tikvahuniversity | Unsorted

Telegram-канал tikvahuniversity - Tikvah-University

308824

Subscribe to a channel

Tikvah-University

የተለያዩ የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች በልዩ ልዩ የትምህርት መስኮች ያስተማሯቸውን ተማሪዎች የካቲት 15 እና 16/2017 ዓ.ም ያስመርቃሉ።

አምቦ ዩኒቨርሲቲ፣ ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ፣ ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ፣ እና ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ በሳምንቱ መጨረሻ ተማሪዎቻቸውን ከሚያስመርቁ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መካከል ይገኙበታል፡፡

ተቋማቱ በቅድመ-ምረቃ እና በድኅረ-ምረቃ ፕሮግራሞች ያስተምሯቸውን ተማሪዎች ያስመርቃሉ።

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

20ኛ ዙር የድረ-ገጽ እና ሞባይል መተግበሪያ ማበልፀግ (Full-Stack Website and Mobile Application Development) ስልጠና በፒያሣ እና በመገናኛ ካምፓስ በምዝገባ ላይ ነን።   

👉 ተግባርን ከንድፈ ሀሳብ ያስተሳሰረ ስልጠና
👉 ፕሮግራሚንግ ትምህርቶችን አካቶ የሚሰጥ
👉 Front-end እና Back-end በአንድ ላይ እስከ Deployment ያካተተ
👉 በተግባር ድረ-ገጾች እና ሞባይል መተግበሪያዎችን እያበለፀጉ የሚሰለጥኑበት
👉 የሥራ ላይ ስልጠና (Internship) የተመቻቸለት

☎️   0906777799 / 0906777755
አድራሻ፦
ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ እና ቁ.2 መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ

Telegram: /channel/sagetraininginstitute
TikTok: sage_training_institute" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@sage_training_institute
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute

Читать полностью…

Tikvah-University

ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች በቅድመ-ምረቃ እና በድኅረ-ምረቃ ፕሮግራሞች ያስተማራቸውን 343 ተማሪዎች ዛሬ ያስመርቃል፡፡

ከተመራቂዎቹ 76ቱ በድኅረ-ምረቃ ፕሮግራም ትሀምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቀቁ ናቸው፡፡

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

41ኛ ዙር የግራፊክ ዲዛይን፣ ቪዲዮ ኤዲቲንግ፣ ሞሽን ግራፊክ እና ዲጂታል ማርኬቲንግ ስልጠና በፒያሣ እና በመገናኛ ካምፓስ በምዝገባ ላይ ነን!

👉 ተግባርን ከንድፈ ሀሳብ ያስተሳሰረ ስልጠና
👉 Advanced Graphic + Video Editing + Motion Graphic + Digital Marketing በአንድ ላይ
👉 ከ50 በላይ ፕሮጀክቶች ያሉት
👉 የሥራ ላይ ስልጠና (Internship) የተመቻቸለት

☎️   0906777799 / 0906777755
አድራሻ፦
ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ እና ቁ.2 መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ

Telegram: /channel/sagetraininginstitute
TikTok: sage_training_institute" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@sage_training_institute
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute

Читать полностью…

Tikvah-University

የወለጋ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኢንስቲትዩት የመውጫ ፈተና ያስፈተናቸው ተማሪዎቹ ከፍተኛ ውጤት ማስመዝገባቸውን አሳውቋል፡፡

በዚህም ኢንስቲትዩቱ ያስፈተናቸው የአንስቴዥያ፣ ሚድዋይፈሪ፣ ሜዲካል ላብራቶሪ ሳይንስ እና ፋርማሲ ተፈታኞች በሙሉ የማለፊያ ውጤት ማምጣታቸውን ግልጿል፡፡

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌኒየም ሜዲካል ኮሌጅ በ2017 አጋማሽ ዓመት የመውጫ ፈተና ካስፈተናቸው የሕክምና ተማሪዎች መካከል 98 በመቶ ተፈታኞች የማለፊይ ውጤት ማምጣታቸውን ገልጿል።

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

21ኛ ዙር ሙሉ የሒሳብ መዝገብ አያያዝ (Modern Accountancy) ስልጠና በፒያሣ እና በመገናኛ ካምፓስ ምዝገባ ላይ ነን። 

👉 ተግባርን ከንድፈ ሀሳብ ያስተሳሰረ ስልጠና
👉 መሠረታዊ አካውንቲንግ እና ኦዲት አሰራር፣ ሙሉ የአካውንቲንግ ሒሳብ አሰራር በፒስቺሪ ተደግፎ እና የግብር አያያዝ ትምህርቶችን አካቶ የሚሰጥ
👉 የሥራ ላይ ስልጠና (Internship) የተመቻቸለት

☎️   0906777799 / 0906777755
አድራሻ፦
ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ እና ቁ.2 መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ

Telegram: /channel/sagetraininginstitute
TikTok: sage_training_institute" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@sage_training_institute
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute

Читать полностью…

Tikvah-University

ወለጋ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያስተማራቸውን 2,717 ተማሪዎች አስመርቋል።

የተቋሙ 19ኛ ዙር ተመራቂዎች በመደበኛ እና በተከታተይ የትምህርት መርሐግብር በመጀመሪያ ዲግሪ፣ በሁለተኛ ዲግሪ እና በሦስተኛ ዲግሪ በተቋሙ ሦስት ካምፓሶች ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ መሆናቸው ተገልጿል።

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

ክፍያቸውን ለፈፀሙ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመውጫ ፈተና ውጤት ዛሬ ተለቋል።

በግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የ2017 ዓ.ም አጋማሽ ዓመት የመውጫ ፈተና የወሰዱ ተፈታኞች ውጤት ሳይለቀቅ መዘግየቱይታወቃል።

ለመጀመሪያ ጊዜ የመውጫ ፈተና የሚወስዱ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተፈታኞችን ክፍያ የሚፈፅሙት ተቋማት ክፍያቸውን ሳያደርጉ በመዘግየታቸው የተፈታኞቹ ውጤት ሳይለቀቅ ቆይቷል።

ተቋማቱ ክፍያውን በመፈፀማቸው የተማሪዎቹ ውጤት ዛሬ ለየተቋማቱ መለቀቁን የኢትዮጵያ የግል ከፍተኛ ትምህርት እና ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋማት ማህበር ለቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ገልጿል።

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

ሰላሌ ዩኒቨርሲቲ በጤናው ዘርፍ በመጀመሪያ እና ማስተርስ ዲግሪ ፕሮግራሞች ያሰለጠናቸውን 339 ተማሪዎች አስመርቋል።

ተመራቂዎቹ 232 በሁለተኛ ዲግሪ እና 107 በመጀመሪያ ዲግሪ በጤና ሳይንስ መስክ መሆናቸው ተገልጿል።

ዩኒቨርሲቲው በተጨማሪም በ Higher Diploma Program ስልጠናቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ 28 መምህራን በዛሬው ዕለት አስመርቋል።

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 612 ተማሪዎችን ዛሬ አስመርቋል።

ከተመራቂዎቹ መካከል 223 በድኅረ-ምረቃ ፕሮግራም ትምህርታቸውን የተከታተሉ ሲሆኑ፤ ቀሪዎቹ 389 ተማሪዎች በመደበኛ፣ በተከታታይ እና በክረምት መርሐግብሮች በመጀመሪያ ዲግሪ የተመረቁ ናቸው።

127 ተማሪዎች በህክምና ትምህርት የተመረቁ መሆናቸው ተገልጿል።

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

ጎንደር ዩኒቨርሲቲ 366 የሕክምና ተማሪዎችን አስመርቋል።

ዩኒቨርሲቲው ዛሬ ያስመረቃቸው ተማሪዎች በተለያዩ የትምህርት መስኮች ከመጀመሪያ ዲግሪ እስከ ሦስተኛ ዲግሪ መርሐ ግብር ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩ ናቸው።

ዩኒቨርሲቲው የሕክምና ተማሪዎችን ሲያስመርቅ ይህ ለ40ኛ ጊዜ ነው።

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

ፒስቺሪ አካውንቲንግ ስልጠና በፒያሣ እና በመገናኛ ካምፓስ ምዝገባ ላይ ነን! 

👉 ንድፈ ሀሳብን ከተግባር ያስተሳሰረ ስልጠና
👉 በፒስቺሪ ላይ የሚሰጥ
👉 የሥራ ላይ ስልጠና (Internship) የተመቻቸለት

☎️   0906777799 / 0906777755
አድራሻ፦
ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ እና ቁ.2 መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ

Telegram: /channel/sagetraininginstitute
TikTok: sage_training_institute" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@sage_training_institute
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute

Читать полностью…

Tikvah-University

ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ባለፈው ሳምንት የመውጫ ፈተና ካስፈተናቸው አጠቃላይ ተማሪዎች ውስጥ 87 በመቶ የሚሆኑትን የማለፊያ ውጤት ማምጣታቸውን ገልጿል፡፡

ዩኒቨርሲቲው በ35 ፕሮግራሞች 1,481 ተማሪዎችን የአጋማሽ ዓመት ሀገር አቀፍ የመውጫ ፈተና አስፈትኗል።

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ባለፈው ሳምንት የተሰጠውን የመውጫ ፈተና ከወሰዱ መደበኛ ተማሪዎቹ መካከል 98 በመቶ ተፈታኞች የማለፊያ ውጤት (ከ50 በላይ) ማምጣታቸውን ገልጿል፡፡

የኤክስቴንሽን፣ የክረምት እና በድጋሜ የመውጫ ፈተናውን ከወሰዱ ተፈታኞቹ መካከል ደግሞ 77 በመቶዎቹ የማለፊያ ውጤት ማግኘታቸውን ዩኒቨርሲቲው ጠቁሟል፡፡

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

ሚዛን ኢንስቲትዩት ኦፍ ቴክኖሎጂ በሦስት ዙር ቴክኖሎጂ ነክ በሆኑ ኮርሶች ያሰለጠናቸውን 127 ተማሪዎች አስመርቋል።

ተመራቂዎቹ በዌብ ዲቨሎፕመንት፣ በሞባይል አፕ ዲቨሎፕመንት፣ በግራፊክስ ዲዛይን፣ በዲጂታል ማርኬቲንግ፣ በቪዲዮ ኤዲቲንግ፣ በቤዚክ ኮምፒውተር ስኪል እና በዳታ ሳይንስ መስኮች ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ ናቸው።

ተማሪዎቹም በመደበኛ፣ በማታ እና በእረፍት ቀናት በአካል እና በኦንላይን ትምህርታቸውን መከታተላቸውን የኢንስቲትዩቱ ሥራ አስኪያጅ አህመድ ሙሀመድ ገልፀዋል።

በ2014 ዓ.ም የተቋቋመው ኢንስቲትዩቱ እስካሁን ከ300 በላይ ተማሪዎችን ከ 2-9 ወር በሚሰጡ ኮርሶች በሰባት ዙር ማስመረቁን ሥራ አስኪያጁ ጠቁመዋል።

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

የመውጫ ፈተና ውጤት መለቀቅን ተከትሎ በርካታ የኮምፕርሄንሲቭ ነርሲንግ ተፈታኞች ቅሬታቸውን ለቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ልከዋል፡፡

"ፈተናው ከብሉ ፕሪንት ውጪ ነው የመጣው" የሚሉት ተፈታኞቹ፤ እርማቱ በድጋሜ ሊታይ ይገባል ሲሉ ይጠይቃሉ፡፡

በጉዳዩ ላይ ትምህርት ሚኒስቴርን ያነጋገርን ሲሆን፤ ከኮምፕርሄንሲቭ ነርሲንግ ፈተና ጋር የተያያዘ ምንም አይነት ቅሬታ ለተቋሙ #አለመድረሱን ሚኒስቴሩ ጠቁሟል፡፡

በውጤታቸው ላይ ቅሬታ ያላቸው ተፈታኞች በትምህርት ሚኒስቴር ውስጥ ለሚገኘው የቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ ማቅረብ እንደሚችሉም ተቋሙ ገልጿል፡፡

በሌላ በኩል ውጤታቸውን ለማየት የተቸገሩ የግል (በድጋሜ) ተፈታኞች፣ ውጤታቸው ወደተፈተኑበት ተቋም የተላከ በመሆኑ ወደተቋማቱ በመሔድ ውጤታቸውን ማየት እንደሚችሉ ሚኒስቴሩ አስረድቷል፡፡

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

የተባበሩት መንግሥታት የዘላቂ ልማት መፍትሔ ጥምረት (SDSN) የአፍሪካ ማዕከል በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከፍቷል፡፡

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተከፈተው የጥምረቱ ማዕከል የጥናትና ምርምር ሥራዎችን በማከናወን ለፖሊሲ አውጪዎች ግብዓት የሚሆኑ ሳይንሳዊ መፍትሔዎችን ያቀርባል ተብሏል።

የማዕከሉ መከፈት ተጨማሪ አቅም እንደሚፈጥር እና በትብብር ለአፍሪካዊ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሄዎችን ለመቅረፅ የራሱን አበርክቶ እንደሚወጣ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተ/ፕሬዝዳንት ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር) ገልፀዋል፡፡

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

#Exit_Exam_Result

የ2017 አጋማሽ ዓመት የመውጫ ፈተና (Exit Exam) ውጤት ኦንላይን የመመልከቻ ሊንክ መስራት ጀምሯል።

https//:result.ethernet.edu.et ላይ በመግባት ExitExam የሚለውን በመምረጥና የራስዎን User Name በማስገባት ውጤትዎን መመልከት ይችላሉ።

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ በቅርቡ ሥራ ያስጀመረው የመሀል-ሜዳ ካምፓስ ትምህርት መስጠት ጀምሯል፡፡

በቅርቡ ተማሪዎችን የተቀበለው ካምፓሱ፤ የመጀመሪያ ቀን የመጀመሪያ የትምህርት ክፍለ-ጊዜ ዛሬ አካሒዷል።

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

#TVTI_Exit_Exam

የመውጫ ፈተና የምትወስዱ የፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ሰልጣኞች በኦንላይን የምዝገባ ጊዜ ዛሬ ያበቃል።

ተከታዩን ማስፈንጠሪያ በመጫን የምታገኙትን ቅፅ በመሙላት ምዝገባ ያድርጉ 👇
https://forms.office.com/r/3KgnK1esuc

ኦንላይን መመዝገብ የማትችሉ አመልካቾች በኢንስቲትዩቱ ዋናው ግቢ በመገኘት በየትምህርት ክፍላችሁ መመዝገብ ትችላላችሁ ተብሏል።

🔔 የምዝገባ ጊዜው ዛሬ የካቲት 10/2017 ዓ.ም ያበቃል።

የመውጫ ፈተናውን #በድጋሜ ለምትወስዱ ተፈታኞች ፈተናው በኢንስቲትዩቱ ዋና ግቢ እና በአዲስ አበባ በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ይሰጣል።

የመዝገባ ብር 500 በኢንስቲትዩቱ የንግድ ባንክ አካውንት በማስገባት ክፍያ በመፈፀም ደረሰኝ መያዝ ይጠበቅባችኋል።

✍ የምዝገባ ጥሪው በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ቴክስታይልና ፋሽን ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የጋርመንት ቴክኖሎጂ ሰልጣኞችንም ይመለከታል።

የመውጫ ፈተናው ከመጋቢት 6-11/2017 ዓ.ም ባለው ጊዜ እንደሚሰጥ ኢንስቲትዩቱ ገልጿል።

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ዱራሜ ካምፓስ በመደበኛ እና በተከታታይ የትምህርት ፕሮግራም በመጀመሪያ ዲግሪ ያሰለጠናቸውን 395 ተማሪዎች ዛሬ አስመርቋል።

በዱራሜ ካምፓስ በመደበኛ እና በተከታታይ የትምህርት መርሐግብር በተሰጠው የመውጫ ፈተና 79 በመቶ ተፈታኞች የማለፊያ ውጤት ማምጣታቸውን የዱራሜ ካምፓስ ቺፍ ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር ዘውዱ ክፍሌ ገልፀዋል።

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

ሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያስተማራቸውን 394 ተማሪዎች አስመርቋል።

የተቋሙ 17ኛ ዙር ተመራቂዎች በቅድመ-ምረቃ እና በድኅረ-ምረቃ ፕሮግራሞች ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ ናቸው።

በቅድመ-ምረቃ ፕሮግራም ከፍተኛ ውጤት አምጥተው የወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚ ለሆኑ አንድ ወንድ እና አንድ ሴት ተማሪዎች የሁለተኛ ዲግሪ ትምህርታቸውን በተቋሙ እንዲቀጥሉ ነጻ የትምህርት ዕድል እንደተሰጣቸው ተገልጿል።

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

ኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ የመጀመሪያ ባች ተማሪዎች የምረቃ ስነ-ስርዓት አካሒዷል።

ዩኒቨርሲቲው ዛሬ ያስመረቃቸው የጤና ተማሪዎች ባለፈው ሳምንት የተሰጠውን የመውጫ ፈተና ወስደው ሙሉ በሙሉ ያለፉ መሆናቸው ተገልጿል።

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ያሰለጠናቸውን 1,513 ተማሪዎችን ዛሬአስመረቀ።

የሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ እንዲሁም በተከታታይ መርሐግብር የቅድመ-ምረቃ እና የድኅረ-ምረቃ ተማሪዎች ዩኒቨርሲቲው ዛሬ ባከናወነው 14ኛ ዙር የተማሪዎች የምረቃ ስነ-ስርዓት መመረቃቸው ተገልጿል።

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

መቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ 998 ተማሪዎችን አስመርቋል።

ዩኒቨርሲቲው በተለያዩ የትምህርት ፕሮግራሞች ስልጠናቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ የ5ኛ ዙር ተመራቂዎች የምረቃ ስነ-ስርዓት ዛሬ አካሒዷል።

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ የመውጫ ፈተና በተቋሙ የወደሰዱ ተፈታኞች ውጤታቸው ኦንላይን የሚያዩበት አማራጭ አዘጋጅቷል።

የተቋሙ ተፈታኞች ተከታዩን ማስፈንጠሪያ በመጠቀምና የራሳቸውን User Name በማስገባት ውጤታቸውን መመልከት እንደሚችሉ ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

የተቋሙ ተፈታኝ ከሆኑ ተከታዩን ሊንክ ይጠቀሙ፦
https://script.google.com/macros/s/AKfycbye3I3K9rESI7a7Xr5NHF6-vX7KNbnJcIkTxyR4L4yn7LEd79-1GkzW0ltCOgrD1LlGnQ/exec

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

"የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመውጫ ፈተና ውጤት እስከ ነገ ይለቀቃል።" - ትምህርት ሚኒስቴር

በግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የ2017 ዓ.ም አጋማሽ ዓመት የመውጫ ፈተና የወሰዱ ተፈታኞች ውጤት እስካሁን አልተለቀቀም።

ከዚህ ጋር በተያያዘ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመውጫ ፈተና ተፈታኞች ቅሬታቸውን ለቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ አቅርበዋል።

ውጤቱ ለምን ከመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች እኩል አልተለቀቀም ስንል የትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራርን ጠይቀናል።

ለመጀመሪያ ጊዜ የመውጫ ፈተና የሚወስዱ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተፈታኞችን ክፍያ የሚፈፅሙት ተቋማቱ መሆናቸውን አመራሩ ገልፀዋል።

ይሁን እንጂ ተቋማቱ ክፍያውን ባለመፈፀማቸው ውጤት መለቀቅ ላይ መዘግየት እንዳጋጠመ ኃላፊው ተናግረዋል።

አሁን ላይ ብዙዎቹ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ክፍያውን እየፈፀሙ በመሆናቸው የተፈታኞቹ ውጤት እስከ ነገ ቅዳሜ የካቲት 8/2017 ዓ.ም እንደሚለቀቅ ኃላፊው ለቲክቫህ አረጋግጠዋል።

የመውጫ ፈተናውን በግል የወሰዱ ድጋሜ ተፈታኞች ውጤትም ወደየተፈተኑበት ተቋማት ይላካል ብለዋል።

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

በራያ ዩኒቨርሲቲ ባለፈው ሳምንት የተሰጠውን የመውጫ ፈተና ከወሰዱ ተማሪዎች መካከል 96.25 በመቶዎቹ ፈተናውን ማለፋቸውን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

የግል ኮሌጅ ተፈታኞችን ጨምሮ ከ400 በላይ ተማሪዎች ከጥር 26-30/2017 ዓ.ም የተሰጠውን የአጋማሽ ዓመት የመውጫ ፈተና በራያ ዩኒቨርሲቲ በመገኘት መውሰዳቸውን ከዩኒቨርሲቲው የተገኘ መረጃ ያሳያል፡፡

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የ2017 ዓ.ም አጋማሽ ዓመት የመውጫ ፈተና ውጤት #እንዳልደረሳቸው የኢትዮጵያ የግል ከፍተኛ ትምህርት እና ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋማት ማህበር ገለፀ፡፡

የመውጫ ፈተና ውጤት ለኮሌጆች እንደተላከ ትናንት የተገለፀ ቢሆንም፤ የተፈታኞች ውጤት እስካሁን ለግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አለመድረሱን የኢትዮጵያ የግል ከፍተኛ ትምህርት እና ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋማት ማህበር ለቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ገልጿል።

የተማሪዎች ውጤት ለግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አለመላኩን ዩኒቲ ዩኒቨርሲቲን ጨምሮ ከተለያዩ የግል ትምህርት ተቋማቱ ማረጋገጣቸውን የማህበሩ ሥራ አስኪያጅ ተፈራ ገበየሁ ገልፀዋል፡፡

በጉዳዩ ዙሪያ ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር መነጋገራቸውን የገለፁት ሥራ አስኪያጁ፤ "ቴክኒካል የሆኑ ነገሮችን ጨርሰን እንልካለን" መባላቸውን ጠቁመዋል፡፡

በመሆኑም ውጤቱ ተጠናቅሮ ለግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱ እስከሚላክ ድረስ የግል ተፈታኞች በትዕግስት እንዲጠብቁ ሥራ አስኪያጁ ጠይቀዋል፡፡

@tikvahuniversity

Читать полностью…
Subscribe to a channel