👉የትንቢት አዝመራ ድንግል ሆይየቤተክርስቲያን ለውዝ ገውዝ በጨረቃ ጊዜየምታፈራ የወይን ፍሬ አበባ የሚሻተትብሽፍሬውም የሚከማችብሽ ጽድቅ ፍሬን እንዳፈራየወንጌል ቡቃያ አድርጊኝ፡፡
👉 መስገጃ መማለጃ የኃጢአት ማስተስረያየምትሆኝ የምሥጢር ታቦት ድንግል ሆይ ወደልጅሽ ወደ ወዳጅሽ ኢየሱስ ክርስቶስ ኃጢአቴነአስተስርይልኝ፡፡
👉ድንግል ሆይ የተገፉት መሸሻየሚያጥሩት አጥር ቅጽር የመዋዕያን ሰማዕታትአክሊል፡፡
👉 ገድላቸውንም ለፈጸሙት ብፁዓን የጻድቃንዋጋቸው የኃጥአዘን ዕረፍታቸው የከሙት ጉልበትየነዳያን ሀብት የንጹሓን መመኪያ ያደፉትምከርኩሰታቸው የሚነጹብኝ ያዘኑትም የሚጽናኑብሽደስ ያላቸው የተድላ ደስታቸው ፍጻሜ፡፡
👉 የመዓስባን ረዳት የደናግል ትዕግሥትበፍጹማን መነኮሳት በሰውነታቸው ውስጥየምታበሪ ዕንቁ በየተራራው በየዋሻውበየጎደጎደው ምድር በሚኖሩ ቅዱሳን ዋጋባሕታውያንን የምትጎበኝ ርግብ ከገዳማውያን ጋራየምትኖር መንፈሳዊት ዖፍ፡፡
👉 በሃይማኖት የሚጋደሉት ጋሻ ጦር የሚዘፍኑትመሰንቆ የዘፈን ዕቃ የልዑል እግዚአብሔርየምስጋና ኃይል የአየራት ምጥቀታቸው የሰማያትልዕልናቸው፡፡
👉 የምድር መሠረት የቀለያት ጥልቀትየሚያዝያ ፀሐይ ብርሃን፡፡
👉የጨረቃና የከዋክብት የነ አርዮብ ብርሃንፀዳላቸው መልካቸው የምድረ በዳም አበቦችፀዳል የገነት አበባ መልክ በውስጣቸውምየተዋሀድሽ መዓዛ ድንግል ሆይ ላፍንጫየሚከረፋው የኃጢአት ክፉ ሽታ ወደ ሰማይእነዳይወጣ በሃይማኖት ሽቱ አጣፍጭኝ፡፡
👉ሰማያዊት ርግብ መንፈሳዊት ንሥርም💚 እመቤታችን💚 ሆይ ሰላምታ ይገባሻል።
👉የአሸናፊ የአብ የወልድ የመንፈስ ቅዱስ ፈቃድ ከቀድሞ የመረጠሽ 💚እመቤታችን 💚ሆይ ሰላምታ ይገባሻል።
👉የዋሂት ርግብ 💚እመቤቴ💚 ሆይ እኔ አገልጋይሽእንዳልሞትየምትጸልዪበት ሰዓት በደረሰ ጊዜ
👉 የስደትሽን ድካም ለደጉ ልጅሽ እያሳሰብሽዉ በፊቱ ፈፅመሽ ስገጂ።
💕የእመቤታችን💕 አማላጅነት አይለየን
ሰላም የተዋህዶ ልጆች በመጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ተብሎ ተጽፋል።
" ዳሩ ግን ጌታን እርሱም ክርስቶስ በልባችሁ ቀድሱት። በእናንተ ስላለ ተስፋ ምክንያትን ለሚጠይቁዋችሁ ሁሉ መልስ ለመስጠት ዘወትር የተዘጋጃችሁ ሁኑ፥ ነገር ግን በየዋህነትና በፍርሃት ይሁን።"
(1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 3:15)
በስቡሕ ቲዩብ በየሳምንቱ የሚቀርብ ጥያቄና መልስ አዘጋጅተናል የመጀመሪያው ክፍል ተለቋል ።ከዚህም በተጨማሪ የተለያዩ የኢኦተቤክ አስተምህሮዋን የጠበቁ መዝሙራትና ስብከቶችን ለመልቀቅ ዝግጅታችን ጨርሰናል ።
https://youtu.be/PSYOezD3RVw
👍ገብታችው አዲስ የተከፈተ የዩቲዩብ ቻናል ስለሆነ ለማበረታታት ና ለመደገፍ በተጨማሪም በፍጥነት እንዲደርሳችሁ Subscribelike ሼር አድርጉን ባታደርጉንም ጥያቄውን ገብታችው ሞክሩት
ጥያቄውን ለማግኘት👇👇👇👇
https://youtu.be/PSYOezD3RVw
https://youtu.be/PSYOezD3RVw
https://youtu.be/PSYOezD3RVw
like እና ሼር ብታደርጉ ክርስትያናዊነት ነው እኛንም ሌላ እንድንሰራ እንበረታታለን።
ስለ ምትከታተሉን እግዚአብሔር ይስጥልን።
ስቡሕ ቲዩብ SIBUH TUBE SUBSCRIBE የሚለውን በመንካት ሰብስክራይብ አድርጉን
SUBSCRIBE
SUBSCRIBE
ሰላም የዚህ ቻናል አባላት ከሁላችሁም ጋር ሰላመ እግዚአብሔር ጋር ይሁንንና ዛሬ ስለ አንድ ነገር መወያየት አለብን ሁላችሁም ግሩፑ ውስጥ ግቡና እንወያይበት ምክንያቱም ክርስትና እምነታችን እየተሸረሸረ ነው።በፍጥነት @zimaredawit21 ግሩፕ join አድርጉ ።
👉የምንወያይበት ርዕስ
1) ሀሳዊ መሲህ በምድራችን በዝተዋል ሁላችንም የምናውቃቸውንና የምንጠረጥራቸውን ሰዎች እያነሳን በምናውቀው መጠን እንነጋገራለን
2) ስለ ንጉስ ቴዎድሮስ
ሁላችሁም ጓደኞቻችሁን አድ በማድረግ እንዲቀላቀሉት አድርጓቸው በማርያም ለክርስትና ህይወቱ ወይም ክርስትና የገባው ገብቶ ይወያያል ለጓደኞቹም ሼር አድ ያደርጋል
ለመወያየት👇👇👇👇
@zimaredawit21
@zimaredawit21
@zimaredawit21
#አይቴብሔራለጥበብወአይቴማኅደራ
#የጥበብሀገሯወዴትነውማደሪያዋስ?
🌿ሰበር ዜና ለጥበብ ፈላጊዎች🌿
መዝ 111-10 "የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው፥ለሚያደርጓትም ሁሉ ታላቅ ማስተዋል አላቸው ምስጋናውም ለዘላለም ይኖራል።"
ሰላም ውድ የኢትዮጵያ ልጆች ይህ ቻናላችን የኢትዮጵያ የጥንት ሊቃውንት አባቶቻችን ያቆዩልን ድንቅ #የዕፅዋት🌿🌱☘🍀🍃🌾 ጥበቦች እና #አስማታዊ ጸሎቶች✍ በኢትዮጵያዊው #መሪጌታነቢየልዑል የተከፈተ ለኢትዮጵያውያን ጥበብ ፈላጊዎች የምናስተዋውቅበት ምርጥ አዲሱ ቻናላችን ነው።ዛሬውኑ #join ብለው ከማያልቀው የጥበብ ፅዋ ተካፋይ ይሁኑ።
#ይቀላቀሉን #ይከታተሉን #እንገርምወታለን #እናስደንቅዎታለን።
ይህን ከታች ያለውን ሰማያዊውን በመጫን ይቀላቀሉ
👇👇👇👇
@orthodo221
@orthodo221
@orthodo221
ወዳጄ ሆይ!
💕የእመቤታችን 💕ክብር
👉 አባትህና እናትህን አክብር ያለን እግዚአብሔር እናቱን እንድንጠላለት የሚፈልግ
ይመስልሃልን?
👉ታዲያ በመናፍቁ ዓለም የሚታየው የክርሰቶስ እናትክብሯን አሳንሰው ልጇን እንወደዋለን የሚሉት ዕብደትስ ምን ትለዋለህ?
👉 እነርሱ “ጌታ ጌታ” እያሉ እንወደዋለን የሚሉት ጌታ ጌትነቱን አምነው የሚገባ ክብር
ሰጥተው አምላክነቱን የተቀበሉት አይደለም።
👉እስኪ እናስብ! ወላጅ እናቴን የጠላ እንዴት የእኔ ወዳጅ ሊሆን
ይታሰባል?
👉ፈጣሪዋን የወለደች ድንግል ማርያም ወድደን ክርስቶስም ከምንም በላይ ብናፈቅረው ፍቅራችን መልክ
ይኖረዋል።
👉ድንግል ማርያም ከጀርባ አድርገህ “ኢየሱስ ኢየሱስ” ማለቱ ግን የጤና አይደለም።
👉ወዳጄ ሆይ! ለመሆኑ እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም እንድንጠላ የሚያደርገን ማን ነው? የቀደመው
እባብ ሰይጣን ነው።
👉በመጽሐፍ ቅዱስ አውሬው ማደሪያውንም ሊሳደብ አፉ እንደከፈተ እናነባለን።
👉 ራእ.13፥6።
“ማደሪያው” የተባለች እግዚአብሔር የቀደሳት እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ናት።
👉 “ልዑል ማደሪያውን
ቀደሰ።” መዝ. 45/46፥4። በመሆኑም የፍቅር እናት ከልብ ስንወዳት በፍቅር እንሞላለን።
👉 ተሳዳቢው የአውሬውን
መንፈስ ከተጠጋን ግን ከፍቅሯ ተለይተን በትዕቢት መኖራችን የማይቀር ነው።
#አይቴብሔራለጥበብወአይቴማኅደራ
#የጥበብሀገሯወዴትነውማደሪያዋስ?
🌿ሰበር ዜና ለጥበብ ፈላጊዎች🌿
መዝ 111-10 "የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው፥ለሚያደርጓትም ሁሉ ታላቅ ማስተዋል አላቸው ምስጋናውም ለዘላለም ይኖራል።"
ሰላም ውድ የኢትዮጵያ ልጆች ይህ ቻናላችን የኢትዮጵያ የጥንት ሊቃውንት አባቶቻችን ያቆዩልን ድንቅ #የዕፅዋት🌿🌱☘🍀🍃🌾 ጥበቦች እና #አስማታዊ ጸሎቶች✍ በኢትዮጵያዊው #መሪጌታነቢየልዑል የተከፈተ ለኢትዮጵያውያን ጥበብ ፈላጊዎች የምናስተዋውቅበት ምርጥ አዲሱ ቻናላችን ነው።ዛሬውኑ #join ብለው ከማያልቀው የጥበብ ፅዋ ተካፋይ ይሁኑ።
#ይቀላቀሉን #ይከታተሉን #እንገርምወታለን #እናስደንቅዎታለን።
ይህን ከታች ያለውን ሰማያዊውን በመጫን ይቀላቀሉ
👇👇👇👇
@orthodo221
@orthodo221
@orthodo221
👉2ኛ) ጌታችን ድንግል ማርያምን "ሴትዮ" ብሎ የጠራበት ዋና ምክንያት ጥልቅ የሆነ ቲኦሎጂካል (Theological) ትንታኔ (ትርጒም) አለው፡፡
👉 ይህም የቤተ ክርስቲ ያናችን ሊቅ ቅዱስ ያሬድ"እንዘ ሥዉር እምኔነ ይእ ዜሰ ክሡተ ኮነ ማየ ረሰየ ወይነ ምልጣን (አንገርጋሪ) ዘቃና -- ከእኛ ተሰውሮ የነበረ፥ ማለትም በዓይነ ትንቢትና በዓይነ ሃይማኖት እንዲሁም በቃለ መጻ ሕፍት ብቻ እየተመራን እናመልከው የነበረ አምላክ አሁን ግልጽ ሆኖ ታየ፡፡
👉 ውኃውንም የወይን ጠጅ አደረገ" እንዳለው፤ አስቀድሞ "ባንተና በሴቲቱ መካከል፥ በዘርዋና በዘርህ መካከል ጠላትነትን አደርጋለሁ፡፡
👉 እርሱ ራስህን ይቀጠቅጣል፤ አንትም ተረከ ዙን ትቀጠቅጣለህ" ብሎ የተናገረው መለኮታዊ ትንቢቱ እንደተፈጸመ ለማመልከት ነው፡፡
👉ምክንያቱም አስቅደሞ በኦሪቱ በውስጥ ታዋቂነት ሴት ብሎ የጠራት ድንግል ማርያም ስትሆን፥
👉 የሴቲቱ ዘር የተባለ ደግሞ ራሱ በኅቱም ድንግልናዋ ተፀንሶ በኅቱም ድንግልና የተወለደና ሥጋችን ተዋሕዶ የተገለጠ፥
👉 ውኃውን ወደ ወይን የቀየረ፥ የዲያብሎስን ራስ በዕለተ ዐርብ የቀጠቀጠ፥ ኢየሱስ ክርስቶስ ነውና፡፡
👉 በመ ሆኑም "ሴትዮ" ያለው ከዚህ ምሥጢርም በማያያዝ ነው (ዘፍ. 3.15። ገላ. 4.4)፡፡
👉"ካንቺ ጋር ምን አለኝ?" ስላለውም፥ ሊቃውንት አባቶቻችን፦ "ከአንቺ ጋር ምን ጠብ አለ? የምትዪውን አደርገዋለሁ፡፡
👉የምትዪኝን ላለማድረግ ምን ምክንያት አለኝ? አደርገዋለሁ"የሚለውን ፍቺና ትንታኔ በመስጠት ተርጒመውታል፡፡
💕የእመቤታችን አማላጅነት💕
👉 በዶኪማስ ቤት
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ " በልዑል ዙፋን ላይ ተቀ ምጦ ያለ እርሱ በበረት ተጣለ፤
👉ሥጋ ሳይሆን የነበረ፥ የማይ ዳሰስ ወልድ ዋሕድ ዛሬ ሥጋን በመዋሐድ ተዳሰሰ፤
👉 ኃጢ አትን የሚያስተሰርይ እርሱ በጨርቅ ተጠቀለለ (ሃይ.አበ. ምዕ. 66÷19። ሉቃ. 2÷6-19) እንዳለው፤
👉 እግዚአብሔር በራሱ የተናገረው መለኮታዊ ትንቢትና በነቢያት አድሮ ያናገረው ትንቢት
👉 እውን ሆኖ የማይታይና የማይመረመር አካላዊ ቃል እግዚአብሔር ወልድ ሥጋን ተዋሕዶ በተገለጠ ጊዜ
👉 የመጀመሪያውን አምላካዊ ተአምር በቃና ዘገሊላ ሰርግ ቤት እንዳደረገ፤
👉 ቅድስት ድንግል ማርያም፥ ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስና ደቀ መዛሙርቱ በሰርጉ ቤት እንደ ነበሩ ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ ያስረዳል (ዮሐ. 2.1-11)፡፡
👉ኢትዮጵያዊው ሊቅ ቅዱስ ያሬድ "ማርያምሰ ተንከተመ እግዚአብሔር ኮነት ለነ (የጥር ፯ እስመ ለዓለም) --
👉ማርያምስ ከእግዚአብሔር ጋር የምንገናኝበት ድልድይ ሆነችልን" እንዳለው፤
👉 ለሰርግ ዕድምተኞች የተዘጋጀ የወይን ጠጅ ማለቁን የተረዳች ርኅርኅተ ልቡና ድንግል ማርያም
👉 እውነተኛውን መፍትሔ መስጠት ወደሚችለው ልጇና አምላኳ ጌታችን መድኃኒታች ኢየሱስ ክርስቶስ
👉 "የወይን ጠጅ እኮ የላቸውም" ብላ ባቀረበችው ጥያቄ
👉"አንቺ ሴት ካንቺ ጋር ምን አለኝ፤ ጊዜየ ገና አልደረሰም"፤
👉 የሚለውን ጥልቅ ምሥጢር ያዘለ ቃል ከተናገረ በኋላ በቀጥታ ጥያቄዋን ተቀብሎ ውኃውን ወደ ወይን ቀይሮአል፡፡
👉በዚህም የአስተና ጋጆቹን ድንጋጤና የሰርጉ ባለቤትን ኀፍረት አስወግዷል፡፡ የመጀመርያ ተአምርንም አድርጎአል፡፡
💕ድንግል ማርያም💕
👉በብዙ ኅብረ መልክ ተመስላለች።
👉በመንፈስ ቅዱስ መሪነት ስለ ሰው ልጅ ተስፋ ድኅነትን ለማብሠር በየጊዜው የተነሡ ነቢያትም
👉ድንግል ማርያምን በብዙ ምሳሌ እየመሰሉ ተናግረውላታል፡፡ በጥቂቱ ለማስታወስ ያህል፦
👉 የወይራ ቅጠል በመያዝ የጥፋት ውኃ መድረቊን ያበሠረች የኖኅ ርግብ (ዘፍ. 8.11)፤
👉ነበልባሉ ሐመልማሉን ሳያቃጥል፥
👉 ሐመልማልም ነበልባሉን ሳያጠፋ በተዋሕዶ ስትምቦገቦግ ሙሴ በደብረ ሲና ያያት ዕፅ (ዘጸ. 3÷1)፤
👉 ውኃ ሳያጠጧት የለመለመች፥ ያበበችና ያፈራች የአሮን በትር፤
👉የኃያላን ኃያል ሳይከፍት ግብቶ ሳይከፍት እንደተዘጋች የወጣባት የሕዝቅኤል በር (ሕዝ. 44÷2-5) ምሳሌዎችዋ ናቸው፡፡
👉ምሳሌ የሆኑበትም ምክንያት ዘመነ ፍዳና ዘመነ ኵነኔ አልፎ የሰላም፥ የፍቅር፥ የነጻነትና ድኅነትና የምሕረት ዘመን እንደደረሰ ያበሰረች ድንግል ማርያም በመሆንዋ በኖኅ ርግብ ትመሰላለች፡፡
👉 እንዲሁም ነበልባለ እሳት የተሰኘው መለኮት ሲሆን፥ ሐመልማል የተሰኘችውም ድንግል ማርያም ናት፡፡
👉ስለሆነም እሳተ መለኮትን ተሸክማለችና የሲና ዕፅ ትባላለች፡፡
👉ድንግል ማርያም ያለዘርዐ ብእሲ በኅቱም ድንግልና ፀንሳ፥
👉በኅቱም ድንግልና ፍሬ ሕይወት ጌታችንን በመውለዷም በአሮን በትር ተመሰላለች፡፡
👉 እንዲ ህም ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤልስ
💕ማርያም ሆይ💕
👉 በእግዚአብሔር ፊት ጸጋን አግኝተሻልና አትፍሪ እነሆም ትፀንሻለሽ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ ስሙም ኢየሱስ ትይዋለሽ ብሎ ያበሠራት
👉 "የእግዚአ በሔር አገልጋይ እነሆ እንደ ቃልህ ይሁንልኝ "
#ስትለው በድምፅ አካላዊ ቃል ከሥጋዋ ሥጋን ከነፍስዋ ነፍስን ነሥቶ፥ በኅቱም ድንግልና ተፀንሶ፥
👉 በኅቱም ድንግልና በመውለዱ ነቢዩ ሕዝቅኤል ባያት በር ትመሰላለች
💕 የድንግል ማርያም💕
👉 ንጽሕናና ቅድስና ከመላእክት ንጽሕናና ቅድስና በላይ ነው፡፡
👉ቅዱሳን መላእክት ደማዊና ሥጋዊ ባሕርይ የሌላቸው ረቂቃንና እሳታውያን እንደሆኑ ይታወቃል (መዝ. 103÷4 (104) ማቴ. 22÷30)፡፡
👉ይሁን እንጂ "ለመላእክትሂ ኢተክህሎሙ ድንጋሌ ኅሊና እስመ አበሱ በፍትወት ወወረዱ ምድረ በመዋዕል ዘቀዳሚ
👉-- ኃጢአትን ከማሰብ መጠበቅ ለመላእክትስ እንኳን አልተቻላቸውም፤
👉በቀደመው ዘመን ያልተሰጣቸውን ሽተው በድለው ከሰማይ ወደ ምድር ወርደዋልና" (መቅ.ተአ.ማ.)
👉ተብሎ እንደተጻፈው ከማኅበረ መላእክት መካከል ኃጢአትን ሠርተው ከማዐርጋቸው ወድቀዋል (2ጴጥ. 4÷4 ይሁዳ. 1÷6 ራእ. 12÷7-9)፡፡
👉ቅድስተ ቅዱሳን
💕ድንግል ማርያም💕
👉 ግን ምድራዊት የአዳምና የሔዋን ዘር ብትሆንም ከጥንት ጀምሮ ንጽሐ ጠባይዕ ያላደፈባት፤
👉 ከኅሊዮ፥ ከነቢ ብና ከገቢር የተለየች፤
👉ርኵሰተ ሥጋና ርኵሰተ ሕሊና የሌላት፥ አደፍ፥ ጒድፍ የማታውቅ፥ ንጽሕት ፍጥረት ናት፡፡
💕ድንግል ማርያም💕
👉 ከወደቁት መላእከት ብቻ ሳይሆን ከቅዱሳን መላእክትም በእጅጉ ትበልጣለች፡፡
👉 ምክንያቱም ኪሩቤልና ሱራፌል የማይነኩት፤ የማይቀርቡት፤ ብሎም በዓይኖቻቸው መመልከት የማይችሉትና በፊቱ የሚበረክ ኩለትን አምላክ ወልዳለችና (2ሳሙ. 22÷11 ኢሳ. 6÷ 1-3 ኢሳ. 37÷16። ራእይ 5÷8-11 7÷12)፡፡
👉ከላይ ከተጠቀሱ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች በተጨማሪ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን "የዐቢ ክብራ ለማርያም እምኵ ሉሙ ቅዱሳን እስመ ድልወ ኮነት ለተወክፎ ቃለ አብ -- ከቅዱሳን ክብር የማርያም ክብር ይበልጣል፡፡
👉የአብ ቃል ለመቀበል ተገብታ ተገኝታለችና (ውዳሴ ማር. ዘረቡዕ)፤
👉 ማርያም ሆይ! መላእክት ያገኑሻል፥ ሱራፌልም ያመስግ ኑሻል
የማንን መዝሙር ፈልገው አጥተው ያውቃሉ
የሊቀ መዘምራን ኪነጥበብ ወ/ቂርቆስ
የሊቀ መዘምራን ይልማ ሃይሉ...
የሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ....
የማንንስ ስብከት ፈልገው ሳያገኙት ቀርተው ያውቃሉ
የመጋቤ ብሉይ ወሐዲስ ቆሞስ አባ ገብረ ኪዳን....
የዲ/ን ዮርዳኖስ አሰፋን ስብከት.....
✝ ሁሉንም በዚህ ቦት በአንድ ላይ ያገኙታል
@habmisbot
@habmisbot
join my channel👇👇
@ortodoxmezmur21
@spiritualquestions
@mahiberemezemiran
start this bot 👉 @habmisbot
የማንን መዝሙር ፈልገው አጥተው ያውቃሉ
የሊቀ መዘምራን ኪነጥበብ ወ/ቂርቆስ
የሊቀ መዘምራን ይልማ ሃይሉ...
የሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ....
የማንንስ ስብከት ፈልገው ሳያገኙት ቀርተው ያውቃሉ
የመጋቤ ብሉይ ወሐዲስ ቆሞስ አባ ገብረ ኪዳን....
የዲ/ን ዮርዳኖስ አሰፋን ስብከት.....
✝ ሁሉንም በዚህ ቦት በአንድ ላይ ያገኙታል
@habmisbot
@habmisbot
join my channel👇👇
@ortodoxmezmur21
@spiritualquestions
@mahiberemezemiran
start this bot 👉 @habmisbot
💕ድንግል ሆይ 💕
👉የመዳን ምክንያት የሆነው ኪዳንሽ ባይኖር ኖሮ
👉 የእሳት ወንዝ ሁሉን ባሰጠመው ነበር፡፡
👉በቃል ኪዳንሽ ከሞት ወደ ሕይወት የምንሸጋገርብሽ
👉የሙሴ በትሩና ዘላለማዊ ምግብ
👉አማናዊ መናን ያስገኘሽልን የወርቅ መሶብ አማላጃችን💖 ድንግል ማርያም ሆይ💖
👉የሕይወት ውሃ የዐማኑኤል እናቱ የኮሬብ ቦታ ነሽ ፤
👉አማሌቃውያን ድል የተነሡባት የሙሴ ክንዱ
👉 የኃያላን ጌታ እናቱ 💖እመቤታችን 💖ሆይ
👉ልዑል እግዚአብሔር በታላቅ ክብር የተገለጸባት የሲና ተራራ ነሽ፡፡
👉የአምላክ ማደሪያው የቃል ኪዳን ታቦት በንጽሕና በቅድስና የተጌጥሽ ቅድስት
👉💖ድንግል ሆይ💖 ኅብስተ ሕይወት
ጌታን ያገኘንብሽ እውነተኛዪቱ ገበታና
👉 የብርሃን እናቱ የወርቅ መቅረዝ ነሽ ፤
👉አምላክ የመረጣቸው ንዋያተ ቅድሳት በውስጧ ያሉ
👉 ጳውሎስ ያደነቀሽ የእውነተኛዪቱ ሊቀ ካህናት ማደሪያው
👉የብርሃን ድንኳኑ አንቺ ነሽ፤ "
💕ድንግል ሆይ💕
👉ሰይጣን እንደ ስንዴ ሊያቸንፈኝ በኔ ላይ ይመኛል (ይሻል) ይቅርታ የሚያደርግልኝ ልጅሽን ለምኝው በኔ ላይ እንዳያሰለጥነው፡፡
👉ጸሎቴም በሚቃረን ፊት በአርበኛ እጅ እንደ ፍላፃ በኃይልም እንደሚወጋ ጦር የጎን አጥንትም እንደሚሰብር እንደሚያቆስልም ይሁን፡፡
👉. ደግመኛም እንደ ሰይፍ የሚቆርጥ እንደ እንደ ጠገራ የሚሰነጥቅ ይሁን ጠላቴም ይህንን አይቶ ይሽሽ ከኔ ጋራ ለመቃረን እንግዲህ አድባም ተንኮሉ ይጥፋ መንገኑም አልጫ ይሁን፡፡
👉 የኃይሉም ብርታት ልምሾ ይሁን የሚጸናናበትም ተስፋ አያግኝ፡፡
👉. መሃይምናን በጥላዋ የሚያድፉባት ታላቂቱ የዘይት ዛፍ ድንግል ሆይ የትንቢት ዝናም የምትጠጭ የሰማይ ደመና ብርሃን የሚጋርድሽ በቤተ መቅደስ ያደግሽ አስቀደሞም ልዑል እግዚአብሔር የተከለሽ ከእስራኤል ወገን የምትሆኚ ቡርክት ፍሬ ሆይ፡፡
👉. ቡሩክ ፍሬ ይኸውም ጌታቸን ኢየሱስ ክርስቶስ ካንቺ የተገኘ በላህዩም መሻከራቸውን ለማለዘብ ከርሱ የመለኮትነት ቅቤ የሚፈሰው እርሱ ካንቺ የተገኘ ድንግል ሆይ አንቺ ደግሞ የኃጢአቴን መሻከር በልጅሽ መለኮትነት ቅቤ አለዝቢልኝ በርሱ ላህይ ደም ግባቴን እንዳገኝ፡፡
💕የእመቤታችን💕 አማላጅነት
የልጇ ቸርነት አይለየን !!!!
ሰላም የተዋህዶ ልጆች በመጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ተብሎ ተጽፋል።
" ዳሩ ግን ጌታን እርሱም ክርስቶስ በልባችሁ ቀድሱት። በእናንተ ስላለ ተስፋ ምክንያትን ለሚጠይቁዋችሁ ሁሉ መልስ ለመስጠት ዘወትር የተዘጋጃችሁ ሁኑ፥ ነገር ግን በየዋህነትና በፍርሃት ይሁን።"
(1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 3:15)
በስቡሕ ቲዩብ በየሳምንቱ የሚቀርብ ጥያቄና መልስ አዘጋጅተናል የመጀመሪያው ክፍል ተለቋል ።ከዚህም በተጨማሪ የተለያዩ የኢኦተቤክ አስተምህሮዋን የጠበቁ መዝሙራትና ስብከቶችን ለመልቀቅ ዝግጅታችን ጨርሰናል ።
https://youtu.be/PSYOezD3RVw
👍ገብታችው አዲስ የተከፈተ የዩቲዩብ ቻናል ስለሆነ ለማበረታታት ና ለመደገፍ በተጨማሪም በፍጥነት እንዲደርሳችሁ Subscribelike ሼር አድርጉን ባታደርጉንም ጥያቄውን ገብታችው ሞክሩት
ጥያቄውን ለማግኘት👇👇👇👇
https://youtu.be/PSYOezD3RVw
https://youtu.be/PSYOezD3RVw
https://youtu.be/PSYOezD3RVw
like እና ሼር ብታደርጉ ክርስትያናዊነት ነው እኛንም ሌላ እንድንሰራ እንበረታታለን።
ስለ ምትከታተሉን እግዚአብሔር ይስጥልን።
ስቡሕ ቲዩብ SIBUH TUBE SUBSCRIBE የሚለውን በመንካት ሰብስክራይብ አድርጉን
SUBSCRIBE
SUBSCRIBE
ሰላም የተዋህዶ ልጆች በመጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ተብሎ ተጽፋል።
" ዳሩ ግን ጌታን እርሱም ክርስቶስ በልባችሁ ቀድሱት። በእናንተ ስላለ ተስፋ ምክንያትን ለሚጠይቁዋችሁ ሁሉ መልስ ለመስጠት ዘወትር የተዘጋጃችሁ ሁኑ፥ ነገር ግን በየዋህነትና በፍርሃት ይሁን።"
(1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 3:15)
በስቡሕ ቲዩብ በየሳምንቱ የሚቀርብ ጥያቄና መልስ አዘጋጅተናል የመጀመሪያው ክፍል ተለቋል ።ከዚህም በተጨማሪ የተለያዩ የኢኦተቤክ አስተምህሮዋን የጠበቁ መዝሙራትና ስብከቶችን ለመልቀቅ ዝግጅታችን ጨርሰናል ።
https://youtu.be/PSYOezD3RVw
👍ገብታችው አዲስ የተከፈተ የዩቲዩብ ቻናል ስለሆነ ለማበረታታት ና ለመደገፍ በተጨማሪም በፍጥነት እንዲደርሳችሁ Subscribelike ሼር አድርጉን ባታደርጉንም ጥያቄውን ገብታችው ሞክሩት
ጥያቄውን ለማግኘት👇👇👇👇
https://youtu.be/PSYOezD3RVw
https://youtu.be/PSYOezD3RVw
https://youtu.be/PSYOezD3RVw
like እና ሼር ብታደርጉ ክርስትያናዊነት ነው እኛንም ሌላ እንድንሰራ እንበረታታለን።
ስለ ምትከታተሉን እግዚአብሔር ይስጥልን።
ስቡሕ ቲዩብ SIBUH TUBE SUBSCRIBE የሚለውን በመንካት ሰብስክራይብ አድርጉን
SUBSCRIBE
SUBSCRIBE
💚ድንግል ኾይ💚
👉የውዳሴሽ ወሬ በዓለም ሁሉ ተሰምቷልና በመንፈስ ቅዱስ እንደተናገርሽ እንዲህ ስትይ እነሆ ከዛሬ ጀምሮ ትውልድ ሁሉ ያመሰግኑኛል፡፡
👉 በውነት ምስጋና ይገባሻል፡፡ የእግዚአብሔር እናቱ ሁነሻልና በውነት መደነቅ ይገባሻል፡፡
👉ዓለምን ሁሉ በመሐል እጁ የያዘ እርሱን ወልደሻልና በዕውነት ብፅዓን ይገባሻል ለዕውነተኛ ፀሐይ መውጫ ሆነሻልና፡፡
👉 በዕውነት መመስገን ይገባሻል ለማለዳው ኮከብ ምሥራቅ ሆነሻልና በውነት መደነቅ ይገባሻል፡፡
👉ለጥምቀት ልጆች መመከያ ሆነሻልና፡፡
👉በውነት ብፅዕና ይገባሻል፡፡ ለሃይማኖት መሠረት ጽናተ ሆነሻልና፡፡
👉 ከኪሩቤል ክብር ገናንነት ላንቺ ይገባል፡፡ ከሱራፌልም ውዳሴ ከመላእክትም እልልታ ከመላእክት አለቆችም ዝማሬ ላንቺ ይገባል፡፡
👉 ከነቢያት ትንቢት ከሐዋርያት ስብከት ላንቺ ይገባል፡፡ ከቅዱሳን ሰማዕታት እናታችን መባል ከመሐይምናንም እመቤታችን መባል ከክርስቲያንም ሁሉ አፍ የመድኃኒታችን ቀንድ መባል ላንቺ ይገባል፡፡
የእመቤታችን አማላጅነት ረድኤት በረከት አይለየን !!!!!
💕እመብርሃን ኾይ💕
👉ርኩሰት የሌለብሽ ሙሽራ ሆይ ዕዳ በደልም የሌለብሽ ንግሥት አንቺን እማልዳለሁ በገናንነትሽም እማፀናለሁ ያሥራ ሁለት ዓመት ታናሽ ብላቴና ስትሆኚ ሰማይና ምድር የማይወስኑትን በወሰነው ሆድሽ እማፀናለሁ፡፡
👉ዓለምን ሁሉ የመላ እርሱንም ዘጠኝ ወር ካምስት ቀን በተሸከመው ማኅፀን እማፀናለሁ፡፡
👉በመውለድም ማኅተሙ ባልተለወጠ የድንግልናሽ ኃይል ሥጋ የለበሰውን ፍጥረት ሁሉ የሚያሳድገውን እርሱን ባሳደገ ጡትሽ ወተት እማለድሻለሁ፡፡
👉ፈረሶቹዋን የሚያደላድል የሕይወት እሳት ሠረገላውንም የእሳት ነበልባል አደረገ እርሱን ባቀፉት ጉልበቶችሽ፡፡ የማይዳሰሰውን እሳት ያለ ጉጠት በዳሰሱት ቅዱሳት እጆችሽ እማልዳለሁ፡፡
👉 ከገሊላው ንጉሥ ከሄሮድስ ፊት ከልጅሽ ከወዳጅሽ ጋራ ስትሸሺ መንገድ በመሄድ በደከሙት ቡሩካት እግሮችሽ በአዳም በፊቱ የሕይወት መንፈስ ያሳደረበት እርሱን በሳሙት ከንፈሮችሽ እማልድሻለሁ፡፡ (ዘፍጥ ፪፣ ፯)
👉ልጅሽን ወስደው እንዳይገሉት ከሄሮድስ ሠራዊት ፈርተሽ ስለ ልጅሽ መራራ ልቅሶ ባለቀሱ ዓይኖችሽ እናቴ እማማ በማለት በታናሽ ብላቴና አንደበት፡፡ (በሕፃን አንደበት) ሲያጫውትሽ የሚጣፍጠውን ነገሩን በሰሙት ጆሮችሽ እማልዳለሁ፡፡
ወዳጄ ሆይ!
💕የእመቤታችን ክብር 💕
👉እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የሌለው ሕይወት ምን ዓይነት ኑሮ ነው? ከፍቅሯ
ተለይቶና ርቆ በትዕቢት መኖርስ ምን ጥቅም አለው?
👉 በትዕቢት ተሞልተው የናቋትና ያሳደዷት አላውያን ነገሥታት
ፍጻሜያቸው ምን እንደሆነ ታሪኩን አታውቀውም እንዴ? እነርሱም ጠፉ መንግሥታቸውም ደግሞ ጠፋ።
👉በመጽሐፍ ቅዱስ “ለአንቺም የማይገዛ ሕዝብና መንግሥት ይጠፋል” ተብሎ እንደተጻፈ። ኢሳ. 60፥12።
👉አዎ! የፍቅር እናት ብናከብራት ራሳችንም እንከበራለን ባናከብራት ደግሞ መዋረዳችንና መናቃችን የማይቀር ነው
👉“የናቁሽም ሁሉ ወደ እግርሽ ጫማ ይሰግዳሉ” ኢሳ. 60፥14
በመጽሐፍ ቅዱስ “እነሆም ከዛሬ ጀምሮ ትውልድ ሁሉ ብፅዕት ይሉኛል” ሉቃ. 1፥48 ብላየተናገረች
👉እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም እኛም ትውልድ ነንና “ብፅዕት” ብለን ልናከብራት ይገባናል።
👉 የእናትነት ፍቅሯና
ጸጋ በረከቷ ምስጢሩን የተረዱ ቅዱሳን
👉አባቶቻችን እንደ ቅዱስ ኤፍሬም፣ ቅዱስ ባስልዮስ፣ አባ ሕርያቆስና አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ወዘተ.
👉 የእመቤታቸን ፍቅር ከአቅማቸው በላይ ሲሆንባቸው “በማሳነስ እንጂ በማብዛት
አይደለም” በማለት ፍቅሯን ገልጸውታል።
👉ይህን ያሉበት ምክንያት ፍቅርዋ ከአጥንታቸው ውስጥዘልቆ ከደማቸው
ጋር ስለተዋሃደ መግለጹ ስለከበዳቸው ነው።
👉ስለዚህ ውድ አንባቢ! በመጨረሻ ልነግርህ የምፈልገው ነገር ቢኖር የእመቤታችን ፍቅር የሌለበት ጉዞ መልህቅ እንደ ሌለው መርከብ ነው።
👉የእመቤታቸን ፍቅር የጎደለው ሕይወት ጣዕም የለውም።
👉በኑሮአችን ሁሉ ሰላምና ፍቅር እንዲኖረን የሰላምና
👉 የፍቅር እናት ስንቃችን ትሁን። ዋሳችንና ጠበቃችንም እናድርጋት።
👉የማይበገር ወጀብም ማዕበልም ቢገጥመን እንኳ በእመቤታችን ረዳትነት ቀዝፈነው ማለፍ እንችላለን።
👉በመሆኑም የእመቤታችን ፍቅር በልቦናችን ጽላት ጽፈን እናኑረው።
#አይቴብሔራለጥበብወአይቴማኅደራ
#የጥበብሀገሯወዴትነውማደሪያዋስ?
🌿ሰበር ዜና ለጥበብ ፈላጊዎች🌿
መዝ 111-10 "የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው፥ለሚያደርጓትም ሁሉ ታላቅ ማስተዋል አላቸው ምስጋናውም ለዘላለም ይኖራል።"
ሰላም ውድ የኢትዮጵያ ልጆች ይህ ቻናላችን የኢትዮጵያ የጥንት ሊቃውንት አባቶቻችን ያቆዩልን ድንቅ #የዕፅዋት🌿🌱☘🍀🍃🌾 ጥበቦች እና #አስማታዊ ጸሎቶች✍ በኢትዮጵያዊው #መሪጌታነቢየልዑል የተከፈተ ለኢትዮጵያውያን ጥበብ ፈላጊዎች የምናስተዋውቅበት ምርጥ አዲሱ ቻናላችን ነው።ዛሬውኑ #join ብለው ከማያልቀው የጥበብ ፅዋ ተካፋይ ይሁኑ።
#ይቀላቀሉን #ይከታተሉን #እንገርምወታለን #እናስደንቅዎታለን።
ይህን ከታች ያለውን ሰማያዊውን በመጫን ይቀላቀሉ
👇👇👇👇
@orthodo221
@orthodo221
@orthodo221
የማንን መዝሙር ፈልገው አጥተው ያውቃሉ
የሊቀ መዘምራን ኪነጥበብ ወ/ቂርቆስ
የሊቀ መዘምራን ይልማ ሃይሉ...
የሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ....
የማንንስ ስብከት ፈልገው ሳያገኙት ቀርተው ያውቃሉ
የመጋቤ ብሉይ ወሐዲስ ቆሞስ አባ ገብረ ኪዳን....
የዲ/ን ዮርዳኖስ አሰፋን ስብከት.....
✝ ሁሉንም በዚህ ቦት በአንድ ላይ ያገኙታል
@habmisbot
@habmisbot
join my channel👇👇
@ortodoxmezmur21
@spiritualquestions
@mahiberemezemiran
start this bot 👉 @habmisbot
💕ድንግል ማርያምም💕
👉በልጅዋና በዶኪማስ መካከል ድልድይ ሆና በሰርጉ ቤት ላይ አንጃቦ የነበረውን ጭንቅና ኀዘን በአማላጅነቷ እንዳስወገደች እናያለን፡፡
👉በዚሁ ላይ ጌታችን "አንቺ ሴት ከአንቺ ጋር ምን አለኝ? ጊዜዬ ገና አልደረሰም" ያለው ኃይለ ቃለም ጥልቅ የሆነ ሃይማኖታዊና መጽሐፍ ቅዱሳዊ ምሥጢር ያለው ከመሆኑም በላይ አባባሉም የቊጣ ወይም የእምቢተኝነት ቃል ሳይሆን የእሺታና የአክብሮት አገላለጽ እንደሆነ በሚገባ መረዳት ተገቢ ነው፡፡
👉ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ድንግል እናቱን "ሴትዮ" ብሎ በመጥራቱ አላከበራትም የሚል የተሳሳት አስተሳሰብ ያለው ሰው ካለም ቢያንስ ቀጥለው የተጠቀሱትን በማስተዋል መገንዘብ ያስፈልጋል፡፡
እነዚህም፦
👉1ኛ) "ሴትዮ" የሚለው ቃል በእኛና አሁን ባለው መረዳት አሉታዊነት ያለው መስሎ ቢሰማንም በዕብራውያንና አዲስ ኪዳን በተተረጐመበት የግሪክ ቋንቋ ግን የአክ ብሮት መገለጫ ነው።
👉 በዚያውም ላይ "አባትህንና እናትህን አክብር" ብሎ ሕግ የደነገገ እግዚአብሔር፥ ቃል ኋላም እኔ ሕግንና ነቢያትን ለመሻር የመጣሁ አይምሰላችሁ፥ ልፈጽም እንጂ ለመሻር አልመጣሁም (ዘጸ. 20.12። ዘዳ. 5.16።
👉ማቴ. 5.17) ብሎ ያጸናው ጌታ፤ ከሁሉም በላይ አብልጦ ለእናትነት የመረጣትን እናቱን አላከበረም ብሎ ማሰብ ፍጹም ድፍረት እንደሆነ ሊረዳና ሊገነዘብ ይገባል፡፡
💕ድንግል ማርያም💕
👉ጌታን ከመውለዷ በፊት፥
👉በወለ ደች ጊዜና ከወለደች በኋላ ድንግል ናት፡፡
👉አስቀድሞ በትንቢተ ኢሳይያስ "ድንግል ትፀንሳለች ወንድልጅም ትወልዳለች ስሙንም አማኑኤል ትለዋለች" ተብሎ እንደተጻፈ፤ ድንግል ማርያም ከመውለዷም በፊት፤
👉 በወለደች ጊዜ ከወለደችም በኋላ ድንግል ናት፤ ተፈት ሖም የላትም (ኢሳ. 7.14)።
👉 ኦርቶዶክሳውያን ሊቃ ውን ትም "እናንት አላዋቂዎች የድንግል ማርያም ጌታን መፅነ ሷን መውለዷን እንደሌሎች ሴቶች አታስመስሉ፤
👉 ለእመቤታችን ለድንግል ማርያም ይህ ሊነገርባት አይገባም፤
👉የእግዚ አብሔርን ቃል ያለ ዘርዐ ብእሲ ፀንሳ ምጥ ሳይሰማት ወለደችው እንጂ (ሃይ.አበ. ጎርጎርዮስ ምዕ. 60.19-20)።
👉"ሥጋ የሌለው እርሱ ሥጋዋን ተዋሕዶ እንደ ሰው ሁሉ ዘጠኝ ወር በእናቱ በጌትነቱ ሳለ በማኅፀኗ ተፀነሰ
👉 ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀንም ከተፈጸመ በኋላ የሚወለ ድበት ቀን ሲደርስ በማይመረመር ግብር በኅቱም ድን ግልና ተወለደ ማኅተመ ድንግልናዋም አልተለወጠም፤
👉ማኅ ተመ ድንግልናዋ ሳይለወጥ ተወለደ እንጂ" (ቅ.ጎርጎርዮስ ነባቤ. ሃይ. አበ. ምዕ. 60.12። ቅ.አትናቴዎስ ሃይ.አበ. ምዕ. 27.37። ሕዝ. 44.1-3)።
💕እመቤታችን💕
👉 ከፍጥረተ አዳምም በቅድስናና በንጽሕና የሚስተካከላት የለም፡፡
👉አዳምና ሔዋን ሕገ እግዚአብሔርን ከመተላለፋቸው በፊት ንጽሐ ጠባይእ ያላደፈባቸው ንጹሐን፥
👉 ቅዱሳን እንደነበሩና ኋላ ግን በኀልዮ፥ በነቢብና በገቢር ኃጢአት ሠርተዋል፡፡
👉 ሕገ እግዚአብሔርን ከመተላለፋቸው የተነሣም ሞተ ሥጋና ሞት ነፍስ ተፈርዶባቸዋል፡፡
👉 ከእነርሱ የተገኘች ድንግል ማርያም ግን እንከን ያለተገኘባት ንጽሕትና ቅድስት ናት፡፡
👉 ከዚህም የተነሣ ኦርቶዶክሳውያን ሊቃውንት፡- "ወኢረኲሰት በምንትኒ እምዘፈጠራ --
👉 ከፈጠራት ጀምሮ በምንም በምን ከድንግልናዋ አልተለወጠችምና (ርኵሰተ ሥጋና ርኵሰተ ኅሊና አልተገኘባትም) ሃይ. አበ. ቴዎዶስዮስ ምዕ. 53÷22 ሕቅ. 44÷1-3)፡፡
👉የኪስኪስ ኤጲስ ቆጶስ ቅዱስ ኤራቅሊስ እመቤታችንን ለመጠብቅ ስለተመረጠ ቅዱስ ዮሴፍ በተናገርበት አንቀጹ
👉 "ከንጹሕ ዘር የተፈጠረች ድንግል የእግዚአብሔር ማደሪያ እንድትሆን አላወቀም፡፡
👉ዘለዓለም መለወጥ የሌለበት ዳግማይ አዳም ክርስቶስ ድንግልና ካላት ገነት እመቤታችን እንዲገኝ አላወቀም" (ሃይ.አበ. ኤራቅሊስ ምዕ. 48፥ ቁ. 31። መኃ. 4.12)፡፡
👉 "ማርያምሰ ታሐቱ እምትካት ውስተ ከርሡ ለአዳም ከመ ባሕርይ ጸዓዳ ማርያም --
👉ከጥንት ጀምሮ በአዳም ውስጥ እንደ ነጭ ዕንቊ ታበራ ነበር" (ሕዳር ጽዮን አራራይ)።
👉"ኦ ድንግል አኮ ዘተአምሪ ርስሐተ ከመ አንስት እለ እምቅድሜኪ ወእምድኅሬኪ አላ በቅድስና ወበንጽሕ ስርጉት አንቲ --
💕ድንግል ሆይ፥ 💕
👉ከአንቺ አስቀድመውና ከአንቺ በኋላ እንደ ነበሩና እንዳሉት ሴቶች እድፍ የምታውቂ አይደለሽም፤
👉በቅድስናና በንጽሕና ያጌጥሽ ነሽ እንጂ" (ቅዳ. ማር.) በማለት ይመሰክሩላታል፡፡
ድንግል ማርያም መሠረተ ድኂን ትሆን ዘንድ ከጥንት ጀምሮ በእግዚአብሔር የተመረጠች ናት፡፡
💕ድንግል ማርያም💕
👉በእግዚአብሔር ዘንድ ከጥንት ጀምሮ ለመሠረተ ድኂን የተመረጠች ናት፡፡
👉 ለዚህም አዳምና ሔዋን የአምላካቸውን ትእዛዝ አፍርሰው የተሠጣቸውን ጸጋና ግርማ አስነጥቀው ራቁታቸው በገነት ቊጥቋጦ በተደበቁበት ጊዜ "አዳም የት ነህ? ብሎ የጠራ እግዚአብሔር ቃል ከአዳም ዘር ከምትወለደው ቅድስት ዘር ተወልዶ እንደሚያድነው የተናገረው መለኮታዊ ትንቢት እንደሆነ እንረዳለን (ዘፍ. 3.9። ማቴ. 18.11-13)፡፡
👉 እንዲሁም ልዑል እግዚአብሔር እባቡንና በእባቡ ውስጥ የተሰወ ረውን ዲያብሎስ ሲረግም
👉 "ባንተና በሴቲቱ መካ ከል፥ በዘርህና በዘርዋም መካከል ጠላትነትን አደርጋለሁ፡፡ እርሱ ራስህን ይቀጠቅጣል::
👉 አንተም ሰኰናውን ትቀጠቅ ጣለህ" (ዘፍ. 3.15) ሲል ለጊዘው በሔዋንና በእባብ መካከል ያለው ጠብ የሚያመለክት ሲሆን መሠረታዊና እውነታዊ ትርጒም ግን ባንተ፥ በዲያብሎስና በድንግል ማርያም ማለት ነው፡፡
👉'ከሴቲቱ የሚወለድ ራስህን ይቀጠ ቅጣል' ያለውም ከድንግል ማርያም ስለሚወለደው የእግዚ አብሔር አብ የባሕርይ ልጅ ወልድ የተናገረው መለኮታዊ ትንቢት ነው፡፡
👉ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስም ይህን እውነት መሠረት አድርጎ
👉 "ወአመ በጽሐ ዕድሜሁ ፈነወ እግዚአ ብሔር ወልዶ ወተወልደ እምብእሲት --
👉የዘመኑ ፍጻሜ በደረሰ ጊዜ እግዚአብሔር ከሴት የተወለደውን ልጁን ላከ" (ገላ. 4.4) በማለት አረጋግጦታል፡፡
👉በተመሳሳይ መልኩ
💕 አባ ሕርያቆስም💕
👉 "አንቲ ውእቱ ተስ ፋሁ ለአዳም አመ ይሰደድ እምገነት" አዳም ከገነት በተሰደደ ጊዜ ተስፋው አንቺ ነሽ በማለት ያስረዳል
(ቅዳሴ ማር.)፡፡
💕የእመቤታችን💕
አማላጅነት አይለየን
💕ድንግል ሆይ💕
ከሚያሰጥም ባሕር ማዕበልም ሞገድ፡፡ ከከበደዓለም ኅልፈት ጥፋት በጸሎትሽ አድኝኝ፡፡
👉 አምላክን የወለድሽ ድንግል ሆይ በላዬያደረውን የኃጢአቴን ሽታ አርቂው፡፡ በጸሎትሽምመዓዛ እንደ ኪሩቤል ዕጣን ሽታ እንደ ሱራፌልምጽንሐሕ ጸሎቴ ደግሞ ያማረ የተወደደእግዚአብሔርም የተቀበለው ይሁን፡፡
👉. ምስጋናን የተመላሽ ድንግል ሆይ እንዳልወድቅከመሰናክል አድኝኝ ደግፊኝ፡፡ ጥልቅቅ የሚያደርግአእምሮ የሚያሰጥ ወይን መጠጥን እንደጠጣልቤ ዕውቀት አጥቷልና፡፡
👉ሕጉን ትእዛዙን ለመጠበቅ እያሰብሁ ሌሊቱንሁሉ እደክማለሁ፡፡ ጥቂትም ቆይቶ አናዋዋርየሚለውጥ ሐሳብ ይመጣብኛል፡፡ የዚህን ዓለምማሠሪያ ከኔ ቁረጭው ሰውነቴ በርሱ ገመድተይዟልና ለርሱም ከገዛት ነጻ አድርጊኝ፡፡
👉 ጸጋ ክብርን የተመላሽ ድንግል ሆይ ከመግፋትከመገፋት አድኝኝ፡፡ ቅድስና የተመላሽ ድንግል ሆይከመበደል ሌላውንም ከመበደል አድኝኝ፡፡ ከደምአፍሳሽ አድኝኝ፡፡ እኔም ደግሞ የሌላውን ደምከማፍሰስ ሠውሪኝ፡፡
👉 የተድላ መፍሰሻ ድንግል ሆይ ከሽንገላ አድኝኝ፡፡ከሸንጋይም ደግሞ ሠውሪኝ፡፡ የምስጋና መፍሰሻድንግል ሆይ ከሽሙጥ ከስድብከሚያስሽሟጥጥና ከሚሰድብ ደግሞ ሠውሪኝ፡፡
ከሚያሰጥም ባሕር ማዕበልም ሞገድ፡፡ ከከበደዓለም ኅልፈት ጥፋት በጸሎትሽ አድኝኝ፡፡
👉አምላክን የወለድሽ ድንግል ሆይ በላዬያደረውን የኃጢአቴን ሽታ አርቂው፡፡ በጸሎትሽምመዓዛ እንደ ኪሩቤል ዕጣን ሽታ እንደ ሱራፌልምጽንሐሕ ጸሎቴ ደግሞ ያማረ የተወደደእግዚአብሔርም የተቀበለው ይሁን፡፡
👉 ምስጋናን የተመላሽ ድንግል ሆይ እንዳልወድቅከመሰናክል አድኝኝ ደግፊኝ፡፡ ጥልቅቅ የሚያደርግአእምሮ የሚያሰጥ ወይን መጠጥን እንደጠጣልቤ ዕውቀት አጥቷልና፡፡
👉 ሕጉን ትእዛዙን ለመጠበቅ እያሰብሁ ሌሊቱንሁሉ እደክማለሁ።
💕ማርያም💕 ትማርሽ
👉ማርያም ትማርሸ፣ ማርያም በሽልም ታውጣሽ፣ ማርያም ጭንሽን ታሙቀው የሚሉ የመልካም ምኞት መግለጫዎች ሲኖሩ ማርያም ታኑርሽ ወይም ታኑርህ የሚሉ ተመሳሳይ ምላሾችን እናገኛለን፡፡
👉ከነዚህ መሰል እምነትንና ባህልን ካቆራኙ አገላለጾች በስተጀርባ ብዙ ሊባል የሚችል ነገር ይኖራል፤ “የማርያምን ብቅል እየፈጨሁ ነው” ግርድፍ በሆነ አፈታት ትርጉሙ እንዲገባን በምን ዓይነት መቼት (ጊዜና ሁኔታ...) እንደሚባል እናስታውስ፡፡
👉 አንድ ሰው ስሙ ሲጠራ ሰምቶ ወይም መስሎት የጠራውን ሰው ለማየት ዙሪያ ገቡን ሲያማትር የሰው ሽታ ሲጠፋበትየማርያምን ብቅል እየፈጨሁ ነው ብሎ የመመለስ ልማድ አለ፡፡
👉ይህ ሁለት ነገር ሊያመላክተን ይችላል፤ ማለትም ጠሪ ብለን ያሰብነው ማንነትንና ተጠሪው የሚሰጠውን ምላሽ፤ አለሁ ብሎ ጠርቶ ዞር ስንል የለሁም የሚለውን በተለያየ መልኩ የሚጎትተንን ጠላት አታላይ ሰይጣንንና ይህን አታላይ የሚያሸንፈው ደግሞ የአዳኙ ክርስቶስ እናትና የእግዚአብሔር ቃል እንደሚላት “የልኡል ኃይል የጋረዳት” “የዘንዶውን ራስ የሚቀጠቅጠውን” የወለደች የእርስዋ ክብር ነው፡፡
👉“ማርያምን ለማክበር በስምዋ ጽዋ እደግሳለሁና ለዚህ በዓል ዝግጅት የሚሆነኝን ብቅል እያዘጋጀሁ ነው አንተ ክፉ ከኔ ራቅ!” የሚል አንድምታን የያዘው ይህ አባባል ዛሬም እኛ እመቤታችንን ስናከብር ዘወትር ከርስዋ የማይለየውንና በምድርም በሰማይም ያከበራትን ሁሉን ቻይ ልጅዋን፣
👉የማዳን እቅዱን በርስዋ ያከናወነውን አብንና ከሥጋ እድፈት ጠብቆ የክርስቶስን ሰው መሆን እውን ያደረገውን መንፈስ ቅዱስን በአንድነት እናከብራለን፤
👉 በርግጥም ይህን የመሰለ ክብር ሰይጣንን ማስደንገጥና ማሸነፉ አጠራጣሪ አይደለም፡፡
👉ስለዚህም እመቤታችንን የልባችን ንግሥት ባደረግናት መጠን ክርስቶስንም የሕይወታችን ንጉሥና ገዢ እናደርገዋለን፡፡
👉እግዚአብሔር ራሱ እመቤታችን የአካሉ እናት ትሆን ዘንድ ፈቅዶ በቅዱስ ዮሐንስ አምሳል “እነሆ እናትህ፤ እናትሽ!” ሲለን ምንኛ መታደላችንንና ልዩ መብት መጎናጸፋችንን አስተውለን “እነሆኝ ልጅሽ” እንበላት፡፡
👉 ከርስዋና ከልጅዋ ርቀን በሄድን ወይም ያለምንም የሕይወት ለውጥ በሌላ ጊዜያችን ማለትም እድሜያችን እየተነነ ከሆነ አታላዩ እየጠራ ዞር በማለት ሲያከራትተን ይኖራል፡፡
👉💕 የእመቤታችንን💕 ዱካ በመከተል እጅዋን ከያዝን እርስዋ ክርስቶስን አቅፋለችና የታላቁ ቤተሰብ ክፍል እንሆናለን፡፡
👉ይህ ከላይ ለማለት የሞከርነውን ጭብጥ አቅፎ በያዘው በቅዱስ በርናርዶስ ምክር እንደምድም
👉“ወደ ክዋክብት ተመልከትና ማርያምን ጥራ!
👉በአደጋ፣ በችግር ወይም በጥርጣሬ ጊዜ ማርያምን አስብ፡፡
👉ስምዋን በከናፍርህ አኑረው፡፡ የእርሷ ስም ከልብህ በፍጹም አይውጣ!
👉በእግር ዱካዋ የአንተን እግር አኑር ከቶ አትጠፋም፡፡
👉ወደርሷ ተማጠን ተስፋ ቁርጠት አይጠናወትህም፡፡
👉እርሷን አስብ አትሳሳትም፤
👉እርሷ እጅህን ይዛህ መውደቅ አይቻልህም፣
👉አትታክትም፣ አትፈራም፣ በጥበቃዋ እየተደሰትክ ወደ ግብህ ትደርሳለህ፡፡"
1⃣⏩እንቆቅልሽ
✍🏾ምን አውቅልሽ❓
የጌታዬን ፊቱን በጨርቅ ባብስ
መልኩ ተስሎበት ያገኘሁት ወደ ቤቴ ስደርስ
እኔ ማን ነኝ?
2⃣✍🏾 እንቆቅልሽ
⏩ምን አውቅልሽ❓
✍🏾ቢበሉት ቢጠቱን የማያልቅ
ቢለብሱት የማያረጅ ቢሸከሙት የማይከብድ
ከጨለማ ከዓለም የሚያላቅቅ
ከክፉ የሚያድን የሚጠብቅ ምንድነው ታውቂዋለሽ?
3⃣⏩እንቆቅልሽ
✍🏾ምን አውቅልሽ❓
⏩በፋሲካ ምሽት ጌታን አሳልፎ የሚሰጠው ማን እንደሆነ የጠየቀ
የወንጌሉ ቋንቋ ፅር የሆነ
በህይወቱ መጨረሻ በእስያ ሀገር በኤፌሶን ያስተማረ ይሄ ቅዱስ ማን ነው
ሌሎችንም ጥያቄዎች ገብቶ ለመሳተፍ ቻናላችንን ይጎብኙ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
ቻናላችን ለመቀላቀል👉 @ortodoxmezmur21👈
👆👆👆👆👆👆👆👆👆
💕እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም 💕
👉ራሱን በራሱ ያጎሳቁል ለነበረው ወጣት ያደረገችው ተአምርና የሰጠችው ምክር †
👉ራስን በራስ ማጎሳቆል የዚህ ዘመን ትልቁ ፈተና ነው፡፡
👉 ብዙ ወጣቶች በዚህ ሱስ ይያዛሉ፡፡
👉ወደ ትዳር ገብተው ራሱ ከዚህ ሱስ መውጣት አቅቷቸው ከትዳር አጋራቸው ጋር የተገባ ሩካቤን የማይፈጽሙ ቊጥራቸው ቀላል አይደለም፡፡
👉እነዚህ ሰዎች ንስሓ መግባት ራሱ ያሳፍራቸዋል፡፡
👉እስኪ ከዚህ ጋር በተያያዘ አንድ ክሪሶስቶሞስ (አፈ ወርቅ) የተባሉ የምሥራቅ ኦርቶዶክስ ሊቀ ጳጳስ ራሱን በራሱ ያጎሳቁል
👉 (Masturbate ያደርግ) ስለ ነበረ አንድ በዓሥራዎቹ ዕድሜ ስለሚገኝ ወጣት የጻፉትን ላካፍላችሁ፡-
👉“አንድ ወጣት አንድ ጊዜ የሚከተለውን ነገረኝ፡፡
👉በዓሥራዎቹ ዕድሜ ውስጥ እያለ ለስፖርቶች በተለይም ለትግል ልዩ ፍላጎት ነበረው፡፡
👉 ወደ ዓሥራ አምስት ዓመቱ ገደማም አንድ የቡድን ጓደኛው ራስን ስለ መበደል ኃጢአት አስተዋወቀው፡፡
👉ከማፈሩ የተነሣም ንስሓ አልገባም ነበር፡፡
👉 አንድ ቀንም ከአንድ ወር በኋላ ከታላቅ ወንድሙ ጋር እየታገሉ እያለ በወንድሙ ደረት ላይ ዘፍ ብሎ ወደቀ፡፡
👉መተንፈስ አልቻለም፡፡ ሞተ፡፡
👉“በዚህ ውስጥ ኾኖም የገዛ አስከሬኑን፣
👉ወንድሙና እናቱ ተደናግጠው እርሱን ለመርዳት ሲሯሯጡ፣
👉 ነፍሱ ደግሞ በጠባቂ መልአኳ ታጅባ ከቤቱ ስትወጣ፣
👉 ከሚኖርበት ከተማም እጅግ ከፍ ብላ በመጨረሻም ወደ ላይ ወደ ሰማይ ስትኼድ ይመለከት ነበር፡፡
👉 ከዚያም ጥልቅ በኾነ ጨለማ ውስጥ ራሱን አገኘው፡፡
👉ከዚያ አልፎም መጨረሻ ላይ ብርሃንንና ገነትን ተመለከተ፡፡
👉“ወደዚህ ብርሃን እንደ ገባም 💕ወላዲተ አምላክን💕 አያትና ጠባቂ መልአኩን ለምን እንደ አመጣው ጠየቀችው፡፡
👉መልአኩም የልጁን አሟሟት በዝርዝር ነገራት፡፡
👉በዚህ ጊዜ 💕እመቤታችን💕 ለዚያ ልጅ ‘ትድንላት ዘንድ እናትህ አጥብቃ እየለመነቺኝ ነው፤
👉 ልጄም ጸሎቷን ሰምቷል” አለቺው፡፡
👉ያ ልጅ ግን በገነት ውበት ስለ ተማረከ በዚህ ይቆይ ዘንድ ለመናት፡፡
👉💕ወላዲተ አምላክ💕 ግን ‘አይኾንም' አለቺው፡፡
👉 ‘ለእናትህ ስትል መመለስ አለብህ፡፡
👉ነገር ግን አድምጠኝ፡- ከአንድ ወር በፊት ስለ ሠራኸው ኃጢአት ልትናዘዝ ይገባል፡፡
👉ይህ እጅግ አስጸያፊ ኃጢአት ነው፡፡
👉 ይህን ለካህን ካልተናዘዝክ፥
👉 ምን እንደሚያገኝህ ተመልከት፡፡'
👉ከዚህ በኋላ 💕ወላዲተ አምላክ 💕የሲዖል ሥቃይ ምን እንደሚመስል እንዲያሳየው ለቅዱስ ሚካኤል አዘዘችው፡፡
👉የሚመለከተው ነገር እጅግ የሚያስፈራ ከመኾኑ የተነሣ፥ ልጁ ራሱን እስከ መሳት ደረሰ፡፡
👉“ከዚያ በኋላም ወደ ጥልቁ ጨለማ፣ ቀጥሎም ወደ ሰማያት፣
👉 ዝቅ ብሎም ይኖርበት ወደ ነበረ ከተማ - ወደ መኖሪያ ቤቱ - ቤተሰቦቹ አስከሬኑን ከብበው ወደሚያለቅሱበት ክፍል ወረደ፡፡
👉 በሰውነቱ ላይ ከፍተኛ የኾነ መጫጫን ከተሰማው በኋላም ነፍሱ ወደ ቦታዋ ተመለሰች፤
👉 ዓይኖቹንም ከፈተ፡፡
👉ከዚያም የኾነውንና የተመለከተውን ኹሉ ለቤተሰቦቹ ነገራቸው፡፡
👉በኀዘን ተጎድታ የነበረችው እናቱም ይህን በሰማች ጊዜ እመቤታችን ከልጇ ከወዳጇ ስላማለደቻት አመሰገነቻት፡፡
👉እጅግ እያለቀሰችም ልጇን ዕቅፍ አድርጋ ሳመችው፡፡”
👉ፈጣኗ ደመና 💕ወላዲተ አምላክ 💕በዚህ ሱስ ውስጥ ያሉትን ኹሉ ከዚህ በደል ይወጡ ዘንድ ትድረስላቸው፡፡