ትዕግስት የታላቅነት ድል ነው!!
የሰው ልጅ መልካምን ነገር ሁሉ የሚያገኘው የተወሰኑ ሰአታትን በመታገሱ ነው።
ፈንዲሻ እንዴት አማረብሽ ቢሏት እሳቱን ስለታገስኩ ነው አለች።የምትሰጠው ነገር ብዙም ይሁን ትንሽ ፈገግታ ጨምር/ሪበት።
/channel/ya_muhammad_saw
የሆነ ቀን ይመጣል…
· ፌስ ቡክህ ላይ ቢፈልጉህ ሁሌም ኦፍ ላይን ነህ፡፡
· በዉስጥ መልዕክት ቢልኩልህ አትመልስም፡፡
· ዋትሳፕ ላይ ቢጠብቁህ አትገባም፡፡
· ስልክህ ለረጅም ጊዜ ቢጠራም አታነሳም፡፡
· በኢሜይልህ ምን ሆንክ ብለው ቢጽፉልህም መልስ አትሰጥም፡፡
· ቆይተህ መጥተህ ‹እባካችሁ አጥፍቻለሁ ዐፍዉ በሉኝ› ትላለህ ተብለህ ብትጠበቅም የለህም፡፡
· ሰዎች ሲጠየቁ ስላንተ አላየንም ጠፍቷል ይላሉ፡፡
· ኋላ ነገሩ ሲጣራ እውነትም ለካ አንተ የለህም ጠፍተሃል፡፡ ላትመለስም ሄደሃል።
· የሞት መልኣክ ወደ አኺራ ከወሰደህ ቆይቷል፡፡
· በርግጥም ምንም እንኳን ወደ መቃብር በመግባት ኦፍ ላይን ብትሆንም ፖስት፣ ኮሜንት፣ ሪፕላይ ማድረግ ባትችልም፤ ኦንላይን ሳለህ የፃፍከው ሁሉ ሳይሠረዝ ሳይደለዝ ዛሬም ድረስ አለ፡፡
· ስለሆነም ከሞትክ በኋላ መልካም ሥራህ ይቀጥል ዘንድ ዛሬ ኦንላይን እያለህ መልካም ነገር ስራ አሁን ላይ ሰደቃ ለመስጠት ሁኔታወች ተመቻችተዋል እጅህ ላይ ባለው ስልክ ለነገው ቤት የተወሰነ ሰድቅ
@ya_muhammad_saw ❤️
"ረሱል(ሰ.ዐ.ወ) ምንም አይነት የሚያስከፋና አሳዛኝ ዜና ሲሰሙ፦ "አልሃምዱ ሊላህ አላ ኩሊ ሃሊን"
በሁሉም ነገር (ጥሩም ሆነ መጥፎ) ለአላህ ምስጋና ይገባው ይሉ ነበር::
(ቡኻሪ ዘግበውታል) - ቡኸሪ ዘግበውልታ"
/channel/ya_muhammad_saw
አቡ ሁረይራ (ረ.ዐ) እንዳወሱት የአሏህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- ‹‹ነፍሴ በእጁ በሆነው ጌታ እምላለሁ አንዳችሁ አመነ አይባልም እኔን ከወላጁና ከልጁ በበለጠ ሁኔታ እስካልወደደ ድረስ፡፡››
عن أبي هريرة رضي الله عنه: أن رسول الله صلى الله عليه وسلم قال:
(فوالذي نفسي بيده، لا يؤمن أحدكم حتى أكون
أحب إليه من والده وولده).
❤ @ya_muhammad_saw ❤
"ነብዩ (ሶ.ዐ.ወ)፦ “ከሥራችሁ ሁሉ ብላጭ ይሆነ፥ ወርቅና ብር ከምትለግሱ የተሻለ ምንዳ የሚያስገኝላችሁና ከጠላት ጋር ተገናኝታችሁ አንገታችሁን ከመሞሻለቅ የበለጠ
ሥራ ልጠቁማችሁን?” በማለት ጠየቁ። “አዎ” አሏቸው። “አላህን ማውሳት” በማለት መለሱ። (ቲርሙዝይና ኢብን ማጀህ)”
- ቲርሙዚይ ዘግቦታ"
❤️ @ya_muhammad_saw ❤️
አቡ ሁረይራ (ረ.ዐ) እንዳወሱት የአሏህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- ‹‹ነፍሴ በእጁ በሆነው ጌታ እምላለሁ አንዳችሁ አመነ አይባልም እኔን ከወላጁና ከልጁ በበለጠ ሁኔታ እስካልወደደ ድረስ፡፡››
عن أبي هريرة رضي الله عنه: أن رسول الله صلى الله عليه وسلم قال:
(فوالذي نفسي بيده، لا يؤمن أحدكم حتى أكون أحب إليه من والده وولده).
❤️ @ya_muhammad_saw ❤️
❤ሰዎች በአንዲት ስህተትህ አማካኝነት አንድ ሺህ መልካም ስራህን ይረሱታል።
❤አላህ ግን በአንዲት መልካም ስራህ አማካኝነት አንድ ሺህ ወንጀሎችህን ይምርልሀል።
@ya_muhammad_saw
👀ምርጥ ኮስሞቲክስ💆💆
ለወንድም ለሴትም የሚሆን👇
☀️ለከንፈር__ሀቅን
☀️ለምላስ__ዚክርን
☀️ለድምፅ__ቁርአንን
☀️ለአይን__እረፍትን
☀️ለእጅ በጎነትን
☀️ለአዕምሮ_ጥበብን
☀️ለፍላጎት_ኢማንን
☀️ለነፍስ _ታዛዥነት
/channel/ya_muhammad_saw ❤
💝 #አሏህ_ከአንተ_ጋር_ከሆነ!!!
➩ አትፈራም...... 🍃
➩ አታዝንም.......... 🍃
➩ አትሸነፍም............... 🍃
➩ ደሀም አትሆንም............. 🍃
➩ ሁሉንም አሏህ ያገራልሀል.........🍃
🚫 ዋናው ነገር ግን አንተ
#ከአሏህ_ጋር_ስትሆን_ነው!!!
💖
❤️ #አሏህ_ይወፍቀን
@ya_muhammad_saw
የኹጥባ ሱናዎች
ለሙስሊሞች ዱንያዊና ሀይማኖታዊ ጉዳዮች መስተካከልና ለመሪዎች ዱዓ ማድረግ የተወደደ ነው፡፡ ነብዩ (ﷺ) የጁምዓ ዕለት ኹጥባ ሲያደርጉ በጣታቸው ወደ ላይ እየጠቆሙ ዱዓ ሲያደርጉ ሰዎችም አሚን ይሉ ነበር፡፡
ኹጥባና ሰላት በአንድ ሰው ቢፈፀሙ ይወደዳል፤ ኹጥባ አድራጊው በተቻለ አቅም ድምፁን ከፍ ቢያደርግ የተወደደ ነው፤ ኹጥባን ቆሞ ማድረግ የተወደደ ነው፡፡
ጃቢር ኢብን ሰሙራ እንዳሉት
‹‹ነብዩ (ﷺ) ቆመው ኹጥባ ካደረጉ በኋላ በመሀል ተቀምጠው ከዚያ እንደገና ቆመው ያደርጉ ነበር››[ሙስሊም 862]
ኹጥባን አጠር ማድረግና የሁለተኘውን ኹጥባ ከመጀመሪያው ይበልጥ አጠር ማድረግ፡፡ ዓማር ባስተላለፉት ሀዲስ ነብዩ (ﷺ) እንዲህ ይላሉ
‹‹የአንድ ሰው ኹጥባ አጠር ማለቱና ሰላቱን ረዘም ማድረጉ የአዋቂነቱ ምልክት ነው፡፡ ሰላትን አስረዝሙ ኹጥባን አሳጥሩ››[ሙስሊም 869]
ኹጥባ አድራጊው ወደ ህዝቦች ዞር ብሎ ሠላምታን ማቅረብ፡- ጃቢር እንዳሉት
‹‹ ነብዩ (ﷺ) ሚንበር[የኹጥባው መድረክ (ምኹራብ)] ላይ ሲወጡ ሠላምታ ያቀርቡ ነበር”
አዛን አድራጊው አዛኑን እስኪያጠናቅቅ ሚንበር ላይ መቀመጥ ኢብን ዑመር እንዳሉት ‹‹ነብዩ (ﷺ) በሚንበር ላይ ወጥተው አዛን አድራጊው አዛኑን እስኪጨርስ ሚንበር ላይ ይቀመጡና ሲጨርስ ተነስተው ኹጥባ ያደርጉ ነበር››
@ya_muhammad_saw
ነብዩ ምን አሉ መሰላቹ :-
------------------
ውስጡ ብናኝ ያህል ኩራት ያለበት ሰው ጀነት አይገባም አሉ ከዛ አንድ ሶሀባ ነበረ ኢኮኖሚካሊ ጥሩ የሆነ ሰው ነውና ሁሌ የሚለብሰው ብራንድ ልብሶችን ብራንድ ጫማዎችን ነው በጣም እራሱን የሚጠብቅ ነበር እና ደነገጠ መለባበሴ ኩራተኛ ያስብለኝ ይሆን በአሁኑ ግዜ አዳዲስ ልብስ መልበስ ብራንድ መኪና መንዳት እንደማለት ነው ከዛ ይህ ሶሀባ ይሄ ይሆናል ብሎ የአላህ መልክተኛ ሰ.ዐ.ወ አንድ ሰው ልብሱ ጥሩ እንዲሆን ይመኛል ጫማው ጥሩ እንዲሆን ይመኛል ኢሄ ኩራት ነው እንዴ አላቸው ውዱ ነብዬም መለሱለት እንዲህማ አይደለም አላህ ውብ ነው ውቦችን ነው ሚወደው አሉት ሁሌ ሚፀዳዱትን ራሳቸውን ሚጠብቁትን ነገር ግን አሉ ኩራት ማለት እውነት ሲመጣለት እውነትን መመለስ አሉ
ሰዎችን ማሳነስ አሉ ዝቅ አድርጎ መመልከት አሉ🥺
ወንድሞቼ እኛስ የት ነን??
አደራ ከኩራት ራሳችሁን ጠብቁ አደራ!!
@ya_muhammad_saw
🕋ሰላትን በተገቢው መልኩ ያለመስገድ
ምክንያቶች:
እነዚህ ምክንያቶች ብዙ ናቸው: አሳሳቢ እንዲሁም ትልቅ ከሚባለው ምክንያቶች:
🛑 ስሜትን መከተል ስለዚህም ነው الله ስሜትን መከተልን ሰላትን ከማጥፋት ጋር አቆራኝቶ የጠቀሰው ።
{فخلف من بعدهم خلف أضاعوا الصلاة وتبعوا الشهوات فسوف يلقون غيا★ إلا من تاب وآمن} ..
ከእነሱም በኃላ ሰላትን ያጓደሉ( የተው) ፍላጎቶችንም የተከተሉ መጥፎ ምትኮች ተተኩ የጀሃነምንም ሸለቆ በርግጥ ያገኛሉ።
🛑 የዚህን ሰላት እውነታ አለመረዳት: አሳሳቢነቷን አለማወቅ: ጥቅሟን አለማወቅ: ትሩፋቷን አለማወቅ: ምንዳዋን አለማወቅ: الله ዘንድ ያላትን ደረጃ አለማወቅ: ሌሎችም ምክንያቶች አሉ።
🛑 ሰላት ላይ ቸልተኛ ከሚያደርጉ ምክንያቶች: አብዘሃኛው ሰጋጅ ሚሰግደው እንደ አካል ስራ ብቻ ነው የአካል እንቅስቃሴ የልብ ስራ የሌለበት: እነሱ ዘንድ መተናነስ መፍራት አላህ ፊት መዋረድ ሚባል ነገር የለም: የሚሉትንም አያስተውሉም የሚሰሩትንም እንደዛው: ስለዚህ ከሰላት ምንም ሳይጠቀሙ ይወጣሉ ። ለልቦቻቸውም ብርሃን ሚባል ነገር አያገኙም: እምነታቸውም ላይ ጭማሬ አያገኙም: ከመጥፎ እንዲሁም ከተጠሉ ነገራቶችም መራቅ አይችሉም ።
✳️ ይህ ሁሉ የሆነው እነሱ ሚሰግዱት የአካል ሰላት እንጂ የነፍስ ሰላት ስላልሆነች ነው። ለዚህች ሰላት ሚገባትን ሃቅ ቢሰጧት: የፈሩ ሆነው ልባቸውን ሰብስበው: ወደ الله ተመልሰው እንዲሁ በሱ ፊት መቆማቸውን እያሰቡ ቢሰግዱ እቺን ሰላት ይወዷት ነበር ልባቸውም ወደ እሷ የተንጠለጠለ ይሆን ነበር ። ለዚህም ነው ነብዩ صلى الله عليه وسلم ሰላት የአይን መርጊያዬ ተደረገች ያሉት
لشيخ العلامة محمد صالح لعثيمين.
📚المصدر فتاوى نور لى الدرب لشريط (72)
@ya_muhammad_saw
:::::::ህይወት ሚስጥር ናት:::::::☜
☞⇡በሕይወትህ ምን እደሚጠብቅህ ፣ምን እንደሚያጋጥምህ አታውቅም። ሁሉንም ነገር ለመቀበል እራስህን ዝግጁ አድርግ። ደግም ሲያጋጥምህ አመስግን፣ ክፉም ሲያጋጥምህ ታጋሽና አመስጋኝ ሁን ። ከችግርም ጋር ምቾት አለና እራስህን አፅናና። ይቺ ምድር የፈተና ቦታ መሆኗን ላፍታም አትዘንጋ።
አላህም እንዲህ ይለናል፦
كُلُّ نَفْسٍ ذَائِقَةُ الْمَوْتِ ۗ وَنَبْلُوكُم بِالشَّرِّ وَالْخَيْرِ فِتْنَةً ۖ وَإِلَيْنَا تُرْجَعُونَ
📖 አል-አንቢያ: 35 📖
ነፍስ ሁሉ ሞትን ቀማሽ ናት፡፡ ለመፈተንም በክፉም በበጎም እንሞክራችኋለን፡፡ ወደኛም ትመለሳላችሁ፡፡
«አስታውስ! አላህ ከታጋሾች ጋር መሆኑን። አላህን በኸይር ጠርጥረው ኸይር ይሰጥሃል።
وَلَسَوْفَ يُعْطِيكَ رَبُّكَ فَتَرْضَىٰ
📖አል ዱሃ :5📖
ጌታህም ወደ ፊት (ብዙን ስጦታ) በእርግጥ ይሰጥሃል፡፡ ትደሰታለህም፡፡
እናም አላህ እዳለው፦
فَاصْبِرْ صَبْرًا جَمِيلًا
📖 አል-መዓሪጅ:5📖
መልካምንም ትዕግስት ታገሥ፡፡
وَاللَّهُ يُحِبُّ الصَّابِرِينَ
📖አሊ-ዒምራን:146 📖
አላህም ትዕግስተኞችን ይወዳል፡፡
@ya_muhammad_saw
የግብረ-ሰዶም ሸሪዐዊ ቅጣቱ፡-
ከነቢያችን (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) በተገኘው ሐዲሥ መሰረት፡ በዚህ ተግባር ላይ ሆኖ ንሰሀ (ተውበት) ከማድረጉ በፊት በአይን ምስክሮች የተገኘ፣ ለአካለ መጠን የደረሰ ሰው ቅጣቱ ‹‹መገደል›› ነው፡፡ ይህም የድርጊቱን አስቀያሚነት፡ ማኃበረሰብ የሚበክል ትውልድ እንዳይቀጥል የሚያደርግ እንቅፋት በመሆኑ ነው፡፡ ሐዲሡ እንዲህ ይነበባል👇
ዐብደላህ ኢብኑ ዐባስ (ረዲየላሁ ዐንሁማ) እንደነገረን የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም)፡- "የሉጥ ህዝቦችን አይነት ስራ የሚሰራን ሰው ካገኛችሁት የሚፈጽመውንም፣ የሚፈጸምበትንም ሰው ግደሉ" (ቲርሚዚይ 1456፣ አቡ ዳዉድ 4462፣ ኢብኑ ማጀህ 2561)፡፡
@ya_muhammad_saw
ድሃ ማለት ማን እንደሆነ ታወቃላችሁ⁉️
የአላህ መልክተኛ (ሰለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም) ከዕለታት አንድ ቀን ከባለደረቦቻቸው ቁጭ ብለው ሳለ፦
“ድሐ ማን እንደሆነ ታውቃላችሁ?” በማለት ይጠይቃሉ።
•
ሰሐቦችም ፦ “እኛ ጋር ድሀ ማለት ምንም ንብረትና ገንዘብ የሌለው ነው” በማለት ይመልሳሉ።
***
የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) ግን፦ “ከኡመቴ ደሀ ማለት የትንሳኤ ቀን በብዙ ሰላቶች፤ ዘካዎችና፤ ፆሞች የሚመጣ ሰው ነው፣ ነገር ግን ይህ ሰው አንድ ወንድሙን ሰድቧል፣ ሌላው ላይ ዋሽቷል፣ የአንዱን ገንዘብ ያለአግባብ ወስዷል፣ የሌላውን ደም አፍስሷል፣ አንዱን መትቷል፣ በሌላው ላይም ድንበር አልፏል፣
***
ያኔም የቂያም ቀን (የምርመራ ቀን) የራሱን ጥሩ ሥራዎች ለበደላቸው በካሳ መልክ አሳልፎ ይሰጣል፣ ጥሩሥራው ለመካሻ አልበቃ ይለውና የበደላቸውን ሰዎች ኃጢያት ይሸከማል፣ ከዚያም ወደ ጀሀነም ይወረወራል” በማለት መለሱላቸው
@ya_muhammad_saw
ውሎ ከ #ቁርዓን ጋር
ሀፍዝ..
ካልሃፈዝክ ,ሙራጃ አድርግ,ሙራጃ ካላደረክ,
ቅራ, ካልቀራህ አድምጥ
/channel/ya_muhammad_saw
#እንተዋወስ
👉. ለመጀመሪያ ጊዜ የፈሰሰው የሰው ልጅ ደም የእናታችን ሀዋ የሀይድ ደም ነው።
👉. ለመጀመሪያ ጊዜ በሶፋዋና በመርዋ የሮጠች ሀጀር ኡሙ እስማዒል ናች ።(ዓለይሃ ሰላም)
👉. ለመጀመሪያ ጊዜ የዘምዘም ውሀ የጠጣው ነብዩ ኢስማዒል አለይሂ ሰላም ናቸው።
👉. ከነብዩሏህ ኢብራሂም በመቀጠል ከነቤተሰቡ ለኢስላም የተሰደደው ዑስማን ኢብን ዐፋን እና ባለቤቱ ሩቅያ ቢንት ሙሀመድ ﷺ ስደቱም ወደ ሀበሻ ነበር።
👉. ለመጀመሪያ ጊዜ ሳሙና የሰራው ነብዩ ሱለይማን ዐለይሂ ሰላም ናቸው።
👉. ለመጀመሪያ ጊዜ በአረብኛ ቋንቋ የተናገሩ ነብዩ ኢስማዒል ዐለይሂ ሰላም ነው።
👉. ለመጀመሪያ ጊዜ ቁርዓን እንዲሰበሰብ ያደረጉ አቡበከር አስሲዲቅ ረድየላሁ ዓንሁ ናቸው።
👉. የመጀመሪያዋ በኢስላም ሸሂዳህ (ሰምአት ) የሆነችው ሱመያ ( ኡሙ አማር ) እንደሆነች ፤
👉. ለመጀመሪያ ጊዜ የሰማዕታት አለቃ የተባሉት ሀምዛ ቢን ዐብዱልሙጦሊብ እንደሆኑ ፤
👉. ለመጀመሪያ ጊዜ አህመድ በሚለው ስም የተጠሩ ነብዩ ሙሀመድ ﷺ እንደሆኑ ፤ እንዲሁም ለመጀመርያ መሐመድ የሚል ስም የተሰየሙ ነብያችን ﷺ ናቸው።
👉. የነብዩ ﷺ የመጀመሪያ ልጅ ከእናታችን ኸዲጃ የተወለደው ቃሲም ነው።
👉. ለመጀመርያ ግዜ ለነብዩ ﷺ ጂብሪል ዓለይሂ ሰላም ያሰገዳቸው ሰላት የዝሑር ሰላት ነው።
👉. ለመጀመርያ ጀነት የሚገባው ኡመት የሙሐመድ ﷺ ነው።
👉. ለመጀመርያ በሰማይ ላይ አዛን ያደረገውጂብሪል ዓለይሂ ሰላም ነው።
👉. ለመጀመርያ ግዜ "ሰብሃን ረቢ ዓዕላ" ያለው እስራፊኤል ዓለይሂ ሰላምነው።
👉. ለመጀመርያ ግዜ የወረደው የቁርአን አንቀፅ ኢቅራእ ነው።
👉. ለመጀመርያ ግዜ መፃፍ የጀመረው ኢድሪስ ዓለይሂ ሰላም ነው።
👉. ለመጀመርያ በተውራት ላይየወረደው ቃል ቢስሚላህ አረሕማን አረሒም ነው።
👉. ለመጀመርያ ግዜ በአላህ መንገድ የተዋጋው ኢድሪስ ዓለይሂ ሰለም ነው።
👉. ለመጀመርያ ግዜ ሰላተል ጋይብ የተሰገደው ለነጃሺ ነው።
👉. ለመጀመርያ የአቡና አደም ቃል የተናገሩት አልሐምዱሊላህ ነው።
👇👇👇👇👇👇
ለማስታወስ ያህል
just ሼር ማድረግ እንዳትረሱ ሼር
ጀዛኩምአላህ ኼር።
/channel/ya_muhammad_saw
💚💚የጀነት በራፍ 8 ናቸው💚💚
1. ባቡ ሰላህ:- ሰላትን አዘውትረው ለሚስግዱ ሚገቡበት በር
2. ባቡ ጂሀድ:- ጂሀድ ለሚወጡ ሰዎች ሚገቡበት በር
3. ባቡ ሰደቃህ:- ሰደቃህ ለሚያወጡ ሰዎች ሚገቡበት በር
4. ባቡ ረያን:- የፆመኞች በር
5.ባቡ ሀጅ:- በየአመቱ ሀጅ ለሚያደርጉ ሰዎች
6.ባቡ ቃዲሚን:- ለታጋሾች እና ይቅርታ አድራጊዎች
7.ባቡ ኢማን:- ለደግ ሰዎች እና እምነታቸውን በደግነት ለሚጠብቁ
8.ባቡ ዚክር:- አላህን በብዛት ለሚያወሱ
ያረቢ ከጀነት ሰዎች አርገን🤲🥰
🖤🖤የጀሀነም በራፍ 7 ናቸው🖤🖤
1.ጀሂም:- በአላህ እና በመልክተኛው አምነው ትእዛዝ ያልጠበቁ ሰዎች ሚገቡበት በር ነው
2.ጀሀነም:- ትልቁ በር ሲሆን ጣኦት አምላኪ ሚገቡበት ነው
3.ሰኢር:- እሳትን ሚያመልኩ ሚገቡበት ነው
4.ሰቀር:- በአላህ የማያምኑ ሚገቡበት ነው
5.ለዛ:- ሙሳን አምላክ ነው ያሉ ሚገቡበት ነው
6.ኸዊያህ:- ኢሳን አምላክ ነው ያሉት ሚገቡበት ነው
7.ኩታማህ:- በአስከፊነቱ ከጀሀነም የላቀ ሲሆን ለአጋሪዎች ተደግሳለች
ያረህማን ከጀሀነም ነጃ በለን🤲🥺
ጀነት ሲገለፅ የሰው ልጅ ተስፈኝነቱ ሚገልፀው በሚወደው ከለር በልምላሜ በአትክልት በዛፎች በአረንጓዴ ከለር ነው።💚💚💚💚💚💚
ኩፍር እና ጀሀነም እንዲሁ የሰው ልጅ በሚፈራው ተስፋ መቁረጡን ሀዘኑን የአደጋውን ከባድነት ሚገልፀው ጥቁር ከለር ነው።🖤🖤🖤
❤ @ya_muhammad_saw ❤
👉የጠዋት ጉርሻ
"አቡዘር (ረ.ዐ) እንዳሉት አንድን ሰው እናቱን በመጥፎ ስም በመጥራት አነወርኩት፡፡ ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉኝ፡- ‹‹አቡ ዘር ሆይ! በእናቱ አነወርከውን? አንተ በውስጥህ የ‹‹ጃሂሊያ›› ባህሪ ያለብህ ነህ፡፡ ባሪያዎቻችሁ ወንድሞቻችሁ ናቸው፡፡ አላህ በእጆቻችሁ ስር አድርጓቸዋል፡፡ ወንድሙ በእጁ ስር የገባለት ሰው ከሚበላው ይመግበው፣ ከሚለብሰው ያጎናጽፈው፣ የማይችሉትንም ነገር እንዲሰሩ አትጠይቋቸው፡፡ ይህንን የምትፈጽሙ ከሆነ ግን እገዟቸው፡፡››
(ቡኻሪ ዘግበውታል) - ቡኸሪ ዘግቦታ"
❤️ @ya_muhammad_saw ❤️
«ሰደቃ የሚሰጥ ሰው ሰደቃው ደሃ ሰው እጅ ላይ ከማረፏ በፊት አላህ እጅ ላይ የምታርፍ መሆኗን ቢያውቅ የሰጪው ሰው ደስታ ከተቀባዩ ደስታ ይበልጥ ነበር።»
ኢብኑል ቀይም🗣
❤️ @ya_muhammad_saw ❤️
አነስ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፉት ነብዩ(ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል ፡- ‹‹አንዳችሁ እምነት ሊኖረው አይችልም - ለራሱ የሚወደውን ለወንድሙ እስካልወደደ ድረስ፡፡››
عن أنس، عن النبي صلى الله عليه وسلم قال:
(لا يؤمن أحدكم حتى يحب لأخيه ما يحب لنفسه).
@ya_muhammad_saw
🔸እህቴ አስተውይ🔸
አጂብ!!ብርድን ፈርተሽ ትሸፈኝያለሽ ብርዱ እንዳያገኝሽ ደራርበሽ ትወጪያለሽ። {ግን የአሏህን ቅጣት ፈርተሽ አትሸፈኚም}የቱ ነው ቅጣቱ ህመሙ ሚበረታው የዛሬ ጊዚያዊው ብርድ ወይስ ያ አስፈሪው እሳት «
@ya_muhammad_saw ❤
👉በፈተና ዉስጥ👇
🌙🌙ሁሌም አላህ በፈተና ውስጥ ብርሃንን ያሳየናል
ፈተና ቢበዛብህ በአላህ ተስፋ አትቁረጥ አላህ ሁሉንም ነገር በፈተና ዉስጥ ነው ሚያሳካልህ ሲጨንቅህ አላህን ለምን ወደሱም ተመለስ ቁርአንን ቅራ ያኔ ሁሉንም ነገር በድል ትወጠዋለህ ድል ከአንተ ጋር ትሆናለች ላኢላሃ ሃኢለላህ ሙሃመደን ረሱለላህ🌙🌙🌙
@ya_muhammad_saw ❤
አላህ ሆይ!🤲
ስላለፈው ጉድለታችን ሁሉ ማረን፣የቀረውን አሳምርልን፣ ዉዴታህን፣ ምህረትህን፣ ጀነትህን አትንፈገን!
አሚን!🤲
@ya_muhammad_saw
የአላህ መልዕክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል;- አላህ ዘንድ ከቀኖች ሁሉ በላጩ የጁምዓ ቀን ነው።
﷽ إِنَّ اللَّهَ وَمَلَائِكَتَهُ يصلون عَلَى النَّبِيِّ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آَمنوا صَلُّوا عليه وَسَلِّمُوا تَسْلِيمًا
የአላህ መልዕክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦ በጁምዓ ቀን በኔ ላይ ሰላዋት ማውረድን አብዙ፣ በኔ ላይ አንድ ሰላዋት ያወረደ አላህ በእርሱ ላይ አስር ሰላዋት ያወርድበታል።
💌ነቢዩ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦💌
ስለሆነ እውቀት ተጠይቆ የደበቀው ሰው
አሸናፊውና የላቀው አላህ በቂያማ ቀን
በእሳት ልጎም ይለጉመዋል።
☞ሶሒሁል ጃሚዕ፡ 6284
@ya_muhammad_saw
📚አሏህ ሆይ በአንተ ለዚህ ማለዳ በቅተናል።በአንተ ለምሽት እንበቃለን። በአንተ ህያው ሆነናል። በአንተም እንሞታለን።መመለሻ ወደ አንተ ነው።
اللهم نسألك خير مافي هذا اليوم وخير ما بعده
وأعوذ بك من شر ما في هذا اليوم وشر مابعده
@ya_muhammad_saw
✅ትልቅ ብሥራት!
~
ለአንድ ወንድምህ ብድር አበድረህ በሆነ የጊዜ ገደብ እንዲመልስልህ ብትስማሙ...
👉 ካበደርክበት ጊዜ አንስቶ እስከተስማማችሁበት ጊዜ ድረስ በገንዘቡ ልክ በየቀኑ እንደምትሰድቅ ይታሰብልሀል።
👉 የጊዜ ገደቡ ተጠናቆ "ሌላ ጊዜ ስጠኝ" ቢልህና ብትስማማ ከዚህ ጊዜ አንስቶ ደግሞ በየቀኑ በመጠኑ ሁለት እጥፍ እንደምትሰድቅ ይቆጠርልሀል።
ማስረጃውስ?
~~~~
... ሶሐባው ቡረይዳ ረዲየላሁ ዐንሁ ነብዩን ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ﷺ እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ ብለዋል: –
(مَنْ أَنْظَرَ مُعْسِرًا فَلَهُ بِكُلِّ يَوْمٍ مِثْلِهِ صَدَقَةٌ)
"ችግረኛን ጊዜ የሰጠ ለሱ በየቀኑ አምሳያውን ሶደቃ አለው።"
•
🎈 ከዚያም እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ አሉ:–
(مَنْ أَنْظَرَ مُعْسِرًا فَلَهُ بِكُلِّ يَوْمٍ مِثْلَيْهِ صَدَقَةٌ)
"ችገረኛን ጊዜ የሰጠ ለሱ በየቀኑ ሁለት አምሳያውን ሶደቃ አለው።"
•
በዚህን ጊዜ "የአላህ መልእክተኛ ሆይ! ‘ችግረኛን ጊዜ የሰጠ ለሱ በየቀኑ አምሳያውን ሶደቃ አለው’ ስትል ሰምቼህ ነበር። ከዚያ ደግሞ ‘ችግረኛን ጊዜ የሰጠ ለሱ በየቀኑ ሁለት አምሳያውን ሶደቃ አለው’ ስትል ሰማሁህ?" አልኳቸው።
🎈 እሳቸውም እንዲህ አሉ: –
•
(لَهُ بِكُلِّ يَوْمٍ صَدَقَةٌ قَبْلَ أَنْ يَحِلَّ الدَّيْنُ ، فَإِذَا حَلَّ الدَّيْنُ فَأَنْظَرَهُ فَلَهُ بِكُلِّ يَوْمٍ مِثْلَيْهِ صَدَقَةٌ ) .
"የእዳው መክፈያ ጊዜ እስከሚደርስ ድረስ ለሱ በየቀኑ አምሳያውን ሶደቃ አለው። ጊዜ ገደቡ ደርሶ ተጨማሪ ጊዜ ከሰጠው ደግሞ ለሱ በየ እለቱ ሁለት አምሳያውን ሶደቃ አለው።"
•
📚 ኢማሙ አሕመድ የዘገቡት "ሶሒሕ" ሐዲሥ ነው።
•
ከዚህም የበለጠውን ደግሞ ተመልከት!
•
ከአቢል የሰር ረዲየላሁ ዐንሁ ተይዞ የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል: –
( مَنْ أَنْظَرَ مُعْسِرًا أَوْ وَضَعَ عَنْهُ أَظَلَّهُ اللَّهُ فِي ظِلِّهِ )
"ችግረኛን ጊዜ የሰጠ ወይም የተወለት አላህ በጥላው ስር ያስጠልለዋል።"
•
📚 ሙስሊም ዘግበውታል።
@ya_muhammad_saw
አራት ነገሮች ሪዝቅን ይሰበስባሉ ፦
....ሌሊት መቆም(መስገድ) ፣ በሌሊቱ ማብቂያ ኢስቲጝፋርን ማብዛት ፣ ምፅዋትን ማዘውተር ፣ በእለቱ መጀመሪያ እና ማብቂያ መዘከር
አራት ነገሮች ደሞ ሪዝቅን ይከለክላሉ፦
ንጋት ላይ መተኛት ፣ ጥቂት መስገድ ፣ ስልቹነት ፣ ከኃዲነት
الإمام ابن القيم رحمه الله 📚 زاد المعاد ~ ٤ / ٣٧٨ .
@ya_muhammad_saw
እኔ ስሞት...
1. ከእኔ ጋር የሚዛመዱ ሁሉንም ነገሮች ሰርዝ ❲ፎቶዎች፣ ቻቶች፣ ቪዲዮዎች❳
2. የኔን ፎቶዎች ወይም መልዕክቶች ለማንም አታጋራ።
3. የኔን ሶሻል ሚድያ ❲ፌስቡክ፣ ቴሌግራም...ወዘተ❳ ሪፖርት በማድረግ አዘጋ።
4. የኔን የሞተ አካል፣ ከሞቴ ጋር የሚገናኝ ማንኛውንም ነገር በፍፁም ፎቶ አታንሳ።
5. አስቤውም ሆነ ሳላስበው ከጎዳውህ ይቅር በለኝ።
6. ለሞተችው ነፍሴ ብዙ ዱዓ አድርግላት።
7. የኔ ወዳጅ ማንኛውም ገንዘብን የተመለከተ ቅሬታ ካለህ በቅንነት ቤተሰቤን ተገናኝና ጠይቅ...ጨርስ።
እባክህ በፍፁም ሌላ ነገር አትንካ... አታስቸግር።
ሞት ወደእኛ መች እንደሚመጣ አናውቅም። በማንኛውም ሰአት እና ጊዜ ከፊቱ ልንቆም እንችላለንና።
ሞት ወደ እኛ ሲመጣ ምንም ማሳወቂያ መልዕክት አይልክምና።
በቃ ይህው ነው መልዕክቴ።
አላህ ረጅምን እድሜ ይስጠን።
ራስህን ጠብቅ፣ በደስታ በጤና ኑር።
👇👇👇
@ya_muhammad_saw