በዛሬው የቃብቲያ ሆስፒታል የምረቃ ስነስርዓት ላይ በአብክመ የወልቃይት ጠገዴ ሰ/ሁመራ ዞን ዋና አስተዳዳሪ የአቶ አሸተ ደምለው ንግግር ሙሉ ቃል
-------
የተከበሩ ዶክተር መንገሻ ፈንታው የአብክመ መንግስት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ሀላፊና የክብር እንግዳ
የተከበሩ አቶ አብዱከሪም መንግስቱ---የአብክመ ጤና ቢሮ ሃላፊ
የተከበሩ አቶ ገብረእግዚብሔር ደሴ----የዞኑ ብልጽግና ፓርቲ ሃላፊ
የተከበሩ ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ---የወልቃይት ጠገዴ አማራ የማንነትና ወሰን ኮሚቴ ሰብሳቢ እና የዞኑ ምክትል አስተዳዳሪና ፀጥታ መምሪያ ሀላፊ
የተከበሩ ሜ/ጀነራል ሰለሞን ቦጋለ----ከፍተኛ መኮነን
የተከበሩ ብ/ጀነራል ወርቅነህ ጉዴታ---503ኛ ኮር አዛዥ
የተከበራችሁ የዞን አመራሮች በሙሉ
የተከበራችሁ የወረዳናከተማ አመራሮች ሙሉ
የተከበራችሁ የሃይማኖት አባቶች፣ሃገር ሽማግሌዎች፣ወጣቶችና ሴቶች
የተከበራችሁ የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን አልሚ ባለሃብቶች
የተከበራችሁ ዲያስፖራዎች
የተከበራችሁ የቃብትያ ከተማ ነዋሪዎችና ቀበሌ አመራሮች፣ የልማት ኮሚቴዎች
ጥሪ የተደረገላችሁ እንግዶቻችን በሙሉ
ክቡራንና ክቡራት!
ከምንም በላይ የለውጡ ጊዜ ከተበሰረበት ጀምሮ ትርጉም ያለው የሕይወት መስዋዕትነት በመክፈል የኢትዮጵያን ሀገረ-መንግሥት ከመፍረስ ለታደጉና ይህንን የነጻነት አየር እንድንተነፍስ ላበቁን የህልውና ትግሉ ሰማዕታት “ስለኢትዮጵያ የከፈላችሁትን አንረሳውም” በሚል መሪ ሀሳብ፣ የአንድ ደቂቃ የህሊና ጸሎት እንድናደርግ በአክብሮት እጠይቃለሁ!
-----------------------------------//----------------------------
አመሰግናለሁ!
ከሁሉም አስቀድሜ በወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ከደረሰው ዘርን መሰረት ያደረገ እልቂት በተጨማሪ በወሳኝ የማኀበራዊ መሰረተ ልማቶች ርቀውና ባይተዋር ተደርገው የነበሩት ወረዳዎች በባለቤታቸው እጅ ከገቡበት ጊዜ ጀምሮ፣ በየደረጃው ባለው አመራር አስተባባሪነት፣ በህዝቡና ዲያስፖራው ቀናኢ ተሳትፎና ደጋፊነት በርካታ መሰረተ ልማቶች ተገንብተው ለሕዝብ ምርቃት መብቃት ችለዋል፡፡
እነዚህ መሰረተ ልማቶች የይቻላል መንፈስ ያሰፈኑ፣ የአይቻልም አስተሳሰብ የሰበሩ ራስ በቅነት የታየባቸው በመሆኑ እንኳን ደስ አላችሁ! እንኳን ደስ አለን!!
በእነዚህ መሰረተ ልማቶች የሕዝባችንን የልማት ተሳትፎ ፍላጎት አይተንበታል፡፡ የአመራሩን አስቦ መምራት መዝነንበታል፤ የዲያስፖራችንን ቁጭት በተግባር አስተውለናል፡፡
ከእልህ፣ ቁጭትና ወኔ የተነሱ፡- ቅን ልቦች፣ በጎ አድራጊዎች፣ ለሥራ የሚተጉ ክንዶች፣ ዛሬ ለቆምንበት የምረቃ ዕለት አብቅተውናል፡፡
ይህ ወዳኋላ የማንመለስበት ወደፊት የምንስፈነጠርበት አርቆ የማየት፣ አልቆ የመስራት ጊዜ ነው፡፡ ጊዜው የትግልም፣ የሥራም ነው፡፡ ትግላችንም ሥራችንም የዛሬ ሳይሆን የነገውን ትውልድ መሠረት ያደረገ ነው፡
በዛሬው ቀን በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን አስተዳደርና ሕዝብ “በአንድ እጅ ነጻነት፣ በሌላው እጅ ልማትን ማረጋገጥ እንደሚቻል ትርክት ሥራን፣ ሥራ ትርክትን እንደ ሚቀይር ይህ ምድር አብነት ሆኗል” በድጋሚ እንኳን ደስ አላችሁ ደስ አለን!!
የማይዝሉ ክንዶችን የትጋት ውጤት ልንመርቅ ስንገናኝ ስለ እነዚያ ክንዶች ማንነት ውቅያኖስን በጭልፋ ቢሆንም ይህን ማስታወስ ተገቢ ነው!!
እነዚያ ብርቱ ክንዶች ሳይዝሉ ኖረዋል፣ እነዚያ ጀግኖች ከልባቸው ላይ እንደታጠቁ ዘመናትን ተሻግረዋል፣ እነዚያ ልበ ሙሉዎች የመከራውን ዳገት አልፈዋል፣ እነዚያ የበረሃ መብረቆች፣ አይደፈሬ አንበሶች ለእውነት ኖረዋል፣ በእውነት ታግለዋል፣ ስለእውነት ፀንተዋል፡፡ የጨለማውን ዘመን በፅናት እና በጀግንነት አልፈዋል፡፡ የሰቆቃውን ማዕበል በብርታት ተሻግረዋል፣ ጣልናቸው ያላቸውን ጠላት በፍትሐዊ ትግል ጥለውታል። ቀበርናቸው ያሉትን ግፈኞች ለታሪክ በሚበቃ መልኩ አስተምረዋቸዋል፡፡ እነዚያ ብርቱ ክንዶች የሚሰሩም፤ የሚታገሉም ናቸው፡፡ እነዚህ ክንዶች ለፍትሐዊ ትግሉ እንደማይዝሉ ሁሉ፤ ለፍቅርም ይዘረጋሉ፡፡
የራሳቸውን አሳልፈው አይሰጡም፤ የሌላውንም አልፈው አይጠይቁም፤ የሰው አይወስዱም፡፡ ለክብር ይሞታሉ፣ ታሪክ ለመስራት ሁሌም ዝግጁ ናቸው፡፡ ትርጉም ያለው መስዋዕትነት መክፈል የታሪካቸው አምድ ነው፡፡ ለነጻነት ሞትን የናቁ ክንዶች ዛሬም ሥራ ላይ ናቸው፡፡
በአባታቸው ባድማ በኩራትና በክብር ይኖራሉ፣ ሁሉንም የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች ያከብራሉ፤ በጀግንነት እና በልበ ሙሉነት ይመላለሳሉ፡፡ ከአባት ባድማ የሚገፋቸው፣ ተወልደው ካደጉበት፣ ታሪክና ሃይማኖት፣ የፀና ቃልኪዳን ከተቀበሉበት ሥፍራ የሚነካካቸው በመጣ ጊዜ ይቆጣሉ፡፡ ለፍቅር የተዘረጉ ክንዶች ለፍትሐዊ ትግል ይነሳሉ፡፡
ኢትዮጵያ ዘመናዊ ሰራዊት ባላደራጀችበት ጊዜ ዳር ደንበር ጠባቂ ነበር፤ በፋሽስት ጣሊያን ስትወረር ነፍጥ አንጋች አርበኛነቱን በአምስት አመቱ ወረራ ተጋድሎ አስመስክሯል፡፡
እኛ የወልቃይት ጠገዴ አማራዎች ለፋሽስት ጣሊያን ያልተንበረከኩት የእነ ደጃዝማች አዳነ መኮነን፣ የፊታውራሪ ኃይሉ ፋሪስ፣ የቀኛ ዝማች ዓባይ ወ/ማርያም፣ የቀኛዝማች መስፍን ረዳ፣ የቀኛዝማች ገብሩ ገ/መስቀል ልጆች ነነ፡፡
እነዚህ ለአብነት የተጠቀሱ አርበኞች ፋሽስት ጣሊያንን ከአፈር የቀላቀሉ፣ እትብታቸው እዚሁ መሬት ላይ የተቀበረ የእኛው አባቶች ናቸው፡፡ የአርበኝነት ታሪክ ሥነ-ልቦናዊ ውርስ ነውና የእነሱ ልጆች ለአማራነታችንም ሆነ ለኢትዮጵያዊ ማንነታችን፣ ለነጻነታችን፣ ለክብራችን የማንከፍለው ዋጋ የለም፡፡
በቀደሙት አርበኞቻችን ስም የትግል ቃል ኪዳኑን ያደሰው ጀግናው የወልቃይት ጠገዴ ሕዝብ አርበኝነት ውርሱ፤ በጎ ታሪክ ትርፉ ነውና በተራዘመ መስዋዕትነት ትሕነግ ለሦስት አስርት ዓመታት ከዘረጋው አፓርታይዳዊ አገዛዝ ትርጉም በሚሰጥ መስዋዕትነት ነጻ ወጥቷል፡፡ ሕዝባችን ያለፈበት የሰቆቃ ታሪክ ግን መቼውንም ቢሆን የሚረሳ አይደለም፡፡ ያለፈውን ይቅር ብንል እንኳ የሆነብንን ፈፅሞ አንዘነጋም!!
ጠላቶቻችን በሕዝባችን ላይ መከራ አብዝተው፣ ማንነቱን ወንጀል አድርገው የአባት የእናት፣ የአያት ቅድመ አያት ርሰቱን ነጥቀው፣ ከሞት የከፋ በደል ቢፈጽሙበትም ሽንፈትን የማይቀበለው ሕዝባችን በፅናት ታግሎ ፍትሐዊ ትግሉ እዚህ ታሪካዊ ምዕራፍ አድርሶታል፡፡
ጀግና በመከራ ይጠነክራል እንጂ በመከራ አንደማይዝል የጀግናው የወልቃይት ጠገዴ ሕዝብ ገድለ-ታሪክ ጉልህ ማሳያ ነው፡፡
ክቡራት እና ክቡራን…!
ዛሬ በጀት የማይበግረው፤ ለፍትሐዊ ትግል የታመነ ማኀበረሰብ መገንባት የተቻለው፤ አመራሩ እና ሕዝቡ እንደ አንድ ልብ መካሪ፤ እንደ አንድ ቃል ነጋሪ መሆን በመቻላቸው ነው፡፡ ዛሬ በዓይን ጥቅሻ መግባባት የሚችል ምሽግም ሆነ የእርሻ ካምፕ ላይ ውሎ ሲያድር ዓላማን የሚያስቀድም ለነጻነቱ ሞትን የናቀ ሁለገብ አርበኛና ሕዝባዊ ኃይል በመገንባት ላይ እንገኛለን፡፡
ኢትዮጵያዊ ማንነት ትህትናና ጀግንነት ነው እንዲሉ አባቶቻችን ትግሉ አስተዋይነትን፣ አርቆ አሳቢነትን እና ትዕግሥትን ይጠይቅ ነበር፡፡
የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ሕዝብ የገፋውን ጥሎ፣ የተጫነውን አሽቀንጥሮ ተወልዶ ባደገበት፣ ታሪክና ቃል ኪዳን በተቀበለበት ሥፍራ ልማት ላይ ነው፡፡ ከልማትም አለው ዓይነት፡፡ ለጤናማ ትውልድ ግንባታ ትልቅ መሠረት በሚጥለው የትምህርትና ጤና መስክ ላይ ትኩረት ተደርጎ እየተሰራ ነው፡፡
"የቻርተር አውሮፕላኑን ወጪ የሸፈነልን ማማይ ምህረቴ ነው"
- የትግራይ ልዑካን
ከድራማ ወደ አክሽን
የደብረፂዮን አንጃ የቀን ተቀን ስራዎቼን ከማደናቀፍ አልፎ አሁን ላይ ግልፅ ወደሆነ የመንግስት ግልበጣ እንቅስቃሴ ውስጥ ገብቷል//
--ከዛሬው የትግራይ ክልል ፕሬዚዳንት ፅ/ቤት መግለጫ ላይ የተወሰደ
እስክትገባለት ድረስ ራሱን ደብቆ ያሽቃብጥልሃል። ማራዘሚያው አጥሮ የደበቀውንና የውስጡን የሚያናጋበት ጊዜ ላይ የደረሰ ሲመስለው መለመላውን ተገላልጦ ይመጣብሃል !!
ፖለታካውም . ኢኮኖሚውም... ዲፕሎማሲውም ...ተቃዋሚውም .ሚዲያውም ሁሉም ይሄንን 👆 "መሳይ" ናቸው ።
( አይ እንግዲህ....ካልተዋጠልኝና ካልመሰለኝ 'ጨርሼ' ነው የምናገረው.. እቀጥላለሁም )
የታፔላ ጨዋታ
ዛሬ ደግሞ በታፔላ ተመጣ ?
Messay Mekonnen ይቺን ጨዋታ ደጋገምካትሳ ? ወሬዋን ከዘራሃት ቀን ጀምሮ እስከዛሬ ድረስ ጭዌዋን ለማጣራት ጥረሃል ? እንዲሁ እያስኬድካት እንደሆነ ነው የተረዳሁህ።ለምን አላማ ?
እርግጥ ነው የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ የማንነትና የነፃነት ጥያቄ ምኑም እንደማይመችህ ካወቅኩኝ ቆይቻለሁ።
ይህ የህዝብ ጥያቄ እኮ አንተ ሁሌም ከምትቀሰቅሰው የ"በአንድ ኢትዮጵያዊነት ጥላ ስር" እሳቤ ጋር እንዴት እንደሚጋጭ አይገባኝም።ከቻልክ አስረዳኝ።አያያዝህን ሳየው ግን ከዛም የዘለለ አላማን የሰነቅክ ያስመስልብሃል።
አቶ ቻላቸው አባይ ስለ ታፔላው ወሬ እንደማያውቁ ተናግረዋል።አለማወቃቸው የሚያያስወቅሳቸው አይደለም።ሚዛን ለመጠበቅ ሞክረዋል።ማጣራት ግን ይችሉ ነበር ።ምክንያቱም እንደተባለው ሳይሆን በቦታው ያለነው እኛ ነን !አቶ ቻላቸው ከእኔ መስማት ይችሉ ነበር።ስልኬም አላቸው።
መሳይም ብትሆን እኛን ማግኘት አልፈለክ ካልሆነ በቀር ልታገኘን ትችል ነበር ።
ለማንኛውም ግን ሚዲያውን ከጊዜ ማሳለፊያነት አውጣና ወደ ሚዲያነት ውሰደው።በታፔላና በገለመሌ ወሬ አትሙላው።
ባጭሩ የታፔላው ቀደዳ አይነፋም ! ውሸት ነው‼️
ሰማዕታትን እንዘክር ጥቅምት 30 /2013 ዓ.ም በማይካድራ ከተማ የጭካኔ ጥግ የታየበት እለት።
ሁመራ፦ጥቅምት 30/2017 ዓ.ም በአማራ ክልል ወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን በማይካድራ ከተማ ጥቅምት 30/ 2013 ዓ.ም በዘረኝነት በአፍቅሮተ ንዋይና አፍቅሮተ ስልጣን የተለከፉ የህውሀት ቡድን አባላት ጭካኔ በይፋ የታየበት ወቅት ነው ።
ለዓመታት በማስመሰያ ጭንብል ተሸፍኖ የቆየው የህውሃት እውነተኛ ባህሪ የዛሬ አራት ዓመት በጥቅምት ወር በማይካድራ ከተማ አደባባይ ላይ ወጣ።ሀውዜን ላይ የታየው የግፍ ጭፍጨፋ ሲያወግዝ የቆየው ሌላ ሀውዜን ማይካድራ ከተማ ውስጥ በይፋ ታየ።
ጥቅምት 30 የግፍ ደም የፈሰሰባት፣ የመከራ ድምጽ የተሰማባት፣ እናቶች አብዝተው ያለቀሱባት፣ ሕጻናት በዋይታ የተመሉባት፣ የጭካኔ ጥግ የታየባት፣ ያጎረሱ እጆች የተነከሱባት፣ ያለበሱ የተሰቃዩባት ምድር ማይካድራ 1ሺህ 563 ንፁሀን ተሰውባት፡፡
ደጎቹ ያለ ሐጥያታቸው ተቀጡባት፣ እንግዳ ተቀባዮቹ ያለ በደላቸው የግፍ ጽዋ ተቀበሉባት፤ ተበዳይ ኾነው ሳለ እንደ በዳይ የተቆጠሩባት፣ ደግ አድራጊዎች ኾነው ሳለ እንደ ክፉ አድራጊ የታዩባት ቀን ጥቅምት 30 ፡፡ እናት የአብራኳን ክፋዮች አጣች፤ ጧሪና ቀባሪዋን በግፍ ተነጠቀች፤ ልጆች ወላጆቻቸውን ተነጠቁ፤ በሞት ጥላ ሥር ተከበው ተጨነቁ፤ ምድሯ በደም ጎርፍ ፣ተጥለቀለቀች ፣በጣረሞት ድምጽ ተመላች፣ በሬሳ ብዛት ተጨናነቀች፣ አዳኝ እና ከልካይ በሌላቸው ንጹሐን ዋይታ ተናወጸች፣ጎዳናዎች በደም ታጠቡ፣ ለአስከሬን ማሳረፊያ ጠበቡ፡፡
ዘር ጠፋባት፤ ማንነት እየተጠየቀ የግፍ ግፍ ተፈጸመባት፤ የጭካኔ የመጨረሻው ጥግ ታየባት፡፡ ከሞታቸው አሟሟታቸው ያስጨንቃል፤ ከሞታቸው አገዳደላቸው ያሰቅቃል፡፡ ለምን ቢሊ አሰቃይተው ገድለዋቸዋል፤ ስቃያቸውን አብዝተው ነብሳቸውን ከስጋቸው ተለይተዋልና፡፡
"ሳምሪ" የተሰኜው ገዳይ ሰራዊት በሰላማዊ እናቶች፣አባቶች፣ወጣቶችና ህጻናት ላይ ብሄር ተኮር የግፍ ጭፍጨፋ አደረገ።በበርሀ ሲሰሩ የነበሩ የቀን ሰራተኞችን ሳይቀር ሰብስቦ በገጀራ አረደ።እናቶችና ህጻናት እያዩ አባቶቻቸውን በጥይት ግንባርና ደረታቸውን እየመታ ጣለ። በመቶዎች የሚቆጠሩ ልጆች ያለ ውላጅ ፤ ሴቶቹ ደግሞ ያለ ባል ቀሩ ። እናቶችም የልጆቻቸውን አስከሬን እንደ በግ ታርደው ወድቀው እያዩ የደም እንባ አፈሰሱ ።
ወያኔ ከራሱ አባላት ውጭ ሌላ ሰው ኢትዮጲያ ውስጥ መኖሩ አይታየው ፤በህውሃት ጎጠኞች እሳቤ መሰረት የአማራ ክልል ተወላጅ ማህበረሰብ ሰዎች አይደሉም፤ስለሆነም ያለ አንዳች ምክንያት በግፍ ተገደሉ።
ጥቅምር 30 /2013 ሰማዕታትን የምናነሳቸው በጥልቅ ሀዘን ብቻ ሳይሆን በቁጭትና እልህም ጭምር ነው።ወገኖቻችን እንደሰው ሳይቆጠሩ ተገደሉ፤ለኛ ግን ወገኖቻችን ሰው ብቻ ሳይሆኑ ሰማዕትም ጭምር ስለሆኑብን ሙት አመታቸውን በማክበር በየአመቱ ስንዘክራቸው እንኖራለን።
ሰማዕታት ወገኖቻችን የህይወት ዋጋ ከፍለው ዘረኝነት የማስወገድ ሸክም እኛ ላይ ጥለዋል።
ዘላለማዊ ክብር ለሰማእቶቻችን!`
Wolkayt tegedie setit humera zone communication
ማይካድራና ጥቅምት 30 ሲዘከሩ...
ብዙዎች አካላቸው ጎድሏል፣ እግራቸውን የተቆረጡ፣ እጆቻቸውን በገጀራ የተቀሙ በርካቶች ናቸው ።ገዳዮቹም በግፍ የገደሏቸውን በአንድ ጉድጓድ በጅምላ ቀበሯቸው፡፡ በጀምላ ተገድለው በጅምላ አፈር ተመለሰባቸው፡፡ አፈር ያልመለሱባቸውን ደግሞ የአራዊት ምሳና እራት ሆኑ፡፡ ጥቅምት 30 ለማይካድራ ጥቁር ቀን ናት፡፡ በዚህች ቀን ብዙዎች የጅምላ ጭፍጨፋውን በብሌናቸው ተመልክተዋል፡፡ የጅምላ መቃብሩንም አይተዋል፡፡ ወገኖቻቸውን በግፍ አጥተው ብቻቸውን የቀሩ ወገኖችም በግራ መጋባትና በሃዘን ተደቁሰውና ዝለው አይኖቻቸውን እያቅበዘበዙ ታይተዋል፡፡ያ ሁሉ መከራ አልፎ ማይካድራ ነጻነቷን ካገኘች ዛሬ ድፍን 4 ዓመትን አስቆጠረች፡፡ የግፍ ቀንበሯን አሽቀንጥራም ጣለች፡፡ አሁን በራሷ ልጆች እየተዳደረች፤ ማንነቷ ተከብሮ እየኖረች ትገኛለች፡፡ ከዚያች የከፋች ቀን ተርፈው ታሪክ ለመንገር፣ የደረሰውን ግፍ ለመመስከር የበቁ ሁሉ በግፍ የተገደሉት፣ በጅምላ የተቀበሩትን እያስታወሱ ቀኗን ያስቧታል፡፡ ዳግም እንዳትደገም፣ ገዳዮች እና ከሃዲዎች ምድሯን እንዳይረግጧት ቃል ኪዳን በመግባት ያከብሯታል፡፡ ለማንነት የተከፈለውን ዋጋ እያሰቡ፤ ሲያምኑ የተካዱበትን ጊዜ እያንሰላሰሉ ይዘክሯታል፡፡ ገዳዮችን የቀጡላቸውን፣ ከሞት መንጋጋ ያወጧቸውን ጀግኖች እያስታወሱ ያከብሯታል፡፡
-------
ማይካድራ - የግፍ ደም የፈሰሰባት፤ የዘር ማጥፋት ወንጀል የተፈጸመባት፤ ዋይታና መከራ አይሎ የታየባት ነበረች - አሁን በእፎይታ ያለች ምድር ነች‼️
(We won't forget , we remember !)
የስብሰባ ጥሪ
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ከወልቃይት ጠገዴ ሰ/ሁመራ ዞን ንግድና ገበያ መምሪያ የተላለፈ የስብሰባ ጥሪ ነው።
ጥሪው በቅባት እህልና ጥራጥሬ አቅራቢና ላኪነት የተሰማራችሁ ነጋዴዎችን ይመለከታል !
.....
የስብሰባው ...
ቦታ -ሰ/ሁመራ ማዘጋጃ ቤት አዳራሽ
ቀን - 3/03/2017 ዓ.ም
ሰዓት - ከጧት 2:00 ጀምሮ
ጉድ በል ጎንደር ...
ያ ነገር ጉድ አፈላ !
የአሜሪካውን የምርጫ ውጤት የተቃወሙ የካማላ ሃሪስ ደጋፊ የነበሩ እንስቶች "የወሲብ እቀባ" አድማን መጥራታቸው ሰማነ !
የዚህ B-4 የተባለው ንቅናቄ አባል የሆነች አንዲት ሴትዎ ባስተላለፈችው የ "ያ ነገር" እቀባ ጥሪ ላይ "ፍቅረኛሽ ትራምፕን መርጦ ከሆነ ያን ነገር ከልክይው።የትዳር አጋርሽ ከሆነ ደግሞ ያን ነገር መከልከል ብቻም አይደለም - ጭራሽ ፍቺ መፈፀም ነው ያለብሽ" ብላለች።
Liberal women irritated by the American election results are calling for a "sex" strike .
.......Really ? 😎
ቆይ ግን "ያ ነገር" እኮ የጋራ ነበር የሚመስለኝ።
በብዙ ነገር እየተቀደምን ኋላ ቀረን መሰል !
(በነገራችን ላይ ይሄንን የ Redacted News የዩቲዩብ ቻነልን ብትከታተሉት አትከስሩበትም )
ለማንኛውም ግን 400 ማጋጣ ቺኮችን ያጫወተው Engonga, "ይህ ንቅናቄ ጊኒ ሳይገባ ልፍጠን ብሎ" ሳይሆን አይቀርም የ"ያ ነገር" ወልፉን ቀድሞ የከተተው!😂😂
እስኪ....Goodnight !
ወያኔ "ትጥቅ ይፈታሉ" ብሎ ካስመዘገባቸው 75 ሺ ታጣቂዎችና ምንም የማያውቁ 'የዋህ' ሰዎቹ መካከል 10 ሺዎቹ ጭራሽ ከመሳሪያ ጋር የማይተዋወቁ "የዋህ ሰዎቹ" መሆናቸው ስለተባነነ ዝርዝሩ ተመላሽ ሆኖ ሌላ የማይባነን ዝርዝር እንዲያመጣ ታዟል 😂😂
--------------------
ቆይ ግን ወያኔ ስንት ጊዜ እንዲሳሳት ነው በመንግስት የተፈቀደለት ? ነው ወይስ ፈቃጁ ሌላ አካል ነው። ሌላ አዲስ አዛዥ ካልመጣ በስተቀረ እነ ሀመር እንደሆኑ ከዛሬ ጀምሮ ፈ*ስ ሆነዋል ።
አይ የኔ ነገር ....ጭራሽ "ወያኔ እንዲሳሳት ተፈቀደለት" ልበል ? አሃ የምን መደባበቅ ነውሳ? ወያኔማ እንዲያጭበረብር ነው እንጂ የተፈቀደለት !
ቆይ ግን ይሄ ሁሉ እሹሩሩ ለሌላው ተነፍጎ ለአንድ ነቀ**ሳ አጭበርባሪ የተፈቀደለት በምን ውል ነው?
ሆሆ ... ለነገሩ እኮ እኔ በአካል ቆሜ ያየሁትና የማውቀው ውል የለም ። ያው እኩል ታይቼ በእሹሩሩ ያልፉኛል በሚል ቀና እሳቤ አውቆ ባላወቀ እየቀባጠርኩ ነው 😂
ለማንኛውም ግን ...
ከጉምጉምታው ተገንጥሎ ፣
ከኳኳታውም ተነጥሎ ፤
የሚታዘበው እየታዘበ ነው።
እንዳለመታደል ሆኖ ውሎዬ ከእኩያን ጋር ሆነና ስኬትን ለመታዘብ አልታደልኩም - ክፉ ጎሮቤት አይስጥህ 😎
ስንቱን ውሸት ፣ ስንቱን ክፋትና ስንቱን ውድቀት ታዘብነው ?
.....
እስኪ ....Goodnight !
የመጣህበትን መንገድ ሊያስቱህ ከሚንጫጩት ተጠንቀቅ - መንገድህን ተከተል!!
Follow your lead !
እግረ መንገድ ......
እኔ በበኩሌ አጀንዳ እየሰጠሁ አይደለም።የእግረ መንገድ ወሬዬ ነው።
ምናልባት አጀንዳችሁ ሆኖ ከተናጠሳችሁም ያው እንደፍጥርጥራችሁ።👇
===============+=========
በአፍሪካ ህብረት አወያይነት የወያኔን ህጋዊ ሰውነት በመመለስና በሌሎች ፖለቲካዊ ጉዳዮች ዙሪያ በመንግስትና በወያኔ መካከል ይደረጋል የተባለው የሁለትዮሽ ውይይት ለህዳር 2017 ዓ.ም ተቀጥሮ ነበር ። ቀኑ የተቆረጠው ግንቦት ወር ላይ በ2016 ዓ.ም ነው።
ለነገሩ አሁን ወያኔ እርስበርሱ እየተናጠሰ ስለሆነ ይህ ውይይት እውን ይሆናል ብዬ አላምንም።
👉ለማንኛውም ግን ....
የአሜሪካው ምርጫ ተጠናቆ ትራምፕ በተመረጠ ማግስት ውይይቱ እንዲካሄድ በመፈለግ ይሄንን ቀን የመረጠው አካል በእውነቱ ወያኔን ጠንቅቆ የተረዳ ምጡቅ ፖለቲከኛ መሆን አለበት ‼️
😎
https://youtu.be/WI9fbbQ-aTo?si=A29eFHXcg4avJUGz
Читать полностью…
ትናንት በወያኔ ገፅ ላይ ከተለጠፈ ከደቂቃዎች በኋላ በተወገደው መግለጫ ላይ ወያኔ ለፌዴራሉ መንግስት ያስተላለፈው መልዕክት
---------------------
//የህወሓት ህጋዊ እውቅና ባለመመለሱ የፕሪቶሪያውን ስምምነት ጥያቄ ውስጥ በማስገባት ስምምነቱን የሚያኮላሽ ነው።አሁንም ቢሆን ከሁሉም በፊት የህወሓት ህጋዊ እውቅና ሊመለስለት ይገባል //
-
የወያኔ ዛቻ
መጋቢት 21/2016 ዓ.ም በሸራተን ሆቴል እነማን ምን መከሩ ?
የወያኔን የባርነት ቀንበር በወልቃይት ጠገዴ ህዝብ ላይ ዳግም ለመጫን ታቅዶ የቆየው ሴራ ወደ ተግባራዊ እንቅስቃሴ የተሸጋገረው በመጋቢት 21/2016 ዓ.ም ከተደረገው የሸራተን ሆቴሉ ምክክር በኋለ ነበር ......
እነማን ምን መከሩ ?
-ሉዓላዊ ሚዲያ በማግስቱ መጋቢት 22 መረጃውን አጋራው
የቃብቲያ ሆስፒታል የምረቃ ስነስርዓት
በቃብቲያ ሁመራ ወረዳ አስተዳደር የውስጥ አቅም የተገነባ ‼️
ህዳር 8 / 2017 ዓ.ም
"ዝንት እየተገለባበጡ መኖር እንደሚችሉ" አምነው የዘለቁቱ ድንገት "የተፈጠፈጡ" እንደሁ
ለዚህ የፍጥፈጣ ወንጀል ቀዳሚ ተጠርጣሪ የማደርገው Psychic ድመቶችን ነው !!
😂
እስኪ ....Goodnight !
"ሰረቀ ብርሃን " - የአለም ሰው !
በተሾሙ 3 ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ባሳዩት የችኩልነትና ያለመረጋጋት ባህሪ ምክንያት ስራዎን ባግባቡ መስራት ስላልቻሉ ከዛሬ ጀምሮ ተጭረዋል!
እባክዎን የቢሮ ቁልፉን አስረክበው ወደሚሄዱበት ይሂዱልነ 😂😂
(በ2009 ዓ.ም የተፃፈ ደብዳቤ)
We remember !
ማይካድራ ላይ በወያኔ የተፈፀመውን ጀኖሳይድ በማጋለጥና ወንጀሉ በአለማቀፉ ማህበረሰብ ዘንድ ይታወቅ ዘንድ ከፊት ተሰልፈው ሰብዓዊ ግዳጃቸውን ከተወጡት መካከል ካናዳዊውን ጄፍ ፒርስን (Jeff Pierce) አለማስታወስ አይቻልም።
Jeff Pierce - simply "Thank you" ‼️
.... በወልቃይት ወረዳ የወልቃይት 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የእንግሊዝኛ ቋንቋ መምህር የሆነው ብርሀኑ ሙጬ የ11ኛ ክፍል ተማሪዎችን "ፈተና ስለምትፈተኑ የያዛችሁትን የሞባይል ስልክ አምጡ" በማለት በቁጥር 18 የሚሆኑ ሞባይሎችን ይዞ ተሰውሯል።
ይህ የስርቆት ወንጀል "መምህራቸውን ሊያከብሩና በጎ አርአያነቱንም ሊከተሉ ይገባቸው ከነበሩ ተማሪዎች ላይ የተፈፀመ መሆኑ " ከሌሎች መሰል የስርቆት ወንጀሎች የተለየ ያደርገዋል።
የወረታ ቀበሌ 3 ልጅ የሆነው ይህ መምህር ከስርቆት ወንጀሉ በላይ ክቡሩን የመምህርነት ሙያ አዋርዷል።
የወልቃይት ወረዳ ትምህርት ቤት "ወንጀለኛውን ወደ ፍትህ ማቅረቡ ከራሱ ከፍትህ እሳቤው እጅግ በላቀ ሁኔታ ግንዛቤንና ትምህርት ሰጭነቱን ታሳቢ በማድረግ በጥቆማ ተባበሩኝ" ሲል ጥያቄውን ለህዝብ አቅርቧል።
እግረ መንገድ ....
Henry kissinger እኤአ ከ1973 - 1977 ዓም ድረስ የአሜሪካ ሴክሬታሪ ኦፍ ስቴት (አሁን ብሊንከን የያዘውን የስልጣን ቦታ ማለት ነው) ሆኖ ያገለገለ ነው። እኤአ በ1973 ዓ.ም የኖርዌዩ የኖቤል ሸላሚ ተቋምም የሰላም ተሸላሚ አድርጎት ነበር።
👇
Henry Kissinger's policy advice on Ethiopia, given in 1972, recommended exploiting internal tensions and divisions within the country, including ethnic, religious, and other differences, to maintain perpetual tension and conflict.
*Key Aspects of Kissinger's Policy Advice*
1. *Exploiting ethnic divisions*: Kissinger suggested using ethnic differences to create conflict and undermine national unity.
2. *Religious divisions*: He also recommended exploiting religious differences to fuel tensions.
3. *Weakening national identity*: Kissinger's strategy aimed to erode Ethiopia's national identity and self-esteem.
*Historical Context*
Kissinger's policy advice built upon earlier colonial strategies, such as Lord Macaulay's 1835 proposal to undermine Ethiopia's spiritual and cultural heritage.
*Sources*
1. National Security Study Memorandum 200 (NSSM 200): Implications of Worldwide Population Growth for U.S. Security and Overseas Interests (1974)
2. "The Kissinger Study on Southern Africa" by Mohamed A. El-Khawas (1978)
3. "Kissinger's Ethiopia Policy" by Theodore M. Vestal (1991)
4. "Ethiopia: A History" by Richard Pankhurst (1998)
*Impact*
Kissinger's proposals have contributed to ongoing ethnic and religious conflicts in Ethiopia, with radicals receiving training and support from external forces.
*Consequences*
1. Divisions and tensions along ethnic and religious lines.
2. Weakened national identity and self-esteem.
3. External interference in Ethiopia's internal affairs.
*References*
1. Vestal, T. M. (1991). Kissinger's Ethiopia Policy. Journal of Ethiopian Studies, 24(1), 1-18.
2. El-Khawas, M. A. (1978). The Kissinger Study on Southern Africa. Journal of Southern African Studies, 4(2), 157-170.
3. Pankhurst, R. (1998). Ethiopia: A History. Wiley-Blackwell.
4. NSSM 200: Implications of Worldwide Population Growth for U.S. Security and Overseas Interests (1974).
ትራምፕ ነገሰም አይደል ?
ይቺ አሽከር ግን የሺ ዢን ፒንግ የልጅ ልጅ ልጅ ሳትሆን አትቀርም።
እስኪ ተመልከቷት - "አበባ አየሁሽ"ን በማንዳሪን እንዴት አሳምራ እንደተጫወተችው ......¡¡
😎(😂)
ትራምፕ ከመመረጡ በፊቱ ስሙን መሬት አውርዶ እየፈጠፈጠ ሲሞጣሞጥ የነበረው ሁሉ አሁን ትራምፕ መመረጡን ሲያውቅ ጊዜ ደሞ ምንም ሳያፍር ተገልብጦ ስሙን ሰማይ ሰቅሎ እየተሞጣሞጠ ያለበት ሁኔታ ላይ ነው ያለው!
ዝምታም እኮ የጨዋ ነበር😎
ምድረ ቡትርፍ ...😂
// ለእርቅና ለሽምግልና ተስማምተዋል ተብሎ እየተሰራጨ ያለው መረጃ ከእውነት የራቀ መሆኑን እናሳውቃለን//
- የወያኔ (የአደመ አንጃ ) መግለጫ