ya_muhammad_saw | Unsorted

Telegram-канал ya_muhammad_saw - ❤ያ ሙሃመድ(ሰ.ዐ.ወ)❤

-

All YOU WANT TO KNOW ABOUT ISLAM IS HERE JUST JOIN AND ENJOY🔥 ⚡️GROUP👇👇 @ya_resulelah_saw @ya_resulelah_saw @ya_resulelah_saw ✍️For any comment👉 @faruqa_11

Subscribe to a channel

❤ያ ሙሃመድ(ሰ.ዐ.ወ)❤

የኹጥባ ሱናዎች

ለሙስሊሞች ዱንያዊና ሀይማኖታዊ ጉዳዮች መስተካከልና ለመሪዎች ዱዓ ማድረግ የተወደደ ነው፡፡ ነብዩ (ﷺ) የጁምዓ ዕለት ኹጥባ ሲያደርጉ በጣታቸው ወደ ላይ እየጠቆሙ ዱዓ ሲያደርጉ ሰዎችም አሚን ይሉ ነበር፡፡

ኹጥባና ሰላት በአንድ ሰው ቢፈፀሙ ይወደዳል፤ ኹጥባ አድራጊው በተቻለ አቅም ድምፁን ከፍ ቢያደርግ የተወደደ ነው፤ ኹጥባን ቆሞ ማድረግ የተወደደ ነው፡፡

ጃቢር ኢብን ሰሙራ እንዳሉት

‹‹ነብዩ (ﷺ) ቆመው ኹጥባ ካደረጉ በኋላ በመሀል ተቀምጠው ከዚያ እንደገና ቆመው ያደርጉ ነበር››[ሙስሊም 862]

    ኹጥባን አጠር ማድረግና የሁለተኘውን ኹጥባ ከመጀመሪያው ይበልጥ አጠር ማድረግ፡፡ ዓማር ባስተላለፉት ሀዲስ ነብዩ (ﷺ) እንዲህ ይላሉ

‹‹የአንድ ሰው ኹጥባ አጠር ማለቱና ሰላቱን ረዘም ማድረጉ የአዋቂነቱ ምልክት ነው፡፡ ሰላትን አስረዝሙ ኹጥባን አሳጥሩ››[ሙስሊም 869]

ኹጥባ አድራጊው ወደ ህዝቦች ዞር ብሎ ሠላምታን ማቅረብ፡- ጃቢር እንዳሉት

‹‹ ነብዩ (ﷺ) ሚንበር[የኹጥባው መድረክ (ምኹራብ)] ላይ ሲወጡ ሠላምታ ያቀርቡ ነበር”

 አዛን አድራጊው አዛኑን እስኪያጠናቅቅ ሚንበር ላይ መቀመጥ  ኢብን ዑመር እንዳሉት ‹‹ነብዩ (ﷺ) በሚንበር ላይ ወጥተው አዛን አድራጊው አዛኑን እስኪጨርስ ሚንበር ላይ ይቀመጡና ሲጨርስ ተነስተው ኹጥባ ያደርጉ ነበር››

@ya_muhammad_saw

Читать полностью…

❤ያ ሙሃመድ(ሰ.ዐ.ወ)❤

ነብዩ ምን አሉ መሰላቹ :-
------------------

ውስጡ ብናኝ ያህል ኩራት ያለበት ሰው ጀነት አይገባም አሉ ከዛ አንድ ሶሀባ ነበረ ኢኮኖሚካሊ ጥሩ የሆነ ሰው ነውና ሁሌ የሚለብሰው ብራንድ ልብሶችን ብራንድ ጫማዎችን ነው በጣም እራሱን የሚጠብቅ ነበር እና ደነገጠ መለባበሴ ኩራተኛ ያስብለኝ ይሆን በአሁኑ ግዜ አዳዲስ ልብስ መልበስ ብራንድ መኪና መንዳት እንደማለት ነው ከዛ ይህ ሶሀባ ይሄ ይሆናል ብሎ የአላህ መልክተኛ ሰ.ዐ.ወ አንድ ሰው ልብሱ ጥሩ እንዲሆን ይመኛል ጫማው ጥሩ እንዲሆን ይመኛል ኢሄ ኩራት ነው እንዴ አላቸው ውዱ ነብዬም መለሱለት እንዲህማ አይደለም አላህ ውብ ነው ውቦችን ነው ሚወደው አሉት ሁሌ ሚፀዳዱትን ራሳቸውን ሚጠብቁትን ነገር ግን አሉ ኩራት ማለት እውነት ሲመጣለት እውነትን መመለስ አሉ
ሰዎችን ማሳነስ አሉ ዝቅ አድርጎ መመልከት አሉ🥺

ወንድሞቼ እኛስ የት ነን??
አደራ ከኩራት ራሳችሁን ጠብቁ አደራ!!

@ya_muhammad_saw

Читать полностью…

❤ያ ሙሃመድ(ሰ.ዐ.ወ)❤

🕋ሰላትን በተገቢው መልኩ ያለመስገድ
ምክንያቶች: 

እነዚህ ምክንያቶች ብዙ ናቸው:  አሳሳቢ እንዲሁም ትልቅ ከሚባለው ምክንያቶች:
🛑 ስሜትን መከተል ስለዚህም ነው الله  ስሜትን መከተልን ሰላትን ከማጥፋት ጋር አቆራኝቶ የጠቀሰው ።
{فخلف من بعدهم خلف أضاعوا الصلاة وتبعوا الشهوات فسوف يلقون غيا★ إلا من تاب وآمن} ..
ከእነሱም በኃላ ሰላትን ያጓደሉ( የተው) ፍላጎቶችንም የተከተሉ መጥፎ ምትኮች ተተኩ የጀሃነምንም ሸለቆ በርግጥ ያገኛሉ።

  🛑 የዚህን ሰላት እውነታ አለመረዳት: አሳሳቢነቷን አለማወቅ: ጥቅሟን አለማወቅ: ትሩፋቷን አለማወቅ: ምንዳዋን አለማወቅ: الله ዘንድ ያላትን ደረጃ አለማወቅ: ሌሎችም ምክንያቶች አሉ።

🛑 ሰላት ላይ ቸልተኛ ከሚያደርጉ ምክንያቶች:  አብዘሃኛው ሰጋጅ ሚሰግደው እንደ አካል ስራ ብቻ ነው የአካል እንቅስቃሴ የልብ ስራ የሌለበት:  እነሱ ዘንድ መተናነስ መፍራት አላህ ፊት መዋረድ ሚባል ነገር የለም: የሚሉትንም አያስተውሉም የሚሰሩትንም እንደዛው:  ስለዚህ ከሰላት ምንም ሳይጠቀሙ ይወጣሉ ። ለልቦቻቸውም ብርሃን ሚባል ነገር አያገኙም: እምነታቸውም ላይ ጭማሬ አያገኙም:  ከመጥፎ እንዲሁም ከተጠሉ ነገራቶችም መራቅ አይችሉም ።

✳️ ይህ ሁሉ የሆነው እነሱ ሚሰግዱት የአካል ሰላት እንጂ የነፍስ ሰላት ስላልሆነች ነው።  ለዚህች ሰላት ሚገባትን ሃቅ ቢሰጧት:  የፈሩ ሆነው ልባቸውን ሰብስበው:  ወደ الله ተመልሰው እንዲሁ በሱ ፊት መቆማቸውን እያሰቡ ቢሰግዱ እቺን ሰላት ይወዷት ነበር ልባቸውም  ወደ እሷ የተንጠለጠለ ይሆን ነበር ። ለዚህም ነው  ነብዩ صلى الله عليه وسلم ሰላት የአይን መርጊያዬ ተደረገች ያሉት

لشيخ العلامة محمد صالح لعثيمين.

📚المصدر فتاوى نور لى الدرب لشريط (72)

@ya_muhammad_saw

Читать полностью…

❤ያ ሙሃመድ(ሰ.ዐ.ወ)❤

:::::::ህይወት ሚስጥር ናት:::::::☜

☞⇡በሕይወትህ ምን እደሚጠብቅህ ፣ምን   እንደሚያጋጥምህ አታውቅም። ሁሉንም ነገር ለመቀበል እራስህን ዝግጁ አድርግ። ደግም ሲያጋጥምህ አመስግን፣ ክፉም ሲያጋጥምህ ታጋሽና አመስጋኝ ሁን ። ከችግርም ጋር ምቾት  አለና እራስህን አፅናና። ይቺ ምድር የፈተና ቦታ መሆኗን ላፍታም አትዘንጋ።

አላህም እንዲህ ይለናል፦


كُلُّ نَفْسٍ ذَائِقَةُ الْمَوْتِ ۗ وَنَبْلُوكُم بِالشَّرِّ وَالْخَيْرِ فِتْنَةً ۖ وَإِلَيْنَا تُرْجَعُونَ

📖 አል-አንቢያ: 35 📖
ነፍስ ሁሉ ሞትን ቀማሽ ናት፡፡ ለመፈተንም በክፉም በበጎም እንሞክራችኋለን፡፡ ወደኛም ትመለሳላችሁ፡፡

«አስታውስ! አላህ ከታጋሾች ጋር መሆኑን። አላህን በኸይር ጠርጥረው ኸይር ይሰጥሃል።

وَلَسَوْفَ يُعْطِيكَ رَبُّكَ فَتَرْضَىٰ

        📖አል ዱሃ :5📖
ጌታህም ወደ ፊት (ብዙን ስጦታ) በእርግጥ ይሰጥሃል፡፡ ትደሰታለህም፡፡

እናም አላህ እዳለው፦
فَاصْبِرْ صَبْرًا جَمِيلًا

      📖 አል-መዓሪጅ:5📖
መልካምንም ትዕግስት ታገሥ፡፡

وَاللَّهُ يُحِبُّ الصَّابِرِينَ

      📖አሊ-ዒምራን:146 📖
አላህም ትዕግስተኞችን ይወዳል፡፡

@ya_muhammad_saw

Читать полностью…

❤ያ ሙሃመድ(ሰ.ዐ.ወ)❤

የግብረ-ሰዶም ሸሪዐዊ ቅጣቱ፡-

ከነቢያችን (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) በተገኘው ሐዲሥ መሰረት፡ በዚህ ተግባር ላይ ሆኖ ንሰሀ (ተውበት) ከማድረጉ በፊት በአይን ምስክሮች የተገኘ፣ ለአካለ መጠን የደረሰ ሰው ቅጣቱ ‹‹መገደል›› ነው፡፡ ይህም የድርጊቱን አስቀያሚነት፡ ማኃበረሰብ የሚበክል ትውልድ እንዳይቀጥል የሚያደርግ እንቅፋት በመሆኑ ነው፡፡ ሐዲሡ እንዲህ ይነበባል👇
ዐብደላህ ኢብኑ ዐባስ (ረዲየላሁ ዐንሁማ) እንደነገረን የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም)፡- "የሉጥ ህዝቦችን አይነት ስራ የሚሰራን ሰው ካገኛችሁት የሚፈጽመውንም፣ የሚፈጸምበትንም ሰው ግደሉ" (ቲርሚዚይ 1456፣ አቡ ዳዉድ 4462፣ ኢብኑ ማጀህ 2561)፡፡

@ya_muhammad_saw

Читать полностью…

❤ያ ሙሃመድ(ሰ.ዐ.ወ)❤

ድሃ ማለት ማን እንደሆነ ታወቃላችሁ⁉️

የአላህ መልክተኛ (ሰለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም) ከዕለታት አንድ ቀን ከባለደረቦቻቸው ቁጭ ብለው ሳለ፦
“ድሐ ማን እንደሆነ ታውቃላችሁ?”  በማለት ይጠይቃሉ።

ሰሐቦችም ፦ “እኛ ጋር ድሀ ማለት ምንም ንብረትና ገንዘብ የሌለው ነው” በማለት ይመልሳሉ።
***
የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) ግን፦ “ከኡመቴ ደሀ ማለት የትንሳኤ ቀን በብዙ ሰላቶች፤ ዘካዎችና፤ ፆሞች የሚመጣ ሰው ነው፣ ነገር ግን ይህ ሰው አንድ ወንድሙን ሰድቧል፣ ሌላው ላይ ዋሽቷል፣ የአንዱን ገንዘብ ያለአግባብ ወስዷል፣ የሌላውን ደም አፍስሷል፣ አንዱን መትቷል፣ በሌላው ላይም ድንበር አልፏል፣
***
ያኔም የቂያም ቀን (የምርመራ ቀን) የራሱን ጥሩ ሥራዎች ለበደላቸው በካሳ መልክ አሳልፎ ይሰጣል፣ ጥሩሥራው ለመካሻ አልበቃ ይለውና የበደላቸውን ሰዎች ኃጢያት ይሸከማል፣ ከዚያም ወደ ጀሀነም ይወረወራል” በማለት መለሱላቸው

@ya_muhammad_saw

Читать полностью…

❤ያ ሙሃመድ(ሰ.ዐ.ወ)❤

እውነተኞቹ ምእምናን በእርግጥ በድሎት (ገነት) ውስጥ ናቸው፡፡
إِنَّ الْأَبْرَارَ لَفِي نَعِيمٍ
(አል-ሙጠፍፊን - 22)

"እውነተኞቹ ምእምናን" ማለትም ጌታ ያዘዛቸውን የሚታዘዙ ግዴታቸውን የሚወጡ አላህን እውነተኛ መፍራትን የሚፈሩ ምእመናን

"በእርግጥ በድሎት (ገነት) ውስጥ ናቸው፡፡" ማለትም የማይቋረጥ የማይነጥፍ የማይወገድ የሆነ የጀነት ፀጋ ውስጥ ለዘልዓለም መዘውተራቸው የተረጋገጠ ነው፡፡

አላህ ከነሱ ያድርገን🤲🏻

@ya_muhammad_saw

Читать полностью…

❤ያ ሙሃመድ(ሰ.ዐ.ወ)❤

إِنَّ الْأَبْرَارَ لَفِي نَعِيمٍ وَإِنَّ الْفُجَّارَ لَفِي جَحِيمٍ

"እውነተኞቹ ምእምናን በእርግጥ በጀነት ውስጥ ናቸው፡፡

ከሓዲዎቹም በእርግጥ በጀሀነም ውስጥ ናቸው፡፡" (አል ኢንፊጧር 13-14)

@ya_muhammad_saw

Читать полностью…

❤ያ ሙሃመድ(ሰ.ዐ.ወ)❤

🔥ሦስቱ የጀሀነም ሸለቆዎች
ከነርሱ እንጠንቀቅ!!!❗️

1⃣ ገይ ( ﺍﻟﻐَّﻲ)🔥

2⃣ ወይል ( ﺍﻟﻮَّﻳﻞ)🔥

3⃣ ሰቀር (ﺳﻘﺮ )🔥
       ሲብራሩ፧

1⃣ 🌑የገይ ሸለቆ🔥🔥🔥
ሁሉንም ሶላቶች በአንድ ሰብስቦ ለሚሰግድ የተዘጋጀ ሸለቆ ነው።
۞ ﻓَﺨَﻠَﻒَ ﻣِﻦ ﺑَﻌْﺪِﻫِﻢْ ﺧَﻠْﻒٌ ﺃَﺿَﺎﻋُﻮﺍ ﺍﻟﺼَّﻠَﺎﺓَ ﻭَﺍﺗَّﺒَﻌُﻮﺍ ﺍﻟﺸَّﻬَﻮَﺍﺕِ ۖ ﻓَﺴَﻮْﻑَ ﻳَﻠْﻘَﻮْﻥَ ﻏَﻴًّﺎ
(ሱርቱ መርየም፣ - 59)✅
ከእነሱም በኋላ ሶላትን ያጓደሉ (የተዉ) ፍላጎቶችንም የተከተሉ መጥፎ ምትኮች
ተተኩ! የገሀነምንም🔥🔥 ሸለቆ በእርግጥ ያገኛሉ፡፡

2⃣ ወይል ሸለቆ🔥🔥
ሸሪዓ ባልፈቀደው ምክኒያት ሶላትን ለሚያዘገዩ ሰዎች የተደገሰች ናት።
ﻓَﻮَﻳْﻞٌ ﻟِّﻠْﻤُﺼَﻠِّﻴﻦَ
(ሱረቱ አል-ማዑን - 4)✅
ወዮላቸው ለሰጋጆች፡፡
ﺍﻟَّﺬِﻳﻦَ ﻫُﻢْ ﻋَﻦ ﺻَﻠَﺎﺗِﻬِﻢْ ﺳَﺎﻫُﻮﻥَ
(ሱረቱ አል-ማዑን - 5)✅
ለእነዚያ እነርሱ ከስግደታቸው ዘንጊዎች ለኾኑት፤ (ሰጋጆች)፡፡

3⃣ ሰቀር ❗️
ሰቀር ደግሞ ሶላትን ለሚተው ሰው ነው የተሰናዳችው።

🔥ይሄ የእሳት ሸለቆ በጣም ከማቃጠሉ የተነሳ አጥንትን የሚጨርስ ነው።

🌍  ሶላት 🌎

የሚተው ሰው ከነፊርዐውንና ሃማን ጋር ነው የሚቀሰቀሰው። የነቢዩን (ﷺ )
ሸፈዓም አያገኝም።


🌸አላህ ሆይ! ሙስሊሞች(ለአንተ ታዛዦች) አድርገህ ግደለን። ከደጋጎች ጎራም መድበን!

🤲 ያረብ አንትው ጠብቀን 🤲

@ya_muhammad_saw

Читать полностью…

❤ያ ሙሃመድ(ሰ.ዐ.ወ)❤

የአረፋ ቀን 9ኛው ዙልሂጃህ ላይ ነው። ኢንሻአላህ መፆሙን አትርሱ

ነብዩ (ሶ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- "የአረፋን ቀን መፆም ያለፉትን እና መጪ አመታትን ሀጢያትን ያሰርሳል/ያብሳል።"
ሙስሊም

Читать полностью…

❤ያ ሙሃመድ(ሰ.ዐ.ወ)❤

#አስሩ ወርቃማ ቀናቶች!☺️

በዚህ የታሪክ ዳራ የዱንያ ህግ ተቀይሩዋል የሳለ ቢላዋ የኢስማኢልን (ዐ:ሰ) አንገት መቁረጥን ተሳነው ደነዘዘም መቼ ነው የሆነው ነብዩ የአላህ ትእዛዝን ለመፈፀም እጅ ሰተው ንጥፍ ያሉ ሰአት ነው  ....
ወደኋላ ተመልሰን ታሪኩን እናጢን ከነባራዊ ህይወታችን እናስተሳስረውማ☺️

فَلَمَّا بَلَغَ مَعَهُ السَّعْيَ قَالَ يَا بُنَيَّ إِنِّي أَرَىٰ فِي الْمَنَامِ أَنِّي أَذْبَحُكَ فَانظُرْ مَاذَا تَرَىٰ ۚ قَالَ يَا أَبَتِ افْعَلْ مَا تُؤْمَرُ ۖ سَتَجِدُنِي إِن شَاءَ اللَّهُ مِنَ الصَّابِرِينَ

ከእርሱ ጋርም ለሥራ በደረሰ ጊዜ «ልጄ ሆይ! እኔ በሕልሜ እኔ የማርድህ ሆኜ አያለሁ፡፡ ተመልከትም፤ ምን ታያለህ?» አለው፡፡ «አባቴ ሆይ! የታዘዝከውን ሥራ፡፡ አላህ ቢሻ ከታጋሾቹ ሆኜ ታገኘኛለህ» አለ፡፡
               [ሱረቱ ሳፋት 102]

Читать полностью…

❤ያ ሙሃመድ(ሰ.ዐ.ወ)❤

۩ የዙልሒጃ ወር ነገ ሰኞ አንድ ብሎ ይጀምራል!

⚡️ዛሬ እሁድ ሰኔ 11/Jun18/2023 በሂጅሪያ አቆጣጠር ደግሞ ዙልቀይዳ 29 በሳዑዲ አረቢያ አዲስ ጨረቃ በመታየቷ የዙልሂጃ ወር በነገው እለት ሰኞ ሰኔ 12/june 19 አንድ ብሎ እንደሚጀመር ታውቋል::

⚡️የኢድ አል አድሃ አረፋ በዓልም እሮብ ሰኔ 21/2015/June 28/2023 እለተ ረቡዕ እንደሚውል ታውቋል፡፡

ከነገ ሰኞ ሰኔ 12/June 19 ጀምሮ እስከ ሰኔ 21/june 28 ድረስ ያሉትን 10 ቀናት በኢባዳ ልናሳልፋቸው ይገባል፡፡

⚡️የዙልሂጃን ዘጠኙንም ቀናት ለመፆም ፍላጎት ያለው ከነገ ሰኞ ሰኔ 12 /2015 ጀምሮ መፆም ይችላል፡፡

ታላቅ ምንዳ የሚያስገኘውን የዙልሒጃ 9 (የአረፋን ቀንን) ለመፆም የሚፈልግም ሰኔ 20/june27/2023 እለት ማክሰኞ መፆም ይችላል::

⚡️ኡዱሂያ ለማረድ ኒያው ያላችሁ ካሁን ሰዓት ጀምሮ ጥፍራችሁን እና ፀጉራችሁን ከመቆረጥ ታቀቡ!

⚡️ከነገ ሰኞ ጀምሮ ያሉትን ተከታታይ አስር ቀናቶች በኢባዳ እናሳልፋቸው!

🤲አላህ ይወፍቀን!!

🙌መልዕክቱን ለሁሉም እናዳርስ !

@ya_muhammad_saw

Читать полностью…

❤ያ ሙሃመድ(ሰ.ዐ.ወ)❤

የአላህ መልዕክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
🕋«ተገቢ ያልሆነ መጥፎ ነገር ከአንደበቱ ሳይወጣ የአሏህን ትእዛዝ ምንም ሳይጥስ ሐጅ ያደረገ ሰው ልክ እናቱ እንደወለደችው ቀን ከኃጢእቶቹ ሙሉ ጠርቶ ይመለሳል»
📚【ቡኻሪ ና ሙስሊም】
💎عن أبي هريرة رضي الله عنه قال:

سَمِعْتُ النبي ﷺ يقول: من حجَّ لله فلم يرفث ولم يفسق رجع كيوم ولدته أمه .

📚متفق عليه

@ya_muhammad_saw

Читать полностью…

❤ያ ሙሃመድ(ሰ.ዐ.ወ)❤

ፍልስጤማዊው ወንድማችን‼

አላህ ለኛም ለነርሱም ነስሩን ያቅርብልን።

Читать полностью…

❤ያ ሙሃመድ(ሰ.ዐ.ወ)❤

Thank you Sheikh Abu Adil.

Читать полностью…

❤ያ ሙሃመድ(ሰ.ዐ.ወ)❤

የአላህ መልዕክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል;- አላህ ዘንድ ከቀኖች ሁሉ በላጩ የጁምዓ ቀን ነው።

﷽ إِنَّ اللَّهَ وَمَلَائِكَتَهُ يصلون عَلَى النَّبِيِّ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آَمنوا صَلُّوا عليه وَسَلِّمُوا تَسْلِيمًا

የአላህ መልዕክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦ በጁምዓ ቀን በኔ ላይ ሰላዋት ማውረድን አብዙ፣ በኔ ላይ አንድ ሰላዋት ያወረደ አላህ በእርሱ ላይ አስር ሰላዋት ያወርድበታል።

Читать полностью…

❤ያ ሙሃመድ(ሰ.ዐ.ወ)❤

💌ነቢዩ (‏ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦💌

ስለሆነ እውቀት ተጠይቆ የደበቀው ሰው

አሸናፊውና የላቀው አላህ በቂያማ ቀን

በእሳት ልጎም ይለጉመዋል።

☞ሶሒሁል ጃሚዕ፡ 6284

@ya_muhammad_saw

Читать полностью…

❤ያ ሙሃመድ(ሰ.ዐ.ወ)❤

📚አሏህ ሆይ በአንተ ለዚህ ማለዳ በቅተናል።በአንተ ለምሽት እንበቃለን። በአንተ ህያው ሆነናል። በአንተም እንሞታለን።መመለሻ ወደ አንተ ነው።


اللهم نسألك خير مافي هذا اليوم وخير ما بعده
وأعوذ بك من شر ما في هذا اليوم وشر مابعده

@ya_muhammad_saw

Читать полностью…

❤ያ ሙሃመድ(ሰ.ዐ.ወ)❤

✅ትልቅ ብሥራት!
~
ለአንድ ወንድምህ ብድር አበድረህ በሆነ የጊዜ ገደብ እንዲመልስልህ ብትስማሙ...

👉 ካበደርክበት ጊዜ አንስቶ እስከተስማማችሁበት ጊዜ ድረስ በገንዘቡ ልክ በየቀኑ እንደምትሰድቅ ይታሰብልሀል።

👉 የጊዜ ገደቡ ተጠናቆ "ሌላ ጊዜ ስጠኝ" ቢልህና ብትስማማ ከዚህ ጊዜ አንስቶ ደግሞ በየቀኑ በመጠኑ ሁለት እጥፍ እንደምትሰድቅ ይቆጠርልሀል።

ማስረጃውስ?
~~~~
... ሶሐባው ቡረይዳ ረዲየላሁ ዐንሁ ነብዩን ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ﷺ እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ ብለዋል: –
‎ (مَنْ أَنْظَرَ مُعْسِرًا فَلَهُ بِكُلِّ يَوْمٍ مِثْلِهِ صَدَقَةٌ)
"ችግረኛን ጊዜ የሰጠ ለሱ በየቀኑ አምሳያውን ሶደቃ አለው።"

🎈 ከዚያም እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ አሉ:–
‎(مَنْ أَنْظَرَ مُعْسِرًا فَلَهُ بِكُلِّ يَوْمٍ مِثْلَيْهِ صَدَقَةٌ)
"ችገረኛን ጊዜ የሰጠ ለሱ በየቀኑ ሁለት አምሳያውን ሶደቃ አለው።"

በዚህን ጊዜ "የአላህ መልእክተኛ ሆይ! ‘ችግረኛን ጊዜ የሰጠ ለሱ በየቀኑ አምሳያውን ሶደቃ አለው’ ስትል ሰምቼህ ነበር። ከዚያ ደግሞ ‘ችግረኛን ጊዜ የሰጠ ለሱ በየቀኑ ሁለት አምሳያውን ሶደቃ አለው’ ስትል ሰማሁህ?" አልኳቸው።

🎈 እሳቸውም እንዲህ አሉ: –

‎(لَهُ بِكُلِّ يَوْمٍ صَدَقَةٌ قَبْلَ أَنْ يَحِلَّ الدَّيْنُ ، فَإِذَا حَلَّ الدَّيْنُ فَأَنْظَرَهُ فَلَهُ بِكُلِّ يَوْمٍ مِثْلَيْهِ صَدَقَةٌ ) .
"የእዳው መክፈያ ጊዜ እስከሚደርስ ድረስ ለሱ በየቀኑ አምሳያውን ሶደቃ አለው። ጊዜ ገደቡ ደርሶ ተጨማሪ ጊዜ ከሰጠው ደግሞ ለሱ በየ እለቱ ሁለት አምሳያውን ሶደቃ አለው።"

📚 ኢማሙ አሕመድ የዘገቡት "ሶሒሕ" ሐዲሥ ነው።

ከዚህም የበለጠውን ደግሞ ተመልከት!

ከአቢል የሰር ረዲየላሁ ዐንሁ ተይዞ የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል: –

‎( مَنْ أَنْظَرَ مُعْسِرًا أَوْ وَضَعَ عَنْهُ أَظَلَّهُ اللَّهُ فِي ظِلِّهِ )
"ችግረኛን ጊዜ የሰጠ ወይም የተወለት አላህ በጥላው ስር ያስጠልለዋል።"

📚 ሙስሊም ዘግበውታል።

@ya_muhammad_saw

Читать полностью…

❤ያ ሙሃመድ(ሰ.ዐ.ወ)❤

አራት ነገሮች ሪዝቅን ይሰበስባሉ ፦

....ሌሊት መቆም(መስገድ) ፣ በሌሊቱ ማብቂያ ኢስቲጝፋርን ማብዛት ፣ ምፅዋትን ማዘውተር ፣ በእለቱ መጀመሪያ እና ማብቂያ መዘከር

አራት ነገሮች ደሞ ሪዝቅን ይከለክላሉ፦
ንጋት ላይ መተኛት ፣ ጥቂት መስገድ ፣ ስልቹነት ፣ ከኃዲነት
الإمام ابن القيم رحمه الله 📚 زاد المعاد ~ ٤ / ٣٧٨ .
@ya_muhammad_saw

Читать полностью…

❤ያ ሙሃመድ(ሰ.ዐ.ወ)❤

እኔ ስሞት...
1. ከእኔ ጋር የሚዛመዱ ሁሉንም ነገሮች ሰርዝ ❲ፎቶዎች፣ ቻቶች፣ ቪዲዮዎች❳
2. የኔን ፎቶዎች ወይም መልዕክቶች ለማንም አታጋራ።
3. የኔን ሶሻል ሚድያ ❲ፌስቡክ፣ ቴሌግራም...ወዘተ❳ ሪፖርት በማድረግ አዘጋ።
4. የኔን የሞተ አካል፣ ከሞቴ ጋር የሚገናኝ ማንኛውንም ነገር በፍፁም ፎቶ አታንሳ።
5. አስቤውም ሆነ ሳላስበው ከጎዳውህ ይቅር በለኝ።
6. ለሞተችው ነፍሴ ብዙ ዱዓ አድርግላት።
7. የኔ ወዳጅ ማንኛውም ገንዘብን የተመለከተ ቅሬታ ካለህ በቅንነት ቤተሰቤን ተገናኝና ጠይቅ...ጨርስ።
እባክህ በፍፁም ሌላ ነገር አትንካ... አታስቸግር።
ሞት ወደእኛ መች እንደሚመጣ አናውቅም። በማንኛውም ሰአት እና ጊዜ ከፊቱ ልንቆም እንችላለንና።
ሞት ወደ እኛ ሲመጣ ምንም ማሳወቂያ መልዕክት አይልክምና።
በቃ ይህው ነው መልዕክቴ።

አላህ ረጅምን እድሜ ይስጠን።
ራስህን ጠብቅ፣ በደስታ በጤና ኑር።
👇👇👇

@ya_muhammad_saw

Читать полностью…

❤ያ ሙሃመድ(ሰ.ዐ.ወ)❤

ያአላህ....

...... ከሞት በፊት ተውበትን🥺

በሞት ሰዓት ሸሃዳን☝️

ከሞት በኃላ ጀነትን ወፍቀን🤲

@ya_muhammad_saw

Читать полностью…

❤ያ ሙሃመድ(ሰ.ዐ.ወ)❤

🍃------------🌷----------------🍃
ሶላትን ትቶ እድገትን መመኘት
ያለቁርኣን ና ዚክር  ቀልብ ትረጥባለች ብሎ ማሠብ

ዒልምን ዘንግቶ ደረጃ አገኛለሁ ብሎ
ማኮፈስ ቂልነት ነው
🍃------------🌷----------------🍃
በወንጀል  እየዋኙ  ሰላሜን አጣሁ አብሰከሰከኝ 
ወንድምን አዋርዶ  ሲያበቃ ቅሌቴ በዛብኝ ሳ  ከሚሉ የዲን  ሞዛዛወች አሏህ ነጃ ይበለን ተውበትን ይስጠን
🍃------------🌷----------------🍃
በናቱ እየተረገመ ከሌላ ሰው ምርቃን የሚፈልግ አይነት ነፈዝ ከመሆን አሏህ ያድነን

ሽማግሌ አባቱን  እየተገላመጠ  ለሌሎች  ሰወች  ደፋ ቀልበስ የሚል አረመኔ አይነት ከመሆን አሏህ ይጠብቀን 
🍃------------🌷----------------🍃
ሲኒማ ሲሉት በሽክታ ዲናዊ ስብሰባ ሲሉት በዝምታ አይነት ከንቱነት ነው

ዱንያን ብቻ ጋላቢ  መድረሻውን ያላወቀ ወይንም  የረሳ ነው 

@ya_muhammad_saw

Читать полностью…

❤ያ ሙሃመድ(ሰ.ዐ.ወ)❤

Eid Ul Adha Mubarak ❤️
May Allah accept your sacrifice and bless your family

Eid mubarak 2 all💥

Читать полностью…

❤ያ ሙሃመድ(ሰ.ዐ.ወ)❤

"የተሰበረ ልባቸውን ጠግኑ፤
ስሜታቸውን ጠብቁ፤
ቃላት ምረጡ፤
ድርጊታችሁን አለስልሱ፤
መልካም ትድድርን አትርሱ፤
ማንንም አታቁስሉ፤
በንፅህና በቀናነት ኑሩ።
ይህ የነቢያት መንገድ፣ የመልካሞች መንገድ ነው።"

አስርቱ ቀናት!!!


وَالَّذِينَ آمَنُوا وَعَمِلُوا الصَّالِحَاتِ أُولَٰئِكَ أَصْحَابُ الْجَنَّةِ ۖ هُمْ فِيهَا خَالِدُونَ

እነዚያም ያመኑት በጎ ሥራዎችንም የሠሩት እነዚያ የገነት ጓዶች ናቸው፡፡ እነርሱ በውስጧ ዘላለም ዘውታሪዎች ናቸው፡፡
                  [ሱረቱ በቀራ 82]

Читать полностью…

❤ያ ሙሃመድ(ሰ.ዐ.ወ)❤

✨የአላህ መልእክተኛ(ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ:–

....አላህን ሶስት ጊዜ ጀነት የለመነ ሰው ጀነት:- "አላህ ሆይ! ጀነት አስገባው ትላለች።

ከእሳት ሶስት ጊዜ በአላህ የተጠበቀ ሰው እሳት:- “አላህ ሆይ! ከእሳት ጠብቀው” ትላለች።]
📚ቲርሚዚ ዘግበወታል።

ጀነትና ጀሀነም ተወዛገቡ…
✨ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል “ጀነትና ጀሀነም ተወዛገቡ። ጀሀነም፦ ‘በውስጤ ጠንካራዎቹ እና በኩራት የሚንቦጣረሩ አሉ’ አለች። ጀነት፦ ‘በውስጤ ደካማዎችና ድሃዎች እንጂ ሌላ አይገቡም’ አለች።

..... በዚህ ግዜ የላቀው አላህ ለጀነት እንዲህ አለ፦ ‘አንቺ ጀነት የእኔ ምሕረት ነሽ። በአንቺ አማካኝነት ለምሻው ባሮቼ ምሕረቴን እለግሳለሁ፡፡’ ለጀሀነምም እንዲህ አለ፦ ‘አንቺ ጀሀነም የኔ ቅጣት ነሽ። በአንቺ አማካኝነት የምሻውን ባሮቼን እቀጣለሁ።’ በማለት በመካከላቸው ፍርድ ሰጠ።”📚 ቡኻሪ ዘግበውታል:

@ya_muhammad_saw

Читать полностью…

❤ያ ሙሃመድ(ሰ.ዐ.ወ)❤

የዙል-ሒጃ 10ቱ ቀናት‼️
▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬
✍የአላህ ሰላምና እዝነት በታላቁ ነብይ በሙሀመድ (ሶለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) እና በባልደረቦቻቸው፣ በቤተሰቦቻቻው ሁሉ ላይ ይሁን፡፡
||
ከተከበሩት ወራት መካከል አንዱ የሐጅ ወር ዙል-ሒጃ ነው።
በነዚህ የተከበሩ በሚባሉት ወሮች ወንጀል አላህ ዘንድ የበለጠ ከባድ የሚሆኑበት፤ መልካም ስራም እጥፍ ድርብ ተደርገው ሚያዙበት ወሮች ናቸው።
ለዚህም የዙል ሒጃን 10ሩን ቀኖች ማጣቀስ ይቻላል።
ከቀናት ሁሉ አላህ ዘንድ የተወደዱት ደግሞ አስሩ የዙል-ሒጃ ቀናት ናቸው።
:
እንደዉም ከዱንያ ቀናት ሁሉ ብልጫ ያላቸው እነዚህ ቀናት ናቸው።
-----------☆☆☆☆☆☆☆-------------

@ya_muhammad_saw

Читать полностью…

❤ያ ሙሃመድ(ሰ.ዐ.ወ)❤

ቁርአን ስኬት ለራቀው ወደ ስኬት ያዳርሰዋል
መርጋት ላቃተው ልብ መርጊያ ማረፊያ ነው
ደስታን ለፈለገ የደስታ ምንጩ ቁርአን ነው
ቁርአን የሂይወት ቅመም የልብ መድሃኒት ነው

በቁአን ለደከመ ሰውነት ብርታል ጉልበት ነው
ለዛለ አእምሮ ለደረቀች ልብ ቀለብ ነው
ላዛነች ልብ ለተሰበረች ሩህ መጠገኛ እዝነት ነው

ቁርአን ህመሙ ለበዛ መዳኛው ለረቀው ፈውስ ነው
መንገዱ ለተፋው ቀኑ ለጨለመበት ብርሃን ነው
ቁርአን ጓደኛ ለሌለው ጓደኛ ነው
ቁርአን የህይወት ማጣፈጫ የልብ ብርሃን ነው🥰 🧡
ቁርአን ውብ ውዱ የአላህ ስጦታ 🧡

ቁርአን ህይወት ነው በፍፁም እንዳትረቀው!
ምንም እንኳን ጉዳይህ ቢበዛ አልመች ቢልህ
ቀጠሮህ ቢበዛ ህመምህ ቢጠናም ከቁርአን
አትዘናጋ!
❤️🎁
#ቁርኣን💫

Читать полностью…

❤ያ ሙሃመድ(ሰ.ዐ.ወ)❤

እኚህን ሰውዬ አወቃችኋቸው? ባለፈ የነፃ ሐጅ የተሰጠው ነው።

ለኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ዱዓእ እያደረገ የሚያሳይ ቪድዮ ነው።

Читать полностью…

❤ያ ሙሃመድ(ሰ.ዐ.ወ)❤

ያ ጀባር!!!🥺

وَلَا تَحْسَبَنَّ الَّذِينَ قُتِلُوا فِي سَبِيلِ اللَّهِ أَمْوَاتًا ۚ بَلْ أَحْيَاءٌ عِندَ رَبِّهِمْ يُرْزَقُونَ

እነዚያን በአላህ መንገድ የተገደሉትን ሙታን አድርገህ አትገምታቸው፡፡ በእርግጥ እነርሱ እጌታቸው ዘንድ ሕያዋን ናቸው፤ ይመገባሉ፡፡
         [ሱረቱ ኢምራን 169]

Читать полностью…
Subscribe to a channel