waltatveth | Unsorted

Telegram-канал waltatveth - AddisWalta - AW

47798

This is Walta Media and Communication Corporate’s official Telegram channel. For more updates please visit https://www.facebook.com/wmcc https://www.youtube.com/c/WaltaTV/featured

Subscribe to a channel

AddisWalta - AW

#ሐሳብ_ላይ
የጠቅላይ ሚኒስትሩ የወለጋ ጎዞ ትርጉሙ እና አንድምታው 👇
https://youtu.be/5uy2vZUZlK4?si=ywOc4F7RPKE6VSVL
ዛሬ ምሽት 3፡00 ይጠብቁን!

Читать полностью…

AddisWalta - AW

የአዲስ ዋልታ የትንሳኤ በዓል የወርቅ ደረጃ አጋር!

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮሙኒኬሽን ቢሮ

Читать полностью…

AddisWalta - AW

ዛሬ የማክሮኢኮኖሚ ኮሚቴ ከአገርበቀል የኢኮኖሚ ሪፎርም አጀንዳ አፈፃፀም ጋር የተያያዙ ሰፋ ያለ መጠነርዕይ ያላቸው ጉዳዮች ላይ ተወያይቷል። - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

Читать полностью…

AddisWalta - AW

#ከተሞቻችን
ጅግጅጋ

የምስራቋ ፈርጥ፣ የብዙኃን መናህሪያ እና የእንግዳ ተቀባይ ሕዝብ ምድር የሆነችው የጅግጅጋ ከተማ ከመዲናችን አዲስ አበባ በስተምስራቅ አቅጣጫ 618 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ትገኛለች፡፡

በአብዛኛው ሜዳማ ተፈጥሯዊ የመሬት ገፅታ የተጎናጸፈችው ይህች ከተማ የሶማሌ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ዋና መቀመጫ ናት፡፡

ከባህር ጠለል በላይ 1ሺሕ 609 ሜትር ከፍታ ላይ የምትገኘው ጅግጅጋ ሞቃታማ የአየር ንብረት አላት፡፡ ከተማዋ በ1916 ዓ.ም በፊታውራሪ ተክለ ሐዋሪያት ተክለ ማርያም እንደተመሰረተች ይነገራል።

ጅግጅጋ የሚለው ቃል መነሻው ሕዝቡ የውሃ ጉድጓዶች ሲቆፍር ከተሰሙ የተለያዩ የ"ጂግ-ጂግ" ድምፆች መሆኑ ይጠቀሳል፡፡ በአካባቢው ማኅበረሰብ "ላአ" ተብሎ ይጠራ እንደነበር እና ይህም በሶማሌ ቋንቋ "ማራኪ እይታ" ማለት እንደሆነ ይነገራል።

የካራማራ ሰንሰለታማ ተራራ ከጂግጂጋ ከተማ በ12 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ይገኛል፡፡ ውብ እና አረንጓዴ መልከዓ ምድራዊ ተፈጥሮ ያለው ይህ ተራራ የካራማራ የድል ብስራት ህያው ምስክርም ጭምር ነው።

ጅግጅጋ በአራት ክፍለ ከተማ እና ሀያ ቀበሌዎች የተዋቀረች ስትሆን ክፍለ ከተማዎቿ ካራማርዳ፣ ዱዳሂዲ፣ ጋራብአሴ እና ቆርዴሬ ይባላሉ፡፡
👇👇
https://www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate/posts/pfbid02kXrPXbE7B9Zo2QiSZStaASibiaWH4tqHiUFMShGMcrqfnkZZ5YcUcwT7SffMBtP8l

Читать полностью…

AddisWalta - AW

የአዲስ ዋልታ የትንሳኤ በዓል ሁለተኛ ደረጃ አጋር

ፍል ውሃ አገልግሎት ድርጅት

Читать полностью…

AddisWalta - AW

የአዲስ ዋልታ የትንሳኤ በዓል የወርቅ ደረጃ አጋር!

የአዲስ አበባ ኮሙኒኬሽን ቢሮ

Читать полностью…

AddisWalta - AW

በሀላባ ዞን በጎርፍ የተወሰዱ ሰዎችን ለማግኘት እየተደረገ ያለው ፍለጋ ቀጥሏል

ሚያዝያ 28/2016 (አዲስ ዋልታ) በሀላባ ዞን ሁለት ወረዳዎች በተከሰተው የጎርፍ አደጋ የአምስት ሰዎች ህይወት እንዳለፈና የሁለቱን አስክሬን ለማግኘት እየተደረገ ያለው ፍለጋ ተጠናክሮ መቀጠሉን የዞኑ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ገለጸ።

የሀላባ ዞን መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ኃላፊ ሐሩና አሕመድ ለአዲስ ዋልታ ዲጂታል ሚዲያ እንደገለጹት ከሁለት ቀናት በፊት ሚያዝያ 26/2016 ዓ.ም በዞኑ ዌራ ዲጆ እና አቶቲ ኡሎ ወረዳዎች በሰውና ንብረት ላይ ጉዳት ያደረሰ የጎርፍ አደጋ ተከስቷል።

በድንገት በተፈጠረው የጎርፍ አደጋ ከአምስት ሰዎች ህይወት ማለፍ በተጨማሪ 14 ፍየሎች መሞታቸውንና 30 ሄክታር ላይ የለማው ሰብል መውደሙን አመላክተዋል።

በተጨማሪም በቁሊቶ ከተማ በሚገኘው አጠቃላይ ሆስፒታል ጎርፍ በመግባት በህክምና መሳሪያዎች ላይ ባደረሰው ጉዳት በአገልግሎቱ ላይ መስተጓጎል መፍጠሩን ተናግረዋል።

ህይወት ካለፈባቸው አምስት ሰዎች ሦስቱ ልጆች ሲሆኑ ከ7 እስከ 12 ዓመት የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ እንደሆኑ ያመላከቱት ኃላፊው የሁለቱ ሰዎች አስክሬን እስካሁን አለመገኘቱን ጠቁመዋል።
👇👇
https://www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate/posts/pfbid0T59YFUU9qVXZhrLLDLwJSew87kKuSwrxTaubYmKrv53wxGoqHDQmqeEzxEZbLdqrl

Читать полностью…

AddisWalta - AW

በአጓጊው የ#ደሞ_አዲስ የግማሽ ፍጻሜ ውድድር በሕዝብ ድምጽ አራት ተወዳዳሪዎች በቀጥታ ወደ ቀጣዩ ዙር ሲያልፉ ሁለት ተወዳዳሪዎች ለመትረፍ ደርሰው አንዱ የቀጣዩን ዙር ተቀላቅሏል።

በዚህም መሰረት ማቲያስ ደርብ፣ እንግዳው አስፋው፣ ታረቀኝ ረጃው እና አብርሃም ኸይሩ ወደ ቀጣዩ ዙር በቀጥታ አልፈዋል።

ለመትረፍ በተሰኘው የውድድሩ ሕግ በሕዝብ ድምጽ አነስተኛ ድምጽ ያገኙት ኃ/ኢየሱስ ታደገ እና ዮሃንስ ወርቁ ስራቸውን አቅርበው በዳኞች ውሳኔ ዮሃንስ ወርቁ ወደ ቀጣዩ ዙር አልፏል።

ኃ/ኢየሱስ ታደገ ደግሞ በዛሬው ደሞ አዲስ የውድድሩ ተሰናባች ሆኗል።

#ደሞ_አዲስ

#አዲስ_ዋልታ

Читать полностью…

AddisWalta - AW

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ለአረጋዊያን፣ እና ለአቅመ ደካሞች የፋሲካ በዓልን ምክንያት በማድረግ ማዕድ አጋርተዋል።

Читать полностью…

AddisWalta - AW

ኤፕሲዊች ታዉን ወደ ፕሪሚዬር ሊግ ማደጉን አረጋገጠ

ሚያዚያ 26/2016 (አዲስ ዋልታ) ኤፕስዊች ታዉን ከ22 ዓመታት በኋላ ወደ እንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግ ተመለሰ።

በቅፅል ስማቸው ዘትራክተር ቦይስ የሚባሉት ኤፕስዊቾች ዛሬ ከሃደርስፊልድ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 2 ለ 0 በሆነ ውጤት ማሸነፉቸውን ተከትሎ ወደ ታላቁ ፕሪሚዬር ሊግ ማደጋቸውን አረጋግጠዋል።

የቡድኑ ማደግ አስገራሚ የሚያደርገው ደግሞ ባለፈው ዓመት ከሶስተኛ ዲቪዚዮን ወደ ሻምፒዮንሽፑ አድጎ ባመቱ ደግሞ ወደ ፕሪሚዬር ሊጉ መመለሱ ነው የተገለጸው።

ይህም ሳውዝሃምፕተን እ.ኤ.አ 2012 ካስመዘገበው ታሪክ ጋር እንዲጋራ አስችሎታል።

በሻምፒዮንሽፑ 24 ቡድኖች የሚሳተፉ ሲሆን በደረጃ ሰንጠረዥ አንደኛና ሁለተኛዎቹ ቡድኖች በቀጥታ ወደ ፕሪሚዬር ሊጉ ያድጋሉ። ሌስተር ሲቲ በኬራን ማኬና ከሚሰለጥነው ኤፕስዊች ታዉን ቀደም ብሎ ወደ ፕሪሚዬር ሊጉ መመለሱ ይታወሳል።

ቀጣዮቹ አራት ቡድኖች የደርሶ መልስ ጨዋታ አድርገው አንደኛ የወጣው ቡድን በሶስተኝነት ፕሪሚዬር ሊጉን ይቀላቀላል፡

Читать полностью…

AddisWalta - AW

እንኳን ለ2016 ዓ.ም የትንሣኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ! - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ

Читать полностью…

AddisWalta - AW

በየአካባቢው የቁም እንስሳት ቅርጫ ማረድ አለመከልከሉ ተገለጸ

ሚያዝያ 25/2016 (አዲስ ዋልታ) በአዲስ አበባ ከተማ የትንሳኤ በዓል ህብረተሰቡ በየቤቱ እና በየአካባቢው የቁም እንስሳትን ቅርጫ ማረድ አለመከልከሉን የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ አስታወቀ።

ቢሮው ለትንሳኤ በዓል ህብረተሰቡ በየቤቱ እና በየአካባቢው የቁም እንስሳትን ቅርጫ ማረድ ተከልክሏል በሚል በማህበራዊ ሚዲያ እየተሰራጨ ያለው መረጃ ሀሰተኛ መሆኑን አስታውቋል።

በየአካባቢው በህገ ወጥ መንገድ እርድ በመፈፀም ለሆቴሎች እና ለስጋ ቤቶች በማከፋፈል ተግባር ላይ የሚገኙ አካላት የቁም እንስሳቱ ጤንነት ባልተረጋገጠበት ሁኔታ የከተማውን ነዋሪ ጤንነት ላይ ጉዳት ስለሚያደርስ ጥብቅ ቁጥጥር እንደሚደረግም ቢሮው ባወጣው መረጃ አመላክቷል።

የከተማው ነዋሪ በዓላትን ሽፋን በማድረግ ጤንነቱ ያልተረጋገጠ እንስሳት አርዶ ማከፋፈል በጤና ላይ የሚያደርሰውን ጉዳት ግምት ውስጥ በማስገባት በህገወጥ እርድ የሚሰማሩ አካላት በሚደረገው ቁጥጥር ተባባሪ እንዲሆን አሳስቧል።

Читать полностью…

AddisWalta - AW

የኢየሱስ ክርስቶስ ስቅለት በዓል በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ እየተከበረ ነው

ሚያዝያ 25/2016 (አዲስ ዋልታ) የኢየሱስ ክርስቶስ የስቅለት በዓል በመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ እየተከበረ ነው።

በዓሉ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋኅዶ ቤተ-ክርስቲያን፣ በካቶሊካዊት ቤተ-ክርስቲያን እና በወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ኅብረት በስግደት፣ በጾም፣ በጸሎት እና በዝማሬ እየተከበረ ይገኛል፡፡

በዕለቱ ቀኑን የሚያወሱ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች የሚነበቡ ሲሆን በዕለተ ስቅለት የተከናወኑ ተግባራት እየታሰበም የስግደት ስርዓት ይከናወናል።

Читать полностью…

AddisWalta - AW

የትንሳኤ በዓልን በአዲስ ዋልታ

የትንሣኤ ዕለት ይጠብቁን!

#ትንሣኤ_በዓል

Читать полностью…

AddisWalta - AW

ምክትል ጠ/ሚ ተመስገን ጥሩነህ እና በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊ አደም ፋራህ ባሕር ዳር ገቡ

ሚያዚያ 24/2016 (አዲስ ዋልታ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ እና በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊ አደም ፋራህ ባሕር ዳር ከተማ ገብተዋል።

የጣና ሐይቅ ፈርጧ፣ የበርካታ ደሴቶች መናኸሪያ፣ የጢስ ዓባይ ፏፏቴ መገኛ፣ የበርካታ ቱሪስቶች መዳረሻ እና የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት መቀመጫ በሆነችው ውቢቷ ባሕር ዳር ከተማ ገብተናል ሲሊ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል።

ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎቹ ባሕር ዳር ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ እና ካቢኒያቸው እንዲሁም የከተማዋ ከንቲባ እና ህዝብ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

Читать полностью…

AddisWalta - AW

ሕዝቡ በሰላም፣ በአንድነትና በልማት ላይ በማተኮር እጅ ለእጅ ተያይዞ መስራት አለበት - ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ

ሚያዝያ 30/2016 (አዲስ ዋልታ) ሕዝቡ በሰላም፣ በአንድነትና በልማት ላይ በማተኮር እጅ ለእጅ ተያይዞ መስራት አለበት ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።

በነቀምቴ ከተማ ወለጋ ስታዲየም የለውጡን መንግስት የሚደግፍ ሰልፍ ''ወለጋ የሰላምና የብልጽግና ምድር'' በሚል መሪ ሃሳብ የአራቱ ወለጋ ዞኖች ነዋሪዎች የተሳተፉበት ሰልፍ ተካሂዷል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በዚህ ወቅት ባስተላለፉት መልዕክት ህዝቡ በሰላም፣ በአንድነትና በልማት ላይ እንዲያተኩር ጥሪ አቅርበዋል።

ሰላም የሁሉ ነገር መሰረት መሆኑን ጠቅሰው ''ሰው ውስጡ ሰላም የሆነ፣ ሀገሩ ሰላም ከሆነ ልክ እንደ ዛሬ በፍቅርና በወንድማማችነት መንፈስ ተገናኝቶ መለያየት ይችላል'' ነው ያሉት።

ከሁሉም በላይ ለልማት፣ የተለያየ ሀሳብ ለማመንጨት አንድነት እጅግ አስፈላጊ መሆኑን የጠቆሙት ጠቅላይ ሚኒስትሩ "ትውልዱን የሚጎዳ ነገር ከማድረግ በመቆጠብ በመመካከር አንድነትን ማጽናት ይገባል" ብለዋል።

ከኢኮኖሚ አኳያ ከለውጡ በፊት ብዙ ችግር ተደቅኖ እንደነበር አንስተው ከለውጡ በኋላ ግን በብዙ ችግሮች ውስጥ ትልቅ የኦኮኖሚያዊ ለውጥ እየተመዘገበ መሆኑን አብራርተዋል።

በለውጡ ዓመታት በተሰራ ሥራ ግብርናንና ከተማን የሚለውጥ፣ ሀገር የሚያሸግር ኢኮኖሚ እየተመዘገበ መሆኑን አስረድተዋል።

''የጀመርነውን ስራ ከግብ ለማድረስ የሚያስቆመን ሃይል አይኖረም፣ በንጹህ ልባችን ሀገር ለመለወጥ ነው እየሰራን ያለነው'' ብለዋል፡፡
👇👇
https://shorturl.at/bQZ24

Читать полностью…

AddisWalta - AW

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ነቅምቴ ገቡ

ሚያዝያ 30/2016 (አዲስ ዋልታ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና የተለያዩ ከፍተኛ የመንግስት ስራ ኃላፊዎች ነቅምቴ ገቡ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከልዑካን ቡድናቸው ጋር ነቀምቴ የገቡት በወለጋ እየተካሄደ ባለው ሀገራዊ ለውጡን የሚደግፍ ሕዝባዊ ሰልፍ ላይ ለመገኘት ነው፡፡

ልዑክ ቡድኑ በነቀምት አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ ደማቅ አቀባበል የተደረገለት ሲሆን ልዑኩ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ፣ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አገኘው ተሻገር እና የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት አመራሮችን ያካተተ ነው፡፡

በድጋፍ ሰልፉ ባለፉት የለውጥ ዓመታት በተለያዩ ዘርፎች የተገኙ ስኬቶችን የሚገልጹ መልዕክቶች እየተላለፉ ሲሆን በወለጋ የተለያዩ አካባቢዎች የተወጣጡ የኅበረተሰብ ክፍሎች እየተሳተፉ ይገኛሉ፡፡

Читать полностью…

AddisWalta - AW

ዛሬ ምሽት በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ፒ.ኤስ.ጂ ከዶርትመንድ ይጫወታሉ

ሚያዚያ 29/2016 (አዲስ ዋልታ) በሁለተኛው ዙር የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የግማሽ ፍጻሜ መርኃ ግብር የፈረንሳዩ ፒ.ኤስ.ጂ ከዶርትመንድ ጋር ምሽት 4 ሰዓት ይጫወታሉ።

ሁለቱ ቡድኖች በኢግናል ኢግና ፓርክ ባደረጉት በመጀመሪያው ዙር ጨዋታ ዶርትመንድ 1 ለ 0 በሆነ ጠባብ ውጤት ማሸነፉ ይታወሳል።

የፈረንሳዩ ሊግ ዋን ሻምፒዮናው ፒ.ኤስ.ጂ ውጤቱን ቀልብሶ ወደ ፍጻሜ ለማለፍ ጠንክሮ እንደሚቀርብ ሲጠበቅ ዶርትመንድ በበኩሉ በውድድሩ ጥሩ አቋም እያሳዬ በመሆኑ ለፈረንሳዩ ቡድን ፈታኝ ሊሆን እንደሚችል ይገመታል።

Читать полностью…

AddisWalta - AW

የጽዱ ጤና ተቋማት ንቅናቄ ተጀመረ

ሚያዚያ 29/2016 (አዲስ ዋልታ) የጤና ሚኒስቴር በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አነሳሽነት የተጀመረው የ“ጽዱ ኢትዮጵያ” ንቅናቄ አካል የሆነውን የጽዱ ጤና ተቋማት ንቅናቄ አስጀምሯልለ።

“ፅዱ የጤና ተቋማት ለተሟላ ጤንነት” በሚል መሪ ሀሳብ ነው ንቅናቄው የተጀመረው።

ንቅናቄው ምቹ የጤና ተቋማትን ለመፍጠር ያለመ መሆኑን የገለፁት የጤና ሚኒስትሯ ዶ/ር መቅደስ ዳባ በዓለም የጤና ድርጅት (WHO) በፈረንጆች 2030 ለማሳካት ከታቀዱት እቅዶች መካከል አንዱ መሆኑን ጠቁመዋል።

ንቅናቄው በተለይም የእናትና የህፃናትን ሞት ከመቀነስ አኳያ ፋይዳው የጎላ መሆኑን ተናግረዋል።

ችግሩን በመቅረፍ ረገድ የጤና ተቋማት የአንበሳውን ድርሻ የሚወስዱ እንደመሆኑ መጠን በአለርት አህሪ የጤና መንደር እና በቅዱስ ጴጥሮስ ሆስፒታል የተጀመረው ይህ ንቅናቄ በተለያዩ የሀገራችን ክፍል በሚገኙ የጤና ተቋማት ላይም እንደሚቀጥል ገልፀዋል።

በንቅናቄው ላይ የጤና ተቋማት እድሳት፣ የመፀዳጃ ቤት ግንባታ፣ ለአቅመ ደካሞች የተገነቡ ሶስት መኖሪያ ቤቶች የማስረከብ እቅድ ተካቷል።

በፈቲያ ሁሰን

Читать полностью…

AddisWalta - AW

ቅዱስ ጊዮርጊስ አሠልጣኝ ዘሪሁን ሸንገታን በጊዜያዊነት አገደ

ሚያዝያ 28/2016 (አዲስ ዋልታ) የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር ስራ አመራር ቦርድ የዋናው ቡድን ዋና አሠልጣኝ ዘሪሁን ሸንገታን ከማሰልጠን ተግባራቸው በጊዜያዊነት ማገዱ ተገለጸ፡፡

የስራ አመራር ቦርዱ ዛሬ ባደረገው አስቸኳይ ስብሰባ የዋናውን ቡድን እንቅስቃሴ የገመገመ ሲሆን በዚህም አሠልጣኝ ዘሪሁን ሸንገታ የዋናው ቡድን ዋና አሠልጣኝ እና አሠልጣኝ ውብሸት ደሳለኝ የበረኞች አሠልጣኝ ተለዋጭ መመሪያ እስኪሰጥ ድረስ ከማሰልጠን ተግባራቸው ታግደው እንዲቆዩ ወስኗል።

በምትካቸውም አሠልጣኝ ደረጀ ተስፋዬ የዋናው ቡድን ምክትል አሠልጣኝ ዋና አሠልጣኝ ሆነው ከሚያዝያ 29 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ በጊዜያዊነት እንዲያሠለጥኑ ተወስኗል፡፡

አሠልጣኝ ሳምሶን ሙሉጌታ ደግሞ የወጣት ቡድኑ ዋና አሠልጣኝ ምክትል አሠልጣኝ ሆነው በጊዜያዊነት እንዲያሠለጥኑ መወሰኑን ከክለቡ የማህበራዊ ትስስር ገፅ የተገኘው መረጃ አመላክቷል፡፡

Читать полностью…

AddisWalta - AW

#አጀንዳ+

የኢትዮጵያ ፈተናዎች እና የትንሳዔዋ እንቅፋቶች፣ ስኬታማው የኢትዮጵያ የፈተና ውስጥ ጉዞ

https://youtu.be/ds401thssjw
ዛሬ ምሽት ይጠብቁን

Читать полностью…

AddisWalta - AW

ዳሞታ ተራራ - የወላይታ ሶዶ ውበት
#ሀገሬ

የዳሞታ ተራራ ከወላይታ ሶዶ ከተማ በስተሰሜን የሚገኝና በደን የተሸፈነ የብዘሃ ህይወት አለኝታ ነው። ተራራው ታሪካዊ፣ ባህላዊና ሃይማኖታዊ ይዘት ያላቸው መስህብ ስፍራዎች የሚገኝበት ነው።

በሀገር በቀል ዕፅዋት የተሸፈነና አረንጓዴ ሸማ የለበሰው ይህ ተራራ በክፍታውና በግርማ ሞገሱ ወደ ከተማዋ የሚገቡትን ጎብኚዎች ቀልብ በመግዛትም ይታወቃል።

ተራራው የሚሸፍነው መሬት 12 ሺሕ 500 ሄክታር ሲሆን ከፍታው ከባህር ጠለል በላይ 3 ሺሕ ሜትር ነው። ዙሪያው 68 ኪሎ ሜትር በላይ ርቀት እንዳለውም ይነገራል።

የዳሞታ ተራራ በወላይታ ሕዝብ ዘንድ በዘርፈ ብዙ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታው የሚታወቅ ታሪካዊ ስፍራ ሲሆን ከህዝቡ ታሪክና ባህል እንዲሁም ጀግንነት ጋር በማቆራኘትም ዳሞታን በሥነ ቃላቸው ያሞጋግሱታል በሙዚቃዎቻቸውም ታሪኩን ያወሣሉ።

ተራራው ከልምላሜው፣ ከዱር እንስሳትና ተፈጥሯዊ ብዝሃ ህይወት ማህደርነት ባሻገር በወላይታ ዞን የሚገኙ ወረዳዎች ስያሜዎቻቸውን ዳሞታን መነሻ አድርገው ይጠሩታል፡፡ ከእነዚህም ወረዳዎች ዳሞት ሶሬ፣ ዳሞት ወይዴ፣ ዳሞት ጋሌ እና ዳሞት ፑላሳ የሚጠቀሱ ሲሆን ለተለያዩ ቀቤሌዎችም የመጠሪያቸው መነሻ ነው የዳሞታ ተራራ፡፡
👇👇
https://shorturl.at/myIOZ

Читать полностью…

AddisWalta - AW

አጓጊው የደሞ አዲስ የቀጥታ ስርጭት የግማሽ ፍጻሜ ውድድር - አሁን 🔥 ወደ ቀጣይ ዙር የሚያልፉ ተወዳዳሪዎች በእናንተ ድምፅ ይወሰናሉ። ተወዳዳሪዎችን በአጭር የፁሑፍ መልዕክት 8970 ይዳኙ! 🎼🎹🥁🎤🎺🎷🎸🎻

#ደሞ_አዲስ

#አዲስ_ዋልታ
👇👇
https://www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate/videos/813826543525101

Читать полностью…

AddisWalta - AW

የትንሳዔ በዓል በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ እየተከበረ ነው

ሚያዝያ 27/2016 (አዲስ ዋልታ) የኢየሱስ ክርስቶስ የትንሳዔ (ፋሲካ) በዓል በመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ በዛሬው እለት በተለያዩ ስነ ስርዓቶች እየተከበረ ይገኛል።

በዓሉ ኢየሱስ ክርስቶስ ክርስቶስ ሞትን ድል አድርጎ የተነሳበት ዕለት የሚታሰብበት ነው።

በዓሉን በማስመልከት የተለያዩ የሀይማኖት መሪዎች ባስተላለፉት መልእክት፤ የትንሳኤ በዓል እግዚአብሄር አምላክ ለሰው ልጆች ያለውን ታላቅ ፍቅር በልጁ ሞትና ትንሳኤ የገለጠበት በመሆኑ ምእመናንም የተራቡትን በማብላትና የተቸገሩትን በመርዳት ሊያከብሩት እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡

ምዕመናን በዓሉን ሲያከብሩ ስለ ሀገር ሰላም እና እድገት እንዲያስቡ እንዲሁም የተቸገሩ ወገኖችን በመደገፍ ሊሆን እንደሚገባ የሀይማኖት መሪዎቹ መልክታቸውን አስተላልፈዋል።

Читать полностью…

AddisWalta - AW

ለአጋሮቻችን፣ለአዲስ ዋልታ ቤተሰቦች እና ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን አደረሳችሁ።

ለአብሮነታችሁ ሁሉ ከልብ እናመሰግናለን። መልካም በዓል!!

ጋዜጠኛ መሀመድ ሀሰን የዋልታ ሚዲያና ኮሙኒኬሽን ኮርፖሬት ዋና ሥራ አስፈጻሚ

Читать полностью…

AddisWalta - AW

የስቅለት በዓል በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታዮች ዘንድ ተከበረ

ሚያዝያ 25/2016 (አዲስ ዋልታ) የኢየሱስ ክርስቶስ የስቅለት በዓል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታዮች ዘንድ ተከብሮ ዋለ።

በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም በተከናወነው ሥነ ስርዓት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ፣ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ ካህናትና ምዕመናን በተገኙበት በጸሎትና በስግደት ተከብሯል።

በትናንትናው እለት የጸሎተ ሐሙስ "ሕፅበተ እግር" ሥነ ስርዓት በእምነቱ ተከታዮች ዘንድ መከበሩ ይታወቃል።

የፊታችን እሁድ ደግሞ የፋሲካ በዓል በመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ በተለያዩ ዝግጅቶች ይከበራል።

Читать полностью…

AddisWalta - AW

የስቅለት በዓል በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን እምነት ተከታዮች ዘንድ ተከበረ

ሚያዝያ 25/2016 (አዲስ ዋልታ) የኢየሱስ ክርስቶስ የስቅለት በዓል በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን እምነት ተከታዮች ዘንድ በልደታ ማሪያም ካቶሊክ ካቴድራል ቤተክርስቲያን በርካታ የእምነቱ ተከታዮች በተገኙበት በተለያዩ ሃይማኖታዊ ሥነሥርዓት ተከበረ።

የቤተክርስቲያንቱ ሊቀጳጳስ ብፁዕ ካርዲናል ብርሃነ ኢየሱስ ሱራፌል በሥነ ሥርዓቱ ላይ በመገኘት ባስተላለፉት መልዕክት ስቅለት ኢየሱስ ክርስቶስ የሰውን ልጅ ከኃጢአት ለማንፃት ሲል በመስቀል ላይ የተሰቀለበት ሁነት መሆኑን ተናግረዋል።

የዚህም መለኮታዊ መልዕክት ማሳያነቱ ከራስ ባለፈ ለሰው ልጆች ሁሉ ዋጋ መክፈልንና የመልካምነት ሁነኛ ማሳያ መሆኑን አስረድተዋል።

የትንሳኤ በዓልም አጠቃላይ የማካፈልና የመረዳዳት መሆኑን ገልጸው በዓሉን እርስ በእርስ በመተሳሰብ፣ በመደጋገፍ፣ መልካምን ሁሉ በማሰብና በማድረግ ጭምር ልናከብረው ይገባል ብለዋል።

በልደታ ማሪያም ካቶሊክ ካቴድራል ቤተክርስቲያን ስቅለትን ያከበሩት የእምነቱ ተከታዮች በበኩላቸው ስቅለት አንዳችን ለሌላችን ዋጋ መክፈልን የሚያስተምር ነው ሲሉ መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

በመሆኑም የስቅለትን ብሎም የትንሳኤን በዓል ስናከብር ሁላችንም ከራሳችን አልፎ ለሌሎች ማሰብንና ማድረግን ዓላማ አድርገን መሆን አለበት ብለዋል፡፡

Читать полностью…

AddisWalta - AW

የትዳር መፍረስ እና የሀብት ክፍፍል
#ሕግ_ይዳኘኝ

ጋብቻ ከሚያስከትላቸው ውጤቶች አንዱ የጋራ ሀብት ነው፡፡ ፍችን ተከትሎ ብዙ ጊዜ ከሚፈጠሩት አለመግባባቶች አንዱ የጋራ ሀብት ክፍፍል ነው፡፡ አንድ ሰው ወደ ጋብቻ ከመግባቱ በፊት የነበረው ሀብትና ንብረት ከሕጋዊ ጋብቻው መፍረስ በኋላ የማን ይሆናል የሚለው ጉዳይ የብዙዎች ጥያቄ ነው፡፡

በዛሬው “ሕግ ይዳኘኝ” መርኃ ግብራችን ትዳር ሲፈርስ ተፋችዎቹ ሀብታቸውን እንዴት እና በምን አግባብ ይከፋፈላሉ በሚለው ርዕሰ ጉዳይ ላይ ትኩረት ይደረጋል።

በተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 62 መሰረት ባልና ሚስት ከግል ጥረታቸውና ከግል ወይም ከጋራ ንብረታቸው የሚያገኟቸው ገቢዎች ሁሉ የጋራ ሀብቶቻቸው ይሆናሉ፡፡ በዚህ ሕግ በአንቀጽ 58(2) መሰረት የአንደኛው ተጋቢ የግል ሀብት ነው ካልተባለ በስተቀር ባልና ሚስት ከተጋቡ በኋላ በግብይት የሚያገኙት ንብረት ሁሉ የጋራ ሀብታቸው እንደሚሆንም ተደንግጓል፡፡ በፍች ወቅትም ይከፋፈላሉ።

በስጦታው ውል ወይም በኑዛዜው ቃል በሌላ አኳኋን ካልተመለከተ በስተቀር በስጦታ ወይም በኑዛዜ የተሰጧቸውም ንብረቶች የጋራ ሀብቶቻቸው ናቸው፡፡ አንደኛው ተጋቢ የግል ሀብቱ መሆኑን ካላስረዳ በስተቀር ማንኛውም ንብረት በአንደኛው ተጋቢ ስም ብቻ የተመዘገበ ቢሆንም እንኳን የጋራ ሀብት እንደሆነ ይቆጠራል ሲል ቤተሰብ ሕጉ በአንቀጽ 63 አስቀምጧል፡፡

ባልና ሚስቱ ከተጋቡ በኋላ አንዱ የግል ሀብቱ በሆነ ንብረት ለውጥ ያገኘው ወይም በግል ገንዘቡ የገዛቸው ወይም የግል ንብረቱን ሽጦ የሚያገኘው ገንዘብ የግል ይባልልኝ ብሎ ለፍርድ ቤት ጥያቄ አቅርቦ ፍርድ ቤቱ ያጸደቀው እንደሆነ የግል ሀብቱ እንደሚሆንም በአንቀጽ 58 ተደንግጓል፡፡
👇👇
https://shorturl.at/ehnL8

Читать полностью…

AddisWalta - AW

ወረርሽኞችን ለመቆጣጠር የተሰሩ ስራዎች በቁጥር
#አዲስ_ዋልታ

Читать полностью…

AddisWalta - AW

የጠ/ሚ ጽሕፈት ቤት የ‘ገበታ ለሀገር' ፕሮጀክቶችን ለክልሎች አስረከበ

ሚያዚያ 24/2016 (አዲስ ዋልታ) የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የ‘ገበታ ለሀገር' ፕሮጀክቶችን ለአማራ፣ ለኦሮሚያ እና ለደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት አስረክቧል።

በተጨማሪም በገበታ ለሀገር የተገነቡ ሎጆችን ስራ የማስኬድ ተግባርን የኢትዮጵያ አየር መንገድ በስካይ ላይት ሆቴል ተቋሙ በኩል እንዲወጣ የስምምነት ፊርማ ሥነ ሥርዓት ተካሂዷል።

ከአራቱ የገበታ ለሀገር ፕሮጀክቶች ሶስቱ (ሃላላ ኬላ ሎጅ፣ ጨበራ ጩርጩራ የዝሆን ዳና ሎጅ እና ወንጪ ኢኮ ሎጅ) በቅርቡ መመረቃቸው የሚታወሰ ሲሆን የጎርጎራ ፕሮጀክት ስራም በመጠናቀቅ ላይ ይገኛል።

በጠቅላይ ሚኒስሩ ከፍተኛ ትኩረት እና አመራር የተከናወነው የ’ገበታ ለሀገር’ ስራ የብሔራዊው የሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ አንዱ ማዕዘን የሆነውን ቱሪዝምን የማሳደግ አላማ ያለው ነው።

እነዚህ ፕሮጀክቶች በመጀመሪያው ፋይናንስ የማሰባሰብ ምዕራፍ የኅብረተሰቡን ድጋፍ በሰፊው ያሰባሰቡ፣ በግንባታቸው ምዕራፍ ግዙፍ የስራ ዕድል የፈጠሩ ብሎም ታላላቅ የመሰረተ ልማት ስራዎች እንዲከናወን በር የከፈቱ ናቸው።

በፈጠራ የተሞላ የፕሮጀክት ስራ እና አስተዳደር እና ፈጣን አፈፃፀም ምን ሊመስል እንደሚችል ማሳያም መሆናቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት አመላክቷል።

ቀጣይ የስራ ማስኬድ እና ማስተዳደር ተግባሩ ለብሔራዊ ሰንደቅ ተሸካሚው የኢትዮጵያ አየር መንገድ በሃላፊነት መሰጠቱም የተሻለ አገልግሎት እንዲሰጥ ከማስቻሉም ባለፈ ለዓለም አቀፍ የቱሪዝም መዳረሻነት ትውውቅ ከፍ ያለ ዕድል ይፈጥራል ተብሏል።

Читать полностью…
Subscribe to a channel