ሌላ አገር የለንም !!
(አሌክስ አብርሃም)
📚 ጦርነት ቀፋፊና አጥፊ ነገር ነው ! ለአሸናፊም ተሸናፊም ጦርነት ቀፋፊ ነገር ነው! ማንም ኢትዮጵያዊ መሞት አይፈልግም ፣ ማንም ኢትዮጵያዊ አካሉ ጎድሎ መኖር አይፈልግም ፣ ማንም ኢትዮጵያዊ በጥይትና ፈንጅ የተቦጫጫቀ የሰው ልጅ አካል አእምሮው ውስጥ
አስቀምጦ እድሜ ልኩን በመጥፎ ትዝታ መኖር አይፈለግም ….ማንም ልጅ ወላጆቹን ፣ ማንም ወላጅ ልጆቹን ፣ የትኛዋም ሚስት ባሏን የትኛውም ማህበረሰብ ያሳደጋቸውን ልጆቹን ገብሮ እድሜ ልኩን ፎቷቸውን እያየ በሀዘን መቆራመት አይፈልግም ! ማንም !!
📚 ጥቁር ታሪክ አለን ! ይሄን መራር ፅዋ ስንጎነጭ የኖርን ህዝቦች ነንና ምሬቱ ገና ከህሊናችን አልደበዘዘም! ምድራችን ላይ የፈሰሰው ደም ገና ወደአፈር አልሰረገም ! የጦርነትን አስከፊ
ገፅታ ለመናገር የታሪክ ክርታሳችንን አንድ ገፅ እንኳን ወደኋላ መግለጥ አይጠበቅብንም ገና እዛው ገፅ ላይ ሁነን ሌላ የሰላም ገፅ ለመፃፍ እየታገልን ያለን ህዝቦች ነን ! ግን ደግሞ ሌላ አገር የለንም !!ከነድህነታችን ከነኋላ ቀርነታችን ፣ ከነደስታና ሀዘናችን በሆነው ልክ ተቀብላ የምታኖር ብቸኛ አገር ይችው ኢትዮጵያ ብቻ ናት ! ውስጧ ሁነን እየተነጫነጭንም ቢሆን የምንወዳት ፣ ሩቅ ሁነን እንደተስፋ ምድር የምናልማት ይችው
ኢትዮጵያ ብቻ ናት ያለችን ! ሌላ አገር የለንም !
📚 ሀገሬ ወንዜ የምንለው ዘፈን ለማሳመር አይደለም …በሰላም ቀን የተዳፈነ የሚመስል ፣በምሬታችን ብዛት የጠፋ የተዘናጋ የሚመስል
የነፍስ ፍቅር ያስያዘን ሌላ አገር በምድር ላይ የለም!የትም ብንሰደድ በየትኛውም ቋንቋና ስልጣኔ ዜግነት ጭምር ብንሸፋፈን የልባችን ሙዳይ ሲከፈት ተሸክመናት የምንጓዘው
አንዲት አገር ብቻ አለችን ኢትዮጵያ ! ሌላ አገር የለንም !! ምክንያትህ ምንም ይሁን ይችን አገር ስትነካ በራስህ ላይ ሞት አውጀሀል!
የኢትዮጵያዊያን ቁጣ የኢትዮጵያዊያን እልህ እና ለመሰዋእትነት መዘጋጀት ሚስጥር ሌላ አይደለም !
📚አገር ስትነካ ‹‹የራሷ ጉዳይ›› እንል ዘንድ ፣ ‹‹ምናገባን›› እንል ዘንድ…‹‹እዛው የበሉት ይዋጣላቸው›› እንል ዘንድ …. ሌላ አገር የለንም ! ለነፍሳችንም ለስጋችንም በወርድና ቁመቷ ፣ በባህል ወግና ስነልቦና ተሰርታ የተሰጠችን ብቸኛ አገር ይችው
ኢትዮጵያ ብቻ ናት ! ሌላ አገር የለንም ! እንኳን ህሊና ያለው ስለነፃነት ጠንቅቆ የሚያውቅ
ህዝብ ይቅርና እቤትህ ያሳደካትን ድመት በርና መስኮት ዘግተህ ልግረፍሽ ብትላት ጥፍሯን
መዛ ወደነብርነት መቀየሯ አይቀርም …ያኔ የግፍ ብትር በትዕቢት ያነሳህበትን ቀን እድሜ
ልክህን ትረግማለህ ! ያ የተመዘዘ ጥፍር በትዛዝም በልምምጥም አይመለስም! የኢትዮጵያ ህዝብ እንደሚባለው ጦረኛ አይደለም … ነፍጥ መዞ አላፊ አግዳሚ ላይ
የሚተኩስ ግፈኛ አይደለም ! የጀግንነቱም የጦረኝነቱም ዋና መነሻ አንድና አንድ ነው ….ሌላ
አገር የለውም ! ርስቱ ኢትዮጵያ ብቻ ናት ! ኢትዮጵያዊ በአገሩ ጉዳይ ሰይጣን ሁነህ ብትመጣበት ቀንዳም ሰይጣን ሁኖ ይጠብቀሃል እሳት ሁነህ አገሩን ልታቃጥል ከመጣህ ገሀነም ሁኖ ይጠብቅሃል ፣ ወንዝ ሁነህ እየጎረፍክ ብትመጣበት ውቅያኖስ ሁኖ
ይጠብቀሃል ! የምንሞትለት ምቾት … አካል የሚጎድልለት ስርዓት ኖሮን አያውቅም!
📚 ኢትዮጵያዊ ለስርዓት አይዋጋም !ስርዓቱ እያፈነው ስርዓቱ እየገደለው ኑሮውን ሲኦል እያደረገበት እንኳን አገር ሲነካ ከበደሉ በላይ የአገሩ መደፈር የሚያብከነክነውና
የሚያስቀድመው፣ የምንሞተው ፣ የምንቆስለው ከበደል ሁሉ በላይ አሻግረን ለምናያት አንዲት ኢትዮጵያ ብቻ ስለሆነ ነው! ሌላ አገር የለንም ! አውቀህም ይሁን በስህተት ፣ሰይጣን አሳስቶህም ይሁን ትእቢትህ ገፍቶህ ይችን አማራጭ የሌላት የነፍሳችንን ሳንዱቅ የነካህ ቀን …. የድመቷ ታሪክ ነው የሚከሰተው! ደመነፍሳዊ አገራችንን የመከላከል ህልውናችንን የማስጠበቅ ቁጣ ከነፍሳችን ሰገባ ተመዞ ይወጣል …
ያኔ ማንም ስለቱን ቀና ብሎ የሚያይበት ወኔ አይኖረውም ! ከዛ በኋላ መተንኮስህ እስኪፀፅትህ ቁጣውን አታቆመውም ! እንኳን የተነኮስክ አንተ ቀርቶ እራሱ ግፍ በዝቶበት የተነሳው ኢትዮጵያዊ ራሱን አያቆመውም ! ምክንያቱም ወደፊት ይሁን ወደኋላ ፣ ወደግራ
ይሁን ወደቀኝ … ኢትዮጵያዊ ሌላ አገር የለውም ! ሌላ አገር የለንም !
ከ3000 ዓመታት በፊት በየመን አገር በተገነቡ ሃውልቶች ላይ የኢትዮጵያ ፊደላት ተቀርፀው ተገኝተዋል። የጥንታውያኑ ቀደምቶቻችንን ታላቅነት ለማመን የሚከብዳቸው ቢኖሩም እውነት ግን ቀስ እያለ ይወጣል።
@EliasGebru
ኢትዮጵያዊነት(Ethiopianism)
(በአርአያ እንዲህነው)
"ፍልስፍና የሁለት የግሪክ ቃላት ጥምረት እንደሆነ ምሁራን ያስረዳሉ።ትርጉሙም #የጥበብ ፍቅር ወይም እዉነትንና ሐቅን መፈለግ እንደሆነ ይገለፃል።
የዛሬዉ ቁም ነገሬ ስለፍልስፍና ትርጉም የማዉራት አይደለም። ነገር ግን አንድ ትልቅ ለዉጥ ያመጣ የረዥም ዘመን ታሪክ ያለዉ የፍልስፍና አይነት መናገር ፈልጌ ነዉ።
Ethiopianizm የሚለዉ የፍልስፍና ዘርፍ #የተጀመረዉ ከቅድመ ታሪክ ወይም prehistory ላይ እንደሆን በርካታ የታሪክ መዛግብቶች ያስረዳሉ። ቅድመ ታሪክ ማለት የሰዉ ልጅ ከተፈጠረበት ማለት ሳይሆን የሰዉ ልጅ ታሪኩን በፅሑፍ ሳይሆን በሌላ መንገዶች ይገልፅበት በነበረበት ዘመን ለማለት ነዉ። ይህ ፍልስፍናም በጥቂት ከባቢ የታጠረ ሳይሆን እዉቅያኖስ ባህርን መሻገር የቻለ እንደነበር መረዳት ይኖርብናል።
ይህ ፍልስፍና የተጀመረዉም ኢትዮጵያ ሀገራችን ኢትዮጵያ የሰዉ ዘር መገኛ የጥበብ #ምንጭ የሥልጣኔ ባለቤት በፈጣሪ የተወደደችና ቃልኪዳንም የተገባላት ሀገር መሆኗ አለም የመሰከረዉ ሐቅ ነዉ።
#እንዴት ተጀመረ?
ከላይ እንደጠቀስኩት ሀገራችን የሰዉ ዘር መገኛ የገነት በር ሀገረ እግዚያብሔር የጥንታዊ ሰዉ አዳም መገኛ የዮቶር ምድር የግዮን ወንዝ መፍለቂያ በመሆኗ፣ አባቶቻችንም ጥበበኞች አስተዋዮችና #የእዉቀት ባለቤቶች በመሆናቸዉ አለምን ያስደነቁ ሥነ ህንፃዎች አብያተ መንግስታት ቤተእምነቶች ገንብተዋል።
ከተማን መስርተዉ የግዥ ልዉዉጥ ማድረግ ችለዋል።
ለዚህም ምስክሮቻችን ትናንት ጥፍተዉ በቅሪት አካል Archaeology ምርምር የሚገኙ ከተሞቻችንና ሌሎች ቁሳቁስ እንዲሁም ግዙፍ ህንፃዎቻችን ዛሬም ቆመዉ የምናያቸዉ ነገር ግን መገንባት ያልቻልናቸዉ ህንፃዎቻችን ምስክሮቻችን ናቸዉ።
#ሌላዉ ነገር በፈጣሪ የተወደደች በመጽሐፍ ቅዱስና በቁራን በፈጣሪዋ የተመሰከረላትመሆኗ ።
ይህ እኛ የምንለዉ ሳይሆን የአለም የታሪክ አባት Herodotus the father of history የሚባዉ ስለኢትዮጵያ ሲፅፍ፥ ኢትዮጵያዊያን መልከመልካሞች የማይዋሹ በፈጣሪ የተወደዱ አማልክት የሚወዷቸዉ ቅዱስ ዉሐ ያላቸዉ ሀገር ገንቢ ህዝቦች እያለ ይፅፋል።
ይህ ብቻ አይደለም ዛሬ የቀኝ ግዛት ወራሪዎችና የታሪክ ዘራፊዎች እንደሚሉት ሳይሆን የኛ ታሪክ በወርቅ የተፃፈ ማስረጃ ያለዉ ነዉ።
አዉሮጳዊያን እሱን የጥበብ የፍልስፍና #የምጡቅ እአዕምሮ ባለቤትነትን ለነሱ ሲሰጡ ለኛ ግን የንቀት ንቀታቸዉ የዝንጀሮን ታሪክ በመጥቀስ የ Darwin ዝግመተ ለዉጥ ፍልስፍና በመጥቀስ ሊሰድቡን ይሞክራሉ።
በሌላ ጊዜ ደግሞ የአፍሪቃ ፍልስፍና ጥበብ የተመሠረተዉ በብሶት ላይ የተመሠረተ ነዉ በማለት ይሳለቃሉ።
George G.M jemes የተባለ ፀሐፊ the stolen legacy ወይም የተሰረቀዉ ትሩፋት #በሚለዉ መፅሐፉ ላይ ፍልስፍናን የጀመሩት ኢትዮጵያዉያን እንደሆኑ ከኢትዮጵያውያን ግብፆች እንደተማሩት ከግብፅ ግሪኮች እንደሰረቁት ይናገራል።
በነገራችን ላይ ግብፅ ላይ የምታዩትን pyramid የገነቡት ኢትዮጵያውያን አባቶቻችን ናቸዉ።
#18 ነገስታት ኢትዮጵያውያን ነገስታት ግብፅን አስተዳድረዋታል፣ ገዳማትን ቤተምንግስቶችንም ገንብተዉባታል።
ይህን የተመለከቱ ከዉቅያኖስ ባህርም አልፈዉ የነበሩ ህዝቦች እኛም እንደ ኢትዮጵያ ሀገር እንሰራለን ጥበብን እንፈልጋለን ከተማን አንገነባለን ለሀገራችን እንታመናለን በማለት የህይወት ፍልስፍናቸዉን ምንጭ ኢትዮጵያዊነት ( ethiopianizm) በማለት ሰየሙት።
ይህ ፍልስፍና ሁለተት አይነት መልክ ነበረዉ።
አንደኛዉ ሃይማኖታዊ ሲሆን ሌላኛዉ political ነበር።
ለዚህም ፍልስፍናቸዉ symbolic አድርገዉ #ይጠቀሙት የነበረዉ በዋናነት የኢትዮጵያን ኦርቶዶክስ ተዋህዶቤተክርስቲያንን ነበር።
ይህ ፍልስፍናም በርካታ የአለም ሀገራትን ከሇላ ቀርነትና ድንቁርና በማላቀቅ የራሳቸዉን የሆነ ሥልጣኔ ባለቤት እንዲሆኑ አስችሏቸዋል።
ይህ በንዲህ እንዳለ ከ18ኛ እስከ 19ኛዉ ዘመን እየተቀነቀነ የአፍሪካን ብሎም የጥቁር ህዝቦችን ከባርነት ያላቀቀዉ የpan #africanizm ወይም አፍሪካዊነት የሚለዉ ፍልስፍናም የተወለደዉ ethiopianizm ከሚለዉ አመለካከት የተቀዳ ነዉ።
pan africanizm የሚለዉ ፅንሰ ሐሳብም በርካታ ድሎችን አጎናፅፏል።
በአለም ላይ እንደ ከብት ይሸጡና ይለወጡ የነበሩ ህዝቦችን ከመሸጥና መለወጥ ታድጓል።
በቀኝ ገዦች ተይዘዉ ይማቅቁ አብታቸዉን ይዘረፉ ቆዳቸዉን ይገፈፉ ሥጋቸዉን ለርኩሰት #ይዳርጉ የነበሩ ህዝቦችን ከባርነት ቀንበር ነፃ አዉጥቷል።
በአለም ላይ ያሉ ጥቁር ህዝቦች እኩል ተደማጭነትና እንደሰዉ የመቆጠር ክብርን እንችላለን የሚለዉን ወኔ አስታጥቋል።
ይህ ሁሉ ሲሆን መዘንጋት የሌለብን ነገር ቢኖር ዛሬ ከመጤፍ የማንቆጥራትና የማናዉቃት ሀገራችን በግፈኞች ከተለያዩ አለማት ተገፍተዉና ተሰደዉ የሚመጡ #ህዝቦችን ተቀብላ ሥራተ መንግስትና መሠረታዊ የወታደር ሳይንስ በማስተማር የነፃነትና የሥልጣኔን ቀበቶ ያስታጠቀች ሀገር መሆኗን ነዉ።
እኛ ግን ለሀገራችን ያለን ግንዛቤ በጣም የወረደና ለመማርም የማንፈቅድ ድኩማነ አዕምሮዎች ነን።
ሌላዉ ነገር የኛን ታሪክ ጠላቶቻችን እንዲፅፉልን እንጠብቃለን።
ጠላት ከፃፈልን ደግሞ ምን ሊፅፍ እንደሚችል መገንዘብ ያለብን ይመስለኛል።
ዛሬ ዛሬ አንዳንድ የወንዝ ዳር ምሁራን #ከጠላቶቻችን በወረሱት ስብከት ኢትዮጵያን ትናንት የተፈጠረች፣ ለአለም የነፃነት ምሳሌ ሳይሆን የጨቋኝ ተምሳሌት አድርገዉ ሲመስሏት ማየት አንጥንትን ይሰብራል!!!
©ንቂኢትዮጵያ
ETHIO፯፯፯
@uthopiawyan
....ሁሉም ነገረ ህዝብና ኢትዮጵያ ሲያምር ... ሲደምቅ... የሚበሳጩ ብዙ ጎረቤት ሀገራት ይኖራሉ።
ኢትዮጵያና ሕዝቧ ከዘመናት ድህነታቸው ቀና እንዳይሉ... ዘለዓለሟን እየተፍገመገመች ትቢያዋን እንድትልስ እንድንኮታኮት እንቅልፍ የማይተኙ የሰይጣን ጉዳይ አስፈጻሚያን የሀገሬና ሕዝቧ ጠላቶች ብዙ ናቸው።
እንዚህ ሀገራት ውኩለ ሰይጣን ስለሆኑ ስለርሱ 24ሰዓታት እንቅልፍ አጥተው ያረጠርጡለታል
ኃጢአት ባልንጀራ ይፈልጋልና የዲያብሎስ አባሪ ተባባሪ እንድንሆን ከህዝባችን መሀል በበዙ ማማለያዎች ለክፋታቸው እንድንተባበር ይመለምሉናል።
በነፍሳችንም በስጋችንም ማረፋችን እያበሳጫቸው ርስ በርስ ጉድጓድ እንድንማማስ ታሪክ ይፈበርኩልናል ክፉኛም ይቃወሙናል።
መነሻችንም የነገ መድረሻችንም ስለሚኮሰትራቸው ተባልተን እንድንበተን እና በአጭር እንድንቀር ስለሚፈልጉ ሌተ ቀን ይመክሩብናል።
ኢትዮጵያን ወደ ታላቅነትዋ ለመመለስ
ርስ በርስ እንግባባ
አንናናቅ
እንከባበር
በአንድ ሀገር ልጅነት እንመን
አንጨካከን
ትልቁን ስዕል እንናፍቅ! አሰባሳቢዋን እናት ሀገር ኢትዮጵያን።
እነዚህ ማፍያወች እኔንም አንዳንድ ነገር ለማድረግ ለመጥለፍ ሙከራ አስደርገው ሞክረው ነበር፡፡ ነገር ግን በፈጣሪ ፈቃድ አለሁ፡፡ ”
ዜድ‟ምን አልባት መፅሃፉን ከፊልሙ ተከትሎ ፅፎብን ነው እንዳይሉህ እንጅ?”
ቴዲ‟ከፈለግህ እንካ ተመልከተው፡፡ እኔ በቅርብ የጻፍሁት የአንድነት ጥሪን እንጅ ነቃማይ፣ነቃዮድ፣…..የጻፍኋቸው 2005ዓ.ም ላይ ነው፡፡ አጠቃላይ ሙሉ በሙሉ ከፊልሙ ለይ ያለው ሃሳብ መፅሃፉን ስቀንሰው ለምሳሌ ንግሳና፣ የሚቀበሉበት ጥበብ ተኳቷል፡፡ ማንበብ ትችላለህ?” ብሎ ከሻንጣው አውጥቶ 320 ገፅ የነበረውንና ከነቃማይ ውስጥ ሳይገባ ተቆርጦ የቀረውን ሃሳብ ጥራዝ ሰጠኝ፡፡ እያንዳንዱን ፅሁፍ በጥንቃቄ ስመረምረው ልጁ ከሚናገረው ውጭ ምንም አደስ የተቀነሰም ይሁን የተጨመረ ነገር የለውም፡፡ በፊልሙ ላይ ተጨማሪ ናቸው ያልኋቸውን እነ ዳም ዳም አሃደ እና እነ ሶፋኪያ ወዘተ እንደሁም የንግስና ጥበብና ሃያልነት በጥራዙ ውስጥ ለመመልከት በቃሁ፡፡
ዜድ‟እሽ ቴድ አሁን ምን አስበሃል ስለ ፊልሙ ስለ አጠቃላይ በፊልሙ ጉዳይ የይገባኛል ጥያቄ፣ክስ ነገር ጀምረክ ነበር?”
ቴድ‟ መክሰስ እችላለሁ፡፡ አሁንም መካሰሳችን የት ይቀር ብልህ ነው፡፡ ነገር ግን እኔ በኔ ሃቅም ሃገር ተሸግሬ ከምከስ ሃገሪቱ፣የቱሪዝም ሚኒስቴርና አጠቃላይ ሃብቱ የኢትዮጲያ ነው የሚሉ መክስና የሃገሪቱን የሞራል ካሳ መቀበል አለባቸው፡፡ እኔ የጥበብ ችግር የለብኝም፡፡ ያሰብሁትና የፃፍሁት ነገር መሬት ወርዶ እያየሁ ነው፡፡ እኔ የምከተለው ጥበብ ነው፡፡ ጥበብ ደግሞ የሚትጠቀመው ወሮ በላውን ነው፡፡?”
ዜድ‟በል በርታ ! እንግድሂ በርታ እኛ ሃገር ውስጥ ሁሉ እንዲህ ነው፡፡ እንኳንም ከጠረንገሌወቹ አመለጥክ፡፡ዋናው በህይወት መኖርህ ነው፡፡ በፊልሙ ጉዳይ ግን ቀልድ የለም ክሰስ፡፡ ”
ብየው ተለያየን፡፡
በጣም የሳዝናል፡፡ ምን አልባት ብላክ ፓንተር ድሮ ቢጀምሩት ኖሮ ድሮ ይሰሩት ነበር፡፡ እኔም ከዚህ ተነስቼ ነው የተሰረቀ ፊልሙ፣መፅሃፉ ወይስ ሃገሪቱ ያልሁት፡፡ ይህ የኔ እይታ ሳይሆን እውነታ ነው፡፡ ሁላችሁም የራሳችሁን እይታ ማስቀመጥ ትችላላችሁ፡፡ በተለይ ደግሞ ነቃዮድን ሲወጣ የምትሉትን ትላላችሁ፡፡ ተቃውሟችን ግን መበርታት አለበት፡፡ የተሸጠው የሃገር ታሪክ እንጅ የአንድ ግለሰብ ስራ ብቻ አይደለም፡፡
ሃገራችን የብዙ ወርቆች፣እንቁዎች፣የከበሩ ድንጋዮች ባለቤት ናት፨ቀደምት አባቶቻችንም ለእያንዳንዱ ዕንቁዎች፣ወርቆችና የከበሩ ድንጋዮች ስም ሰይመዋል፨
===== አስማት አዕናቁ ====
በግዕዝ ድንጋዮችን(ማዕድናትን) በሚከተለው አኳኋን ከአይነትና መልክ ተመዝግቦ ይገኛል።።
ዕብን==ድንጋይ የምድር አጥንት
ዕንቁ==ልዩ የከበረ ድንጋይ
ዕብነ አስሐትያ==የውርጭ ድንጋይ
ዕብነ በረድ==የበረዶ ድንጋይ/ነጭ
ዕብነ ኮከህ==ወፈጥ/አለት
ዕብነ ማዕዘንት==የማዕዘን ድንጋይ
ዕብነ መደልው==የድንጋይ ሚዛን
ዕብነ ሰንፔር.....ዕንቁ የከበረ ድንጋይ
ዋርሕ.....የሚያበራ ዕንቁ
በርኔባሉ......ዕንቁ
አቦለ......ከፋይ የወርቅ ድሪም
ቢረሌ.....ብረሌ ዕንቁ ማርያም
ሉል......ምሉዕ ሉል
ጊል.......ሰማያዊ ቀለም ያለው ዕንቁ
ቃማ......የወርቅ ማርዳ
ገማ.......ዝርግፍ የወርቅ አጫዋች
ጥልም......ግምጃ መሳይ ዕንቁ
ዐርሱ.......ዕንቁ
ህያክንቶስ....ግምጃ መሳይ ዕንቁ
ሰርዶንክስ....ጥፍር መሳይ ዕንቁ
ሰፌሮስ......ሰማያዊ ወርቃማ ነቁጥ ያለበት ዕንቁ
ስቅጢስ.......ዕንቁ
ቀንዶራጢስ......ግርሽ ዓይነት ብር ዕንቁ
አማቴስጦስ.....ብጫ ዕንቁ
አቃስ......ዕንቁ
አትራኮስ.....ዕንቁ
አካጥስ.....ዕንቁ
ኢያሰጲድ......እሳት የሚመስል ዕንቁ
ኬፋስ......ዕንቁ
ክሪጶራስ........እሪያናማ ዕንቁ
ክርስጵራክርስ......ዕንቁ
ያስቢስ......ቀይ ዕንቁ
ጵራስስ......ዕንቁ
እለ ቄጥሩ.......የወርቅ የብር ጉብጉብ
እለ ቄጥሩ.....ብጫ ዕንቁ
ሱስናብራ.......ቅጥር ናስ
ባሪራ......ዕንቁ
ተንካር......የከበረ ድንጋይ ዕንቁ
ወራውሬ.......ዕንቁ
ሊጊር.......ግምጃ መሳይ ዕንቁ
ሰንፔር......ዕንቁ
ሶፎር......ዕንቁ
በልግር......የከበረ ድንጋይ
አሥታር........ዕንቁ
አስፋር.......የከበረ ድንጋይ
አክዶር......ዕንቁ
አውፈር........የወርቅ ሥፍራ
ኢያሴሜር......ዕንቁ
ዋህር.......የሚያበራ ዕን
ውህር.......የሚያብረቀርቅ ዕንቁ
ዳር........ዕንቁ
ሊቃ.......ዕንቁ
በጼቃ.......የከበረ ነጭ ድንጋይ
ቤዜቃ.........ዕንቁ
ኅብረ ወርቅ.......ወርቀ ዘቦ ዕንቁ
አቂቅ.......ቢልቃጥ መልክ ዕንቁ
ዐዘቁ.......ቅርጽ ያለው ዕንቁ
ኖብ.......የተለበጠ ወርቅ
በሕትምት.......የወርቅ ማርስ
ብረት.......ነሐስ መሳይ ዕንቁ
ያክንት.......ሰማያዊ ዕንቁ
ቁሪት.........ዕንቁ
ባዝግና.......ዕንቁ
*ሰርድዮን.....ዕንቁ
**ሰርድዮን___ደም የሚመስል ዕንቁ
ሶርዮን___ዕንቁ
ተምያን____ግብዝ ወርቅ
ትጳዝዮን____ዕንቁ
ቴጳዝዮን____ዕንቁ
ቆጳዝዮን____አረንጓዴ ዕንቁ
ንጳላዮን____ዕንቁ
አርከርሴምቶን____ኅብረ ወርቅ ድንጋይ
አክዲን____ዕንቁ
ኤላውጦን____የወርቅ ምድር/አገር
ኦኒክዮን____ዕንቁ
ከልቄዶን____በእሳት የጋለ የነጠረ የመሰለ ዕንቁ
ከርሴምቶን____ዕንቁ
ከርከዴን____ዕንቁ
ጳዜዮን____ዕንቁ
ጳዝዮን____ዕንቁ(እምነ በኀ ቅድስት ቤተክርስቲያን ስርጉት ዓረፋቲሃ ወስእልት በዕንቆጳዝዮን)
ጥካ.......ዕንቁ
ፔካ......ነጭ ዕንቁ
(ሰላም ለአብራክኪ በስብሐተ ልዑል ዘአስተብረካ፥እም አመ ወሀቡኪ ብፅዐ ውስተ ኦሪታዊት ታዕካ፥ማርያም ድንግል መንበር ዘእብነ ፔካ...........)
ከዱዋ____ዕንቁ
አቤግያ___ዕንቁ
አያፌቅያ____ዕንቁ
ጊዛ____ዕንቁ
ባሕርይ____ዕንቁ
ድጋይ____ዕንቁ
ዱሪ____ዕንቁ
ዘምሩድ____የከበረ ድንጋይ
አከቴ____ዕንቁ
ፈርድ____ዕንቁ
ሰደፍ____የዕንቁ ድንጋይ
ጽነፍ____ድሪ ከዕንቁ የተሰራ
አጣጥዕ____ዕንቁ
አፍሬጥልስ____ዕንቁ
ኢያሴጲስ____ዕንቁ
በሃገራችን ስለሚገኙ ዕንቁዎች ዝርዝር ተመልክተናል፨ይህ እንግዲህ ቀደምት አባቶቻችን ምን ያህል ከማዕድናት ጋር ግንኙነት እንደነበራቸው ለዚያውም በራሳችን የግዕዝ ቋንቋ እንዲህ ተመዝግበው ስናይ ከፍተኛ እውቀት እንደነበራቸውና የግዕዝንም ታላቅነት የምናይበት ነው፨ከነዚህ ከተዘረዘሩት በተጨማሪም እጅግ ብዙ የሆኑ ዕንቁዎች እና ሌሎች የከበሩ ማዕድናት መኖራቸውን የሚናገሩ ጥንታዊ ብራናዎች በየገዳማቱ ይገኛሉ፨ዛሬ ወርቅ በተወደደበት ዘመን ቀደምት ኢትዮጵያን ግን ከወርቅ በላይ ዕንቁ እያማረጡ ይጫወቱ ነበር።
======ጥበብ=====
አርበኛ ሌፍተናንት ጄነራል ጃገማ ኬሎ የበጋው መብረቅ!!!
ከፍቅረማርቆስ ደስታ
ጃገማ ኬሎ አጀሴ ገላ
ኦፍጀጁ ባንደ ቀዌን ኦሼ ላማ
ጃጋማን ዱላ ኤፍኬሌቲ ገሌ
ኤቦደን ቀዌ በጅኤ ገሌ
ባንዳ እሼ ገንቱ ኮኬ እሼ ቀሌ
ጃጋማ አካም ጀርተሬ ሌንጫ ጅባት ወለካ
ሳቦንቲቻ ኦሮሞ የእሰ ሌሊ በከካ።
በ1913 ዓ.ም ማክሰኞ ማታ በጥር 20 ምሽት በጅባትና ሜጫ ወረዳ፤ በድንዲ ወረዳ ዮብዲ የሚባል ቦታ ጀግናው ጃገማ ኬሎ ከአባታቸው ከኬሎ ገሮ እና ከእናታቸው ደላንዱ ተወለዱ።
አባታቸው ትልቅ ሠው ስለነበሩ ካላቸውም ሃብትና ንብረት ብዙውን ያወረሱት ለጃገማ በመሆኑ በተጨማሪም አባታቸው ከሰጧቸው ትልቅ ቦታ በመነሳት “አባቱ የመረጠው” በሚል ገና በለጋ እድሜያቸው ለዳኝነት መቀመጥ፣ በገዳ እርከን ፎሌ ደረጃ (ዕድሜያቸው ከሃያ አምስት እስከ ሠላሳ ሁለት) ከደረሱ ወጣቶች ጋር ፈረስ ግልቢያ፣ ጦር ውርወራ፣ ጋሻ አነጋገብና ምክቶሽ፣ ውሃ ዋና ረሃብና ጥም መቋቋምን እየተማሩ በጥሩ ስነምግባር አደጉ።
ፋሺስቱ የጣሊያን መንግሥት በ1928 ዓ.ም. ኢትዮጵያን በመውረር አዲስ አበባን ሚያዚያ 27 ቀን ከተቆጣጠረ በኋላ ወደ ምዕራቡ የአገሪቷ ክፍሎች በመስፋፋት ጭልሞና ጋጂ አካባቢን ተቆጣጥሮ ይዞታውን ለማስፋፋትና ለሚያደርገው ሙከራ የመሸጋገሪያ ምሽግ ጊንጪ አካባቢ በመሥራት ለመጠቀም ሙከራ ሲያደርግ የነበረ ቢሆንም፣ አርበኛው ጃግማ ኬሎ የመሸጋገሪያ መሥመሮችን በመዝጋትና የደፈጣ ውጊያ በማድረግ የጠላትን ጦር በእንቅስቃሴ ሲገቱ ቆይተዋል፡፡
የበጋው መብረቅ በጦር ሜዳ ውሏቸው በፋሺስቱ የጣሊያን ወራሪ ጦር ላይ ካገኙት አንፀባራቂ ድል አንዱ በኅዳር ወር 1933 ዓ.ም. የተገኘው ነው፡፡ ይህም የአዲስ ዓለምን ጽዮን ማርያም ምሽግ በመሰበር 70 የጣሊያን ወታደሮችን በመግደል፣ 1,500 ጠመንጃ በመማረክ፣ እንዲሁም 80 የወገን እስረኞችን በማስፈታት ከፍተኛ ወታደራዊ ድል ተቀዳጅተዋል፡፡
በመጋቢት 1933 ዓ.ም. በጭልሞ ምሽግና ጊንጪ አካባቢ በተደረገ ከፍተኛ ውጊያም የጠላት ጦር ቅስሙ ስለተመታ መኪና ያገኙት ወደ አምቦ ሲሸሹ ሌሎች ወደ አዲስ ዓለም የሸሹ ሲሆን የሸሹትን እግር በእግር መከታተል፣ በየመንገዱ በመቁረጥና በመበተን የጠላት ጦር ከጥቅም ውጭ አድርገዋል።
የአርበኛው የጦር ሜዳ ድል አድራጊነት ዝነኝነት በአገር ሁሉ እየናኘ የመጣ ሲሆን፣ በዚሁ በ1933 ዓ.ም. ወደ ጅማ ከዘመተው የደጃዝማች ገረሱ ዱኪ ጦር ጋርም ወታደራዊ ቅንጅት በመፍጠር በደቡብ ምዕራብ የመሸገውን የፋሽስት ጦርን መውጪያና መግቢያ አሳጥተዋል፡፡
በፋሺስት ላይ የፈጸሙት የላቀ ጀብዱና ታላቅ ገድላቸው ‹‹የበጋው መብረቅ›› የሚል የጀግንነት ስያሜ የተሰጣቸው ጄኔራል ጃገማ አገሪቷ ነፃ ከወጣች በኋላና አፄ ኃይለሥላሴ ከእንግሊዝ ስደት እንደተመለሱ ከፍተኛውን ሚና ከተጫወቱት ድንቅ አርበኞች መካከል ስማቸው በግንባር ቀደምትነት ይጠቀሳል፡፡
የጃገማ ፉከራ
ገዳይ በልጅነቱ
ዶቃ ሳይወጣ ከአንገቱ
ጃጌ ጃገማቸው
እንደገጠመ የሚፈጃቸው
በአባት በእናቱ ኦሮሞ
ፍዳውን አስቆጠረ ከምሮ ከምሮ
ጃገማ አንድ ወንድና አምስት ሴት ልጆች፣ አምስት የልጅ ልጆችና አራት የልጅ ልጅ ልጆችን አፍርተዋል፡፡ መጋቢት 29 ቀን 2009 ዓ.ም ከዚህ አለም በሞት ተለይተዋል።
መስዕዋትነት ከፍለው ነፃ ሃገር ስላስረከቡን ሁሌም ስንዘክርዎት እንኖራለን።
እንኳን ተወለዱልን ጀግናው አባታችን
@uthopiawyan
ዲዮጋን ከዕለታት አንድ ቀን መብራት አብርቶ ከገበያው መካከል ገብቶ ውድያና ወዲህ ሲመላለስ አንድ ግብሩን የሚያውቅ ሰው ቀርቦ "ዲዮጋን! ዛሬስ በቀትር ጊዜ መብራት ይዘህ በገበያ መካከል ትዞር ጀመር? ለምንድነው?" ቢለው።
"ሰው ጠፍቶብኝ እፈልጋለሁ" አለው ዲዮጋን። "ይህ የምታየው ሁሉ ሰው አይደለምን?" ቢለው፣ "አይ! እኔ ይህ እዚህ የሚታየው ሕዝብ ሁሉ ሰው አልለውም" ዲዮጋን መለሰ። "እንዴት?" ቢለው፣ "ይህ የምታየው ሕዝብ ሁሉ ከእውነት የራቀ ሐሰትን ያጸደቀ የራሱን ጥቅም ያወቀ ለግል ምኞቱ የሚገዛ የሰው አካል የለበሰ ውስጡ ከእንስሳዎች ያነሰ ስለሆነ ሰው አልለውም" አለው።
"ታዲያ፣ አንተ የምትፈልገው ሰው እንዴት ያለ ነው?" ቢለው። ዲዮጋንም አለ "የግል ጥቅሙን የማይሻ ሰውን እንደራሱ የሚያይ ሐሰትን የጠላ ለእውነት ያደላ ሲሆን ነው::"
ከ ፍልስፍና መንደር
"እምዬ ያልታደለች" በበረከት በላይነህ
እምዬ ያልታደለች
ተመዘኚ ሲሏት— መዛኝ ነኝ ትላለች
እምዬ ሰከረች
ልትመዘን ወጥታ — መዛኝ ሆና ቀረች!
የቅቤን ስብራት — በቅመም ለማከም
በወቀጣ መዛል — በድለዛ መድከም
የቅቤን ወለምታ — በቅመም ለማሸት
ሲደቁሱ አድረው — ሲቀይጡ ማምሸት
የቅቤን ጉብዝና — በቅመም ለማትጋት
እያመሱ መዋል — እየፈጩ ማንጋት
ይልቅ ግድ የለሽም !
ለቅቤ ጥፍጥና
ለቅቤ መአዛ
ቅመም ከመደቆስ —ቅመም ከማበጠር
ከቅቤያችን በፊት —ከብቶቹን ነው ማንጠር
እንስራ ወዝውዞ
በጢሳጢስ ናውዞ
ለቅቤ ከማማጥ —ለአይብ ከማማጥ
ከወተቱ በፊት — እስቲ ላሟ ትናጥ
ማለቢያ ከማስፋት —ማለቢያ ከማጥበብ
ከግቷ አስቀድሞ
ከሆዷ አስቀድሞ —ምግቧን ነው ማጠብ
ለምሽቱ ድምቀት — ቀኑን ሳይበርዙ
እንዲህ ነው ፊተኞች — ‘ሩቅ የሚጓዙ
እንዲህ ነው መስማማት — መግባባት ከዛፉ
ከስር ሳይመትሩ — አይታይም ጫፉ !
ግራ ነኝ ይለኛል
ቀኝ ነኝ ይለኛል —መሀል ነኝ ይለኛል
ዳሩ ካልተያዘ — መሀል የት ይገኛል?
እውቀት አባ አያልቄ
እውቀት አባ አይፈሬ —ጥያቄ ሲያድለው
ለግራም የራሱ — ግራና ቀኝ አለው
ለቀኝም የራሱ — ቀኝና ግራ አለው
መሃልም ለራሱ — ሌላ መሀል አለው
እይዉ!
ሰው መጠየቅ ትቷል
ሰው ፍለጋ ትቷል —ሰው ማጣጣም ትቷል
ለመንስኤ ዝሏል —ለአመክንዮ ታክቷል
በጥድፊያ ሊያስታግስ —የመሰንበት ሱሱን
ጥያቄ ነው ይላል —የከሸፈ መልሱን
ነፍስያን ተብትቦ —በስሜት ሰንሰለት
መቀያየጥ ሆኗል —መጠያየቅ ማለት
መመሳሰል ሆኗል —መመላለስ ማለት
ኩሬ ነው?
ወንዝ ነው?
ሃይቅ ነው?
ባህር ነው? ጎርፍ ነው?
ገባሩ? ጅረቱ? ማእበሉ? ምንጮቹ?
አዞ አለ? አሳ አለ?
እኮ የምን ጥያቄ ! እኮ የምን ክርክር !
በቃ!
“ዋና ነው!” ይልሽና ከነልብሱ ንክር።
አዎ!
“ዋና ነው!” ይልሻል “አጨብጭቢ!” ይልሻል
“ዋናህስ?” አትበይው
አሽሟጠጠች ብሎ — ችሎት ያቆምሻል
ያው!
ችሎቱ የእነሱ —ችሎታው የሌላ
ይልቅ አጨብጭቢ —አዞ እራቱን ይብላ!
ለንክር ጭብጨባ —ለዝፍዝፍ ጭብጨባ
ሆዱ አሳ ሲለው — አዞ ለሚያረባ
ተመልከች!
ሽንቁራም እውቀትሽ —ንፋሱን ሲነዛ
ከጋላቢሽ ይልቅ —የሚገለብ በዛ
ንፋሳም እውቀትሽ —ውርጩን እየነዛ
ከሚያነደው ይልቅ —የሚያከስለው በዛ
ግልብልብ እውቀትሽ —ወላፈን ደሞዙ
የሚለበለቡት — ከሚበስሉት በዙ።
እይው!
ማእዘን አፍርሶ —ግድግዳ እያደሰ
ወለሉን ሰውቶ —ጣሪያ እየቀለሰ
ቅርንጫፍ ሊያሳምር —ስር እየበጠሰ
እልፍኝ ተደፈረ —አጥር ተገሰሰ
መስማት ጥንቡን —ጣለ ማየት ረከሰ
ቋንቋ መነመነ — ለትርጉም አነሰ
ቆይ እኔ የምልሽ!
ተፈጥሮ ሂደቷ — እንዲህ ሳይጓደል
ለመሮጥ መንደርደር — ግድ ነበር አይደል?!
ታዲያ! ቀረ እኮ ነው ‘ምልሽ
መንደርደር መመርመር መፈከር መዘርዘር
አኩርፈው የሄዱት — በየት በኩል ነበር?
የወል ቀማሽ ሁላ
ድፍርስ እየጠጣ — ሽርክት እየበላ
በግርድፍ አኝኮ — ለግርድፍ ተሻምቶ
“ውጫለሁ!” ይልሻል — ወደ ሆዱ ተፍቶ
የምር ደስ አይልም!
የጥርስን በአንጀት
የጆሮን በምላስ — ʻያፍንጫን በመዳፍ
ግብር እያቀማሙ — ዋጋና ስም መጻፍ
የምር ደስ አይልም!
የልብን ደረት ላይ
የነፍስን ልብስ ላይ— ቀያይጦ በማፍካት
ጣእምን መመርመር —ውበትን መለካት
ደስስስስስ አይልም!
እምዬ!
አትላፊ አትዳሪ ከእንክርዳድሽ
ይልቅ
ወንፊት ግዢ ለወንፊትሽ
ሰፌድ ግዢ ለሰፌድሽ
ቀማሽ ሲደራረብ —ጣእም ተቀያየጠ
ባለቤት ሳያጌጥ —ውበት አመለጠ
ከእህሉም አይደለ
ከቅመሙም አይደል
ጨው አንሶም አይደለ
የምላስ ህመም —ነው ጣእም የገደለ
ምን አረገሽና!
ቀቃዩ ጠባሹ
ከታፊው አማሹ
ወቃጩ ነስናሹ
ለርካሽነትሽ — ይጠየቅ ቀማሹ
ማገዶ ቢራቀቅ
ምጣድ ቢቀያየር — ጋጋሪ ቢንጋጋ
በቀማሽ ልክ ነው —የገበታሽ ዋጋ
ኧረ ሚዛን! ሚዛን!
ኧረ መዛኝ! መዛኝ!
በልክ የሚሰፍር በልክ የሚገዛኝ!
እንደየቃናችን — ማድመቅ ያላወቀ
ቀማሽ አሳነሰን — እያደባለቀ!!!
ውድ ቤተሰቦቻችን ዛሬም እንደ ሌላው ጊዜ አዲስ መፅሐፍ እንድታነቡ እንጋብዛለችዋለን
ቀደም ብላችሁ ምታቁት አንድሮሜዳ የተሰኘ መፅሃፍ በዶክተር ሮዳስ ታደሰ እና በዶክተር ጌትነት ፈለቀ ፅህፈት ለገብያ ቀርቧል።
አሁን ይኸዉ መፅሐፍ በቁጥር ሁለት መመለሱን እያበሰርን እንድታነቡነት እንጋብዛለን።
ጥምቀት በዮርዳኖስ ወንዝ ተከበረ።
በዛሬው ዕለት በእስራኤል (እየሩሳሌም) የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ገዳማት ሊቀጳጳስ ብፁዕ አቡነ እንባቆም እንዲሁም የገዳሙ መነኮሳት እየሱስ ክርስቶስ በተጠመቀበት ቦታ "ዮርዳኖስ ወንዝ" ወርደው በዓሉን አክብረዋል።
በዮርዳኖስ ወንዝ የሚከበረው በዓል ለሁሉም አብያተ ክርስቲያናት ተራ የተሰጠ ሲሆን ፣ ዛሬ የግሪክ ኦርቶዶክስ እና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ነገ የሶሪያና የግብጽ፣ በቀጣይ የአርመን፣ የሩሲያ እና ሌሎችም ያከብራሉ።
የዘንድሮው በዓል የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመከላከል በወጣው መመሪያ መሠረት የእንቅስቃሴ ገደብ ስለተጣለ ለመግባት የተፈቀደው ለተወሰኑ ሰዎች ብቻ በመሆኑ ብዙ ምዕመናን መሄድ አልቻሉም።
"ሰው የተማረ ይግደለኝ ይላል እኔ ግን ወሎዬ ይግደለኝ እላለሁ ብዙ ጊዜ:
.
.ወሎ አንድ እስላም አንድ በግ ያርዳል አርዶ ክርስቲያኑ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ይላል እርሱ ቢስመ አላህ ኢረ አማን ኢረ አሚን ..
.
አንድ ቃል ነው በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ እንደ ማለት ነው።
.
አንዱን በግ አርደው ይሄ በወዲህ በኩል ይጠብሰዋል ያም በወዲያ በኩል ይጠብሰዋል ከዛ በሰላም በፍቅር ይመገባሉ: ይሄ በየትም ሀገር ላይ የሌለ ብስለት ነው "
(ሎሬት ጸጋዬ ገ/መድኅን)
🔶መርበብተ ሰለሞን🔶
ከዕለታት በአንድ ቀን ሰለሞን አንበሳ መደብ ሲወጣ የያክንት ቀለበቱን በዙፋኑ ላይ አኑሯት ወጣ።ሰለሞን በጥበብ ውሀውን በመዘወር አግብቶት በዙፋኑ ስር ይሄድ ነበር።ሰይጣንም የአምላክ ስም የተፃፈበት ነውና እንዳያቃጥለው ፈርቶ ከነምንጣፋ አንስቶ በዙፋኑ ስር በሚሄደው ውሃ ውስጥ የሰለሞን ቀለበቱን ጣለበት።"ወቀለበ ዓሣ" ይላል አንድ ዓሳ ቀለበቱን ቀልቦ ውጧታል።
ሰይጣን ይህን ካደረገ በኃላ ሰለሞን እስኪመለስ ድረስ የሰለሞንን ልብስ መንግስቱን ለብሶ ሰለሞንን በመምሰል በዙፋኑ ላይ ተቀመጠ።ከዚያም ሰለሞን ተመልሶ ሊገባ ቢል ደጅ አጋፋሪው፣ዙፋን ጠባቂው ተመለስ አለው።ሰለሞንም "ኸረ እኔ ንጉሳችሁ ነኝ" አለ።እነርሱም "ስንት ሰለሞን አለ? ሰለሞንስ በዙፋኑ ተቀምጧል ተመለስ" ብለው አባረሩት።ከዚያም ሰለሞን ወጥቶ በገዛ ከተማው የከተማ ለማኝ ሆኗል።
ሰለሞን ለዚህ ያበቃው እና እንዲህ የሆነበት ዋናው ም/ክ ምንድን ነው? ቢባል ከዕለታት በአንድ ቀን አንድ የራበው ሰው በከተማው ሲለምን ሰምቶት "ይህ ሰው ምንድን ነው?" ብሎ ጠየቀ። እነርሱም "ርቦት ይለምናል" አሉት።ሰለሞንም ይህን ሰምቶ "ረኀብ ምንድን ናት?ቀንድ አላት ትዋጋለች?ወይስ ጅራት አላት ትጋረፋለች?ረኀቡን አምጥታችሁ አሳዩኝ" ብሎ ነበርና እግዚአብሄር ትዕቢት ስለማይወድ ሊቀጣውና ሊያስተምረው ነው።ምክንያቱም ሰለሞን የንጉስ ልጅ ስለሆነ ሳይርበው ይበላል ሳይጠማው ይጠጣል ከእልፍኝ ወጥቶ ወደ አዳራሽ ከአዳራሽ ወጥቶ ወደ እልፍኝ እያለ በማር በወተት በሞግዚት ስላደገ በኃላም ስለነገሰ ረኀብን አያቅምና።
ሰለሞንም መስሎ ዙፋን ላይ የተቀመጠው ሰይጣንም እጅ ቢነሱት የማይመልስ ፍርድ የማይሰማ የማይፈርድና የማይተች ኾነ።በቤተ መንግስትም ያሉት ይህ ነገር ግራ ቢገባቸውና ቢቸግራቸው በዘመናቸው ሳቤላ(ኤልዳና) ወደምትባል ነቢዪት ሄደው "የሰለሞን ነገር ቸገረን እጅ ቢነሱት የማይመልስ ፍርድ የማይሰማ ሆነ" አሏት።
ርሷም ይህን ከሰማች በኃላ ቅዳሜ ቅዳሜ ሰለሞን ዳግም ኅግ ያስነብብ ስለነበር "መፃህፋን በፊቱ ዘርግታችሁ ንባቡን እያልከሰከሳችሁ እያጠፋፋችሁ አንብቡ ሰለሞን እንደሆነ ምሁር ነውና አያስችለውም ንባቡን ያርማችኋል ይመልሳችኋል" አለቻቸው።እነርሱም በአጠገቡ ሆነው ንባቡን እያበላሹ ቢያነቡ የማይመልሳቸው(የማያርማቸው) ሆነ።እነርሱም ሰለሞን እንዳልሆነ በዚህ አውቀው "ጊዜ ይግለፀው" ብለው ዝም አሉ።
ንጉስ ሰለሞንም በገዛ ከተማው እየዞረ ቢለምንም ሰይጣን የሰውን ልቦና አጨክኖበት የሚመፀውተው አጥቶ "እውን ይህን የመሰለ ጎበዝ ርቦት ነው?ሰላይ ነው እንጂ" እያሉት ምግብ አጣ።በሰባተኛው ቀን ከመሠግራነ ዓሣ(ዓሣ ከሚያሰግሩ) ሰዎች ሂዶ ቢለምን እስራዔል ሞቶ ያደረ ዓሣ አይበሉምና ዓሣውን ሰጡት።
ሰለሞንም በጣም ስለራበው የአሳው ሆድ ዕቃውን አውጥቼ እበላለሁ ብሎ የአሣውን አፍ ቢፈረቅቅ በያክንት ዕንቁ የተሰራችው ሰይጣን ከባህር ውስጥ ወርውሯት ይኸው ዓሣ የዋጣት ቀለበቱ ኩል ብላ ወደቀች።ሰለሞንም በመገረም "ቀለበቴ ከዚህ ምን አመጣሽ" ብሎ ከጣቱ ላይ መልሶ ቢያደርጋት የቀድሞ ክብሩ ተመልሶለት በዚያ የነበሩ ሸማ አጣቢው ወገን ጠባቂው ባለ ፈረሱ ባለ ሰረገላው ሁሉ "ንጉሳችን ከዚህ ምን አመጣው?" ብለው ክብብ አድርገውታል።
በዚህ ጊዜ ሰለሞን ከመንግስቴ ያወጣኝ ሰይጣን አለና እንዳያመልጣችሁ ብሎ ፀሎት እየፀለየ ሂዶ ያንን ልቡሰ ስጋ ጋኔን ከያዘው በኃላ መሬቱን ቆፍሮ ከትቶት አምልጦ እንዳይወጣ "መርበብተ ሰለሞን(የሰለሞን መረብ(ወጥመድ))" በሚባል ስመ አምላክ በተፃፈበት ደፍኖበታል ዐትሞበታል።በዚህ ቀለበት ምክንያት የያዛቸውን ልቡሳነ ሥጋ አጋንንትን አስሮ ገሚሱን ጭቃ ረጋጭ፣ገሚሱን ግንብ ገንቢ፣ገሚሱን ድንጋይ ፈላጭ፣ውሀ ቀጂ አድርጓቸዋል በኃላም በህንድ አስሯቸዋል ይላሉ መተርጉማን "ወአክሊል ለሰለሞን" በሚል ትርጓሜ ሐተታቸው ላይ።
ይህም "መርበብተ ሰለሞን" ወይም "ማህተመ ሰለሞን" በመባልም ይታወቃል።ይህን "መርበብተ ሰለሞን" የሚባለውን ሰይጣን የታሰረበት መረብ ወይም ወጥመድ በኢትዮጲያ የነበሩ ባለጠልሰሞች በስዕል መልኩ በብዙ ጥቅሎች ላይ ይስሉታል።በዚህ "መርበብተ ሰለሞን" በሚባለው የኢትዮጲያ ስዕሎች እጅግ በርካታ ጥናት በባሕር ማዶ ምሁራን በጥልቀት ተደርጓል።
ይህ "መርበብተ ሰለሞን" የተሰኘው ሰይጣን የታሰረበት መረብ ወይም ወጥመድ በኢትዮጲያ ጣና ሐይቅ ዳርቻ ባህር ውስጥ ታስሮ እንደሚገኝ አንዳንድ ምሁራንና ሊቃውንት ይናገራሉ
© ሚስጥረኢትዮጵያ
👉 ስለ ናዚ እና ስለ አዶልፍ ሂትለር ትንሽ እንበል ...👈
👉1.የናዚዎች የዘረኝነት ጭፍጨፋ ሆሎካስት ተብሎ ይጠራል ፡፡
👉2.ሆሎካስት የተጀመረው በ 1933 ልክ አዶልፍ ሂትለር ስልጣን ሲይዝ ሲሆን ያበቃው ደሞ በ 1945 ናዚ ሲሸነፍ ነው ፡፡
👉3.በሰአቱ በአውሮፓ 9 ሚሊየን ጂዊሾች ይኖሩ የነበረ ሲሆን ሂትለር ከ 5-6 ሚልን የሚሆኑትን አስገድሏል ፡፡
👉4.ጅዊሾችን ማግባት ወይም ከነሱ ጋ ግንኙነት መፈፀም የተከለከለ ነበር ፡፡
👉5.ጅዊሽ የሆነ ማንኛውም ህፃን( እርጉዝ እናቶች ሳይቀሩ ) አይታለፉም ፡፡ ይገደላሉ ፡፡
👉6,,,3.4 ሚልየን የናዚ ወታደሮች ጦርነቱ ካለቀ በዋላ በአሜሪካ በራሺያና በእንግሊዝ ተባባሪነት ተቀጥተዋል ፡፡
👉7.የናዚ አመራሮች ፕላናቸውን ሆሎካስት ብለው አይጠሩትም ፡፡ Final solution እንጂ ፡፡ ወይም ባጭሩ የኮድ ቋንቋቸው Final solution ይባላል ፡፡
👉8.ናዚ የሚለው ቃል NAZI (“Nationalsozialistishe Deutsche
Arbeiterpartei” (“National Socialist German Worker’s Party”).የሚለውን ይወክላል ፡፡
👉9.ሂትለር 6 ትላልቅ የመግደያ ካምፖችን አሰረቷል ፡፡ 1.Chelmno, 2.Belzec, 3.Sobibor 4.Treblinka 5,Auschwitz and Majdanek 5 እና 6 ሰዎች በአሰቃቂ ሁኔታ የሚገደሉባቸው ካምፓች ናቸው ፡፡
👉10. አምስተኛው ካምፕ ተልቁና ብዙ ሰው (1.1 ሚልየን ሰው) የተገደለበት ካምፕ ነው፡፡ ይህካምፕ አሁንም ድረስ ያለ ሲሆን በአመት በ 500,000 ሰዎች ይጎበኛል ፡፡
👉11. ሰዎች ወደካምፖቹ የሚገቡት ለሻወር ነው ተብለው ተታለው ነበር ፡፡
👉12.ከሞታቸው በፊት አንዳንዶቹ ሰዎች ላይ ልክ እንደ አይጥ medical experiment test ይደረግባቸው ነበር ፡፡
👉13.አንድ ቀን ሂትለር የአጎቱን ልጅ አፓርታማ በስህተት አፈንድቷል ፡፡
👉14. አዶልፍ ሂትለር በአጠቃላይ 11 ሚሊየን ሰዎችን አስገድሏል ፡፡
👉15. ከዚህ ሁሉ ሞት በዋላ ሂትለር በ 56 አመቱ April 30 1945 አ.ም መሸነፉን ሲያውቅ እራሱን በገዛ ሽጉጡ ገደሏል ይባላል እንጂ ምንም የሚታወቅ ነገር የለም ሰዉየዉ ተሰዉሯል።
@uthopiawyan
በኢትዮጵያ ጥንታዊ ከተማ
ረቡዕ 2019/12/11
የቅሪተ አካል ተመራማሪዎች በኢትዮጵያ ጥንታዊ ከተማ ማግኘታቸውን አስታወቁ፡፡ ከተማዋ ለ1400 ዓመታት ተቀብራ ቆይታለች የተባለ ሲሆን ጥንታዊ ከተማዋ ለብዙ መቶ ዓመታት ምስራቅ አፍሪካን ከመቆጣጠርም ባለፈ እንደ ሮም ካሉ ሌሎች ታላላቅ ኃይሎች ጋር የንግድ ልውውጥ ታደርግ እንደነበር ተነግሯል። የአክሱም ስልጣኔ የምስራቅ አፍሪካ እና የአረብ አካባቢዎችን እንደ አውሮፓውያኑ ከክርስቶስ ልደት በፊት ከ80 ዓመተ ዓለም እስከ 825ዓ.ም. ድረስ የተቆጣጠረ ሲሆን ይህም ከሮም ከፋርስ እና ቻይና ስልጣኔ ጋር እኩል የሚለካ ነው። ይህች ቀዳሚ የስልጣኔ ምንጭ የሆነች ከተማ በኢትዮጵያውያን ዘንድ በታሪክ እንደማትታወቅ የገለፁት የሜሪላንድ ባልቲሞር ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎች ከተማዋ ከአከሱም ስልጣኔ በፊት የነበረች ናት ብለዋል። በአፍሪካ ውስጥ ትልቁ ስልጣኔ እንደሆነም ነው በጥናታችን አረጋግጠናል ያሉት፡፡ ‘ቤተ ሳማቲ’ የሚባለው ይህ ቦታ ትናንሽ ሕንፃዎችን ፣ ቤቶችን እና ባዛሊካ ተብሎ የሚታወቅ አንድ ትልቅ አራት ማዕዘን ቅርፅ ያለው ሕንፃንም የያዘ ነው። ይህ አራት መዓዘን ህንፃ በሮማ ግዛት ውስጥ በመጀመሪያ ለሕዝብ አስተዳደር እና ለፍርድ ቤቶች ፣በኋላ ላይ ደግሞ የክርስትና አምልኮ ቦታዎች ሆነው ያገለግሉ ነበር ፡፡ የአክሱም ስልጣኔ እንደ ግብጽ ግሪክና ሮም ስልጣኔ የበለጠ እንዲታወቅ እንሰራለን ብለዋል የባልቲሞር ተመራማሪዎች፡፡ የአክሱም ስልጣኔ ከጥንታዊ ስልጣንዎች አንዱና ጠንካራው መሆኑን ማሳወቅ ቀዳሚ ስራቸው እንደሆነም ገልጸዋል ፡፡ እንደ ዴይሊ ሜል ዘገባ በቤተ ሳማቲ ከተገኙ ግኝቶች መካከል የወርቅ ቀለበቶች የነበሩ ሲሆን ዲዛይኑ በሮማ ስልጣኔ ዘመን የነበሩትን ይመስላል ፡፡ በአጠቃላይ አክሱም ስልጣኔና የተገኘችው ከተማ አካባቢው ቀደምት የስልጣኔ ቦታመሆኑን እንደሚያመለክት የተገለጸ ሲሆን በአካባቢው ከፍተኛ የንግድ ለውውጥ መኖሩንም ያሳያል ተብሏል፡፡
ምንጭ፡- ዴይሊ ሜይል
https://am.al-ain.com/article/new-ancient-city-found-in-ethiopia
@uthopiawyan
🛑🛑🛑🛑🛑🛑🛑🛑URGENT🛑🛑🛑🛑🛑🛑🛑🛑🛑🛑🛑
🛑🛑🛑🛑🛑🛑🛑🛑🛑🛑🛑🛑🛑🛑🛑🛑🛑🛑🛑🛑🛑🛑
🇪🇹 አሳፋሪውን የወሲብ ቀስቃሽ ዘፈን ከዩቲውብ ለማውረድ reportዎ ያስፈልገናል
ይሄን ከሀገራችን እሴት ያፈነገጠ ዘፈን report በማድረግ ከዩቲውብ እንዲወርድ ይተባበሩን። ዛሬ ላይ እንደቀላል ካለፍነው ባጭር ጊዜ የዚህ አይነት ክሊፖች እየተስፋፉ የሚሄዱ ነው የሚሆነው።
Report ለማረግ ከስር ያለውን ሊንክ በመጫን ከቪዲዮ ስር በስተቀኝ የሚገኝውን 'Report' የሚለውን በመጫን በ Gmail አካውንቶ በመግባት(sign in በማረግ) sexual content -> graphic sexual activity የሚለውን መምረጥ ነው።
#Share በማረግም መልክቱን አዳርሱ
https://www.youtube.com/watch?v=EevL0PfQGDg
ብላክ ፓንተር ኢትዮጵያዊ አልፃፈውም ይላሉ። ፀሐፊው አሜሪካዊ ነው ይሉታል። መልሰው ደግሞ ታሪኩ የኢትዮጵያ ነው ይላሉ። አክለውም ባህዳር አካባቢ የምትገኝ ቦታ እንደሆነች የእኛ የሆኑ የቅርብ ሰዎች ይመሰክራሉ።
እንዴት መጣ መረጃውስ ከየት ተገኘ የሚል ጥያቄ ማንሳት አይፈለገም። ይሄን ባሉ ጊዜ የሚፈጠር መዘዝ አለና። እናም አይሉም።
እሥካሁን ብዙ የሚዲያ አካላትን ሣገላብጥ አዲሥ አድማስ ጋዜጣ ላይ ስለብላክ ፓንተር ተፅፎ አንብቢያለሁ።
ይሄውም ይሄ ጋዜጣ በስፋት ብላክ ፓንተርን በጥርጣሬ አይን ከማየቱም ባሻገር ሁነኛ የመልስ መምቻ ሰጥቷል።
እንደገዜጣው ዘገባ አፍሪካ ደስ አይልሽም ወይ?
በሚሉ ጥያቄዎችን አካቶ ሲያበቃ የፓተንት ችግር ካልሆነ በስተቀር ብላክ ፓንተርን የፀፈው አሜሪካዊ ሊሆን አይችልም ይላል።
ያውም አፍሪካን አሸናፊ አድርጎ፣ ያውም ኢትዮጵየን ገናና እና በቴክኖሎጅ የበለፀገች ሀገር አድርጎ በሆሊውድ አለም ቀፍ ሊየስተዋውቅ የሚችል ነጭ መግኘት ዘበት ነው በማለት ፅፏል።
ይሄን ያሉ ከብዙሃኑ ሚዲያ አንዱ ነው። ሌሎች ግን ስለብላክ ፓንተር አፋቸውን ሞለተው ያወሩ እና ስለ ፀሐፊው ማውራት ይደክማቸዋል።
ዛሬ ይሄን እሳቤ አልፎ በሁለተኛ ደረጃም ደግሞ የደረሲ ቴዎድሮስ መዝገቡ ሁለተኛ ሥራው ነቃዮድ በአውሮፓ ሠማይ ላይ እየተውለበለበ ነው።
ትናንት ብላክ ፓንተር ወይም ነቃማይ አለምን ጉድ አሰኝቷል። የዛሬው ነቃዮድስ ምን ይባል ይሆን?
ጀግናን ጀግና ብትል ኢትዮጵያ ምን ታጣ ይሆን? ይሄን አወዛጋቢ ጥያቄስ አንስታ ማንም ከሚልከሰከስበት ሚድያ ላይ ደራሲው ቢጠየቅ እና መልስ ቢሰጥ ምን ታጣ ይሆን?
ነውስ አሜሪካ ሚሳኤል ወደ ኢትዮጵያ ታስወነጭፍ ይሆን?
ጥያቄው ለሁሉም ይመለከታል! አዳርሱት።
......ዮርዳኖስ ሐበሻ....
የተዘረፈው ፊልሙ፣መፅሃፉ ወይስ ሃገሪቱ!!!!!!
ነቃማይ የሚል የደራሲ ቴወድሮስ መዝገቡን መፅሃፍ ያላነበበ ወጣት ያለ አይመስለኝም፡፡ ነቃማይ ምጡቅ ሰማይ የጥበብ መፅሃፍ እንደደሆነና የጥበብን ሃያልነት በተለይ እኛ ኢትዮጲያዊያን ምን ያህል ጠቢባን አባቶችና አያቶች እንደነበሩንና ጥበቡ ተወርውሮ የወረደ እንደሆነ ያትታል፡፡ አሁን ስለ መፅኃፍ ምንም ማለት አልፈልግም፡፡ አሁን ማውራት የምፈልገው ስለ Black panther filem ነው፡፡ ይህን ፊልም ስመለከት ነቃማይ የሚባለው መፅሃፍ ሃሳብ መሆኑ ግራ አጋብቶኛል፡፡ ስለዚህ ወይ መፅሃፉ ተሰርቋል ወይ ተተርጉሟል አሊያም የሆነ ጨዋታ እንዳለው የራሴን ግምት ያዝሁ፡፡ በነገራችን ላይ ፊልሙ በዩቲዩብ 43‚ 437‚702 በላይ ተመልካች ያገኘ ባለፈው ሳምንት ነው፡፡እንዲሁም 600 ሚሊዮን ዶላር ወደ 18 ቢሊዮን ብር ገቢ አስገኝቷል፡፡
ስለዚህ ፊልም መረጃወችን ሳሰባሰብ Black Panther expected to be first film shown in Saudi Arabian cinema after 35 years ban lifts…..ወዘተ የሚሉ አጥጋቢ ያልሆኑ መረጃወችን ለማግኘት ችያለሁ፡፡
ታሪኩ ሙሉ በሙሉ የምስራቅ አፍሪካ ታሪክ እንደሆነ ፊልሙን ያየ መመስከር ይችላል፡፡ እኔ ከመነሻው እስከ መድረሻው የፊልሙ ሃሳብና የመፅሃፉ ሃሳብ እየተመሳሰለ ግራ አጋብቶኝ ነበር፡፡ ከመፅሃፉ ሃሳብ ወስዶ የፊልም ዳሬክተሩ የሆነ ሽሽት ለማድረግ አንዳንድ አዳዲስ ነገሮችን ጨምሮበታል፡፡
ቢሆንም ከመፅሃፉ ጋር የተወሰዱ ሃሳቦች በሙሉ እንደሚከተለው ተራ ቁጥሮች ይስተዋላል፡፡
ከላይ ሚመለከቱት ተራ ቁ.1. ፊልሙ ከሰማይ ተወረወረ እና የአፍሪካ አህጉርን መታ መፅሃፉ ከላይ ከሰማይ የተላከ ጥበብ ነው ይለዋል፡፡ነቃማይ እራሱ ነው፡፡
2. ፊልሙ ያ ከሰማይ የተወረወረ የኮከብ ስባሪ በእፅዋትና በስነ ምህዳር ላይ ጉዳት አደረሰ ይላል መፅላፉ ከሰማይ የተወረወረ ነቃማይ አለም የምትፈልገው ሃያል ምስጢር ቀጥ ብሎ ሲወርድ……የሆነ ተጽኖ በምድር ላይ አሳደረሰ፡፡
3. በመፃፉ የተሳለው ምድር ኢትዮጲያ ከአባይ ሸለቆ አካባቢ ሲሆን በፊልሙ የተሳለው ዋካንዳ ተብሎ የሚጠራው ግዛት ነው፡፡ በነገራችን ላይ ምስራቅ አፍሪካ ዋካንዳ ተብሎ የተሰየመው በመፅሃፉ ላይ ቀራኒዮ የሚለው ቃል ነው፡፡ ምክንያቱም በምስራቅ አፍሪካ የተጠኑ ከ235 በላይ አለም አቀፍ ጥናቶች ላይ አንድም ዋካንዳ የሚባል ግዛት አለመኖሩና ታሪኩ የአባይ ሸለቆ እስከ ኦሞ ወንዝ ድረስ ያለውን መቼት ፊልሙ ይተርካል፡፡
4. በ4 ቁጥር ላይ የተቀመጡት የኢትዮጲያ ህዝቦች እንደሆኑ ሁላችንም የምናቀው ነው፡፡ በፊልሙ ደግሞ አንድ የዋካንዳ ጎሳ አድርጎ ስሏቸዋል፡፡ እነዚህ ህዝቦች አፍሪካ ምድር ላይ ከሙርሲ ጎሳወች ጀምሮ እስከ ናጀሪያ ቢፈለጉ የሚገኙት በኦሞ ወንዝ ዳርቻ ብቻ መሆኑ፡፡
5. ዲቻላ የሚባለው ተዋናይ የሚጠጣው የንግስና ጥበብ እፅዋቱ ኢትዮጲያ ውስጥ የአንድ ሃረግ አበባ ሆኖ መገኘቱና በመፅሃፉ ውስጥም ተቆርጦ የቀረ ታሪክ መኖሩ፡፡
6. ኒያ ከፀጉሯ እያወረደች ጠላት ስትከላከልበት የነበረ ነቃማይ በጨረረ ሰወችን ሲገድል የነበረ አለም ቀረ የሰጣት ነቃማይ ምስጢር ነው፡፡
7. በመፅሃፉ ውስጥ ተቆርጦ ወደ ነቃዮድ የተሸጋገረውን ዳም ዳም የሚባሉ ሮቦቶች ናቸው፡፡
8. ላይ ከጣቱ ባሉ ቀለበቶች ከሰማይ ሮቦት እንዲወርድ የጠራበት ምስጢር ሲሆን 9 ቁጥር ላይ የሚታየው አዲስ የረቀቀ ቴክሎሎጅ ውጤት /ሮቦት ወረደ፡፡
ይህን ሁሉ ከተመለከትሁ በኋላ የግዴታ ወደ ነቃማይ ደራሲ ወጣት ቴወድሮስ መዝገቡ አመራሁና አንዳንድ ነገሮችን ስለ ፊልሙና ስለ መፅሃፉ ጠየቅሁ፡፡ ምን አልባት የመፅሃፉን ሃሳብ እስክሪፕት ሸጦላቸው ከሆነ በሚል ጥርጣሬ ነበር ወደ ልጁ ያመራሁት፡፡
ከወጣቱ ጋር ያደረግሁትን ቃለ ምልልስ ቃል በቃል ላስቃኛችሁ፡፡
ዜድ ‟ቴድ ብላክ ፓንተርና ነቃማይን እንዴት አየሃቸው ማን ነው ሌባው አንተ ወይስ እነሱ?ፊልሙን በትክክል ካየሀው ታሪኩም የፊልሙ መቼትም ከአባይ ሸለቆ እስከ ኦሞ ወንዝ የሚያጠነጥን ታሪክ ነው”
ቴዲ ከትከት ብሎ ሳቀና‟እኔ ፊልሙን እንዳየሁት በጣም ተሰምቶኝ ነበር፡፡ ምክንያቱም በፊልሙ እኔ ለምን አልከበርሁም፣ተጠቃሚ መሆን አለብኝ የሚል እሳቤ ሳይሆን እንዴት የሃገርን ታሪክ ያክል ካለ ማንም ፍቃድ ሃሰቡን ወስደው ይሰሩታል ነው፡፡ ፊልሙንም ቅደም ተከተሉን እያዘበራረቁ ሰሩት፣ይህም ወይ የፊልሙ ዳሬክተር መፅሃፉን በትክክል አልተረዳውም ወይ መፅሃፉን ለመሸሸ ሲል የተጠነቀቀው እና ሌላ አንዳንድ ነገሮችን ጨማምሮ ከመፃፉ ሽሽት ያደረገ አስመስሎታል እንጅ ፊልሙ ከመፃፉ የሚለየው ነገር የለው፡፡በቀላሉ ዲቻላና የዲቻላ አባት አለም ቀረና መህርጌታ ግሩም ብየ ያስቀመጥኋቸው አላባዊያን ናቸው፡፡”
ዜድ ‟እሽ ማለቴ ተዘረፍሁ የምትልበት አጋጣሚ ካለ ብታብራራልኝ?ወይም የመፅሃፉን ሃሳብ ሙሉ በሙሉ ነገርሁት ሰው አለ የምትለው ነገር ካለህ ወይም እንዴት እንደተረጎሙት መፅሃፉን ቀጥታ ውስደው ወይስ ሳይታተም ሃሳቡን አግንተውት ነው ትላለህ?”
ቴዲ‟መዘረፉንማ አንተም እያየከው ነው፡፡ ሁሉም ሰው አይቶታል፡፡ ነቃማይን አንብቦ በተረዳው መጠን ብላክ ፓንተር ነው ብለዋል፡፡መፅሃፉን ያላበቡት ደግሞ ብላክ ፓንተር ኢትዮጲያዊ ፊልም ነው፡፡ለምን ሃገሪቱን ሳያስፈቅዱ ሰሩት እያሉ ተቃውሞ እያደረጉ ነው፡፡”
ዜድ‟ምን አልባት ግልፅ ያልሆነልኝ ነገር እንዴት አድርገው ወሰዱብህ ነው?”
ቴዲ ‟ወዳጄ ታሪኩ ብዙ ነው፡፡ ነሃሴ ወር 2009ዓ.ም አንድ የማዕድን ቁፋሮ ላይ የተሰማራ ድርጅት ማናጀር በሆኑ ሰወች በኩል አገኘሁት፡፡ የመፅሃፉን ሃሳብ ስነግረው በጣም ወደደውና እንድሸጥላቸው ጠየቁኝ፡፡ እኔም እሽ ብየ 750ሺህ ብር እንግዛህ ሲሉ ችግር የለውም አልኋቸውና እንድሰጣቸው ጠየቁኝ፡፡ 750ሺህ ጊዜዊ እንጅ ዋና ክፍያህ አይደለም ሲሉኝ ከፍላሸ ኮፒ አድርጌ ሰጠኋቸው፡፡ ከዛም ምንም ብር ሳይሰጡኝ ስራውን ይዛው ከሃያ ቀን በላይ አመላለሱኝ፡፡ ከዛ በኋላም አንድ ጊዜ አንድ ሰው ይየው ሌላ ጊዜ ሌላ ሰው ይየው እያሉ እኔን ወደ ኋላ ማንሸራተት ጀመሩ፡፡ ከዛም ከአንድ ወር በኋላ ከ750 ወደ 500ሺህ ከዛም ወደ 300ሺ ከዛም ወደ 200ሺ ውለው አድረው ምልልስ ሲበዛብኝ 60ሺ ሽጥ አሉኝ፡፡ የሚያቀርቡልኝን ሁሉ አማራጮች እሽ እሽ እያለሁ ነበር፡፡ ምክንያቱም እነሱ ለማሳተም ሁሉን ነገር ጨርሰው ስለነበር አንዴ ከጀ በወጣ ነገር የነበረኝ አማራጭ እሽ ነበር፡፡ በዚህ ወቅት መፅሃፉን የወሰደብኝ ሰው በተለያዩ ቋንቋወች ከውጭ ሰወች ጋር ይደዋወል ነበር፡፡ በዛ ላይ እኔን ሲያገኘኝ ይርበተበታል፡፡የምጠይቀውን ሁሉ እሽ ይላል፡፡ቢሮ ቀጥሮኝ ስሄድ አሁን አሁን እያለ ብዙ ነገር ካንገላታኝ በኋላ 40ሺህ ብር ካልሆነ አንስማማም አሉኝ፡፡ ከዛም እኔ እሽ ማለት ግዴታየ ነበር፡፡ በዚህ አርባ ሽህ ብርም ሊያሳትሙት ተስማምተን አንዴ 20ሺህ ብር በቼክ ሌላ ጊዜ 6ሺህ ብር ፃፉልኝ፡፡ እኔም አሁን ታሁን ሊያሳትሙት ነው እያልሁ ስጠብቅና ቀሪ ሂሳቤን ሲጠይቅ ስራህን ውሰድ አንፈልገውም አሉኝ፡፡ ይህ ጊዜ ከሰጠኋቸው ከ8 ወር በኋላ ነበር፡፡ በዛ ወቅት አስተርጉሞ ሸጦት እንደጨረሸ የገባኝ ፊልሙ ስመለከት ነው፡፡ እኔም ምንም ማለት አይደለም ሰርታችሁት ቢሆን መልካም ነበር ብየ የሰጠኋቸውን 377 ገፅ መፅሃፍ ወደ 273 ገፅ ዝቅ አድር ዋና የጥበቡን ቁልፍ አስቀርቼ በሌላ ህትመት ቤት ታተመ፡፡ ልክ መፅሃፉ እንደወጣ ፊልሙም አብሮ ወጣ፡፡ ማለተም 2010 ሚያዚያ ወር ላይ ለእይታ በቃ፡፡እንዲያውም
የጃገማ ፀሃይ!!!!!!!
ጠየቀችው ልጅት፣
ይህንን ሳተና፣ይህንን ጅግሳ፣
ሲራመድ የኖረ፣
ሲጨፍር የኖረ፣
በባንዳ መቃብር፣በሰላቶ ሬሳ።
ደግማ ጠየቀችው፣
ጃገማ ግን ማነው????
የኬሎ ልጅ ማነው????
እንደ አደይ አበባ፣
እንደ መስቀሏ ወፍ፣ የተሽሞነሞነው፣
በአበሻ ጦር ሜዳ፣
በዲሞፍተር ቃንቄ፤ ሜዳይ ያሸገነው?
ኧረ ይህ ሰው ማነው?????
እየገራረማት፣
እየደናነቃት፣
ዘመን በማይሽረው፣
በአባቷ ወላፈን፣ በቃንቄው ተገርማ፣
ጠየቀች አባቷን፣
በጨዋ ልጅ ወገብ፣ ጎንበስ ቀለስ ብላ፣
ጃገማ አባ ዳማ፣
የበረሃው ግለት፣ የናዳው ስባሪ፣
የጠላትን ምሽግ፣
የሰላቶን ክምር ደርምሶ ፎካሪ።
ጀግና ልብ እንጅ የለውም ምላስ፤
እንኳንስ ስሙ ጥላው የሚዋስ።
ብሎ ጃገማ፤
አልጋውን ንቆ ድንገት ቀጥ አለ፤
በሃሳብ ጥሻ፤
በትዝታ ጦር እየሸለለ።
""" ዘራፍ!!!!!!!
ዘራፍ!!!!!!
ዘራፍ ፣አካኪ ዘራፍ!!!!!!!!
ጃገማ ኬሎ፣
የጦቢያ ዶቃ፣ የዳማ ፈረስ፣
ጎራው ላይ ሲዘልቅ፣ ምሽግ እሚያፈርስ።
ሃይ ዘራፍ ብሎ፣ ዘሎ ሲገባ፣
ይዝረጠረጣል ባንዳና ሌባ።
ዘራፍ ጃገማ ባለውጅግራ፣
ጎጆ መስርቷል፣
ቃል ኪዳን አስሯል፣ ከጦቢያ ጋራ።
ስማ ንገረው፣ ያን የባንዳ ዘር፣
እንጫጫዋለሁ፣ እንደ ጎመንዘር!!!!
የበጋው መብረቅ፣ የእሳቱ ጉማጅ፣
እንደ እርጥብ ቃሪያ፣
የሚለበልብ፣ ስሙ የሚፋጅ፣
የአባ ዳማ ልጅ፣
ከዘር ማንዘሩ፣ ጠላት አዋራጅ።""
"""
ብሎ ሲፎክር
እንደ ፈላ መጅ፣ እንደጀበና፣
ፊቱ ለበሰ ፣
ኢትዮጲያ የሚል፤ ቀስተ ደመና።
ይች ልጅ ጠየቀች፣
አባቷን ደጋግማ፣ ደጋግማ ጠየቀች፣
በአበሻ ልጅ ማእረግ፣
የዚህን ጃውሳ፣ አይን አይኑን እያዬች።
ጅግሳው ጃገማ፣
በሸገነው ቃሉ፣ ባጭሩ ነገራት፣
መቼስ የጀግና ልጅ፣የአባት ወግ አይጠፋት።
ትክዝክዝ እንዳለ፣
እንባ እንዳቀረረ፣
ይኸው ይኸ ጀግና፣ እንዲህ ተናገረ፣
አየሽ የትምወርቄ፤
አርበኛ በደሙ፤
ጀግና በድምድሙ፤
በአጥንቱ መግሮ ፤በተሰራች ሃገር፤
ከሞት ይቆጠራል፤
ለሠላቶ ውላጅ፤
የሚቆራርሱት ጣቢታ መጋገር።
ባንዳ ቀኑ ገጥሞት፤
ወንበር የሰጡት ቀን፤ ሃገር ይወገሻል፤
አርበኛም ዱር ወዶ፤
ካገር ሞት የኔ ሞት፤
ይቅደምና ልሙት፤
እያለ ከቤቱ ከደጁ ይሸሻል።
ግን እንዲህም ሆኖ፤
በአርበኞቹ ጥላ፤
በደም የተዋጀ፤
በአጥንት የታጠረ፤
የነፃነት ቅኔ፤
በትውልዱ ቀለም፤
እየተማገረ ቅኔው እስኪፈታ፤
አይፈርስም ሰንደቁ፤
በአልብላቢት ከንፈር፤ በምላስ ሩምታ፤
ያኔ ይፈወሳል፤
ምን አገባኝ ይሉት፤ የዘመን በሽታ።
እየውልሽ ልጄ፤
የጃገማን ድንበር፤
የጃገማን ሰንደቅ፤
ቀስተ ደመናውን፤
ብጣሽ ጨርቅ እያሉ፤
በርኩሰት አፋቸው፤ ንቀው ያዋረዱ፤
በየመሸታው ቤት፤
ቂጡን ገልቦ ሚሄድ፤
ችው ችው የሚባል፤ ቡችላ ወለዱ።
እናምልሽ ልጄ፤
ሞተን የሰራናት፤
ወድቀን ያነሳናት፤
ኢትዮጲያ እምትባል፣
ገራሚ አገር አለች፣
እድሜዋን ፈጀችው፣
አርበኛን አዋርዳ፣ ባንዳ እየሰቀለች።
ዘመን ቡቱቶዋን፤
እከክዋን አራግፋ፤
ባንዳ ቤቱ ሲፈርስ፣
ሰላቶ ሲረክስ፣ ፊቱ ሲገረጣ፣
ያኔ ነው የኔ ልጅ፣
የጃገማ ፀሃይ፣
በአበሾቹ ሰማይ፣ ቀድማ የምትወጣ።
ኧረ ትውጣ!!!!!!!!!"
"""
( ብወደው፣ብወደው ለማልጠግበው፣ ለጄኔራል ጃገማ
ኬሎና ለልጁ የትም ወርቅ ጃገማ)
✍ጃኖ
እንዳታልፍ!!!
የ666 ቃላቶች
# ቺክ ፦ በዚህ ቃል ብዙዎች ተጠምደዋል ። ሴቶች ወይም እህቶች ማለት
ያስጠላቸዋል ። የዘመኑ አስፀያፊ ወጣት ቺክ እያሉ መጥራት እጅግ
ያስደስተዋል ። # ሰይጣን ይኼን ቃል የተጠቀመበት ትውልዱን አመንዝራ
ለማድረግ ነው ። በተለይም እርኩሳን የ666 ተከታዮች ይህ ቃል ይጣፍጣቸዋል
።
# አንቺ ፦ወንዱን አንቺ ወይም በሴቶች ቅጽል (ማዕረግ) መጥራት የመጣው
# ከእርኩሳን_ግብረሰዶማዊያን ነው ። የሚያስገድዳቸውም የተዋረሳቸው
ሰይጣን ነው ። የሚያስቡት እንደስልጣኔ ነው ። ወንዱን በወንድ ቅጽል መጥራት
ፈጽሞ አይመቻቸውም ። ዛሬ በየዩኒቨርስቲዎች ይህን ቃል የሚጠቀሙት በጣም
ብዙዎች ናቸው ። ስለዚህም ወንዱን በሴት ቅጽል የሚጠሩ የ666 ሰይጣን
ያለባቸው ናቸው ።
# መጥበስ ፦ይህ ቺክ የሚሉ ጅሎች የሚጠቀሙት ቃል ሲሆን የዚህ ቃል ባለቤት
የሆነው አጋንንት አላማው ማስመንዘር ነው ። ቃሉ ራሱ ትርጉሙ ከአላማው ጋር
የሚሄድ ነው ። ይህም በሲኦል እሳት ማቃጠል ወይም መጥበስ ማለት ነው ።
# አስበላኝ ፦ይህ አስተዋውቀኝና ከልጅቱ ጋር ልሴስን ለማለት የሚጠቀሙት ቃል
ነው ።
# ጋይስ ፦ ይህ ቃል የርኩሳን ግብረሰዶማውያን ነው ። የመጣውም gay men
ከሚለው ሲሆን ይህም ግብረሰዶማዊ ሰውየ ማለት ነው ።
ሌሎችም እንደ
# ችከላ
# ላሽ_በል
# ጨምጫሚ
# ባርጫ
# ውስጤ ነው
ወዘተ... ያሉት ቃላት # እርኩስ_መንፈስ ያለባቸው ሰዎች የሚጠቀሟቸው
ቀልጃጃ ቃላት ናቸው ። አዎ አራዳዎቹ የሚጠቀሟቸው ቃላት ።
ሌላ የ666 ተከታዮች ወይም # አስፀያፊዎች_ግብረሰዶማዊያን መለያቸው፦
- አንዳንዶቹ በጣም ሰፊና የሚያስጠላ ሱሪ ይለብሳሉ -በጣም ትልልቅ ጫማ
ይለብሳሉ
- ሱሪያቸውን ዝቅ አድርገው ይለብሳሉ
- ወንዶቹ ከጆሯቸው ላይ ጉትቻ ያደርጋሉ
- የእጃቸውን ጣት ስታይል የ666 ምልክት ያደርጋሉ
-የተቀዳደደ ሱሪ በጣም ይወዳሉ
- የሰውነት የክብደት መቀነሻ ብለው የሚያነቡት የኢሉሚናቲ መጽሐፍ ስላለ
አንዳንዶቹ በጣም የከሱና የተጎሳቆሉ ናቸው ።
-በሱሶች የተጠመዱ ናቸው
-የውጭ ሀገር ሙዚቃና የሀገር ውስጥም hip hop (የጭፈራ ) ሙዚቃ
ይመቻቸዋል
-የአውሬውን ምልክት ወይሞ አውሬውን(የእባብ ምስል) በግንባራቸው ወይም
በቆዳቸው ላይ ይነቀሳሉ -ሌሎችም
# የዮሐንስ_ራዕይ እንዲህ ይላል
ምዕራፍ 13 ቁጥር 18
- # አእምሮ ያለው # የአውሬውን_ቁጥር ይቁጠረው ፤ቁጥሩ የሰው ቁጥር ነውና
፥ ቁጥሩም # ስድስት_መቶ_ስድሳ_ስድስት ነው
ምዕራፍ 14 ቁጥር 9 -11
9....... # ለአውሬውና_ለምስሉ የሚሰግድ በግንባሩም ወይም በእጁ ምልክቱን
የሚቀበል ማንም ቢኖር
10.ርሱ ደግሞ በቁጣው ጽዋ ሳይቀላቅል ከተዘጋጀው # ከእግዚአብሔር_ቁጣ
ወይን ጠጅ ይጠጣል ፥ በቅዱሳንም መላእክትና በበጉ ፊት # በእሳትና_በዲን
ይሳቀያሉ ።
11. የስቃያቸውም ጢስ # ለዘላለም_አስከ_ዘላለም ድረስ ይወጣል ፥
ለአውሬውና ለምስሉ የሚሰግዱ የስሙንም ምልክት የሚቀበል ሁሉ ቀንና ሌሊት
እረፍት የላቸውም ።
# share ብታደርጉ ምናልባት ሳያውቁ የሚያደርጉ ማለትም እነዚህን አስፀያፊ
ቃላት የሚጠቀሙ እንዳሉ እነሱን ትታደጋላችሁ!!!
ሗላ በእሳት ሲቃጠሉ ማዘን አይሰራም !
#የኢትዮጵያ ተዋጊዋ አምላኳ ነውና ወድቀቷን እና ሽንፈቷን አታይም፡፡ ይልቁንስ የትንሳኤ ዘመኗ እንደቀረበ እናስተውል::<< እነርሱም፡ ከተስፋቸው ከኢትዮጵያ፡ ከትምክሕታቸውም፡ ከግብጽ የተነሣ ይፈራሉ ያፍሩማል" (ኢሳ. ፳፥ ፭)s።: ቶማስ ሙር እኮ ኢትዮቶጵያ ያላት እንዲሁም ፕሌቶ አትላንቲስ ያላት የቃል-ኪዳን ምድር ኢትዮጵያ ናት።
ፍራርሲክ ቤከን እኮ "ዘ ኒው አትላንቲክ" ያላት በኋላም ፕሮክለስ የተባለ 415-482 ዓ.ም የነበረ እንዲሁም የፕሌቶን አስተሳስብ የቀረፀ ሰው እንዲህ ይለናል "ፕሌቶ አትላንቲስ ፍፁማዊ አገር የሰላም አገር የፍቅር አገር :የበረከት አገር ያላት ፊክሽናል አለም ሳትሆን የኢትዩጵያ_ግዛት ነው" ብሎ ያኔ ፅፋታል።>>
#ኢትዮጵያ የቃል ኪዳን ሀገር ስለሆነች፣ የሚገነቧት ይገነባሉ፣ ሊያፈርሷት የሚሞክሩ ደግሞ ይፈርሳሉ"
"ኢትዮጵያ የቃል ኪዳን ሀገር ትላለህ አሰኪ የቱ ነገሯ ነው እንዲህ የሚያስብላት" ? ያላችሁኝም ብዙወች ናችሁ ....
በጥንት ልደተ ክርስቶስ የፐርሻዎ ንግስት እኮ ኢትዩጵያን ለመውጋት ዘምታ ጦሯን አስጨርሳ ተመለሰች ይላል ።ታላቁ እስክንድር 127 ሀገራትን ሲገዛ ኢትዩጵያን አልገዛም።ንግስት ማክዳ እኮ ጠቢቡ ሰለሞንን የጠየቀች ጠቢብ ነች።
# ኢትዮጵያ በግብፅ 18 የነገስታትን አንግሳለች።
ሜምኖን የተባለዉ ኢትዮጵያዊ የግብፅ ንጉስ ከ1320 አ.አ እስከ ሴፕዩምስኬኩረስ 170 አ.ም የቆመ ሀዉልት እንደነበረዉና ሀዉልቱም ጠዋት ጠዋት ፀሀይ ሲያርፍበት የክራር ድምፅ ያሰማ እንደነበር ሄሮዱተስ በፓፒረስ ወረቀት ላይ አስፍሮት ይገኛል።
#ከማንም አገር ያልተዳቀለ የራሳችን የሆነ ይህም ብቻ ሳይሆን ለዓለም ፊደላት መሰረት የሆነ ፊደል፣ አሀዝ፣ የቀን መቁጠርያ ለአለም የሠጠች።ከአለም መጀመሪያ እግዚያብሔርን ስታመልክ የኖረች እስከ አለም መጨረሻ የምትኖር እና የምታሳምን ኢትዮጵያ ናት ምክንያተም የቃል-ኪዳን ምድር ናት።
#አሐሜኔስ የተባለ ኢትዮጵያዊ ለመጀመሪያ ጊዜ ፕላኔቶች እንዳሉ የተናገረ ሰው ነው። ይህ አሐሜኔስ የተባለው ኢትዮጵያዊ 16 ፕላኔቶች እንዳሉ የተናገረ ሲሆን፤ ፀሀይን ለመዞር ስንት ግዜ እንደሚፈጅባቸው፤ በስንት ምህዋር እንደሚዞሩና በውስጣቸው ያሉትን ፍጥረታትን ጽፍል።NASA እንኳን አስካሁን እርገጠኛ የሆነው ዘጠኝ ፕላኔቶች እንዳሉ ነው ነገር ግን ገና 7 ፕላኔቶች ይቀራሉ።
#ከአራራት ተራራ ግርጌ ከግዮን መፍለቂያ ጀምረው ሜዴትራንያንን ተሻግረው እስከ የመን ድረስ ሰፊ ግዛት የነበራቸው የዛሬዎቹን የአትላንቲክና የሕንድ ውቅያኖሶችን ጨምሮ መላው አፍሪቃን በስማቸው የሰየሙ።ውቅያኖስን አቋርጠው በዛሬዎቹ አማሪካና አውሮፓ : ኢስያን ቀድመው የሰፈሩ።በጥንት ስሟም ምሥር የተባለች የምትጠራዋን ግብጽን ኢትዮጵያኖች ለመጀመሪያ ጊዜ ምሥርን ስላበቀሉባት ምሥር እየተባለች እንጥትጠራ ያደረጉ።
#ኢትዮጵያ ከሌሎች የዓለም ሀገራት በተለየ የምስጢራት እና የጥበባት መገኛ ነች ፡፡ ለዚህም ዋንኛው መንስኤ በምድራዊ ሰማያትና በሰማያተ ሰማያት በሚገኙት መላእክት ቅዱሳን አባቶች ብሎም የአዳም ልጆች መካከል ግንኙነት ከሚፈጠርባቸው በምድር ላይ ከሚገኙት ሰባቱ የክብር ቦታዎች መካከል አራቱን ይዛ መገኘቷ (በነገራችን ላይ እኒህ የሚስጥር ቦታወች የት አካባቢ ናቸው በሰፊው አመለስበታለሁ)፡፡
#ሀገራችን ኢትዩጵያ ብዙ የመከራ ጊዚያት እንደምታሳልፍና ንጋት እንደሚመጣ አስቀድመው በማየት ለብዙዎቻችን ተናግረዋል፣ ጽፈዋል፣ በየበረሀውም ጩኸዋል። ብዙ ቅዱሳንም ከፍ ከፍ ያሉት እንደሚወርዱ፣ ዝቅ ዝቅ ያሉ
ዝቅ ዝቅ ያሉትም ከፍ እንደሚሉ፣ የወጡት እንደሚገቡና የገቡትም እንደሚወጡ በምልክት አይተው ተናግረዋል። የኢትዮጵያ አምላክ አገራችንን አይጥላትም ።
#ኢትዮጵያ ነፃነቷን ጠብቃ የኖረችው ረጅም ወንዝ ስላለን ነው? ተራሮች ስላሉን ነው? አይደለም። በአፍሪካ ከሌሶቶ በላይ ተራራ ላይ የተመሰረተ አገር የለም፣ ከኪሊማንጃሮ የሚበልጥ ተራራም የለም፤ ነገርግን ከቅኝ ግዛት አላመለጡም።
#ኢትዮጵያ ለማጥፋት የሳጥናኤል ልጆች ለ700 አመታት ስትፈተን የነበር እንዲሁም በአድዋ ጊዜ ከሰራዊቱ ጋር ሆኖ የተዋጋ የረዳት እኮ ቅዱስ ጊዮርጊስ ነው።ለምን ካልኸኝ የቃል ኪዳን ምድር ስለሆነች እናቶቻችን “የኢትዮጵያ አምላክ” የሚሉት ጠንካራ አምላክ ስላለን እንጅ በኛ ሀይል አይደለም።
#ኢትዮጵያ የዓለም መነሻ ነበረች፤አሁንም የዓለም መጨረሻና መደምደሚያ የቃል ኪዳን አገር መሆኗ ገሀድ እየሆነ ነው፡፡
© ትንቢተ ኢትዮጵያ
ሰላምታዬ ለሁላችሁ ይድረሳችሁ!
የሳጥናኤል ጎል ኢትዮጵያ! ቁጥር 4! ባለፈው ሳምንት ለአንባብያን መቅረቡ ይታወቃል። በመሆኑም መፅሐፉ፣ ባለፉት 2 ዓመታት በሀገሪቱ እየተከናወኑ ያሉና ሊከናወኑ የታቀዱ ተግባራትን ያሰፈረ፤ ግራ ቀኙ ግራ ገብቶት ለቆየውና ለደነዘዘው ከድንዛዜው እንዲነቃ የሚያደርግ፣ ተግባራቱንና ተግባሪዎቹን ገና ከመነሻው ጀምሮ አውቆና ተረድቶ በዝምታ ሲከታተል የቆየውን ደግሞ ከራሱ ጋር ሲነጋገር በቆየው ሀሳቡና መረዳቱ ላይ ሌላ ሀሳብና መረዳት የጨመረ ሆኖ አግኝተነዋል!!!
ስለሆነም:
1. “ኢትዮጵያን በአገዛዛቸው ስር አድርገው ያለ አንዳች ስስት ለተቃራኒው ሀይል ሊሰጡ የተዘጋጁ” ስለተባሉት፣ በCIA ምስጢራዊ ስልጠናና ተልዕኮ ተሰጥቷቸው የደም ቃልኪዳንም ገብተው በዚህች ሀገር ስለነገሱት፣ የኢትዮጵያ ህዝብ ከሰማይ የወረደ እንጂ ካለፈው ወንበዴ ፓርቲ ተፈልቅቆ የወጣ የማይመስለውን የዚህ የአሁኑን መንግስት ስለሚመሩት ምልምል ባለስልጣናትና በሌሎች ዘርፎች ላይ ተሰማርተው የማይናበቡ መስለው ግን ተናበው እንዲሰሩ ተደርገውና ተመርቀው ስለተላኩት ሌሎች ምልምል ኢትዮጵያውያን፤
2. በአገዛዛቸው ወቅት ሊሰሩ ስላሰቡት(አሁን እየተሰሩ ስላሉት) ስራዎችና ሴራዎች ሁሉ ተመራቂዎቹን ወክሎ ማብራርያ ስለሰጠው “የፍቅርና የማማለል ፊት እያሳየ የርኩሰትና የክፋት ዕቅዶቹን ሲተነትን ስለታየው” ተመራቂ(የአሁኑ መንግስት አደንዛዡ መሪ)፤
3. በማብራሪያውም፣ ያለ አንዳች ተቃውሞና ጉርምርምታ በስልጣን ላይ ተደላድሎ በመቀመጥ መንግስታዊ መልክ ኑሯቸው እንዲሰሩ የታቀዱትን “እንቅፋት የሆነውን ብሔርና ሀይማኖት የማፅዳት” እና “ ሀገሪቱን ለአለቃቸው ሳጥናኤል የማዘጋጀት” ዕቅዶችን እንዴት ለመተግበር እንዳቀዱ(ባለፉት 2 ዓመታት በተግባር ስለታዩት ነገሮች)
4. “የአንዳምን ስልጣኔ” ተብሎ በመፅሐፉ ስለተገለፀው፣ “Civilization based on Perfection” ወይም “Civilization based on Completion” ብዬ ደግሞ እኔ ስለምጠራውና “መሰረቱን በፍፁምነትና ምሉዕነት ላይ ስላደረገው”፤ እግዚአብሔራዊና ህገ ልቦናዊ መሰረት ይዞ ለ5ሺህ አመታት የኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን ስልጣኔ ሆኖ ስለቆየው፣ አሁንም በአማኝ ህዝቦችና በሰሜናዊው ማህበረሰብ ተወስኖ ስለሚገኘው፣ ወደፊትም “የኢትዮጵያ ትንሳኤ” ተብሎ በሚነገረውና በተስፋ በሚጠበቀው ዘመን ሀገራዊ ሆኖና ጠንክሮ ዳግም ስለሚያንሰራራው ስልጣኔ፤
5. ይህን “የአንዳምን ስልጣኔ”ን እና የአንዳምን ስልጣኔ አራማጅ የሆነውን ብሔር(አምሐራ) እንዲሁም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያንን በምልምሉ የመንግስት መሪ(ሌሎቹም እንዳሉ ሆኖ) ለማክሰምና ለማጥፋት ስላነሳሷቸው አስገዳጅ ምክንያቶች፤
6. CIA በሀገሪቱ ሲያደርግ ስለነበረው መንግስታዊ ስራና ሴራ፤
7. CIA የጣሊያን መከፋፈያ ዘዴ የነበረውን Ethnic Federalism እና ይህን ስርዓት የሚያረጋግጠውን ህገመንግስት አስይዞ ስልጣን ላይ አስቀምጦት ስለነበረው፤ በአሁኑ ሰዓት በኢትዮጵያ ህዝብም በራሱ በCIAም አንቅሮ ስለተተፋው ፓርቲ፤
8. CIA “በሰይጣናዊ መንገድ በልፅጋ ለአለቃቸው ዝግጁ የሆነች ከአንዳምን ስልጣኔ ነፃ የሆነች አርቲፊሻል ኢትዮጵያን” ለመፍጠር ለምን አዳዲስ ምልምል ባለስልጣናት እንዳስፈለጉትና በምን አይነት ዘዴ የቀድሞዎቹ ባለስልጣናት ተወግደው በነዚህ እንዲተኩ እንደሚያደርጉ(እንዳደረጉ)፤
9. በአንድ በኩል የአንዳምን ስልጣኔ አራማጅ የሆነውን ብሔርና ብሔራዊዋን ሀይማኖት ለማክሰምና ለማጥፋት የሚረዱትን፤ በሌላ በኩል ጥፋቶቹን ሁሉ በነሱ ላይ በመለጠፍ ለዘለዓለም ሰበብ ሆነው ያገለግሏቸው ዘንድ በCIA ስለሚደገፉት እንደ “ኦነግ” ስለመሳሰሉት የታጠቁ ቡድኖች(መሪው እንደሚረዳቸው በአፉ መመስከሩ ልብ ይሏል)፤
10. ኢትዮጵያን በአሁኑ ሰዓት የኢኮኖሚ ቅኝ ግዢ ለማድረግ ስለሚለፋው ቢሊየነሩ ሰው ዕቅድ፤
11. “Cashless Societyን መፍጠር” የሚለውን የተለመደውን ዕቅዳቸውን ለመፈፀምና ህዝቡን በቁጥር ቁጥጥር ስር ለማዋል ስላቀዱት በ”የዓለም ገንዘብ ድርጅት ተወካይ” ስለተብራራው ዕቅድ፤
12. በወሲባዊ ቪድዮዎችና ልቅነት ዙርያ ስለታቀደው በ”የዓለም የስነ ጥበብና የኪነ ጥበብ ዘርፍ ተወካይ” ስለተብራራው ዕቅድ፤
13. ከዚህ ቀደም በዚህ ፔጅ ስለተፃፈው CSE (Comprehensive Sexuality Education) ~ ሁለገብ ወሲባዊ ትምህርትን ጨምሮ ህዝቡን ግብረ ሰዶማዊ ለማድረግ ስለታቀደው በ”የዓለም የግብረሰዶማውያን ማህበር ተወካይ” ስለተብራራው ዕቅድ፤
14. ወጣቱን ለመያዝ ስለታቀደው በ”ፊፋ ተወካይ” ስለተብራራው ዕቅድ፤
15. ተፈጥሯዊ መስለው የተሰሩትን ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸውን ረቂቅ ነፍሳት (አንበጣ …. ወዘተ) ጨምሮ ሰለታቀደው በ”የዓለም አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ተወካይ” ስለተብራራው ዕቅድ፤
16. በአሁኑ ሰዓት “የአረንጓዴ አሻራ” ተብሎ በአስደንጋጭ ሁኔታ በዓመት በቢልየን የሚቆጠሩ ህዝቡ የማያውቃቸው ረቂቅ ችግኞችን የመትከል ዘመቻን ጨምሮ ስለታቀደው በ”የዓለም ምግብ ድርጅት ተወካይ” ስለተብራራው ዕቅድ፤
17. በ”የዓለም ቅርስ ጥበቃ ድርጅት ተወካይ” ስለተብራራው ሴረኛ ዕቅድ፤
18. በ”የዓለም የናኖ ቴክኖሎጂ ዘርፍ ተወካይ” ስለተብራራው ዕቅድ፤
19. በDepopulation አጀንዳ ዙርያ በወረርሽኝ፣ በክትባት እንዲሁም በሌሎች መንገዶች ሊሰራ ስለታቀደው በ”የዓለም ጤና ድርጅት ተወካይ” ስለተብራራው ዕቅድ፤
….. በዝርዝር የምታገኙት ከዚሁ መፅሐፍ ነውና፤ ብታነቡት ጥሩም ብቻ ሳይሆን ግዴታ ይሆናል!!!!!!! በአሁኑ ሰዓት እየሆነ ያለውን ነገር በአግባቡ ለማወቅ ስለሚረዳ፤ ግራ መጋባቱንም ስለሚያጠራ!!!
በአንድ ወቅት ላይ አንዲት ጣሊያናዊት ጋዜጠኛ የኩባውን መሪ ፊደል ካስትሮ አግኝታ ስለ ኢትዮ-ሶማሊያ ጦርነት አንድ ጥያቄ አነሳችላቸው.....
ጣሊያናዊቷ ጋዜጠኛ፦≪ በሶማሊያና በኢትዮጵያ መካከል በተደረገው ጦርነት ኩባ ከኢትዮጵያ ጋር አጋር ሆና ተሰልፋ ነበር?≫
ፊደል ካስትሮ፦≪ እንደማንኛውም ወዳጅና ወንድም ሀገር በተወሰነ መልኩ አግዘናቸዋል።≫
ጣሊያናዊቷ ጋዜጠኛ፦≪ በተወሰነ መልኩ ሳይሆን ለድሉ መገኘት የኩባ ወታደሮች አስተዋጽኦ ከፍተኛ ሆኖ ሳለ፣ ኢትዮጵያዊያን ግን ጦርነቱን ያሸነፍነው በእኛ ጀግንነት ነው ይላሉ፣ እውነት እርስዎም በኢትዮጵያዊያን ጀግንነት የመጣ ድል ነው ብለው ያምናሉ?≫
ፊደል ካስትሮ፦≪ ጀግንነት በእርግጥ ለኢትዮጵያዊያን ብርቅ ነገር ነው ብዬ አላስብም። 'ኢትዮጵያዊያን ጀግኖች ናቸው? ወይስ ጀግኖች አይደሉም?' የሚለውን ምስክርነት እኔ ልሰጥሽ ከምችለው በላይ የሚሰጡሽን ሰዎች ለምን አትጠይቂያቸውም?≫
ጣሊያናዊቷ ጋዜጠኛ፦≪ እነማናቸው እነሱ?≫
ፊደል ካስትሮ፦≪ የራስሽ አያቶች ናቸዋ!≫
በአንድ ወቅት ላይ አንዲት ጣሊያናዊት ጋዜጠኛ የኩባውን መሪ ፊደል ካስትሮ አግኝታ ስለ ኢትዮ-ሶማሊያ ጦርነት አንድ ጥያቄ አነሳችላቸው.....
ጣሊያናዊቷ ጋዜጠኛ፦≪ በሶማሊያና በኢትዮጵያ መካከል በተደረገው ጦርነት ኩባ ከኢትዮጵያ ጋር አጋር ሆና ተሰልፋ ነበር?≫
ፊደል ካስትሮ፦≪ እንደማንኛውም ወዳጅና ወንድም ሀገር በተወሰነ መልኩ አግዘናቸዋል።≫
ጣሊያናዊቷ ጋዜጠኛ፦≪ በተወሰነ መልኩ ሳይሆን ለድሉ መገኘት የኩባ ወታደሮች አስተዋጽኦ ከፍተኛ ሆኖ ሳለ፣ ኢትዮጵያዊያን ግን ጦርነቱን ያሸነፍነው በእኛ ጀግንነት ነው ይላሉ፣ እውነት እርስዎም በኢትዮጵያዊያን ጀግንነት የመጣ ድል ነው ብለው ያምናሉ?≫
ፊደል ካስትሮ፦≪ ጀግንነት በእርግጥ ለኢትዮጵያዊያን ብርቅ ነገር ነው ብዬ አላስብም። 'ኢትዮጵያዊያን ጀግኖች ናቸው? ወይስ ጀግኖች አይደሉም?' የሚለውን ምስክርነት እኔ ልሰጥሽ ከምችለው በላይ የሚሰጡሽን ሰዎች ለምን አትጠይቂያቸውም?≫
ጣሊያናዊቷ ጋዜጠኛ፦≪ እነማናቸው እነሱ?≫
ፊደል ካስትሮ፦≪ የራስሽ አያቶች ናቸዋ!≫
#ከተራ_ምንድን_ነው?
ከተራ 'ከበበ' ካለው የግእዝ ግሥ የወጣ ነው፡፡ ፍችው ውኃ መከተር፣ መገደብ ማለት ነው፡፡
በጥምቀት ዋዜማ ታቦተ ሕጉ ከቤተ መቅደስ ወጥቶ ውኃ ባለበት አካባቢ ስለሚያድር የየአጥቢያው ሕዝብ እየተሰበሰቡ በወንዝ ዳር ወይም በምንጭ አካባቢ ድንኳን ይተከላሉ፡፡ ድንኳንም ከሌለ ዳስ ሲጥሉ ይውላሉ፡፡ የምንጮች ውኃ እንዲጠራቀም ይከተራሉ (ይገድባሉ) ጉድጓድ እየተቆፈረ ውኃው እንዳይሄድ በመገደብ ለመጠመቂያ (ለጥር 11) ዝግጁ የሚያደርጉበት ዕለት ነው፡፡
በተጨማሪ በአቅራቢያ የሚገኙት ቤተክርስቲያናት ተሰብስበው ከዚሁ ከተቆፈረው ገንዳ ወይም ከተገደበው ጅረት አጠገብ ባለው ዳስ ወይም ድንኳን ታቦቶቻቸውን ያሳድራሉ ሊቃውንቱም በዚያው እግዚአብሔርን በማህሌት ሲያመሰግኑ ያድራሉ።
በበዓለ ጥምቀት የታቦታቱ ወደ ወንዝ መውረድ መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ በእደ ዮሐንስ ለመጠመቅ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ በዋዜማው የመሄዱ ምሳሌ ነው፡፡ ታቦቱ የጌታችን፣ ምሳሌ ሲሆኑ ካህናቱ የመጥምቁ ዮሐንስ ምሳሌ ናቸው፡፡ መዘምራኑና ሕዝቡ ደግሞ ዮሐንስ ያጠመቃቸው ሕዝቦች ምሳሌዎች ናቸው፡፡
መልካም የከተራ በዓል