እንዲወስዱ ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ ይገኛል" ብለዋል።

በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በወረቀት እና በኦንላይን ድብልቅ በሆነ መልኩ ለመጀመሪያ ጊዜ የተሰጠ ሲሆን፤ 30 ሺህ የሚጠጉ ተማሪዎች ፈተናቸውን በኦንላይን መውሰዳቸው ይታወሳል።

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

💨⚡️ ለብዙ ሰዓት ከምትወዱት/ከምትወዷት ጋር እንድታወሩ የሚያስችላችሁን 3000 mah የባትሪ አቅም ያለውና አዳዲስ የቴክኖሎጂ ትሩፋቶችን ይዞ በአንዴ እስከ 8 ሰው ድረስ የሚያስጠቅመውን ልዩ ቅመም MIFIን ገዝተን ፈጣን 4G ኢንተርኔት እንጠቀም! ለ30 ቀን ከሚቆይ ነጻ 30ጊባ ዳታ ጉርሻ ጋር 😋

ከሳፋሪኮም ጋር አንድ ወደፊት ⚡️

🔗 የ M-PESA ሳፋሪኮም መተግበሪያን በዚህ ሊንክ እናውርድ፦ https://play.google.com/store/apps/details?id=et.safaricom.mpesa.lifestyle

#SafaricomEthiopia

Читать полностью…

Tikvah-University

#ጥቆማ

የወለጋ ዩኒቨርሲቲ ሪፌራል ሆስፒታል በተለያዩ ክፍት የሥራ መደቦች ላይ አመልካቾችን አወዳድሮ ለመቅጠር ይፈልጋል።

የምዝገባ ጊዜ፦
እስከ ሰኞ የካቲት 17/2017 ዓ.ም

የምዝገባ ቦታ፡-
ወለጋ ዩኒቨርሲቲ ሪፌራል ሆስፒታል የሰው ሀብት አስተዳደርና ልማት የሥራ ሂደት ቢሮ ቁ. 85

➫ አመልካቾች የምታቀርቡት የሥራ ልምድ ከሥራ መደቡ ጋር ቀጥታ ግንኙነት ያለው መሆን እንዲሁም ደመወዝና ከመቼ እስከ መቼ እንዳገለገሉ የሚገልጽ መሆን አለበት።

➫ አመልካቾች የትምህርት ማስረጃችሁን ዋናውና የማይመለስ አንድ ኮፒ ማቅረብ ይጠበቅባችኋል፡፡

➫ አመልካቾች የምታቀርቡት የሥራ ልምድ ማስረጃ የመንግሥታዊ መስሪያ ቤት ካልሆነ የገቢ ግብር መክፈላችሁን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባችኋል፡፡

➫ ዜሮ ዓመት ለሚጠይቁ የሥራ መደቦች የምትወዳደሩ አመልካቾች የሥራ-አጥ ካርድ ማቅረብ ይጠበቅባችኋል።

አስፈላጊውን መስፈርት የምታሟሉ አመልካቾች መወዳደር ትችላላችሁ የተባለ ሲሆን፤ የፈተና ቀን በውስጥ ማስታወቂያ ይገለጻል ተብሏል።

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

#ጥቆማ

5 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ኮደርስ ኢንሼቲቭ ነፃ ስልጠናን ለመከታተል ይመዝገቡ።

ዓለም አቀፍ ተቀባይነት ያለው ሰርትፍኬት ማግኘት የሚያስችልዎትን ስልጠና ይውሰዱ።

የስልጠና ዘርፎች፦

► ዌብ ፕሮግራሚንግ
► አንድሮይድ ማበልፀግ
► ዳታ ሳይንስ

ስልጠናውን በስምንት ሳምንት ያጠናቀቁ ሰልጣኞች ዓለም አቀፍ ተቀባይነት ያለው ሰርተፊኬት ይሰጣቸዋል።

ለመመዝገብ 👇
https://www.ethiocoders.et/

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

#ጥቆማ

የካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ በ2017 ዓ.ም በአምስት የትምህርት መስኮች በፖስት ቤዚክ የመጀመሪያ ዲግሪ ፕሮግራም በግል ወይም በመንግሥት ስፖንሰርነት ትምህርታችሁን መከታተል የምትፈልጉ አመልካቾችን ይቀበላል፡፡

የማመልከቻ ጊዜ፦
እስከ የካቲት 20/2017 ዓ.ም

የትምህርት መስኮች፦

✍️ Comprehensive Nursing
✍️ Neonatal Nursing
✍️ Emergency & Critical Care Nursing
✍️ Midwifery
✍️ Medical Laboratory Technology

መስፈርቶች፡-
► ዲፕሎማ ወይም TVET ደረጃ-4 ከታወቀ ተቋም
► የሥራ ልምድ አይጠይቅም
► COC ወስዶ ያለፈ/ያለፈች
► ከሥራ ቦታ የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችል/የምትችል
► የመግቢያ ፈተና ማለፍ የሚችል/የምትችል

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያስተማራቸውን 397 ተማሪዎች አስመርቋል።

ተመራቂዎቹ በመደበኛ፣ በማታ፣ በሳምንቱ መጨረሻ እንዲሁም በክረምት መርሐግብር ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ ናቸው።

ዩኒቨርሲቲው በዛሬው ዕለት 5ኛ ዙር የምረቃ ስነ-ስርዓት ያከናወነ ሲሆን፤ የጤና ሳይንስ እና የቡና ትምህርት ክፍል ተማሪዎችን ለመጀመሪያ ጊዜ አስመርቋል።

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

ጎንደር ዩኒቨርሲቲ "የጎንደር ቃልኪዳን ቤተሰብ" የተመሠረተበትን ስድስተኛ ዓመት አክብሯል።

በ2012 ዓ.ም "የጎንደር ቤተሰብ ፕሮጀክት" በሚል የተጀመረው ፕሮግራም ስድስተኛ ዓመት በዓል፥ የዩኒቨርሲቲው አዲስና ነባር ተማሪዎችና የቃልኪዳን ወላጆች በተገኙበት ተከብሯል፡፡

ባለፉት ስድስት ዓመታት ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ተመድበው የነበሩ ተማሪዎች በፕሮጀክቱ ትስስር ተፈጥሮላቸውና የቃልኪዳን ወላጆችን አግኝተው ትምህርታቸውን በሚገባ ሲከታተሉ መቆየታቸውን ምስክርነት ሰጥተዋል።

"የጎንደር ቃልኪዳን ቤተሰብ ፕሮጀክት" ተሞክሮ በአሜሪካ፣ በካናዳ፣ በአውሮጳ እና በጃፓን በሚገኙ የትምህርት ተቋማት የተለመደ አሠራር እንደሆነ ጥናቶችን ዋቢ በማድረግ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት አስራት አፀደወይን (ዶ/ር) ተናግረዋል።

ፈንድ ፎር ኢኖቬሽን ኢን ዴቨሎፕመንት በተባለ የፈረንሳይ ተቋም ድጋፍ በጎንደር የቤተሰብ ትስስር ፕሮጀክት ላይ ምርምር እየተካሄደ እንደሚገኝም የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ገልፀዋል።

የሰላም ሚኒስቴር ለፕሮጀክቱ ዕውቅና እንደሚሰጥና አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ አሳውቋል።

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ በህክምና እና በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች አስመርቋል።

ዩኒቨርሲቲው በመጀመሪያ ዲግሪ 398 እና በሁለተኛ ዲግሪ 236 በድምሩ 634 ተማሪዎች አስመርቋል።

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

መቱ ዩኒቨርሲቲ በመጀመሪያ እና በሁለተኛ ዲግሪ ፕሮግራሞች ያስተማራቸውን 1,407 ተማሪዎች አስመርቋል፡፡

ከተመራቂዎቹ 226ቱ በሁለተኛ ዲግሪ ፕሮግራም ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ ናቸው።

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 2,524 ተማሪዎችን አስመርቋል።

ተመራቂዎቹ በመደበኛ እና በተከታታይ የትምህርት መርሐግብር በመጀመሪያ ዲግሪ እና በድኅረ-ምረቃ ፕሮግራሞች ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ ናቸው።

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

ዲላ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያስተማራቸውን 518 ተማሪዎች አስመርቋል፡፡

ተመራቂዎቹ በመደበኛ፣ በቅዳሜና እሑድ እንዲሁም በክረምት መርሐግብር በመጀመሪያ፣ በሁለተኛ እና በሦስተኛ ዲግሪ ፕሮግራሞች ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ ናቸው።

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

4ኛ ዙር የኮምፒውተር ፕሮግራሚንግ እና ዳታቤዝ (Computer Programming and Database) ስልጠና በፒያሣ እና በመገናኛ ካምፓስ ምዝገባ ላይ ነን።

🔔 ፈጥነው ይመዝገቡ!

👉 ተግባርን ከንድፈ ሀሳብ ያስተሳሰረ ስልጠና
👉 C++, Java እና Python ፕሮግራሞች ከፍ ባለ ደረጃ (Advanced Level) በጋራ የሚሰጡበት
👉 ፕሮጀክቶችን እየሠሩ የሚሰለጥኑበት

☎️  0906777799 / 0906777755
አድራሻ፦
ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ እና ቁ.2 መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ

Telegram: /channel/sagetraininginstitute
TikTok: sage_training_institute" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@sage_training_institute
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute

Читать полностью…

Tikvah-University

#ጥቆማ

የእንግሊዘኛ ቋንቋ ምዘና ፈተና (IELTS Test) በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ይሰጣል!

ብሪቲሽ ካውንስል ከድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር የ'IELTS' ፈተና የካቲት 29/2017 ዓ.ም ይሰጣል፡፡

ዩኒቨርሲቲው ፈተናውን መውሰድ የሚፈልጉ አመልካቾች የኦንላይን ምዝገባ በማድረግ ላይ ይገኛል።

ኦንላይን ይመዝገቡ 👇
https://forms.gle/LxdEGVCMDZaPpACV7

ለበለጠ መረጃ፦
☎️ 0923032129

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

ብር በነፃ በመላክ የ M-PESAን ነፃ አገልግሎት እናጣጥም! ከ M-PESA ወደ የትኛውም የሳፋሪኮም ስልክ በነፃ እንላክ!

#MPESASafaricom #MPESAEthiopia

Читать полностью…

Tikvah-University

Artificial Intelligence and Data Science ስልጠና በፒያሣ እና በመገናኛ ካምፓስ ምዝገባ ላይ ነን!

👉 ከፍተኛ ልምድ ባላቸው መምህራን የሚሰጥ
👉 ንድፈ ሀሳብን ከተግባር ጋር በማዛመድ የሚሰጥ ስልጠና

☎️   0906777799 / 0906777755
አድራሻ፦
ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ እና ቁ.2 መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ

Telegram: /channel/sagetraininginstitute
TikTok: sage_training_institute" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@sage_training_institute
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute

Читать полностью…

Tikvah-University

#ጥቆማ
#BongaUniversity

ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የጤና ሙያ መስኮች ባለሙያዎችን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል፡፡

➤ የሥራ መደብ፦ በጤና መስኮች
➤ ተፈላጊ ባለሙያዎች ብዛት፦ 37
➤ ተፈላጊ የትምህርት ደረጃ፦ ከመጀመሪያ ዲግሪ ጀምሮ
➤ የሥራ ቦታ፦ ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ

መስፈርቱን የምታሟሉ ባለሙያዎች ከዛሬ የካቲት 13/2017 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት ተከታታይ አስር የሥራ ቀናት በዩኒቨርሲቲው የብቃትና ሰው ሃብት አስተዳደር ሥራ አስፈጻሚ ቢሮ ወይም አዲስ አበባ ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ወኪል ቢሮ ሽሮሜዳ ከአሜሪካ ኤምባሲ ፊት ለፊት በመገኘት ማመልከት ትችላላችሁ ተብሏል፡፡

የፈተና ጊዜ በቀጣይ ይገለጻል፡፡ (ዝርዝር የሥራ ማስታወቂያው ከላይ ተያይዟል፡፡)

ለተጨማሪ መረጃ፦
0111561725 / 0911102250

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ 85 የሕክምና ዶክተሮች እና 160 የጤና ሳይንስ ተማሪዎችን ቅዳሜ የካቲት 15/2017 ዓ.ም ያስመርቃል፡፡

መቱ እና ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲዎችን ጨምሮ በርካታ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በሳምንቱ መጨረሻ ተማሪዎቻቸውን ያስመርቃሉ።

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

2ኛ ዙር የፎቶግራፊ፣ ቪዲዮግራፊ፣ ግራፊክ ዲዛይን እና ቪዲዮ ኤዲቲንግ ስልጠና በመገናኛ ካምፓስ ምዝገባ ላይ ነን። 

👉 ተግባርን ከንድፈ ሀሳብ ያስተሳሰረ ስልጠና
👉 Photography, Cinematography, Videography, Graphic Design and Video Editing በአንድ ላይ
👉 ፕሮጀክቶችን በስቱዲዮ እና በመስክ በመስራት የሚሰጥ

☎️   0906777799 / 0906777755
አድራሻ፦
ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ እና ቁ.2 መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ

Telegram: /channel/sagetraininginstitute
TikTok: sage_training_institute" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@sage_training_institute
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute

Читать полностью…
Subscribe to a channel