ዘወትር እሁድ የሚጠብቁት የሪፖርተር ጋዜጣ የተለያዩ መረጃዎችን ይዞ በገበያ ላይ ይገኛል
በድረገጻችን https://www.ethiopianreporter.com/ ላይም ያገኙታል።
----------||----------
የሪፖርተር ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ
ፌስቡክ↠ https://bit.ly/2Iv9bZB
ትዊተር↠ https://bit.ly/35qeNwV
ቴሌግራም↠ https://bit.ly/3Qb4N1M
ዩቲዩብ ↠ https://bit.ly/3p0jUQY
ቲክቶክ ↠ https://bit.ly/3Ruxsyv
የ ስራ ማስታወቂያዎች ↠ EthiopianReporterJobs.com
Join us on 👇/channel/weperspective
ሲፈለግ የነበረው የሕግ መጽሐፍ
በሁለት ቅጽ ተከፋፍሎ ታትሟል
የተጠቃሰሱ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ሰበር ሰሚ ችሎት
ከቅጽ 1-25 የታተሙ እና ከ2006 እስከ 2015 የተሰጡ ያልታተሙ ዉሳኔዎች
በመላከ ጥላሁን( LLB/LLM)
ይህን በዋጋ ሊተመን የማይችል የፌደራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የታተሙ እና ያልታተሙ ዉሳኔዎችን በአንድ ላይ አጠቃሎ የያዘ መጽሃፍ ላይ አስተያየት የመስጠት እድል አግኝቻለሁ፡፡
ይህ ስራ ዳኛ መላከ ጥላሁን ትጋት እና ብቃት የተሞላበት ስራ በመስራት እነዚህን ለበርካታ ዓመታት ያልታተሙ ዉሳኔዎችን ጭምር በጥንቃቄ ሰብስቦ እና የታተሙትን ዉሳኔዎች አጠቃልሎ በጉዳዮች ዓይነት ከፋፍሎ በማቅረብ በቀላሉ ተደራሽ እንዲሆኑ የተደረገበት ነዉ፡፡
ይህ ጥንቅር ለጠበቆች፤ዳኞች እና ለምሁራን ጠቃሚ ግብዓት ነዉ፡፡የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት አስገዳጅ የሕግ ትርጉም በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ዳሰሳ ተደርጎ የሚሰጥበት ነዉ ተብሎ የሚገመት ሲሆን በመጽሐፉ ጉዳዮች በደንብ የተደራጁ እና በዉሳኔዉ እልባት ያገኘዉን የሕግ ጭብጥ በቀላሉ ለማግኘት የሚረዳ እንዲሁም ማጠቃለያዎቹ አጭር እና መረጃ ሰጪ ናቸዉ፡፡ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የሚሰጣቸዉን ዉሳኔዎች ለማናቸዉም ሥራ መመርመር እና መጠቀም ለሚፈልግ ማንኛዉም ሰዉ ይህን ጥንቅር እንዲጠቀም እመክራለሁ።
አልማው ወሌ
የቀድሞ የፌ/ጠ/ፍ/ቤት ስበር ሰሚ ዳኛ
አሁን ጠበቃና የሕግ አማካሪ
4ኪሎ ምኒልክ ት/ቤት ፊት ለፊት ከሮሚና ዝቅ ብሎ።
ሥልክ፦ 0912735000
0905222224
ይህ የእነሆ መጻሕፍት የቴሌ ግራም ቻናላችሁ ነው የተለያዩ አዳዲስ መጻሕፍት ይተዋወቁበታል። የእነሆ መጻሕፍት ግብዣችን ጥቆማ ይቀርብበታል።
/channel/enhobooks
#ፍርሃትህን_ተጋፈጠው!!!
የወደቅከው በፍርሃት የተነሳ ነው እንጂ አቅም አንሶ ወይም ስለማትችል አይደለም።
ፍርሃት አቅምህ አሽመድምዶ እራስህ አሳንሰህ እንድታይ ያደርግሀል። ነገርግን እውነታው ያ አይደለም። ፍርሃት እንዳይሰማ የማይቻል ቢሆንም ፍርሃትህ የህይወት መሪ አለማድረግ እና አለማደመጥ የአንተ ድርሻ ነው።
ፍርሃቱ እያለብህ ማድረግ የለብህ ነገር መፈፀም አለብህ። ልጅ እያለን ትምህርት ቤት የምናውቀውን ነገር ፊት ላይ ወጥተን ለሌሎች አቅርቡ ስንባል ፍርሃት እና ብርክ ብርክ ይለን ነበር። ከዚህም አልፎ የምናውቀው ነገር ሁሉ ይጠፋብን ነበር። ፈርተን ስናወራ እና ሲስቁብን የበሰ ከዚህ በኃላ ሰው ፊት ወጥቼ አናወራም እንል ነበር። እናም አሁን በህይወታችን ብዙ ነገሮች መሞከር አቆምን፤ ምክንያቱም በልጅነታችን እንደተሳቀብን አሁን ብንወድቅ ወይም ብንሳሳት ይስቁብኛው ብለን ስለምናስብ።
ፍርሃትህን አሸንፈው። ምክንያቱም ብዙ ህልሞች የሞቱት በፍርሃት መሆኑን እወቅ። ሩቅ የሚያስጉዝ አቅም አሳስሮ የሚያስቀምጥህ ፍርሃት የተበለ ነቀዝ ነው። ምን ይሉኝ ይሆን ብለህ አትስብ፤ የሚሉትን ይበሉ፤ ግን መኖር አለብኝ ብለህ የምታስበው ኑር። ደፋር ሁን፤ ፍርሃት እንኳን ዙሪያህ ቢከብህም። አንተ የሚወቅስህ እና አትችልም የሚልህ አብዛኛው ጊዜ ምንም ነገር ሞክሮ የማያወቅ የመቀመጥ ንጉስ፣ የጥላቻ አለቃ የሆነ ሰው ነው። ተዋቸው ያሉትን ይበሉ። ዛሬ እኳ ነው ዳዴ የምትለው ከሆነ ጊዜ በኃላ ምን ያህል እርቀት ከእነሱ እንደሚኖርህ አስብ።
በህልምህ አትቀልድ፤ በህልምህ አታሹፍ፤ መከፈል የለበት ዋጋ ከፍለህ መድረስ የለብህ ነገር ጋር ድረስ። ፍርሃት ተጋፈጠው፤ እንደምትችል እመን። አሁን ጀመሪ ነህ። ማንንም አልሰማህ ሲልህ አይዞህ ሁሉም ከመውደቅ ነው መራመድ ቀላል የሆለት። ምን ይሉኛ የሚለው ፍርሃት ከብዙ ነገር ወደኃላ እንዳስቀረህ ስታስብ ልትቆጭ ይገባል። ዋናው ፈጣሪ የሚከብርበት ሰው የማይጎዳ ነገር ከሆነ ለምን ብለህ ነው የምትሳቀቀው። ሰው ፊት ወጥተህ ማቅረብ ስትጀምር ስትንቀጠቀጥ፣ የሌለብህ መንተባታብ ስንተተባተብ፤ አይገርም ነገሩ ሳታውቀው ቀርታህ አይደለም። ነገር ግን ፍርሃት ስላለሸንፈከው ነው።
አየህ ትክክል ነው ወይ ያልኩት ብለህ ስትጨነቀ የባሰ ምንም እንደማያውቀው ሰው ትሆናለህ። እና ፍርሃት ያስመለጠህ ብዙ ዕድሎች እንዳሉ አይሰማህም። ስለዚህ ፍርሃት ህልምህ ከመግደሉ በፊት አንተ ተጋፈጠው።
✍️ህልመኛው
📕📕📕
(በየቀኑ አነቃቂ መልእክቶችን፣ ከምናሳትማቸው መጽሐፍት ፒዲኤፍ፣ የገንዘብና የመጽሐፍት ሽልማቶችን ለማግኘት የፌስቡክና ቴሌግራም ገጾቻችንን ይቀላቀሉ።)
ቴሌግራም- /channel/teklu_tilahun
ፌስቡክ ገጽ 1- https://bit.ly/3sNq5Kd
ፌስቡክ ገጽ 2- https://bit.ly/3sJcsMa
Ethiopia in Theory - Elleni Centime Zeleke
የ1966 አብዮት እና በአብዮቱ ዙሪያ የነበሩ ኀልዮቶች (Theories) በድህረ አብዮት ዓመታት ፣ በቅድመ እና ድኅረ ምርጫ-97 እና የቅርብ ዘመን የኢትዮጵያ ፖለቲካ ላይ ስላሳደሩት ተጽዕኖ በሚዳስሰው መጽሐፍ ዙሪያ የኢትዮጵያ ቡክ ፎረም አሰናኞችና ተሳታፊዎች ውይይት ያደርጋሉ።
የውይይቱ ሊንክ:
https://www.clubhouse.com/invite/b36S0GJWq9Dw60GN5AEpeoykRDpRFOVD53R:sfyjXXKaDs0wd5CtxvyEbYqvTLkHZJWRDgO6EF1K4RQ
#ዛሬ_የሕይወታችሁ_የመጀመሪያው_ቀን_ቢሆን!
እንደምን አደራችሁ የሃገሬ ሰዎች፡፡
“ዛሬ የሕይወታችሁ የመጀመሪያው ቀን ነው!” ብትባሉ . . .
• ምን በማድረግ ቀኑን ትጀምራላችሁ?
• ምንስ በማቆም ቀናችሁን ትጀምራላችሁ?
• የትኛውን ነገር በመርሳትና ወደኋላ በመተው ሕይወታችሁን ትጀምራላችሁ?
• ከየትኛው መርዛማ ግንኙነት በመለየት ወደፊት ለመሄድ ውሳኔን ታስተላልፋላችሁ?
• ለወደፊቱስ ምን አይነት እቅድ ታወጣላችሁ?
• እስካሁን ተጨንቃችሁ ምንም ለውጥ ያላመጣችሁትን የትኛውን ጭንቀት ለመተው ትወስናላችሁ?
በሉ እንግዲያው፣ “ዛሬ ለተቀረው ዘመናችሁ የመጀመሪያው ቀን ነው”!
“Today Is The First Day Of The Rest Of Your Life” - Charles Dederich
መልካም ቀን ይሁንላችሁ!
ዶ/ር ኢዮብ ማሞ
/channel/weperspective
አንድ ሀገር ከሌሎች ሀገራት የምትበደርበት ምክንያት ብዙ ቢሆንም ዋናው የካፒታል ችግር በተፈጠረ ወቅት ነው! የብድር ዕዳን መክፈል አለመቻል (በኢኮኖሚ እድገት መገታት ምክንያት፤ የፖለቲካ አለመረጋጋት በመኖሩ ምክንያት እና የሀገሪቷ ፋይናንስ ተቋማት እንቅስቃሴ ጤነኛ በማይሆንበት ወቅት ሊሆን ይችላል) እንዲሁም እዳን ለመክፈል አለመፈለግ ደግሞ ተጨማሪ ዕዳ የመክፍል አቅም መዳከም (Default) ውስጥ ይካተታሉ፡፡
የውጪ ብድር አወሳሰድ ባህሪ የቀጥታ ብድር (የውጪ ምንዛሬውን በቀጥታ መስጠት)፤ የቁሳቁስ እና የአገልግሎት ብድር፤ የፕሮጀክት ብድር (አበዳሪ ሀገርት ለተበዳሪ ሀገራት ፕሮጀክት በመስራት ዕዳውን ማስመዝገብ! ለምሳሌ ፈጣን መንገድ በመገንባት ወጪውን እንደዕዳ ማስቀመጥ)፤ የቦንድ ሽያጭ፤ ወዘተ ሊሆን ይችላል፡፡
ሀገራት የውጪ ዕዳ ውስጥ እያሉ ተጨማሪ በመበደር ሰርተው እዳቸውን በመክፈል ከዕዳ ለመላቀቅ አልያም ከተመጣጣኝ የዕዳ መጠን ጋር አብረው ለመኖር ሊመርጡ ይችላሉ፡፡ ብድር እና የብድር ወለድ አለመክፈል ሀገራት በቀጣይ ብድር እንዳያገኙ ከማድረጉ በተጨማሪ አበዳሪ ቢያገኙም ከስጋት የተነሳ ከፍተኛ ወለድ ሊጣልባቸው ይችላል፡፡
ለምሳሌ……
በኢኮኖሚ እድገት መቀዛቀዝ ምክንያት ራሽያ እና ዩክሬን በ1998፤ አርጀንቲና በ2001 እና ቬንዚዮላ በ2017 (በዓለም ላይ ለ11 ጊዜ ዕዳ መክፈል ያልቻለች የሚል ዝርዝር ውስጥ የገባች ሀገር ነች)፤ ከዕዳ ክምችት የተነሳ ግሪክ በ2012 እና ሌባኖስ በ2020፤ በፖለቲካ አለመረጋጋት ምክንያት አርጀንቲና በ2014 እና 2019፤ ኢኳዶር በ2008 እና በ2020፤ ወዘተ ዕዳ መክፈል ያልቻሁ ነበሩ፡፡
አንዳንድ ሀገራት ሌሎች ሀጋራት ዕዳ ለመክፈል በተቸገሩ ጊዜ ቴክኒካል እገዛ በማድረግ ዕዳዋ እንዲቃለል ሊያደርጉ ይችላሉ (ተጨማሪ በማበደር፤ የውጪ ምንዛሬ በካሽ በመስጠት፤ ቦንዶቿን በመግዛት እና ስቶኮቿን በመግዛት) የዚህ አይነቱ ዘዴ Bailout Funds ይባላል (ሜክሲኮ ዕዳ ያለመክፈል ደረጃ ላይ በደረሰች ወቅት አሜሪካ፤ ካናዳ፤ ወዘተ ይህንን ስልት ተጠቅመዋል)፡፡
በዓለም ላይ ያሉ ሀገራትን የእዳ መጠን መረጃ እና ወደፊት ስለመክፈል እና ስላለመክፈል አዝማሚያ መረጃ የሚያወጡ ዓለም አቀፍ ተቋማት አሉ ዋነኞቹ Fitch Ratings (በአሜሪካ እና በእንግሊዝ መቀመጫውን አድርጎ የሀገራትን የእዳ የመክፈል አቅም ደረጃ ያወጣል) እንዲሁም የአሜሪካዎቹ Moody's Investors Service እና Standard & Poor's (S&P Global Ratings) የሚባሉም አሉ፡፡ የዓለም አበዳሪ ሀገራት፤ ግለሰቦች እና ተቋማት የዚህ ተቋም የሀገራት ብድር የመመለስ ወይም ያለመመለስ ደረጃን በመጠቀም የማበደር ውሳኒያቸው ያስተካክላሉ፡፡
ለምሳሌ ለሀገራት እዳ የመክፈል አቅማቸውን ለመለካት የሚጠቀመው ደረጃ በጣም ጠንካራ የገንዘብ ፈሰስ አድራጊ ለሆነ ሀገር AAA ሲሰጥ ጭራሽ መክፈል ያልቻለችን ሀገር D ብሎ ያስቀምጣል፡፡ ከ AAA እስከ D ባለው ዝርዝር ውስጥ ብዙ ደረጃዎች አሉ፡፡
ጥሩ የሚባለው ደረጃ (AAA)፤ ከፍተኛ ደረጃ (AA+, AA, AA-)፤ ከመካከለኛ በላይ ደረጃ (A+, A, A-)፤ ዝቅተኛ መካከለኛ ደረጃ (BBB+, BBB, BBB-)፤ የኢንቨስትመንት ያልሆነ ደረጃ (BB+, BB, BB-)፤ በቅርብ መታየት ያለበት (B+, B, B-)፤ ጉልህ አደጋ ያለው (CCC+, CCC)፤ መክፈል ያልቻለ (CCC-, CC)፤ የተበላሹ ተበዳሪዎች ደረጃ (C, DD, D) ተብለው ይፈረጃሉ፡፡
ለምሳሌ፡ በ2023 ጥሩ የሚባለው ደረጃ ማለትም AAA ውስጥ ያሉ ሀገራት አውስትራሊያ፤ ዴንማርክ፤ ጀርመን፤ ኔዘርላንድ፤ ሉግዘምበርግ፤ ሲዊድን፤ ሲዊዘርላንድ፤ ሲንጋፖር፤ ኖርዎይ ናቸው። Fitch Ratings የዛሬ አምስት ወር አሜሪካን ከነበረችበት AAA ወደ AA+ ዝቅ አድርጓታል፡፡
በዚህ ወር ከተመለከትን ኢትዮጲያን ከነበረችበት CC ወደ C ዝቅ አድርጓታል (ሀገሪቷ December 14, 2023 በአመት ሁለት ጊዜ ከሚከፈለው የቦንዱ ወለድ ውስጥ 33 ሚሊየን ዶላር ካለመክፈሏ ጋር ተያይዞ የደረጃ ለውጥ አድርጓል (ጠቅላላ በቦንድ የተወሰደው ብድር ለአስር ዓመት ቆይታ ማለትም ከDecember 2014 ጀምሮ አንድ ቢሊየን ደላር ሲሆን መክፈያው December 2024 ነው)፡፡ በየዓመቱ ከ62 ሚሊዮን ዶላር ወለድ ስትከፍል ቆይታለች።
ኢትዮጲያ በቅርብ አመታት ብድራቸውን መክፈል ካልቻሉት ጋና (ያለባት ዕዳ መጠን 47.3 ቢሊየን ዶላር) እና ዛምቢያ (ያለባት ዕዳ መጠን 6.3 ቢሊየን ዶላር) ጋር የውጪ ዕዳቸውን በሚጠበቀው ልክ መከፈል ካልቻሉት ደካማ ሀገራት ተርታ ተመድባለች፡፡
የኢትዮጲያ መንግስት የቦንድ ዕዳውን (የኢትዮጵያ ቦንድ ባለቤት ካፒቱሉም አሴት ማኔጅመንት ኩባንያ ይባላል) በተመለከተ አዲስ የድርድር አዝማሚያ ያለው ሲሆን የክፍያ መጠናቀቂያ ወቅት እንዲራዘም (ቢያንስ ለአራት ዓመታት)፤ የቦንዱ ወለድ መጠን እንዲቀንስ (ከ6.625 ከመቶ ወደ 5.5 ከመቶ ይገኙበታል) እንዲሁም አበዳሪዎችን እኩል ማስተናገድ የሚል መርኅ ማስጠበቅ ምክንያት ናቸው፡፡ ኢትዮጲያ በጠቅላላ 28.2 ቢሊየን ዶላር የደረሰ የውጪ ዕዳ አለባት፡፡
የውጪ እዳ አለመክፈል በቀጣይ ብድር ያለማግኘት እንዲሁም ብድር ቢገኝ እንኳን ከስጋት የተነሳ ከፍተኛ ወለድ ለመክፈል መገደዷ አይቀርም ይህ ደግሞ ከፍተኛ የውጪ ምንዛሬ እጥረት ላለበት ኢኮኖሚ በቀላሉ የሚታይ አደጋ አይደለም! የኢትዮጲያ ኢኮኖሚ ይህንን ዕዳ ባለመክፈል የመጣን ጫና ለመቋቋም በማሰብ የውጪ ምንዛሬ ግኝት ለመጨመር በሚል የውጪ ምንዛሬ ፖሊሲ ማሻሻያ ሊያደርግ ይችላል (ገንዘብን ማዳከም ሊጨምር ይችላል!)፡፡ ከዕዳ አለመክፈል ፍረጃ ለመውጣት ወሳኙ ጉዳይ ኢኮኖሚን ጠንካራ ለማድረግ የምርታማነት አቅምን ማሳደግ እና የተረጋጋ የፖለቲካ ሁኔታ መፍጠር መሆናቸው ግልጽ ነው፡፡
ከየኢኮኖሚ ባለሙያ ዋሲሁን በላይ ገጽ የተወሰደ
ሸገር ሼልፍ - በአንዷለም ተስፋዬ - ታህሳስ 19፣2016
https://youtu.be/r2O9FxSa6rM
#Ethiopia #ShegerFMRadio #ShegerShelf #AndualemTesfaye
Graphic Design and Visual Art Workshop
📅 Dec 30, 2023
📍 Mexico
🙏 @Hayugashaw
Want to be in a creative field of work?
... be a visual artist?
... be a graphic designer?
Join us on our Free workshop, experience sharing and networking event on the upcoming Saturday afternoon!
1. Get to meet with invited professionals and artists.
2. Get to experience a day of our visual art and Graphics design classes.
3.Discuss FAQs of joining creative fields of work.
4. Be inspired and learn from their journey.
Door opens at 7:30 till 11:30... Local local time.
register now!!
✅ only limited spot
‼️ Last chance to secure a spot in our one month trainings ‼️
Register here: https://forms.gle/1xmqPUYjU4nSCBLH6
Call us: 0911745308/ 0988747878 or @merahyancontact
Make sure to connect with us @merahyan Instagram | TikTok
@weperspective
Life is a complex and dynamic phenomenon, characterized by the ability of organisms to grow, reproduce, undergo metabolism, and respond to their environment. It encompasses a wide range of forms and functions, from single-celled organisms to multicellular organisms like plants and animals. The definition of life can vary across scientific, philosophical, and cultural perspectives.
Читать полностью…ተጠንቀቁ!
ስለትዳራችሁ ስለባላችሁ ለሌላ ወንድ የምታሙ ሴቶች እነዚህን እኔ የማውቃቸውን የአራት እህቶች መጥፎ ገጠመኞች ተመልከቱና ትዳራችሁን ታደጉ።
የአራቱ እህቶች ገጠመኝ (ስማቸው ለዚህ ፅሁፍ የተቀየረ)
ሰኪና ትባላለች። ባሏ ጋር በመለስተኛ ጉዳይ ተጋጭተዋል። የ9ኝ ወር ነብሰ ጡር ናት። ከባሏ ጋ ያላቸው ግጭት ተራና የተለመደ የባልና የሚስት ግጭት ነው። ነገር ግን ጉዳዩን አክብዳ በመመልከት ባሏ እያሰቃያት እንደምትኖር ቢሮ ውስጥ ለምታውቀው ኤፍሬም ለተባለ ሰው ደጋግማ ታወራዋለች። ኤፍሬም ሁኒታውን ሊጠቀምበት ፈለገ። ነይ እኔ ቤት እኔ ጋ እንኖራለን። ይላታል። ሰኪና ዛሬ ከኤፍሬምም ከባሏም አይደለችም። ያ ያማረ ትዳር ተበትኗል።
መኪያ ትባላለች ። በተደጋጋሚ ስለ ባሏ ያላትን የተሳሳተ ግንዛቤ በቅርብ አውቀዋለሁ ለምትለው ሚኪ ለተባለ ልጅ ስለ ባሏ ክፉነት፣ ስለባሏ በዳይነት፣ የሱ እርዳታ እንደሚያስፈልጋት፣ እንዲመክራት ደጋግማ ትወተውተዋለች፣ የባሏን ገመና ሁሉ ትዘረግፍለታለች። ሚኪ በሂደት መኪያን የማባለግ ፍላጎቱን በአዘኔታ ሽፋን ለውሶ ቀረበ። እስኪ በአካል እንገናኝ ይላታል። ወደ ቤቱ እንድትመጣና ከሱ ጋ መኖር እንደምትችልምእንደምትችል ደጋግሞ ይወተውታት ጀመር። እሷ ግን ፈቃደኛ አልሆነችም። ሊያባልጋት እንደፈለገ ብታውቅም ከሱ መራቅ ግን አልቻለችም። ሚኪ ያሰበው አልሳካ ሲለው መልሶ በደካማ ጎኗ ያስፈራራታል። የባሏን ገመና ስለመበተኗ እያነሳ ያሸማቅቃታል።
ይህ በሚኪና በመኪያ መካከል ያለው የቴሌግራም የቻት ጉድ ለባሏ ደርሶ መኪያ ትዳሯን አጥታለች።
ነዒማ ትባላለች። ከባለቤቷ ጋ መሰረታዊ ግጭት የላቸውም። ግን በወሲብ መጣጣም አልቻሉም። ስንፈተ ወሲብ አለበት። እሷ ይህንን ሆነ ብሎ እሷን ጠልቶ ለቅጣት እየተጠቀመው ነው ብላ አሰበች። ባለመነጋገርም ለአመታትም ያለ ወሲብ ግንኙነት በአንድ አልጋ ላይ ከረሙ። መፍትሄ ብላ ያሰበችው እሱን አማክሮ አሳምኖ በጋራ መፍትሄ መፈለግን ሳይሆን በኢማኑና በጥንካሬው ለምታደንቀው ዶክተር ጉዳዩን አማከረችው። ያማከረችበት መንገድ ግን ትክክል አልነበረም። ዶክተሩ አጋጣሚውን መጠቀም ፈለገ። እዛው በግል ፋርማሲው ሊደፍራት ሞከረ። አንቺኛዋ ከዚህ የባሰ ነገር ውስጥ ከመግባትሽ በፊት እረፊ! በግል ችግርሽን ከባልሽ ጋር ብቻ መፍትሄ እንድትፈልጊ ብዙ አማራጮችን ነግሬሻለሁ። በአደባባይም ይሄው ደገምኩት። አደጋ ላይ ነሽ።
ሉባባ ትባላለች። ምንም እንኳን ባሏ እጅግ ታታሪና ቤቱን ወዳጅ አወሷንም አፍቃሪ ቢሆንም ለሉባባ ግን ፍፁም ሊዋጥላት አልቻለም። በተደጋጋሚ ፌስቡክ ላይ ታዋቂ ለሆኑ ሰዎች፣ ባሏ ሲያደንቃቸው ለሰማቻቸው ጓደኞቹ፣ ለቀናት ላወቀችው ሰው፣ ለኡስታዞች ባሏን እንደማትወደው፣ ጨካኝ እንደሆነ፣ ክፉ አረመኔ እንደሆነ፣ ደካማ እንደሆነ የመናገር ሱስ አለባት። በስልክ፣ በቻት አጀንዳዋ ባሏን ለሌላ ወንድ ማብጠልጠል ነው። ሉባባ በተደጋጋሚ የምታገኘው ግን ልታማክራቸው የሞከሩት ሁሉ ለብልግና ሲፈልጓት፣ እነሱ የተሻሉ መሆናቸውን እየገለፁ ከባሏ ሲያራርቋትና ሲመኟት እንጅ ትዳሯን ለማስቀጠል ሲሞክሩላት አይደለም። ግን በነሱ መፈለግን ከባሌ አጥቸዋለሁ ብላ ላሰበችው ፍቅር ማስታገሻ አድርጋው ዘልቃለች። በመጨረሻም ትዳሯን በዚሁ አጥታለች።
እነዚህ የማስታውሳቸው እህቶች ናቸው። አብዱልጀሊል ታዋቂ ነው በሚል ለኔም ስለባሎቻቸው ነውር ካማከሩኝ ከመቶ ሴቶች በላይ መካከል ለከፋ ሁኔታ የተጋለጡት ናቸው።
____
በባልና በሚስት መካከል ያለን አለመስማማት፣ የባልን ገመና፣ የባልን ደካማ ጎን የሱ ወይም ያንቺ የቅርብ ዘመድ፣ ሽማግሌ፣ ባለሙያ ካልሆነ በፌስቡክ፣ በሚዲያ፣ በስራቦታ ላወቅሽው ወንድ ስለባልሽ ክፋት የምትተርኪ እህት ምን ፈልገሽ እንደሆነ አንቺም ታውቂዋለሽ!
የምታማክሯቸው፣ የምታሙላቸው ወንዶች ለችግሮቻችሁ መፍትሄ ከመፈለግና ትዳራችሁ እንዳይፈርስ ከመጣር ይልቅ ፣ ከፊሎቹ የልጆቻችሁን አባት ክፉነት፣ ደካማነት እያጋነኑና እያጋጋሉ እነሱ የተሻሉ መሆናቸውን በመግለፅ ወደ እነሱ እንድታስቡ በማድረግ ወይም ቀጥተኛ ባልሆነ መንገድ እነሱ ሊጠቀሙባችሁ ሞክረው ወይም ተሳክቶላቸው አባልገው ትተዋችኋል። አገባሻለሁ ያለ ላያገባሽ ከባልሽ አትባባሽን መረዳት አቅቷችሁ ስንቶቻችሁ ትዳራችሁን በትናችኋል?
አብዛኛው ወንድ ያዘነልሽ መስሎ አጥፊሽ ነው። መለየት በማትችይው የለበጣ እዝነት ለክፉ ዓላማው የሚያመቻችሽ ነው። ባልሽን ያነወርሽበትን እሱ ጠንካራ እንደሆነ እየገለፀ፣ ከልጆችሽ አባት በላይ አዛኝሽ መስሎ እየቀረበ ለእደናው እያዘጋጀሽ ነው።
የስንቶቻችሁን ታሪክ እና መጨረሻውን አንዳንዷ እጅግ የተዋረደውን መጨረሻ አዋይተሽኛል። እረፊ ዕህት ዓለም! ወላህ ከባልሽ በላይ ወገን የለሽም‼ ባልሽ ላንች የፈለገውን ጨካኝ ቢሆንኳ ለሌላ ወንድ ስለሱ ባወራሽ ቁጥር አላህ እየቀጣሽ ነው።
…………
እህትዓለም! የልጆችሽ አባት ምን ክፉ ቢመስልሽ ወገንሽ ነው። ወንድምሽ ነው። የልጆችሽ ጥላ ነው። የልጆችሽ ስጋ ነው። የእሱን ደካማ ጎን በመዘርዘር ከተለያዩ ወንዶች ጋ የምታደርጊው (ማማከር በሚሉት ሽፋን) ግንኙነት መጨረሻው አደገኛ ነው። ስለዚህ በተለይ ታዋቂ ናቸው በሚል በየሚዲያው ለምታውቁት ወንድ የቤታችሁን ምስጥር የምትዘረግፉ ባለትዳሮች አላህንም ፍሩት!!
እኔኳ የስንቱን ቤት ነውር ሰማሁት! የስንቷን መጨረሻ ታዘብኩት።
***
ዐብዱልጀሊል አሊ ካሳ እንደጻፈው
ቴዎድሮስ ገብሬ በእኔ የንባብ ልማድ በየትኛውም የውጭ የስነ-ሰብ ምሁር ንድፈ ሀሳብ አይሰፈርም፡፡ የእገሌ ደቂቅ ነውም አይባልም፡፡ ይልቁኑስ ነገ በወጉ ሊጠና የሚገባውን ሥነ-ጽሁፋዊ “ቴዎሪና ሜቶዶሎጅ” እየተከለ ያለ ይመስላል፡፡ ምናልባት የዓለም ሥነ-ጽሑፍ ጥናት ፈር አስያዦቹ ጆናታን ከለር እና ሜሪ ሮዛሪዎ አምሳ ዓመት ያልሞላው “ወጣት” (ለእንደሱ ዓይነት የሥነ-ጽሁፍ አጥኝ ዕድሜው ገና የሚባል ስለሆነ) ላይ ያዩት ነገርም ይኼ ሳይሆን አይቀርም፡፡
መዝጊያ፤ ይህ መዝጊያ የተወዳጅ ሚድያ የመዝገበ-አእምሮ ቦርድ አባላት አቋም የሚንጸባረቅበት ነው፡፡
ሀገራችን ብዙ ያልተነገረላቸው መምህራን ይዛለች፡፡ መምህር የሁሉም ሙያ አባት ቢሆንም ተገቢውን እውቅና እና ክብር ሲያገኝ ብዙም አይስተዋልም፡፡ ሌሎችን ያበቃል፤ እንደሻማ ቀልጦ ያስተምራል ነገር ግን በስተፍጻሜ ይዘነጋል፡፡ ተወዳጅ ሚድያ እና ኮሚኒኬሽን ጥሩ ምስክርነት እያላቸው ነገር ግን ወደ ህዝብ ላልደረሱ ሰዎች ሁሌም ጋሻ ነው፡፡ ካሉበት ቦታ ወጥተው ስራቸው እና የህይወት ተሞክሯቸው ለአደባባይ እንዲበቃም ይጥራል፡፡
መምህር ቴዎድሮስ ገብሬ በተማሪዎች የሚከበር ብቻ ሳይሆን ለሀገሪቱ የስነጽሁፍ መንገድ አዲስ መንገድ ያመለከተ ነው፡፡ ይህ ደግሞ ከመምህር የሚጠበቅ ነው፡፡ መምህር አዲስ ስልት ፈጣሪ፤ ያልተሄደበትን መንገድ ሞካሪ ነው እንጂ በባህላዊ መንገድ የሚነጉድ አይሆንም፡፡ ከላይ የህይወት ታሪኩን ያየንለት ሰው ቴዎድሮስ ገብሬ ጥልቅ ንባቡ አዲስ እይታ እንዲመለከት አግዞታል፡፡ ይህ ጥረቱ ደግሞ መና ሆኖ አልቀረም፡፡ በታላላቆቹ መምህራን ሳይቀር መደነቅ የቻለ ነበር፡፡ ታዲያ እንዲህ አይነት የሰላ ሂስ መሰንዘር የሚችሉ ሊቆች ምነው ቢበዙልን፡፡
ተወዳጅ ሚድያ በቅርቡ በሚታተመው መዝገበ-አእምሮ ውስጥ የመምህር ቴዎድሮስን ታሪክ ለመካተት ስንወስን ከላይ የተቀመጡት ጉዳዬች አሳማኝ ሆነው ስላገኘናቸው ነው፡፡ ባደረግነው ምርምር መምህሩ ሊመሰገን እና ሊሸለም የሚገባው ነው፡፡ ምክንያቱም አዲስ መንገድ አመለክቷል፡፡ እንዲህ አይነት ሰዎችን ለታሪክ ማስቀመጥ ትልቁ ሃላፊነታችን ስለሆነ ይህንኑ አደራ ተወጥተናል፡፡ ይህ መጣጥፍ በጋዜጠኛ ይነገር ጌታቸው አርታኢነት በጋዜጠኛ እዝራ እጅጉ አዘጋጅነት ዛሬ ታህሳስ 13 2016 በተወዳጅ ሚድያ ዲጂታል ሚድያዎች የተቀመጠ ነው፡፡ በዚህ ጽሁፍ ላይ ሀሳብ ካለዎት በ0911416678 መሰንዘር ይችላሉ፡፡
ቴዎድሮስ ባለፉት 20 ዓመታት የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ቆይታው ከ22 የሚልቁ ጥናታዊ ጽሁፎችን ለንባብ አብቅቷል፡፡ “በይነ-ዲስፕሊናዊ የሥነ-ጽሑፍ ንባብ” የተሰኘ የአንድ ብዙ የሆነ መጽሐፍን ለአንባቢያን አድርሷል፡፡ እነዚህ ጥናቶች ወሰናቸው እጅጉን ሰፊ ነው፡፡ ከፍ ብለን እንደጠቀስነውም ቴዎድሮስን ረቂቅ የሚያደርጉትም ይመስላሉ፡፡ ከሥነ-ማኅበረሰብ እስከ ሥነ-ልቡና፣ ከታሪክ እስከ ፍልስፍና ይዘልቃሉ፡፡ ፊዚክስን በሚቶሎጅ ፣ ሳይንስን በሃይማኖት ይሞግታሉ፡፡ ወዲህ የተክለሃይማኖትን ገድል በጆሴፍ ካምቤል የተጋድሎ ሚዛን ይሰፍራሉ፡፡ ወዲያ የልብ ወለድ ድርሰቶችን ከታሪክ መጻሕፍት በላይ ሀቀኛ የዘመን ምስክር ያደርጋሉ፡፡
ቴዎድሮስ ገብሬ ከሰፊው አንባቢ ጋር የተገናኘው በ2001 ዓ.ም ለንባብ ባበቃው “በይነ-ዲስፕሊን የሥነ-ጽሁፍ ንባብ” መጽሐፉ ቢሆንም ከዚያ ቀድም ብሎ ግን በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ውስጥ መነጋገሪያ መሆኑ አልቀረም፡፡ በሁለት ምክንያቶች፤ ቀዳሚው ትልቁ የሥነ-ጽሁፍ መምህር ዮናስ አድማሱ (ዶ/ር) በተማሪያቸው ከመደነቃቸው ይመነጫል፡፡ ዮናስ ለተማሪዎቻቸው የሰጡትን የቤት ሥራ ሲያርሙ እንግዳ ጉዳይ ገጠማቸው፡፡ ሁለተኛ ዲግሪውን ማጥናት ከጀመረ ቀናት ያስቆጠረው ቴዎድሮስ ገብሬ ያቀረበው ጽሁፍ ግራ አጋባቸው፡፡ አስጠሩት፤ “ይህን ጽሁፍ አንተ ነህ የሠራኸው እንዳልል ሀሳቡ በፍጹም በአንተ ደረጃ ያለ ተማሪ የሚያቀርበው አይደለም፡፡ አይ የአንተ አይደለም እንዳልል እንዲህ አድርጎ በአማርኛ የሚጽፍ የውጭ አገር ዜጋ የለም፡፡ እስኪ ንገረኝ?” አሉት፡፡ የራሱ መሆኑን አስረዳቸው፡፡
የአማርኛ ሥነ-ጽሁፍ ጥናት ባለሟሉ ዮናስ በቀጣይ ቀን ክፍል ውስጥ ያወሩት ስለምንም አልነበረም፡፡ “ይኼውላችሁ ልጆች አንድ ነገር ልንገራችሁ፤”አሉ፡፡ “አውሮፕላን መብረር የሚችለው በተፈቀደለት ከፍታ ብቻ ነው፡፡ ከዛ በላይ ከወጣ ራሱን ለአደጋ ያጋልጣል፡፡ ስለሆነም ከተፈቀደላችሁ ከፍታ በላይ ወደ ላይ ስትወጡ ተጠንቀቁ፤”፡፡ ዮናስ ተማሪያቸውን እያሰቡ ክፍል ውስጥ ይህን ይበሉ እንጂ ያንን ያረሙትን ጥናት ግን ለሚያከብሯቸው ወዳጆቻቸው ሁሉ ማካፈላቸው አልቀረም፡፡
በመሆኑም ቴዎድሮስ ገብሬ ገና የሁለተኛ ዲግሪውን ትምህርት በጀመረ በጥቂት ወራት ውስጥ ስሙ በሥነ-ጽሁፍ ትምህርት ክፍሉ ብቻ ሳይሆን በሌሎችም ምሁራን ዘንድ ይታወቅ ያዘ፡፡ ከእነዚህ መካከል የወቅቱ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት እንድርያስ እሸቴ ተጠቃሽ ናቸው፡፡ ጥቁሮች በተማሪነት እንኳን ለመግባት በሚቸገሩበት የአሜሪካን ዩኒቨርስቲ ውስጥ በመምህርነት ያገለገሉት፤ የኢትዮጵያን ኪንና ሥነ-ጽሁፍ በወጉ ያጠኑት የፍልስፍናው ሊቅ እንድርያስ በሚመሩት ግቢ ውስጥ እየተማረ ያለ “ልጃቸውን” መጨረሻ ለማየት መጓጓታቸው አልቀረም፡፡
ስለሆነም ቴዎድሮስ የሁለተኛ ድግሪ መመረቂያ ጽሑፉን ሲያቀርብ ባልተለመደ መልኩ የዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት ተገኙ፡፡ ቀኑ ለተማሪው ቴዎድሮስ ብቻ ሳይሆን ለመምህሩ ዮናስም ዕረፍት መስጠቱ የሚቀር አይመስልም፡፡ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የቀድሞ መማሪያ ክፍሎች (OCR) ያልበቃቸው የቴዎድሮስ ገብሬ ሀሳቦች ከዚያ ወዲያ ከልካይ አልነበራቸውም፡፡ በተማረበት ሥፍራ መምህር ተባለ፡፡ በጌታቸው ኃይሌ (ፕ/ር) እና ዮናስ አድማሡ (ዶ/ር) ትጋት ወደፊት የተጓዘው የኢትዮጵያ ሥነ-ጽሁፍ ጥናት ሦስተኛውን መሪ አገኘ፡፡
የእርሱ ዘመን እውቀት ማዕከል አልባ ነው፡፡ እንደ አባቶቹ በበሩ ከሚያልፍ ጅረት ቀድቶ ከመጠጣት ከፍ ይላል፡፡ ብዙ እውነቶች ብዙ መንገዶች በሚታዩበት የዓለም የሥነ-ጽሑፍ ጥናት ውስጥ ራሱን ካልቃኘ የተቸካይነቱ ዕዳ ግለሰባዊ ብቻ አይመስለኝም፡፡ የአገሩን ሥነ-ጽሁፍ ይዞት እስከመሞት ይደርሳል፡፡ እዚህ ሥፍራ ላይ በነባሩ መንገድ ስለማይዳኝ ብቻ ከሥነ-ጽሁፍ ትምህርት ቤቱ ተገፍቶ የኖረውን አዳም ረታ ቴዎድሮስ ገብሬ ባይደርስለት ኑሮ አሁን የቆመበት ቦታ ላይ ይገኝ ነበር? ብሎ መጠየቅ ያሻል፡፡ ከ“ማሕሌት” እስከ “የስንበት ቀለማት” የተንጣለለው የአዳም “ቤተ-ሙከራ” ሁነኛ ባለሙያ ባያገኝ ኖሮ ኦናነቱ መልሶ አያፈርሰውም ነበር? ወይ ብሎ ማሰብም ይገባል፡፡
ቴዎድሮስ ገብሬ አስቀድመን እንዳየነው የሁለተኛ ዲግሪ ጥናቱን ከሌሎች ጉዳዮች ጋር አጣምሮ “በይነ-ዲስፕሊናዊ የሥነ-ጽሁፍ ንባብ” በማለት ለአንባቢ ያቀረበው በ2001 ዓ.ም ነው፡፡ ወቅቱ ለኢትዮጵያ ሥነ-ጽሁፍ ብቻ ሳይሆን አጠቃላይ ለሆነው የአገሬው “አካዳሚያዊው” ምልከታም የብራ መብረቅ የሚባል ሳይሆን አይቀርም፡፡ ድንገት ወድቆ እልፎችን የሚያስደነግጥ፡፡
“የእኔ ሥፍራ የቱ ጋር ነው?” የሚያስብል፡፡ ቴዎድሮስ በዚህ ሥራው የበርካታ የጥናት መስኮችን ድንበር እያፈረሰ አንድ ላይ ቀይጧቸዋል፡፡ መጓተት የሚቀናቸውን “ዲስፕሊኖች” በሥነ-ጽሁፍ አርቋቸዋል፡፡ ሃይማኖት ፀረ-ሳይንስ ነው መባሉን ሽሮ እምነትን ሳይንሳዊ አድርጎታል፡፡ ልብወለድን አተርኮ የልቡና ጠባሳችንን ቁልጭ አድርጎ አሳይቷል፡፡ ዮናስን እንዲህ ያለው ልህቀቱ ሳይሆን አይቀርም ሦሰተኛ ድግሪውን ጨርሶ እርሱ ክፍል እየገባሁ እስክማር እጓጓለሁ እንዲሉ ያደረጋቸው፡፡ ሞት ቀደማቸው እንጂ!
ቴዎድሮስ ማንም የማይነቀንቃቸውን የአገሬው ምሁራን በመጽሐፉ ማነጋገሩ የቀደመ ቢሆንም ባሕር ማዶ የታወቀው ግን “Myth and Sexuality: A Mythopoeic Reading of Le’tum Aynegallign” የተባለ ጥናቱን ካቀረበ በኋላ ነው፡፡ ይህ ወቅት ሁለት “ጎረምሶች” አንድ ላይ የገጠሙበት ይመስለኛል፡፡ ቀዳሚው ማሳያዬ የሁለቱ ሰዎች ትውውቅ ነው፡፡ ቴዎድሮስ ገና በአፍላነቱ ዘመን ብሔራዊ ቤተ-መጽሐፍትና ቤተ-መዛግብት ኤጀንሲ እየገባ ሲያነብ ያገኛቸው የነበሩ አሮጌ መጽሐፍት የነተበ የእጅ ጽሑፍ ያለባቸው ነበሩ፡፡
እነዚህ ጽሑፎች በ1950ዎቹ አጋማሽ ወጣት የነበረው ስብሃት ገብረእግዚአብሄር ያሰፈራቸው ናቸው፡፡ የቴዎድሮስና ስብሃት ትውውቅ መጽሐፍ ላይ ነው፡፡ ትልቁ ጸሐፊ ያነበባቸውን መጻሕፍት በነፍስ ጥቅሻ ትልቁ የሥነ-ጽሁፍ ሰውም ከዓመታት በኋላ አግኝቷቸዋል፡፡ ይህ መንገድ ቴዎድሮስና ስብሃት በልቡና እንዲጎራበቱ ማድረጉን እርግጠኛ አይደለሁም፡፡ ነገር ግን የስብሃት ገብረእግዚአብሔርን ሥራዎች የዘመናት ቅኔ ለመፍታት ቴዎድሮስ ገብሬ የሚባል ሰው በኢትዮጵያ ሥነ-ጽሁፍ ጥናት ታሪክ ውስጥ መጠበቅ ነበረበት፡፡
ስብሃት ገዳማዊውን የአገሬው “ጥበበ ቃል” ልማድ የበጠበጠ “ጎረምሳ” ከተባለ፤ቴዎድሮስም የቀደመው የኢትዮጵያ ሥነ-ጽሁፍ ጥናት የጠበበው አቻው መሆኑ የሚያከራክር አይደለም፡፡ አንዳንዴ እንደውም የዘመንን ግንብ አፍርሰው አብነት ትምህርት ቤት እንዳለ ተማሪ ቅኔ የሚነጣጠቁ ሁላ ይመስላሉ፡፡ ማስረጃችን የቴዎድሮስ ጥናት ነው፡፡ እማኛችን ደግሞ “ሌቱም አይነጋልኝ” የተባለ “ተናዋሪ”፡፡
ቴዎድሮስ ገብሬ ለዘመናት በአገሬው አንባቢ ውግዝ ተብሎ የኖረውን ድርሳን አንስቶ “የፍቅር እስከ መቃብር” አቻ “የአደፍርስ” እና “ከአድማስ ባሻገር” እኩያ ያደርገዋል፡፡ ይህ ሽግግር በአንባቢው ልቡና ውስጥ ሚታዊ መልክ የሚኖረው ይመስላል፡፡ ከሴተኛ አዳሪነት ለቅድስና እንደመጠራት ያለ ሃይማኖታዊ ገድል፡፡ ቴዎድሮስ “ሌቱም አይነጋልኝ”ን በኢትዮጵያ ጥንታዊ ድርሳናት ውስጥ ፈልጎ ያሳየናል፡፡ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መልኩን በርብሮ ይገልጥልናል፡፡ ታዲያ ከዚህ በላይ አመጽ፤ከዚህ በላይ “ጉርምስና” እና አፍራሽነት ከየት ይመጣል?!
ዮናስ አድማሱ(ዶ/ር)የተማሪያቸውን የቴዎድሮስ ገብሬን ማንነት ለመረዳት ብዙ ጊዜ አልፈጀባቸውም፡፡ ወደዱት፤እንዲያሻው እንዲያስብ እንደፈለገው እንዲሞግት ዕድሉን ሰጡት፡፡ እርሱም አከበራቸው፡፡ የተማሪና መምህር ግንኙነቱ በጦፈ ክርክር ተተካ፡፡ ትናንት “ሰባሪህ” ይሆናሉ የተባሉት አንጋፋ መምህራን በምርቃቱ ሰሞን እዚህ ቅር አሉት ፡፡
ዮናስ ጠንከር ያለ ምስክርነት ፃፉ፡፡ ፍቃደ አዘዘ(ዶ/ር) ከጎኑ ቆሙ፡፡ ይሁንና በተቋማዊ አሰራር ችግር ምክንያት የሁለቱ ምኞት በቶሎ የሚደርስ አልሆነም፡፡ ዮናስ ተበሳጩ፡፡ ሥራዬን እለቃለሁ ብለው ተቆጡ፡፡ ፍቃደ አዘኑ፡፡ ልጁን ማጣት የለብንም ብለው ተሟገቱ፡፡አምሮታቸው ትክክለኛ ተተኪን ፍለጋ ብቻ አይመስልም፡፡ ይህ ሰው ለነገው የኢትዮጰያ ሥነ-ጽሁፍ ጥናት አስፈላጊ እንደነበር እርግጠኞች ነበሩ፡፡ አሰልቺ የመሰለው ውስጣዊ ክርክር ከዘጠኝ ወራት በኋላ እልባት አገኘ፡፡ቴዎድሮስ ገብሬ በአገሪቱ ስመ-ጥር ዩኒቨርስቲ የሥነ-ጽሁፍ መምህር ሊሆን ጉዞ ጀመረ፡፡
እዚህ ላይ ግን በኮተቤ ከነበረውም በላይ ያወዛገበውን የሁለተኛ ድግሪ ማሟያ ጥናት ሳያነሱ ማለፍ ንፉግነት ነው፡፡ ንትርኩ ልማድ ከማፍረሱ ነበር፡፡ የተመረጡ የአማርኛ ልብወለዶችን ከርዕይ መነጠቅ አንፃር ሲተነትን ግርታው ናረ፡፡ ትልልቅ የፍልስፍና እና የሥነ-ልቡና ንድፈ ሀሳቦችን ተመርኩዞ ድርሰቶቹን መፈተሸ ያስኬዳል አያስኬድም ተባለ፡፡ዘገየ እንጂ ወደ ሰፊው አንባቢም መድረሱ አልቀረም፡፡ የሁለተኛ ዲግሪ መመረቂያ ጥናቱን ያካተተው “በይነ-ዲስፕሊናዊ የሥነ-ጽሁፍ ንባብ” መጽሐፍ በ2001 ዓ.ም ለንባብ ሲያበቃ ዝምታ የዋጠው የኢትዮጵያ ሥነ-ጽሁፍ ጥናት አንዳች ነገር እንደወደቀበት ተናወጠ፡፡
ጋዜጣ ላይ የክርክር አጀንዳ ሆነ፡፡አድናቆቱም ዘገየ እንጂ አልቀረም፡፡ የአማርኛ ሥነ-ጽሁፍ ጥናትን ቀያሪነቱ ታወጀ፡፡ ቴዎድሮስ በእዚህ ሥራው ላይ ዮናስ አድማሱን አልዘነጋቸውም፡፡ “ተቀመጥ በወንበሬ ተናገር በከንፈሬ ያለከኝ አንተን አመሰግንሃለሁ ”ብሎ ስብሃት አደረሰ፡፡ አላቆመም፤ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተነባቢ በሆነው የምርምር መጽሔት ላይ ጥናቱ ሲታተምም የአማርኛ ሥነ-ጽሁፍ ባለውለታውን- ዘከረ፡፡
“በይነ-ዲስፕሊናዊ የሥነ-ጽሁፍ ንባብ” መጽሐፍ የተለያዩ የጥናት መስኮችን ያጎራበተና አንዱን ከአንዱ ያዋደደ ነው፡፡ የሥነ-ሥዕል መምህሩ አገኘሁ አዳነ እንደሚለው ቴዎድሮስ ለኢትዮጵያ ሥነ-ጽሁፍ ብቻ ሳይሆን ለዘመነኛው የኢትዮጵያ ሥነ-ሥዕልም ውለታን ትቷል፡፡ “የስድሳዎቹ የዘመን ምልክቶች እነ ሶሎሞን ደሬሳ፣ ክፍሌ ብጽአት፣ ግርማ ኪዳኔ፣ ስብሐት ገብረእግዚአብሔር እና በሰባዎቹ ግድም ደግሞ እነ ስዩም ወልዴ የደከሙበትን ነገረ-ሥዕል በምዕተ ዓመቱ መባቻ ቴዎድሮስ ገብሬ የካሰው [የሚክሰው] ይመስላል፡፡” የአገኘሁ ምሥክርነት አላበቃም፡፡
የሥነ ሥዕል ዓለም ሓቲታዊ አንጻር ባለቤት ቸግሮት ብቅ ጥልቅ በሚሉ የጊዜው ጥራዝ ነጠቅ "ሙያተኛ ነን" ባዮች ሲወጣ ሲወርድ፣ ቴዎድሮስ ገብሬ የተባለ መፍትሄ እንደመጣለት የሚመሰክሩ፣ በሥነ ሥዕል ጉዳይ ላይ የተሠሩ የቅርብ ጊዜ ጥናቶቹ ጥሩ ማሳያዎች ናቸው። "አካል በሥነ-ጽሑፍ ውስጥ"፣ "የነገሮች መቃ(የ)(ለ)ጥ፣ የበቀለ አሻራዎች" እና "በቀለ መኰንን በብሔራዊ ትዕምርት ፍለጋ ውስጥ" የሚሉት መጣጥፎችም ለእዚህ ጠንካራ አብነት ይሆናሉ፡፡
የቴዎድሮስ ከሥነ-ጽሁፍ ያለፈ አስተዋጽዖ (በቀጣዩ ክፍል በስፋት ተዳሷል) በመገናኛ ብዙሃንም ላይ ያረበበ ነው፡፡ በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን የቲቪ መዝናኛ ቻናል ሥራ አስኪያጁ ዘካርያስ ብርሃኑ የቀድሞ መምህሩ ስለራሱ አያውራ እንጂ ተማሪዎቹ ግን በኢትዮጵያ ሥነ/ኪነ-ጥበብ ውስጥ የጎላ አስተዋጾን እያበረከቱ ነው ይላል፡፡ ቴዎድሮስም የዳር ተመልካች አለመሆኑን ይጠቅሳል፡፡ ለዚህ ደግሞ እማኙ ዘካሪያስ በኃላፊነት የሚመራው ጣቢያ “ፍቅር እስከ መቃብር” ልብወለድን ወደ ቴሌቪዥን ድራማ ለመቀየር እያደረገ ባለው ጉዞ የቀድሞ መምህሩ ለስክሪፕት አዘጋጆች፣ ለዳይሬክተሮች፣ለተዋንያን ወዘተ በሥነ-ጽሁፍና ፊልም ላይ ያለውን ተክህኖ (Mastery) እያካፈለ እንደሆነ ያነሳል፡፡
የሚድያ ሰው ዘካሪያስ ቴዎድሮስን ሲገልጸው አንድ ትልቅ መምህር ሀገራችን እንዳፈራች በማሰብ ነው፡፡ ዘካሪያስ የሰጠን ምስክርነት ተጨምቆ ሲቀርብ እንዲህ ነው፡፡
‹‹……በከፍተኛ የትምህርት ዓለም ቆይታዬ ካጋጠሙኝ እጅግ ድንቅና ልዩ መምህራን አንዱ ቴዎድሮስ ገብሬ ነው።በእውቀትና በስነምግባር ሞልቶ የተረፈው ሰው የሱን ያህል አላየሁም።እሱን ማወቄና በእሱ መማሬ በሕይወቴ ካጋጠሙኝ እጅግ መልካም አጋጣሚዎች አንዱ ነው፡፡
ስለ እሱ የአካዳሚክ ድንቅ ሰውነት ማንም የሚያወራው በመሆኑ ብዙ ማለት አልፈልግም ።ይልቅስ በሚዲያዎች ላይ ያለው አስተዋጽኦ ብዙም የሚታወቅ አይመስለኝም።ይህም የሆነው እሱ በሚዲያዎች ላይ የመቅረብ ፍላጎት ስለሌለው ነው።ስላደረገውም፣ ስላስደረገውም መልካም ውለታ እንዲነገርና እንዲጻፍ አይፈልግም።ጎልተውና ሰምረው በወጡ በርካታ የሥነጥበብ የሚዲያ ሥራዎች ጀርባ የቴዲ ተማሪ የሆኑ ጋዜጠኞች እንዳሉ ጥርጥር የለውም።በየሚዲያው ያሉ እሱ ያስተማራቸው ጋዜጠኞች በወሳኝ ሰዓት አብዝተው ይፈልጉታል።በተለይ አምኖ በገባበት እርዳታ ከባለቤቱ በላይ እንቅልፍ ሲያጣ ማየት ያስገርማል።የሚደረግለት ምስጋና እና ቃል እስኪያጣ ድረስ በምክርና ዕውቀት ያጠግበዋል።
በ2005 በሬድዮ ፋና በተዘጋጀው ታላቅ ሀገር አቀፍ የግጥም ውድድር የቴዲ ሚና ትልቅ ነበር።›› በማለት ዘካርያስ ምልከታውን አስቀምጦ ነበር፡፡
የሚድያ ሰው እና በለባዊ ኢንተርናሽናል ት/ቤት የሀገረ በቀል እውቀት ዲፓርትመንት መስራች የሆነው የአሻም ሬድዮ ፕሮግራም አዘጋጅና አቅራቢ ሚካኤል አለማየሁ/ የእናኑ ልጅ/ ቴዎድሮስን መምህሩ ተመራማሪውና ተጋዳሊው ቴዎድሮስ ገብሬ ሲል ይገልጸዋል፡፡ ሚካኤል ቴዲን ለመግለጽ ቃላት ቢያጥረውም እኔ ላይ በጎ ተጽእኖ በመፍጠሩ ላመሰግነው ወዳለሁ ይላል፡፡ ሚኪ ጋር ያሉት ሀገር በቀል አስተሳሰቦች በዋናነት በቴዲ የተቃኙ እና የመምህሩ አሻራ ያረፈባቸው ናቸው፡፡ ሚካኤል ምስክርነቱን ሲሰነዝር፦
‹‹ሥነ ጽሑፍ ጥንተ ተፈጥሮ በይነ - ዲሲፕሊናዊ ነው። እዚህ ተፈጥሮው ላይ መሠረት ያረገ በይነ- ዲስፕሊናዊ የሆነ ንባብ ፣ ትምህርትና ምርምር ይፈልጋል። ከዚህ አንጻር የኢትዮጵያ የሥነ ጽሑፍ ንባብ ትምህርትና ምርምር ከበይነ - ዲስፕሊናዊ አንጻር አሁን ምን ደረጃ ላይ ነው ያለው ብሎ መጠየቅ ያስፈልጋል። ጥያቄውንም መሠረት አድርጎ ጥናት ማረግ የሚመለከተን ሰዎች የቤት ስራ ነው።
የሥነ ጽሑፍ ንባብ ትምህርትና ምርምር በይነ - ዲስፕሊናዊ መሆን እንዳለበት በተጨባጭ ካሳዩ ምሁራን አንዱ እና ዋንኛው ቴዲ ነው ፡፡ በተለየ ሁኔታ ለእኔ እሱ ነው። " በይነ- ዲሲፕሊናዊ የሥነ ጽሑፍ ንባብ " መጻሕፉን ፣ በምርምር መጽሔቶች ላይ ያሳተማቸውን ጽሑፎችና በክፍል ውስጥ የሚሰጣቸው ትምህርቶች ዋንኛ እና አንዱ መሆኑን ይመሰክራሉ።
ቴዎድሮስ ገብሬ የሥነ ጽሑፍ ንባብ ፣ ትምህርትና ምርምር ተጋዳሊ ነው። ከነባሩ የሥነ ጽሑፍ ንባብ ትምህርትና ምርምር ልማድ ያወጣን ተጋዳሊ ነው። ለዚህም " የሃያኛው ክፍለ ዘመን የአማርኛ ሥነ ጽሑፍ ማስተማሪያ መጻሕፍት ሁኔታ ፤ ታሪካዊ - ሒሳዊ ቅኝት " የሚለውን ጥናቱን ዋቢ አረጋለሁ።
ከሥነ ጽሑፍ የበይነ -ዲሲፕሊናዊ ባህር ጋር ያገናኘ ድልድይ ነው - ቴዎድሮስ ገብሬ።›› በማለት ሚካኤል ሀሳቡን ይገልጻል፡፡
በኮሌጁ ለ4 ዓመታት አብሮት ያሳለፈው አብነት መንግሥቴ ቴዎድሮስ ኮተቤ የገባው እንደ ብዙዎቹ ተማሪዎች ሊማር ብቻ አልነበረም ይላል፡፡ ይልቁንስ ትልልቅ የሥነ-ጽሁፍ ድርሰቶችንና ኀልዮቶችን አንብቦ ስለነበር ብዙ ነገሮች ላይ መምሕራኑን መሞገቱን ያስታውሳል፡፡
“በኮሌጅ እያለን ባሉን እረፍት ጊዜያት አንዳንዴም ትምህርቱን እያስተጓጎለ ወደ ወመዘክር ቤተ-መጽሀፍት በመሔድ ከሚማረው ትምህርት ጋር ተያያዥነት በሌለው ንባብ ይጠመድ እንደነበር ትዝ ይለኛል፡፡በዚህም ወቅት ንባቡ ታላላቅ የዓለም ሥነ-ጽሁፍ ስራዎችን፣ የፍልስፍ፣ የሥነ-ልቦና የካልቸራል አንትሮፖሎጅ እና ሌሎች የሒውማኒቲ እውቀት ዘርፎችን በወጉ አጥንቷል፡፡”
በይነ-ዲስፕሊናው የሥነ-ጽሁፍ አተያዩን በወጉ የገፈበት ከዚያ ወዲያ ሳይሆን አይቀርም፡፡ የያኔው ቴዎድሮስ የአማርኛ ሥነ-ጽሁፍን በስነ-ልቡና ንድፈ ሐሳቦች በጥልቀት ለመመርመር ብዙ ጥሯል፡፡ ፍልስፍናዊ ሀሳቦችን እየተዋሰ ኢትዮጵያዊ ድርሰቶችን ለማጠየቅ የሔደበትም መንገድ ለእኩዮቹ ብቻ ሳይሆን ለመምህራኑም እንግዳ ሆኗል፡፡ቴዎድሮስ ወዲህ በክፍል ውስጥ ውጤቱ ተወዳጅና መነጋገሪያ መሆኑ ባይካድም የእርሱ ቀልብ ግን ከወመዘክር ለመራቅ አልተቻለውም፡፡ ከኮተቤ ብሔራዊ እየተጓዘ ለልጅነት ቤቱ ስብሃት ማድረሱን ቀጠለ፡፡ ለልብስና ጫማ የሚሠጠውን ገንዘብ መጽሐፍ እየገዛበት የንባብ አምሮቱን ሊቆርጥ ከጊዜው ጋር ነጎደ፡፡
ይኼኛው ቴዎድሮስ ተማሪና የተመራማሪነት አምሮት ያለው ብቻ አልነበረም፡፡ ይልቁኑስ ያደረ የደራሲነት ፍላጎቱም አብሮት ነበር፡፡ ግጥሞችንና አጭር ልብወለዶችን እየፃፈ ለጓደኞቹ ማስነበቡን ቀጠለ፡፡ ፀሐፌ-ተውኔትነቱም የቀደመ እንጂ አዲስ አልነበረም፡፡ በዚያ የአፍላነቱ ዘመን የቀድሞው የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ከሰተብርሃን አድማሱን(ዶ/ር) ጨምሮ ሌሎች እኩዮቹ የተወኑባቸውን ቴአትሮች ጽፏል፡፡ ይህ ግን የራስ ፈለግን ለማሰስ የተሄደ እርቀት እንጂ መድረኮችን እየፈለጉ ከዝና ማማ ላይ ለመድረስ መታገል አልነበረም፡፡ ለዚህም ነው ቴዎድሮስ የአፍላነት ዘመን ድርሰቱ ተወዶ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ለመድረክ ይብቃ ሲባል አልፈልግም የሚል አስገራሚ መልስ የሠጠው፡፡
እንዲህ ያለው የቴዎድሮስ በራስ ዛቢያ እየተንቀሳቀሱ ለቀሪው ዓለም ጀርባን መስጠት ብርቅ ጠባዩ አይደለም፡፡ በአፍላነቱ ዘመን ስብሃት ገብረእግዚአብሔርን እንደሚወደው የሚያውቁ ወዳጆቹ ስብሀትን አግኝተናል እናስተዋውቅህ ቢሉት ”እኔ ጉዳዬ ከድርሰቱ እንጂ ከእርሱ አይደለም“ ሲል እምቢታውን ገልጿል፡፡ በጎልማሳነቱ ዘመንም በዓለም የሥነ-ጽሁፍ ጥናት ውስጥ ስሟ የገነነው ደራሲና ተመራማሪ ሜሪ ሮዛሪዎ በምርምር ሥራው ተደማ፤አዲስ አበባ በመጣች ወቅት ልታገኘው ብትፈልግ ባለቤቴን ልልካት እችላለሁ እኔ ግን አይመቸኝም ሲል መልሷል፡፡
የዚህ አይገመቴ ጠባዩ ቁንጮ ግን ፓስፖርት ኑሮት አለማወቁ ነው፡፡ ለምን? ፓስፖርት ከያዘ በወዳጅ ዘመድ ግፊት ለሚያማልሉት የውጭ አገር ጥያቄዎች ምላሽ እንዲሰጥ ሊገደድ ነዋ! ፍርሃቱም እሱ ነው፡፡ቴዎድሮስ ከኢትዮጵያ መውጣት አይፈልግም፡፡ እሱን ደግሞ በጋንቤላ መምህራንና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ መምህርነቱ ወቅት እንግሊዝ አገር የመማር ዕድል ይመቻችልህ ሲባል አልፈልግም ብሎ አረጋግጧል፡፡
ብርሃኑ ደቦጭ የረጅም ዓመታት ጓደኛውን ሲያስብ አንዱ የሚደንቀው ነገርም ይኼ ነው፡፡ ከአገሩ ሳይወጣ ፣የታላላቆቹን የምዕራቡ ዓለም ዩኒቨርስቲዎች ደጃፍ ሳያረግጥ በጥልቅ ንባቦቹ ብቻ ዘመኑን ዋጅቷል፡፡ በእርግጥም ቴዎድሮስ በአገሬው የሥነ-ጽሑፍ ትምህርት ልማድ ውስጥ ብቻ ለማለፍ ሞክሮ ቢሆን ዛሬ የምናወራለት እርሱነቱ መፈጠሩ ያጠያይቃል፡፡ የአብነት ገለጻ ይበልጥ ግዙፍ ይነሳል፡፡
“በንባብ ውስጥ ራሱን ያገኘ፤ራሱን የሰራ እንጂ የቅድመ ምረቃም ሆነ የድህረ ምረቃ ትምህርት ተሞክሮው በእውቀቱና በአስተሳሰቡ ላይ የጎላ ተጽዕኖ የፈጠሩበት ሰው አይመስለኝም፡፡ ገና የመጀመሪያ ዓመት የኮሌጅ ተማሪዎች ሳለን ከሚቶሎጅ፣ከፍልስፍና፣ከሥነ-ልቡና፣ከአንትሮፖሎጂ እንደውም ለሥነ-ጽሁፍ ተዛምዶ ይኖራቸዋል ተብሎ ከማይታሰቡ እንደ ፊዚክስ ካሉ ዲስፒሊኖች ቴዎሪ ወስዶ ለሥነ-ጽሁፍ ማናበቢያና መተንተኛ ይጠቀም ነበር፡፡ ለምሣሌ የሠይፉ መታፈሪያን ግጥም በquantum Physics ንድፈ ሀሳብ ለመተንተን ሞክሯል፡፡ እነዚህ ሁኔታዎች ቴዎድሮስ ቀድሞም ቢሆን የ literary interpretation እና የ literary philosophy አተያይ እንደነበረው እማኝ ይሆናሉ፡፡ በአሁን ዘመን ሥራዎቹ ላይ ላቅ ይል ካልሆነ፡፡ …ገና የአንደኛና የሁለተኛ ዓመት ተማሪዎች እያለን የሚያነሳቸው ሥነ-ጽሑፋዊ ጉዳዮች ከበርካታ ዓመታት በኋላ በትላልቅ የሥነ-ጽሑፍ ጆርናሎች ላይ በዐቢይ ርዕሰነት ሲወሱ ማየቴም ይህንን ድምዳሜዬን ይበልጥ ያጠናክረዋል፡፡”
የቴዎድሮስ የኮሌጅ ቆይታ ከፍ ተብሎ እንደተጠቀሰው በጥልቅ ንባብ ብቻ የታጀበ አይደለም፡፡ በትምህር ቤት በሚሰጡት የቤት ሥራዎች ላይ ያቀርባቸው የነበሩ ጽሁፎቹ ዛሬም ኪናዊ ኅሩይ ናቸው፡፡ማስረጃችን የሦስተኛ ዓመት ተማሪ እያለ ያቀረበው ”ተርም ፔፐር“ ነው፡፡ ይህ ጥናት በአዳም ረታ “ማኅሌት” መድብል ውስጥ ከተካተቱ አጫጭር ታሪኮች አንዱ የሆነውን “ኤልዛቤል” በመውሰድ ከዘመናዊ አተራረክ አንፃር ቃኝቷል፡፡
ጽሁፉ በጊዜው ለመምህሩ ብቻ የቀረበ ቢሆንም ኋላ ላይ ግን ትኩረትን ሳበ፡፡አስተውሎቱና ኀሰሳው ከፍ ያለ ነበረና በ1992 ዓ.ም የኢትዮጵያ ሥነ-ጽሁፍ ጥናት ሊቃውንት በጋር ባሳተሙት የምርምር መጽሔት ላይ ተካተተ ፡፡
ቴዎድሮስ የኮተቤ ተማሪነቱ ቆይታው ከፍ ብለን የጠቀስነውን ዓይነት ዘመን ተሻጋሪ ሥነ-ጽሁፋዊ ልህቀት እንዳለው ቢያረጋግጥም እርሱ ግን የሚረካ አልነበረም፡፡ ወደ መጀመሪያ ድግሪ ማሙያ ጽሁፉ እንለፍ ፡፡ ይህ ጥናቱ በዳኛቸው ወርቁ “አደፍርስ” ልብ ወለድ “እንደወረደ” (stream of consciousness) ሥነ-ጽሑፋዊ አንፃር ላይ ያተኮረ ነው፡፡ እዚህ ላይ በሥራውና በራሱ ላይ የነበረውን መተማመን የሚያሳይ አንድ ነገር እንጥቀስ፡፡ ቴዎድሮስ ጥናቱን ካጠናቀቀ በኋላ ክፍለ-ትምህርቱ ፈታኝ መምህራንን በሚመድብ ሰዓት ጥያቄ አነሳ፡፡ የእኔን መመረቂያ ጽሁፍ የሚፈትኑ ሰዎች ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ መሆን አለባቸው አለ፡፡
ሙግቱ ከውጤት ይልቅ ለማወቅ ያለውን ጉጉት ያሳያል፡፡ ቴዎድሮስ በሚያውቁትና በሚያውቃቸው መምህራን ቢፈተን ከፍተኛ ውጤት እንደሚያገኝ እርግጥ ነበር፡፡ እርሱ ግን ከውጤቱ በላይ ያስተማሩት መምህራን ደጋግመው የሚያነሷቸውን ትላልቅ የሥነ-ጽሁፍ ሰዎች በእዚያ ዕድሜው ለመሞገት ጓጓ፡፡ ይሁንና ጥያቄው ተቀባይነት አላገኘም፡፡ በመሆኑም ብዙዎች እንደጠበቁት የኮተቤ ቆይታውን ከፍተኛ ውጤት በማምጣት ደመደመ፡፡
ከዚህ በኋላ ያለ ሕይወቱ ወደ ጋምቤላ ይወስደናል፡፡ የጋምቤላ መምህራንና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ መምህር ሆነ፡፡የወዳጆቹ ስጋት አንጋፋ መምህራን ያሉት የኮተቤ መምህራን ኮሌጅ የጠበበው ቴዎድሮስ ገብሬ በጋምቤላ የሚኖረው ቆይታ እንዴት ይሆናል? የሚለው ነበር፡፡ እርሱ ግን ብዙም ግድ አልሰጠውም፡፡ ከዓለሙ እንደራቀ ባሕታዊ በመጽሐፍት ብቻ ተከቦ በዚያች የበርሃ ገነት ኑሮን ለመደ፡፡ የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንሲ ኢንስቲትዩት ምክትል ዳይሬክተርና የቀድሞው የቴዎድሮስ ገብሬ ተማሪ ወንድወሰን አንዱአለም ወቅቱን እንዲህ ያስታውሰዋል፡፡
10 popular self-help books
1. "Atomic Habits" by James Clear
2. "The Four Agreements" by Don Miguel Ruiz
3. "The Subtle Art of Not Giving a F*ck" by Mark Manson
4. "You Are a Badass" by Jen Sincero
5. "Mindset: The New Psychology of Success" by Carol S. Dweck
6. "The Power of Now" by Eckhart Tolle
7. "Daring Greatly" by Brené Brown
8. "Grit: The Power of Passion and Perseverance" by Angela Duckworth
9. "The 5 Second Rule" by Mel Robbins
10. "How to Win Friends and Influence People" by Dale Carnegie
Join us @weperspective
" እነሆ ከዚህ ያማረ ስፍራ ሆኜ ወደ ጥሞና ዓለም ነጎድኩኝ :: ከኔዋ ሴት ርቄ በውጥን ውስጥ ወደራሴ የትውስታ ማሕደር ተጓዝኩኝ :: ከዕድሜዬ ማለዳ ጀምሮ ጥያቄዎች ነበሩኝ :: ግን ለምን እናቴ ጠላቺኝ ?! ለምንስ በኔ ላይ ፈርዳ በሐሰት መሰከረች ?! በእናቴ ዕዳ ለምንድናው የምቀጣው ብዬ ስባዝን ከረምኩኝ ::
የኋላ ኋላ ድህነት ክፉ መሆኑን ተረዳሁ :: ድሃ ለመኖር ሲል ክብሩንና ስሙን አውልቆ ሊጥል ይችላል :: በተለይ አግኝቶ ማጣት ደስታን ያመሻል :: እናቴ ላይም አልፈርድ ዘንድ ራሴን ገሰጽኩኝ :: አብሬ ያልኖርኩትንና ፈተናውን ያልተጋራሁት ሰው ላይ እፈርድ ዘንድ እኔ ማነኝ ? ዛሬ በሁለት እግሬ ስቆም ለኔ ከዳዴ ጀምሬ ቀና ለማለቴ ጎንበስ ያሉ ሰዎች መኖራቸውን አልረሳሁም :: "
★★★
አርምሞ
በኤልያስ ገብሩ አዕምሮ
አስራስድስተኛ ዕትም
ገጽ / 239
ጃዕፈር መጻሕፍት
መጽሐፉ ገበያ ላይ ይገኛል !!
ትዘታ ዘ አራዳ :- በኢትዮጵያ ተማሪዎች ትግል ደማቅ ስም ስለነበረው ጥላሁን ግዛው - በተፈሪ ዓለሙ ታህሳስ 20፣2016
https://youtu.be/o1Pes2fAQPY?si=ypqDzlqIRpLnYEil
#Ethiopia #ShegerFM #Tizitazearada #TillahunGizaw
ተማጽኖ
(በእውቀቱ ስዩም)
አቤቱ
የጠፈር ባለቤቱ
በየብስ ነህ፥ በባህር፥ በምድር ነህ በሰማይ?
በቅጡ ለማናውቅህ ፥ በድንግዝግዝ ለምናይ
አቤቱ የፍጥረት አባት
ከሰማኸኝ ምናልባት
ኮረብታውን ሜዳ አድርገው ፤ ኮረኮንቹን አለስልሰው
የፎይታየን አድራሻ፥ ርቀቱን ቀንሰው
አልልህም!
ጽናት ስጠኝ ፤ ብርቱ አድርገኝ! በየርምጃው እንዳይደክመኝ
ከቀንበሮች ሁሉ መርጠህ፥ ምችለውን አሸክመኝ
አቤቱ! የጠፈሮች ሁሉ መስራች
አፈራርቀህ የምትሰጥ፥ መርዶና የምስራች !
ተወስነህ የማትገኝ ፤ በጊዜና በቦታ
ወሰን የሌለህ ዝምታ
እኔ ልጅህ-ሲመቸኝ ፤ ሲመቸኝ አማኝ
ባይመችህም ስማኝ
ካደፈጠው እዳ ሁሉ፥ በየበስ፥ ባየር በቀላይ
ከአውሎ ነፋስም በላይ
ከመሬት መራድም ይልቅ
ሰው ነው ሰውን ሚያሳቅቅ
ሰው ነው የሰው አደጋ
ደግሞ በሌላ ገጹ፥ ሰው ነው ለሰው ልጅ ጸጋ
ከስጦታው አካፍለኝ ፥ ካደጋው አስመልጠኝ
አልሳሳት አልልህም፥ የሚታረም ስህተት ስጠኝ !
መጽሐፈ ጨዋታ
(ምዕራፍ ሁለት)
ርዕስ፦የኔ ብጤ ሰማይ
ዘውግ፦ ግጥም
ገጣሚ፦መስፍን ወንድወሰን
ሂስ አቅራቢ
ሃያሲና ደራሲ ደረጀ በላይነህ
አዘጋጅና አቅራቢ፦
ሰሎሞን ንጉስ
እሁድ ምሽት 12፡00
ማክሰኞ ቀን 7፡30
በአሻም ቲቪ ይቀርባል።
ሸገር ካፌን አላደንቅም ! ሃይሌ ገብረስላሴ ጎበዝ ሯጭ ነው ማለት ማሳነስ ነው። ሃይሌ ጎበዝ ሯጭ አይደለም ፤ ሩጫ ራሱን ነው ። ሸገርን ማድነቅ ማሳነስ ነወ።
ሸገር ብዙ ሸጋ ፕሮግራሞች አሉት—የሸገር ጨዋታ፣ ሸገር ካፌ፣ ሸገር ሸልፍ፣ ሸገር መቆያ፣ የሸገር ወሬ፣ የአዘቦት ተረክ፣ ለዛ፣ ከቤት እስከ ከተማ ወዘተ
ሸገር ኬክ ቢሆን የሸገር ጨዋታ ክሬሙ ነው። ላለፉት 23 አመታት መአዝዬ ደራሲዎችን፣ ዲፕሎማቶችን፣ ፖለቲከኞችን፣ ተዋናዮችን፣ የታሪክ ተመራማሪዎችን፣ ባለሃብቶችን፣ ሙዚቀኞችን፣ ምሁራንን፣ የህግ ባለሙያዎችን፣ ዶክተሮችን፣ ፕሮፌሰሮችን ወዘተ ቃለመጠይቅ አድርጋለች።
ታዲያ ቃለመጠይቅ ብርቅ ነው ወይ? ሊባል ይችላል መልሱ አዎ ነው። የመአዚ ጨዋታ ለዛ አለው፣ ደረቅ ጥያቄና መልስ አይደለም፤ flow አለው። እንደሚፈስ ወንዝ ነው።
እጅግ አድርጌ የማስታውሳቸው፦
ተስፋዬ ሳህሉ—በልጅነታችን ተረታቸውን ስንሰማ አድገናል። ከመአዚ ጋር ሲያወሩ የዋህ ነፍሳቸው፤ ጨዋታ አዋቂነታቸው፣ ግልጽነታቸው ይታያል።
ፕሮፈሰር መስፍን ወልደማርያም —ለብዙ አመታት በኢትዮጵያ ፖለቲካ በታዛቢነትም፣ በተሳታፊነትም ኖረዋል። መአዚ ፒያሳ ድረስ ቤታቸው ሄዳ ነው ያወራቻቸው። በአይነህሊናዬ ሳሎናቸው ውስጥ ሲጋራ እያጨሱ ሲያወሩ ነው የሳልኩት። የደነቀኝ ዲሲፕሊንድ የሆነ፣ የማይነቃነቅ ስብእና ነው ያላቸው። የቁስና የገንዘብ ሰው አይደሉም።
በሃይሉ ገብረመድህን—የበሃይሉ ጨዋታ ለ16 ሳምንት ነው የዘለቀው። የብዙዎችን ልጅነት፣ አስተዳደግ ስለሚያወሳ ነው ለረዥም ሰአት በሃይሉ እንዲያወራ የፈቀድኩት ብላለች መአዚ። እነዛ 16 ሳምንቶች የአንድ ሰው ታሪክ አይደሉም። የአንድ ትውልድ ታሪክ ናቸው። በዚያ ላይ ወረ—ሻሼ ነው። የወንዜ የሻሸመኔ ልጅ ነው።
ነቢይ መኮንን—ነቢይ ጋዜጣ ሲያዘጋጅ፣ ሲተረጉም፣ ሲገጥም፣ ሲያወራ ሁሉም ይዋጣለታል። ጨዋታ አዋቂ ነው። በ70ዎቹ ደርግ እንዴት አስሮ፣ እንደገረፈው ሲያወራ እየሳቀ ነው።
ፍስሐ አጥላው—በሰሜን አሜሪካ የሚኖሩ ትልቅ ኢንጂነር ናቸው። Atari, HP ወዘተ ሰርተዋል። አሁን በግእዝ/ኢትዮፒክ ፊደላት የምጽፍላችሁ በእርሳቸው የተነሳ ነው። በእርግጥ አሁን ብዙ መተግበሪያዎች አሉ። ነገር ግን የመጀመሪያውን የአማርኛ የኮምፒውተር መጻፊያ የሰሩት ፍስሐ ናቸው። የUNICODE ብቸኛ አፍሪካዊ አባል ናቸው። ከመአዛ ጋር ለ4 ሳምንት የተላለፈ ማለፊያ ቆይታ አድርገዋል።
አውግቸው ከበደ/ኅሩይ ሚናስ—የአእምሮ ህመም ባይፈታተናቸው ከኢትዮጵያ ታላላቅ ደራሲያን አንዱ ይሆኑ ነበር። በፈጠራም (እብዱ ቢጩ፣ አስመዝግቤያለሁ) በትርጉምም (የአንገት ጌጡ) የተዋጣለቸው ስራዎች ናቸው። መአዚ እያባበለች ብዙ አስወርታዋለች።
አሊ ቢራ—አቤት አነጋገር፣ አቤት ጨዋታ። ንግግሩ እንደ ሙዚቃው ይጣፍጣል። ቃለመጠይቁ የተደረገው በጣም በተጣበበ ግዜ እና በማይመች ሁኔታ ቢሆንም በጣም ሸጋ ቆይታ ነበር። አሊ ቀኑን ሙሉ ሲያወራ ቢውል፣ ሳይሰለቸኝ የምሰማው ይመስለኛል።
አሃዱ ውብሸት— የጋሽ ውብሸት ወርቃአለማሁ ልጅ ነው። አሜሪካ ውስጥ በትልቅ ዩኒቨርስቲ፣ ሃዋርድ መሰለኝ የስነጽሁፍ ፕሮፌሰር ነው። ከመአዚ ጋር የተጫወቱት ለአንድ ሳምንት ቢሆንም፣ በብዛት ያወሩት ስለ ስነጽሑፍ በመሆኑ አልረሳሁትም።
ፕሮፌሰር አንድሪያስ እሸቴ— ረጋ ብለው ነው የሚያወሩት። አንዴ ምሁር ማለት ለእውነት የቀረበ ትክክለኛ ሃሳብ፣ በሙከራ ሳይሆን ቁጭ ብለው በማሰብና በማሰላሰል የሚደርሱበት ናቸው የሚል ነገር አነበብኩ። ከዚያ ወዲህ ምሁር ሲባል መጀመሪያ ትዝ የሚሉኝ ፕሮፌሰር አንድሪያስ ናቸው። በእርግጥ በፖለቲካ አድርባይነት ይታማሉ። ወያኔ ስልጣን ሲይዝ ገና ለገና ሹመት ይሰጠኛል ብለው፣ ጨርቄን ማቄን ሳይሉ ከአሜሪካ መጡ እያሉ ያሟቸዋል። መሌም አላሳፈራቸውም የአዲሳባ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንትነት ሰጣቸው። ከአንድሪየስ ከሃሳባቸው ሌለ ትዝ የሚለኝ ሲያወሩ ድምጻቸው፣ ሲጋራ የዘጋው ጉሮሮዋቸው ነው።
አሰፋ ጫቦ — ከነብይ መኮንን ጋር ወዳጅ ነበሩ። የሚኖሩትም አሜሪካ ነበር። መአዛ አሜሪካ በሄደችበት ቃለመጠይቅ ልታደርግላቸው የቻለችው ለሁለቱም ወዳጅ በሆነው ነብይ መኮንን አማካኝነት ነው። አንደበታቸውም፣ ብእራቸውም እኩል ይታዘዙላቸዋል፤ እኩል ይጣፍጥላቸዋል። በዚየ ላይ ደፋር፣ ቅን የጋሞ መንፈስ ናቸው።
አብነት አጎነፍር—ሌላ ፕሮግራም ላይ ቃለመጠይቅ ሲሰጥ ሰምቼ አላውቅም። የድምጹን ቅላጼ እወድለታለሁ። ብዙ የሚሰራ እንጂ ብዙ የሚያወራ አይደለም።
ለማንኛውም ሁሉንም የሸገር የጨዋታ እንግዳ ፕሮግራሞች ከዩትዩብ ላይ አውርዳችሁ፣ በሚመቻችሁ ቦታና ግዜ ማዳመጥ ትችላላችሁ። ፋይሎቹ ወደ 600+ ይጠጋሉ። የፋይል ሳይዙ ወደ 30 ጊጋባይት ይጠጋል።
በነገራችን ላይ የመጽሀፍት ትረካ የአዘቦት ተረክ ስብስቦችን ዩትዩብ ላይ ማግኘት አልቻልኩም። እንዴት እንደሚገኝ የሚያውቅ አለ?
* ቴዎድሮስ ሸዋንግዛው እንዳለው ::
ውድ የመጻሕፍት አፍቃሪዎች!
በድርሰት እና በኢትዮጽያውያን ደራስያን ላይ የማቀርባቸውን ልዩ ልዩ ፕሮግራሞች አማራጭ ማሰራጫ ይሆንልኝ ዘንድ የከፈትኩትን የዩትዩብ ቻናል ትጎበኙልኝ ዘንድ (በተለይ ሰብስክራይብ በማድረግ) በክብር ጋብዣችኋለሁ!
endalegetamultimedia?si=TLc9gsFj6vqjr6r8" rel="nofollow">https://youtube.com/@endalegetamultimedia?si=TLc9gsFj6vqjr6r8
ኑ!
በቻናሉ አማካይነት ቤተሰብ እንሁን። አገራችንንና ማንነታችንን አጮልቀን እንይበት! እንወዳጅበት!! እንማከርበትም!!!
(እንዳለጌታ ከበደ)
የገንዘብ ፍሰት
በሮበርት ኪዮሳኪ
መጽሐፉ ትርጉም ነው ::
ሙሉ መጽሐፉ ነው የተተረከው ::
https://youtu.be/aKvIkzGX8yE?si=vsyKdgtFK8gK18og
Join us @weperspective
ሰው በሰኖትራክ ብቻ አይኖርም!
(በእውቀቱ ስዩም)
አንዴ አድምጡኝማ !
በቀደም የሆነ ሚድያ ላይ አንዲት ሴት ቀርባ ስለ ውሻዋ ታወጋለች፤ ውሻየ እንደዚህ አይነት ምግብ ትወዳለች፤ ውሻየ ተጎድታብኝ ታማብኝ አይነት ነገር እያወራች ፤ ታለቅሳለች ፤ አንዱ ከንግግሯ ቲንሽ ቆርሶ ቲክታክ ላይ ወዝፎታል፤ ከቪድዮው ግርጌ ያለውን አስተያየት መስጫው ቃኘት ሳረገው ሴትዮይቱን አላስተረፏትም፤ እንዳትሸጥ እንዳትለወጥ ብቻ ሳይሆን እንዳትከራይ አድርገው ዘልፈዋታል፤ “ብንሄድ ይሻላል “ ከሚለው የቸከ የመነቸከ መፈክር ጀምሮ፤ ጠገራ ስድቦች እና ኦሪጅናል ርግማኖች ወርደውባታል፤
“ ውሻ የሌለው ሰው ፍቅርን እና መፈቀርን አያውቅም “ ያለው ማን ነበር? ከውሻ ጋር ከኖሩ ፈላስፎች አንዱ-ዲዮጋን ወይም ሾፐናወር ሊሆን ይችላል፤ ብዙ የከተማችን ሰው ውሻ ማሳደግ የሚችልበት ሁኔታ የለውም፤ ስለዚህ የነ ቡቺን ፍቅር ጣእም አያውቀውም፤ የቤት እንስሳ የሚንከባከቡ ሰዎችን እንደ ቀበጥ እንጂ እንደ ጥሩ ሰው ለማየት ይችግረዋል፤
ውሻየን እንቁላል ጥብስ አበላታለሁ’ የሚል ነገር ስትሰማ የምትናደድ ሰው ችግርህ ምንድነው? ሲጀመር አሳዳሪው ከቻለ እንኳን እንቁላል እቁብ ቢያበላው ምን አገባህ? ሰዎች ለሚያሳድጉት ውሻ ድመት ወዘተ ያላቸው ፍቅር ከወለዱት ልጅ ያነሰ እንዳልሆነ ማወቅ ያን ያህል ከባድ ነው?
በቀደም የአህያ ስጋ ለገበያ መቅረቡን ተከትሎ የተወዘተረ ቀልድ ነበር፤ የቀልዱ ጭብጥ እንዳመትበአል ዘፈን አይቀየርም፤ የሆነ ሰው የአህያ ስጋ በልቶ ሲወጣ አላፊ አግዳሚውን መራገጥ ይጀምራል፤
ባለ አምስት ኮከብ ጮሌ “ስማርት” ነኝ ብለህ ታስባለህ፤ ያም ሆኖ አህያን ስታስብ፥ ከስንት አንዴ እጅግ ሲመራት የምትሰንዘረው ርግጫዋ ነው ትዝ የሚልህ? ሌላው ቢቀር አህያ ባይኖር ኢትዮጵያ ውስጥ ገበያ ይኖራል? በነገራችን ላይ ፥ “ከአህያ ጋራ የዋለች ላም ፈስ ተምራ መጣች “ የሚል ተረት ስንቀባበል የኖርን ደንቃድንቅሰዎች ነን እኮ! በውኑ ከአህያ ችሎታዎች ውስጥ ዋናው መፍሳት ነውን ? ደሞስ አህያ ብትፈሳ ፥ ደልቷት ቁንጣን እንዲቀላት አይደለም፤ የጭንቅ መወጫ ነው አባ! እስቲ በአህያ ኮቴ ውስጥ ቆመህ ነገሩን አስበው! አገር ሰላም ብለህ በቆምክበት ቦታ ፥ የሆኑ ሰዎች መቶ ኪሎ የበቾ ጤፍ ትከሻህ ላይ ቢጥሉብህ ፥ እንኳን በቂምህ በእንብርትህ አትፈሳም?!
ሰው በሲኖትራክ ብቻ አይኖርም! የአንስሳትን እገዛም ይፈልጋል፤ ግን የሚያገለግሉንን እንስሳት ከመበደል እና ከመዋረድ ይልቅ ለወሮታቸው የሚመጥን ርህራሄ ማሳየት የመንፈስ ስልጣኔ ነው ብየ አምናለሁ፤
የቴዎድሮስ አመጽ ግብታዊ አይደለም፡፡ ትርጉም አለው፤ ታሪክ አለው፡፡ ፋይዳው የትናንትን ሕመም ማወቅ የዛሬን ሽረት መመኘት ነው፡፡ “ሌቱም አይነጋልኝ” ለዘመናት ፀያፍ የሆነን ነገር በአደባባይ የሰበከ ድርሳን ነበር፡፡ በቴዎድሮስ “ቤተ-ሙከራ” ውስጥ ሲያልፍ ግን ሕመማችን መሆኑ ተረጋገጠ፡፡ ውቤ በርሃ ለለውጥ ያጎፈሩ ኢትዮጵያዊያን ስፍራ ነው፡፡ ለአርነት የጋበዝነው ትምህርት ከራሳቸው ያኳረፋቸው፤ ዝመና ያልነው ነገር መቀበሪያ የሆናቸው-የአብዮቱ ትውልድ አምሳዮች፡፡ ኦ! ስብሃት ለአብ ገብረእግዚአብሔር በማወቅም ይሁን ባለማወቅ ስናነውርህ ኑረናልና ይቅርታህን እንለምናለን ማለት ይኖርብን ይሆን ?
“Myth and Sexuality: A Mythopoeic Reading of Le’tum Aynegallign” በነባሩ የኢትዮጵያ ሥነ-ጽሁፍ ጥናት ላይ እንዲህ ያለ “አብዮታዊ” እርምጃ ሲወስድ በውጩ ዓለም ያሉ ምሁራንም ለአገሬው ሥነ-ጽሁፍ ጆሮ መስጠታቸው አልቀረም፡፡ ለዚህ ደግሞ ጆናታን ከለር (Jonathan culler) አብነት ይሆናል፡፡ ከለር የዘመናችን የሥነ-ጽሁፍ ጥናት መሠፈሪያ ተደርገው ከሚቆጠሩ ጥቂት ምሁራን አንዱ ነው፡፡ ይህ ሰው ከፍ ብዬ የጠቀስኩትን የሥነ-ጽሁፍ ምርምር ካነበበ በኋላ ለአጥኝው ያለውን አድናቆት ገልጿል፡፡ በእርግጥ እንዲህ ያለ አጋጣሚ ለቴዎድሮስ ገብሬ አዲስ አይደለም፡፡ ጥቁር አሜሪካዊቷ የቴክሳስ ዩኒቨርስቲ አንጋፋ ምሁርና ታዋቂ ደራሲ ሜሪ ሮዛሪዎም በተጠቀሰው ጥናት መደመሟ አልቀረም፡፡
ቴዎድሮስ አውቆትም ሆነ ሳያውቀው በሚያነሳቸው ጥናቶች ውስጥ እጅጉን ኢትዮጵያዊ ነው፡፡ አንድም በርዕሰ ነገር አንድም ነገሩን ለማጥናት በሚሔድበት መንገድ፡፡ ለያይተን እንመልከተው፡፡ ኢትዮጵያ “ከክበረ-ነገስት” ወዲህ ይህ ነው የሚባል አገሩን የሚያኖር ውል ያሰረች አይመስልም፡፡ የዶናልድ ሌቪንን ቃል ልዋስና የድሕረ አብዮቷ ኢትዮጵያ ከትናንቷ የተፋታች በመንፈስ ግርግር የምትናጥ ከሆነች ውላ አድራለች፡፡ ጉዳዩ የነባሩን ሚት መጤንን አስፈላጊነት፤ የውል ልቡናችንን ቁስል መሻርን ግዴታነት ይጠይቃል፡፡
ቴዎድሮስ ገብሬ በአንድ በኩል ራሱም የአብዮቱ ልጅ ነው (1966 ነው ውልደቱ)፡፡ ሕፃንነቱን ያሳለፈው በደም የተሸመነን የአገር ምንትስ ተከናንቦ ነው፡፡ ይህ እጣ ፋንታ የእርሱ ብቻ ሆኖ አልቀረም፡፡ ዛሬም የልጆቹ ዘመን ያንን ያስንቃል፡፡ በመሆኑም በበርካታ ጥናቶቹ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነትን ዳግም ያጤናል፡፡ ከወል እብደታችን ብንወጣ ብሎ መፈወሻ ፍለጋ ይባዝናል፡፡ በእኔ የንባብ ምልከታ ተከታዮቹ ሰባት ጥናቶች ጉልህ ጠባያቸው ኢትዮጵያዊነት ነው፡፡
1)የነገሮች መቃ(የ)(ለ)ጥ፤የበቀለ አሻራዎች፣ 2) The Representation of Nation and National Identity in Modern Literature, 3) Ethiopia and Ethiopianness in Modern Amharic literature,4) Period,History, and Literary art: Historicizing Amharic Novels,5) Abbay and Nile ;Tsegaye’s Romantic Obsession, 6) የስንበት ቀለማት ድኅረ ቃል 7) ሐቲተ በእነተ እብደት፡ ሥነ-አዕምሯዊ የሥነ-ጽሁፍ ንባብ.
እነዚህ ጥናቶች በቁጥር በርካታ ቢባሉም ያላቸው ሚና ቤተ-ሙከራዊነት ይመስለኛል፡፡ አንድን መድኃኒት ለማግኘት መባዘን፡፡ ቴዎድሮስ ለመጨረሻ ጊዜ ባስነበበን የበቀለ መኮንን ሥዕሎች ቅኝት ላይ መድኃኒት ያለውን እንዲህ ይነግረናል፡፡ “በደም የተሸለመው የወል ትውስታችን በሕመም የተመታው የጋራ ልቡናችን ሽረቱም የሚገኘው በጋራ ከሚከናወን የፈውስ ሥርዓት (collective Catharsis) ነው ብዬ አምናለሁ፡፡”
የቴዎድሮስ ገብሬን ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት አስቀድሜ እንደገለጽኩት በአንድ በኩል ከጥናት ፍሬ ነገሩና የቆሰለን የወል ልቡናን ከማከም ጋር ቢተሳሰርም በሌላ መልኩ ከጥናት ፈለጉ ይቆራኛል፡፡ ይህ ማለት በእርሱ ጥናት ውስጥ ሰፊ ግዛትን ይዘው የሚገኙት አንድምታ፣ ፍካሬ እና ትርጓሜ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስቲያን ውስጥ የተለመዱ ከመሆናቸው ይቀዳል፡፡ ቴዎድሮስ የውጭ ምሁራንን ለሐሳቡ መደገፊያ ይጠቀም ይሆናል እንጂ ምልከታና መራቀቁ ፈጽሞ ኢትዮጵያዊ ነው፡፡
እንደ ቀደሙት የአገሬው ሊቃውንት በምናቡ ሽቅብ ወጥቶ “ለቴክስቱ” ትርጓሜ ይጽፋል፡፡ አንድምታ ያዘጋጃል፡፡ በፍካሬው በጸሐፊውና አንባቢው መኻል ያለን ሥፍራ ይሞላል፡፡ ወጥ ድርሰቱን ወደ ሌላ ደረጃ ያሸጋግራል፡፡ ቴዎድሮስ እንዲህ ያለ ተግባሩን ”continuation of creativity” ይለዋል፡፡ ሚናው አዲስም ጥንታዊም ነው፡፡ አዲስነቱ በዘመናዊው ሥነ-ጽሁፋችን ውስጥ አንድምታና ትርጓሜ ቦታ ከማግኘታቸው ይገናኛል፡፡ ጥንታዊነቱ ልማዱን በቀደመው የቤተ-ክርስቲያን ትምህርት ውስጥ ከመመልከታችን ይመነጫል፡፡ እዚህ ላይ የቴዎድሮስ ሚና “ኒዎ” ደብተራነት (Neo Debtra) መሆኑ ይገለጥልናል፡፡
“ደብተራው“ቴዎድሮስ በአንድምታና ትርጓሜ የማይደርስበት “ዲስፕሊን” የለም፡፡ The Genius Loci of Addis Ababa በተሰኘ ጥናቱ የእኛዋን አድባር በዘመናዊው የሥነ-ምድር ጥናት (Modern Geography) ውስጥ ይበይናታል፡፡”አካል በአማርኛ ሥነ-ጽሁፍ ውስጥ“ በሚል የምርምር ሥራው ከማሕሌት እስከ ስንበት ቀለማት ልብወለዶች የተዘረጋውን የአዳም ረታ ኢ-ንቁ አዕምሮ ግዛቱ ያደርገዋል፡፡ ስፍራ ነጠቃው አንድም የደራሲውን ልቡና ተራራና ሸለቆ መውጣት ይጠይቃል ፡፡አንድም በራስ ልቡና ላይ ሳይሰለቹ መጓዝን ይፈልጋል፡፡
ቴዎድሮስ ሁለቱን ጉዳዮች ካጣመረ በኋላ ሥነ-ጽሁፋዊ መበያዎችን (literary motifs) መሰላሉ አድርጎ ከፍታው ላይ ይወጣል፡፡ድርሰቱን እንደ አዲስ ያዋልዳል፡፡ በዚህ መንገድም ተጨቋኞቹን ገፀ-ባሕርያት ማኅሌትና ዘውዴ መከወኛ(ከ ይጠብቃል) ሳይሆን ከዋኝ ያደርጋቸዋል፡፡ ከአብዮተኛ ያስተካክላቸዋል፡፡ተግባራቸው ወንዳዊውን ሥርዓት እንዴት እንደገነደሰ ያስረዳል፡፡የቀደመው ሥነ-ጥበብ መናድና የወንዳዊውን ዓለም መናጥ ያስከትላል፡፡
የቴዎድሮስ ኢትዮጵያዊ መልክ “ሐቲተ በእንተ እብደት፡ ሥነ-አዕምሯዊ የሥነ-ጽሁፍ ንባብ” በሚል ምርምሩ ላይም ጎልቶ ይታያል፡፡ሙግቱ የኢትዮጵያዊያን የአዕምሮ ሕመም መነሻና መድረሻ ላይ ነው፡፡ እብደት መሠፈሪያው ባሕል ከሆነ ኢትዮጵያዊ የሆነው እብደታችን ኢትዮጵያዊ ሕክምና ያስፈልገዋል ያላል፡፡ስጋቱ ትምህርታችን የአሜሪካን ስነ-አዕምሯዊና ስነ-ልቡናዊ ጉዳዮች በሚተነትኑ መጽሐፍት እየተሰጠ የእኛ ሽረት ከየት ይገኛል የሚል ነው፡፡
የበርሃው ባሕታዊ የጥናት መንገድ ኢትዮጵያዊ ብቻ ሳይሆን ግላዊም ጭምር ነው፡፡ የእርሱ ጥናቶች የራሱ በሆኑ ልዩ ልዩ ጌጦች ያሸበረቁ ናቸው፡፡ አንድም በቋንቋው ልህቀት አንድም በያዘው ኃልዮት፡፡ ከቋንቋ አንፃር የቴዎድሮስ ዐረፍተ ነገሮች እንደ ግጥም ቤት የሚመቱ እንደ ሙዚቃ ”ሪትም“እና ምት ያላቸው ስሜት ቆንጣጭ ናቸው፡፡ በሌላ አነጋገር ጥናቶቹ ራሱ እንደ ሥነ-ጽሁፍ የመቆጠር አቅም ያላቸው በሙዚቃዊ ቋንቋም ለመለካት የቀረቡ መሆናቸውን መገንዘብ ያሻል፡፡ (ምናልባት በተማሪነቱ ዘመን የተውኔትና ልብ ወለድ ደራሲ ስለነበር ከዛ የወረሰው ይሆናል)፡፡ እዚህ ላይ የውጭ ቃላትን ወደ አማርኛ የሚመልስበት መንገድና የግርጌ ማስታወሻ አጠቃቀሙን እናክልበት፡፡
"የመምህርነት ውሃ ልክ" ነው ትለዋለች ተማሪው ባንቺአየሁ አለሙ። ስለ ተከበረው መምህሯም ከታች ያለውን ምስክርነት አስፍራለች፦
"..........በተማሪዎች ቋንቋ "ያለፋል!" ይባላል። በመልፋት ሂደት የእህል ወፍጮ ሲወቀር እህልን እንደሚገረድፍና እንደሚሰልቅ ልክ እንደዛ፤ ሲያስተምር በሚያነሳቸው ነገረ ጉዳዬች ተማሪዎች በንድፈ -ሃሳብ በመታገዝ ጽሑፍን እንድንተነትን ቴዲ ያመላክታል። ለዚህ ዋቢዬ critical reading and text analysis የተባለው course ነው።
እኔ የማንበቢያ መነጽሬ እለዋለሁ። ምክንያቴ ደግሞ በንባብ ወቅት ቴክስቱ የሚጠራቸውን ሃሳቦች ተከትለን ሌላን ጽሑፍ እንድናነብ ቢጋብዘን ቀዳሚውን ቴክስት ሳንረሳ ወደተጠራው ሃሳብ ተጉዘን የዘገንነውን ይዘን በመመለስ ከቀዳሚው ቴክስትጋ እንዴት እንደምናዛምድ በጸጋዬ ገብረመድኀን አባይ ግጥም ማሳያነት አስተምሮኛል። በዚህ ግጥም የተነሱ ጉዳዬች ሲጠሩ "አቤት ባይ" ሃሳቦች የትየለሌ ናቸው።
ከ"አባይ የአማልክት አንቀልባ"ነት <<እስከ ሜዲተራኒያ ጢስ>> ድረስ። ነገር ግን ቴዲ <<በንባብ ሜዲተራኒያ ከደረሳችሁ የቻላችሁትን ዘግናችሁ ወደ አባይ ተመለሱ ከዛ አማምጣችሁ አንዳች ነገርን አዋልዱ እንጂ እዛው አትቅሩ!>> ባይ ነው እንዲህ ነው መምህር።
በመጀመሪያው የተማሪነት ዘመኔ መምህር ቴዎድሮስ አንድ ትምህርት ነው ያስተማረኝ ፤ነገር ግን በርካታ የንባብ መስኮቶችን ጠቁሞኛል። ይህ ነገሩ ስለገዛኝ ለሁለተኛ ጊዜ ወደ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ለመማር እንድሄድ አግዞኛል። ቴዲ ዋርካ ነው። በትምህርት ያስጠልላል። ሲያስተምር አይሰስትም ።በጥሞና ለተከተለው ንባቡ ሩቅ ስለሆነ የመቶ ሜትር ሯጭ መሆንን ይጠይቃል ።አንብቦ ተዘጋጅቶ ለመጣ ቴዲን መከተል አይቸገርም። ከንባብ ለራቀ ተማሪ ግን ...
በሁለተኛው የተማሪነት ዘመኔ መምህር ቴዎድሮስ ለጥናቴ ጽሑፍ አማካሪዬ ነበር። በእያንዳንዱ ምእራፍ የነበረው ማረቅ ግሩም ነበር። ቴዎድሮስ ጥቂት ነገርን ከተማሪው ካገኘ ያንን ማጉላት ያውቅበታል።
ሥነ ጽሑፍን በዘመን መንፈስ ስለመቃኘት፣ የገጸ ባህሪያት የልቡና ውቅር ትንተና፣ ለገድል ስለ መጠራት ወደ ቅጽር ስለመዝለቅና ከቅጽር ስለማምለጥ፣ የሥነጽሑፍ በይነ-ዲስኘሊናዊነት፤ እነዚህ ከቴዲ ትምህርትና የጥናት ጽሑፎቹን በማንበብ የሚገኙ እውቀቶች ናቸው። የቴዲን የመመረቂያ ጽሑፎች ፍለጋ በኮተቤ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ ተማሪ ሳለሁም ሆነ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ላይብረሪ ውስጥ የመመረቂያ የጥናት ወረቀቶቹን ባስስም ላገኛቸው አልቻልኩም። እስከአሁን ድረስ ይቆጩኛል ።ለምን ጠፉ? ቴዲ <<አንድን ቴክስት ስታነቡ ከተነገራችሁ ውስጥ ያልተነገራችሁን ፈልጉ>> ይለን ነበር። የቴዎድሮስ ገብሬ የመጀመሪያና የሁለተኛ ዲግሪ ማሟያ ጥናታዊ ጽሑፎች በላይብረሪዎቹ ውስጥ ያለመኖራቸው ምክንያት ምን ይሆን?
ለኔ ቴዲ እንደ ወዳጅ በ2001 ዓ/ም የመጨረሻ አመት ተማሪ ሆኜ የግጥም መጽሐፍ አሳትሜ ብሔራዊ ትያትር ለምረቃ ኘሮግራም በእንግድነት እንዲገኝ መምህሬን ጋበዝኩት እግዚአብሔር ያክብረው በሰአቱ በስፍራው ተገኝቷል እድለኛ ነሽ ባንቺ አልኳት እራሴን እንዲህ አይነት መምህር ከስንት አንዴ ነው የሚገኘው።"በማለት ባንቺ ምስክርነት ሰጥታለች።
ቴዎድሮስ መገለጥ የሚፈልገው በግላዊ ኑሮው አይደለም፡፡ እንደ አንድ መምህርና ተመራማሪ በሥራዎቹ ተጽዕኖና በተማሪዎቹ ስኬት ደስታውን ይሰፍራል፡፡ ይህም ሆኖ ግን የቅርብ ወዳጆች በቤተሰባዊ ሕይወቱም ስኬታማ እንደሆነ ይመሰክራሉ፡፡ አብነት መንግሥቴ ከቴዎድሮስ ጀርባ ያለችው ሴት የስኬቱ ሁሉ ምንጭ ናት ይላል፡፡ ይህንን ደግሞ ያረጋገጠው ከማንም ሳይሆን ከራሱ ነው፡፡
“ቴዎድሮስ የትዳር አጋሩ እመቤት ወርቁን (ቴዎድሮስ በሚጠራበትና ወዳጅ ዘመድም እርሱን ተከትሎ በሚገለገልበት መጠሪያ ስሟ ኤሟ) ኤሟ በእኔ ሕይወት ውስጥ wild pearl ነች ይላል፡፡ wild pearl” ንጽሕናን ከድንቅነት ከማጣመሩም በላይ የሚገኝበት መንገድም በእድል ብቻ ነው- ከስንት አንዴ፡፡ እዚህ ላይ “በይነ ዲሲፕሊናዊ የሥነ- ጽሁፍ ንባብ” በተሰኘው መጽሐፉ ላይ ባlቤቱን ያመሰገነበትን መንገድና የመጽሐፉን አበርክቶ ለእርሷ ማድረጉን እናክልበት፡፡”
እመቤት የመጀመሪያ ድግሪዋን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በሕግ ትምህርት ሁለቱን የሁለተኛ ዲግሪዎቿን ደግሞ ከአሜሪካን ዩኒቨርስቲዎች በIntellectual Property Law እና በInternational Development ብታጠናም ለሥነ-ጽሁፍ ግን እጅጉን ቅርብ ናት፡፡ እንደውም የቴዎድሮስ የቅርብ ወዳጆች እርሷ የምታነሳቸው ፈታኝ ጥያቄዎች ጥናትና ምርምሮቹ ይበልጡኑ ስል እንዲሆኑ አግዘውታል ይላሉ፡፡
አብነት መንግሥቴም በሀሳቡ ይስማማል፡፡ “ኤሟ የአንድ ሴትና የጥንድ ወንድ ልጆች አባት ያደረገችው የሚወዳት ሚስቱ ብቻ ሳትሆን ቴዎድሮስን ቴዎድሮስ እንዲሆን በማድረግ ሒደት ውስጥ ትልቅ ሚና ያላት ሴት ናት” ይላል፡፡ “የእርሱ ጥናቶች አካዳሚያዊ ዕድገት ለማግኘት አልያም ለገንዘብ ተብለው የሚሰሩ አይደሉም፡፡ ይህ ደግሞ በመምሕር ደሞዝ ቀርቶ በሌላውም ቤተሰብ በኩል ቢሆን ኢኮኖሚያዊ ጫናን እንዲሚፈጥር ጥርጥር የለውም፡፡ ኤሟ ግን የእርሱን ጫና መርጣ ቴዎድሮስን በልኩ እንድናገኘው ያደረገች ብርቱ የትዳር አጋር ናት፡፡”
አስተርዮ ቴዎድሮስ
አንዳንድ ሰው በጊዜ አይለካም፡፡ በስፍራ አይወሰንም፡፡ ይልቁኑስ መንፈስ ሆኖ ሁሉም ጋር ያረባል፡፡ ሥጋ ለብሶ ረቂቅ ይሆናል፡፡ ፍሬድሪክ ሔግል ናፖሊዎን ቦናፓርቲን ባየበት ቅጽበት የተሰማው ስሜት ጥሩ መንደርደሪያ ሳይሆነን አይቀርም፡፡ “የዘመናችንን ነፍስ ፈረስ ላይ ተቀምጦ ሽምጥ ሲጋልብ አየሁት፤ በእርግጥም ሁሉም ነገር አንድ ሰው ላይ ተጠራቅሞ በፈረስ ጀርባ ከአጽናፍ እስከ አጽናፍ ሲገን መመልከት ስሜትን ይነካል፡፡”የሄግል ገለፃ ድንበር አፍራሽ ነው፤የሚታይን በማይታይ፤ የማይታይን በሚታይ የሚተካ፡፡
የቴዎድሮስ ትውልድ አይነተኛ መልኩ አርምሞን መራጭነቱ ነው ፡፡ አብዮት ከሚሉት ምንትስ በኋላ የአደባባይ ሰውነት ቦታ አጥቷል፡፡ቁዘማና መብሰልሰሉ ከራስ ጋር ሆኗል፡፡ ወደ ውስጥ ወደራስ ብቻ መጓዝ ለእልፎች ታድሏል፡፡ ይህ ጉዞ ስውር ዳናዎችን ይተው ካልሆነ የሚታይ የሚዳሰስ አይደለም፡፡ ረቂቅ ነው፡፡ በመልከአ ልቡና ላይ የሚደረግ ነውና አሰሳውም ከፍ ይላል፡፡ ስለ ቴዎድሮስ ገብሬ በጥቂቱ ለማውራት ስንሞክር ሌለኛው አንፃር ይህ ይመስላል፡፡ቴዎድሮስ አንድም ሄግል ናፖሊዎን በገለፀበት መንገድ ይበየናል፡፡ ይህም ሰጋ ለበስ ረቂቅነቱ ነው፡፡ ቴዎድሮስ የሥነ-ጽሑፍ መምህር ብቻ ሳይሆን ራሱም ሥነ-ጽሁፍ ነው፡፡
ሥነ-ጽሁፍደግሞየታሪክ፣የፍልስፍና፣የሚቶሎጅ፣የኪን፣የሥነ-ልቡና...ወዘተ ማደሪያ ነው፡፡ በመሆኑም ቴዎድሮስና ሥነ-ጽሁፍ ድንበር ሽረው ይዋሃዳሉ፡፡ አንዳቸው በአንዳቸው ውስጥ ያድራሉ፡፡ አካላዊነት ይከስማል፡፡ ሰውነት ወደ ሥነ-ጽሁፍ ጽንሰ ሀሳብነት (ገጸ-ባሕሪ መሆንንም ይጨምራል) ያድጋል፡፡ ምንድን ነው? ምን አይደለም? ይከተላል፡፡ ቴዎድሮስ ገብሬ እንደ ሰው ምን ዓይነት ነው? ከሚል ክርክር ተላቆ የሥነ-ጽሁፍ ወሰን የት ድረስ ነው? ጥያቄ ይመጣል፡፡
‹‹…..በዚያ ግቢ ውስጥ ከብዙዎች ጋራ የማይገናኝ፤በእዚያ አስቸጋሪ በረሃ በጣም ፈታኝ በሆነ የአየር ፀባይ ውስጥ ያለ ማቋረጥ የሚያነብ፤በሌላ ትምህርት ክፍል ተማሪዎች ጭምር ስሙ የሁል ጊዜ መነጋገሪያ የሆነ፤ምሽት በሆነና ስለ አስተማሪዎች በተነሳ ቁጥር ስሙ እየተነሳ የረጅም ሰዓት አጀንዳ የሚሆን አንድ ሰው ነበረ … ቴዎድሮስ ገብሬ የሚባል፡፡›› ይላል ወንድወሰን
የጋምቤላው “ባይተዋር” እንደ ሌሎች ባልደረቦቹ የባሮ ወንዝ ነፋሻማ ዓየር አላጓጓውም፡፡ ዛፍ ስር ተቀምጠው ካርታ እንደሚጫወቱት፣ስስ ልብስ ለብሰው በብስክሌት እንደሚቀዝፉት እኩዮቸ ሊሆን አልዳዳውም፡፡ ይልቁኑስ በእዚያ በርሃ ሥነ-ጽሁፍን ሊያጠምቅ እንደመጣ “ባሕታዊ” ማስተማር ጀመረ፡፡ ተከታይ አላጣም፡፡ ብዙዎች ስለ ሥነ-ጽሁፍ ለማወቅ ጉጉት አደረባቸው፡፡
በሥፍራው ከነበሩት “ደቀ-መዛሙርት” አንዱ የሆነው ወንድወሰን አንዱአለም ቴዎድሮስ የሥነ-ጽሁፍ መምህር ቢሆንም ዝናው ግን ከክፍለ ትምህርቱ ከፍ ያለ እንደነበር ያስታውሳል፡፡ “በግቢው ተማሪዎች፣ በአካባቢው ነዋሪዎች፣ በክልልና በከተማ አስተዳደሩ አመራሮች ጭምር የሚወደስ የሚከበርና የሚፈራ የብዙ ጊዜ አጀንዳ የሆነ ሰው እንደነበር እኔ ምስክር ነኝ ”ይላል፡፡ “ብዙዎች በእርሱ በመማራቸው ራሳቸውን እንደ እድለኛ ይቆጥራሉ፡፡ ዛሬም ድረስ በተለያየ ደረጃ ላይ ሆነው ስሙን ሲያነሱት መስማትም የተለመደ ነው”፤ሲልም ይደመድማል፡፡ ፡
የበርኻው የሥነ-ጽሁፍ መምህር ሕይወቱ አማናዊ ነው፡፡ በእርሱ ውስጥ ዛሬ ለነገ መሸጋገሪያ ብቻ አይደለችም፡፡ ጋምቤላ ሁኖ ስለነገው ደጋግሞ ማሰቡ ባይቀርም መምህርነቱን ግን ወዶታል፡፡ ኮተቤ ላይ ለተለየው ወዳጁ ይፅፍለት የነበረው ደብዳቤም ይህን ያረጋግጣል፡፡ ቴዎድሮስ ለአብነት ይልካቸው በነበሩ ደብዳቤዎቹ ላይ ተማሪዎቹ ለውጥ እያመጡለት መሆኑን ፈተናውንና ውጤታቸውን ኮፒ እያደረገ በመላክ ደስታውን ይገልጽ ነበር፡፡ ከአብነት ትውስታ ጥቂት እንዋስ፡፡ ”ቴዎድሮስ ማስተማር ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ ለተማሪዎቹ ፍጹም ክብር አለው፡፡ ይህ ማለት ሰፊ ዝግጅት ከማድረግ አንስቶ ለተማሪዎቹ ሳይሰስት ያለውን ሁሉ እያካፈለ በሚኖራቸው ውጤት መደሰትን ይጨምራል ፡፡“
በእርግጥም እንዲህ ያለው የመምህሩ ቴዎድሮስ ገብሬ ጠባይ በእርሱ ሥር ያለፉ ተማሪዎቹ ሁሉ ትዝታ ሳይሆን አይቀርም፡፡ “በይነ-ዲስፕሊናዊ የሥነ-ጽሁፍ ንባብ” የተሰኘውን መጽሐፍ ካነበበ በኋላ ለሥነ-ጽሁፍ ጥናት እጁን የሰጠው የአለ የሥነ-ጥበብና ዲዛይን ትምህርት ቤት ዳይሬክተሩ አገኘሁ አዳነ የስድስት ኪሎን ደጃፍ ከረገጠ በኋላ በሩቅ ያወቀውን ሰው በቅርብ ሲያገኘው የተሰማውን ስሜት እንዲህ ይገልፃል፡፡ “ሰውዬው አዋቂ ብቻ ሳይሆን ስስት የሌለበት፣ ጥንቅቅ ያለ ምሑር፣ የተማሪን ጥቂት ጥረት በደግነት አግዝፎ የሚያበረታ አባት መሆኑን እመሰክርለታለሁ።” የአገኘሁን አስተያየት ሌላው የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ አንጋፋው የቴአትር መምህር አሰፋ ወርቁም ይጋራዋል፡፡
የሥነ-ፅሁፍ ዕውቀቱ ያስገርማል፡፡ የማስተማር ዘዴው ለተማሪዎች ከፍ ያለ ነፃነትን የሚሰጥ ከመሆኑም በላይ በየሳምንቱ በሚሰጣቸው የቤት ሥራዎች ብቁ እንድንሆን ያላሰለሰ ጥረት ያደርጋል፡፡ ቴዎድሮስ ለእኔ የስነ-ፅሁፍን ምንነት ለመረዳት፣ አቅጣጫዎችን በይበልጥ እንዳውቅ፣ ያደረገኝ ሰው ነው፡፡
የቀድሞ ተማሪው ይነገር ጌታቸው ቴዎድሮስ ማሰብን የሚያበረታታ የተለየ መምህር እንደሆነ ያስረዳል ፡፡ “የአገሬው ዘመናዊ ትምህርት ከሞላ ጎደል የሰጠሁህን ሰፍረህ መልስ የሚል ”ብድራዊ“ መንገድን የሚከተል ነው፡፡ እርሱ ግን ለጠየቀው ጥያቄ ምላሹ እውነትም ይሁን ሀሰት እንዴት? የሚለውን ጉዳይ ተማሪዎቹ እንዲያስረዱት ያበረታታል፡፡ይነገር መምህሩን ሲያስብ የፈላስፋው ዘረዓያቆብን አባባል ይስታውሳል፡፡ ”ትምህርት ያልተሟላን ሰውነት መሙያ ከሆነ፤ ለእሱ ተግባር በልኩ የተፈጠረው ቴዎድሮስ ገብሬ ነው“፤ ይላል፡፡
ብርሃኑ ደቦጭ ቴዎድሮስን ጎበዝ መምህርና ብርቱ ተመራማሪ ብቻ ሳይሆን የተማሪዎቹን ስኬት እንደራሱ የሚቆጥር ደግ ሲል ይጠራዋል፡፡ “ያስተማራቸው ልጆች ጥሩ ውጤት ካመጡ እዚያው እንዲቀጠሩ ብዙ ይጥራል፡፡ በዚህ ብቻ ግን አያቆመም፡፡ ለአዳዲስ ባልደረቦቹ መብትና ጥቅምም የእርሱን ያህል የሚታገል የለም፡፡”የመምህሩ ቴዎድሮስ አስተዋጾ በእርግጥም በመማሪያ ክፍል ብቻ የሚሰፈር አይደለም፡፡
የሚዲያ ባለሙያው ዘካርያስ ብርሃኑ ጎበዙም ሆነ ሰነፉ ተማሪ ስለቀድሞ መምህሩ በአድናቆት የሚያወራው አንድ ነገር ስለመኖሩ ይገልፃል፡፡ እሱም ዕውቀትና መልካምነትን አጣምሮ መያዙ ነው፡፡ የጋምቤላ ተማሪውና የዛሬው ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊ ወንድወሰን አንዱአለም ምስክርነትም ከዚህ ጋር ይስማማል፡፡ ወንድወሰን ዲፕሎማውን ከጨረሰ በኋላ የሥራውን ዓለም አሐዱ ብሎ የጀመረው በጋምቤላ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ባለች አነስተኛ የገጠር ቀበሌ መምህር በመሆን ነበር፡፡ ይሁንና የቀድሞ መምህሩ ያለውን ሥነ-ጽሁፋዊ መረዳት በወጉ ያውቅ ስለነበር በቻለው አቅም ሁሉ ሊረዳው ደፋ ቀና ማለቱን ቀጠለ፡፡ እንዲማር አብዝቶ ጎተጎተው፡፡
አንዱአለምም ይሁንታውን ሰጥቶ በጂማ ዩኒቨርስቲ የክረምት መርሃ ግብር ለመማር ተመዘገበ፡፡ ቴዎድሮስ ግን ለተሻለ ነገህ ወደ አዲስ አበባ መጥተህ አድቫንስ ስታንዲንግ ብትማር ይሻላል አለው፡፡ ምክሩ ለማለት ያህል ብቻ አልነበረም፡፡ መምህሩ ለራሱ ከማትበቃው ደሞዙ ላይ ለትራንስፖርት ልኮ የቀድሞ ተማሪውን አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ እንዲመዘገብ ረዳው፡፡ አላበቃም፡፡ ትምህርት ከጀመረም በኋላ የኪስ ገንዘብ እየሰጠ አስተማረው፡፡ ዛሬ ወንድወሰን የቀድሞ መምህሩን አሁን ለደረሰኩበት ደረጃ ያደረሰኝ ሌላኛው አባቴ ነው ይላል፡፡
የቴዎድሮስ እንዲህ ያለው ደግነት በተማሪዎቹ ውስጥ ጎልቶ ይስተዋል እንጂ ለሚያውቁት ሁሉ ግን የተለመደ መሆኑን የረጅም ጊዜ ወዳጁ ብርሃኑ ደቦጭ ይናገራል፡፡ እማኝ የሚጠራው ራሱን ነው፡፡ "ባንድ ወቅት ስልኬ እክል ገጥሞት ለተወሰነ ጊዜ ብጠፋበት አዲስ ስልክ ገዝቶ ሲፈልገኝ አገኘሁት"፤ይላል፡፡ ተማሪው አገኘሁ አዳነም በሕይወት ውጣውረድ ውስጥ ሁሉ አብሮ የሚደክም እውነተኛ ወዳጅ ይለዋል፡፡
ቴዎድሮስ ገብሬ በጋምቤላ መምህራንና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ሰፊ ተቀባይነትና አንቱታን ቢያተርፍም እርሱ ግን ራሱን ለማሳደግ የበርሃዋን ገነት መሰናበት ነበረበት፡፡ በመሆኑም በ1995 ዓ.ም ሁለተኛ ዲግሪውን ለማጥናት አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲን ተቀላቀለ፡፡አንጋፋዎቹ መምህራን አሁንም ከጠያይሞቹ ሕንፃዎች ስር አልጠፉም፡፡ዮናስ አድማሱ (ዶ/ር) ስመ ገናና ናቸው፡፡ ፍቃደ አዘዘ(ዶ/ር) ዘመናትን ከኢትዮጵያ ሥነ-ጽሁፍ ጋር እንደ ጅረት ተጉዘዋል፡፡
ቴዎድሮስ በጋምቤላ ቆይታው የመጣለትን በእንግሊዝ አገር የመማር ዕድል አንዱንም ያሳለፈው የኮተቤ መምህሩን ማስፈራሪያ ተቋቁሞ እንደሚገኝ ለማሳየት ነበር፡፡ የመጀመሪያ ዲግሪ መመረቂያ ጽሁፍ አማካሪው ተማሪውን ሲሰናበተው ”አንተ ጎረምሳ በዚህ ጥጋብህ ከቀጠልክ እነዚያ ሽማግሌዎች ይሰብሩሀል ተጠንቀቅ አለው፡፡“የቅኔው ፍች የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ አንጋፋ የሥነ-ጽሁፍ መምህራን ለእንዲህ ያለው ድፍረትህና ልማድ አፍራሽነት ቦታ የላቸውም ተጠንቀቅ የሚል ነበር፡፡ ወቅቱ ደረሰና ሁለቱ ወገኖች ተገናኙ፡፡“ሰባሪና ተሰባሪ” ተፋጠጡ፡፡
ቴዎድሮስ ገብሬ
(ተባባሪ ፕሮፌሰር)
ቴዎድሮስ ገብሬ (ተ/ፕ) በዓለም ታላላቅ የምርምር መጽሔቶች ላይ በርካታ ጥናቶችን ለንባብ ያበቃ የሥነ-ጽሁፍ ተመራማሪና መምህር ነው፡፡ ስመ ጥር በሆኑት “ብላክ ዌል”፣“ካላሉ”እና “ኖርዝ ኢስት አፍሪካን ስተዲስ” ካቀረባቸው ምርምሮች በተጨማሪም በአማርኛ ቋንቋ “በይነ-ዲስፕሊናዊ የሥነ-ጽሑፍ ንባብ” የሚል መጽሐፍና በርካታ ጥናቶችን ለአንባብያን አቅርቧል፡፡
ቴዎድሮስ ከአገሩ ሳይወጣ በጥልቅ ንባቡና ምርምሮቹ ጆናተናን ከለርና ሜሪ ሮዛሪዎን ከመሰሉ የዘመናችን የሥነ-ጽሁፍ ሊቃውንት አድናቆትን ያተረፈ ስኬታማ ኢትዮጵያዊ ምሁር ነው፡፡
በዚህ መነሻም ድርጅታችን ተወዳጅ ሚድያ እና ኮሚኒኬሽን በሥነ-ጽሁፍ፣ በቴአትር ፣በፊልም እና በሚድያ ዘርፎች የተለየ አስተዋጽኦ ያላቸውን ኢትዮጵያዊያን የሕይወት ታሪክ ለመሰነድ የጀመረው ፕሮጀክት አንድ አካል ሆኗል፡፡ ይህ ግን በቀላሉ የተሳካ አይደለም፡፡ ቴዎድሮስ ገብሬ (ተ/ፕ) እንደ አንድ መምህርና ተመራማሪ መገለጤ ባስተማርኳቸው ተማሪዎች ስኬትና በምሰራቸው ጥናቶች ከፍታ እንጂ በእኔ ሰዋዊ የሕይወት ጉዞ መሆን የለበትም የሚል ጽኑ ዕምነት አለው፡፡ይሁንና ማስረሻ ፈጠነ (ፕ/ር) ባደረጉት ጥረት በራሱም ባይሆን በተማሪዎቹና ባልደረቦቹ ምስክርነት የቴዎድሮስ ገብሬ የሕይወት ታሪክ እንዲህ ተሰንዷል፡፡
ተወዳጅ ሚዲያና ኮሚኒኬሽን ዓላማችንን በመረዳት የዚህን ታዋቂ መምህርና ተመራማሪ የሕይወት መንገድ እንድንሰንድ ለተባበሩን ሁሉ ምስጋና ያቀርባል፡፡
ከቀድሞ የቴዎድሮስ ገብሬ (ተ/ፕ) ተማሪዎች አንዱ የሆነው ደራሲና ጋዜጠኛ ይነገር ጌታቸው/ማዕረግ/ የጽሁፉን አርትዖት በመሥራትና የመጣጥፉን ሁለተኛ ክፍል (አስተርዮ ቴዎድሮስን) ሙሉ በሙሉ በማዘጋጀት ላደረገው አስተዋጾ በእናንተ በአንባብያን ስም ክብረት ይስጥልን እንላለን፡፡
በተጨማሪም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የአለ የሥነ-ጥበብ እና ዲዛይን ትምህርት ቤት መምህር አገኘሁ አዳነ ድልነሣሁ የቴዎድሮስ ገብሬን ምስል በስኬች ሰርቶ ስላስረከበን ብቻ ሳይሆን በቴዎድሮስ ላይ ሀሳቡን ስለሰነዘረ ምስጋናችን ወደር የለውም፡፡ ወዳጃችን ሲሳይ ጫንያለውም የቴዎድሮስን ታሪክ በእንዴት ያለ መልኩ ማደራጀት እንዳለብን ጥልቅ ሀሳብ ስለለገሰን ሲስ ባለበት እናመሰግነዋለን፡፡
ይህ ጽሁፍ በሁለት ክፍሎች የተዋቀረ ነው፡፡ ቀዳሚው በአብዮት ዘመን ተወልዶ አብዮት የታጠነውን የጨርቆሱን ብላቴና ያስታውሳል፡፡ ተማሪውንና መምሕሩን ቴዎድሮስን ይፈልጋል፡፡ሁለተኛው ክፍል ግን ከዚህ ይለያል፡፡ ሰዋዊውን መሠፈሪያ ትቶ ረቂቁን ምሑራዊ ፈለግ ይከተላል፡፡ በዓለም ዓቀፍ የምርምር መጽሔቶች ስሙ ስለሚጠቀሰው፤ሀሳቡ እንጂ እርሱ ስለማይታየው ቴዎድሮስ ያትታል፡፡
ዕዝራ እጅጉ (ዋና አዘጋጅ)
መልካም ንባብ፡፡
ኀሠሣ ቴዎድሮስ
ቴዎድሮስ ገብሬ ውልደቱ 1966 ዓ.ም ነው፡፡ ንጉሳዊው ሥርዓት በቃህ ተብሎ ወታደራዊው መንግሥት መጣሁ በሚልበት፤ የቀድመው ልማድ ተሽሮ አዲሱ ፍኖት በሚጠረግበት-ዘመን፡፡ ማሕበራዊ ምስቅልቅሉ፣ ነጭና ቀይ ጥለት የለበሰው የአገሬው ሽብር ሁሉ የትዝታው አካል ናቸው፡፡ በደም በተዋጀው የኢትዮጵያዊነት መንፈስ ውስጥ አዲስ አበባ ጨርቆስ ሰፈር የተወለደው ቴዎድሮስ ብዙም ጨዋታ የሚስበው ታዳጊ አልነበረም፡፡ እስከ ዘጠኝ ዓመቱ ከእኩዮቹ ጋር እየዋለ ኳስ ቢጫወትም ኋላ ላይ ግን የጓደኞቹም መንገድ ግድ አልሰጠው፡፡
ይልቁኑ ልብ-ወለዶችን እያሳደደ ማንበብ ጀመረ፡፡ታሪክና ፍልስፍናን ይፈልስ ያዘ፡፡ ኳሱን ራቀ፤ ብሽሽቁን ሸሸ፡፡ የራሱን ዓለም በልኩ የሰራ መሰለ፡፡ ታናሽ ወንድሙ እንዳለ ገብሬ የቴዎድሮስ አብሮ አደጎች መጽሐፍቱ ናቸው ይላል፡፡
ደስታውም ንዴቱም የሚቀዳው ከእነርሱ ነው፡፡ መጽሐፍት ያነባል፤ የራዲዮ ድራማ ያደምጣል፡፡ በልኩ የሚሟገተው ባያገኝም ከንባቡና ከማድመጡ ያገኛቸውን ጉዳዮች ይዞ ያወራል፡፡ እንዳለ ታላቅ ወንድሙን እንደ ልጅ ቤተ-ዘመድ ቤት እንኳን የመሄድ ፍላጎት ያልነበረው እንደሆነ ያስታውሳል፡፡“እኛ አውዳመትን አስመልክተን በየቤቱ ስንዞር እርሱ ፍላጎት አልነበረውም፡፡ በኋላ ጉትጎታው ሲበዛበት አክስታችን ቤት መሔድ ጀመረ፡፡ ለዚያውም እርሷ ቤት መጽሐፍት አለ ተብሎ!”
የቴዎድሮስ ገብሬ ልጅነት ካለ መጽሐፍት የሚታሰብ አይመስልም፡፡ የታሪክ ተመራማሪውና ኀያሲው ብርሃኑ ደቦጭም በዚህ ሀሳብ ይስማማል፡፡ ብርሃኑና ቴዎድሮስ ትውውቃቸው የአንደኛ ደረጃ ተማሪ እያሉ ነበር፡፡ ደገኛ ቦታ ሲውሉ፡፡ ደገኛ የተባለው ሥፍራ ያየኔው ወመዘክር የአሁኑ ብሄራዊ ቤተ-መዛግብትና ቤተ-መጽሐፍት ኤጀንሲ ነው፡፡ሁለቱ ታዳጊዎች ከመንደራቸው ርቀው ይጓዛሉ፡፡ መሄዳቸው እንደ እኩዮቻቸው በኳስ ጨዋታ ሰፈራቸውን ለማስጠራት አይደለም፡፡ ማቅናታቸው እንደ አብሮ አደጎቻቸው ለውሃ ዋና አልያም ለድብድብ ሆኖ አያውቅም፡፡ ሰርክ ልማዳቸው ንባብ ነው፡፡ ከጨርቆስ ተነስተው ሼህ መንደፈርን አልፈው ብሄራዊ ይደርሳሉ፡፡ ሲያነቡ ውለው ስለ መጽሐፍት እያወሩ ሰፈራቸው ይመለሳሉ፡፡
ቴዎድሮስ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቱን የተከታተለው ፃድቁ ዮሃንስ እና ፈለገ- ዮርዳኖስ ትምህርት ቤቶች ነው። የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ደግሞ ዳግማዊ ምኒሊክ ፡፡ ታናሽ ወንድሙ “ልክፍት” ሲል የሚጠራው የቴዎድሮስ የንባብ ፍቅር የሁለተኛ ደረጃ ተማሪ ሆኖም ከሰፈሩ ሲርቅ ባሰ እንጂ አልቀነሰም፡፡ እንዳለ እንደሚያስታውሰው ታላቅ ወንድሙ ለምሣ ተብሎ የሚሰጠውን ገንዘብ ጾሙን እየዋለ መጽሐፍት ይገዛበት ነበር፡፡ “በእርግጥ እንደቤተሰብ መጽሐፍ ከገዛሁ ጾሜን ብውልስ የሚለው የቴዎድሮስ ሐሳብ የሚደገፍ አልነበረም፡፡ ኋላ ላይ ግን አባታችን ነፃነቱን ሰጠው፡፡ ድንበሩን አከበረለት፤አስከበረለት፡፡”
ብርሃኑ ደቦጭ የቴዎድሮስ የታዳጊነት ዘመን ንባብ 'ይሄን መጽሐፍ አንብቤዋለሁ ለሚል ዝና አልነበረም“ ይላል፡፡የትኛውን መጽሐፍ ለምን እና እንዴት ማንበብ እንዳለበት ገና በእዚያ እድሜው የሚያውቅ ጥንቁቅ ስለመሆኑም ያስታውሳል፡፡ በእርግጥም የታዳጊው ቴዎድሮስ ለንባብ መሸፈት የአንድ ወዳጁ ትውስታ ብቻ አይደለም፡፡ የረጅም ጊዜ ጓደኛው አብነት መንግሥቴ ትዝታ እንደውም ለፊት ፈገግታን ይለግሳል፡፡ “የበዓሉ ግርማ ኦሮማይ በዳግም ሕትመት ለአንባብያን ሲበቃ አዲስ አበባ በመጽሐፉ ወሬ ተመታች፡፡
ብዙዎች ተቀዳድመው ለመግዛት በየመደብሩ በር ተገኙ፡፡ ብላቴናው ቴዎድሮስም ያለችውን ገንዘብ ይዞ ሊገዛ ተሰለፈ፡፡ከመኻል ግን አንድ ያልጠበቀውን ድምጽ ሰማ፡፡ ዘበኛው ነው፡፡ “ተራ ይዘህ ልትሽጥ ነው አይደል ?! ውጣ” አለው፡፡ ታዳጊው ለራሴ ላነበው ነው ቢል የሚያምነው አላገኘም፡፡ ውጣ… ውጣ… ተባለ፡፡ እጅ አልሰጠም፡፡ ሰለፈኞቹም በትህትናውና በልጅነት ፊቱ ላይ ጨክነው አልጨከኑም፡፡ገዝቶ ወደ ቤቱ ሔደ፡፡”
ቴዎድሮስ የ12ኛ ክፍል ትምህርቱን ያጠናቀቀው በ1983 ዓ.ም ነው፡፡ ይሁንና ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋም ከመግባቱ በፊት ለሦስት ዓመታት ያህል ንባብን ሕይወቱ አድርጎ ሊዘልቅ ሞክሯል፡፡በዚህ ወቅትም በሀገርአቀፍ ህዝብና ቤት ቆጠራ በረዳት ካሪቶግራፊነት እንዲሁም በአስተባባሪነት ተሳትፏል፡፡ ይህም ሆኖ ግን የትምህርቱን ነገር እርግፍ አድርጎ አልተወውም፡፡ በ1987 ዓ.ም የኮተቤ መምህራን ኮሌጅን ተቀላቀለ፡፡ምርጫው የማይጠበቅ አልነበረም፡፡ የልጅነት ሕልሙን ሊኖር የኢትዮጵያ ቋንቋዎችና ሥነ-ጽሁፍ ትምህርት ክፍል ገባ፡፡
አለመኖር - ዳዊት ወንድማገኝ (ዶ/ር) (Replay)
https://www.clubhouse.com/room/mW1393yY?utm_medium=ch_room_xr&utm_campaign=98dKo-gn0neMKaTKMDXwMw-839466