እውነተኞቹ ምእምናን በእርግጥ በድሎት (ገነት) ውስጥ ናቸው፡፡
إِنَّ الْأَبْرَارَ لَفِي نَعِيمٍ
(አል-ሙጠፍፊን - 22)
"እውነተኞቹ ምእምናን" ማለትም ጌታ ያዘዛቸውን የሚታዘዙ ግዴታቸውን የሚወጡ አላህን እውነተኛ መፍራትን የሚፈሩ ምእመናን
"በእርግጥ በድሎት (ገነት) ውስጥ ናቸው፡፡" ማለትም የማይቋረጥ የማይነጥፍ የማይወገድ የሆነ የጀነት ፀጋ ውስጥ ለዘልዓለም መዘውተራቸው የተረጋገጠ ነው፡፡
አላህ ከነሱ ያድርገን🤲🏻
@ya_muhammad_saw
إِنَّ الْأَبْرَارَ لَفِي نَعِيمٍ وَإِنَّ الْفُجَّارَ لَفِي جَحِيمٍ
"እውነተኞቹ ምእምናን በእርግጥ በጀነት ውስጥ ናቸው፡፡
ከሓዲዎቹም በእርግጥ በጀሀነም ውስጥ ናቸው፡፡" (አል ኢንፊጧር 13-14)
@ya_muhammad_saw
🔥ሦስቱ የጀሀነም ሸለቆዎች
ከነርሱ እንጠንቀቅ!!!❗️
1⃣ ገይ ( ﺍﻟﻐَّﻲ)🔥
2⃣ ወይል ( ﺍﻟﻮَّﻳﻞ)🔥
3⃣ ሰቀር (ﺳﻘﺮ )🔥
ሲብራሩ፧
1⃣ 🌑የገይ ሸለቆ🔥🔥🔥
ሁሉንም ሶላቶች በአንድ ሰብስቦ ለሚሰግድ የተዘጋጀ ሸለቆ ነው።
۞ ﻓَﺨَﻠَﻒَ ﻣِﻦ ﺑَﻌْﺪِﻫِﻢْ ﺧَﻠْﻒٌ ﺃَﺿَﺎﻋُﻮﺍ ﺍﻟﺼَّﻠَﺎﺓَ ﻭَﺍﺗَّﺒَﻌُﻮﺍ ﺍﻟﺸَّﻬَﻮَﺍﺕِ ۖ ﻓَﺴَﻮْﻑَ ﻳَﻠْﻘَﻮْﻥَ ﻏَﻴًّﺎ
(ሱርቱ መርየም፣ - 59)✅
ከእነሱም በኋላ ሶላትን ያጓደሉ (የተዉ) ፍላጎቶችንም የተከተሉ መጥፎ ምትኮች
ተተኩ! የገሀነምንም🔥🔥 ሸለቆ በእርግጥ ያገኛሉ፡፡
2⃣ ወይል ሸለቆ🔥🔥
ሸሪዓ ባልፈቀደው ምክኒያት ሶላትን ለሚያዘገዩ ሰዎች የተደገሰች ናት።
ﻓَﻮَﻳْﻞٌ ﻟِّﻠْﻤُﺼَﻠِّﻴﻦَ
(ሱረቱ አል-ማዑን - 4)✅
ወዮላቸው ለሰጋጆች፡፡
ﺍﻟَّﺬِﻳﻦَ ﻫُﻢْ ﻋَﻦ ﺻَﻠَﺎﺗِﻬِﻢْ ﺳَﺎﻫُﻮﻥَ
(ሱረቱ አል-ማዑን - 5)✅
ለእነዚያ እነርሱ ከስግደታቸው ዘንጊዎች ለኾኑት፤ (ሰጋጆች)፡፡
3⃣ ሰቀር ❗️
ሰቀር ደግሞ ሶላትን ለሚተው ሰው ነው የተሰናዳችው።
🔥ይሄ የእሳት ሸለቆ በጣም ከማቃጠሉ የተነሳ አጥንትን የሚጨርስ ነው።
🌍 ሶላት 🌎
የሚተው ሰው ከነፊርዐውንና ሃማን ጋር ነው የሚቀሰቀሰው። የነቢዩን (ﷺ )
ሸፈዓም አያገኝም።
🌸አላህ ሆይ! ሙስሊሞች(ለአንተ ታዛዦች) አድርገህ ግደለን። ከደጋጎች ጎራም መድበን!
🤲 ያረብ አንትው ጠብቀን 🤲
@ya_muhammad_saw
የአረፋ ቀን 9ኛው ዙልሂጃህ ላይ ነው። ኢንሻአላህ መፆሙን አትርሱ
ነብዩ (ሶ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- "የአረፋን ቀን መፆም ያለፉትን እና መጪ አመታትን ሀጢያትን ያሰርሳል/ያብሳል።"
ሙስሊም
#አስሩ ወርቃማ ቀናቶች!☺️
በዚህ የታሪክ ዳራ የዱንያ ህግ ተቀይሩዋል የሳለ ቢላዋ የኢስማኢልን (ዐ:ሰ) አንገት መቁረጥን ተሳነው ደነዘዘም መቼ ነው የሆነው ነብዩ የአላህ ትእዛዝን ለመፈፀም እጅ ሰተው ንጥፍ ያሉ ሰአት ነው ....
ወደኋላ ተመልሰን ታሪኩን እናጢን ከነባራዊ ህይወታችን እናስተሳስረውማ☺️
فَلَمَّا بَلَغَ مَعَهُ السَّعْيَ قَالَ يَا بُنَيَّ إِنِّي أَرَىٰ فِي الْمَنَامِ أَنِّي أَذْبَحُكَ فَانظُرْ مَاذَا تَرَىٰ ۚ قَالَ يَا أَبَتِ افْعَلْ مَا تُؤْمَرُ ۖ سَتَجِدُنِي إِن شَاءَ اللَّهُ مِنَ الصَّابِرِينَ
ከእርሱ ጋርም ለሥራ በደረሰ ጊዜ «ልጄ ሆይ! እኔ በሕልሜ እኔ የማርድህ ሆኜ አያለሁ፡፡ ተመልከትም፤ ምን ታያለህ?» አለው፡፡ «አባቴ ሆይ! የታዘዝከውን ሥራ፡፡ አላህ ቢሻ ከታጋሾቹ ሆኜ ታገኘኛለህ» አለ፡፡
[ሱረቱ ሳፋት 102]
۩ የዙልሒጃ ወር ነገ ሰኞ አንድ ብሎ ይጀምራል!
⚡️ዛሬ እሁድ ሰኔ 11/Jun18/2023 በሂጅሪያ አቆጣጠር ደግሞ ዙልቀይዳ 29 በሳዑዲ አረቢያ አዲስ ጨረቃ በመታየቷ የዙልሂጃ ወር በነገው እለት ሰኞ ሰኔ 12/june 19 አንድ ብሎ እንደሚጀመር ታውቋል::
⚡️የኢድ አል አድሃ አረፋ በዓልም እሮብ ሰኔ 21/2015/June 28/2023 እለተ ረቡዕ እንደሚውል ታውቋል፡፡
ከነገ ሰኞ ሰኔ 12/June 19 ጀምሮ እስከ ሰኔ 21/june 28 ድረስ ያሉትን 10 ቀናት በኢባዳ ልናሳልፋቸው ይገባል፡፡
⚡️የዙልሂጃን ዘጠኙንም ቀናት ለመፆም ፍላጎት ያለው ከነገ ሰኞ ሰኔ 12 /2015 ጀምሮ መፆም ይችላል፡፡
ታላቅ ምንዳ የሚያስገኘውን የዙልሒጃ 9 (የአረፋን ቀንን) ለመፆም የሚፈልግም ሰኔ 20/june27/2023 እለት ማክሰኞ መፆም ይችላል::
⚡️ኡዱሂያ ለማረድ ኒያው ያላችሁ ካሁን ሰዓት ጀምሮ ጥፍራችሁን እና ፀጉራችሁን ከመቆረጥ ታቀቡ!
⚡️ከነገ ሰኞ ጀምሮ ያሉትን ተከታታይ አስር ቀናቶች በኢባዳ እናሳልፋቸው!
🤲አላህ ይወፍቀን!!
🙌መልዕክቱን ለሁሉም እናዳርስ !
@ya_muhammad_saw
የአላህ መልዕክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
🕋«ተገቢ ያልሆነ መጥፎ ነገር ከአንደበቱ ሳይወጣ የአሏህን ትእዛዝ ምንም ሳይጥስ ሐጅ ያደረገ ሰው ልክ እናቱ እንደወለደችው ቀን ከኃጢእቶቹ ሙሉ ጠርቶ ይመለሳል»
📚【ቡኻሪ ና ሙስሊም】
💎عن أبي هريرة رضي الله عنه قال:
سَمِعْتُ النبي ﷺ يقول: من حجَّ لله فلم يرفث ولم يفسق رجع كيوم ولدته أمه .
📚متفق عليه
@ya_muhammad_saw
#update አንዋር መስጂድ
የሟቾች ቁጥር 14 ደርሷል እየተባለ ነው አሁንም አንዋር መስጂድ ውስጥ ያሉ የተጎዱ ወንድሞች አሉ ምናልባት ከዚህ በኋላም የሟቾች ቁጥር ከዚህ ሊበልጥ ይችላል አላህ ይድረስላቸው!
.
በአላህ ዱዓ አድርጉ 😭
💜 የመጀመሪያው እቅድህ
ፈጅር ሰላት መነሳት ካልሆነ ቀሪውን
ቀንህ ብታቅድም ምንም ዋጋ የለውም
የስኬትን ጅማሮ ከስረሀልና ።
ኢንሿ አላህ ሁላችንም ለፈጅር ሰላት እንዘጋጅ!
@ya_muhammad_saw
በዛ ስፍራ ልቦች ይረጋጋሉ...
የልቦችን ሸክም ፣ የአይኖችን እንባ ፣የልቦችን ስብራት ለመጠገን ለመቅለል እግሮች ወደ ቤቱ ያመራሉ ...
ወደርሱ በተራመዱት እያንዳንዱዋ እርምጃ ...
በውስጡ በተቀመጡበት ግዜ ልክ መላኢኮች እስቲغፋር ሚጠይቁልን ..
በሚስረቀረቁ ድምፃች በየወቅቱ ወደርሱ በመጣራት ለአድማሱ ውበትን ሚያላብስን ያ ሰላማዊ ስፍራ መስጂድ!!! 🥺❤️
#የአላህ ቤት ❤️
وَمَنْ أَظْلَمُ مِمَّن مَّنَعَ مَسَاجِدَ اللَّهِ أَن يُذْكَرَ فِيهَا اسْمُهُ وَسَعَىٰ فِي خَرَابِهَا ۚ أُولَٰئِكَ مَا كَانَ لَهُمْ أَن يَدْخُلُوهَا إِلَّا خَائِفِينَ ۚ لَهُمْ فِي الدُّنْيَا خِزْيٌ وَلَهُمْ فِي الْآخِرَةِ عَذَابٌ عَظِيمٌ
የአላህንም መስጊዶች በውስጣቸው ስሙ እንዳይወሳ ከከለከለና እርሷንም በማበላሸት ከሮጠ ሰው ይበልጥ በዳይ ማነው? እነዚያ ፈሪዎች ኾነው እንጂ ለእነርሱ በቅርቢቱ ዓለም ውርደት አላቸው፡፡ ለነርሱም በመጨረሻይቱ አገር ታላቅ ቅጣት አላቸው፡፡
[ሱረቱል በቀራ 114]
/channel/ya_muhammad_saw
🍃------------🌷----------------🍃
ሶላትን ትቶ እድገትን መመኘት
ያለቁርኣን ና ዚክር ቀልብ ትረጥባለች ብሎ ማሠብ
ዒልምን ዘንግቶ ደረጃ አገኛለሁ ብሎ
ማኮፈስ ቂልነት ነው
🍃------------🌷----------------🍃
በወንጀል እየዋኙ ሰላሜን አጣሁ አብሰከሰከኝ
ወንድምን አዋርዶ ሲያበቃ ቅሌቴ በዛብኝ ሳ ከሚሉ የዲን ሞዛዛወች አሏህ ነጃ ይበለን ተውበትን ይስጠን
🍃------------🌷----------------🍃
በናቱ እየተረገመ ከሌላ ሰው ምርቃን የሚፈልግ አይነት ነፈዝ ከመሆን አሏህ ያድነን
ሽማግሌ አባቱን እየተገላመጠ ለሌሎች ሰወች ደፋ ቀልበስ የሚል አረመኔ አይነት ከመሆን አሏህ ይጠብቀን
🍃------------🌷----------------🍃
ሲኒማ ሲሉት በሽክታ ዲናዊ ስብሰባ ሲሉት በዝምታ አይነት ከንቱነት ነው
ዱንያን ብቻ ጋላቢ መድረሻውን ያላወቀ ወይንም የረሳ ነው
@ya_muhammad_saw
Eid Ul Adha Mubarak ❤️
May Allah accept your sacrifice and bless your family
Eid mubarak 2 all💥
"የተሰበረ ልባቸውን ጠግኑ፤
ስሜታቸውን ጠብቁ፤
ቃላት ምረጡ፤
ድርጊታችሁን አለስልሱ፤
መልካም ትድድርን አትርሱ፤
ማንንም አታቁስሉ፤
በንፅህና በቀናነት ኑሩ።
ይህ የነቢያት መንገድ፣ የመልካሞች መንገድ ነው።"
አስርቱ ቀናት!!!
وَالَّذِينَ آمَنُوا وَعَمِلُوا الصَّالِحَاتِ أُولَٰئِكَ أَصْحَابُ الْجَنَّةِ ۖ هُمْ فِيهَا خَالِدُونَ
እነዚያም ያመኑት በጎ ሥራዎችንም የሠሩት እነዚያ የገነት ጓዶች ናቸው፡፡ እነርሱ በውስጧ ዘላለም ዘውታሪዎች ናቸው፡፡
[ሱረቱ በቀራ 82]
✨የአላህ መልእክተኛ(ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ:–
....አላህን ሶስት ጊዜ ጀነት የለመነ ሰው ጀነት:- "አላህ ሆይ! ጀነት አስገባው ትላለች።
ከእሳት ሶስት ጊዜ በአላህ የተጠበቀ ሰው እሳት:- “አላህ ሆይ! ከእሳት ጠብቀው” ትላለች።]
📚ቲርሚዚ ዘግበወታል።
ጀነትና ጀሀነም ተወዛገቡ…
✨ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል “ጀነትና ጀሀነም ተወዛገቡ። ጀሀነም፦ ‘በውስጤ ጠንካራዎቹ እና በኩራት የሚንቦጣረሩ አሉ’ አለች። ጀነት፦ ‘በውስጤ ደካማዎችና ድሃዎች እንጂ ሌላ አይገቡም’ አለች።
..... በዚህ ግዜ የላቀው አላህ ለጀነት እንዲህ አለ፦ ‘አንቺ ጀነት የእኔ ምሕረት ነሽ። በአንቺ አማካኝነት ለምሻው ባሮቼ ምሕረቴን እለግሳለሁ፡፡’ ለጀሀነምም እንዲህ አለ፦ ‘አንቺ ጀሀነም የኔ ቅጣት ነሽ። በአንቺ አማካኝነት የምሻውን ባሮቼን እቀጣለሁ።’ በማለት በመካከላቸው ፍርድ ሰጠ።”📚 ቡኻሪ ዘግበውታል:
@ya_muhammad_saw
የዙል-ሒጃ 10ቱ ቀናት‼️
▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬
✍የአላህ ሰላምና እዝነት በታላቁ ነብይ በሙሀመድ (ሶለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) እና በባልደረቦቻቸው፣ በቤተሰቦቻቻው ሁሉ ላይ ይሁን፡፡
||
ከተከበሩት ወራት መካከል አንዱ የሐጅ ወር ዙል-ሒጃ ነው።
በነዚህ የተከበሩ በሚባሉት ወሮች ወንጀል አላህ ዘንድ የበለጠ ከባድ የሚሆኑበት፤ መልካም ስራም እጥፍ ድርብ ተደርገው ሚያዙበት ወሮች ናቸው።
ለዚህም የዙል ሒጃን 10ሩን ቀኖች ማጣቀስ ይቻላል።
ከቀናት ሁሉ አላህ ዘንድ የተወደዱት ደግሞ አስሩ የዙል-ሒጃ ቀናት ናቸው።
:
እንደዉም ከዱንያ ቀናት ሁሉ ብልጫ ያላቸው እነዚህ ቀናት ናቸው።
-----------☆☆☆☆☆☆☆-------------
@ya_muhammad_saw
ቁርአን ስኬት ለራቀው ወደ ስኬት ያዳርሰዋል
መርጋት ላቃተው ልብ መርጊያ ማረፊያ ነው
ደስታን ለፈለገ የደስታ ምንጩ ቁርአን ነው
ቁርአን የሂይወት ቅመም የልብ መድሃኒት ነው
በቁአን ለደከመ ሰውነት ብርታል ጉልበት ነው
ለዛለ አእምሮ ለደረቀች ልብ ቀለብ ነው
ላዛነች ልብ ለተሰበረች ሩህ መጠገኛ እዝነት ነው
ቁርአን ህመሙ ለበዛ መዳኛው ለረቀው ፈውስ ነው
መንገዱ ለተፋው ቀኑ ለጨለመበት ብርሃን ነው
ቁርአን ጓደኛ ለሌለው ጓደኛ ነው
ቁርአን የህይወት ማጣፈጫ የልብ ብርሃን ነው🥰 🧡
ቁርአን ውብ ውዱ የአላህ ስጦታ 🧡
ቁርአን ህይወት ነው በፍፁም እንዳትረቀው!
ምንም እንኳን ጉዳይህ ቢበዛ አልመች ቢልህ
ቀጠሮህ ቢበዛ ህመምህ ቢጠናም ከቁርአን
አትዘናጋ!
❤️🎁
#ቁርኣን💫
ያ ጀባር!!!🥺
وَلَا تَحْسَبَنَّ الَّذِينَ قُتِلُوا فِي سَبِيلِ اللَّهِ أَمْوَاتًا ۚ بَلْ أَحْيَاءٌ عِندَ رَبِّهِمْ يُرْزَقُونَ
እነዚያን በአላህ መንገድ የተገደሉትን ሙታን አድርገህ አትገምታቸው፡፡ በእርግጥ እነርሱ እጌታቸው ዘንድ ሕያዋን ናቸው፤ ይመገባሉ፡፡
[ሱረቱ ኢምራን 169]
በኦሮሚያ ክልል ሸገር ሲቲ እየተካሄደ ያለውን የመስጅድ ማፍረስ ዘመቻ አስመልክቶ በስልጤ ዞን የዳሎቻ ከተማ ሙስሊሞች ተቃውሟቸውን አሰምተዋል።
Читать полностью…ወንጀላችን ነው ወላሂ ሌላ ምንም አደለም ባንተ ወንጀል ነው እዚ ወንድማችን ሚሞተው ባንቺ ወንጀል ነው እዚ እህታችን የተጠቃችው በኔ ወንጀል ነው እንዲ የተደፈርነው😭ለአሏህ ብላቹ አፉ በሉኝ🙏አሁን ምንም መፍትሄ የለውም ኢስቲግፋርናዱዐ ብቻ!
Читать полностью…«በታላቁ አንዋር መስጂድ በሰላማዊ ምእመናን ላይ የደረሰውን ጉዳት ተከትሎ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ሼይኽ ሐጂ ኢብራሒም ቱፋ ከሚመለከተው የፌደራል ፓሊስ ኮሚሽን ጋር የተፈጠረውን ቀውስ ለማረጋጋት እና ባስቸኳይ የተጎዱትን ለማትረፍ በሚቻልበት መንገድ ላይ እየተነጋገሩ ቆይተዋል::
በተፈፀመው ጥቃት ጉዳት የደረሰባቸው ወንድሞቻችን የህክምና እርዳታ እንዲያገኙ ወደ ሆስፒታል እንዲወሰዱ አምቡላስ ወደ ቦታው እንዲደርስ እያደረጉ ይገኛሉ::
ታላቁ ኣንዋር መስጂድ ከውጥረት ነፃ እንዲሆን ፣በመስጂዱ ውስጥ የሚገኙ ምዕመናንም በሰላም ወደቤታቸው እንዲገቡ የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ፕሬዝደንት ሼይኽ ሱልጣን አማንን ጨምሮ ሶስት ከፍተኛ አመራሮች ከመጅሊሱ ተወክለው ወደ ቦታው በማምራት ከፀጥታ ኃይሉ ጋር ይህን ተፈፃሚ እንዲሆን እየሰሩ ይገኛሉ::
ከሁሉም ነገር በፊት ሰብኣዊነት መቅደም ስለሚኖርበት የተጎዱትን ወደ ህክምና ቦታ ለማድረስ እና በመስጂዱ ያሉ ምዕመናን በሰላም ወደቤታቸው እንዲገቡ ለማድረግ በሚደረገው ጥረት በአንዋር መስጂድ እና በዙርያው ያለው የፀጥታ ኀይሉም ይህ ተፈፃሚ እንዲሆን የበኩሉን ሓላፊነት እንዲወጣ ጥሪ እናቀርባለን::»
©: ኡስታዝ አቡበከር አሕመድ
🤲አላህ ሆይ በዲናችን ላይ የመጣብንን ፈተና አንሳልን!!
✨✨✨የምዕመናንን ልቦናዎች አስማማ በሃቅ ላይ አንድነታችን የሚጠናከር አድርገው ዲናችንን ከፍ ለማድረግ እየለፉ ያሉትን ሁሉ ከፍ አድርጋቸው ዲናችንን ለማዋረድ የሚጥሩትን ሁሉ አዋርዳቸው::
⚡️በማንችለው ፈተና አትፈትነን
#ኢላሂ ሙስሊሞች አድርገህ እንደፈጠርከን ሙስሊሞች እንደሆንን በተውሂድ ላይ ግደለን
መጨረሻችንን አሳምርልን ከመጥፎ አሟሟትም ጠብቀን
🤲አላህ ሆይ እኛንም ቤተሰቦቻችንንም ካስጨነቀን ነገር ሁሉ በቅርቡ ፈርጀን ጌታችን ሆይ የጠየቅንህን ሁሉ ስጠን ልባችንንም ደስ የሚሰኝ አድርግልን
#የአለማት ጌታ ሆይ በምድርም በሰማይም የሚሳንህ የለምና ምኞታችንን ሁሉ ፈጽምልን ቀልባችንን አንተን በመታዘዝ ላይ የሚንጠለጠል አድርግልን':
#አሏህ ሆይ በመሃሪነትህ ማረን፣ ችሮታህንም እዝነትህንም አውርድልን፣ ፀጋህንም አታሳጣን... አሏህ ሆይ ካንተ ብቻ እንከጅላለን ክጃሎታችንን ሙላልን:: እገዛህንም እንሻለን እና እርዳን፣ባንተ ላይ ሙሉ እምነታችንን አድርገናል እና በሌሎች ላይ የምንደገፍ አታድረገን
አላህ ሆይ በጥበቃህ ጠብቀን በክብርህ አክብረን በጸጋህ አክብረን። በእዝነትህም ማረን አንተ ከአዛኞች ሁሉ በጣም አዛኝ ነህና🤲
@ya_muhammad_saw