tikvahuniversity | Unsorted

Telegram-канал tikvahuniversity - Tikvah-University

308824

Subscribe to a channel

Tikvah-University

የካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ ያስተማራቸውን የጤና ሳይንስ ባለሙያዎች ነገ መጋቢት 13/2017 ዓ.ም ያስመርቃል።

ተመራቂዎቹ በጠቅላላ ህክምና በመጀመሪያ ዲግሪ፣ በስፔሻላይዜሽን፣ በሰብ ስፔሻላይዜሽን እና በኅብረተሰብ ጤና ሳይንስ በድኅረ-ምረቃ ፕሮግራሞች ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ ናቸው።

ኮሌጁ በሰብ-ስፔላሻላይዜሽን ተማሪዎች ሲያስመርቅ ለመጀመሪያ ጊዜ መሆኑ ተገልጿል።

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

4ኛ ዙር የህንፃ ኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታ ስልጠና ምዝገባ ላይ ነን!

🔔 ፈጥነው ይመዝገቡ!

👉 ተግባርን ከንድፈ ሀሳብ ያስተሳሰረ ስልጠና
👉 የሳተላይት ዲሽ መስመር ዝርጋታ በተጨማሪነት የሚሰጥበት 
👉 ከትምህርት ቢሮ የCOC ምዘና የተዘጋጀለት

☎️  0906777799 / 0906777755
አድራሻ
ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ
ቁ.2: መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ

Telegram: /channel/sagetraininginstitute
TikTok: sage_training_institute" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@sage_training_institute
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute

Читать полностью…

Tikvah-University

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የሚገኙ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የጋራ ፎረም ተመስርቷል፡፡

በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ዛሬ በተካሔደ የምስረታ መድረክ፤ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ፣ በክልሉ የሚገኙ የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች እና ኮሌጆች ከፍተኛ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

ክልሉ እና የከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱ ሀብትና አቅማቸውን በማቀናጀት በጋራ ለመሥራት የፎረሙ መመስረት ትልቅ ፋይዳ ይኖረዋል ተብሏል።

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ፣ ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ፣ ጂንካ ዩኒቨርሲቲ እና ዲላ ዩኒቨርሲቲ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከሚገኙ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት መካከል ይጠቀሳሉ።

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

#AAU #NGAT

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከ3,300 በላይ ለሚሆኑ የብሔራዊ ድኅረ-ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና አመልካቾች ፈተናውን ይስጣል፡፡

ዩኒቨርሲቲው ለ3,337 አመልካቾች ነገ መጋቢት 12/2017 ዓ.ም በጠዋት እና ከሰዓት መርሐግብር በተለያዩ የፈተና ማዕከላት ፈተናውን እንደሚሰጥ ታውቋል፡፡

(ተቋሙ ያወጣው የተፈታኞች ሙሉ ስም፣ User Name እና የፈተና ማዕከላት ዝርዝር ከላይ ተያይዟል፡፡)

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

የአካውንቲንግ እና ፋይናንስ የመውጫ ፈተና (Exit Exam) የሦስት ወር ስልጠና በፒያሣ እና በመገናኛ ካምፓስ ምዝገባ ላይ ነን!

🔔 ፈጥነው ይመዝገቡ!

👉 በተመረጡ የዩኒቨርሲቲ መምህራን የሚሰጥ ስልጠና፣
👉 ፈተና ላይ የሚመጡ ኮርሶች በሙሉ ክለሳ ይደረጋል፣
👉 ከ1,000 በላይ ጥያቄዎችን በመስራት ለፈተናው ብቁ እንድትሆኑ የምናደርጋችሁ ይሆናል።

☎️   0906777799 / 0906777755
አድራሻ
ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ
ቁ.2: መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ

💥 ሴጅ ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት

Telegram: /channel/sagetraininginstitute
TikTok: sage_training_institute" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@sage_training_institute
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute

Читать полностью…

Tikvah-University

#ጥቆማ

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሰብአዊ መብቶች ማዕከል ሠራተኞችን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል።

የሥራ መደብ፦
➫ Procurement Officer
➫ Account’s Clerk/Cashier
➫ Legal Officer (for Adama Project office)

🗓 የማመልከቻ ጊዜ፦
እስከ መጋቢት 19/2017 ዓ.ም

ለበለጠ መረጃ 👇
https://chr-aau.org/vacancy/

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

45ኛ ዙር የግራፊክ ዲዛይን፣ ቪዲዮ ኤዲቲንግ፣ ሞሽን ግራፊክ እና ዲጂታል ማርኬቲንግ ስልጠና በፒያሣ ካምፓስ ቅዳሜ መጋቢት 13/2017 ዓ.ም በቅዳሜ እና እሑድ መርሐግብር ይጀምራል። 

👉 ተግባርን ከንድፈ ሀሳብ ያስተሳሰረ ስልጠና
👉 Advanced Graphic + Video Editing + Motion Graphic + Digital Marketing በአንድ ላይ
👉 ከ50 በላይ ፕሮጀክቶች ያሉት
👉 የሥራ ላይ ስልጠና የተመቻቸለት

☎️   0906777799 / 0906777755
አድራሻ
ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ
ቁ.2: መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ

Telegram: /channel/sagetraininginstitute
TikTok: sage_training_institute" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@sage_training_institute
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute

Читать полностью…

Tikvah-University

#ጥቆማ

በሆቴል እና ቱሪዝም ሙያዎች ተወዳድረው ይሸለሙ!

የምዝገባ ጊዜ 👇
እስከ አርብ መጋቢት 12/2017 ዓ.ም.

ውድድሩ ከሚያዝያ 2017 ዓ.ም አጋማሸ ጀምሮ እንደሚካሄድ የቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት አሳውቋል።

በውድድሩ ለመሳተፍ ክፍያ የማይጠየቅ ሲሆን፤ ኢንስቲትዩቱ ለሚያሸንፉ ሽልማት አዘጋጅቷል፡፡

በውድድሩ ለመሳተፍ ፍላጎት ያላችሁ የዘርፉ ሙያተኞች በኢንስቲትዩቱ ጥናት እና ምርምር ክፍል 2ኛ ፎቅ በአካል በመገኘትና የምዝገባ ቅፅ በመሙላት ምዝገባ ማድረግ ይችላሉ ተብሏል፡፡

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

#ጥቆማ

ለጥናታዊ ወረቀት አቅራቢዎች የቀረበ ጥሪ !!

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር እና የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት በጋራ በመሆን ከግንቦት 8 እስከ 10/2017 ዓ.ም (May 16-18 2025) የሚቆይ ዓለም-ዓቀፍ የቴክኖሎጂ ኤክስፖና ኮንፍረንስ “Ethiopian Tech Expo - ETEX 2025” ያዘጋጃሉ፡፡

በመሆኑም በዚህ በአይነቱ ልዩና የመጀመሪያ በሆነ ዓለም-ዓቀፍ የቴክኖሎጂ ኤክስፖና ኮንፍረንስ ላይ የአካዳሚክ ማኅበረሰቡ ጥናታዊ ወረቅት እንዲያቀርቡ እንጋብዛለን፡፡

Call for Papers – Ethiopian Tech Expo 2025 (ETEX 2025)!

We are excited to invite researchers, scholars, and professionals to submit their papers for ETEX 2025!

📅 Event Date: May 16th – 18th, 2025
📍 Venue: Addis International Convention Center (AICC)

🎯 Thematic Areas:
🔹 Cybersecurity in the AI Era
🔹 Cybersecurity in Smart Cities
🔹 Quantum Computing
🔹 Fintech
🔹 Trustworthy AI

📌 Submission Details:
✅ Deadline: April 20, 2025
✅ Acceptance Notification: April 30, 2025
✅ Submission Mode: Email
✅ Paper Template: IEEE Format
🏆 Incentives: Selected papers will receive special recognition!

📩 Submit your papers now:
Etexconference@insa.gov.et

Join us in shaping the future of AI, cybersecurity, and emerging technologies.

#ETEX2025 #CallForPapers #INSA #ArtificialIntelligence #Cybersecurity #Fintech #Innovation #Security #Transformation

Читать полностью…

Tikvah-University

#ጥቆማ

የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ “ተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማዎች” በሚል ጭብጥ ላይ ሙያዊ ውይይት አዘጋጅቷል፡፡

ውይይቱ የፊታችን ቅዳሜ፣ መጋቢት 13/2017 ዓ.ም ከሰዓት 8፡00 ሰዓት በኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ የብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደ ሥላሴ የሥነ ጥበባት ማዕከል ይካሔዳል፡፡

የጉግል ማፕ አድራሻ፦
https://maps.app.goo.gl/GwKfjcwg1jmqsfG76

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

#ERMP

የ2024 ብሔራዊ የህክምና ስፔሻሊቲ ስልጠና (ERMP) አመልካቾች ምደባ (Matching) ከሳምንታት በፊት ይፋ መደረጉ ይታወቃል፡፡

ይሁን እንጂ በስድስት የስፔሻሊቲ ፕሮግራሞች ማለትም Anesthesiology CCPM, Emergency and CCM, Family Medicine, General Surgery, Obstetrics & Gynecology እና Pediatrics & CH ያልተመረጡ ቦታዎች በመኖራቸው ለድጋሜ አመልካቾች ክፍት ሆነው ነበር።

በዚህም ከ300 በላይ አመልካቾች የደረሱ ሲሆን፤ ሁሉንም በገምገም ብቁ የሆኑ እጩዎች ለክፍት ቦታዎቹ መመረጣቸውን ጤና ሚኒስቴር ገልጿል።

የተመረጣችሁ አመልካቾች በኢሜይ አድራሻ ermpvacantspots@gmail.com አማካኝነት መመረጣችሁን የሚያረጋግጥ መልዕክት ይደርሳችኋል ተብሏል።

ለሬዚደንሲ የተመረጡ አጠቃላይ አመልካቾች የመጨረሻ ዝርዝር ለተመደቡባቸው ዩኒቨርሲቲዎች/ህክምና ኮሌጆች በቅርቡ እንደሚላክ ሚኒስቴሩ አሳውቋል።

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

በደቡብ ሱዳን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ነጻ የድኅረ-ምረቃ የትምህርት ዕድል በኢትዮጵያ ላገኙ 36 የደቡብ ሱዳን ህክምና ሀኪሞች አሸኛኘት አድርጓል፡፡

ሀኪሞቹ በተለያዩ የኢትዮጵያ የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ነጻ የስፔሻሊቲ ትምህርታቸውን የሚከታተሉ ይሆናል፡፡

ነጻ የትምህርት ዕድሉ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የአቅም ግንባታና የሰው ሃብት ልማት ትብብር እንደሚያጠናክር በጁባ የኢትዮጵያ አምባሳደር ነቢል መሐዲ ተናግረዋል፡፡

የኢትዮጵያ መንግሥት ለደቡብ ሱዳን የህክምና ተማሪዎች ነጻ የትምህርት ዕድል መስጠት የጀመረው በ2006 ዓ.ም ሲሆን፤ እስካሁን ከ100 በላይ የዕድሉ ተጠቃሚዎች በተለያዩ የስፔሻሊቲ ፕሮግራሞች መመረቃቸውን ከደቡብ ሱዳን የኢትዮጵያ ኤምባሲ የተገኘው መረጃ ያሳያል፡፡

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

24ኛ እና 25ኛ ዙር ሙሉ የሒሳብ መዝገብ አያያዝ (Modern Accountancy) ስልጠና ቅዳሜ መጋቢት 13/2017 ዓ.ም በፒያሣ እና በመገናኛ ካምፓስ በቅዳሜ እና እሑድ መርሐግብር ይጀምራል። 

👉 ተግባርን ከንድፈ ሀሳብ ያስተሳሰረ ስልጠና
👉 መሠረታዊ አካውንቲንግ እና ኦዲት አሰራር፣ ሙሉ የአካውንቲንግ ሒሳብ አሰራር በፒስቺሪ ተደግፎ እና የግብር አያያዝ ትምህርቶችን አካቶ የሚሰጥ
👉 የሥራ ላይ ስልጠና (Internship) የተመቻቸለት

☎️   0906777799 / 0906777755
አድራሻ
ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ
ቁ.2: መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ

Telegram: /channel/sagetraininginstitute
TikTok: sage_training_institute" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@sage_training_institute
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute

Читать полностью…

Tikvah-University

#NileExecutiveLeadershipAcademy

ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ''ናይል አመራር አካዳሚ'' የተባለ የከፍተኛ አመራሮች ማሰልጠኛ ማዕከል ሥራ አስጀምሯል

የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ 2ኛ ዙር የአመራር ልማት ፌሎውስ ባስመረቀበት ወቅት አካዳሚው (NELA) ይፋ ሆኗል።

አካዳሚው ራዕይ ያላቸው ተቋማዊ እና የማኅበረሰብ ለውጥ ማምጣት የሚችሉ ከፍተኛ አመራሮችን ለማፍራት የሚያስችል ነው ተብሏል።

አካዳሚው ዩኒቨርሲቲው የአመራር ፈጠራ አህጉራዊ ማዕከል ለመሆን የሰነቀው ስትራቴጂክ ዕቅድ አካል መሆኑ ተገልጿል።

ዩኒቨርሲቲው የተሻለ ክህሎት፣ ጥበብ እና ዕውቀት ያለው አመራር ለመገንባት የሚያስችሉ ተግባራት እያከናወነ እንደሚገኝ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት መንገሻ አየነ (ዶ/ር) ገልፀዋል።

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

በሦስቱም ቅርንጫፎቻችን (መገናኛ፣ ሜክሲኮ እና ጀሞ) እንዲሁም በኦንላይን በምንሰጣቸው ስልጠናዎች በ Advanced Level እና 90% Practical በሆነ ካሪኩለም እንዲሁም ዘመኑ ያፈራቸውን የላብራቶሪ እና የስቱዲዮ እቃዎችን በማሟላት ምዝገባ ላይ ነን!

ከሁሉም ስልጠናዎቻችን ላይ ታላቅ የዋጋ ቅናሽ አድርገናል! አሁኑኑ ይመዝገቡና ትልቅ ለውጥ ወደሚያመጡበት ተቋም ይቀላቀሉ!

የብዙ ዓመት ልምድና ብቃት ባላቸው አሰልጣኞች! ከትምህርትና ስልጠና ጥራትና ቁጥጥር ባለስልጣን ሙሉ ዕውቅና ካለው ሰርተፊኬት ጋር!

🎯 Graphics Design
🎯 Video Editing
🎯 Digital Marketing
🎯 Photography
🎯 Videography
🎯 Cinematography
🎯 Adobe Photoshop
🎯 Fullstack Webapp Development
🎯 Programming Language
🎯 Interior Design
🎯 English Language
🎯 Database
🎯 Basic Computer
🎯 Accounting Softwares
🎯 Engineering Softwares
🎯 SPSS & STATA
🎯 MS-Project
🎯  Foreign & Local Languages

አድራሻ
✅ መገናኛ መተባበር ህንፃ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 419 (ሊፍት ይጠቀሙ)  ☎️ 0991929303
✅ ሜክሲኮ ኬኬር ህንፃ 6ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 639 (ሊፍት ይጠቀሙ) ☎️ 0991929304
✅ ጀሞ 1 አንደኛ በር ካኩ ቢዝነስ ሴንተር 3ኛ ፎቅ ☎️ 0991926707

Читать полностью…

Tikvah-University

በነፃ ብር በመላክ የM-PESAን ነፃ አገልግሎት እናጣጥም! ከM-PESA ወደ የትኛውም የሳፋሪኮም ስልክ በነፃ እንላክ!

#MPESASafaricom #MPESAEthiopia

Читать полностью…

Tikvah-University

#NGAT

ብሔራዊ የድኅረ-ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) በመሰጠት ላይ ይገኛል።

አመልካቾች በመላ ሀገሪቱ በመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ በሚገኙ የፈተና ማዕከላት ፈተናውን እየወሰዱ ነው።

ምስል፦ ወራቤ ዩኒቨርሲቲ እና የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

🌐 እጅግ ፈጣን ዋይፋይ በአዲስ ቅመም! ሊያውም ከጉርሻ ጋር 🤗

💨⚡️ እስከ 6 ሰዓት የሚቆይ የባትሪ አቅም ያለውና አዳዲስ የቴክኖሎጂ ትሩፋቶችን ይዞ በአንዴ እስከ 8 ሰው ድረስ የሚያስጠቅመውን ልዩ ቅመም MIFIን ገዝተን ፈጣን 4G ኢንተርኔት እንጠቀም!

🍰  ለ30 ቀን ከሚቆይ ነጻ 30ጊባ ዳታ ጉርሻ ጋር!

ከሳፋሪኮም ጋር አንድ ወደፊት ⚡️
  
🔗 የM-PESA ሳፋሪኮም መተግበሪያ በዚህ ሊንክ እናውርድ፦ https://play.google.com/store/apps/details?id=et.safaricom.mpesa.lifestyle

#SafaricomEthiopia

Читать полностью…

Tikvah-University

#NGAT

የድኅረ-ምረቃ ፕሮግራሞች ብሔራዊ የመግቢያ ፈተና (NGAT) ነገ መጋቢት 12/2017 ዓ.ም ከጠዋት 3፡00 ሰዓት ጀምሮ ይሰጣል፡፡

ፈተናው በመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ በሚገኙ የፈተና ማዕከላት የሚሰጥ ይሆናል፡፡

ተፈታኞች ወደ ፈተና ማዕከል በምትሔዱበት ወቅት የመፈተኛ User Name እና Password እንዲሁም ማንነታችሁን የሚገልጽ መታወቂያ መያዝ ይጠበቅባችኋል፡፡

በምዝገባ ወቅት ፕሪንት ያሉትን ፎቶዎን በግልፅ የሚያሳይ Test Admission Ticket (TAT) መያዝም አይዘንጉ፡፡

ማንኛውም ተፈታኝ ፈተናው ከመጀመሩ 30 ደቂቃ በፊት በፈተና ማዕከል መገኘት የሚጠበቅበት ሲሆን፤ ተንቀሳቃሽ ስልክ ይዞ በፈተና ማዕከል መገኘት ፈፅሞ የተከለከለ ነው፡፡

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

በሀገሪቱ የሚገኙ ትምህርት ቤቶችን በዲጂታል የመመዝገብ (School Mapping) ሥራ ጀምረናል። - ትምህርት ሚኒስቴር

ከሕዝብ ለቀረቡ ጥያቄዎች ምላሽ የሰጡት የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር)፤ በሀገሪቱ ውስጥ የሚገኙ ትምህርት ቤቶችን በሙሉ ቴክኖሎጂን በመጠቀም ማፕ የማድረግ ሥራ እየተሰራ እንደሚገኝ ገልፀዋል።

በዚህም ትምህርት ቤቶቹ በሚገኙባቸው አካባቢዎች ያሉ ተማሪዎች ብዛትን በማየት የት ነው ትምህርት ቤት መገንባት የሚያስፈልገው የሚለውን በደረጃ ለይተናል ብለዋል።

በጉዳዩ ላይ ከክልል ትምህርት ቢሮዎች ኃላፊዎች ጋር መወያየታቸውንም ሚኒስትሩ ጠቁመዋል።

በ School Mapping ፕሮጀክቱ አማካኝነት የተጎዱ እንዲሁም ትምህርት ቤት በጣም የሚያስፈልጋቸው አካባቢዎች ተለይተው፥ ዝርዝር እየወጣ መሆኑን ተናግረዋል።

ፕሮጀክቱ ሙሉ ለሙሉ ሲተገበር የትምህርት ቤት አቅርቦት ለሁሉም በእኩል ለማዳረስ ያስችላል ብለዋል።

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

ከUAE ገንዘብ በM-PESA እንቀበል! 10% ስጦታ እና 1ጊ.ባ ኢንተርኔት ተጨማሪ አሁኑኑ እናግኝ! ቪዛ፣ ማስተርካርድ ወይም አሜክስ ካርድ በመጠቀም በካሽ ጎ በኩል እንላክ።

የምንዛሬ ተመን
1 AED = 34.5 ብር

ተከታዩን ሊንክ በመጠቀም 'ካሽ ጎ'ን እናውርድ 👇 https://play.google.com/store/apps/details?id=com.bankofabyssinia.cashgo

ገንዘብዎን በዳሽን ባንክ ዕለታዊ የውጭ ምንዛሬ ያግኙ + 10% ስጦታ

#MPESAEthiopia #MPESASafaricom

Читать полностью…

Tikvah-University

#MoE

የመምህራን ትምህርት ኮሌጆች የብቃት ማረጋገጫ ምዝገባና ዕውቅና ስርዓት ሊተገበር ነው።

የመምህራን ማሰልጠኛ ኮሌጆች ጥራትና ፈተናዎች ላይ ትኩረት ያደረገ የምክክር መድረክ ተካሒዷል።

በምክክር መድረኩ ላይ የተገኙት የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር)፥ በትምህርት ዘርፍ ከቅድመ አንደኛ እስከ ከፍተኛ ትምህርት የተለያዩ ሪፎርሞች ተቀርፀው ተግባራዊ እየተደረጉ መሆኑን አንስተዋል።

የተጀመሩ የሪፎርም ተግባራት ውጤታማ እንዲሆኑ ለመምህራን ልዩ ትኩረት በመስጠት መስራት እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።

የአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አየለች እሸቴ በበኩላቸው "ከመምህራን ስልጠናና አስተዳደር ጋር የተያያዙ ችግሮችን በሚገባ ለይቶ መፍታት ካልተቻለ የትምህርት ጥራትን ማረጋገጥ አይቻልም" ብለዋል።

በዚህም የመምህራን ማሰልጠኛ ኮሌጆች ብቃት ማረጋገጫ ምዝገባና ዕውቅና ሥርዓትን ወደ ትግበራ ማስገባት ያስፈልጋል ተብሏል።

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

አስደናቂ ቀን 🎉🏃‍♀️

የሳፋሪኮም ቅድሚያ ለሴቶች 5ኪሜ ሩጫ 16 ሺህ የሚሆኑ አስደናቂ ሴቶችን አንድ ላይ አሰባስቧል፤ እጅግ በጣም በደመቀ ሁኔታ ጥንካሬያቸውን አሳይቷል! አንደኝነታቸውን አስመስክረዋል💪✨

ቀጠሯችሁን አክብራቹ ስለተገኛቹ እናመሰግናለን! በቀጣይ ዓመት በሰላም እንገናኝ!

#SafaricomEthiopia #Andegna #አንደኛ #1Wedefit #FurtherAheadTogether

Читать полностью…

Tikvah-University

#Fake_Account_Alert

ሰላሌ ዩኒቨርሲቲ በተቋሙ ሎጎ እና ‘Selale University’ በሚል ስያሜ በተከፈተ የፌስቡክ ገጽ የሚተላለፍ መረጃ ሐሰተኛ እና ዩኒቨርሲቲውን የሚወክል እንዳልሆነ ገልጿል፡፡

የሰላሌ ዩኒቨርሲቲ ይፋዊ የፌስቡክ ገጽ Salale University /Official Page/ የሚል ሲሆን፤ 70 ሺህ ተከታዮች እና 38 ሺህ ላይክ ያለው መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

ትክክለኛውን የሰላሌ ዩኒቨርሲቲ የፌስቡክ ገጽ ለማግኘት 👇
https://web.facebook.com/salaleuniversity

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

22ኛ ዙር የድረ-ገፅ እና ሞባይል መተግበሪያ ማበልፀግ (Full-Stack Website and Mobile Application Development) ስልጠና በፒያሣ እና በመገናኛ ካምፓስ የፊታችን ቅዳሜ መጋቢት 13/2017 ዓ.ም በቅዳሜ እና እሑድ መርሐግብር ይጀምራል።   

👉 ተግባርን ከንድፈ ሀሳብ ያስተሳሰረ ስልጠና
👉 ፕሮግራሚንግ ትምህርቶችን አካቶ የሚሰጥ
👉 Front-end እና Back-end በአንድ ላይ እስከ Deployment ያካተተ
👉 በተግባር ድረ ገጾችን እና ሞባይል መተግበሪያዎችን እያበለፀጉ የሚሰለጥኑበት
👉 የሥራ ላይ ስልጠና (Internship) የተመቻቸለት

☎️   0906777799 / 0906777755
አድራሻ
ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ
ቁ.2: መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ

Telegram: /channel/sagetraininginstitute
TikTok: sage_training_institute" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@sage_training_institute
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute

Читать полностью…

Tikvah-University

#EducationDiplomacy

ወሎ ዩኒቨርሲቲ ባሳለፍነው ቅዳሜ 20 የህክምና ባለሙያዎችን በስፔሻሊቲ ማስመረቁ ይታወቃል።

ከተመራቂዎቹ መካከል ሁለቱ ከሶማሊያ እና ከደቡብ ሱዳን የመጡ ሀኪሞቹ ሲሆኑ፤ የኢትዮጵያ መንግሥት ነጻ የትምህርት ዕድል ተጠቃሚ መሆናቸው ተገልጿል፡፡

ዶ/ር አብዱራህማን ረሺድ ከሶማሊያ እና ዶ/ር ጂየንግ አትያን ከደቡብ ሱዳን በጠቅላላ ቀዶ ሕክምና የስፔሻሊቲ ትምህርታቸውን ላለፉት አራት ዓመታት በወሎ ዩኒቨርሲቲ ተከታትለው አጠናቀዋል።

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

ተራዝሟል!

በመጀመሪያ ዲግሪ ተመርቃችሁ የብቃት ምዘና ፈተና ለመፈተን በመጠባበቅ ላይ ለምትገኙ የጤና ባለሙያዎች የፈተና ምዝገባው እስከ መጋቢት 10/2017 ዓ.ም የተራዘመ መሆኑን ጤና ሚኒስቴር አሳውቋል፡፡

የአመልካቾች ምዝገባ ከየካቲት 24/2017 ዓ.ም እስከ መጋቢት 07/2017 ዓ.ም ድረስ ሲከናወን መቆየቱ ይታወቃል።

ይሁን እንጂ አንዳንድ ተመራቂዎች የቴምፖራሪ ዲግሪ ያልደረሰላቸው መሆኑንና (ቴምፖራሪ ዲግሪ መያዝ ግዴታ በመሆኑ) ምዝገባው እንዲራዘምላቸው መጠየቃቸውን ተከትሎ፤ ምዝገባው ለተጨማሪ ሦስት ቀናት ማለትም እስከ መጋቢት 10/2017 ዓ.ም የተራዘመ መሆኑን ሚኒስቴሩ ገልጿል፡፡

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

#DebarkUniversity

ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ የግዕዝ ቋንቋ ስልጠና መስጠት ጀመረ።

ዩኒቨርሲቲው ከ300 በላይ ፍላጎት ላላቸው የዩኒቨርሲቲው እና የአካባቢው ማህበረሰብ አባላት የመካከለኛ ጊዜ የግዕዝ ቋንቋ ስልጠና መስጠት ጀምሯል።

በደባርቅ ከተማ አስተዳደር ውስጥ ከሚገኙ አድባራት መስፈርቱን አሟልተው በተመረጡ የቋንቋው ምሁራን የሚሰጠው የግዕዝ ቋንቋ ስልጠና በቅዳሜና እሑድ መርሐግብር ለሦስት ተከታታይ ወራት የሚሰጥ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል፡፡

ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ በመጀመሪያ ዲግሪ ፕሮግራም የግዕዝ ቋንቋ ትምህርት ክፍል ለመክፈት በማቀድ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል።

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

#Digital_ID

ዩኒቨርሲቲዎች የብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ (ፋይዳ) ምዝገባ ማድረግ ጀምረዋል።

በሰኔ 2017 ዓ.ም የሚሰጠውን የመውጫ ፈተና የሚወስዱ ዕጩ ተመራቂዎች የፋይዳ መታወቂያ ሊያወጡ እንደሚገባ ትምህርት ሚኒስቴር ማሳወቁ ይታወሳል።

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

ወሎ ዩኒቨርሲቲ 20 የስፔሻሊቲ ህክምና ባለሙያዎችን አስመርቋል።

ተመራቂ ሬዚደንት ሀኪሞቹ የስፔሻሊቲ ትምህርታቸውን ላለፉት አራት ዓመታት በወሎ ዩኒቨርሲቲ ተከታትለው ያጠናቀቁ ናቸው።

ተመራቂዎቹ 11 የጠቅላላ ቀዶ ሕክምና እና 9 የማህጸንና ጽንስ ህክምና ስፔሻሊቲ ሀኪሞች መሆናቸው ተገልጿል።

@tikvahuniversity

Читать полностью…
Subscribe to a channel