ya_muhammad_saw | Unsorted

Telegram-канал ya_muhammad_saw - ❤ያ ሙሃመድ(ሰ.ዐ.ወ)❤

-

All YOU WANT TO KNOW ABOUT ISLAM IS HERE JUST JOIN AND ENJOY🔥 ⚡️GROUP👇👇 @ya_resulelah_saw @ya_resulelah_saw @ya_resulelah_saw ✍️For any comment👉 @faruqa_11

Subscribe to a channel

❤ያ ሙሃመድ(ሰ.ዐ.ወ)❤

🗞 የሰው ልጅ ቁርአንን በቀራና
ባስተነተነ ቁጥር ልቡ ውስጥ
የአላህ ፍቅር ይጨምርለታል ..

๏ የሚወደው ነገር ሁሉ
ቁርአን ይሆናል ፣ በመቅራቱ ይደሰታል
በማጣቱም ያዝናል!
አላህ ከቁርአን ሰዎች ያድርገን


የቁርአን ሰዎች የአላህ ቤተሰቦች ናቸው 😍😍

@ya_muhammad_saw

Читать полностью…

❤ያ ሙሃመድ(ሰ.ዐ.ወ)❤

ሮናልዶ ሱጁድ ሲወርድ ❤️

@ya_muhammad_saw

Читать полностью…

❤ያ ሙሃመድ(ሰ.ዐ.ወ)❤

⇘ሰው ሁሉ ተሳሳች ነው👒

‹‹ረሱል ﷺ እንዲህ ብለዋል ፦ " ባትወነጅሉ ኖሮ እናንተን አጥፍቶ፣ እያጠፉ የአላህን ምህረት እየጠየቁ የሚምራቸው ሕዝቦች ይፈጥር ነበር"›› ሙስሊም ዘግበውታል🍃

»ሰው ሁሉ ተሳሳች ነው ፣ስህተት ተፈጥሯዊ ተግባሩ ነው፣ ከነርሱ በላጩ ደግሞ ተመላሾች ናቸው።

‹‹ረሱል ﷺ እንዲህ ብለዋል ፦ "የአደም ልጅ ሁሉ ተሳሳች ነው ከተሳሳቾች ሁሉ የበለጠ ደግሞ ንስሃ ገቢዎች ናቸው"›› ቲርሚዚይ ዘግበውታል

»አንተ ስታምፀው እርሱ ሊምርህ ጸጸትህን በናፍቆት ይጠብቃል! አንተስ ምህረቱን አልናፈክምን?

««አላህም ቃል ገባ ፦

🍃""ባሪያዎቼ ሆይ! በየእለቱ በቀንና በሌሊት ወንጀል ትፈፅማላችሁ እኔ ሁሉንም ወንጀል እምራለሁ ። እናም ወንጀላችንን ማረን በሉኝ እምራችኃለሁ።""


🍂رَبَّنَا فَاغْفِرْ لَنَا ذُنُوبَنَا وَكَفِّرْ عَنَّا سَيِّئَاتِنَا وَتَوَفَّنَا مَعَ الْأَبْرَارِ

🤲«ጌታችን ሆይ! ኃጢአቶቻችንንም ለኛ ማር፡፡ ክፉ ሥራዎቻችንንም ከኛ አብስ፡፡ ከንጹሖቹም ሰዎች ጋር ግደለን፤» (አሊ-ዒምራን :193)

@ya_muhammad_saw


👒👒_____________🌿🌿

Читать полностью…

❤ያ ሙሃመድ(ሰ.ዐ.ወ)❤

✨ሰልማን አል-ፋሪሲይ (ረ.ዐ) እንዳወሱት ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡-

‹‹በጁምዓ ቀን ገላውን የታጠበ፤ በተቻለው መጠን ንፅህናውን የጠበቀ፤ (ፀጉሩን) ቅባት የተቀባ፤ ከዚያም (ወደ መስጊድ) የሄደ በሁለት ሰዎች መካከልም ሳይለያይ አላህ የጻፈለትን ያህል ከሰገደ፤ ከዚያም ኢማሙ ሲናገር ዝም ካለ (በወቅቱ ካለው) ጁሙዓና ከበፊቱ ባለው ጁሙዓ መካከል የፈፀማቸውን ወንጀሎች አላህ ይምረዋል፡፡
(ቡኻሪ ዘግበውታል)

🇪🇹ሀገራችን ሰላም የሚሆንበት
የታመመ የሚድንበት
ያሰብነው ሁሉ የሚሳከበት ጁምዐ ይሁንልን 🤲

@ya_muhammad_saw

Читать полностью…

❤ያ ሙሃመድ(ሰ.ዐ.ወ)❤

የማለዳ ስንቅ ለቀልብዎ❤️

#ቁርኣን

@ya_muhammad_saw

Читать полностью…

❤ያ ሙሃመድ(ሰ.ዐ.ወ)❤

➧.ቀለሙ ተነስቶ ወረቀቱ በደረቀ ጉዳይ አትጨነቅ።

ላንተ ያለው ሁሉ ቀኑ ፈጠነም ዘገየም መምጣቱ አይቀሬ ነው። «ይሆናል» በተባለው ጊዜ የመጣ ነገር ሁሉ ደግሞ ለበጎ ነው‼️

....በመሄዱ ላይ የቆረጠ
እሱን በመርሳት ላይ ቁረጥ/ወስን
ሳታውቀው በፊት ደስተኛ ሆነህ
ትኖር እንደነበርም አትርሳ… 🍁✨

@ya_muhammad_saw

Читать полностью…

❤ያ ሙሃመድ(ሰ.ዐ.ወ)❤

ሰላት ዕድሜ ቢሆን ማሰላመት ሞት ነው ,..
ጥያቄው እኛስ በትክክል ሰግደናል ወይ?
.
መወለድ አዛን ቢሆን ሞት ኢቃማ ነው...
ጥያቄው እኛስ ጠሃራ ላይ ነን ወይ?
.
የዚህች ዓለም ሕይወት የዚህኑ ያህል አጭር ናት...
ስለዚህ ሁሌም መዘጋጀት ግድ ይላል። ተዘጋጅቶ መተኛት፣ ተዘጋጅቶ መነሳት
ቢስሚከ ረቢ ወዶዕቱ ጀንቢ

@ya_muhammad_saw

Читать полностью…

❤ያ ሙሃመድ(ሰ.ዐ.ወ)❤

ጥሩ ጓደኛና ሪዝቅ የአላህ ስጦታ ናቸው🎁

Читать полностью…

❤ያ ሙሃመድ(ሰ.ዐ.ወ)❤

ዕድሜህ በሄደ ቁጥር በዚህች ዓለም ሕይወት ላይ ያዘንክባቸው ነገሮች ሁሉ ያን ያህል ዋጋ ሊሠጣቸው እንደማይገባ ትረዳለህ። ዱንያ እንዲሁ ናት። ታሸንፋለህ ትሸነፋለህ፣ ታዝናለህ ትስቃለህ፣ ታገኛለህ ታጣለህ፣ ሙሲባ ይመጣል ይሄዳል፣ ሰው ይሄዳል ይተካል፣ ዱንያ ላይ ለዘላለሙ አብሮህ የሚዘልቅ መልካምም ሆነ መጥፎ ነገር የለም። የነገሮች መወለድና መሞት ያለ ነዉና ብዙ አትገረም።
ቀናችሁን ከምትጀምሩባቸው ነገሮች ሁሉ ምርጦቹ ዚክር፣ ሶላትና ዱዓ ናቸው።

@ya_muhammad_saw

Читать полностью…

❤ያ ሙሃመድ(ሰ.ዐ.ወ)❤

✨የሰዎች ልብ ንፁህና መልካም
      እንዲሆንልህ ከፈለግክ  ....

....አንተም ለነሱ ልብህን ንፁህና
     መልካም አድርግላቸው

(وَلَا تَسْتَوِي الْحَسَنَةُ وَلَا السَّيِّئَةُ ۚ ادْفَعْ بِالَّتِي هِيَ أَحْسَنُ فَإِذَا الَّذِي بَيْنَكَ وَبَيْنَهُ عَدَاوَةٌ كَأَنَّهُ وَلِيٌّ حَمِيمٌ)

" መልካሚቱና ክፉይቱም (ጸባይ) አይተካከሉም:: በዚያች እርሷ መልካም በሆነችው ጸባይ (መጥፎይቱን) ገፍትር :: ያን ጊዜ ያ ባንተና በእርሱ መካከል ጠብ ያለው ሰው እርሱ ልክ እንደ አዛኝ ዘመድ ይሆናል፡፡"
      📚[ፉሲለት 34]

....መልካምነት ከራስ ነው የሚጀምረው
መልካም ስትሆን በአጠገብህ የሚገኙት
መልካም ይሆኑልሃል

መጥፎ ስትሆንም በአጠገብህ የሚገኙት. መጥፎ ይሆኑብሃል ::

...ጥሩ ሰው ጠፋ ከማለት አንተ
      ጥሩ ሆነህ የመጀመሪያው ሁን

@ya_muhammad_saw

Читать полностью…

❤ያ ሙሃመድ(ሰ.ዐ.ወ)❤

የፈጅር ሶላትህን ስለምን ተሳልፋለህ?
ተነስ፣ በርታ፣ ስገድ፣ ዱዓ አድርግ...
ስኬት፣ ደስታ፣ መረጋጋት፣... ከደጃፍ ይመጣሉ።

ኢንሻ አሏ

@ya_muhammad_saw

Читать полностью…

❤ያ ሙሃመድ(ሰ.ዐ.ወ)❤

★"ለማሳካት ደፋ ቀና የምንልለት ሕልም ይኖረናል፡

..በለሊት ሶላትና ልባዊ በሆነ ዱአ እንበርታ የሌሊት ቀስቶች ኢላማቸውን አይስቱምና፡፡

★"ልንደርስበት ያሰብንው ቦታና ታጥቀን የተነሳንለት ..አላማ ይኖረናል፦በዱአ እንጠንክር ዱአ ትልቁ የምእመናን መሳሪያ ነውና፡፡

★"ያስጨነቀንና መላ መፍትሔ ያጣንለት ሀሳብ ይኖረናል በአሏህ (ሱ ወ ) እንወከል *እንመካ* በሱ የሚተማመኑትን አላህ ጥሎ አይጥልምና፡፡

@ya_muhammad_saw

Читать полностью…

❤ያ ሙሃመድ(ሰ.ዐ.ወ)❤

ጁምዓ.....

ረሱሉና ﷺ እንዲህ ብለውናል :

" ጁምዓ ቀን እኔ ላይ ሰለዋት ማውረድን አብዙ ..
የኡመቴ ሰለዋት ሁሌ ጁምዓ ቀን ይቀርብልኛል..
እኔ ላይ ያወረደው ሰለዋቱ የበዛ የበለጠ ወደኔ ቅርብ ይሆናል "
" أَكْثِرُوا عليَّ مِنَ الصَّلاةِ في يومِ الجمعةِ ؛ فإنَّ صَلاةَ أُمَّتي تُعْرَضُ عليَّ في كلِّ يومِ جُمُعَةٍ ، فمَنْ كان أكثرَهُمْ عليَّ صَلاةً ؛ كان أَقْرَبَهُمْ مِنِّي مَنْزِلَةً ."
رواه البيهقي

ሰሉ አለ ነቢ
ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም

@ya_muhammad_saw

Читать полностью…

❤ያ ሙሃመድ(ሰ.ዐ.ወ)❤

የሱብሂ ሰላትና ሰይጣን

ኢማኖን ለመጠበቅ የሱብሂ ሰላት ወሳኘ ቦታ ይይዛል ይህ ሰላት በስራ   ምክንያት ወይም በሌላ ነገር ማሳበብ አይቻልም ከስንፍና ውጪ.

🌈ሰይጣን ሶስት መሰናክል ያደርጋል እንድታመልጠን በወቅቱ ተነስተን ኡዱ አድርገን ከሰገድናት ቀናችንን በድል ጀምረናል ማሻ አላህ ካልሆነ ግን ወሳኘ ቦታ ላይ ከባድ ነጥብ ጥለዋል በጠዋቱ ሶስት ለዜሮ እየተመሩ እንደሆነ ይረዱ.

⛅️🌤አንዱም አላማ ሰዎች ሰግደዋት በጠዋቱ ወደ ስራ እንዲሰማሩ ነው ግን እየተጠቀምንበት አይደለም.


ነብዩ ﷺ  እንዲህ አሉ

ስይጣን ስትተኙ ሶስት ቆጠሮዎችን ጭንቅላታችሁ ጀርባ ያስራል. በያንዳንዱም ቋጠሮ   እንዲህ ይላል,  ለሊቱ ረጅም ነው ተኛ. ተነስተን  አላህን ካስታወስን አንደኛው ቋጠሮ ይፈታል, ኡዱ ስናደርግ ሁለተኛው ቋጠሮ ይፈታል, ስንሰግድ ሶስተኛው ቋጠሮ ይፈታል በዚህም በመልካም ሰነልቦና ንቁ እንሆናለን አለበለዚያ   ደካማ  የተከዝን  ልብ ኖሮን ቀኑን እጀምራለን.  ብሀሪ 1091

عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ أَنَّ رَسُولَ اللَّه صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ يَعْقِدُ الشَّيْطَانُ عَلَى قَافِيَةِ رَأْسِ أَحَدِكُمْ إِذَا هُوَ نَامَ ثَلَاثَ عُقَدٍ يَضْرِبُ كُلَّ عُقْدَةٍ عَلَيْكَ لَيْلٌ طَوِيلٌ فَارْقُدْ فَإِنْ اسْتَيْقَظَ فَذَكَرَ اللَّهَ انْحَلَّتْ عُقْدَةٌ فَإِنْ تَوَضَّأَ انْحَلَّتْ عُقْدَةٌ فَإِنْ صَلَّى انْحَلَّتْ عُقْدَةٌ فَأَصْبَحَ نَشِيطًا طَيِّبَ النَّفْسِ وَإِلَّا أَصْبَحَ خَبِيثَ النَّفْسِ كَسْلَانَ
1091 صحيح البخاري كتاب التهجد باب عقد الشيطان على قافية الرأس إذا لم يصل بالليل

@ya_muhammad_saw

Читать полностью…

❤ያ ሙሃመድ(ሰ.ዐ.ወ)❤

የማለዳ ስንቅ ለቀልብዎ❤️

#ቁርኣን

@ya_muhammad_saw❤️

Читать полностью…

❤ያ ሙሃመድ(ሰ.ዐ.ወ)❤

ﺍﻟﺤﻴﺎﺓ ﻣﺴﺘﻤﺮﺓ ﺳﻮﺍﺀ ﺿﺤﻜﺖ ﺃﻡ ﺑﻜﻴﺖ

ህይወት ቀጣይ ናት ብትስቅም ብታለቅስም....

ﻻ ﺗﺤﻤﻞ ﻧﻔﺴﻚ ﻫﻤﻮﻣﺎً ﻟﻦ ﺗﺴﺘﻔﻴﺪ ﻣﻨﻬﺎ

...ራስህን ሃሳብ አታሸክም  አይጠቅምህም እና....
ﺍﻟﻘﻠﻖ ﻻ ﻳﻤﻨﻊ ﺃﻟﻢ ﺍﻟﻐﺪ ﻭﻟﻜﻨﻪ ﻳﺴﺮﻕ ﻣﺘﻌﺔ ﺍﻟﻴﻮﻡ

ጭንቀት የነገን ህመም አይከላከልም ነገር ግን የዛሬን ደስታ ያጠፋል...

@ya_muhammad_saw

Читать полностью…

❤ያ ሙሃመድ(ሰ.ዐ.ወ)❤

#አላሁ_አክበር
አለምን እያነጋገረ ያለው የ Cristiano Ronaldo የሱጁድ ጉዳይ👌
ወደከፍታ የመቃረብ ጅማሮው ወደመሬት ከመጠጋት ነው❤
#ሱጁድ
የስጁድን ጥቅም ብታውቁ ኖሮ እስከ የውመል ቂያማ ድረስ ባልተነሳችሁ ነበር ረሱል ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም❤
ምንጭ መሀመድ ኢማም Facebook page

Читать полностью…

❤ያ ሙሃመድ(ሰ.ዐ.ወ)❤

۞إِنَّ أَكْرَمَكُمْ عِندَ اللَّهِ أَتْقَاكُم

☞አላህ ዘንድ በላጫችሁ በጣም አላህን ፈሪያችሁ ነው፡፡ ۞
(ቁርአን 49:13)

ያ አላህ! አንተን ከሚፈሩ ባሮችህ አድርገን።

🤲አሚን🤲

@ya_muhammad_saw

Читать полностью…

❤ያ ሙሃመድ(ሰ.ዐ.ወ)❤

አስቂኝ_ቂሷ

⇛አንዱ ነው…የሆነችን ሴት ማጨት ፈልገ። ነገር ግን ዉስጡ ሙሉ በሙሉ አልተቀበላትም። ልጫት ወይስ ትቅርብኝ የሚል ሃሳብ ይመላለስበታል። ይሄን ዉስጣዊ ውዝግቡን ለማስተካከል  ቁርአን ልክፈትና መጀመሪያ ዐይኖቼ ባረፉበት አንቀጽ መልእክት ላይ  በመመስረት ዉሳኔ እወስናለሁ ብሎ ወሰነ። በዚሁ መሰረት ቁርአኑን በእጆቹ ያዘና ከፍተው። ሱረቱል ጣሃ ነበር የተከፈተው። መጀመሪያ አይኖቹ ያረፉባት የጌታችን ቃልም፦
«خذها ولا تخف»
የሚለው ነበር። «ያዛት። ምንም አትፍራ።» የሚል ነው ትርጉሙ። ―አትፍራ!! ያዛት የሚለውን ቃል በማየቱ ተደስቶ ለማጨት ወሰነ። ግለሰቡ በአንድ ነገር ግን ተሸውዷል። እሱም ይች የምትያዘው ነገር ምንድን ነች የሚለውን አለማስተዋሉ ነው።

•እባብ ነች።

ሸይኽ ሷሊህ አል ዑሶይሚ

@ya_muhammad_saw

Читать полностью…

❤ያ ሙሃመድ(ሰ.ዐ.ወ)❤

ኢላሂ ..........🤲

ወዳንተ አላራምድ ያለንን የወንጀል ሸክም አራግፍልን!

@ya_muhammad_saw

Читать полностью…

❤ያ ሙሃመድ(ሰ.ዐ.ወ)❤

قُلْ هَٰذِهِ سَبِيلِي أَدْعُو إِلَى اللَّهِ ۚ عَلَىٰ بَصِيرَةٍ أَنَا وَمَنِ اتَّبَعَنِي ۖ وَسُبْحَانَ اللَّهِ وَمَا أَنَا مِنَ الْمُشْرِكِينَ

➧.ይህች መንገዴ ናት፡፡ ወደ አላህ እጠራለሁ፡፡ እኔም የተከተለኝም ሰው በግልጽ ማስረጃ ላይ ነን፡፡ ጥራትም ለአላህ ይገባው፡፡ እኔም ከአጋሪዎቹ አይደለሁም» በል፡
{108} (سورۃ يوسف)

@ya_muhammad_saw

Читать полностью…

❤ያ ሙሃመድ(ሰ.ዐ.ወ)❤

☞ አይናችን ሃላልን ለማየት ይናፍቃል፤

☞ ጆሮዋችን ሀላል የፍቅር ቃላቶችን ለመስማት ናፍቀዋል፤

☞ እጆቻችን ሃላልን ለመንካት፣ ስጦታን ለመቀበል ጓግተዋል

☞ እግሮቻችን ሃላል ላይ ለመቆም ቸኩለዋል፤

☞ አንደበታችን ከሃላል ጋር ለመጫወት ናፍቀዋል፤

☞ ጥርሳችን፣ፊታችን በሃላል ፈገግ ለማለት ተርበዋል፤

☞ ጐናችን በሃላል ጋደም ለማለት መጠባበቅ ተያይዘዋል፤

☞ ያረብ አንዳች አካላችንን ሃራም ላይ ሳታሳርፍ በሃላል ዘውጀን

አሚን ያረብ 🤲🤲

@ya_muhammad_saw
               

Читать полностью…

❤ያ ሙሃመድ(ሰ.ዐ.ወ)❤

የማለዳ ስንቅ ለቀልብዎ❤️

#ቁርኣን

@ya_muhammad_saw❤️

Читать полностью…

❤ያ ሙሃመድ(ሰ.ዐ.ወ)❤

ሱብሀነክ እውቀቱ አለምን ያካበበ ጌታ አለህ ስለምን ስትል ህይወትህን በጭንቀት ትገፋለህ?
እውነተኛ ደስታንም ከርሱ ዘንድ ታገኛለህ ወደ መንገዱ  ሂድ!!!
አላህዬ ኮ አለልህ/ሽ አብሽር☺️

عَالِمُ الْغَيْبِ وَالشَّهَادَةِ الْكَبِيرُ الْمُتَعَالِ

ሩቁንና ቅርቡን ዐዋቂ ታላቅ የላቀ ነው፡፡
                    [ሱረቱ ረእድ 9]

@ya_muhammad_saw

Читать полностью…

❤ያ ሙሃመድ(ሰ.ዐ.ወ)❤

ውዱ ነብዬ ምን እንዳሉ ታውቃላችሁ?

ማንኛውም ሙስሊም ላይ መማር ግዴታ ነው!

@ya_muhammad_saw

Читать полностью…

❤ያ ሙሃመድ(ሰ.ዐ.ወ)❤

"ሌሊቱን በመኝታው ላይ በሰላም ያሳለፈ፣ጤነኛ የሆነና ለቀኑ የሚሆን በቂ ሲሳይ ያለው ሰው ዓለምን ከነ ሁለመናዋ እንደጨበጠ ይቆጠራል።"
ረሱል( ﷺ )

ይህ ሁሉ ካለህ አልሃምዱሊላህ! በል

@ya_muhammad_saw

Читать полностью…

❤ያ ሙሃመድ(ሰ.ዐ.ወ)❤

የልብ መድረቅ አጋጥሞሃል?

.... እናም አላህ ይህንን እንዲያነሳልህ  ትፈልጋለህ? በጀነት ውስጥ የነብዩ (ሶ.ዐ.ወ) አጋር መሆን ትፈልጋለህ/ሽ ? ያን ሁሉ ከፈለግህ በአባቱ ቦታ ወላጅ አባት ሁን፣ ቸር ሁንለት፣ ራሱን አብስ፣ ቸር ሁን፣ በተጠማ ነፍሱ ላይ ፈገግታን አድርግ።

የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፡- “እኔና የቲም ልጅን የሚንከባከበው እንደ እነዚህ ሁለቱ በጀነት ውስጥ እንሆናለን ።በመረጃ ጠቋሚ እና በመሃል ጣቶቹ እያመለከቱ ” (ቡኻሪ)

አላህም እንዲህ ብሏል፡- "ምንን ይለግሱ ዘንድ ይጠይቁሃል በላቸው ከመልካም ነገር የምትለግሱት ለወላጆች፣ ለዘመዶች፣ ለየቲሞች፣ ለችግረኞችና ለመንገደኛ ነው። ከመልካምም ነገር የምትሠሩትን ሁሉ አላህ ዐዋቂ ነው።"አል-በቀራህ 215

ጥሩ መልክቶችን ይቀበሉ
መልካምነት ልክ እንደበረዶ ነው የሸፈነውን ነገር ሁሉ ያሳምራል::ሁላችንም አህለል ኸይር ነን

@ya_muhammad_saw

Читать полностью…

❤ያ ሙሃመድ(ሰ.ዐ.ወ)❤

መሳአል ኸይር ወዳጆቼ
ሰዉን ከማነወር ተጠንቀቁ
በሆነ አጋጣሚ የዚህ ዓይነት ወሬ ልትሰሙ ትችላላችሁ፡፡
 
*
*     ይሄ ጅብ ፊት ብላ በትዳር ጠያቂዋ የተሳለቀች  ያች ቆንጆ  ኮረዳ በእሣት ቃጠሎ ምክንያት ፊቷ ተበላሸ፡፡

*    “ይሄ ዘገምተኛ” ብላ የሌላን ቤተሰብ ልጅ ያነወረች ነፍሰ ጡር እናት አካለ ሥንኩል ወለደች፡፡

* “ሾፌርማ ሞቼም አላገባም” ብላ ሥራዉን ያናናቀች ያች ኮረዳ - ድንገት ሌሊት ላይ ታማ በመኪናው ሆስፒታል ወሰዳት፡፡

* ቁስል ስታክም የምትዉል ናት ጊዜ የላትም አትመጥነኝም ብሎ ያጣጣላትን ወጣት - አደጋ ደርሶበት አከመችው፡፡

* ወሬ መልቀም ከመቼ ወዲህ እንጀራ ሆነ ብላ ያሾፈችበት ሰውዬ የግል ጉዳዩዋን በዜና መልክ አሠራጭቶ ዝነኛ ሆነበት፡፡

*   ሥራሽ በየዓመቱ መፈልፈል ብቻ ነው እንዴ ብላ በጓደኛዋ ያላገጠች ኮረዳ አግብታ ዓመታት አለፉ እስካሁን አልወለደችም፡፡

*   በእግሩ አንካሳነት የሳቀው የከፍታ ዝላይ ስፖርተኛ - ጋንግሪን ይዞት እግሩ ተቆረጠ፡፡

* ሁሌም ሴት ልጅ ነው የምትወልደው ብላ በአሽሙር የወጋቻት ያች ሴት - ያላት አንድ ልጇ ሞተባት፡፡
    
 
በሰው መሳቅና ሰዉን መናቅን እስልምና አጥብቆ ይቃወማል፡፡

ሰው የከንፈሩን ዋጋ ያገኛል፣ አላህ የተበዳይ ዋጋ ይክሳል፣ ይበቀልለታል፣ ያቆይለታል እንጂ አይረሳለትም፡፡

Читать полностью…

❤ያ ሙሃመድ(ሰ.ዐ.ወ)❤

አሏህ  ሆይ !
፨ ወዳንተ ካልሆነ ልመናም ጩኸት ነው!
፨ ባንተ ላይ ካልሆነ ተስፋም ባዶነት ነው!
፨ ስላንተ ካልሆነ ንግግርም ውሸት ነው!
፨ ካንተ ጋር ካልሆነ  ንግድም ኪሣራ ነው!
፨ ስለ ክብርህ ካልሆነ ፍቅርም እንግልት ነው!
፨ በመንገድህ ካልሆነ ሞትም መከራ ነው!!

****
፨ አላህ ሲቀር ሁሉም ነገር ጠፊ ነው ።
፨ አኺራ ሲቀር ሁሉም አገር አላፊ ነው  ።
፨ ጀነት ሲቀር ሁሉም ድሎት ረጋፊ ነው  ።
፨ ጀሀነም ሲቀር ሁሉም መከራ ጤና ነው  ።

ያ አሏህ!!
ያ ረሕማን!
ያዘልጀላሊ ወልኢክራም!

ይህ ዉዴታህንና ቅበላህን ከጅለው የተነሱ ባሮችህ ድምፅ ነው።

ወደንሃል ዉደደን፤
ለመንህ ስማን፤
ተማፀንህ ተቀበለን፤

Читать полностью…

❤ያ ሙሃመድ(ሰ.ዐ.ወ)❤

አብዛኛውን ጊዜ ዱዓዎች
ስኬታማ የሚሆኑት በሚስጥር
ወደ አላህ ሲደርሱ ነው ።

إِذْ نَادَىٰ رَبَّهُ نِدَاءً خَفِيًّا

ጌታውን የምስጢርን ጥሪ በተጣራ ጊዜ (አስታውስ)፡፡
*መርየም* 3

๏ ከሰው ልጅ ጆሮ እና አይን
የምትደብቃቸው የህመሞችህ
ሹክሹክታዎች የምድር እና የሰማያት
ጌታ ይሰማልሃል ። ጌታህን በዱዓህ
አናግረው ፣ ቅሬታህን ንገረው ፣
ልመናህን አሰማው ።
ከእርሱ የሚያስደስትህንም ተጠባበቅ ።

@ya_muhammad_saw

Читать полностью…
Subscribe to a channel