#እዬዬ
.
.
ከሩቅ ይታየኛል
'ካድማስ ወዲያ ማዶ
አይመሽ ወይ አይነጋ፤
ጭጋግ የወረሰው ያልታደለ ቀንሽ፣
ገብቶሽ እንደው እንጃ፤
በለቅሶ ሲታጀብ የታፈነው ሳቅሽ፡፡
በትላንት ጀምበር
እንባሽ ላይታበስ ፀዳሉ ላይፈካ፣
ጥምሽን ላይቆረጠው ረሃብሽ ላይረካ፣
የፊትሽ ወጋገን በሀዘን ሲታረስ፣
"እዬዬ"ሽን ሳቂው፤
ወትሮም ቤተኛሽ ነው እየሳቁ ማልቀስ፡፡
እየሳቁ ማልቀስ እየሞቱ መኖር፣
ላንቃ እያኘከ እያከኩ ማደር፣
የኋሊት መዘመን ሲተልቁ ማነስ፣
ሰብስቦ መበተን ደምሮ መቀነስ፡፡
ነው እና ያንቺ እጣ፤
በሆነብሽ ሁሉ ብዙ አትከፊ፣
በእንባ ጎርፍ አለም እየሳቅሽ እለፊ፡፡
✍ abiye12
ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@poimfitsae @poimfitsae
@poimfitsae @poimfitsae
የጨለመ ጊዜ
""""""""""""""""
ለምን?
ጊዜ ዘመን ሰዓት እያዋጀን፤
ለብርሃን ስንሮጥ
እንደ እሳት እራት ብርሃኑ ፈጀን?
ለምን?
እያደር ሰቆቃ እያደር ጭካኔ፤
ለአዘቅዝቆ ኗሪው
መትረየስ ነበረ የሚገባው ለኔ?
ለምን?
በሚስቴ አስክሬን ሀዘን 'ምቆራመድ
በልጆቼ እሬሳ በቁጭት የምነድ
ከሀገሬ ቆሜ በሀገሬ የምሰደድ
ለምን?
ብለን ስንጠይቅ
እሳት ሲለቁብህ
አንተ ምጣድ ሆነህ ዝምብለህ ተጋገር፤
በነገር ቢጠብሱህ
አንተ ምድር ሆነህ በሆድ ችለህ እደር፤
እንረድህ ሲሉህ
ትንፋሽህን ውጠህ ከአንገትህ በል ሰበር፤
በጨለመ ጊዜ
ጠይም ፀሀይ አስብ ደም ያለበት ጀንበር፤
እውትና ንጋት ይፈካል እያደር!
የሚል መልስ አለ እንዴ?
ልክ ያጣ ቀን ሲኖር
ለካም ቤተ መቅደስ ይኖራል ወንበዴ!
አብርሃም ፍቅሬ
(የቅዳስ ልጅ)
ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@poimfitsae @poimfitsae
@poimfitsae @poimfitsae
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
...ፍቅር........
...
ያኔ አንቺን ሳገኝሽ
ልቤም አዝኖ ነበር.....
ተስፍዬ ተሟጦ
ባዶ ሆኔ ነበር....
ያኔ ስንገናኝ
የህይወቴ ምእራፍ
አእላፍ ገፆቹ....
ተሞልተው ነበረ
በዝብርቅርቅ ስሜት
ሙሉ መስመሮቹ.....
....
አዎን የኔ ሀዊ
ተስፋዬን አብርተሽ
አዲስ አርገሽኛል....
ክፍተቶቼን ሞልቶ
ፍቅርሽ ከልሎኛል
የረጠበው አይኔ
ያዘሉትን እንባ
በፍቅርሽ አብሰሽ...
ይኸውልሽ ልቤ
ዛሬ ላለሁበት
ለደስተኛው ፍቅርሽ
ማንነትን ሰጠሽ..
..
..ውዴ.....
እስኪ መልሽልኝ
በእኔና ባንቺ ቃል
ለፍቅራችን እምነት
ቃልኪዳን ስናስር
እስኪ ማን ነበሩ?.....
ከከዋክብት ውጪ
ያዩ ከነበሩ
አምጪ ይጠየቁ
የፍቅራችንን ጥግ
ያቁ ከነበሩ....
........
አዎ አስከፋሻለሁ
ይህንን አውቃለሁ
ብትቀየሚኝም
ጨክነሽ አይደለም
..ሚስቴ....
ፍቅርሽ ያፈቅርሻል....
በውስጡ አስፍሮ
ሁሌም ሳትወጪ
ንግስቱ አድርጎ
በልቡ ሾሞሻል.....
ፍቅርሽ እንዳይጠፋ
በትልቅ ሸራ ላይ
በደማቁ ብእር
ስምሽን አስፍሮታል...
...
እናም ይኸውልሽ
በፍቅሬ አትወላውይ
ጥርጥር አይግባሽ
አወድሻለሁኝ.....
ይህ ስለማይገባሽ
ቃሉም ደስ አይልም
አፈቅርሻለሁኝ
ለ ፍቅር
ከ አፍቃሪሽ
✍ተፃፈ በ @Mak_bale
21.3.2013
@joftdav
@joftdav
@joftdav
❔ይህን ያውቁ ኖሯል❔
👉ሻርኮች ማንኛውንም በሽታ የመቋቋም ከፍተኛ ብቃት አላቸው። በጣም ገዳይ የሆነው ካንሰር እንኳን ለነሱ ምንም አይደለም
@poimfitsae
📌📌📌📌📌📌📌📌📌📌📌📌📌📌
@poimfitsae @poimfitsae
በየትኛውም ሁነት ላይ ግጥም ለማፃፍ
> ለፍቅረኛዎ
>ለወዳጅ ዘመድ
>ለሀዘን ወዘተ
የፈለጉትን መፅሀፍ ለማስላክ
የምግብ አሰራር
ፈረንሳይኛ ቋንቋ መማሪያ
ልብ ወለድ
ታሪክ...ወዘተ
@ft2194 👈 ይህንን ሊንክ ተጭነው ያናግሩኝ!!
@poimfitsae @poimfitsae
📌📌📌📌📌📌📌📌📌📌📌📌📌📌
🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
፨፨፨፨ የእርዳታ ጥሪ ፨፨፨፨
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
➢ #ለወገን_ደራሽ_ወገን_ነው👈👈👈
🙏🙏 🙏🙏 🙏🙏 🙏🙏 🙏
ችግር የሚገባበት አይታወቅምና ዛሬ በእኔ ላይ ደርሶ #የድረሱልኝ_ጥሪዬን ወደናንተ ወደ ወገኖቼ ዘርግቻለሁ። ፈጣሪ የሚሰጥበት መንገድ አይታወቅምና ምናልባት ፈጣሪ በእናንተ በተከበራችሁ #በኢትዮጵያ ህዝብ በኩል ከደረሰልኝ ብዬ #የአባቴን ህይወት ትታደጉልኝ ዘንድ ክብር የኢትዮጵያን ህዝብ እማፀናለሁ።
🙏
ወገኖቼ ሆይ #ሰው_ያለቤተሰብ_ያለ እናትአባትባዶነውና ቤተሰብ ያለው እናት አባት ያለው ሁሉ አይቶና ስሜቴን ተረድቶ ውድ #አባቴን እንድትታደጉልኝ ስል እማፀናለሁ።
🙏
በምስሉ ላይ የምትመለከቱት #አባቴ አቶ ጌትዬ አሰፋ በደረሰበት የጠና #የኩላሊት\ህመም ምክንያት በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል #የኩላሊት_እጥበት ሲያረግ ቆይቶ በመጨረሻም #የጥቁር_አንበሳ_ሆስፒታል የሀኪሞች ቦርድ ወደ #ውጪ ሄዶ እንዲታከምና በአጭር ጊዜ ውስጥም ወደ ውጫገር ሄዶ ህክምናውን ካላገኘ #በህይወት_የመቆየቱ ጉዳይ አጠራጣሪ በመሆኑ ዛሬ ችግሬን ችግራችሁ ህመሜን ህመማችሁ አርጋችሁ በፈጣሪ ስም #የአባቴ_ህይወት በእጃችሁ ነውና እንድትታደጉልኝ በመማፀን እጠይቃለሁ።
🙏
በዚህ መሰረት ወደ ውጪ ሄዶ ለመታከም የሚያስፈልገው ገንዘብ በአጠቃላይ ከ800,000 ብር በላይ ስለሆነና የተጠየቀውን ገንዘብ እኔ ለመሸፈን አቅሙ ስለሌለኝ ወደናንተው ክብር የሀገሬ ህዝቦች እጄን ዘርግቻለሁ።
🙏
ምንም እረዳት የሌለኝ በመሆኑ የሀገሬ ህዝብ እባካችሁ የእርዳታ እንድትዘረጉልኝ እጠይቃለሁ
🙏
እኔን መርዳት ወይም ማገዝ የሚፈልግ ከታች በተጠየሰው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር
➢➢ 1000352655655
ወይም
➢➢📞0967103695 ☎️
➢➢📞0914062986 ☎️
ማግኘንና ማናገር ይችላል።
✉️✉️✉️✉️ በራስ መተማመን ✉️✉️✉️✉️
ለአንድ ግለሰብ ከሚያስፈልጉት መሠረታዊ የስነ-ልቦና እሴቶች መካከል አንዱና ዋነኛው በራስ መተማመን (self confidence) ነው፡፡ ብዙዎቻችን በራስ መተማመናችን አነስተኛ ወይም ከነጭራሹ ባለመኖሩ ምክንያት ያጣናቸው ብዙ ነገሮች አሉ፡፡ ለመሆኑ በራስ መተማመን ምንድን ነው ?? በራስ መተማመንን የተለያዩ ምሁራን የተለያዩ ፍቺዎች ሰጠውታል ሆኖም ጭብታቸው ተመሳሳይ ሆኖ ስላገኘሁት አንዱን ብቻ ልንገራችሁ፡፡ ጎልማን በራስ መተማመን ማለት ይለናል በራስ መተማመን ማለት ስለ ራሳችን ችሎታ በቂ የሆነ እውቀት እና እምነት ኖሮን ከዚህ በመነሳት ደግሞ በግፊት እና በጫና ውስጥ ስንሆን ጥሩ ውሳኔዎችን መስጠት ነው ይለናል፡፡ በራስ መተማመን የራስ እውቀት እና ክብር (self esteem) እና የራስን ችሎታን የማወቅና ውጤታማ በሆነ መልኩ ነገርን እፈጽማለሁ ብሎ በራስ ላይ እመነት መጣል (self efficacy) ድምር ውጤት ሲሆን፤ በራስ የሚተማመን ሰው መገለጫዎቹም…….. ስለ ነገ ሲያስብ መልካም መልካሙ ነው የሚታየው፣ በራሱ የሚተማመን ሰው ምክንያታዊ በመሆን ምን ይመጣልን ከግምት ውጥ በማስገባት እና አደጋን በመጋፈጥ (risk taker) ኢላማውን ለመምታት የሚታትር ነው ፣ በእራሱ የሚተማመን ሰው እራሱን በትክክለኛ ደረጃ የሚወድ ነው….. ወዘተ በአንጻሩ ደግሞ በራሱ የማይተማመን ሰው ደግሞ የሚሞክራቸው ነገሮች የሚሳኩለት የማይመስሉት፣ ነገን ሲያስብ መጥፎው ብቻ እና ውድቀቱ ፈጥኖ የሚታየው፣ አቅሙን አሟጦ ለመጠቀም የሚፈራ ወዘተ… መገለጫዎች ያሉት ነው፡፡
ዛሬ በራስ መተማመናችን አነስተኛ ስለሆነ ስላጣናቸው ነገሮች ለማውራት ሳይሆን የተነሳሁት እንዴት በራስ መተማመንን መገንባት እንችላለን ወይም ያለንን አጠንክረን እንሄዳለን የሚለውን ለማየት ነው፡፡ ስለዚህ በራስ መተማመንን እንዴት መገንባት እንችላለን?? የሚከተሉትን ነጥቦች አብረን እንያቸው…… መልካም ንባብ ተመኘሁ፡-
1.በራስ መተማመንህን የሚሸረሽሩ ሃሳቦችን ነቅሰህ አውጣ፡- በአዕምሮህ ውስጥ ያሉትን አልችልም፣ አይሳካልኝም፣ እወድቃለሁ እና አይሆንልኝም የሚሉ አሉታዊ ሃሳቦችን ለያቸው፡፡ እነዚህ ሃሳቦች የጨለምተኛነትን ዘር በውስጥህ በመዝራት የራስ ዕውቀትህን በማሳነስ በእራስ መተማመንህን ይሸረሽሩታል፡፡
2.አሉታዊውን ሃሳቦች ወደ አዎንታዊ ቀይራቸው፡- ከላይ የተጠቀሱትን አሉታዊውን ሃሳቦች ወደ ምክንያታዊ ወደ ሆኑ አዎንታዊ ሀሳቦች ቀይራቸው ለምሳሌ እችላለሁ፣ እሞክረዋለሁ ፣ አሳካዋለሁ ወደ ሚሉ ሃሳቦች ቀይራቸው እነዚህን እራስን የማበረታቻ እና ለራስ ዕውቅና መስጫ ሃሰቦች ቀስ በቀስ አዳብራቸው፡፡
3.አዎንታዊ ሃሳቦችህን ትኩረት ስጣቸው፡- አዕምሮህ አሉታዊውን ሃሳቦች ብዙ ትኩረት እንዳይሰጠቸው ለአዎንታዊው ሃሳቦች ሰፊ ቦታና ጊዜ ስጣቸው፡፡ ለማሳካት የምታልመው ን ጉዳይ ትኩረት በመስጠት ይህን ጉዳይ ወደ ትናኝሽ ሃሳቦች በመቀየር ወደ ተግባር ግባ፡፡ በዚህም ከሰዎች እርዳታ ለመጠየቅ፣ ስትሳሳት ይቅርታ ለማለት እና የማይሆን ነገር ሲመጣ ወይም ስትጠየቅ በአክብሮት አይሆንም ለማለት አትፍራ፡፡ ሁልጊዜም ከዚህ በፊት ያሳካሃቸውን ነገሮች እና ጠንካራ ጎኖችህን አስባቸው፡፡
4.ዙሪያህን በጥንቃቄ ቃኘው፡- በዙሪያህ ላሉ አዎንታዊ ሀሳቦችን እንድታስብና መልካም ድርጊቶችን እንድታከናውን ለሚያደርጉህ እና ለሚያግዙህ ወዳጆችህ ሰፊ ጊዜ ስጥ፣ በአንጻሩ ስለ ራስህ መጥፎ እንድታስብና ምቾት የማጣት ስሜት እንዲሰማህ ከሚያደርጉ ሰዎች እና ድርጊቶች በተቻለህ መጠን እራቅ ካልሆነ ደግሞ ምክንያታዊ በሆነ መንገድ ነቀፌታቸውን ተመልከት፡፡ ለዚህ እንዲረዳህ ደግሞ የተወሰነ ጊዜ በመውሰድ እነዚህን ሰዎች እና ድርጊቶች ለይተህ አውጣ፡፡
5.ችሎታህን ለይተህ አውጣ፡- እያንዳንዱ ሰው ቢያንስ በአንድ ነገር ላይ ጎበዝ ነው፡፡ ስለዚሀም አንተም ጎበዝ የሆንክበትን ወይም ብሰራው አሳካዋለሁ የምትለውን ነገር ነቅሰህ በማውጣት ትኩረትህን ወደእዚህ አድርገው፡፡ ተጨማሪ የሆኑ ጊዜህን የምታሳልፈበትና ስኬታማ የምትሆንበትንም ነገሮች እግረ-ሃሳብህን ለይተህ አውጣና ትኩረትህን ስጠው፡፡
6.በራስህ ኩራ፡- ባሉህ አዎንታዊ እና በጎ ጎኖች ምክንያት ተገቢ እና መጠነኛ የሆነ ኩራትን ኩራ፡፡ ከሰዎች ጋር ባለህ መልካም፣ ግንኙነት፣ አዳማጭ በመሆንህ፣ የሰውን ችግር መረዳት በመቻልህ፣ ውጥረትን በመቋቋም ብቃትህ ፣ እስካሁን ባሳካሀቸው ስኬቶችህ እና በመሳሰሉት ጥሩ ስሜት እንዲሰማህ በማድረግ ኩራትህን ጨምር፡፡
7.ሁሌም ራስህን ሁን፡- አዳዲስ ሰዎችን ስትተዋወቅ .........continue on t.me/poimfitsae
@poimfitsae @poimfitsae
ሂወቴ ❤ ልቤ ሁሉ😍 ነገሬ....ከሁሉም😘 በላይ ደሞ #እናቴ 💕 የኔ እናቴም አባቴም እህቴም💑 ወንድሜም ጓደኛዬም ፍቅሬም💏
የኔ የመጀመሪያዬም የመጨረሻዬም የትም አለም ላይ የማትደገሚዋ ልዩዋ እንስት👰 የልቤ ንግስት የትኛዋም ሄዋን👰 የማትተካሽ እናቴ የኔ እዚህ የመድረሴ መሰረቴ ምንም ቃላት ብደረድር አንቺን የማይገልፅሽ💖
💕💕 "እናቴ እንኳን ተወለድሽል"💞💞
ከዚህ በላይ የኔን እድሜ ጨምሮ ሰጥቶሽ የነማቱ ሳላን እድሜ 💕💞ሰጥቶሽ ብዙ ዘመንን ብትኖሪልኝ ደስ ይለኛ
ታቂ የለ አንቺ 💞💖ከሌለሽ ቤቱ ሁሉ ጭር እንደሚል
እናቴ ምንም ባሳዝንሽ 💟 ልጅሽ ሁል ጊዜም ይወድሻል ፍቅሬ አንቺ ነሽ ልላ ፍቅር የለኝም መቼም ክፉሽን💗💓💓💜💕 አልፈልግም ጭራሽ ማለት ነው እናቴ ወድሻለሁ ሁል ጊዜም ኑሪልኝ 💋💋💋💋💋💋💋💋💋💜💜💜💜
🎂🎂🎂🎂🎂
🎂🎂መልካም ልደት ሂወቴ🎂🎂
እኛ ምንጠይቀው
ዘላቂ መፍትሔ
ለሀገሪቱ ችግር ፣ ላጋጠመን እዳ
መንግስት የሚሰጠን ፣ እለታዊ አጀንዳ
ቀኝ እጅ ይታሻል ወይ ፣ ግራ እግር ሲጎዳ
💯ይቀላቀሉን💯👇
@Titland @Titland
@Titland @Titland
@Titland @Titland
@Titland 👈Join as
@Beki_B
/channel/titland
"አልቻልኩም አቅም የለኝም!" አትበል ካልክ ግን አትችልም አቅምም አይኖርህም፡፡
አንተ ስለራስ ለራስህ የምትለውን ነህ፡፡በውስጥ ለራስህ የምትነግረው ታሪክ(ጥሩም ሆነ መጥፎ) በውጪ ሁኔታ ራሱን ይገልጣል፡፡ውጫዊ ሁኔታው በውስጥህ ምርጫና ውሳኔ የተፈጠረ ነው፡፡የውጪው አለም የውስጡ ግልባጭ ነው፡፡ሁኔታው ላይ በማተኮር ሁኔታውን መለወጥ አይቻልም፡፡ሁኔታው የሚለወጠው ውሳጣዊ ምርጫና ውሳኔያችን ሲለወጥ ብቻ ነው፡፡
መምረጥ ለሰው ብቻ የተሰጠ የከበረ ስጦታ ነው፡፡ዛፍ ብንሆን ኖሮ ሁኔታው መጥፎ ሲሆን ምን ይውጠን ነበር?
ፈጣሪ ይመስገን ሰው ነንና አሁን ያለንበት ሁኔታ መጥፎ ቢሆንም እንኳን አእምሯችንን በመጠቅም ወደ ጥሩ መለወጥ እንችላለን፡፡
ይህንን ለማድረግ(ሁኔታውን ለመቆጣጠር) ግን አእምሯችን የሚሰራበትን መንገድ ማወቅ ይገባናል፡፡አእምሯችን በሁለት አገልግሎት አሉት፡፡የመጀመርያ የትላንትን ተዘክሮ( memory ) መዝግቦ መያዝ ነው፡፡ሁለተኛው የአእምሯችን አገልግሎት ደግሞ የመጪ ጊዜ መሪ ካርታ ሆኖ ማገልገል ነው፡፡የመጀመሪያው የአእምሮ አገልገሎት የአጭርና የረጅም ጊዜ ትዝታዎችን መዝግቦ የሚይዝ መሳርያ ሆኖ ማገልገል ነው፡፡ስማችንን፣ የምንኖርበትን ቦታ፣ ዘመዶቻችንን፣ የተማረነውን ትምህርት፣ የስልካችንን ፓስወርድ፣ ሐይማኖታችንን....ወዘተ ለአጭር እና ለረጅም ጊዜ የምንገለግልባቸውን መረጃዎች አእምሯችን አቅፎ ይዟል፡፡በአእምሯች ውስጥ ሀላፊ ጊዜ ያጋጠሙን ጥሩና መጥፎ ትውስታዎች አሉ፡፡ነገር ግን አእምሯችን ብዙ ጊዜ በሀላፊ ጊዜ ያጋጠሙን መጥፎ ነገሮች ላይ የመወዘፍ አመል አለበት፡፡የትላንት ስህተታችንን እያገዘፈ በቁጭት ውስጥ ያስረናል፡፡አሁን የሆነ ስራ ለመስራት ስንነሳ ከዚህ ቀደም ያጋጠሙንን መጥፎ ክስተቶች እንዳለ በመዘርዘር ሊያስቆመን ያስፈራራናል፡፡አእምሮን በዋናነት የሀላፊ ጊዜ ትዝታ መጋዘን አድርግ መጠቀም ከጥቅሙ የይልቅ ጉዳቱ ያመዝናል፡፡እውነተኛው የህይወት አቅጣጫ ወደ ትላንት የሚመራ አይደለም፡፡እውነተኛው የህይወት አቅጣጫ ወደ ነገ እና ወደ መጪ ጊዜ የሚመራ የእድገት ጉዞ ነው፡፡እኛ የምንፈልገው መጪ ጊዜ ግን በራሱ ሰዓት ድንገት የሚከሰት ነገር አይደለም፡፡የምንፈልገው መጪ ጊዜ እኛ ራሳችን ለራሳችን መፈጠር አለብን፡፡ይህንን ለማድረግ ደግሞ የአእምሯችንን ከትላንት ትዝታ ወደ ነገ አላማና ተስፋ ማዞር አለብን፡፡በሚመጣው ጊዜ ላይ ምርጥ ህይወት ለመቅጨት አእምሯችን የሚመጣው ጊዜ ጠቋሚ ካርታ ሆኖ እንዲያገለግለን መፍቀድ አለብን፡፡ ባለመታደል ግን አብዛኞቻችን አእምሯችንን የምንጠቀመው የሀላፊ ጊዜ ትዝታዎች መጋዘን አድርገን ነው ፡፡የሚመጋውን የህይወታችንን ምዕራፍ የምንተነብየው ከዚህ ቀደም በነበረን እውቀት ፣ ገንዘብና ልምድ ነው፡፡ይህ ከሆነ ደግሞ አዲስ ነገር በህይወታችን አይከሰትም፡፡በመጪው ጊዜ ላይ አዲስ ነገር የሚከሰተው አእምሯችንን የመጪ ጊዜ ካርታ አድርገን መጠቀም ስንችል ብቻ ነው፡፡እውነት ነው አእምሯች ከፊትለፊታችን ያለን ወይም አሁን የሌለን እውነታ(future) የመፍጠር አቅም አለው፡፡በዚህ መልኩ አእምሮን መጠቀም ወኔ እና እምነትን ስለሚጠይቅ አብዛኞቻችን በዚህ መልኩ አእምሮን መጠቀም ያስፈራና፡፡አእምሯችንን መጪ ጊዜን እንዲፈጥርልን አድርገን መጠቀም ስንጀምር ምቾት አይሰጠንም፡፡ምክንያቱም አእምሯችን የሚወስደን ከዚህ ቀደም አይተነው ወደ ማናውቅበት አዲስ ቦታ ነው፡፡ይህ ደግሞ ያስፈራል፡፡ማንም ሰው ወደ ማያውቅበት እንግዳ ቦታ ተጉዞ መደናገር አይሻም፡፡በጣም ጥቂት ሰዎች ግን ቢያስፈራም ወደዚህ አዲስ አለም ይጓዛሉ፡፡እውነኛ እደገት እና ህይወት የሚገኘው ወደዚኛው ቦታ የመጣን ዕለት ብቻ ነው፡፡ይህ የአለም ስልጣኔ ሁሉ ምንጭ ነው፡፡መጪ ጊዜን መፍጠር እጅግ ከባድና ፈታኝ ስራ ነው፡፡
ለምሳሌ ለአንድ አፍታ አሁን ካላቹበት ሁኔታ ውጡ፡፡የዛሬ ሀምሳ ወይም አስራ ወይም አምስት ወይም ደግሞ አንድ አመት ወደፊት ተጉዛቹ በምትፈልጉበት ቦታ ራሳቹን አስቀምጡ፡፡
የምትወዱትን ነገር ብቻ እየያደረጋቹ ራሳቹን ተመልከቱ፡፡ ያ አዲስ አለም ምን ይመስላል?
ከዚህ ቀደም አይታቹ በማታውቁትና ፈጽሞ ልዩ በሆነ ሁኔታና ድባብ ራሳቹን በአእምሯቹ screen ልታዩ ትችላላቹ?
ያን በውስጣቹ የምትመለከቱትን ትልቅ አለም እንደ ምታሳኩት ታምናላቹ?
ከአሁኑ ሁኔታ ጋር የሰማይና የምድር ያህል ልዩነት ቢኖረውም እንኳን ይሆናል የሚል እምነት በውስጣቹ አለ?
አሁን የሚታየውን ሁኔታ ሳይሆን የማይታየውን አዲስ አለም ታምናላቹ?
አብዛኞቻችን ይህንን አናደርግም፡፡በውስጣችን የምናልመውን ትልቅ ሀሳብ ለማሳካት ወኔ የለንም፡፡
በውስጣቸው ባለ ትልቅ ሀሳብ ለሚተማመኑ ሰዎች ግን ጊዜውን ጠብቆ ሁሉም ይቻላል፡፡የማይታየወን የሚያምን የማይቻለውን ያደርጋል፡፡እምነት ተራራን የመናድ ሁኔታን የመለወጥ ሀይል አለው፡፡ከሁኔታው በላይ ከፍ ብለን እናስብ፡፡
#መልካም_ቀን!
💯ይቀላቀሉን💯👇
@Titland @Titland
@Titland @Titland
@Titland @Titland
@Titland 👈Join as
@Beki_B
/channel/titland
ናፈቀኝ ሀገሬ
"""""""""""""""
ብዕሬን ሸክፌ
ሀሳብ አጠንፍፌ
ቃላት አጣልፌ
ሄድኩኝ ከወረቀት፤
ቅኔ ልደረድር
ግጥሜን ልሰድር
ከመድብሌ ልከት!
ሀገር ብዬ ጀመርኩ
ሀገሬን ላልጨርስ
ጦማሬን ከትቤ፤
ዋ ብሎ አስፈራራኝ
ከራሴ እያጣላ
አመንትቶ ቀልቤ!
.
.
ለምን አልሽ አለሜ?
.
.
እንደምን ይፃፋል
ስለሀገር ግጥም
ጦቢያ ይሉት ቅኔ፤
ሁሉም አስሮ ይዞት
ዘር የሚሉት ብሂል
የአስተሳሰብ ጠኔ፤
የአባ ጃርሶ ቁጣ
የአቶ መርዕድ ዱላ
የት አለና? ዛሬ፤
የፅዮን ስፍስፍ ልብ
የከድጃ ገር ነፍስ
ርቆ ሄዶ ከኔ፤
የትርንጎ ውበት
የአለሚቱ ምክር
ጠፍቶ ከዘመኔ፤
እንደምን ይፃፋል
ሀገር ይሉት ግጥም
ሀገር ይሉት ቅኔ!
.
.
ጉድ አለ በሀገሬ
.
.
አዬ ጉድ ነው መርዶ
ሰው ከራስ ተሰዶ
ከእምነቱ እረክሶ፤
እሩቅ እሩቅ ሲሄድ
እሳትን ሲላመድ
እያደር ተናንሶ፤
ስክነት ይሉት ጠፍቶ
ሰው እብሪትን ሽቶ
እሳትን ተላብሶ፤
አባት አንገት ደፍቶ
እናትን ሆድ ብሷት
አይኖቿ አልቅሶ፤
እህት በእህቷ
ወንድም በወንድሙ
ጦር ሰይፍ ተማዞ፤
መከባበር ጠፍቶ
ልጂት እናት ንቃ
ልጅ አባቱን አ'ዞ!
ሰው በቁም ታርዞ
ሲሄድ ሲፈረጥጥ
ቁልቁሉን እሩጫ
የእውር ድንብር፤
እንዴት ከግጥሜ ላይ
ጎላ ብላ ትፃፍ
ቅኔ ያላት ሀገር?
.
.
እንዴት? .....እንዴት?
.
.
ወገን ተከፋፍሎ
እገደል ተምሎ
በዘርና በጎጥ፤
በነጮች ሰበካ
ከሀገር ተሰዶ
በድኑን ሲቀመጥ፤
በዳንኪራ ፈዞ
ቁሙን ተገንዞ
ከሀገር ሲፈረጥጥ፤
እና እንዴት ተብሎ
ስለ ሀገር ይፃፍ
ሀገር ትቆላመጥ?
.
.
ተመልከች ዓለሜ
.
.
ሀገር ማለት ሰው ነው
ሰው ነው
ሰው ነው ሀገር፤
ሰው ከሌለ የለም
ሀገር ይሉት ወሬ
ሀገር ይሉት ነገር!
ሰብዕና ጎድሎ
በሌላ ተደልሎ
በቁም ተቀምጦ እሩቅ ከከነፈ፤
ምን ተብሎ ቅኔ
ምን ተብሎ ግጥም
ስለ ሀገር ተፃፈ?
.
.
(እናማ)
.
.
ስለሀገር ያሰብኩት
ብዙ የተለምኩት
ባሸተው ሰንፍጦ
ብቀምስ ጎመዘዘኝ፤
ከእውነቱ ተውኩና
ከተስፋ አጠቀስኩኝ
ብዕሬን አነሳሁ ከወረቀት ልቀኝ፤
ሀሳቤን ሳሰፍር
የሚል ግጥም ፃፍኩኝ
ሀገሬ ላይ ቆሜ ሀገሬ ናፈቀኝ!
(ሀገሬ ናፈቀኝ)
አብርሃም ፍቅሬ
(የቅዳስ ልጅ)
ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@poimfitsae @poimfitsae
@poimfitsae @poimfitsae
አንቺ ከሄድሽ ወዲ
.
.
አንቺ ከሄድሽ ወዲ
ናፍቆት በሹል መርፌው እየጠቀጠቀ
ለየዋሁ ልቤ ስቃይ እያረቀቀ
እማላገኝሽን
እማላገኝሽን
አንቺን አምጣት አለኝ
እሷን አምጣት አለኝ
ቆራርጦ አፈራርሶ ካፈር ሊያዳቅለኝ
እስትንፋሴን ነጥቆ ከጉድጓድ ሊጥለኝ
አንቺ ከሄድሽ ወዲህ
መሰለኝ መቃብር
ያለሁበት ሰፈር
ዘልዬ ቦርቄ
ያደኩበት መንደር
ደሞም ባከባቢው
የሚወጣው ድምፀት
የሚሰማው ጩኸት
መሰለኝ የሲኦል
ጫጫታ'ና ሁካታ፥
የአጋንንት ፉጨት
የሐጣን ዋይዋይታ፥
የሐጥአን እሪታ...
እንዲም አስባለሁ
ሰፈርተኛው ሁሉ
ሞልቶለት ሲዘክር
ይመስለኛል የኔ
የአርባዬ ተስካር
የሰማንያ ተስካር
ሙት አመቴን ማውሻ
እኔን ማስታወሻ
ደግሶ ማልቀሻ...
አንቺ ከሄድሽ ወዲ
አለሜ በሙሉ ተመሰቃቀለ
ሁሉ በኔ አየለ
ህሊናዬ ዛለ
ዋለለ ቆሰለ
መላው ሰውነቴም
ነደደ ከሰለ
ከሰለ
.
.
እንደው ባጠቃላይ
አንቺ ከሄድሽ ወዲ
ምናለ ያልሆንኩት ምናል ያላረግሽኝ
አንድ ጊዜ ሄደሽ አስሬ ገደልሽኝ!!!
ማይክል ሰለሞን
(የቡዜ ልጅ)
ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@poimfitsae @poimfitsae
@poimfitsae @poimfitsae
▣▣▣▣▣▣▣▣▣▣▣▤▤▣▣▣▣▣▣▣▣▣
.....የጷጉሜ ገፃቼ.....
በፀጥታዬ ውስጥ ትልቅ ጩኸት ይሰማኛል። ባለመናገሬ መሀል ሀያል ቃላትን አምቄያለሁ። የምር ውዴ የምነግረው አጥቼ ሰሚ ሲጠፋብኝ ለአንዲት ጨረቃና ለአእላፍ ከዋክብቶች ሁላ ሳይቀር ለፍልፌያለሁ።
ህይወት ግን ምን አይነት ናት.........
እሷ ባለችው እንጂ እኛ ባሰብነው፤ አይናችን እንደሚመለከተው
እንጂ ልባችን
እንደሚያስበው አናስኬዳትም.... እኔም ለዚህ ነበር
የእኔ አንቺን
ማፍቀር ብቻ
ደስታዬን ሙሉ ያደርገዋል፤ የእኔ ፍቅር ለሁለታችንም ይበቃል ብዬ አስብ የነበረው....
ነገር ግን ውዴ ለካ ሁሉም ስህተት ነበር ያንዱ
ማፍቀር የሁለቱንም
ፍቅር
አይተካምና.....
..ህይወቴ.........
ዝም ብለሽ ትሄጃለሽ ብዬ አላሰብኩም ነበር, ደግሞም አንቺ ነበርሽ
ተናግሮ ከሄደ ይልቅ
ዝም ብሎ የሄደን ሰው
መጠበቅ እጅጉን
ይጎዳል ያልሽኝ...
ደግሞሞ በበፊቱ ፍቅርሽ የተሰራብሽን በደል ህመሙን እያወቅሽ
በስቃዩ ውስጥ እየኖርሽ
ለሌላው ታጋሪዋለሽ ብዬ
አላስብም ነበር....
ውዴ በመሄድሽ አላዘንኩም
ቂምም አልያዝኩም
ምክንያቱም
ምናልባት ከኔ ያጣሽውን ከሌላው ለማግኘት ልብሽ ከጅሎ ይሆናል የማዝነው
........................................................................................................................................................................................................ ይቀጥላል........
#እንዲቀጥል_vote_ሰጠት_ሰጠት
^ከ~ጷጉሜ ገፃቼ ውስጥ የተቀነጨበ
4ተኛው ገፅ የመጀመሪያው ክፍል^
✍ተፃፈ በ @Mak_bale
4,13,2012
@joftdav
@joftdav
@joftdav
🎧🎧🎧🎧🎧🎧🎧🎧🎧🎧🎧🎧🎧🎧
ልዩ ልዩ ግጥሞችን!!
🖊በ ፅሁፍ
🎙በ ድምፅ
🎥በ ቪዲዮ አሰርተው
ለወዳጅዎ
ለፍቅረኛዎ
ለልጅዎ
ለእህት/ወንድም
ለፈለጉት ሰው ልደት ፣ የፍቅር መግለጫ ፣ የይቅርታ መጠየቂያ ፣ የሀዘን መግለጫ የሆኑ፤
ሀሳብን የሚገልፁ አንጀትን የሚያርሱ ግጥሞችን ለማሰራት 👉 @ft2194 ላይ ያናግሩኝ!!
@poimfitsae @poimfitsae
🎤🎤🎤🎤🎤🎤🎤🎤🎤🎤🎤🎤🎤🎤
ሀገር እንደ ሀገር ስታነባ አምርራ
የወገንን ስጋ ሲበላው አሞራ
መግደልና መሞት
የለት ተእለት ዜና ሆኖ እየተወራ
ሰላም ወዴት አለች
ወዴት ኮበለለች ወዴት ሄደች ሸሽታ
ሰብአዊነታችን
ከምን ተቀበረ ወርዶ ከከፍታ
ሀበሻነታችን
መለያ ስማችን
የዋህነታችን ስለምን ተፋቀ
ስለምን የሰው ልጅ
ከእንስሳነት ወርዶ ከክፋት ወደቀ
ሀገርን እንደ ሀገር
ሞገስ ያለበሰው የሀገር ጠባቂ
ለምን ተሰቃየ
ተፈተነ ክንዱ በወገን ሰባቂ
ለሀገር አንገቱን
ሰቶ ለሚሰዋ መስውአት ወታደር
ሞቱ ለህይወት ነው
ለሀገር ህልውና ለመለዮ ክብር
ዛሬም ወገን አለህ
የሞትክለት ህዝብህ ክብርህን አይረሳም
ስጋህ ቢቀበርም
አላማህ ትልቅ ነው ከግቡ አይገታም
ለሀገር የሞተ
ከኗሪ በላይ ነው የሰውነት ልኩ
ሞተ አይባልም
እሬሳ አይባልም የአንበሳ ነው መልኩ
አበሻነት ስሙእንታቀፍ
ከምግባሩ ራቀ ከፋ መሰይጠኑ
ስለምን ይወጋ
ስለምን ይታመስ ወገን በወገኑ
ይበቃል ይገታ
የመከራው ዝናብ ከጣራችን ይንጠፍ
ፅልመቱን ገርስሰን
በሀበሻነት እቅፍ ዛሬም እንታቀፍ
ከ ፍፁም ጥበበ
@poimfitsae @poimfitsae
ይድረስ ..ለማይደርስልን መንግስት
።
።
እንደምነህ መንግስት እኛ አለን በደህና
ባመቻቸህልን የለውጥ ጎዳና
ሺዎችን ገብረን ፣ ለአንድ ብልፅግና
እየተሰበርን ሰበር በሚል ዜና
ተራ እየጠበቅን ፣ ለሞት ተሰልፈን
እግረ መንገዳችን ፣ ድንገት ከሞት ተርፈን
ከደብዳቢ ጋራ
ደብዳቤ እስክንልክ፣ በደማችን ፅፈን
እኛ አለን በተድላ
እንደምነህልን?
እንደምነህልን ካልንህስ በኋላ?!
እኛ አለን በድሎት
እኛ አለን በፀሎት
ከገዳያችን ጋር ፣ ቀብር ስናስፈጥም
ስንኖር ኢትዮጵያዊ
ስንሞት ምን እንደሆንን ፣ ባናረጋግጥም
እኛ አለን በተአምር ፣ እኛ አለን በደህና
እየተገደልን
"መግደል መሸነፍ ነው" ፣ በሚል ፍልስፍና!
አንተ ግን እንዴት ነህ?
እልፎች ሚቃወሙህ ፣ የብዙዎች ምርጫ
ፍትህ ለሚጠይቅ ፣ የምትሰጥ መግለጫ
የእልፎች አሻጋሪ ፣ የእልፎች እንቅፋት
ትኩረት የምትሰጥ
ከሰዎች ነፍስ ይልቅ ፣ ለአበቦች መጥፋት
እንደምነት አንተ?!
#ሼር ድምፃችን ይሠማ
@Titland @Titland
@Titland @Titland
@Titland @Titland
@Titland 👈Join as
@Beki_B
/channel/titland
🛎🛎🛎🛎🛎🛎🛎🛎🛎🛎🛎🛎🛎🛎
Pdf መፅሀፍቶችን ፈልገው አጥተዋል??
ለምን @ft2194 ላይ አያናግሩኝም ታዲያ😊
እመጓ
ተልሚድ
የምግብ አሰራር
ፈረንሳይኛ መማሪያ
እነዚህ ጥቂቶቹ ናቸው ሌሎችም መፅሀፍት በእጃችን ስለሚገኙ ከእርስዎ የሚጠበቀው inbox ብቻ
@poimfitsae @poimfitsae
🛎🛎🛎🛎🛎🛎🛎🛎🛎🛎🛎🛎🛎🛎
ኑሮ በየቀኑ የምንወጣው ተራራ ነው፡፡አንዱን ጨርሰን ስንደሰት ሌላኛው ይደቀናል፡፡ሌላኛውን ስንወጣ የባሰው ደግሞ ይጠብቅናል፡፡
+
የማያቋርት ስቃይ አለብን፡፡ስቃዩ ግን ጥሩ ነው፡፡ትክክለኛ አቅማችን የሚወጣው ከትክክለኛ ፈተና ጋር ስንታገል ነው፡፡
+
ብዙ ሰው ከፊቱ ያለውን ተራራ ግዝፈት እንጂ በውስጡ ያለውን የፈጣሪን ጉልበት አያውቅም፡፡ ተራራው ከፊትለፊቱ ሲደቀን የሚወጣበትን መንገድ ከመፈለግ ይልቅ ማማረርን ይመርጣል፡፡ምክንያቱም ማማረር ቀላል ነዋ፡፡
+
ማለቃቀሱን ማንም ያውቅበታል፡፡ወደ ተራራው ጫፍ የሚወስደውን መንገድ ማገኘት ግን ከባድ ነው፡፡ይህ የጥቂት ጀግና ሰዎች ስራ ነው፡፡ላብ፣ ደምና እንባ ማፍሰስን ይጠይቃል፡፡ብዙ ሰዎች ደግሞ ይህን ማድረግ አይፈልጉም፡፡ፊሪ እና ሰነፍ ናቸው፡፡በራሳቸው ጉልበት ፤ በፈጣሪያቸውም ሐይል እምነት የላቸውም፡፡ምኞታቸው ሁሉም ነገር ከልጋ በአልጋ አንዲሆን ነው፡፡ህይወት ደግሞ ተራራ በተራራ እንጂ አልጋ በአልጋ አይደለም፡፡
+
አለም አሁን ካለችበት ከፍታ የደረሰችው በችግር ነው፡፡ችግር ባይኖር? ሰዎች ዛሬም ድረስ በዋሻ ውስጥ ነበርን፡፡መብራት፣ መኪና፣ እርሻ፣ ፕሌን፣ ኢንተርኔት፣ ስልክ፣ ኮምፒውተር፣ ቤትና ሁሉም ለሰው ልጆች ጠቃሚ የሆኑ ነገሮች የተወለዱት በችግር ምክንያት ነው፡፡ሰዎች ችገራቸውን ለማሸነፍ ሲታገሉ ዛሬ ፍጹም ልዩ የሆነ አለም ፈጥረዋል፡፡ታዲያ ምስጋና ለአቶ ችግር አይገባም ትላላችሁ?
+
ከፊትለፊታችሁ ያለው ተራራ ምንድን ነው? ችግራችሁ ምንድን ነው? ገንዘብ ማጣት? ስራ አጥነት? የተበላሸ ትዳር? ስደት? በሽታ? በራስ መተማመን ማጣት? ሱስ? ምንድን ነው?
+
ችግራችሁን የምትመለከቱትስ እንዴት ነው? ተራራችሁን የምታዩት እንዴት ነው?
ሊያሳድጋችሁ እንደመጣ ስጦታ? ወይስ ሊያስቆማችሁ እንደመጣ ፈተና?
+
ይህ የምርጫ ጉዳይ ነው፡፡ብዙ ሰው ችግሩን እንደ ጠላት ይመለከታል፡፡ችግራችሁን እንደ ወዳጅ አድርጋችሁ ካያችሁ ግን እናንተ ትክክለኛ ጀግና ናችሁ፡፡እሱን ለማሸነፍት ስታነቡ፣ ሰው ስታማክሩ፣ ሞያ ስትለማመዱ፣ ስትነግዱ፣ ገንዘብ ስትቆጥቡ፣ ጸሎት ስታደርጉ ፍጹም ሌላ ሰው ትሆናላችሁ፡፡ሌሎች ከታች ሆነው ሲያማርር እናንተ ከተራራው ጫፍ ትደርሳላችሁ፡፡ከአናቱ ሆናችሁ ንጹ አየር ትምጋላችሁ፡፡በከፍታው ያለውን ቪውም enjoy ታደርጋላችሁ፡፡ሌላ ችግር ሲጋረጥባችሁም አትደናገሩም፡፡ሌላ መፍትሄ ፈልጋችሁ ታሸንፉታላችሁ፡፡
+
#መልካም_ቀን
💯ይቀላቀሉን💯👇
@Titland @Titland
@Titland @Titland
@Titland @Titland
@Titland 👈Join as
@Beki_B
/channel/titland
እልፍ ከሲታዎች ፣ ቀጥነው የሞገጉ
“ሥጋችን የት ሄደ” ፥ ብለው ሲፈልጉ
በየሸንተረሩ ፤ በየጥጋጥጉ
አስሰው አስሰው ፥ በምድር በሰማይ
አገኙት ቦርጭ ሆኖ ፥ አንድ ሰው ገላ ላይ፡፡
።።።
(“ኗሪ አልባ ጎጆዎች”፤ በዕውቀቱ ስዩም)
💯ይቀላቀሉን💯👇
@Titland @Titland
@Titland @Titland
ከአንድም ሁለት ሶስቴ
ተራራ ወጣሁኝ ፣ ከአንቺ ጋር አብሬ
የሌለሽ ጊዜ ግን
ወለል ካለው ሜዳ ፣ አልሄድ ይላል እግሬ
ነይ መልሱን ንገሪኝ ፣ ምንድነው ችግሬ?
ምንድን ነው ችግርሽ
እግር ይይዛል ወይ ፣ እንደጓያ ፍቅርሽ😂??
💯ይቀላቀሉን💯👇
@Titland @Titland
@Titland @Titland
@Titland @Titland
@Titland 👈Join as
@Beki_B
/channel/titland
የምትፈልገው ነገር ትልቅ ከሆነ አትቸኩል፡፡ትልቅ ነገር ትልቅ ትዕግስት ይጠይቃል፡፡የህይወት ውድድር ማራቶን እንጂ መቶ ሜትር አይደለም፡፡
-
አሁን በሰዎች መካከል ለማንጸባረቅ እና ስኬታማ ለመምሰል አትጣር፡፡አቋራጭ መንገድም አትፈልግ፡፡በጠባቧ መንገድ እውነትን ይዘህ ተጓዝ፡፡ለስኬትህ ብለህ አትስረቅ ፣ አትዋሽ::
ስኬታማ ለመምሰል ራስህን አትጣ!
-
ይልቅ አንገትህን ድፋና በመጪዎቹ ሶስት፣ አምስት እና እስርት አመታት ልፋ፡፡የምትፈልገው ስኬት ካልመጣ strategy እያቀያየርክ እንደገና ልፋ፡፡
አሁን ጓደኞችህ ሲዝናኑ- አንተ ላብህን ጠፍአድርገህ ስራ!
እኩዮችህ በገንዘባቸው ፋሽን ሲከተሉ - አንተ ትንሽም ብትሆን ገንዘብህን ቢዝነስ ላይ invest አድርግ!
አነሱ ቴሌቪዥን ወይም ኳስ ሲመለከቱ - አንተ አንገትህን አቀርቅረህ ምርጥ መጽሐፍ አንብብ!
ለሚቆራረጠው ጊዜያዊ ስሜት ሳይሆን በረጅም ጊዜ ለሚመጣው ትልቅ ደስታ ኑር!
ልፋትህን ውደድ! ስቃይህን አፍቅር!
የድል አክሊል እና የስኬት ዋንጫ የሚዘጋጅልህ የሚዘጋጅልህ በመከራ ውስጥ አልፈህ ስትሄድ ብቻ ነው! ዝቅ ብለህ ስትሰራ ቀና ብለህ መሄድህ አይቀርም! እና አሁን ምን እየጠበክ ነው?
#መልካም ቀን
💯ይቀላቀሉን💯👇
@Titland @Titland
@Titland @Titland
@Titland @Titland
@Titland 👈Join as
@Beki_B
/channel/titland
አዲስ አመት በአዲስ ነገር/ብር/
(✍በረከት በዛብህ)
ይሄ ነዉ ጂማሬ አዲስ ባዲስ ነገር
አሮጌ 50 ብር በ አዲስ ሲቀየር
እነ መቶብሮች ከሰዉ እጅ ሲጠፉ
እነ 10ብሮች::::----
የማያልቅ ሠፌድ ዘላለም ሢሠፉ
እነ 5ብሮች:::---
ለማይፈላ ቡና ፍሬዉን በመልቀም እስካሁን ሢለፉ
እነ 1ብሮች ለቃላቸዉታምነዉ ሚዛን ሳያደሉ
ከጊዜም በኋላ እነ 5ብሮች ከትልቅ ማንነት በሳንቲም ሢቀሉ
ወሬዉን ሣያወራ ወሬኛም ላመሉ፡፡
፡፡፡ ፡፡፡፡......
ታድያ ከዚህ በላይ ምናለ አዲስ ነገር
ከአዲስ ዘመን ጋ ገንዘብን መቀየር፡፡
# መልካም_ቀን!
💯ይቀላቀሉን💯👇
@Titland @Titland
@Titland @Titland
@Titland @Titland
@Titland 👈Join as
@Beki_B
/channel/titland