ለዚህ መንፈሳዊ ቻናል ተከታታይ ምእመናን ምእመናት በሙሉ ለቻናሉ እንዲሁም ለግሩፑ 100 በላይ ሼር በማድረግ ስታበረክቱ ከke birr ሽልማት ጀምሮ ላቅ ያለ ስጦታ ለማበርከት ስራ ጀምረናል ። እና በዚህ መሳተፍ እና መሸለም የምትፈልጉ ። ከታች ያሉ ሊንኮችን ሼር በማድረግ የሽልማት ወሳጆች ትሆናላችሁ ።
👇👇👇👇
@uraman4u123
@uraman4u13
@uraman4u12
ጸጋ ክብርን የተመላሽ ቅድስት
ድንግል ሆይ❤
👉በጸሎትሽ ረዳትነት አምኜ ሳለሁ የማቸነፍ ጥሩር እንድለብስ የመለኮትንም ሰይፍ እንድታጠቅ አውቃለሁ፡፡
👉 እርስ በርሳቸውም ይረዳዳሉ፡፡ የኔ ሃይማኖት ያንቺ ጸሎት የልዑል እግዚአብሔር ማዳን ዳግመኛም የኔ መታመን ያንቺ ልመና የልዑል አግዚአብሔር ይቅርታ እርስ በርሳቸው ይረዳዳሉ፡፡ እኔ ባንቺ አምኜ ሳለሁ ግዳጄን የማግኘቴ ተስፋ አንቺ ስለኔ ተግተሽ መለመንሽ እግዚአብሔርም ቸል ሳይልና ሳይነቅፍ ግዳጄን መስጠቱ እርስ በርሳቸው ይረዳዳሉ፡፡
👉 እኔ በስምሽ እለምናለሁ አንቺም ስለኔ ትማለጃለሽ፡፡ ልጅሽም ስላንቺ የልመናዬን ዋጋ ይሰጠኛል እኔ ለፍቅርሽ ካልተጋሁ አንቺ እኔን ለማዳን አትተጊም፡፡ ልጅሽም እኔን ይቅር ለማለት አይተጋም፡፡
👉 እኔ በስምሽ ግዳጄን ሁሉ ማግኘት እመኛለሁ፡፡ አንቺ ለኔ አማላጅ ነሽ፡፡ ልጅሽም ግዳጄን የሚሰጠኝ ነው፡፡ እኔ የተጸማሁ ነኝ፡፡ አንቺ የወርቅ መጥለቂያ ነሽ፡፡ ልጅሽም የሕይወት ውሀ አዘቅት ነው፡፡
👉 የመለኮትን ዕንቁ ለመግዛት እኔ ነጋዴ ነኝ፡፡ አንቺ የሕይወት መርከብ ነሽ፡፡ ልጅሽም የበጎ ነገር ሁሉ ድልብ በውስጡ ያለበት የትርፍ ሥፍራ ነው፡፡
👉 እኔ ገደሉን ለማለፍ ወደ ብርሃን ሥፍራ ለመድረስ የቸኮልሁ ነኝ፡፡ አንቺ የመድኃኒት ድልድይ ነሽ፡፡ ልጅሽም ለተገፉት መጸጊያ የተድላ ደስታ ሥፍራ ነው፡፡
👉 እኔ የምንፈስ ቅዱስን ሃብት የምፈልግ ድሀ ነኝ፡፡ አንቺ የክብር ሁሉ መከማቻ ነሽ፡፡ ልጅሽም ለባለሟልነትና ለክብር ለማሞገስ የሽልማት ጌጽ ነው፡፡
👉 እኔ እለምናለሁ አንቺ ጸሎቴን ታሳርጊያለሽ ልጅሽም ኃጢአቴን ያስተሠርያል፡፡ የልቤን ግዳጅ ይሰጠኛል፡፡ እኔ ቁስለኛ ነኝ አንቺ የመድኃኒት ሙዳይ ነሽ፡፡ ልጅሽም ባለ መድኃኒት ነው፡
ለጥያቄዎቹ ቁጥር አስቀምጫለሁ እና በተሰጣቸዉ በቁጥሩ መሠረት በመሳተፍ የበረከት ተሳታፊ ሁኑ ። ጥያቄዎች 3ት ናቸው ። ከትንሽ ሰአታት በኋላ ለሁሉም ጥያቄዎች መልስ ይሰጥባቸዋል ። እና ግን የቻላችሁትን ለመመለስ ሞክሩ ስትለፉ ነዉ ማወቅ ማገላበጥ መጠየቅ መረዳት የሚመጣው እና በርቱ ምእመናን ።
Читать полностью…2 ከአበው መኻከል ____
👉 እመቤታችንን በፍጹም ልቡናው ከመውደዱ የተነሣ ከሠርክ ጸሎት በኋላ ሌሎች መነኮሳት ለመኝታ ወደ የበኣታቸው ሲሄዱ ርሱ ወደ ቤተ ክርስቲያን በመሄድ
👉 በቅድስት ድንግል ማርያም ሥዕል ፊት ቆሞ በፊቷ እየተማለለ እና ሦስት መቶ ስግደትን እየሰገደ ይጸልይ ነበር፡፡
👉በእያንዳንዱ ስግደቱም “ኦ እግዚእየ ኢየሱስ ክርስቶስ አርእየኒ እመከ አሐተ ሰዓተ፤ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ለአንዲት ሰዓት እናትህን አሳየኝ” እያለ ተማጽኗል፡፡
👉 ለሰባት ዓመት ከቈየ በኋላ፤ በታላቅ ግርማ ተገልጻለት የአምላክን እናት ፊት ለማየት በቅቷል፤
👉 ርሷም ምን እንደሚሻ ስትጠይቀው የንግሥተ ሰማይ ወምድር፤ የርሷን ገጽ ያዩ ዐይኖቹ ሌላ ነገርን ማየት እንደማይፈልጉና ከልጇ እንድታማልደው ብቻ ለመናት፡፡
👉 ቅድስት ድንግል ማርያምም ከሦስት ቀን በኋላ የዕረፍቱ ቀን መሆኑን ካሳውቀችው በኋላ ባርካው ወደ ሰማይ ዐረገች፤ ይህ ቅዱስ አባት መልኳን የማየት ክብር ካገኘ በኋላ በሦስተኛው ቀን ዐርፏል፡፡
ማነው ይሄ ቅዱስ
ሀ አባ ኤፍሬም
ለ አባ ህርያቆስ
ሐ አባ ጊወርጊስ ዘጋስጫ
መ አባ ይስሐቅ
1 በእንዚራ ስብሐት መጽሐፉ ላይ፡-
“ኦ ንግሥት ይገንዩ ለኪ ነገሥት ወለኪ ንግሥታት ይትቀነያ ወኪያኪ የአኲታ ወለስምኪ ይገንያ ወለኪ ይሰግዳ ወለክብርኪ የሐልያ ጢሮስ ወሲዶና ሰብአ ግብጽ ወኢትዮጵያ ፊንቂ ወሮምያ ማሮን ወአርማንያ በሥነ ጸዳልኪ ይትፌሥሓ ወበላሕይኪ ይትሐሠያ፤
👉❤ ንግሥት ሆይ ነገሥታት ለአንቺ ያገለግላሉ፤ ነግሥታትም አንቺን ያመሰግናሉ፤ አንቺንም ያሞግሳሉ፤ ለስምሽም ያጐነብሳሉ፤ ለአንቺ የጸጋ ስግደትን ይሰግዳሉ፤ ለክብርሽም ምስጋናን ያቀርባሉ፡፡ ጢሮስና ሲዶና የግብጽና የኢትዮጵያ ሰዎች፣ ፊንቄና ሮምያ፣ ማሮንና አርማንያ በወጋገንሽ ውበት ደስ ይሰኛሉ፤ በደም ግባትሽም እሰይ ይላሉ፤” በማለት ገልጦታል፡፡ ይህ ቅዱስ __ይባላል ?
ሀ ቅዱስ ኤፍሬም
ለ አባ ህርያቆስ
ሐ አባ ጊወርጊስ ዘጋስጫ
መ ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ
✝️ድንግል_ሆይ !---የሚወዱሽ የተወደዱ ናቸው
✝️ንግስት_ሆይ !---የሚያከብሩሽ የከበሩ ናቸው
✝️ንፅሕት_ሆይ !---የሚቀድሱሽ የተቀደሱ ናቸው
✝️ፍስሕት_ሆይ !---የሚመርቁሽ የተመረቁ ናቸው።
✝️ልዕልት_ሆይ ! ---የሚያደንቁሽ የተደነቁ ናቸው
✝️ውድስት_ሆይ !---ለንግሥትነትሽ
የሚገዙ ሁሉ የተባረኩናቸው።
✝️ድንግል_ሆይ ! ንፅህናን እንደ መላዕክት የለበሽ ፣ እንደ ነብያት መንፈስ ቅዱስን የተሞላሽ ፣ነሽ አሸናፊ በሚሆን በልዑል እግዚአብሔር እጅ የታነፅሽ የመለኮት ማደሪያ
ነሽ ። ስለዚህ ክብርት ነሽ ።"እናከብረዋለን
ድንግል ሆይ !ባንቺ ያመንን ልጆችሽ ከመከራ ስጋት መከራ ነፍስ ከክፉ ሁሉ ጠብቂን አሜን አሜን አሜን !
ድንግል እመቤቴ ማርያም ሆይ
እንግዲህ በርሱ ላይ አሰልጥኝኝ እራሱን እረግጠው ዘንድ፡፡
👉 በበኩር ልጅሽ መስቀል ፍላፃ እነድፈው ዘንድ አሰልጥኚኝ፡፡ ሰለባ የሌለው ይህን ጎስቋላ እገለው ዘንድ ንግሥት ሆይ አሰልጥኝኝ፡፡
👉ንግሥት ሆይ ይህን በመለኮት ሰይፍ ራሱን እቆርጠው ዘንድ፡፡ ንግስት ሆይ ይህን ዕቡይ ትዕቢተኛ እሳለቅበት ዘንድ ተይኝ፡፡
👉 የልጅሽ እጅ የጸናው ክንዱም በኔ እጅ ይዞ ይጣለው መንፈሳዊ ረቂቅ ኃይሉም ጥልቀቱም ወደማይታወቅ ርዝመቱም ወደማይገኝ ወደ ገሃነም ገደል ይጣለው፡፡
👉 የሲኦልንም መዝጊያ ይቆልፍበት ይህ ሐሰተኛ ቀማኛ ከውስጧ እንዳይወጣ፡፡
👉 በድንግልናሽ ላይ የስድብ ነገር ስለ ተናገረ ቀናሁ፡፡ መንፈሳዊውንም ፅንስሽን ስላሳበለ ቀናሁ በድንግልና መውለድሽንም ስለሰደበ ቀናሁ፡፡
👉 በናዝራዊው በልጅሽ ላይ የአይሁድን ልቡና ስላከፋበት ቀናሁ፡፡ የዓለም መድኃኒት ርሱን እንዲገድሉ ስላስጨከናቸው ቀናሁ፡፡ ስላንቺም ስድብ ስለ ልጅሽም ቀናሁ፡፡
👉 በመዝሙር እንደተናገረ እንዲህ ሲል፡፡ የቤትህ ቅናት በልታኛለችና፡፡ የሚላገዱህ መላገድ በላዬ ወደቀ፡፡ (መዝሙር ፷፱፣ ፱)
👉 ነቢዩ እንግዲህ አንቺን የእግዚአብሔር ቤት አለሽ፡፡ የሚላገዱህ መላገድ በላዬ ወደቀ ያለውም የአይሁድ ተናግሮት ነው፡፡ ሰይጣን ካስተማራቸው ምቀኝነት የተነሣ በእግዚአብሔር ልጅ ላይ የተናገሩት ስድብ ነው የዮሴፍ ልጅ ነው ሲሉ፡፡ (ሜቴ፣ ፲፫፣ ፶፭ )
👉 የእግዚአብሔር ሀገር ሆይ እኔ ስላንቺ ደስ እሰኛለሁ ነቢያት ፀሐይን ለመውለድ እንደተዘጋጀች ጎሕ ያዩሽ ነባቢት ኤዶም ሆይ ባንቺ ኃሤትን አደርጋለሁ፡፡
👉 ሰሎሞን ወንድምሽ እንደተናገረ እንዲህ ሲል ይህች ማናት እንደ ማለዳ ብርሃን የምትታይ፡፡ (መኃ፣ ፮፣ ፲)
👉 ዳግመኛም እርሱ መሸከሚያ ብሎ ጠራሽ ተናግሯልና እንዲህ ሲል፡፡ ሰሎሞን ለራሱ መሸከሚያ አሠራ፡፡ (መሐ፣ ፫፣ ፱)
👉 ልጅሽ ኢየሱስ ክርስቶስ ሰሎሞን ይባላል ሰሎሞን ማለት ፍቅር ሰላም ማለት ነው ጳውሎስ እንደተናገረ እንዲህ ሲል፡፡ በመስቀሉ ሰላምን አደረገ ድልንም ገደለው፡፡
👉 ብዙዎች ነቢያትና ጻድቃን አንቺን ሊያዩ ወደዱ አላዩም ምሳሌሽን እንጂ፡፡ የልጅሽን የመለኮትነቱን ምሥጢር ያየን እኛ ግን በቅድስት ጠረጴዛ ሥጋውንና ደሙን ቁርባኑን ተቀበልን አንድ አካል አንድ አምሳል በመሆናችን የተመሰገንን ነን፡፡
👉 የእግዚአብሔር ልጅ ትሕትናው የተደነቀ ነው፡፡ ይህ የተደነቀ ትሕትና እንደምን ያለ ነው፡፡ ለዚህ አንክሮ ይገባል፡፡
እህት ወንድሞቼ ምእመናን እኔ በእዉነቱ የማገኘው ስጋዊ ጥቅም የለም ግን ለመንፈሳዊ ህይወቴ በዚህ የእመቤታችን ቻናል እናንተ እንድታዉቁልኝ እየለፋሁ እና እየደከምሁ እገኛለሁ ። እና እኔ ከእናንተ በላይ ብዙ ሰዉ እንዲማር እፈልጋለሁ አሁን ትንሽ ናችሁ ይሄን ቻናል የምትከታተሉ እና ቤተሰብ በዛ እንድንል የምታረጉ ሰዎችን ትምህርት እንዲማሩ የምታረጉ እናንተ ናችሁ ። እና በዚህ ቻናል አድድድድ እና ሼር በማድረግ ሁላችንም የበረከት ተሳታፊ እንሁን ።
ሀሳብ አስተያየት
@woladite11
አድድ እና ሼር ለማድረግ
@uraman4u12
@uraman4u123
1 ቀስተ ደመና የተባለው የቱ ነዉ
ሀ ) ድንግል ማርያም
ለ ) ቅዱስ መስቀል
ሐ ) ስጋወ ደሙ
መ ) የሀገራችን ባንዲራ
ሠ ) መልስ የለም
ረ ) ሁሉም
የያዕቆብ መሰላል ምን ነበረች
የወርቅ መሰላል ድንግል ማርያም ናት እንላለን ።
የመሠላሏ ጫፍ ደሞ ህሊናዋ
ከያዕቆብ መሠላል እግዚአብሔር ተቀምጦባት ነበር ማለት
በድንግል ማርያም ህሊና ከእግዚአብሔር ሀሳብ በቀር ሌላ ገብቶበት አያውቅም ማለት ነዉ።
ሌላ ምንም ነገር ያልገባባት ፍጽምት
የእግዚአብሔር ከተማ እርሷ ናት።
አማላጅነቷ አይለየን !!!
"ማር " ልበል በምድር " ያም " ልበል በሰማይ
የማይጠግቡት መና የማይጨርሱት ሲሳይ
መንፈስ ቅዱስ አይቶ ሰርቶ በምስጢሩ አፌ ላይ
ጣፈጠ ስምሽ አጠረሩ እናቴ 21🥰
☦️ቅድስት ሆይ ለምኝልን🤲🌸
ድንግል_ሆይ !---የሚወዱሽ የተወደዱ ናቸው
ንግስት_ሆይ !---የሚያከብሩሽ የከበሩ ናቸው
ንፅሕት_ሆይ !---የሚቀድሱሽ የተቀደሱ ናቸው
ፍስሕት_ሆይ !---የሚመርቁሽ የተመረቁ ናቸው።
ልዕልት_ሆይ ! ---የሚያደንቁሽ የተደነቁ ናቸው
ውድስት_ሆይ !---ለንግሥትነትሽ የሚገዙ ሁሉ የተባረኩ
ናቸው። …………
🌹ድንግል ማርያም ከክፉ ትጠብቀን🙏
እህት /ወንድሞቼ
መንፈሳዊ ኮርሶችን በ pdf በ ppt በ doc በ word እንዲዘጋጅላችሁ የምትፈልጉ የምታስተምሩበትን ኮርስ ርዕስ በመናገር በምትፈልጉት መንገድ አዘጋጅተን እንሰጣለን ።
ለማስተማር ብቻም ሳይሆን መማርም ጭምር የምትፈልጉት ማወቅ የምትሹት ካለ እናዘጋጃለን ።
ነገር ግን በክፍያ ነዉ ።
ክፍያው በአንድ ገጽ pdf 2t birr ብቻ ነዉ የሚታሰበው ።
ጥቅሙ በጣም ብዙ ነዉ።
ማወቅ በምትፈልጉት መርጣችሁ በምትሰጡት ርዕስ ነዉ የሚዘጋጅላችሁ
እና ለመንፈሳዊ ህይወት በጣም ቆንጆ ነዉ
የምትፈልጉ በዉስጥ መስመር አዋሩኝ
@woladite11
@woladite11
3 👉 “እመቤታችን በሁሉም እርምጃዎቿ ጐበዝና የተከበረች ነበረች፤ የምትናገረው በጣም ጥቂት ሲሆን ርሱም ለማድረግ አስፈላጊ በሚሆንበት ብቻ ነበር፤
👉 በጣም ዝግጁ ሆና የምትሰማና በቀላሉ ንግግር ለማድረግ የምትችል ናት፤ ለእያንዳንዱ ሰው አክብሮትና ክብር (ሰላምታ) ትሰጣለች፤
👉 ቁመቷ መኻከለኛ ነው፤ አንዳንዶች ግን ቁመቷ ከፍ ያለ እንደነበር ይናገራሉ፤ ከእያንዳንዱ ሰው ጋር ያለምንም ፍርሀት በግልጽነት ያለምንም ሳቅና መጯጯኽ ትናገራለች፤
👉በተለይ ፈጽማ ለቁጣ የምትጋበዝ አልነበረችም፤ መልኳ እንደ ደረሰ የስንዴ አዝመራ ያማረ ጸጒሯ ቀያማ ነው፤
👉ዐይኖቿ ብሩሃትና የዋህ የሆኑ ቀለማቸውም ፈዘዝ ያለ ቡናማ ሆኖ የዐይኖቿ ብሌኖች የዘይት-አረንጓዴ ይመስላል፤
👉የዐይኖቿ ቅንድብ (ሽፋሽፍት) ከፊል ክብና ደማቅ ጥቁር ናቸው፡፡
👉 አፍንጫዋም ረዥም፣ ከናፍሮቿ ቀይና ምሉእ ሲሆኑ በቃሎቿ ጣፋጭነት የተመላባቸው ነበሩ፤
👉ፊቷ ክብ እንቁላልማ ዐይነት ቅርጽ ነበረው፡፡ እጆቿ ረዥምና ጣቶቿም በጣም ረዣዥም ነበሩ፤ ከማንኛውም ያልተገባ ኩራት ሙሉ በሙሉ የነጻች ስትሆን ግድ የለሽነት ፈጽሞ አልነበረባትም፤
👉 የሚመጡትን ነገራት በፍጹም ትሕትና ትቀበል ነበር፤ ተፈጥሯዊ ቀለማት ያላቸው፤ ማለትም በቤት ድር የተሠሩ ልብሶችን ትለብስ ነበር፤
👉ይህም በእጅጉ አብሯት የሚሄደው አለባበስና ይህ እውነታ በራሷ ላይ በምታደርገው ቅዱስ ልብስ አሁን ቅሉ ሊረጋገጥ የሚችል እውነታ ነው፤
👉 በመንገዶቿ ሁሉ በመለኮታዊ ጸጋ የተመላች ነበረች፤” ሲል ስለ ድንግል ማርያም ገልጿል፡፡
ሀ የቆጵሮሱ ሊቀ ጳጳስ ቅዱስ ኤጲፋንዮስም
ለ የእስክንድርያው ቅዱስ አትናቴዎስ
ሐ የብህንሳዉ ሊቀ ጳጳስ አባ ህርያቆስ
መ የሶርያው ቅዱስ ኤፍሬም
የመልክአ ማርያም ደራሲ
የአምላኩን እናት
👉ቅድስት ድንግል ማርያምን ፊቷን ለማየት ሽቶ
👉 “ሰላም ለመልክእኪ ዘተሠርገወ አሜረ ዘያበርህ ወትረ ፍቅርትየ አንቲ እንተ ታበድሪ ፍቅረ አርእዪኒ ገጸ ዚኣኪ ማርያም ምዕረ ዘኢይሰምዖ ካልእ እንግርኪ ነገረ”
👉ዘወትር የሚያበራ ፀሓይን ጌጥ ላደረገ መልክሽ ሰላምታ ይገባል፤
👉ፍቅርን የምትመርጪ (የምታስቀድሚ) አንቺ ፍቅረኛዬ ማርያም
👉ሌሌላየማይሰማው ነገርን እነግርሽ ዘንድ አንድ ጊዜ ያንቺን ፊት ግለጪልኝ፤” በማለት ተማፅኗታል፡፡
ከፈጠረው ፍጥረት አምላክ
በዚች ምድር ምን ጣፋጭ ተገኝቶ
ከወተት ከማር
ምን ተገኝቶ ጣፋጭ በዚች ምድር
ከወተት ከማር
ለጣፋጭነቱ የሌለው አምሳያ
ማርና ወተት ነዉ የድንግል መጠሪያ
ማር ወተት ነዉ የድንግል መጠሪያ
የስሟ መጠሪያ
ንዒ ሀቤነ ኦ ድንግል ንዒ ሀቤነ
ምስለ ወልድኪ ፍቁርኪ
ኢየሱስ ክርስቶስ ከመ ትባርኪ ላዕሌነ
@uraman4u13
እህት ወንድሞቼ ምእመናን እኔ በእዉነቱ የማገኘው ስጋዊ ጥቅም የለም ግን ለመንፈሳዊ ህይወቴ በዚህ የእመቤታችን ቻናል እናንተ እንድታዉቁልኝ እየለፋሁ እና እየደከምሁ እገኛለሁ ። እና እኔ ከእናንተ በላይ ብዙ ሰዉ እንዲማር እፈልጋለሁ አሁን ትንሽ ናችሁ ይሄን ቻናል የምትከታተሉ እና ቤተሰብ በዛ እንድንል የምታረጉ ሰዎችን ትምህርት እንዲማሩ የምታረጉ እናንተ ናችሁ ። እና በዚህ ቻናል አድድድድ እና ሼር በማድረግ ሁላችንም የበረከት ተሳታፊ እንሁን ።
ሀሳብ አስተያየት
@woladite11
አድድ እና ሼር ለማድረግ
@uraman4u12
@uraman4u123
1 የያዕቆብ መሠላል ጫፏ የ __ ምሳሌ ናት ።
ሀ የእመቤታችን
ለ የእመቤታችን የቃሏ
ሐ በድንግል ቃል ህጸጽ የሌለበት
መሆኑ
መ ሁሉም
ሠ መልስ የለም
ከመ እምጽቡር ጽሩየ ገብራ
ከጭቃ የሚገኝ ወርቅ ከጭቃ ስናወጣዉ
የጭቃዉ ፀባይ በወርቁ ዉስጥ እንደሌለ
ከአዳምና ከሄዋን ፀባይ ስትገኝ
የአዳምና የሄዋን እርግማን ያላረፈባት
ወርቅ ናት ።
ንጹሕ ፀባይ ያላት ማለት
👉 ድንግልናዋ ወርቅ የሆነ
👉ህሊናዋ ወርቅ የሆነ
👉 አካሏ ወርቅ የሆነ
በንጽሓ ፀባይ የበለፀገች ባለፀጋ ስለሆነች
እርሷን አገኘ።
ስለዚህ እመቤታችን 5500 ዘመን የሰው ፀባይ ጎስቁሎ በነበረበት ሰዓት
ብቻዋን ሰዉ ሁና በእግዚአብሔር የታየችልን
ንጽሕት እጅ መንሻ ናት ማለት ነዉ።
ስለዚህ
እስመ አፍቀረ ንጉሥ ስነኪ
ያንን ዉበት ወዶ እርሱ ወደዚች ምድር መጣ።
👉 የእግዚአብሔር ከተማ ስለሆነች
👉ህሊናዋ ፈጽሞ ቅዱስ ስለሆነች
የእመብርሃን
አማላጅነቷ አይለየን !!!!
ድንግል ኾይ❤
ሥጋ የለበሰ ሁሉ መመኪያ ድንግል ሆይ ነፍስ የተዋሀዳቸው ፍጥረት ሁሉ አክሊል የዓለም ሁሉ ቤዛ ነፍሴን ከክፉ ነገር ወደ ገሃነምም ከምትወስድ የጥፋት መንገድ አድኛት፡፡
👉 ሳትዘራ ስንዴ ያፈራች ዝናምም ሳይዘንምባት የወይን ፍሬ ያስገኘች ማረሻ ያልዞረባት እርሻ ድንግል ሆይ የኦሪትና የነቢያት ቃል ዝናምን አጠጭኝ በሐዋርያት ወንጌል ቃል ፈሳሽነትም ሐዲስና ብሉይን እንዳፈራ አድርጊኝ፡፡
👉 የኃይል መንፈስ የተመሉትን የተደነቁ የተመረጹትን ሐዋርያት ዋጋ እንድቀበል አድረጊኝ ልቡና የሚገልጽ ዕውቀት የሚያበዛወን መንፈስ የተመሉ ሐዋርያትን ዕሤት እንድቀበል ማለቴ ግን በኔ ገድል በትሩፋቴ አይደለም ባነቺ ደግነት በንጽሕናሽም ነው እንጂ፡፡
👉 በጸሎትሽም ረዳትነት ይህንን ላገኝ እወዳለሁ ድንግል ሆይ በሃይማኖት ጭንጫ ላይ የተመሠረተች መሠረት የማትፈርስ የነፋሳት ኃይል የጎርፍ ፈሳሽ የዝናምም ወጀብ የማይበረታባት አጥር ቅጽር ሆይ እኔን ከጥፋት ጎርፍ በዓመፀኞችና በበደለኞች ላይ ከምትመጣው የመቅሠፍት ኃይል አድኝኝ፡፡
👉 የመለኮት አዳራሽ ድንግል ሆይ የሰማይ ሠራዊት ፆታ ያደረብሽ ንጽሕት ሆይ፡፡ ኅብሩ ልዩ ልዩ በሚሆን ብርሃን በተጌጸ የቅዱሳን አዳራሽ ውስጥ መኖርን ክፈዪኝ፡፡
እመብርሃን እናቴ ትንፋሽሽን እፍ በይብኝ
ፅናትሽን እፍ በይብኝ፤
ወይም ይችን የሞት ጽዋ፥
ጥላዋ ነፍሴን ካፈናት
እንዳልጠጣት አሳልፊያት
መራራ ክንፏን ገንጥለሽ ቀጠሮ ቃሏን ግደፊያት
አለዚያም ፅናትሽን ስጭኝ ልጠጣው ኪዳነ ውሉን
የኔ ፈቃድ እምነትሽ ነው ያንች ፍቃድ ብቻ ይሁን።
እንደ ጳውሎስ እንድፀና ፣ በፍርሃት እንዳልታሰር
በውስጠ ከሚታገለኝ በስጋ አውሬ እንዳልታወር
ለየዕለቱ ሞት እንዳልሰንፍ
የኪዳኔ ቃል እንዳይነጥፍ
ቃልሽ በሕሊናየ ዲብ ፣ ኃይልሽ በሕዋሴ ይረፍ።
ፍርሃት ቢያረብብኝም አንች ካለሽኝ አልሰጋም
ኩርምት ብየ እችልበት ፣ እሸሸግበት አይጠፋም
የግማደ መስቀሌን ጉጥ እታገስበት አላጣም
አለዚያማ ብቻየን ነኝ ፣ ኢትዮጵያም
ያላንች የላት
አንች አፅኝኝ እንድፀናላት።
አስርጭብኝ የእምነት ቀንጃ፤
ለስጋቴ አጣማጅ አቻ
ለጭንቀቴ መቀነቻ።…
እባክሽን ብቻየን ነኝ ፈራሁ
እሸሸግበት ጥግ አጣሁ
እምፀናበት ልብ አጣሁ …
_እመብርሃን ሆይ ❤
በዕውነት መመስገን ይገባሻል
👉ለማለዳውው ኮከብ ምሥራቅ ሆነሻልና በውነት መደነቅ ይገባሻል፡፡ ለጥምቀት ልጆች መመከያ ሆነሻልና፡፡ በውነት ብፅዕና ይገባሻል፡፡ ለሃይማኖት መሠረት ጽናተ ሆነሻልና፡፡
👉 ከኪሩቤል ክብር ገናንነት ላንቺ ይገባል፡፡ ከሱራፌልም ውዳሴ ከመላእክትም እልልታ ከመላእክት አለቆችም ዝማሬ ላንቺ ይገባል፡፡
👉 ከነቢያት ትንቢት ከሐዋርያት ስብከት ላንቺ ይገባል፡፡ ከቅዱሳን ሰማዕታት እናታችን መባል ከመሐይምናንም እመቤታችን መባል ከክርስቲያንም ሁሉ አፍ የመድኃኒታችን ቀንድ መባል ላንቺ ይገባል፡፡
👉 ከመሲሓውያን ነገስታት አፍ ንግሥታችን መባል ከልዑላንም መላእክት በላይ ከፍ ከፍ ማለት ከታችኞችም ፍጡራን ላንቺ መገዛት ይገባል፡፡ እንግዲህ አንቺ ከሰማይ ትበልጫለሽ ከተራሮችም ከፍ ትያለሽ፡፡ ስለ አንቺም እንዲህ እላለሁ ከፀሐይ ብርሃን ከጨረቃም ድምቀት አንቺ ትበልጫለሽ፡፡
👉 ስለ አንቺ እንዲህ እላለሁ፡፡ ከአርዮብ መልክ ከመብረቅም ብርሃን አንቺ ታበሪያለሽ፡፡
👉 ስላንቺ ደግሞ እንዲህ እላለሁ በሰማይ ካሉ ትጉሃን መላእክት ትከብሪያለሽ፡፡
👉ከመናብርትም ከሥልጣናትም ትቀደሻለሽ፡፡
👉ስላንቺም እንግዲህ እንዲህ እላለሁ መልኩ አስተያየቱ ልዩ ልዩ ከሚሆን አበባ ፍሬ ትሸቻለሽ፡፡
👉 አሁንም ደግሞ ወደ ልጅሽ እጮሃለሁ፡፡ እንዲህ ስል አቤቱ በምሕረትህ አስበኝ በመስቀል ላይ በምስማር ተቸንክረህ ሳለህ የቀኙን ወንበዴ እንዳሰብከው፡፡
👉 አቤቱ በምሕረትህ አስበኝ፡፡ ስለ ንጹሑ አቤል ደም አማላጅነት፡፡ ስለ ሰው መሆንህ ትንቢት ምስክርነት ስለሞቱት ሰማዕታት አማላጅነት፡፡
👉 አቤቱ አስበኝ በጸራ ወርቅ ምንጭ ወንጌልህን ለማስተማር ስላፈሰሱ ስለ ጴጥሮስና ጳውሎስ ደም መፍሰስ አማላጅነት፡፡
👉አቤቱ በምሕረትህ አስበኝ፡፡ ባንተ ዘንድ የተወደደው የድንግልናው መዓዛ እንደ ተጣፈጠ ሽቱ፡፡
👉በካህናቱ ራስ ላይ ስለ ተቀላቀለው ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ አማላጅነት፡፡
👉 አቤቱ በቸርነትህ አስበኝ ስለ ሐዋርያትህ ደም ስለ ሥጋዌህ ምስክርነት ስለ ፈሰሰው አማላጅነት አቤቱ በይቅርታህ ብዛት አስበኝ ስለ መዋዕያን ሰማዕታት ደም ስለ ስምህ ምስክርነት አማላጅነት፡፡
እሳት የማያቃጥላት ዕፅ፦
እሳት ከነደደ የማያቃጥለው ዛፍ የለም።
ነቢዩ ሙሴ ግን እሳት እየነደደባት እሳት የማያቃጥላት ፅፀ ጳጦስ የተባለች ዛፍ በደብረ ሲና አይቶ ተደንቆ ነበር።
ያቺ ዕፀ ጳጦስ የድንግል ማርያም ምሳሌ ናት።
እሳቱ ከዛፏ ጋር እየነደደ ቢታይም እንዳላቃጠላት ሁሉ፥ ድንግል ማርያምም ጌታችን ክርስቶስን ጸንሳ በወለደች ጊዜ እሳተ መለኮቱ አላቃጠላትም።
አንድም፥እሳት የተባለ ሞት ነው።
ሁሉንም ዛፎች ማውደም የሚችለው እሳት ዕፀ ጳጦሷን ማቃጠል እንዳልቻለ ሁሉ፥ የአዳምን ልጆች በሙሉ የሚበላውና የበላው ሞትም፥ በእርሷ በእመቤታችን ላይ በእሳት አምሳል ታይቷል፤
አፍርሶ አበስብሶ ያስቀራት ዘንድ ግን አልተቻለውም።
እሳተ መለኮት ያላቃጠላትን ጳጦስ፥ አዳም በዕፀ በለስ ያነደደው እሳት/ሞት እንዴት ያቃጥላት ዘንድ ይቻለዋል?
.....ሊቀ ሊቃውንት ሥሙር አላምረው
🌹#ኪዳነ ምህረት ሆይ🙏
"ባንቺ የተፈጸመው ድንቅ ነገር ለማንም ያልተደረገ እረቂቅ ነገር ነው። ኅብስት ህይወት ጌታን ያስገኘሽልን ድንግል ሆይ እናመሰግንሻለን። ኢየሱስ ክርስቶስ ስጋዬን የበላ ደሜንም የጠጣ የዘላለም ሕይወትን ይወርሳል በማለት ያስተማረን ከአንቺ የነሳውን ሥጋ እና ደሙን እንበላ እና እንጠጣ ዘንድ ነው። በሄዋን ምክንያት የተዘጋ ገነት በአንቺ የተከፈተብሽ ድንግል ሆይ በአንቺ ድንቅ ነገር እረቂቅ ሚስጥር ተደረገልን። ከአንቺ የተዋሐደውን ሥጋና ደም ተቀበልን። ገነት መንግስተ ሰማያት የምንወርስብሽ ድንግል ሆይ እናመሰግንሻለን። ከድቅድቅ ጨለማ ሳለን ብርሃን የተመለከትንብሽ። የብርሃን እናቱ ድንግል ማርያም ሆይ እናመሰግንሻለን። በማህጸን የፈጠርሽን አምላክ በማህጽንሽ የተሸከምሽው ድንግል ሆይ እናከብርሻለን።
የእመቤታችን ኪዳነ ምህረት በረከቷ ፍቅራ በሁላችን ላይ ይደርብን።
አሜን አሜን አሜን