Entrepreneurship, Digital Marketing & Business Management ስልጠና በፒያሣ እና በመገናኛ ካምፓስ ምዝገባ ላይ ነን።
👉 የሽያጭ መንገዶች እና ቢዝነስ ፕሮፖዛል አዘገጃጀት ብቃትን የሚያገኙበት
👉 ዲጂታል ማርኬቲንግ በተግባር የሚሰጥበት
👉 በተጨማሪነት የቢዝነስ አመራር እና ሥራ ፈጠራ (Enterprenurship) ስልጠናን አካቷል
👉 ለመክፈት የሚያስቡት ቢዝነስ ከስልጠና እስከ ማማከር ተካቶ የሚሰጥ
👉 የሥራ ላይ ስልጠና የተመቻቸለት
☎️ 0906777799 / 0906777755
አድራሻ
ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ
ቁ.2: መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ
Telegram: /channel/sagetraininginstitute
TikTok: sage_training_institute" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@sage_training_institute
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute
#TVTI
በፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት በደረጃ 7 (2ኛ ዲግሪ) ለመማር ያመለከታችሁና የድኅረ-ምረቃ የመግቢያ ፈተና (NGAT) ተፈትናችሁ ማለፊያ ነጥብ ያመጣችሁ በሙሉ እስከ አርብ መጋቢት 26/2017 ዓ.ም ከቀኑ 6:00 ሰዓት ድረስ በኢንስቲትዩቱ ሬጅስትራርና አልሙናይ ዳይሬክቶሬት በአካል ተገኝታችሁ ሪፖርት እንድታደርጉ ተቋሙ አሳስቧል፡፡
@tikvahuniversity
አነስተኛ ትራክተር የሠሩ ወጣቶች 👏
የመጀመሪያው ዙር የክህሎት ኢትዮጵያ ፕሮግራም ተሰታፊዎች የሆኑት ስመኝ ኢሳያስ እና ጓደኞቿ ግብርናን የሚያዘምን አነስተኛ ትራክተር ሠርተዋል፡፡
ፈጠራው ከሰባት በላይ የግብርና አገልግሎቶችን በአንድ አጣምሮ የያዘ ሲሆን፤ ማረሻ፣ መዝሪያ፣ ሰብል ማጨጃ፣ መውቂያ፣ እህል ማበጠሪያ፣ ሰብል ማጓጓዣ እና የመስኖ ውሃ ፓምፕ የግብርና ሥራዎች ማከናወን የሚያስችል ቴክኖሎጂ ነው፡፡
ተጠቃሚዎች እንደ አቅምና ፍላጎታቸው በሙሉ ወይም በተናጠል ቴክኖሎጂውን መግዛት እንደሚችሉ የፈጠራው ባለቤቶች ገልፀዋል፡፡
ሁሉንም አገልግሎቶች የሚሰጠው ይህ ቴክኖሎጂ በአንድ ሚሊዮን ብር ለገበያ ቀርቧል፤ ማረሻ እና ለመስኖ ልማት የሚውል የውሃ ፓምፕ የያዘው ቴክኖሎጂ ደግም በ327 ሺህ ብር ብቻ መግዛት ይችላሉ ተብሏል፡፡
Multi-Purpose Mini Tractor የተሰኘው ቴክኖሎጂው በተለያዩ የእርሻ ማሳዎች ላይ ተሞክሮ ውጤታማነቱ ተረጋግጧል፡፡ #PMOEthiopia
@tikvahuniversity
2ኛ ዙር የዓለም አቀፍ ግብይት (Import and Export Business) ስልጠና በፒያሣ እና በመገናኛ ካምፓስ ምዝገባ ላይ ነን!
🔔 ፈጥነው ይመዝገቡ!
👉 ተግባርን ከንድፈ ሀሳብ ያስተሳሰረ ስልጠና
👉 ሀገራዊ እና ዓለም አቀፋዊ አሰራሮች የሚተነተንበት
👉በዘርፉ ከፍተኛ ልምድ ባላቸው አሰልጣኞች የሚሰጥ
☎️ 0906777799 / 0906777755
አድራሻ
ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ
ቁ.2: መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ
Telegram: /channel/sagetraininginstitute
TikTok: sage_training_institute" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@sage_training_institute
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute
#RemedialExam
የ2017 ትምህርት ዘመን የሪሚዲያል ተማሪዎች ከማዕከል የሚሰጥ ፈተና ከግንቦት 26-30/2017 ዓ.ም እንደሚሰጥ ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል፡፡
በሚኒስቴሩ የአካዳሚክ ጉዳዮች መሪ ሥራ አስፈጻሚ ኤባ ሜጄና (ዶ/ር) በቀን መጋቢት 15/2017 ተፈርሞ ለሁሉም የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች እና ለሁሉም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በጻፉት ሰርኩላር፤ የ2017 ዓ.ም የሪሚዲያል ተማሪዎች የማጠቃለያ ግምገማ ከ100% ከማዕከል እንደሚሆን አስታውሰዋል፡፡
የሪሚዲያል ተማሪዎች ከዚህ በፊት 70% በማዕከል እና 30% በተቋማት የሚዘጋጁ ምዘናዎችን ይወስዱ የነበረ ሲሆን፤ ከ2017 የትምህርት ዘመን ጀምሮ የሪሚዲያል ተማሪዎች የማጠቃለያ ምዘና ከ100% ከማዕከል እንዲሰጥ በጥቅምት 2017 ዓ.ም መወሰኑ ይታወሳል፡፡
በዚህም የ2017 ዓ.ም የሪሚዲያል ተማሪዎች በሚማሩበት ተቋም የሚሰጥ የተከታታይና የማጠቃለያ ፈተና ውጤት ለትምህርት ሚኒስቴር የሚላክ ይሆናል፡፡ ከዛም በማዕከል በሚሰጥ ፈተና የተማሪዎቹ መቀጠል እና አለመቀጠል የሚወሰን ይሆናል፡፡
(ከላይ የተያያዘውን ሰርኩላር ትክክለኛነት ቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ከትምህርት ሚኒስቴር አረጋግጧል፡፡)
@tikvahuniversity
🌐 እጅግ ፈጣን ዋይፋይ በአዲስ ቅመም! ከጉርሻ ጋር 🤗
💨⚡️ እስከ 6 ሰዓት የሚቆይ የባትሪ አቅም ያለውና አዳዲስ የቴክኖሎጂ ትሩፋቶችን ይዞ በአንዴ እስከ 8 ሰው ድረስ የሚያስጠቅመውን ልዩ ቅመም MIFIን ገዝተን ፈጣን 4G ኢንተርኔት እንጠቀም!
🍰 ለ30 ቀን ከሚቆይ ነጻ 30ጊባ ዳታ ጉርሻ ጋር!
ከሳፋሪኮም ጋር አንድ ወደፊት ⚡️
🔗 የM-PESA ሳፋሪኮም መተግበሪያ በዚህ ሊንክ እናውርድ፦ https://play.google.com/store/apps/details?id=et.safaricom.mpesa.lifestyle
#SafaricomEthiopia
የሀገር አቀፍ የድኅረ-ምረቃ ፕሮግራም የመግቢያ ፈተና (NGAT) ውጤት መመልከቻ ፦ https//:result.ethernet.edu.et
@tikvahuniversity
#TVTI #ExitExam
የፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት የ2017 ትምህርት ዘመን የመውጫ ፈተና ከነገ መጋቢት 18/2017 ዓ.ም ጀምሮ ለሁለት ተከታታይ ቀናት ይሰጣል።
ፈተናው በኢንስቲትዩቱ ዋና ግቢ እና በኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ በሚገኙ የፈተና ማዕከት እንደሚሰጥ ተገልጿል።
ኢንስቲትዩቱ የመውጫ ፈተና የሚወስዱ የተቋሙን ሰልጣኞች እና በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ቴክስታይልና ፋሽን ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የጋርመንት ቴክኖሎጂ ሰልጣኞች ምዝገባ በኦንላይን እና በአካል ምዝገባ ሲያደርግ መቆየቱ ይታወቃል።
(ነገ መጋቢት 18/2017 ዓ.ም የሚጀምረው የኢንስቲትዩቱ የመውጫ ፈተና መርሐግብር ከላይ ተያይዟል።)
@tikvahuniversity
#ScholarshipTip
ለ University of Calabria Scholarships 2025 ያመልክቱ!
በካላብርያ ዩኒቨርሲቲ የ2025 ስኮላርሺፕ ሙሉ ወጪዎ ተሸፍኖ በጣልያን ሀገር ትምህርትዎን እንዲከታተሉ የሚያስችሉ ነው፡፡
ነጻ የትምህርት ዕድሉ በመጀመሪያ ዲግሪ እና በማስተርስ ደረጃ የሚሰጥ ሲሆን፤ አፍሪካውያን (ከአውሮጳ ውጭ ያሉ) ተማሪዎችን ተጠቃሚ ያደርጋል፡፡
የማመልከቻ ጊዜ የሚያበቃው፦
ሚያዝያ 02/2017 ዓ.ም
ለማመልከት 👇
https://www.unical.it/internazionale/intenational-students/unical-admission/
@tikvahuniversity
ጎማን መልሶ ጥቅም ላይ የሚያውል ማሽን የሠሩ ፈጣሪዎች 👏
ሰለሞን ታፈሰ እና ጓደኞቹ የክህሎት ኢትዮጵያ 2ኛ ዙር ተወዳዳሪዎች ሲሆኑ፤ ጥቅም ላይ የዋሉ ጎማዎችን በመጠቀም የተለያዩ ምርቶችን ለመስራት የሚያስችል ማሽን ፈጥረዋል።
ማሽኑ የወዳደቁ ጎማዎችን በመጠቀም የህጻናት መጫወቻ ስፍራዎች፣ የእግረኞች መንገድ ታይልስ እንዲሁም Rubberized አስፓልት ለመገንባት የሚውል ማቴሪያልን ያመርታል።
የማምረቻ ፕሮጀክቱ 15 ማሽኖችን በውስጡ የያዘ ሲሆን፤ 500 ኪሎ ግራም ምርት በሰዓት የማምረት አቅም አለው።
20 ሚሊዮን ብር እንደፈጀ የሚናገሩት ፈጣሪዎቹ፤ ምርቶቻቸውን ለማከፋፈል ገበያ እንደሚፈልጉ ገልፀዋል። #PMOEthiopia
@tikvahuniversity
#ScholarshipTip
ለ Mandela Rhodes Scholarships 2025-26 ያመልክቱ!
በማንዴላ ሮድስ ፋውንዴሽን የሚሰጠው ነጻ ትምህርት ዕድል፣ ሙሉ ወጪዎ ተሸፍኖ በደቡብ አፍሪካ ትምህርትዎን/ምርምርዎን እንዲከታተሉ የሚያስችል ነው፡፡
ነጻ የትምህርት ዕድሉ በማስተርስ ደረጃ እንዲሁም ለምርምር የሚሰጥ ሲሆን፤ አፍሪካውያን ተማሪዎችን/ተመራማሪዎችን ተጠቃሚ ያደርጋል፡፡
የማመልከቻ ጊዜ የሚያበቃው፦
ሚያዝያ 13/2017 ዓ.ም
ለማመልከት 👇
https://www.mandelarhodes.org/scholarship/apply/
@tikvahuniversity
የኤሌክትሪክ ዊልቼር የሰራው ወጣት 👏
አቤል ማስረሻ የክህሎት ኢትዮጵያ 2ኛ ዙር ተወዳዳሪ ሲሆን፤ አካል ጉዳተኞችን ተጠቃሚ የሚያደርግ የኤሌክትሪክ ዊልቼር ሰርቷል።
Mobix Smart Electric Wheelchair የተሰኘው ፈጠራው፤ እጅግ ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎች ተገጥሞለታል።
የኤሌክትሪክ ዊልቼሩ በሞባይል አፕ አማካኝነት እና በጆይስቲክ የሚሰራ የመቆጣጠሪያ አማራጭ የተሟላለት ነው።
ዊልቼሩ እስከ 65 ሺህ ብር ዋጋ የወጣለት መሆኑ ተገልጿል።
የፋይናንስ ድጋፍ ቢደረግለት በብዛት ለማምረት ፍላጎት እንዳለው የገለፀው ወጣቱ፤ ምርቱን ከኢትዮጵያ በተጨማሪ ለአፍሪካ ገበያ ለማቅረብ እንደሚሰራ ገልጿል። #ጠቅላይ_ሚኒስትር_ጽህፈት_ቤት
@tikvahuniversity
የኮምፒውተር ፕሮግራሚንግ እና ዳታቤዝ (Computer Programming and Database) ስልጠና በፒያሣ እና በመገናኛ ካምፓስ ምዝገባ ላይ ነን!
🔔 ፈጥነው ይመዝገቡ!
👉 ተግባርን ከንድፈ ሀሳብ ያስተሳሰረ ስልጠና
👉 C++, Java እና Python ፕሮግራሞች ከፍ ባለ ደረጃ በጋራ የሚሰጡበት
👉 ፕሮጀክቶችን እየሰሩ የሚሰለጥኑበት
☎️ 0906777799 / 0906777755
አድራሻ
ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ
ቁ.2: መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ
Telegram: /channel/sagetraininginstitute
TikTok: sage_training_institute" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@sage_training_institute
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute
የካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ በተለያዩ የጤና ሙያ መስኮች ያስተማራቸውን 186 ተማሪዎች አስመረቀ።
ኮሌጁ በሰብ-ስፔሻላይዜሽን ለመጀመሪያ ጊዜ እንዲሁም በመጀመሪያ ዲግሪ፣ በስፔሻላይዜሽን እና በሁለተኛ ዲግሪ ፕሮግራሞች ያስተማራቸውን ተማሪዎች አስመርቋል፡፡
ተመራቂዎቹ በውስጥ ደዌ፣ በቀዶ ጥገና፣ በማህፀንና ፅንስ፣ በአፍ ውስጥ በመንጋጋና በፊት ቀዶ ጥገና፣ በጤና አጠባበቅ ስርዓት፣ በኅብረተሰብ ጤና፣ በስነ-ተዋልዶ እና በሌሎች የህክምና መስኮች ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ መሆናቸው ተገልጿል፡፡
@tikvahuniversity
#NGAT
ሦስተኛው ዙር ብሔራዊ የድኅረ-ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) ዛሬ መጋቢት 12/2017 ዓ.ም ተሰጥቷል።
ፈተናው በመላ ሀገሪቱ በመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ በሚገኙ የፈተና ማዕከላት ሲሰጥ ውሏል።
ምስል፦ ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ እና ዲላ ዩኒቨርሲቲ
@tikvahuniversity
#PostgraduateAdmission
የድኅረ-ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና ውጤት መለቀቅን ተከትሎ ዩኒቨርሲቲዎች ለ2017 አጋማሽ ዓመት የድኅረ-ምረቃ ቅበላ ማስታወቂያ ማውጣት ጀምረዋል፡፡
➫ የ'NGAT' ውጤትዎ 50 ከመቶ እና ከዚያ በላይ ሊሆን ይገባል፡፡
➫ ውጤትዎን ይመልከቱ 👉 https://result.ethernet.edu.et
➫ ዕውቅና ካለው ከፍተኛ ትምህርት ተቋም የተመረቁ መሆንዎን የሚገልፅ የመጀመሪያ ዲግሪ ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው ያስፈልጋል፡፡
➫ የቅርብ ጊዜ ፓስፖርት መጠን አራት ፎቶግራፍ ያስፈልጋል፡፡
➫ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በኩል የምዝገባ ክፍያ በመፈፀም ደረሰኝ ሊይዙ ይገባል፡፡
@tikvahuniversity
በነፃ ብር በመላክ የM-PESAን ነፃ አገልግሎት እናጣጥም! ከM-PESA ወደ የትኛውም የሳፋሪኮም ስልክ በነፃ እንላክ!
#MPESASafaricom #MPESAEthiopia
#ጥቆማ
የስነ-ጥበባት አውደ ርዕይ በኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ ተከፍቷል፡፡
በዩኒቨርሲቲው የስነ-ጥበባት ትምህርት ክፍል መምህራን እና ተማሪዎች ትብብር የተዘጋጀው አውደ ርዕዩ ለሦስት ቀናት ለታዳሚያን ክፍት ሆኖ ይቆያል፡፡
በአውደ ርዕዩ የስዕል ሥራዎች፣ አጫጭር ፊልሞች፣ ሕብረ-ዝማሬዎች፣ ዘመናዊ ውዝዋዜዎች እና በመሣሪያ የተቀነባበሩ መዚቃዎች ለታዳሚዎች ቀርበዋል፡፡
@tikvahuniversity
#ጥቆማ
#MinT
ተመራማሪ ነዎት? ለዕርስዎ የሚሆን ዕድል እንጠቁምዎ!
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከ Science Grant Council Initiative (Africa-UK Physics Partnership Programme) ጋር በመተባበር የዘርፉን ተመራማሪዎች ተጠቃሚ የሚያደርግ Intra-Africa Research Mobility and Networking ዕድል አመቻችቷል።
ከስር የተያያዘው መመሪያ ውስጥ የተጠቀሱ መስፈርቶችን የምታሟሉ አመልካቾች https://nrfconnect.nrf.ac.za ማስፈንጠሪያን በመጠቀም መመዝገብ እንደምትችሉ ተገልጿል።
ፕሮግራሙን በተመለከት አርብ መጋቢት 26/2017 ዓ.ም ጠዋት ከ4:00-5:30 በ Online Meeting ገለጻ ይሰጣል።
ለገለጻው የመመዝገቢያ ሊንክ 👇
https://zoom.us/j/93571712656pwd=jVWClRmrV7HfmRidFAg6324YWZhNT9.1
Meeting ID: 935 7171 2656
Passcode: 3UPWJA
መመሪያ፦
http://www.mint.gov.et/web/am/%E1%88%98%E1%88%A8%E1%8C%83%E1%8B%8E%E1%89%BD
@tikvahuniversity
#ETA
የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የ2017 ዓ.ም ተመራቂ ተማሪዎችን ዝርዘር መረጃ እንዲልኩ የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን አሳስቧል።
በዚህም ተቋማቱ ፈቃድ በተሰጣቸው የትምህርት መስኮች፣ የትምህርት ደረጃ፣ መርሐግብር እና ካምፓስ የተመረቁ ተማሪዎችን መረጃዎች በድኅረ-ምረቃ ደረጃ እና በመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎች መውጫ ፈተና ያለፉ ብቻ ከዚህ በፊት በተላከው ቅጽ መሰረት ዝርዝር መረጃውን ከመጋቢት 16-30/2017 ዓ.ም በሶፍት እና በሀርድ ኮፒ እንዲልኩ ባለሥልጣኑ ጠይቋል።
@tikvahuniversity
የኮምፒውተር ጥገና እና ኔትዎርኪንግ (Computer Maintenance and Networking) ስልጠና በፒያሣ እና በመገናኛ ካምፓስ ምዝገባ ላይ ነን።
👉 ንድፈ ሀሳብን ከተግባር በማዛመድ የሚሰጥ ስልጠና
👉 የሥራ ላይ ስልጠና የተመቻቸለት
☎️ 0906777799 / 0906777755
አድራሻ
ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ
ቁ.2: መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ
Telegram: /channel/sagetraininginstitute
TikTok: sage_training_institute" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@sage_training_institute
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute
የካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ የፖስት ቤዚክ መደበኛ ተማሪዎች የመጀመሪያ ዓመት አንደኛ ሴሚስተር ምዝገባ ከመጋቢት 17-22/2017 ዓ.ም መሆኑን ገልጿል።
የማመልከቻ እና የሴሚስተር ምዝገባ ክፍያ በኮሌጁ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት መከፈል እንዳለበት ተገልጿል።
ትምህርት መጋቢት 29/2017 ዓ.ም ይጀምራል ተብሏል።
@tikvahuniversity
በነፃ ብር በመላክ የM-PESAን ነፃ አገልግሎት እናጣጥም! ከM-PESA ወደ የትኛውም የሳፋሪኮም ስልክ በነፃ እንላክ!
#MPESASafaricom #MPESAEthiopia
4ኛ ዙር የፋይናንስ እና ካፒታል ማርኬት ስልጠና በፒያሣ እና በመገናኛ ካምፓስ ምዝገባ ላይ ነን!
👉 ፈጥነው ይመዝገቡ!
የካፒታል ማርኬት ገበያ በኢትዮጵያ ተጀምሯል። እርስዎም በሴጅ ኢንስቲትዩት የሚሰጠውን የፋይናንስና ካፒታል ማርኬት ስልጠና በመውሰድ በገበያው ለመሳተፍ ራስዎን ያዘጋጁ።
ብቁ በሆኑ መምህራን የሚሰጠውን ስልጠና ይውሰዱና ትግበራውን ይጠባበቁ!
☎️ 0906777799 / 0906777755
አድራሻ
ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ
ቁ.2: መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ
Telegram: /channel/sagetraininginstitute
TikTok: sage_training_institute" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@sage_training_institute
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute
🌐 እጅግ ፈጣን ዋይፋይ በአዲስ ቅመም! ከጉርሻ ጋር 🤗
💨⚡️ እስከ 6 ሰዓት የሚቆይ የባትሪ አቅም ያለውና አዳዲስ የቴክኖሎጂ ትሩፋቶችን ይዞ በአንዴ እስከ 8 ሰው የሚያስጠቅመውን ልዩ ቅመም MIFI ን ገዝተን ፈጣን 4G ኢንተርኔት እንጠቀም!
🍰 ለ30 ቀን ከሚቆይ ነጻ 30ጊባ ዳታ ጉርሻ ጋር!
ከሳፋሪኮም ጋር አንድ ወደፊት⚡️
🔗 የM-PESA ሳፋሪኮም መተግበሪያ በዚህ ሊንክ እናውርድ፦ https://play.google.com/store/apps/details?id=et.safaricom.mpesa.lifestyle
#SafaricomEthiopia
የዲጂታል ማርኬቲንግ ስልጠና በፒያሣ እና በመገናኛ ካምፓስ ምዝገባ ላይ ነን!
👉 በሁለት ወር ምርጥ የዲጂታል ማርኬቲንግ ባለሙያ የሚያደርግዎት
👉 ንድፈ ሀሳብን ከተግባር ያስተሳሰረ ስልጠና
☎️ 0906777799 / 0906777755
አድራሻ
ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ
ቁ.2: መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ
የበለጠ ይጠብቁ ...
💥 ሴጅ ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት 💥
Telegram: /channel/sagetraininginstitute
TikTok: sage_training_institute" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@sage_training_institute
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute
በፀጥታ ችግር ምክንያት በኢትዮጵያ ከ7.2 ሚሊዮን በላይ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታቸው አልተመለሱም፡፡ - የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር)
በባሕር ዳር በመካሔድ ላይ በሚገኘው የአማራ ክልል የትምህርት ንቅናቄ መድረክ ላይ የተገኙ የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር)፤ በፀጥታ ችግር ምክንያት በኢትዮጵያ ከ7.2 ሚሊዮን በላይ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታቸው እንዳልተመለሱ ተናግረዋል።
በአማራ ክልልሉ በዘንድሮው የትምህርት ዘመን 7 ሚሊዮን ተማሪዎችን መዝግቦ ለማስተማር ቢታቀድም፤ በፀጥታ ችግር ምክንያት የተመዘገቡት ተማሪዎች 2.8 ሚሊየን ብቻ መሆናቸው ተገልጿል፡፡
ችግሩን ለመቅረፍ በትምህርት ዘመኑ በሁለት ዙር በተደረጉ ኢ-መደበኛ ምዝገባ 76 ሺህ ተማሪዎች ብቻ መመዝገባቸውን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ ገልፀዋል።
መድረኩ በክልሉ የትምህርት ዘርፍ በደረሰው ጉዳት ላይ በመምከር ቀጣይ አቅጣጫዎችን እንደሚያስቀምጥ ይጠበቃል፡፡
@tikvahuniversity
#ጥቆማ
5 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ኮደርስ ኢንሼቲቭ ነፃ ስልጠናን ለመከታተል ይመዝገቡ።
ዓለም አቀፍ ተቀባይነት ያለው ሰርትፍኬት ማግኘት የሚያስችልዎትን ስልጠና ባሉበት ሆነው ይውሰዱ።
የስልጠና ዘርፎች፦
► ዌብ ፕሮግራሚንግ
► አንድሮይድ ማበልፀግ
► ዳታ ሳይንስ
► አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ፋንዳሜንታልስ
ለመመዝገብ 👇
https://www.ethiocoders.et/
በተሰጠው ስምንት ሳምንት ስልጠናውን ሲያጠናቅቁ፥ ዓለም አቀፍ ተቀባይነት ያለው ሰርተፊኬት ይበረከትልዎታል።
@tikvahuniversity
4ኛ ዙር የፎቶግራፊ፣ ቪዲዮግራፊ፣ ግራፊክ ዲዛይን እና ቪዲዮ ኤዲቲንግ ስልጠና ምዝገባ ላይ ነን!
👉 ተግባርን ከንድፈ ሀሳብ ያስተሳሰረ ስልጠና
👉 Photography, Videography, Cinematography, Graphic Design and Video Editing በአንድ ላይ
👉 ፕሮጀክቶችን በስቱዲዮ እና በመስክ በመስራት የሚሰጥ
☎️ 0906777799 / 0906777755
አድራሻ
ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ
ቁ.2: መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ
Telegram: /channel/sagetraininginstitute
TiTok: sage_training_institute" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@sage_training_institute
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute
#AAU
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በትብብር የሚሰጠውን 'ሊድ ላይፍ ዲዛይን ላብ' / LEAD Life Design Lab የትምህርት ፕሮግራም ለመከታተል ይመዝገቡ!
ፕሮግራሙ ተማሪዎች ከፅንሰ ሐሳብ ትምህርት በተጨማሪ ተግባር ተኮር ክህሎቶችን እንዲያዳብሩ የሚያስችል ነው።
ተማሪዎች በሚኖራቸው የትምህርት ቆይታ በኮሙኒኬሽን፣ በቴክኖሎጂ እና በሌሎች 13 ክህሎቶች ታንፀው እንዲወጡ የሚያስችል ፕሮግራም መሆኑ ተገልጿል፡፡
በፕሮግራሙ የሚሰጡ ስልጠናዎች በአካል እና በኦንላይን አማራጮች ተደራሽ ይሆናሉ።
በፕሮግራሙ ለመሳተፍ ይመዝገቡ 👇
https://leadlifedesignlab.com/
@tikvahuniversity