tikvahuniversity | Unsorted

Telegram-канал tikvahuniversity - Tikvah-University

308824

Subscribe to a channel

Tikvah-University

የቅድመ-ምረቃ ፕሮግራም ዕጩ ተመራቂዎች የመውጫ ፈተና የመጀመሪያ ቀን ፈተና በዛሬው ዕለት ሲሰጥ ውሏል።

ተፈታኞች በዛሬው መርሐግብር የአካውንቲንግ እና የአካውንቲንግና ፋይናንስ ትምህርት ፈተና ወስደዋል።

የመጀመሪያ ቀን ፈተና አሰጣጡ በርከት ባሉ ዩኒቨርሲቲዎች ስኬታማ የነበረ ቢሆንም፤ በተወሰኑ ዩኒቨርሲቲዎች ችግሮች እንደነበሩ ለቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ የደረሱ መረጃዎች ያሳያሉ።

ፈተናው ይጀመራል ከተባለበት ሰዓት ዘግይቶ መጀመር፣ የቴክኒክ ችግር እንዲሁም የመብራት መቋረጥ ችግር መከሰታቸውን ሰምተናል።

በሌላ በኩል እንደ ተንቀሳቃሽ ስልክ ያሉ ያልተፈቀዱ ነገሮችን ወደ ፈተና ማዕከል ይዘው ለመግባት የሞከሩ ተፈታኞች መያዛቸውም ታይቷል።

እስከ መጪው አርብ ጥር 30/2017 ዓ.ም የሚሰጠውን ፈተና፤ በድጋሚ የሚወስዱትን ጨምሮ በጠቅላላው 176 ሺህ ተማሪዎች እንደሚወስዱ ይጠበቃል።

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

የ2017 ዓ.ም አጋማሽ ዓመት የቅድመ-ምረቃ ፕሮግራም ዕጩ ተመራቂዎች የመውጫ ፈተና መሠጠት ጀምሯል።

ፈተናው ከዛሬ ጀምሮ እስከ ጥር 30/2017 ዓ.ም ድረስ ለአምስት ተከታታይ ቀናት ይሰጣል።

ተፈታኞች በዛሬው መርሐግብር የአካውንቲንግ እና የአካውንቲንግና ፋይናንስ ትምህርት ፈተና በመውሰድ ላይ ይገኛሉ።

ፈተናውን በድጋሚ የሚወስዱትን ጨምሮ በጠቅላላው 176 ሺህ ተማሪዎች የመውጫ ፈተናውን እንደሚወስዱ ይጠበቃል ሲል ትምህርት ሚኒስቴር መግለፁ ይታወቃል።

ምስል፦ ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

በ2017 ዓ.ም አጋማሽ ላይ የሚሰጠውን የቅድመ ምረቃ ፕሮግራሞች የመውጫ ፈተና ለመውሰድ 176 ሺህ ተማሪዎች ተመዝግበዋል።

ፈተናውን በድጋሚ የሚወስዱትን ጨምሮ በጠቅላላው 176 ሺህ ተማሪዎች የመውጫ ፈተናውን እንደሚወስዱ ይጠበቃል።

ፈተናው በኢትዮጵያ በሚገኙ በሁሉም የኒቨርሲቲዎች የሚሰጥ ሲሆን፤ ተጠሪነቱ ለትምህርት ሚኒስቴር ያልሆነው የመከላከያ ዩኒቨርሲቲ ውስጥም እንደሚሰጥ በትምህርት ሚኒስቴር የአካዳሚክ ጉዳዬች መሪ ሥራ አስፈጻሚ ኤባ ሚጀና (ዶ/ር) ለአሐዱ ራዲዮ ተናግረዋል።

የግል ኮሌጅ ተማሪዎችም በመረጡትና በአቅራቢያቸው በሚገኝ የመንግስት ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ፈተናቸውን ይወስዳሉ ብለዋል።

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

በሦስቱም ቅርንጫፎቻችን ( መገናኛ፣ ሜክሲኮ እና ጀሞ) እና በኦንላይን በምንሰጣቸው ስልጠናዎች በ Advanced Level እና 90% Practical በሆነ ካሪኩለምና ዘመኑ ያፈራቸውን የስቱዲዮ እቃዎች በማሟላት ከሁሉም ስልጠናዎቻችን ላይ ታላቅ የዋጋ ቅናሽ አድርገናል! አሁኑኑ ይመዝገቡና ትልቅ ለውጥ ወደሚያመጡበት ተቋም ይቀላቀሉ!

ከትምህርትና ስልጠና ጥራትና ቁጥጥር ባለስልጣን ሙሉ ዕውቅና ካለው ሰርተፊኬት ጋር! የብዙ ዓመት ልምድ እና ብቃት ባላቸው አሰልጣኞች!

🎯 Graphics Design
🎯 Video Editing
🎯 Digital Marketing
🎯 Photography
🎯 Videography
🎯 Cinematography
🎯 Adobe Photoshop
🎯 Full-stack Web App Development
🎯 Programming Language
🎯 Interior Design
🎯 English Language
🎯 Database
🎯 Basic Computer
🎯 Accounting Softwares
🎯 Engineering Softwares
🎯 SPSS & STATA
🎯 MS-Project
🎯  Foreign & Local Languages

አድራሻ፦
1. መገናኛ መተባበር ህንፃ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁ. 419 (ሊፍት ይጠቀሙ)  ☎️ 0991929303
2. ሜክሲኮ ኬኬር ህንፃ 6ኛ ፎቅ ቢሮ ቁ. 639 (ሊፍት ይጠቀሙ ሁለተኛውን ሊፍት) ☎️ 0991929304
3. ጀሞ 1 አንደኛ በር ካኩ ቢዝነስ ሴንተር 3ኛ ፎቅ ☎️ 0991926707

Telegram: /channel/topinstitutes

Читать полностью…

Tikvah-University

Management Exit Exam Full Day Schedule; AAU
Tuesday February 04, 2025 (ጥር 27/2017 ዓ.ም)

Читать полностью…

Tikvah-University

Artificial Intelligence and Data Science ስልጠና በፒያሣ እና በመገናኛ ካምፓስ ምዝገባ ላይ ነን!

👉 ከፍተኛ ልምድ ባላቸው መምህራን የሚሰጥ ስልጠና
👉 ንድፈ ሀሳብን ከተግባር ጋር በማዛመድ የሚሰጥ ስልጠና

☎️   0906777799 / 0906777755
አድራሻ፦
ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ እና ቁ.2 መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ

Telegram: /channel/sagetraininginstitute
TikTok: sage_training_institute" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@sage_training_institute
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute

Читать полностью…

Tikvah-University

ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ወደ M-PESA ዋሌታችን ገንዘብ በመላክ፥ በየትኛውም ሁኔታ በቀላሉ እንክፈል! እንገበያይ! በM-PESA ሁሉም ቀላል ነው!

#MPESASafaricom #FurtherAheadTogether

Читать полностью…

Tikvah-University

2ኛ ዙር መሰረታዊ የኮምፒውተር (Basic Computer) ስልጠና በፒያሣ እና በመገናኛ ካምፓስ ምዝገባ ላይ ነን።

👉 Microsoft Word, Excel, Access, Powerpoint, Publisher እና ሌሎች የኮምፒውተር አጠቃቀሞችን አካቶ የሚሰጥ ስልጠና
👉 ለሁለት ወር የሚቆይ ስልጠና

☎️   0906777799 / 0906777755
አድራሻ፦
ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ እና ቁ.2 መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ

Telegram: /channel/sagetraininginstitute
TikTok: sage_training_institute" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@sage_training_institute
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute

Читать полностью…

Tikvah-University

አሶሳ ዩኒቨርሲቲ በ2017 ዓ.ም ለአቅም ማሻሻያ ትምህርት (Remedial Program) የተመደቡለትን ተማሪዎች እየተቀበለ ነው።

ዩኒቨርሲቲው በትምህርት ሚኒስቴር ለተመደቡለት ሦስት ሺህ ለሚሆኑ የሪሚዲያል ተማሪዎች ጥር 22 እና 23/2017 ዓ.ም ሪፖርት እንዲያደርጉ ጥሪ ማስተላለፉ ይታወቃል።

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

🎁 ለሁላችን የሚሆን አዲስ ቅመም!

💨⚡️ እንደ ዋይፋይ 6 እና 3000 mah የባትሪ አቅም የመሳሰሉ አዳዲስ የቴክኖሎጂ ትሩፋቶችን ይዞ የመጣውን ልዩ ቅመም MIFIን ገዝተን ፈጣን 4G ኢንተርኔት እንጠቀም! ለ30 ቀን ከሚቆይ ነጻ 30ጊባ ዳታ ጉርሻ ጋር! በአንድ ግዜ እስከ 8 ሰው ድረስ ያስጠቅማል። 😋 ከሳፋሪኮም ጋር አንድ ወደፊት⚡️

🔗 የM-PESA ሳፋሪኮም መተግበሪያ በዚህ ሊንክ እናውርድ፦ https://play.google.com/store/apps/details?id=et.safaricom.mpesa.lifestyle

#MPESASafaricom #SafaricomEthiopia #1Wedefit #Furtheraheadtogether

Читать полностью…

Tikvah-University

#ጥቆማ

በኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር የተቋቋመው የሰብዓዊነት ትምህርት ቤት (School of Humanity) በመደበኛ መርሐግብር በሰብዓዊነት ትምህርት በዲፕሎማ ፕሮግራም ለአንድ ዓመት ፍላጎት ያላቸውን አመልካቾች ተቀብሎ ማስተማር ይፈልጋል፡፡

መስፈርቶች
➭ በማንኛውም የትምህርት መስክ የመጀመሪያ ዲግሪ ያለው/ያላት፣
➭ በሰብዓዊነት መስክ ለማገልገል ጥልቅ ፍላጎት ያለው/ያላት፣
➭ ዕድሜያቸው ከ20-40 ዓመት የሆኑ አመልካቾች ይበረታታሉ፣
➭ አመልካቾች ትምህርት ቤቱ የሚሰጠውን የፅሑፍ ፈተና ማለፍ ይጠበቅባቸዋል

የማመልከቻ ቦታ፦
ሳሪስ አደይ አበባ በሚገኘው የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር ግቢ

የማመልከቻ ጊዜ፦
ከጥር
22-30/2017 ዓ.ም

ለማመልከት ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

➭ የመጀመሪያ ዲግሪ ዋናውና ሁለት ኮፒ፣
➭ ስቱድንት ኮፒ ዋናውና ሁለት ኮፒ፣
➭ 2x3 የሆነ ሁለት ፎቶግራፍ፣

ክፍያን በተመለከተ ሳሪስ፣ አደይ አበባ በሚገኘው የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር ሰብዓዊነት ትምህርት ቤት ካምፓስ ሲገኙ መረጃ የሚያገኙ ይሆናል፡፡

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

#DebreBerhanUniversity

በ2017 ዓ.ም ለአቅም ማሻሻያ ትምህርት (Remedial Program) ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች ምዝገባ የካቲት 6 እና 7/2017 ዓ.ም እንደሚከናወን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

https://tinyurl.com/dbu-rcp-2017 ሊንክ ላይ በመግባትና የአድሚሽን ቁጥራችሁን በማስገባት የተመደባችሁበትን ግቢ ማወቅ የምትችሉ መሆኑ ተገልጿል።

ወደ ዩኒቨርሲቲው ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

➭ የ8ኛ ክፍል ውጤት ዋናውና ኮፒው፣
➭ የ12ኛ ክፍል ውጤት ዋናውና ኮፒው፣
➭ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
➭ አራት ፓስፖርት 3×4 ጉርድ ፎቶግራፍ፣
➭ ብርድ ልብስ፣ አንሶላ፣ ትራስ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ።

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

በኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር የተቋቋመው የሰብዓዊነት ትምህርት ቤት

የሰብዓዊነት ትምህርት ቤቱ (School of Humanity) በመጀመሪያ ዙር 50 ተማሪዎችን ተቀብሎ በዲፕሎማ ፕሮግራም ለማስተማር ዝግጅት አጠናቋል፡፡

በፕሮግራሙ አሥራ ሁለት ኮርሶች የሚሰጡ ሲሆን፤ ሞራል ኢቲክስ፣ ሂውማኒቴሪያን ዲፕሎማሲ፣ ኢንቫይሮመንታል ኤቲክስ ኮርሶች ተካተዋል፡፡ ኮርሶቹ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እና ሌሎችም ዩኒቨርሲቲዎች በተውጣጡ ምሁራን የተዘጋጁ ናቸው፡

በሰብዓዊነት ትምህርት ቤቱ ገብቶ ለመሠልጠን የሚፈልግ ሰው በማንኛውም የትምህርት መስክ የመጀመሪያ ዲግሪ ሊኖረው ይገባል ተብሏል፡፡

ትምህርት ቤቱ በዲፕሎማ ፕሮግራም ትምህርት መስጠት የሚጀምር ሲሆን፤ በቀጣይ በመጀመሪያ እና በሁለተኛ ዲግሪ ፕሮግራም ተማሪዎችን ተቀብሎ እንደሚያሰለጥን ተገልጿል፡፡

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

ዩኒቨርሲቲዎች የመውጫ ምዘና ላልወሰዱ መምህራን ማስረጃ እንዳይሰጡ ትምህርት ሚኒስቴር አሳሰበ፡፡

ሚኒስቴሩ ለዩኒቨርሲቲዎች እና ለክልል ትምህርት ቢሮዎች በጻፈው ደብዳቤ፥ የመውጫ ምዘና ላልወሰዱ መምህራን ማስረጃ እንዳይሰጥ አሳስቧል፡፡

በሚኒስቴሩ የመምህራን ትምህርት አመራሮች ልማት መሪ ሥራ አስፈጻሚ ሙሉቀን ንጋቱ (ዶ/ር) ከሳምንት በፊት የተጻፈው ደብዳቤ፥ "በክረምት መርሐግብር ከዲፕሎማ ወደ መጀመሪያ ዲግሪ ለመሸጋገር የትምህርት ማሻሻያ ስልጠና የሚከታተሉ መምህራን፣ ስልጠና ሳያጠናቅቁ መረጃ እየተሰጠ እንደሆነ" ደርሼበታለሁ ብሏል፡፡

በክረምት መርሐግብር ከዲፕሎማ ወደ መጀመሪያ ዲግሪ የትምህርት ደረጃ ለማሻሻል ስልጠና እየወሰዱ ያሉ መምህራን፣ የማስተማር ሙያ (PGDT) መውሰድና የመውጫ ምዘና ማጠናቀቅ እንዳለባቸው በመስከረም 2017 ዓ.ም የትምህርት ሚኒስቴር ማሳወቁን በደብዳቤው ገልጿል፡፡

ይሁን እንጂ አንዳንድ ክልሎች ከዚህ በተለየ የማስተማር ሙያ ስልጠናም ሆነ የመውጫ ምዘና ላልወሰዱ መምህራን፣ የደረጃ ዕድገት እየሰጡ መሆኑናቸውን መረዳቱን አሳውቋል፡፡

ማንኛውም ሠልጣኝ የትምህርት ማስረጃ ማግኘት የሚችለው የትምህርት ምዘና ወስዶ ማለፍ ሲችል መሆኑ እየታወቀ፣ የዲግሪ ትምህርታቸውን እንደጨረሱ በማድረግ የትምህርት ደረጃ ማሻሻያና የደረጃ ዕድገት የሚሰጡ አንዳንድ ተቋማት መኖራቸውን ሪፖርተር ያነጋገራቸው መሪ ሥራ አስፈጻሚው ተናግረዋል፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር ወጪያቸውን በመሸፈን የሚያስተምረው የበቁ መምህራንን ለማፍራት ነው ያሉት ኃላፊው፤ ማንኛውም ተቋም የመውጫ ምዘና ወስደው ላላለፉ ዕጩ መምህራን ምንም ዓይነት ማስረጃ እንዳይሰጥ በደብዳቤ ማሳወቁን አስረድተዋል፡፡ #ሪፖርተር

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

4ኛ ዙር የፋይናንስ እና ካፒታል ማርኬት ስልጠና በፒያሣ እና በመገናኛ ካምፓስ ምዝገባ ላይ ነን!

👉 ፈጥነው ይመዝገቡ!

የካፒታል ማርኬት ገበያ በኢትዮጵያ ተጀምሯል፡፡ እርስዎም በሴጅ ስልጠና ኢንስቲትዩት የሚሰጠውን የፋይናንስና ካፒታል ማርኬት ስልጠና በመውሰድ በገበያው ለመሳተፍ ራስዎን ያዘጋጁ፡፡

በብቁ መምህራን የሚሰጠው ስልጠናው፤ እንዴት አንድ ግለሰብ ወይም ተቋም ከስጋት ነጻ በሆነ መንገድ በገበያው ላይ መሳተፍ እንደሚችል ግልፅ ያደርጋል፡፡

ስልጠናውን ይውሰዱና ትግበራውን ይጠባበቁ!

☎️ 0906777799 / 0906777755
አድራሻ፦
ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ እና ቁ.2 መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ

Telegram: /channel/sagetraininginstitute
TikTok: sage_training_institute" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@sage_training_institute
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute

Читать полностью…

Tikvah-University

ዛሬ መሠጠት የተጀመረውን የቅድመ-ምረቃ ፕሮግራም ዕጩ ተመራቂዎች የመውጫ ፈተና በጥብቅ የፈተና ዲሲፕሊን እንዲሰጥ እያደረጉ መሆኑን ዩኒቨርሲቲዎች ገለፁ።

ወለጋ ዩኒቨርሲቲ ተፈታኞች ወደፈተና ማዕከላት ይዘው እንዳይገቡ የተከለከሉ ነገሮችን ፍተሻ በማድረግ መያዙን ገልጿል።

በዚህም ዩኒቨርሲቲው ኩረጃ እና ስርቆት የሚያግዙ ክልክል የቴክኖሎጂ ውጤቶችን ይዘው የተገኙ ተማሪዎችን ወደ መፈተኛ ክፍሎች እንዳይገቡ አድርጓል።

ምስል፦ ወለጋ ዩኒቨርሲቲ

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

8ኛ ዙር የዲጂታል ማርኬቲንግ ስልጠና በመገናኛ ካምፓስ የፊታችን ቅዳሜ የካቲት 01/2017 ዓ.ም ይጀመራል! 

👉 በሁለት ወር ምርጥ የዲጂታል ማርኬቲንግ ባለሙያ የሚያደርግዎት
👉 ንድፈ ሀሳብን ከተግባር ጋር ያስተሳሰረ ስልጠና

☎️  0906777799 / 0906777755
አድራሻ፦ ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ እና ቁ.2 መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ

የበለጠ ይጠብቁ ...
💥 ሴጅ ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት 💥

Telegram: /channel/sagetraininginstitute
TikTok: sage_training_institute" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@sage_training_institute
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute

Читать полностью…

Tikvah-University

#ExitExamSchedule

ሀገር አቀፍ የመውጫ ፈተና ከጥር 26-30/2017 ዓ.ም ጀምሮ እንደሚሰጥ ይታወቃል፡፡

የፈተናው ሙሉ መርሐግብር (የሚሰጡ ፈተናዎች ዝርዝር፣ የፈተና ቀንና ሰዓት፣ የመፈተኛ ማዕከላት እንዲሁም የተፈታኞች ዝርዝር) ከላይ ተያይዟል፡፡

እሑድ የካቲት 2/2017 ዓ.ም ጠዋት የኢኮኖሚክስ ትምህርት የመውጫ ፈተና በአምቦ እና በወለጋ ዩኒቨርሲቲዎች እንደሚሰጥም መርሐግብሩ ያሳያል፡፡

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

#ExitExamSchedule #AAU

ሀገር አቀፍ የመውጫ ፈተና ከሰኞ ጥር 26/2017 ዓ.ም ጀምሮ እንደሚሰጥ ይታወቃል፡፡

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የመውጫ ፈተና ለመፈተን የተመዘገባችሁ የፈተናው የመጀመሪያ ሁለት ቀናት መርሐግብር (ጥር 26 እና 27/2017 ዓ.ም) ከላይ ተያይዟል።

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

Accounting Exit Exam Full Day Schedule; AAU
Monday February 03, 2025 (ጥር 26/2017 ዓ.ም)

Читать полностью…

Tikvah-University

#ጥቆማ

ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በማንኛውም የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲ ተመድበው "የጀማሪ መርሐግብር የቅድመ ምህንድስና ትምህርታቸውን ካጠናቀቁ" ተማሪዎች መካከል በዘርፉ የተሻለ ክህሎትና ዝንባሌ ያላቸውን ተማሪዎች #በዝውውር ተቀብሎ #በመጀመሪያ_ዲግሪ ማስተማር ይፈልጋል።

በዝውውር ቅበላ የሚደረግባቸው የትምህርት መስኮች፦

1. ፋሽን ኢንጂነሪንግ (Fashion Engineering)
2. ቴክስታይል ኢንጂነሪንግ (Textile Engineering)
3. ቆዳ ውጤቶች ኢንጂነሪንግ (Leather Products Engineering)
4. ቴክስታይል ኬሚካል ፕሮሰስ ኢንጂነሪንግ (Textile Chemical Processing Engineering )

የትምህርት ካምፓስ፦
በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ቴክስታይል እና ፋሽን ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት

ለማመልከት፦
https://forms.gle/gSypn17ttmm8k4746

ለተጨማሪ መረጃ:-
0938882020 / 0918187249

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

5 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ኮደርስ ኢንሼቲቭ ነጻ ስልጠናን ይከታተሉ!

በሀገር አቀፍ ደረጃ 460 ሺህ ሰዎች የኢትዮጵያን ኮደርስ ስልጠና እየወሰዱ ሲሆን፤ 130 ሺህ ሰዎች ስልጠናውን በማጠናቀቅ ሰርትፍኬት መውሰዳቸውን የኢኖቬሽና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ገልጿል፡፡

የስልጠና ኮርሶች፦

► ዳታ ሳይንስ
► ፕሮግራሚንግ ፋንዳሜንታል
► አንድሮይድ ፕሮግራሚንግ

ስልጠናው የሚሰጠው ዓለም አቀፍ የዲጂታል ክህሎቶችን በኦንላይን በማስተማር ከሚታወቀው ዩዳሲቲ ተቋም ጋር በመተባበር ነው፡፡

ስልጠናውን በስምንት ሳምንት ያጠናቀቁ ሰልጣኞች ዓለም አቀፍ ተቀባይነት ያለው ሰርተፊኬት ይሰጣቸዋል።

ለመመዝገብ 👇
https://www.ethiocoders.et/

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

"በዳግም ምዝገባው ሒደት በራሳቸው ፈቃድ ሳይመዘገቡ የቀሩ እንጂ እኔ ሔጄ የዘጋሁት ተቋም የለም።" - የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን

ባለሥልጣኑ ባወጣው “አዲስ ስታንዳርድ” መሰረት ዳግም ምዝገባ እንዲያደርጉ ባለፈው መስከረም ለግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጥሪ ማድረጉ ይታወቃል።

በተቀመጠላቸው የጊዜ ገደብ ሰነዶቻቸውን ያልላኩ ተቋማት ከዘርፉ በራሳቸው ፈቃድ እንደወጡ ይቆጠራል መባሉ ይታወሳል፡፡

በዚህ ሒደት 84 ተቋማት ለዳግም ምዝገባው ሰነዶቻቸውን ሳይልኩ በመቅረታቸው እንደተሰረዙ ተነግሯል፡፡

273 ተቋማት ደግሞ ሰነዶቻቸው ወደ ባለሥልጣኑ ቢልኩም የሚፈለጉትን ሰነዶች በሙሉ ያሟላ አንድም ተቋም አለመገኘቱን በባለሥልጣኑ የፈቃድ አሰጣጥ እና የጥራት ኦዲት ም/ዋና ዳይሬክተር ውብሸት ታደለ ለሸገር ኤፍኤም ተናግረዋል።

እነዚህ ሰነድ ያጓደሉ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማትም ሰነዶቻቸውን እንዲያሟሉ ተጨማሪ 45 ቀን የጊዜ ገደብ እደተሰጣቸውም ገልፀዋል፡፡

ሰነዶቻቸውን ካልላኩ 84 ተቋማት ውጪ ባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ ያገደውም ሆነ የሰረዘው ተቋም እንደሌለ አንስተዋል፡፡

ከእነዚህ መካካል የተለያየ ምክንያት በማቅረብ ድጋሚ ዕድል እንዲሰጣቸው የጠየቁ ተቋማት መኖራቸውንና ጥያቄያቸውም እየታየ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

የዳግም ምዝገባ ሥራው በሒደት ላይ ሲሆን፤ በአሁን ሰዓት የሰነድ ማጣራት ሥራ እየተከወነ እንደሚገኝና በመጪዎቹ ሳምንታት ሰነድ ያሟሉ ተቋማት የመስክ ምልከታ በአዲስ አበባ እና በክልል እንደሚደረግ ጠቅሰዋል፡፡ ከመስክ ምልከታው በኋላ የተቋማቱ የመዘጋት ወይም የመቀጠል ዕጣ ፈንታ ይወሰናል ተብሏል፡፡ #ShegerFM

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

ወራቤ ዩኒቨርሲቲ በ2017 ዓ.ም ለአቅም ማሻሻያ ትምህርት (Remedial Program) የተመደቡለትን ተማሪዎች እየተቀበለ ነው።

ዩኒቨርሲቲው የሪሚዲያል ተማሪዎች ጥር 21 እና 22/2017 ዓ.ም ሪፖርት እንዲያደርጉ ጥሪ ማስተላለፉ ይታወቃል።

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

#DebreMarkosUniversity

በ2017 ዓ.ም ለአቅም ማሻሻያ ትምህርት (Remedial Program) ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች ምዝገባ ጥር 28 እና 29/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

የምዝገባ ቦታ፦
➭ የስማችሁ የመጀመሪያ ፊደል ከA-H የሆነ የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች በቡሬ ካምፓስ
➭ የስማችሁ የመጀመሪያ ፊደል ከA-E የሆነ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች በቡሬ ካምፓስ
➭ ሌሎቻችሁ የማኅበራዊ እና የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች በዋናው ካምፓስ

ወደ ዩኒቨርሲቲው ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

➭ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
➭ የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል ውጤት ካርድ ዋናውና ኮፒው፣
➭ አራት 3×4 ጉርድ ፎቶግራፍ፣
➭ ብርድ ልብስ፣ አንሶላ እና ትራስ ልብስ፡፡

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

2ኛ ዙር የኮምፒውተር ጥገና እና ኔትዎርኪንግ (Computer Maintenance and Networking) ስልጠና በፒያሣ እና በመገናኛ ካምፓስ ምዝገባ ላይ ነን።

👉 ንድፈ ሀሳብን ከተግባር ጋር በማዛመድ የሚሰጥ ስልጠና
👉 የሥራ ላይ ስልጠና (Internship) የተመቻቸለት

☎️   0906777799 / 0906777755
አድራሻ፦
ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ እና ቁ.2 መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ

Telegram: /channel/sagetraininginstitute
TikTok: sage_training_institute" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@sage_training_institute
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute

Читать полностью…

Tikvah-University

"የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ ከቀጣይ ዓመት ጀምሮ የተማሪዎች የከፍተኛ ትምህርት ዩኒቨርሲቲ ምርጫ ውስጥ ይገባል።" - ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር)

የትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች በዩኒቨርሲቲው ጉብኝት አድርገዋል።

በዚህም ዩኒቨርሲቲው የበለጠ ውጤታማ እንዲሆን በጥናት ላይ የተመሰረተ ድጋፍ እንደሚደረግ የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ ከ2018 ዓ.ም ጀምሮ የተማሪዎች የከፍተኛ ትምህርት ዩኒቨርሲቲ ምርጫ ውስጥ እንደሚካተትም ጠቁመዋል። #ENA

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

በሦስቱም ቅርንጫፎቻችን ( መገናኛ፣ ሜክሲኮ እና ጀሞ) እና በኦንላይን በምንሰጣቸው ስልጠናዎች በ Advanced Level እና 90% Practical በሆነ ካሪኩለምና ዘመኑ ያፈራቸውን የስቱዲዮ እቃዎች በማሟላት ከሁሉም ስልጠናዎቻችን ላይ ታላቅ የዋጋ ቅናሽ አድርገናል! አሁኑኑ ይመዝገቡና ትልቅ ለውጥ ወደሚያመጡበት ተቋም ይቀላቀሉ!

ከትምህርትና ስልጠና ጥራትና ቁጥጥር ባለስልጣን ሙሉ ዕውቅና ካለው ሰርተፊኬት ጋር! የብዙ ዓመት ልምድ እና ብቃት ባላቸው አሰልጣኞች!

🎯 Graphics Design
🎯 Video Editing
🎯 Digital Marketing
🎯 Photography
🎯 Videography
🎯 Cinematography
🎯 Adobe Photoshop
🎯 Full-stack Web App Development
🎯 Programming Language
🎯 Interior Design
🎯 English Language
🎯 Database
🎯 Basic Computer
🎯 Accounting Softwares
🎯 Engineering Softwares
🎯 SPSS & STATA
🎯 MS-Project
🎯  Foreign & Local Languages

አድራሻ፦
1. መገናኛ መተባበር ህንፃ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁ. 419 (ሊፍት ይጠቀሙ)  ☎️ 0991929303
2. ሜክሲኮ ኬኬር ህንፃ 6ኛ ፎቅ ቢሮ ቁ. 639 (ሊፍት ይጠቀሙ ሁለተኛውን ሊፍት) ☎️ 0991929304
3. ጀሞ 1 አንደኛ በር ካኩ ቢዝነስ ሴንተር 3ኛ ፎቅ ☎️ 0991926707

Telegram: /channel/topinstitutes

Читать полностью…

Tikvah-University

📣 ለሁሉም ፍሬሽማኖች እኛ ጋር መልስ አለ!

📚 ፈተና ደርሶ ሞጁል ለመጨረስ ያለው ጥድፊያ ከሰለቻችሁ ሰፊ የአማርኛ ማብራሪያ ማስታወሻዎች እኛ ጋር ታገኛላችሁ።
✍️ ማጥናት በቃኝ ጥያቄ ብቻ ልስራ ካላችሁም እያንዳንዱን ምዕራፍ በደንብ መረዳታችሁን የሚፈትኑ ጥያቄዎች ከመልስ እና ማብራሪያቸው ጋር ታገኛላችሁ።
🚀 የበፊት ፈተናዎችን ከነመልሶቻቸው ከፈለጋችሁም ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች የተሰበሰቡ የMid-Term እና Final ፈተናዎችን እኛ ጋር ታገኛላች።

ሁሉንም www.zegju.com ላይ በ250 ብር ብቻ ታገኛላችሁ!

📞 ለበለጠ መረጃ 0928665592 ወይም @zegjusupport ቴሌግራም ላይ አነጋግሩን።

እንዴት መመዝገብ እንደምትችሉ ለማየት 👇
/channel/ZegjuExamPrep

አሁኑኑ www.zegju.com ላይ ይመዝገቡ!

Читать полностью…

Tikvah-University

#Scholarship_Opportunity

ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ፣ አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ፣ አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እና ኖርዌጂያን ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በጋራ ባላቸው የ Ethiopian Norwegian Network in Computational Mathematics (ENNCoMat) ፕሮጀክት በ2018 ዓ.ም በመደበኛው መርሐግብር ከዚህ በታች በተጠቀሱት ፕሮግራሞች በሁለተኛ ዲግሪ ተማሪዎች ተቀብሎ ማስተማር ይፈልጋል፡፡

1. Master of Science in Mathematical Modelling
ፕሮግራሙ የሚሰጥበት ቦታ፦ Arba Minch University
ብዛት - 1
2. Master of Science Degree in Applied Mathematics
ፕሮግራሙ የሚሰጥበት ቦታAdama Science and Technology University
ብዛት - 1
3. Master of Science in Computational Mathematics
ፕሮግራሙ የሚሰጥበት ቦታ፦ Hawassa University
ብዛት - 1

ኖርዌይ በሚገኘው ተባባሪ የኒቨርሲቲ ከ6-10 ወር ድረስ የሚሰጠውን የትምህርት ስልጠና ለመውስድ ፍቃደኛ የሆናችሁ አመልካቾች ለጉዞ የሚያስፈልጉ ዶክመንቶች እስከ የካቲት 30/2017 ዓ.ም ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባችኋል፡፡ (ዝርዝር የማመልከቻ መስፈርቶች ከላይ በምስል ተያይዟል፡፡)

ማሳሰቢያ
አመልካቾች እስከ ጥር 30/2017 ዓ.ም የማመልከቻ ፎርሙን በሚከተለው ቅጽ https://forms.gle/YLBoy38hQT2Sgxfs6 ላይ በመግባት መረጃዎችን መሙላት ይጠበቅባችኋል። ምዝገባው የሚከናወነው በኦንላይን ብቻ ነው፡፡

የመግቢያ ፈተና የሚሰጥበት ቀን በቀጣይ የሚገለፅ ይሆናል።

የመግቢያ መስፈርቱን አሟልተው ያለፉ ተማሪዎች ኖርዌይ ሄደው በሚማሩበት ጊዜ የሚኖሩበትንና የትራንስፖርት ወጪዎችን በውሉ መሰረት ፕሮጀክቱ የሚሸፍን ይሆናል።

የመግቢያ መስፈርቱን አሟልተው ያለፉ ተማሪዎች ሀገር ውስጥ በሚኖሩበት ወቅት ስፖንሰር የሌላቸው ከሆነ አነስተኛ የኪስ ገንዘብ፣ የወጪ መጋራት ክፍያ፣ የትምህርት ወጪዎችና የምርምር ወጪዎችን ፕሮጀክቱ የሚሸፍን ይሆናል። (ዝርዝር መረጃ ከላይ በምስል ተያይዟል፡፡)

@tikvahuniversity

Читать полностью…
Subscribe to a channel