wlkayi | Unsorted

Telegram-канал wlkayi - Asfaw abreha

9711

News

Subscribe to a channel

Asfaw abreha

ስህተት ያለ ነው።መሬትን ረግጦ መሳሳትና ፎቅ ላይ ተንጠልጥሎ መሳሳት ግን ለየቅል ነው።
ይልቅስ ይህ stunt ሰውያችን ተሳፋሪ አይደለም - የአውሮፕላኑ ሰራተኛ መሆኑ ነው የገረመኝ 😂😂

Читать полностью…

Asfaw abreha

// አንድ ወስላታ በሚዲያ ቀርቦ እኔን "የቀድሞው ፕሬዚዳንት" እያለ ሲጠራኝ ነበር አሉ።እሱ ችግር የለውም።ፖሊስ ጋ ቀርቦ መልስ ይሰጥበታል።የእነዚህ ሰዎች ችግር ስራ አለመስራታቸው ብቻ አይደለም።ከበፊት ጀምሮ የወንጀልና የሌብነት ኔትወርካቸው እንደሚጋለጥና እንደሚጠይቁ ስለሚያውቁ የትግራይ ፖለቲካ እንዲስተካከል አለመፈለጋቸው ነው።በዘረፋ የተሰማሩባቸው የወርቅና የመዳብ ማዕድናቱ ከእጃቸው እንዲወጣ አይፈልጉም።የትግራይ ፖለቲካ ተበላሽቶ የቀረው በነዚህ ሰዎች ምክንያት ነው //

- ቮ*ካው

Читать полностью…

Asfaw abreha

የአሜሪካው ፕሬዘዳንት Sleepy Joe ስልጣን ከመልቀቁ በፊት ልጁ ሃንተር ባይደን ለፈፀማቸው በርካታ ወንጀሎች ሙሉ ይቅርታን አደረገ !

ሲሾም ያልበላ ሲሻር ይቆጨዋል 😂😂

Full pardon order from the Office of the President of the United States for all crimes committed by the President's son, Hunter Biden, from 1970-2024

Читать полностью…

Asfaw abreha

እኒህ አባት ከመንበረ ሰላማ ውግዘት የሚድኑ አይመስሉም 😎

"ድሮም አንድ ነን ፤ አሁንም አንድ ያድርገን - ኢትዮጵያ የሚለውን ስም ይመልስልን አምላክ"

Читать полностью…

Asfaw abreha

የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ አለምአቀፋዊ ፣ አካባቢያዊና ውስጣዊ ጉዳዮችን አስመልክተው ከERI- TV ጋር ያደረጉት ቃለመጠይቅ

https://www.youtube.com/live/y-NFdmuZyMg?si=GH0JWrsorYyCBuMZ

Читать полностью…

Asfaw abreha

Israeli soldiers desecrate a Greek Orthodox Church in the Lebanese town of Deir Mimas, and conduct a mocked homosexual wedding in the church.

Читать полностью…

Asfaw abreha

እነሱ እንዲህ ናቸው።እና የነሱ ምክር ታዲያ ለኛ ምን ሊረባ ?
Be ware !!

//ጀርመኖቹ እያሸነፉ መሆናቸውን በተረዳን ጊዜ ሩሲያውያኑን ማገዝ አለብን።ሩሲያውያኖቹ ያሸነፉ ሲመስለን ደግሞ ጀርመኖቹን እናግዛለን።እንዲህ እያደረግን እርስበርሳቸው እንዲገዳደሉ ማድረግ ይኖርብናል //

ሃሪ ትሩማን ( እ.ኤ.አ 1941 )

- እስኪ ....Goodnight !

Читать полностью…

Asfaw abreha

"This war is all about money"

አሜሪካ የዩክሬኑን ጦርነት እንዲቀሰቀስ አድርጋ ግፋ በለው ከማለት በዘለለ በርካታ የጦር መሳሪያዎቿን እስከመስጠት የደረሰችው የዩክሬንን ማዕድን ለመዝረፍ ከመሻት እንጂ ለዩክሬንና ህዝቧ ግድ ኖሯት አልነበረም።
-------------
Lindsey Graham ትናንት የተናገረውን እውነታ Tucker Carlson እጅግ ቀድሞ ነግሮን ነበር።

Читать полностью…

Asfaw abreha

እነ ልብ አይሞት "ወልቃይት ጠገዴ ስንገባ የወርቅ ማምረቻ ቦታ እንሰጣችኋለን" ብለው ወረፋ አስይዘው እየቀፈሏቸው ያሉ የቻይና ካምፓኒዎች ነፍ ናቸው አሉ 😂

___

ሴናተር ሊንድሴይ ግራሃም "This war is all about money" ካለው የዩክሬን ነገር ጋር ተመሳስሎብኝ እኮ ነው።
ጋሼ Lindsay Graham "ዩክሬን ውስጥ የምንጫወተው 2-7 ትሪሊዮን ዶላር ለሚገመተው ማዕድኗ ስንል" ነው አላለም ?

Читать полностью…

Asfaw abreha

// የእነ ደብረጽዮን ቡድን ከዚህ ቀደም "ጠላት ናቸው" ብሎ ከፈረጃቸው አካላት ጋር እየተደራደረ ወንበር ለማስመለስ ሌት ተቀን እየሰራ ይገኛል//
-------------
- በአሁኑ ሰዓት ቮ*ካው መግለጫ እየሰጠ ነው

( የኢትዮጵያን ሰ/ዓላማ የጠላው ግን የቮ*ካው ቢሮ ነው ወይስ ካሜራማኑ ? 😎)

Читать полностью…

Asfaw abreha

እግረ መንገድ....
ይህ የፀረ ታንክ ሚሳኤል መተኮሻ ነው። Kornet anti tank ይባላል።
ይህ ግርማይ የተባለው የወያኔ ወታደር በወቅቱ በነበረው የመከላከያ አደረጃጀት ውስጥ አንድ ወታደራዊ ዕዝ ሁለት kornet ፀረ ታንክ ሚሳኤል መተኮሻ ብቻ እንደነበሩት ሲናገር ሰምቼው ነበር።
ትግራይ ወስጥ ከነበረው ሰሜን ዕዝ ላይ በወያኔ ከተዘረፉት ሁለት ኮርኔቶች መካከል ይሄኛውን በጦርነቱ ጊዜ ተጠቅመውበታል። ሁለተኛው መሳሪያ ግን ችግር እንደነበረበት ግርማይ ተናግሯል።በዚህ መሳሪያ 34 ታንኮችንና ዙ 23 መሳሪያዎችን እንደደመሰሰበትም በኩራት ሲነገር አይቸዋለሁኝ።
የኔ ጥያቄ ...ይህ መሳሪያ አሁን የት ነው ያለው ?

Читать полностью…

Asfaw abreha

Medvedev published footage of the strike of the newest Oreshnik missile on Yuzhmash.

Video via Medvedev's official page in X/TASS

Читать полностью…

Asfaw abreha

በወያኔ የጦር አዛዦች እና በቮድካው ቡድን መካከል ያለውን ወቅታዊ "ፍቅር"(😂) ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ምላሽ 👇

ጥያቄ -"የግድያ ሙከራ እንደተደረገብህ ከተገለፀ በኋላ ይህ ሙከራ በአርሚ 60 አባላት እንደተፈፀመ በሶሻል ሚዲያው እየተሰራጨ ነው።ይኼንን ተከትሎም በዚህ ወንጀል ላይ የአርሚ 60 አባላት ፈፅመውታል መባሉን የአርሚ 60 አዛዥ ጄኔራል ህንፃ አስተባብሏል። ምን ትላለህ ?"

የአክሱም አስተዳዳሪ ሰሎሞን ማዕሾ ምላሽ - "የጄ/ል ህንፃን ምላሽ ሰምቸዋለሁ። ህንፃ በዚሁ ቃለመጠይቁ ላይ እኔና እሱ ጓደኞች እንደሆንን ተናግሯል።እሺ ይሁን ጓደኞች ነን ...ነገር ግን ወንጀሉ ይጣራ ማለት ሲገባው ለምንድነው ተሽቀዳድሞ የተከላከለው (Defend ያደረገው) ?"

Читать полностью…

Asfaw abreha

" በወያኔ ዙሪያ ለምን ትፅፋለህ ፣ ምንም አያገባህም " የሚሉ አንዳንድ መካሪ መሰል መደዴዎችን እያየሁ ነው።እነዚህ ሰዎች ደግሞ የወያኔ ሰዎች እና " ከወያኔ ጋር መስራት ይቻላል" የሚሉት የኛዎቹ እንጉልፋቶዎች ናቸው።
ኖኖኖኖ ከእነሱ ጋር'ማ አልፋታም።ምክንያትም አላማም አለኛ !! መካሪ መሳይ መደዴዎቹም ከዚህ የFB ቤቴ ውስጥ ይጠረጋሉ።

ዳይ ወደ ደደቢቶች ....😂
- ሰለሞን መዓሾ በቮ*ካው የተሾመ የአክሱም አስተዳዳሪ ነው።ከተደረገበት የግድያ ሙከራ ለጥቂት ተርፏል።ይሄንን ኦፐሬሽን የፈፀሙት ደግሞ በጄኔራል ህንፃ ወልጊዎርጊስ ከሚታዘዘው አርሚ60 የተመለመሉ ወታደሮች ናቸው።አስተዳዳሪው ከአክሱም ወጣ ብላ ምፍልላይ ወደምትባል ቦታ በመጓዝ ላይ እንደደረሰ ነበር መኪናው ላይ የተኩስ እሩምታ የከፈቱበት።
---
አርሚ 60 ተምቤን ላይ የሰፈረ ጦር ነው።ለሚሽን የተመረጡ ወታደሮቹን ወደ አክሱም ልኮ ያስራል ይገድላል።
የማዕከላይ (አክሱም) የፀጥታ ሰዎች ደግሞ ወደ ተምቤን ይላኩና ተምቤን ውስጥ ያፍናሉ ይገድላሉ።
ለዛም ነው ጄኔራል ህንፃ ለአንድ ሚዲያ በሰጠው ቃል ላይ " ውንጀላው ውሸት ነው።ሲጀመር ደሞ የእኛ ጦር ተምቤን ነው ያለው" ሲል የመለሰው ።

*** እነ ጄኔራል ህንፃ ይሄንን ድንዙዝ ታጣቂ በነፃ ዝውውር እያጫወቱት ነው - ለአፈናና ለግድያ ባይሆን ጥሩ ነበር😎

Читать полностью…

Asfaw abreha

ሥራ ትርክትን ይለውጣል፣ ትርክት ሥራን ይቀይራል!!
ቀን 8/03/2017ዓ/ም
ቃብትያ ከተማ-ጎንደር-አማራ-ኢትዮጵያ
አመሰግናለሁ!!

Читать полностью…

Asfaw abreha

//እዚህ ላይ ለመፃፍ በሚሰቀጥጥ የመስፈርት ዝርዝር መሠረት የተመለመሉ የአርሚ (TDF) አባላት ሌሊት ሌሊት የተለየ ስልጠና እየተሰጣቸው ነው //

---- የምስጢራዊው ስልጠና ምንነትና ግብ ያልተረዳውና ስጋቱን (ጭንቀቱን) በዚህ ፅሑፉ የገለፀው ዮሴፍ በርሄ የተባለው የባይቶና ልጅ ነው።ታስታውሱ እንደሆነ ባለፈው መቀሌ በነበረው የDDR ፕሮግራም ዕለት የኢትዮጵያ ህዝብ መዝሙር ሲዘመር ከወንበሩ ባለመነሳት ንቀቱን ከገለፁት ሁለት ሰዎች አንደኛው ነው።

P.S
----
ዮሴፍ የዚህን ምስጢራዊ ስልጠና መስፈርትና ግብ ምንነት ከእስከዛሬው የወያኔ ጉዞና ሂደት በመነሳት በተረዳሁት ልክ ምክንያታዊ መላምቴን እንድሰጠው ከፈቀደልኝ .....
' 👇'
አላማው - ግድያ ነው
መስፈርቱ - ታዛዥ ፣ ህወሐትን ሃይማኖቱ ያደረገ፣ እና ጨካኝ ታጣቂ መሆን አለበት
ኢላማው - የትግራይ ጊ/አስተዳደር ሹመኞች

Читать полностью…

Asfaw abreha

የኛዎቹ ብቻ ይመስለኝ ነበር - አማሪካኖቹም ህዝባቸውን ይዋሻሉ ለካ ¡¡

Sleepy በልጁ የፍርድ ሂደት ዙሪያ አስተያየቱን እንዲሰጥ ሲጠየቅ የፍ/ቤቱን ውሳኔ እንደሚያከብር ገልፆ ልጁ ጥፋተኛ ሆኖ ከተገኘ የፍ/ቤቱ ውሳኔ ተፈፃሚ እንደሚሆንና ልጁ የመንግስትን Pardon (ይቅርታ) እንደማያገኝ ተናግሮ ነበር።

👆 ቪዲዮው ላይ Sleepy ከ5 ወር በፊት ( June ) ምን እንደተናገረ አዳምጡ

Читать полностью…

Asfaw abreha

እግረ መንገድ ...
"የሌባ አይነደረቅ..." ብላችሁ በእንግሊዝኛ ንገሩልኝ እስኪ ? 😂😂

እ .ኤ.አ በ1937 ዓ.ም ከኢትዮጵያ የተዘረፈውን የራስ ደስታ ዳምጠው ሜዳሊያ በጨረታ ለመሸጥ ማስታወቂያ አውጥቶ የነበረው Swiss auction house በተቆርቋሪ የውጭና የውስጥ ዜጎች አማካኝነት በተከፈተበት የውግዘት ዘመቻ ሳቢያ ለጊዜውም ቢሆን ፕሮግራሙን ሰርዞታል ተብሏል።

Читать полностью…

Asfaw abreha

ወንበሯ ...
በአሁኑ ሰዓት የመቀሌ ከተማ አስተዳደር ፅ/ቤት በፖሊሶች ተከቧል።እንታይ ጉዱ?😂
ቮ*ካው ትናንትና ብርሃነ ገብረየሱስ የተባለውን ሰውዬ ( ከላይ በምስል የሚታየውን) የመቀሌ ከንቲባ አድርጎ ሾሞት ነበር።
ምናልባት 1- ነባሩ ከንቲባ 'ወንበሯን' አለቅም ብሎ ይሆናል ።
ምናልባት 2 - አዲሱ ከንቲባ 'ወንበሯን' አትቀመጥባትም ተብሎ ይሆናል።

Читать полностью…

Asfaw abreha

"መስሪያ ቤታችንን ግን ምን ነካው?" አለ የመብራት ሃይል ሰራተኛ 😂

እስኪ ....Goodnight

Читать полностью…

Asfaw abreha

Romanian presidential candidate Călin Georgescu:

“no one can defeat God.”

Читать полностью…

Asfaw abreha

// እዚህ አዳራሽ ውስጥ ከሚገኙት 193 የUN አባል አገራት መካከል 22ቱ ብቻ ናቸው "በብሪጣኒያ አልተወረርንም ወይንም ከብሪጣኒያ ጋር ጦርነት አልገጠምንም" ብለው አፋቸውን ሞልተው መናገር የሚችሉት ።
ብሪጣኒያ ሩሲያን በጠብ ጫሪነት ለመክሰስም ሆነ ለመተቸት ሞራል የላትም //
- በUN የሩሲያ አምባሳደር ኔቤንዢያ

Читать полностью…

Asfaw abreha

ወያኔ የዘራችው አሜኬላ አድጎ እራሷን ወያኔን መቀርጠፍ ይዟል።
መማር ለፈለገ ከወያኔ በላይ ጥሩ 'ት/ቤት' አያገኝም 😎

//እኔ እንደርታዊ ነኝ ትግራዋይነትን በግድ ልትጭኑብኝ አትችሉም//
- የመቀሌው ሰው

Читать полностью…

Asfaw abreha

Rules based order 😂

Читать полностью…

Asfaw abreha

በፍልፈሎቿ አማካኝነት የተላለፈው የወያኔ መልዕክትና አቋም ....

መቀሌ በነበረው የዛሬው የDDR የመክፈቻ ስነስርዓት ላይ የኢትዮጵያ ህዝብ መዝሙር ሲዘመር ከመቀመጫቸው ባለመነሳት ንቀታቸውን የገለፁት
👉 - የተገንጣዩ የውናት ፓርቲ ዋና ፀሓፊው ዶ/ር ደጀን መዝገቡ
👉 -የሌላኛው ተገንጣይ የባይቶና ፓርቲ አባል ዮሴፍ በርሄ

Читать полностью…

Asfaw abreha

ቻይናዊው "ትራምፕ" የትራምፕ ደጋፊዎችን ልብ ሲሰልብ 😂😂

Читать полностью…

Asfaw abreha

//ሉዓላዊ ግዛታችንን እስክናስመልስ ድረስ ሙሉ ትጥቃችንን አንፈታም።ሲጀመርም እኮ የምንፈታቸው የጦር መሳሪያዎች ወደ ፌዴራል መንግስት (አዲስአበባ) የሚጫኑ አይደሉም።መሳሪያዎቹ ተሰብስበው እዚሁ ትግራይ ውስጥ በተመረጠ ቦታ ላይ ይከማቻሉ//

- አቶ ተስፋአለም (የቮድካው የህወሓት አንጃ አባል)
=======

ዘኢትገርም .!!!!
.. ውሃ ቅዳ ውሃ መልስ የሆነ ነገር።ይሄማ መንግስት የጦር መሳሪያዎቹን በአደራ እንዳስቀመጠ ይቆጠራል 😎

Читать полностью…

Asfaw abreha

በወቅቱ መረጃው በቸልታ ሊታይና ተገቢውን ትኩረት ላያገኝ ይችላል።
አንድን መረጃ ዳግም መለጠፍ ግድ ሊሆን ከሚችልባቸው አጋጣሚዎች መካከል ይሄ አንዱ ነው።
ዛሬ የወያኔ ወታደሮችን ትጥቅ የማስፈታት ስራ ሊጀመር እንደሆነ ኮሚሽነር ተመስገን ጥላሁን በመግለጫ ማሳወቃቸውን ታሳቢ በማድረግ ይህ የቀደመ ስታተስ ወቅታዊነቱን አይተን ከጥቂት editing ጋር በድጋሚ ተለጠፈ
👇
============
መልስ የሚሰጠኝ ካለ ጥያቄ አለኝ ጓዶች

DDR ማለት "ቦርድና ጡሮታ" የሆነችው ከመቼ ወዲህ ነው ?
=================
DDR ሲባል ታጥቀው ሲዋጉ የነበሩ የአንድ ቡድን አባላትን ትጥቅ በማስፈታትና የወደፊት ኑሯቸውን የሚያግዝ ተመጣጣኝ የመቋቋሚያ ድጋፍ በማድረግ ወደ ሰላማዊ ህይወት እንዲመለሱ ማድረግ ነው።
ነጮቹም ቢሆን ምህፃረ ቃሉንና እሳቤውን ሲወረውሩልነ እንዲያ ማለት እንደሆነ ነው የነገሩነ ።
👇
What is the concept of DDR?
Disarmament, Demobilization and Reintegration (DDR) is a process through which members of armed forces and groups are supported to lay down their weapons and return to civilian life.
ወዲህ ደግሞ የወያኔው ጄኔራል ፃድቃን ገብረትንሳኤ ለ"DDR" የተለየ ትርጉም ሰጥተው እየነገሩን ነው።
በዚህ መድረክ ላይ ጄኔራል ፃድቃን ገብረትንሳኤ ...
"በDDR ዙሪያ በተነሳው ላይ ዳንኤል ብርሃኔ በገባው ልክ ለማብራራት ሞክሯል። ለመረጃ እንዲሆናችሁ ግን እኔ አንድ ነገር ልንገራችሁ።እስካሁን ድረስ በDDR ምክንያት ከሰራዊታችን እየተቀነሱ ያሉት እኮ በትግራይ የፀጥታ ሃይሎች ዕዝ አማካኝነት "ሰራዊቱ ውስጥ ሊቆዩ አይገባም" ተብሎ የተወሰነባቸው ታጣቂዎች ናቸው። እነዚህ የሰራዊታችን አባላት ደግሞ በዕድሜ የገፉና በጉዳት እና መሰል ምክንያቶች በውትድርናው ለመቀጠል የማይችሉ ናቸው።ይሄ ደግሞ የሰራዊታችንን ብቃትና ዝግጁነት የሚያጠናክር እንጂ የሚበትን አይደለም "
---------------------------------------------------------------

P.s
እንዴት ነው ነገሩ ?
በእድሜ መግፋት ሳቢያ ከሰራዊቱ የሚሰናበቱት "ጡሮታ ወጡ" እየተባለና እንዲሁም በጦር ጉዳት ሳቢያ የሚሰናበቱት ደግሞ "ቦርድ ወጡ" እየተባለ ስሰማ ነበር ያደግኩት።እና ታዲያ ከመቼ ወዲህ ነው "ጡሮታና ቦርድ" DDR ሆነው የተከሰቱት ?

ቪዲዮው 👇

Читать полностью…

Asfaw abreha

የመኪናውን ቁልፍ እውስጥ ረስተውት ስለወጡ መላ ቅጡ ጠፍቶባቸዋል
😂😂😂

እስኪ ....... Goodnight

Читать полностью…

Asfaw abreha

በአንድ እጁ ራሱን በራሱ ለማስተዳደር የሚያበቃውን የነጻነት ትግል በሌላ እጁ የልማት ትግል እያደረገ የሚገኘው ሕዝባችን በአማራ ልማት ማህበር (አልማ) እና በህዝቡ ተሳትፎ የተጣለው የዕውቀት በር ቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤት ግንባታ መሰረት ድንጋይ፣ ተጀምሮ የቆመውን የቃብትያ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ገሚሱን ግንባታ በቀናዒ ልጆቹ ተገንብቶ ሲጠናቀቅለትና ሲመረቅለት ደስታው ልዩ ነው፡፡
ጤናው የተጠበቀ ዜጋን የመገንባትና የአገልግሎት ተደራሽነትን በማስፋት የህዝቡን በሽታን የመከላከልና የማከም ዐቅም የሚያሳድግ፣ እንዲሁም የትምህርት ልማት የነገ ተስፋ፤ የነገ ብሩህ ሕይወት፤ የብርሃናማ ትውልድ ምልክት ነውና አዳኝ ትውልድ ግንባታው በሁሉም ዘርፍ ተጠናክሮ ይቀጥላል፡፡

ከዓመታት የፀና ተጋድሎ፣ ለእውነት ከተከፈለ መስዋዕትነት በኋላ ነጻነትህን እያጣጣምክ ያለህው የተከበርከው ጀግናው የወልቃይት-ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ሕዝብ ሆይ…!

ነጻነትህ የመስዋዕትነት ውጤት ነው፡፡ በዙሪያህ ያለው አንጻራዊ ሰላም የአንተ ትጋት ውጤት ነው፡፡ የጨለማው ዘመን ዳግም እንዳይመለስ በእጅህ የገባውን ነጻነት አፅና፤ በፍትሐዊ ትግል መንገድ ታምነህ ቁም!!

በቀኝ በግራ ሲነሳብን የነበረውን ትንኮሳ እየመከትን ለዛሬው የልማት ፍሬ እንደበቃነው፤ ነገም ትርጉም በሚሰጥ መስዋዕትነታችን ነጻነታችን ተከብሮ፤ ልማታችን ሰፍቶ ይቀጥላል፡፡

ከታሪክ ያልተማሩ፡- ሺህ ከሚሊዮን የፖለቲካ ሴራ ደጋሾች፣ ዙሪያ ገባውን በክህደት ሊሞሉ እንቅልፍ ያጡ የክፋት ልቦች ቢኖሩም፣ እውነተኛና ፍትሐዊ ጥያቄ ያነገበው ጀግናው የወልቃይት-ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ሕዝብ ለጨለማው ዘመን አበጋዞች አይንበረከክም፡፡ በሴረኞች የሴራ ቦይ አንነፍስም፣ ከፍትሐዊው ትግላችን ዓላማ ንቅንቅ አንልም!

ክቡራት እና ክቡራን…!

በአንድ እጃችን ነጻነታችንን እንጠብቃለን፣ በሌላኛው እጃችን ልማታችንን እናስቀጥላለን በሚል ወኔ፣ ቁጭት፣ እልህና ተስፋ ተላብሰን በደም የተገኘውን ነፃነት በላብ ለማፅናት እየተጋን እንገኛለን፡፡ የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ሕዝብ ነጻነቱን፣ ሰላሙን እና ማንነቱን እያጣጠመ ነው፡፡ ነገር ግን ሰላሙና ነጻነቱን የበለጠ እንዲያጣጥም መንግሥት የወልቃይት ጠገዴን ጥያቄ በሰላማዊና በሕጋዊ መንገድ ምላሽ መሰጠት ይኖርበታል፡፡

ወልቃይት ጠገዴ የእውነትና ፍትህ ጥያቄ ነው የጠየቀው፤ የማንንም አይፈልግም፣ የሌላውን ስጡኝ አይልም፣ የበጌምድር-ጎንደር ባላባትነቱ፤ አማራዊ ማንነቱ በታሪክ፣ በመረጃና በማስረጃ የተደገፈው እውነቱ ግን ሊከበር ይገባል፡፡
የወልቃይት ጠገዴ ሕዝብ የሚታገለው የፖለቲካ አመለካከት አለ እንጂ የሚታገለው ሕዝብ የለም፡፡ በማንም ላይ ጥላቻ የለውም፣ የራሱን ግን ለማንም አሳልፎ አይሰጥም፣ አማራዎች ነን ከአማራም የአማራ የዘር ግንድ መነሻ ይህ የቆምንበት ምድር ነውና ማንነታችን ሊከበር ግድ ይላል፡፡

የወልቃይት ጠገዴ የማንነት ጥያቄ እንዲመለስ በትዕግስት እየጠበቅን ነው፣ የወልቃይት ጠገዴን የእውነት ጥያቄ በአስቸኳይ መመለስ ለሀገር፣ ለሕዝብና ለመንግሥት ጠቃሚ ነው፡፡

የወልቃይት ጠገዴ ጉዳይ የአማራን የህልውና ጥያቄ የመመለስ ጉዳይ ብቻ ሳይሆን ዘረፈ ብዙ የኢትዮጵያ ደህንነት ጉዳይ ስለመሆኑ ደግመን ደጋግመን አሳሰበናል፤ ዛሬም ይህንኑ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡

ወልቃይት ጠገዴ ላይ ትንኮሳ ለማድረግ፤ ለዳግም ወረራ ተጋላጭ እንድንሆን መዋቅር ለማፍረስ የሚሞክር ካለ ፈጽሞ አይሳካለትም፤ ሕዝባችን ወደፊት ይራመዳል እንጂ ወደኋላ አይመለስም፡፡ ከልማታችን ጎን ለጎን ሰላማችንንም እናስከብራለን፡፡

የወልቃይት ጠገዴ ሕዝብ ያለእርስቱ ተፈጥሮ ካበጀለት ወንዙ ተከዜ አልፎ አይሻገርም፡፡ ተፈጥሮ ካበጀለት ወሰኑ፤ አያት ቅድመ አያቶቹ ባወረሱት ርስቱ ላይ ተራምዶ ለወረራ ለሚመጣ የግዛት ተስፋፊ ኃይል ግን ትዕግስት የለውም፡፡ ወደጨለማው ዘመን ላለመመለስ በብርሃን ፍጥነት ይፋለማል፡፡ በሰላሙና በነጻነቱ ላይ ከመጡበት አይታገሰም፡፡ በጠንካራ የሥነ ልቦና ዝግጅት አካባቢውን ነቅቶ መጠበቁን ይቀጥላል፡፡ ሁልጊዜም ቢሆን ትርጉም ላለው መስዋዕትነት ዝግጁ ነን!!
ክቡራትና ክቡራን
በዚህ የምረቃ ፕሮግራም ላይ የታደማችሁ በሙሉ በተለይም እንግዶቻችን አንድ ልብ እንድትሉልን የምንፈለገው ቁም ነገር!
ሕገ-መንግሥቱ ከመጽደቁ በፊት፣ ያለሕገ-መንግሥት አንቀጽ በወረራ ለሰላሳ ዓመታት የተያዘብንን መሬት፣ በጉልበት ሊደፈጠጥ የተሞከረው አማራዊ ማንነታችን፣ ዛሬ ሕጋዊ ዕውቅና እንዲሰጠን የሕገ-መንግሥት አንቀጽ ጠቅሰን የምንጠይቀው ሕግና ሥርዓት አክባሪዎች በመሆናችን ነው፡፡ ይህን እውነታ መላው የኢትዮጵያ ብሔር ብሄረሰቦች እንዲያውቁልን እንፈልጋለን፡፡
ለተፈጸመብን የዘር ማጥፋት ወንጀል፣ ተቆጥሮ ለማያልቀው ግፍና በደልም የፍትሕና የሞራል ካሳ እንደሚገባን እናውቃለንና ፍትሕ ወዳድ ኢትዮጵያዊያንን ይዘን አበክረን እንጠይቃለን፡፡ የፌዴራሉ መንግሥት በጉዳዩ ላይ ታሪካዊ ስህተት እንዳይፈጽም አብዝተን እናሳስባለን!!
በመጨረሻም

የወልቃይት ጠገዴ ሕዝብ የዘመናት የማንነት ትግል አዲስ ምዕራፍና የታሪክ እጥፋት ላይ ይገኛል፡፡ ጥያቄችን በዘላቂነት የተቋጨ ባለመሆኑ ዛሬም ትግል ላይ ነን፡፡ ትግላችን ደግሞ ራስን የመሆን ክቡር ትግል ነው፡- ትግሉ የራስን ዕድል በራስ የመወሰን ትግል ነው፡፡

ወልቃይት ጠገዴ ጎንደር ነው፣ ጎንደር-አማራ ነው! አማራ ደግሞ ኢትዮጵያ ነው፡፡ የትግላችን ዓላማ ግን ከዚህም የተሻገረ ነው፡፡ ትግላችን የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራን ኮሪደር አስከብሮ የኢትዮጵያን ህልውና የመጠበቅ ሀገራዊ ትግልም ነው፡፡

የወልቃይት ጠገዴ ትግል መርሁ ሁሌም ዝግጁ ሆኖ መገኘት፤ መቆሚያ ምሰሶው ደግሞ አንድ እውነት፣ አንድ ማንነት፣ ምንጊዜም ጎንደሬ-አማራነት፤ ፅኑ ኢትዮጵያዊነት የሚል ነው፡፡

ወልቃይት ጠገዴ የኢትዮጵያ አንገትም፣ የምድር በርም ናትና ከሕዝቡ አብራክ የወጣነው በየደረጃው ያለነው መሪዎች የማንነት ጥያቄው በህግና በሰላም ለመቋጨት የሰመረ የህዝብና የመንግስት ግንኙነትና መስተጋብር እየፈጠሩ ህዝቡ አንድነቱን እንዲያጠናክር በሚገባ አዘጋጅተን ከመራነው በታሪክ ውስጥ በደማቅ ቀለም የሚጻፍና በትውልዶች ዘንድ ሲጠቀስ የሚኖር አኩሪ ክንዋኔ እንፈፅማለን፡፡

ዘመኑን ባልዋጀ ሁኔታ የትግል አስተሳሰብ ትጥቅ አስፈቺ የሆነ የመዘናጋት እና ሰላሙን የሚያውክ መንገድ ከመረጥን ደግሞ እኛም ሆንን ሕዝባችን ለሌላ ዙር የባርነትና የጨለማ ዘመን እንመለሳለን፤ ለትውልዱ ይህን የጨለማ ዕዳ ካወረስን ትውልዱ ሲረግመን ይኖራል፡፡ ስለሆነም በመጭው ትውልድ ላለመረገምና ዕዳ ላለማውረስ፣ የትግሉ ሰማዕታትን አደራ ላለመጣል የብርሃን መንገዱ ላይ በትግል እንፀናለን፡፡

አንድ እውነት፣ አንድ ማንነት፣ ምንጊዜም ጎንደሬ-አማራነት፤ ፅኑ ኢትዮጵያዊነት የትግል ቃልኪዳናችን ሆኖ ይቀጥላል፡፡

ይህ ሲሆን ልማት፣ ሰላምና ደኅንነት ሳይነጣጠሉ የሚቀጥሉ ጉዳዮች እንዲሆኑ ማድረግ ይቻላል፡፡ ሰላም የልማት መሳሪያ ነው፡፡ ልማት የሰላም መጠበቂያ ነው፡፡ ደህንነት የሁለቱም ዋስትና ነው፡፡ ከልማት፣ ሰላምና ደኅንነት ተልዕኳችን አኳያ የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ሕዝብና አመራር የትኛውም ችግር የማይበግረው እና ከዓላማው የማይናወጥ ሆኖ ቋሚና ዘላቂ ታሪክ መስራቱን ይቀጥላል፡፡

Читать полностью…
Subscribe to a channel