weperspective | Unsorted

Telegram-канал weperspective - Perspective

-

Subscribe to a channel

Perspective

እነዚህ የውጪ መጽሐፎች የሚያስፈልጓችሁ ካላችሁ በደንብ ተመልከቷቸው ::

ዋጋቸው እያንዳንዱ የሚሸጠው 300 ብር ነው ::

ኦርደር ለማድረግ

Link - @thesunmon
Call - 0949006262

Читать полностью…

Perspective

Heroic Leadership
Leading with Integrity and Honor

Price - 350

To Order - @thesunmon

Читать полностью…

Perspective

The Theories Of Human Nature
Classical and contemporary reading

By :- Donald C . Abel

Only 1# Copy

For Order -

link 👉 @thesumon

Call 👉 0949006262

Читать полностью…

Perspective

‹‹ስለ እራቁት ነው እንዴ ?››
------
መቼ’ለታ እንደነገርኳችሁ አዳዲሶቹ መፅሐፎቼን ለመሸጥና ከአንባቢዎቼ ጋር ለመገናኘት ዛሬ ከሰአት በኋላ ሚሊኒየም አዳራሽ ተቀምጫለሁ፡፡


ብዙ ዓይነት ሰው አገኘሁ፤ ብዙ መፅሐፍት ሸጥኩ፤ ብዙ ሳቅኩ፡፡



ከሁሉ የገረሙኝን ምልልሶች መርጬ ላጋራችሁ፡፡

ለማስታወስ ያህል የቡና ቁርስ እና ለእርቃን ሩብ ጉዳይ የተባሉትን ሁለት መፅሐፎቼን ጠረጴዛ ላይ ደርድሬ ከአላፊ አግዳሚው ወደ እኔ የሚመጣውን ሰው ሰላም እያልኩ እያስተናገድኩ ነው፡፡


ሁለት ጠና ያሉ ዘናጭ ሴቶች ተጠጉኝ፡፡


አንደኛዋ ተገዳ የቆመች በሚመስል አኳኋን ከልቧ ሳትሆን ዙሪያ ገባውን ስታማትር ሌላኛዋ ለእርቃን ሩብ ጉዳይን አነሳችና፣
‹‹ሰላም›› አለችኝ፡፡
‹‹ሰላም›› መለስኩ፡፡
‹‹የራስሽ ታሪክ ነው ይሄ?››
‹‹አይደለም››
‹‹አናቃቂ ትምህርት ነው?››
‹‹ አይ አይደለም››
‹‹ታዲያ ምንድነው?››
‹‹አጫጭር ታሪኮች ናቸው፡፡ ልቦለድ››
‹‹ማለት?››
‹‹የፈጠራ ጽሁፍ››
‹‹ስንት ነው ዋጋው?››
‹‹ሶስት መቶ›››
‹‹አይቀንስም?››
‹‹ውይ እናትዬ አይቀንስም››
‹‹በይ እሺ በርቺ››
‹‹አመሰግናለሁ››


ሄዱ፡፡


አንዲት ወጣትና ቀጭን ልጅ ደግሞ ከሩቅ ስትበር መጣችና ልክ ጠጋ ብላ ስታየኝ
‹‹ውይ…ሜሪ ፈለቀን መስሽኝ ነበር››
‹‹አ…አይደለሁም››
‹‹አንቺ ማነው ስምሽ?››
‹‹ሕይወት››
‹‹እንደ ሜሪ ፈለቀ አይነት ነው የምትጽፊው …?››
‹‹እ….››
‹‹ሜሪ ፈለቀ የለችም እዚህ?››
‹‹እኔንጃ…አላየኋትም…እዚያ ጋር አዘጋጆቹ አሉ እነሱን ጠይቂያቸው››

በመጣችበት ፍጥነት ጥላኝ ሄደች፡፡


አራት ምርጥ ሽቷቸው ከእነሱ ቀድሞ የደረሰ ሂጃብ ያደረጉ ቆነጃጅት ተጠጉኝ፡፡


‹‹ለእርቃን ሩብ ጉዳይ…ስለ እራቁት ምናምን ነው እንዴ?›› አንደኛዋ ጠየቀችኝ፡፡
‹‹እ….›› አልኩ የምላት ግር ብሎኝ፡፡
‹‹ይሄኛውስ ስለምንድነው?…›› (የቡና ቁርስን አንስታ)
‹‹አጫጭር ታሪኮች ናቸው››
‹‹ሁለቱም ያንድ ሰው ናቸው?››
‹‹ አዎ…እኔ ነኝ የጻፍኳቸው››
‹‹እንዴ…አንቺ ነሽ ደራሲዋ?›› (ፊቷ እያበራ)
‹‹አዎ…››

ማሻላህ! (ሁለቱ ባንድነት)

‹‹ሴትንማ ማበረታታት አለብን እንግዛ››
‹‹ግዴለም ይሄ ራሱ ለእኔ በቂዬ ነው›› (አፍሬ)
‹‹እንዴ…እንገዛለን…የቡና ቁርሱ ስንት ነው?››

ሶስት የቡና ቁርስ ገዝተውኝ ከነመልካም ጠረናቸው ሄዱ፡፡



ደግሞ አንድ ተለቅ ያለ ሰውዬ መጣ፡፡
‹‹እንዴት ዋልሽ?› (ሁለቱንም መፅሐፍት አንስቶ እያየ)
‹‹ይመስገን ደህና››
‹‹ ምን ሆኛለሁ አለሽ?››
‹‹እ››
‹‹ምን ሆኛለሁ የሚለው መፅሐፍ…የትእግስት ዋልተንጉስ››
‹‹እ…አይ የራሴን ብቻ ነው የያዝኩት…››
‹‹እሺ…የዮሃንስ ሞላ አዲስ የግጥም መጽሐፍስ…?››
‹‹እሱንም አልያዝኩም…ሁሉም ደራሲ የራሱን ብቻ ነው የያዘው..ዮሃንስ ግን ያውልህ›› (ፊት ለፊቴ እየጠቆምኩ)

ግራ እንደተጋባ መፅሐፎቹን ቦታቸው መልሶ ወደ ዮሃንስ ሳይሆን ወደ አንሶላ መሸጫው ሄደ፡፡
ሰውየው ምን ሆኗል?

ደግሞ ሌላ ደልደል ያለ ሰውዬ ሰላም ብሎኝ ከተጠጋኝ በኋላ ፣


‹‹ስለምንድነው…ለምን መጻፍ ፈለግሽ…ማሳተም አይከብድም ወይ…ከዚህ በምታገኚው ገቢ ነው ኑሮሽን የምትገፊው….ለምን ስነልቦና ላይ አትፅፊም›› ብሎ በጥያቄ ጎረፍ ከመታኝ በኋላ የቱን ሊገዛ ይሆን ብዬ ስጠብቅ፣

‹‹በይ እሺ…እኔ እንኳን ፊልም እንጂ ንባብ ላይ እስከዚህም ነኝ›› ብሎኝ እብስ አለ፡፡


የሆነው ሆኖ የያዝኩትን መጽሐፍ ሁሉ ገዝታችሁ ለደገፋችሁኝ፣ ላበረታችሁኝ እና ላዝናናችሁኝ አንባቢዎቼ ሁሉ ቁና ሙሉ ምስጋና!
አልቋል ብዬ ለመለስኳችሁ ይቅርታ፤ ሁለቱም መፅሐፍ አሁንም ጃፋር ጋር ስለሚገኝ እዚያ ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ቸር ይግጠመን !

Читать полностью…

Perspective

ሀገር ያጣ ሞት - ሄኖክ በቀለ ለማ (Replay)

*ደራሲው በተገኘበት የተደረገ ውይይት

https://www.clubhouse.com/room/MO8WkoN5?utm_medium=ch_room_pxr

Читать полностью…

Perspective

" ማደግ የሚናፍቀኝ እንደነ ‘እገሊት‘ እንደነ ‘እገሌ‘ ለመሆን ሆነ ። እንደ‘ራሴ‘ መሆን መኖሩን የማውቅበት ስንዝር የሀሳብ ክፍተት አልነበረኝም ። እገሊትና እገሌን ለመሆን ስኳትን ብዙ ስብርባሪ እገሌዎችን ሆንኩ ።   ሁሉንም የምሞክር ፣ ልክና ስህተትን ልክ ሆኜና ተሳስቼ የምፈትን ፣ ቀናና ወልጋዳውን ቀንቼና ተወላግጄ የማረጋግጥ ሆንኩ ። ምክንያቱም ትክክለኛ መንገድ የሚሉትን በዱላና በስድብ ሊያሳምኑኝ ሲሞክሩ እንጂ ሲኖሩት አይቼ የማላውቅ ነኛ ! .. "

ጠበኛ እውነቶች
በሜሪ ፈለቀ
አምስተኛ ዕትም

Читать полностью…

Perspective

" ... አባቱ ሲገደሉ በዓይኑ አይቷቸዋል ። በራፋቸው ላይ ነው የተገደሉት ። ዳግማዊ አመሻሽ ላይ ወደ ቤት በሚወስደው ጭር ያለ ቀጭን መንገድ እየገሰገሰ ሰፈር ሲደርስ  ከወዳጃቸው ጋር እየተጓዙ አባቱን በርቀት አይቷቸዋል። እንዲያዩት ስላልፈለገ ወደኋላ ቀረት ብሎ ከአይናቸው ሰወር አለ ። ቤታቸው መግቢያ ጋር ሲደርሱ የተቃቀፉ መሰለው ። ብዙም ሳይቆይ ግን አባቱ ወደቁ ። ወዳጃቸው አካባቢያቸውን ቃኘት እያደረጉ ከሩጫ ባልተናነሰ ፍጥነት  ከዳግማዊ በተቃራኒ አቅጣጫ መሄድ ጀመሩ ። ዳግማዊ እየሮጠ አባቱ ጋ ሲደርስ ጣር ላይ ነበሩ ። ከደረታቸው የሚፈስ ደማቸውን እና በእጃቸው ፍራፍሬና የተጠቀለለ ኬክ መያዛቸውን እኩል ቃኘው ። የቅድስት አስራ አምስት ዓመት ልደት በዓሏ ነበር ። በጣር ስቃይ ውስጥ ሆነው እጁን ጨብጠው ቤተሰቡን እንዲንከባከብ ለመኑት ። ዳግማዊ ገዳያቸውን ከመከተልና አባቱን ከማንሳት የቱ እንደሚቀድም ግራ ገብቶት ዋለለ ። በደመ—ነፍስ የእናቱን፣ የእህቱን፣ የወንድሙን፣ የሚያስታውሰውን ሰው ስም ሁሉ በጩኸት ተጣራ። ... "

ጠበኛ እውነቶች
በሜሪ ፈለቀ
አምስተኛ ዕትም

በመደብሮቻችን ይገኛል !

Читать полностью…

Perspective

" የሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ የማይታወቅ ክስተት እንኳን ቢሆን ቀጣይ አለው ። ከመጀመሪያ ወይ ካለፈው የሚያይዘው ግምድ የድር ያህል የቀጠነ ቢሆንም ... ሁሌም ከመሃል ቆመህ ራስህን ስታገኘው መጀመሪያውን የምትጠይቀው ለዛ ማነው ። "

ከገጽ 101
ርዕስ - ጠበኛ እውነቶች
በሜሪ ፈለቀ

አምስተኛውን ዕትም በሁሉም መጻሕፍት መደብር ያገኙታል ::

መልካም ንባብ !

Читать полностью…

Perspective

¹ . ግራጫ ቃጭሎች
ደራሲ አዳም ረታ
የመጀመሪያው የ 1997 ዕትም
ይዞታ - ያገለገለ
መሸጫ ዋጋው - 450


² , ወንጀልና ቅጣት
ደራሲ - ፌይዶር ዶስቶቭስኪ
ተርጓሚ - ካሳ ገ/ሕይወት እና ፋንቱ ሳህሌ
የመጀመሪያው የ 1997 ዕትም
ይዞታ ያገለገለ
መሸጫ ዋጋ - 450

ለማዘዝ በ Telegram - @thesunmon

Читать полностью…

Perspective

" እናቴን ተመኘኋት " ይህ ርዕስ " ጠበኛ እውነቶች " ከሚለው መጽሐፍ ውስጥ ከአራቱ መሐል የአንዱ ታሪክ ነው :: የጽሑፉን ይዘት በአጭሩ በዚህ ድራማ ለማሳየት ተሞክሯል :: አምስተኛው ዕትም መጽሐፍ መደብሮች ላይ ይገኛል ሸምቱና አንብቡ :: መጽሐፉን እስክታነቡት ድረስ በዚህ ድራማ ይመቻችሁ 👍


https://youtu.be/W-SBEnlm7k4?si=dLEl5lBXiW-c6Dt2

Читать полностью…

Perspective

ለአምስተኛ ጊዜ የታተመው " ጠበኛ እውነቶች " መጽሐፍ የፊታችን ቅዳሜ በሁሉም መጻሕፍት መደብሮች እንዲሁም በአዟሪዎች እጅ ላይ ታገኙታላችሁ ::

መጽሐፉ በ 80 Gram ወረቀት እና በ ክሬም ( ሽሮ መልክ ) ወረቀት በከፍተኛ ጥራት ታትሟል :: 252 ገጾች አሉት :: መጽሐፉ በውስጡ አራት አጫጭር ታሪኮችን ይዟል ::

Читать полностью…

Perspective

እነዚህ ከገበያ ላይ የጠፉ መጻሕፍት ናቸው :: በቅናሽ መግዛት ከፈለጋችሁ በ 0949006262 ይደውሉ ወይንም በ ቴሌግራም ሊንክ @thesunmon በኩል ያነጋግሩን ::

Читать полностью…

Perspective

🌻 «ፀሓይ ከጨለማዬ ምን አለሽ?»

🕚 ነገ በጃዕፈር መጻሕፍት መደብር ያገኙታል።

Читать полностью…

Perspective

Must Read 30 books !

Читать полностью…

Perspective

" በሰዎች ዘንድ ተስፋ የሌለን ብንመስልም እንኳን ዋናው ነገር በፈጣሪ ዘንድ ያለው ተስፋችን ነው።ሕይወት ጠመዝማዛም ብትሆን ውብና ተስፋን የተሞላች ናት! በዚህ ዓለም ሁሉ ነገር አበቃ፤አከተመ ባልንበት ጊዜ የሚቀጥል የተሻለ እድል፤ የምናውቀውና የተለመደው በር የተከረቸመ ቢመስልም ወለል ብሎ የሚከፈት ሌላ በር፤ዙሪያችን ጭው ያለ በረሃ ቢሆንም የለመለመ መስክ የሆነ ስፍራ ላይ እንዳለ ተምሬያለሁ።ዕድል ፊቷን ያዞረችብን በመሰለን ጊዜ እንኳ ቢሆን አብዝቶ በትጋት መጓዝ እንጂ ተስፋ መቁረጥ አይገባም። ትጋት የተስፋ ልጅ ናት። ተስፋ ደግሞ በእኛና በፈጣሪ መካከል የእምነት ድልድይ ስለመኖሩ ማረጋገጫ ነውና ! "

   " ሰበዝ " ከተሰኘው ከዶ/ር ዓለማየሁ ዋሴ እሸቴ መጽሐፍ የተቀነጨበ ::


 
@weperspective

Читать полностью…

Perspective

Constitutional Law: A Contemporary Approach ( 2d Ed . 2011 )
Gregory E. Maggs & Peter J. Smith,

Abstract

The second edition of the textbook, which is suitable either for a one- or two-semester course, strives to make constitutional law easily teachable and readily accessible for students. The authors have selected the cases very carefully and provided fuller versions of the opinions so that students get a good sense of the Court's reasoning. Text boxes call the students' attention to important aspects of each opinion, and the book is filled with introductions, points for discussion, hypotheticals, and executive summaries. The authors present a diversity of views on every subject, and, reflecting some of their own disagreements, the authors have written point-counterpoint discussions on many disputed questions.

We have only 1 Copy

To Order - @thesunmon
0949006262

Читать полностью…

Perspective

The Theories Of Human Nature
Classical and contemporary reading

By :- Donald C . Abel

Only 1# Copy

For Order -

link 👉 @thesumon

Call 👉 0949006262

Читать полностью…

Perspective

እነዚህ በ INTERNATIONAL POLITICS ላይ የተጻፉ መጽሐፎች የምትፈልጉ ካላችሁ መሸጫቸው እጅግ ቅናሽ ነው በ ቴሌግራም Order ለማድረግ ይህን @thesunmon ሊንክ ተጠቀሙ ::

Читать полностью…

Perspective

📌"ነገረ መጻሕፍት" ቅዳሜ ይካሄዳል።

በዛጎል የመጻህፍት ባንክ የሚዘጋጀው "ነገረ መጻሕፍት" የመጻህፍት ውይይት የቦታ ለወጥ አድርጎ ነገ ቅዳሜ ጥቅምት 30  2017 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ጀምሮ ምኒልክ ሆስፒታል አካባቢ በሚገኘው "FSS" አዳራሽ ውስጥ ይካሄዳል።

በዚህ መሰናዶ ላይ  ጓድ ፋሲካ ሲደልል፣ እና ኮሎኔል መርሻ ወዳጆ ተጋባዥ እንግዶች ሲሆኑ ለውይይት የሚቀርቡ አብይ ርዕሰ ጉዳይ "የታኅሣሥ ግርግር(1953 ዓ.ም) እና የግንቦቱ መፈንቅለ መንግስት(1981 ዓ.ም) " ይሰኛል።የፕሮግራሙ አዘጋጅና አቅራቢ ደራሲ እንዳለጌታ ከበደ ነው።

ለተጨማሪው: /channel/EventAddis1

Читать полностью…

Perspective

ይህን የተመሰከረለት መጽሐፍ አነበባችሁት ?
አምስተኛው ልዩ ዕትም ወደማለቁ ነው :: ካልገዛችሁት ግዙ እና አንብቡት ::
ትወዱታላችሁ
ትማሩበታላችሁ
ራሳችሁን ታገኙበታላችሁ ::


አዲስ አበባ ጃፋር መጽሐፍ መደብርን ጨምሮ በሁሉም መጽሐፍ መሸጫ ያገኙታል ::

እንዲሁም :-

ባህር ዳር
ናዝሬት
ሐዋሳ ያሉ መጽሐፍ መደብሮች ውስጥ ታገኙታላችሁ ::

Читать полностью…

Perspective

ሰላም ወዳጆች ስለ መጽሃፍት ማስታወሻዎች/ አበርክቶዎች/dedications ይቺን ሶስት ጥያቄ የያዘች ቅጽ በመሙላት ተባበሩን። https://docs.google.com/forms/d/1fDw86HvJP3CBfW7WWCWfZ0N-vt71ROs5-qZ4eb79GeI/edit

Читать полностью…

Perspective

ከዐፄ ምኒሊክ ሰራዊት ጋር
አዘጋጅ - በአሌክሳንደር ቡላቶቪች
ትርጉም በአምባቸው ከበደ
ይዞታ - የተነበበ ( ያገለገለ ) በጥሩ ሁኔታ ላይ ያለ

ለማዘዝ - በቴሌግራም ሊንክ @thesunmon ይጠቀሙ

Читать полностью…

Perspective

ስብስብ ግጥሞች
ገጣሚ - በዕውቀቱ ስዩም
ያለን ብዛት - ሁለት ፍሬ
ይዞታ - የተነበበ ( ያገለገለ )


ለማዘዝ - በቴሌግራም @thesunmon

Читать полностью…

Perspective

የቃየን መሥዋዕት
ደራሲ ሠርቅ ዳ .
ይዞታ - የተነበበ ግን በጥሩ ሁኔታ ላይ ያለ
መሸጫ ዋጋው - 300 ብር

ለ Order በ Telegram Link - 👉 @thesunmon

Читать полностью…

Perspective

📌የሜሪ ፈለቀ "ጠበኛ እውነቶች"መጽሐፍ አምስተኛ ዕትም መጽሐፍ ለንባብ በቃ

ከዓመታት በፊት ለንባብ የቀረበው የደራሲ ሜሪ ፈለቀ "ጠበኛ እውነቶች" አምስተኛ ዕትም መጽሐፍ ለአንባቢያን ቀርቧል። 

"ጠበኛ እውነቶች" መጽሐፍ በ4 ክፍሎች የተከፈለ ልብወለድ ሲሆን የተለያዩ ማህበራዊ እና ግላዊ ሕይወትን የሚዳስስ መፅሐፍ ነው። በዚህ መጽሐፍ ውስጥ የተካተቱ የአራቱ ታሪኮች ርዕሳቸው ቅዳሴና ቀረርቶ፣ቀላውጦ ማስመለስ፣ እናቴን ተመኘኋት፣ምርጫ አልባ ምርጫ ይሰኛሉ ::

መጽሐፉ በ252 ገፆች የተቀነበበ ሲሆን በ350 ብር የጀርባ ዋጋ ለአንባቢያን ቀርቧል። በተለያዩ መጻሕፍት መደብሮችም ይገኛል ተብሏል።

ለተጨማሪው:/channel/EventAddis1

Читать полностью…

Perspective

«ፌሚንዝም ...
.
... አስተሳሰብ ነው ... እንቅስቃሴም ነው ... እምነትም ነው!
.
ከምእራቡ የመነጨ ... የሴቶችን በደል መቃወምን ተገን ያደረገ ... የፆታን ሚናን አደባልቆ የወንዱን አባወራነት፣ ቤተሰብ ጠባቂነት፣ መሪነት ሰልቦ ሴቷን አደባባይ ያሰጣና ለአውሬዎች ያጋለጠ ... እናትነትን የቤት እመቤትነትን አንቋሾ ትውልድ ቀራጭነቷን የነጠቀ ነው!
.
የሚናው መደበላለቅ ሄዶ ሄዶ ወንዱ ሴት እንዲጠላ ሴቱም ወንድ እንዲጠየፍ አድርጎ ከተፈጥሮ አጋጭቶ Homosexualityን ያፈራና ያበረታታ ... ብሎም በደስታ እጦትና ተስፋ መቁረጥ ህፃናት ሳይቀሩ አካላቸውን እያስበለቱ ፆታ ለመቀያየር የሚተጉበትን ማህበረሰብ የፈጠረ ሁኗል!
.
Feminism በርግጥ FEMINAZi ሁኗል!
.
ወዲህ ተመሳሳይ መዝሙር ይዘመራል ... መብት ይከበር፣ በደል በዛ፣ ወንዱ ጨቋኝ ሆነ እትትት ግትት ... እንዲህ ያሉ ወንዶች ራቂ ... እንዲህ ካለው ጋር መኖር አትችይም ... እንዲህ ያለው ጥንቅር ይበል ... ራስሽን ገንቢ፣ ለራስሽ ዋጋ ስጪ፣ ያለወንድ መኖር ትችያለሽ ... ከዛስ?
.
ከዛስ?
.
ወንፊቱ በጠበበ ቁጥር የሚያልፈው እህል ይቀንሳል ... ይሄን መልሺ ያንን አታግቢ የተባለች ምስኪን መስፈርቷ ሲበዛ አማራጯ ይጠባል ... ነፍሷን ክባ ክባ የመጣውን ሁሉ እየናቀች ትመልሳለች ... በሂደት ተስፋ ወደ መቁረጥና አላህ ሐራም ያደረገውን ወደ መዳፈር ትገባለች ... የሚረባ ወንድ አጣን ብለው ወደ ማዶ የሄዱ የሉንም?
.
ያገባችውስ ... በየቦታው ይሄ አይነት ግንኙነት Toxic ነው በተባለች ቁጥር ባሏን ደመኛ እያደረገች ... እስካሁን በሰላም የኖረችውን እንደመሰበር፣ ለራስ ዋጋ አለመስጠት አርጋ እያሰበች ... ያለችበትን ጠልታ ... "Strong Independent Women" ይሉት ብሂል አፍቅራ ... ከዚህ ጋር እድሜዬን ከማባክን ብቻዬን በነፃነት ልኑር ትልና የራሷ መላጣ ሳይታያት በባሏ ገበና ተሳልቃ ትዳሯን ትበትናለች ... ከዛ ከህዝቡም ከአቅሏም ስትናቆር ራሷን ታሞኝበት ዘንድ ያለወንድ መኖር ይቻላልን ታቀነቅናለች ... አይቻልም የኔ እህት ...  አይቻልም!
.
እሱም በየሚድያው ዘራፍ የሚሉትን እያየ ... ያንን ይዘው እንደበቀቀን የሚያስተጋቡትን እየፈራ ... በዚህ ደሞ የፌሚንዝሙ መርዝ እሱንም ከሚናው እያዛነፈው ... ወንድነቱን እየሸረሸረው ...  አሁን ከዚች ጋር ብኖር ባል እኔ ነኝ እሷ እያለ ትዳርን እንዲፈራ እንዲሸሽ ... የሐላሉ መንገድ ዳገት ሆኖበት ዝሙትን አማራጭ እንዲያደርግ ... ወይ ደሞ ሟምቶና ፈስቶ የኃላፊነት ድርሻውን ተናዙል አርጎ ሁለት ባል ባንድቤት ይፈጥራል ... ምእራቡ እንደዛ ነው ... የኛም አያያዝ አስፈሪ ነው
.
ግን ግን ...
.
... በሆነ ገጠመኝ ቡሻጋ ሚስቱን በደለና ሁላችንንም ቡሻጋ የምንመስላቸው ... ወንዶችን በቡሻጋ መስለው ዲስኩር የሚነፉ ... ጥላቻ የሚዘሩ ... በየገጠመኛቸው ያቆሰላቸውን እያከኩ የሚጮሁ ... ወይ ደሞ ... ሙሽሪት ስታለቅስ አይተው እየተብከነከኑ ሁሉንም ሸምሱ በዳይና አስለቃሽ ... ሁሏም ሙሽሪት ንፁህና ቀና አድርገው የሚስሉ ... ጣሳችሁ! ተመለሱ! ሲባሉ ደሞ መብታችንን እንዳንጠይቅ አታሸማቁን የሚሉን እባካችሁ ወደቀልባችሁ ተመለሱልን!
.
እና ደሞ በተናጠል እገሊት ፌሚኒስት ነሽ ስላሏችሁ አትሆኑም ... ምናልባት በቀቀን ትሆኑ ይሆናል ... እርግጠኛ የምንሆነው ግን ወይ በእድሜ ብስለት ወይ ደሞ በበሳል ባል ትቶብታላችሁ።
.
እኛ ግን የመሰለንን ሳይሆን ያየነውን እናወራለን ... እንዳይከፋችሁ!»
©: Bin Ali

/channel/sunrisebookss

Читать полностью…

Perspective

በብዙ አንባቢዎች ዘንድ ሲፈለግ የነበረውና ከገበያ ጠፍቶ የነበረው የሜሪ ፈለቀ " ጠበኛ እውነቶች " መጽሐፍ አምስተኛው ዕትም በቅርብ ቀን ይጠብቁን !!

Читать полностью…

Perspective

"A book is a timeless vessel that carries the wisdom of generations, inviting minds to sail through its pages and explore the boundless oceans of knowledge within."

Читать полностью…

Perspective

48 Books To Read In 2024. 📚
-
Communication:-
How to talk to anyone
Talk like ted @carminegallospeaker
How to win friends and influence people.
The Communication book .

Human. Behaviour:-
The Laws of human nature @robertgreene
Games people play
Thinking Fast and slow
Influence

Self help:-
Beyond good and evil
13 Things Mentally Strong People Don't do Amy Morin, LCSW
The Five Regrets of the dying.
What to say when you talk to yourself.

Personal finance:-
Just keep buying Nick Maggiulli fx
Rich dad poor dad Robert Kiyosaki
I will teach you to be rich
The Intelligent investor

Productivity:-
Atomic habits James Clear
Getting things done @dallen45
How to finish everything you start
Do it today Darius Foroux

Relationship:-
How to be an adult in relationship
Closer to love Vex King
Men are from Mars women are from Venus
How to not die alone Logan Ury

Business:-
The personal MBA
Your next five moves Patrick Bet-David
What they teach you at Harvard business school.
Zero to one .

Critical thinking:-
Think again @adamgrant
Predicatbly Irrational Dan Ariely
Factfulness
The art of thinking Clearly.

Mental health :-
Why has nobody told me this before Dr Julie
The body keeps the score
You can heal your life @louise_hay_affirmations
The happiness trap

Creativity :-
Originals @adamgrant
Steal like an artist
The war of art .
Creativity inc

Discipline:-
Discipline is destiny Ryan Holiday
Can't hurt me
Make your bed .
The power of self discipline

EQ (Emotional intelligence)
Emotional intelligence.
Emotional agility Susan David
The power of now Eckhart Tolle
Permission to feel
-
@weperspective
-
-
Save and share with your friends.
-

Читать полностью…

Perspective

ሸገር ሼልፍ፦ መግባት እና መውጣት ከበዕውቀቱ ስዩም ወግ ተራኪ አንዷለም ተስፋዬ - ጥር 3፣2016     

https://youtu.be/HYf8uYVzHb0   

#Sheger_Shelf #Bewketu_Seyoum #Andualem_Tesfaye #Sheger_Tereka #ሸገር_ሼልፍ #ትረካ #በዕውቀቱ_ስዩም #መውጣት_እና_መግባት

Читать полностью…
Subscribe to a channel