ረመዳንን ለመቀበል ስናስብ ብዙ ሁኔታዎች...
ከፊታችን ድቅን ይላሉ አይደል ...
አላህዬ እኮ በቅፅበት ሁኔታዎችን ሚቀይር..
ቻይ የሆነ ቃዲር ጌታ ነው አልሀምዱሊላህ ...
ዛሬም ተስፋ አለን አላህዬ አይተወንም ...
እኛ ብቻ በስራ እና በዱዐ አንዘናጋ...
የአላህ ድል ቅርብ ነው!!!
أَمْ حَسِبْتُمْ أَن تَدْخُلُوا الْجَنَّةَ وَلَمَّا يَأْتِكُم مَّثَلُ الَّذِينَ خَلَوْا مِن قَبْلِكُم ۖ مَّسَّتْهُمُ الْبَأْسَاءُ وَالضَّرَّاءُ وَزُلْزِلُوا حَتَّىٰ يَقُولَ الرَّسُولُ وَالَّذِينَ آمَنُوا مَعَهُ مَتَىٰ نَصْرُ اللَّهِ ۗ أَلَا إِنَّ نَصْرَ اللَّهِ قَرِيبٌ
በእውነቱ የእነዚያ ከበፊታችሁ ያለፉት (ምእምናን መከራ) ብጤ ሳይመጣችሁ ገነትን ልትገቡ ታስባላችሁን? መልክተኛውና እነዚያ ከርሱ ጋር ያመኑት «የአላህ እርዳታ መቼ ነው?» እስከሚሉ ድረስ መከራና ጉዳት ነካቻቸው፤ ተርበደበዱም፡፡ ንቁ! የአላህ እርዳታ በእርግጥ ቅርብ ነው (ተባሉም)፡፡
[ሱረቱ በቀራ 214]
አላህዬ ሻዕባንን በመልካም ስራ ይባርክልን
ረመዳንንም በኢማን በአፍያ በሰላም ላይ ሆነን ያድርሰን ደርሰውም ከሚጠቀሙበት ያድርገን ድሉን ይወፍቀን🤲
#ሻዕባንን_በእስቲግፋር!
@ya_muhammad_saw
ሰዎች በኢሻእ እና በፈጅር ሰላት ላይ ምንዳውን ቢያውቁ ኖሮ ተንፈቅፍቀው ይመጡ ነበር ረሱል ሰ.አ.ወ................. ከሚሰግዱት ያድርገን 🤲
@ya_muhammad_saw
💚 ልብስህን እንደ ሚስማር ነገር
ወግቶ ቢይዝብህ ለማላቀቅ
ወደ ኃላ ትመለሳለህ‥
💥 ልክ እንደዛውም ልብህን ወንጀል
ሲይዝብህ ተፀፅተህ ተመለስና
ከወንጀል ተውባ አድርገህ አላቅቃት።
@ya_muhammad_saw
በዝቅታ ከፍታ ሚገኝበት ብቸኛ ስፍራ
የውስጥ ሰላም ማግኛ ሱጁድ🥰
በሱጁድ ወደሱ ...
كَلَّا لَا تُطِعْهُ وَاسْجُدْ وَاقْتَرِب ۩
ይከልከል አትታዘዘው፡፡ ስገድም፤ (ወደ አላህ) ተቃረብም፡፡
[ሱረቱ ዐለቅ 19]
@ya_muhammad_saw
በጌታዋ ላይ ሙሉዕ እምነት ካላት ልብ ተክቢራን ከምትደጋግም ምላስ ውዱዕ ከምታደርግ አጅ የተወረወረች ድንጋይ መቼም አላማዋን አልሳተችም አስትምም !!
القدس عصمت فلسطين 🇯🇴
አላህዬ ድሉን ከኛ ጋር ያድርግልን🤲
فَلَمْ تَقْتُلُوهُمْ وَلَٰكِنَّ اللَّهَ قَتَلَهُمْ ۚ وَمَا رَمَيْتَ إِذْ رَمَيْتَ وَلَٰكِنَّ اللَّهَ رَمَىٰ ۚ وَلِيُبْلِيَ الْمُؤْمِنِينَ مِنْهُ بَلَاءً حَسَنًا ۚ إِنَّ اللَّهَ سَمِيعٌ عَلِيمٌ
አልገደላችኋቸውም ግን አላህ ገደላቸው፡፡ (ጭብጥን ዐፈር) በወረወርክም ጊዜ አንተ አልወረወርክም፡፡ ግን አላህ ወረወረ (ወደ ዓይኖቻቸው አደረሰው)፡፡ ለአማኞችም ከርሱ የኾነን መልካም ጸጋ ለመስጠት (ይህን አደረገ)፡፡ አላህ ሰሚ ዐዋቂ ነውና፡፡
[ሱረቱ አንፋል 17]
صلى الله عليه وسلم🧡
ሰሉ አለል ሀቢቢል ሙስጠፋ...
مَّن يُطِعِ الرَّسُولَ فَقَدْ أَطَاعَ اللَّهَ ۖ وَمَن تَوَلَّىٰ فَمَا أَرْسَلْنَاكَ عَلَيْهِمْ حَفِيظًا
መልክተኛውን የሚታዘዝ ሰው በእርግጥ አላህን ታዘዘ፡፡ ከትእዛዝም የሸሸ ሰው (አያሳስብህ)፡፡ በእነሱ ላይ ጠባቂ አድርገን አልላክንህምና፡፡
[ሱረቱ ኒሳእ 80]
@ya_muhammad_saw
عن أبي حمزة أنس بن مالك الأنصاري- خادم رسول الله صلي الله عليه وسلم _ رضي الله عنه قال: قال رسول الله صلي الله عليه وسلم : (( لله أفرح بتوبة عبده من أحدكم: سقط على بعيره، وقد أضله في أرض فلاة))
(متفق عليه).
“የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዓ.ወ) አገልጋይ አቡ ሐምዛ አነስ ኢብኑ ማሊክ አል-አንሷሪይ (ረ.ዓ) መልእክተኛው (ሰ.ዓ.ወ) እንዲህ ብለው መናገራቸውን አስተላልፈዋል፡-ከእናንተ አንዳችሁ ምድረበዳ መሬት ላይ ያጣትን ግመሉን በድንገት ሲያገኝ ከሚሰማው ደስታ የበለጠ አላህ በባሪየው ንሰሃ የረካል፡፡”
(ቡኻሪና ሙስሊም)
@ya_muhammad_saw ❤
وَلَا تَهِنُوا وَلَا تَحْزَنُوا وَأَنتُمُ الْأَعْلَوْنَ إِن كُنتُم مُّؤْمِنِينَ
እናንተም የበላዮች ስትኾኑ ምእመናን እንደኾናችሁ አትስነፉ፤ አትዘኑም፡፡
[ሱረቱ ኢምራን 139]
የመካ መስጂደል ሐረም ኢማም ሰኡድ ሹረይም በጁመአ ኹጥባቸው ይህን ብለው ነበር ::
=> ዋጋ ተወደደ
=> ሴቱ ተራቆተ
=>መስጂዶች ባዶ ቀሩ
=> የአላህ ድንጋጌዎች ተሰረዙ
=> የሰረቀን ማባበል
=> ሙጃሂዱ በሰንሰለት ሲታሰር
=> ዚና ሃላል ሲሆን
=> ጋብቻ ሳይቻል ሲቀር
=>ሴቶች የወንድ የበላይ ሲሆኑ
=> የሙስሊሞች ሐገር በጠላት እጅ ሲያዝ
=> ድሆች ከዝናብ ስር ያለ ጥላ
ከቂያማ ምልክቶች ቲንሹ ብቻ ቀረ። በዚህን ግዜ ያለብን ተውባ ብቻ ነው!
እባካቹሁን ከተበሳ ከረጢት ተጠንቀቁ!!!
ለሰላት ብለን ውዱእ እናደርጋለን ነገር ግን <ዉሀውን በኢስራፍ እንጠቀማለን> ይህ
የተበሳ ከረጢት ነው።
ለምስኪን እና ለተቸገረ ገንዘብ እንሰጣለን በሌላ በኩል<የበታችነት በሚሰማቸው> መልክ
እናያለን ይህ የተበሳ ከረጢት ነው።
ለይል እንሰግዳለን፣ ቀን እንጾማለን፣አላህ ያዘዘን እንሰራለን ግን ለማትረባ ዱንያ <ሲረተል
ረሂምን እንቆርጣለን> ይህም የተበሳ ከረጢት ነው።
በጾም ወቅት ጾመን ከረሃብ ሶብር እናደረጋለን ነገር ግን <በምላሳችን እንሳደባለን
እንራገማለን> ይህም የተበሳ ከረጢት ነው።
ሴቷ በልብሷ ላይ አባያ እና ሂጃቧን ለብሳ ግን <ሽቶዋ የሚያውድ> ይህም የተበሳ
ከረጢት ኑው።
እንግዳን ተቀብለን በመልካም መስተንግዶ አስተናግደን ሲወጣ <ስሙን አይቡን በሃሜት
እናነሳለን> ይህም የተበሳ ከረጢት ነው።
አባካቹሁን የለፋቹሁለትን የኸይር ስራ በተበሳ ከረጢት ውስጥ አትሰብስቡ በቀላሉ ፈሶ
ከንቱ ይሆናል እና!!
@ya_muhammad_saw ❤
🍂وَإِذَا قُرِئَ الْقُرْآنُ فَاسْتَمِعُوا لَهُ وَأَنصِتُوا لَعَلَّكُمْ تُرْحَمُونَ🍂
🍃ቁርኣንም በተነበበ ጊዜ እርሱን አዳምጡ፡፡ ጸጥም በሉ፡፡ ይታዘንላችኋልና፡፡🍃(ሱረቱል አዕራፍ 204)
====================
🍂የአላህ ራህመት(እዝነት) እጅግ በጣም ቅርብ ነው። 🍃
🍂ቁርአን በተነበበ ጊዜ ፅጥ ብለህ በማዳመጥም ቢሆን የአላህን እዝነት ፈልግ/ጊ!!🍃
@ya_muhammad_saw 💙
عن أبي موسى الأشعري رضي الله عنه قال:
قال رسول الله ﷺ :
" إن بين يدي الساعة أياما يرفع فيها العلم، وينزل فيها الجهل، ويكثر فيها الهرج، والهرج : القتل ".
📚رواه البخاري 7064
ረሱል ﷺ
✨ ቂያማህ ሲቃረብ ዕውቀት ይነሳል/ይወገዳል፡ አለማወቅ/መሃይምነት ይሰፍራል፡ ግድያ ይበዛል ብለዋል🌴
ሀቂቃ ያለንበት ወቅት ይመስላል።
አንድም ነገር ሳይነግሩን አልሄዱም፡
صلوات ربي وسلامه عليه ❤️
@ya_muhammad_saw
#የረሱል ﷺ ህይወት ትውስታ በሰው ልጆች ጠቅላላ የኑሮ ገፅታ ላይ ብርቱ ተፅዕኖ ያሳድራል መልካም አሻራንም ያሳርፋል።
በነፍስ ውስጥ የእምነት ጥንካሬን ይፈጥራል ፣ በመልካም ስብዕና ያስውባል ፣ በቅንነት ብርሀን ያፈነጥቃል ፣ በጀግንነት ስሜት ያበረታል ፣ በታማኝነት ካባ ያስጌጣል ፣ በመሪነት ያሸልማል።
ሌላም ሌላም…
ምክንያቱም ረሱል ﷺ ለሰው ልጆች ብርሃንን የሚለግስ የፅናት እና የመልካም ስራ ታላቅ ተምሳሌታዊ ስብዕና ባለቤት ከሁሉ በላይ ደግሞ ለዓለማት እዝነት የተላኩ ስለነበሩ ነው።
{وَمَا أَرْسَلْنَاكَ إِلاَّ رَحْمَةً لِّلْعَالَمِينَ} [الأنبياء 107]
(ሙሐመድ ሆይ!) ለዓለማትም እዝነት አድርገን እንጂ አልላክንህም"
(አል’አንቢያእ: 107)
⇩⇩⇩
@ya_muhammad_saw
📚የሰደቃ ጥቅሙ📚
✅《مَّثَلُ ٱلَّذِينَ يُنفِقُونَ أَمْوَٰلَهُمْ فِى سَبِيلِ ٱللَّهِ كَمَثَلِ حَبَّةٍ أَنۢبَتَتْ سَبْعَ سَنَابِلَ فِى كُلِّ سُنۢبُلَةٍ مِّا۟ئَةُ حَبَّةٍ وَٱللَّهُ يُضَٰعِفُ لِمَن يَشَآءُ وَٱللَّهُ وَٰسِعٌ عَلِيمٌ》
✅《የእነዚያ ገንዘቦቻቸውን በአላህ መንገድ የሚለግሱ ሰዎች (ልግስና) ምሳሌ በየዘለላው ሁሉ መቶ ቅንጣት ያለባቸውን ሰባት ዘለላዎች እንደ አበቀለች አንዲት ቅንጣት ብጤ ነው፡፡ አላህም ለሚሻው ሰው (ከዚህ በላይ) ያነባብራል፡፡ አላህም ችሮታው ሰፊ ዐዋቂ ነው፡፡》
📚 سورة البقرة (261)
〰〰〰〰〰〰〰〰〰
@ya_muhammad_saw ❤
ነብዩ ﷺእንዲህ ይላሉ፦
«ነፍሴ በእጁ በሆነችው ጌታዬ እምላለሁ
ገዳይ ለምን እንደገደለ ሟችም ለምን
እንደተገደለ የማይታወቅበት ዘመን ይመጣል!»
እውነቶን ነው ያረሱለላህ (ሰ.ዐ.ወ)
〰〰〰〰〰〰〰〰〰
@ya_muhammad_saw ❤
1.አንድ ቀን ለፈጅር ትነቃለክ፣እናም ፀሐይ በምእራብ ወጥታ ታገኛታለክ።
2.አንድ ቀን ቁርአንን ትከፍታለህ ነገር ግን ገፆቹ ባዶ ሆኖ ታገኛለህ።
3.አንድ ቀን ወደ ሶላት ትቻኮላለህ ነገር ግን አንድም ሱራ ማስታወስ ይከብድሃል።
4.አንድ ቀን ለተውበት ወደ አላህ ትሄዳለህ ነገር ግን የተውባ በሮች ተዘግተው ታገኛለህ።
"አንድ ቀን"ነገ ሊሆን ይችላል
ያን ጊዜ ወደ አላህ መመለስ በጣም ዘግይታልና
አሁን ጊዜ እያለን ወደርሱ እንመለስ።
ነገንም ላንኖር እንችላለን።
ሞት ለህያው ነፍስ ሁሉ ነውና።
@ya_muhammad_saw
አንዳንድ ሰው እየተበደለ ችሎ የሚኖረው አፀፋውን መመለስ አቅቶት ሳይሆን
.
.
በአስተሳሰብ ከበዳዩ ስለሚሻል ነው☺️
እናም ውዶቼ የወራቶች ሁሉ ንጉስ የሆነው የረመዷን ወር ወደኛ እየገሰገሰ ነው ታድያ ለምን አፉ አንባባልም?
ካጠፋቹም ይቅርታ ካላጠፋቹም ይቅርታ ጠይቁ ይቅርታ መጠየቅ መሸነፍ ሳይሆ ትልቅነትን መግለፅ ነው።🫂
አውቄም ሆነ ሳላውቅ አስቀይሜያቹህ ከሆነ ለአላህ ብላቹ አውፍ በሉኝ እኔም አውፍ ብያለሁ🥰
ያአላህ ሁላችንንም በዚህ ታላቅ ወር ተጠቃሚዎች አድርገን 🤲
@ya_muhammad_saw
..."ምንም እንደማያየን አድርገን ወንጀል እንሰራለን፤
እሱም በእዝነቱ ምንም እንዳላየ ሆኖ ይምረናል"🥺❤️አላህዬ...
وَالَّذِينَ عَمِلُوا السَّيِّئَاتِ ثُمَّ تَابُوا مِن بَعْدِهَا وَآمَنُوا إِنَّ رَبَّكَ مِن بَعْدِهَا لَغَفُورٌ رَّحِيمٌ
እነዚያም ኃጢአቶችን የሠሩ ከዚያም ከእርሷ በኋላ የተጸጸቱ ያመኑም ጌታህ ከእርሷ በኋላ በእርግጥ መሓሪ አዛኝ ነው፡፡
[ሱረቱ አዕራፍ 153]
#ሻዕባንን በእስቲግፍር
@ya_muhammad_saw
وَالَّذِينَ آمَنُوا وَعَمِلُوا الصَّالِحَاتِ وَآمَنُوا بِمَا نُزِّلَ عَلَىٰ مُحَمَّدٍ وَهُوَ الْحَقُّ مِن رَّبِّهِمْ ۙ كَفَّرَ عَنْهُمْ سَيِّئَاتِهِمْ وَأَصْلَحَ بَالَهُمْ
እነዚያም ያመኑ፣ በጎዎችንም የሠሩ፣ በሙሐመድ ላይም የወረደው እርሱ ከጌታቸው ሲኾን እውነት ስለ ኾነ ያመኑ ከእነርሱ ላይ ኃጢአቶቻቸውን ያባብሳል፡፡ ኹኔታቸውንም ሁሉ ያበጃል፡፡
[ሱረቱ ሙሀመድ 2]
ሰሀባውም ቀና ብሎ ጨረቃዋን አየ መልሶም እሳቸውን አየ ደጋግሞ ተመለከተ በርግጥም ውበታቹ የበለጠ ነው አለ ...
ሰማይዋን ተመልከት የጨረቃዋንም ውበት አስተውል ረሱሌኮ ከዚህ በላይ ውብ ነበሩ...
ሰለዋቱ ረቢ ወሰላሙሁ አለይከ ያ ሀቢበላህ 🥰 ..
@ya_muhammad_saw
سبحانك اللهم ربنا وبحمدك اللهم اغفر لي
አላህ ሆይ ከጎዶሎዎች ሁሉ የጠራህ ነህ፤
ጌታችን ሆይ!ምስጋናም ላንተ ነው፤
አላህ ሆይ ማረኝ!
@ya_muhammad_saw
#ወላጆችህ አንተ ዘንድ በህይወት አሉ?
የደስታቸው ምንጭ ሁን ፣ተንከባከባቸው፣ዱዐ አድርግላቸው ፣አውራቸው...
#ከወላጆችህ በአካል ርቀሀል?
በስልክ ዘይራቸው፣ሀዲያ ላክላቸው፣ባሉበት እንዲጠብቃቸው ዱዐ አድርግላቸው...
#ወላጆችህ ወደ አኼራ ሂደውብሀል?
ሰደቀቱል ጃሪያ ሁንላቸው፣ብርሀን እንዲሆንላቸቸው ዱዐ አድርግ፣በነሱ ስም ሰድቅላቸው...
۞ وَقَضَىٰ رَبُّكَ أَلَّا تَعْبُدُوا إِلَّا إِيَّاهُ وَبِالْوَالِدَيْنِ إِحْسَانًا ۚ إِمَّا يَبْلُغَنَّ عِندَكَ الْكِبَرَ أَحَدُهُمَا أَوْ كِلَاهُمَا فَلَا تَقُل لَّهُمَا أُفٍّ وَلَا تَنْهَرْهُمَا وَقُل لَّهُمَا قَوْلًا كَرِيمًا
ጌታህም (እንዲህ ሲል) አዘዘ፡- እርሱን እንጂ ሌላን አትገዙ፡፡ በወላጆቻችሁም መልካምን ሥሩ፡፡ በአንተ ዘንድ ኾነው አንዳቸው ወይም ሁለታቸው እርጅናን ቢደርሱ ፎህ አትበላቸው፡፡ አትገላምጣቸውም፡፡ ለእነርሱም መልካምን ቃል ተናገራቸው፡፡
[ሱረቱ ኢስራእ 23]
ሱረቱል ካህፍ ከጁምኣ እስከ ጁምኣ ብርሃን ነው
ልብን ህያው የሚያደርግ የልብ ቀለብ ነው🥰
{الْحَمْدُ لِلَّهِ الَّذِي أَنزَلَ عَلَىٰ عَبْدِهِ الْكِتَابَ وَلَمْ يَجْعَل لَّهُ عِوَجًا ۜ}
"ምስጋና ለአላህ ለዚያ መጽሐፉን በውስጡ መጣመምን ያላደረገበት ሲሆን በባሪያው ላይ ላወረደው ይገባው፡፡"
[ሱረቱል ካህፍ:1]
••❥ ደስታ የደቂቃ ትውስታ ነች ።
••❥ ሐዘን የወንጀል ማበሻ ነች።
••❥ ቁጣ የሸር መንገድ ነች ።
••❥ የጊዜ ክፍተት ኪሳራ ነው ።
••❥ ኢባዳ ትርፋማ ንግድ ነች ።🤗
@ya_muhammad_saw 💙
ኢንና ሊላሂ ወዒና ኢለይሂ ራጅዑን
ኡስታዝ ማህሙድ ዩኑስ ወደ አኼራ ሄዷል!
በጄይሉ ቲቪ እየተዘጋጀ በአፍሪካ ቲቪ የሚቀርበውን የልጆች ፕሮግራም በማዘጋጀትና በሌሎች ኢስላማዊ ሚዲያዎችና ትምህርት ቤቶች በመምህርነት እና ዲናዊ ሥራዎች ደማቅ አሻራ የነበረው ኡስታዝ ማህሙድ ዩኑስ በቱርኪዬ ሃገር በህክምና ሲረዳ ቆይቶ ወደ አኼራ መሄዱ ተሰምቷል።
ኡስታዝ ማህሙድ ለህዝበ ሙስሊሙ ባበረከተው እውቀት ተኮር የተርቢያ ሥራ የራሱን አስተዋፅኦ ማኖር የቻለ ሲሆን፤ የገጠመውን ህመም ተከትሎ በተለያዩ ኢስላማዊ እና የሶሻል ሚዲያዎች በተደረገ የድጋፍ ጥሪ ውጪ ሀገር ሄዶ እንዲታከም ህዝበ ሙስሊሙ ርብርብ ማድረግ ችሎ ነበር::
የገጠመው ህመም አልጋ ላይ አውሎት የከረመው ኡስታዝ ማህሙድ የጤና ሁኔታው ተሻሽሎ ለሚወዳቸው ልጆቹ እና ቤተሰቡ እንዲሁም ወደ ሚዲያው ዘርፍ ተመልሶ ህዝበ ሙስሊሙን ማስተማሩን እንዲቀጥል ለማድረግ በገንዘብ እና በዱዓ እገዛ ላደረጋችሁ ሁሉ አላህ መልካም ስራችሁን ይቀበላችሁ::
ለወንድማችን ኡስታዝ ማህሙድ ዩኑስም አላህ ምህረቱን እንዲለግሰው፤ ማረፊያውን በጀነተል ፊርደውስ እንዲያደርግለት እና መልካም ስራውን እንዲቀበለው ሚንበር ቲቪ ይመኛል።
قال العلامة ابن عثيمين رحمه الله :
« من حق الرسول ﷺ أن تصلي عليه،
لأن الله أنقذك به من الضلالة، ودلك إلى الرشد عن طريقه ﷺ، فلا طريق يُوصل إلى رضوان الله تعالى وجنته إلا طريق محمد ﷺ ».
📚 فتاوى نور على الدرب (209/12)
ሸይኽ ሷሊህ #ኢብኑ_ዑሰይሚን አሏህ ይዘንላቸውና እንዲህ ይላሉ🌴
ረሱል ﷺ ባንተ ላይ ካላቸው ሀቆች፡ በሳቸው ላይ ሶላዋት ልታደርግ ነው።
ማክነያቱም አሏህ በሳቸው ሰበብ ከጥመትና ከጨለማ አውጥቶሀል፡ ወደ ቀጥተኛው መንገድም መርቶሀል።
[ደግሞም እወቅ]
ወደ አሏህ ውዴታና ጀነት የሚያደርስ መንገድ የለም 👉 #የሙሀመድ ﷺ መንገድ ቢሆን እንጂ🌴
صلوات ربي وسلامه عليه ❤️
@ya_muhammad_saw
🌺ሶብር 🌺
ትግስት የዚህ አለም ሀብት የመጭው አለም ስኬት ናት። አላህ ለታጋሾች ትልቅ ስጦታን ሰጣቸዋ በገነትም አበሰራቸው።
وَلَنَبْلُوَنَّكُم بِشَيْءٍ مِّنَ الْخَوْفِ وَالْجُوعِ وَنَقْصٍ مِّنَ الْأَمْوَالِ وَالْأَنفُسِ وَالثَّمَرَاتِ ۗ وَبَشِّرِ الصَّابِرِينَ
ከፍርሃትና ከረኃብም በጥቂት ነገር፣ ከገንዘቦችና ከነፍሶችም፣ ከፍራፍሬዎችም በመቀነስ በእርግጥ እንሞክራችኋለን፡፡ ታጋሾችንም (በገነት) አብስር፡፡
''ትግስት ከኢባዳዎች አንዱና ምንዳውም የላቀ ነው። አላህ ትእግስትን ከሶላት ጋር አብሮ በማቆራኘት ጠቅሶታል።
يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا اسْتَعِينُوا بِالصَّبْرِ وَالصَّلَاةِ ۚ إِنَّ اللَّهَ مَعَ الصَّابِرِينَ
እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በመታገስና በሶላት ተረዱ፡፡ አላህ (በእርዳታው) ከታጋሾች ጋር ነውና፡፡
الَّذِينَ إِذَا ذُكِرَ اللَّهُ وَجِلَتْ قُلُوبُهُمْ وَالصَّابِرِينَ عَلَىٰ مَا أَصَابَهُمْ وَالْمُقِيمِي الصَّلَاةِ وَمِمَّا رَزَقْنَاهُمْ يُنفِقُونَ
እነዚያን አላህ በተወሳ ጊዜ ልቦቻቸው የሚጨነቁትን፣ በደረሰባቸውም (መከራ) ላይ ታጋሾችን፣ ሶላትንም አስተካክለው ሰጋጆችን፣ ከሰጠናቸውም ሲሳይ የሚለግሱትን (አብስር)፡፡
''ሳትፈተንና መከራን ሳትቀምስ ጀነትን የምታገኝ መሰለህን? አስታውስ! ጀነት ለነዚያ መከራና ችግር ባጋጠማቸው ጊዜ እንዲህ ለሚሉት ናት፦
الَّذِينَ إِذَا أَصَابَتْهُم مُّصِيبَةٌ قَالُوا إِنَّا لِلَّهِ وَإِنَّا إِلَيْهِ رَاج
/channel/ya_muhammad_saw
❇️ማዘን ከፈለክ ብዙ ምክንያቶች መደርደር ትችላለህ፣ ብዙ የጎደሉህ ነገሮችን እያሰብክ መብሰልሰል ትችላለህ፤ ልደሰት ስትል ግን በምን እንደምደሰት እንኳን አላውቅም ልትል ትችላለህ።
እኔ ግን ልንገርህ እየተነፈስክ መሆኑ ብቻ ሊያስደስትህ ይገባል ምክንያቱም ትንፋሽህ እስካልቆመ ድረስ ምንም ነገር ለማሳካት እድሉ አለህ። ድጋሚ ለመማር፣ ድጋሚ ለመስራት፣ ድጋሚ ንግድ ለመሞከር፣ ድጋሚ ለማፍቀር ብቻ ብዙ እድሎች አሉህ። ታዲያ ከዚህ በላይ ምን ደስ የሚል ነገር አለ? ከሁሉ በላይ ደግሞ የሚጠብቅህ የሚወድህ በመንገድህ ሁሉ የሚቀድም አላህ አለ። ተደሰት ወዳጄ! እናም ውዷ እህቴ
@ya_muhammad_saw ❤
🖊ትንሽ ምክር ለሙዕሚኗ እህቴ🌹
~~~~~~~~~~~~~~~~~~
#ቤትሽ_የደስታ_ይሆን_ዘንድ‼️
1/ምንጊዜም አስታውሽ ባልሽ ወደ አሏህ መቃረቢያ ወደ ጀነት መዳረሻ መሆኑን‼️
2/ ወደ መኝታሽ ከመሄድሽ በፊት ለባልሽ ተሞሸሪለት‼️
3/ሁልጊዜም አዲስ ነገር ላይ ጉጉት ይኑርሽ‼️
4/ሲወጣ የሚለብሰውን ልብስ በጊዜው አዘጋጅ‼️
5/በሚወደው ምግብ ላይ ትኩረት አድርጊ‼️
6/ብቻውን በሚሆንበት ጊዜ፣ ድምፅሽን ከፍ አታድርጊ ‼️
@ya_muhammad_saw ❤