በልፍዓተይ ተስፋ ሲታወቅ የነበረውና ከ"ትግራይ ትስዕር " በኋላ ደግሞ በ"ሰብ ዝሰዓነ ሰብ" የምናውቀው ብርሃነ ገ/ገርግስ በወር 48,657 ብር እየተከፈለው ሲዋሽ ከነበረበት የዲጂታል ወያኔ ስራው መባረሩን የሰማሁት ዛሬ ነው ።
'ቮድካውንና የደብረፂዮንን ቡድን ለማጣላት በመሃል ሽብልቅ እየገባ አስቸግሯል" ተብሎ ነው አሉ የተባረረው !
-----------
በመጨረሻም ወንድም በወንድሙ ላይ ይነሳል! 😂😂
የጉድ አገር
White House Press Secretary Karine Jean-Pierre:
"I grew up in New York, where we went to brunches with drag queens. This was what was needed. They entertained you, they are terribly talented. I even recently had the opportunity to see drag stars in a small gay pub."
Western Liberalism leads to complete DEGENERACY ‼️
የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደርና ህወሓት ጠብጫሪ መጣጥፎችንና መግለጫዎችን በማውጣት በህዝባችንና በአስተዳደሩ መካከል ክፍተት ለመፍጠርና ጥርጣሬ እንዲነግስ አቅደው እየሰሩ ነው። ህወሓት መራሹ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር በተለይም በባለቤቱና በባለርስቱ እጅ የሚገኘውን የወልቃይት ጠገዴን አካባቢ በ"ጠላቶቻችን በሃይል የተወረረ" የሚል አደገኛ ስምና ትርክት ፈጥሮ እራሱ ጠላቴ ነው ወዳለው ወደዚሁ የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ 'እስከነ ወታደሬና ትጥቄ በሃይል እገባለሁ' እያለ ቀን ቆርጦ ሲፎክር ሰንብቷል ። ከሰሞኑ ደግሞ ትገባላችሁ ብሎ ያደራጃቸውን ታጣቂዎችና ሚሊሺያዎች ሽሬ ላይ ሰብስቦ የተፈናቃይ መታወቂያና ባጅ አድሏል።
በትናንትናው ዕለትም የጊዚያዊ አስተዳደሩ የትራንስፖርት ቢሮ ወያኔ በተፈናቃይ ስም ያደራጃቸውን ታጣቂዎችና ሚሊሻዎች ወደ ምዕ/ትግራይ የሚያመላልሱ የህዝብ ማመላለሻ ባለንብረቶች እንዲመዘገቡ የጠራበት ማስታወቂያ ሊያስተላልፍ ከተፈለገው መልእክት በበለጠ በእርሻ ስራ ላይ የሚገኘውን ህዝባችንን በስነ-ልቦና ለመጉዳት ያለመ የፕሮፓጋንዳ መልዕክት ለመሆኑ ለመረዳት የሚያዳግት አይደለም።
ወንጀለኛው ከንፁሁ ፤ ታጣቂውም ከሰላማዊው ሰው ባልተለየበትና ተገቢው የማጣራት ስራ ባልተሰራበት ሁኔታ የፕሪቶሪያውን የሰላም ስምምነት ባደባባይ በጣሰው በወያኔው ቡድን "የተፈናቃይ ስም" ስለተሰጠው ብቻ አሸባሪንና ወንጀለኛን ተቀብለን ህዝባችንን ሰላም እንዲነሳ ከቶውንም አንፈቅድም !!
ወልቃይት ጠገዴ፦ የአማራ የትግል መነሻ፡ የነፃነት ዓርማ፡ የአንድነታችን ሚስጢር !!!
ሱዳን ውስጥ የመሸገው የወያኔ ጦር ሰራዊት አባላት ዛሬ በኡምራኩባ ሰላማዊ ሰልፍ አድርገዋል!
ትጥቃቸውን ካምፕ ትተው የመጡት እነዚህ ሰላማዊ ሰልፈኞች(😂) ከወያኔው "ቴትራ" ባንዲራ በተጨማሪ የሱዳንን ሰንደቅ አላማ ከፍ አድርገው ሲያውለበልቡ ውለዋል።
( የኢትዮጵያን ሰንደቅ አላማ ያያችሁ ....አላየንም ባካችሁ 😂)
Avoid the gay !
በዚህ የሚበሳጭ ባለስልጣን ካለ እሱ ወይ ከሸኔ አለያም ከወያኔ ጋር የተነካካ ቢሆን ነው 😂
ያም ሆነ ይህ Avoid the gay !
.... BREAKING: Russia will deliver the same type of weapons to conflict zones to strike western assets of those countries that deliver weapons to Ukrain.
አፍጥንልኝማ ጋሼ ፑቲን 😂😂
" የጠለምትንና የወልቃይት ጠገዴን ህዝብ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ስም አንደበቱን አፍኖ ወራሪዎች ያሻቸውን እንዲያቀረሹ የፈቀደው ማይክ ሃመር ግን እንዳው ምን ያስቀየምነው ነገር ቢኖር ነው ?¡ 😎
ለነገሩ አገሪቱስ ብትሆን 60+ ሚሊዬን ህዝብን በtotal blackout ጀቡና "እየመከርኩ ነው" እያለችም አዶል? Monologue እና "ምክር" ወዴትና ወዴት ?
ወደ ቅድሙ ወጋችን ስንመለስ ይሄ ቅኝ ገዢያችን ማይክ ሃመር "የኢትዮጵያን ከፍተኛ ሹማምንት በማባበልም በታህዲድም ተፅዕኖ አሳርፌና አክብጄ ጭኜ እስከ ሰኔ 30 ድረስ ወያኔን እንዲሸልሙ አስማምቻቸዋለሁ ብሏል አሉ (አስገድጃቸዋለሁ ላለማለት ...ዲፕሎማት አይደል?😂) - ያው ከመሄዱ በፊት ለአሜሪካን ኤምባሲ ባልደረቦቹ brief ሲያደርግ !
በወሬያችን ላይ ግን ይሄ አየሩን የሞላው የሰሞኑ የወያኔዎቹ የ"hash-tag ሰኔ 30 " ዘመቻ ኮፒ ራይቱ የማይክ ሃመር ነው።
=======
.....የራሱን ሞት በቀጠሮ አስይዞ የወያኔ ከሞት የመነሳት ዜና የሚያስፈነድቀው የወያኔ ኮልኮሌ ብዛት ......እግዞ ያሰኛል😂😂
በያን ሰሞን ነው።በአንድ የወያኔ ደጋፊ የቴሌግራም ቻናል ላይ የተመለከትኩትን የዚህን መረጃ ተአማኒነት በመጠራጠሬ ችላ ብዬው ነበር ። መዲድ እያሉ የሚጠሩት ጄነራል ዮሐንስ ወ/ጊዮርጊስ በአንድ መድረክ ላይ ካደረገው ንግግር መካከል የተወሰደ እንደሆነ መረጃው ይገልጻል።
ምንጩ "ጄኔራሉ ተናግሯቸዋል" ብሎ ከዘረዘራቸው መካከል 👇
- ጠላቶቻችን የብልፅግና ዲቃላዎችን ፈጥረው እርስ በርሳችንን አባልተው ትግራይን ለማጥፋት እየሰሩ ነው።
- የጠላቶቻችን ወቅታዊ አቅም ደካማ ነው ፣ ሞሽሙሿል።በግራና በቀኝ ተወጥረዋል።ከዚህ ቀደም እንዳደረጉት ምንም ማድረግ አይችሉም።
- ብልፅግና የአማራ ሃይሎችና ሻዕቢያ በከባድ ጭንቅ ውስጥ ናቸው።እኛን አይችሉንም ።
ወ.ዘ.ተ ...... የሚሉ ናቸው።
እነዚህ ከላይ የተጠቀሱት ነጥቦች እና መዘክር አባዲ ዘሞ በ"ውጥንቅጡ ቀን"(😂) ዋዜማ ላይ ተደረገ ባለው የወያኔዎቹ ምክክር ላይ የተነሱት አንዳንድ ነጥቦች ተመሳሳይ ናቸው።
በዚሁ የወያኔዎቹ ምክክር ላይ ከፍተኛ የወያኔ ወታደራዊ አዛዦች ተሳታፊ እንደነበሩም ታውቋል።
( እናሳ ? መረጃውን ችላ እንዳልኩት ቢቀር ይሻል ነበር ወይስ.........?😂)
በመርህ ደረጃ የሕዝቡ የመልማት ጥያቄና ፍትሃዊ ተገቢነት ያለው የሪሶርስ አጠቃቀም ጊዜ የማይሰጠውና በፖለቲካ አስተዳደር ምክንያት የማይገደብ በመሆኑ የበጀትና የመሰረታዊ መሰረተ ልማት ጥያቄዎች እንዲመለሱ መጠየቃችንን አናቆምም፡፡
የወሰንና ማንነት ጥያቄችንን በዚህ መሰል ሁኔታዎች ማዳፈን እንደማይቻል የመጣንበነት የትግል መንገድ ምስክር ነው፡፡ ሕዝባችን በየትኛውም አስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ ቢሆን እንኳ ለነጻነትና ለክበሩ ይፋለማል፡፡ በባህላቻን እጅ መንሳት እንጂ፤ እጅ መስጠት አናውቅም!! ከጠለምት አማራ የሚሰረቅ ማንነት፤ ዳግም የሚወረር መሬት የለም!!
የጠለምት አማራ ማንነትና ወሰን አስመላሽ ኮሚቴ
ማይጠምሪ-ጎንደር
ግንቦት 13/2016
ቸር አውለኝ ብዬ በዘዴ የተለየሁት የቅድሙ ወዳጄ አሁንም ሊፋታኝ አልቻለም።
ይኼው አሁን ከመሸ ደውሎ ደካማ መንግስት እና ሳሙራይ አንድ ናቸው አላለኝም ?
"ቸር አሳድረኝ" ብዬ ጆሮው ላይ ጥርቅም ¡
(...shooting on the foot)
እስኪ ....Goodnight !
ተናግሮ አናጋሪ ...........
አንድ ወዳጄ ነው ።"የአማራ ክልላዊ መንግስት እና የኢትዮጵያ ፓርላማ አንድና አንድ ናቸው" ብሎ ወሬ ጀመረልኝ።
ይህ ወዳጄ በዚህ ንፅፅሩ ምን ለማለት እንደፈለገ ስላልገባኝና ምናልባትም ወደ ሌላ አነካኪ የፖለቲካ ወሬ ሊዶለኝ እንደፈለገ ስለተረዳሁት "ቸር አውለኝ" ብዬ ወሬውን ሳይጨርስ በዘዴ ተለየሁት ።
እርግጥ ስለ ፓርላማው የማውቀው አንድ ሀቅ አለ።በገዢው መንግስት የቀረበለትን ረቂቅና ሪዞሉሽን በሙሉ እየተቀበለ በማፅደቅ ፓርላማችንን የሚተካከለው የለም።ኧረ እንደውም በአለም ብቸኛው ፓርላማ ሳይሆን አይቀርም !
የፓርላማ ተወካዮቹ "ለምን ?" እና "እንዴት ?" የሚሉትን ቃላት ሰምተው የሚያውቁም አይመስሉም።😎 ቆይ ግን ሁሌም "YES" ግን አይደብርም ?
ፓርላማው አንድን ረቂቅ ውድቅ ያደረገበትን አጋጣሚ የሚጠቁመኝ ካለ ግን ለፀፀት ዝግጁ
ነኝ! 😂
ያ ጦሰኛ ወዳጄ ፓርላማውና የአማራ ክ/መንግስት አንድ መሆናቸውን ሊያሳምነኝ ብሎ የጀመረውን ከንቱ መጋጋጥ ፉርሽ ያደረኩበትን ዘዴ እያሰብኩኝ ፈገግ እያልኩ ያለሁበት ሁኔታ ላይ እገኛለሁ ¿¡¡
ለራስ ሲቆርሱ አያሳንሱ ....
በልዩ ሁኔታ የሰረዝከውን በልዩ ሁኔታ ዳግም ከመዘገብከው ስርዝ ድልዝ ጋር በእኩል "ዜጋ ነህ" ትለዋለህ ¡¡
"በልዩ ሁኔታ" ይበል?¡
ትግራይ ውስጥ ሿሚዎቹም ተሿሚዎቸም ራሳቸው ወያኔዎቹ ሆነው የለ'ንዴ ?
የክልሉ ስልጣን ከሞንጆሪኖና ከአለም ገብረዋህድ እጅ አልወጣም - ጌቾ ዝምብላ ባምቡላ ነገር ነች ለካ ! 😂
በትናንትናው ዕለት የተጠናቀቀው የህወሓት ስብሰባ የተለያዩ የሹመቶችንና ምደባዎችን በማድረግ ለቀጣይ ስብሰባ በቀጠሮ ተለያይቷል።ጌታቸው ረዳ በዚህ የህወሐት ስብሰባ ላይ አልነበረም።
እናማ በዚሁ የሹመትና ምደባ ጉዳይ ላይ ....
1- ከወራት በፊት በቮ**ካው ተሹሞ የነበረው የክልሉ ዋና ኦዲተር ዶ/ር ንጉስ ገብረጊወርጊስ ተሽሮ ዶ/ር ረዳኢ በርሄ ተሹሟል።
እዚህ ላይ ....
👉 ቮ**ካው የሾመው በሞንጆሪኖና በአለም ገብረዋህድ ተሻረ ! አንድ በል
👉መንግስታዊ ሹመት በፓርቲ እየተሰጠ ነው ማለትም ነው። ሁለት በል
2- ሌላው የህወሓት ሹመት ለአቶ አለም ገብረዋህድ የተበረከተው ነው።ምደባው በሞንጆሪኖ ጥቆማ አቅራቢነት የፀደቀ ሆኖ በምክትል ር/መስተዳድር ደረጃ የህወሓት ሊቀመንበር አማካሪ ሆኖ ተመድቧል።
እዚህ ላይ ....
👉የአንድ ም/ር/መስተዳድር ደሞዝና ሙሉ ጥቅማጥቅም መንግስት ይከፍላል ማለትም አይዶል ? ሶስት በላ 😎
ትህነግ ለሰላም እጁ የማይዘረጋ፤ ህልዉናዉን በግጭት አዙሪት የመሰረትና በሰዉ ልጅ ደም የጨቀየ አጥፊ ቡድን ነዉ!
ትህነግ ገና ሀ ብሎ ጫካ የገባዉ እና ማንፌስቶዉን ለመጻፍ ብዕሩን ያነሳዉ በአማራ ህዝብ ጥላቻ ተመስርቶ መሆኑን ለሶስት አስርት ዓመታትና በላይ በአማራ ህዝብ ላይ የፈጸመዉ ግፍና መከራ አፍ አዉጥቶ ይናገራል።
አሸባሪው የትህነግ ቡድን ዘመናትን ባስቆጠረዉ ስር የሰደደ ጥላቻዉ አማራንና አማራነትን ሲያሳድድ፣ ሲያስር፣ ሲጨፈጭፍና ሲያስጨፈጭፍ ኑሯል። ከስህተቱ ሳይማር አሁንም የጥፋት ተግባሩን ቀጥሎበታል። ቡድኑ የአማራ የሆነን ሀብትና ንብረት በየደረሰበት ይዘርፋል መዉሰድ ያልቻለዉን ደግሞ ያወድማል።
ይህ ለእርቅና ለሰላም እጁ የማይዘረጋ ህልዉናዉን በግጭት አዙሪት የመሰረት እና በደም የጨቀየ ቡድን ዛሬም በአማራ ህዝብ ላይ የጥፋት በትሩን አንስቶ በሰሜን ጎንደር አድርቃይ ወረዳ አሊጣራ ቀበሌ አንካቶ በተባዉ ጎጥ ከ15 በላይ ንጹሀንን ጨፍጭፏል፤ ህጻናትንም ሳይቀር ገድሏል። በአካባቢው የሚኖሩ ዜጎችን በማፈናቀል የለመደ የዝርፊያ ተግባሩን ፈጽሟል።
በራያ በኩል ከሰሞኑ በፈጸመዉ ወረራም ንጹሀንን ገድሏል የተለያዩ ግለሰቦችን አግቶ ወስዷል። ከታገቱት መካከልም ግንቦት 30/2016 ዓ.ም ሌሊት በራያ አላማጣ ወረዳ የወደፊት አበበ ቀበሌ ነዋሪዎች
1ኛ. ዝናቡ ዳድኤ
2ኛ. ሃፍቱ ባራንቶ
3ኛ. ሰይድ ዋዩ ይገኙበታል።
በዚሁ አካባቢ አሸባሪ ቡድኑ የአማራ የሆነን ሀብትና ንብረት ሁሉ በማዉደም ግብሩ የሆነዉን መደበኛ ተግባሩን ፈጽሟል። ቡድኑ በራያ እና አካባቢዉ ከዚህ በፊት በፈጸመዉ ወረራ የአርሶአደሩን ከብቶች አርዶ እየበላ የተረፉትን የአማራ ሀብትና ንብረት ስለሆኑ ብቻ የጥላቻ አይኑ እንስሳት መሆናቸዉን ከልሎት አማራ መስለዉና ሁነዉ እንዲታዩት ስላደረገዉ በጥይት ደብድቦ በመግደል የፈጸመዉን ግፍ ነዉ እየደገመዉ የሚገኘዉ።
የአማራ ህዝብ በትህነግ ይሄን ሁሉ ግፍና መከራ እየተቀበለ ያለዉ ለሰላም፣ ለእርቅ፣ ለአብሮነት እና ለሀገራዊ አንድነት ካለዉ ቀናኢ ተፈጥሯዊ ስሪት መሆኑ የማይካድ ሀቅ ነዉ።
ነገር ግን የአማራ ህዝብ ግፍ አንገሽግሾት መከራ እንደ እሬት መሮት በቃኝ ብሎ የተነሳ እለት ክንዱን ከትህነግ በላይ የሚያዉቅም የሚመሰክርም የለም።
ሽሬ ውስጥ የነበረው የትናንቱ ሆይሆይታ ተራ "ጓይላ" መስሎኝ ነበር።
አሁን አስታወስኩት ---- ለግንቦት 30 ቀጥራችሁን ነበር ለካ !!
እንደተረዳነው ከሆነ ግን የያዛችሁት በጣም ትንሽ ነው። የሚበቃንን ያህል አልያዛችሁልንም ¡¡😎
የተበተነው ዱቄት.....😂
The "pronounced dead TPLF" discovered to be still breathing at funeral home !
Miraculous 😎
እስኪ ....Goodnight !
ለዚህ አጭር ተንቀሳቃሽ ምስል Caption (ርዕስ)ስጡት ብትባሉስ?
ለምሳሌ 👇
"ህዝብና በህዝብ ዘንድ ተቀባይነትን ያገኘ መንግስት "
እስኪ.......Goodnight !
በግንቦት 20 ዋዜማ ላይ የወያኔ የምክክር አጀንዳ የነበረው 👇
"Tigray - post Abiy and Isayas"
( "ከኢሳያስና ከአቢይ በኋላ ስለምትኖረው ትግራይ)
========
"ጠላቶቻችን በጭንቅ ውስጥ ናቸው ፤ ምንም የላቸውም"ም ተብሏል !
😎
//"የአለማቀፉን ፍርድቤት (ICC) ያቋቋምነው እኮ ለአፍሪካውያን እና እንደ ፑቲን ላሉ ጠላቶቻችን ነው" ሲል አንድ የአሜሪካ ከፍተኛ ባለስልጣን ተናግሮኛል//
-ICC's Chief prosecutor kharim khan with CNN
"ከጠለምት አማራ የሚሰረቅ ማንነት የለም"
(ከጠለምት አማራ ማንነትና ወሰን አስመላሽ ኮሚቴ
በወቅታዊ ጉዳይ ላይ የተሰጠ መግለጫ)
የጠለምት አማራ ማንነትና ወሰን አስመላሽ ኮሚቴ እና ኮሚቴው የወከለው መላ ሕዝቡ ለሰላም ካለን ጉጉት የተነሳ ነጻ ያልወጡ የምስራቅ ጠለምት ሦስት ቀበሌዎች እና ግማሽ የአንድ ቀበሌ ቦታ ማለትም፡- ‹ደገብራይ›፣ ‹ሜዳ›፣ ‹ሀምሾምድር› እና ‹ጥርሰጌ› የተባሉት ቀበሌዎች እንዳሉ እያወቅን፤ ግጭት የማቆም ስምምነት አካል የሆነውን የፕሪቶሪያ ስምምነት በማክበር ለሰላም የምንችለውን ዋጋ ሁሉ ስንከፍል መቆየታችን ይታወቃል፡፡ አሁንም ለሰላም መከፈል ያለበትን ዋጋ ለመክፈል ዝግጁዎች ነን፡፡ ይሁን እንጂ በትሕነግ በኩል ያሉ በሕግና በመርህ፣ በስምምነትና በግልግል ዳኝነት ያለመገዛት ፍላጎቶች በእኛ በኩል ለሰላም የሰጠነውን ከፍ ያለቦታ ዋጋ የሚያሳጣ ሆኖ ይታያል፡፡
የፕሪቶሪያ ስምምነት በግልጽ በወረቀት ከሰፈሩ የስምምነቱ ፍሬ ነገሮች ውጭ በሆነ መንገድ በትሕነግ በኩል ትርጉምና ማብራሪያ ሲሰጥበት፣ ጉዳዩ የሚመለከተው የፌዴራል መንግሥቱ ይህ ነው የሚባል እርምት እርምጃም ሆነ ማስተባበያ ሲሰጥ አላየንም፡፡ ይህ ሁኔታ በትሕነግ በኩል እያደገ ሂዶ ራያን በኃይል በመውረር የፕሪቶሪያውን ስምምነት በግልጽ ጥሶታል፡፡
በፕሪቶሪያው ስምምነት መሠረት የተቀመጡትን ከእሱ የሚጠበቁ ኃላፊነቶችና ግዴታዎች ተግባራዊ ሳያደርግ ማለትም፡- ድርጅቱ የሰላም ስምምነቱን ከምር ተቀብሎ ትጥቅ ሳይፈታ፣ ያደራጀውን ሠራዊት ሳይሸኝ፤ ቀጠናውንም ወደተሟላ ሰላም ሳይመልስ ኢትዮጵያን ሲወጋ በከረመበት ትጥቅ፣ አደራጅቶ ሰሜን ዕዝን በወጋበትና ከስምምነቱ በኋላም አደራጅቶ ባስቀጠለው ታጣቂ ኃይሉ አማካይነት ለአራተኛ ዙር በኃይል ራያን በመውረር የፕሪቶሪያውን ስምምነት ገደል ከቶታል፡፡
ትሕነግ ይህን ያደረገው ችግሮችን በሰላም ከመፍታት ይልቅ በጉልበት የመፍታት ፍላጎት ስላለው ነው፡፡ በዚህ ድርጊቱ ይህ ነው የሚባል ተቃውሞም ሆነ አጸፋዊ ምላሽ ያልተሰጠው በመሆኑ ተመሳሳይ ወረራ በጠለምት እና በወልቃይት-ጠገዴ አካባቢው እያሰበ ይገኛል፡፡
በወታደራዊ እንቅስቃሴዎቹም ሆነ በኃላፊነት ደረጃ በተቀመጡ መሪዎቹ በኩል ቀጣይ አቅጣጫውን ከወዲሁ እያሳየ ነው፡፡ እኛ የጠለምት አማራዎች ይህንን ሁኔታ በማየት ሕዝባችን ራሱን የመከላከል ተፈጥሯዊ መብቱን እንዲጠቀም ጥሪ ለማቅረብ እንገደዳለን፡፡
በተጨባጭ እንደሚታየውም በትሕነግ በኩል አሁንም ጠባጫሪነቱ አልተገደበም፡፡ በምስራቅ ጠለምት በኩል የሚያደርጋቸው እንቅስቃሴዎችን በልዩ ትኩረት ለማየት እንገደዳለን፡፡
ከመነሻው ትሕነግ ፕሪቶሪያ ላይ ከፈረመው ባለ 15 አንቀፅ ሰነድ ውስጥ ሙሉ ለሙሉ ትጥቅ እንደሚፈታና ተዋጊዎቹ በሙሉ ወደ ተሃድሶ (ማሰልጠኛ) ካምፕ እንደሚገቡ፦ በአንቀፅ 6 ላይ “Disarmament, Demobilization, and Reintegration (DDR)” ተብሎ የሰፈረው ክፍል በግልፅ ሳይተገበር፤ እንዲሁም በፕሪቶሪያው ስምምነት ከፀጥታና ደህንነት ጉዳዮች ጋር በተያያዘ የመተማመን መልሶ ግንባታን በተመለከተ በአንቀፅ 7 ላይ ስለ ‹Confidence-building measures› በግልፅ የተደነገጉ የስምምነቱ ፍሬነገሮች ወደተግባር ሳይቀየሩ ሁኔታዎች ወደኋላ ከመጎተት አልፈው ግልጽ የስምምነት ጥሰት ተፈጥሯል፤ በዚህም ሁኔታዎች ሌላ መልክ ይዘዋል፡፡
በተመሳሳይ ሁኔታ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ መስተዳድር የሆኑት ም/አስተዳዳሪ ሌ/ጀኔራል ታደሰ ወረደ ከሰሞኑ በሰጡት መግለጫ የፌዴራል መንግሥትና የሀገር መከላከያ ሰራዊት የፕሪቶርያው ስምምነት በአግባቡ እየተፈፀመ አይደለም ሲሉ ለዘለፋ የቀረበ ትችት ሰንዝረዋል፡፡ ራሱ የጣሰውን ስምምነት ሌሎች እንዲያከብሩለት የሚፈለገው ይህ ኃይል ቀውስ ጠማቂነቱን፤ ግጭት አምራችነቱን ቀጥሏል፡፡
ይህ ሁኔታ ለሰላም ብዙ ዋጋ እንደከፈለ የጠለምት አማራ እጅግ አሳዝኖናል፤ አሳስቦናል፡፡
በመሆኑም፡-
የጠለምት አማራ ማንነትና ወሰን አስመላሽ ኮሚቴ አሁንም በሕግ የበላይነት የሚያምን፣ ለሰላም ትልቅ ቦታ የሚሰጥ በመሆኑ ጥያቄዎችን የኢፌዴሪ ህገ የመንግሥት በአንቀጽ ቁጥር 48 የአከላለል ለውጦችን በሚመለከት የፌደሬሽን ምክር ቤት “የሕዝብ አሰፋፈር እና ፍላጎትን መሰረት” በማድረግ እንዲወሰን ሕገ-መንግሥታዊ ስልጣን በሚሰጠው መሰረት፣ ይህንኑ ጥያቄም “ከሁለት አመት ባልበለጥ ጊዜ ውስጥ የፌደረሽን ምክርቤት የመጨረሻ ውሳኔ ይሰጥበታል።” በማለት በግልፅ የሚደነግግ በመሆኑ የቀረበው ጥያቄ ምላሽ ሳያገኝ ዓመታት ስለተቆጠሩ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ጥያቄችንን መሰረት በማድረግ በታሪካዊ ዳራው መሰረት እንዲወሰንልን ስንል በድጋሚ እንጠይቃለን!!
የአማራ ክልል መንግሥት በወሰንና ማንነት ጉዳዮች ዙሪያ የትግሉ ባለቤት በመሆኑ፤ በቀጣይም ትግሉን በሙሉ ባለቤትነት አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪያችንን ስናቀርብ ክልሉ የገጠመው ውስብስብ ችግር አንዱና ዋነኛው ፍትሐዊው የአማራ ሕዝብ ጥያቄዎች አለመመለስ መሆኑን በማስታወስ ነው፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ በቀጣይም ከጸረ-ወራራ ትግሉ አኳያ በቀደመ አቋሙ ጸንቶ እንዲቀጥል ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡
ትሕነግ አሁንም በራያ ያካሄደውን የጦር ወረራ በጠለምት፣ እንዲሁም በወልቃይት-ጠገዴ ለመድገም የቀየሰው ስልት፡- ከፊት ተፈናቃይ የሚለው አካል በማስቀደም በግራና በቀኝ የራሱ “የትግራይ ፀጥታ ኃይል" ብሎ እያሰለጠነና እያደራጀ፤ የተደራጁ ኃይሎቹን ለማስገባት ሙሉ ዝግጅት ላይ ነው። የፌዴራል መንግሥትም በዚህ ላይ የተለሳለሰ አቋም እያሳየ በመሆኑ ህዝብ እያስቆጣ ይገኛል። ሕዝባችንም የራሱን ተፈጥሯዊ የመከላከል መብቱን ለመጠቀም የሚገደድ በመሆኑ ራሱን ለሁንተናዊ ትግል እንዲያዘጋጅ እናደርጋለን!!
የጠለምት፣ ራያና ወልቃይት-ጠገዴ የአማራ ማንነትና ወሰን በዘላቂነት እንዲጸና ስትታገል የቆየህው መላው የአማራ ሕዝብና ዲያስፖራ ወገናችን በሙሉ፡- ወራሪውና ዘራፊው የትሕነግ ቡድን የሚያደርገውን የትግራይ ሪፐብሊክ ምስረታ እንቅስቃሴ ላይ መሆኑን በመገንዘብ ይህን የጥፋት ዓላማውን ለማምከን በሚደረገው ትግል ተሳትፏችሁን አጠናክራችሁ እንድትቀጥሉ ታሪካዊ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡
የአማራ ሕዝብ ለዘመናት ሲታገልላቸው የኖሩ ሦስቱም የአማራ ታሪካዊ ርስቶች ማለትም ጠለምት፣ ራያ እና ወልቃይት-ጠገዴ ከማንነትና ከርስት ባሻገር ቁልፍ አገራዊ የህልውና ጉዳዮች ናቸው፡፡ እነዚህ አካባቢዎች በትሕነግ እጅ ዳግም ከወደቁ ድርጅቱ ለረዥም ዓመታት ሲሰራበት የቆየውን የመገንጠል አጀንዳውን እውን እንደሚያደርገው ታውቆ እነዚህ ግዛቶች የኢትዮጵያ ሀገረ-መንግሥት ህልውና ቁልፍ ጉዳዩች ሆነው መታየት እንዳለባቸው፣ የኢትዮጵያን አንድነት የሚወዱ ወገኖች ሁሉ የትግላችን አጋር እንዲሆኑ ለመላው አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡
ባለፉት ሦስት ዓመታት የካፒታልና የመደበኛ በጀት ክልከላ ተደርጎብን፤ በበጀት ክልከላ የሚጣል ማንነት እንደሌለን በጽናት ቆመን አሳይተናል፡፡ ለአማራ ማንነታችን ከዚህ በላይም ዋጋ ለመክፈል ዝግጁ ነን፡፡