tikvahuniversity | Unsorted

Telegram-канал tikvahuniversity - Tikvah-University

308824

Subscribe to a channel

Tikvah-University

Top Training Institute ከአሁን ቀደም ከሚሰጣቸው የኮምፒውተር እና የቋንቋ ስልጠናዎች በተጨማሪ በ Photography, Videography & Cinematography ስልጠናዎችን ዘመናዊ ካሜራዎችን በማሟላት በሙያው የረጅም ጊዜ ልምድ ባላቸው አሰልጣኞች መስጠት የጀመረ መሆኑን በአክብሮት ይገልጻል።

አድራሻ፦
● መገናኛ መተባበር ህንፃ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁ. 419 (ሊፍት ይጠቀሙ) ☎️ 0991929303
● ሜክሲኮ ኬኬር ህንፃ 6ኛ ፎቅ ቢሮ ቁ. 639 (2ኛውን ሊፍት ይጠቀሙ) ☎️ 0991929304
● ጀሞ 1 አንደኛ በር ካኩ ቢዝነስ ሴንተር 3ኛ ፎቅ ☎️ 0991926707

@Top_trainings

Join our Telegram Channel:
/channel/topinstitutes

Читать полностью…

Tikvah-University

#ETA

የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን በጥር 2017 ዓ.ም የሚሰጠውን ሀገር አቀፍ የመውጫ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎችን መረጃ እንዲልኩ ሁሉንም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጠይቋል።

በዚህም ተቋማቱ ፈቃድ በተሰጣቸው ትምህርት መስኮች፣ የትምህርት ደረጃ፣ መርሐግብር እና ካምፓስ በጥር ወር 2017 ዓ.ም ለሚሰጠው የመውጫ ፈተና ለመጀመሪያ ጊዜ የሚፈተኑ ዕጩ ምሩቃን ዝርዝር መረጃ ከታህሳስ 1-15/ 2017 ዓ.ም በሶፍት እና በሀርድ ኮፒ እንዲልኩ ባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ አሳስቧል።

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

በቱርክ በተደረገ የዓለም ሮቦቲክስ ኦሎምፒያድ ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች ተሳትፈዋል።

ከ90 አገራት የተውጣጡ 1,400 ተወዳዳሪዎች በውድድሩ በመሳተፍ እጅግ ዘመናዊ የሆኑ የሮቦቲክስ ፕሮጀክቶችን አቅርበዋል።

የኢትዮጵያ ሀገር አቀፍ ሮቦቲክስ ውድድር አሸናፊዎች የሆኑት የኮተቤ ትምህርት ዩኒቨርሲቲ STEM ማዕከል ተማሪዎች በረከት አሰፋ፣ ቅድስት አልታሰብ እና ልዑል መስፍን በውድድሩ ኢትዮጵያን ወክለው ተሳትፈዋል።

ተማሪዎቹ የራሳቸው ፈጠራ የሆነን ADABTA የተሰኘ ዘርፈ ብዙ ሮቦት ለዕይታ አቅርበዋል። ሮቦቱ ለግብርና፣ ኢንዱስትሪ እና ጤና መስኮች አገልግሎት የሚሰጥ ነው ተብሏል። #STEMpower

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

በM-PESA በነጻ ወደ ማንኛውም የሳፋሪኮም ቁጥር ገንዘብ በመላክ፥ ያለ-ክፍያ ገንዘብ መላክ የሚሰጠውን ደስታ እናጣጥም!

የM-PESA ሳፋሪኮም መተግበሪያን በዚህ ሊንክ እናውርድ፦ https://play.google.com/store/apps/details...

የቴሌግራም ቻናላችንን እዚህ እንቀላቀል 👉 /channel/Safaricom_Ethiopia_PLC

ስለ አገልግሎታችን ማንኛውንም ጥያቄ ወይም መረጃ  በቴሌግራም ቻናላችን /channel/Safaricom_Ethiopia_PLC 24/7 ማግኘት ይቻላል!

#MPESASafaricom  #FurtherAheadTogether

Читать полностью…

Tikvah-University

ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የ2017 ትምህርት ዘመን አዲስ ገቢ የመጀመሪያ ዓመት ተማሪዎችን ዛሬ መቀበል ጀምራል።

በ2017 ዓ.ም ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደቡ መደበኛ ተማሪዎች እንዲሁም በ2016 ዓ.ም በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርታቸውን ተከታትለው የማለፊያ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች ህዳር 26 እና 27/2017 ዓ.ም ሪፖርት እንዲያደርጉ ዩኒቨርሲቲው ጥሪ ማድረጉ ይታወቃል፡፡

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ከ2 ሺህ በላይ የ2017 ትምህርት ዘመን አዲስ ገቢ ተማሪዎችን ዛሬ መቀበል ጀምራል።

ዩኒቨርሲቲው በ2017 ዓ.ም ለተመደቡ የአንደኛ ዓመት አዲስ ገቢ ተማሪዎች እንዲሁም በ2016 ዓ.ም በዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ የሪሚዲያል ትምህርታቸውን ተከታትለው የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ላመጡ ተማሪዎች ለህዳር 26 እና 27/2017 ዓ.ም ጥሪ ማድረጉ ይታወቃል፡፡

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

የጋዜጠኝነት ስልጠና በቅዳሜ እና እሑድ መርሐግብር ምዝገባ ላይ ነን!

👉 መሠረታዊ የጋዜጠኝነት መርሆች
👉 የመዝናኛ ፕሮግራም ጋዜጠኝነት፣ የፕሮግራም ዝግጅት እና ዶክመንተሪ ዝግጅት
👉 የሞባይል ጋዜጠኝነት እና YouTube Journalism አካቷል
👉 የሥራ ላይ ስልጠና (Internship) አካቷል

ስልጠናው ለስድስት ወር የሚቆይ ሲሆን በቅዳሜ እና እሑድ መርሐግብር ይሰጣል።

☎️ 0906777799 / 0906777755
አድራሻ፦
ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ እና ቁ.2 መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ

የበለጠ ይጠብቁ ...
💥 ሴጅ ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት 💥

Telegram: /channel/sagetraininginstitute
TikTok: sage_training_institute" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@sage_training_institute
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute

Читать полностью…

Tikvah-University

በየካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ በመደበኛ የማስተርስ ፕሮግራም በ General Public Health እና በ Reproductive Health የትምህርት መስኮች ለመማር ከጤና ቢሮ የተላካችሁና የመግቢያ ፈተና ተፈትናችሁ ያለፋችሁ ትምህርት የሚጀመረው ህዳር 30/2017 ዓ.ም መሆኑን ኮሌጁ አሳውቋል።

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

Top Training Institute ከአሁን ቀደም ከሚሰጣቸው የኮምፒውተር እና የቋንቋ ስልጠናዎች በተጨማሪ በ Photography, Videography & Cinematography ስልጠናዎችን ዘመናዊ ካሜራዎችን በማሟላት በሙያው የረጅም ጊዜ ልምድ ባላቸው አሰልጣኞች መስጠት የጀመረ መሆኑን በአክብሮት ይገልጻል።

አድራሻ፦
● መገናኛ መተባበር ህንፃ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁ. 419 (ሊፍት ይጠቀሙ) ☎️ 0991929303
● ሜክሲኮ ኬኬር ህንፃ 6ኛ ፎቅ ቢሮ ቁ. 639 (2ኛውን ሊፍት ይጠቀሙ) ☎️ 0991929304
● ጀሞ 1 አንደኛ በር ካኩ ቢዝነስ ሴንተር 3ኛ ፎቅ ☎️ 0991926707

@Top_trainings

Join our Telegram Channel:
/channel/topinstitutes

Читать полностью…

Tikvah-University

#ጥቆማ

በህንድ አገር የሚሰጥ የአጭር ጊዜ ስልጠና ለመከታተል እድሎችን ይመልከቱ፡፡

የህንድ መንግስት በቴክኒካል እና ኢኮኖሚ ትብብር ፕሮግራም (ITEC) ሙሉ ወጪያቸው የሚሸፈን የተለያዩ ስልጠናዎች ለተለያዩ አገራት ይሰጣል፡፡

ዝርዝር መረጃ ለመጠየቅ 👇
itec.addisababa@mea.gov.in

ስለ ፕሮግራሙ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት፦
https://www.itecgoi.in/index

ምስል 1 ፦ በ ITEC ፕሮግራም ሙሉ ወጪያቸው ተሸፍኖ የአጭር ጊዜ ስልጠና ለመውሰድ ወደ ህንድ በቅርቡ የሚሔዱ ኢትዮጵያውያን

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

መቱ ዩኒቨርሲቲ ለ2017 ዓ.ም ሪሚዲያል ተማሪዎች ጥሪ አላደረገም።

"ዩኒቨርሲቲው ለ2017 ዓ.ም ሪሚዲያል ተማሪዎች ለታህሳስ 7 እና 8/2017 ዓ.ም እንደጠራ" ተደርጎ በማኅበራዊ ሚዲያ የተሰራጨው መረጃ ሐሰት መሆኑን ተቋሙ ገልጿል።

በይፋ ጥሪ እስከሚደረግ ድረስ ተማሪዎች በትዕግስት እንዲጠብቁ ዩኒቨርሲቲው ጠይቋል።

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

ለማይቋረጥ የኢንተርኔት ጌም ወሳኙ የማይቋረጥ ኢንተርኔት ነው። አሁኑኑ የሳፋሪኮምን የ4G ዋይፋይ ጥቅል ከM-PESA ሳፋሪኮም mini app በመግዛት በጌማችን እንፍታታ!

#MPESASafaricom
#SafaricomEthiopia
#FurtherAheadTogether

Читать полностью…

Tikvah-University

ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ በ2017 አዲስ ለተመደቡ የአቅም ማሻሻያ (Remedial) ፕሮግራም ተማሪዎች ጥሪ አላደረገም።

"በ2017 ዓ.ም ከትምህርት ሚኒስቴር ወደ ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደቡ የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ ህዳር 30 እና ታህሳስ 1/2017 ዓ.ም እንደሆነ" የሚገልፅ በማኅበራዊ ትስስር ገጾች የሚዘዋወረው መረጃ #ሐሰተኛ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

በ2017 ዓ.ም አዲስ የተመደቡ የሪሚዲያል ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜን ወደፊት የሚያሳውቅ መሆኑን የገለፀው ዩኒቨርሲቲው፤ ጥሪ እስከሚደረግ ተማሪዎች በትዕግስት እንዲጠብቁ ጠይቋል።

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

የፊታችን ቅዳሜ ህዳር 28/2017 ዓ.ም 19ኛ ዙር የድረ-ገፅ እና ሞባይል መተግበሪያ ማበልፀግ (Full-Stack Website and Mobile Application Development) ስልጠና በመገናኛ ካምፓስ በቅዳሜ እና እሑድ መርሐግብር ይጀምራል።   

👉 100% በተግባር የተደገፈ ስልጠና
👉 መሠረታዊ የኮምፒውተር እና ፕሮግራሚንግ ትምህርቶችን አካቶ የሚሰጥ
👉 Front-end እና Back-end በአንድ ላይ እስከ Deployment ያካተተ
👉 በተግባር ድረ-ገፆችን እና ሞባይል መተግበሪያዎችን እያበለፀጉ የሚሰለጥኑበት
👉 የሥራ ላይ ስልጠና (Internship) የተመቻቸለት

☎️    0906777799 / 0906777755
አድራሻ፦ ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ እና ቁ.2 መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ

Telegram: /channel/sagetraininginstitute
TikTok: sage_training_institute" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@sage_training_institute
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute

Читать полностью…

Tikvah-University

በ2017 ዓ.ም በአክሱም ዩኒቨርሲቲ በሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርት ለመማር የተመደባችሁ አዲስ ተማሪዎች የመግቢያ ቀናት ታህሳስ 1 እና 2/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦
- የ8ኛ፣ የ10ኛ እና የ12ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
- ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
- የቅርብ ጊዜ አራት ጉርድ ፎቶግራፍ፣
- አንሶላ፣ የትራስ ጨርቅ፣ ብርድ ልብስ፡፡

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

#ተጨማሪ #ETA

ሁሉም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የአዲስ ተማሪዎቻቸውን ዝርዝር መረጃ እንዲልኩ የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን አሳስቧል።

ባለሥልጣን መ/ቤቱ የትምህርት ጥራትና አግባብነትን ለማስጠበቅና ለመከታተል ያስችለው ዘንድ ሁሉም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የአዲስ ተማሪዎችን ዝርዝር መረጃ በወቅቱ እንዲልኩለት ይጠበቃል።

በመሆኑም ተቋማቱ ፈቃድ በተሰጣችሁ ትምህርት መስኮች፣ ትምህርት ደረጃ፣ መርሐግብር እና ካምፓስ በ2017 ዓ.ም የተመዘገቡ አዲስ ተማሪዎችን ዝርዝር ብቻ ከታህሳስ 1-15/ 2017 ዓ.ም በሶፍት እና በሀርድ ኮፒ እንዲልኩ ባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ አሳስቧል።

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

#ጥቆማ

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በጤና ሳይንስ ኮሌጅ በሁለተኛ ሴሚስተር በመደበኛ መርሐግብር ለአመልካቾች ክፍት የሆኑ ተጨማሪ የድኅረ-ምረቃ ፕሮግራሞችን ይፋ አድርጓል።

የሁለተኛ ዲግሪ ፕሮግራሞች፦
- MSc in Medicinal Chemistry
- MSc in Pharmaceutical Analysis
- MSc in Pharmacognosy

የሦስተኛ ዲግሪ ፕሮግራሞች፦
- PhD in Pharmacognosy
- PhD in Pharmaceutics
- PhD in Social & Administrative Pharmacy
- Sub-Specialty in pediatrics neurology

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የድኅረ-ምረቃ መግቢያ ፈተና ለመውሰድ የማመልከቻ ቀናት ከህዳር 23 እስከ ታህሳስ 11/2017 ዓ.ም እየተከናወነ እንደሚገኝ ይታወቃል።

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

#አቢሲንያ_ባንክ

ቀጣይ ዙር የጥያቄ እና መልስ ውድድር ቅዳሜ ህዳር 28 ከረፋዱ 4:30 በፌስቡክ ፔጃችን ላይ ይደረጋል። በየሳምንቱ አስር አሸናፊዎች ይሸለማሉ! ዛሬውኑ የፌስቡክ ፔጃችን በመቀላቀልና ቀላል ጥያቄዎችን በመመለስ ይሸለሙ!

የፌስቡክ ሊንክ 👇
https://www.facebook.com/BoAeth

አቢሲንያ የሁሉም ምርጫ!
#Facebook #giveaway #contest #Boa #bankinginethiopia #banksinethiopia #bankofabyssinia #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ

Читать полностью…

Tikvah-University

ለህንፃ የኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታ ስልጠና ፈላጊዎች ምዝገባ ላይ ነን።

🔔 ፈጥነው ይመዝገቡ!

👉 ተግባርን ከንድፈ ሀሳብ ያስተሳሰረ ስልጠና
👉 የሳተላይት ዲሽ መስመር ዝርጋታ በተጨማሪነት የሚሰጥበት 
👉ከትምህርት ቢሮ የCOC ምዘና የተዘጋጀለት

☎️   0906777799 / 0906777755
አድራሻ፦ ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ እና ቁ.2 መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ

Telegram: /channel/sagetraininginstitute
TikTok: sage_training_institute" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@sage_training_institute
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute

Читать полностью…

Tikvah-University

#ጥቆማ

5 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ኮደርስ ኢንሼቲቭ ነፃ ስልጠናን ለመከታተል ይመዝገቡ።

ዓለም አቀፍ ተቀባይነት ያለው ሰርትፍኬት ማግኘት የሚያስችልዎትን ስልጠና ይውሰዱ።

የስልጠና ዘርፎች፦

► ዌብ ፕሮግራሚንግ
► አንድሮይድ ማበልፀግ
► ዳታ ሳይንስ

ስልጠናውን በስምንት ሳምንት ያጠናቀቁ ሰልጣኞች ዓለም አቀፍ ተቀባይነት ያለው ሰርተፊኬት ይሰጣቸዋል።

ለመመዝገብ 👇
https://www.ethiocoders.et/

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

እውነትም ቅመም! ቅመም Itel Proን ዛሬውኑ ገዝተን ያለባትሪ ስጋት በሽ በሽ እንበል! ዛሬውኑ ወደ ሳፋሪኮም ሱቆች በማቅናት፣ ስልካችንን ገዝተን ለ90 ቀናት በሚቆይ 5ጊ.ባ. ወርሃዊ ጥቅል እና 1000 የሳፋሪኮም ደቂቃ ጉርሻ እናግኝ!

የቴሌግራም ቦታችንን /channel/official_safaricomet_bot በመጠቀም የአየር ሰዓት ወይም ልዩ ልዩ ጥቅሎችን እንግዛ!
  
🔗 የM-PESA ሳፋሪኮም መተግበሪያ በዚህ ሊንክ እናውርድ፦ https://play.google.com/store/apps/details?id=et.safaricom.mpesa.lifestyle

ስለ አገልግሎታችን ማንኛውም ጥያቄ ወይም መረጃ በቴሌግራም ቻናላችን /channel/Safaricom_Ethiopia_PLC 24/7 ማግኘት ይቻላል!

#MPESASafaricom #SafaricomEthiopia #1Wedefit #Furtheraheadtogether

Читать полностью…

Tikvah-University

አክሱም ዩኒቨርሲቲ በ2017 ዓ.ም የሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርት ለመማር ለተመደቡ አዲስ ተማሪዎች አድርጎት የነበረውን ጥሪ አራዝሟል።

ዩኒቨርሲቲው የ2017 ዓ.ም የሪሚዲያል ፕሮግራም አዲስ ገቢ ተማሪዎች የመግቢያ ቀናት ታህሳስ 1 እና 2/2017 ዓ.ም ብሎ የነበረ ቢሆንም፤ የመግቢያ ቀናት ላልተወሰነ ጊዜ የተራዘመ መሆኑን አሳውቋል።

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

ሦስት የደቡብ ክልል ዩኒቨርሲቲዎች ከክልል የጤና ሳይንስ ኮሌጆች የትምህርት ዕድል ተሰጥቷቸው በሚማሩ መምህራን ላይ ሕገወጥ ተግባር እየተፈተመባቸው መሆኑ ተሰማ።

ዩኒቨርሲቲዎቹ መምህራኑን ከትምህርት ገበታቸው ማገድ፣ በገንዘብ መደራደር እና መምህራኑ ትምህርታቸውን የጨረሱበትን ማስረጃ ባለመስጠት ሕገወጥ ድርጊት ላይ መሰማራታቸው ለሕ/ተ/ም/ቤት በቀረበ ጥቆማ ተገልጿል፡፡

ይህ የተገለጸው ባለፈው ሳምንት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሰባተኛ መደበኛ ስብሰባ፣ የጤና ሚኒስቴር የሥራ ኃላፊዎች ከምክር ቤት አባላት ለቀረባለቸው ጥያቄዎች ምላሽ ሲሰጡ መሆኑን ሪፖርተር ዘግቧል፡፡

አዳነ አደቶ (ዶ/ር) የተባሉ የምክር ቤት አባል ለጤና ሚኒስትሯ ዶ/ር መቅደስ ዳባ ባቀረቡበት ጥያቄ በሐዋሳ፣ በወላይታ ሶዶ እና በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ከክልል ጤና ሳይንስ ኮሌጆች የትምህርት ዕድል አግኝተው የሚማሩ መምህራን ላይ ሕገወጥ ተግባር እየተፈተመባቸው ነው ብለዋል፡፡

ሦስቱ ዩኒቨርሲቲዎች ከክልል ጤና ሳይንስ ኮሌጆች የትምህርት ዕድል ተሰጥቷቸው የሚማሩ መምህራንን ከትምህርት ገበታቸው እንዲታገዱ ማድረግ፣ በገንዘብ መደራደር እና ሌሎች ሕገወጥ ተግባሮች ላይ መሰማራታቸውን አስረድተዋል፡፡

ድርጊቱ የመልካም አስተዳደር ችግር ከመሆኑም በላይ የመንግሥትን ሥራ አደናቃፊ መሆኑን በማመን የሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ ከጤና ሚኒስቴር ጋር በመሆን ጉዳዩን እንዲያጣራ የም/ቤቱ አባል ጠይቀዋል፡፡

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ኃላፊ ዓለሙ ታምሶ እስካሁን በዩኒቨርሲቲው ይህንን ዓይነት ድርጊት ስለመኖሩ መረጃ የለኝም ብለዋል፡፡ ነገር ግን እንዲህ ዓይነት ድርጊት የሚፈፅሙ አካላት ካሉና ለፓርላማው የቀረበው ጥቆማ ተጨባጭ ከሆነ፤ ዩኒቨርሲቲው ድርጊቱን በፈፀሙ ግለሰቦች ላይ በፍጥነት ዕርምጃ እንደሚወስድ ለሪፖርተር አስረድተዋል፡፡

"በተለይ ይህንን ዓይነት ድርጊት የሚፈጽሙ ሰዎች ሕገወጥ መሆናቸው ታምኖበት ተጠያቂ እንዲሆኑ ይደረጋል" ያሉት ኃላፊው፤ አንድ መምህር ትምህርቱን በአግባቡ ከጨረሰ በኋላ የትምህርት ማስረጃ የማያገኝበት ምክንያት የለም ብለዋል፡፡

ሪፖርተር ከፓርላማ አባል የቀረበውን ጥያቄ መሠረት አድርጎ የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ እና የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ኃላፊዎችን በስልክ ለማግኘት ጥረት ቢያደርግም ሳይሳካ መቅረቱን ጠቁሟል፡፡ #ሪፖርተር

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

#MizanTepiUniversity

በ2017 ዓ.ም ለሪሚዲያል ፕሮግራም ሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁና ከዚህ በፊት በተላለፈው የጥሪ ጊዜ በተለያዩ ምክንያቶች መመዝገብ ያልቻላችሁ ተማሪዎች ህዳር 30 እና ታህሳስ 1/2017 ዓ.ም በአካል በመገኘት መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል፡፡

የምዝገባ ቦታ፦
- የማኅበራዊ ሳይንስ መስክ ተማሪዎች ሚዛን አማን ከተማ በሚገኘው ዋናው ግቢ፣
- የተፈጥሮ ሳይንስ መስክ ተማሪዎች ቴፒ ከተማ በሚገኘው ቴፒ ግቢ፡፡

ለምዝገባ ስትሐየዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦
- የ12ኛ ብሑራዊ ፈተና ውጤት፣
- ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
- ዘጠኝ የቅርብ ጊዜ 3x4 ጉርድ ፎቶግራፍ፣
- ብርድ ልብስ፣ አንሶላ፣ ትራስ ጨርቅ እና የስፖርት ትጥቅ፡፡

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

የግራፊክ ዲዛይን፣ ቪዲዮ ኢዲቲንግ፣ ሞሽን ግራፊክ እና ዲጂታል ማርኬቲንግ ስልጠና በፒያሣ እና መገናኛ ካምፓስ ምዝገባ ላይ ነን።

👉 100% በተግባር የተደገፈ ስልጠና
👉 Advanced Graphics + Video Editing + Motion Graphics + Digital Marketing በአንድ ላይ
👉 ከ50 በላይ ፕሮጀክቶች ያሉት
👉 የሥራ ላይ ስልጠና (Internship) የተመቻቸለት

☎️ 0906777799 / 0906777755
አድራሻ፦ ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ እና ቁ.2 መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ

Telegram: /channel/sagetraininginstitute
TikTok: sage_training_institute" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@sage_training_institute
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute

Читать полностью…

Tikvah-University

ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌኒየም ሜዲካል ኮሌጅ በኅብረተሰብ ጤና የማስተርስ ፕሮግራም (MPH) የ2017 ዓ.ም የእረፍት ቀናት መልካቾች ምዝገባ የሚካሔደው ህዳር 27 እና 28/2017 ዓ.ም መሆኑን አሳውቋል።

ገለፃ ህዳር 28/2017 ዓ.ም የሚሰጥ ሲሆን ትምህርት ህዳር 29/2017 ዓ.ም ይጀምራል ተብሏል።

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

#ArsiUniversity

በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና ወስዳችሁ የማለፊያ ውጤት በማምጣት አርሲ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ የመጀመሪያ ዲግሪ መደበኛ መረሐግብር ተማሪዎች የመግቢያ ቀናት ታህሳስ 1 እና 2/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦
- የ8ኛ ክፍል ውጤት ዋናውና ኮፒው፣
- ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
- የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
- ስድስት 3×4 ጉርድ ፎቶግራፍ፣
- አንሶላ፣ ትራስ ጨርቅ፣ ብርድ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ።

የምዝገባ ቦታ፦
- የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች በቦቆጂ ካምፓስ
- የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች በግብርና ኮሌጅ ካምፓስ

Note:
ለሪሚዲያል ፕሮግራም አርሲ ዩኒቨርሲቲ ለተመደባችሁ ተማሪዎች ወደፊት ጥሪ ይደረጋል ተብሏል።

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

ነጻ የትምህርት ዕድል

ባህርዳር ዩኒቨርሲቲ በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ የማጠቃለያ ፈተና ወስደው ከፍተኛ ውጤት (500 እና ከዛ በላይ ከ600) ያስመዘገቡ ተማሪዎችን ሙሉ ነጻ የትምህርት ዕድል በመስጠት በ2017 ዓ.ም በመደበኛ መርሐግብር ማስተማር ይፈልጋል፡፡

የማመልከቻ ጊዜ የሚያበቃው፡-
ታህሳስ 3/2017 ዓ.ም

ለማመልከት የሚያስፈልጉ፦
➭ የ12ኛ ክፍል ካርድ ውጤት ዋናውና ኮፒ፣
➭ የማመልከቻ ክፍያ 300.00 (ሦስት መቶ) ብር

የማመልከቻ ቦታ፦
በየአካዳሚክ ክፍል ባሉ ሬጅስትራር ጽ/ቤቶች

የትምህርት ፕሮግራም ምደባ ከሌሎች የመደበኛ ተማሪዎች ጋር በውድድር እንደሚመደቡ ዩኒቨርሲቲው ገልጿል፡፡

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ከብሪትሽ ካውንስል ጋር በመተባበር 5ኛ ዙር የእንግሊዘኛ ቋንቋ ምዘና ፈተና (IELTS Test) ሰጥቷል።

29 ተፈታኞች በወረቀት የተሰጠውን ምዘና ወስደዋል።

6ኛ ዙር የ IELTS ምዘና ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በመጪው የካቲት እንደሚሰጥ ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

በ2017 የትምህርት ዘመን አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች ቅበላ ረቡዕ ታህሳስ 2/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ምዝገባ ታህሳስ 3 እና 4/2017 ዓ.ም የሚከናወን ሲሆን፤ ትምህርት ታህሳስ 7/2017 ዓ.ም ይጀምራል ተብሏል፡፡

የምዝገባ ቦታ፦

- የተፈጥሮ ሳይንስ የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች አርባ ምንጭ ከተማ በሚገኘው አባያ ካምፓስ፣
- የስማችሁ የመጀመሪያ ፊደል ከ A እስከ R የሆናችሁ የማህበራዊ ሳይንስ የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች አርባ ምንጭ ከተማ በሚገኘው ጫሞ ካምፓስ፣
- የስማችሁ የመጀመሪያ ፊደል ከ S እስከ Z የሆናችሁ የማህበራዊ ሳይንስ የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች ሳውላ ከተማ በሚገኘው ሳውላ ካምፓስ

ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦
- ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት፣
- የ12ኛ ክፍል ሰርተፍኬት ዋናውና ሁለት ኮፒ፣
- አንሶላ፣ የትራስ ጨርቅ እና የስፖርት ትጥቅ፡፡

@tikvahuniversity

Читать полностью…
Subscribe to a channel