#MaddaWalabuUniversity
መደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ በ2017 ዓ.ም አዲስ የተመደባችሁ እና በ2016 ዓ.ም የአቅም ማሻሻያ (Remedial) ትምህርታችሁን በመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ተከታትላችሁ የማለፊያ ውጤት ያስመዘገባችሁ ተማሪዎች ምዝገባ ህዳር 9 እና 10/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡
ወደ ዩኒቨርሲቲው ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦
- የ12ኛ ክፍል የትምህርት ማሰረጃ ዋናውና ኮፒው፣
- ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
- የ8ኛ ክፍል የትምህርት ማስረጃ ዋናውና ኮፒው፣
- አራት 3X4 ጉርድ ፎቶግራፍ፣
- ብርድ ልብስ፣ አንሶላ፣ ትራስ ጨርቅ እና የስፖርት ትጥቅ።
የትምህርት ማመልከቻ እና ምዝገባ የሚከናወነው በኦንላይን http://estudent.mwu.edu.et/auth/login ሊንክ በመጠቀም ስለሆነ በተጠቀሱት ቀናት በመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ሮቤ ካምፓስ በአካል በመገኘት በኦንላይን ምዝገባ አድርጉ ተብሏል፡፡
በ2017 ዓ.ም ለሪሚዲያል ትምህርት በመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ወደፊት እንደሚገለፅ ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡
@tikvahuniversity
#ጥቆማ
ወሎ ዩኒቨርሲቲ በ2016 ዓ.ም የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ካመጡ ተማሪዎች መካከል በ2017 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በግእዝ ቋንቋና ስነ-ጽሑፍ የትምህርት መስክ በመጀመሪያ ዲግሪ ለመማር ፍላጎት ያላቸውን ተማሪዎች ከሁሉም የሀገሪቱ ዩኒቨርሲቲዎች ተቀብሎ በመደበኛ ፕሮግራም ማሰልጠን ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም መስፈርቱን የምታሟሉና ፍላጎቱ ያላችሁ አመልካቾች ከ8ኛ-12ኛ ክፍል ሙሉ የትምህርት ማስረጃችሁን ይዛችሁ በወሎ ዩኒቨርሲቲ ደሴ ካምፓስ በአካል በመቅረብ እስከ ህዳር 7/2017 ዓ.ም ድረስ ማመልከት የምትችሉ መሆኑ ተገልጿል።
በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች የሪሚዲያል ፕሮግራም ተምራችሁ ወደ ፍሬሽማን ፕሮግራም ያለፋችሁ ተማሪዎች የዕድሉ ተጠቃሚ መሆን ትችላላችሁ ተብሏል።
@tikvahuniversity
የፊታችን ቅዳሜ ህዳር 7/2017 ዓ.ም Advanced Standards and Practices of Accounting ስልጠና በመገናኛ ካምፓስ ይጀምራል።
👉 IFRS + Peachtree + Asset Valuation + IFRS Conversion + IPSAS + Quick Book በአንድ ላይ
👉 ስልጠናው ሙሉ በሙሉ በተግባር የተደገፈና ፒስትሪ (Peachtree Software) ላይ የሚሰጥ ነው።
☎️ 0906777799 / 0906777755
አድራሻ፦ ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ እና ቁ.2 መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ
Telegram: /channel/sagetraininginstitute
TikTok: sage_training_institute" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@sage_training_institute
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute
#JinkaUniversity
በ2016 ዓ.ም የሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርታችሁን በጂንካ ዩኒቨርሲቲ ተከታትላችሁ የማለፍያ ውጤት ያመጣችሁ እንዲሁም በ2017 ዓ.ም በፍሬሽማን ፕሮግራም አዲስ የተመደባችሁ ተማሪዎች የ2017 ዓ.ም ምዝገባ የሚከናወነው ህዳር 11 እና 12/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።
ወደ ዩኒቨርሲቲው ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦
- ከ8ኛ ክፍል ጀምሮ ያሉ የትምህርት ማስረጃዎች ዋናውና ኮፒው፣
- አራት 3X4 ጉርድ ፎቶግራፍ፣
- አንሶላ፣ ትራስ ጨርቅ እና የስፖርት ትጥቅ።
@tikvahuniversity
🛑 ለቢዝነሶች የቀረበ ጥሪ 🛑
https://mesirat.acceleratorapp.co/application/new?program=mesirat-entrepreneurs-application-form-seventh-cohort ላይ ተመዝግበው፦
- በፋይናንስ፣
- በማርኬቲንግ፣
- በቴክኖሎጂ፣
- በኔትወርኪንግ፣
- የባለሙያ አማካሪዎችን በማግኘት፣
- በአገልግሎት ሰጪነት እና
- በአማካሪነት ድጋፍ ያግኙ።
የመስራት ስራ ፈጠራ ፕሮግራም አካል ይሁኑና ቢዝነስዎ እንዲያድግ አጠቃላይ ድጋፍን ያግኙ።
ፕሮግራማችን የባለሙያ ምክር ማግኘት፣ ጠቃሚ ግብአቶች እና ተመሳሳይ አስተሳሰብ ካላቸው ስራ ፈጣሪዎች ጋር ንቁ እድገትን ለማፋጠን የተነደፈ ነው።
ሴቶች እና አካል ጉዳተኞች እንዲያመለክቱ ይበረታታሉ!
#መስራት #ስራፈጠራ #MesiratEthiopia #Entrepreneurship #Opportunity #GPM #Mesirat
2ኛው አገር አቀፍ የቴክኖሎጂ ማበልጸጊያ ፕሮግራም ነገ ህዳር 4/2017 ዓ.ም ይጀመራል።
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር፣ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት እና የኢንተርፕረነርሺፕ ልማት ኢንስቲትዩት ፕሮግራሙን በጋራ አዘጋጅተውታል።
መርሐግብሩ በአገር አቀፍ ደረጃ የቴክኖሎጂ ፈጠራ ተሰጥኦ ያላቸውን ወጣቶች በአንድ ማዕከል በማሰባሰብ ክህሎታቸውን በማሳደግ ከውጪ የሚገቡ ቴክኖሎጂዎችን የሚተኩ፣ ምርትና ምርታማነትን የሚያሳድጉ ችግር ፈቺ ቴክኖሎጂዎችን እንዲፈጥሩ የሚያስችል ነው።
@tikvahuniversity
🔊 🌟 ገቡ ገቡ ገቡ! የሳፋሪኮም #1ወደፊት የዲጂታል ሙዚቃ ውድድር ምርጥ 10 ኮከቦቻችን ወደ ሙዚቃ ስልጠናው ገብተዋል! በቆይታቸውም የሚኖራቸውን ጊዜ ተከታተሉን!
#SafaricomEthiopia
#1Wedefit
#FurtherAheadTogether
#DigitalMusicChallenge
#BuleHoraUniversity
በ2017 የትምህርት ዘመን ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ መደበኛ የቅድመ-ምረቃ ተማሪዎች ወደተቋም የመግቢያ ጊዜ ህዳር 9 እና 10/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።
ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦
- ከ8ኛ-12ኛ ክፍል የትምህርት ማስረጃ ዋናውና ሁለት ኮፒ፣
- ስምንት 3×4 ጉርድ ፎቶግራፍ፣
- አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ ትራስ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ፡፡
@tikvahuniversity
#ሎርካን_ሜዲካል_ኮሌጅ
🔔 የበርካታ ዓመታት ልምድ ባላቸው ሐኪሞችና ምሁራን ባለቤትነት የሚመራው ሎርካን ሜዲካል ኮሌጅ ምዝገባ ጀምሯል❗️
BSc fields of study:
→ Doctor of Medicine
→ Doctor of Dental Medicine
→ Bachelor of Dental Science
→ Nursing
TVET Programs:
→ Dental Therapy
→ Nursing
→ Medical Laboratory
→ Pharmacy
→ Radiography
★ የ CPD ማዕከል አገልግሎት!
☎️ 0913398780 / 0911596059
አድራሻ፦
CMC አደባባይ ከፀሐይ ሪል እስቴት ጀርባ ከ ICMC ጠቅላላ ሆስፒታል አጠገብ
Facebook: https://www.facebook.com/Lorcanmedicalcollege
#WolloUniversity
በ2017 ዓ.ም በወሎ ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባችሁ የመጀመሪያ ዓመት መደበኛ ተማሪዎች እና በ2016 ዓ.ም የሪሚዲያል ፕሮግራም ተምራችሁ ያለፋችሁ መደበኛ ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ ህዳር 13 እና 14/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።
ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦
- የ12ኛ ክፍል ሰርተፊኬት፣
- ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት
- የ8ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
- አራት ጉርድ ፎቶግራፍ፣
- ብርድ ልብስ፣ አንሶላ፣ ትራስ ልብስ፣ የስፖርት ትጥቅ።
የተመደባችሁበትን ግቢ ለማወቅ 👇
Telegeram Bot: @WU_Registrar_bot
Website: https://tinyurl.com/wu-Registrar-s
@tikvahuniversity
የኢትዮጵያ የግል ከፍተኛ ትምህርት እና ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋማት ማህበር የ2017 ዓ.ም መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን አካሒዷል፡፡
በጉባኤው የማህበሩ የ2016 ዓ.ም የውጭ ኦዲተር ሪፖርት፣ የ2016 ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት እና የ2017 በጀት ዓመት መሪ ዕቅድ በማህበሩ ሥራ አስኪያጅ ተፈራ ገበየሁ ቀርቧል፡፡
የማህበሩ ፕሬዝዳንት አረጋ ይርዳው (ዶ/ር) የግል ትምህርት ዘርፉ አሁናዊ ሁኔታ እና ቀጣይ ስትራቴጂ ላይ ገለፃ አድርገው ሰፊ ውይይት ተደርጓል፡፡
በአጠቃላይ በአገሪቱ ከሚገኙ ተማሪዎች መካከል 41 በመቶ በግል ተቋማት እንደሚገኙና እንዚህ ተቋማት ባለፉት ሦስት አስርት ዓመታት በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ዜጎችን አስመርቀው ለስራ ያበቁና አሁንም እያበቁ እንደሆነ በትምህርት ሚኒስቴር የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ዴስክ ኃላፊ እዮብ አየነው (ዶ/ር) ገልፀዋል፡፡
በሀገሪቱ ካሉ 386 ተቋማት HEMIS የመረጃ ቋት መረጃቸውን ያስገቡ ተቋማት 131 ብቻ መሆናቸው ትልቅ ክፍተት መሆኑን አንስተዋል፡፡
@tikvahuniversity
#BuleHoraUniversity
በ2016 ዓ.ም እና በ2017 ዓ.ም ሀገር አቀፍ የድኅረ ምረቃ መግቢያ ፈተና (NGAT) ወስዳችሁ ያለፋችሁ ተማሪዎች የሚያስፈልጋችሁን ሙሉ መረጃ በመያዝ ከጥቅምት 30/2017 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ አስራ አምስት (15) የሥራ ቀናት ምዝገባ እንድታደርጉ ዩኒቨርሲቲው አሳስቧል።
በቅድሚያ ኦፊሺያል ትራንስክሪፕት ማስላክ ይኖርባችኋል ተብሏል።
የድኅረ-ምረቃ የትምህርት መስኮች፦
1.Gadaa and Peace Studies (MA)
2.Gadaa and Governance Studies(PhD)
የምዝገባ ቦታ፦
ቡሌሆራ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደር ህንጻ ቢሮ ቁ. 59
@tikvahuniversity
#ሜድስኬፕ_ጤና_ሳይንስና_ቢዝነስ_ኮሌጅ_እንጅባራ_ካምፓስ
✔️ ሙሉ ዕውቅና እና ፈቃድ ያለው ኮሌጃችን፤ ልምድ ባላቸው ስፔሻሊስት ሀኪሞችና የጤና ባለሙያዎች የተቋቋመ ኮሌጅ ነው።
ለ2017 የትምህርት ዘመን በሚከተሉት የትምህርት መስኮች በመደበኛ፣ በቅዳሜና እሁድ፣ በኤክስቴንሽን መርሐግብር ምዝገባ ጀምረና
በመጀመሪያ ዲግሪ እንዲሁም በዲፕሎማ
➫ በፋርማሲ
➫ በነርሲንግ
➫ በማኔጅመንት
➫ በአካውንቲንግ እና ፋይናንስ
➫ በማርኬቲንግ ማኔጅመንት
➫ በኢኮኖሚክስ
➫ በኮምፒውተር ሳይንስ
➫ በእንሰሳት ጤና
➫ በአይሲቲ
በሪሚዲያል ፕሮግራም
➫ በ Natural Science
➫ በ Social Science
በኮሌጃችን ሲማሩ በነፃ የሚሰጡ ስልጠናዎች፦
✍️ Basic Computer Skills & Programming
✍️ የህይወት ክህሎት ስልጠና
✍️ Peachtree Accounting
አድራሻ፦
እንጅባራ ከተማ ዋናው አደባባይ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ፊት ለፊት
ስልክ ቁጥር፦
0995222294 / 0962791808 / 0921940650
#UniversityOfGondar
ለ2017 የትምህርት ዘመን በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ ገቢ ተማሪዎች እንዲሁም በ 2016 ዓ.ም የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች የነበራችሁና የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ቀናት ህዳር 12 እና 13/ 2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።
የመጀመሪያ ቀን ትምህርት የሚጀምረው ህዳር 16/2017 ዓ.ም መሆኑ ተገልጿል።
@tikvahuniversity
መቐለ ዩኒቨርሲቲ ከ2,700 በላይ ተማሪዎች ዛሬ ማስመረቁ ይታወቃል።
በተማሪዎቹ የምርቃት ስነ-ስርዓት ላይ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ጌታቸው ረዳ ምን አሉ?
በሰሜኑ ጦርነት ወቅት በመቐለ ዩኒቨርሲቲ ላይ ከደረሰው ቁሳዊ ውድመት ባሻገር፥ የሕይወት ዋጋ የከፈሉ፣ የአካል ጉዳት የደረሰባቸው እና አድራሻቸው የጠፋ ተማሪዎች መኖራቸውን ፕሬዝዳንቱ ገልፀዋል።
ጦርነቱ በተማሪዎች እና በዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ ላይ ከፍተኛ የማኅበራዊ ጫና ማስከተሉን ፕሬዝዳንቱ አንስተዋል።
መምህራንና የትምህርት አመራሮች ለ17 ወራት ያለ ደመወዝ በቀናነት ለሙያቸው ታምነው ማገልገላቸውን በማድነቅ አመስግነዋል።
የክልሉን የትምህርት ዘርፍ መልሶ ለማቋቋምና የደመወዝ ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር እንደሚሰራ ተናግረዋል። #AshamTv
@tikvahuniversity
ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌኒየም ሜዲካል ኮሌጅ በኅብረተሰብ ጤና የማስተርስ ፕሮግራም (MPH) መደበኛ እና የዕረፍት ቀናት አመልካቾች የቃል ፈተና አርብ ህዳር 6/2017 ዓ.ም ጠዋት 3:00 በተቋሙ አካዳሚክ ህንጻ እንደሚሰጥ ገልጿል።
@tikvahuniversity
ይሄኔ እኮ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ይህን አልሰሙም፤ የሀገር ውስጥ በረራችንን በM-PESA ስናደርግ 5% ተመላሽ አለን። ይህን አጋጣሚማ እፍስ ነው እንጂ!
M-PESA ላይ እንመዝገብ፣ በM-PESA እንገበያይ!
🔗 የM-PESA ሳፋሪኮም መተግበሪያን በዚህ ሊንክ እናውርድ ፡ https://play.google.com/store/apps/details?id=et.safaricom.mpesa.lifestyle
የቴሌግራም ቻናላችንን እዚህ እንቀላቀል 👉 /channel/Safaricom_Ethiopia_PLC
ስለ አገልግሎታችን ማንኛውንም ጥያቄ ወይም መረጃ በቴሌግራም ቻናላችን /channel/Safaricom_Ethiopia_PLC 24/7 ማግኘት ይቻላል!
#MPESASafaricom #FurtherAheadTogether
#RayaUniversity
ለ2017 የትምህርት ዘመን ራያ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ የአንደኛ ዓመት አዲስ ተማሪዎች እንዲሁም በ2016 ዓ.ም በዩኒቨርሲቲው የአቅም ማሻሻያ መርሐግብር (Remedial Program) ወስዳችሁ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ቀናት ህዳር 9 እና 10/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡
@tikvahuniversity
#AssosaUniversity
በ2016 ዓ.ም በሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርታችሁን ተከታትላችሁ የማለፊያ ውጤት ያስመዘገባችሁ እንዲሁም በ2017 ዓ.ም በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባችሁ አንደኛ ዓመት ተማሪዎች የ2017 ዓ.ም የመግቢያ ጊዜ ህዳር 16 እና 17/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።
ወደ ዩኒቨርሲቲው ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦
- የ12ኛ ክፍል ውጤት ዋናውና ኮፒው፣
- ከ8ኛ-12ኛ ክፍል የትምህርት ማስረጃዎች ዋናውና ኮፒው፣
- አራት 3X4 ጉርድ ፎቶግራፍ፣
- አንሶላ፣ ብርድልብስ እና ትራስ ጨርቅ፣
- የስፖርት ትጥቅ።
@tikvahuniversity
በቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት በቀን መርሐግብር ስልጠናችሁን ለመከታተል ተመዝግባችሁ ፈተና ያለፋችሁ አዲስ ሰልጣኞች በሙሉ ከህዳር 4-6/2017 ዓ.ም በኢንስቲትዩቱ በመገኘት ሲስተም ላይ እንድትመዘገቡ ተብሏል።
@tikvahuniversity
#DebreTaborUniversity
በደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ በ2016 ዓ.ም የሪሚዲያል ፕሮግራም ተከታትላችሁ የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ እንዲሁም በ2017 ዓ.ም የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት አምጥታችሁ ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ የአንደኛ ዓመት (Freshman) ተማሪዎች የ2017 ትምህርት ምዝገባ ህዳር 9 እና 10/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡
ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦
- ከ8ኛ-12ኛ ክፍል የትምህርት ማስረጃዎች ዋናውና ኮፒው፣
- አራት 3x4 የሆነ ፎቶግራፍ፣
- ብርድልብስ፣ አንሶላ፣ ትራስ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ፡፡
በ2017 ዓ.ም የሪሚዲያል ፕሮግራም እንድትከታተሉ በደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች በሌላ ማስታዎቂያ ጥሪ ይደረግላችኋል ተብሏል።
@tikvahuniversity
የፊታችን ቅዳሜ ህዳር 7/2017 ዓ.ም 4ኛ ዙር የጋዜጠኝነት ስልጠና በመገናኛ ካምፓስ ይጀምራል።
ልምድ ባላቸው ጋዜጠኞች በመሰልጠን ከፍተኛ ልምድ ለማግኝት ቀድመው ይመዝገቡ።
በስልጠናው የሚሰጡ፦
👉 መሠረታዊ የጋዜጠኝነት መርሆች
👉 የብሮድካስት ጋዜጠኝነት፣ የፕሬስ ጋዜጠኝነት እና የዲጂታል ሚዲያ ጋዜጠኝነት
👉 የመዝናኛ፣ የመደበኛ ፕሮግራም ዝግጅት እና ዶክመንተሪ ዝግጅት ተካተዋል።
👉 የሥራ ላይ ስልጠና (Internship) አካቷል፡፡
ስልጠናው ለሦስት ወር የሚቆይ ሲሆን በማታ፣ በቅዳሜና እሑድ፣ በቀን እና በርቀት ይሰጣል።
☀️ በተመጣጣኝ ዋጋ፣ በምቹ ቦታ እና በዘርፉ ባሉ ብቁና የተመረጡ ጋዜጠኞች የሚሰጥ።
☎️ 0906777799 / 0906777755
አድራሻ፦ ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ እና ቁ.2 መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ
Telegram: /channel/sagetraininginstitute
TikTok: sage_training_institute" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@sage_training_institute
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute
#DebarkUniversity
ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ በ2017 ዓ.ም አዲስ የተመደባችሁ መደበኛ አንደኛ ዓመት እና በ2016 ዓ.ም በመደበኛ የሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርታችሁን ተከታትላችሁ ያለፋችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ቀን ህዳር 18 እና 19/2017 ዓ.ም መሆኑን ከዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡
በቅጣት ምዝገባ፦ ህዳር 20/2017 ዓ.ም
ትምህርት የሚጀመርበት ቀን፦ ህዳር 20/2017 ዓ.ም
ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦
- የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል ሰርቲፊኬት፣
- ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
- አራት 3×4 ጉርድ ፎቶግራፍ፣
- አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ ትራስ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ፡፡
@tikvahuniversity
#GondarUniversity
በጎንደር ዩኒቨርሲቲ በ2017 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የተመደቡ አዲስ ገቢ የቅድመ-ምረቃ ፕሮግራም የመደበኛ እና በ2016 የትምህት ዘመን አቅም ማሻሻያ (Remedial) ፕሮግራም ሲከታተሉ ቆይተው የማለፊያ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ቀናት ህዳር 12 እና 13 2017 ዓ.ም መሆኑን ገልጿል።
@tikvahuniversity
#MoH
የ2024 ትምህርት ዘመን የብሔራዊ የህክምና ስፔሻሊቲ ስልጠና (ERMP) አመልካቾች ምዝገባ ከህዳር 3-17/2017 ዓ.ም እንደሚከናወን ጤና ሚኒስቴር አሳውቋል፡፡
ለበለጠ መረጃ፦
https://www.moh.gov.et/en/ermp-announcements
@tikvahuniversity
ቅዳሜ ህዳር 7/2017 ዓ.ም 16ኛ ዙር ሙሉ የሒሳብ መዝገብ አያያዝ (Principles and Practices of Accounting) የስድስት ወር የቅዳሜ እና እሑድ ስልጠና በፒያሣ ካምፓስ ይጀምራል።
👉 100% በተግባር የተደገፈ ስልጠና
👉 መሠረታዊ የአካውንቲንግ እና ኦዲት አሰራር፣ ሙሉ የአካውንቲንግ ሒሳብ አሰራር በፒስቺሪ ተደግፎ እና የግብር አያያዝ ትምህርቶችን አካቶ የሚሰጥ
👉 የሥራ ላይ ስልጠና (Internship) የተመቻቸለት
☎️ 0906777799 / 0906777755
አድራሻ፦ ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ እና ቁ.2 መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ
Telegram: /channel/sagetraininginstitute
TikTok: sage_training_institute" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@sage_training_institute
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute
#ArbaMinchUniversity
በ2017 ዓ.ም አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባችሁ እና በ2016 ዓ.ም የሪሚዲያል ፕሮግራም በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተከታትላችሁ የማለፊያ ውጤት ያስመዘገባችሁ የቅድመ-ምረቃ መደበኛ ፕሮግራም ተማሪዎች ሪፖርት ማድረጊያ ቀናት ህዳር 7 እና 8/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።
ምዝገባ ኅዳር 9 እና 10/2017 ዓ.ም የሚከናወን ሲሆን፤ ትምህርት ረቡዕ ኀዳር 11/2017 ዓ.ም ይጀምራል ተብሏል፡፡
ሪፖርት ማድረጊያ ቦታዎች፦
- የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች አርባ ምንጭ ከተማ በሚገኘው አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ዋና ግቢ፣
- የስማችሁ የመጀመሪያ ፊደል ከ A እስከ Q የሆናችሁ የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች አርባ ምንጭ ከተማ በሚገኘው ጫሞ ካምፓስ፣
- የስማችሁ የመጀመሪያ ፊደል ከ R እስከ Z የሆናችሁ የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ሳውላ ከተማ በሚገኘው ሳውላ ካምፓስ።
ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦
- ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ሁለት ኮፒ፣
- የ12ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ዋናውና ሁለት ኮፒ፣
- አራት 3×4 ጉርድ ፎቶግራፍ፣
- አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ ትራስ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ።
@tikvahuniversity
#ScholarshipOpportunity
ነፃ የትምህርት ዕድል!
ክቡር ኮሌጅ ከአጋር ተቋማት ጋር በመተባበር ለዚህ ዓመት በመደበኛው ፕሮግራም በመጀመሪያ ዲግሪ መማር ለሚፈልጉ ተማሪዎች ውስን የትምህርት ዕድል (Scholarship Opportunity) አመቻችቷል፡፡
በዚህ ብቃትን መሰረት አድርጎ በተዘጋጀ የከፍተኛ ትምህርት ዕድል ለመሳተፍና ለመወዳደር ከታች ያለውን ማስፈንጠሪያ በመጫን ማመልከት ትችላላችሁ።
ያመልክቱ 👉 Scholarship.kibur.edu.et
✍️ ክቡር ኮሌጅ ሊሸፍን ያዘጋጀው የገንዘብ መጠን ለአንድ ተማሪ 50,000 ብር ነው፡፡
✍️ ሴት አመልካቾች ቅድሚያ ይሰጣቸዋል፡፡
✍️ ለነፃ የትምህርት ዕድል ያለው ቦታ ለአስር (10) ተማሪዎች ነው፡፡
✍️ የተዘጋጀው በመደበኛ መርሐግብር (በቀን) ብቻ መማር ለሚፈልጉና ለሚችሉ ተማሪዎች ብቻ ነው።
✍️ ይህ የትምህርት ዕድል የተመቻቸው በአዲስ አበባና ዙሪያዋ ለሚኖሩ ተማሪዎች ሲሆን፤ ምግብና የመኖሪያ ዶርም አያካትትም።
✍️ አመልካቾች ከዚህ በፊት የመጀመሪያ ዲግሪ የሌላቸውና ትምህርት ሚኒስቴር ያስበመጠውን የመግቢያ ነጥብ ያሟሉ መሆን ይኖርባቸዋል።
✍️ ማመልከት የሚቻለው እስከ ህዳር 7/2017 ዓ.ም ድረስ ብቻ ነው፡፡
Scholarship.kibur.edu.et
ለበለጠ መረጃ፦
☎️ 0113698558 / 0904848586
ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ለመጀመሪያ ጊዜ በእንስሳት ህክምና ያሰለጠናቸውን ሐኪሞች ዛሬ አስመርቋል።
ዩኒቨርሲቲው ለመጀመሪያ ጊዜ በእንስሳት ህክምና ሲያሰለጥናቸው የቆዩ 21 ሐኪሞችን አስመርቋል።
የዩኒቨርሲቲው Veterinary Medicine Department ወደ ትምህርት ቤት መሸጋገሩም ተገልጿል።
@tikvahuniversity
#BoranaUniversity
#Revised
በ2016 ዓ.ም በቦረና ዩኒቨርሲቲ በሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርታችሁን ስትከታተሉ ቆይታችሁ የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች፣ በ2016 ዓ.ም ትምህርት ጀምራችሁ በአንደኛ ሴሚሰቴር በውጤት እና በተለያዩ ምክንያቶች ዊዝድሮዋል በመሙላት ያቋረጣችሁ ተማሪዎች እንዲሁም በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ወስዳችሁ የማለፊያ ውጤት አምጥታችሁ ቦረና ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች ምዝገባ የሚከናወነው ህዳር 9 እና 10/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡
ትምህርት የሚጀመረው ህዳር 12/2017 ዓ.ም መሆኑ ተገልጿል፡፡
ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦
- የ8ኛ ክፍል ሰርቲፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
- ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
- የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ዋናውና ኮፒው፣
- ስምንት 3×4 ጉርድ ፎቶግራፍ፣
- አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ ትራስ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ።
@tikvahuniversity