tikvahuniversity | Unsorted

Telegram-канал tikvahuniversity - Tikvah-University

308824

Subscribe to a channel

Tikvah-University

#AAEB

ከ4-8ኛ ክፍል ያሉ ተማሪዎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ የሂሳብ እና የእንግሊዝኛ ማጠናከሪያ ትምህርት በቴሌቪዥን መስጠት ሊጀምር ነው፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ከአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ጋር በመተባባር የማጠናከሪያ ትምህርቱን ከዛሬ የካቲት 25/2017 ዓ.ም ጀምሮ በቴሌቪዥን ስርጭት መስጠት ይጀምራል ተብሏል፡፡

የትምህርት ስርጭቱ በ AMN Plus ከሰኞ እስከ አርብ ከ11፡00 እስከ 2፡00 ሰዓት እንዲሁም ቅዳሜ እና እሑድ ጠዋት ከ2፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት እንደሚሰጥ የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዘላለም ሙላቱ (ዶ/ር) ገልፀዋል።

በስርጭቱ የእንግሊዝኛ እና ሂሳብ ትምህርቶች በእንግሊዝኛ፣ በአማርኛ እና በአፋን ኦሮሞ ቋንቋዎች እንደሚሰጥ ተናግረዋል።

ትምህርቱ በ AMN Plus ቻናል እንዲሁም በአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ እና በአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ የማኅበራዊ ሚዲያ አማራጮች ይተላለፋል ተብሏል።

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

⛺️🗺 ሃይኪንግ ላይ ሆናችሁ ዳታ መጠቀም ፈልጋችሁ ታውቃላችሁ? እነሆ አዲስ ቅመም!

💨⚡️ የትም ይዛችሁት መሄድ የምትችሉትና እስከ 6 ሰዓት የሚቆይ የባትሪ አቅም ያለው፣ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን ይዞ በአንዴ እስከ 8 ሰው ድረስ የሚያስጠቅመውን ልዩ ቅመም MIFIን ገዝተን ፈጣን 4G ኢንተርኔት እንጠቀም! ለ30 ቀን ከሚቆይ ነጻ 30ጊባ ዳታ ጉርሻ ጋር 😋

ከሳፋሪኮም ጋር አንድ ወደፊት ⚡️

🔗 የ M-PESA ሳፋሪኮም መተግበሪያን በዚህ ሊንክ እናውርድ፦ https://play.google.com/store/apps/details?id=et.safaricom.mpesa.lifestyle

#MPESASafaricom #SafaricomEthiopia #1Wedefit #Furtheraheadtogether

Читать полностью…

Tikvah-University

20ኛ እና 21ኛ ዙር የድረ-ገፅ እና ሞባይል መተግበሪያ ማበልፀግ (Full-Stack Website and Mobile Application Development) ስልጠና በፒያሣ እና በመገናኛ ካምፓስ የፊታችን ሰኞ መጋቢት 01/2017 ዓ.ም በቀን መርሐግብር ይጀመራል!

👉 ተግባርን ከንድፈ ሀሳብ ያስተሳሰረ ስልጠና
👉 የፕሮግራሚንግ ትምህርትን አካቶ የሚሰጥ
👉 Front-end እና Back-end በአንድ ላይ እስከ Deployment ያካተተ
👉 በተግባር ድረ-ገፆችን እና ሞባይል መተግበሪያዎችን እያበለፀጉ የሚሰለጥኑበት
👉 የሥራ ላይ ስልጠና (Internship) የተመቻቸለት

☎️ 0906777799 / 0906777755
አድራሻ

ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ
ቁ.2: መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ

Telegram: /channel/sagetraininginstitute
TikTok: sage_training_institute" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@sage_training_institute
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute

Читать полностью…

Tikvah-University

#ASTU

አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን አስመርቋል።

የዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ ትምህርት ቤት፣ ቅድመ-መጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት፣ መጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት፣ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፣ የአካሚክ ሠረተኞች መኖሪያ ህንጻ፣ ባለ አራት ወለል የታደሰ የንግድ ማዕከል ህንጻ እና የሠረተኞች መዝናኛ ላውንጅ የተመረቁ ፕሮጀክቶች መሆናቸው ተገልጿል።

ዕድሳት ተደርጎባቸውና ተገንብተው የተመረቁት ፕሮጀክቶች፥ የትምህርት ጥራትን ለማምጣት እንዲሁም የተቋሙን ሠራተኞች እርካታ ለማምጣት ያግዛሉ ተብሏል።

ዩኒቨርሲቲው የዳታ ማዕከል፣ የምርምር ፓርክ እና ዘርፈ-ብዙ አገልግሎት የሚሰጥ አዳራሽ ግንባታዎች እያከናወነ መሆኑ ተጠቁሟል።

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

21ኛ፣ 22ኛ እና 23ኛ ዙር ሙሉ የሒሳብ መዝገብ አያያዝ (Modern Accountancy) ስልጠና ሰኞ መጋቢት 01/2017 ዓ.ም በፒያሣ እና በመገናኛ ካምፓስ በቀን እና በማታ መርሐግብር ይጀመራል!

👉 ተግባርን ከንድፈ ሀሳብ ያስተሳሰረ ስልጠና
👉 መሠረታዊ አካውንቲንግ እና ኦዲት አሰራር፣ ሙሉ የአካውንቲንግ ሒሳብ አሰራር በፒስቺሪ ተደግፎ እና የግብር አያያዝ ትምህርቶችን አካቶ የሚሰጥ
👉 የሥራ ላይ ስልጠና (Internship) የተመቻቸለት

☎️ 0906777799 / 0906777755
አድራሻ
ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ
ቁ.2፡ መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ

Telegram: /channel/sagetraininginstitute
TikTok: sage_training_institute" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@sage_training_institute
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute

Читать полностью…

Tikvah-University

እንኳን ለ፻፳፱ ኛው የዓድዋ ድል መታሰቢያ እና የጥቁር ሕዝቦች የድል በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

የበለጠ ይጠብቁ ...
ሴጅ ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት

Congratulations on the 129th Anniversary of Adwa Victory Day!

Expect More ...
Sage Training Institute

Telegram: /channel/sagetraininginstitute
TikTok: sage_training_institute" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@sage_training_institute
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute

☎️   0906777799 / 0906777755
አድራሻ
ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ
ቁ.2: መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ

Читать полностью…

Tikvah-University

#AAUCHS

የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በቅድመ-ምረቃ ፕሮግራም ያሰለጠናቸውን 179 ተማሪዎች አስመርቋል።

153 ተማሪዎች በሜዲካል ዶክትሬት፣ 21 ተማሪዎች በጥርስ ህክምና እና 23 ተማሪዎች ደግሞ በአኔስቴዥያ የመጀመሪያ ዲግሪ ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ ናቸው።

ከአጠቃላይ ተመራቂዎቹ መካከል 165 ተማሪዎች የላቀ ውጤት በማስመዘገቡ የተመረቁ መሆናቸው ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

#Update

የጤና ተመራቂዎች የሙያ ብቃት ምዘና (COC) አመልካቾች ምዝገባ ከነገ የካቲት 22/2017 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት ቀናት ክፍት እንደሚሆን ይጠበቃል።

የሙያ ብቃት ምዘና ለመውሰድ እየጠበቁ የሚገኙ የጤና ተመራቂዎች ምዝገባ በየካቲት መጀመሪያ ለማከናወን ዕቅድ ተይዞ የነበረ ቢሆንም በተለያዩ ምክንያቶች መዘግየት አጋጥሟል።

አሁን ላይ አጋጥመው የነበሩ ችግሮች መፍትሔ በማግኘታቸው ከነገ ቅዳሜ የካቲት 22/2017 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት ጥቂት ቀናት የአመልካቾች ምዝገባ (በድጋሜ ተፈታኞችን ጨምሮ) እንደሚደረግ ከጤና ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

በ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ለመውሰድ ከ600 ሺህ በላይ ተማሪዎች ተመዝግበዋል፡፡ - የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት

ለዘንድሮ የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የተማሪዎች ምዝገባ ከታህሳስ 6 እስከ ጥር 6 ቀን 2017 ዓ.ም መከናወኑን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር እሸቱ ከበደ (ዶ/ር) አስታውሰዋል፡፡

በዚህም ከ608 ሺህ በላይ የተፈጥሮ ሳይንስ እና የማኅበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች መመዝገባቸውን ገልፀዋል።

ሀገር አቀፍ ፈተናው በወረቀት እና በበይነ መረብ የሚሰጥ ሲሆን፤ ክልሎች በኦንላይን እና በወረቀት የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎችን መረጃ እስከ የካቲት 25/2017 ዓ.ም ድረስ ለይተው እንዲያሳውቁ ይጠበቃል፡፡

የፈተና ዝግጅቱ ከኢኮኖሚክስ በስተቀር ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ያሉ የትምህርት አይነቶችን ያካተተ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡ ኢኮኖሚክስ በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት የገባ በመሆኑ ለዚህ ዓመት ከ12ኛ ክፍል ብቻ እየተዘጋጀ መሆኑን አንስተዋል። #ENA

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

#ጥቆማ

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለደረጃ አንድ የቻይንኛ ቋንቋ ሰርተፊኬት ፕሮግራም ምዝገባ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡

150 ተመዝጋቢዎች በፕሮግራሙ ይሳተፋሉ ተብሏል፡፡

ለደረጃ ሁለት የቻይንኛ ቋንቋ ሰርተፊኬት ፕሮግራም ምዝገባ ያደረጉ አመልካቾች ትምህርት ነገ የካቲት 22/2017 ዓ.ም ይጀመራል፡፡

የምዝገባ ቦታ፦
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ኮንፊሽየስ ኢንስቲትዩት ቢሮ፥ 6 ኪሎ ዋና ግቢ፣ ፎረም ህንጻ፣ 8ኛ ፍሉር ጠዋት ከ3፡00-5፡00 ሰዓት

የስልጠናው ቦታ፦
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ 6 ኪሎ ካምፓስ

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በንግድ ሀሳብ ፈጠራ ውድድር አሸናፊ ለሆኑ ተወዳዳሪዎች ሽልማት ሰጠ።

የዩኒቨርሲቲው የኢንተርፕርነርሺፕና ቴክኖሎጂ ማበልጸጊያ ዳይሬክቶሬት ባዘጋጀው የንግድ ፈጠራ ውድድር ላይ በባለሙያዎች ድጋፍና ክትትል የተደረገላቸው 23 የፈጠራና ንግድ ሀሳቦች ቀርበዋል።

በውድድሩ ከቀረቡ ሀሳቦች መካከል ከ1-3ኛ ደረጃ ላገኙ ተወዳዳሪዎች፥ ፈጠራቸውን ወደ ተግባር ለመለወጥ የሚያስችል የገንዘብ ሽልማት ተሰጥቷል።

አንደኛ ደረጃ ለወጣ የመነሻ ካፒታል ብር 200,000፣ በሁለተኛነት ለተመረጠ ብር 150,000 እንዲሁም በሦስተኛነት ለተመረጠው ብር 100,000 ሽልማት ተበርክቷል።

በውድድሩ ቀርበው አሸናፊ የሆኑት የፈጠራ ሀሳቦች የአካባቢውን ችግር ፈቺ መሆናቸው ተገልጿል። የቀረቡት የፈጠራ ሀሳቦች ምንድን ናቸው?

➦ የማይድኑ ነገር ግን በዘላቂነት መድኃኒት የሚሰጣቸው ታማሚዎቹ ባሉበት ሆነው የባለሙያ ድጋፍ እንዲያገኙ በቴሌ ሜዲሲን የሚታገዝ የፈጠራ ሀሳብ፣

➦ በአባቢያችን የሚገኙ ደረቅና ፍሳሽ ቆሻሻዎችን በመጠቀም የሚሰራ የተፈጥሮ ማዳበሪያ፣

➦ ተማሪዎችን ሊያግዝ የሚችል ሰው ሰራሽ አስተውሎትን የሚጠቀም መተግበሪያ። #ሀዩ

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

#DillaUniversityAlumniForum

ዲላ ዩኒቨርሲቲ የቀድሞ የተቋሙ ምሩቃን የሚገናኙበት መድረክ አዘጋጅቷል፡፡

ወደ ድሞው የእውቀት ቤታችሁ ለመሔድ በተከታዩ ሊንክ ይመዝገቡ 👇
https://forms.office.com/r/EXc4rmXFYB

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

⛺🗺 ሃይኪንግ ላይ ሆናችሁ ዳታ መጠቀም ፈልጋችሁ ታውቃላችሁ? እነሆ አዲስ ቅመም!

💨⚡ የትም ይዛችሁት መሄድ የሚያስችላችሁ እስከ 6 ሰዓት የሚቆይ የባትሪ አቅም ያለውና አዳዲስ የቴክኖሎጂ ትሩፋቶችን ይዞ በአንዴ እስከ 8 ሰው ድረስ የሚያስጠቅመውን ልዩ ቅመም MIFIን ገዝተን ፈጣን 4G ኢንተርኔት እንጠቀም! ለ30 ቀን ከሚቆይ ነጻ 30ጊባ ዳታ ጉርሻ ጋር 😋

ከሳፋሪኮም ጋር አንድ ወደፊት⚡
  
🔗 የM-PESA ሳፋሪኮም መተግበሪያ በዚህ ሊንክ እናውርድ፦ https://play.google.com/store/apps/details?id=et.safaricom.mpesa.lifestyle

#MPESASafaricom #SafaricomEthiopia #1Wedefit #Furtheraheadtogether

Читать полностью…

Tikvah-University

#UoGAlumni

70ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን ማክበር ላይ የሚገኘው ጎንደር ዩኒቨርሲቲ፤ የተቋሙን የቀድሞ ምሩቃን መመዝገብ ጀምሯል።

ይህም የቀድሞ የዩኒቨርሲቲው ተመራቂዎችን አብረዋቸው ከተማሩ ጋር ለማገናኘት እና ዩኒቨርሲቲው በሚያከናውናቸው ተግባራት አበርክቶ ለማድረግ ያስችላል ተብሏል።

ተከታዩን ሊንክ በመጫን ይመዝገቡ 👇
https://alumni.uog.edu.et

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

4ኛ ዙር የፋይናንስ እና ካፒታል ማርኬት ስልጠና በፒያሣ እና በመገናኛ ካምፓስ ምዝገባ ላይ ነን!

👉 ፈጥነው ይመዝገቡ!

የካፒታል ማርኬት ገበያ በኢትዮጵያ ተጀምሯል። እርስዎም በተቋማችን የሚሰጠውን የፋይናንስ እና ካፒታል ማርኬት ስልጠና በመውሰድ በገበያው ለመሳተፍ ራስዎን ያዘጋጁ።

ስልጠናው ብቁ በሆኑ መምህራን ይሰጣል። ስልጠናውን ይውሰዱና ትግበራውን ይጠባበቁ!

☎️    0906777799 / 0906777755
አድራሻ
ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ
ቁ.2: መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ

Telegram: /channel/sagetraininginstitute
TikTok: sage_training_institute" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@sage_training_institute
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute

Читать полностью…

Tikvah-University

የካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ በ2017 ዓ.ም በፖስት ቤዚክ የመጀመሪያ ዲግሪ ፕሮግራም በግል ወይም በመንግሥት ስፖንሰርነት ለመማር የሚፈልጉ አመልካቾችን ለመቀበል ላወጣው ማስታወቂያ ያመለከታችሁ የመግቢያ ፈተና አርብ የካቲት 28/2017 ዓ.ም ጠዋት 3፡00 እንደሚሰጥ ገልጿል፡፡

ፈተናው በኮሌጁ የስብሰባ አዳራሽ 7ኛ ወለል ላይ የሚሰጥ ሲሆን፤ አመልካቶች ማንነታችሁን የሚገልፅ መታወቂያ መያዝ ይጠበቅባችኋል ተብሏል፡፡

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

#ጥቆማ

የቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት የኢትዮጵያ ቱሪዝም ክህሎት ውድድር (Ethiopian Tourism Skills Competition) አዘጋጅቷል፡፡

በውድድሩ ለመሳተፍ ክፍያ የማይጠየቅ ሲሆን፤ ኢንስቲትዩቱ ለሚያሸንፉ ሽልማት አዘጋጅቷል፡፡

በውድድሩ ለመሳተፍ ፍላጎት ያላችሁ የዘርፉ ሙያተኞች በኢንስቲትዩቱ ጥናት እና ምርምር ክፍል 2ኛ ፎቅ በአካል በመገኘትና የምዝገባ ቅፅ በመሙላት ምዝገባ ማድረግ ይችላሉ ተብሏል፡፡

የምዝገባ ጊዜ፦
ከየካቲት 25/2017 ዓ.ም እስከ መጋቢት 10/2017 ዓ.ም

የውድድር ሙያዎች፦
➫ Cultural Food Preparation
➫ Foreign Food Preparation
➫ Pastry Work
➫ Bakery Work
➫ Barista
➫ Bartending
➫ Tour Guiding
➫ Laundry Work
➫ Housekeeping
➫ F&B Service
➫ Front Office Service
➫ New Food Recipe Innovation
➫ New Beverage Recipe Innovation
➫ Innovative Leadership
➫ Tour Operating

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

#MoH

የጤና ባለሙያዎች የብቃት ምዘና ፈተና በመጋቢት 2017 ዓ.ም ይሰጣል።

ፈተናውን የምትወስዱ ተፈታኞች ምዝገባ ከዛሬ የካቲት 24/2017 ዓ.ም እስከ መጋቢት 7/2017 ዓ.ም ይከናወናል።

ፈተናውን የምትወስዱ የመንግሥትም ሆነ የግል ተቋማት ተመዛኞች በኦንላይን http://hple.moh.gov.et/hple ላይ በመግባት ምዝገባ ማድረግ ትችላላችሁ ተብሏል።

በተጠቀሱት ቀናት እንድትመዘገቡና ሲስተሙ የሚሰጣችሁን የፈተና መለያ ቁጥር (Registration No.) የያዘ ስሊፕ Print አድርጋችሁ መያዝ ይኖርባችኋል።

ለተጨማሪ መረጃ፦
0115186275 / 0115186276

እያንዳንዱ የፈተና ጣቢያ በየሙያ መስኩ ማስተናገድ በሚችለው ከፍተኛ የተመዛኝ ቁጥር ልክ ገደብ ስለተቀመጠለት፥ ተመዛኞች ምዝገባውን ቀድማችሁ በማጠናቀቅ ተጠቃሚ መሆን የምትችሉ መሆኑ ተገልጿል።

Note:
በጥር 30/2017 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር የተሰጠውን የመውጫ ፈተና ተፈትናቹ ያለፍችሁና በዚህ የብቃት ምዘና ፈተና ለመቀመጥ የተዘጋጃችሁ ነገር ግን ቴምፖራሪ ዲግሪ ከተቋማችሁ ያልደረሰላችሁ ተመዛኞች ከትምህርት ሚኒስቴር ይህ ጉዳይ ቀጥታ ከሚመለከተው የሥራ ክፍል የትብብር ደብዳቤ ማያያዝ ይጠበቅባችኋል ተብሏል።

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

#ጥቆማ

የእንግሊዘኛ ቋንቋ ምዘና ፈተና (IELTS Test) በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ይሰጣል!

ብሪቲሽ ካውንስል ከድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር የ'IELTS' ፈተና የካቲት 29/2017 ዓ.ም ይውሰዱ!

ዩኒቨርሲቲው ፈተናውን መውሰድ የሚፈልጉ አመልካቾች የኦንላይን ምዝገባ በማድረግ ላይ ይገኛል።

ለበለጠ መረጃ፦
☎️ 0923032129

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

#MoE

በሰኔ 2017 ዓ.ም የሚሰጠውን የመውጫ ፈተና የሚወስዱ ዕጩ ተመራቂዎች የፋይዳ መታወቂያ ሊያወጡ ይገባል። - ትምህርት ሚኒስቴር

የካቲት 21/2017 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ተፈርሞ ለሁሉም የመንግሥት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተላከ ሰርኩላር፤ ብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ (ፋይዳ) የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተማሪ እና የሠራተኞችን መረጃ በተደራጀ መልኩ ለመያዝ ጠቀሜታ እንዳለው ይገልጻል።

የሀገር አቀፍ ፈተናዎችን ደህንነት ለማስጠበቅ አስፈላጊ መሆኑንም ያትታል።

በዚህም በሰኔ 2017 ዓ.ም የሚሰጠውን የመውጫ ፈተና የሚወስዱ ዕጩ ተመራቂዎች ፈተናውን ለመውሰድ የፋይዳ መታወቂያ ሊያወጡ እንደሚገባ አሳስቧል።

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

ዶ/ር ኤልሳቤት አርአያ 👏

ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ ህክምና ትምህርት ቤት 3.93 CGPA በማምጣት የወርቅ ሜዳልያ ተሸላሚ

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በቅድመ-ምረቃ ፕሮግራም ያሰለጠናቸውን 179 ተማሪዎች ዛሬ ማስመረቁ ይታወቃል።

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

2ኛ ዙር የህንፃ ኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታ ስልጠና በምዝገባ ላይ ነን!

🔔 ፈጥነው ይመዝገቡ!

👉 ተግባርን ከንድፈ ሀሳብ ያስተሳሰረ ስልጠና
👉 የሳተላይት ዲሽ መስመር ዝርጋታ ስልጠና በተጨማሪነት የሚሰጥበት
👉ከትምህርት ቢሮ የ'COC' ምዘና የተዘጋጀለት

☎️ 0906777799 / 0906777755
አድራሻ
ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ
ቁ.2: መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ

Telegram: /channel/sagetraininginstitute
TikTok: sage_training_institute" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@sage_training_institute
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute

Читать полностью…

Tikvah-University

በነፃ ብር በመላክ የM-PESAን ነፃ አገልግሎት እናጣጥም! ከM-PESA ወደ የትኛውም የሳፋሪኮም ስልክ በነፃ እንላክ!

#MPESASafaricom #MPESAEthiopia

Читать полностью…

Tikvah-University

በኦሮሚያ ክልል በ2017 ዓ.ም ከ212 ሺህ በላይ ተማሪዎች ሀገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ይወስዳሉ፡፡ - የኦሮሚያ ክልል ትምህርት ቢሮ

በኦሮሚያ ክልል በ2017 ዓ.ም ከ212 ሺህ በላይ ተማሪዎች ሀገር አቀፍ ፈተና የሚወስዱ ሲሆን፤ 59 በመቶ የሚሆኑት የተፈጥሮ ሳይንስ ቀሪዎቹ ደግሞ የማኅበራዊ ሳይንስ ተፈታኝ መሆናቸውን የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ቶላ በሪሶ (ዶ/ር) ለፋና ዲጂታል ተናግረዋል፡፡

ሀገር አቀፍ ፈተና በወረቀት እና በኦንላይን ይሰጣል ያሉት ኃላፊው፤ ከ50 ሺህ በላይ የሚሆኑ ተማሪዎች ፈተናውን በኦንላይን የሚወስዱበት ሁኔታ እየተመቻቸ ነው ብለዋል፡፡ ተማሪዎች ፈተናውን በኦንላይን የሚወስዱባቸው ማዕከላት እየተለዩ እንደሆነ ጠቁመዋል። #FMC

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

የዲጂታል ማርኬቲንግ ስልጠና በፒያሣ እና በመገናኛ ካምፓስ ምዝገባ ላይ ነን!

👉 በሁለት ወር ምርጥ የዲጂታል ማርኬቲንግ ባለሙያ የሚያደርግዎት
👉 ንድፈ ሀሳብን ከተግባር ያስተሳሰረ ስልጠና

☎️ 0906777799 / 0906777755
አድራሻ
ቁ.1:
ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ
ቁ.2: መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ

የበለጠ ይጠብቁ ...
💥 ሴጅ ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት 💥

Telegram: /channel/sagetraininginstitute
TikTok: sage_training_institute" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@sage_training_institute
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute

Читать полностью…

Tikvah-University

የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ አዲስ ፕሬዝዳንት ተመድቦለታል።

ንጉሥ ታደሰ (ዶ/ር) ከየካቲት 18 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ሆነው ተሹመዋል።

ፍቅሬ ደሳለኝ (ፕ/ር) ከ2009 ዓ.ም ጀምሮ የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት በመሆን ሲያገለግሉ ቆይተዋል።

ዩኒቨርሲቲው ራስ ገዝ ለመሆን የተለያዩ ፖሊሲዎችና መመሪያዎች ዝግጅት በመጠናቀቅ ላይ መሆናቸው በሥራ ርክክብ ወቅት ተገልጿል።

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

ፒስቺሪ አካውንቲንግ ስልጠና በፒያሣ እና በመገናኛ ካምፓስ ምዝገባ ላይ ነን!

👉 ንድፈ ሀሳብን ከተግባር ያስተሳሰረ ስልጠና
👉 በፒስቺሪ ላይ የሚሰጥ
👉 የሥራ ላይ ስልጠና (Internship) የተመቻቸለት

☎️   0906777799 / 0906777755
አድራሻ
ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ
ቁ.2: መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ

Telegram: /channel/sagetraininginstitute
TikTok: sage_training_institute" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@sage_training_institute
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute

Читать полностью…

Tikvah-University

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የ2017 አጋማሽ ዓመት የተማሪዎች የምርቃት ስነ-ስርዓት በሳምንቱ መጨረሻ ያካሒዳል።

በዚህም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ ተማሪዎች የምረቃ ስነ-ስርዓት ቅዳሜ የካቲት 22/2017 ዓ.ም እንደሚካሔድ ተገልጿል።

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

#ጥቆማ

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የአድዋ ድል መታሰቢያ በዓልን ምክንያት በማድረግ ልዩ የተማሪዎች ሴሚናር አዘጋጅቷል።

ሴሚናሩ "ኢትዮጵያዊነት እና አፍሪካዊነት በእኔ ትውልድ" በሚል ጭብጥ ላይ ይመክራል።

ሴሚናሩ አርብ የካቲት 21/2017 ዓ.ም ጠዋት 3:00 ሰዓት በዋናው ግቢ ራስ መኮንን አዳራሽ ይካሔዳል።

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

ዝግጁ ነሽሽሽሽሽ?
የሳፋሪኮም ቅድሚያ ለሴቶች 5ኪሜ ሩጫ ምዝገባ ተጀምሯል! M-PESAን ተጠቅመሽ 540 ብር የነበረውን ቲሸርት በ 389 ብር ብቻ አግኚ!!!
ከM-Pesa ጋር አብረን እንፍጠን።

#SafaricomEthiopia #Andegna #WomensRun #MPESASafaricom

Читать полностью…
Subscribe to a channel