የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት ከቅዳሜ ጀምሮ ተግባራዊ ያደረገው እርምጃ የዘገየ ቢሆንም አስፈላጊና ተገቢ ነው - ምንም እንኳን ጦረኞቹ ቀድመው አከማችተው ሊሆን ቢችልም ቅሉ ¡¡
ለነገሩ አሁን አማራጭ አቅራቢ ያጣሉ ብላችሁን ነው? 😎
የሃዘን መግለጫ!!
*
የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን እና የወልቃይት ጠገዴ አማራ የማንነትና ወሰን አስመላሽ ኮሚቴ አባል የሆነው ወንድማችን ታጋይ ወረታ አዛናው ድንገተኛ ህልፈተ ሕይወት የተሰማውን ልባዊ ሃዘን ይገልፃል።
ክቡር ወንድማችን አቶ ውረታው አዛናው
ከአባቱ ከአቶ አዛናው በርሔና ከእናቱ ወ/ሮ ትደግ ለማ በ1949 ዓ/ም በጎንደር ክፍለ ሃገር በዳባት አውራጃ በወልቃይት ጠገዴ ብላምባ መድሃኒአለም ተወለደ። የልጅነት እድሜው በወልቃይት ጠገዴ ባህል በአባቱና በእናቱ እንክብካቤ ያደገ ሲሆን እድሜው ለስራ ሲደርስ በገበሬው አባቱ ውስጥ ሁኖ ቆላ ከደጋ እንዲሁም መዘጋ ወልቃይት አያናዝጊ በመውረድ እያረሰና እያመረተ ወላጆቹን የሚያስደስትና በአካባቢው ማህበረሰብ ክብር የሚሰጠው ሁኖ ያደገ ነበር ። ክቡር ወንድማችን ታጋይ ወረታው አዛናው በአገራችን ኢትዮጵያ በተፈጠረው የንጉሱ ስርአት ለውጥ ተከትሎ የግብርና ስራውን በመተው በደርግ ዘመነ መንግስት የኢትዮጵያ ወታደር በመሆን ሃገሩን ኢትዮጵያ ከኦጋዴን እስከ ምፅዋ በተደረገው የአገር ሉአላዊነት የማስከበር ዘመቻና ውጊያዎች በመሳተፍ በመካናይዝድ የጦር ክፍል በአምሳ አለቃነት ማእረግ በሁሉም ግንባሮች አውደ ውጊያ በመሳተፍ ለሃገሩ ሉዓላዊነትና አንድነት መከበር የበኩሉን የተወጣ የወልቃይት ጠገዴ ምድር ያፈራው ጀግና ወንድማችን ነበር ።
ክቡር ወንድማችን አቶ ወረታ አዛናው ከደርግ ውድቀት በኋላ በግል የንግድ ስራ ተሰማርተው ከአዲስ አበባ እስከ ጎንደር መተማ ከመተማ እስከ ገዳሪፍ ፖርት ሱዳን ድረስ እየነገደ ለእናት ሀገሩን በታታሪነትና አርአያነት ግብር ከፋይ ነጋዴ ነበር። ክቡር ወንድማችን አቶ ወረታው አዛናው ከንግድ ስራው ጎን ለጎን የወልቃይት ጠገዴ የማንነት ጥያቄ ሲነሳ የፊት ከከፋኝ እስከ ወልቃይት ጠገዴ ማንነትና ወሰን አስመላሽ ኮሚቴ መስራች ታጋይ በመሆን የማንነትና የወሰን ጥያቄው ዳር እንዲደርስ ለህዝባችን ጥያቄ መረጋገጥ ሲል ዋጋ በመክፈል ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያደረጉ ጀግና ነበሩ።
የማንነት ኮሚቴ ከመሰረቱት ግንባር ቀደም ታጋይ የነበረው ወረታው አዛናው ኮሚቴ ከመመስረት ባሻገር ህገ መንግስቱን መሰረት አድርጎ የወልቃይት ጠገዴ ጥያቄ በመቀሌ፣በባህር ዳርና በአዲስ አበባ በማቅረብ የሞገተና ስለ ህዝብ መብት የተከራከረ ጀግና ነበር።
ክቡር ወንድማችን አቶ ወረታው አዛናው የወልቃይት ጠገዴ የማንነት ጉዳይ ህገ መንግስታዊና የመብት ጥያቄ መሆኑ በፅኑ በመረዳት የህዝቡን ማንነት፣ፍላጎትና ታሪካዊ ዳራዎች በውል በመረዳት በከፍተኛ ስብሰባዎች በመገኘት በአንደበተ ርትዑነቱ የወልቃይት ጠገዴ የማንነቱ ጥያቄ በግልፅ በማቀረብ ጥያቄው እንዲደምቅና እንዲቀጣጠል አይተኬ ሚና የተጫወቱ ጀግና ታጋይ ነበር።
ህወሓት በህገ መንግሥቱ መሰረት የቀረበለትን ጥያቄ መመለስ ሲችል የወልቃይት ጠገዴ የማንነት ጥያቄ በማፈን ታጋዮቹን ማፈን፣ማሰርና መግደል ሲጀመር የህወሃት የቀደመ ግፍ የሚያውቀው ታጋይ ወረታው በሰላማዊ መንገድ ጥያቄው እንደማይመለስ ሲገባው ህዝቡን በማስተባበር ህዝባዊ አመፅ እንዲነሳ ካስተባበሩና ከመሩ ግንባር ቀደም ታዮች አንዱ ነበር።
ክቡር ወንድማችን አቶ ወረታው አዛናው በወልቃይት ጠገዴ የማንነት ና የወሰን ጥያቄ አንስቶ በመታገሉ ምክንያት በአምባ ገነኑ የወያኔ መንግስት ብርሸለቆን ጨምሮ በተለያዩ እስር ቤቶች ታስሯል፣ ተሰቃይቷል፣ተንገላቷል ። ህወሓት በሰሜን እዝ ላይ የከፈተው ጥቃት ተከትሎ በነበረው ጦርነት የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ ከህወሃት የማንነት ጭቆና ነፃ እንዲወጣ ህዝቡን በማስተባበር ና በመምራት ጉልበቱንና ገንዘቡንሳይሰስት ለትግል ያዋለ ጀግናችን ነበር።
ታጋይ ወረታው አዛናው ሃቀኛ፣ለአመነበት ትግል ግንባሩን የሚሰጥ ለብዙዎች አርአያ የሚሆን ኩሩ ጀግና ነበር።
ክቡር ወንድማችን አቶ ወረታው አዛናው ባለ ትዳርና የ3 ልጆች አባት በመሆን ቤቱንና ቤተሰቦቹን በአግባቡ ያስተዳድር የነበረ አባት ነበር።
ወንድማችን በንግዱ አለም ተሰማርቶ ለንግድ ስራ ጥር 13 /2017 ዓ/ም ከጎንደር- ምድረገነት/አብደራፊ/ በግሉ መኪና እየተጓዘ ባለበት ወቅት ማንነታቸው ባልታወቁ ታጣቂዎች በተተኮሰበት ጥይት ተመትቶ የወልቃይት ጠገዴ አማራ ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ መስራችና አባል፣ የሀገሩን ሰንደቅ በደምና በላብ ያስጠበቀው ጀግና ልበደፋር አባታችን አቶ ወረታው አዛናው በድንገት ከመካከላችን በሞት ተለይቶናል። የቀብር ስነ ስርአቱም መላ ቤተ ሰቦቹ፣ የወልቃይት ጠገዴ አስመላሽ ኮሚቴ አባላትና የዞኑ አመራሮች በተገኙበት ተወልዶ ባደገበት ወልቃይት ብላምባ ደብረ ገነት መድሐኔ አለም ቤተ ክርስቲያን ጥር15/2017 ዓ.ም ተፈጽሟል ።
በወልቃይት ጠገዴ አማራ የማንነትና ወሰን ኮሚቴ አባል በወንድማችን ወረታ አዛናው የተፈፀመው ግድያ ለአማራዊ ማንነታችን ለማጽናት በሚደረግ ትግል ላይ የተቃጣ ጥቃት እንጂ ግለሰባዊ ግድያ አድርገን አንመለከተውም። የማንነትና የወሰን ኮሚቴ አባላትና የወ/ጠ/ሰ/ሁመራ ዞን አመራሮች ወንጀለኞችን አሳዶ ለመያዝና የህግ የበላይነት እንዲከበር ከአከባቢው አስተዳደር አመራሮች እና ህዝብ ጋር በመተባበር የጋራ ጠላት የሆኑት በወንድማችን ታጋይ ወረታ አዛናው ላይ ግድያ የፈፀሙ ወንጀለኞች ለህግ እንዲቀርቡ በትብብር የምንሰራ መሆኑን እንገልፃለን!
ለቤተሰቡ፣ ለወዳጆቹና ለትግል አጋሮቹ መፅናናትን እንመኛለን ።
በደም የፈካ ነፃነት እስከ ሞት የታመነ አማራነት!!
የወልቃይት ጠገዴ አማራ ማንነት ኮሚቴ
ጥር 17/2017ዐ/ም
ሁመራ-አማራ-ኢትዮዽያ
የአርሚ 92 ኮር 2 አመራር የሆነው አብርሃ ሃይሉ ተካ 2 ፓትሮል ይዞ በመምጣት ጥይት ተኩሶ ሰልፉን ከበተኑት በኋላ የውቅሮ ወጣቶችን በዱላ ቀጥቅጠዋቸዋል።
👆 ይህ ወጣት አንዱ ነው። አብዛኞቹ ደግሞ ህክምና ላይ ናቸው ተብሏል
"ደግነቱ እኛ ድመቶቹ አለን " አላለችም ?
(👆 ቪዲዮ - ውሻው ርቦታል ።እፊት ለፊቱ የተቀመጠውን ስጋ እንዳይበላ ደግሞ ካሜራው ስጋው ላይ አነጣጥሯል።ውሻው አስቦ አስቦ አንድ መላ ዘየደ ! ውሻው ውሮዬን ከመጤፍ ባለመቁጠሩ በከባዱ መሳቱን የተረዳው እጅግ ዘግይቶ ይመስለኛል - 😂 )
እስኪ....Goodnight !
የወልቃይት ጠገዴ የአማራ ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ እና ያካባቢው ህዝቡ ከወያኔ ጋር መቼም ቢሆን ሊመክርና ሊተባበር እንደማይችል ስለታወቀ ቀድሞ የሁለቱም ስም ሊጠለሽና ኮርነር ሊደረጉ የግድ አስፈላጊ ነበርና በያቅጣጫው ተዘመተባቸው።
በ"ታፔላ ፅሑፍ" ሳይቀር ተዘመተባቸው።
አሁን ግልጥልጥ ብለው መጡ።
ከወያኔ ጋር ምክር አያዋጣህም።እንኳን ላንተ ይቅርና ለመላ ኢትዮጵያም አልበጀም - አይበጅምም ! አይ ካልክ ግን መክረህ እየው ከማለት ውጪ ምን ይባላል ?
ከወያኔ ጋር መክሮ መጨረሻውን ያየ ሰው ግን እንጃ ...........😎
(ከዚህ በፊት ከወያኔ ጋራ ተመክሮ የማያውቅ አስመሰልከውሳ ?)
Trump after Anthony Fauci and John Bolton security detail were removed: "They can hire their own security, they all made a lot of money."
የኮቪድ ተረክና ክትባቱ አስፈፃሚ ተከፋይ ኖሯል ለካ - ጨካኝ ‼️
የመቀሌ ባንክ ቤቶች ዛሬ በህዝብ ተጣበው ነው የዋሉት።የወያኔ ወታደራዊ አዛዦች መግለጫ ከተሰማበት ሰዓት ጀምሮ የከተማዋ ነዋሪ ሩዝ ማኮሮኒ ፓስታ ዘይት ከሰልና መሰል የፍጆታ ዕቃዎችን ሲሸምት ውሏልም ተብሏል።
-----
በነገራችን ላይ እኔ እዚህ ላይ የምፅፋቸው በሙሉ ቀላል ቢመስሉም ረቂቅ እውነቶችን ግልፅ የሚያደርጉ ናቸው።
እስኪ ለእግረ መንገድ ...............👇
"የወያኔ ታጣቂዎች በአ.ሽ.አ ቡድን (አድዋ ሽሬ አክሱም ተወላጆች) የበላይነት የሚመሩና የሚዘወሩ ናቸው።
ከእነዚህ ከሶስቱ መካከል ደግሞ የአድዋ ተወላጆቹ የበላይ በላይ ሆነው በበላይነት ሰራዊቱን ይዘውሩታል።
እዚህ ላይም አያበቃም ።ከአድዋዎቹ ተወላጆች መካከል ደግሞ "የእዳጋ ዓርቢ" ተወላጆቹ የበላይ በላይ በላይ ሆነው ሰራዊቱን በበላይነት ይዘውሩታል።
ከወያኔ ወታደራዊ አዛዦች መካከል 50+ ጄኔራሎች የእዳጋ ዓርቢ ተወላጆች ናቸው።የእዳጋ ዓርቢ ህዝብ ቁጥር ግን 3000 አይሞላም 😎
"The only reason , I know , to ask for a pardon is because you think you've committed a crime"
- Adam Kinsinger in 2022
- ባይደን በመጨረሻው የዋይት ሃውስ ቆይታው pardon ከቸራቸው ሰዎች መካከል አንዱ ነው።
😂
በነገራችን በዚህ የወያኔ አዛዦች ስብሰባ ላይ የአድዋና የአክሱም ተወላጅ ያልሆኑ ወደ 20 የሚጠጉ ጄኔራሎች ስብሰባውን ረግጠው ወጥተዋል።
አሁን ገብረአዴት ያነበበው የአቋም መግለጫ የአ.ሸ.አ (አድዋ ሽሬ አክሱም) ተወላጅ ወታደራዊ አዛዦች የወሰኑት ነው።
ሂድ እንግዲህ .....
/// የኢትዮጵያ ፌዴራል መንግስትና የምርጫ ቦርድ የትግራይን ህዝብ ወደ ባርነትና ጥፋት ለመዳረግ የተለያዩ ሴራዎችን እየሸረቡ ነው።ከሴራዎቹ መካከልም የህወሓትን ህጋዊ ሰውነት ላለመመለስ እየተደረገ ያለው ሴራ አንዱ ነው። ///
- ከደቂቃዎች በፊት የህወሓት ቁጥጥር ኮሚሾን ካወጣው መግለጫ
ሰበር መረጃ
የወያኔ ወታደራዊ አመራሮች ስብሰባ ላይ ሰንብተው ነበር።በዚህም መሠረት በኮር አመራሮች የድምፅ ብልጫ መሠረት ትግራይ በደብረፅዮን አንጃ መመራት አለባት ብለው መወሰናቸው ታውቋል።
ያው የቮድካው መንግስት ያበቃለት ይመስላል። መፈንቅለ መንግስት - is on the making .
በነገራችን ላይ የወያኔ ጦር ሰራዊት በደረጃ የተዋቀረው
-1- በግምባር
-2- በአርሚ
-3- በኮር
-4- በክ/ጦር
... እያለ ነው የሚቀጥለው
በዚህም መሰረት የኮር አዛዦቹ የግምባርና የአርሚ አመራሮችን በድምፅ ዘርረው ነው ውሳኔውን ያሳለፉት !
ሞን'ጮ'ሪኖ ከወታደራዊ አመራሮች መካከል የኮር አዛዦቹን ለይታ ለተከታታይ ቀናት ስትሰበሰብና ኦሬንቴሽን ስትሰጥ ሰንብታ ነበር -ጥረቷ ይኼውና ፍሬ አፍርቶላታል።
P.s
በነገራችን ላይ ወታደራዊ ውሳኔዎችና ዘመቻዎች በድምፅ ብልጫ ሲፈፀሙ ለመጀመሪያ ጊዜ የሰማሁት አሁን ነው።
በሁለተኛው የአለም ጦርነት ወቅት ጀርመኖቹ ኖርማንዲ ላይ ምሽጋቸውን (banker) ሲገነቡ የሰሩት ነው።
እነ "ነውር ጌጡ" ... on ma mind😂
ከወልቃይት ጠገዴ ጠለምት አማራ ምሁራን ማህበር በወቅታዊ ሁኔታ አስመለክቶ የተሰጠ መግለጫ
የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ስር በመተዳደር ላይ ይገኛል፡፡ ዞኑ በክልሉ አንፃራዊ ሰላም እና መረጋጋት ከሚታይባቸው አከባቢዎች በግንባር ቀደምትነት ከሚጠቀሱት አንዱ ነው፡፡ አከባቢው 1983 ዓ/ም በህውኃት መራሹ ኢህአዴግ መንግስት ትግራይ ክልል ተብሎ በሚጠራዉ ክልል፤ ህዳር 29/1987 የፀደቀው የኢፌዴሪ ህገ መንግስት ተግባራዊ ከመደረጉ በፊት፣ ያለ ህዝቡ ፍላጎት እና ፈቃድ ህገ-ወጥ በሆነ መልኩ መካለሉ የሚታወቅ ነው፡፡ ከለውጡ በኃላ ጥቅምት 24/2013 ጀምሮ በተካሄደው የህግ ማስከበር ዘመቻ ማህበረሰቡ ከትህነግ-ወያኔ ነጻ በመሆን፤ ተጠሪነቱ ለአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የሆነ ከወልቃይት ጠገዴ ማንነት እና ወሰን አስመላሽ ኮሚቴ መሰረት ያደረገ የዞን አስተዳደር በማደራጀት ራሱን በራሱ እያሰተዳደረ ይገኛል፡፡
ትህነግ-ህውኃት በፕሪቶርያው የዘላቂ ሰላም እና ተኩስ ማቆም ስምምነት በኋላ በ30 ቀናት ውስጥ ትጥቅ በመፍታት አከባቢው ወደ ዘላቂ ሰላም፣ መልሶ ግንባታ/Rehabilitation and restoration/፣ ሀገራዊ መግባባት እና አገር ግንባታ እንዲመለስ ግዴታውን መወጣት ሲገባው፤ ላለፉት 40 ዓመታት በወልቃይት ጠገዴ ማህበረሰብ ላይ አማራዊ ማንነቱን ምክንያት በማድረግ እና ለታላቋ ሀገረ ትግራይ ምስረታ ምቹ ይሆን ዘንድ የፈፀመው የዘር ማፅዳት ወንጀል በካደ መልኩ ብቻ ሳይሆን በቀጣይ ለመፈፀም ያቀዱትን ዘር ፍጅት እቅድ በሚያሳብቅ መልኩ፤ በሀገሪቱ ህግ እና ስርዓት የሌለ በስመ ተፈናቃይ የክልል ሉዓላዊነት እና ግዛት ማስመለስ በሚል የውንብድና እና ማጭበርበር ባህርይ በመጠቀም በወልቃይት ጠገዴ ማህበረሰብ የዳግም ወረራ እና ጦርነት ስጋት ፈጥሮ ይገኛል፡፡
የወልቃይት ጠገዴ ማህበረሰብ ህግ እና ስርዓት ተከትሎ የወልቃይት ጠገዴ ማንነት እና ወሰን አስመላሽ ኮሚቴ በማቋቋም ህጋዊ እና ፍትኃዊ የሆነ የአማራ ማንነት ጥያቄ ለፌደሬሽን ምክር ቤት እና በወቅቱ ለነበረው የትግራይ ክልል መንግስት ታህሳስ 7/2008 ዓ/ም ለትግራይ ክልል ርዕሰ መስተዳደር፣ ለትግራይ ክልል ህውኃት ፅ/ቤት፣ ለትግራይ ክልል ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ፅ/ቤት በፅሁፍ እና በአካል በመቅረብ ጥያቄውን አቅርበዋል፡፡ ሆኖም ግን ይህ ተከትሎ የሰጠው ምላሽ አፈና እና ግድያ ነበር፡፡ ሐምሌ 05/2008 ዓ/ም የወልቃይት ጠገዴ ወሰን እና አስመላሽ ኮሚቴ በጎንደር ከተማ አመራሩ ሙሉ በሙሉ ለማጥፋት እና በሽብር ወንጀል በመክሰስ እስከ ለውጡ ጊዜ ድረስ የፖለቲካ እስረኛ ማድረጉ የሚታወስ ነው፡፡
በለውጡ መንግስት በመላ ሀገሪቱ የነበሩ የማንነት እና ወሰን ጥያቄዎችን ምላሽ ለመስጠት የአስተዳደር ወሰን እና የማንነት ጉዳዮች ኮምሽን የተቋቋመ ሲሆን ትህነግ-ወያኔ በወልቃይት ጠገዴ አማራ ማህበረሰብ ያደረሰውን ዘር ማፅዳት ወንጀል ተጠያቂ ላለመሆን ይህን በሀገሪቱ ፓርላማ በአዋጅ የተቋቋመውን ኮሚሽን በ100% ድምፅ ውድቅ በማድረግ ወደ ክልሉ ገብቶ ምንም ዓይነት ስራ እንዳይሰራ፤ ለህግ እና ስርዓት ተገዢ አለመሆኑ አስመስክሮ አልፏል፡፡
ትህነግ-ህውኃት ለውጡን ባለመቀበል ክልላዊ ዲፋክቶ ስቴት [Defacto state] በሚመስል ሁኔታ ጥቅምት 24/2013 ዓ/ም ማዕከላዊ መንግስቱን በኃይል ለመቆጣጠር እና ለ30 ዓመታት የነበረው አንባገነናዊ የኢህአዴግ ስርዓት ለመመለስ ጦር መስበቁ የሚታወስ ነው፡፡ ይህን ተከትሎ በተለይ በወልቃይት ጠገዴ አማራ ማህበረሰብ ማንነት ተኮር የማይካድራ ጅምላ ጭፍጨፋ እና የሁመራ ንፁኃን አሰቃቂ ግድያ ከመፈፀም ባሻገር፤ ሀገሪቱ ለ2 ዓመታት የዘለቀ የእርስበርስ ጦርነት በመክተት ከባድ አገራዊ ኪሳራ አስከትሏል፡፡ ጦርነቱን ተከትሎ የፕሪቶርያ ስምምነት መፈራረም ቢቻልም፤ ትህነግ-ህውኃት የስምምነቱ ዋና ግብ እና ትኩረት የነበረው DDR በታቀደው መልኩ ለሁለት ዓመታት ሳይፈፀም እንዲቆይ ከማድረግ አልፎ በቅርቡ የተጀመረው የትግራይ ቀድሞ ተዋጊዎች ትጥቅ ማስፈታት ሂደት እንዳይቀጥል <<ወፍሪ እምቢታ>> የእምቢተኝነት ዘመቻ የተሰኘ የአመፅ እና ግርግር ተግባር ላይ ይገኛል፡፡
ይህ የአመፅ እና ግርግር ተግባር መላው የኢትዮጵያ ህዝብ እና ሰላም ወዳድ የሆነው የዓለም ማህበረሰብ ሊቃወመው ይገባል፡፡ እንዲሁም የኤፌዴሪ መንግስት የወልቃይት ጠገዴ እና ጠለምት አማራ ማህበረሰብ የዘመናት የአማራ ማንነት ጥያቄ ምላሽ/እዉቅና በመስጠት እና በጀት በመፍቀድ ሀገሪቱ የጀመረችውን የሰላም ግንባታ የተሟላ እንዲሆን ጥሪያችን እያቀረብን በስመ ተፈናቃይ የሚሰበከውን <<የትግራይ ሉዓላዊ ግዛት>> የተሰኘ የውሸት ፕሮፖጋንዳ ዘመቻ፣ ህዝባችን ነፃ ለማውጣት በሚል ድራማ ሆነ የመገንጠል ፍላጎት ህዝባችንን ስለማይመለከተው ዳግም ዘር ፍጅት ለመፈፀም የሚደረግ ማንኛውንም እንቅስቃሴ እያወገዝን የህዝባችን የመኖር ተፈጥሯዊ መብቱ፣ ማንነቱ እና ኢትዮጵያዊነቱን ለመጠበቅ ማንኛውንም መስዋዕትነት ለመክፈል ዝግጁ እንዲሆን ለማሳወቅ እንወዳለን፡፡
የማህበረሰባችን ዘርፈ-ብዙ ችግሮች ለመፍታት እንተጋለን!!!
የወልቃይት ጠገዴ ጠለምት አማራ ምሁራን ማህበር
ጥር/2017 ዓ/ም
ሁመራ
ውቅሮ 👆
በተለያዩ የትግራይ ከተሞች የፀጥታ ሃይሉ እና ወጣቶች መካከል ሃይል የተቀላቀለባቸው ግጭቶች እየተስተዋሉ ነው ።
ዛሬ ጧት 12 ሰዓት ጀምሮ የውቅሮ ወጣቶች የወያኔ አዛዦችን በመቃወም ሰልፍ ቢወጡም ሰልፉን ጥይት በመተኮስ ከበተኑት በኋላ እስካሁን ድረስ በርካታ ወጣቶችን እያሰሯቸው ነው ተብሏል።
በላይ ማናዬ ግን እንዲሁ "Wash" የምትደረግ የዋህ ነገር ነህ ልበል ?
ከወያኔ ጋር መክረህ መጨረሻ ላይ በውጤቱ ምን ልታተርፍ አስበህ ነው ?
በቃሉ አላምረው ነው የለኮሰህ ?
ስትሞቅ ሰንብተህ ነበር።ዛሬ ገነፈልክ
- Once tplf , always stupid ‼️
መግለጫ ያወጡት የወያኔ ወታደራዊ አመራሮች ..
- የቀበሯቸውን መድፎችና መሰል ከባድ መሳሪያዎችን እየቆፈሩ ማውጣት ጀምረዋል
-በተለያዩ ግንባሮች ምሽጎችን በመቆፈር ተጠምደዋል
- የሚሊሻ ሰራዊት አባላትን ከፊሉን እያባበሉ ከፊሉን ደግሞ እያስገደዱ የታጠቁትን መሳሪያ እየተረከቧቸው ነው።
- በራማና ዛላምበሳ በኩል ከኤርትራ የጦር መሳሪያዎችን በገፍ እያስገቡ ነው
Candace Owens promised to publish evidence that Macron's wife is a man.
Owens said on X that she would confirm her words on January 30 and publish information.
She contacted Macron and asked him to answer her honestly whether Brigitte Macron is a biological woman or a man, and also asked to provide a photo of the first lady in her youth, before publishing the "investigation" material.
Last September, two women who claimed that Macron's wife was transgender were sentenced to a fine of 500 euros for "public slander".
😂😂
የእናቴ ቀሚስ ጠለፈኝ 😂
//ሩሲያ hypersonic missile የሰራችው በኦባማ አገዛዝ ጊዜ ከአሜሪካ በሰረቀችው ቀመር ነው//
- ትራምፕ
//መቼም ቢሰረቅ የሚሰረቀው የቀመሩ ኮፒ ነው። ኦርጂናሉ ቀመር ከእርስዎ ጋር አለ።እስኪ ሰርተው ያሳዩን//
- እኔ ከጦቢያ😂😂😂
// በተቻለ መጠን ደም ሳይፈስ ሰልፉ እንዳይደረግ እንሰራለን።ይህ የማይቻል ከሆነ ግን አማራጭ አይኖረንም - ጥይቶቻችንን እላያቸው ላይ እናፈሰዋለን //
-የትግራይ ደቡባዊ ዞን ህዝብ የወያኔ ወታደራዊ አዛዦችን በመቃወም ለነገ የተቃውሞ ሰልፍ ለማድረግ መወሰኑን ተከትሎ ጄኔራል ዮሃንስ(መዲድ) የተባለው የደቡብ ግምባር አዛዥ ዛሬ አዲጉዶም ከተማ ውስጥ የሬጅመንት አዛዦችን ሰብስቦ ከተናገረው።
ምንጭ - ደስዬ አሸናፊ
ውሳኔውን የምትደግፉ ሲባል እጆች ሹግ (ችቦ) መስለው ወጡ -
የምትቃወሙ ሲባል አንገቶች ተጣመሙ - 😂
የወያኔ ወታደራዊ አዛዦች ቮድካውን አይወዱትም ‼️
ጌቾ የይምሰል ጨዋታው ይቅርብህ - ይልቅ የሚመስልህን ተቀላቀል 😎
👆👆 የፕሪቶሪያው ስምምነት - -
===========
- ወያኔን ከመሰልቀጥ አድኖ
ዳግም የአገር በሽታነቱን ያስቀጠለ ስምምነት .....
( ወያኔን ብላችሁ ስንቱን አሸሻችሁት ይሆን ? )
ሰበር - መረጃ
(በወያኔ መንደር መፈንቅለ መንግስት ...on the making )
"14ኛውን የህወሓት ጉባኤ ያደረገው አንጃ በወሰነው ውሳኔ መሠረት የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደርን አስተካክሎ የማዋቀሩ ስራ ባስቸኳይ እንዲተገበር ወስነናል"
-ከደቂቃዎች በፊት ከተሰጠው የወያኔ ወታደራዊ አዛዦች መግለጫ
-
የወያኔ ወታደራዊ አዛዦች የደብረፅዮን፣ የሞንጆሪኖ ና የአለም ገብረዋህድ አንጃ ያደረገውን ጉባኤ ተቀብለው ውግንናቸውን የገለፁበት ውሳኔ ነው።
አሁን ጥያቄው የቮድካው አንጃ ይሄንን የወታደሮቹን ውሳኔ በፀጋ ይቀበለዋል ወይ የሚለው ነው።
እንግዴህ ከወደ ትግራይ ግድም ተከታታይ መግለጫዎች ይጠበቃሉ ማለት ነው !
እፀድቅ ብዬ ባዝላት ተንጠልጥላ ቀረች 😂😂
// ትግራይ ያልተሳተፈችበት እና
የምርጫ ቦርዱ ያሻውን እንዲያደርግ የሚፈቅድ አዲስ ህግ በማፅደቅ ህወሓት ህጋዊ ሰውነቱ ወደነበረበት እንዲመለስለት ለቦርዱ ላቀረበው ጥያቄ አዎንታዊ ምላሽ እንዳያገኝ ተደርጓል።በወቅቱ ከቦርዱ የተሰጠው ምላሽ ከነሐሴ 3/ 2016 ዓም ጀምሮ ልክ እንደአዲስ ፓርቲ የተመዘገበ መሆኑን የሚገልፅ እንደነበር የሚታወስ ነው //
የህወሓት የቁጥጥር ኮሚሽን
P.s-
ታስታውሱ እንደሆነ ህወሓትን ህጋዊ ለማድረግ ታስቦ በፓርላማው የፀደቀ ህግ ነበር።እሱን ህግ ነው እንግዲህ "ትግራይ ያልተሳተፈችበት ነው" የሚሉት ። ህጉ የፀደቀ ጊዜ ግን ህወሓት ከሁሉም ቀድሞ መግለጫ በማውጣት ህጉን ያወደሰና የባረከ አልነበረም።
ጆሮዬ ነው ወይንስ ....ጆሮዬ ?😂
" አሁን ሌሎቹ ፓርቲዎች በሙሉ ከስመው ብልፅግና ነው ያለው።ስለዚህ ግጥሚያው ያለው በTPLF እና በህወሐት መካከል ነው።ብልፅግና የ"ፋሺስት" ፓርቲ ነው።"
- ዶ/ር ገብረአብ ባርናባስ
(የደብረፅዮኑ አንጃ የወያኔ አባል)
የወልቃይት ጠገዴ እርሻ ልማት ስራ አስኪያጅ ወንድማችን ነጋ ባንትይሁን ከሁመራ ለቃብቲያ ዘርባቢት ጠጠር መንገድ
100,000 ብር ገቢ አድርጓል።
ከልብ እናመሠግናለን❗️
በወጣ ይተካ
---------------
ሁላችሁንም የቃብቲያ ዘርባቢት መንገድ ልማት ተሳታፊ እንሁን
የመንገድ ፕሮጀክቱ ሒሳብ ቁጥሮች
KABTIYA ZERBABIT ROAD CONSTRACTION
👉ንግድ ባንክ 1000668208065
👉አቢሲኒያ ባንክ 215871363
👉አማራ ባንክ 9900039470075
👉አባይ ባንክ 221-111-11717086-13
#kabtiyahumeraweredap