wlkayi | Unsorted

Telegram-канал wlkayi - Asfaw abreha

10124

News

Subscribe to a channel

Asfaw abreha

ሶስት ባድ አፕሎች ስለ Bad apple እየተነተኑ ነው።
ኮሶስቱም በጣም የተበላሸው bad apple ምን ቢል ጥሩ ነው ?
👉 "አቶ ሬድዋን ሁሴን 'በትግራይ የእርዳታ አሰጣጥ ሂደቱን ሊያበላሹ የሚችሉ የውጫ ሃይሎች አሉ' ብለው በተለየ ሁኔታ የወነጀሉት ኤርትራን ነው"

** በውነቱ የተንታኞቹ ባዶነት በጣም ያሸማቅቃል። እነዚህ ሰዎች መሬት ላይ የተሰራውን ታሪክ በፍፁም የማያውቁ ባይተዋሮች ነው።

ትንተና ግን እንዲህ ረክሷል እንዴ ?
ትንተና በራሱ 'Bad apple' ሆኗል በሉኛ🤣🤣
_____

Читать полностью…

Asfaw abreha

ጋዜጣዊ መግለጫው ቀርቶ በቅጡ በኮነነኝ 🤣

Читать полностью…

Asfaw abreha

"ኢሳያስ አፈወርቂ፣አቢይ አህመድ እና የአማራ ልሂቃን የትግራይን ህዝብ አያውቁትም።ትግራዋይነት ጣሊያን ጠፍጥፎ ከሰራትና ጫጩት ከምታክለው ኤርትራ ጋር የሚወዳደር ማንነት አይደለም።አንመጣጠንም"
-- ኪዳነ አመነ

👇
" እንዲህ አይነት የአእምሮ ችግር መቼ ሊድን ወይም ሊቀየር እንደሚችል እግዚአብሔር ብቻ ነው የሚያውቀው "
-- አቶ ኢሳያሳ አፈወርቂ የኪዳነ አመነ አይነት ሰዎችን በተመለከተ ከአመታት በፊት ለተጠየቁት ጥያቄ ሲመልሱ 🤣🤣

Читать полностью…

Asfaw abreha

ከልደቱ የተለየ ነገር ስለማይጠበቅ ለጊዜው እንተወው...
እንደው ግን ያቺ የትናንትናዋ ልጅ "ዜማ ቀይራለች" ብያችሁ አልነበር ?
ይኼው የዛሬ ጀግናዋ ደግሞ "ክደቱ" ሆኗል።
(የዛሬና የትናንት ዜማዎቿ☝️☝️)

Читать полностью…

Asfaw abreha

በቃ ይቺ ልጅ ጭራሽ ለየላት ።
ምኑን ከምኑ አገናኘችውሳ ?
የዛሬን አያድርገውና እነ ቮድካው ፕሪቶሪያ የከተሙ ቀን የተቀኘችላቸው መሆኑ እኮ ነው።
ዛሬ እማ "ጌቾ አማራ ነው፤ ደብረፂዮንም ኤርትራዊ ነው.. እኛን አይወክሉንም" ከሚሉት መሃል ተዘንቃ በሌላ ሙዚቃ እያበደች ነው።

P.s
በነገራችን ላይ የዛን መንደር ክፍፍል በጣም ወድጄዋለሁ።ትንሽ ቦርቀቅ ቢል ደግሞ የሆነ መካከል ላይ ኢትዮጵያዊነት ይገኝ ይሆናል።
አለበለዚያ ግን አሁን አብዛኛውን ሰው ተስፋ አድርጎ የሚጠብቀውን ውጤት እኔ አልጋራውም።
እንደውም በእእእእጅጅጅጅጅጉጉጉጉ እለያለሁ !

P.s.s
ይሄ ሙዚቃ ግን በትግርኛ ይተርጎምላት ይሆን ?እስኪ....Goodnight !😂

Читать полностью…

Asfaw abreha

እነ 360 ህዝብን Panic ውስጥ ያስገባል ያሏቸውን አዳዲስ አጀንዳዎች እየፈጠሩ ለቀጣይ ትንታዎቻቸው እየተዘጋጁ ነው።

የ ዩ ቲዩብ ሽቀላው አደጋ ውስጥ ገባ'አ 😂

Читать полностью…

Asfaw abreha

አንድ የፖላንድ የፓርላማ አባል ይሄንን ቪዲዮ በማጋራቱ ምክንያት ለሁለት ሳምንት ያህል በማርላማው ውይይቶች ላይ እንዳይሳተፍ ታግዶ ነበር።

A Polish MP was banned from sessions for sharing this video

Читать полностью…

Asfaw abreha

እውነት መጨረሻ ላይ ስታሸነፍ ሁሉም መናዘዛቸው ግድ ነው ።
እነ ደርምሴም በቀጣይ will follow suit !
😂😂

Читать полностью…

Asfaw abreha

እሱ የፓርቲው ከፍተኛ አባል ነው። ፓርቲው የሰላም ስምምነቱን ፈርሟል።
ወዲህ ደግሞ ዳያስፖራ ተጋሩ ስምምነቱን መቃወማቸውን እየደገፈ ነው።

ግራ ነገር !

Читать полностью…

Asfaw abreha

ዙኬ ዛሬን ካልቀጣኝ እድለኛ ነኝ ! በውነቱ እሱ በማይወደው ነገር ስመጣበት ባይቀጣኝ ነው የሚገርመኝ ።
ወያኔ በተምቤን ዋሻዎች ውስጥ ሆኖ መግለጫ ከመስጠት ተረፈ !

ይኼን ሰውዬ የሚመክር ጠፋ'ንጂ 😂
ዜሌንስኪ የሩሲያን የአየር ድብደባ በመስጋት በመሬት ስር ባለ የባቡር ጣቢያ (Metro) ውስጥ ሆኖ ፕሮፓጋንዳ እየሰራ ነው።
#Parody ...☝️☝️☝️

እስኪ ....Goodnight !

Читать полностью…

Asfaw abreha

አይ ትንታኔ እቴ ...

ምንም እንኳን እውነታውን ብዙም ሳይቆይ የምናውቀው ቢሆንም ሃብታሙ አያሌው የትጥቅ ማስፈታቱን ምንነትና እንዴትነት በገባው ልክ ተንትኖልናል።
ሃብታሙ ስለ ትጥቅ መፍታት ሲተነትን የተጠቀመውን ንፅፅር ግን ራሱ ደብረፂዮንም ቢሆን ደፍሮ የሚገባበት አይደለም።
ሲጀመር ንፅፅሩ በራሱ የጀመረውን ሃሳብ አይደግፍለትም እኮ 😂
ያም ሆነ ይህ ግን በ1983 ዓ.ም የኢትዮጵያ ጦር ሰራዊት አባላት የተበተኑበትን አገባብ በሰራዊቱ አባላት ዘንድ ሲነገር በተለያዩ ጊዜያት ሰምተናል።
እነዚህ የሰራዊት አባላት ሌላው እንኳን ቢቀር በየባንክ ቤቱና በየተቋማቱ በጥበቃ ስራ ላይ ተሰማርተው እንዳይሰሩ የተሰራባቸው ሴራ የትዬለሌ ነበር።

ለማንኛውም እስኪ "ትንታው" ን አዳምጡለት

Читать полностью…

Asfaw abreha

Marjorie Taylor Greene , US house of representatives member

Читать полностью…

Asfaw abreha

እ.ኤ.አ በ1998 ዓ.ም በIRA እና በሰሜን አየርላንድ መንግስት መካከል የተፈረመውን የሰላም ስምምነት ፈረንጆቹ the 'Good friday agreement ' እያሉ ይጠሩታል።
በወቅቱ IRA(Irish Republican Army ) ከገዢው መንግስት ጋር ስምምነቱን ከፈረመ በኋላ በስምምነቱ ያልተደሰቱ አንዳንድ የIRA አባላት በሽብር ስራ ላይ ተሰማርተው በአገሪቱ በሚገኙ የተለያዩ ተቋማት ላይ ጉዳት አድርሰው ነበር።
እናም እኒህ ምሁር ከGood friday agreement ትምህርት ተወስዶ ጥንቃቄ ይደረግ እያሉ ነው ።

Читать полностью…

Asfaw abreha

ኤዲት አድርጋት እንጂ ቮድካው ?

"Desarmed ወያኔ" ምናምን የምትል ነገር ጨምርባት 😂😂

Читать полностью…

Asfaw abreha

The 'Nuclear boy'

ጁመዓ ሙባረክ !

Читать полностью…

Asfaw abreha

ጣልቃ አትግቡብን 🤣

I like this !

Goodnight !

Читать полностью…

Asfaw abreha

በቀጣዩ የፈረንጆች አመት ሊፈጠር የሚችለው የሃይል እጥረት ስጋት ውስጥ የጣላቸው አውሮፓውያን ከወዲሁ የማገዶ እንጨት ፍለጋ ላይ እየተራኮቱ እንደሆነ አንዳንድ ምንጮች እየገለፁ ነው።

እየተራኮቱ 🤣🤣

Читать полностью…

Asfaw abreha

የ 'ልሳነ ግፉዓን ድርጅት' መግለጫ
👇
ኢትዮጵያችን ዳግም በአሸናፊነት፣ በታላቅ ድልና፣ በግሩም ልዕልና በጠላቶቿ መቃብር ላይ ከፍ ብላ ቆማለች!
***
በኢትዮጵያ መንግሥትና በአሸባሪው የትግራይ ሕዝብ ነፃ አውጭ ግንባር /ትህነግ/ መካከል በደቡብ አፍሪካዋ ከተማ ፕሪቶሪያ ውስጥ ከጥቅምት 13 እስከ 23 ድረስ ሲደረግ የነበረው የሰላም ንግግር ጦርነት በማቆም፣ የትህነግን ትጥቅ በማስፈታት፣ ትግራይ በፌደራሉ መንግስት ቁጥጥር ስር እንድትሆን በማድረግና፣ ለጦርነት መንስኤ የነበሩትን የእብሪትና የህገወጥነት መንገዶች ለማረም በሚያስችል መልኩ መቋጨቱ ለሀገራችን ኢትዮጵያና ለመላው ሕዝባችን ሰላም ያወርዳል የሚል ተስፋ እንድንሰንቅ አስችሎናል።
ስለሆነም ድርጅታችን ልሳነ ግፉዓን ይህን የሰላምና የፍትህ ተስፋ ያሳየንን ኃያሉን እግዚአብሔር እያመሰገነ፥ ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ እንኳን ደስ ያላችሁ! እንኳን ደስ ያለን ለማለት እንወዳለን።

ሰላም የሁሉም ነገር መሰረት እንደሆነ ልሳነ ግፉዓን በፅኑ ያምናል! ሰላም ያለፍትህ እንደማይፀናም እንዲሁ!

ያለ ሰላም ትውልድ መተካት፣ በክብር በሀገር ላይ መኖር፣ ፍትህ ማስፈን፣ ስልጣኔና እድገትን መጎናፀፍ አይቻልም። የሰላም ዋጋ እጅግ ውድና የከበረ እንደሆነ ድርጅታችን በፅኑ ያምናል። ስለዚህም ስለ ሰላም የተደከመውን ድካምና የተከፈለውን መስዋዕትነት በእጅጉ እናደንቃለን፡ እናከብራለን።

በኢትዮጵያ መንግሥትና በፋሽስቱ ትህነግ/ወያኔ መካከል የተደረሰው የሰላም ስምምነት ከእነ እንከኖቹም ቢሆን ለኢትዮጵያ ሀገራችንና ለሰላም ወዳዱ ሕዝባችን በዲፕሎማሲው መስክ የተጎናፀፍነው ታላቅ ድል ነው ብለን እናምናልን። ምንም እንኳ ለዚህ ሁሉ መሰረቱ በጦር ሜዳ የተገኘው ታላቅ ድል መሆኑ ግልፅ ቢሆንም፥ ይህን ውጤት ተጠቅሞ ፋሽቱንና ከፋሽቱ ጀርባ መሽገው ኢትዮጵያን ሲያደሙ የኖሩትን የውጭ ሃይሎች በሚያኮላሽ መልኩ የተደረገው የዲፕሎማሲ ተጋድሎ ሀገርን፣ ህዝብንና፣ ትውልድን እጅግ ያኮራ ተግባር ነው። ለዚህም ስኬት ከፍተኛ አመራር የሰጡ፣ በሰላም ንግግሩ ላይ የተሳተፉ፣ ምክር የለገሱና፣ በተለያየ መልኩ ድጋፍ ያደረጉ ውድ የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆችን ማመስገን እንወዳለን። “በጥባጭ እያለ ማን ጥሩ ይጠጣል” እንዲሉ፡ ሰላምን በአንድ ወገን ፍላጎትና ተሳትፎ ማረጋገጥ አስቸጋሪ መሆኑ የታወቀ ነገር ነው። ስለዚህ ስለ ሰላም ሁሉም ወገን ዘብ መቆም ይኖርበታል። በአንፃሩ ደግሞ እንደ ትህነግ ከፅንሰቱ ጀምሮ እስከ ሞቱ ድረስ የሀገርንና የህዝብን ሰላም በማደፍረስ፣ የሰላማዊ ዜጎችን ውድ ሕይወት በመንጠቅ፣ ጭካኔና መለያየትን በትውልድና በሀገር ላይ በማንገስ፣ የሰለጠነና የሰየጠነ ዘረኛና ፋሽስት ቡድን ጋር ስለ ሰላም መነጋገርም ሆነ ሰላምን ማምጣት “ጉምን እንደ መዝገን” ያለ ነገር ነው። ለዚህም ነበር ይህ እኩይ ቡድን ለ 27 ዓመታት የመንግሥት ስልጣን ይዞ፣ እስከ አፍንጫው ታጥቆና፣ የሕዝብንና የሀገርን ሀብት በብቸኝነት ተቆጣጥሮ እያለ፣ ስለ ሰላም ማውራትም ሆነ ሰላምን ማስፈን የማይቻል ሆኖ ያለፈው።

ዛሬ የተገኘው የሰላም ተስፋና የፋሽቱ ወያኔ በሃይል መንበርከክ በትህነግ የባህሪ ለውጥ ምክንያት፣ ሰላም ወዳድነት፣ ወይም እንዲሁ እንደዋዛ በችሮታ የተገኘ አይደለም። ይልቁንም የኢትዮጵያ አለኝታዎች በሰሜን ዕዝ ውስጥ በደረቅ ሌሊት በጭካኔ ታርደው፣ የማየካድራ ንፁሃን በግፍ ተጨፍጭፈው፣ የአፋር ንፁሃን ወገኖቻችን በጅምላ ተጨፍጭፈው፣ የአማራ ህዝብ ከወሎ እሰከ ጎንደር፡ ከሸዋ እስከ ወለጋ በግፍ ታርደው፣ እናቶቻችንና ሴት ልጆቻችን በአደባባይ ተደፍረውና ተዋርደው፣ የእምነት ተቋማቶቻችን ተረግጠውና ተመዝብረው፣ የሀገርና የሕዝብ ንብረቶች በጭካኔ ወድመውና ተዘርፈው፣ “ኢትዮጵያን ወይም ሞት!” ያሉ የጥምር ሃይላችን የቁርጥ ቀን ልጆች ከፋሽስቶች ጋር በ3 ዙር ጦርነት አንገት-ለአንገት ተናንቀውና ክቡር ደማቸውን በጀግንነትና በክብር አፍስሰው፣ በአጠቃላይ ተነግሮ የማያልቅና ህልቆ መሳፍርት የሌለው ግፍና መከራ በሕዝባችንና በሀገራችን ላይ ከደረሰ በኃላ የተገኘ አንፃራዊ “ሰላም” ነው።

የትህነግ/ወያኔን ትጥቅ ለመፍታትና ከዘላለማዊ ድምሰሳ የተረፉትን ጥቂት መሪዎቹንና ጭፍሮቹን ወደ ካምፕ ለማስገባት መስማማቱን በመርህ ደረጃ ብንቀበለውም፥ “ድመት መንኩሳ፣ አመሏን አትረሳ” ነውና፡ ዛሬ ትህነግ በኢትዮጵያ አናብስት ብርቱ ክንድ ክፉኛ በመደቁሶ ምክንያት እጅ ቢሰጥም እንኳን ተፈጥሯዊ የሆነውን ክህደትና ፋሽታዊ ምግባሩን ለቅፅበት ይተዋል ብለን አናምንም። ስለሆነም መንግሥትና የሚመለከታቸው አካላት በሙሉ የተደረሰው የሰላም ስምምነት ሙሉ በሙሉ ወደ ተግባር መቀየርና የትህነግ/ወያኔ የቀደመ ፋሽስታዊ ማንነቱ እንዳያገረሽ ሆኖ መወገዱ በተግባር መረጋገጥ ይኖርበታል። በአንፃሩ ደግሞ አስተማማኝና አስፈላጊ የጥንቃቄ እርምጃዎች ባለመወሰዳቸውና ጥቃቅን ክፍተቶች በመተዋቸው ምክንያት ህዝባችን ለዳግም ሽብርና ፋሽስታዊ ጥቃት እንዳይጋለጥ በእጅጉ እንሰጋለን። ስለሆነም መንግሥት ከወዲሁ አስፈለጊ የጥንቃቄና የመፍትሄ እርምጃዎችን በቁርጠኝነት ይወስድ ዘንድ በትህትና እንጠይቃለን።

የትህነግ/ወያኔ የፋሽስትነቱ መገለጫና የጭካኔው መጀመሪያና መጨረሻ በወልቃይት፣ ጠገዴና፣ ጠለምት ወገኖቻችን ላይ የፈፀመው የዘር ማፅዳትና ማጥፋት ወንጀል ነው ብለን እናምናለን። ይህ እኩይ ቡድን በ1972 ዓ.ም ተከዜን ተሻግሮ የአማራን ዘር ለማጥፋት በወልቃይት የጀመረውን ጭካኔውንና ፀረ-ሰላም ጉዞውን ከ1600 በላይ የሆኑ ሰላማዊ አማራዎችን ማይካድራ ላይ በጀምላ ጨፍጭፎ የ 40 ዘመናት የጭካኔ ታሪኩን ወልቃይት ላይ በአሰቃቂ ሁኔታ ፅፎ አልፏል።

ብሂሉ “የ ሺ ፍልጥ፣ ማሰሪያው ልጥ” ነውና፥ የዚህ ሁሉ ተጋድሎና ድል መቋጫው የኢትዮጵያ እስትንፋስ፣ የጠላቶቻችን ሴራ ማጠንጠኛ፣ የሕዝባችን ሰቆቃ መቋጫና፣ የፋሽስቱ መቀበሪያ የሆነችው የወልቃይት ህዝብ ጉዳይ ነው። የወልቃይት ጉዳይ የፍትህ ጉዳይ ነው! የወልቃይት ሕዝብ ጥያቄ የአማራ ማንነት ጥያቄ ነው! የወልቃይት ሕዝብ ጥያቄ ለኢትዮጵያ አንድነትና ሉዓላዊነት የተከፈለ የ 40 ዓመታት ሰቆቃና ግፍ መቋጫ ጥያቄ ነው! በወልቃይት ላይ የሚጠየቀው ፍትህ ኢትዮጵያ ሀገራችን በትህነግ/ወያኔ ለተቀበለችው መከራና ፍዳ ሁሉ መቋጫ ነው! የወልቃይት ጥያቄ የአማራ ወጣቶች “ወልቃይት ብረሳሽ ቀኜ ትርሳኝ” እያሉ ደረታቸውን ለፋሽስቱ የጥይት አረር የሰጡለት የትውልዶች ጥያቄ ነው! የወልቃይት ጥያቄ በአለፉት ሁለት ዓመታት ብቻ በሺዎች የሚቆጠሩ የኢትዮጵያ ውድ ልጆች ከአራቱም አቅጣጫ ተሰባስበው በአንድነትና በጀግንነት ክቡር ደማቸውን ያፈሰሱለት የሀገር ሉዓላዊነት ጥያቄ ነው!

ሰላም የሚፀናው ፍትህን በማረጋገጥ ነው! ያለ ፍትህ ሰላም የለም! ስለሆነም መንግስት እጅግ ላጓተተው የወልቃይት ሕዝብ የአማራ ማንነት ጥያቄ በግልፅነትና በቁርጠኝነት አፋጣኝና ፍትሃዊ መልስ መስጠት ይገባዋል። ያኔ ኢትዮጵያ ሀገራችን በጠላቶቿ ላይ የተቀዳጀቻቸው አንፀባራቂ ድሎች ሁሉ ማሳረጊያ ያገኛሉ! ምክንያቱም ፀረ-አማራና ፀረ-ኢትዮጵያ የሆነው ትህነግ/ወያኔ በደደቢት ዋሻ ውስጥ የጠነሰሰውን የጥፋት ራዕይ ትግበራ በወልቃይት ህዝብ ላይ እንደ ጀመረው ሁሉ ፍፃሜውም ወልቃይት ላይ ፍትህን በመበየንና ርትዕን በማንገስ ሊረጋገጥ ይገባል ብለን በፅኑ ስለምናምን ነው!

ኢትዮጵያ አሸንፋለች!

ልሳነ ግፉዓን ድርጅት

ጥቅምት 27/ 2015

Читать полностью…

Asfaw abreha

ማንም Deny አያደርገውም
🤣🤣

Читать полностью…

Asfaw abreha

አንድ ዋሾ ከሃቅ ጋር ድንገት ሲጋፈጥ የሚፈጠረው Collusion ....

አብሶ ኦንላይን ላይ ተሁኖ እማ ...😂😂

Читать полностью…

Asfaw abreha

ስታሊን ገብረስላሴ .."TDF የትግራይ ሰራዊት ነው፤በህወሓት አይታዘዝም። ህወሐት ህገወጥ ፓርቲ ነው" ብሏል።

የህወሓትን ህገወጥነት ሲጀመርም አለም ያወቀው ቢሆንም TDF'ን የሚመራው ማነው ተብሎ ስታሊን ቢጠየቅስ ?
ያ ማነው እንኳን ...በሎም የሚለው ልጅ ነው ?😂😂

Читать полностью…

Asfaw abreha

የጄኔራል ሞተርስ መኪኖች ከ1000 ዓመታት በኋላ ነዳጅ አይጠጡም።በኤሌክትሪክ እንዲንቀሳቀሱ ይደረጋሉ።ይህ ሲሆን Sleepy (አዝጉ) እማኝ ሆኖ ለማየት ከወዲሁ ጠንክሮ እየሰራ ነው።
አጃኢብ !! 😂😂

" General Motors cars will become fully electric by 3035 .."
- Sleepy ( አዝጉ )

እስኪ ...Goodnight !

Читать полностью…

Asfaw abreha

መቼም ዘንድሮ የማንሰማው የለም 😂
"ደብረፂዮን ኤርትራዊ ስለሆነ አይወክለንም " እያሉ ነው።

#warning_violent_and_bullying
//አሳልፎ የሰጠን ተብታባው ደብረፂዮን ነው።ይሄንን ኤርትራዊ አንቃችሁ ግደሉት//
-

Читать полностью…

Asfaw abreha

በሱዳን የሚገኘው የሰላም መረዳጃ አማራ ማህበር አባላት ትናንት ባካሄዱት ስብሰባ በደቡብ አፍሪካ የተደረሰውን የሰላም ስምምነት እንደሚደግፉ አቋማቸውን ገልፀዋል።
የማህበሩ ሊቀመንበር ወ/ሮ ቦሰና አለሙ እንደገለፁት በሱዳን ህይወቱን እየገፋ ያለው የአማራ ህዝብ አሁን እየታየ ያለው የሰላም ጭላንጭል ባሳደረበት ተስፋ ምክንያት ወደ ትውልድ አገሩ ለመመለስ ከወትሮው በተለየ ሁኔታ እየጠየቀ ይገኛል ብለዋል።

Читать полностью…

Asfaw abreha


ይሄ ደሞ አለላችሁ☝️☝️
//ከሁሉም ሰው ጋር ወሬ ያስጠላኝ እኔን ብቻ ነው'ንዴ ?// --- ዳዊት ከበደ

ምን ተፈጠረ ዴቭ ?😂

እዚህ የሚራኮተው የመንጋው ነገር ነው ግራ ያጋባን እንጂ የገባቸው እማ ግራ ተጋብተው እያየናቸው ነበር።
በነገራችን ላይ የethio 360ውን አያ ደርምሴን ዛሬ አድንቄዋለሁ። ገብቶታል -ደብሮታልም።
ኧረ በስማምዬ ... እሱ ራሱ አብሮ ሰምጦ የለ እንዴ ? ከወትሮው 'ትንታው' የተለየ የሚመስል ነገር ዛሬ ተንትኗል።በትንታኔው ላይ በስምምነቱ ዙሪያ ወ*ያ*ኔዎቹ ተቃውሟቸውን እንዲያጠናክሩ መክሯል። "ስምምነቱ አያዋጣችሁም" ሲል አመሽቷል !
__________________________

Читать полностью…

Asfaw abreha

https://www.youtube.com/watch?v=bDYFdXVtyaI&feature=share&utm_source=EJGixIgBCJiu2KjB4oSJEQ

Читать полностью…

Asfaw abreha

"Return to Africa " ?

Carlos Martens Bilongo በፈረንሳይ የፓርላማ አባል ናቸው።
ከሁለት ቀናት በፊት እኒህ ግለሰብ ንግግር እያደረጉ ባሉበት ወቅት ከፓርላማ አባላቱ መካከል ግሪጎር ደ ፎርና ከተባለው አባል ጎላ ያለ ድምፅ ተሰማ።
ዘረኛውን ድምፅ ሁሉም አባል ሰምቶታል ።
ግሪጎር "ዝም በልና ወደ አገርህ ወደ አፍሪካ ተመለስ" ሲል ነበር ጮኾ የተናገረው -
" Qu'il(s) retourne(nt) en Afrique "
( Return to Africa )
በዚሁ ሳቢያ በአባላቱ መካከል ንትርክ በመነሳቱ የፓርላማው ውይይት ተቋርጦ ተበትኗል።

Читать полностью…

Asfaw abreha

ስምምነቱን የሚያውኩ አንዳንድ አካላት ሊኖሩ ይችላሉ !!

☝️ ማርቲን ፕላውት ከBBC ዘገባ ውስጥ መርጦ ያስተጋባት excerpts ነች

Читать полностью…

Asfaw abreha

//ወ*ያ*ኔ*ን ትጥቅ ማስፈታት የሚችል ምድራዊ ሃይል የለም//
--- ካሳ ሃይለማርያም .....የሊላይ ሃይለማርያም ወንድም ነው።
አንዱ በግላጭ ሌላኛው በማስክ ወያኔ ወያኔ የሚጫወቱ ናቸው 😂😂

Читать полностью…

Asfaw abreha

😎😎
ድምፂ ወያኔ ከ11 ደቂቃ በፊት 👇

// " ፋሺስቱ ጠላታችን እያካሄደ ካለው ጭካኔ የተሞላው የድሮን ጥቃት ለመገላገል ትግላችንን አጠናክረን መቀጠል አለብን" ሲሉ ከዚህ በፊት የድሮን ጥቃት ሰለባ የሆኑ ሰዎች ተናገሩ//

Читать полностью…
Subscribe to a channel