tikvahuniversity | Unsorted

Telegram-канал tikvahuniversity - Tikvah-University

308824

Subscribe to a channel

Tikvah-University

#MoE

ትምህርት ሚኒስቴር በቁልፍ የአፈጻጸም አመላካቾች (KPIs) ከሁሉም የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ጋር ስምምነት ተፈራረመ።

ስምምነቱ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማቱ ብቃትና ችሎታ ያላቸው ምሩቃንን በማፍራት ሂደት ውስጥ ተጠያቂነትን ከማስፈን ባለፈ ውጤታማነትን ለማረጋገጥ የሚያስችል ነው ተብሏል፡፡

ስምምነቱ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ግልጽነትና ተጠያቂነትን ያሰፈነ አመራር እንዲከተሉ፣ አገሪቱ ለምታወጣው ሀብት ተመጣጣኝ ውጤት እንዲያስገኙ፣ የአፈጻጸም አቅማቸው እንዲገመገምና ለስኬቱም ዕውቅና እና ሽልማት እንዲያገኙ የሚያስችል መሆኑ ተገልጿል፡፡

በስምምነቱ ወቅት ንግግር ያደረጉት የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) "ዩኒቨርሲቲዎች የሚመደብላቸው በጀት ባስመዘገቡት ውጤት ልክ እንደሚሆን" ገለፀዋል።

የስምምነት ውሉ በየዩኒቨርሲቲዎቹ ስር ወደሚገኙ ኮሌጆች፣ ትምህርት ክፍሎች እና ሌሎች ፅህፈት ቤቶች በየደረጃው እንደሚወርድ ይጠበቃል።

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

#MekelleUniversity

በቅርቡ በትምህርት ሚኒስቴር ፀድቆ የተላከው የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ወጥ-የሆነ የምግብ ሜኑ በመቐለ ዩኒቨርሲቲ ተግባራዊ መደረግ መጀመሩን ተከትሎ የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች ተቃውሞ አሰምተዋል፡፡

መቐለ ዩኒቨርሲቲ ከቅዳሜ ታህሳስ 12/2017 ዓ.ም ጀምሮ አንድ ዳቦ ለቁርስ እያቀረበ እንደሚገኝ የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች ለቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ተናግረዋል። ከዚህ በፊት ዩኒቨርሲቲው መጠናቸው አነስተኛ የሆነ ሁለት ዳቦ ለቁርስ ያቀርብ እንደነበር ተማሪዎች አስታውሰዋል፡፡

"ዕለታዊ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የምግብ ተመን ወጪ አንድ መቶ ብር በሆነ ማግስት፥ አንድ ዳቦ ለቁርስ ማቅረብ ማሻሻል አይደለም" ሲሉ ተማሪዎቹ ቅሬታቸውን አቅርበዋል፡፡

ከታህሳስ 1/2017 ዓ.ም ጀምሮ የአንድ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ ዕለታዊ የምግብ ወጪ ተመን ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) እንዲሆን መንግሥት መወሰኑ ይታወቃል። በዚህም የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የምግብ ሜኑ በሁሉም ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ወጥነት እንዲኖረው ለማድረግ ተመሳሳይ የምግብ ሜኑ በትምህርት ሚኒስቴር ተዘጋጅቶ ለሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች ተልኳል፡፡

መቐለ ዩኒቨርሲቲ ከተቋሙ የተማሪዎች ህብረት ጋር በመነጋገር የመቐለ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች የምግብ ሜኑን አዘጋጅቶ ወደ ትግበራ መግባቱን ገልጿል። (አዱሱ የዩኒቨርሲቲው ሜኑ ከላይ ተያይዟል)

በማሻሻያውና በቀረበው የዳቦ መጠን ላይ ደስተኛ ያልሆኑ የዋናው ግቢ እና የዓዲ ሓቂ ግቢ ተማሪዎች ድርጊቱን በመቃወማቸው ለድብደባ እና ለእስር መዳረጋቸውን ገልፀዋል።

የክልሉ ፓሊስ ኮሚሽን ወደ ካምፓሶቹ የፀጥታ አካላት መላኩ ተነግሯል። በፓሊስ እና በተማሪዎቹ መካከል በተፈጠረ ግጭት ተማሪዎች የድብደባ ጥቃት እንደደረሰባቸው ተነግሯል። በዋናው ግቢ የተማሪዎች መመገቢያ አዳራሽ ላይ ጉዳት የደረሰ ሲሆን፤ ይህንንም ተከትሎ የታሰሩ ተማሪዎች መኖራቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡ በሁለቱ ካምፓሶች የተፈጠረው ግርግር በአሁኑ ሰዓት ሙሉ በሙሉ መቆሙ ታውቋል።

ዩኒቨርሲቲው ባወጣው መግለጫ "በምግብ ሜኑው ላይ የሚስተካከሉ ነገሮች ካሉ ብሔራዊ ሜኑ በይዘት እና በጀት ደረጃ እስካልተለየ ድረስ ጥያቄዎች በተማሪዎች ህብረት በኩል ቀርበው ማስተካከል እንደሚቻል" ገልጿል፡፡ ተማሪዎች ቅሬታቸውን በሰላማዊ መንገድ መግለፅ እንዳለባቸውም ጠቁሟል፡፡

ከሚመለከተው የማኔጅመንት አካላት ጋር ውይይት መጀመሩን የገለፀው የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ሀብረት፤ "ያለአግባብ የታሰሩ ተማሪዎች እንዲፈቱና ያለ በቂ መረጃ በተማሪዎች ላይ እርምጃ እንዳይወሰድ" ጠይቋል፡፡ ዩኒቨርሲቲው ያዘጋጀው አዲሱ የምግብ ሜኑ ሙሉ ለሙሉ ተግባራዊ እስከሚሆን ድረስ ነባሩ ሜኑ እንዲቀጥልም ህብረቱ ጥሪ አድርጓል፡፡

መቐለ ዩኒቨርሲቲ በተፈጠረው ጉዳይ ላይ ይፋዊ መግለጫ እንደሚሰጥ ይጠበቃል፡፡

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለአምስት የተቋሙ ምሁራን የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ሰጠ።

የዩኒቨርሲቲው የሥራ አመራር ቦርድ ህዳር 25 ቀን 2017 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ ለአምስት የተቋሙ ምሁራን የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ መስጠቱን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

በዚህም፦

➤ ዶ/ር አለማየሁ ተ/ማርያም በስፔሻል ኒድስ ኢጁኬሽን
➤ ዶ/ር አስራት ወርቁ በጂኦቴክኒካል ኢንጂነሪንግ
➤ ዶ/ር መኮንን እሸቴ በፕላስቲክ ሰርጀሪ
➤ ዶ/ር ሚርጊሳ ካባ በፐብሊክ ሄልዝ
➤ ዶ/ር ተባረክ ልካ በዴቨሎፕሜንት ጂኦግራፊ መስኮች ከላይ ከተጠቀሰው ቀን ጀምሮ የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ የተሰጣቸው መሆኑ ተገልጿል።

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሥራ አመራር ቦርድ በህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ''ስለ ራስገዝ ዩኒቨርሰቲ ለመደንገግ በወጣ'' አዋጅ ቁጥር 1294/2015 በተሰጠው ስልጣን መሠረት ነው በዩኒቨርሲቲው ሴኔት የቀረቡለትን የማዕረግ ዕድገት ማፅደቁ ተመላክቷል።

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

😍 የምርጥ አስሩን ቆይታ እንከታተል!

የ#1Wedefit ዲጂታል የሙዚቃ ውድድር ኮከቦቻችን ያደረጉትን አስደሳች ቆይታ የመጀመሪያው ክፍል በYouTube ቻናላችን ላይ እንድትከታተሉ እንጋብዛችኋለን! 👉🏾
https://youtu.be/Z_Fymkjk0Po?si=b-hyA4jQhahrOV-I

#SafaricomEthiopia
#1Wedefit
#FurtherAheadTogether #DigitalMusicChallenge

Читать полностью…

Tikvah-University

36ኛ እና 37ኛ ዙር የግራፊክ ዲዛይን፣ ቪዲዮ ኢዲቲንግ፣ ሞሽን ግራፊክ እና ዲጂታል ማርኬቲንግ ስልጠና በፒያሣ እና በመገናኛ ካምፓስ ሰኞ ታህሳስ 21/2017 ዓ.ም ይጀምራል።

👉 100% በተግባር የተደገፈ ስልጠና
👉 Advanced Graphics + Video Editing + Motion Graphics + Digital Marketing በአንድ ላይ
👉 ከ50 በላይ ፕሮጀክቶች ያሉት
👉 የሥራ ላይ ስልጠና (Internship) የተመቻቸለት

☎️ 0906777799 / 0906777755
አድራሻ፦ ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ እና ቁ.2 መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ

Telegram: /channel/sagetraininginstitute
TikTok: sage_training_institute" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@sage_training_institute
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute

Читать полностью…

Tikvah-University

ዲላ ዩኒቨርሲቲ በ2017 የትምህርት ዘመን ለአቅም ማሻሻያ (ሪሚዲያል) ፕሮግራም የተመደቡለትን ተማሪዎች በመቀበል ላይ ይገኛል፡፡

ዩኒቨርሲቲው አዲስ ገቢ የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች ታህሳስ 14 እና 15/2017 ዓ.ም ሪፖርት እንዲያደርጉ ጥሪ ማስተላለፉ ይታወሳል።

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

#Updates

የመውጫ ፈተና

በ2017 ትምህርት ዘመን አጋማሽ ዓመት ላይ የሚሰጠው የቅድመ ምረቃ ዕጩ ተመራቂዎች የመውጫ ፈተና (Exit Exam) ከጥር 26-30/2017 ዓ.ም ይሰጣል።

የድኅረ-ምረቃ መግቢያ ፈተና

ሀገር አቀፍ የድኅረ-ምረቃ ፕሮግራሞች (NGAT) የ2017 ትምህርት ዘመን አጋማሽ ዓመት የመግቢያ ፈተና ከጥር 7-9/2017 ዓ.ም እንደሚሰጥ መገለፁ ይታወቃል።

ፈተናው ለአዲስ የሁለተኛ እና የሦስተኛ ዲግሪ አመልካቾች በመላ ሀገሪቱ በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች የሚሰጥ ሲሆን፤ የአንድ ጊዜ የ NGAT ፈተና ውጤት ለሁለት ዓመት ያገለግላል ተብሏል።

ይመዝገቡ፦
https://ngat.ethernet.edu.et/login

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

በሦስቱም ቅርንጫፎቻችን ( መገናኛ፣ ሜክሲኮ እና ጀሞ) እና በኦንላይን በምንሰጣቸው ስልጠናዎች በ Advanced Level እና 90% Practical በሆነ ካሪኩለምና ዘመኑ ያፈራቸውን የስቱዲዮ እቃዎች በማሟላት ከሁሉም ስልጠናዎቻችን ላይ ታላቅ የዋጋ ቅናሽ አድርገናል! አሁኑኑ ይመዝገቡና ትልቅ ለውጥ ወደሚያመጡበት ተቋም ይቀላቀሉ!

ከትምህርትና ስልጠና ጥራትና ቁጥጥር ባለስልጣን ሙሉ ዕውቅና ካለው ሰርተፊኬት ጋር! የብዙ ዓመት ልምድ እና ብቃት ባላቸው አሰልጣኞች!

🎯 Graphics Design
🎯 Video Editing
🎯 Digital Marketing
🎯 Photography
🎯 Videography
🎯 Cinematography
🎯 Adobe Photoshop
🎯 Full-stack Web App Development
🎯 Programming Language
🎯 Interior Design
🎯 English Language
🎯 Database
🎯 Basic Computer
🎯 Accounting Softwares
🎯 Engineering Softwares
🎯 SPSS & STATA
🎯 MS-Project
🎯  Foreign & Local Languages

አድራሻ፦
1. መገናኛ መተባበር ህንፃ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁ. 419 (ሊፍት ይጠቀሙ)  ☎️ 0991929303
2. ሜክሲኮ ኬኬር ህንፃ 6ኛ ፎቅ ቢሮ ቁ. 639 (ሊፍት ይጠቀሙ ሁለተኛውን ሊፍት) ☎️ 0991929304
3. ጀሞ 1 አንደኛ በር ካኩ ቢዝነስ ሴንተር 3ኛ ፎቅ ☎️ 0991926707

Telegram: /channel/topinstitutes

Читать полностью…

Tikvah-University

የግራፊክ ዲዛይን፣ ቪዲዮ ኢዲቲንግ፣ ሞሽን ግራፊክ እና ዲጂታል ማርኬቲንግ ስልጠና በፒያሣ እና መገናኛ ካምፓስ ምዝገባ ላይ ነን። 

👉 100% በተግባር የተደገፈ ስልጠና
👉 Advanced Graphics + Video Editing + Motion Graphics + Digital Marketing በአንድ ላይ
👉 ከ50 በላይ ፕሮጀክቶች ያሉት
👉 የሥራ ላይ ስልጠና (Internship) የተመቻቸለት

☎️   0906777799 / 0906777755
አድራሻ፦ ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ እና ቁ.2 መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ

Telegram: /channel/sagetraininginstitute
TikTok: sage_training_institute" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@sage_training_institute
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute

Читать полностью…

Tikvah-University

ከክፍያ ተላቀን ያለገደብ በM-PESA ወደ የትኛውም የሳፋሪኮም ስልክ ቁጥር አሁኑኑ ገንዘብ እንላክ! በ M-PESA ሁሌም ቅናሽ ሁሌም ነፃ አለ!

የ M-PESA ሳፋሪኮም መተግበሪያን በዚህ ሊንክ እናውርድ፦ https://play.google.com/store/apps/details?id=et.safaricom.mpesa.lifestyle

የቴሌግራም ቻናላችንን እዚህ እንቀላቀል 👉 /channel/Safaricom_Ethiopia_PLC

ስለ አገልግሎታችን ማንኛውንም ጥያቄ ወይም መረጃ በቴሌግራም ቻናላችን /channel/Safaricom_Ethiopia_PLC 24/7 ማግኘት ይቻላል!

#MPESASafaricom #FurtherAheadTogether

Читать полностью…

Tikvah-University

20ኛ ዙር ሙሉ የሒሳብ መዝገብ አያያዝ (Principle and Practice of Accounting) የ6 ወር የቅዳሜ እና እሑድ መርሐግብር ስልጠና በፒያሣ እና በመገናኛ ካምፓስ ምዝገባ ላይ ነን። 

👉 100% በተግባር የተደገፈ ስልጠና
👉 መሠረታዊ አካውንቲንግ እና ኦዲት አሰራር፣ ሙሉ የአካውንቲንግ ሒሳብ አሰራር በፒስቺሪ ተደግፎ እና የግብር አያያዝ ትምህርቶችን አካቶ የሚሰጥ
👉 የሥራ ላይ ስልጠና (Internship) የተመቻቸለት

☎️    0906777799 / 0906777755
አድራሻ፦ ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ እና ቁ.2 መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ

Telegram: /channel/sagetraininginstitute
TikTok: sage_training_institute" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@sage_training_institute
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute

Читать полностью…

Tikvah-University

ነጻ የማስተርስ የትምህርት ዕድል

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለ2017 የትምህርት ዘመን ሁለተኛ መንፈቅ ዓመት አመልካቾች ነጻ የማስተርስ የትምህርት ዕድል አዘጋጅቷል።

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ስር የሚገኘው Addis Ababa University-Mastercard Foundation (AAU-MCF) Africa Health Collaborative Project ለ2017 ዓ.ም ሁለተኛ መንፈቅ ዓመት በአ.አ.ዩ በጤና ዘርፍ ዙሪያ ለሚሰጡ የድህረ-ምረቃ ማስተርስ ፕሮግራሞች ከመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች በቀን (መደበኛ) ፕሮግራሞች ከ2007 ዓ.ም ጀምሮ ከተመረቁ ለሴት አመልካቾች አንዲሁም ለአካል ጉዳተኛ አመልካቾች በጦርነት ወይም በሌላ ተፈጥሮአዊ ወይም ሰው-ሠራሽ በሆነ ምክንያት ለተፈናቀሉ ምሩቃን፣ ለስደተኛ አመልካቾች እንዲሁም ከገጠሪቱ የሀገራችን ክፍል ለመጡ በተለይ በኢኮኖሚ የኑሮ ደረጃቸው ዝቅተኛ ለሆኑ ምሩቃን ነጻ የትምህርት ዕድል አዘጋጅቷል፡፡

ነጻ የትምህርት ዕድሉ የትምህርት ክፍያን (tuition fee)፣ የኪስ ገንዘብ (monthly stipend)፣ የምርምር ጥናት ወጪ ከፍያን (thesis research support) እና የኮምፒውተር (Laptop) ግዢን ያካትታል፡፡

(ተጨማሪ ዝርዝር መረጃ ከላይ ተያይዟል።)

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

#MoH

የ2024 ትምህርት ዘመን የብሔራዊ የህክምና ስፔሻሊቲ ስልጠና (ERMP) አመልካቾች ፈተና ታህሳስ 22/2017 ዓ.ም እንደሚሰጥ ጤና ሚኒስቴር አሳውቋል፡፡

የ ERMP 2024 ፈተና መመሪያ ለማግኘት፦
https://www.moh.gov.et/en/media/1

የ ERMP 2024 ተፈታኞች ዝርዝር ለማየት፦
https://www.moh.gov.et/en/media/170

List of candidates who were matched last year and are not eligible this year:

ባለፈው ዓመት ለ ERMP የተመረጡና ዘንድሮ መፈተን የማይችሉ ዕጩዎች ዝርዝር፦ https://www.moh.gov.et/en/media/171

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

በትግራይ ክልል የ8ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና መሰጠት ተጀመሯል።

በክልሉ በተሳለጠ የትምህርት ፕሮግራም ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩ 26,156 የ8ኛ ክፍል ተማሪዎች ዛሬ ፈተናቸውን መውሰድ ጀምረዋል።

ክልል አቀፍ ፈተናው በ451 ትምህርት ቤቶች እየተሰጠ ይገኛል።

የተማሪዎቹ የፈተና ውጤት በአምስት ቀናት ውስጥ እንደሚገለፅና ወደ 9ኛ ክፍል የሚያልፉ ተማሪዎች በቀጥታ የ9ኛ ክፍል ትምህርታቸውን እንደሚከታተሉ የኢዜአ ዘገባ ያሳያል።

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

በሦስቱም ቅርንጫፎቻችን ( መገናኛ፣ ሜክሲኮ እና ጀሞ) እና በኦንላይን በምንሰጣቸው ስልጠናዎች በ Advanced Level እና 90% Practical በሆነ ካሪኩለምና ዘመኑ ያፈራቸውን የስቱዲዮ እቃዎች በማሟላት ከሁሉም ስልጠናዎቻችን ላይ ታላቅ የዋጋ ቅናሽ አድርገናል! አሁኑኑ ይመዝገቡና ትልቅ ለውጥ ወደሚያመጡበት ተቋም ይቀላቀሉ!

ከትምህርትና ስልጠና ጥራትና ቁጥጥር ባለስልጣን ሙሉ ዕውቅና ካለው ሰርተፊኬት ጋር! የብዙ ዓመት ልምድ እና ብቃት ባላቸው አሰልጣኞች!

🎯 Graphics Design
🎯 Video Editing
🎯 Digital Marketing
🎯 Photography
🎯 Videography
🎯 Cinematography
🎯 Adobe Photoshop
🎯 Full-stack Web App Development
🎯 Programming Language
🎯 Interior Design
🎯 English Language
🎯 Database
🎯 Basic Computer
🎯 Accounting Softwares
🎯 Engineering Softwares
🎯 SPSS & STATA
🎯 MS-Project
🎯  Foreign & Local Languages

አድራሻ፦
1. መገናኛ መተባበር ህንፃ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁ. 419 (ሊፍት ይጠቀሙ)  ☎️ 0991929303
2. ሜክሲኮ ኬኬር ህንፃ 6ኛ ፎቅ ቢሮ ቁ. 639 (ሊፍት ይጠቀሙ ሁለተኛውን ሊፍት) ☎️ 0991929304
3. ጀሞ 1 አንደኛ በር ካኩ ቢዝነስ ሴንተር 3ኛ ፎቅ ☎️ 0991926707

Telegram: /channel/topinstitutes

Читать полностью…

Tikvah-University

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በራሳቸው ላይ ግለ ግምገማ እንዲያካሒዱ የሚደነግግ ረቂቅ መመሪያ ተዘጋጀ፡፡

ሁሉም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን የጥራት ኦዲት ስታንዳርድ መሠረት፣ በየጊዜው በተቋም ወይም በፕሮግራም ደረጃ ግለ ግምገማ ማካሔድ እንዳለባቸው የሚደነግግ ረቂቅ መመሪያ ለግምገማ ቀርቧል፡፡

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱ ግለ ግምገማውን የሚያደርጉት ባለሥልጣኑ በሚያዘጋጀው የግለ ግምገማ መመሪያ መሠረት እንደሚሆን የተገለጸ ሲሆን፤ የማንኛውም ተቋም የግል ግምገማ ሪፖርት ተቀባይነት ባገኘ በአራት ወራት ጊዜ ውስጥ የጥራት ኦዲት ግምገማ መደረግ ይኖርበታል ተብሏል፡፡

በረቂቅ መመርያው እንደተገለጸው ተቋማዊም ሆነ የፕሮግራም ጥራት ኦዲት በተቋም ደረጃ የሚደረግ ሆኖ፣ ተቋሙ ከአንድ በላይ ካምፓሶች የሚኖሩት ከሆነ በተመረጡ ካምፓሶች የጥራት ኦዲት መደረግ አለበት፡፡

ረቂቅ መመሪያው በኢትዮጵያ ውስጥ በሚንቀሳቀስ በማንኛውም የመንግሥት እና የግል እንዲሁም ከውጭ ለሚመጣ የከፍተኛ ትምህርት ተቋምና የትምህርት ፕሮግራም ላይ፣ በተጨማሪም በፌዴራል ደረጃ ለተቋቋመና ከውጭ አገር ለሚመጣ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ተቋም ላይ ተፈጻሚ ይሆናል ተብሏል፡፡

የትምህርትና ሥልጠና ባለሥልጣን ሁሉም የመንግሥት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት፣ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት፣ በፌዴራል መንግሥት በጀት የሚተዳደሩና በውጭ አገር ባለሀብቶች በፌዴራል ደረጃ ፈቃድ የወሰዱ የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ተቋማት ረቂቅ መመርያውን አስመልክቶ ያላቸውን አስተያየት እንዲያቀርቡ ጠይቋል፡፡ #ሪፖርተር

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

ለበይነ መረብ (Online) ስልጠና ፈላጊዎች ምዝገባ ላይ ነን።

🔔 ፈጥነው ይመዝገቡ!

👉 ባሉበት ሆነው በተመጣጣኝ ዋጋ የሚማሩበት
👉 100% በተግባር የተደገፈ ስልጠና
👉 ሁሉም በአካል ለሚማሩ ተማሪዎቻችን ያሉት ዕድሎችና የአሰጣጥ ደረጃችን በሙሉ እንደተጠበቁ ይቀጥላሉ።

☎️ 0906777799 / 0906777755
አድራሻ፦
ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ እና ቁ.2 መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ

Telegram: /channel/sagetraininginstitute
TikTok: sage_training_institute" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@sage_training_institute
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute

Читать полностью…

Tikvah-University

ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ የ2017 ዓ.ም የአቅም ማሻሻያ (Remedial) ፕሮግራም አዲስ ገቢ ተማሪዎችን በመቀበል ላይ ይገኛል፡፡

ወደ ተቋሙ የተመደቡ የ2017 ዓ.ም ሪሚዲያል ተማሪዎች ታህሳስ 14 እና 15/2017 ዓ.ም ሪፖርት እንዲያደርጉ ዩኒቨርሲቲው ጥሪ ማድረጉ ይታወሳል፡፡

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

#AdigratUniversity

በ2017 የትምህርት ዘመን ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች የመግቢያ ቀናት ጥር 1 እና 2/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

ወደ ዩኒቨርሲቲው ስትሔዱ የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የወሰዳቹበት ማስራጃዎች፣ ፎቶግራፍ፣ የመኝታ አልባሳት እና የስፖርት ትጥቅ መያዝ እንደሚገባችሁ ዩኒቨርሲቲው ገልጿል፡፡

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

#WolloUniversity

በ2017 ዓ.ም ወሎ ዩኒቨርሲቲ ለሪሚዲያል ፕሮግራም የተመደባችሁ ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ ጥር 3 እና 4/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

የምዝገባ ቦታ፦
- የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ደሴ ግቢ፣
- የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ኮምቦልቻ ግቢ።

(የዩኒቨርሲቲው መልዕክት ከላይ ተያይዟል።)

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

#BongaUniversity

ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በቡና ሳይንስ የትምህርት መስክ የ PhD ፕሮግራም መስጠት ጀምሯል፡፡

በዩኒቨርሲቲው PhD in Coffee Science የመጀመሪያ ቀን ትምህርት የመጀመሪያ Class በዛሬው ዕለት ተጀምሯል፡፡

ዩኒቨርሲቲው በኢትዮጵያ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ታሪክ በቡና ሳይንስ የ PhD ፕሮግራም በመጀመር ቀዳሚው ዩኒቨርሲቲ ሆኗል።

በቡና ሳይንስ የትምህርት መስክ በመጀመሪያ ዲግሪ ፕሮግራም ለመጀመሪያ ጊዜ ያሰለጠናቸው 34 ተማሪዎች ባለፈው ሰኔ ያስመረቀው ዩኒቨርሲቲው፤ በመስኩ በማስተርስ መርሐግብር ተማሪዎችን በማሰልጠንም ላይ ይገኛል።

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ አዲስ የሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ ተመድቦለታል።

የማዕድን ሚንስትር ዴኤታ ሚሊዮን ማቲዮስ ከህዳር 18/2017 ዓ.ም ጀምሮ የደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ ሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ ሆነው ተመድበዋል።

አቶ ሚሊዮን ከዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት እና ሌሎች ኃላፊዎች ጋር ትውውቅና ውይይት አድርገዋል።

ላለፉት አመታት የደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ ሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ ሆነው ሲያገለግሉ የነበሩት የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) በቅርቡ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ ሆነው መመደባቸው ይታወሳል፡፡

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

#WolaitaSodoUniversity

በ2017 ዓ.ም ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች የመግቢያ ቀናት ታህሳስ 20 እና 21/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ምዝገባ የሚከናወነው ታህሳስ 21 እና 22/2017 ዓ.ም ሲሆን፤ ትምህርት ታህሳስ 24/2017 ዓ.ም እንደሚጀምር ተገልጿል።

ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

- የ8ኛ ክፍል ሰርተፍኬት ዋናውና ኮፒው፣
- ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት፣
- የ12ኛ ክፍል ሰርተፍኬት ዋናውና 2 ኮፒ፣
- አንሶላ፣ ትራስ ጨርቅ እና የስፖርት ትጥቅ።

የምዝገባ ቦታ፦
➫ በዩኒቨርሲቲው ዋናው ካምፓስ (ወላይታ ሶዶ)
➫ በዩኒቨርሲቲው ዳውሮ ታርጫ ካምፓስ (ዳውሮ ታርጫ)

(ተጨማሪ መረጃ ከላይ ተያይዟል።)

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

#ይመዝገቡ

የሁዋዌ አይሲቲ ውድድር 2024/25 ፕሮግራም ይፋ ሆኗል፡፡

በ9ኛው ዓለም አቀፍ የ2024/25 አይሲቲ ውድድር ለመሳተፍ የምትፈልጉ እስከ ታህሳስ 2017 ዓ.ም መጨረሻ ድረስ መመዝገብ ይኖርባችኋል፡፡

ኔትዎርኪንግ፣ ክላውድ ኮምፒውተር እና አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ውድድሩ ከሚደረግባቸው የአይሲቲ ዘርፎች መካከል ይጠቀሳሉ።  

በሁዋዌ የICT ውድድር (Huawei ICT Competition 2024-2025) ለመሳተፍ በቅድሚያ የሁዋዌ ICT አካዳሚ አባል ይሁኑ።

የአካዳሚው አባል ለመሆን 👇
https://e.huawei.com/en/talent/portal/#/

ለውድድሩ ምዝገባ ለማድረግ 👇
https://bit.ly/SAR2024-2025

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

#NGAT_EXAM

ሀገር አቀፍ የድኅረ-ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) በቀጣይ ወር ይሰጣል።

የ2017 ትምህርት ዘመን አጋማሽ ዓመት የ NGAT ፈተና ከጥር 7-9/2017 ዓ.ም ይሰጣል።

በመላ ሀገሪቱ በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ለሚሰጠው ፈተና ይመዝገቡ፦
https://ngat.ethernet.edu.et/login

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

#አቢሲንያ_ባንክ

ይሸለሙ!
ቀጣይ ዙር የጥያቄ እና መልስ ውድድር ቅዳሜ ታህሳስ 12 ከረፋዱ 4:30 በፌስቡክ ፔጃችን ላይ ይደረጋል። በየሳምንቱ አስር አሸናፊዎች ይሸለማሉ! ዛሬውኑ የፌስቡክ ፔጃችን በመቀላቀልና ቀላል ጥያቄዎችን በመመለስ ይሸለሙ!

የፌስቡክ ሊንክ 👇
https://www.facebook.com/BoAeth

አቢሲንያ የሁሉም ምርጫ!
#Facebook #giveaway #contest #Boa #bankinginethiopia #banksinethiopia #bankofabyssinia #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ

Читать полностью…

Tikvah-University

ጥራትን ከሚገርም ዋጋ ጋር ይዞ የመጣውን አዲሱን Kimem Itel Pro እናስተዋውቅዎ! በአቅራቢያችን ወደ የሚገኝ የሳፋሪኮም ሱቅ ጎራ ብለን የግላችን እናድርገው። በቅመም አይቴል ፕሮ እንንበሽበሽ!

#SafaricomEthiopia #FurtherAheadTogether

Читать полностью…

Tikvah-University

ለበይነ መረብ (Online) ስልጠና ፈላጊዎች ምዝገባ ላይ ነን።

🔔 ፈጥነው ይመዝገቡ!

👉 ባሉበት ሆነው በተመጣጣኝ ዋጋ የሚማሩበት
👉 100% በተግባር የተደገፈ ስልጠና
👉 ሁሉም በአካል ለሚማሩ ተማሪዎቻችን ያሉት ዕድሎችና የአሰጣጥ ደረጃችን በሙሉ እንደተጠበቁ ይቀጥላሉ።

☎️   0906777799 / 0906777755

አድራሻ፦ ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ እና ቁ.2 መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ

Telegram: /channel/sagetraininginstitute
TikTok: sage_training_institute" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@sage_training_institute
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute

Читать полностью…

Tikvah-University

#DireDawaUniversity

በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ የማጠቃለያ ፈተና ወስዳችሁ ለሪሚዲያል ፕሮግራም ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች የመግቢያ ቀናት ጥር 3 እና 4/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

የማመልከቻ ቀን ጥር 5/2017 ዓ ም መሆኑ ተገልጿል።

(በምስሉ የተያያዙ ተጨማሪ መረጃዎችን ይመልከቱ።)

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

#BoranaUniversity

በ2017 ዓ.ም ቦረና ዩኒቨርሲቲ በሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርታችሁን እንድትከታተሉ የተመደባችሁ የመግቢያ ጊዜ ታህሳስ 22 እና 23/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ወደ ዩኒቨርሲቲው ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

- የ8ኛ ክፍል ሰርተፍኬት ዋናውና ኮፒው፣
- ከ9ኛ-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
- የ12ኛ ክፍል ውጤት ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
- ስምንት 3x4 የሆነ ፎቶግራፍ፣
- አንሶላ፣ ብርድልብስ እና ትራስጨርቅ።

@tikvahuniversity

Читать полностью…
Subscribe to a channel