uraman4u12 | Unsorted

Telegram-канал uraman4u12 - የእመቤታችን አንድምታ ወዳሴ ቅዳሴ

-

በዚሕ ቻናል የእመቤታችን ዉዳሴዋ ንባቡና ትርጓሜዉ በአንድምታ ይቀረባል። ከኛ የሚጠበቀዉ መማር ብቻ ነዉ። አምላክ ከኛ ጋ ይሑን የእመቤታችን አማላጅነት አይለየን። ሐሳብ አስተያየት 👇👇👇👇👇👇 @woladite11

Subscribe to a channel

የእመቤታችን አንድምታ ወዳሴ ቅዳሴ

✞✞ # ልቦናዬ_በጎ_ነገርን_አወጣ እኔስ የማርያምን ክብር
እናገራለሁ ፡፡በማብዛት አይደለም በማሳነስ ነው እንጂ፡፡
.
✞ እኔስ የድንግልን ውዳሴ እናገራለሁ መዘንጋት ባለበት
ቃል በማስረዘም አይደለም በማሳጠር ነው እንጂ ፡፡
.
✞ ድንግል ሆይ በኃጢያት ፍትወት የተፀነሽ አይደለሽም
በሕግ በሆነ ሩካቤ ከሐና ከኢያቄም ተወለድሽ እንጂ ፡፡
.
✞ ድንግል ሆይ አንገታቸው እንደሚገዝፍ እንደ
ዕብራዊያን ሴቶች ልጆች በዋዛ ያደግሽ አይደለሽም
በንፅሕና በቅድስና በቤተ መቅደስ ኖርሽ እንጂ ፡፡
.
✞ ድንግል ሆይ ምድራዊ ሕብስትን የተመገብሽ
አይደለሽም ከሠማይ ሠማያት የበሠለ ሠማያዊ ኀብስትን
ነው እንጂ፡፡
.
✞ ድንግል ሆይ ካንቺ አስቀድሞ ከአንቺ በኋላም እንዳሉ
ሴቶች እድፍ የምታውቂ አይደለሽም በንፅሕና በቅድስና
ያጌጥሽ ነሽ እንጂ ፡፡
.
✞ ድንግል ሆይ የሚያታልሉ ጎልማሶች ያረጋጉሽ
አይደለሽም የሠማይ መላእክት ጎበኙሽ እንጂ፡፡ እንደተነገረ
ካሕናትና የካሕናት አለቆች አመሠገኑሽ እንጂ ፡፡
.
✞ ድንግል ሆይ ለዮሴፍ የታጨሽ ለመገናኘት አይደለም
ንፁሕ ሆኖ ሊጠብቅሽ ነው እንጂ ::
.
✞ እንዲሁም ስለሆነ እርሱ ቅዱስ ልዑል እግዚአብሔር
አብ ንፅሕናሽን ባየ ጊዜ ስሙ ገብርኤል የሚባል ብርሃናዊ
መልአኩን ወደ አንቺ ላከ መንፈስ ቅዱስም በላይሽ
ይመጣል የልዑል ኃይልም ይጋርድሻል አለሽ እንጂ ፡፡
.
✞ እመቤቴ አንቺን የሚመስልሽ ማንም ምንም የለም
እኛም እንወድሻለን እናገንሻለን፡፡
አማላጅነቷ አይለየን!!

Читать полностью…

የእመቤታችን አንድምታ ወዳሴ ቅዳሴ

“ቅድስተ ቅዱሳን የአምላክ እናት ስለ እኛ ያለማቋረጥ ትጸልያለች። ሁሌም ትጎበኘናለች። በልባችን ወደ እሷ ስንዞር እዚያ ትገኛለች። ከጌታ በኋላ እሷ ለሰው ልጆች ታላቅ ጥበቃ ነች። በዓለም ላይ ለቅድስተ ቅዱሳን የእግዚአብሔር እናት የተሰጡ ስንት አብያተ ክርስቲያናት አሉ! ቅድስተ ቅዱሳን ቲኦቶኮስ በተገለጠበት ቦታ ሰዎች ከሕመማቸው የሚፈወሱባቸው የፈውስ ምንጮች ስንት ናቸው እናም እነዚያን ምንጮች የታመሙትንና ጤነኞችን ይፈውሱ ዘንድ የባረካቸው! እሷ ያለማቋረጥ ከጎናችን ናት፣ እና ብዙ ጊዜ እንረሳታለን።
☦️ አረጋዊ ታዴዎስ, Homily on the Dormition of theotokos

Читать полностью…

የእመቤታችን አንድምታ ወዳሴ ቅዳሴ

ስለ አንዲት ሴት አይደለም የምናወራው
***

ስለ አንዲት ሴት አይደለም የምናወራው ...ከሴቶች መሃል በልዩነት ተባርካ ስለተገለጠች ብጽእት ሴት እንጅ።

ስለ አንዲት እናት አይደለም የምናወጋው......ዳግም የእናትነት ክብሯን ፍጥረት ስለማያገኘው ስለ አምላክ እናት ነው እንጅ።

ስለ አንዲት ቅድስት አይደለም የምንጽፈው....ቅድስና የባህሪ የሆነን ጌታ የማህጸኗ ፍሬ ይሆን ዘንድ የተገባት ስለ ቅዱስ አምላክ እናት እንጅ።

ስለ አንዲት ድንግል ሴት አይደለም የምናሳውቃችሁ....እናትነትን ከድንግልና ጋር አስተባብራ የያዘች እናታዊት ድንግል ሴት እንጅ ።

መንፈስቅዱስ ስለተቀበለች አንዲት ሴት አይደለም የምንናገረው......መንፈስ ቅዱስ ልሳን ሆኖ ምስጋና እና ክብሯን ስለሚገልጥላት ብቸኛዋ ሴት እንጅ።

ድምጿ ጽንስ ስለሚያዘልል አንዲት ንጽህት ሴት እንጅ።

እሷ ሳትኖር በፊት ነብያት በትንቢት ስላመላከቷት ሴት እንጅ።

አባቷ አዳም የመዳኑ ቀን እንደደረሰ ያውቅ ዘንድ ሊያያት ስለናፈቃት ውብ ሴት እንጅ።

<< ቅድስት ድንግል ማርያም >>

Читать полностью…

የእመቤታችን አንድምታ ወዳሴ ቅዳሴ

የማርያም እርገት ከመፅሀፍ ቅዱስ

ከብዙ ፕሮቴስታንት ወንድሞች ጋር ሳወራ የማይቀር ና የሚያስቀኝ ብሎም ገምቼ የማላጣው ጉዳይ ነው ።

ነገርን ከስሩ እንዲሉ አበው ከሞት እንጀምር እስኪ ሮሜ 5:12 ጀምሮ ስናነብ  ስለዚህ ምክንያት ኃጢአት በአንድ ሰው ወደ ዓለም ገባ በኃጢአትም ሞት፥ እንደዚሁም ሁሉ ኃጢአትን ስላደረጉ ሞት ለሰው ሁሉ ደረሰ፤  ስለዚህም በአዳም ህግ መጣስ መዘዝ ሞት ገባ  ነበያቱ ሁሉ ስሐ ሞት ፍርሃት ነበረባቸው ምክንያቱም ሞት ቦታ የመቀየር ጉዳይ ከመሆኑም ባሻገር ነብዩ ኢሳያስ እንዳለ ፅድቃችን የመርገም ጨርቅ ሆነ በማለት በእግዚአብሔር ዘንድ ሞገስ የነበራቸው እነሱ ሳይቀር ከሞት ከሞትም ደሞ ከሲኦል ይድኑ ዘንድ አልነበራቸው እና ነው ሞት ህዝቡ ላይ ሰልጥኖ በነበረበት በዛን ወቅት ነበያቱም ሀጥአኑም ሞት ሀይል ነበረው
                         ታዲያ
አሁን ላይ አባቶቻችን , ፃድቃናት , ሰማዕታት  ሞትን አለ ልክ ሲዳፈሩት , ሲመኙት ብሎም ወደው እና ፈቅደው  ሲጋደሉ ማየት  ከሐዋርያት መካከል ቅዱስ ጳውሎስም ወደ ጌታው መሄድን እንደሚናፍቅ ማንበባችን እና ማየታችን ከየት የመጣ ድፍረት ነው ብሎ መጠየቅም መንገርም ለ አንድ ክርስቲያን ለቀባሪ ማርዳት የመሠለ የቂል ነገር ቢመስልም እንየው
                   ድፍረት
ለዚህ ምክንያቱ ሞት የቀደመ ሀይሉ ስለሌለ እና መዋረዱ ነው ይኼስ እንዴት ሆነ ቢሉ የማይችለውን እውጣለው ብሎ የዋጣቸውንም መትፋቱ ነው ለመሆኑ የማይችለው ማነው? የተዋጡት ኋላ የተተፉትስ?
ሰማይን ያለ ምሶሶ ምድርንም ያለ ካስማ ያቆመ አምላክ ሰው የመሆኑ ምስጢር ዛሬም በስንዱዋ እመቤት በቤተክርስቲያናችን ምስጢረ ስጋዌ ነው  ። ሆኖም አምላክ እንዴት ሰው ሆነ ሰውስ እንዴት አምላክ ሆነ ብለን እውነተኛ የፅድቅ ፀሀይን ያስገኘችዋን ምስራቅ እንመርምራት

         አንቺ ምስራቅ ነሽ ልጅሽ ደሞ እውነተኛ የፅድቅ ፀሀይ

የ15 አመት ብላቴና ሳለሽ እሳተ መለኮቱ በሆድሽ ባደረ ጊዜ እንደምን አላቃጠለሽ 7ቱ መጋረጃዎችስ በማህፀንሽ ወዴት ተሰናዱ , ታናሽ ሙሽራ ስትሆኚ እንግዳ ስርዓት በሆድሽ ሲፈፀም እንደምን ቻልሺው ለዚህ አንክሮ ይገባል !!
የነበያት ፣ የፃድቃን ፣ የሰማዓታት ወይም የወታደር ሳይሆን የአምላክ እናት ስትሆኚ እድሜሽ 16 ደርሶ ነበር ። ይኼ ህፃንሽ ጥቂት ጥቂት እያለ አደገ መፅሀፍ ልጅሽን አስቀድሞ በአባቱ ሲያውቀው በምኞት እና በተስፋ ይመጣል ይወለዳል ያድነናል ብሎ ያውቀዋል በኋላም በድንግሊቱ እቅፍ እስከ 3 አመት ቀጥሎም የ12 አመት ልጅ ሆኖ ሲያውቀው በመጨረሻም የ30 አመት ጎልማሳ ሆኖ ለ3 አመት ነው ያየው በአጠቃላይ 10 ዓመት እንኳን አይሆንም  ፤ አቤት ግን ስለ ልጅሽ የአሁኑ ሰው የሚያውቀው ካንቺ በላይ ነው ¶¶
ወደቀደመ ነገሬ ስመለስ ቀዳማዊው አዳም ያመጣው ሞት ዳግማዊው አዳም ሞተ  ይኼኔ ሞት እንደለመደው የማይችለውን አምላክን እውጣለው ሲል ለ5500 አመት የዋጣቸውን ተፋቸው።

        ወደ ጀመርነው
ተራ ያይደለ አምላክን , ምድራዊ ያይደለ ሰማያዊውን የወለድሽ አንቺ ትሞቺ ዘንድ እንዴት ሆነ ? አንቺስ ሞትሽለት እንጂ ከቶ አልወሰደሽም ብል ይነሰኝ። ይኼ ሆኖ ሳለ የማርያምን እርገት ብዙ ወንድሞች ከመፅሀፍ ሲጠይቁኝ እንዳልነው አስቀድመን ነገርን ከስሩ ማየት መልካም ነውና ይቺን ጥያቄ እጠይቃለው "ሞቷን ከመፅሀፍ አሳዩኝ?" ማንም መልሶልኝ አያውቅም ። አንድ ቀን ግን አንድ ወንድም መለሰልኝ " አላውቅም በመፅሀፍ የማርያም ሞት የለም " ታዲያ ማን ነገረህ " አላውቅም"

              

Читать полностью…

የእመቤታችን አንድምታ ወዳሴ ቅዳሴ

#ዘመን_አይሽሬው_የቅድስት_ኪዳነ_ምህረት_ድንቅ_ተአምር:-

ልመናዋ ክብሯ በእኛ ለዘላለም በእውነት ይደርብንና አምላክን የወለደች በድንጋሌ ሥጋ በድንጋሌ ነፍስ የጸናች ክብርት እመቤታችን ያደረገችው ተአምር ይህ ነው፡-

ስሙ ስምዖን የሚባል ቅምር በሚባል አገር የሚኖር እጅግ ባለጸጋ ሰው ነበር፡፡ እንደ አብርሃም እንግዶችን እየተቀበለ ድኆችን እየመገበ የሚኖር ጻድቅ ነበር፡፡

የበጎ ነገር ሁሉ ጠላት ሰይጣን በዚህ ሥራው ቀናበትና ሊፈትነው በሦስት አረጋዊ ሽማግሌዎች ተመስሎ ‹‹ሥላሴ ነን›› ብሎ እንደ አብርሃም እንደተገለጠለት ሆኖ ተገለጠለት፡፡ ‹‹ሰይጣን ራሱ የብርሃን መልአክ እንዲመስል ራሱን ይለውጣል›› እንዳለ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ፡፡ 2ኛ ቆሮ 11፡14፡፡ ስምዖንም የዕውነት ሥላሴ መስለውት ተቀበላቸውና ተንከባከባቸው፡፡ የሚበሉት ምግብ ሲያቀርብላቸው እነርሱ ግን ‹‹ምግብ አንበላም፤ የምንጠይቅህን ግን ትፈጽምልን ዘንድ ቃል ግባልን›› አሉት፡፡ ስምዖንም የሚጠይቁትን ለመፈጸም ቃል ገባላቸው፡፡ እነርሱም ቃል ካስገቡት በኋላ ‹‹እንግዲያውስ የምትወደን ከሆነ አንድያ ልጅህን ሰዋልን›› አሉት፡፡ ስምዖን መጀመሪያ ላይ ቢደነግጥም በኋላ ግን ‹‹አብርሃም ልጁን ሊሠዋ አልነበረምን፣ እኔንም ሊፈትኑኝ ይሆናል›› ብሎ ለማረድ ወሰነ፡፡ አንድያ ልጁንም ሊሠዋው በተዘጋጀ ጊዜ ‹‹ተው›› የሚል ድምጽ የሚሰማ መስሎት ቢጠብቅ የሚሰማው ድምጽ ስላጣ አንድያ ልጁን አረደው፡፡ እንዲመገቡም ይዞላቸው ቀረበ፡፡ እነርሱም ‹‹መጀመሪያ አንተ ቅመስልን›› ሲሉት ቀመሰው ነገር ግን ወዲያው እነዚያ ሰዎች ከእርሱ ተሰወሩበት፡፡

ስምዖንም ሰይጣን በፈተና እንደጣለውና እንደተጫወተበትም ሲያውቅ አእምሮውን ሳተ፡፡ ከዚያ በኋላ ምግብ የሚባል ነገር አላሰኘውም፡፡ ይልቁንም የሰው ሥጋ የሚበላ ሆነ እንጂ፡፡ በመጀመሪያ የራሱን ቤተሰቦች አንድ በአንድ በላ፡፡ ቀጥሎም ጎረቤቶቹን፣ ጓደኞቹን ሁሉ በላ፡፡ አንት የውኃ መንቀልና ጦር ብቻ ይዞ ከቤቱ ወጥቶ በመሄድ በመንገድ ላይ ያገኘውን ሰው ሁሉ እየገደለ ይበላ ጀር፡፡ የበላቸውም ሰዎች ቁጥር በአጠቃላይ 78 ሆነ፡፡

ከዚህም በኋላ በመንገድ ሲጓዝ ተቀምጦ የሚለምን በደዌ የታመመ አንድ ደኀ አገኘና ሊበላው ፈለገ፡፡ ነገር ግን ወደ እርሱ በተጠጋ ጊዜ ቁስሉን አይቶ ተጸየፈው፡፡ ደኀውም ሰው ‹‹ስለ እግዚአብሔር ብለህ ከያዝከው ውኃ አጠጣኝ›› አለው፡፡ ስምዖንም ዝም ብሎት ሄደ፡፡ አሁንም ድኀው ‹‹በውኃ ጥም ልሞት ነውና ስለ ጻድቃን ብለህ ከያዝከው ውኃ አጠጣኝ›› አለው፡፡ ስምዖንም ዝም ብሎት ሄደ፡፡ ዳግመኛም ለ3ኛ ጊዜ ድኀው ‹‹ስለ አዛኝቷ አምላክን ስለወለደች ስለ ድንግል ማርያም›› አለው፡፡ በዚህም ጊዜ ስምዖን የእመቤታችንን ስም ሲጠራ ሲሰማ ሰውነቱን አንዳች ነገር ወረረው፡፡ ወደ ድኀውም ተመልሶ ‹‹አሁን የጠራከውን ስም እስኪ ድገመው? ስለ ማን አልከኝ?›› አለው፡፡ ድኀውም ‹‹ስለ አዛኝቷ አምላክን ስለወለደች ስለ ድንግል ማርያም›› አለው፡፡ ስምዖንም ‹‹ይኽቺስ ደግ እንደሆነች፣ በምልጃዋም ከሲኦል ነፍሳትን እንደምታወጣ ከህፃንነቴ ጀምሬ ሰምቼው ነበር እናትና አባቴ ይነግሩኝ ነበርና›› አለው፡፡ ድኀውም ‹‹አሁንም በእርሷ ተማጽኜብሃለሁ›› አለው፡፡ በዚህም ጊዜ ስምዖን ‹‹በል ንሣ አምላክን ስለወለደች ስለ ክብርት ድንግል ማርያም እንካ ጠጣ›› ሰጠው፡፡ ከማነሷም የተነሣ ከጥሪኝ ውኃ በቀር ወደ ጉሮሮው አልወረደም፡፡

በለዔ ሰብእም ከዚያች ጊዜ በኋላ አእምሮው ተመለሰለት፡፡ እንዲህም አለ፡- ‹‹በአንድ ዋሻ ውስጥ ገብቼ ስለ ኃጢያቴ አለቅሳለሁ፣ ሥጋዬ ከአጥንቴ እስኪጣበቅ እጾማለሁ፣ ወዮሊኝ ወዮታ አለብኝ›› አለ፡፡ ከዚህም በኋላ ወደ ዋሻ ገብቶ ምግብ ሳይበላ ውኃም ሳይጠጣ 21 ቀን ኖረና በረኀብ ሞተ፡፡

የጨለማ አበጋዞች ሰይጣናትም እያስፈራሩ እጅግ እያስደነገጡ ነፍሱን ወደ ሲኦል ሊወስዷት መጡ፡፡ ክብርት እመቤታችንም ፈጥና በመካከላቸው ተገኘችና አንዳች የሠራት በጎ ነገር እንዳለች መረመረች፡፡ እነርሱም እመቤታችንን ‹‹ከሰማይ በታች ከዚህ ኃጢአት የበለጠ አለን?›› አሏት፡፡ ክብርት እመቤታችንም ስለስሟ ብሎ ለድኀው ምጽዋት አድርጎ የሰጣትን ያችን ጥርኝ ውኃ በጎኑ አይታ ደስ አላት፡፡

ያችንም ነፍስ በመፍራትና በመንቀጥቀጥ ከእግዚአብሔር ፊት አደረሷት፡፡ ‹‹ጥርስ ማፋጨት ወዳለበት የሥቃይ ቦታ ውሰዷት›› የሚል ድምጽ ከዙፋኑ ወጣ፡፡ ክብርት እመቤታችንም ‹‹ልጄ ወዳጄ ይህችን ነፍስ ማርልኝ›› እያለች ሰገደች፡፡ ጌታችንም ‹‹እናቴ ሆይ! ሰባ ስምንት ነፍሳትን የበላ እንዴት ይማራል?›› አላት፡፡ እርሷም ‹‹ልጄ ሆይ! የካቲት 16 ቀን በጎለጎታ የገባህልኝ ቃልኪዳንህን አስብ እንጂ፤ ‹ስምሽን የጠራውን፣ መታሰቢያሽን ያደረገውን፣ በስምሽም ቀዝቃ ውኃ ያጠጣውን፣ የተራበ ያለበላውን እምርልሻለው› ብለኸኝ የለምን?›› አለችው፡፡ የክብር ባለቤት ጌታችንም ‹‹እውነት ነው መሐላዬን አላፈርስም›› አላት፡፡ ወዲያውም መላእክቱን ‹‹እስኪ ሚዛን አምጥታችሁ ያችን ጥርኝ ውኃ በአንድ ሚዛን፣ እነዚህንም 78 ነፍሳት በአንድ ሚዛን አድርጋችሁ በሚዛን አስቀምጡ›› ብሎ አዘዛቸው፡፡

መላእክትም በሚዛን ቢያስቀምጧት ጥርኝ ውኃዋ ከሰባ ስምንቱ ነፍሳት ይበልጥ መዝና ተገኘች፡፡ ከዚህም በኋላ ጌታችን ‹‹ስለ አንቺ ስል ምሬያታለው›› አለ፡፡ ያችም ነፍስ አምላክን በወለደች በክብርት እመቤታችን አማላጅነት ድና ወደ መንግሥተ ሰማያት ገባች፡፡

የበላኤ ሰብእ እመቤት የብርሃን እናቱ ቅድስት ኪዳነ-ምህረት ወላዲተ አምላክ ከቃልኪዳኗ ረድኤት በረከት ትክፈለን!

Читать полностью…

የእመቤታችን አንድምታ ወዳሴ ቅዳሴ

እንኳን እመቤታችን ከስደት ተመልሳ ቁስቋም የገባችበት በዓል ቀን በሰላም አደረሳችሁ




ህዳር 6

በዚህች ቀን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከልጇ አንዲሁም ከዮሴፍና ሶሎሜ ጋር 3 ዓመት ከ 6 ወር በስደት ከተንገላታች በኋላ ወደ አገራቸው የተመለሱበት ቀን ነው፤

👉 ከግብጽ ሲመለሱ ጌታችን በእመቤታችን ጀረባ ላይ ሆኖ እነዚያ እውራንን ባበሩ ጣቶቹ ወደ ኢትዮጵያ ይጠቁም ያመለክት ነበር፤

👉እመቤታችንም ልጄ ሆይ ለምንድነው ጣትህን የምታመለክተው ብትለው

👉 "ያቺ የተባረከች አገር ናት እኔን የሚያመልኩ አንቺን የሚማልዱ በፍቅርሽ የነደዱ ቅዱሳን መነኮሳት የሚፈልቁባት አገር ናት፤

👉 ያንቺ ዘመዶች ሰቅለው ይገድሉኛል በዚህች አገር ያሉ ግን ሳይዩኝ ያመኑኛል፤

👉አስራት በኩራትሽ ትሁን ብሎ ሰጥቷታል፡፡

👉በኪደተ እግራቸውም ጣና ሐይቅን፤

👉ዋልድባንና ሌሎችንም ቦታዎች ዞረው እንደባረኩ ድርሳነ ኡራኤልና ተአምረ ማርያም ላይ በስፋት ተጽፏል፡፡ 👉እመቤታችንን ከሐና ማህጸን ፈጥሮ ከፍጥረተ ዓለም ለይቶ ከሁሉ አልቆ የእናት አማላጅ ትሁናችሁ ብሎ የሰጠን እግዚአብሔር ይመስገን።

👉 ዳግመኛም በዛሬዋ ቀን በኢትዮጵያ ምድር ታላቅ አምድ ወደቀ ይህም የመናገሻው ባህታዊ አባ ኤልያስ ነው፤ በ 400 ዓመት እድሜው ህዳር 6 1874 ዓ/ም አረፈ፤ በአጼ ምኒሊክ ዘመነ መንግስት ማለት ነው፤ የቅርብ ጊዜ ነው፤ ይህ አባት በግራኝ መሐመድ ወረራ ጊዜ የነበረ ነው፤ በዚያን ጊዜ በተለይ ኦሮሞዎች "አያና ውቃቢ" እያሉ በጣም ያከብሩት ነበር፤ ከመናገሻ እንጦጦ ኪዳነምሕረት እየተመላለሰ ሱባኤ እየገባ ጸሎት ያደርግ ነበር፤ በዛሬዋ ቀን ይህ አባት ሲሞት በኢትዮጵያ ሰማይ ላይ ከዋክብት ሲበታተኑ ሲራወጡ ታየ የተጉለቱ አባ በላይነህም ይህንን ምልክት አይቶ የአባ ኤልያስን መሞት ተረዱ ወደ መናገሻ ቢመጡ ሞቶ ተቀብሮ አገኙት፤ጎንደር ላይም በተመሳሳይ ከዋክብት ሲበታተኑ እነ አለቃ ወልደ ቂርቆስ በአይኔ አየሁ ሲሉ መስክረዋል ይላል መርስሄ ሐዘን ''ትዝታዬ ስለራሴ የማስታውሰው" በሚለው መጽሐፋቸው የከተቡልን። የሚገርመው ይህ አባት ከቤተመንግስት ወገን ሲሆን ተድላ ደስታን ንቆ 400 ዓመት በቅድስና በተጋድሎ የኖረ መናገሻንና እንጦጦ ኪደነምሕረትን በጸሎቱ የባረከ ይህንን የመሰለ ቅዱስ አለመዘከሩ ታሪኩ አለመጻፉ የታሪክ ጸሐፍት ወዴት አሉ ሊቃውንቱስ ወዴት ተደበቁ ያሰኛል፤ ከእመቤታችንንና ከመናገሻው አባ ኤልያስ በረከት ያሳትፈን። አሜን !!!

Читать полностью…

የእመቤታችን አንድምታ ወዳሴ ቅዳሴ

"እግዚአብሔር የሰው ልጅን ያዳነበት መንገድ በዕለተ ዐርብ በመሰቀሉና መከራን በመቀበሉ ብቻ የሚመስለውና ከነገረ መስቀሉ ውጪ ያለው ጉዳይ የሚጠቅም የማይመስለው ሰው ካለ ነገረ ድኅነትን ሙሉ በሙሉ አልተረዳም፡፡ እንደዚያ ቢሆን ኖሮ እግዚአብሔር በድንግል ማርያም ተፀንሶ ተወልዶ ሠላሳ ዓመታትን መቆየት ሳያስፈልገው ልክ የመጀመሪያውን አዳም እንደፈጠረው የሠላሳ ዓመት የሆነ ሥጋንና ነፍስን ለራሱ ፈጥሮ መለኮቱን አዋሕዶ ሰው መሆን ይችል ነበር፡፡ ይህንን ቢያደርግም ሦስት ዓመታት በምድር ላይ አስተምሮ በጊዜው ተሰቅሎ የማዳን ሥራውን መፈጸም ይችል ነበር፡፡

እርሱ ግን ማዳኑን የጀመረው በማሕፀን ከመፀነስ ነበር፡፡
አረጋዊው ስምዖን ‘ዓይኖቼ ማዳንህን አይተዋል’ እንዳለ ማዳኑንም የጀመረው ሕፃን ሆኖ በመታቀፉ ነው፡፡ ሉቃ. ፪፥፴ የጌታ የማዳን ሥራ ወሳኙ ታሪክ ከመስቀሉ ጋር በችንካር የታሰረበት ብቻ ሳይሆን በድንግል ማርያም እቅፍ በፍቅር የታሰረበት ቅፅበትም ነው፡፡ ክርስቶስ ሊያስታውሰው የማይፈልገው የልጅነት ሕይወት ያለው አይደለምና ስለ ክርስቶስ የሚሰብኩም ሁሉ ይህንን ድንቅ የሕፃንነት ጊዜውንና ያደገበትንሁኔታ ቸል ሊሉ አይገባም፡፡

ክርስቶስን ‘በመስቀል ላይ እንደተሰቀለ ሆኖ’ በሰዎች ልቡና እንዲሣል በመጀመሪያ በድንግል ማርያም እቅፍ እንደተወለደ ሆኖ መሣል ይገባዋል፡፡ ልብህ ውስጥ ሳይወለድ የሚሰቀል ክርስቶስ ካለ ለወለደችው እናቱና ለድንቅ ልደቱ ዋጋ ልትሠጥ አትችልም፡፡

መስቀል መሸከሙ ዘልቆ የሚሰማህ በልጅነቱ ያቀፈችውን ድንግል ማየት ስትችል ነው፡፡ ሐሞትና ከርቤ መጠጣቱ የሚያስለቅስህ ድንግልናዊ ወተትን ካጠባችው እናቱ ጋር አብረህ ስትሆን ነው፡፡ አልፋና ኦሜጋ እኔ ነኝ ላለው ክርስቶስ በምድር ላይ በቆየበት መዋዕለ ሥጋዌው አልፋው ድንግል ማርያም ስትሆን ኦሜጋው መስቀል ነበር፡፡ የተሰቀለ ቀን ብቻ አይተህ ልታውቀው አትችልም፡፡ ሁለተኛ አዳምነቱ ዘልቆ የሚሰማህ ወደ ልደቱ ስትመለስ ነው፡፡ የሰው ልጅ ቁስልም የሻረው ጌታ ሊወለድ ካለበት ቅፅበት ጀምሮ ነው፡፡

በገነት ዛፎች መካከል አንድ የረከሰ መልአክ እና አንዲት ሴት ተነጋግረው ተስማምተው ያበላሹትን የሰው ልጅ ታሪክ ድጋሚ ሊጽፈው የፈቀደው እግዚአብሔር በተቀደሰ መልአክና በአንዲት ሴት መካከል ንግግር አስጀመረ፡፡

ሰይጣን በምድር ከሚርመሰመሱ አራዊት መካከል
ተንኮለኛውን እባብን መርጦ ሔዋንን በማሳመን የሰው ልጅ ከገነት አስወጥቶታል፡፡ እግዚአብሔር ደግሞ በሰማያት ከሚያመሰገኑ ብርሃናዊያን መላእክቱ መካከል ከዋነኞቹ አለቆች አንዱን ቅዱስ ገብርኤልን መርጦ ድንግል ማርያምን እንዲያበሥራት ላከ፡፡

ሁለተኛይቱ ሔዋን ድንግል ማርያም ከመጀመሪያይቱ ሔዋን እጅግ በብዙ ነገሮች ትለያለች፡፡ ሔዋን የተቀደሰው ገነት ውስጥ ተፈጥራ ፈጣሪዋን የበደለች ስትሆን ድንግል ማርያም ግን በእርግማን በረከሰው ምድር ላይ ተፈጥራ የተቀደሰች ናት፡፡

የቀደመችው ሔዋን በገነት መካከል ሥራ ፈትታ የምትመላለስና የእባብን ድምፅ ሰምታ አዳምን ለሞት የምትዳርግ ስትሆን አዲሲቱ ሔዋን ግን ራስዋ ምድራዊት ገነት ሆና አዳምን ያስገኘች ናት፡፡ ከዚህች ገነት ተፀንሶ የተወለደው ሁለተኛው አዳም እንደ ቀድሞው አዳም ተባርሮ የወጣ ሳይሆን ‘ሙሽራ ከጫጕላው እልፍኝ እንደሚወጣ’ ከእርስዋ የወጣ ሙሽራ ነው፡፡

ይህችኛይቱ ሔዋን የሰው ልጅ ቃልዋን ቢሰማ ‘የሔዋንን ቃል ሰምተሃልና የተረገምህ ትሆናለህ’ ተብሎ የሚሞትባት ሔዋን አይደለችም፡ ፡ ይህች ድንግል ቃልዋን ብንሰማ የምንባረክባት ከአንደበትዋ የሚወጣው ቃል እንደ ሔዋን ካለመታዘዝ ፍሬ እንድንበላ ሳይሆን ‘የሚላችሁን ሁሉ አድርጉ’ የሚል የሚያድን ቃል ነው፡፡ ዮሐ. ፪፥፭

ያችኛይቱ ሔዋን ከአዳም ተገኝታ የተሠራችና አዳም ወደ
እርስዋ እያየ ‘ይህች አጥንት ከአጥንቴ ይህች ሥጋ ከሥጋዬ ናት’ የሚላት ናት፡፡ ይህችኛይቱ ሔዋን ድንግል ማርያም ግን ከአዳም የተገኘች ሳትሆን አዳምዋ ክርስቶስ ሥጋው በጅራፍ ግርፋት ሲቆስልና አጥንቶቹ ሲቆጠሩ በጭንቀት እያየች ‘ይህ አጥንት ከአጥንቴ ነው ፤ ይህ ሥጋም ከሥጋዬ ነው’ የምትል ሔዋን ናት፡፡

የቀደመችዋ ሔዋን አዳምዋ በእርስዋ ምክንያት ጠፍቶ ‘አዳም ሆይ ወዴት ነህ?’ ተብሎ ሲፈለግ በዛፎች መካከል ሆኖ ከአባቱ ከእግዚአብሔር ‘ፈርቼ ተሸሸግሁ’ የሚል አዳም ሲሆን ሁለተኛይቱ ሔዋን ግን አዳምዋን ፍለጋ የምትጨነቅና ወዴት ነህ? ስትለው አዳምዋ ‘በአባቴ ቤት እኖር ዘንድ እንዲገባኝ አታውቁምን’ ብሎ የሚመልስላት ከአባቱ እቅፍ ያልተለየ አዳም እናት ናት፡፡

ለድንግል ማርያም ክርስቶስ ከእርስዋ የተገኘ አዳምዋ ብቻ ሳይሆን በቀናተኞቹ ቃየኖች አይሁድ በግፍ የተገደለባት አቤልዋም ጭምር ነው፡፡ ልዩነቱ የአቤል ደም ወንድሙን የሚከስስ ደም ሲሆን የእርስዋ ልጅ የክርስቶስ ደም ግን ‘ከአቤል ደም ይልቅ የሚሻለውን የሚናገር’ ‘ከኃጢአት ሁሉ የሚያነጻ ደም’ ነው"

Читать полностью…

የእመቤታችን አንድምታ ወዳሴ ቅዳሴ

ቅዱስ ኤፍሬም እንዲ አለ ፦
 
የቀደመችው ሔዋን የወለደችው ነፍሰ ገዳዮን ቃየንን ነበር ፤ ማርያም ግን ሕይወትን የሚሰጥን ልጅ ወለደች። የቀደመችው ሔዋን የገዛ ወንድሙን ደም የሚያፈስስ ቃየንን ወለደች ፤ ድንግል ማርያም ግን ለወንድሞቹ ደሙን የሚያፈስሰውን ክርስቶስን ወለደች።

የመጀመሪያይቱ ሔዋን ልጅዋን ቃየንን በምድር እርግማን ምክንያት ሲፈራና ሲቅበዘበዝ አየችው ፤ ድንግል ማርያም ግን ልጅዋ ክርስቶስ እርግማንን  ተሸክሞ ወሰዶ በመሰቀሉ ሲቸነክረው አየች ። 
 
አባ ጊዮርጊስ እንዲ አለ ፦

ለእኔስ ድኅነት ድንግል ማርያም ትወለድ ዘንድ ሔዋን እንኳንም ከዕፀ በለስ ፍሬ በላች አልሁ። ሔዋን የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ጠብቃ ቢሆን በገነት ፍሬዎች እየተደሰተች ብቻዋን ከባልዋ  ጋር በኖረች ነበር ።

ማርያምም የኃጢአትዋን ፍዳ ለማስቀረት ከልጅ ልጆችዋ ባልተወለደች ነበር ። ያሳታት እባብም መርዙ በክርስቶስ በመለኮቱ ጨውነት አልጫ ባልሆነ ነበር ።

ፍቅሯን በልቦናችን ጣዕሟን በአንደበታችን እናታች እማምላክ ወላዲተ አምላክ ታሳድርብን።

Читать полностью…

የእመቤታችን አንድምታ ወዳሴ ቅዳሴ

ድንግል ሆይ

👉አንቺን  ያሳደደሽ  ሔሮድስ እኔን የማያሳድደኝ ጌታ  በእቅፌ  ስለሌለ ነዉ።

👉 እኔ በልቤ  ያነገሥሁት  'የተወለደውን የአይሁድ  ንጉሥ ' ስላልሆነ  ሔሮድስ  ከኔ ጋር ጠብ የለዉም ።

👉 የሔሮድስን ሥልጣን አደጋ ላይ  የሚጥል  ንጉሠ ሰላም  በእኔ እቅፍ የለም።

👉 አሁን ግን ፍቀጂልኝና  ሔሮድስን ማስደሰት ትቼ  ልጅሽን  በልቤ  ልቀበለው ።

👉 የልቤን  ክርስቶስ  ሔሮድስ  እንዳይገድልብኝ  እኔም  እንደ አንቺ ልሰደድ ።

👉 እርሱን  አቅፌ  መከራ ቢደርስብኝ  እንኳን  ጽናት እንደማገኝ በአንቺ አይቻለሁና  የልጅሽን ፍቅር  በልቤ  አኑሪልኝ።

የ 💕እመቤታችን 💕 አማላጅነት  ረድኤት በረከት  አይለየን

Читать полностью…

የእመቤታችን አንድምታ ወዳሴ ቅዳሴ

የተመረጽሽ 

ድንግል 

እመቤቴ ማርያም ሆይ 

👉ምን ያህል ክብር ተሰጠሽ የያዕቆብ ልጅ ምን ያህልስ ጸጋ ተቀበልሽ፡፡ የእስራኤል ልጅ ሆይ ምን ያህልስ ምስጋና ከበበሽ የይሁዳ ልጅ ሆይ ምን ያህል ባለሟልነት አገኘሽ፡፡

 👉 እነሆ ከኪሩቤል ትበልጫለሽ ከሱራፌልም ከፍ ከፍ ትያለሽ ከትጉሃን የሰማይ መላእክትም ሁሉ በመዓረግ አንቺ ትበልጫለሽ የድንግልናሽም ምስጋና ለዘወትር አይፈጸምም፡፡

👉 በዓለም ሁሉ ትመሰገኛለሽ በየዘመኑም ሁሉ ትወደሻለሽ፡፡ በየጊዜው ንጽሕት ነሽ፡፡ በየስፍራው ሁሉ ቅድስት ነሽ፡፡ የአንደበቱም ሁሉ ቡረክት ነሽ ከላህይሽም የሚያምር የለም፡፡ የንጋትም ውጋጋን ቢሆን፡፡

👉 ከቁመትሽም የሚያምር የለም ሰሌንም ቢሆን የሊባኖስ ዛፍም ቢሆን፡፡ ከጥርሶችሽ የሚነጣ የለም፡፡ ወተትም ቢሆን በረድም ቢሆን፡፡ ከዓይንሽም ፀዳል የሚበራ የለም፡፡ በሰማይ ፊት ለፊት የሚያበራ የወርቅ ዘውድም ቢሆን፡፡

👉 ካፍንጫሽም ዕፁብ የሚሸት የለም፡፡ ከልብስሽም ሽታ የሚበልጥ የለም፡፡ ከልበኔም ቢሆን ሐንክሶም ቢሆን፡፡ አስጰዳቶስም ናርዱም ቢሆን፡፡ ዋጋውም የበዛ ሌላ ሽቱ ቢሆን፡፡

👉ሰውነትሽ ሁሉ ያማረ የተወደደ ነው፡፡ በመንፈስ ቅዱስ ኃይል የተጋረደ ነው፡፡ ገላግልቶቿን በክንፎቿ የምትታቀፍ ንጽሕት ርግብ ሆይ፡፡ ክብርሽን ገናንነትሽን እናገር ዘንድ ፍቅርሽ ያነቃቃኛል፡፡ ወለላውን ማር ለመቅዳት ለምን እሰንፋለሁ፡፡ ለሚበላው የጣፈጠ ነው፡፡ ወተቱንስ ለመቅዳት ለምን እሰንፋለሁ፡፡ ለሚጠጣው ያማረ የተወደደ ነውና፡፡

👉የትንቢት አበባ ለማሽተት ለምን እሰንፋለሁ፡፡ የመዓዛው ሽታ ላፍንጫ ያማረ ነውና፡፡ የሃይማኖት ሽቱ ለማጣፈጥ ለምን እሰንፋለሁ፡፡ እርሱን በመንካት እጆቼ ይሻተታሉና፡፡ 

የ💕እመቤታችን 💕
አማላጅነት አይለየን

Читать полностью…

የእመቤታችን አንድምታ ወዳሴ ቅዳሴ

ቅዱስ ኤፍሬም እንዲ አለ ፦

የቀደመችው ሔዋን የወለደችው ነፍሰ ገዳዮን ቃየንን ነበር ፤ ማርያም ግን ሕይወትን የሚሰጥን ልጅ ወለደች። የቀደመችው ሔዋን የገዛ ወንድሙን ደም የሚያፈስስ ቃየንን ወለደች ፤ ድንግል ማርያም ግን ለወንድሞቹ ደሙን የሚያፈስሰውን ክርስቶስን ወለደች።

የመጀመሪያይቱ ሔዋን ልጅዋን ቃየንን በምድር እርግማን ምክንያት ሲፈራና ሲቅበዘበዝ አየችው ፤ ድንግል ማርያም ግን ልጅዋ ክርስቶስ እርግማንን ተሸክሞ ወሰዶ በመሰቀሉ ሲቸነክረው አየች ።

አባ ጊዮርጊስ እንዲ አለ ፦

ለእኔስ ድኅነት ድንግል ማርያም ትወለድ ዘንድ ሔዋን እንኳንም ከዕፀ በለስ ፍሬ በላች አልሁ። ሔዋን የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ጠብቃ ቢሆን በገነት ፍሬዎች እየተደሰተች ብቻዋን ከባልዋ ጋር በኖረች ነበር ።

ማርያምም የኃጢአትዋን ፍዳ ለማስቀረት ከልጅ ልጆችዋ ባልተወለደች ነበር ። ያሳታት እባብም መርዙ በክርስቶስ በመለኮቱ ጨውነት አልጫ ባልሆነ ነበር ።

ፍቅሯን በልቦናችን ጣዕሟን በአንደበታችን እናታች እማምላክ ወላዲተ አምላክ ታሳድርብን።

Читать полностью…

የእመቤታችን አንድምታ ወዳሴ ቅዳሴ

የሚከተሉትን ጥያቄዎች በትክክል መልሱ

መልሱን በኮሜንት መስጫው አስቀምጡ

1 የአለም ብርሃንን ያስገኘችልን ቅድስት ___ ትባላለች

2 በረት የከብቶች ማደሪያ ሁኖ ሳለ ለምን እጅጉን ከበረ ?

3 የዛሬዉ ቀን ታህሣሥ 19 አመታዊው በዓል የማን እና ለምን ይከበራል ?

ሁላችሁም ተሳተፉ !!!

መልስ በ comment ላይ አስቀምጡ።

Читать полностью…

የእመቤታችን አንድምታ ወዳሴ ቅዳሴ

💓💔እግዚአብሔር💔❤

ዘላለማዊ ኃይሉንና አምላክነቱን ለዓለም ከገለጸበት ታላቅ ሥራ መካከል በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያም የገለጸው ድንቅ ሥራው በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ቀዳሚውን ሥፍራ ይይዛል፡፡ ይህንን ኹኔታ ድንግል ማርያም ‹‹ብርቱ የኾነ እርሱ ታላቅ ሥራን በእኔ አድርጓል፤ ስለዚህም ፍጥረት ኹሉ ያመሰግኑኛል›› /ሉቃ.፩፥፵፱/ በማለት ገለጸችው፡፡
ቅድስት ኤልሳቤጥም ‹‹የጌታዬ እናት›› አለቻት /ሉቃ.፩፥፵፫/፡፡ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ‹‹ከሴቶች መካከል ተለይተሽ የተባረክሽ ነሽ›› አላት /ሉቃ.፩፥፳፰/፡፡ ቅዱስ ዳዊት ደግሞ ‹‹ልጄ›› ይላታል /መዝ.፵፬፥፱/፡፡ ሰሎሞንም ‹‹እኅቴ›› ይላታል /መኃ.፭፥፩/፡፡ ለወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስም እናት ኾና ተሰጥታዋለች /ዮሐ.፲፱፥፳፮/፡፡ ይህን ድንቅ ምሥጢር ውስንና ደካማ የኾነ አእምሮ ሊገነዘበው ከሚችለው በላይ ነው፡፡
ቅዱስ አግናጥዮስ ዘአንጾኪያ ለኤፌሶን ክርስቲያኖች በጻፈው መልእክቱ እንደገለጸው ‹‹የቅድስት ማርያም ዘለዓለማዊ ድንግልና፤ አማኑኤልን መውለዷና የማይሞተው ጌታ መሞቱ›› እነዚህ ሦስቱ ከዚህ ዓለም ጥበበኞችና ገዢዎች የተሰወሩ ምሥጢራት ናቸው፡፡ ቅዱስ አግናጥዮስ ‹‹እነዚህ ድንቅ ምሥጢራት በራሳቸው ከንግግርና ከቋንቋዎች ኹሉ በላይ ኾነው የሚነገሩ በእግዚአብሔር የዝምታ መጐናጸፊያ የተጠቀለሉ ድብቅና ጣፋጭ ምሥጢሮች ናቸው›› ይላል፡፡
የእመቤታችን ምስጋናዋ የበዛለት ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊም ‹‹አቤቱ መሰንቆ ልቡናዬን አነቃቃ፤ የልቤንም እንዚራ፡፡ ድምፁን ከፍ አድርጎ የዳዊት ልጅ የኾነችውን፣ የጌታውን እናት ድንግል ማርያምን ያመሰግናት ዘንድ፤ ለዓለም ሕይወት የሚሰጠውን የወለደች እናቱ የኾነች እርሷን ከፍ ከፍ ያደርጋት ዘንድ›› ብሏል፡፡ በሌላም አንቀጽ ደግሞ ‹‹ከሕሊናት ኹሉ በላይ ለኾነ ለዚህ ነገር አንክሮ ይገባል፡፡ ምድራዊት ሴት ፈጣሪዋን ወለደችው፤ እርሱም እናቱን ፈጠረ›› አለ፡፡ ስለእነዚህ ነገሮች ኹሉ ምን ማለትን እንችላለን? እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ስለ ድንግል ማርያም ያልተናገረበት ጊዜ፤ ያላናገረው ቅዱስ እንደሌለ እንመለከታለን፡፡

አማላጅነቷ አይለየን!!!

@uraman4u12
@uraman4u12
@uraman4u12

Читать полностью…

የእመቤታችን አንድምታ ወዳሴ ቅዳሴ

✝አዲስ ማስታወቂያ ከማኅሌታይ ያሬድ ፕሮሞሽን ✝
ሰላም እንደምን ሰነበታችሁ የልዑል እግዚአብሔር ቤተሰቦች የእናታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ልጆች

✝ መንፈሳዊ ቻናል ላላቹ በሙሉ አዲስ ጂፒ ስለጀመርን በየቻናላቹ መጠን እንድትመዘገቡ በልዑል እግዚአብሔር ስም ጋብዘኖታል!!!

✝ ቻናላቹን ከስር በተዘረዘረው ደረጃ ማስመዝገብ ትችላላቹ!

⓵.ደረጃ ከ150-500
⓶.ደረጃ ከ500-1000/1k
⓷.ደረጃ ከ1k-5k
⓸.ደረጃ ከ5k-10k
⓹.ደረጃ ከ10k-20k
⓺.ደረጃ ከ20k-30k

✝ በዚህ መሠረት ቻናላቹን መመዝገብ ስለጀመርን እንድትመዘገቡ እንጠይቃለን!

࿇ ለመመዝገብ👇
📨 @habmisget
࿇ ማኅሌታይ ያሬድ ስለመረጡ እናመሠግናለን
✅ @habmisget

share አድርጉት ቻናል ላላቸው በሙሉ
@mekra_abaw
@yaredpromotion

Читать полностью…

የእመቤታችን አንድምታ ወዳሴ ቅዳሴ

💚በአጭር ጊዜ በብዙ የጥበብ አፍቃሪያን
ተወዳጅነትን ያገኘው የጥበብ ቻናል
እነሆ ብለናችኋል።
ሁሉንም ጥበብ ቢጠይቁ ካሉበት ይደርስዎታል
መርጌታ ነቢየ ልዑል ዘብሔረ ቡልጋ


ሰማያዊውን በመጫን ይቀላቀሉን
👇👇👇👇👇👇👇👇
@Mergetanebiyeliul
@Mergetanebiyeliul
Mergetanebiyeliul

Читать полностью…

የእመቤታችን አንድምታ ወዳሴ ቅዳሴ

ማርያም ንጽሕት ድንግል
ወላዲተ አምላክ ማእምንት
ሰአሊተምህረት ለዉሉደሰብእ
ሰአሊ ለነ ሀበ ክርስቶስ ወልድኪ
ይስረይ ኃጢአተነ ሰአሊ ለነ ቅድስት

ህርያቆስ እና ኤፍሬም
እንዳመሰገኑሽ
እኔም ታጥቄ
ድንግል ላገልግልሽ

ቅዱስ ዳዊትም በበገና
እንደጠራ አንቺን ማርያም ሆይ
ልጥራዉ ስምሽን

Читать полностью…

የእመቤታችን አንድምታ ወዳሴ ቅዳሴ

♥️♣️"ልጁን ስለሰጠን የጌታ እናት የምስጋና ጸሎት በገና ቀን"

♥️♣️♥️♣️♥️♣️♥️♣️♥️♣️♥️♣️

. .

በደላችንን ይምረን ዘንድ ጸሎታችንን ወደ እግዚአብሔር እና ወደ ልጅሽ ዙፋን አንሺ። ቅዱስ ስምህን ለሚያከብሩ ሁሉ በእምነት እና በፍቅር ተአምር የሚሰሩ ጌታ ሆይ አንተን የሚያመልኩ ሁሉ ጸጋውን ይጨምርላቸው። በጌታ ምህረትን ለማግኘት የተገባን እንዳልሆንን እና ለዚህም አንተን እንፈልግሃለን አንተ ረዳታችን እና ፈጣን ረዳታችን ነህና።
ወደ አንተ የምንጸልይ እኛን ስማ; ሁሉን ቻይ በሆነው መሸፈኛህ ጠብቀን እና ነፍሳችንን እንዲጠብቅ አምላክ ልጅህን ለምነው።

የተሳሳቱትን በትክክለኛው መንገድ ምራ ፣ አዛውንቶችን ደግፈ ፣ ሕፃናትን ጠብቅ እና ሁላችንንም በምህረትህ ጠብቀን። ሁላችንን ከሀጢያት ጥልቅ አውጣን እና የልባችንን አይኖች ለድነት ፍለጋ ያብራልን።

ላንቺ እመቤቴ የሰማያዊ ክብር የምድርም ተስፋ ነሽ።

በአንተ በመጠበቅ እና በረድኤትህ ተጠብቀንና መዳንን፣ ክብርን፣ ምስጋናን፣ ምስጋናን እና አምልኮን ስለ ሁሉም ነገር እናምጣ እና ከፍ ከፍ እናድርገው፣ ሁሉን ሰጪና ፈጣሪ፣ አሁንም እና ለዘላለም ለዘመናት ምስጋና ይሁን ኣሜን።

መልካም ገና ለሁላችሁ ከክርስቶስ ጋር እና ከክርስቶስ ጋር ሙሉ

Читать полностью…

የእመቤታችን አንድምታ ወዳሴ ቅዳሴ

📕«#ወር በገባ በ21 #እመቤታችን ድንግል ማርያም ናት»🌹

🌹=>የአምላክ እናቱ እመ-ብርሃን ድንግል ማርያም:-
🌹=»በ3 ወገን (በሥጋ: በነፍስ: በልቡና) ድንግል
🌹=»በ3 ወገን (ከኀልዮ: ከነቢብ: ከገቢር) ንጽሕት
🌹=»ሳትጸንስ: በጸነሰች ጊዜና ከጸነሰች በሗላ ድንግል
🌹=»ጌታን ሳትወልድ : በወለደችው ጊዜና ከወለደችው በሗላ ድንግል ስትሆን እናትም ድንግልም መሆኗን አምነን እንመሰክራለን::

💖+እመቤታችን ከፍጥረት ሁሉ በላይ ክብርትና ንዕድ ናት:: ሊቃውንት አበው እንዳስተማሩን በዚህ ዕለት እንዲህ ብለን እንጸልያለን::
"ረስዪ ፍና ትሕትና አእጋርየ ይሑሩ:
ትዕቢትሰ ለአምላክ ጸሩ"
(እመቤቴ ሆይ ትዕቢትን አምላክ ይጠላልና እግሮቻችን በትሕትና እንዲሔዱ አድርጊ) አሜን ፫🙏

Читать полностью…

የእመቤታችን አንድምታ ወዳሴ ቅዳሴ

⛪️🌿 " " ⛪️🌿

🍒ህዳር 21 የጥንታዊቷ ኢትዮጵያ ሀገራችን መናገሻ ከተማ በሆነችው አክሱም ከተማ ውስጥ በምትገኘው በርዕሰ አድባራት ወገዳማት አክሱም ጽዮን ማርያም ቤተክርስቲያን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እምነት ተከታዮች ዘንድ ታላቅ የሆነ ሃይማኖታዊ ሥርዓት በታላቅ መንፈሳዊ ሥነ ሥርዓት ይፈጸማል ።

የኅዳር ጽዮን ማርያም በዓል ስለ 8 ዓበይት ነገሮች ይከበራል ።

1. ታቦተ ጽዮን በምርኮ በሄደችበት በሀገረ ፍልስጤም ዳጎን የተባለ የአህዛብን ጣኦት አድቅቃ በድል የተመለሰችበትን ዕለት በማሰብ ። 1ኛ ሳሙ 1– 6

2. ታቦተ ጽዮን ንጉሥ ሰሎሞን ወደ ሠራላት ቤተመቅደስ በክብር የገባችበትን ዕለት በማሰብ ። 1ኛ፣ ነገ 8 ፣ 1–66

3. ታቦተ ጽዮን በንግሥት ሳባ ልጅ በቀዳማዊ ምኒልክ አማካኝነት ወደ ኢትዮጵያ ምድር የገባችበትን ዕለት በማሰብ ።

4. የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት በአብርሀ ወአጽብሃ ዘመነ መንግሥት በኢትዮጵያ ብሔራዊ ሃይማኖት መሆኗ የታወጀበት ዕለት በመሆኑ ።

5. በብሉይ ኪዳን መስዋዕተ ኦሪት /የእንሳት ደም ከሚሰዋባት ሙኵራብ / ወደ ሀዲስ ኪዳን/ አማናዊው በግ የኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ስጋውና ክቡር ደሙ የሚፈተትበት /" ጽዮን ማርያም ተብላ ወደ ቤተክርስቲያንነት የተቀየረችበት ዕለት በመሆኑ ።

6. የቀደሙ ነብያት ስለእመቤታችን በተለያየ ህብረ አምሳል ያዩበት ፤ ለምሳሌ ነብዩ ዕዝራ በሃገር መንፈሳዊት ፣ ሕዝቅኤል በተዘጋች ቤተመቅደስ ፣ ዘካርያስ በተቅዋመ ወርቅ ወዘተ ያዩበትን ዕለት በማሰብ ።

7. በአረመኔዋ ዮዲት ጉዲት ከመፍረሱ በፊት ፤ በሁለቱ ደጋግ ወንድማማች የኢትዮጵያ ነገሥታት በነበሩት በዘመነ አብርሀ ወአጽብሃ በወርቅና በዕንቁ የተሠራው ባለ አሥራ ሁለት ክፍሉ ቤተመቅደስ ሥራው ተጠናቅቆ ለመጀመሪያ ጊዜ ቅዳሴ ቤቱ የተከበረበትን ዕለት በማሰብ ።

8. በዮዲት ጉዲት መነሳት ምክንያት ለ600 ዓመታት ያህል ወደ ዝዋይ ገዳም ተሰድዳ የነበረችው ታቦተ ጽዮን የስደት ዘመኗን ፈጽማ ወደ መንበረ ክብሯ አክሱም ጽዮን የተመለሰችበት ዕለት በመሆኑ ፤ ይህንና ይህን በመሳሰሉ ምክንያቶች የህዳር ጽዮን በዓል በታላቅ ድምቀት ይከበራል🙏❣️🙏

Читать полностью…

የእመቤታችን አንድምታ ወዳሴ ቅዳሴ

የተመረጽሽ 

ድንግል እመቤቴ ማርያም ሆይ


👉 ይህ የተደነቀ ነው፡፡ በሁሉም ዘንድ መንክር ነው፡፡ በአምላክ ዘንድ ግን አይደነቅም፡፡

👉 በሰው ልጆች ዘንድ የተደነቀ ነው፡፡ ምሕረቱ እንደ ባሕር በሆነው ዘንድ ግን አይደነቅም በፍጡር ዘንድ ድንቅ ነው በፈጣሪ ዘንድ ግን አይደነቅም፡፡

👉 ድንግል ሆይ የኔ ምሕረት በልጅሽ ዘንድ ስላንቺ አይደነቅም ስለ ስምሽም የኔ ይቅር መባል በልጅሽ ዘንድ አይደነቅም ስለ ጸሎትሽም የኔን ኃጢአት ማቀለል በልጅሽ ዘንድ አይደነቅም፡፡

👉 ስለ ልመናሽም የኔን ዕዳ በደል ማቅለል በልጅሽ ዘንድ አይደነቅም ባንቺ እታመናለሁ፡፡ በዚህ ዓለም ከፀብ ከክርክር ከሞት ታድኝኝ ዘንድ በሚመጣውም ዓለም ማዕበል ሞገድ ከሚፈላው የእሳት ባሕር ታድኝኝ ዘንድ፡፡

👉 ድንግል ሆይ እታመንሻለሁ ከተሠወረው መከራ በግልጽም ከሚመጣብኝ ጥፋት ሁሉ በዚህ ዓለም እንድታድኝኝ በሚመጣውም ዓለም ከገሃነመ እሳት ጥርስ ማፋጨት ጽኑ ልቅሶም ካለበት ከሚያስጨንቅ መቅሠፍት ትሠውሪኝ ዘንድ እኔም ባንቺ አማላጅነት በልጅሽም ምሕረት የታመንሁ ነኝ፡፡ በፈረሰኞች ሰልፍ በሠረገላም መንኮራኩር የምታመን አይደለሁም፡፡ ባንቺና በልጅሽ ብቻ እታመናለሁ እንጂ፡፡

👉 ሰይፍ በማስላት ፍላፃ በማትባት ጦር በመወርወር ቀስት በመገተር የምታመን አይደለሁም በጸሎትሽ ረዳትነት በልጅሽ ብርታት እታመናለሁ እንጂ፡፡
፰. በመዝሙር እንደተባለ በቀስቴ የምታመን አይደለም ጦሬም አላዳነኝም ከቀኝ ከፊትህ ብርሃን በቀር ደግሞ እንዲህ አለ የፈረስ ኃይል አይፈቅድም፡፡ በሰው ጭንም ደስ አይለውም እግዚአብሔርን በሚፈሩትና ቸርነቱን ደጅ በሚጸኑ ደስ ይለዋል እንጂ፡፡ ነፍሴ በእግዚአብሔር ታመነች ከጧት እስከ ሌሊት እስራኤል በእግዚአብሔር ታመነ።

Читать полностью…

የእመቤታችን አንድምታ ወዳሴ ቅዳሴ

💛 ድንግል_ሆይ ከአይኖችሽ ፈሶ በተወዳጁ ልጅሽ
ፊት ላይ የወረደውን መሪር እንባ አሳስቢ 🙏

+ #እመቤታችንም ከልጇ ከወዳጇ #ከኢየሱስ_ክርስቶስ ጋር #ትዕማን ወደምትባል አንዲት ከበርቴ ባለሀብት ቤት ሄዳ ቁራሽ እንጀራንና ለልጇም ጥቂት ወተትን ለመነቻት፡፡

+ ያቺ ክፉ ሴት ግን ልብን በሀዘን የሚሰብር ክፉ ንግግርን ተነጋረቻት፡፡ ጻድቅ ዮሴፍም ‹‹እንግዳን ካለ ይሰጡታል ከሌለ በሰላም ይሸኙታል እንጂ ለምን ክፉ ንግግርን ትናገሪያታለሽ?›› እያለ ሲነጋገሩ አሽከሯ ኮቲባ የእመቤቷን ቁጣ ሰምታ መጥታ ጌታችንን ከመሬት ላይ ጥላ እንደ ድንጋይ አንከባለለችው፡፡

+ እመቤታችንም እጅግ ደንግጣ እያለቀሰች ልጇን ፈጥና ልታነሣው ስትል ዮሴፍ ‹‹ተይው አታንሽው ኀይሉን ያሳይ›› አላት፡፡

+ ያንጊዜም ትዕማንን ምድር አፏን ከፍታ ዋጠቻት፡፡ ገረዷ ኮቲባም በለምጽ ተመታች፡፡ በቤታቸውም ውስጥ በሕይወት የቀረ የለምና የሩቅ ቤተሰቦቿም ጦጣ ሆነው ከተራራ ወደ ተራራ ሸሹ፡፡ እመቤታችን ፣ ዮሴፍና ሰሎሜም በትዕማን ቤት 6 ወር ከተቀመጡ በኋላ መልአኩ ተገልጦ ከዚያ እንዲወጡ አዘዛቸውና ወጡ፡፡

+ _______________________
🙏 አዘክሪ ድንግል አንብዐ መሪረ
ዘውኅዘ አምአእይንትኪ ወወረደ ዲበ ገጸ ፍቁር ወልድኪ 🙏

🍂 #ድንግል_ሆይ ከአይኖችሽ ፈሶ በተወዳጁ ልጅሽ
ፊት ላይ የወረደውን መሪር እንባ አሳስቢ 🙏

Читать полностью…

የእመቤታችን አንድምታ ወዳሴ ቅዳሴ

...የእግዚአብሔር እናት በስዕሉ ያሉ አይኖቿ ለምን ያለቅሳሉ ????
🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺☦️🌺🌺🌺🌺🌺🌺
እንባዋ ከባድ እንባ ነው ምክንያቱም ሰዎች እንደ እናት ባይወዷትም፣ ሁላችንንም እንደ ልጅ ትወደናለች፣ ምክንያቱም እሷ የክርስቲያን ሀገር እናት ነች።

የእግዚአብሔር እናት ታለቅሳለች ምክንያቱም በተለየ መንገድ መኖር እንዳለብን ታውቃለች። ልጇ በጣም ጣፋጭ የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ ልጇ ስለ እኛ መዳን በመስቀል ላይ ሞተ። ሲደበደብ፣ ሲሳለቅበት፣ ሲተፋበት አየችው። ለእኛ ሲል ሲሰቃይ አይታለች። እኛ ደግሞ በመዳን መንገድ ከመሄድ ይልቅ ወደ እግዚአብሔር እና ወደ ሰማያዊ ነገሮች ትንሽ እንደምንመለከት እና በሥጋዊ ምኞት ራሳችንን እንደምንጎተት ታያለች።

ወደ ወላዲተ አምላክ እንሩጥ። ሁሉንም ነገር ታውቃለች። በእምነት እንጂ ወደ እመቤታችን እንሩጥ።

በክርስቶስ የምናምን፣ የቤተክርስቲያን ህያዋን አባላት የሆንን እና በወላዲተ አምላክ የምናምን እናታችን እንደ እናታችን እንቁጠረን፣ በድፍረት ወደ እርሷ እንሩጥ። እንሩጥ እና እንጸልይላት።

(አርኪማንድራይት ስምዖን ክሪዮፖሎስ)

🌹🌹🌹🌹🌹🌹🙏🏻🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
"እናቴን ማልቀስ አቁም በዓይንሽ የሚወለደው የፈውስ ምንጭ አይገባኝምና....እኔ ብቻዬን ነኝና እናቴን አቅፈኝ ምክንያቱም እኔ ብቻዬን ነኝና እናቴን አቅፈኝ።"

Читать полностью…

የእመቤታችን አንድምታ ወዳሴ ቅዳሴ

በግሩፑ  የተደሰታችሁ  እስኪ  add አድርጉ  @uraman4u123

Читать полностью…

የእመቤታችን አንድምታ ወዳሴ ቅዳሴ

በግሩፑ  የተደሰታችሁ  እስኪ  add አድርጉ  @uraman4u123

Читать полностью…

የእመቤታችን አንድምታ ወዳሴ ቅዳሴ

👉 ከማኅሌተ_ጽጌ ምዕራፎች መካከል የተወሰኑትን ላቀርብላችሁ ወደድኩ እናንተም ላልደረሱት አድርሱ ቅድስት ቤተክርስቲያንን እንወቃት።

👉ጽጌ አስተርአየ ሠሪፆ እምዐፅሙ፣
ለዘአምኃኪ ጽጌ ለገብርኤል ምስለ ሰላሙ፣
ወበእንተዝ ማርያም ሶበ ሐወዘኒ መዓዛ ጣዕሙ፣
ለተአምርኪ አኃሊ እሙ፣
ማኅሌተ ጽጌ ዘይሰመይ ስሙ

👉የክርስቶስ እናቱ ማርያም ሆይ መልአኩ ገብርኤል፣
    ደስ ይበልሽ እያለ ከአቀረበልሽ ሰላምታ ጋር ፣
    እጅ ከነሳሽ ሰው ዐጽም የጽጌረዳ አበባ በቅሎ ታየ፣
    ስለዚህ የተአምርሽ የጣዕሙ ዜና ባስደሰተኝ ጊዜ ፣
    ስሙ የአበባ ማኅሌት ለሚባል ተአምርሽ እዘምራለሁ።

ታሪክ ፦

በኢያሪኮ የሚኖር አንድ አስቴራስ የሚባል አገልጋይ ዲያቆን ነበር። እርሱም በሉቃ 1:26 የተጻፈውን ብሎም የቅዱስ ገብርኤልን ብስራት የቅድስት ኤልሳቤጥን ሰላምታ በአንድ ላይ የያዘውን
#በሰላመ_ቅዱስ_ገብርኤል የሚለውንን እና የእመቤታችንን ምስጋና ዘወትር ያለማቋረጥ ይጸልይ ነበር። ከዕለታት በአንድ ቀን ይህ ዲያቆን ለተግባር ከሀገሩ ተነስቶ በረኸውን አቋርጦ በዱሩ ሲሄድ ርኅራኄ የሌላቸው ክፉ አረሚዎች ዘርፈው ገድለው በመንገድ ጥለውት ይሄዳሉ። እመቤታችንም የእርስዋ ተአምር በእርሱ ይገለጥ ዘንድ ፈቃዷ ነውና በእዚያ ለሚኖር ለአንድ ዲያቆን በራእይ ተገልጣ '' ወዳጄ ሆይ ቤተክርስቲያንን በቅን የሚያገለግልና በእኔና በልጄ ዘንድ ጸሎቱ የተወደደችለት ዲያቆንን ስለገደሉት ሰዎች አዝኛለሁ፣ ሂድና ከጓደኞችህ ጋር በመንገድ ዳር የተቀበረውን ወዳጄን አውጥታችሁ ከቤተክርስቲያን አጸድ ቅበሩት አለችው።

እርሱም በነገረችው መሠረት ከጓደኞቹ ጋር ሂዶ አስከሬኑን ባወጣ ጊዜ ርሔ እንደሚባል ሽቱ መዓዛው እጅግ ደስ የሚያሰኝ ከአፉ የበቀለ አንድ የጽጌረዳ አበባ 🌹 አገኙ ደራሲው ይህንን አይቶ በዚህ አንጻር እመቤታችንን አመሰገናት

መንክር_እግዚአብሔር_በላዕለ_ቅዱሳኒሁ።
እግዚአብሔር1በቅዱሳኑ_ላይ_ድንቅ_ነው።
                                                     መዝ 67 : 35

Читать полностью…

የእመቤታችን አንድምታ ወዳሴ ቅዳሴ

ይህ በእመቤታችን ቻነል በሚለቀቁ ትምህርቶች ዘወትር የሚቀርብላችሁ የመንፈሳዊ ጥያቄ ነዉ በርቱ እና በርከትን አግኙ

1 የተመረጸች 💕ድንግል 💕 የሰማዩን ሠራዊት አሠገደቻቸዉ ሲል ምን ማለት ነዉ?

2 የአዳምን መርገመ ሥጋ መርገመ ነፍስ ያጠፋችለት ቅድስት ማን ትባላለች ?

3 ሰለበረት _____ ልክ ነዉ

ሀ ሕዝቅኤል ካየው ሠረገላ በለጠ
ለ ዳንኤልም ካየው ኪሩባዊ ዙፋን የበለጠ
ሐ ከጽርሃ አርያም ቁመት ረዘመ
መ ከሰማይ ዳርቻ ሰፋ
ሠ መልስ የለም
ረ ሁሉም

መልሳችሁን ከታች በኮሜንቱ ላይ አስቀምጡ ሀሳብ አስተያየትም ስለ ቻናሉ ስጡ ። በጥያቄው በመሳተፍ የበረከት ዋጋ አግኙ!!!!!

Читать полностью…

የእመቤታችን አንድምታ ወዳሴ ቅዳሴ

💕እመቤታችን 💕


የተመረፀች ድንግል የሰማዩን ሠራዊት አሰገደቻቸው፡፡

👉 የዓለም ጌጽ ሽልማት የሁሉ አባት የሚሆን መላእክትን የፈጠረ ጌታ ከርሷ ተወልዷልና፡፡

👉 በረት ተመሰገነ ምድርን በውሃ ላይ ያጸናት እርሱ ስለተጠጋባት ድንግልም የመላእክትን አለቆች ገዛቻቸው በኪሩቤል ላይ የሚቀመጥ እሱ በማኅፀኗ ስላደረ፡፡

👉 በረት ኪሩቤል እንደሚሸከሙት ዙፋን ሆነ ስፍራውም እንደ ጽርሐ አርያም ድንግል እንደ አብ ሆነች አንድ ልጅም በጎል ተጥሎ በጨርቅ ተጠቅሎ ተገኘ፡፡

👉 ዮሴፍና ሰሎሜ በወዲህና በወዲያ ላምና አህያም በወዲህና በወዲያ በበረቱ ጐንና ጐን ባራቱ ማዕዘን በዙፋኑ ቀኝና ግራ በጐንና በጐኑ አራቱ እንስሶች እንዳሉ፡፡

👉 የሰማይ ሥርዓት በምድር ላይ ተሠራ፡፡ ቤተ ልሔም ሰማይን መሰለች ስለ ፀሐይም በቅዱሳን ላይ የሚያበራ ለዘወትርም ጨለማ የማይቃወመው ኅልፈት ጥፋትም የሌለበት ዕውነተኛ ፀሐይ በውስጧ ተገኘ፡፡

👉 የብርሃኑም ክበብ መምላትና መጉደልን ስለሚያፈራርቅ በጨረቃ ፈንታ በዕብራይስጥ ማሪሃም የተባለች የድንግልናዋም ምስጋና በሁሉ የመላ ነው፡፡ ለዘወትርም የማይጐድል እመቤታችን የተመረፀች ድንግል ማርያም ተገኘች ስለ ከዋክብትም መላእክተ ብርሃን ታዩ፡፡

👉 ወደዚህ ማኀበር አንድነት እኖር ዘንድ ማን በከፈለኝ ከመላእክት ጋር እንዳመሰግን ከዋላጅቱም ጋር እንዳደንቅ ከእርኞችም ጋር እንዳገለግል፡፡

 👉 በረቱንም እጅ እነሣ ዘንድ ማን በከፈለኝ የሙታን ሕይወት የኃጥአንም ንጸሕና የቅቡፃን ተስፋ የተጨነቁትንም የሚያድን ጌታ ወደተቀመጠበት፡፡

👉 የዓለም ሁሉ መድኃኒት የምትሆን ብላቴና እግሯ የተመላለሰበቱን ምድር እስም ዘንድ ማን በከፈለኝ፡፡

👉 ይቅርታን የምታሰጥ ብላቴና ጥላዋ ይነካኝ ዘንድ ማን በከፈለኝ፡፡ የብርሃን ልጅ ወደ ሄደችበት እከተላት ዘንድ ማን በከፈለኝ የእግሯንም ጫማ እሸከም ዘንድ ማን በከፈለኝ፡፡

💕የእመቤታችን 💕 አማላጅነት አይለየን !!!

Читать полностью…

የእመቤታችን አንድምታ ወዳሴ ቅዳሴ

✝አዲስ ማስታወቂያ ከማኅሌታይ ያሬድ ፕሮሞሽን ✝
ሰላም እንደምን ሰነበታችሁ የልዑል እግዚአብሔር ቤተሰቦች የእናታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ልጆች

✝ መንፈሳዊ ቻናል ላላቹ በሙሉ አዲስ ጂፒ ስለጀመርን በየቻናላቹ መጠን እንድትመዘገቡ በልዑል እግዚአብሔር ስም ጋብዘኖታል!!!

✝ ቻናላቹን ከስር በተዘረዘረው ደረጃ ማስመዝገብ ትችላላቹ!

⓵.ደረጃ ከ150-500
⓶.ደረጃ ከ500-1000/1k
⓷.ደረጃ ከ1k-5k
⓸.ደረጃ ከ5k-10k
⓹.ደረጃ ከ10k-20k
⓺.ደረጃ ከ20k-30k

✝ በዚህ መሠረት ቻናላቹን መመዝገብ ስለጀመርን እንድትመዘገቡ እንጠይቃለን!

࿇ ለመመዝገብ👇
📨 @habmisget
࿇ ማኅሌታይ ያሬድ ስለመረጡ እናመሠግናለን
✅ @habmisget

share አድርጉት ቻናል ላላቸው በሙሉ
@mekra_abaw
@yaredpromotion

Читать полностью…

የእመቤታችን አንድምታ ወዳሴ ቅዳሴ

✝አዲስ ማስታወቂያ ከማኅሌታይ ያሬድ ፕሮሞሽን ✝
ሰላም እንደምን ሰነበታችሁ የልዑል እግዚአብሔር ቤተሰቦች የእናታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ልጆች

✝ መንፈሳዊ ቻናል ላላቹ በሙሉ አዲስ ጂፒ ስለጀመርን በየቻናላቹ መጠን እንድትመዘገቡ በልዑል እግዚአብሔር ስም ጋብዘኖታል!!!

✝ ቻናላቹን ከስር በተዘረዘረው ደረጃ ማስመዝገብ ትችላላቹ!

⓵.ደረጃ ከ150-500
⓶.ደረጃ ከ500-1000/1k
⓷.ደረጃ ከ1k-5k
⓸.ደረጃ ከ5k-10k
⓹.ደረጃ ከ10k-20k
⓺.ደረጃ ከ20k-30k

✝ በዚህ መሠረት ቻናላቹን መመዝገብ ስለጀመርን እንድትመዘገቡ እንጠይቃለን!

࿇ ለመመዝገብ👇
📨 @habmisget
࿇ ማኅሌታይ ያሬድ ስለመረጡ እናመሠግናለን
✅ @habmisget

share አድርጉት ቻናል ላላቸው በሙሉ
@mekra_abaw
@yaredpromotion

Читать полностью…

የእመቤታችን አንድምታ ወዳሴ ቅዳሴ

" ከመይትፌሣሕ ሕፃን ሶበይሬኢ እሞ
እትፌሣሕ አንሰ ሥዕለኪ በርእይ ወተሳልሞ
ተአምረላህኪ ድንግል ለፀሐየ ቀትር እስከ አጽለሞ
እስመ ፍቅርኪ ጽጌት ፍሥሕት ለአስካልኪ አሕመሞ
ለቤዛ ዚአየ ከመይክዐው ደሞ "


[ ድንግል ሆይ ሕፃን ልጅ እናቱን ባየ ጊዜ እንደሚደሰት ፥ የሃዘን ታምርሽ የቀትር ፀሐይን እስከ አጨለመው ድረስ እኔም ሥዕልሽን በማየትና በመሳለም እደሰታለሁ፡፡ የደስታ አበባ ፍቅርሽ ልጅሽን መከራ መስቀልን እንዲቀበል አድርጎታልና፡፡ ይህም ለኔ ቤዛ [ ካሳ ] ደሙን ያፈስስ ዘንድ ነው፡፡ ]



[ አባ ጽጌ ድንግል ]

Читать полностью…
Subscribe to a channel