#update አንዋር መስጂድ
የሟቾች ቁጥር 14 ደርሷል እየተባለ ነው አሁንም አንዋር መስጂድ ውስጥ ያሉ የተጎዱ ወንድሞች አሉ ምናልባት ከዚህ በኋላም የሟቾች ቁጥር ከዚህ ሊበልጥ ይችላል አላህ ይድረስላቸው!
.
በአላህ ዱዓ አድርጉ 😭
💜 የመጀመሪያው እቅድህ
ፈጅር ሰላት መነሳት ካልሆነ ቀሪውን
ቀንህ ብታቅድም ምንም ዋጋ የለውም
የስኬትን ጅማሮ ከስረሀልና ።
ኢንሿ አላህ ሁላችንም ለፈጅር ሰላት እንዘጋጅ!
@ya_muhammad_saw
በዛ ስፍራ ልቦች ይረጋጋሉ...
የልቦችን ሸክም ፣ የአይኖችን እንባ ፣የልቦችን ስብራት ለመጠገን ለመቅለል እግሮች ወደ ቤቱ ያመራሉ ...
ወደርሱ በተራመዱት እያንዳንዱዋ እርምጃ ...
በውስጡ በተቀመጡበት ግዜ ልክ መላኢኮች እስቲغፋር ሚጠይቁልን ..
በሚስረቀረቁ ድምፃች በየወቅቱ ወደርሱ በመጣራት ለአድማሱ ውበትን ሚያላብስን ያ ሰላማዊ ስፍራ መስጂድ!!! 🥺❤️
#የአላህ ቤት ❤️
وَمَنْ أَظْلَمُ مِمَّن مَّنَعَ مَسَاجِدَ اللَّهِ أَن يُذْكَرَ فِيهَا اسْمُهُ وَسَعَىٰ فِي خَرَابِهَا ۚ أُولَٰئِكَ مَا كَانَ لَهُمْ أَن يَدْخُلُوهَا إِلَّا خَائِفِينَ ۚ لَهُمْ فِي الدُّنْيَا خِزْيٌ وَلَهُمْ فِي الْآخِرَةِ عَذَابٌ عَظِيمٌ
የአላህንም መስጊዶች በውስጣቸው ስሙ እንዳይወሳ ከከለከለና እርሷንም በማበላሸት ከሮጠ ሰው ይበልጥ በዳይ ማነው? እነዚያ ፈሪዎች ኾነው እንጂ ለእነርሱ በቅርቢቱ ዓለም ውርደት አላቸው፡፡ ለነርሱም በመጨረሻይቱ አገር ታላቅ ቅጣት አላቸው፡፡
[ሱረቱል በቀራ 114]
/channel/ya_muhammad_saw
🗞 የሰው ልጅ ቁርአንን በቀራና
ባስተነተነ ቁጥር ልቡ ውስጥ
የአላህ ፍቅር ይጨምርለታል ..
๏ የሚወደው ነገር ሁሉ
ቁርአን ይሆናል ፣ በመቅራቱ ይደሰታል
በማጣቱም ያዝናል!
አላህ ከቁርአን ሰዎች ያድርገን
የቁርአን ሰዎች የአላህ ቤተሰቦች ናቸው 😍😍
@ya_muhammad_saw
⇘ሰው ሁሉ ተሳሳች ነው👒
‹‹ረሱል ﷺ እንዲህ ብለዋል ፦ " ባትወነጅሉ ኖሮ እናንተን አጥፍቶ፣ እያጠፉ የአላህን ምህረት እየጠየቁ የሚምራቸው ሕዝቦች ይፈጥር ነበር"›› ሙስሊም ዘግበውታል🍃
»ሰው ሁሉ ተሳሳች ነው ፣ስህተት ተፈጥሯዊ ተግባሩ ነው፣ ከነርሱ በላጩ ደግሞ ተመላሾች ናቸው።
‹‹ረሱል ﷺ እንዲህ ብለዋል ፦ "የአደም ልጅ ሁሉ ተሳሳች ነው ከተሳሳቾች ሁሉ የበለጠ ደግሞ ንስሃ ገቢዎች ናቸው"›› ቲርሚዚይ ዘግበውታል
»አንተ ስታምፀው እርሱ ሊምርህ ጸጸትህን በናፍቆት ይጠብቃል! አንተስ ምህረቱን አልናፈክምን?
««አላህም ቃል ገባ ፦
🍃""ባሪያዎቼ ሆይ! በየእለቱ በቀንና በሌሊት ወንጀል ትፈፅማላችሁ እኔ ሁሉንም ወንጀል እምራለሁ ። እናም ወንጀላችንን ማረን በሉኝ እምራችኃለሁ።""
🍂رَبَّنَا فَاغْفِرْ لَنَا ذُنُوبَنَا وَكَفِّرْ عَنَّا سَيِّئَاتِنَا وَتَوَفَّنَا مَعَ الْأَبْرَارِ
🤲«ጌታችን ሆይ! ኃጢአቶቻችንንም ለኛ ማር፡፡ ክፉ ሥራዎቻችንንም ከኛ አብስ፡፡ ከንጹሖቹም ሰዎች ጋር ግደለን፤» (አሊ-ዒምራን :193)
@ya_muhammad_saw
👒👒_____________🌿🌿
✨ሰልማን አል-ፋሪሲይ (ረ.ዐ) እንዳወሱት ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡-
‹‹በጁምዓ ቀን ገላውን የታጠበ፤ በተቻለው መጠን ንፅህናውን የጠበቀ፤ (ፀጉሩን) ቅባት የተቀባ፤ ከዚያም (ወደ መስጊድ) የሄደ በሁለት ሰዎች መካከልም ሳይለያይ አላህ የጻፈለትን ያህል ከሰገደ፤ ከዚያም ኢማሙ ሲናገር ዝም ካለ (በወቅቱ ካለው) ጁሙዓና ከበፊቱ ባለው ጁሙዓ መካከል የፈፀማቸውን ወንጀሎች አላህ ይምረዋል፡፡
(ቡኻሪ ዘግበውታል)
🇪🇹ሀገራችን ሰላም የሚሆንበት
የታመመ የሚድንበት
ያሰብነው ሁሉ የሚሳከበት ጁምዐ ይሁንልን 🤲
@ya_muhammad_saw
➧.ቀለሙ ተነስቶ ወረቀቱ በደረቀ ጉዳይ አትጨነቅ።
ላንተ ያለው ሁሉ ቀኑ ፈጠነም ዘገየም መምጣቱ አይቀሬ ነው። «ይሆናል» በተባለው ጊዜ የመጣ ነገር ሁሉ ደግሞ ለበጎ ነው‼️
....በመሄዱ ላይ የቆረጠ
እሱን በመርሳት ላይ ቁረጥ/ወስን
ሳታውቀው በፊት ደስተኛ ሆነህ
ትኖር እንደነበርም አትርሳ… 🍁✨
@ya_muhammad_saw
ሰላት ዕድሜ ቢሆን ማሰላመት ሞት ነው ,..
ጥያቄው እኛስ በትክክል ሰግደናል ወይ?
.
መወለድ አዛን ቢሆን ሞት ኢቃማ ነው...
ጥያቄው እኛስ ጠሃራ ላይ ነን ወይ?
.
የዚህች ዓለም ሕይወት የዚህኑ ያህል አጭር ናት...
ስለዚህ ሁሌም መዘጋጀት ግድ ይላል። ተዘጋጅቶ መተኛት፣ ተዘጋጅቶ መነሳት
ቢስሚከ ረቢ ወዶዕቱ ጀንቢ
@ya_muhammad_saw
ዕድሜህ በሄደ ቁጥር በዚህች ዓለም ሕይወት ላይ ያዘንክባቸው ነገሮች ሁሉ ያን ያህል ዋጋ ሊሠጣቸው እንደማይገባ ትረዳለህ። ዱንያ እንዲሁ ናት። ታሸንፋለህ ትሸነፋለህ፣ ታዝናለህ ትስቃለህ፣ ታገኛለህ ታጣለህ፣ ሙሲባ ይመጣል ይሄዳል፣ ሰው ይሄዳል ይተካል፣ ዱንያ ላይ ለዘላለሙ አብሮህ የሚዘልቅ መልካምም ሆነ መጥፎ ነገር የለም። የነገሮች መወለድና መሞት ያለ ነዉና ብዙ አትገረም።
ቀናችሁን ከምትጀምሩባቸው ነገሮች ሁሉ ምርጦቹ ዚክር፣ ሶላትና ዱዓ ናቸው።
@ya_muhammad_saw
በኦሮሚያ ክልል ሸገር ሲቲ እየተካሄደ ያለውን የመስጅድ ማፍረስ ዘመቻ አስመልክቶ በስልጤ ዞን የዳሎቻ ከተማ ሙስሊሞች ተቃውሟቸውን አሰምተዋል።
Читать полностью…ወንጀላችን ነው ወላሂ ሌላ ምንም አደለም ባንተ ወንጀል ነው እዚ ወንድማችን ሚሞተው ባንቺ ወንጀል ነው እዚ እህታችን የተጠቃችው በኔ ወንጀል ነው እንዲ የተደፈርነው😭ለአሏህ ብላቹ አፉ በሉኝ🙏አሁን ምንም መፍትሄ የለውም ኢስቲግፋርናዱዐ ብቻ!
Читать полностью…«በታላቁ አንዋር መስጂድ በሰላማዊ ምእመናን ላይ የደረሰውን ጉዳት ተከትሎ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ሼይኽ ሐጂ ኢብራሒም ቱፋ ከሚመለከተው የፌደራል ፓሊስ ኮሚሽን ጋር የተፈጠረውን ቀውስ ለማረጋጋት እና ባስቸኳይ የተጎዱትን ለማትረፍ በሚቻልበት መንገድ ላይ እየተነጋገሩ ቆይተዋል::
በተፈፀመው ጥቃት ጉዳት የደረሰባቸው ወንድሞቻችን የህክምና እርዳታ እንዲያገኙ ወደ ሆስፒታል እንዲወሰዱ አምቡላስ ወደ ቦታው እንዲደርስ እያደረጉ ይገኛሉ::
ታላቁ ኣንዋር መስጂድ ከውጥረት ነፃ እንዲሆን ፣በመስጂዱ ውስጥ የሚገኙ ምዕመናንም በሰላም ወደቤታቸው እንዲገቡ የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ፕሬዝደንት ሼይኽ ሱልጣን አማንን ጨምሮ ሶስት ከፍተኛ አመራሮች ከመጅሊሱ ተወክለው ወደ ቦታው በማምራት ከፀጥታ ኃይሉ ጋር ይህን ተፈፃሚ እንዲሆን እየሰሩ ይገኛሉ::
ከሁሉም ነገር በፊት ሰብኣዊነት መቅደም ስለሚኖርበት የተጎዱትን ወደ ህክምና ቦታ ለማድረስ እና በመስጂዱ ያሉ ምዕመናን በሰላም ወደቤታቸው እንዲገቡ ለማድረግ በሚደረገው ጥረት በአንዋር መስጂድ እና በዙርያው ያለው የፀጥታ ኀይሉም ይህ ተፈፃሚ እንዲሆን የበኩሉን ሓላፊነት እንዲወጣ ጥሪ እናቀርባለን::»
©: ኡስታዝ አቡበከር አሕመድ
🤲አላህ ሆይ በዲናችን ላይ የመጣብንን ፈተና አንሳልን!!
✨✨✨የምዕመናንን ልቦናዎች አስማማ በሃቅ ላይ አንድነታችን የሚጠናከር አድርገው ዲናችንን ከፍ ለማድረግ እየለፉ ያሉትን ሁሉ ከፍ አድርጋቸው ዲናችንን ለማዋረድ የሚጥሩትን ሁሉ አዋርዳቸው::
⚡️በማንችለው ፈተና አትፈትነን
#ኢላሂ ሙስሊሞች አድርገህ እንደፈጠርከን ሙስሊሞች እንደሆንን በተውሂድ ላይ ግደለን
መጨረሻችንን አሳምርልን ከመጥፎ አሟሟትም ጠብቀን
🤲አላህ ሆይ እኛንም ቤተሰቦቻችንንም ካስጨነቀን ነገር ሁሉ በቅርቡ ፈርጀን ጌታችን ሆይ የጠየቅንህን ሁሉ ስጠን ልባችንንም ደስ የሚሰኝ አድርግልን
#የአለማት ጌታ ሆይ በምድርም በሰማይም የሚሳንህ የለምና ምኞታችንን ሁሉ ፈጽምልን ቀልባችንን አንተን በመታዘዝ ላይ የሚንጠለጠል አድርግልን':
#አሏህ ሆይ በመሃሪነትህ ማረን፣ ችሮታህንም እዝነትህንም አውርድልን፣ ፀጋህንም አታሳጣን... አሏህ ሆይ ካንተ ብቻ እንከጅላለን ክጃሎታችንን ሙላልን:: እገዛህንም እንሻለን እና እርዳን፣ባንተ ላይ ሙሉ እምነታችንን አድርገናል እና በሌሎች ላይ የምንደገፍ አታድረገን
አላህ ሆይ በጥበቃህ ጠብቀን በክብርህ አክብረን በጸጋህ አክብረን። በእዝነትህም ማረን አንተ ከአዛኞች ሁሉ በጣም አዛኝ ነህና🤲
@ya_muhammad_saw
ﺍﻟﺤﻴﺎﺓ ﻣﺴﺘﻤﺮﺓ ﺳﻮﺍﺀ ﺿﺤﻜﺖ ﺃﻡ ﺑﻜﻴﺖ
ህይወት ቀጣይ ናት ብትስቅም ብታለቅስም....
ﻻ ﺗﺤﻤﻞ ﻧﻔﺴﻚ ﻫﻤﻮﻣﺎً ﻟﻦ ﺗﺴﺘﻔﻴﺪ ﻣﻨﻬﺎ
...ራስህን ሃሳብ አታሸክም አይጠቅምህም እና....
ﺍﻟﻘﻠﻖ ﻻ ﻳﻤﻨﻊ ﺃﻟﻢ ﺍﻟﻐﺪ ﻭﻟﻜﻨﻪ ﻳﺴﺮﻕ ﻣﺘﻌﺔ ﺍﻟﻴﻮﻡ
ጭንቀት የነገን ህመም አይከላከልም ነገር ግን የዛሬን ደስታ ያጠፋል...
@ya_muhammad_saw
#አላሁ_አክበር
አለምን እያነጋገረ ያለው የ Cristiano Ronaldo የሱጁድ ጉዳይ👌
ወደከፍታ የመቃረብ ጅማሮው ወደመሬት ከመጠጋት ነው❤
#ሱጁድ
የስጁድን ጥቅም ብታውቁ ኖሮ እስከ የውመል ቂያማ ድረስ ባልተነሳችሁ ነበር ረሱል ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም❤
ምንጭ መሀመድ ኢማም Facebook page
۞إِنَّ أَكْرَمَكُمْ عِندَ اللَّهِ أَتْقَاكُم
☞አላህ ዘንድ በላጫችሁ በጣም አላህን ፈሪያችሁ ነው፡፡ ۞
(ቁርአን 49:13)
ያ አላህ! አንተን ከሚፈሩ ባሮችህ አድርገን።
🤲አሚን🤲
@ya_muhammad_saw
አስቂኝ_ቂሷ
⇛አንዱ ነው…የሆነችን ሴት ማጨት ፈልገ። ነገር ግን ዉስጡ ሙሉ በሙሉ አልተቀበላትም። ልጫት ወይስ ትቅርብኝ የሚል ሃሳብ ይመላለስበታል። ይሄን ዉስጣዊ ውዝግቡን ለማስተካከል ቁርአን ልክፈትና መጀመሪያ ዐይኖቼ ባረፉበት አንቀጽ መልእክት ላይ በመመስረት ዉሳኔ እወስናለሁ ብሎ ወሰነ። በዚሁ መሰረት ቁርአኑን በእጆቹ ያዘና ከፍተው። ሱረቱል ጣሃ ነበር የተከፈተው። መጀመሪያ አይኖቹ ያረፉባት የጌታችን ቃልም፦
«خذها ولا تخف»
የሚለው ነበር። «ያዛት። ምንም አትፍራ።» የሚል ነው ትርጉሙ። ―አትፍራ!! ያዛት የሚለውን ቃል በማየቱ ተደስቶ ለማጨት ወሰነ። ግለሰቡ በአንድ ነገር ግን ተሸውዷል። እሱም ይች የምትያዘው ነገር ምንድን ነች የሚለውን አለማስተዋሉ ነው።
•እባብ ነች።
ሸይኽ ሷሊህ አል ዑሶይሚ
@ya_muhammad_saw
قُلْ هَٰذِهِ سَبِيلِي أَدْعُو إِلَى اللَّهِ ۚ عَلَىٰ بَصِيرَةٍ أَنَا وَمَنِ اتَّبَعَنِي ۖ وَسُبْحَانَ اللَّهِ وَمَا أَنَا مِنَ الْمُشْرِكِينَ
➧.ይህች መንገዴ ናት፡፡ ወደ አላህ እጠራለሁ፡፡ እኔም የተከተለኝም ሰው በግልጽ ማስረጃ ላይ ነን፡፡ ጥራትም ለአላህ ይገባው፡፡ እኔም ከአጋሪዎቹ አይደለሁም» በል፡
{108} (سورۃ يوسف)
@ya_muhammad_saw
☞ አይናችን ሃላልን ለማየት ይናፍቃል፤
☞ ጆሮዋችን ሀላል የፍቅር ቃላቶችን ለመስማት ናፍቀዋል፤
☞ እጆቻችን ሃላልን ለመንካት፣ ስጦታን ለመቀበል ጓግተዋል
☞ እግሮቻችን ሃላል ላይ ለመቆም ቸኩለዋል፤
☞ አንደበታችን ከሃላል ጋር ለመጫወት ናፍቀዋል፤
☞ ጥርሳችን፣ፊታችን በሃላል ፈገግ ለማለት ተርበዋል፤
☞ ጐናችን በሃላል ጋደም ለማለት መጠባበቅ ተያይዘዋል፤
☞ ያረብ አንዳች አካላችንን ሃራም ላይ ሳታሳርፍ በሃላል ዘውጀን
አሚን ያረብ 🤲🤲
@ya_muhammad_saw
ሱብሀነክ እውቀቱ አለምን ያካበበ ጌታ አለህ ስለምን ስትል ህይወትህን በጭንቀት ትገፋለህ?
እውነተኛ ደስታንም ከርሱ ዘንድ ታገኛለህ ወደ መንገዱ ሂድ!!!
አላህዬ ኮ አለልህ/ሽ አብሽር☺️
عَالِمُ الْغَيْبِ وَالشَّهَادَةِ الْكَبِيرُ الْمُتَعَالِ
ሩቁንና ቅርቡን ዐዋቂ ታላቅ የላቀ ነው፡፡
[ሱረቱ ረእድ 9]
@ya_muhammad_saw