♥️#ሕግ_እና_ፀጋ♥️
📌#ክፍል_አንድ (1)
============
♥️እንግዲህ እንዲህ ያለ ተስፋ ካለን #እጅግ_ገልጠን_እንናገራለን፥
2 ቆሮንቶስ 3 ፡12፤♥️
✍️በብሉይ/በአሮጌው ኪዳን እና በአዲስ ኪዳን
✍️በሙሴ እና በክርስቶስ
✍️በሕግ እና በፀጋ
✍️በእንስሶች ደም እና ክቡር በሆነው በኢየሱስ ደም መካከል ያለውን ልዩነት ያልተረዳ እና ጠንቅቆ የማያውቅ ሰው ብዙ እውነቶችን ያበላሻል። መጽሃፍ ቅዱስን ከፋፍሎ ባለ ማጥናት /2ጢሞ 2፡15 /
♦️እግዚአብሔር የአዲስ ኪዳን አገልጋዮች እንድንሆን ብቁወች አደረገን።
ፊደል /የሙሴ ሕግ ይገድላል መንፈስ/አዲስ ኪዳን ግን ሕይወትን ይሰጣል። 2ቆሮ 3፡6
✍️ሕግ በሙሴ ዘመን ለእስራኤል ህዝብ የተሰጠ ነበር ። ዮሐ 1፡17, ሮሜ 9፡4
❤️ፀጋ በክርስቶስ ከዘላለም ዘመናት በፊት የተሰጠ። 2ጢሞ 1፡9-11,
✍️ሕግ የሞት አገልግሎት ነው።
❤️ፀጋ የሕይወት አገልግሎት ነው። 2 ቆሮ 3፡7
✍️በሙሴ በኩል የተፈጸሙ ታምራቶች መካከል ውሀን ወደ ደም መቀየር ሲሆን ይህም የሞት አገልግሎትን ሲወክል
❤️ጌታ ኢየሱስ ግን የመጀመርያ ተዐምራቱን ያደረገው ሰርግ ቤት ነው ውሃን ወደ ወይን በመቀየር ሰማያዊና በመንፈስ ቅዱስ የሆነ ደስታ እና ሕይወትን አስጀመረ። ዩሐ 2 ,ዘፀ 7፡14-22
✍️የሕጉ አገልግሎት በመጣበት ጊዜ 3000 ሺ ሰወች ሲሞቱ። ዘፀ 32፡28
❤️የሕይወት አገልግሎት ፀጋ ግን በባለ ሀምሳ ቀን ለ3000ሺ ሰወች ሕይወትን ሰቷል። ሐሥ 2፡1-
ይቀጥላል........
ወንጌል ስለማን ነው????
=================
ልናስተውለው የሚገባን ነገር፦
👉ወንጌል ባለጠግነትም ድሀ መሆንም አይደለም
👉ወንጌል ልሳንም ጥምቀትም አይደለም
👉ወንጌል ከሰው ልጆች ተግባር ጋር የሚገናኝ አይደለም
❤️ወንጌል ነገር ሳይሆን ማንነት ነው እርሱም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።
ጌታ ኢየሱስ ስለ ሀጥያታችን እና ስለበደላችን መሞቱን,መቀበሩን እና መነሳቱን የሚያውጅ ለሰው ልጆች ሁሉ የሆነ የእግዚአብሔር የማዳን ሀይል ነው።
ሮሜ 1 (Romans)
3-4፤ ይህም ወንጌል በሥጋ ከዳዊት ዘር ስለ ተወለደ እንደ ቅድስና መንፈስ ግን ከሙታን መነሣት የተነሣ በኃይል የእግዚአብሔር ልጅ ሆኖ ስለ ተገለጠ ስለ ልጁ ነው፤ እርሱም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።
ሮሜ 1 (Romans)
16፤ በወንጌል አላፍርምና፤ አስቀድሞ ለአይሁዳዊ ደግሞም ለግሪክ ሰው፥ ለሚያምኑ ሁሉ የእግዚአብሔር ኃይል ለማዳን ነውና።
📌የወንጌል ዋነኛው መልዕክት
==================
የእግዚአብሔርን የማይለዋወጥ ፍቅር ለሀጥያተኞች የሚያውጅ እና በክርስቶስ የቤዛነት ስራ ሰዎች ከ እግዚአብሔር ቁጣ እንዲተርፉ፤ እና የዘላለምን ሕይወት በነጻ በእምነት እንዲቀበሉ ኃጢአት የሚያስከፍለውን ክፍያ ለመክፈል ማለትም ከሁሉ የከፋውን ሞትን ለመሻር ክርስቶስ ከ ድንግል ማርያም በድንግልና ተወልዶ ሰው ሆኖ መሞቱን፣ መቀበሩን፣ ከሞት መነሣቱን የሚናገር መልካም የምስራች ነው። ( ሐዋ13:28-40,ሐዋ13:38-41፣ ሮሜ.3:21-28፣ 1ቆሮ.15:3-4)።
የአብ ፍቅር
የወልድ ጸጋ
የመንፈስ ቅዱስ ሕብረት ከእናንተ ጋር ይሁን።
ሀሳቡን ከወደዱት ሼር ያርጉት
@tttgraceversion
@tttgraceversion
🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
በየእለት ህይወታችሁ ሳቃችሁን ሊቀማ የሚችል አይናችሁን በእንባ የሚሞላ ብዙ ጉዳይ ሊገጥማችሁ ይችላል።
⏩በዙህ ወቅት ከሚያስለቅስና ከሚያሳዝን ጉዳያችሁ አይናችሁን አንሱና ትኩረታችሁን የደስታ ሁሉ ምንጭ ወደሆነው ወደ እየሱስ አድርጉት ያኔ በሀዘን ፈንታ የደስታ ዘይት በህይወታችሁ ሲፈስ ታዩታላችሁ።
⏩የሳቅነው ሁሉ ሞልቶልን ሳይሆን ሁሉ በሁሉ፣ ሁሌም ሙሉ የሆነው እየሱስ የህይወታችን ባለቤት እና ጌታ ከእኛ ጋር ስለሆነ ነው።
👉የደስታችን እና የሳቃችን ባለቤት እየሱስ ይባረክ።
👉ደግሜ እላችሗለው ሁል ግዜ በጌታ ደስ ይበላችሁ።
የአብ ፍቅር
የወልድ ጸጋ
የመንፈስ ቅዱስ ሕብረት ከእናንተ ጋር ይሁን።
ሀሳቡን ከወደዱት ሼር ያርጉት
@tttgraceversion
@tttgraceversion
🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
የድነታችን ዋስትና
✍️ የድነታችን ዋስትና የሚረጋገጠው በእግዚአብሔር ያለንን እምነት ጠብቆ በማቆየት ችሎታችን አይደለም።
✍️ አዲሱ ኪዳን በእኛ እና በእግዚአብሔር መካከል ያለ ኪዳን አለመሆኑን አስታውስ። እግዚአብሔር ከራሱ ጋር ያደረገው ኪዳን ነው (ዕብራውያን 6:17–19)።
✍️ በዚህ በአዲሱ ኪዳን ሥር ድነታችን የተጠበቀው በአንድ ወገን በእግዚአብሔር እና በሌላኛው ወገን ደግሞ በእግዚአብሔር መካከል ነው።
✍️ ያልጀመርነው እና የማናስቀጥለው ወይም የማንጠብቀው ኪዳን ተጠቃሚዎች ነን። ስለዚህ በእርሱ መቀጠላችንን እርግጥ የሚያደርግልን እግዚአብሔር ነው።
የአብ ፍቅር
የወልድ ጸጋ
የመንፈስ ቅዱስ ሕብረት ከእናንተ ጋር ይሁን።
ሀሳቡን ከወደዱት ሼር ያርጉት
@tttgraceversion
@tttgraceversion
🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
በሚሻለው መኖር
✍️ ሕጉ ማዕከል ያደረገው ሰውን ሲሆን፤ ጸጋ ግን ማዕከል ያደረገው ኢየሱስን ነው።
✍️ ሕጉ አንተ ማድረግ ያለብህ ላይ ሲያተኩር፤ ጸጋ ግን ኢየሱስ ያደረገልህ ላይ ያተኩራል።
✍️ ሕጉ፣ አንተ ባለመታዘዝህ ምክንያት ውድቅ ተደርገሃል ሲል፤ ጸጋ ደግሞ በኢየሱስ መታዘዝ ምክንያት አንተ ብቁ ሆነሃል ይላል።
✍️ በሕጉ ስር የምትጸድቀው ትክክል ስትሰራ ነው ሲል፤ በጸጋ ስር ደግሞ የምትጸድቀው በትክክል ስታምን ነው ይላል።
የአብ ፍቅር
የወልድ ጸጋ
የመንፈስ ቅዱስ ሕብረት ከእናንተ ጋር ይሁን።
ሀሳቡን ከወደዱት ሼር ያርጉት
@tttgraceversion
@tttgraceversion
🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
❤️#መልከጼዴቅ_የክርስቶስ_ምሳሌ❤️ =====================
✍️ ክርስቶስ በብሉይ ኪዳን (Christ in Old Testament )
♦️የብሉይ(የአሮጌው) ኪዳን መፅሐፍት ስለ ክርስቶስ የሚያወሩ እና ወደ ክርስቶስ የሚተረጎሙ ናቸው፡፡
✍️ጌታ ኢየሱስ የብሉይ ኪዳን መጽሐፍት ስለ እርሱ እንደሚያወሩ ተናግሯል ዮሐ 5:39,45-47
✍️በሕግ(በ5ቱ የሕግ መጽሐፍት) እና በነብያት ሁሉ ስለ እርሱ የተፃፈውን ተረጎመላቸው። ሉቃ 24:19-
✍️ መልከጼዴቅ በአብርሃም ዘመን ይኖር የነበረ እና የክርስቶስ ክህነት እና ንግስና በምሳሌ እንዲገልጥ እግዚአብሔር የተጠቀመበት ሰው ነው።
ዘፍ14:17-
✍️ በእግዚአብሔር ልጅ(በኢየሱስ ክርስቶስ) ተመስሎ(ምሳሌ)ሆኖ ለዘላለም ይኖራል እንጂ ራሱ ለአብራሃም የተገለጠው ክርስቶስ አይደለም።
✍️መጽሐፍ ቅዱስን በጥልቀት ካጠናን መልከጼዴቅ በታሪክ ውስጥ የነበረ ሰው እንደሆነና የክርስቶስን ክህነታዊ እና ንጉሳዊ (ካህንም ንጉስም) አገልግሎትን ምሳሌ(ጥላ) እንዲሆን እግዚአብሔር የተጠቀመው ሰው ነበር።
✍️እናትና አባትና የለውም ሲል መጽሐፍ ቅዱስ መልከጼዴቅ የተገኘበት ወይም የተወለደበት መነሻ የለውም ማለት አይደለም። ይልቅ ግን በቀላሉ ካየን ስለ መልከጼዴቅ መነሻና ስለቤተሰቡ(ወላጆቹ) የተጻፈ ወይም የተመዘገበ ታሪክ በብሉይ ኪዳን የለም ማለት ነው። የመልከጼዴቅ ክህነት እንደ ሌዊ ልጆች ክህነት ከመነሻ ጋር ምንም ግንኙነት የለም።
✍️ዕብ ምዕ. 7፥3፤ አባትና እናት የትውልድም ቍጥር የሉትም፥ ለዘመኑም ጥንት ለህይወቱም ፍጻሜ የለውም፥ ዳሩ ግን በእግዚአብሔር ልጅ ተመስሎ ለዘላለም ካህን ሆኖ ይኖራል።
( ይህን ሲል የመልከጼዴቅ ክህነት የተጀመረበት ጊዜና ያበቃበት በብሉይ ኪዳን ታርክ አልተመዘገበም ለማለት ነው።)
"ለዘላለምም ካህን ሆኖ ይኖራል"፦ ሲል በሕይወት መኖርን ቀጥሏል ለማለት ሳይሆን መልከጼዴቅ ያገለገለው ክህነታዊ አገልግሎት ቀጥሏል ለማለት ነው።
(ይህ ደግሞ የመልከጼዴቅ ሞት በመጽሓፍ ቅዱስ አለመገለጹን እንጂ መልከጼዴቅ የማይሞት መሆኑን ለማመልከት አይደለም።)
ዕብራውያን 7 (Hebrews)
24፤ እርሱ ግን ለዘላለም የሚኖር ስለሆነ የማይለወጥ ክህነት አለው፤.....
26፤ ቅዱስና ያለ ተንኮል ነውርም የሌለበት ከኃጢአተኞችም የተለየ ከሰማያትም ከፍ ከፍ ያለ፥ እንደዚህ ያለ ሊቀ ካህናት ይገባልና፤
✍️ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከጌታም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን።
በመተማመን ቅረብ
✍️ በታላቅ መተማመንና በደፋርነት የመኖር ቁልፍ ኃጢአትህ በሙሉ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እንደተሰረየልህ መረዳትና የእግዚአብሔር ተወዳጅ ልጅ በመሆንህ የሰማይ አባትህ ባንተ እንደማይቆጣ ማወቅ ነው።
✍️ ኃጢአቶችህ በሙሉ በመስቀል ላይ በኢየሱስ ሥጋ ላይ ተፈርዶባቸው ተቀጥተዋል፣ ይህ እውነት ነው ግን በአንተ የሆነ አይደለም።
✍️ ኃጢአታቸው ሁሉ ላንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ይቅር እንደተባለ የማይተማመኑ ብዙ አማኞች አሁንም ከጥፋተኝነት፣ ከፍርሃትና ከመኮነን ጋር እየታገሉ ነው።
✍️ እነዚህ ሰዎች በወደቁ ቁጥር ምሕረትን ለመቀበልና በሚያስፈልጋቸው ጊዜ የሚረዳቸውን ጸጋ ለማግኘት ወደ ጸጋው ዙፋን በድፍረት ከመቅረብ ይልቅ ልክ አዳምና ሔዋን በኤደን ገነት እንደተደበቁት ሁሉ እነሱም ከሰማያዊ አባታቸው ይደበቃሉ። በማፈርና በፍርሃትም አንገታቸውን ይደፋሉ። (ዕብ4፡16)።
✍️ ግን አንተስ ኃጢአቶችህ በሙሉ ይቅር የተባሉ ለመሆናቸው ማረጋገጫ አለህ? ኢየሱስን ጌታህንና አዳኝህ አድርገህ በተቀበልክበት ቅፅበት ያለፈው፣ የአሁን እና የወደፊት ኃጢአትህ በሙሉ ይቅር ተብሏል።
✍️ የእግዚአብሔር ቃል በኤፌ 1፡7 ላይ “በውድ ልጁም፥ እንደ ጸጋው ባለ ጠግነት መጠን፥ በደሙ የተደረገ ቤዛነታችንን አገኘን እርሱም የበደላችን ስርየት።” ይለናል።
✍️ ዳግም ስትወለድ አንዴ በክርስቶስ ውስጥ ስለሆንክ የበደል ሥርየት ለማግኘት መሞከር አይጠበቅብህም።
✍️ ይህ የኃጢአት ሥርየት የተገኘው አንተ በሠራኽው ሥራ ሳይሆን እርሱ በጸጋው ባለጠግነት የሰጠህ አንተ ያልከፈልክበትና ያልተገባህ ሞገስ ነው!
የአብ ፍቅር
የወልድ ጸጋ
የመንፈስ ቅዱስ ሕብረት ከእናንተ ጋር ይሁን።
ሀሳቡን ከወደዱት ሼር ያርጉት
@tttgraceversion
@tttgraceversion
🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
#እኔነት
እኔነት የትሕትና መንገድ ተጻራሪ፣ የትሕትና ጸር ነው። እኔነት ለአህያዊ አስተሳስብ ዳርጎ እኔ ከሞትኩ የሚያሰኝ እዳ ነው። እኔነት መተካከልን ብቻ እያሳየ፣ በመተው ፈንታ ይገባኛል የሚያሰኝ ስግብግብ የአልጠግብ ባይነት መንፈስ ነው። እኔነት ባልንጀሬን በማለት ፈንታ፣ እኔ እብስ የሚያሰኝ ቁራኛ ነው። እኔነት የክርስትያናዊ ሕይወት ፍጹም ተጻራሪ ነው። እኔነት በክርስቶስ ኢየሱስ ያልነበረ የዓለማዊነት ርዝራዥ ነው።
እኔነት ትእቢትን አድርቶ ለስብራት የሚዳርግ ደመኛ ነው። ዘማሪው "መጎንበስ የጠላ ድንገት ይሰበራል፣ እኔነት ሲበዛ ትእቢትን ያደራል" ብሎ ዘምሯል። እኔነት ራስን ብቻ እንጂ ሌላውን የሚከልል መጋረጃ ነው። እኔነት በሌላው ሥራ ሳይቀር ራስን ለማሳየት ከፍ ያለ ማማ ላይ መውጣት ነው። እኔነት ከእርሱ ነው፣ በእርሱ ነው፣ለእርሱ ነው በማሰኘት ፈንታ፤ ከእኔ፣ በእኔ፣ ለእኔ የሚያሰኝ እብሪት ነው። እኔነት ለራስ ብቻ በማግበስበስ ሌላውን መርሳት፣ ሲብስም መጨፍለቅ ነው።
እኔነት ዘማሪዋ "ዛሬም እኔ ነገም እኔ ወሬዬ እኔ፣ ልመናዬ እኔ... አወይ አልጠግብ ባይነቴ፤" እንዳለችው እኔ እኔ እያለ የሚያስለፈልፍ ዛር ነው።
እኔነት ለጌታ ያልተሰጠ ሕይወት ንጽብርቆሽ ነው። የቤተ ክርስቲያን ዝብርቅርቆሽ ሁሉ ከእኔነታችን የተወለደ ነው። እኔነት ራስን አሞግሶ ሌላውን የማንኳሰስ እብደት ነው። ተከባብሮ እና ተቻችሎ መኖር ያቃተን እኔነታችን ማሸነፍ ስላቃተን ነው። ከወንድም ጋር ከመክበር ብቻ መድመቅ ውዴታችን ስለሆነ ነው። በማይለያይ እንደውም በአንድ አይነት ነገር ሁሉ ሳይቀር እየተለያየን እዚህም እዛም ያስደኮነን ሌላ ሳይሆን የእኔነት እርሾ ነው።
በክርስትና ጉዟችን ውስጥ እርግጠኛ መሆን ያለብን አንድ ነገር ባልተካደ ሕይወት ጌታን እንዳንከተል ነው። ይህ ትግል ተወጣሁት የምንለው ሳይሆን፣ የዝንትዓለም ትግላችን ነው። እያደባ የሚከተለንን እኔነት እየተዋጋን ወደ ፊት እንቀጥል።
#መጋቢ_ስንታየሁ_በቀለ
/channel/tttgraceversion
❤️#መዳን_ለምናደርገው_መልካም_ተግባር #የሚሰጥ_ዋጋ_አይደለም።
====================
ኤፌሶን 2:4-9 (ሕያው ቃል)
------------------
4 ነገር ግን እግዚአብሔር ለምህረቱ እና ለፍቅሩ ወሰን የሌለው አምላክ በመሆኑ
5 ምንም እንኳን በሀጥያታችን ምክንያት የሞትን ብንሆንም በጸጋው ብቻ አድኖ ከሙታን ባስነሳው በክርስቶስ ሕያዋን አድርጎናል።
6 እግዚአብሔር ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር አስነስቶ በሰማያዊው ስፍራ አብሮ አስቀምጦናል።
7 እግዚአብሔር ይህን ያደረገልን በክርስቶስ አማካኝነት ለሰዎች ሁሉ የሰጠው እጅግ ታላቅ የሆነው ጸጋው በሚመጡት ዘመናት በእኛ እንዲገለጥ ፈቃዱ ስለሆነ ነው።
8 ኢየሱስ ክርስቶስን በማመናችሁ በጸጋው ድናችኋልና ይህም እናንተ በራሳችሁ ያገኛችሁት ሳይሆን የእግዚአብሔር ስጦታ ነው።
9 መዳን ለምናደርገው መልካም ተግባር የሚሰጥ ዋጋ አይደለም። "ማንም ሰው ደህንነትን ያገኘሁት በበጎ ስራዬ ነው ሊል አይገባም"።
Efe. 2
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁴ Araarri Waaqayyoo garuu baay'ee waan ta'eef, jaalala isaa isa guddaa sanaan nu jaallate.
⁵ Nuyi irra-daddarbaa keenyaan karaa hafuuraa du'oo taanee utuma jirruu, inni warra Kristosii wajjin jiraatan nu godhate; isin ayyaana Waaqayyootiin fayyifamtan.
⁶ Karaa Kristos Yesus isumaa wajjin du'aa nu kaase, isumaa wajjin bantii waaqaa keessaa iddoo nuuf kenne, nu teessises.
⁷ Inni arjummaa karaa Kristos Yesus nuuf godhe sanaan, baraa dhufu humdumaattuu baay'ina ayyaana isaatii isa hammas hin jedhamne argisiisuudhaaf kana godhe.
⁸ Isin ayyaana Waaqayyootiin karaa amantii fayyifamtan; inni immoo kennaa Waaqayyoo ti malee, gochaa ofii keessanii miti;
⁹ hojiidhaanis miti, namni tokko illee akka ittiin of hin janyetti.
Eph 2 (NLT)
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁴ But God is so rich in mercy, and he loved us so very much,
⁵ that even while we were dead because of our sins, he gave us life when he raised Christ from the dead. (It is only by God's special favor that you have been saved!)
⁶ For he raised us from the dead along with Christ, and we are seated with him in the heavenly realms—all because we are one with Christ Jesus.
⁷ And so God can always point to us as examples of the incredible wealth of his favor and kindness toward us, as shown in all he has done for us through Christ Jesus.
⁸ God saved you by his special favor when you believed. And you can't take credit for this; it is a gift from God.
⁹ Salvation is not a reward for the good things we have done, so none of us can boast about it.
✍️ 2ቆሮንቶስ 13 (2 Corinthians)
14፤ የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ የእግዚአብሔርም ፍቅር የመንፈስ ቅዱስም ኅብረት ከሁላችሁ ጋር ይሁን። አሜን።
@tttgraceversion
@tttgraceversion
@tttgraceversion
የዓለም ጋጋታ 👣👣👣
================
👉ሰዎች ለምንድነው የሚተቹህ ❓
✔ አንተ የደረስክበትን መድረስ ሳይችሉ ሲቀሩ
✔ አንተ ያለህ ነገር እነርሱ ከሌላቸው
✔ የአንተን ነገር ሊኮርጁ ሞክረው ሳይሳካላቸው ሲቀር ... ይላሉ እንግዲህ ||
በክርስቶስ የሆነ ከዚህ ዓለም ጋጋታ ነጻ መሆን አለበት ምክንያቱም ያለን ጊዜ ጥቂት ነው ሙሽራው ልመጣ በደጅ ነው ።
✔መወራት ያለበት ክርስቶስ ነው
✔መሰበክ ያለበት ክርስቶስ ነው
✔መዘመር ያለበት ክርስቶስ ነው
✔መታየት ያለበት ክርስቶስ ነው
በክርስቶስ የሆነ ምንም አያስፈልገውም ፣ #በክርስቶስ_ተሞልቷልና ። የሚያወራው ክርስቶስን ብቻ ነው ፣ እንደ ነብሴ ጡር ሴት ሁሌ የሚያምረው #ስም ክርስቶስ ኢየሱስ ፦
✔ጠዋት ክርስቶስ
✔ቀትር ላይ ክርስቶስ
✔ማታም ክርስቶስ
በክርስቶስ ተሞልተናል ከውስጣችን የሚወጣው ክርስቶስ ብቻ ነው ።
(ወደ ቆላስይስ ሰዎች 2: 9-11 )
፤ በእርሱ የመለኮት ሙላት ሁሉ በሰውነት ተገልጦ ይኖራልና። #ለአለቅነትና_ለሥልጣንም_ሁሉ_ራስ_በሆነ በእርሱ ሆናችሁ #ተሞልታችኋል። የሥጋንም ሰውነት በመገፈፍ፥ በክርስቶስ መገረዝ፥ በእጅ ባልተደረገ መገረዝ በእርሱ ሆናችሁ ደግሞ ተገረዛችሁ።
@tttgraceversion @tttgraceversion
👆👆👆👆👆👆👆👆
======================
መዝሙር 121 (Psalms)
1፤ ዓይኖቼ ወደ ተራሮች አነሣሁ፤ ረዳቴ ከወዴት ይምጣ?
2፤ ረዳቴ ሰማይና ምድርን ከሠራ ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው።
3፤ እግርህን ለመናወጥ አይሰጠውም፤ የሚጠብቅህም አይተኛም።
4፤ እነሆ፥ እስራኤልን የሚጠብቅ አይተኛም አያንቀላፋምም።
5፤ እግዚአብሔር ይጠብቅሃል፥ እግዚአብሔርም በቀኝ እጅህ በኩል ይጋርድሃል።
6፤ ፀሐይ በቀን አያቃጥልህም ጨረቃም በሌሊት።
7፤ እግዚአብሔር ከክፉ ሁሉ ይጠብቅሃል፥ ነፍስህንም ይጠብቃታል።
8፤ ከዛሬ ጀምሮ እስከ ዘላለም እግዚአብሔር መውጣትህና መግባትህን ይጠብቃል።
Far. 121
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ Iji koo gara gaarotaatti ol in ilaala, gargaarsi koo eessaa dhufa?
² Gargaarsi koo Waaqayyo biraa in dhufa; inni immoo isa bantiiwwan waaqaa, lafas uumee dha.
³ Inni miilli kee akka sigigaatu hin godhu, inni si eegus hin mugu.
⁴ Kunoo, inni Israa'elin eegu, matumaa hin mugu, hin rafus.
⁵ Waaqayyo si eega, Waaqayyo gaaddisa kee ti, inni gara mirga kee jira.
⁶ Guyyaa aduun si hin rukutu, halkanis ji'i si hin miidhu.
⁷ Waaqayyo hamaa hundumaattii si eega, inni jireenya kee in eega.
⁸ Waaqayyo gad ba'uu kee, ol galuu kees ammaa jalqabee hamma bara baraatti in eega.
የጌታ ጸጋ ከመንፈሳችን ጋር ይሁን። አሜን።
@tttgraceversion
@tttgraceversion
@tttgraceversion
@tttgraceversion
❤️ #ሜምፊቦስቴ❤️
==================
✍️ ክርስቶስ በብሉይ ኪዳን (Christ in Old Testament )
♥️የእግዚአብሔር በክርስቶስ የሆነውን የማዳን ስራ እንመለከታለን
✍️ንጉስ ዳዊት እና ሜምፊቦስቴ ፦
2ሳሙ 4፡4, 9፡4-13
✍️ሜምፊቦስቴ የሳኦል የልጅ ልጅ የዮናታን ልጅ ነው፡፡
ሽባ የሆነበትም ምክንያት የአያቱን እና የአባቱን ሞት የሰማች ሞግዚት ይዛው ለመሸሽ ስትሞክር ከእጇ በመውደቁ ነው፡፡
2ሳሙ 4፡4
✍️የሜምፊቦስቴ አያት የሆነው ሳኦል የንጉስ ዳዊት ቀንደኛ ጠላት እንደነበር ይታወቃል፡፡
✔️እንዲሁ የሰው ልጆች ምንጭ የሆነው አዳም በሀጥያት ምክንያት የእግዚአብሔር ጠላት ሆነ፡፡ ሮሜ 5፡9
✍️የሜምፊቦስቴ ሞግዚት ይዛው ልትሸሽ ስትሞክር ነው በ 5 አመቱ ወድቆ ሽባ የሆነው፡፡
✔️እንዲሁ የሰው ልጅ በክርስቶስ በማመን በፀጋ ብቻ እንጂ ሞግዚት በሆነው በሙሴ ህግ ህይወት ሊያገኝ እና ሊፀድቅ አይችልም፡፡
ገላ 2፡16, 3፡17-21,ሉቃ 14፡15
✍️የሜምፊቦስቴ አባት ዮናታን የንጉስ ዳዊት የልብ ጓደኛ ከመሆኑ የተነሳ ንጉሱ ስለ ዮናታን ቸርነት እና ምህረት ማድረግ ፈለገ፡፡ 2ሳሙ 9፡7
✔️እግዚአብሔር ለሀጢያተኛው ሰው በክርስቶስ በኩል ምህረት ማድረግ እና ከቁጣው ሊያድነው ፈለገ።
ዮሐ 3፡14-18,ሮሜ 3፡21,ሮሜ 4፡22- ,5:1, ኤፌ 2፡4-6
✍️ሜምፊቦስቴ ይኖር የነበረው ሎዶባር (ምድረበዳ) በሚባል ቦታ ነበር፡፡ 2ሳሙ 9፡4
✔️የሰው ልጅም በሀጥያቱ ምክንያት ከእግዚአብሔር መገኝት እና መግቦት ርቆ ይኖር ነበር፡፡ ኤፌ 2፡11, 1ጴጥ 2፡25
✍️ሜምፊቦስቴ ካለበት ቦታ ወደ ንጉስ ዳዊት እንዳይሄድ እግሩ ሽባ ነው ንጉስ ዳዊት ግን መልዕክተኛ በመላክ ወደ እርሱ እንዲመጣ አደረገው፡፡ 2ሳሙ 9፡1-2
✔️ሀጥያተኛ የሆነውም የሰው ልጅ በራሱ መልካም ስራ በአምላክ ፊት ተቀባይነት ማግኘት ስለማይችል እግዚአብሔር ግን በክርስቶስ ወደ ራሱ ማቅረብ ፈለገ፡፡ ኤፌ2፡8, ሮሜ 3፡21-24,ሮሜ 5፡6-10,
✍️ንጉስ ዳዊት ስለ ዮናታን ሲል ለሜምፊቦስቴ ቸርነትን በማድረግ
2ሳሙ 9፡7
1) እንደ ንጉስ ልጅ ሆነ
2) ከንጉሱ ጋ በማእድ ተቀምጦ ንጉሱ የሚበላውን በላ
3) በኢየሩሳሌም ከንጉሱ ጋር መኖር ጀመረ
4) የአያቱን ምድራዊ ርስት መለሰለት
✔️እንዲሁ እግዚአብሔር ለሀጥያተኛው በክርስቶስ ምክንያት
1) ልጅ አደረገው
2) በክብር በክርስቶስ በቀኙ አስቀመጠን
3) የሕይወት እንጀራ የሆነው ክርስቶስ ምግቡ ሆነለት
4) በአዲሲቱ ኢየሩሳሌም በክርስቶስ መኖር ጀመረ
5) በአዳም ምክንያት ያጣነውን ከዚያም በላይ በክርስቶስ ባረከን ፡፡ ኤፌ 1፡3, ዮሐ 1፡12,1ዮሐ 3፡1-,ዮሐ 6
ኤፌ 2:6-7,ዕብ12:22-24
🤔🤔ቅዱሳን ልብ ሊሉት የሚገባ ፦
✍️ሜምፊቦስቴ በንጉስ ዳዊት ቸርነት እንዲህ ቢሆንም አሁንም ግን #እግሩ #ሽባ #ነው፡፡
✔️ሰው በክርስቶስ አምኖ ከዳነ በኃላ ለመኖር መፍጨርጨር የለበትም ይልቅስ ጻዲቅ በእምነት በሕይወት ይኖራል፡፡
@tttgraceversion
@tttgraceversion
👆👆👆👆👆👆👆👆
በትክክል ለማመን አስተሳሰብህን ቀይር
✍️ ንስሐ ፡- ቃሉ ሜታኖያ የሚል ሲሆን፣ ሜታ ማለት ለውጥ ኖያ ማለት ደግሞ ኖውስ ከሚለው ቃል የመጣ አስተሳሰብ የሚል ትርጉም የያዘ ነው። ስለዚህ ሜታኖያ ማለት የአስተሳሰብ ለውጥ ማለት ነው።
✍️ አስተሳሰብን መቀየር አስፈላጊ የሆነው ለምንድነው? ምክንያቱም ትክክለኛ እምነት ወደ ትክክለኛ አኗኗር የሚመራ በመሆኑ ነው።
✍️ ስለ እግዚአብሔር ጸጋ፣ በክርስቶስ ስላለህ ጽድቅና ለጽድቅ ተለይተህ መጠራትህን በትክክለኛ መንገድ ስታምን ሁሉም ነገር ይለወጣል!
✍️ ይህ ለውጥ የተመሠረተውም ባንተ የፈቃድ ኃይል ላይ ሳይሆን ለምታምነው የወንጌል እውነታ ምስክር ሆኖ በሚቆመው፣ በኃያልነትና በንቃት በውስጥህ በሚኖረው ቅዱስ መንፈስ ኃይል ላይ ነው።
✍️ በትክክለኛ መንገድ ስታምን የጌታ ፍቅር ልብህን በጥልቅ ስለሚነካው ከሽንፈት በላይ መኖር ትጀምራለህ።
✍️ የትኛውንም ፈተና የምትፋለምበት ኃይል የሚገኘው ከውጭ ሳይሆን ከውስጥ በመሆኑ ከውስጥ ወደ ውጭ ትለወጣለህ።
@tttgraceversion
@tttgraceversion
@tttgraceversion
@tttgraceversion
👆👆👆👆👆👆
መንፈስ ቅዱስ
😇ክርስትና ማለት መንፈስ ቅዱስ በሰው ልጆች ህይወት ራሱን የሚገለጥበት ህይወት ማለት ነው።
😒አንድ ሰው በህይወቱ ስኬታማ አይደለም ማለት ያለ መንፈስ ቅዱስ ህይወቱን እየመራ ማለት ነው።
💭መንፈስ ቅዱስ ህይወታችሁ ላይ ሲገለጥ፣
➡️ወደ እውነት ይመራቹኋል
➡️ያስተምራቹኋል፣
➡️እየሱስ ያለውንም ሁሉ ያስታዉሳቹኋል።
➡️መሪያችሁ ይሆናል
➡️ያጽናናቹኋል፣
➡️በራሳችሁ መስራት ማትችሉትን ነገሮች መስራት እንድትችሉ ሃይል ይሆናቹኋል።
➡️ወዳጃችሁ ይሆናል፣
ከእግዚአብሄር የራቃችሁ ያህል ሲሰማችሁ ወደ እርሱ ይመልሳቹኋል፣
➡️ወደ ሃጥያት እንዳትገቡ በልባችሁ የንሰሃ መንፈስ ይከታል።
🎁የሚያስፈልጋችሁ ሁሉ በመንፈስ ቅዱስ ውስጥ ተጠቃሎ አለ:: ደስታ ቢሆን, ሰላም ቢሆን, ቅባት ቢሆን...
@tttgraceversion @tttgraceversion
@tttgraceversion @tttgraceversion
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆
👉 ነገር ግን #ኢየሱስን #ከሙታን #ያስነሣው የእርሱ መንፈስ በእናንተ #ዘንድ #ቢኖር፥ ክርስቶስ ኢየሱስን #ከሙታን #ያስነሣው እርሱ በእናንተ በሚኖረው #በመንፈሱ፥ #ለሚሞተው ሰውነታችሁ ደግሞ #ሕይወትን #ይሰጠዋል።"
(ወደ ሮሜ ሰዎች 8:11)
👉 #እግዚአብሔር አብ #የመጨረሻ #ኃይሉ #የገለጠው ልጁን ኢየሱስ ክርስቶስን #ከሙታን መካከል በመንፈስ ቅዱስ #ኃይል #ሲያስነሳው ነው።
👉 #ኢየሱስ #ክርስቶስ ከሙታን ከመነሳቱ #በፊት እና ከሙታን ከተነሳ #ቡኃላ ብዙ የሞቱ ሰዎች ከሙታን #ተነስተዋል ግን እግዚአብሔር #የመጨረሻ #ኃይሉን የተጠቀመው #ኢየሱስ ክርስቶስን ከሙታን #ለማስነሳት #ብቻ ነው። ምክኒያቱም👇👇
👉 #ኢየሱስ በመስቀል ላይ ተሰቅሎ ሲሞትና ሲቀበር #ብቻውን አልሞተም #ብቻውን አልተቀበረም።
👉 #የዓለምን ህዝብ #ሁሉ ኃጢያትና መርገም #ተሸክሞ ነው #የሞተው፤ ከሙታንም መካከል #በኩር ሆኖ በመንፈስ ቅዱስ #ኃይል #ሲነሳ በኃጢአታቸው ምክኒያት የሞቱትን #ሰዎች #ሁሉ ይዞ ነው #ከሙታን የተነሳው።
👉 አየህ #እግዚአብሔር በመንፈስ ቅዱስ በኩል #maximum #ኃይሉን #የገለጠው ኢየሱስን ከሙታን #ለማስነሳት ነው #ምክኒያቱ ኢየሱስ #ከሙታን መካከል በኩር ሆኖ #ሲነሳ #ብቻውን አልተነሳም በጣም #ብዙዎችን ነው ከሙታን #ይዞ #የተነሳው።
👉 ይሔ #መንፈስ #ቅዱስ ደግሞ በአንተና በአንቺ #ውስጥ #አለ ወዳጄ ይሔ #ቃል #ከገባህ አንተ የምር #ክብር #ገላጭ ነህ።
🎤 ይቅርታ 🎤
፨ ይቅርታ :- ልንሞት ስንል ወይም አቅም ስናጣ ወይም ምርጫ ሳይኖረን ወይም አለቃችንና የበላይ ስለሆነ .... የምንሰጠው ቃላችን ሳይሆን ..... በምንቀጥለው ሕይወት ውስጥ ከኛ ለሚያንሱም ለሚበልጡንም የምንሰጠው ከክርስቶስ የተማርነው የቅድስና ባህርይ ነው ።
፨ ይቅርታ ስሜት አይደለም ... ባህርይ ነው
፨ ይቅርታ ቀን እስኪያልፍ ነው ... አንድ ቀን እበቀላለው ዝቅ ያልኩ አስመስላለው የምንለው ዕድሜ ማራዘሚያ አይደለም ።
፨ ይቅርታ :- የሰውን መለወጥ ሳላረጋግጥ አልሰጥም አላደርግም የምንለው አይደለም ... ተለወጠም አልተለወጠም የቅድስና ባህርይ ስለሆነ ብቻ ከኛ ወደ ሰው ዘር ሁሉ የምናንፀባርቀው ባህርይ ነው ።
፨ በፍጹም ልብ ይቅር የማለት እውነተኛ ባህርይ ይኑረን ።
(1ኛ የዮሐንስ መልእክት ምዕራፍ 4)
----------
18፤ ፍጹም ፍቅር ፍርሃትን አውጥቶ ይጥላል እንጂ በፍቅር ፍርሃት የለም፥ ፍርሃት ቅጣት አለውና፤ የሚፈራም ሰው ፍቅሩ ፍጹም አይደለም።
19፤ እርሱ አስቀድሞ ወዶናልና እኛ እንወደዋለን።
20፤ ማንም። እግዚአብሔርን እወዳለሁ እያለ ወንድሙን ቢጠላ ሐሰተኛ ነው፤ ያየውን ወንድሙን የማይወድ ያላየውን እግዚአብሔርን ሊወደው እንዴት ይችላል?
21፤ እግዚአብሔርንም የሚወድ ወንድሙን ደግሞ እንዲወድ ይህች ትእዛዝ ከእርሱ አለችን።
የአብ ፍቅር
የወልድ ጸጋ
የመንፈስ ቅዱስ ሕብረት ከእናንተ ጋር ይሁን።
ሀሳቡን ከወደዱት ሼር ያርጉት
@tttgraceversion
@tttgraceversion
🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
#የሚያስጨንቃቹን_በእርሱ_ላይ_ጣሉት።
- ምንድነው የሚያስጨንቅሽ? ምንድነው የሚያስጨንቅህ? የሚያሳስባቹስ ነገር ምንድነው?
የትኛውም የግልህ ጉዳይ ሊሆን ይችላል ፣ "#ማንም_አይረዳኝም" ልትዪ ትችያለሽ። ነገር ግን አንድ እውነት አውቃለሁ ፣ #ላንቺ_ካንቺ_በላይ_የሚያስብ_እግዚአብሔር_አባት_አለሽ ፤ #ላንተ_ካንተ_በላይ_የሚያስብ_እግዚአብሔር_አባት_አለህ። አባት ለልጁ እንደሚንሰፈሰፍ እና የሚያስፈልገውን ነገር እንደሚያደርግለት ፣ እንደሚጠብቀው ፣ ላንተም ከምድራዊ አባት ይልቅ የሚያስብ የሰማዩ አባት አለህ።
✅ እስቲ ካጣኸው ነገር ፣ ከሚያሳስብህ እና ከሚያስጨንቅህ ነገር ጋር ትግል #አትታገል! ፤ #ለሰማዩ_አባትህ_እድሉን_ስጠው! #ለራስህ_የምትታገል_ከሆነ_እርሱ_ለመስራት_ይቸገራል ፣ ቀለል አድርገው! ፣ ጭንቀትህን ልቀቀው! አባትህ ላይ ጣለው! ያኔ እርሱ ስለአንተ ይሰራል በሚያስፈልግህ ነገር ይሞላሃል።
— 1ኛ ጴጥሮስ 5፥7 “እርሱ ስለ እናንተ ያስባልና የሚያስጨንቃችሁን ሁሉ በእርሱ ላይ ጣሉት።”
🧐 እስቲ የሰማይ ወፎችን ተመልከት!....... #አይዘሩም! #አያጭዱም!...... "ነገ ምን እንበላለን?" ብለው #በጎተራም_አይከቱም!። ልብስ ለብሰው መኪና ኑሮዋቸው ለቅንጦት ኑሮ አይደለም ፣ #ለዋነኛው_ለምግባቸው እንኳ ፈጽሞ አይጨነቁም! እስቲ አስተውል!....... አንዳንዴ "እንዴት ያስቀናሉ!" እስከምትል ድረስ ትገረምባቸዋለህ። አንድ ነገር ልንገርህ ፣ እንዲህ ጭንቀት የሌለበት ኑሮ የሚያኖራቸው #ያንተው_አባት እኮ ነው።
— ማቴዎስ 6፥26
“ወደ ሰማይ ወፎች ተመልከቱ፤ አይዘሩም አያጭዱምም በጎተራም አይከቱም፥ #የሰማዩ_አባታችሁም_ይመግባቸዋል፤ እናንተ ከእነርሱ እጅግ አትበልጡምን?”
ጥቅሱን በደንብ ተመልከት! <<".....#የሰማዩ_አባታችሁም ይመግባቸዋል...." ነው የሚለው እንጂ #አባታቸው አይልም። እስቲ አስበው.... አባትህ ልጆቹ ላልሆኑት ያውም እዚሁ ምድር ላይ ከዓለም ጋር ለሚጠፉ ፣ ሳይጨነቁ እንዲኖሩ ካደረገ...... ላንተ ደሞ ምን ያህል እንደሚጨነቅልህ Imagine! የሚገርመው እኮ ፣ አባትህ የሚመግባቸው እዚሁ ምድር ላይ ለሚጠፉ ፍጡራን ነው። አንተኮ ዘላለማዊ ነህ! ፈጽሞ ከእነርሱ ትበልጣለህ።
⏩ተጨንቀህ ያስጨነቀህን ነገር አታስተካክለውም! “ከእናንተ ተጨንቆ በቁመቱ ላይ አንድ ክንድ መጨመር የሚችል ማን ነው?” (ማቴ 6 ፣ 27)
ነገር ግን አንተ ከሁሉ አስቀድመህ #እግዚአብሔርን_ብቻ_ፈልግ! #እርሱን_ብቻ_አስቀድም! ሌላው ነገር በሙሉ እግዚአብሔር ያስተካክለዋል። የሚያስፈልግህን የሚያውቀው የሰራህ አካል እንጂ አንተ አይደለህም። እርሱን ደግሞ አባትህ ይሰጥሃል።
ማቴዎስ 6
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
³²..... ይህ ሁሉ እንዲያስፈልጋችሁ የሰማዩ አባታችሁ ያውቃልና።
³³ ነገር ግን አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ፥ ይህም ሁሉ ይጨመርላችኋል።
³⁴ ነገ ለራሱ ይጨነቃልና ለነገ አትጨነቁ፤ ለቀኑ ክፋቱ ይበቃዋል
የአብ ፍቅር
የወልድ ጸጋ
የመንፈስ ቅዱስ ሕብረት ከእናንተ ጋር ይሁን።
ሀሳቡን ከወደዱት ሼር ያርጉት
@tttgraceversion
@tttgraceversion
🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
አብርሐምና ሳራ እጅግ ባረጁ ጊዜ ልጅ የሚወልዱ አይመስሉም ነበር።ዮሴፍ በወንድሞቹ በተሸጠና ወደ ወህኒም በወረደ ጊዜ ያየው ህልም ከህልም የዘለለ ነገር አለው ብሎ ማስብ ዳገት ነበር።ሙሴ ከቤተ መንግስት ወጥቶ ተራ እረኛ ሲሆን ህዝብን ያሻግራል ብሎ ማመን ከባድ ነበር።ዳዊት ለንግስና ከተቀባ በኋላ ሳኦል ሲያሳደው በበረሀም ሲሸሸግ ተመልሶ ወደ ንግስና ይመጣል ብሎ ማሰብ አስቸጋሪ ነበር።ከተቀበረ አራት ቀን የሆነው አላዛር ነፍስ ዘርቶ ሰው ይሆናል ብሎ ማሰብ ሞኝነት ይመስል ነበር።
ሰው ለማሰብ የሚከብደውን ነገር እግዚአብሔር ግን በቀላሉ ያደርገዋል።ወዳጆቼ እግዚአብሔር የተናገራችሁን ቃልም የገባላችሁን ነገር እናንተ ባሰባችሁት መንገድ ላይሆን ይችላል እንጂ ሳያደርገው አይቀርም።እንዲህ ይላቹሀል
"ለእናንተ የማስባትን አሳብ እኔ አውቃለሁ፤ ፍጻሜና ተስፋ እሰጣችሁ ዘንድ የሰላም አሳብ ነው እንጂ የክፉ ነገር አይደለም"።ኤር 29፡11
የአብ ፍቅር
የወልድ ጸጋ
የመንፈስ ቅዱስ ሕብረት ከእናንተ ጋር ይሁን።
ሀሳቡን ከወደዱት ሼር ያርጉት
@tttgraceversion
@tttgraceversion
🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
እግዚአብሔር ለአንተ ያለው ፍቅር
✍️ እግዚአብሔር ለአንተ ያለው ፍቅር በሁኔታዎች የማይለዋወጥ ነው። ኢየሱስ ይወደኛል! የማውቀው ይህንን ነው! ዛሬም እግዚአብሔር እንደሚወድህ ታምናለህ? ዘላለማዊ በሆነ ፍቅር ይወድሃል!
✍️ አሁን እያለፍክበት ያለው ችግር ሳይዝህ ራስህን በተከፈተ ሰማይ ሥር፣ ከሁኔታዎች ጋር ባልተገናኘ በእርሱ ሞገስ ተከበህ ስትራመድ እንድትመለከት አበረታታለሁ።ነለወደፊትህ መልካም ነገሮች ጠብቅ።
✍️ እርሱ ለአንተ ባለው ፍቅር እመን፤ የአይኑ ብሌንና የልቡ ሀሴት እንደሆንክ በሙሉ ልብህ እመን። ከፍተኛ ሞገስ ያለህ እጅግ የተባረክና በጥልቅ የተወደድክ እንደሆንክ አስብ።
✍️ እግዚአብሔር ለአንተ ያለው ፍቅር በሁኔታዎች የማይለዋወጥ፣ እጅግ ንፁህና አስደናቂ ነው። ሁሉም ነገር ከአንተ ብቃት ጋር የተገናኘ ሳይሆን አንተ በእግዚአብሔር ዓይኖች ማን ከመሆንህ ጋር የተገናኘ ነው።
✍️ አሮጌው የሕግ ኪዳን አፅንኦት የሚሰጠው አንተ ለእግዚአብሔር ስላለህ ፍቅር ነው። አዲሱ የጸጋ ኪዳን አፅንኦት የሚሰጠው ግን እግዚአብሔር ለአንተ ስላለው ፍቅር ነው።
የአብ ፍቅር
የወልድ ጸጋ
የመንፈስ ቅዱስ ሕብረት ከእናንተ ጋር ይሁን።
ሀሳቡን ከወደዱት ሼር ያርጉት
@tttgraceversion
@tttgraceversion
🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
ሰላም
✍️ ሰላም ማለት በሕይወትህ ውስጥ ችግር አለመኖር አይደለም። በሕይወትህ ውስጥ ትልቅ ውድቀት ውስጥ ሆነህም ሰላምን መለማመድ ይቻላል።
✍️ ከኢየሱስ ጋር የምትለማመደው እውነተኛ ሰላምም ያ መረዳትህን የሚያልፈው ሰላም ነው።
✍️ በተፈጥሯዊው መንገድ ስናየው፣ መጥፎ ነገሮች ውስጥ ሆነህ ሰላምና እረፍት ይሰማሃል ማለት ትርጉም የሚሰጥ ነገር አይደለም፣ በመለኮታዊ መንገድ ግን በተመሰቃቀሉ ነገሮች መሃል ሆነህም በሰላም መሞላት ትችላለህ።
✍️ ዓለም ሰላም፣ ህብርና ጸጥታን የሚተረጉመው በሚሰማን ስሜት ላይ በመመሥረት ነው። ወዳጄ፣ በውስጥህ የሚሰማህን ግራ መጋባት በቋሚነት ለማረጋጋት ውጫዊ አካባቢዎችን መጠቀም አትችልም።
✍️ በውስጥህ የሚሰማህን የሚነካና ግራ መጋባትህን ወደ ሰላም የሚመልሰው ኢየሱስ ብቻ ነው። ጌታ ከአጠገብህ በመሆኑና በውስጥህ ባለው ዘላቂ ሰላም ውጫዊ አካባቢህን ማረጋጋት ትችላለህ።
✍️ ምክንያቱም በኢየሱስ ለውጥ ሁልጊዜም ከውስጥ ወደ ውጪ ነው።
✍ክርስቶስ ♥ የእግዚአብሔር ሁሉ ነገር!!
*****************
✍ክርስቶስ እኛን ልጆች ያደረገ የእግዚአብሔር ልጅ ነው!! ዮሐ 20፡31
✍ክርስቶስ እኛን ከሞት ያዳነ የእግዚአብሔር ኃይል ነው!! 1ቆሮ 1፡24
✍ክርስቶስ እኛን ከሞት ያስመለጠ የእግዚአብሔር ጥበብ ነው!! 1ቆሮ 1፡24
✍ክርስቶስ እኛን በክብሩ ልክ ያከበረ የእግዚአብሔር ክብር ነው!! ሐዋ 7፡55
✍ክርስቶስ እኛን ያጸደቀ የእግዚአብሔር ጽድቅ ነው!! ሮሜ 3፡21
✍ክርስቶስ እኛን ከማይጠፋ ዘር ዳግመኛ የወለደ የእግዚአብሔር ቃል ነው!! 1ኛ ጴጥ 1፡23
✍ክርስቶስ እኛን ለማዳን የተገለጠ የእግዚአብሔር ጸጋ ነው!! ቲቶ 2፡11
✍ክርስቶስ እኛ በሕይወት እንኖር ዘንድ የተገለጠ የእግዚአብሔር ፍቅር ነው!! 1ዮሐ 4፡9
✍ክርስቶስ እኛ እንድናውቀው የተሰጠ የተሰወረ የጥበብና የእውቀት መዝገብ ያለበት የእግዚአብሔር ሚስጥር ነው!! ቆላ 2፡2
✍ክርስቶስ እኛን እንዲሁ መውደዱን የገለጠበት የእግዚአብሔር ስጦታ ነው!! ዮሐ 3፡16
✍ክርስቶስ እኛን የእግዚአብሔር ወራሾች ያደረገ የእግዚአብሔር ሁሉን ወራሽ ነው!! ዕብ 1፡2
✍ክርስቶስ የእግዚአብሔር ነው!! 1ኛ ቆሮ 3፡23
ወዳጄ፦
✍እግዚአብሔር በክርስቶስ በኩል ያልሆነ አንዳች ነገር የለውም!!
✍እግዚአብሔር አለምን የፈጠረውም በልጁ ነው!!........አለምን ከራሱ ጋር ያስታረቀውም በልጁ ነው!!.......አለምን የሚጠቀልለውም በልጁ ነው!!
👉ክርስቶስ የእግዚአብሔር ነው እኛ ደግሞ የክርስቶስ ነን!!
★መጽሐፍ እንደሚል........
❝ሁሉ የእናንተ ነው፥ #እናንተም_የክርስቶስ_ናችሁ #ክርስቶስም_የእግዚአብሔር_ነው።❞
—1ኛ ቆሮንቶስ 3: 23
♥ክርስቶስ የእኛና የእግዚአብሔር ሁሉ ነገር ነው!!
የአብ ፍቅር
የወልድ ጸጋ
የመንፈስ ቅዱስ ሕብረት ከእናንተ ጋር ይሁን።
ሀሳቡን ከወደዱት ሼር ያርጉት
@tttgraceversion
@tttgraceversion
🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
ደሙ ከኩነኔ ይጠብቅሃል
✍️ ኢየሱስ ተላልፎ በተሰጠበት ምሽት ስለ ደሙ ምን እንዳለ ታውቃለህ? በመጨረሻው ራት ወቅት ኢየሱስ ፅዋውን አንስቶ “ይህ ለእናንተ ጥበቃ የፈሰሰው የአዲስ ኪዳን ደሜ ነው" ብሏል? በጭራሽ!
✍️ እርሱ ያለው “ስለ ብዙዎች ለኃጢአት ይቅርታ የሚፈስ የአዲስ ኪዳን ደሜ ይህ ነው” (ማቴዎስ 26÷28) ነው። ደሙ የፈሰሰው ለኃጢአትህ ይቅርታ ነው። የኢየሱስ ደም ይጠብቀናል?
✍️ አዎን፣ በእርግጥ ይጠብቀናል! ደሙ ከዲያብሎስ ጥቃቶች ቢጠብቀንም የኢየሱስ ደም የፈሰሰበት ዋነኛ ምክንያት ግን ይህ አይደለም።
✍️ ወዳጄ የአዳኛችን ደም የፈሰሰበት ዋናው ምክንያት ስለ ኃጢአታችን ይቅርታ ነው። ይህ ማለት የኢየሱስ ደም በተጨማሪም ከየትኛውም አይነት ኩነኔ ጥበቃ ያደርግልናል።
✍️ የኢየሱስ ደም ጻድቅ እንዳደረገህና ኃጢአትህ ሁሉ ይቅር እንደተባለ መገለጥ ካለህ፣ ከከሳሹ ከሚመጣብህ ኩነኔ ሁሉ ተጠብቀሃል ማለት ነው። ይህንን መረዳት ይገባሃል።
✍️ ምክንያቱም ወደ እግዚአብሔር ዙፋን በድፍረት ለመቅረብና እርሱን እንደ አፍቃሪ አባት ለማየት መተማመን ይሰጥሀል።
✍️ ከኩነኔ መጠበቅህን ማወቅ በኃጢአት፣ በሱስ፣ ወይም ዛሬ በእስራት በያዘህ ነገር ላይ ሁሉ እንድትነግሥ ያደርግሃል።
የአብ ፍቅር
የወልድ ጸጋ
የመንፈስ ቅዱስ ሕብረት ከእናንተ ጋር ይሁን።
ሀሳቡን ከወደዱት ሼር ያርጉት
@tttgraceversion
@tttgraceversion
🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
ሁልጊዜ የተወደድክ ነህ
ይህ ለእኔ እንደ ኖኅ ውኃ ነው፤ የኖኅ ውኃ ደግሞ በምድር ላይ እንዳያልፍ እንደ ማልሁ፥ እንዲሁ አንቺን እንዳልቈጣ እንዳልዘልፍሽም ምያለሁ። ኢሳ 54፡9
✍️ ኢየሱስ የገለጠልን እግዚአብሔር የልጆቹን ስህተቶች በፍቅርና በጸጋ የሚመልስ መልካም አባት ነው። ኃጢአት ስትሠራ እግዚአብሔር ቡጢ አይጨብጥም፣ ከጆሮዎቹ ትኩስ እንፋሎት አይወጣም ወይም ሊገርፍህ ቀበቶውን አይፈታም። ኃጢአት ስትሠራ እግዚአብሔር የማያደርጋቸው ሌሎች ነገሮችም እነዚሁልህ።
✍️ አይፈርድብህም ወይም ኃጢአቶችህን አይቆጥርም!
✍️ የጥፋተኝነት ቅጣት ወደምታገኝበት አይልክህም!
✍️ እስክትስተካከል ብሎ ከአንተ አይርቅም!
✍️ ከቤተሰቡ አይነጥልህም! …
✍️ ግን ይቆጣል? በጭራሽ። እግዚአብሔር ኃጢአት ላይ የነበረውን ቁጣ ሁሉ መስቀል ላይ አፍስሷል። የቀረ ቁጣ የለውም። በአንተ ኃጢአት አሁንም ይቆጣል ብሎ ማሰብ፣ ኢየሱስ ጥሩ ሥራ አልሠራም ወይም እንደገና መጥቶ መሞት ያስፈልገዋል እንደማለት ነው።
✍️ ኃጢአት ስትሠራ እግዚአብሔር ግድ ይለዋል? በጣም። ኃጢአቶቻችን እኛን የሚጎዱን በመሆናቸው ያዝናል። ኃጢአት ሰውን ይጎዳል፣ ወዳጅነትን ያበላሻል፣ ቤተሰብን ያጠፋል።
✍️ እግዚአብሔር ለባህርያቶችህ ግድ ያለው ለአንተ ግድ ስላለው ነው።
✍️ እግዚአብሔር ልክ እንደ መልካም አባት በሕይወትህ እንድትበለጽግ ይፈልጋል። ለችግሮች በር እንድትከፍት አይፈልግም። ብትከፍትም ግን አባትህ መሆኑ ይቀጥላል፣ አንተም ሁልጊዜ ተወዳጅ ልጁ ነህ።
@tttgraceversion @tttgraceversion
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆
የቅዱሳት መጽሐፍ የተመሰሉባቸው ተምሳሌቶች
እነዚህም፥
የእግዚአብሔር ቃል ምግብ ነው ያበረታል፡ 1ቆሮ 3፥2 ፣ ዕብ 5፥13-14
የእግዚአብሔር ቃል ውሃ ነው ያረካል ያጥባልም። ኤፌ 5፥25-26
የእግዚአብሔር ቃል ማር ነው ይጣፍጣል። መዝ 19፥10፣ መዝ 119፥103
የእግዚአብሔር ቃል ወተት ነው ያሳድጋል። 1ጴጥ 2፥1-3
የእግዚአብሔር ቃል ሰይፍ ነው ጠላትን ይወጋል የልብ ሸለፈትን ይገርዛል። ኤፌ 6፡17፣ ዕብ 4፡12
የእግዚአብሔር ቃል እሳት ነው ገለባውን ያቃጥላል ።ኤር 23፥29
የእግዚአብሔር ቃል መዶሻ ነው ድንጋዩን ልብ ያደቅቃል። ኤር 23፥29
የእግዚአብሔር ቃል መብራት ነው ጨለማን ይገፈፋል። መዝ 119፥105
የእግዚአብሔር ቃል መስተዋት ነው ገድለትን ያሳያል።
የእግዚአብሔር ቃል መልሕቅ ነው ያድናል /ይተክላል/ ዕብ 6፥18-19
የእግዚአብሔር ቃል ዘር ነው ይበዛል / ያድጋል/ ማር 4፥20፣ 1ጴጥ 1፥23
የእግዚአብሔር ቃል መንፈስ ነው በመንፈስ ይስተዋላል
የእግዚአብሔር ቃል ዝናብ ነው ያረሰርሳል። ኢሳ 55፥11-12
@tttgraceversion
@tttgraceversion
👆👆👆👆👆👆
መከራ
🏆ክርስትና በክርስቶስ ድል የማድረግ ህይወት ነው::
ነገር ግን በዚህ አለም እስካለን ድረስ ከጨለማ ጋር ውጊያ🤺 አለብን::
1ጴጥ 1:6-9
🔥እሳት🔥 እና ግፊት የወርቅን🌟✨ ጥራት ይመዝናሉ::
💫ቅባትን የመቀበያ ቁልፍ ሚስጢር በመከራ እና በስደት ማለፍ ነው:: ይህም የእግዝአብሔርን ባህሪ እንዲኖረን ያደርጋል::
💫ለክርስቲያን መሰደድ የተለመደ ነው:: ኢየሱስን እንኳ "ሰይጣን" ብለውታል::😈😈
💫ስለ ኢየሱስ ስም ብለን የምናልፍበት መከራ ሁሉ በኀላ በሰምያዊው ዙፉን ፊት ያሸልመናል::
ይህ ግን በስንፍና, በኅጢኅት ወይም መንፈሳዊ ደንብን በመጣስ ያመጣነውን መከራ አይጨምርም::
💫ስደትን በዚህ አውድ ስንመለከተው, ክርስቶስ የኖረውን አኗኗር መኖር ነው::
💫እግዚአብሔር ከአቅማችን በላይ እንድንፈተን አሳልፎ አይሰጠንም::
ያዕ 1:2-4
መዝ 23:4 "በሞት ጥላ መካከል እንኳ ብሄድ አንተ ከእኔ ጋር ነህና ክፉን አልፈራም፤ በትርህና ምርኵዝህ እነርሱ ያጸናኑኛል።"
@tttgraceversion @tttgraceversion @tttgraceversion @tttgraceversion
👆👆👆👆👆👆👆👆
❤#የሕይወት_እንጀራ❤
#ክፍል_ሃያ_አራት (24)
❤#የጥበብ_መጀመሪያ
#እግዚአብሔርን_መፍራት_ነው❤
=====================
መዝሙር 111
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
² የእግዚአብሔር ሥራ ታላቅ ናት፥ ደስ በሚሰኙባት ሁሉ ዘንድ የተፈለገች ናት።
³ ሥራው ምስጋናና ግርማ ነው፤ ጽድቁም ለዘላለም ይኖራል።
⁴ ለተአምራቱ መታሰቢያን አደረገ፤ እግዚአብሔር መሓሪና ይቅር ባይ ነው።
⁵ ለሚፈሩት ምግብን ሰጣቸው፤ ኪዳኑንም ለዘላለም ያስባል።
⁶ የአሕዛብን ርስት ይሰጣቸው ዘንድ ለሕዝቡ የሥራውን ብርታት አሳየ።
⁷ የእጆቹ ሥራ እውነትና ፍርድ ነው፤ ትእዛዙም ሁሉ የታመነ ነው፥
⁸ ለዘላለምም የጸና ነው፥ በእውነትና በቅንም የተሠራ ነው።
⁹ መድኃኒትንም ለሕዝቡ ሰደደ፥ ኪዳኑንም ለዘላለም አዘዘ፤ ስሙ የተቀደሰና የተፈራ ነው።
¹⁰ የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው፥ ለሚያደርጓትም ሁሉ ደኅና ማስተዋል አላቸው፤ ምስጋናውም ለዘላለም ይኖራል።
Ps 111 (AMP)
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
² The works of the Lord are great, sought out by all those who have delight in them.
³ His work is honorable and glorious, and His righteousness endures forever.
⁴ He has made His wonderful works to be remembered; the Lord is gracious, merciful, and full of loving compassion.
⁵ He has given food and provision to those who reverently and worshipfully fear Him; He will remember His covenant forever and imprint it .
⁶ He has declared and shown to His people the power of His works in giving them the heritage of the nations .
⁷ The works of His hands are truth and justice ; and all His decrees and precepts are sure (fixed, established, and trustworthy).
⁸ They stand fast and are established forever and ever and are done in truth and uprightness.
⁹ He has sent redemption to His people; He has commanded His covenant to be forever; holy is His name, inspiring awe, reverence, and godly fear.
¹⁰ The reverent fear and worship of the Lord is the beginning of Wisdom and skill ; a good understanding, wisdom, and meaning have all those who do . Their praise of Him endures forever.
✍️ 2ቆሮንቶስ 13 (2 Corinthians)
14፤ የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ የእግዚአብሔርም ፍቅር የመንፈስ ቅዱስም ኅብረት ከሁላችሁ ጋር ይሁን። አሜን።
@tttgraceversion
@tttgraceversion
@tttgraceversion
👆👆👆👆👆👆👆👆
❤️በኖህ መርከባችን ኢየሱስ❤️
1) መርከቡ የሚሰራው ከማይሰጥም ከጎፈር እንጨት =የጌታ ኢየሱስ ከሀጥያት ውጭ የሆነ ሰውነት(ስጋ)
2) ሕይወት የሚታደግ = አዳኝነቱ
3) ባለ አንድ በር = በሩ እኔ ነኝ ያለ ዮሐ 10
4) እጠፋለሁ እንዳንል በሩን ከኃላ የዘጋው እግዚአብሔር ነው = የዘላለም ሕይወት ዋስትና ዮሐ 6:37-40, 10:27
5) ውስጡ ባለ 3 ደርብ = በሥላሴ ምክር የተዘጋጀ የሰው ልጆች መድሃኒት
6) የጥፋት ውሃ ከታችም ከላይም ከጎንም ሲመታው ወደ ታች በመስጠም ፋንታ በውስጡ ያሉትን በሙሉ ተሸክሞ ወደላይ የተንሳፈፈ = የፍርድ ውሃ ይዞ ያላስቀረው ቅጣታችንን ሁሉ ተቀብሎ ሀጥያተኞችን በመታደግ በውስጡ ሰውሮ በትንሳኤ ከሙታን ተለይቶ የተነሳ ወደላይ ከፍ ከፍ በማለት በአባቱ ቀኝ በክብር ቅዱሳንን በውስጡ ይዞ የተቀመጠ ከቅዱሳን ጋር ሊነግስ በክብር የሚመጣው
የናዝሬቱ ኢየሱስ
👌 የአምላክ ጥበብ
👌የሰማይ ድምቀት
👌የመላእክት ምግብ
👌የነብያት ናፍቆት
👌የሀጥያተኞች ተስፍ
👌የቅዱሳን ርስት
👌የመዳን ቀንዳችን
✍️ ከፍርድ ያመለጥንብህ የኖህ መርከባችን የናዝሬቱ ኢየሱስ ነው፡፡ ስምህ ይባረክ እንገዛልሃለን እናመልክሀለን።
@tttgraceversion
@tttgraceversion
@tttgraceversion
@tttgraceversion
👆👆👆👆👆👆
❤#ዘመንን_መዋጀት❤
===============
✍️ጌታ ኢየሱስ በሐዋርያው ጳውሎስ በኩል ቀኖችን እና ዘመኑን እንድንዋጅ ያሳስበናል፦
‹‹ቀኖቹ ክፉዎች ናቸውና ዘመኑን ዋጁ››
ይለናል፡፡ ኤፌ 5:16-17
✍️ጊዜን ለመግለፅ የተጠቀመበት የግሪክ ቃል ‹‹ #ካይሮስ ›› የሚል ሲሆን ትርጓሜውም በጊዜ ውስጥ ከታወቀና በአግባቡ ጥቅም ላይ ሊውል ከሚገባው መልካም ዕድል ጋር የተቆራኘ ነው፡፡ ይህንኑ ቃል በገላትያ መልዕክቱ ላይ ሲጠቀምበት ‹‹እንግዲያስ ጊዜ ካገኘን ዘንድ ለሰው ሁሉ ይልቁንም ለኃይማኖት
ቤተሰቦች መልካም እናድርግ›› (ገላ 6፡10) በማለት በሚያልፍ ጊዜ የማያልፍ ሥራ ሊሰራ እንደሚቻል ይናገራል።
✍️ለምሳሌ ጊዜን እና ዘመንን በመዋጀት የተጠቀሙ የብሉይ ኪዳን የእምነት አባቶችን እንመልከት፦
📌የጥበብ መንፈስ ያደረባቸው ዳንኤልና ጓደኞቹ ናቡከደነፆር ጠቢባንን ለመግደል ትእዛዝ ባወጣ ጊዜ ያደረጉት ነገር ቢኖር ጊዜን በመግዛት የጌታን ፈቃድ መለመን ነበር፡፡ ዳን 2:14-23
📌በዳዊት ሠራዊት ውስጥ የነበሩት እስራኤላውያን የሚገባውን ያደርግ ዘንድ ዘመኑን የሚያውቁ ጥበበኞቹ የይሳኮር ልጆች እንደ ነበሩ መጽሐፍ ይነግረናል፡፡ 1ዜና 12:32
✍️በኤፌሶን መጽሐፍ እግዚአብሔር እንዴት እንወጀን በመስረዳት እኛ ደግሞ ዘመኑን (ጊዜ) እንዴት እንደምንዋጅ ይነግረናል። እግዚአብሔር ሰውን ይዋጅና የዋጀው ሰው ጊዜን እንዲዋጅ ትዕዛዝ ይሰጣል፡፡ በእርግጥም የተዋጀ ይዋጃል፡፡
✍️ሐዋርያው በመቀጠል ‹‹ዘመኑን ዋጁ›› ይለናል፡፡ መዋጀት መቤዠት ከሚለው ቃል ጋር አንድ ዓይነት ሲሆን ሁለቱም አስቀድሞም የራስ የነበረን ንብረት ዋጋ ከፍሎ በመግዛት መልሶ የራስ ማድረግን የሚያሳዩ ቃላት ናቸው፡፡
እንግዲህ ጊዜን እንድንገዛ፣ እንድንዋጅ ወይም እንድንቤዥ ታዘናል ፡፡
✍️ጊዜ ለምን መዋጀት አስፈለገው? ጊዜ መዋጀት ያስፈለገው ቀኖቹ ክፉዎች ስለሆኑ ነው፡፡ ቀኖች በራሳቸው ክፋትም ሆነ መልካምነት የላቸውም፡፡ ነገር ግን
በመንፈሳዊ ዓለም ክፋትን
የሚያውጠነጥኑ የክፋት መንፈሳውያን ሠራዊት አሉ፡፡
እነዚህም አካል አልባ መናፍስት ያቀነቀኑትን ክፋት የሚገልጡባቸው የአመፅ ልጆች በየስፍራው ሞልተዋል፡፡ የሁለቱ ድምር ቀኑን ክፉ ያደርገዋል፡፡
ክፉው ክፉ ሰዎችን ተጠቅሞ ቀኑን ክፉ ማድረግ የቻለው የሚጠቀምባቸው ሰዎች በጊዜ ውስጥ ስለሚኖሩና ጊዜው በእጃቸው ስላለ ነው፡፡
ታዲያ ለክፉ ሰዎች መጠቀሚያ የሆነው ጊዜ ለአማኞችም ተሰጥቷል፡፡ ነገር
ግን በጥበብ በመመላለስ፣ ጊዜውን መግዛትና መልካም ማድረግ የእኛ የአማኞች ሃላፊነት ነው። ክፋት በሞላበት ዓለም ውስጥ መልካም በማድረግ ዘመኑን ልንዋጅ እንችላለን፡፡
✍️ጳውሎስ ‹‹ስለዚህ የጌታ ፈቃድ ምን እንደሆነ አስተውሉ
እንጂ ሞኞች አትሁኑ፡፡›› (ቁ፡17)
በራሳችን ማስተዋል ተደግፈን፤ በዐይናችን ፊት መልካም መስሎ የታየንን ልናደርግ አይገባም፡፡ ነገር ግን ለዘመኑና ለጊዜው የሚሆነውን የጌታን ፈቃድ ለማወቅ ልንተጋ፣ በተገለጠልንም ጊዜ ያለማመንታት ልናደርገው ይገባናል፡፡
ለዚህም አውነተኛ አብነታችን ጌታ ኢየሱስ ራሱ ነው፡፡ በሕዝብ መካከል ባገለገለበት ሶስት ዓመት ተኩል ውስጥ ‹‹ቀን ሳለ የላከኝን ፈቃድ ላደርግ ሥራውንም ልፈፅም ይገባኛል፡፡›› በማለት ሥራውን አከናወነ፡፡ በመጨረሻም በመስቀል ላይ
የሚሰዋበት ጊዜ ሲደርስ በአባቱ ፊት ተደፍቶ ‹‹ አባት ሆይ የአንተ ፈቃድ እንጂ
የእኔ ፈቃድ አይሁን›› (ዮሐ 9፡) አለ፡፡ የአባቱንም ፈቃድ ለማወቅ በብርቱ ጩኸት ከእንባ ጋር ፀሎትንና ምልጃን አቀረበ፡፡ በመታዘዙም ሁላችንን አተረፈ፡፡
እኛም የታዘዝነው ይህንን ፈለግ እንድንከተል ነው፡፡ ታዲያ ‹‹የጌታን ፈቃድ እንዴት አውቃለሁ?›› ብለን ልንጠይቅ እንችል ይሆናል፡፡
ፈቃዱን ለማወቅ የግድ ነቢይ ፍለጋ መሄድ ወይም ሕልምና ራዕይ ልናይ
አያስፈልገንም፡፡ በእግዚአብሔር መንፈስና በእግዘአብሔር ቃል የታደሰ አዕምሮ ካለን፣ በጎውን፣ ፍፁሙንና ደስ የሚያሰኘውን የጌታ ፈቃድ ለይተን ማወቅ እንችላለን፡፡ (ሮሜ 12፡2)
ጳውሎስ ለቆላስያስ ቅዱሳን ‹‹የፈቃዱ እውቀት መንፈሳዊ ጥበብና አዕምሮን ሁሉ እንዲሞላባችሁ እየለመንን ስለ እናንተ ፀሎትን አልተውንም . . . (ቆላ፡- 1፡9) እንደሚል፣ የፈቃዱ እውቀት መንፈሳዊ ጥበብንና ማስተዋልን ሁሉ እንዲሞላብን ጌታን ልንጠይቅ ይገባል፡፡
ለአዲሱ ፍጥረት የሆነው መንፈሳዊ ጥበብ ይህ ነው፡፡ የጌታን ፈቃድ ማስተዋልና በማስተዋል የተረዳነውንም፣ ሁኔታው የሚጠይቀውን ዋጋ በመክፈል፣ ከክፉው ተናጥቀን በገዛነው ጊዜ ውስጥ የተካፈልነውን የሰማይ ሕይወት ምድር ላይ በመግለጥ የምስራቹን ቃል እያወጁ ሰዎችን ወደ ክርስቶስ እንዲመጡ በማድረግ ጌታ በቀኑ እና በዘመኑ ወደ ሕይወታችን ያመጣውን መልካም አጋጣሚ ለጌታ ክብር አየተጠቀምን በዘመናችን ጌታችንን ልናከብር ይገባናል።
2 ቆሮንቶስ 13፡14
የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ የእግዚአብሔርም ፍቅር የመንፈስ ቅዱስም ኅብረት ከሁላችሁ ጋር ይሁን። አሜን።
@tttgraceversion
@tttgraceversion
@tttgraceversion
@tttgraceversion
👆👆👆👆👆👆
💁♂የትዳር ጓደኛ እንዴት እንምረጥ?💁
የሕይወት ጓደኛ ምርጫ መስፈርቶች
ትዳር ምስረታ ማሰብ ሲጀመር፣ ትዳር እንዲጸና ማድረግ የሚያስችሉ መጽሐፍ ቅዱሳዊና ሰብዓዊ መስፈርቶች መኖራቸው ቸል ሊባል የሚገባው ነጥብ አይደለም፡፡ ጋብቻ መለኮታዊም ሰብዓዊም ተቋም እንደ መሆኑ መጠን፣ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መርኆዎችና፣ ሰብዓዊ ተሞክሮዎች፣ ቋሚና ዘላቂ መመሪያዎች እንዲሁም አላፊና ተለዋዋጭ ሁኔታዎች ተገናዝበው የሚተገበሩበት ሲሆን፣ ምንጊዜም ቢሆን ለመለኮታዊው፣ ዘላቂና ቋሚ ለሆነው መስፈርት ቅድሚያ ሊሰጥ ይገባል፡፡
👉1. ምርጫው በውስጣዊ ማንነት እንጂ ውጫዊ በሆኑ ነገሮች ላይ ብቻ እንዳይመሰረት መጠንቀቅ፣
ምንም እንኳ ውጫዊ ውበት ወይም ነገሮች በጋብቻ ግንኙነት ውስጥ የራሳቸው ድርሻ ያላቸው መሆኑ ባይካድም፣ ውስጣዊ ውበት፣ የአስተሳሰብ ቁንጅና፣ በእምነት የተሞላ ቅንና ሩህሩህ ልብ፣ እንዲሁም ሙያ የላቀ ትኩረት ሊሰጣቸው ወይም ተመዛዝነው ሊታዩ ይገባል፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ ውጫዊ ውበታቸውን መንከባከብ ላይ ብቻ ለሚያተኩሩ አማኝ እህቶች ሲመክር “…ለእናንተም ጠጕርን በመሸረብና ወርቅን በማንጠልጠል ወይም ልብስን በመጎናጸፍ በውጭ የሆነ ሽልማት አይሁንላችሁ፣…” ካላቸው በኋላ የላቀውን ነገር ሲያመለክታቸው “…ነገር ግን በእግዚአብሔር ፊት ዋጋው እጅግ የከበረ የዋህና ዝግተኛ መንፈስ ያለውን የማይጠፋውን ልብስ ለብሶ የተሰወረ የልብ ሰው ይሁንላችሁ …” በማለት የትኩረት አቅጣጫቸውን እንዲቀይሩ ያሳባቸዋል (1ጴጥ.3፡3-4፤ )። ይህ ምክር ለወንዶችም ጠቃሚ ነው፡፡
👉2. ለጋብቻ የታሰበው ወንድ ወይም የተመረጠችው ሴት አማኝ መሆኑን/ኗን ማረጋገጥ
ክርስቲያናዊ ጋብቻ ቃል ኪዳናዊ ግንኙነት እንደ መሆኑ መጠን መከናወን ያለበት አማኝ በሆኑ ተቃራኒ ጾታ ባላቸው ሁለት ግለሰቦች መካከል ነው፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ ለዚህ ጉዳይ ትኩረት የሰጠ ሲሆን፣ “… ከማያምኑ ጋር በማይመች አካሄድ አትጠመዱ፤ ጽድቅ ከዓመፅ ጋር ምን ተካፋይነት አለውና? ብርሃንም ከጨለማ ጋር ምን ኅብረት አለው? ክርስቶስስ ከቤልሆር ጋር ምን መስማማት አለው? ወይስ የሚያምን ከማያምን ጋር ምን ክፍል አለው? ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስም ከጣዖት ጋር ምን መጋጠም አለው? …” በማለት የሚያቀርበው ሙግት በተለይ ከጋብቻ አንጻር በጥልቀትና በጥሞና ሊታይ የሚገባው እውነታ ነው (2ቆሮ.6፡14-16) ፡፡
👉3. የወደፊት ተጣማጆች ልብ ዝንባሌ መሰረቱ እውነተኛ ፍቅር እንጂ የሌሎች ነገሮች ግፊት እንዳይሆን መጠንቀቅ፣
በተቃራኒ ጾታዎች መካከል መሳሳብ፣ መፈላለግ መኖሩ ተፈጥሯዊ ጉዳይ በመሆኑ አንዱ ሰው ሌላውን ማፍቀር ኃጢአት አይደለም፡፡ ስለዚህ ከሁሉ አስቀድሞ አንድ ወንድ ወይም አንዲት ሴት ለጋብቻ ሲታሰብ መነሳት ያለበት ጥያቄ፣ በእርግጥ ይህን/ይህቺን ሰው እወደዋሁ/እወዳታለሁ? የሚለው እንጂ፣ ምን አለው? ከማን ወገን ነው? …ወዘተ ሊሆን አይገባም፡፡
ይህን ጉዳይ አውጥቶ አውርዶ የመወሰን ግላዊ ነጻነትን የሚጋፉ አያሌ ልምዶች ቤተ ክርስቲያን አካባቢ መኖራቸው እሙን ሲሆን፣ ውጤታቸውም አስከፊ ነው፡፡ ከነዚህም ምክንያቶች መካከል የፍቅር ግንኙነቱን ከሚፈልጉት አንዱ “እግዚአብሔር አንቺን/አንተን ሰጥቶኛል” ብሎ ጥያቄ ማቅረብ፣ አንዳንድ ነቢያት ነን ባዮች “አከሌን/እከሊትን እንድታገቢ/እንድታገባ እግዚአብሔር ተናግሮኛል” ሲሉ የሚያመጡት አሳሪ መልዕክት፣ እንዲሁም
ማንም ሰው የፍቅር ስሜት የሌለውን ሌላ ሰው አግብቶ ሰላም ያለበት፣ የተረጋጋና የእግዚአብሔር በረከቶች የሚከተሉት ኑሮ መሥርቶ መኖር ስለሚቸገር ራስን እጅግ አስቸጋሪ በሆነ ሥራ መጥመድ ይሆናል፡፡ እንዲህ ዓይነት ግንኙነት ውስጥ ዘሎ ከተገባ በኋላ ችግሮች ውሎ አድሮ መከሰት ሲጀምሩ “እግዚአብሔር እንዲህ ያለ ሁኔታ ውስጥ ስገባ ለምን ዝም አለኝ?” ብሎ ለማማረር መሞከር ስሜት ሊሰጥ የማይችል ቂልነት መሆኑን መገንዘብና ኃላፊነቱን መውሰድ ግድ ይላል፡፡
👉4. ብስለትና ዝግጁነትን መመዘን
ጋብቻ ቤተሰባዊ ኑሮን ለመመሥረት ሕጋዊ የመግቢያ በር ስለሆነ ቀጣዩን ኃላፊነት ወስዶ ለመኖር ከሚያስችለን ሁለንተናዊ ብስለት ደረጃ ላይ እንገኛለን? ብሎ ራስን መጠየቅና ሁኔታዎችን መመዘን ብልህነት ነው፡፡ ብስለት አካላዊ፣ አእምሮአዊ፣ ማኅበራዊና መንፈሳዊ ገጽታዎችን ሊያጠቃልል የሚችል ሲሆን፣ ሁለት ከተለያዩ ጾታዎች፣ ጀርባ ታሪኮች፣ አመለካከቶች፣ እውቀት ደረጃ፣ የአስተዳደግ ባሕል የመጡ ሰዎች የጋራ ጎጆ ቀልሰው አንድ ሥጋ ሆነው አብረው ለመኖር ሲጣመሩ ያስተሳሰራቸውን ጽኑ ፍቅርና እነዚህን ልዩነቶች አጣጥመው ወደፊት ለመራመድ ብስለት ያስፈልጋቸዋል፡፡ እርስ በእርስ እየተናበቡ ፍቅርን ለመለዋወጥ፣ የአንዱ ብርታት የሌላውን ድካም እየሸፈነ የሚመች ረዳት የመሆን ሚናውን ለመወጣት ዝግጁ መሆን ከእያንዳንዱ የትዳር አጋር ይጠበቃል፡፡ እንዲህ ሲባል ግን ፍጹምነትን መጠበቅ ይኖርብናል ማለት አይደለም፡፡
ይቀጥላል ......
✍ ፓ/ር ሙሴ በላይነህ
@tttgraceversion
/channel/tttgraceversion