ረመዷን ከምትወደው ምግብ የመራቅ ችሎታህ የሚታይበት ብቻ ሳይሆን ከአላህ የሚያቀርቡ ስራ የምትሰራበት ሀራምን የመራቅ አቅምህ የሚፈተንበትም ወር ነው።
@ya_muhammad_saw
አምላኬ ሆይ!
~በሰዎች መካከል አቆምከኝ፣ወዳንተ እንዳመላክትም ዕድል ሠጠኸኝ፣እኔም ስላንተ ተናገርኩ፤ ስለታላቅነትህም መሰከርኩ። ሰዎችም በመልዕክትህ ላይ ታማኝ እንደሆንኩ አሰቡኝ፣አምነውኝም ወደኔ ቀረቡ፣እኔ ራሴን የማውቅ፣በራሴ የኢማን ሁኔታም የማፍር ሆኜ ሳለሁ ከኔ ብዙ ነገር ጠበቁ።
•ኢላሂ ...ከአሳሳቾች አታድርገኝ፤ በምላስ ወዳንተ ከሚጠሩት በተግባር ግን ከዲን ከሚያርቁት አታድርገን፤ ለሌሎች መካሪ ራሴን ግን ዘንጊ አታድርገኝ።
ሰዎች ከሚያስቡኝ በላይ አድርገኝ። ከዕለት ወደ ዕለትም ብርታትና ፅናቱን ስጠኝ።
ጥሩ ሙስሊምና ጎበዝ አማኝ አድርገህ ግደለኝ። ከደጋጎች ጋርም ቀስቅሰኝ።
@ya_muhammad_saw
وَالصَّافَّاتِ صَفًّا
መሰለፍን በሚሰለፉት፡፡
فَالزَّاجِرَاتِ زَجْرًا
መገሠጽንም በሚገሥጹት፤
فَالتَّالِيَاتِ ذِكْرًا
ቁርኣንንም በሚያነቡት እምላለሁ፡፡
إِنَّ إِلَٰهَكُمْ لَوَاحِدٌ
አምላካችሁ በእርግጥ አንድ ነው፡፡☝️
@ya_muhammad_saw
#ወንድሜ
ሰላት ለምን እንደቀልድ ያመልጥካል??
ለምን??
ጤነኛ ነህ , ንፁ አየር ትተነፍሳለህ , ትበላለህ , ትጠጣለህ , እንደልብህ ትተኛለህ ግን ሰላትን አትሰግድም🙊
ለምን????
ጠይቅ ራስህን አላህ እኮ ወደዚህች ምድር ያመጣን እሱን በብቸኝነት እንድንገዛው ነው።
ወንድሜ ትሞታለህ እኮ
ላትመለስ ታሸልባለህ እኮ
ይህችን ምድር ትተዋታለህ እኮ
ቀብር ትገባለህ እኮ
ታድያ ምን ሰንቀካል ለወደፊቱ ቤትህ ምን አዘጋጅተካል?
ጠይቅ ራስህን⁉️
ወደአላህ ተመለስ ነገ የሚባል ቀን የለም ዛሬውኑ ተውበት አድርግ ሰላትህንም ስገድ ያኔ ዱንያህም አኼራህም ያማረ ይሆናል።✨
@ya_muhammad_saw
ይህ ሰበር ዜና በጣም አስደንጋጭ ነው
ይህን እርኩስ ተግባር ለማክሸፍ
①.ህብረተሰቡን የማንቃት ስራ መስራት
② የጠዋትና የማታ አዝካር ላይ መበርታት
③ ከቁርአን ጋር ያለንን ግንኙነት ማጠናከር
④ የፆም መያዣና መፍጠሪያ ለተቸገሩ ወገኖቻችን እኛው አለው እንበላቸው
⑤ ይህን የድግምት ስራ በመስራት ላይ ያለን አካል እጅ ከፍንጅ ከያዝነው የማያዳግም እርምጃ የሚወሰድበትን ሁኔታ ማመቻቸት
ሙስሊም ወገኖቻችንን ሁሉ ከከሀዲያን ተንኮል አላህ ይጠብቅልን
@ya_muhammad_saw
ረመዳንን ለመቀበል ስናስብ ብዙ ሁኔታዎች...
ከፊታችን ድቅን ይላሉ አይደል ...
አላህዬ እኮ በቅፅበት ሁኔታዎችን ሚቀይር..
ቻይ የሆነ ቃዲር ጌታ ነው አልሀምዱሊላህ ...
ዛሬም ተስፋ አለን አላህዬ አይተወንም ...
እኛ ብቻ በስራ እና በዱዐ አንዘናጋ...
የአላህ ድል ቅርብ ነው!!!
أَمْ حَسِبْتُمْ أَن تَدْخُلُوا الْجَنَّةَ وَلَمَّا يَأْتِكُم مَّثَلُ الَّذِينَ خَلَوْا مِن قَبْلِكُم ۖ مَّسَّتْهُمُ الْبَأْسَاءُ وَالضَّرَّاءُ وَزُلْزِلُوا حَتَّىٰ يَقُولَ الرَّسُولُ وَالَّذِينَ آمَنُوا مَعَهُ مَتَىٰ نَصْرُ اللَّهِ ۗ أَلَا إِنَّ نَصْرَ اللَّهِ قَرِيبٌ
በእውነቱ የእነዚያ ከበፊታችሁ ያለፉት (ምእምናን መከራ) ብጤ ሳይመጣችሁ ገነትን ልትገቡ ታስባላችሁን? መልክተኛውና እነዚያ ከርሱ ጋር ያመኑት «የአላህ እርዳታ መቼ ነው?» እስከሚሉ ድረስ መከራና ጉዳት ነካቻቸው፤ ተርበደበዱም፡፡ ንቁ! የአላህ እርዳታ በእርግጥ ቅርብ ነው (ተባሉም)፡፡
[ሱረቱ በቀራ 214]
አላህዬ ሻዕባንን በመልካም ስራ ይባርክልን
ረመዳንንም በኢማን በአፍያ በሰላም ላይ ሆነን ያድርሰን ደርሰውም ከሚጠቀሙበት ያድርገን ድሉን ይወፍቀን🤲
#ሻዕባንን_በእስቲግፋር!
@ya_muhammad_saw
ሰዎች በኢሻእ እና በፈጅር ሰላት ላይ ምንዳውን ቢያውቁ ኖሮ ተንፈቅፍቀው ይመጡ ነበር ረሱል ሰ.አ.ወ................. ከሚሰግዱት ያድርገን 🤲
@ya_muhammad_saw
💚 ልብስህን እንደ ሚስማር ነገር
ወግቶ ቢይዝብህ ለማላቀቅ
ወደ ኃላ ትመለሳለህ‥
💥 ልክ እንደዛውም ልብህን ወንጀል
ሲይዝብህ ተፀፅተህ ተመለስና
ከወንጀል ተውባ አድርገህ አላቅቃት።
@ya_muhammad_saw
በዝቅታ ከፍታ ሚገኝበት ብቸኛ ስፍራ
የውስጥ ሰላም ማግኛ ሱጁድ🥰
በሱጁድ ወደሱ ...
كَلَّا لَا تُطِعْهُ وَاسْجُدْ وَاقْتَرِب ۩
ይከልከል አትታዘዘው፡፡ ስገድም፤ (ወደ አላህ) ተቃረብም፡፡
[ሱረቱ ዐለቅ 19]
@ya_muhammad_saw
በጌታዋ ላይ ሙሉዕ እምነት ካላት ልብ ተክቢራን ከምትደጋግም ምላስ ውዱዕ ከምታደርግ አጅ የተወረወረች ድንጋይ መቼም አላማዋን አልሳተችም አስትምም !!
القدس عصمت فلسطين 🇯🇴
አላህዬ ድሉን ከኛ ጋር ያድርግልን🤲
فَلَمْ تَقْتُلُوهُمْ وَلَٰكِنَّ اللَّهَ قَتَلَهُمْ ۚ وَمَا رَمَيْتَ إِذْ رَمَيْتَ وَلَٰكِنَّ اللَّهَ رَمَىٰ ۚ وَلِيُبْلِيَ الْمُؤْمِنِينَ مِنْهُ بَلَاءً حَسَنًا ۚ إِنَّ اللَّهَ سَمِيعٌ عَلِيمٌ
አልገደላችኋቸውም ግን አላህ ገደላቸው፡፡ (ጭብጥን ዐፈር) በወረወርክም ጊዜ አንተ አልወረወርክም፡፡ ግን አላህ ወረወረ (ወደ ዓይኖቻቸው አደረሰው)፡፡ ለአማኞችም ከርሱ የኾነን መልካም ጸጋ ለመስጠት (ይህን አደረገ)፡፡ አላህ ሰሚ ዐዋቂ ነውና፡፡
[ሱረቱ አንፋል 17]
صلى الله عليه وسلم🧡
ሰሉ አለል ሀቢቢል ሙስጠፋ...
مَّن يُطِعِ الرَّسُولَ فَقَدْ أَطَاعَ اللَّهَ ۖ وَمَن تَوَلَّىٰ فَمَا أَرْسَلْنَاكَ عَلَيْهِمْ حَفِيظًا
መልክተኛውን የሚታዘዝ ሰው በእርግጥ አላህን ታዘዘ፡፡ ከትእዛዝም የሸሸ ሰው (አያሳስብህ)፡፡ በእነሱ ላይ ጠባቂ አድርገን አልላክንህምና፡፡
[ሱረቱ ኒሳእ 80]
@ya_muhammad_saw
عن أبي حمزة أنس بن مالك الأنصاري- خادم رسول الله صلي الله عليه وسلم _ رضي الله عنه قال: قال رسول الله صلي الله عليه وسلم : (( لله أفرح بتوبة عبده من أحدكم: سقط على بعيره، وقد أضله في أرض فلاة))
(متفق عليه).
“የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዓ.ወ) አገልጋይ አቡ ሐምዛ አነስ ኢብኑ ማሊክ አል-አንሷሪይ (ረ.ዓ) መልእክተኛው (ሰ.ዓ.ወ) እንዲህ ብለው መናገራቸውን አስተላልፈዋል፡-ከእናንተ አንዳችሁ ምድረበዳ መሬት ላይ ያጣትን ግመሉን በድንገት ሲያገኝ ከሚሰማው ደስታ የበለጠ አላህ በባሪየው ንሰሃ የረካል፡፡”
(ቡኻሪና ሙስሊም)
@ya_muhammad_saw ❤
وَلَا تَهِنُوا وَلَا تَحْزَنُوا وَأَنتُمُ الْأَعْلَوْنَ إِن كُنتُم مُّؤْمِنِينَ
እናንተም የበላዮች ስትኾኑ ምእመናን እንደኾናችሁ አትስነፉ፤ አትዘኑም፡፡
[ሱረቱ ኢምራን 139]
ሰበር‼
======
✍ የረመዿን ጨረቃ በሃገረ ሳዑዲ ዓረቢያ ስለታየች ነገ ሰኞ መጋቢት 02, 2016 E.C. (March 11, 2024 G.C.) የረመዿን የመጀመሪያ ቀን ይሆናል።
አላህ የምንጠቀምበት ያድርገን!
ረመዷን ሙባረክ!
✴️ 🌙 *عاجل* ..
*تم رصد هلال رمضان في مرصد سدير*
*غداً الاثنين أول أيام شهر رمضان المبارك*
*{تقبل الله منا ومنكم صالح الاعمال}*
BREAKING NEWS: The Crescent of Ramadan 1445/2024 has been sighted in Saudi Arabia!
Subsequently, Ramadan 1445/2024 begins tomorrow, 11 March 2024
Taraweeh Prayers will begin in the Two Holy Mosques after Isha Prayers
#ቁርዐን
✨የልባችን ብርሃን
✨የቀብራችን ኑር
✨የረህማኑ ቃል
✨የነብዬ ስጦታ
✨የበሽታዎች መድሀኒት
መንድሞቼ/እህቶቼ የተከበረው የቁርዐን ወር ወደኛ እየገሰገሰ ነው።
በደስታ ተቀብለን በቁርዐን እናፍካው ✨
@ya_muhammad_saw
#ረመዷን
✨የቁርዐን ወር
✨የዱዐ ወር
✨የሰደቃ ወር
✨የሀሰናት ወር
✨ይቅር የምንባባልበት ወር
✨መልካም ስራዎች በእጥፍ የሚባዙበት ወር
✨የረህማኑ በረካ የሚወርድበት ወር
ተናፍቀካል 💥
@ya_muhammad_saw
#ረመዷን✨
ያረብ ይህንን ረመዷን በናፍቆት በጉጉት እየጠበቅነው ነውና አደራህን ደርሰው ከሚፆሙት ከምንዳውም ከሚጠቀሙት አድርገን።
@ya_muhammad_saw
"የለይል ሰላት ባይኖር ኖሮ ዱንያ ታስጠላ ነበር"
ይሉ ነበር አንድ ታላቅ ሰው
የዱንያ ማማሯ ለአላህ በማደር ነው
ደስታ ማለት የነፍስን ፍላጎት ገፍቶ ለራህማኑ መዋደቅ ነው
ስኬት ማለት የለሊቶችን ትርፋማነት ተረዶቶ
ለከፍታ መንደርደር ነው
{وَالَّذِينَ يَبِيتُونَ لِرَبِّهِمْ سُجَّدًا وَقِيَامًا}
"እነዚያም ለጌታቸው በግንባራቸው ተደፊዎችና ቋሚዎች ኾነው የሚያድሩት ናቸው፡፡"
[ሱረቱል ፉርቃን:64]
❤️ @ya_muhammad_saw ❤
"ተረጋጋና በደንብ አንብብ"
1.ሶላት ከእንቅልፍ ይበልጥ ነበር ነገር ግን ተኛክ
2.ቁርአን መቅራት ያረጋጋህ ነበር ግን ከሱ ራክ
3.ኢስቲግፋር ሪዝቅን ያሰፋ ነበር ግን ተዘናጋህ
4.አዝካር(አላህን ማውሳት) በቀንህ ላይ በረካ ይጨምር ነበር ግን ተሰላቸክ
5.የተውበት በር ሁሌም ክፍት ነበር ግን ቸኮልክ
#ሻዕባንን_በእስቲግፋር
@ya_muhammad_saw
1.አንድ ቀን ለፈጅር ትነቃለክ፣እናም ፀሐይ በምእራብ ወጥታ ታገኛታለክ።
2.አንድ ቀን ቁርአንን ትከፍታለህ ነገር ግን ገፆቹ ባዶ ሆኖ ታገኛለህ።
3.አንድ ቀን ወደ ሶላት ትቻኮላለህ ነገር ግን አንድም ሱራ ማስታወስ ይከብድሃል።
4.አንድ ቀን ለተውበት ወደ አላህ ትሄዳለህ ነገር ግን የተውባ በሮች ተዘግተው ታገኛለህ።
"አንድ ቀን"ነገ ሊሆን ይችላል
ያን ጊዜ ወደ አላህ መመለስ በጣም ዘግይታልና
አሁን ጊዜ እያለን ወደርሱ እንመለስ።
ነገንም ላንኖር እንችላለን።
ሞት ለህያው ነፍስ ሁሉ ነውና።
@ya_muhammad_saw
አንዳንድ ሰው እየተበደለ ችሎ የሚኖረው አፀፋውን መመለስ አቅቶት ሳይሆን
.
.
በአስተሳሰብ ከበዳዩ ስለሚሻል ነው☺️
እናም ውዶቼ የወራቶች ሁሉ ንጉስ የሆነው የረመዷን ወር ወደኛ እየገሰገሰ ነው ታድያ ለምን አፉ አንባባልም?
ካጠፋቹም ይቅርታ ካላጠፋቹም ይቅርታ ጠይቁ ይቅርታ መጠየቅ መሸነፍ ሳይሆ ትልቅነትን መግለፅ ነው።🫂
አውቄም ሆነ ሳላውቅ አስቀይሜያቹህ ከሆነ ለአላህ ብላቹ አውፍ በሉኝ እኔም አውፍ ብያለሁ🥰
ያአላህ ሁላችንንም በዚህ ታላቅ ወር ተጠቃሚዎች አድርገን 🤲
@ya_muhammad_saw
..."ምንም እንደማያየን አድርገን ወንጀል እንሰራለን፤
እሱም በእዝነቱ ምንም እንዳላየ ሆኖ ይምረናል"🥺❤️አላህዬ...
وَالَّذِينَ عَمِلُوا السَّيِّئَاتِ ثُمَّ تَابُوا مِن بَعْدِهَا وَآمَنُوا إِنَّ رَبَّكَ مِن بَعْدِهَا لَغَفُورٌ رَّحِيمٌ
እነዚያም ኃጢአቶችን የሠሩ ከዚያም ከእርሷ በኋላ የተጸጸቱ ያመኑም ጌታህ ከእርሷ በኋላ በእርግጥ መሓሪ አዛኝ ነው፡፡
[ሱረቱ አዕራፍ 153]
#ሻዕባንን በእስቲግፍር
@ya_muhammad_saw
وَالَّذِينَ آمَنُوا وَعَمِلُوا الصَّالِحَاتِ وَآمَنُوا بِمَا نُزِّلَ عَلَىٰ مُحَمَّدٍ وَهُوَ الْحَقُّ مِن رَّبِّهِمْ ۙ كَفَّرَ عَنْهُمْ سَيِّئَاتِهِمْ وَأَصْلَحَ بَالَهُمْ
እነዚያም ያመኑ፣ በጎዎችንም የሠሩ፣ በሙሐመድ ላይም የወረደው እርሱ ከጌታቸው ሲኾን እውነት ስለ ኾነ ያመኑ ከእነርሱ ላይ ኃጢአቶቻቸውን ያባብሳል፡፡ ኹኔታቸውንም ሁሉ ያበጃል፡፡
[ሱረቱ ሙሀመድ 2]
ሰሀባውም ቀና ብሎ ጨረቃዋን አየ መልሶም እሳቸውን አየ ደጋግሞ ተመለከተ በርግጥም ውበታቹ የበለጠ ነው አለ ...
ሰማይዋን ተመልከት የጨረቃዋንም ውበት አስተውል ረሱሌኮ ከዚህ በላይ ውብ ነበሩ...
ሰለዋቱ ረቢ ወሰላሙሁ አለይከ ያ ሀቢበላህ 🥰 ..
@ya_muhammad_saw
سبحانك اللهم ربنا وبحمدك اللهم اغفر لي
አላህ ሆይ ከጎዶሎዎች ሁሉ የጠራህ ነህ፤
ጌታችን ሆይ!ምስጋናም ላንተ ነው፤
አላህ ሆይ ማረኝ!
@ya_muhammad_saw
#ወላጆችህ አንተ ዘንድ በህይወት አሉ?
የደስታቸው ምንጭ ሁን ፣ተንከባከባቸው፣ዱዐ አድርግላቸው ፣አውራቸው...
#ከወላጆችህ በአካል ርቀሀል?
በስልክ ዘይራቸው፣ሀዲያ ላክላቸው፣ባሉበት እንዲጠብቃቸው ዱዐ አድርግላቸው...
#ወላጆችህ ወደ አኼራ ሂደውብሀል?
ሰደቀቱል ጃሪያ ሁንላቸው፣ብርሀን እንዲሆንላቸቸው ዱዐ አድርግ፣በነሱ ስም ሰድቅላቸው...
۞ وَقَضَىٰ رَبُّكَ أَلَّا تَعْبُدُوا إِلَّا إِيَّاهُ وَبِالْوَالِدَيْنِ إِحْسَانًا ۚ إِمَّا يَبْلُغَنَّ عِندَكَ الْكِبَرَ أَحَدُهُمَا أَوْ كِلَاهُمَا فَلَا تَقُل لَّهُمَا أُفٍّ وَلَا تَنْهَرْهُمَا وَقُل لَّهُمَا قَوْلًا كَرِيمًا
ጌታህም (እንዲህ ሲል) አዘዘ፡- እርሱን እንጂ ሌላን አትገዙ፡፡ በወላጆቻችሁም መልካምን ሥሩ፡፡ በአንተ ዘንድ ኾነው አንዳቸው ወይም ሁለታቸው እርጅናን ቢደርሱ ፎህ አትበላቸው፡፡ አትገላምጣቸውም፡፡ ለእነርሱም መልካምን ቃል ተናገራቸው፡፡
[ሱረቱ ኢስራእ 23]
ሱረቱል ካህፍ ከጁምኣ እስከ ጁምኣ ብርሃን ነው
ልብን ህያው የሚያደርግ የልብ ቀለብ ነው🥰
{الْحَمْدُ لِلَّهِ الَّذِي أَنزَلَ عَلَىٰ عَبْدِهِ الْكِتَابَ وَلَمْ يَجْعَل لَّهُ عِوَجًا ۜ}
"ምስጋና ለአላህ ለዚያ መጽሐፉን በውስጡ መጣመምን ያላደረገበት ሲሆን በባሪያው ላይ ላወረደው ይገባው፡፡"
[ሱረቱል ካህፍ:1]